Friday, May 4, 2012

አንዳንድ የማቅ አባላት የሲ. አይ. ኤ. ሰላዮች ሆነው ተገኙ

ቤተ ክህነት አካባቢ “የቀን መጋኛ” በመባል የሚታወቀው ባያብል ሙላቱ የሰጠውን መረጃ ዊኪሊክስ (wikileaks) ይፋ አድርጓል
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
ምንጭ፡ ዐውደ ምሕረት ድረ ገጽ
በርካታ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ሌሎች ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት የተለያየ ነው። ማኅበሩ እውነተኛ ማንነቱን ደብቆ በቅድሚያ ቤተክርስቲያንን ከዚያም የመንግስትን ሥልጣን ለመያዝ በግልጾቹም በስውሮቹም አመራሮች እየተደገፈ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችን አባላቱ በቅጡ አልተረዱም። ቤተክርስቲያን እኛ ባንኖር ኖሮ ጠፍታ ነበር። ያለንላት እኛ ነን። ቤተክርስቲያን ሰው ስለሌላት አስራታችሁን ለማኅበረ ቅዱሳን አውጡ በማለት የሚያሰወራውን ወሬ  እና በአካፋ ተቀብሎ በማንኪያ የሚሰጠውን ስጦታ በማመን የተታለሉ ወገኖች ይገኛሉ። እውነቱን ከማህበሩ ጋር ለበርካታ አመታት በቅርብ የሰሩ ወገኖችና እንቅስቃሴውን በሙላት የተረዱ የቤተክርስቲያን ልጆች ያውቁታል። 
ማኅበሩ ፖለቲካ ውስጥ ያለው ሚና እስከ ምን ድረስ እንደሆነ ብዙዎቻችን አናውቅም። መንግስት ፓለቲካው ላይ ያለውን ፍለጎት በሌላ መንገድ እንዳይጠረጥረው ከመንግስት  ጋር የመንግስት ሰው መስሎ ለመስራት ይሞክራል። ከተቃዋሚዎች ጋር ደግሞ እነርሱን መስሎ ይመላለሳል። ይህን እውነት ምርጫ 97 ላይ የማኅበሩ አመራሮች ከቅንጅት ጋር የነበራቸው ግንኙነት በቂ ማስረጃ ነው። አሁን ደግሞ እነርሱ esatን esat ደግሞ ደጀ ሰላምን እየጠቀሱ የዋልድባን ነገር ለማጮህ የሚሄዱበትን መንገድ ማስተዋል በቂ ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ ማህበሩ ከውጭ አገር መንግስታትና ከሲ አይ ኤ ጋር ያለው ግንኙነት እስከ ምን ድረስ እንደሆነ አናውቅም ነበር። እድሜ ለዊኪ ሊክስ እውነታውን አውቀናል። ይህን ነገር እኛ ብንዘግበው ውሸታም ትሉን ይሆናል። ዊኪ ሊክስ ግን ነገሩን ያገኘው ከአሜሪካ መንግስት ምስጢራዊ ፋይሎች ውስጥ ነው። የአሜሪካ መንግስት ወሬ አቀባይ አድርጎ ባያብል ሙላቱ የሚባል ሰውን እንደሚጠቀም ነግሮናል።
ወሬ በማመላስና በመቅለስለስ ልዩ ችሎታ አለው የሚባለው ባያብል ባለፈው የጥቅምት ሲኖዶስ ላይ እንቅልፍ አጥቶ የማቅን አጀንዳ ለማስፈጸም አንዳንድ አባቶችን ከመግባባት አልፎ መመሪያም በመስጠት የስብሰባውን አቅጣጫ ለማስቀየር ሲደክም እንደነበር ይታወቃል። አንዳንዶች ከኋላ ሆኖ የሲኖዶስን ስብሰባ ለመምራት የሚሞክር “ደፋር” ሰው ነው ይሉታል። ባያብል የቤተክርስቲያን ጉዳዮችን በሚመለከት የአሜሪካን መንግስትን በራሱ አቅጣጫ (ማኅበሩ በሚፈልገው መንገድ) ይመራው እንደነበር የዊኪ ሊክሱ ዘገባ ያስረዳል። ይህ የዲ/ን ሙሉጌታ ጽሑፍም ይህን አስመልክቶ ዝርዝር መረጃዎችን ያስነብበናልና በትኩረት እናንብበው።

የጽሑፉ ዓላማ: "ማህበረ ቅዱሳን" በመባል ስለሚታወቀው ሀገር ለባዕዳን አሳልፎ የመስጠትና የማውደም ልዩ ተልዕኮ ያለው ድርጅት አባላት እነማን ናቸው? በምን ዓይነት የስራ ድርሻስ ተሰማርተው ይገኛሉ? የሚሉትንና ሌሎች በርካታ አንኳር ጥያቄዎችን ከወቅታዊ የቤተ-ክርስቲያኒቱ ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች ጋር አገናኝቶ ያብራራል:: ርእሱን ማዕከል ያደረገ ከፊል የጸሐፊው እውነተኛ የህይወት ምስክርነትም በጽሑፉ መግቢያ ላይ ተካቷል:: መልዕክቱን በእርጋታ ያንብቡት፡፡ ሀገርን ከእውነተኛ መሳይ አጥፊ ቡድን ለመታደግም የድርሻዎትን ይወጡ::

ወቅቱ በሀገራችን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ታህሳስ 2000 /ም ነበር፡፡ ጊዜው አመሻሹ ላይ 12:30 ይሆናል፡፡ ራዚል ካፊቴርያ (መኻል ፒያሳ) "ለአንድ ጉዳይ እፈልጋለሁ እባክህ" ተብዬ ነበር ከአንድ የቀድሞ ወዳጄ የጠበቀ ተማጽኖ ቀርቦልኝ ወደ ስፍራው ያቀናሁት:: በስፍራው ላይ ተገኝቼ ወንድማዊ ሰላምታ እንደተለዋወጥንም "እንዲህ እንኳን ተፈላልገን አናውቅም፡፡ ወደ 6 ወይም 7 ጊዜ ነው የደወልክልኝ በደህና ነው? የፈለግከኝ ለምንድር ነበር?" የሚለው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር:: ለጥያቄዬ መልስ ሳላገኝ አስተናጋጅዋ ትደርስና ምን ልታዘዛችሁ?” በማለት ከፊታችን ትቆማለች:: አስታውሳለሁ ወቅቱ የጾም ወቅት ነበር ታዲያ ይህ ወዳጄ "አይ! እኔ .." በማለት የጀምርኩትን ንግግሬን ያቋርጥና "ለእሱ ወተትና ለስላሳ ኬክ ለእኔ ደግሞ ቀጭን ሻይ አምጪልኝ" ይላል:: ደግሜ "አይ እኔ ምንም ነገር አልወስድም ይልቁንስ በጊዜ የፈለግከኝን ጉዳይ ንገረኝና ወደ ስራዬ ልሂድ እለዋለሁ" አስተናጋጅዋ እንደቆመች፣ እሱም አበክሮ እኔ የማዝልህን ካልጠጣህና ካልበላህ ብሎ የሙጥኝ ብሏል:: አማራጭ አልነበረኝም ፊቴን ወደ አስተናጋጅዋ በማዞር "የእኔ እህት እኔ ምንም ነገር አልወስድም ለሱ ግን ትእዛዙን አምጪለት" በሚለው ተስማምተን ስናበቃ አሁንም እንዲህማ አይሆንም ጋባዡኮ እኔ ነኝ” በማለት ነገሩን ሲያስረዝም "ስትስማሙ ጥሩኝ በማለት" አስተናጋጅዋ ሄደች::

