Tuesday, May 1, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግርና የአንድ አድርገን ዘገባዎች

አንድ አድርገን የተባለው የማኅበረ ቅድሳን ብሎግ በማኅበሩ “ግልገል ካድሬዎች” የሚዘጋጅ  ብሎግ ነው። ማኅበርዋ በተለመደው እናንተ ባትኖሩ ቤተክርስቲያን ትጠፋለች የሚለው አታላይና ስሜት ቀስቃሽ “ወንጌሏ” ቀልባቸውን ሰልባ ለሥራ ያነሳሳቻቸው ሕጻናተ አእምሮ አባላትዋ የማኅበረ ቅዱሳን ስውሩም ግልጹም አመራሮች የሚያዙባትና እንቅስቃሴዋን በንቃት እየተከታተሉ ከማኅበሩ የመረጃ ክፍል የሚገኙ መረጃዎችን እንደ ወረደ በግልብ ስሜት ባልታረመ ብዕር ተጽፈው የሚቀርቡባት ስድ ብሎግ ስትሆን የአጻጻፍ ስልትዋና የቋንቋ አጠቃቀምዋ ከማህበሩ ሌሎች ብሎጎች ለየት ያለ ነው።
ጸሀፊዎቹ “ሕጻናት” ስለሆኑ በአፃፃፍ ስልታቸው በማስመሰል እንኳ ሊደብቁት የሚገባቸውን ከማኅበሩ ጋር ያለቸውን ግንኙነት ለመደበቅ አልተቻላቸውም። ሕጻን መች ይደብቃል። ለማህበራቸው ማኅበረ ቅዱሳን ያላቸው አመለካካት ከጭፍን ፍቅር የመነጨና በተለይ ማኅበሩ የተወቀሰ ዕለት እሳት እንደበዛበት ሽሮ በቶሎ የሚገነፍል ነው።
ማኅበረ ቅዱሳን ከመንግስት ጋር ያለውን የአቋም ልዩነት እንደነ ደጀ ሰላምና ገብርሄር አጠይሞ ሣይሆን በግልጽ አቋሙን የሚያሳውቅበት አንድ አድርገን፣ በውስጣቸው ያለውን ፓለቲካዊ ማንነት በግልፅ እንዲታይ ጥረት የሚያደርጉበት አንድ አርገን፣ ከዚህ ማንነታቸው በመነሳትም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ሕፃን በሆነው አእምሮአቸው ለመውቀስ ሞክረዋል ሲጀምሩም እንዲህ ነበር ያሉት።
“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምክር ቤቱ አባላት በተነሱላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተው ነበር ፤ ስለ ሀይማኖት አክራሪነት ላይ በተነሳው ጥያቄ ላይ በተነሳ ጥያቄ ላይ ውሀቢዝምን ካስረዱ በኋላ አንዳንድ የዚህ አይዲዎሎጂ ተከታይ የሆኑ ሰዎችን ‹‹የማህበረ ቅዱሳን ተቃራኒ›› በማለት መስለዋቸዋል ፤ ይህ ምን ማለት ነው? ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የተረዱት ማህበረ ቅዱሳን የሀይማኖት አክራሪነት የሚያራምድ ማህበር አድርገው ነው የሚያስቡት ፤ ሰው ሀይማኖቱን ሲጠብቅ እንዴት አክራሪ ይባላል? ፤ ከአባቶች የተረከቡትን እምነታቸውን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ስራ ቢሰሩ እንዴት የሀይማኖት አክራሪዎች ሊባሉ ይችላሉ ? ፤ ጠቅላይ ሚኒስትራችን የእውቀት ማነስ ከሌለብዎ በስተቀር ይህን ማለት ባልቻሉ ነበር ፤ እኔ በበኩሌ ወሀቢዝም የሚለውን አይዲዎሎጂ በመሰረቱ የገባዎት ራሱ አይመስለኝም ፤ አለማወቅ ሀጥያት አይደለም ነገር ግን አለማወቅን እንደ እውቀት ቆጥሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ በምክር ቤቱ ተገቢ ያልሆነ አስተያየት መስጠት ተገቢ አይደለም ፤”
በመጀመሪያ ደረጃ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስረዱት ስለወሀቢዝም ሳይሆን ስለሠለፊያ ነው። የሠለፊያ አባላት በቅርብ እንኳ በግብጽ ምርጫ እንዳይወዳደሩ ታግደዋል። ቀጥተኛ አላማቸው በከፍተኛ የአክራሪነት ስሜት ተነሳስተው ሙስሊም ባልሆነ ሌላ ህዝብ ላይና በጠቅላላው በሙስሊሙም ማኅበረሰብ ላይ አምላክህን የምታገኘው እኛ ባልንህ መሰረት ነው። ከዚያ ውጭ ሌላው መንገድ ወደ ሞት ስለሚያደርስ እኛ ቀድመን እናስወገድህ የሚል አይነት ነው። ከዚህ አንፃር እስኪ ማህበረ ቅዱሳንን እንመዝነው።
