Thursday, May 31, 2012

የጠላት ከፍታ

Read in PDF               ምንጭ፡- ቤተ ጳውሎስ ብሎግ
ጴጥሮስና ዮሐንስ በተሰጣቸው ጸጋ በተአምራት ወደ ላይ ሲወጡ ያየው ሲሞን መሠርይ እኔም እንደ እነርሱ ማድረግ እችላለሁ ብሎ በምትሐት ወደ ላይ ከፍ ሲል ጴጥሮስና ዮሐንስ ከታች ወደ ላይ ሲመጣ አዩት፡፡ ጴጥሮስም ችኩል ነውና እናማትብበት አለ፡፡ ዮሐንስ ግን “ከፍ ከፍ ይበል ለአወዳደቁ እንዲመች” አለው በማለት አንድ መምህር በልጅነቴ አጣፍጠው የነገሩኝን አልረሳውም፡፡

Tuesday, May 29, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ስውር አመራሮች እጅ በውጭ ያለውን ሲኖዶስ ሲፈታተን

ምስክር ከአሜሪካ (ጸሐፊው የአባት ስም ጨምረው አልላኩም)
በሃይማኖት ሽፋን የተሰባሰቡ ፖለቲከኞች ስብስብ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን የሲኖዶስ ስብሰባ በቀረበ ቁጥር የሲኖዶስ ስብሰባዎችን በማወክ ግብር መገለጥ ከጀመረ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው። በአገር ውስጥ ተወስኖ የነበረውን ይህን እኩይ ተግባሩን በውጭ አገር በሚገኘው ስደተኛው ሲኖዶስ መካከልም ተግባራዊ ለማድረግ መንቀሳቀሱንና በተወሰነ መልኩ የተሳካለት መስሎ እየታየ መሆኑን አንዳንድ ምንጮች እየገለጹ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን በስውር አመራሮቹ በኩል በአሁኑ ጊዜ በውጭ ያለውን ሲኖዶስ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ የቀረበው ለምን እንደሆነ በውጭ የሚገኙ አባቶች በሚገባ መረዳት አለባቸው የሚል እምነት አለኝ።ከዚህ ቀደም ከአገር ቤት ወደ አሜሪካ ተልከው እዚያ ተመድበው የነበሩትን የማኅበሩን ደጋፊ አባ አብርሃምን በመጠቀም ማኅበሩ የራሱን አቅም ይበልጥ ለማጠናከር በር ተከፍቶለት የነበረ ሲሆን፣ እርሳቸው ለቤተክርስቲያኒቱ ሳይሆን ለማኅበረ ቅዱሳን ጥቅም መቆማቸው በመረጋገጡ በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እንዲተኩ ተደርጓል። እርሳቸውም ቤተክርስቲያኒቱን ከማቅ ሕገ ወጥ አሰራር ነጻ ለማድረግ የጀመሩትን ጥረት ለማደናቀፍ የተንቀሳቀሱትን የዶ/ር መስፍንን «ክህነት» መሻራቸው በማኅበሩ ላይ ትልቅ ኪሳራ ማስከተሉን ከማኅበሩ ውስጥ አዋቂዎች እየተገለጸ ነው። ይህም የማኅበሩ ስውር አመራር በአገር ቤት ያለውን ብቻ ሳይሆን በውጪ የሚገኘውን ሲኖዶስም ቆርጦ ለመግባትና ለመከፋፈል የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል አድርጎታል። ለውጪው ሲኖዶስ እንደ እጅ መንሻ ይዞ የቀረበውም የዋልድባን ጉዳይ ሲሆን፣ ስውር አመራሩ ቀደም ብሎ የዋልድባን ጉዳይ በማንቀሳቀስና ህዝብን ለተቃውሞ በማነሳሳት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ በአሜሪካ የተቃውሞ ሰልፍና የሚዲያ ላይ ዘመቻ በመክፈትና አጀንዳውን ወደ አቡነ መልከጼዴቅ በሚያምኑት ሰው በኩል ይዞ ጠጋ በማለት የእርሳቸውን ትኩረት ለመሳብ ጥረት አድርጓል። በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲና በሎስ አንጀለስ በዋልድባ ዙሪያ ይካሄዳል የተባለው ሰላማዊ ሰልፍ እየተመራ ያለው በማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሏል። ማኅበሩ የዋልድባ ጉዳይ ጨንቆት ሳይሆን በጉዳዩ ቅር የተሰኘውን በስደት የሚኖረውን ኦርቶዶክሳዊ ለመጠቀም እና ሌሎች የራሱን አጀንዳዎች ለመፈጸም እንደሆነ በሚያካሂዱት የቴሌኮንፍረንስ ውይይት ውስጥ ገብቶ ለሚያዳምጥ ግልጽ ነው። አሁን እንደሚስተዋለው በዚህ ማኅበረ ቅዱሳን በሚመራው ቴሌኮንፍረንስ እና ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በስደተኛው ሲኖዶስ ታቅፈው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትም ሳያውቁ እየተሳተፉበት ነው። ይህ ሁኔታ በኋላ የሚያስከትለው ፈተና ለአብያተ ክርስቲያናቱና አገልጋዮች ካህናት የታያቸው አይመስልም።  ማቅ እያደረገች ያለችው የዋልድባን ጉዳይ ተጠቅማ፣ እውቅናን ለማትረፍ፣ ከዚያም በስደት ባሉ አብያት ክርስቲያናት ውስጥ ሰርጎ በመግባት በፊት ሞክረው ያልተሳካላቸውን የመከፋፈል ስራ ለማከናወን ነው።  ይህንንም ለመከላከል ካህናቱ፣ ምዕመናኑ እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ነቃ ነቃ እንዲሉ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

Sunday, May 27, 2012

በእውኑ‘”ማህበረ ቅዱሳን” (ሰለፊያ) እየተዘጋ አይደለምን???

“ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር” እንዲሉ በግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የታዮ ክስተቶችን ትንታኔ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡
ሁላችንም እንደምናውቀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራሱን በቅዱሳን ስም “ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል የሰየመው የፖለቲካ ድርጅት ለአለፉት ሁለት አሥርት አመታት በቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ይህ በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰው ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ሁሉም የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚያውቁት ሐቅ ነው፡፡
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳስነበብናችሁ ለመሆኑ ማቅን ማን መሠረተው? እነማንስ ስም ሰጡት የሚለውን እውነታ ስንመለከት ‹‹ማቅ›› የተሀድሶ ኮሚቴ ይባሉ በነበሩ የደርግ ደጋፊ አባላት የተመሠረተ ሲሆን ይኽ የጥፋት መልዕክተኛ ዘር ግንዱ እነኮሎኔል አጥናፉ አባተ ካቋቋሙት ”ጊዜያዊ የተሐድሶ ጉበኤ” ይነሳል። ጊዜያዊ የተሐድሶ ጉባኤ የማኅበረ ቅዱሳን አባቱ መሆኑ ነው። ይኽ አባቱ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ለማፍረስ እና በውስጥዋም ሥርዐት አልበኝነት በማንገስ ቤተ ክርስቲያን ደካማ እንድትሆን ለደርግ ያገለገለ ነው። አገልሎቱ ሁለት መልክ ነበረው - የሞተውን ሥርዐት ለመመለስ እና የየግል ጥቅማቸውን ማሳደግ እንዲሁም በሃይማኖት ሽፋን ስውር አላማን ማስፈጸም ነው፡፡