"የጠራኸኝ ለምን ጉዳይ ነበር?"::አልኩት። አሱም  "አዎ! ነገሩ እንኳን የተወሳሰበ ነው" በማለት ይጀምርና እያለቃቀሰ ከአስር አመታት በፊት የነበረችውን የሴት ጓደኛውን ታሪክ አንስቶ ብዙ የግል ጉዳዮቹን ካወራ በኋላ በአሁን ሰአት የሚከፍለው የቤት ኪራይ ገንዘብ፣ የሚበላው ምግብ ጭምር እንደቸገረው ይገልጽልኛል:: አክሎም “አንተን ለማግኘት ከኮልፌ ፒያሳ ድረስ የመጣሁት እንኳን በእግሬ እያቆራረጥኩ ነው::” ይለኛል፡፡ እኔ ደግሞ በበኩሌ ከእኔ የሚፈልገውን በአጭሩ ይገልጽልኝ ዘንድ "ታዲያ አሁን ከእኔ የምትፈልገው ምንድነው? ምን እንድረዳህ ትፈልጋለህ?" ስል ጠየኩት::
ቋንቋው ስለገባኝ ነገሩን ራሴ ላሳጥረው በማለት "ምን ያህል ነው የሚያስፈልግህ?" አልኩት:: “ወዳጄ” ሆዬ በጉዳዩ ሳይሆን በመልእክተኝነት ነበር የጠራኝ፡፡ በድጋሜ ስልኩ ይጮኸል (ቀደም ብሎም ሁለት ጊዜ ጠርቶ የካፊቴሪያው ጫጫታ አላሰማ ብሎኛል በማለት ወደ ውጭ ወጥቶ ሴኮንዶችን አነጋግሮ ተመልሶአል እኔም የጠራኸኝ አንተ ነህ” በማለት ስልኩን እንዲዘጋ ብጠይቀው የመለሰልኝ መልስ ይረዱኝ ዘንድ የደወለኩላቸውን ሰዎች እየጠበኩአቸው ስለሆነ ነው ይቅርታ” ሲል ምላሽ ሰጠኝ:: እዚህ ላይ አንድ ነጥብ ማብራራት እፈልጋለሁ ይኸውም ወተትና ኬክ እንድበላና እንድጠጣ ግድ ያለኝ በጾም ወቅት ገደፈ ብሎ በመረጃ በማስደገፍ እኔን በአደባባይ ለማሳጣት ነበር::

በዚህ ሰዓት ልቤም እአምሮዬም ብቻ ሁለመናዬ ወትሮ ከማውቀው በላቀ ነቃ ብሏል:: ስሙን ጠርቼም "ትሰማኛለህ ለእኔም ቤቱ ስላልተመቸኝ ቦታ እንቀይር ብዬ ብደግ አልኩ" "እሺ እዚህ አጠገቡ ወዳለው ካፌ እንሂድ" በማለት ሻንጣዬን ከእጄ ነጥቆ ቀድሞኝ ወጣ:: ወደ ቤቱ እንደገባንም ገና ሳንቀመጥ "ይህማ የባሰበት ነው" በማለት ቀድሞኝ በመውጣት ወደ ራዚል መለሰኝ:: ወደ ወጋችን ተመልሰን ሳንገባም ለአራተኛ ጊዜ ስልኩ ጠራ:: እርሱም ገና አንድ ጊዜ እንደጠራ ቃል ካፉ ሳይወጣ ጥርቅም አድርጎ ዘጋው፤ (ኮድ መሆኑ ነው) አንድ ደቂቃ በማይሞላ ልዩነት ውስጥ አራት የሲቪል ልብስ የለበሱ ግለሰቦች (የመንግስት የደህንነት አባላት መሆናቸው ነው) ወደተቀመጥኩበት ጠረጴዛ ድረስ በመምጣት በቁጥጥር ስር እንደዋልኩና ምንም ነገር ለማድረግ ሙከራም ማድረግ እንደሌለብኝ፣ ተነስ ስባል ብቻ ተነስቼ ከካፍቴራው በር አጠገብ መጥታ በምትቆመው መኪና መግባት እንዳለብኝ በትእዛዝ መልክ ነገሩኝ:: ትዕዛዙ ከዚህ ትእዛዝ ያለፍኩ እንደሆነ በራሴ ላይ እንደፈረድኩ የሚያሳስብ ቃል ሁሉ ታክሎበታል::

በዚህ ተስማምቼ መኪናዋ እስክትመጣ ድረስ ለጥቂት ደቂቃዎች በአግራሞት ዓይኖቼን እንደ ዓይን ብሌን በጠራው መስተዋት አሻግሬ ወደ ውጭ ሳማትር ዓይኔም ቢሆን አልቀናውም:: በር አጠገብ ኩልኩል ብለው የቆሙት አራቱ ባያብል ሙላቱ የሚገኝበት በወቅቱ የማህበሩ ሰብሳቢና ዋና ጸሐፊ የነበሩትን ሳምሶንና ግርማ መታፈሪያን አራተኛውን ስሙን ለጊዜው ማስታወስ አልቻልኩም የማህበሩ (የማህበረ ቅዱሳን) ከፍተኛ የስራ አመራር አባል ዓይን ዓይኔን ያዩኛል:: እናማ መኪናዋም መጣች “ወዳጄም” ለበላተኛ አውሬ አስረክቦኝ ቀድሞኝ በመውጣት ከማህበሩ አባላት ጋር ቆሞ ያየኝ ጀመር:: በግራም በቀኝም ከፊትም ከኋላም ተከብቤ ከካፍቴሪያው እንደወጣሁም፣ ደህንነቶቹ የያዙት ሰው በትክክል የሚፈለገው ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል የሚባለው ሰው ለመሆኑ ሲጠይቁ ከሁሉም ቀድሞ ፊት የቆመው ባያብል ሙላቱ ራሱን ነቅነቅ አድርጎ አረጋገጠላቸው "ግባ ምን ትጠብቃለህ" ተብዬ ወደ መኪናዋ አስገብተው ፒያሳ ወደሚገኘው 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የነፍስ ግድያ ምርመራ ክፍል አስረክበውኝ ተለያየን፡፡

ከዚህ ቀደም "ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን?" የሚለውን ክፍል አንድ መጽሐፌን እንዳሳተምኩ 24 ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውዬ (በማህበረ ቅዱሳን ከሳሽነት) በተለምዶ ገዳም ሰፈር በመባል በሚታወቀው ፖሊስ ጣቢያ ለሦስት ቀናት ከርሜያለሁ:: ቆይቼም አደገኛ ቦዘኔ ተብዬ ከሰሜን ሆቴል ማዶ ወደሚገኘው አንድ ማጎሪያ ጣቢያ ወርጃለሁ:: በዚህ ሁሉ ጎብኝዎቼ በባያብል ሙላቱ የሚመራ የማህበሩ የጀርባ አጥንት የሆኑ አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት ነበሩ:: ልብ ይበሉ! ጉብኝቱ ራርተውልኝ ስንቅ ለማቀበል ሳይሆን ከእኔ አልፈው የጣቢያዎቹን አዛዦች ለማስፈራራት ጭምር ነበር::

