Wednesday, May 2, 2012

ይድረስ ለመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው

እርስዎ በብፁዕ አባታችን በአቡነ ጎርጎርዮስ ጥቂት ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተምረው መልካም መንፈስ እንደነበረዎት ጓደኞችዎ ይመሰክራሉ፤ ለእግዚአብሔር ወንጌልም ቀናተኛ ደቀ መዝሙር ነበሩ። አሁን እያስተማሩት ያለው ትምህርት ግን በሰውም ሆነ በጌታ ዘንድ ያስጠይቀዎታልና በብሎግዎ ከጻፉት ላይ አንዳንድ ኦርቶዶካስዊ ያልሆኑ ትምህርቶችን እንዲያርሙ ልጠቁመዎት ወደድሁ። ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር!
መልክአ ሚካኤል በሚለው ርእስ ከጻፉት ውስጥ፦
 «መልክዕ፦ ቅዱሳን የሚመሰገኑበት መንፈሳዊ ድርሰት ነው። ከራስ ጠጉራቸው ጀምሮ እስከ አግር ጥፍራቸው ድረስ ያለውን የአካላቸውን ክፍል እየዘረዘረ ያመሰግናቸዋል» ብለዋል።
ቅዱሳን መላእክት ሰማዕታት እና ጻድቃን ክቡራን ናቸው። ያከበራቸውም ብቻውን ሌላ ሳይጨምሩ ሁልጊዜ በመንፈስ የሚያመልኩት ሕያውና ቅዱሱ አምላክ ነው። መላእክትም ይሁኑ ሰማዕታት ቅዱሳን ሁሉ የቅድስናቸው ምስጢር አንዱን አምላክ ማምለካቸው ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናውቃቸው ቅዱሳን ሁሉ ዝማሬያቸው፣ ምስጋናቸውና ቅዳሴያቸው ሁሉ ለአንዱ ለሥላሴ ብቻ ሆኖ ነው የምናገኘው። እርስዎ እንደሚያስተምሩት ቅዱሳን ሌሎች ቅዱሳንን ከራስ ጸጉራቸው እስከ ጥፍራቸው ድረስ ግጥም እየገጠሙ ምስጋና ሲያቀርቡላቸው አንድም ቦታ አናይም። እኛም የአባቶቻችን ነቢያትና ሐዋርያትን ፈለግ ተከታዮች ነንና አንዱን ቅዱስ አምላክ ብቻ ልናመሰግን ይገባል። ለምሳሌ ሙሴ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ የተገለጠውን አምላክ ስሙን እየጠራ አመሰገነ እንጂ የነርሱን ጸጉርና ጥፍር እየጠቀሰ ሲያመሰግን አናነብም። ኢያሱም የሙሴን አምላክ እንጂ ሙሴን ሲያወድስ አናይም፤ ነቢያትም ሁሉ ነገሥታትም ሁሉ ምስጋናቸው ለእግዚአብሔር ነው።
በመሠረቱ በዜማ፣ በቅኔና በዝማሬ በቤተ መቅደስ ቆመን የምናቀርበው ምሥጋና አምልኮ ነው። ክቡር ቅዱስ የሆነ ሰውን በአካል አግኝተን የምንሰጠው ሰላምታ አክብሮት ነው። ይኸውም ዝቅ ብሎ እጅ በመንሳት ጉልበት በመሳም እጅ በመሳም፤ ከተቀመጥንበት ብድግ በማለት፤ እንደየባህላችን የምናደርገው እንግዳን የመቀበል ሥርዓት ነው። በማህሌት እና በዜማ በጌታ አደባባይ የምናቀርበው ግን አምልኮ ነው። ቅዱሳን መላእክት ለዳንኤልና ለዮሐንስ በተገለጡላቸው ጊዜ በግንባራቸው ተደፍተው ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ተቀብለዋቸዋል። ይህም በድንገት የተገለጠ ነገር ስለሆነ ነው እንጂ በየወሩ ቀን እየቆጠሩ ያደረጉት ነገር አይደለም። መላእክትም ቅዱሳን  ናቸውና እንኳንስ በየቀኑ የሚሰጣቸውን ስግደትና አምልኮ በእንግድነት በተገለጡ ጊዜ የተደረገውን ከሚገባው በላይ የሆነ አክብሮት አልተቀበሉትም። እርሱም፦ «እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ» ይላል  ራዕይ 229
ዛሬ እኛ እያደረግን ያለው ግን በየቀኑና በየወሩ ቀን መድበን ላልተገለጠልን መልአክ ምስል አቁመን ምስጋና እና ስግደት ማቅረብ ነው። ይህ ስሕተት ነው እላለሁ። እነ ዳንኤል ተገልጦላቸው ነው በግንባራቸው ተደፍተው ዝቅ ብለው የተቀበሉት። እኛ መልአኩ መቼ ተገልጦልን ነው ስግደትና አምልኮ የምናቀርበው? ወይስ ምስል መገለጥ ነው ሊሉን ነው? ዳንኤል በግንባሩ የተደፋው ምስል መስሎ ነው ወይስ መልአክ ተገልጦለት? ይህን ጥያቄ ከመልክአ ሚካኤል ወይም ከድርሳነ ሚካኤል ሳይሆን ከዚያው ቤተ ክርስቲያናችን ከምትቀበለው ከሰማኒያ አንዱ መጽሐፍ እንዲመልሱልን እጠይቃለሁ።
መልክኣ ሚካኤል ስለ ሚካኤል ጸጉር፣ ጥፍር፣ ጥርስ፣ ኩላሊትና አንጀት እያነሳ የሚያመሰግን ድርሰት ነው። ለመሆኑ የዚህ መልክዕ ደራሲ የሚካኤልን ጸጉር የት አየው? ሚካኤል አካል ያለው መንፈስ ነው ዕብ 114 የሚካኤል  ጥፍርስ ምን አይነት ጥፍር ነው? ኩላሊትና አንጀት ለምግብ ሥራ የተሠሩ የሥጋ ለባሽ ብሎቶች ናቸው። ደራሲው ስለመልአኩ አንጀትና ኩላሊት እያለ የማያውቀን ረቂቅ ፍጡር ሲያመሰግን ከየትኛው የእግዚአብሔር ቃል ተነሥቶ ነው? ዳንኤልና ዮሐንስ መልክአ ሚካኤል እያዜሙ ጥፍሩንና ጸጉሩን እያሳመሩ በየወሩ ምስጋና ሲያቀርቡ ታይተዋልን? ለምን ወደ እውነቱ አንመለስም?
መላከ ሰላም ነገር ሲያጋንኑ እንዲህ ብለዋል፦
 «ምስጋና መቅረብ ያለበት ለእግዚአብሔር ብቻ እንጂ እንዴት ለፍጡራን ይቀርባል? እንዲህ ዓይነቱ መንገድ የእግዚአብሔርን ክብር መጋፋት ነው፤ የሚሉ አሉ። ዞር ብለው ደግሞ ትንሽ ውለታ የዋለላቸውን ሰው አፋቸውን ሞልተው ሲያመሰግኑ ይሰማሉ፥ የባሰባቸው ደግሞ «እኔ እንዲህ ዓይነት ሰው ነኝ፤ ብለው ራሳቸውን ሲያወድሱ ይደመጣሉ»