ማኅበረ ቅዱሳን በጎንደር በደብረማርቆስና በደብረ ብርሃን በፕሮቴስታንቶች ላይ፣ በሐረር፣ በመቀሌ፣ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በጎንደር በአዋሳና በሌሎችም ከተሞች “ተሀድሶ” ብሎ በጠመዳቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ ያደረሰውን የድብደባና የሕይወት ማጥፋት ወንጀሎች ለማስተባባል የመጣለትን የሚናገረውና ማመዛዘን የማይችለው ሕጻነ አእምሮው አንድ አድርገን አቅም ያለው አይመስለንም። ስለደብረ ብርሀኑ ዘግናኝ ወንጀል በተለይ ነጭ ለባሹ ማንያዘዋል በግልጽና በጀብደኝነት ስሜት ምን እንዳደረገ እዚያው ቢሮዋችሁ ሊነግራችሁ ይችላል። ጥያቄውን ከፈለጋችሁ ሥላሴ ኮሌጅ እንዴት ገባህ? ብላችሁ መጀመር ትችላላችሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበረ ቅዱሳንን አክራሪ ያሉት አንድ አድርገን እንዳለው ሃይማኖቱን ስለጠበቀ አይደለም። በሀይማኖትና በሃይማኖተኛነት ስም ሌሎችን ስለሚገድል ስለሚያሳድድና በግልጽ ኢትዮጵያን በመሰለ ግማሽ የሚሆነው ህዝብዋ ኦርቶዶክሳዊ ባልሆነባት አገር ስለመንግስታዊ ሀይማኖት አስፈላጊነት አጥብቆ ስለሚሰብክና ለዚህም እንደሚታገል ስለሚገልጽ ነው። ሀይማኖት ጠባቂነት መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው በማስተማርና መኖር ነው እንጂ ሰይፍ መዞና ድንጋይ ጨብጦ “ጉዳዩ የክር ጉዳይ ነው ለሃይማኖቴ እገላለሁ” ማለት አይደለም። ይህ አክራሪነት ነው። ማኅበረ ቅዱሳን “የጥምቀት ተመላሽ” የሚላቸውን ወጣቶች ያደራጃቸው ስለሃይማኖት  እንዲያሳድዱ፣ እንዲደበድቡና እንዲገድሉ እንጂ ከሱስ ተላቀው ህብረተሰቡን ከማወክ ነፃ ወጥተው እንደ መጽሀፍ ቅዱስ ትምህርት እንዲኖሩ ለማድረግ አይደለም። ለነገሩ ከጥምቀት ሲመለሱ ሰክረውና “ጨርቅ ሆነው” ነው። ብዙ ወጣቶችን በከተራ እና በጥምቀት ዕለት እንዲህ ሆነው ማየት ተለመደ ነው። ይህም የማቅ ውጤት ነው። እርሱ የመለመላቸው ለአሸባሪ ተግባሩ እንጂ የእነርሱ ሕይወት በቃለ ወንጌል ተለውጦ ለራሳቸው መዳን እንዲሆንላቸው፣ ለቤተ ክርስቲያናቸውም ተስፋ እንዲሆኑ አይደለም። ስለዚህ እንደተሰበከላቸው አሸባሪነታቸውን በተክለ ሐይማኖት፣ በዑራኤል፣ በእግዚአብሄር አብና በሚካኤል በተግባር አስመስክረዋል።
ቢያንስ ዑራኤልና ተክለ ሃይማኖት አካባቢ ያሉ የቤተክርስቲያን ልጆችን ለመደብደብ የሚሯሯጡት ልጆች ምንም አይነት መንፈሳዊነት የሌላቸው እና አሁንም ከሱስና ከነውር ስራዎች ያልተላቀቁ መሆናቸውን እናውቃለን። ማኅበረ ቅዱሳንም የሚፈልገው ሕይወታቸውን ሳይሆን ጉልበታቸውን ስለሆነ ልጆቹን እያስተማራቸው ያለው ቤተክርስቲያንን በጉልበታቸው እንዲጠብቁ እንጂ ሕይወታቸውን ለክርስቶስ እንዲሰጡ ስላልሆነ በልጆቹ ህይወት ምንም መንፈሳዊ ለውጥ ማየት አልተቻለም። ልጆቹም ሰው በደበደቡ ቁጥር ቤተክርስቲያንን ያገለገሉ እየመሰላቸው እየተደባደቡ ይኖራሉ። አንድ አድርገን ይህ ከቶ ምን ይሆን? የእናንተ አእምሮ እንደሚተረጉመው ከአባቶች የተቀበሉትን ሃይማኖት ለልጆች ማውረስ ትሉ ይሆናል እኮ?
ጠቅላይ ሚኒስትሩን የእውቀት ማነስ አለብዎት ሲል በድፍረት የተሳደበው አንድ አድርገን እውቀት እንዴት እንዳነሳቸው ያስረዳን ከእርስዎ በላይ አውቃለሁ በማለት ነው። ጉድጓድ ውስጥ ያለች እንቁራሪት የሰማዩ ስፋት በጉድጓዱ አፍ ልክ ይመስላታል!! አሉ። ይደንቃል! ምን እየፃፋችሁ እንደሆነ እንኳ ያልገባችሁ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን በእውቀት ማነስ መተቸታችሁ ያስገርማል። ለእናንተ ዕውቀት ማለት ያችው ማህበራችሁ በመቁኑን እየሰፈረች የምትሰጣችሁ “መረጃ” ነች። ለእናንተ እውነት ማለት ማህበራችሁ የሚያደርገውና እንደ በጎ ምግባር የሚያወራው ክፉ ሥራው ብቻ ነው። ዕውቀትን በተመለከተ እንኳን በእናንተ በተረት አባቶቻችሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዕውቀት አይታሙም።