ይህ ሰው (ባያብል ሙላቱ) እንዲህ ያለ የሽፍታ ስራ በመስራት እጅግ የታወቀ ነው:: በጠቅላይ ቤተ-ክህነት አከባቢም ቅጽል ስሙ "የቀን መጋኛ" በመባል ይታወቃል:: “የሌሊቱስ ማን ነው?” ያሉ እንደሆነ የጠቅላይ ቤተ-ክህነት የሌሊት ዘቦች ነገሩን ቢተርኩት በእነርሱ ያምራል:: ውድ አንባቢ! የፈቀዱልኝ እንደሆነ የሰማሁትንና ሁሉ የሚያውቀውን ታሪክ በአጭር እንደሚከተለው ልተርክልዎት::

"ስሙ አይጠራም!" ይላሉ ጨዋታውን ሲያደምቁት:: አንዳንድ ጊዜ ጥቁር ካባ ለብሶ ዘውድ ደፍቶ ከታች ወደ ላይ ከላይ ወደ ታችም ይመላለሳል:: ደግሞም ወቅት አለው ይላሉ ጦር ይዞ፣ ህጻን ልጅ ታቅፎ የሚንቀሳቀስበት:: አንድ ጊዜ ይህን ያጫውተኝ ለነበረ ወዳጄ "ስፍራው ቤተ-ክህነት አይደል መልአክ ቢሆንስ" ስለው "ሲጋራ ያጨሳል አሉ" ብሎ እርፍ አለ:: በተለይ በጠቅላይ ቤተ-ክህነት ልዩ ዝግጅት ሲኖርና በታላላቅ ክብረ በዓላትማ ብርሌ አንቆ (“ጠጅ” እየጠጣ መሆኑ ነው) እሳት ሲሞቅ ነው የምናየው
በማለት የሰሚን የልብ ትርታ ይጨምራሉ:: ልብ ይበሉ: ካርታም ይጫወታል!

አንዳንድ ጊዜም በቁጥርም በርከት ብለው ከታች አከባቢ (አዲሱ የጠቅላይ ቤተ-ክህነት ህንጻ በቆመበት ማለት ነው) እሱን የሚመስሉ በቁመታቸው አጠር ያሉና መጠነኛ የሰውነት ቅርጽ ልዩነት የሚስተዋልባቸውን በግራ በቀኙ አቅፎ የሰው አይሉት የጅብ ዓይነት ሳቅ እየሳቁ ወደ ሊቃነ ጳጳሳቱ መኖሪያ ቤት ሲያመራ እናየዋለንም ይላሉ:: ወደ በር አከባቢ የሚመጣበት ወቅትም እንዳለ ይናገራሉ::
በነገራችን ላይ እሳቱ የሚነድበት ስፍራ ላይ ዓመድ ያገኙ እንደሆነ በተደጋጋሚ በቀን ለማረጋገጥ ቢሞክሩም ምንም አዲስ ነገር እንደማያገኙ ይናገራሉ:: ታዲያ በዚህ የማይያዝ የማይጨበጥ ፍጥረት ግራ የተጋቡ የጠቅላይ ቤተ-ክህነት ዘቦች እናቱ እንደጠፋችበት ቡችላ ከቤት ወደ ቢሮ ከቢሮ ወደ ቢሮ የሚተላለፈውን ሊቀ ጳጳስና መነኩሴ ሲሸኝና ሲያመላልስ ወዲያ ወዲህ ሲል ጸሐይ የምትጠልቅበት ሰው ነው ይሉታል፡፡ባህሪውን በሚገባ የሚያውቁት እነዚህ ሰዎች ፈልገው ከጠቅላይ ቤተ-ክህነት ቅጽር ግቢ የማያጡት ባያብል ሙላቱን "የቀን መጋኛ" በማለት ሰይመውታል::

ከጥቂት ጊዜያት በፊት አቢይ አፈወርቅ በተባሉ አንድ ጸሐፊ "የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች በዊክሊክስ ፋይሎች" ሲሉ ከአንዳንድ የኢንግሊዝኛ ሰነዶች ያገኙትን መረጃ ወደ አማርኛ በመመለስ ለንባብ ባበቁት ጽሑፋቸው ውስጥ ባያብል ሙላቱ ተብሎ ስለሚታወቀው ማህበሩን ለበርካታ ዓመታት በመምራት ስለሚታወቀው "የማህበረ ቅዱሳን" ከፍተኛ የስራ አመራር አባል ምስጢራዊ የስራ ድርሻ እግረ መንገዳቸውን እንደሚከተለው አጋልጠዋል::

"እንዲያውም ከሁለቱ ፓትርያርኮችና ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ያለው ባይብል ሙላቱ የተባለው ታዋቂ ባንከኛ ከኤምባሲው የፖለቲካ ኦፊሰር ጋር ፌብሩዋሪ 7 ቀን 2007  ተገናኝቶ በሁለቱም ቤተክርስቲያናት መሀል ኦፊሽያል ያልሆነ ግኑኝነት ሲያደርግ መቆየቱን መስክሯል፡፡አክሎም "ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት ያለው ባያብል ሙላቱ በሁለቱም ወገኖች መኸል ኦፊሽያል ያልሆነና በገለልተኛ ሰዎች መልእክት አስተላላፊነት የሚካሄድ ቋሚ ግኑኝነት እንደነበረው ነግሮናል::" (ገጽ 2)
1. ይህ ሰው ለኤምባሲው ከሁለቱ ፓትሪያሪኮች ጋር የጠበቀ ግኑኝነት አለኝ ሲል መናገሩ ከቅጥፈትም በላይ ወንጀል ነው:: ከአስርት ዓመታት በላይ እንደ ኪሩቤል ሰይፍ እየተገለባበጠ ከስልጣን ካብ ሳይወጣ በበላይነት የሚመራው ማህበር በውጭ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት እንደሌለው እየታወቀ እንዲያውም በአንጻሩ "መናፍቃን" ናቸው እያለ በሬ ወለደ ወሬውን በሚነዛባቸው ጋዜጦቹና መጽሔቶቹ እየዘመተባቸው የጠበቀ ግኑኝነት አለኝ ሲል የአሜሪካ ኤምባሲን ማደናገሩ የማይነጋ መስሏት እንደሚባለው ነው፡፡
ይህን በተመከተ በውጭው የሚገኙት የሃይማኖት መሪዎች መልስ ቢሰጡበት የበለጠ ግልጽ ይሆናል:: በተረፈ ግን ባያብል ሙላቱ ማለት ከወንጀለኛም በላይ ሀገር ሻጭ ባንዳ መሆኑን ሁሉ ያውቀው ዘንድ ይገባል:: በሀገር ድህንነት ጉዳይ የሚመለከታቻቸው አካላትም ይህ በቀላሉ የሚታለፍ አጀንዳ ባለመሆኑ ነገሩን ትኩረት ሰጥተው እርምጃ ይወስዱበት ዘንድ በዚህ አጋጣሚ እጠይቃለሁ::
2. ይህ ሰው ማንን ወክሎ ማንስ ቢልከው ነው የቤተክርስቲያንን የውስጥ ጉዳይና መረጃዎቿን ለ3ኛ አካል የሚያስተላልፈው? የሚለው ጥያቄ በቀላሉ የሚታለፍ አይሆንም:: ማህበሩን ወክሎ እንዳይባል ከሰ///መ ስር የሆነው ማህበር አሁንም መምሪያው ሳያውቀው ከ3ኛ አካል የመገናኘት ስልጣን የለውም፡፡ እንዲህ ዓይነት የዱላ ቅብብሎሽ እንዳለም ቤተ-ክርስቲያን የምታውቀው ነገር አለመኖሩ ጉዳዩ የበለጠ ትኩረት እንደሚሻ የሚያመላክት ነው፡፡ ተቀጥሮ መስራት አይችልም ወይ ለሚለው ምስጢሩ በአደባባይ ተገለጠ እንጂ ሌባም እስኪያዝ ድረስ ንጹህ ነው፡፡

