Thursday, May 3, 2012

የበአታ ለማርያም የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤት ግንባታና የማቅ ፕሮፓጋንዳ


ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኘውን የደብረ ኀይል ወደብረ ጥበባት በዓታ ለማርያም የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤትን በ4.6 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ሚያዚያ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. የግንባታ ውል ስምምነት መፈራረሙን የማኅበሩ ድረገጽ ሚያዝያ 18/2004 ዓ.ም ገለጸ፡፡ ማኅበሩ በጠቅላይ ቤተክህነት አምሳል በስሩ ካደራጃቸው ክፍሎች አንዱ በሆነው “የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል” ይህ ፕሮጀክት እንደሚከናወን ማኅበረ ቅዱሳን አስታውቋል፡፡

በፊርማው ስነስርአት ላይ ማኅበሩን ወክሎ የፈረመውና የተናገረው ዲ/ን ሙሉጌታ ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹ 4.6 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ፕሮጀክት ቀርጾ የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤት ለመገንባት ከዚህ በፊት አድርገነው አናውቅም፡፡ ይህ ትልቅ እድገት ነው፡፡ ምእመናንም ማኅበረ ቅዱሳንን ማመን የቻሉበት ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ ማኅበረ ቅዱሳን ይሥራው ለማለት መቻል ሙሉ ለሙሉ በማኅበሩ ላይ እምነት እንዳሳደሩ ነው የሚያሳየው፡፡ እኛም በታማኝነት ትኩረት ሰጥተን እንድንሠራ የሚያደርገን ነው፡፡ ጨረታውን ከብዙዎቹ የሕንጻ ሥራ ተቋራጮች ጋር ተወዳድሮ ያሸነፈው ድርጅት በማኅበሩ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገና አብሮ የኖረ ነው፡፡ ሥራውንም በጥራትና ከተያዘለት ጊዜ ቀደም ብሎ በማጠናቀቅ ያስረክባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን በኩልም ሥራውን ለማፋጠን አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጣለሁ›› በማለት ገልጿል፡፡

በቅድሚያ ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ ያደረገበት አላማ ሌላ ቢሆንም ለትምህርት ቤቱ ሕንጻ ለመገንባት መነሳቱ ጥሩ ጅምር ነው። እኛም እያልን ያለነው በቤተክርስቲያን ስም የሚለምነውን በተገቢው መንገድ ለቤተክርስቲያን ማዋል አለበት ነው። ‘4.6 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ፕሮጀክት ቀርጾ የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤት ለመገንባት ከዚህ በፊት አድርገነው አናውቅም፡፡’ በማለቱም እውነት መስክሯል። ከዚህ የበለጠ ብር እያለው በአካፋ ያገባውን በማንኪያ እንኳ አላወጣም። ጧፍና እጣን ለተቸገሩ የገጠር ቤተክርስቲያኖች ሰጥቻለሁ እያለ ምእመናንን አያታልል ነው ጥያቄው።