“ማህበሩን ለማያውቀው ሰው እንዲህ ነው ብሎ ለንግግር ማጣፈጫዎ መጠቀምዎ ተገቢ አይደለም ፤ ከበታችዎ ያሉት ሰዎች እውነቱን ሳይሆን መስማት የሚፈልጉትን ነገር ነው የሚግርዎት ፤ ከወራት በፊት ሳያስቡ የሚናገሩት አቦይ ስብሀት ‹‹ማህበረ ቅዱሳን የቤተክህነት እዳ ነው ›› በማለት ከአንድ የሀገር ሽማግሌ ሊጠበቅ የማይችል ንግግር በአደባባይ ተናገሩ ፤ እኔ በበኩሌ እርጅና ሊሆን ይችላል በማለት አልፌዋለሁ ፤ ሰው ሲያረጅ ወደ ህጻንነት ይመለሳል ይባላል ፤ ይህ ነገር እውነት መሆኑን የዛኔ ነው ያየሁት ? በዚህ አጋጣሚ ጭንቅላት ያለው ሁሉ አያስብም የሚል ጥቅስ በልጅነቴ አንብቤ ነበር  ፤ ለካንስ እውነት መሆኑ የገባኝ ዘንድሮ ነው ፤ ያኛው የትግል አጋርዎ በቅርቡ በውጭ ሚዲያ ሀገራችንን የማይመጥን አሳፋሪ ቃለ መጠይቅ ያደረገው አቶ ታምራት ላይኔ ፓትርያርክ ሸኝቶ ፓትርያርክ ሲያመጣልን ፤ አቦይ ስብሀት ደግሞ መደራጀቱ ያላማራቸው ማህበረ ቅዱሳን ላይ የቃላት ጦርነት ይከፍቱ ጀመር ፤ ቤተክርስትኒቷ ጌታ በወንጌል ‹‹ አይችሉሽም››ተብላለች ፡፡”
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለማህበሩ የተናገሩት ለንግግር ማጣፈጫነት አይደለም። የጽዋ ማህበራችሁ የመንግስትም የቤተክርስቲያንም ሸክምና ችግር ስለሆነ ነው እንጂ። ደግሞስ የትኛው ጨውነታቸሁ ነው ለንግግር ማጣፈጫነት እንድታገለግሉ የሚያደርጋችሁ? እናንተ እኮ ጣዕም የለሽ አልጫዎች ናችሁ። ከበታች ያሉ ሰዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እውነቱን ቢነግሯቸው ኖሮማ እስካሁንም ማህበሩ በትክክለኛ ቦታው ላይ ተቀምጦ በተገኘ ነበር። ይህንንም እሳቸው የተረዱት አልፈው በሚወጡ ነገሮች ነው። የእናንተ የአሸበሪነት ልክ እኮ ከደርብ በላይ ነው። ሞልቶ ከፈሰሰው ያወቁትን እውነት ነገሩን እንጂ እናንተማ እንድ ቀንም እንኳን እንድትኖሩ የማያሰነብት ግፍና የህዝብ ደም ያለባችሁ ናችሁ።
አቦይ ስብሀት “ማህበረ ቅዱሳን የቤተከህነት ዕዳ ነው” ብለው መናገራቸውን የማንነትህ መገለጫ የሆኑ ተራና ተልካሻ ቃላትን ተጠቅመህ ወቅሰሃቸዋል። እግረ መንገድህንም የስድብ ሊቅነትህን በጥቅስ ለማስደገፍ ሞክረሀል። እኛ በበኩላችን ከአቦይ ስብሀት ከሰማናቸው ቁም ነገሮች አንዱ እና ዋነኛው ይህ ንግግራቸው ነው እንላለን። ማቅን ለመግለጥ ጥሩ ቃል ቸግሮን ነበር አሳቸውም “የቤተክህነት ዕዳ ነው” ብለው በዐጭር ቃል በሙላት ገልጸውታል። በዚህ እናመሰግናቸዋለን። ማቅ የቤተክህነት ዕዳ ለመሆኑ የሲኖዶስ ስብሰባ ሲደርስ የስብሰባውን አቅጣጫ ለማስቀየርና እርሱ በሚፈለግው መንገድ ለመንዳት አመራሮቹ የሚያደርጉትን ዕንቅልፍ አልባ ሩጫ በግልጥ ያስረዳል።
አቦይ ስብሀትን ለመንካት ማህበረ ቅዱሳን “መደራጀቱ ያላማራቸው ማህበረ ቅዱሳን ላይ የቃላት ጦርነት ይከፍቱ ጀመር” ብለሀል። መደራጀት ለምን? የቤተክርስቲያን ልጆችን ለማሳደድ? ፓትርያርክን ለማውረድ? የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ? መልስ ይኖርህ ይሆን? አይመስለኝም። ይህንን የአቦይ ስብሃት ንግግር ለማርከስ በማሰብ ባለቤትና ማሰሪያ አንቀጽ ባልተስማማበት አረፍተ ነገርቤተክርስትኒቷ ጌታ በወንጌል ‹‹ አይችሉሽም›› ተብላለች ፡፡”ብለሀል። ችግራችሁ ይሄ ነው። በቤተክርስቲያንና በማህበራችሁ መካከል ያለውን ልዩነት አታውቁም ለእናንተ ቤተክርስቲያን ማለት 20 አመት ያልሞላው የጽዋ ማህበር ነው። ኦርቶዶክሳዊነት ማህበረ ቅዱሳን መሆን ነው። መናፍቅነትም ማህበሩን መቃወም ነው። ከዚህ ያለፈ አመለካከት የላችሁም። ይሄ ጠባብ አመለካከታችሁ ነው፣ ሰውን ያህል ክቡር ፍጡር እንኳ ለመግደል የሚያስጨክናችሁ። እንዲህ ያለው ሀሳብ ነው ሰለፊያ ያሰኛችሁ። ሰው ስታሳድዱ ክርስትናን የኖራችሁት ይመስላችኋል። ስትገድሉ የማህበራችሁን ህልውና ያስቀጠላችሁ ይመስላችኋል። ያደረባችሁ የአጋንንት መንፈስ የቤተክርስቲያንን ህልውና አሳጥቶ ማህበራችሁን ቤተክርስቲያንን አድርጎ ያሣያችኋል። በዚህ ማንነት ታውራችሁ ህዝቡን “ከኛ የተሻለ መሪ አታገኝም። አባቶችን አትስማ ቤተክርስቲያንን አትስማ። እኛን ብቻ ስማ” ትላላችሁ። ይህን አስተሳሰባችሁን መቃወም ክርስቲያናዊ ግዴታ ስለሆነ ዝም ልንላችሁ አልቻልንም። ልብ ካላችሁ ልብ በሉ።
በማህበራችሁና በቤተክርስቲያን መካከል ያለውን ልዩነት ተረዱ። ምን እንደሚያገናኛቸው እወቁ። ምን እንደሚለያቸውም ጠንቅቃችሁ ተረዱ። ለእናት ቤተክርስቲያን ቅድሚያ ስጡ። ይህን ካደረጋችሁ ለእውነት ወገን የምትሆኑበት ቀን ሩቅ አይሆንም።
ይቀጥላል
ምንጭ፦ http://www.awdemihret.blogspot.com/