3ኛ. “ታዋቂ ባንከኛ” የምትለዋን የ Martin Lawrence "Blue Streak" የተሰኘውን የአሜሪካ ሙቪን አስታውሶኛል:: ፊልሙን ከዚህ ቀደም ላያችሁት ምን እያልኩ እንደሆነ ግልጽ ነው:: እዚህ ፊልም ላይ ማርቲን ፍቅረኛውን የተዋወቃት የባንክ ባለ ሞያ ሆኖ ሳለ ነበር፡፡ ውሎ አድሮ የማይገለጥ የለምና በአንደበቱም እንዳረጋገጠላት ለካ ታዋቂ ካዝና ቦርቧሪ/ዘራፊ ሆኖ ኖሯል፡፡

አቢይ አፈወርቅ አሁንም በመቀጠል እንዲህ ይተረጉማሉ፡፡
 "አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ ታዋቂ ሰዎችንና የቤተ-ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ያካተተ 20 ሰዎች ያሉበት ቡድን ለማደራደር ያደረገው ሙከራ መክሸፉን ያስታወሰው ሪፖርቱ፣ ግዝቱን በተመለከተም ውስጥ አዋቂ የሆነውና ከኤምባሲው ጋር ግንኙነት ያለው ባያብል ሙላቱ ያቀረበውን ትችት አጣቅሷል::"[1] ይልና ትችቱን በዚህ መልክ ያስቀምጠዋል "የሀይማኖትን ማእረግ መግፈፍ ማለት ልክ አንድ ሰው ከፖለቲካ ስልጣኑ እንደማውረድ ቀላል አይደለም:: ይህ ከአሁን በፊት ተወስዶ የማያውቅ ግዙፍ ርምጃ ነው:: ምክንያቱም ሹመቱ የእድሜ ልክ ነውና ብሏል::
ክህነትን ከፖለቲካ ጋር በማነጻጻር ሰው በፖሊቲካ አለም ቢያጠፋ ተመልሶ ወደ ስልጣን መምጣት/ወውጣት እንደሚችልና እንደሚቻል ሲናገር፣ የሃይማኖት ነገር ግን የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም እንደማለት ነው በማለት ይገልጸዋል:: ይህ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱ ትምህርት ነው ሲል በሪፖርቱ ነጮችን ሲያደናግር እናገኘዋለን:: እውነት ነው ክህነት ለዘለአለም ነው:: ግንብ አይደለም የሚፈርሰው! እንደ መጽሐፍ ቅዱስና እንደ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ስርዓተ ትምህርት አንድ ካህን ከክህነት አገልግሎት ሊያጎድለው የሚችለውን ስራ ፈጽሞ የተገኘ እንደሆነ በመሪዎች/አባቶች በሚሰጠው ቀኖና ለተወሰነ ጊዜ ከአገልግሎት ታግዶ ይቆያል:: የተሰጠውን የጾምና ጸሎት ጊዜ ገደብ ሲያገባድድም ወደ ቀድሞ ማዕረጉ ተመልሶ/በመመለስ አገልግሎቱን መስጠት ይቀጥላል:: ማቴ. 18:18 ላይ ቢመለከቱ ማሰር ብቻ ሳይሆን የታሰረም መፍታት እንዳለ ነው የሚያስተምረው፡፡ የዚህ ሰው ትንታኔ ግን “የቄስ ሚስት አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሐፍ አጠበች” ነው የሚያሰኘው::

ባያብል የእርቅ ሙከራውን በተመለከተ ደግሞ እንዲህ ይላል
 "የኢ/ኦ/ቤ/ን በ2 ሺህ ዓመታት ታሪኳ አይታው የማታውቀው አጣብቂኝ ውስጥ ነው የገባችው፡፡ ይህንን በሁለቱ ወገኖች መሀል የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት ምንም እንኳን በርካታ ታዋቂ ሰዎች ቢጥሩም ሁኔታው ከመስከኑ በፊት እየባሰበት መሄዱ አይቀርም አለ::" ይላል በገጽ 3 ላይ፡፡

ኤምባሲው አንዴ ተታሏልና “ታድያ አንተ ምን ትላለህ?” በማለት ውስጠ አዋቂ ነኝ ባይ ኪስ አውላቂውን ባያብል ሙላቱን መጠያየቃቸው አሁንም ባያስወቅሳቸውም የሰጠው መልስ ግን መመርመሩ ግድ ነው:: እንዲህ ላለ ጽንስን የሚያስወርድ/የሚያስጨነግፍ የማያምን ምላስ መጽሐፍ ቅዱስ ሆኖ እስኪታይ ድረስ ምላስህ ከትናጋህ ጋር ይጣበቅ ነው የሚለው:: ለበለጠ መረጃ የሉቃስ ወንጌል 1:20 ይመልከቱ::

ማሳሰቢያ
ኤምባሲው በየጊዜው ለበላዮቹ በሚልካቸው ሰነዶች ተሳስቶ ስለሚያስት አሳች ባያብል ሙላቱ ከተባለ "የማህበረ ቅዱሳን" ከፍተኛ የስራ አመራር የሆነው ግለሰብ የነበረውን ድብቅ/ምስጢራዊ ግንኙነት በተመለከተ ጻፍኩ እንጂ ስለ ተጠቀሰው የመረጃ መርበብ/ሚዲያ በቤተ-ክርስቲያን ላይ የተጻፈውን ዘገባ ተቀባይነት አለው - የለውም እያልኩ እንዳልሆነ አንባቢ ይገነዘብልኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ፡፡
በዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
yetdgnayalehe@gmail.com
United States of America[1] ሰነዱ በተደጋጋሚ “ከኤምባሲያችን ጋር ግንኙነት ያለው ባያብል ሙላቱ” ሲል ምን ማለት እንደሆነና ምን ዓይነት የስራ ድርሻ እንደሚያመላክት ልብ ይበሉ:: ያልሰማ ይስማ የሰማ ያሰማ!__

58 comments:

 1. thank you thank you thank you aba selama. this is really good. we love you.

  ReplyDelete
 2. what? r they mad? who is he any way? if he is mks top person. he is killing him self.

  ReplyDelete
 3. ማቅ የሀገር ጠላት ነው። ማቅ የቤተክርስቲያን ጠላት ነው። ማቅ የእውነት ጠላት ነው። ሊወገድ የሚገባው አሸባሪ ሰለፊ ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ደምሰ ማሙየMay 5, 2012 at 1:12 PM

   ማህበረ ቅዱሳን ጠላትነቱ ለበተክሪስቲያንንና ለሃገር ለማይጠቅሙ ነው ስለዚህ አትቀባጥር

   Delete
  2. ፃ መንፈሰ ርኩስ! እንዲህ የሚያስለፈልፍህ መንፈስ እርኩስ ነዉና ወንድሜ ሆይ ወደ ፀበል ብትሔድ መልካም ነው፡፡

   Delete
 4. bravo mule. endihe new engi bechahene anketeketkachew eko. lenegero lmk ewneten kyazu and sewem bezu new.