ይህ አባባልዎ አስተዋይ ልብ ላለው ሰው ትዝብት ላይ የሚጥልዎት ነው። እኛ ውለታ የዋለልንን ሰው የምናመሰግንበት መንገድና የቤተ ክርስቲያናችን የዋሕ ምዕመን እርስዎን ጨምሮ መላእክትን የሚያመሰግኑበት መንገድ የተለያየ ነው። ውለታ የዋለልንን ሰው «እግዚአብሔር ይስጥልኝ አመሰግናለሁ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ» ብለን ለበጎ ውለታው በጎ ምላሻችንን እንሰጣለን እንጂ ውለታ ለዋለልን ሰው አመት፣ ወርና ቀን መድበን በከበሮና በጸናጽል በዝማሬና በምስጋና አናመልከውም። ለመላእክት እያደረግን ያለው ግን ከራስ ጸጉራቸው እስከ እግር ጥፍራቸው ድረስ እያነሳን በየቀኑ ምስጋና ማቅረብ ነው። ይህ ልዩነት የለውምን? ይህ የእግዚአብሔርን ክብር መጋፋት አይደለም ይላሉ? እስኪ አንባቢ ይፍረደን፦ ውለታ ለዋለልን ሰው የምንሰጠው ምላሽና በየወሩ በአል ተዘጋጅቶ ለመላእክት የሚቀርበው አንድ ነው? ውለታ ለዋለልን ሰው «አርዳኝ ፈጥነህ ድረስልኝ አድነኝ ማረኝ ይቅር በለኝ» ብለን እናውቃለን? አይደለም! ይህ ልመና መቅረብ ያለበት ሁሉን ለሚሰማው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው። ቅዱሳንን ግን ሥራቸውንና እምነታቸውን በማድነቅ እናከብራቸዋለን ስለነርሱም እግዚአብሔርን እናመሰግናለን እንጂ ወር እና ቀን መድበን አምልኮ መሰል ምስጋና ማቅረብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።
ከዚህ ባዕድ አምልኮ ጋር ጌታን ለመጨመር የሞከሩትን እንመልከት፦
«በአዲስ ኪዳን በመልክአ ቅዱሳን ቅዱሳንን ማመስገን እንዲገባ አብነት ሆኖ መንገድ ያሳየ፥ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይኸውም፦ «የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ያያሉና፥ ጆሮዎቻችሁም ይሰማሉና ብፁዓት ናቸው።» በማለት ደቀመዛሙርቱን በማመስገኑ ታውቋል። ማቴ ፲፫፥፲፮።  በዚህ የጌታ ቃል ውስጥ፦ «ለአዕይንቲክሙን እና ለአዕዛኒክሙን» እናገኛለን። «የእናንተስ የራስ ጠጉራችሁ ሁሉ እንኳን የተቈጠረ (የከበረ) ነው። ከሚለው ደግሞ «ለስእርተ ርእስክሙ፤» የሚለውን እናገኛለን» ብለዋል።
መላከ ሰላም - ጌታ እንደርስዎ አስተሳሰብ ለማለት ፈልጎ አይደለም እንደዚህ ያለው። ይህ ቃል እራሱ ጌታ ቅዱሳን ከተገለጠላቸው መለኮታዊ ምሥጢር የተነሳ ያገኙትን ከፍተኛ ክብር ለመግለጥ ተናገረው እንጂ ለጆሮአቸውና ለዓይኖቻቸው በየወሩ ምስጋና እንድናቀርብ ያሳየን መንገድ አይደለም። ነቢያት ያላዩትን፣ አባቶቻቸው ያልሰሙትን እራሱን ክርስቶስን በአካል ተገልጦ በማየታቸው እድለኛ መሆናቸውን በዚህም ደስ እንዲላቸውና አምላካቸውን እንዲያከብሩ የገለጠላቸው ቃል ነው። እርስዎ ግን «በመልክአ ቅዱሳን ቅዱሳንን ማመስገን አብነት ሆኖ ያሳየ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው» ብለዋል፤ በእውነት ይህ ቃል ጌታ በመልካቸው ቅዱሳንን እንድናመሰግን ያስተማረው ትምህርት ነው? እስኪ ረጋ ብለው በመንፈሳዊ ልብ ያስተውሉት።
«የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለማኑሄና ለሚስቱ ተገልጦ የእግዚአብሔርን መልእክት በነገራቸው ወቅት፥ «ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ (መታሰቢያህን እያደረግን፥ ስምህን እየጠራን እንድናመሰግንህ) ስምህ ማን ነው? ብለውታል። እርሱም «ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃላችሁ? ብሎአቸዋል። መሳ ፲፫፥፲፯። የነቢያት አለቃ ሙሴ በመዝሙሩ እንደተናገረ ድንቆችን የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው። ዘጸ ፲፭፥፲፩። በመሆኑም የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ከእግዚአብሔር ድንቆች አንዱ ነው። ከዚህም መልክአቸው «ለዝክረ ስምከ፤ ብሎ ድንቅ ከሆነው ስማቸው እንደሚጀምር እንረዳለን»
 ለማኑሄ የተገለጠው መልአክ ሚካኤል መሆኑን የጠቀሱት ጥቅስ አይናገርም። ለማኑሄ የተገለጠው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን ከየት አገኙት? «ድንቆችን የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው» ማለትዎ ትክክል ነው «ስሜ ድንቅ ነው» ያለው ሚካኤል ነው ሲሉ ግን ስለ እግዚአብሔር ከተናገሩት ጋር ይጋጫል።  እርሱ ራሱ ሊገልጠው ያልፈገውን ስም እኛም ዝም ብንል የተሻለ ይሆናል።