በዚህ መነሻነት ግን ዋና ጸሐፊው “ምእመናንም ማኅበረ ቅዱሳንን ማመን የቻሉበት ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ ማኅበረ ቅዱሳን ይሥራው ለማለት መቻል ሙሉ ለሙሉ በማኅበሩ ላይ እምነት እንዳሳደሩ ነው የሚያሳየው፡፡” ያለው አነጋገር ግን ዝቅ ብሎ “ለፕሮጀክቱ የገንዘብ ወጪውን 3.5 ሚሊዮን ብር የሸፈኑት በደቡብ አፍሪካ ነዋሪ የሆኑ 3 የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆችና በጎ አድራጊዎች” ናቸው ከተባለው ጋር ከተነጻጸረ ችግር አለበት። 3 የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ማኅበሩን አምነው ያደረጉትን ምእመናን ማቅን አመኑ አያሰኝም። ምናልባት እኮ እነዚህ 3 ሰዎች ማቅን ያመኑት የማቅ አባላት /ደጋፊዎች ስለሆኑ ይሆናል። አሁን ያለው ሁኔታ የሚያሳየው ምእመናን በማቅ ላይ እምነት እያጡ መምጣታቸውን ነው። ከሰሞኑ እንኳ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ብር አገኝበታለሁ ብሎ የቋመጠለትንና በአልጠግብ ባይነት በሰው 100 ብር እያስከፈለ ሊያተርፍበት ያሰበውን የእግር ጉዞ፣ ዋጋው በዝቷል። ማቅም እንደጠበቅነው ስላልሆነ እስካሁን ያታለለን ይበቃል በሚል ተመዝጋቢ እንኳ እንዳጣና እንዳራዘመው ውስጥ አዋቂ ምንጮች እየተናገሩ ነው።
የአይጥ ምስክር ድንቢጥ እንዲሉ “ጨረታውን ከብዙዎቹ የሕንጻ ሥራ ተቋራጮች ጋር ተወዳድሮ ያሸነፈው ድርጅት በማኅበሩ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገና አብሮ የኖረ ነው፡፡” ተብሎ በዋና ጸሐፊው ምስክርነት የተሰጠለት ተቋራጩ አቶ አስማማው አያሌው በበኩሉ ለማቅ ሲመሰክር “ጨረታውን ስጋበዝ አሸንፋለሁ ብዬ አላሰብኩም፡፡ የገንዘቡ መጠን ከፍ ሲል ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳን ጓዳውን ስለማውቀው ከየት አምጥቶ ነው ብዬ ስጋት ነበረኝ፡፡ ለዚህ ደረጃ በመብቃቱ ተደስቻለሁ፡፡ …  ለማኅበረ ቅዱሳን ገንዘብ ከመስጠት ገንዘብ መውሰድ መጀመር የጥሩ እድገት ምልክት ነው፡፡” ሲል የድንቢጥ ምስክርነቱን ሰጥቷል። የማቅን ጓዳ አውቀዋለሁ ማለቱ ሰዎች እንደሚያስወሩበት ማቅ የናጠጠ ሃብታም ሳይሆን መናጢ ደሃ ነው በማለት ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ማቅ የሚወራበትን ለመሸፋፈን የሰጠው አስተዛዛቢ ምስክርነት ነው። ግን ደግሞ ሳይወዱ አንድ እውነት መስክሯል። “ለማኅበረ ቅዱሳን ገንዘብ ከመስጠት ገንዘብ መውሰድ መጀመር የጥሩ እድገት ምልክት ነው።” በማለት። ልክ እኮ ነው ማቅ እስከ ዛሬ ሲወስድ ብቻ እንጂ ሲሰጥ፣ በቤተክርስቲያን ስም ሲነግድ እንጂ የሚገባትን ለቤተክርስቲያን ሲያደርግ አልታየም። በእውነቱ ለተቋራጩ ለአቶ አስማማው አያሌው ብቻ ሳይሆን ለቤተክርስቲያንም በ20 ዓመት ውስጥ ይህን ማድረጉ አንድ እርምጃ ተደርጎ ሊቆጠርለት ይገባል። ወይ ለካስ ለድጓ ማስመስከሪያው ለቤተልሔምም ሕንጻ አሰርቻለሁ ብሏል - ሁለት እርምጃ ይሁን።

በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ የተገኙ ወንድሞችና እኅቶች ሰጡ በተባለው አስተያየትም “ዛሬ በማኅበረ ቅዱሳን ታሪክ ታላቅ ነገር የታየበት ነው ብለዋል፡፡ ከ12 ዓመት በፊት ይህ ክፍል ሙያ አገልግሎትና ተራድኦ ክፍል እያለ ለገዳማት ጧፍ በመላክ ነው የጀመረው፡፡ ዛሬ ታላላቅ ቅዱሳት ቦታዎች ላይ በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ ወጥቶ ሥራዎችን እንድንሠራ እግዚአብሔር ስለፈቀደልን ወደ ኋላ መመለስ አንችልም፡፡ ወደፊት ከዚህ በላይ የሆኑ ፕሮጀክቶች ይጠብቁናልና ሁላችንም በእግዚአብሔር ፈቃድ ታጥቀን መነሣትና መተባበር ይገባናል፡፡  ገጽታችን ገዘፍ እያለ ሲመጣ ጠላት ይደነግጣል፡፡ ክፉ ለሚያስቡልን ደግ እንዲያስቡ አቅም የሚፈጥር ነው፡፡ በጎ ተጽእኖ መፍጠር ያስችላል” አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ይላል ድረገጹ፡፡

እኛ እያልን ያለነው ደግሞ ማቅ ይህን ለማድረግ ረፍዶበታል ነው። እስከ ዛሬ ያለ ተቆጣጣሪ ሲሰበስበው የኖረውን ገንዘብ የት ያስገባው የት አይታወቅም። ጧፍና ዕጣን ልኬያለሁ እያለ ሲደልለን፣ በምእመናን ገንዘብ እኛኑ ሲያሳድደን፣ ለአንጋፋ አመራሮች የድርሻ የድርሻቸውን ሲሰጥ እንደነበር የአደባባይ ምስጢር ነው። ከዚህ ቀደም ብርሃኑ ጎበና ለቤት መስሪያ የተበደረውን 300 ሺህ ሳይከፍልና ሲጠየቅ “እናንተ መጽሐፌን ደጋግማችሁ እያተማችሁ ተጠቃሚ ሆናችሁ የለም ወይ?” የሚል መልስ በመስጠት አሜሪካ መግባቱ በሰፊው ሲወራ ነበረ። የጠየቀው ግን የለም። ነግ በእኔ ነውና አመራሮቹ አፍነው እዚያው አስቀርተውታል። ዳንኤል ክብረትም ከማኅበሩ አመራር ሲለቅ እንዲሁ 500 ሺሁን ላፍ ማድረጉ በሰፊው ተወርቶ ነበር። እርሱንም የጠየቀ ስለመኖሩ የሚታወቅ ነገር የለም። እንደቤተልሔምና ቤተመቅደስ “ምስጢር” የሆኑት አመራሮቹ ለአባላቱ ጨርሶ ሳያሳዩ አመራሮቹ አፍነው ይዘውታል ነው የሚባለው።