Friday, May 25, 2012

በፍርድ ፈንታ ደም ማፍሰስ በጽድቅ ፈንታ ጩኸት(ኢሳ. 5÷7)፡፡

www.betepawlos.com የተወሰደ
                       አንዲት ሕጻን ልጅ ሞታ የጎጃሟ አልቃሽ፡-
                         “ምን ዓይነት ቄስ ናቸው የማይጠብቁ ዕቃ
                         እበተስኪያን ጓሮ እጣኒቱ ወድቃ”
በማለት የሀዘን ቅኔ (ሙሾ) አሰምታለች፡፡ የቄሱ አንዱ ሥራ ዕጣን መጠበቅ ሲሆን ዋነኛው ሥራቸው ግን ሕጻናትን መጠበቅ ወይም ማሳደግ ነው፡፡ ሕፃናት ከቤተ ክርስቲያን አደባባይ ሊቀመጡ አባቶቻቸውን እያዩ ሊማሩ ሲገባ ከቤተ ክርስቲያን ጓሮ ከመቃብር ውስጥ ሲወድቁ ማየት አሳዛኝ ነው፡፡ አልቃሿ በሕፃናት ማለቅ ቀሳውስቱ ለምን አይጸልዩም ማለቷ ሲሆን ከዚያ ባሻገር ግን ትውልድን ለምን ይቀጫሉ? ማለቷ ነው፡፡ አባቶች አደራቸውን ባለመወጣታቸው ትውልዳችን የሞት ልጅ ሆኗል፡፡ ራሱን በራሱ እየመራ የዘመን ምርኮኛ፣ የኃጢአት ግዞተኛ ሆኗል፡፡ ይልቁንም በአባቶች ፈንታ እንዲተኩ ከዐውደ ምሕረቱ ሊቀርቡ የሚገባቸው ወጣቶች እየተገፉ ወደ መቃብር ስፍራ መውረዳቸው ዛሬም ልብ ያለውን የሚያስለቅስ ነው፡፡

Wednesday, May 23, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪ ጳጳሳት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ባልተከተለ መንገድ መወገዝ የሌለባቸውን የቤተ ክርስቲያን ልጆች “አወገዝን” አሉ

ነውራችን ተሸፈነልን ብለውና ከማኅበሩ የሚከፈላቸውን ረብጣ ብር ከግምት በማስገባት፣ እንዲሁም ከማኅበረ ቅዱሳን ጎን ብንቆም ፓትርያርክነቱ ለእኛ ይሆናል በሚል ክፉ ምኞት ተይዘው ለአንድ ወንበር እርስ በርስ እየታገሉ፣ የቤተክርስቲያንን ሳይሆን የማኅበሩን አላማ ለማሳካት በግንቦቱ ሲኖዶስ ከመጠን በላይ ሲፋንኑ የነበሩት አባ አብርሃም፣ አባ ዲዮስቆሮስና አባ ሳሙኤል፣ እንዲሁም አባ ጢሞቴዎስ፣ “ምንም ቢሆን ማኅበረ ቅዱሳን የከሰሳቸውን ሰዎችና ማኅበራት ሁሉ ሳናወግዝ አንበተንም፤ ማኅበረ ቅዱሳን ያጠናው በቂ ነው፤ እነርሱን ጠርቶ ማነጋገር አያስፈልግም” በሚል የማኅበረ ቅዱሳንን ክስ ብቻ በመቀበልና ተከሳሾቹን ሳያነጋግሩ ፍትሀዊነት የጎደለውን ፍርድ በመፍረድ “አውግዘናል” ማለታቸው ተሰማ። እነዚህ በስም የተጠቀሱ የሰሙኑን የሲኖዶስ ስብሰባ ማኅበረ ቅዱሳን በአቡነ ጢሞቴዎስ ቤት ያገባላቸውን ግብር በምሳ ሰአት እየበሉ፣ የቀኑን ውሎ ለማኅበሩ አመራሮች ሪፖርት እያቀረቡና በቀጣዩ ስብሰባ ላይ ማድረግ ስለሚገባቸው መመሪያ ከማኅበሩ አመራሮች እየተቀበሉ ሲኖዶሱን ሲያውኩ መሰንበታቸው ይታወሳል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በታሪክ ፊት ተጠያቂ የሚሆንበትን ስህተት ፈጸመ

ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት
 • ውሳኔው አባ ሰረቀ ብርሃንና ዲ/ን በጋሻውን አይመለከትም
 • ማቅ ከሰንበት ማደራጃ ውጭ ሆኗል
 • የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመትንም በሐምሌ ሲሰባሰቡ እንደሚፈጸም ታውቋል፡፡

Tuesday, May 22, 2012

ቅዱስ ሲኖዶሱና ዘጠነኛ ቀኑ

   
 • አባ አብርሃም የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ላለማስረከብ አስቂኝ መከራከሪያ አቀረቡ
 • ማኅበሯ ሌላው መንገድ ሁሉ አላስኬድ ሲላት አይመጥንም በሚል የሰንበት ማደራጃና መምሪያ ኃላፊነትን ከመምኅር እንቁባህሪ ላይ ለመንጠቅ የምታድረገው ሙከራ አልተሳካላትም።
 • ማኅበረ ቅዱሳንን የመፍረስ ስጋትን ጥሎበት የነበረው የማኅበራት መተዳደሪያ ደንብ እንደገና ውድቅ እንዲሆን እንቅልፍ አጥቶበት የነበረ ሲሆን እንደገና እንዲጠና ታዟል።   
አሁን በቅርቡ እንኳ ወደ ሐረር ሀገረ ስብከት እንደ ደረሱ ለኔ የተመደበችው መኪና የትኛዋ ነች ብለው ሲጠይቁ ከእሳቸው በፊት ነበሩት አቡነ ዮሴፍ ይሄዱበት የነበረችውን መኪና ሲያሳዩዋቸው ከት ብለው ስቀው እኔ በዚህ መኪና ልሄድ? ብለው ጠይቀው ይህ መኪና ስለማይመጥነኝ በአስቸኳይ ከሞኤንኮ አዲስ መኪና ይገዛ ብለው አዲስ መኪና አስገዝተው በእስዋ መንፈላሰፍ ጀምረዋል። ድንቄም አባትነት።
አባ አብርሃም ርስት ጉልቴ ነው ያሉትን የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ የታዘዙትን ትዕዛዝ ለመቃመም ከተነሳው ጥያቄ ጋር የማይሄድ እኔ ከእርስዎ እሻላለሁ የሚል መከራከሪያ አቀረቡ። እኔ ምን አለኝ እና ነው መልስ የምባለው ሲሉ የነበሩት ሰው አሁን በራሴ ወጪ አጣሪ ተልኮ ከእኔ እና ከእርሰዎ ማን ጥሩ ስራ እንደሰራ ይጣራ ሲሉ ጠይቀዋል። ይህም ጥያቄ አሜሪካ ለመመለስ ያላቸውን ከፍተኛ ጉጉት ያሳያል ተብሏል። ስውየውን የሚያስጨንቃቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ባሉበት ቦታ ሁሉ ተገኝተው አባትነትን ማሳየት ሳይሆን ጥቅምና ምቾት ባለበት ቦታ ላይ መንቀባረር መሆኑንም አሜሪካ ለመመለስ ያላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ያሳያል።

Monday, May 21, 2012

ተወጋዦች አውጋዦች፣ አውጋዦች ተወጋዦች የሆኑባት ቤተክርስቲያን

ውግዘት ከእውነተኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርትና በእርሱ ላይ ከተመሰረተው እውነተኛ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ በተቃራኒ የቆመን የቤተክርስቲያን አባል (አገልጋይ/ምእመን) ቤተክርስቲያን መክራና ዘክራ አልመለስም ብሎ አቋሙን በግልጽ ሲያሳውቅና በእንቢተኛነቱ ሲጸና መጨረሻ ላይ ቤተክርስቲያን ያን አባሏን ከአንድነቷ ለመለየት የምትወስደው እርምጃ ነው። ይህም ሲሆን ቤተክርስቲያን ቅድሚያ የምትሰጠው ለውግዘት ሳይሆን አባሏን በንስሃ ለመመለስ ነው። ሁሉንም አማራጮች ተጠቅማና ሊያስወቅሳት የማይችለውን እድል ሰጥታ አባሏ አልመለስ ብሎ በኑፋቄው/በክህደቱ ሲጸና እያዘነች የምታስተላለፈው የከበረ ውሳኔዋ ነው። በዚህ መንገድ የተላለፈ ውግዘት ተቀባይነት አለው። ከዚህ ውጪ በቂም በቀል፣ በጥላቻ፣ አንዱን ወገን አስደስቶ ሌላውን ለመጉዳት የሚደረግ ውግዘት ግን ተቀባይነት የለውም። የማቅና እርሱ አእምሮአቸውን የተቆጣጠረው ጳጳሳት እንዱ ችግር ውግዘት ምን እንደሆነና በምን ምክንያት እንደሚተላለፍ አለማወቃቸው ነው። ውግዘት ለእነርሱ ቂምን መወጫ፣ ጠላትን ማጥቂያ መሣሪያ ነው።

Sunday, May 20, 2012

የ“ኢሳት” የዜና ማእከል እና “የማህበረ ቅዱሳን” ጊዜያዊ ጋብቻ!


ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

ሙሉውን የጽሑፉን ይዘት ከማንበብዎ በፊት÷ በPDF ለማንበብ
1.     ጸሐፊው በጽሑፋቸው ውስጥ የጠቀሱትን የዜና ማዕከል “ማህበረ ቅዱሳን” በመባል ስለሚታወቀው መንፈሳዊ ካባ ያጠለቀ ጸረ ቤተ-ክርስቲያን ጸረ ሀገርና ጸረ ትውልድ ማኅበርን በተደጋጋሚ ሽፋን በመስጠት ጽድቁን በዜና መልክም ሆነ በሐተታ ተጠቃሹ የዜና ማዕከል ለአድማጮች ያቀረባቸውን ፍጹም ሚዛኑን የሳተና የተንጋደደ ዘገባን ብቻ በማስመልከት ያነጣጠረ ለመሆኑ÷
2.    አሁንም በጽሑፉ ውስጥ የተካተቱ ማናቸውም ሂሶችና ጥያቄዎች “ማህበረ ቅዱሳን” በማስመልከት እጃቸውን የጨመሩ የክፍሉ ሰራተኞች/ግለሰቦች/ እንጅ የመደብሩ ባልደረባዎችን በመላ የማያጠቃልል ለመሆኑ÷
3.    የጸሐፊው ዓላማም ሆነ የጽሑፉ ግብ በማጣመም ሌላ አንድምታ በመስጠትም “በኢሳት” የመጣ በዓይኔ ብሌን” በማለት አካኪ ዘራፍ የሚልም ስለማይታጣ  “ኢሳት” “ማህበረ ቅዱሳንን” በተመለከተም ሆነ “ደጀ-ሰላም” በመባል የሚታወቀውበኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያንና በተከታዮችዋ ላይ ሁከትን ለመፍጠር ታጥቆ የተነሳ የማህበሩ (“የማህበረ ቅዱሳን’) በአንድ ራስ ላይ ተደራቢ ምላስ/ልሳን ሆኖ የበቀለ ድረ ገጽ ዋቢ እያደረገ የሚዘግባቸው ዘገባዎችና የሚያቀርባቸው ማናቸውም ዓይነት ሀተታዎች ፍጹም ከእውነት የራቁና ነጭ ሐሰት መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በወንጀል የሚያስጠይቅ ስራ እየሰራ ለመሆኑ÷
4.    በተጨማሪም “ኢሳት” ጭራሽ “የማህበረ ቅዱሳን” ልሳን አስኪያስመስልበት ድረስ እየሄደበት ያለውን አካሄድ ማለት ነፍሰ ገዳይን የመታደግ ስራ ትክክል አለመሆኑ ለማሳየት ምንም በማያሻማ ግልጽ በሆነ አማርኛ የቀረበ ጽሁፍ ለመሆኑ÷
5.    በመጨረሻም “ለኢሳት” ለብቻ ተብሎ የሚታለፍ እውነት አለመኖሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ከአንደበት የሚወጣ ቃል የሰውን ልብ ከማሸፈት በላይ ህይወትም ይቀጫልና በተለይ የጉዳዩ ቀዳሚ ባለቤቶችና ሰላባዎች ሊሆኑ የሚችሉ/የምንችል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን እምነት ተከታዮችና ምእመን ሰላም ለመጠበቅ ሲባል ይህን ጽሑፍ ሊዘጋጅ ግድ ብለዋል። ደግሞም ሰው ይከበራል እንጅ ስጋ ለባሽ ሆኖ የሚፈራ፣ አምልኮም የሚገባው አንድ ስንኳ አለመኖሩን በሚያምን ልብ ተጻፈ። ጽሑፉ ልዩነትን የሚያሳይ እንጂ የክስ ደብዳቤም ሆነ የስሞታ ማመልከቻም አይደልም።

Saturday, May 19, 2012

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ 10 ጳጳሳትን ይዘው ወደ አክሱም ሄዱ

 • መምህር ዕንቆባሕርይ ከሰንበት ማደራጃ አይነሳም
 • የሚወገዝ ሰውም የለም
 • የደ/ር መስፍን ክህነት መሻር ይነሳልን ብለው ነበር  አልተሳከላቸውም
 • አባ አብርሃም የአሜሪካውን ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ታዘዋል
 • የማኅበረ ቅዱሳን ድረገጾች ውሸት እየፈበረኩ መዘገባቸውን ቀጥለዋልና የዘገቡትን ገልብጦ መረዳት ያስፈልጋል
በPDF ለማንበብ (ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት)
ከሲኖዶስ ስብሰባ በስተጀርባ ሆኖ እንዳሻው ከሚጋልብባቸው ጳጳሳቱ ጋር የመከረውን ሁሉ ከስብሰባው መካሄድ ቀደም ብሎ የሲኖዶስ ውሳኔ አስመስሎ በማቅረብ ሕዝብን በተሳሳተ መረጃ ማደናገርና የተናገረው ሳይሆን ሲቀር ሊያፍር ሲገባው፣ ነገር ግን «ማፈር ደህና ሰንብት» ያለው ማኅበረ ቅዱሳን በድረገጾቹ ውሸት እየፈበረከና ምኞቱን የሲኖዶስ ውሳኔ አስመስሎ ማቅረቡን ቀጥሏል። ከሰሞኑ እንኳ እነ እገሌ ዛሬ ይወገዛሉ አለ። ነገር ግን እንኳን ውግዘት እዚያ በሚያደርስ ሁኔታ የተደረገ ማጣራት አልተካሄደም። ማህበሩ በተሀድሶነት የከሰሳቸው ግለሰቦች ጉዳይ በተገቢው መንገድ ተጠንቶ ስላልቀረበና ግለሰቦቹም ተጠርተው ስላልተጠየቁ እንዲሁም ምላሻቸው ስላልተሰማ፣ ጉዳዩ በዚህ የህግ አግባብ ተሰርቶ ወደፊት እንዲታይ የተባለውን፣ «ከዛሬ ጀምሮ በእያንዳንዱ የውሳኔ ሐሳብ ላይ በጥንቃቄ እየተወያየ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል።» ሲሉ ድረገጾቹ እንደተለመደው የልባቸውን ተምኔት ጽፈዋል። ይህ እንደማይሆን፣ ቅዱስነታቸው 10 ጳጳሳትን ይዘው ለቅዱስ ያሬድ በዓል ወደአክሱም ተጉዘዋልና፣ ዛሬ፣ እንኳን ይህ ፈጽሞ ያልተጣራና በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በተወሰነበት ደረጃ የሚገኘው ጉዳይ ውሳኔ ሊያገኝ ቀርቶ የሲኖዶስ ስብሰባም እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል።

Friday, May 18, 2012

ቤተክርስቲያናችን ውስጥ የተከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት በቅድሚያ ቅዱስ ሲኖዶስ በ1991 ዓ.ም ያወጣውን ህግ ማሻሻል እንዳለበት ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ዘገበ

ይህን የዜና ቤተክርስቲያን ዘገባ ተከትሎ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንዴት እንሰደባለን በሚል ቀድሞ ያልተያዘ ሌላ የውዝግብ ሰበር አጀንዳ ፈጥረዋል። በሌላው ሚዲያ ብንሰደብ ምንም አይደል፤ እንዴት በእኛው ጋዜጣ እንዴት እንሰደባለን? በሚል ለዛሬ 7/8/2004 ዓ.ም የጋዜጣው አዘጋጆች ቀርበው እንዲጠየቁ ጳጳሳቱ ሁሉ ተስማምተዋል ተብሏል። ግን በዛሬው የሲኖዶስ ስብሰባ ውሎ «አዘጋጆቹ ተጠርተው ይቅረቡ» ያሉት አባቶች ያደረጉትንና የሚከተላቸውን ስላወቁ ዛሬ ሀሳባቸውን ቀይረው ይግቡ አይግቡ የሚል ውዝግብ ውስጥ ገብተው ውለዋል። ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደሩፋኤል ፈታሒም «ንስሐ ግቡ ብለን መጠቆማችን ስህተት ከመሰላቸውማ ጉዱን ሁሉ እንዘረዝርላቸዋለን» ማለታቸው ሲዘገብ ትናንት ከጉርምስና ጠባይ ያልተላቀቁትና ሲደነፉ የነበሩት አባ ሳሙኤልና አባ አብርሃም ዛሬ ይግቡና እንጠይቃቸው የሚል ድፍረት አጥተው ሳያነጋግሯቸው የዛሬው ስብሰባ ተጠናቋል።

በማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖ ህልውናውን የካደ ኮሌጅ

በ PDF ለማንበብ (እጅግ የሚያሳዝንና ሁሉም ሰው ሊያነበው የሚገባ፤ ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት)
-       አንድ የቤተክርስቲያንን ልጅ ለማባረር ሲል እራሱን ሕጋዊ ሰውነት የሌለው አድርጎ የሚያሳይ የክስ ወረቀት ለሰበር ሰሚ ችሎት አቀረበ
-       ኮሌጁ በሰበር ሰሚ ችሎት ከረታ ለተማሪዎቹ ከፍተኛ አደጋ አለው
የኢዮቤልዩ በዓሉን ለማክበር ጥቂት ዓመታት የቀሩትና ከተመሰረተ 69 ዓመት የሆነው የቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ከመምህር አሰግድ ሣህሉ ጋር ባለው የሕግ ክርክር በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የገጠመውን ሽንፈት ሽሮ በድል እንድወጣ ያስችለኛል ያለውን የይግባኝ አቤቱታ ለሰበር ሰሚ ሲያቀርብ ሕጋዊ ሰውነት የሌለኝና ከአንድ ግለሰብ እንኳ ያነስኩ ነኝ ሲል ህልውናውን ካደ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ሰባተኛ ቀን ውሎ

በ PDF ለማንበብ (ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት)
 • አንዳንድ ግለሰቦችን ሊቃውነት  ጉባኤ ጠርቶ ስላላነጋገራቸው ጠርቶ እንዲያነጋግር ታዘዘ
 • አቡነ ገብርኤል ከአዋሳ አይነሱም
 • የሰንበት ማደራጀውና የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ ታየ
 • ዲ/ን አሸነፊ መኮንን ይወገዝ ተብሎ አልቀረበም
በትናንትናው ዕለት በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ከተነጋገረባቸው ጉዳዮች አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን እንዲወገዙ ከቋመጠባቸው ግለሰቦች አንዳቸውም ሳይወገዙ እንደ ገና መታየት ያለባቸው ነገሮች እንዲታዩና ሲኖዶሱ ሊቃውነት ጉባኤው ሰዎቹን ጠርቶ በጥንቃቄ መርምሮ ይወሰን የሚለውን ባለማሟላቱ እንደገና ያላነጋገሩዋቸውን ሰዎች እንዲያነጋግሩ ታዘዘ።አባ ሰረቀ እና ዲ/ን በጋሻው የውግዘት ሀሳብ እንዳልቀረበባቸውም ታውቋል። በጋሻው በትናንትናው ዕለት ሊቃውንት ጉባኤ ሊያነጋግረው ፈልጎ ተጠርቶ የነበረ ቢሆንም ሊቃውንት ጉባኤው ራሱ በሲኖዶሱ በመጠራቱ ሳያነጋግሩት ቀርተዋል። ደጀ ሰላም ዲ/ን በጋሻው ሊለማመጥ ሄደ ያለው ከሀቅ የራቀ ሲሆን ሊቃውንት ጉባኤው ስለጠራው መሄዱ ታውቋል።

Thursday, May 17, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ክፍል የዋልድባን ጉዳይ በተመለከተ የቤተ ክህነቱ አጣሪ ኮሚቴን ሪፖርት ያልዘገበበትን ምክንያት እንዲያብራራ ተጠየቀ

በ PDF ለማንበብ (ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት ብሎግ)
ህዝብ ሆይ ስማ!! ተነስ! ታጠቅ! ዝመት! ዋልድባ ገዳም ተተረማመሰ። እያለ በድረ ገጾቹ ግልጽ ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እያደረገ ያለው የመንፈሳዊነት ጭላጩ እንኳ የሌለው ማኅበረ ቅዱሳን በዋልድባ ጉዳይ ከቤተክህነት የተሰጠውን መግለጫ ላለመዘገብ መወሰኑ የቤተክህነቱን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ አስቆጣ።
የህዝብ ግንኙነት መምሪያው የሰንበት ማደራጃ መምሪያውን ማኅበረ ቅዱሳን ለምን ዜናውን እዘግባለሁ ካለ በኋላ ባሉት ህጋዊ ሚዲያዎቹ ሁሉ ላለመዘገብ መወሰኑን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጥበት በማዘዝ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው በደብዳቤ ጠይቋል።
ለዚህ ጥያቄ የራሱን መልስ መስጠት የማይችለው ሰንበት ማደራጃ መምሪያው ጉዳዩ የማህበሩን የሚዲያ ክፍሎች

የቅዱስ ሲኖዶስ የስድስተኛ ቀን ውሎ እንዴት ነበር?

·        ማኅበረ ቅዱሳን የመፍረስ አደጋ ያሰጋዋል
·        ውግዘቱ ሥርአተ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ ነው፤ ይወገዛሉ የተባሉት ግለሰቦች ተጠርተው አልተጠየቁም
·        አባ ሠረቀብርሃንና ዲ/ን በጋሻው ስማቸው ይወገዙ ከተባሉት ውስጥ የለም  
በ PDF ለማንበብ (ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት) 
በትናንትናው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶስ በስድስተኛ ቀን ውሎው ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ያነሳ ሲሆን የጠዋቱ የማኅበራት ጉዳይ ነው። ከሰዓት በኋላ ደግሞ የተነሳው የሃይማኖት ህጸጽ አለባቸው ስለተባሉ ግለሰቦችና ማኅበራት ጉዳይ ነው።

Wednesday, May 16, 2012

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ለማኅበረ ቅዱሳን የአስር ቀናት የጊዜ ገደብ አስቀመጠ

በአልታዘዝ ባይነቱ የሚታወቀውና ለማደራጃ መምሪያውና ለጠቅላይ ቤተ ክህነት መመሪያና ትእዛዝ ተገዢ ከመሆን ይልቅ «እኔን ማንም አያዘኝም» በሚል አቋሙ ጸንቶ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን «ተዳፍኖ ቀርቶልኛል» ሲል ቸል ያለው የመስከረም 12/2002 ውሳኔ ዳግም ተቀስቅሶ በማኅበሩ ውስጥ ፍርሀትና ሽብር ማንገሱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች እየተናገሩ ነው። አንዳንድ ጳጳሳትን በልዩ ልዩ መንገድ እየደለለና እየሸነገለ እድሜውን ሲያራዝም የቆየው ማኅበረ ቅዱሳን፣ በተለይም በሟቹ አቡነ ይስሀቅ፣ እንዲሁም አሁን ባሉትና «ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል» በሚለው አገር አጥፊ ስልት ቤተክህነቱን በስጋ ዘመዶቻቸውና በወንዛቸው ልጆች ባጥለቀለቁት አቡነ ህዝቅኤል የስራ አስኪያጅነት ዘመን እጅግ ተጠቃሚ የሆነው ማቅ፣ አሁን ግን ጊዜ እንደከዳውና የቁርጥ ቀን እንደደረሰበት መታዘብ ተችሏል።

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያው ለማኅበረ ቅዱሳን ከባድ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጻፈ

ደብዳቤውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ


 • የ2002 ዓ/ም ውሳኔ በ 10 ቀን ውስጥ እንዲፈጸም ያዛል። ይህ ካልሆነ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።
 • ደብዳቤው ማህበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያንን ሕገ ደንብና የበላይ አካላትን ትዕዛዝ በመቃረን ላይ እንደሚገኝና ይህን ማስተካከል ለነገ የማይባል ጉዳይ እንደሆነ ያሰምርበታል።
ይህን ደብዳቤ አስመልክቶ የ ዐውደ ምህረት ዘገባ፦