«ቅዱሳን መላእክት በኃይልም በሥልጣንም ገናና ሆነው መፈጠራቸውን መካድ አይገባም። ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ የመልአኩን መልክዕ፥ ኃይልና ሥልጣን ሲመሰክር፦ «እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፥ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶአልና፥ ቀርቦም ከመቃብሩ አፍ ላይ ድንጋይዋን አንከባሎ በላይ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ፥ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። እርሱንም ከመፍራት የተነሣ መቃብሩን የሚጠብቁ ታወኩ፥ እንደ በድንም ሆኑ፤» ብሏል። ማቴ ፳፰፥፪-፬።»
 በዚህ እንስማማለን ምክንያቱም መላእክቱ ከጌታ ተልከው ሲመጡ በጌታ ክብር ነውና የሚመጡት የጌታ መልእክተኞች ሥልጣናቸውም ሆነ ክብራቸው ታላቅ ነው። በዚህ ሁኔታ በሚገለጡልን ጊዜ እራሳችንን ዝቅ አድርገን በትሕትና አክብረን እንቀበላቸዋለን፤ ምስጋናችንን ግን ሞገስ ክብርና ኃይል ለሆናቸው ለኃያሉ አምላክ እንሰጣለን። እነርሱም የቆሙት ለእግዚአብሔር ክብር ስለሆነ አገልግሎታቸውም ለመንግሥቱ ስለሆነ በምስጋናችን ደስ ይላቸዋል። እነርሱ ከርሱ የተነሣ ነው ይህን ክብር የተጎናጸፉት፤ እኛም አምላካችንን እነደነርሱ ብንታዘዘው ያከብረናል ሞገስ ይሆነናል።
«ሚካኤል ሆይ! . . . የተጨነቁትን ዘወትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኔንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ ይላል። እስራኤል ዘሥጋ የፈርዖን ሠራዊት ደርሶባቸው ሞትን በመፍራት በተጨነቁ ጊዜ የደረሰላቸው፥ በደመናም የጋረዳቸው መጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል ነው» ዘጸ ፲፬፥፲፱።
መላከ ሰላም- ፈጥነህ ድረስልኝ ብለን መጸለይ ያለብን ወደ ሚካኤል አምላክ ወይስ ወደ ራሱ ወደ ሚካኤል? ወደ ሚካኤል የጸለዩ የእምነት ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ አሉን? «አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።» አለ ጌታ። ማቴ 66 መላከ ሰላም ይህን የጌታ ቃል ያምኑታል? አባታችን ማን ነው? ሚካኤል ወይስ እግዚአብሔር? ጌታ በስውር ላለው ባትህ ጸልይ ብሎ አስተማረን እርስዎ ደግሞ ወደ ሚካኤል መጸለይ እንደሚገባ እያስተማሩ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን እንስማ ወይስ እርስዎን? መናፍቁ ማን ነው? ጸሎት አምልኮ ነው። በምስጋና፣ በትሕትና፣ በጸጥታና በእምነት ከሰማዩ አባታችን የምንነጋገርበት ቋንቋ ነው። ዋናው አምልኮ ጸሎት ነው። እውነተኞች ኦርቶዶክሳውያን ሲያስተምሩን «ጸሎት ብሂል ተናግሮ ምስለ እግዚአብሔር» ትርጉም፦ ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ማለት ነው ብለውናል። ጸሎት ማለት ከሚካኤል ጋር መነጋገር ነው ብለው ግን አላስተማሩንም። ይህን ባዕድ ነገር ወደ ቤተ ክርስቲያን ያስገባብን ዘርዐ ያዕቆብ ነው ብለው ነግረውናል። እርስዎስ ለምን የዘርዐ ያዕቆብን ስሕተት  ይደግሙታል?
«እስራኤል የፈርዖን ሠራዊት ደርሶባቸው በተጨነቁ ጊዜ ፈጥኖ ደርሶ በደመና የጋረዳቸው ሚካኤል ነው» ብለዋል። በጠቀሱት ጥቅስ ላይ ግን ሚካኤል በደመና ጋረዳቸው የሚል ቃል ናገኝም። እርስዎ ከምን አገኙት? የእግዚአብሔርን ምስጋና እንዲህ ለፍጡራን አሳልፎ ለመስጠት ይህን ያህል ጥልቅ ጉድጓድ የሚቆፍሩት ለምንድር ነው? ቃሉ የእስራኤል ረዳት ማን እንደነበር ሲናገር «ሙሴም ለሕዝቡ አትፍሩ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብጻውያን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ እግዚአብሔር ስለእናንተ ይዋጋል እናንተም ዝም ትላላችሁ» ይላል። ዘጸ 1413-14  የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ፤ እግዚአብሔር ስለናንተ ይዋጋል አለ እንጂ የሚካኤልን ማዳን እዩ ሚካኤል ስለናንተ ይዋጋል አይልም። ቃሉ ያላለውን ሚካኤል ነው ማለት የስሕተት ትምህርት ነው። ማህበረ ቅዱሳን የስህተት ትምህርት ያስተምራል እያልን የምንጮኸው ለክስ አይደለም። የእግዚአብሔር ቃል የማይለውን በፈጠራ ስለምታስተምሩ ነው እንጂ።
እሥራኤልን ከፈርዖን ያዳናቸው ሚካኤል ቢሆን ኖሮ ባሕሩን ከተሻገሩ በኋላ ባቀረቡት ምስጋና እና ዝማሬ «ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ» በማለት ፈንታ «ንሴብሖ ለሚካኤል ስቡሐ ዘተሰብሐ» ባሉ ነበር። ቃሉ «በዚያን ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ እንዲህም አሉ፤ በክብር ከፍ ከፍ ብሏልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ ጉልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው» ዘጸ 151 ዳዊትም ከረጅም ዘመን በኋላ «መርሖሙ መዓልተ በደመና ወኩሎ ሌሊተ በብርሃነ እሳት» ቀን በደመና መራቸው፥ ሌሊቱንም ሁሉ በእሳት ብርሃን» አለ መዝ 7814 በየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ውስጥ እስራኤልን በደመና የመራቸው እግዚአብሔር መሆኑን ይናገራል እንጂ ሚካኤል ነው የሚል አናገኝም።
«የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ  ይሰፍራል ያድናቸውማል» የሚለው ቃል ትክክል ነው እንቀበለዋለን እርስዎ የተረዱት ግን በተሳሳተ መንገድ ነው። መልአኩ የሚሰፍረው እግዚአብሔርን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ እንጂ እራሱን መልአኩን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ አይልም። የነገር ሁሉ መጀመሪያው እግዚአብሔርን መፍራት ነው። እግዚአብሔርን ሳያከብሩ ሚካኤልን አከብራለሁ እያሉ የሚያሾፉ ሰዎች አሉ። ሚካኤል ግን እግዚአብሔርን ሳንታዘዝ የርሱ ወዳጅ መስለን ብንቀርብ አይቀበለንም «ሄሮድስም እግዚአብሔርን ስላላከበረ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ» የሐዋ 12 ይላል። መልአኩ ማዳን ብቻ ሳይሆን ይገድላል፤ ይህ ፍርድ ግን እግዚአብሔርን በመታዘዝና ባለመታዘዝ የሚወሰን ነው።
ስለዚህ ዛሬ የቤተ ክርስቲያናችን ምዕመን በጥንቆላ፤ በዝሙትና በባእድ አምልኮ እንዲሁም በአጋንንት ሥራ ተጠምዶ ከርሞ ገብርኤል ወዳጄ ሚካኤል አማላጄ እያለ ዳቦ እየጋገረ በየወሩ የሚያደርገውን ቀልድ ቢያቆም ከመቀሰፍ ይድናል እላለሁ። ሚካኤል በዳቦ አይታለልም፤ እግዚአብሔርን ስናመልክ ያከብረናል እግዚአብሔርን ካላመለክን ግን ይቀስፈናል።
መላከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔም ከመጸሐፍ ቅዱስ ያላገኙትን የስሕተት ትምህርት ቢያርሙ ጥሩ ነው። ተሳስተው ከሆነም ከዚህ በኋላ አይድገሙት፤ ንስሐም ይግቡበት፤ እምቢ ካሉ ግን የማህበረ ቅዱሳን ዶክትሪን እንጂ የኦርቶዶክስ እምነት አድርገው አያስተምሩት። በሕግ አምላክ!
ይቀጥላል
መሪጌታ ገረመው ነኝ  