ማኅበሩ ለበአታ የአቋቋም ትምህርት ቤት ለማስገንባት ባሰበው ሕንጻ የራሱን ገጽታ በአባላቱ ፊት ለመገንባት መሞከሩን ወንድሞችና እኅቶች የተባሉት የማህበሩ ሰዎች በሰጡት አስተያየት ውስጥ አንብበናል። የሚገርመው የማቅ ሰዎች ስለ ራሳቸው መግዘፍ እንጂ ስለ ቤተ ክርስቲያኗ እድገት ማሰብ የሚችል ልብ የላቸውም። “ገጽታችን ገዘፍ እያለ ሲመጣ ጠላት ይደነግጣል፡፡ ክፉ ለሚያስቡልን ደግ እንዲያስቡ አቅም የሚፈጥር ነው፡፡ በጎ ተጽእኖ መፍጠር ያስችላል” የተባለው አስተያየት ይህንኑ የሚጠቁም ነው። በቤተክርስቲያን ስምና ዝና እየነገደ የራሱን ገጽታ ሲገነባ የኖረው ማቅ እንደ ፊኛ ተነፍቶ የገዘፈ ቢመስለውም የሚተነፍስበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። የሕንጻው ግንባታ ጉዳይ አሁን የሁሉም ትኩረት በእርሱ ላይ ስላረፈ ትኩረት ለማስለወጥ የተጠቀመበት ስልት እንጂ ሌላ ተደርጎ አይወሰድም። ለሁሉም የሕንጻው መገንባት ለቤተ ክርስቲያናችን ይጠቅማልና ማቅን በዚሁ ቀጥል እንለዋለን። ነገር ግን የወሰደውንና ወደካዝናው ያስገባውን ያህል እንኳ ለቤተክርስቲያን ሳያደርግ ብዙ ባያወራ ይመረጣል የሚሉ ብዙዎች ናቸው።

15 comments:

 1. ጅማሬህ ታናሽ ቢሆንም ፍጻሜህ ታላቅ ነው፡፡
  በእጣንና ጧፍ ድጋፍ የተጀመረ ስራ መጨረሻው ከህንጻ ግንባታም በላይ ለመስኖ ልማት ግድብ በመገደብ፤ገዳማት መብራት እንዲያገኙ በማድረግ፤የገጠሪቱ አብያተ ክርስቲያን ልክ እንደ ከተማው እኩል አገልግሎት የምትሰጥበት ዘመን እንዲመጣ ስራ በመስራት ገና ብዙ ነገር ማየታችን አይቀርም፡፡ገና ምን ተሰርቶ፤እግዚአብሔር ስራቸውን እየባረከላቸው፤በቁጥር እየበዙ፤ደጋፊ እያፈሩ ሲሄዱ ብዙ ስራዎችን ለቤተክርስቲያናችን እንደሚሰሩ ለማመን በሚያደርጉት ስብሰባ ወይም ሪፖርት ወይም የእግር ጉዞ ላይ አንድ ቀን ብቻ መገኘት በቂ ነው፡፡ወይም ቤአድባራቱ እና ገዳማቱ እሄዱ ድጋፍ የተደረገላቸውን የአብነት ተማሪዎች እና መምህራን መጠየቅ ብልህነት ነው፡፡ይመስለኛል አሁን ከሳሹ ሌላ አጀንዳ ያለው ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete
 2. I am really amazed by ur motives... What is wrong with you guys with MK? What did you do for our church so far? I mean why don't you focus on ur objective to distract our church as a 'reformist' or tehadiso? I personal evolve in this project and there is nothing bad in its aim.
  Pls stop a while and think twice!