Tuesday, May 15, 2012

ዜና ቤተክርስቲያን በ«ቀሲስ» ዶ/ር መስፍን ላይ «የጤና ዶ/ሩ ከክህነታቸው ተሻሩ» በሚል ርእስ ዘገባ አወጣ

Read in PDF
·        «ዶ/ሩ የማኅበረ ቅዱሳን ቀንደኛ አባል፣ … በሥራ  ድክመትና ዛሬ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጃቸውን ግለሰቦች በድርጅቱ ውስጥ በመሰግሰጋቸው ተነቅቶባቸው የተባረሩ ናቸው» ብሏል
·        ማኅበረ ቅዱሳንን በሰይጣን መስሎታል
የዘገባው ሙሉ ቃል ከነትንታኔው ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል
«ዶ/ር መስፍን ተገኝ የተባሉት የማኅበረ ቅዱሳን ቀንደኛ አባል ያለ ሀገረ ስብከቱ ሊቀ  ጳጳስ ፈቃድ በሰሜን አሜሪካ ባሉ ስቴቶች በመዘዋወር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ባደረጉት ኢ-ቀኖናዊ እንቅስቃሴና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ባልጠበቀ ሁኔታ አባቶችን እርስ በርስ የሚያጣላና የሚከፋፍል፤ በማለት የታገዱበትንና ከዚህ ቀደም ድረገጻችን አውጥቶት የነበረውን ደብዳቤ አትሞታል።«ዶ/ር መስፍን ተገኝ ቀደም ሲል በኃላፊነት ይሠሩበት ከነበረው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ በሥራ  ድክመትና ዛሬ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጃቸውን ግለሰቦች በድርጅቱ ውስጥ በመሰግሰጋቸው ተነቅቶባቸው የተባረሩ ናቸው፡፡

በብፁዕ ዐቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው በውጭ ያለው የሲኖዶስ ስብሰባስ እንዴት ነበር?

በዋሽንግተን ዲሲ ከግንቦት 1-3 ስለተካሄደው 33ኛው የሲኖዶስ ስብሰባ አስመልክቶ በርካታ መልዕክቶች እና መረጃዎች በኢ-ሜይል ደርሰውናል። ከዚህ ቀጥሎ የዘንድሮውን ስብሰባ የሚገመግም ጽሑፍ እንዲሁም በመጨረሻ ቅዱስ ሲኖዶሱ ያወጣውን መግለጫ ለአባ ሰላማ አንባቢያን አቅርበናል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ተጋርጦበት ከነበረው አደጋ አመለጠ  
ከላይ ያለው ሊንክ ካልሰራ እዚህ ላይ ይጫኑ 

የተጠቀሰው ርዕስ ላይ በመጫን ሙሉውን ንባብ ከቋጠሮ ድረ ገጽ ላይ ማንበብ ይቻላል። በደረሱን በርካታ የኢሜይል መልዕክቶች መሰረት በጽሑፉ ላይ በተገለጸው ትዕይንት የማህበረ ቅዱሳን እጅ ሊኖርበት እንደሚችል ብዙዎች ጠቁመዋል። በሀገር ቤትም በውጭም መፈናፈኛ ያጣው «ማህበረ ቅዱሳን» የሚሸሸግበት ለመፈለግ በስደት ወዳለው ቅዱስ ሲኖዶስ ጠጋ ጠጋ ማለቱ አይቀርምና ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልን ተጨባጭ ሁኔታዎችን ይፋ ለማድረግ እንሞክራለን። ለዚህም ይረዳን ዘንድ በዓለም ዙሪያ የምትገኙ አንባብያን የምታገኙአቸውን መረጃዎች በመላክ እንድትተባበሩን ጥሪ እናቀርባለን።

ቅዱስ ሲኖሶሱ ያወጣውን መግለጫ ለማንበብ የሚከተለው ላይ ይጫኑ

በዛሬው ጠዋት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ይቀርባሉ የተባሉት የዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ አዘጋጆች ሳይቀርቡ ቀሩ

Read in PDF
ስብሰባው አሁንም በቅዱስነታቸው እየተመራ ይገኛል
አቡነ ሳሙኤልና አቡነ አብርሃም የጋዜጣው አዘጋጆች ይወገዙልን እያሉ ነው።
ሲኖዶሱ በትናንትናው ዕለት ቀኑን ሙሉ በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ላይ በወጣው ጽሁፍ ላይ ሲወያይ የዋለ ሲሆን ወደማምሻው ላይ ፈራ ተባ እያለ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅና ምክትል ዋና አዘጋጅ እንዲጠሩ የወሰነ መሆኑ ታውቋል። ጋዜጣው ላይ ከተጻፈው ሁሉ አብዛኛዎቹን ያበሳጨው ሀብታሞች ናቸው ተብሎ የተጻፈው ሲሆን ነገ ብንለምን ማን ያምነናል በማለት ቁጣቸውን ገልጸዋል። 
ማሕበረ ቅዱሳንን ደግሞ ያቃጠለውና በአባቶች በኩል ሾልኮ ሊገባ የፈለገው በጋዜጣው መንግስት በአሸባሪነት እንደፈረጃቸው መጻፉና ዶ/ር መስፍን መወገዙ መዘገቡ ነው። የማህበሩ አመራሮች በጋዜጣው ክፉኛ የተበሳጩ ሲሆን ወዳጅ ፍለጋና ህዝብ ማሳሳቻ የጋዜጣው አዘጋጅ የማያውቁትና ከውጭ የተዘጋጀ ነው በማለት አለቃቅሰዋል። የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ ግን በጻፉት ጽሁፍ እንደሚኮሩና በእውነተኛነቱም እንደማይጠራጠሩ እየገለጹ ይገኛሉ።

Monday, May 14, 2012

ቤተክርስቲያናችን ውስጥ የተከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት በቅድሚያ ቅዱስ ሲኖዶስ በ1991 ዓ.ም ያወጣውን ህግ ማሻሻል እንዳለበት ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ዘገበ

ከጥቂት አመታት ወዲህ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ በርካታ ችግሮች እየተከሰቱ መሆናቸውን በየጊዜው ከሚዳያዎች እያስተዋልን ነው። የአንዲት ቤተክርስቲያን አባቶችና ልጆች ጎራ ለይተው እየተወዛገቡና አንዱ ሌላውን እየወነጀለ ይገኛል። በዚህ መካከል እየተጎዳ ያለው ምእመኑና አገልጋዩ ነው። በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል በስብሰባ ላይ እየተፈጠረ ያለው አለመግባባትና ክፍፍል ምንጩ ምንድን ነው? የሚለው ብዙ እያነጋገረ ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወደጵጵስና የመጡ አባቶች ማንነት፣ እንዲህ እንዲሆኑ ነጻነት የሰጣቸው ህግና ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በተሳሳተ መንገድ የፈጠሩት «የእከክልኝ ልከክልህ» ግንኙነት ራሳቸውን ትልቅ ትዝብት ውስጥ የጣላቸው ሲሆን፣ ማኅበሩ አፍኜ እይዘዋለሁ ያለውና በሌላ በኩል እየተነፈሰው ውስጥ ለውስጥ ይፋ ያደረገው ብዙ ገበናቸው ቤተክርስቲያኒቱን ስም እያጎደፈና ለብዙዎች መሳለቂያ እያደረጋት መሆኑን የዜና ቤተክርስቲያን ዘገባ ያመለክታል።«ቤተክርስቲያንንና መንጋዎቿን ከወቅታዊ አደጋ ለመታደግ ከግንቦቱ ሲኖዶስ የሚጠበቅ የህልውና ውሳኔ» በሚል ርእስ ጋዜጣው ባሰፈረው ወቅታዊ ጽሑፍ ቤተክርስቲያኒቷ ህልውናዋ በብዙ መንገድ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ገልጿል። የችግሩ ዋና ምንጮችም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መሆናቸውን ያተተው ጽሁፉ፣ ከመነሻው በአሿሿማቸው ውስጥ የምእመናን ተሳትፎ አለመኖሩ፣ በሁሉም አቅጣጫ ለጵጵስና ብቃት ያላቸውና በሰው ፊትም የተመሰከረላቸው እንዲሆኑ የሚያደርግ አንቀጽ አለመካተቱ የችግሩ መንስኤ ነው። በርእሰ አንቀጹ ላይም ጋዜጣው «… በጳጳሳት ምርጫ ጊዜ የካህናትና የምእመናን ተሳትፎ የለም፤ እንደ ስምኦን ቀሬናዊ ቆሞሳቱን ከመንገድ እየጎተቱ ለጵጵስና የሚመርጧቸው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ናቸው።» ብሏል። ይህ ትክክለኛ ምስክርነት ነው። አንዳንዶቹ ጵጵስና የተሾሙት ለቦታው ስለሚመጥኑ፣ ጥሩ የሕይወት ምስክርነት ስላላቸው፣ በትምህርት በኩልም ለሹመቱ የሚያበቃ ትምህርት የተማሩ ስለሆኑ አይደለም። አንዳንዶቹን እንደብፁዕ አቡነ መርሐጽድቅ ያሉት አባቶች «ይህንንስ ጳጳስ ከምናደርገው ብንድረው አይሻልም ወይ?» ሲሉ እንደቀልድ የተወሰደ ግን በኋላ ላይ እውነተኛ ሆኖ የተገኘ አስተያየት ሰጥተው ነበር። ግን ማን ሰምቶ? ይኸው አሁን እንደእነዚህ ያሉት ቤተክርስቲያንን የሚያውኩ ሆነዋል። እንደእነዚህ ያሉትን ሰዎች በጵጵስና መሾም ተመልሶ ራስ ምታት የሆነው ለቤተክርስቲያኒቱ ነው። በዘመናቸው ብዙ ክፍተቶች ያሉትንና የቀደሙትን ሕጎች የተኩትን እነዚህን ህጎች እንዲወጡ የፈቀዱትን ፓትርያርክ ጳውሎስንም ብዙ ዋጋ እያስከፈላቸው እንደሆነ ይታያል።