  ReplyDelete
 5. mk sirase eyetegelete new. anchi yager telat.

  ReplyDelete
 6. teret teret? yelam beret! eshi! ketilina ...

  ReplyDelete
 7. dn mulugeta betam asazenkegn kuchithn mewetath new?wechew gud@!

  ReplyDelete
 8. If your statement is true why don't you post the your reference link. Endelelaw gize hulu yehem wushet silehone bicha new.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቀና ብለህ እያ ማፈሪያ ማቅ የተቀመጠልህን ነገር ማየት አቅጦህ አትዘባርቅ

   Delete
 9. This indicates that MK has very dynamic and highly calibrated members. Why do you worry about each individual member personal issues? You are like devil you count the weak side of human beings! Please return to God! Mk is growing each year with graces of God. MK is now celebrating its 20 years anniversary!!! Long live MK!!!!!

  ReplyDelete
 10. ሁላችንም ከምናዉቀዉ ወጪ ምን ተናገረ
  እንደ ህዝብ ግንኙነት የተጠቀዉን መመለሱ ምን ክፋት አለዉ
  ከአሜሪካ ኤምባሲ አይደለም አሁን ያለዉን የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ እናንተ ሄዳችሁ ብትጠይቁ ተመሳሳይ መረጃ ታገኛላችሁ

  ReplyDelete
 11. kkk...ahun yih hulu dikam mkn kemengst gar lemagachet new? Atilfa mengist ewnetawn tenkiko yawkal.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጠንቅቆ ስለሚያቃችሁ እኮ ነው ሰለፊያ የተባላችሁት

   Delete
  2. ደምሰ ማሙየMay 5, 2012 at 12:59 PM

   ይህ ሁሉ እኮ አለማወቃችሁ ነው ስለዚህ እባካችሁ በአባቶች እግር ስር ቁጭ በሉና ተማሩ መማርን ያስተማረን እርሱ እራሱ መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው

   Delete
  3. even if u struggle the MK u will not win because GOD is always with MAHIBERE KIDUSAN .

   Delete
  4. KA...KA...KA...EGZIABHER MECHEM KEWUSHET GAR WEGNO AYAWKIM!!!!

   Delete
 12. Amilak masitewalun yisitachihu engi min enilalen. When you do such things, MK is becoming strong and strong every day. Thanks for helping us to shine more. Amen

  ReplyDelete
 13. አንዳንድ የማቅ አባላት የሲ. አይ. ኤ. ሰላዮች ሆነው ተገኙ
  Dear Abaselma The titel and the story you write is ARAMBA ENA KOBO.

  You are full of negativity.Why don't you write some thing constrictive for a change please .

  ReplyDelete
 14. i have readv the document of wikileaks but i have never seen that bayabel is part of CIA,he has a relation with EOTC synodos ia addis and synodos in USA.What makes it wrong he is doing good things.  you mad,don't kill your time go and dance at protestant house.

  ReplyDelete
 15. የዊኪ ሊክ ጽሁፍን እንደተረዳሁት ትኩረት ሰጥቶ የሚያትተው በሁለቱ /በአገር ቤት ባለውና በስደተኛው/ ሲኖዶሶች መካከል ስላለው ልዩነትና ችግር መፍትሄ የማፈላለግን ጉዳይ ነው ፡፡ ይህን ችግር የአሜሪካ ኤምባሲ ሊያተኩርበትና ሊከታተል የፈለገበት ምክንያት ደግሞ ስምምነት የሚገኝበትን መንገድ ለመሻት ነው እንጅ ፣ የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ለመገልገል ፣ ውስጥ ለውስጥ በሥውር ለመሥራት አቅዶና ፈልጐ አይደለም፡፡ አሜሪካ የሌለውና ከእኛ ቤተ ክርስቲያን የሚፈልገው ምን አለንና በድብቅ ይሠራል ? አንድ የሚፈልጓት ቅመ አያታችን ነበረች ፣ እሷንም ወስደዋታል ፡፡ ታዲያ ሌላ ምን አለ? ታቦት?

  ወደ ነገሩ ልመለስና በሁለቱም የቤተ ክርስቲያን አባቶች አሿሿም ላይ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እንዳለ ስለተመለከተ ፣ ይኸን ለመፍታት የሚቻልበትን መንገድ ለመፈለግ ፣ እየተሠራ እንደሆነ ጽሁፉ ያስረዳል ፡፡ በዛም ጉዞ ውስጥ ደግሞ የግለሰቦች ስም ተጠቅሷል ፡፡ በደፈናው ስም በመጠቀሱ ደግሞ የሲአይኤ ሠራተኛ አያስብልም ፡፡ ባያብል የተባለው ሰው ከሁለቱም ወገን ካሉ አባቶች ጋር እንደሚግባባ ፣ ገለጻውም ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችንን ችግር የተገነዘበ ሰው እንደ ሆነ ስለሚያስረዳ ፖሎፍ የተባለው ሰላምን ለመፍጠር ሊጠቀምበት ስለሚፈልግ ግንኙነት ፈጥሯል ማለት እችላለሁ ፡፡ ባያብል እየሠራ ያለው ለኤምባሲው በመደበኛ ሠራተኛነት ተቀጥሮ ይሁን ፣ በፈቃዱ ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት ተቆርቁሮ ፣ የተገለጸ ነገር የለም ፡፡ የራስ ግምትንና አቋምን መግለጽ ይቻላልና የተፈለገው መለያ ይሰጠው ፡፡ አሁን መጨረሻው ላይ ከአንድ አንባቢ አስተያየት ያነበብኩት ግን የማኀበሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንደሆነ የሚገልጽ ስለሆነ ፣ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሁሉም ጋር በኀብረትና በቀናነት መሥራት ግዴታው እንደሚሆን እገምታለሁ ፡፡

  ከላይ እንደገለጽኩት መልካም ግንኙነቱ ስላለን ፣ አሜሪካኖች የተነሱትና የሚሠሩት ጥቅም ለሚያስገኝላቸው ጉዳይ ቢሆን ግን በቀጥታ ኘሬዘዳንቱንና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወይም አቡነ ጳውሎስን ለማነጋገር ምንም የሚያግዳቸው እንቅፋት የለም ፡፡ ለአገር የሚበጅን ጉዳይ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር ተቀራርቦ መሥራት የሲአይኤ ሠራተኛ መሆንን አይገልጽምና ቢያንስ ርዕሱ ይቀየር እላለሁ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሁለት ነገር
   1 ስለ ታቦት ምን እንደሚፅፍ የማያውቀው ሙሌ አንድ ጊዜ ታቦተ ፅዮን የለችንም ብሎ ስለፃፈ ታቦቱ አያስጨንቀውም
   2 ሙሌ አንብቦ የመረዳት እና አሪፍ ፅሁፍ የመፃፍ ችግር አለበት:: ስለዚህ ምን እንደሚል አያውቀውም::

   Delete
 16. ጸሐፊው እውነትን አደባባይ ለማውጣት የሚያደርገውን ጥረት አደንቃለሁ ምክንያቱም ሁሉን ነጻ ሊያወጣ የሚችለው የተደበቀ እውነት ሳይሆን ግልጽ የሆነው ነውና፡፡ ነገር ግን በቅንነት ቢሆን ሐሳብም አለኝ