40 comments:

 1. semihin wishetu yegermal bieyehalihu, ant kendegnaw diabilos ena yewhanen assasachew nehe. Letifatih guggadune arekenh eye masike mehonune terrda. Yemitnagerew bediabilos andebet selehone ayergermengenme awaki meseleh esachewn lemarem memokereh leserawit gehanem nigrachew engi leyewahan ayehun yemitiden khon libe yestihe; bekidusan lay yeminager andebet yezegal.

  ReplyDelete
 2. አንተ ስምህን “መሪ ጌታ” ብለሀል፡፡ እኔ ግን መሪ “ሰይጣን ብልህ” እወዳለሁ፡፡ ለመሆኑ በጽሁፍህ “የኛ የኛ” እያልክ የምትዘበራርቀው አንተ ማን ሆነህ ነው? ኦርቶዶክስ ነኝ ለማለት ነው እንዴ? ማነን ለማታለል ነው ይሄ ሩጫ? መልኣከ ሰላም የጻፉት ትክክለኛውን የቤተክርስቲያናችንን አስተምህሮ መሆኑን እኛ እናውቃለንና ዝም በል፡፡ እኛ የምናደርገውን እናውቃለንና ያንተንና መሰሎችህን የአጋንንት ምክር አንፈልግም፡፡ ሁሉን ነገር ከማህበረ ቅዱሳን ጋር ማያያዛችሁን ትታችሁ ያንንው የሉተርን የሞት ፍልስፍናችሁን ዘባርቁ፡፡ መሠረት ስለሌላችሁ የምትይዙ የምትጨብጡትን እያጣችሁ በመሆናችሁ የምትናገሩትንም አታውቁትም፡፡”የኛ የኛ” አትበሉ እናንተ ምንም የላችሁምና:: የነበራችሁን እውነተኛ እምነት ክዳችሁ ለሰይጣንና ለመልእክተኞቹ የተዘጋጀውን መስመር የመረጣችሁ ስለሆነ ንስሀ ግቡ በደላችሁን ይቅር ሊላችሁ ጌታ ዝግጁ ነውና፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. I do not care what you believe in and what you know you are doing. If the ideas raised is wrong disproof it with the Word of God. Otherwise you are smiply saying that you know, when you donot know anything at all about the subject at hand.

   Delete
  2. wendme betselot menfes honeh aymrohin kift argina tikikileghawun neger tereda enji bechifn yemayigebu kalatoch atitsaf.wey ewketu kaleh metsihaf kidusawi honeh asireda...

   Delete
 3. mikegna zendow ante kalitemesegenihima meche des yilihina> Kidusanin awarido Kiristian mehon fetsimo yelem. Ante worada wushimahin enkua ayi tsegurish, ayi tirisish, ayi akenafirish eyalik tameseginat yele. minew lekidusan sihon angebegebeh? Ye awuriew menfes enji antin atihonim endih yemiaskebatirih.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Who told you that Michael has got a body like yours or like one of your wushimas for that matter

   Delete
 4. Ayi Geremew... Betam geremkegn..
  Lemehonu Mergeta negn new yalkew? Shame on u!
  Sint yikefluhal pentewochu lezih tsihuf?

  ReplyDelete
 5. Demo betsadiku abatachin sim metachihu gin ahun nektenal wetmedu ayseram tinish ke orthodox gar yemikerareb tsihuf enkuan alakerebkim ante kesis Dejenen lemetechet minim moral yelehim.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I do not know Kesis Dejene, but if he wrote what the writter in this blog is critisizing defenitly he cannot be a Christian he must be a michaelian.

   Delete
 6. Dear Merigeta Geremew.
  I have a question for you?
  what are you doing in Ethiopia orthodox tewahedo christian church .why don't you go to Protestant church who share your way of thinking about angels.don't west your time to change our believe .I personally is a witness what st Michael did for me.
  Please please let us keep what is best for us and you go away to your protestant friends.
  We always know who is our Almighty God Jesus Christ and who are angels and saints. Just for your information neither my grand father nor me are mahebere kidusan .My grand father passed away 25 years ago.If you think this is mahibere kidusan doctrin not ethiopian orthodox so he was and I am mahebere kidusan too.
  Thank you

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thanks a lot. I completely share your words. In such case my grand grand parents were and parents are mahibere kidusan and me too, my kids as well!

   Delete
 7. ayi miriseyian geribaw

  ReplyDelete
 8. You better to locked your big mouth. If your christian , will not curse ur brother protestant better than you atleast called Jesus instead of to call aba abrham kale tedek as saint. Your test is seems like mafya killer mk. Mk now change strategy to attack our country and eotc by using illdgal mahiber organized on behalf of eotc balwold mahiber. Those elements came usa by providing of false information such like false father and mother false db it is time to inform fbi to arrest them or dna test. Other wise to stop as tools of mk to attack eotc. Long live for aba sel editor that provide as true God word.