  ReplyDelete
 3. የምስክር ት/ቤቱ በአሁኑ ጊዜ ከ70 እስከ 80 ተማሪዎችን ብቻ የሚያስተናግድ ሲሆን፣ የአቋቋም ምስክር ት/ቤቱ ሲጠናቀቅ እስከ 170 ተማሪዎችን መቀበል የሚችል ነው፡፡ ተማሪዎቹ በከፍተኛ ሁኔታ የማደሪያ ቤት ችግር ስለሚያጋጥማቸው በሁለት ዓመት መጨረስ የሚገባቸው ወረፋ በመጠበቅ አራት ዓመታት ይፈጅባቸዋል፡፡ የጎጆ ወረፋ በመጠበቅ ረጅም ጊዜ ይቃጠላል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ዓላማ ያደረገው ይህንን ችግር መቅረፍ ነው፡፡ ይህ ግንባታ ዛሬ ላሉት ተማሪዎች ብቻ ትኩረት ያደረገ ሳይሆን ወደፊት ማማር ለሚፈለጉ ሁሉ ደረጃውን የጠበቀ ጉባኤ ቤቶችን መገንባት ነው

  ReplyDelete
 4. Abaselam

  Yihe yishala,

  Ye MK sira bednb stafu....

  Great....

  ReplyDelete
 5. the mk money is a lot so, for next they have spend for wongel in rural areas . they have millions and millions birr . keep it up mk but donot forget the wonegel.

  ReplyDelete
 6. dear aba selama
  By any means do you have any positive attitude in your mind.you always write negative things.Just MEKAWEM BECHA.you need to come to your mind ,you need to pray hard,I really feel sorry for you.It looks like you are personal enemy for our beloved EOTW church teaching and our traditions which is based on our Bible.And also I always wonder why you hate Mehabere Kidusan that much. I am not a member.If you hate them just leave them alone and do your best yourself instead of following what they do ,what they say etc etc and keep complaining. please please please do your part positively if you really have a concern about our EOTw church or as I told you yesterday go away to your protestant friends.They have very big adarash which can accommodate you.
  Thank you

  ReplyDelete
 7. uuuuuuuu maletachihu min yahil endasarernachu yasayal. You will see a lot in the future that MK will proliferate and work for the church. What surprises me is that people will now more about mk even through you b/c the justifications you gave are infevore of mk. So you the mafias please return to your church instead of attacking your mother church. I appriciate how stupied you are.

  ReplyDelete
 8. sera kemeftat lejen lafatat yemibal teret ale hager bet yenantem sera yeh hone. sew kegziabhar gar yetalal yehe eko yegziabhar sera new egziabhar yakeberewen degmo manem ayawardewem meknyatum egziabhar kersu gar newewna. selaezih ebakachu ende sew lemaseb mokru chenqlatachun lebego neger tetqemubet. Bemelkam neger yemaydesetew diyabilos bech new enantem yegbru lejoch eyaderegachu selehone qombelachu erasachun betmeleketu yaw selementewaweq. Egziabhar lebon yestachu.

  ReplyDelete
 9. Selam Abba Selamawoch Mahibere Kidusan Abune Pawlosin Deg Abat malet Jemiroal yesinodos sibseba lijemer sil melesiles mekilesiles yabezal Be 24 8 2004 berasu biloog lay Hige Wetsi Hig Askebar Bemil Ris lay simezegib Abune Pawlosin lemamesgen Mokirewal yih min yibalal?

  ReplyDelete
 10. I believe you guys learn a lot from a comment, I am really confused about your blog why don't you change your name. please don't tell us who you are because it is very easy to know you are belongs to which church. please write about Wengel(Bible)instead of protest mother church or the kids of ETWTC. If you change your mind and start doing together with your brothers and sisters in Christ for mother church God will bless all of us.

  ReplyDelete
 11. "እኛ እያልን ያለነው ደግሞ ማቅ ይህን ለማድረግ ረፍዶበታል ነው።"

  What did you do on your part?
  Mention a single project on your side.

  ReplyDelete
 12. አባ ሰላማ ብሎጎች
  እስኪ የናንተን ፕሮጀክት አሳዩን? በማንኪያ የተሰራም ቢሆን!! ልዩነቱ እዚህ ላይ ነው። ሁሉንም ነገር ሲቃዎሙ መኖርና መስራት በጣም ይለያያሉ። እግዚአብሔር እንዲሰራባችሁ ራሳችሁን አስተካከሉ!!
  ታው.

  ReplyDelete
 13. aba selamawoch: please please improve your mind. u are so late and became out of the Bible. don't blame your mother church. instead go to the many historical and holy place and do sth for them so that u will get blessed. does Bible say "insult and blame your brothers and sisters?" what way are u following? God bless EOTw and Ethiopia.

  ReplyDelete
 14. አባ ሰላማ ብሎጎች
  እስኪ የናንተን ፕሮጀክት አሳዩን? በማንኪያ የተሰራም ቢሆን!! ልዩነቱ እዚህ ላይ ነው። ሁሉንም ነገር ሲቃዎሙ መኖርና መስራት በጣም ይለያያሉ። እግዚአብሔር እንዲሰራባችሁ ራሳችሁን አስተካከሉ!!
  ታው.

  ReplyDelete