  ReplyDelete
 17. ይህ አስተያየት 'ማሩ አይምረር ወተቱ አይጥቆር' በሚል ርእስ ማቅ በብሎጉ ላይ ላሰፈረው
  ጽሑፍ የተሰጠ የግል አስተያየት ስላላወጣው በዚህ እንዲወጣ ለከዋለሁና መዝናችሁ ወስኑበት:-

  እንደሚታወቀው ማቅ የደጋፊዎቹን ብቻ እንጂ ትንሺ ከተቃወሙት አይደለም ጽሑፍን ሰውን ከመግደለ እንደማይመለስ የደረሰበትን ዲያቆን ሙሉጌታን ጠይቆ መረዳት ይቻላል:: ወገኖቻችን ናቸውና የእግዚአብሔር ምህረት ያግኛቸው:: ሰሞኑን ደግሞ ሞቱ እንደተቃረበ ተገንዝቦ ነው መሰል እንደ እብድ ውሻ ያገኘውን ሁሉ ለመንከስ እየጣረ ስለሆነ እውነተኛ የጌታ ልጆች ሙሉ የጌታን የጦር ልብስ በመልበስ ሁለት አፍ ካለው የበለጠውን የቃሉን ሰይፍ በቀኝ እጃችሁ በመጨበጥ ንቁ ተጋደሉ ክፉው ባህሪው መግደልና መስረቅ ስለሆነ::

  'ያእቆብን ወደድኩ ኤሳውን ጠላሁ' (ይላል ቃሉ)

  ሰውን ሁሉ እንድንወድ እንጂ መጥላት እንደሌለብን የታዘዝን ብንሆንም ተግባሩን በማየትና በንጹሕ ሕሊና በመመዘን ግን ለሃገርና ለሕዝብ የማይጠቅም ሆኖ በአንጻሩ ጎጂ ሲሆን ሰዎችን ሳይሆን ሥራውን አጥብቆ መቃወም ክፋት ያለው አይመስለኝም::

  ከዚህ አንጻር ታዲያ ማቅ ለሃገር ብዙ መልካም ቁምነገር ማበርከት የሚችል የብዙ በርካታ ምሁራን ስብስብ መሆኑ ባይካድም በመማር ብቻ መልካም መሆንና የመልካም ሥራ ባለቤት መሆን ያስችለዋል ብዬ አላምንም:: ምድራችንም ሆነች ቤተክርስቲያናችን ያዋቂዎች/የተማሩ ሰዎች እጥረት/ችግር ያለባት አይመስለኝም:: ከራስ ወዳድነት የጸዳና ለሌላው ወገኑ መልካም የሚያስብ ንጹህ ልብ ያለው የታማኝ ዜጋ እጥረት እንጂ! ያውም በመንፈስ የሚቃጠል!!!

  ውድ ወገኖቼ! አንዳንድ በምሰጣቸው አስተያየቶች ተመስርታችሁ እንዲህ ናት እንዲያ ናት ወይም የእኛ ደጋፊ አይደለችም በማለት እንደፈረዳችሁ እገምታለሁ:: ለዚህ መረጃ መጥቀስ ቢያስፈልግ በዚህ ብሎግ ላይ የምሰጣቸው የግሌ አስተያየቶች የውሃ ሺታ ሆነው መቅረታቸው ብቻ በቂ ምስክር ናቸው::

  እኔ በበኩሌ የሁላችንም የልብ አምላክ እንደሚያቀው መሻቴ አንድ እና አንድ ብቻ ነው:: እሱም ንጹህና ያልተበረዘው የጌታ ወንጌል በዚች ሁላችንንም ባሳደገች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብሎም በምድራችን ዙሪያ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሲሰበክና ሕዝባችን የሚያመልከውን አምላክ በሚገባ አውቆ በነጻነት ሲያመልክ ማየት ነው:: በእውነት ነው የምላችሁ ከዚህ ውጭ ሌላ የተደበቀ ሕልም የለኝም:: እንዲያው ግንዛቤ እንዲኖራችህ ያህል እንጂ የልቤን ለእናንተ መንገር ፈልጌ አይደለም:: በዚህ ዓላማዬ ደግሞ ውጤት ከላይ ከሰማይ አምላክ እንደሚገኝና የእኔና የመሰል ወንድሞቼ እንባ አንድ ቀን እንደሚታበስ እጅግ የጸና እምነት አለኝ/አለን:: መቼም ሁላችንም በዚች ሁለንተናዊ ችግር በከበባት ምድር ውስጥ ተወልደን ያደግን ሰዎች ያለመታደል ሆኖ መደማመጥና በጋራ ለመልካም ሥራ መቆም አቅቶናል:: ምድራችን ፕ/ር መስፍን በደቂቀ እስጢፋኖስ መጽሐፍ ላይ እንደጠቆሙት ብልጭ ብለው ድርግም ያሉና የሚሉ ሰዎች ባለቤት እንጂ ቀጣይ እድል አግኝተው በውስጣቸው የተጸነሰውን መልካምና ጠቃሚ ጽንስ ወልደው በማሳደግ የታወቁ አልነበሩም/አይደሉምም:: ታዲያ በዚህ መልኩ ስትታይ የምድራችን መለያ ባሕሪ በጽንስ አስወራጅነቷ እንጂ ወልዳ በማሳደግና ለቁም ነገር በማብቃት ባለመሆኑ 'ከስልጣኔ በር ላይ ቀድመን ደርሰን በሩ ላይ ተገትረን ስንቀር ከኋላ የመጡት እየቀደሙን የገቡት' በማለት ልብ የሚሰብር ቃል ያስተላለፉት:: ለነገሩማ እሳቸውም ቢሆኑ እድሜ ልካቸውን ለራሳቸው ሳይሆን ለሕዝብ መብትና ነጻነት አይደል ሲታገሉና ሲጮሁ የኖሩት ያውም ብዙ ዱላ በላያቸው እየወረደባቸው:: ዛሬም እያልን ያለነው ከውገረው ከበለውና አሳደው በፊት ማነው? ዓላማው ምንድነው? የሚለው ይቅደም ነው:: አንዱ ያንዱን ስም ጥቁር ቀለም አይቀባ ነው:: እስቲ በዚች ቤተ ክርስቲያን ማን ምን እያደረገ እንደሆነ ቆም ብለን በሰከን መንፈስ እንመዝነው እስቲ ለህሊናችን ነጻ ፍርድ እራሳችንን እናስገዛውና የራሳችንን ውሳኔ እንስጥ

  ስለዚህ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢዎች! ዛሬ እኛ ኢትዮጵያውያን ቢያንስ ማን ማነው? የተባለውን ጥያቄ ማነው? የተባለው ወገን በእራሱ እንዲመልስለት ሳይሆን በእለት ከእለት ተግባሩ እያየንና እየመዘን የምንመልሰው መሆን አለበት እንጂ እኔ እንዲህ ነኝ ያለ ሁሉ ነው ብለን የምንቀበልበት ደረጃ ላይ አይደለንምና የማንን ማንነት መልስ ለራሱ ለሕዝቡ ብንተወው መልካም ይመስለኛል::

  ከዚህ በተረፈ ሁሉንም ወቅትና ታሪክ ስለሚገልጠው ቅን ፈራጅ ለሆነው ጌታ ብንተወው መልካም ነው እያልኩ ለዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ (መልእክቱ ላይ ብቻ በማተኮር) አድናቆቴን ሳልነፍገው ለሁላችንም የሚበጀን እውነትን በእውነትነቱ ከልብ በመፈለግና በማድረግ በጋራ ስንንቀሳቀስ ነውና እግዚአብሔር ይርዳን ማስተዋልንም ያብዛልን:: አሜን:: የእናንተም ሆነ የሌሎች ማንነት በጌታ ፊት የተገለጠ ነው:: በእሱ ዘንድ መሆን እንጂ ማስመስል የለምና በዚህ ደስ ይበለን አሜን! አሜን!! አሁንም አሜን::

  መሻቴ የሁላችንንም መልካምነት እንጂ ሌላ አይድለም

  ሰላም ለሕዝባችንና ለቤተ ክርስቲያናችን!!!