20 comments:

 1. ጐበዝ ጉዳያችሁ ነፍስ መግደልን ካካተተ በማስረጃ አስደግፉና ወደ ፍርድ ቤት ሄዳችሁ አመልክቱ ፡፡ በብሎግ ላይ ተደጋግሞ ብቻውን ነፍሰ ገዳይ ማለት ሃሜት ይመስላል ፡፡ በቃላት ጦርነት ባደረጋችሁት ጉዳይ እንኳን ፍርድ ቤት ዳኝቷችሁ አልነበረም ፡፡ ለዚህም ከፍተኛ ወንጀል ደግሞ ህግን መጠቀሙ አግባብ ነውና ፣ እውነት ካላችሁ የፍትህ ያለህ ብላችሁ ወደ መንግሥት አቤት በሉ ፡፡ አለበለዚያ የሃሰት ውንጀላ ፣ ተራ አሉባልታ ነው ፡፡ ፍርድ ተሰጥቶ ፣ ወንጀለኛ የሆነው ተቀጥቶ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩ በፍርድ ተደምድሟልና ዘወትር አይወሳም ፡፡ በሌሎች የአቤቱታ ጽሁፋችሁ ካነሳችሁት ውጭ በዚህ ገጽ እንኳን በተለያየ ቦታ ላይ ጉዳዩ ተነስቷል ፡፡