  ReplyDelete
 9. እናስተውልMay 3, 2012 at 7:25 AM

  ወገን፦ ምነው ዝም ብለን ሰይጣን ምናምን እያልን ጸሐፊውን ከመሳደብ እና ከመኮነን የተናገራቸውን ነጥቦች አንድ በአንድ እያነሳን እንዴት ትክክል እንዳልሆነ መናገር አይሻልም? ለምሳሌ ጸሐፊው እስራኤልን ከፈርኦን የተከላከለ ሚካኤል ነው የሚለው ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ እንደሌለው ተናግሮአል። እውነቱንም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያ አይልም። ታዲያ ጀግና ማለት ይህ እንዴት ትክክል እንዳልሆነ ማስረዳት ነው (መረጃ እየጠቀሱ)። እንዲሁ ዝም ብሎ ኡ ኡ ማለት ጊዜው እያለፈበት አይመስላችሁም? ለምን እስራኤል ባህሩን ከተሻገሩ በሁዋላ ለእግዚአብሔር ብቻ ምስጋና አቀረቡ? ይህ ትክክለኛ ጥያቄ ነው። የጭፍን አካሄድ ለማንም አይጠቅምም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. No, he know that very well. The church has always taught that with lots of evidences but he and his followers will not listen as they are already taken by the devil's spirit. Dingay lay weha mafises ena le protestant masiredat anid nachew, Egzeabher yemeretachew dan yalew kalihone beteker!

   Delete
 10. ለመሪጌታ ገረመው
  ዕውቀትዎና ጥበብዎ ድንቅ ነው ፤ ምርምርዎም ደግሞ እግጅ ረቂቅ ነው ፡፡ ሁሉንም እንዲመረምሩና መልስ ካለዎት እንዲያስነብቡን ከመግለጫዎችዎ አስከትዬ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አቀርባለሁ ፡፡

  “አንዳንድ ኦርቶዶካስዊ ያልሆኑ ትምህርቶችን እንዲያርሙ ልጠቁመዎት ወደድሁ”
  - የኦርቶዶክስና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለመላእክትና ለቅዱሳን አክብሮትና ምስጋና በማቅረብ ከኘሮቴስታንት እምነት ይለያሉ ፡፡ በእርሶ ዘንድ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች የሚባሉት ከየት የፈለቁ ናቸው ፡፡ ወይስ ኘሮቴስታንታዊ ያልሆኑ ትምህርቶች ለማለት ፈልገው ሳያስቡት ይኸኛው ቃል ተደነቀረ ? ለትምህርቶቹ ምንጫቸውን ማለቴ ነው ፡፡

  “በማህሌት እና በዜማ በጌታ አደባባይ የምናቀርበው ግን አምልኮ ነው።”
  - የሚቀድሰው መምህር ፣ በውጭም የሚሰግደው ምእመን ለመላእክትና ለድንግል ማርያም የአክብሮት ስግደትን እናደርጋለን ብሎ ሲመሰክር ፣ ምን ዓይነት ክህሎት ቢሰጥዎት ፣ በሰዎች አስተሳሰብ /አእምሮ/ ውስጥ ገብተው የአምልኮ መሆኑን ለማወቅ ቻሉ ? ምናልባት ይኸ መገለጥ የሚሉት ነገር ደርሶዎት ከሆነ የችሎታዎ ምንጭ ከቅዱስ መንፈስ ወይስ ከርኩስ መሆኑንስ ለይተውታል ?

  “እኛ መልአኩ መቼ ተገልጦልን ነው ስግደትና አምልኮ የምናቀርበው?”
  - ይኸኛው ጥያቄ ሹመትዎን ባያስቀድሙልኝ ኑሮ አንተ አንቺ ያባብለን ነበር ፡፡ ምክንያቱም የሌለ ፍጹም አዲስ ትምህርት ስለሆነብኝ ነው ፡፡ በመገለጥ ብቻ የምናመልክ ከሆነማ እግዚአብሔርም ተገልጦልን አያውቅምና ስለምልዎ ጽሁፍዎን አሁኑኑ ያሻሽሉ ፡፡ የክህደት ዘርን ዘርተዋልና በሚያውቁት ቋንቋ ያስተካክሉልን

  “ከመልክአ ሚካኤል ወይም ከድርሳነ ሚካኤል ሳይሆን ከዚያው ቤተ ክርስቲያናችን ከምትቀበለው ከሰማኒያ አንዱ መጽሐፍ እንዲመልሱልን እጠይቃለሁ።”
  - መሪጌታ የተባሉበትን የተቀሩትን የትውፊት መጽሐፍ ለምን ይቃወማሉ ? ወይ ይፈራሉ ? መጽሐፍ ቅዱስ እኮ ተሟልቶና ተጠናቆ የተጻፈ መጽሐፍ አይደለም ፡፡ የአሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ትምህርት እንኳን አጠናቅቆ አላካተተም ፡፡ እስቲ ልብ ብለው ይመልከቱ ፤ ይሁዳ ሁለት ገጽ ብቻ ነው ህይወቱን ሙሉ አስተምሮ ያለፈው ? የተቀሩትስ እንዲያውም አንድ ገጽ ለዓይነት እንኳን ያስተማሩት ያልተገለጸላቸው ምን ሠርተው አለፉ ይባላል ? በቀናው መንገድ ብንፈትሽ የተጻፉት የአዋልድ መጽሐፍ እንኳን አጠናቀው የተፈጸመውን ፣ ለህዝብ የተላለፈውን ትምህርት ሁሉ አላሰፈሩትም ፡፡ የተሰዋውን ትተን ሁለት አርድዕት ብቻ ናቸው በጽሁፍ ያስተማሩት ፤ የተቀሩትስ የት ደረሱ ምን ፈጸሙ ? የጢሞቴዎስና የቲቶ ትምህርቶች ምን ይሉ እንደ ነበር አውቀዋል ?