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Selam,

   Create a reconcile within yourself first. The church has its own belief and your belief does not belong to us and our beloved church, and I assure you what ever fight we go we will defend the church till death. So, please find your place where your belief belongs for, with no doubt the protestant church, which is the congregation of selfishness with selfish people. I myself was their member and know everything from A to Z. Thanks to God, am back to the true church and has got my place and peace and eternal life in it, alas.

   And true Christians never ever say, crying for that and this, e.g.'የእኔና የመሰል ወንድሞቼ እንባ......', which you always shamelessly say it in every of your comments. If you do so, keep it for yourself. You know what, such are the words the protestants (old friends) use while they really were not doing it or showing a practical life, love others with out any condition etc.

   Delete
  2. If you are really living what you are writing, please expose yourself, tell us who you are,put your picture, then we will follow you. Other wise, you are from wolves. Ewunetin yeyaze erasun ayidebikim!!!!!!!!!!!!!!

   Delete
  3. አሁን አንቺ እኮ ባንቺ ቤት ሰው ይገድላል ብለሽ ስትዋሺ ቅር ያላለሽ ውሸት ያልመሰለሽ ለጌታ ስለምታደርጊው ነው አይደል?
   አይ ግብዟ ሰላም::

   Delete
  4. "ለነገሩማ እሳቸውም ቢሆኑ እድሜ ልካቸውን ለራሳቸው ሳይሆን ለሕዝብ መብትና ነጻነት አይደል ሲታገሉና ሲጮሁ የኖሩት ያውም ብዙ ዱላ በላያቸው እየወረደባቸው"

   previously you seem Anti Ethiopian Orthodox Church, now ur real identity is becoming clear. Anti EPRDF, you r kinjit.

   Delete
 18. yihe mulugeta yemibal sew gin min yakil dekama endehone berasu eyegeletse new. mawashe enkua endet endehone ayawukim. dekama!

  ReplyDelete
 19. አይ ማህበረ ቅዱሳን\ የተደበቀ አላማችሁንና የቤተክርስቲያን ጠላትና የሐገር ጠላት እንዲሁም የለየላችሁ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የተለያየ ሸቀጥ ነጋዴዎችና አሸባሪዎች መሆናችሁን በመላው ዓለም ያሉ ምዕመናንና መንግሥት ስለነቃባችሁ ያንን ለማረሳሳት የቀየሳችሁት የማዘናጊያ መንገድ ነው እንጂ እውነት እናንተ ከመቼ ወዲህ ነው ለቤተክርስቲያን አስባችሁ የምታውቁ? ነው አጠቃቀስኩ ለማለት ነው? ከፅሑፉ መግቢያ ላይ እንደተገለፀው 20 ዓመት ሙሉ በቤተክርስቲያን ሥም ምዕመኑን ስትዘርፉ የኖራችሁትን ብር አሁን ከግራ ከቀኝ ከላይ ከሰማይም ሰለተነቃባችሁ በትራክ የዘረፋችሁትን በማንኪያ ልትሰጡ መሞከራችሁ ነው ? ኪ\\\ኪ\\ኪ\\ኪ\ እግዚአብሔርን ማታለል አይቻልም።
  እውነትም ቴረሪስት፡666

  ReplyDelete
 20. ማቅ ድሮውንም ሌላ አጀንዳ የለውም፡፡ ሀሳቡ እንቅስቃሴው ህልሙ ሁሉ 4 ኪሎ ቤተመንገስት ነው፡፡ ሥልጣን እንደ ጠላ አሻሮ የትም የሚገኝ እየመሰለው ይደክማል እንጂ መቼም አያገኘው፡፡ እርሱ የእውነት ጠላት ነው፡፡ ፈቅራቸው ከሀሰት ጋር ነው፡፡ የማቅ ትክክለና አባትም ዲያቢሎስ ነው፡፡ የዲያቢሎስ ልጆች በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሀይልና ስልጣን ይወድቃሉ፡፡

  ReplyDelete
 21. Are Abuna Timotewos and Abune Gerima CIA Agents? They are not in my opinion. But they are equally referenced in this cable document with Bayable.

  We need to look the whole message and the perspective of wikileaks.

  The writer twists the message of the cable for his purpose i,e deceiving people.

  On February 6, Poloff and senior political FSN met
  with Ethiopian Orthodox Church (EOC) officials Abuna
  Timotewos, Dean of the Trinity College (the EOC's school for
  top church officials), and Abuna Germina, the EOC's foreign
  relations officer to discuss reports of a deepening rift
  within the EOC. Both bishops are members of the Holy Synod
  in Addis Ababa and are long-serving, senior members of the
  EOC. On February 7 Poloff met with Bayabel Mulatu, a
  respected Ethiopian banker who is well-connected to the Synod
  and Patriarchs in both Ethiopia and in the US.

  ReplyDelete
 22. ማህበረ ቅዱሳን 20ኛ አመቱን ሊያከብር ነው! ይገርማል!
  1 ሰውን በመክሰስ
  2 መነኮሳትን በማሳደድ
  3 ቤተክርስቲያንን በመዝረፍ
  4 ኢየሱሳውያንን በመግደል
  5 ወንጌልን በማጣመም
  6 አገርን በመካድ
  ስንቱ ተነግሮ! አመተ ምህረት የሌላቸው አመተ አለምን የሚቆጥሩ የተዋህዶ ጀግኖች!ኢየሱስን የሚያውቁ ነገርግን ኢየሱስ የሌላቸው! የሚያከብሩት የ እድሜ ዘመን ከላይ ወደታች እንዲዎርድላቸው አደራ እላለሁ! ከአሁን በኋላ የማቅ አባልነቴን በገዛ ፈቃዴ ልቅቂያሉ! ግልባጭ ለአባ ሰላማ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቂቂቂ ሳቅቼ ሞተሁት አለች አሉ ያነት ብጤዋ ፍልፈል !!! እንግዲህ ምን ትሆን የኑፋቄ መረባችሁን ይበጣጥስ ዘንድ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ በራሱ ሰዎች የመሰረተው ማህበር ለቅድስት ቤተክርስቲን ተላቶች ሳይተኛ እና የጎን ውጋት እንደሆናችሁ 20ኛ ዓመቱን ሊከብር ነው፡፡ አይናችሁ ደም ለበሰ ፡፡

   Delete
  2. ማን ይሉሃል?

   Delete
  3. Ha ha ha
   who do you think recognize you in MK?

   Delete
  4. የማነህ ገንገበት አነጋገርህ ሁሉ ምንም እውቀት የሌለህ ባዶ የንብ ቀፎ መሆንህን ያሳብቅብሃል፡፡ ማነው እንዳንት ያለውን የማህበሩ አባል ያደረገው በል እኔ እስካሁን በማህበር አባልነቴ ስኖር በአነጋገሩ እንዳንተ ያለ ጭፍን ጥላቻ ያለው ክርስቲን አጋጥሞኝ አላውቅም፡፡ አትጃጃል አንተ! ለነገሩ ባለጌ አፉን እንጂ እግሩን አያዳልጠውም ይባል የለ፡፡

   Delete
 23. Ur title is'ANDAND' but u write about only one person.Why so?This shows wrong generalization and ur mere, unfaithfull,uneducated and untrusted presentation.