  "በጠመዳቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ ያደረሰውን የድብደባና የሕይወት ማጥፋት ወንጀሎች"
  "ስለሃይማኖት እንዲያሳድዱ፣ እንዲደበድቡና እንዲገድሉ እንጂ "
  "ሰውን ያህል ክቡር ፍጡር እንኳ ለመግደል የሚያስጨክናችሁ። "

  ReplyDelete
 2. this is good and interesting. good job awdemihret.

  ReplyDelete
 3. አንጀቴ ቅቤ ጠጣ እንዲህ ነው እንጂ ጥሁፍ

  ReplyDelete
 4. ወገኑን በድንጋይ ደብዳቢ፣
  እውር ፈረስ ጋላቢ፣
  ትልቅ ትንሹን ተሳዳቢ፣
  የዳቢሎስ አጃቢ፣
  ማቅ ማጂራት መችው ሰድቦ ለሰዳቢ፣
  ባለ ውቃቢ ነው ድቤ ደብዳቢ፣
  ባለጌ የእናቱን ቀሚስ ገላቢ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. You know that should belong to you. So, I did as follows!

   ወገኑን በድንጋይ ደብዳቢ፣
   እውር ፈረስ ጋላቢ፣
   ትልቅ ትንሹን ተሳዳቢ፣
   የዳቢሎስ አጃቢ፣
   ተሐድሶው አባሰላማ ብሎግ ማጂራት መችው ሰድቦ ለሰዳቢ፣
   ባለ ውቃቢ ነው ድቤ ደብዳቢ፣
   ባለጌ የእናቱን ቀሚስ ገላቢ::

   Delete
  2. Ofcourse, that was what the message is about.
   You see now you are talking, talking about who you are, well introduction. Let me tell you, I am the Orthodox family but I am participating in this and say something which I am not supposed to do, so, I confesse that me myselfe, you MK, the diablos MK, Abaselame blog and any MK blogs are not good for our Orthodox believer. Please! let us stay away from our mother church with our bad behaviors.

   Delete
 5. xebib be xibebu aymeka hayalim be hayilu.be iwunet inante ye bete krstian lijoch bithonu malet le bete krstian yeqomachihu bithonu indezh ahnet tsihuf attsifum.minim inkuwan mogn bihonum minim inkuwan hitsan bihonum ye sew lij betefetiro aynaqim lemin ke egziabher yetesexe tsega alena;andadirgoch ewuqet laynorachew yichilal ewuqet gin mengiste semayat ayasgebam;andadirgoch hitsan lihonu yichilalu hitsaninet gin ke mengiste semayat aykelekilwum,wanaw neger erashin mazegajet new .hitsanin awaq madreg bemichil endihum awaqin hitsan madreg bemichil be egzabiher mamenina higun mexebeq bicha new.