  “ኩላሊትና አንጀት ለምግብ ሥራ የተሠሩ የሥጋ ለባሽ ብሎቶች ናቸው። ደራሲው ስለመልአኩ አንጀትና ኩላሊት እያለ የማያውቀን ረቂቅ ፍጡር ሲያመሰግን ከየትኛው የእግዚአብሔር ቃል ተነሥቶ ነው?”
  - በመሳ 13፡17 ራስዎ የጠቀሱት መልአኩ በሰው አምሳል እንደተገለጠ ነው ፡፡ ዘፍጥረትን 18ንና 19ን ካስተዋሉት አብርሃምና ሎጥ ያስተናገዷቸው በሰው የተመሰሉ የሚበሉና የሚጠጡ መላእክት ነበሩ ፡፡ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንዳስተናገዱም ተብሎ ተገልጿልና በሰው አምሳል አካልና ብልት ውዳሴው መተንተኑ ስህተት አይደለም ፡፡

  “ምስጋና መቅረብ ያለት ለእግዚአብሔር ብቻ እንጂ እንዴት ለፍጡራን ይቀርባል ?”
  - ምስጋናችን እስካላለቀብን ድረስ ለሁሉም እንደየደረጃውና እንደየአግባቡ የአምልኮትና የአክብሮትና ምስጋናና ስግደት ቢቀርብ ነውሩ ምኑ ላይ ነው ? ምስጋና የጨረሳችሁ ካላችሁ ቆጥቡ ፤ እኛም ሊያልቅብን ሲል መቆጠብ እንጀምራለን ፡፡ ማመስገን ትህትናን ይገልጻል እንጅ ክህደትን አያመጣም

  “መላእክቱ ከጌታ ተልከው ሲመጡ በጌታ ክብር ነውና የሚመጡት የጌታ መልእክተኞች ሥልጣናቸውም ሆነ ክብራቸው ታላቅ ነው።”
  - ክብራቸው ታላቅ መሆኑን ካወቁ ማመስገኑና የአክብሮት ስግደትን መፈጸሙ ለምን ይከብድዎታል ? ለራስዎ ያልተቀበሉትን ሌላም አጃቢና ተከታይ ለምን አስፈለገዎ ? ወይስ የአህያዋ ጉዳይ ነው ፡፡ ”የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” የሚለውንም እንቀበላለን ካሉ በእውነት ሳይሸራርፉ ሳያከፋፍሉ ከልብ ይቀበሏቸው ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Do you mean what you say Bible is not complete? has this idea also being shared by the church fathers? Was there any time in history, when church fathers/leaders declared and requested debteras to complete the Bible?
   This must be from the devil it self and probably you are the undercover in the church.

   Delete
  2. Thank you very much. ”የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል”

   This is how we should answer them. If you wanna stick to BIBLE stick also to this word. Isaiyas 56:5 I will set up within my temple and my walls a monument 1 that will be better than sons and daughters. I will set up a permanent monument 2 for them that will remain.

   ትንቢተ ኢሳይያስ 56:4-5 "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና። በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" Dear Abaselamoch, I again repeat for you, If you wanna trust only on what it is in BIBLE, Please stick also to ትንቢተ ኢሳይያስ 56:4-5. This is the reason why we name our church. Ye Abune Tekilehaimanot, YeMichael Betekiristian, YeGebreil Betekristian, Ye kidist Kirstos Semira..... etc.. Because GOD said he is going to give them names which won't be forgotten like mine and your name.

   The most interesting part, in all of our churches, we say Kidus, kidus, kidus Yeserawit geta lul Egiziabiher.. and we read Gospel, Bible.

   Amilak lehulachinim mistirun yigiletsilin.

   AMEN

   Delete
  3. ለመሪጌታ ገረመው ጠበቃ
   ከብዙ ቦታዎች ላይ ማስረጃዎች ማቅረብ ብችልም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ የሚመሰክረውን ከዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 21፡25 ፣ 2ዐ፡3ዐ-31 አስነብብህና ሐዋርያውንም ሰይጣን ትለው እንደሁ ሞክር ፡፡
   "ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል"
   "ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፏል"

   እኔም በጽሁፌ ሌላ ቃል አልጨመርኩም ፡፡ ሁሉ ተጽፎ ስላልቀረበ ሐዋርያትና አርድዕት ያስተማሩዋቸው በቃልና በጽሁፍ ለጥንት አባቶቻችን የደረሱና ፣ እውነትነታቸው ተመርምሮ ቤተ ክርስቲያናችን አምና የተቀበለቻቸው መንፈሳዊ ትምህርቶች አሉአት ፡፡ ይህን እያወቁና ተምረው አድገውበት ለምን በሰማንያ አንዱ መጽሐፍ ላይ ብቻ ማለት ፈለጉ የሚል ጥያቄ ነገር ለመሪጌታ አቅርቤአለሁ ፡፡ ይህንኑም በአጭሩ ለማለት የደፈርኩት ብዙውን የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህርትና ምሥጢር ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው እንጅ በቂ ማስረጃዬን ላስነብብ ብል ብዙውን ምክንያቶቼን መደርደር እችል ነበር ፡፡ ይህን ስል ግን ለማሟላት በማለት ማንም እየተነሳ እየጻፈ የልብ ወለድ ጽሁፍ እንዲያስነብበን ለመጋበዝ አይደለም ፡፡ መጽሐፎቹም ሆነ ትምህርቶቹ ተጠናቅቀው ቀደም በቤተ ክርስቲያናችን ይገኛሉና ፡፡

   Delete
 11. To Melake Selam Dejen,

  Please focus on your usual services. They are so angry of your true teachings, and wanted to divert your attention to them that you will devote your time in answering to them rather than giving services to the Christians. So, ignore this heretics, we know them very well who they are.

  ReplyDelete
  Replies
  1. and please read the bible and concentrate to teach the people the truth. dont serve the devil until your death.

   Delete
 12. Seyitanim beberihan amsal yigelestal tebilo yel, mergeta tebyewis yeseyitanu menfes akal ayedil! Tadiy be meregeta sim begelets min addis neger alew:: Ye tinbitu hulu mefetsemiya newa!

  ReplyDelete
 13. Meri-Geta Geremew ,i agree with your idea, they are insulting you because you are right.I believe insulting is a sign of weakness because insults are virtually always about the individual opponent and not the subject of the debate/argument. To me, an insult from my opponent indicates that they don't have a sufficient grasp of the subject being debated. Since they can't speak logically in defense of their position they resort to personal insults in order to feel better about themselves. It is both a sign of weakness and not being sure of their own knowledge. Keep Going MY Brother.

  ReplyDelete
 14. Selam selam ,
  i think this is the place where debats and arguments flow from two diffrent opponents. but i wonder why people curse and insult the writer instade of giving responcs to the argument. if he is right we cant scape from the truth by insulting him.