Sunday, May 13, 2012

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ስላለው የሲኖዶስ ስብሰባ ዙሪያ ሦስት ዋና ዋና ዘገባዎች

በትናንትናው ዕለት በአቡነ አብርሃም ቤት ልዩ ስብሰባ ተካሄደ
ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት ብሎግ
የዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ እና የአቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካ መነሳት አጀንዳዎች ነበሩ፡፡
በትናንትናው ዕለት አቡነ አብርሃም ቤት እስከ ምሽቱ የዘለቀ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን ስብሰባውም ሁለት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል፡፡ የመጀመሪያው በዛሬው ዕለት በቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያ አጀንዳ የሆነውና አብዛኛዎቹን ጳጳሳት ያለልዩነት በአንድ ጎራ ላይ ያቆመው የዜና ቤተክርስቲን ጋዜጣ ዘገባ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሲኖዶሱ በአጀንዳነት አለመያዙ አቡነ አብርሃምንና ማኅበረ ቅዱሳንን እጅግ በጣም ያበሳጨው የአሜሪካ አኅጉረ ስብከት ጉዳይ እንደገና ወደ አጀንዳ የሚገባባት መንገድን ማመቻቸት ነው፡፡ 

Friday, May 11, 2012

ደብዳቤው የማን ነው?

Read in PDF

በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰራተኞች ስም “ተበተነ” የተባለው ደብዳቤ የተረቀቀውና የተሠራጨው በማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ እና የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞች ሐሳብ አለመሆኑ ተገለጸ

በዓመት ሁለት ጊዜ የሚደረገውን መደበኛ የሲኖዶስ ስበስባ ከመበጥበጥ ቦዝኖ የማያውቀውና የተለያዩ የራሱን አጀንዳዎች የቤተክርስቲያኗ አጀንዳዎች አስመስሎ በመቅረጽና በተለያዩ መንገዶች አሳስቶና አስፈራርቶ የሀሳቡ አስፈጻሚዎች ባደረጋቸው አንዳንድ ጳጳሳት በኩል ለሲኖዶስ እንዲቀርብለት ከፍተኛ ገንዘብ እየመደበ ሲያውክ መኖሩ የሚታወቅ ነው። በዚህ በግንቦቱ ሲኖዶስ ላይም ቤተክርስቲያኗን የሚበጠብጥበትን መላ ሲዘይድ እንደሰነበተና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰራተኞች ስም ደብዳቤ አርቅቆ እንደበተነ ውስጥ አዋቂ ምንጮች እየተናገሩ ነው።የጠ/ቤተ ክህነቱ ሠራተኞችየዳኛ ያለህ! ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዳኝነት ይታይላትየሚል ጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አሰራጩ” በሚል ርእስም፣ በግልጽ የሚሰሩት የማኅበሩ “ስውር” ድረገጾች ደጀሰላምና አንድ አድርገን ወሬውን አናፍሰውታል።

ሰበር ዜና፦ መጋቢ ሀዲስ በጋሻው ደሳለኝና አባ ሠረቀ ብርሃን ከኑፋቄ ክስ ነጻ ወጡ?

በግንቦት 2 ቀን 2004 ዓ/ም ቀጥሎ በዋለው የሲኖዶስ ስብሰባ መጋቤ ሀዲስ በጋሻው እና አባ ሠረቀ ወ/ሳሙኤል ማቅ  «የሐይማኖት ህጸጽ» አለባቸው ብሎ ያቀረበው ክስ ተመርምሮ  ከክሱ ነጻ እንደወጡ ዐውደምህረት ዘገበች።  ነገሮች በፖለቲካዊ አሰራር በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ሊቀለበሱ የሚችሉበት ሁኔታ ሊኖር ስለሚችል አባ ሰላማ ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለችው ነው።  ስለሆነም  እውነታነቱን አረጋግጠን የመጨረሻውን ውሳኔና  የጉዳዩን ዝርዝር ለአንባብያን ለማቅረብ እየሰራን መሆኑን እንገልጻለን። እውነት ታሸንፍ ዘንድ ጸሎታችን ነው። ዝርዝሩን ይጠብቁ - - -

Wednesday, May 9, 2012

የዘንድሮው የግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ማኅበረ ቅዱሳን አንገት በደፋበት፣ ደጋፊው የነበሩት ጳጳሳት በተሻማቀቁበት ሁኔታ እንደሚካሄድ ይጠበቃል

ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የማኅበረ ቅዱሳን አንዱ ስራ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደውን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በውጥረት ውስጥ እንዲካሄድ ማድረግ ነው። ለወትሮው ከሲኖዶስ ስብሰባ ቀደም ብሎ ማኅበረ ቅዱሳን በሚከፍላቸውና በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ጫና ለማሳደር በሚል በሚከፈቱት የግል ጋዜጦችና መጽሔቶች ብዙ ብዙ እያጻፈና እርሱ እንዲቀርብለት የሚፈልገውን አጀንዳ የቤተክርስቲያን አጀንዳ አስመስሎ በማስተጋባት፣ የሲኖዶሱን ስብሰባ አቅጣጫ ለማስለወጥና አባቶች እንዳይስማሙ፣ ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ውሳኔ እንዳይወስኑ በመከፋፈልና በገንዘብ በመደለል ሁሉ ቤተክርስቲያንን ሲያውክ ለመኖሩ ያለፈው የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ጥሩ ማሳያ ነው። በግንቦቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ግን ጋዜጦችና መጽሔቶች ይህን ዜና እንዳትዘግቡ የተባሉ ይመስል ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ዝምታን የመረጡ ይመስላል።ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የማኅበሩን ማንነት “አክራሪ” በሚል ከገለጹት ወዲህ በማኅበሩ ውስጥ ፍርሀት ነግሷል ነው የሚባለው። ሚያዝያ 30 ለንባብ የበቃው መፍቀሬ ማህበረ ቅዱሳን የሆነው “ፍኖተ ነጻነት” የተባለው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍተሕ ፓርቲ (አንድነት) ልሳን “የፖለቲካው ውጥረት ሩብ ጉዳይ።” በሚል ርእስ ስር ባቀረበው ጽሁፍ ውስጥ እንዲህ የሚል ሀሳብ ሰፍሯል። አንዳንድ የኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታዮችም የሃይማኖት መሪዎቻቸውን እንደ መንግሥት ‹‹ካድሬ›› ይቆጥሯቸዋል፡፡ ስሙን እንዳልጠቅስ ያስጠነቀቀኝ አንድ መምህር ግን የማህበረ ቅዱሳን ራሱን ነጻ አድርጎ ለመጓዝ ያደረገው ጥረት ለምእመናኑ መጽናኛ ሆኗቸዋል፡፡ ሰሞኑን አቶ መለሰ ለፓርላማ ባቀረቡት ንግግር ማህበረ ቅዱሳንን ከሙስሊም ጽፈኞች መሳ ለመሳ መፈረጃቸው ተዳፍኖ የቆየውን ተቃውሞ እንዲያገረሽ ምክንያት ሆኗል፡፡ ሆኖም ማህበሩን ወክለው ስሜታቸውን የሚያጋሩኝ ኃላፊዎችን ለማግኘት አልቻልኩም፡፡ መረጃ የሰጡኝ አካላትም ስማቸውንና ኃላፊነታቸውን ደብቀውኛል፡፡ የሚገርመው ሁሉም የጠቆሙኝ አደባባይ በተባለ የጡመራ መድረክ ላይ ኤፍሬም እሸቱ ያሰፈረውን ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ አባባል አልስማማም›› የሚለውን ጽሑፍ ነው፡፡ ‹‹የማህበሩን አቋም በድረገጻችን ላይ አስፍረናል፤ ተጨማሪ ነገር ለመናገር አልፈልግም›› ያሉኝ አንድ የማህበሩ ኃላፊ በደምሳሳው የአቶ መለሰ አስተያያት ስህተት ላይ የተመሠረተ መሆኑን በምክንያት አስደግፈው አስረድተውኛል፡፡ በኃላፊው ማብራሪያ መሠረት ማህበሩ የጥምቀት በአል አከባበርን በበላይነት አስተባብሮ አያውቅም፡፡ ስለዚህም በበአሉ ላይ የሚስተጋቡ መፈክሮች ይዘት ስህተት አይደለም፡፡ ቃሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡›› ካሉ በኋላ አክራሪነቱ ግን እንደማይመለከታቸውና ክርስትናም እንደማይፈቅደው አብራርተዋል፡፡ በኦርቶዶክሳውያኑ የሚነሳውን ጥያቄ ካባባሱት ክስተቶች መሀከል በዋልድባ ገዳም ላይ ተጀመረ የሚባለው ልማት በመነኮሳቱ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም በሃይማኖቱ ተከታዮች እና በመንግስት መሀከል የፈጠረው ውጥረት ሌላው የተቃውሞው አካል ነው፡፡ (ገጽ 14) ሲል ማቅ የሚገኝበትን ተጨባጭ ሁኔታ አስነብቦናል። የማኅበሩ ሰዎች የጠቆሙትን የኤፍሬም እሸቴን ጽሁፍና የማኅበሩን አቋም ድረገጻችን ሰፊ ምላሽ የሰጠበት መሆኑ ይታወሳል።

ማኅበረ ቅዱሳን በሲኖዶሱ ስብሰባ ሊያሳካቸው የሚፈልጋቸው ግቦች ዋነኛው የአቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካው አኅጉረ ስብከት መነሳት ነው።

ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት ብሎግ
የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ይጀምራል። በዚህ ስብሰባ ላይ ማኅበሩ ሊያሳካቸው የሚፈልጋቸው በርካታ አጀንዳዎች እንዳሉትና እነርሱንም ለማሳካት ማንኛውንም ጥረት እንደሚያደርጉ በተለያዩ መንገድ እየገለጹ  ይገኛሉ። በድረ ገጾቻቸው ከሚያሰሙት ኳኳታ በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስ አፋቸውን ከፍቶ ፊታቸውን ጸፍቶ በየሜዳው እያስለፈለፋቸው ዘንድሮ አሳባቸውን ለማሳካት እስከ ደም ማፍሰስ ድረስ የሚሄድ ዝግጁነት እንዳደረጉ በደብረ ብርሀን ከተማ እጁን በደም የታጠበው ማን ያዘዋል ነግሮናል። እራሱን ሳያዘጋጅና ሳያስብበትም ሰለፊያ ወካይ ስማቸው መሆኑን ነግሮናል። ሲኖዶሱ ለማኅበረ ቅዱሳን ሀሳብ የማይገዛ ከሆነ በ2001 ዓ.ም. ተከስቶ የነበረውን ሁኔታ እንደግመዋለን ሲል እግረ መንገዱን በ2001 ዓ.ም. የነበረውን ግጭትና የፓትርያርክ የማውረድ ሙከራ ከጀርባ ሆኖ ሲመራው የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን ነው ሲል ባልተራመ አንደበቱ፣ ጨዋነትን ባጣ ቋንቋና ትዕቢት ገልጿል።
 እንዲያውም ሲኖዶሱ የሚሰበሰበው ማኅበረ ቅዱሳን ሰርቶ የጨረሰውን ጉዳይ ለማጽደቅ ነው ሲል የመንፈስቅዱስን ቦታ ነጥቆ ለማኅበረ ቅዱሳን ሠጥቷል። ከታሪክ የማይማሩትና ተንኮልና ገንዘብ ብቻቸውን የምንፈልጋቸውን ነገር ለማድረግ በቂያችን ነው ብለው የሚያስቡት የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጸሎት ትተው እንደ ማራቶን ሩጫ የተንዛዛና እንደ ጀማሪ ማራቶን ሯጭ የተጎተተ ስብሰባ የሚያበዙትም ስለዚህ ነው። የነ ማን ያዘዋልን የታክሲ ላይ ውይይት እዚህ ላይ በመጫን ከደጀ ብርሃን ብሎግ ያንብቡ
ለዛሬ ማኅበረ ቅዱሳን ካልተፈጸሙ ሞቼ እገኛለሁ ከሚልባቸው ጉዶዮች አንዱን እናቀርባለን።

Monday, May 7, 2012

እያረፈበት ያለው ትችት እያደከመው ያለው ማኅበረ ቅዱሳን እባካችሁን ተውኝ ሲል ተማጸነ

ተማጽኖው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በማኅበሩ ላይ ለተናገሩት የተሰጠ መልስ ነው ተብሏል
የዘራውን በማጨድ ሥራ የተጠመደው ማኅበረ ቅዱሳን በስሙ በሚጠራው ድረገጹ ላይ “ማሩ አይምረር፤ ወተቱ አይጥቆር” በሚል ርእስ እባካችሁን ተውኝ የሚል አይነት ተማጽኖ አቀረበ። ድረገጹ ሚያዝያ 24/2004 ዓ.ም በሰቀለው በዚህ ጽሑፍ ላይ እንደወትሮው ሁሉ የተለመደውንና እንደሞኝ ዘፈን በየቆመበት ሁሉ የሚደጋገመውን አንድ አይነት ፈሪሳዊ ጽድቁን በማስተንተንና ራሱን እንከን የለሽ አድርጎ በማቅረብ ሐተታውን የጀመረው ድረገጹ፣ አክራሪ የሚል ስም የተሰጠኝ ለቤተክርስቲያን የድርሻዬን ስለተወጣሁ ነው ሲል ተከራካሪ ባጣበት በዚህ ሰአት ለራሱ ጠበቃ ሆኗል።ማኅበሩ ምንም እንኳን ማኅበሩን በራሳቸው ፈቃደኝነት የተሰባሰቡ ኦርቶዶክሳውያን ቢመሠርቱትም የማኅበሩ መሠረታዊ ዓላማ ግን ቤተ ክርስቲያን ተልእኮዋን ለማሳካት በምታከናውናቸው ተግባራት የልጅነት ድርሻውን” መወጣት ነው ብሎ በወረቀት ላይ የሰፈረ ደንቡን ቢያነበንብም፣ በተግባር እያደረገ ያለው ግን ከዚያ በተቃራኒው መሆኑን ከማኅበሩ ፍላጎትና አላማ፣ እንዲሁም ፍላጎቱንና አላማውን ለማሳካት ከሚያደርገው ግልጽና ስውር አካሄድ መገንዘብ ይቻላል። ማኅበሩ እንዳለው መሰረታዊ አላማው ቤተክርስቲያን ተልእኮዋን እንድታሳካ የድርሻውን መወጣት ነው ወይስ በቤተክርስቲያን ስም የራሱን ዝናና ክብር እየካበ ራሱን ከፍ ማድረግ? የሚለውን ከአባላቱና አመራሮቹ፣ እንዲሁም ከጭፍን ደጋፊዎች ይልቅ ትክክለኛ ማንነቱን በማስረጃ በተደገፈ ሁኔታ እየገለጡ ያሉት ወገኖች ቢናገሩ ይሻላል። መጽሐፍም “ሌላ ያመስግንህ እንጂ አፍህ አይደለም ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይደለም።” ይላል (ምሳ. 27፡2)።

የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ከገቡበት አጣብቂኝ ለመውጣት ወደ ፓትርያርኩ ቢሮ እግር አብዝተዋል

 • የማቅ ተከፋዩ አባ ኅሩይ ማኅተም ይዘው ተሰውረው ሰነበቱ
 • ዘግየት ብሎ በዐውደ ምህረት ድረገጽ እንደተዘገበው አባ ኅሩይ (የሰንበት ማደራጃና መምሪያ ኃላፊ) ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደርገዋል
የማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ አመራሮች ሰሞኑን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጽ/ቤት ወጣ ገባ ማለት ይዘዋል። ምንጮቻችን እንደጠቆሙት የማቅ አመራሮች የሚመላለሱበባቸው ሁለት ዋነኛ ጉዳዮች አሉዋቸው። የመጀመሪያው ከአባ ሠረቀ ብርሃን ጋር በዋናነት ያጣላቸውና “ሂሳባችሁን አስመርምሩ። ያላችሁን የገንዘብ ዝርዝር አሳውቁ። ገንዘብ አጠቃቀማችሁ ግልጽና ተጠያቂነት ያለው ይሁን።” የሚለው አጀንዳ እንደገና ስለተቀሰቀሰ እሱ “አይሁን አይደረግብን” ለማለትና የቅዱስነታቸውን ልብ ለማራራት ነው። ሁለተኛውና ዋነኛው ደግሞ ቅዱስነታቸው የማህበሩ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጣቸው የግብር ስም ከሰለፊያ ዝቅ ያለ እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ፓትርያርኩ መንገድ እንዲያዘጋጁላቸው ለመጠየቅ ነው።

Friday, May 4, 2012

አንዳንድ የማቅ አባላት የሲ. አይ. ኤ. ሰላዮች ሆነው ተገኙ

ቤተ ክህነት አካባቢ “የቀን መጋኛ” በመባል የሚታወቀው ባያብል ሙላቱ የሰጠውን መረጃ ዊኪሊክስ (wikileaks) ይፋ አድርጓል
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
ምንጭ፡ ዐውደ ምሕረት ድረ ገጽ
በርካታ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ሌሎች ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት የተለያየ ነው። ማኅበሩ እውነተኛ ማንነቱን ደብቆ በቅድሚያ ቤተክርስቲያንን ከዚያም የመንግስትን ሥልጣን ለመያዝ በግልጾቹም በስውሮቹም አመራሮች እየተደገፈ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችን አባላቱ በቅጡ አልተረዱም። ቤተክርስቲያን እኛ ባንኖር ኖሮ ጠፍታ ነበር። ያለንላት እኛ ነን። ቤተክርስቲያን ሰው ስለሌላት አስራታችሁን ለማኅበረ ቅዱሳን አውጡ በማለት የሚያሰወራውን ወሬ  እና በአካፋ ተቀብሎ በማንኪያ የሚሰጠውን ስጦታ በማመን የተታለሉ ወገኖች ይገኛሉ። እውነቱን ከማህበሩ ጋር ለበርካታ አመታት በቅርብ የሰሩ ወገኖችና እንቅስቃሴውን በሙላት የተረዱ የቤተክርስቲያን ልጆች ያውቁታል። 

Thursday, May 3, 2012

የበአታ ለማርያም የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤት ግንባታና የማቅ ፕሮፓጋንዳ


ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኘውን የደብረ ኀይል ወደብረ ጥበባት በዓታ ለማርያም የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤትን በ4.6 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ሚያዚያ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. የግንባታ ውል ስምምነት መፈራረሙን የማኅበሩ ድረገጽ ሚያዝያ 18/2004 ዓ.ም ገለጸ፡፡ ማኅበሩ በጠቅላይ ቤተክህነት አምሳል በስሩ ካደራጃቸው ክፍሎች አንዱ በሆነው “የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል” ይህ ፕሮጀክት እንደሚከናወን ማኅበረ ቅዱሳን አስታውቋል፡፡

በፊርማው ስነስርአት ላይ ማኅበሩን ወክሎ የፈረመውና የተናገረው ዲ/ን ሙሉጌታ ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹ 4.6 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ፕሮጀክት ቀርጾ የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤት ለመገንባት ከዚህ በፊት አድርገነው አናውቅም፡፡ ይህ ትልቅ እድገት ነው፡፡ ምእመናንም ማኅበረ ቅዱሳንን ማመን የቻሉበት ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ ማኅበረ ቅዱሳን ይሥራው ለማለት መቻል ሙሉ ለሙሉ በማኅበሩ ላይ እምነት እንዳሳደሩ ነው የሚያሳየው፡፡ እኛም በታማኝነት ትኩረት ሰጥተን እንድንሠራ የሚያደርገን ነው፡፡ ጨረታውን ከብዙዎቹ የሕንጻ ሥራ ተቋራጮች ጋር ተወዳድሮ ያሸነፈው ድርጅት በማኅበሩ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገና አብሮ የኖረ ነው፡፡ ሥራውንም በጥራትና ከተያዘለት ጊዜ ቀደም ብሎ በማጠናቀቅ ያስረክባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን በኩልም ሥራውን ለማፋጠን አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጣለሁ›› በማለት ገልጿል፡፡

Wednesday, May 2, 2012

ይድረስ ለመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው

እርስዎ በብፁዕ አባታችን በአቡነ ጎርጎርዮስ ጥቂት ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተምረው መልካም መንፈስ እንደነበረዎት ጓደኞችዎ ይመሰክራሉ፤ ለእግዚአብሔር ወንጌልም ቀናተኛ ደቀ መዝሙር ነበሩ። አሁን እያስተማሩት ያለው ትምህርት ግን በሰውም ሆነ በጌታ ዘንድ ያስጠይቀዎታልና በብሎግዎ ከጻፉት ላይ አንዳንድ ኦርቶዶካስዊ ያልሆኑ ትምህርቶችን እንዲያርሙ ልጠቁመዎት ወደድሁ። ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር!
መልክአ ሚካኤል በሚለው ርእስ ከጻፉት ውስጥ፦
 «መልክዕ፦ ቅዱሳን የሚመሰገኑበት መንፈሳዊ ድርሰት ነው። ከራስ ጠጉራቸው ጀምሮ እስከ አግር ጥፍራቸው ድረስ ያለውን የአካላቸውን ክፍል እየዘረዘረ ያመሰግናቸዋል» ብለዋል።
ቅዱሳን መላእክት ሰማዕታት እና ጻድቃን ክቡራን ናቸው። ያከበራቸውም ብቻውን ሌላ ሳይጨምሩ ሁልጊዜ በመንፈስ የሚያመልኩት ሕያውና ቅዱሱ አምላክ ነው። መላእክትም ይሁኑ ሰማዕታት ቅዱሳን ሁሉ የቅድስናቸው ምስጢር አንዱን አምላክ ማምለካቸው ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናውቃቸው ቅዱሳን ሁሉ ዝማሬያቸው፣ ምስጋናቸውና ቅዳሴያቸው ሁሉ ለአንዱ ለሥላሴ ብቻ ሆኖ ነው የምናገኘው። እርስዎ እንደሚያስተምሩት ቅዱሳን ሌሎች ቅዱሳንን ከራስ ጸጉራቸው እስከ ጥፍራቸው ድረስ ግጥም እየገጠሙ ምስጋና ሲያቀርቡላቸው አንድም ቦታ አናይም። እኛም የአባቶቻችን ነቢያትና ሐዋርያትን ፈለግ ተከታዮች ነንና አንዱን ቅዱስ አምላክ ብቻ ልናመሰግን ይገባል። ለምሳሌ ሙሴ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ የተገለጠውን አምላክ ስሙን እየጠራ አመሰገነ እንጂ የነርሱን ጸጉርና ጥፍር እየጠቀሰ ሲያመሰግን አናነብም። ኢያሱም የሙሴን አምላክ እንጂ ሙሴን ሲያወድስ አናይም፤ ነቢያትም ሁሉ ነገሥታትም ሁሉ ምስጋናቸው ለእግዚአብሔር ነው።