  ReplyDelete
  Replies
  1. hesan mehonun seyamne newa wendem adegeyalewe kene belay leke yelem lemil yetekesekew tekese ayseram. yesehufu alma and aderegen yalebeten bota masayet new bezhe degmo tesaketoletal

   Delete
 6. TEHUFESE ENDIHE NEW. GELTSE YEHONE MELEKT YALEWAN YETEBRARA. BERTULEN.

  ReplyDelete
 7. I consider myself a Tehadiso Ethiopian Orthodox even though I am not a member of any organized group. There are things I think that need to be reformed in the Ethiopian Orthodox Church.

  I like some of the articles that are published here. They address the specific areas that I think the Ethiopian Church needs to be reformed. But many other articles bother me. They seem to attack the Ethiopian Church on everything that it differs from Protestantism.

  I think the blog owners should rethink what they stand for. Does Tehadiso mean Protestantism for them?

  I am perfectly fine if the blog owners believe that the ultimate goal of reforming the Ethiopian Church is that it becomes a Protestant denomination. But they have to clearly state that, and we will look for other platforms where our idea is clearly promoted.

  ReplyDelete
  Replies
  1. You guy you and your thinking, believes,heart, mind, etc shall be reformed before and after you en-long your tong and mouth on EOTC. Truth is true nothing shall be reformed EOTC rules, i.e. dogima and kenona but as i said you and tehadiso menafikan shall be reformed.

   Delete
 8. Good trial. We know why you guys are doing this. Do you remember what Dn Ephrem mentioned on his article to respond to our PM?
  ....
  እንግዲህ በኦርቶዶክሳውያን እና በተሐድሶዎቹ መካከል ሲደረግ የቆየው ትግል አዲስ ምዕራፍ የሚያገኘው እነዚህ ኦርቶዶክስን ለመከለስ (ለማደስ) የሚፈልጉ ሰዎች “በፖለቲካው ጉያ ምቹ ቦታ ባገኘን” የሚለው ሙከራቸው ተሳክቶ በራሱ በመንግሥት ስም ዓላማቸውን ማራመድ ከጀመሩ ነው። ከነዚህም አብዛኞቹ የኢሕአዴግ የፖለቲካ መስመር ደጋፊዎች በመምሰል (በተለይም ከ1997 ዓመተ ምሕረቱ ምርጫ - ምርጫ ’97) እና ውዝግቡ ጀምሮ ማኅበረ ቅዱሳን ለቅንጅት ማሸነፍ ትልቅ ሚና ተጫውቷል በማለት በመንግሥት ልምጭ የራሳቸውን ዱላ ለማሳረፍ በብዙ ሲጥሩ እንደነበር ይታወቃል። በይፋም ጽፈዋል። የጠ/ሚኒስትሩ አጭርና ብዙ መልእክት የተሸከመች ዐረፍተ ነገር “እነዚያ መንግሥትን ተገን አድርገው ቤተ ክርስቲያኒቱን ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች/ ተሐድሶዎች መንግሥትን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ተሳካላቸው ማለት ነው?” የሚል ስሜት ያጭራል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዲያቆን ኤፍሬም አሜሪካ ተቀምጦ የሚለው መሰረተ ቢስ ነገር ነው፡፡ ተሀድሶ እያላችሁ ስማቸውን የምታጠፏቸው ሰዎች ወንጌል እንጂ ሌላ ድብቅ አጀንዳ የላቸውም። ለዚህ አላማቸው የሚጠጉት ደግሞ ወደ አመኑትና ወደሚሰብኩት ጌታ ነው እንጂ ወደ መንግስት አይደለም። እንዲያ ለማድረግ ማንነታቸው አይፈቅድላቸውም። ማቆች ግን ፖለቲካንና ሃይማኖትን ኣጣቀሳችሁ የምትሄዱ ከወንጌል ውጪ የሆናችሁ ስብስቦች ስለሆናችሁ ፖለቲከኞችን (መንግስትንም ሆነ ተቃዋሚዎችን) መጠጋት የምትፈልጉ እናንተ ናችሁ። ከምርጫ 97 በፊት ከቅንጅት ጎን ተሰልፋችሁ የነበራችሁ እናንተ ናችሁ። ከዛ በኋላ ደግሞ ኢህአዴግ ነን አላችሁ። የዳንኤል ክብረት ቁጣ ዳግም እንዳይቀሰቀስ እንጂ የማህበሩ ዋና ጸሓፊ ዲያቆን ሙሉጌታ እኮ አባኞቹ የማቅ አባላት የኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ናቸው ቦ ነበር። ይህ እንዴት ተረሳና ነው ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ማቅን የሚያስጠነቅቅ ነገር በፓርላማ ሲናገሩ ኤፍሬም ነገሩን ገልብጦ ተሐድሶ የሚሉትን የአየር ላይ ስም ወደ መንግስት በማላከክ መንግስትን በተሀድሶ ደጋፊነት ለመክሰስ ዳር ዳር ያለው። ይህ የማኅበረ ቅዱሳን አመል ነው። ለማህበረ ቅዱሳን ተሐድሶ ማነው ቢባል ማኅበረ ቅዱሳንን የሚቃወም ሁሉ የሚቃወም ሁሉ ተሀድሶ ነው። በእነርሱ ዶግማ መሰረት መናፍቅ የሃይማኖት ሕጸጽ ያለበት ሰው ሳይሆን ማህበሩን በአንድም በሌላም የሚቃወም ሁሉ መናፍቅ ተሀድሶ ነው።