  ReplyDelete
 15. «እስራኤል ዘሥጋን በመንገዳቸው ሁሉ የጠበቃቸው፥ መና ከሰማይ ያወረደላቸው፥ ተአምራትን ያደረገላቸው፥ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ርስታቸው የመራቸው፥ በደመና መጋረጃ የጋረዳቸው፥ በክንፎቹም የሸፈናቸው መጋቤ ብሉይ የተባለ ቅዱስ ሚካኤል ነው»በማለት በብሎግዎ ላይ ጽፈዋል። ገረመኝና አንዳንድ ጥያቄዎችና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎችን አቀረብኩልዎ!!
  ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው- ይህንን ከየትኛው መጽሐፍ ላይ አገኙት? ሚካኤል ነው የሚል ተጽፏል? ወይስ ነገረ ሥራው ሚካኤልን ይመስላል ብለው ያልተገለጸውን አቅኚ ሆነው ነው? እግዚአብሔር ሚካኤል ስለመሆኑ ያልገለጸው ረስቶ ወይም ተሳስቶ እርስዎ ግን በትርጉም ፈትተውት ያገኙት እውቀት ነው?
  መቼም እንደማይቀበሉኝ አውቃለሁ፣ እኔን ሳይሆን ለዚያውም መጽሐፍ ቅዱስን።
  ዘፍ 21፥17
  31፥11
  48፥16
  ዘጸ 3፥2
  14፥19
  33፥1-3
  ዘኁ 22፥22 - 22፥23 - 22፥24 - 22፥25 - 22፥26 - 22፥27 - 22፥31 - 22፥32 22፥34 22፥35
  አንድም ቦታ ሚካኤል የሚል ስም ተጠቅሶ አይገኝም። እግዚአብሔር ስሙን ያልጠቀሰው ለምን ይመስልዎታል? እኛስ ስሙን መጥቀስ ለምን ይገባናል? የኛ መጥቀስ እግዚአብሔር ያልጠቀሰውን ጉድለት ለመሙላት ነው ወይስ ስውር የሆነውን ሚካኤል በትርጉማችን ገልጸን በማውጣት መልአኩን ለማክበር?
  ለዚያውም ስሙ ባልተገለጸ መልአክ እጅ እግዚአብሔር ያደረገውን ድንቅና ተአምራት ለሚካኤል ለመስጠት «እስራኤል ዘሥጋን በመንገዳቸው ሁሉ የጠበቃቸው፥ መና ከሰማይ ያወረደላቸው፥ ተአምራትን ያደረገላቸው፥ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ርስታቸው የመራቸው፥ በደመና መጋረጃ የጋረዳቸው፥ በክንፎቹም የሸፈናቸው መጋቤ ብሉይ የተባለ ቅዱስ ሚካኤል ነው» ማለት በፍጹም ትልቅ ስህተትና ክህደት ነው።
  እርስዎ እግዚአብሔር ያለውን ለምን መተው ይወዳሉ?
  ዘፍ 28፣15 «እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና»
  ዘጸ 6፣6 «ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው። እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከግብፃውያንም ባርነት አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ»


  ዘጸ 6፣7ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

  ዘጸ 6፣8 «ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እሰጣት ዘንድ ወደ ማልሁባት ምድር አገባችኋለሁ እርስዋንም ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ»
  ዘጸ 10፣3 «ሙሴም አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ አሉትም። የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በፊቴ ለመዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ»
  ዘጸ 13፣21 «በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ፥ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና ዓምድ፥ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ»
  ዘጸ 14፥24
  ንጋትም በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዓምድ ሆኖ የግብፃውያንን ሠራዊት ተመለከተ፥ የግብፃውያንንም ሠራዊት አወከ። 25 የሰረገሎቹንም መንኰራኵር አሰረ፥ ወደ ጭንቅም አገባቸው ግብፃውያንም። እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ አሉ»
  ዘጸ 15፥3 «እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው»
  ዘጸ 16፥15
  የእስራኤልም ልጆች ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደ ሆነ አላወቁምና እርስ በእርሳቸው። ይህ ምንድር ነው? ተባባሉ። ሙሴም፦ ትበሉት ዘንድ እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው»
  ከብዙ በጥቂቱ እስራኤል ዘሥጋን የመገባቸው፣የጠበቃቸው፣ያሻገራቸው፣ የጋረዳቸው እግዚአብሔር እንጂ እርስዎ እንዳሉት ሚካኤል የሚባል መልአክ አይደለም።
  ዘሌ20፥24 ነገር ግን እናንተን፦ ምድራቸውን ትወርሳላችሁ ትወርሱአትም ዘንድ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ አልኋችሁ። እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ»
  ዘዳ 26፣8 እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ድንጋጤ፥ በተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን
  ዘዳ 26፣9 ወደዚህም ስፍራ አገባን፥ ወተትና ማር የምታፈስሰውንም ይህችን ምድር ሰጠን።
  ቀሲስ- እርስዎ ግን በድፍረት በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀው ላልተገለጠና ላልተጻፈ የመልአክ ስም ሰጥተው፣ ያሻገራቸው፤ መናን የመገባቸው፣ ወተትና ማር የምታፈሰውን ሀገር ያወረሳቸው ሚካኤል ነው ይላሉ። እግዚአብሔር እኔ ነኝ እያለ እርስዎ ግን የለም ሚካኤል ነው ማለትዎ ለምን ይሆን? ላልተገለጠ መልአክ ክብሩን ከእግዚአብሔር ላይ ወስደው ሲሰጡ ለእኔ እንደተደረገ ይቆጠራል የሚል ይመስልዎት ይሆን? ላልተገለጠና ላልተጻፈ የመልአክ ስም ክብሩን ሁሉ መስጠትዎ ሳያንስ ሌሎችም ይህንኑ ስህተትዎን እንዲቀበሉና ፊታቸውን ወዳልተነገረውና እግዚአብሔር ወዳልገለጸው መልአክ እንዲመልሱ ማስተማርዎ ያሳዝናል !! በለዘበ ምላስ የሚናገሩትና የሚጽፉትን ለራስዎ እንዲመች ተርጉመው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ማጣመምዎ ለምንድነው?
  ምናልባት እግዚአብሔር ይቅር ቢልዎ ንስሐ ይግቡበት!! ምክንያቱም እኔ ሰራሁ ያለውን ላልተጻፈ መልአክ ሰጥተው፣ አስቀንተውታልና!!
  እርስዎ እግዚአብሔር ያደረገውን ተአምራት ሁሉ ለሌላ አውለው እንዳስቀኑት ሰዎች ሆነዋል።
  ዘኁ 14፣22-23 በግብፅ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ተአምራቴንና ክብሬን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ አሥር ጊዜ ስለ ተፈታተኑኝ፥
  ነገሬንም ስላልሰሙ፥ በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም ከእነርሱም የናቀኝ ሰው ሁሉ አያያትም» ይላልና ያስቡበት!!!!
  ከዚህ በፊት «በደጀ ብርሃን» ብሎግ የወጣ ጽሁፍ

  ReplyDelete
 16. Dear Aba Selama,

  I pray that you will consider my following respectful request in a sober and just manner.

  I should note at the outset that I'm not a member of Mahbere Kidusan or any such associaiton. I note, however, that you viciously attack Mahbere Kidusan on various issues. I do not question your right to do so. The questions I pose to you are:

  1. Is your method (a continuous barrage of insults) the right way to debate differences among church related blogs and associations?
  2. Are such attacks consistent with the teachings of Jesus Christ and the bible?
  3. What would the arch enemies of our beloved church think when its own children tear each other apart the way you're bent on doing it?
  4. Are you, as it is alleged, members of the Protestant Church and are aiming to destroy EOTC?

  On the one hand, it is evident that our church is suffering from incompetent leadership, corruption, mutual hatred, disunity, huge problems facing Abennet schools, monasteries, and debres including our historic monastery in Jerusalem, the increasing attacks by fundamentalist Moslems, the spreading of Pentacontalists, etc. and on the other hand you, Aba Selama, are waging war within the church. Would this be of any benefit?

  Finally, if you have differences with Mahbere Kidusan or any other group, why don't you find more appropriate mechanisms for a sober discussion and conflict resolution in accordance with Christian doctrines and guidelines instead of engaging such shameful mutual recriminations?

  Please respond. If you're capable of it, please stopy your shameful practices of slinging your relentless arrows that are more aking to the practices of man's most dangerous enemy, the kind of hell.

  ReplyDelete
 17. U got money to write this tera

  ReplyDelete
  Replies
  1. are bakehe. weset new lemalet lemin mikneyat atakerbeme. yeterawoche aleka

   Delete
 18. Mk by himself called teraaaassssssss

  ReplyDelete
 19. እነ ዳንኤል ተገልጦላቸው ነው በግንባራቸው ተደፍተው ዝቅ ብለው የተቀበሉት። እኛ መልአኩ መቼ ተገልጦልን ነው ስግደትና አምልኮ የምናቀርበው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. የእነ ዳንኤልና ዮሐንስን መሰል ዓይን በግንባርህ ሲፈጠር የማይታዩትን መንፈሳዊ አካላት እንደ እነርሱ ለማየት ትችላለህ ፡፡ እምነትህን አጠንክርና በእነርሱ እምነት ልክ አድርሰው ፤ ካላየሁ አላምንም አትበል ፤ ይኸ እንዲሆን አንዳንዶች የሚፈልጉት መንገድ ነው ፡፡ ለመንፈሳዊ አካል ፣ መንፈሳዊ ስግደትና ጸሎት እንደሚገባ መጽሐፍ ይናገራል /ዮሐ 4፡24/ ፡፡ የተዘራው ክፉ ዘር ብዙ የዋሃንን ሊያታልልና ሊያደናቅፍ ስለሚችል እንድትጠነቀቅ ይህን እላለሁ ፡፡ ዮሐንስ ቅድመ ዓለም የነበረውን የአምላክ አኗኗር ለመቃኘት የበቃውና በመጀመሪያ ቃል ነበረ ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ፣ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ለማለት የቻለው በእምነቱ ጥንካሬና ፣ አምላክም እንዲገለጥለት ስለፈቀደ ነው ፡፡ ዘፍ 28፡12 ያዕቆብ በመሰላል የሚወጡ የሚወርዱ የእግዚብሔር መላእክት የተገለጹለት እምነቱ ጠንካራ ስለነበር ነው፡፡ በህልም የሆነውን እንዳትንቀው ደግሞ እግዚብሔር ዮሴፍን ይመራው የነበረ በህልም እየነገረ ነው /ማቴዎስ ምዕራፍ 1 – 2/፡፡

   Delete
 20. Who run the business of mk? Efrem e she tu or daniel keseret? Birhanu gubo bella or go banen is share holder.? I gues this guyes very smaret to make easy money in this way.

  ReplyDelete
 21. መጽሃፍ ቅዱስ የማይለውን መደገፍ ኦርቶዶክሳዊነት አይደለም
  መጽሃፍ ቅዱስ የማይለውን መቃዎም ተሃድሶነት አይደለም
  ይህ አባባል ሁሌ ይገርመኛል! ሰው ሁሉ ክርስቲያን የሆነው(የተባለው) በክርስቶስ እየሱስ ነው!ስለክርስቶስ ደግሞ የወንጌል (የመጽሃፍ ቅዱስ) ቃል ይነግረናል። ስለዚህ የሚባለው ነገር ሁሉ የወንጌልን ቃል ይቃዎማል ወይስ አይቃዎምምም ነው ትልቁ ነገር እንጂ ኦርቶዶክስን ይደግፋል ተሃድሶን ይቃዎማል የሚባል ነገር አይደለም ሁለት ሽህ የማይሞላው እድሜ ይዘን በሙሴ የተደረገውን የኛ ነው የኛ አይደለም ማለት አይገባንም። ሁሌም ቢሆን የመስቀሉን ነገር እንድናይ አደራ እላለሁ!

  ReplyDelete
 22. I said that strongly The Bible is not complete as it is we can give some instant
  in Mat 27-9 Erimas said that where the prohibit Erimas Said the word in matthew ......and the like

  ReplyDelete
 23. leuel Amelke lebona yistachew

  ReplyDelete
 24. Silemelaikt Lemawok Mejemeriya metsaf kidusn be menfesawi ayin Temar keziya yigebahal ( Yalawekehun neger Zimbileh betekiristiyan yastemarechiun Atikawom Le betekiristiyan Jardiya Atihun Ate Jardiya)

  ReplyDelete
 25. "እነ ዳንኤል ተገልጦላቸው ነው በግንባራቸው ተደፍተው ዝቅ ብለው የተቀበሉት። እኛ መልአኩ መቼ ተገልጦልን ነው ስግደትና አምልኮ የምናቀርበው?"
  concentrate on "fasting and praying" like daniel to see the Angels.
  By the way have you ever seen God like his followers? why do you then worship him?

  ReplyDelete
 26. begize temeles, yetinbit mefetsemia atihun mergeta yetebalk,amlak belayih lay yalewun kifu menfes aswogidilh

  ReplyDelete