   Delete
  2. መቼም ይህን ጽሁፍ ስትጽፍ የኤግዚቢሽን ማዕከሉን ቪዲዮ አላየህ ይሆናል ወይም ከእነርሱ አንዱ ሆነህ አይናችሁን ጨፍኑ ላሙኛችሁ እያልከን ካልሆነ በቀር በአሁን ሰዓት ተሃድሶን የለም በማለት ማስተባበል በማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። ጥፋቱንም በግልጽ እያዬነዉ ነዉ። የዚህ ቡድን አላማ አራማጆችም በዉስጥም ያሉት ሆኑ በግልጽ ሚና ለይተዉ ማለት በፕሮቴስታንቱ ጎራ ያሉት በድፍረት ስለ ተሃድሶ ንቅናቄና በእነርሱ አነጋገር ስኬታቸዉን እየነገሩን ነዉ።
   “አሮጊቷ ሳራ” እኛን ወለደች እያላችሁን ነዉ። የክርቶስን ወንጌል ከሁለት ሺህ ዓመት በላይ ስትሰብክ የኖረች ቤተ ክርስቲያን አሮጊት ናት እናድሳት እያላችሁ፥
   ውስጣችሁ የማይቀበለዉን ፥አረጀ የምትልሉትን የእኛን ቋንቋ እየተናገራችሁ ፥
   በአላማ የማይመስሏችሁን አባቶቻችንን የናንተም እንደሆኑ አድርጋችሁ ለማደናገር ስትሞክሩ እያዬን፥
   ትናንት እነርሱ ቅዱሳኑን እንደናከብር፥ አማላጅ እንደሚሆኑን፥ የቀደሙትን አባቶቻችንን ፍኖት እንድንከተል ያስተማሩንን አባቶቻችንን እናንተ ወርቃማ ብላችሁ ነገር ግን ከእነርሱ የተለዬ ትምህርት ስታስተምሩን እያዬን እንዴት መናፍቃን በቤታችን ዉስጥ የሉም እንላለን?
   ተሃድሶ መናፍቃን በቤተክርስቲያናችን ዉስጥ ከላይ እስከታች አላችሁ፥ ትታወቃላችሁም ። አላማችሁም አንድና አንድ ነዉ። ይህም ቤተክርስቲያናችንን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ወይም እንደ ህንድ ቤተክርስቲያን ለሁለት መክፈልና የቻላችሁትን ያህል መንጋ ከቤቱ ማስኮብለል እንዲሁም መንፈሳዊና ቁሳዊ ሃብቷን መዝረፍ። የመጀመሪያዉ በእግዚአብሔር ቸርነት አይሆንም፥ ሁለተኛዉ ግን እናንተ እንደምታስቡት ባይሆንም አንዳንድ “... ከኛ ወገን ስላልነበሩ ወጡ” የተባሉትን ማስኮብላችሁ፥ በርግጥ እስካሁንም እንደታዬዉ ሃብቷን ማባከናችሁ አይቀርም።
   እንዳዉም አሁን አሁን እየታዬ ያለዉ የማህበረ ቅዱሳንና የሌሎች ማህበራት መምህራነ ወንጌል በሚያደርጉት ጥረት ምዕመናኑ ከምትገምቱት በላይ ስለ እናንተ ግንዛቤ እየያዘ ስለመጣ የሞት ሽረት ትግል እያደረጋችሁ መሆኑን ነዉ።
   ስለዚህ ይህች ‘አይናችሁን ጨፍኑ ላሙኛችሁ’ ነገር አሁን ላይ አትሰራም። ባይሆን ትንሽ የአርምሞ ጊዜ ወስዳችሁ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ። ለዚህ ደግሞ እግዚአብሔር ይርዳችሁ።

   Delete
 9. Yidires Le Deje Selam Azegagoch ( D Efirem-D Alula-Kesis Yared Wzet...)Minew Deje Selamn Ke Esat radio -Esat radion Ke Dejes Selam magenaget min Yibalal?Min Gingunet Alachew ? Esat Radio sile Waldiba Zegebe malet Min malet new ?Esatm Deje Selam Yetebalew Blogg Sile Waldiba Zegebe eyalu magenaget lemin asfelege ?Ene Ye Mahibere Kidusan Abal neg Deje Selam melkam neger neberat ahun gin Zare ginguneta kepoletikega Gar kehone Nege Degimo Kemenafikan gar yitebaberal malet new ?
  Deje Selam yepoletikan neger lerasachew tewlachew- yehayimanot timihirt akirbu- lemenafikanu mels azegagu-tehadison asafiru Mahibere Kidusann Ashebar-Akirari yasbalew Deje Selam & Ahat Tewahedo & And adirgen -Gebir Her nachew yasblal yesewn sim eyanesu masadedi -ye chirchin Melkam neger alemasayet -yesewn Kibir menkat-
  Kahinatun Ato malet -Papasun mawared-sebakiwin zemariwn masaded lemehonu Dr Kesis Mesfin Kinetachew tagede tebale Gin Yikedsalu endet hone ?yeman kinet sihon new wigzet yemiseraw ?
  Aba Sereken -D Begashawn- Kesis Getachew Donn Ato yemalet mebtu yemanew ?

  ReplyDelete
 10. 100 %true mefin twogez kekedse kidase lehon aychlem lemehonu he was not priest.

  ReplyDelete
 11. I am living in USA . i WAS MK BUT ONE DAY ONE FATHER TOLD ME WHAT BIBLE SAYS ABOUT SALVATION AFTER THAT . I stop mk and now i am one of reformer of Ethiopian orthodox church

  ReplyDelete
  Replies
  1. lol... You just kidding.

   Delete
 12. ለምድራዊ መንግስት ጥብቅና የቆማችሁ ፤ ጠ/ምሩም ፓትርያኩም ከ መቶ ዓመት በኃላ ያልፋሉ፤፤ ከመቶ ሚሊዮን ዓመት በላይ በሰማይም በምድርም ለዘላለም ከክርስቶስና ከቅዱሳኖች ጋር የምትኖረዋ የተዋህዶ ቤ/ክ ትፋረዳችኋለች፡፡ መንግስት የአገር ደህንነት መረጃ ስላለው ባትደክሙ ነፋስና / የመውጊያውን በትር ስለት ላይ ቆማችኋል ፤ እርሱ ባለቤቱ ይሁናችሑ………እግዚአብሔር ያጥናችሁ፣ ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ያጥናሽ፤ እንደ አሜባ የተበጣጠሱ ልጆችሽ ቁርጠት ይዟቸው ለመድሐኒት መግዟ አስጨንቀውሻልና / አስለቅሰውሻልና፡፡../

  ReplyDelete
 13. በጣም ያሳዝናል። ሰው አንዴት ሳያመዛዝን ይናገራል? ይህ ነገር አውነት ቢሆን ኖሮ ብሎግ ላይ ሳይሆን መፃፍ ያለበት ተበዳዮች ተገቢውን ፍርድ አንድያገኙ ለፍርድ ቤት ነበር። ሆኖም ግን አውነት ስላልሆነ እንተርኔት ላይ ብቻ ተፃፈ። ለነገሩ ይህንን የፃፈው ሰው መሰሎቹ ያወሩትን አሉባልታ ይዞ አንደሆነ በደንብ ያስታዉቃል።ስለሁሉም ነገር አግዚአብሔር ልቦና ይሥጣችሁ።

  ReplyDelete