  ReplyDelete
 24. good job, Mulla:)

  ReplyDelete
  Replies
  1. Here in Kenya,Nairobi a nun from debre libanos monastery her name is called Emmahoy Wolete tinsae and her nick name "Erub guday" and a monk from Australia his name is called Abba Gebreegziabher now "Ermiyas" they got married each other by getting assistance from a priest who is the member of "mahibere kidusan" serving at medihanialem Ethiopian orthodox church a year ago and now they are a parent of one child whose name is called "Nebiyu".
   Good job Mk.
   N.B. The priest who is the member of mk is also called Kesis Gebreegziabher. Now the married nun is living with this priest untill she travel to Australia.

   Dear readers you can't found this news from hamer or simatsidk because this is done by themselves have you got me, if this is done by someone else who is not the member of this evel "MK" you can find it at the top of their news magazine as a head line or as breaking news.

   Delete
 25. አቤት ዲያቆን ሙሉጌታ እንዴት ጊዜ የተረፈህ ወያኔ ነህ። ስል ማህበረቀዱሳን ለመከራከር አይዳዳኝም ነገር ግን እንዴት ሕዝበ ክርስቲያኑን ለማሳሳት የመለስ አፍ ሆነህ ማህበረ ቀዱሳንን ከቅንጅት ጋር እንዳገናኘኸው ይገርማል። መለስ እኮ ሰሞኑን ጥያቄያነሱትን ሙስሊሞችንም አሁን እንዳልከው በጪ አካል የሚታገዙ የቅንጅት ርዥራዦች ይላቸዋል አንተ ደግሞ አንዴ ክርስቲያን መሰል ሳይቶች ላይ አንዴ ደግሞ በፖለቲካ ሳይቶች ላይ እየመጣህ እንደበቀቀን መለስ የጮኸውን ጩኸት ታላዝናለህ አይ አለመታደል!!!!!!!!! "ይህም ያልፋል" ያኔ ምን ትሆን ይሆን። እግዚአብሄር ሃገራችንንና ሕዝባችን ይጠብቅልን። ከዲያቆን መሰል አጉል ፖለቲከኞች ይጠብቀን።

  ReplyDelete
 26. I used to be Tehadsso then Protestant church goer. Now I am wondering about the so called "Tehaddso"! They see themselves as a group clearly understand Holy Bible! The realty is they can't even interpret English properly. The document does NOT say Bayabel Mulatu being a member of cia. Full of lie.

  ReplyDelete
 27. i understand Bayabel is working to solve the problem between the church in US and Addis ,he is not spying for protestants.BRAVO BAYABEL.the wikilik doesn't say he is the member of CIA.but what is wrong if he is a member of CIA?

  ReplyDelete
 28. በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያላችሁን ቀስትና ጦር አስወነጨፋችሁ:: ጦራችሁና ቀስታችሁ እንኳን ቢያልቅ በሊዝም ቢሆን ተከራይታችሁ ማቅ ላይ መርገፋችሁ አይቀርም:: የሚገርመው ግን ማቅም ራሱን እንደሚመታ ሚስማር እየጠበቀ በናንተና በመሰሎቻችሁ የሚሰነዘርበትን ጥቃት እያለፈ ነው:: ወደፊት ደግሞ የሁላችሁንም መድረሻ ያሳየናል:: ለአሁኑ ግን በማቅ ላይ የምትሰነዝሩት ጥቃት ሁሉ ከጥላቻ ላይ ብቻ የተመሰረተ ለመሆኑ ጠንቋይ መፈለግ አያስፈልግም:: ውሸቱን ስትጨርሱ ምን እንደምትሉ እናንተና የስምሪት አለቆቻችሁ ብቻ ናችሁ የምታውቁት::
  ሙሉጌታ

  ReplyDelete
 29. give me the source that u got the information

  ReplyDelete
 30. Ere bakachihu...maninetachihun eyegeletachihu mehonun teredut...Mahiberekidusanin yemayawik EOTC liji/miemen yelem..behulum ewinetegna ye Orthodox lijoch zend yetamen lebetekirstian yemiyasfeligat mahiber new.ke Betekinet yilk hizbu yemiyaminew mahibere kidusanin silehone zim bilachihu batidekimu tiru new...

  Enante(aba selama) leboch nachihu...leba beber endemayigeba hulu enantem yematitaweku ye menafikan lijoch nachihu..Egziabher Enanten sil betekirstianachin selam sil yaswegidilin!!!!AMEN

  ReplyDelete
 31. It is good writing because it showes how the writer is foolish .he couldnt undertsand what the subject matter is written in the whole statement. pls the writer re-read it or ask the translation if you donot understand!How somebodys name listed with the embassiy could considerd as that? By this analysis we do have thousends of Ethiopians working with the embassy formaly.Are you going to say ..... What a shame it is ! It showes you have a blined view to MK . let God open your Eye

  ReplyDelete
  Replies
  1. The matter is H/giorgies does not know English!

   Delete
 32. እንደ አንድ ታዛቢ የምለው እንኳን ሆኑ:እሰይ ድንቅ አደረጉ የማቅ አባላት;ሙሉ ጋኔን እፈር::ስለዚህ ቢሆኑማ ጥሩ ነው አሁን ካለህበት አሜሪካ ሊያባርሩህ ይችላሉ ማለት ነው::ያልከው ዉሸት ነው እንጂ ቢሆንማ መለስም ማኅበሩን እንዲህ በሚዲያ አይሰድበዉም ነበር;አምላኩ አሜሪካ ስለሆነ::እውነት ነው ብለህ ከተቀብክማ አፍህን ዝጋ::እግዚአብሔርን ለማይፈራ እንደ አንተ ላለው ሙሉጋኔን አሜሪካ አምላኩ ስለሆነ እነሱንም ፍራቸው::አንተ እንደሳልከውና እንደምትለው እንዲህ ጨካኝ ማኅበር ከሆነ እኮ አንተንም እንደ ገነት ቆጥረህ ከምትመጻደቅበት አሜሪካ እንዳያስወጣህ:መለስንም ከስልጣኑ እንዳያወርደው ተጠንቀቁ::

  ReplyDelete
 33. Mk rename himself as unite of Sundayschool here in USA that other strategy to kill our church fathers. Close source from Dallas said false priest who have naive of formal education his name kesis Erget kulla traveled to Ethiopia last week to transfer gubo or corruption money to shermuta papas to attack abune fanuel. On the otherhand to deliver yangster money to start arab style uprising by using of fake kint also to spy Eotc and gov. Any of you will see him any where just take care him and go to heaven.

  ReplyDelete
 34. ማቅ አንዳንድ አባላት የሲ,አይ,ኤ አባላት ናቸው ላልከው እንደ አንድ ታዛቢ የምለው እንኳን ሆኑ:እሰይ ድንቅ አደረጉ;ሙሉ ጋኔን እፈር::ስለዚህ ቢሆኑማ ጥሩ ነው አሁን ካለህበት አሜሪካ ሊያባርሩህ ይችላሉ ማለት ነው::ያልከው ዉሸት ነው እንጂ ቢሆንማ መለስም ማኅበሩን እንዲህ በሚዲያ አይሰድበዉም ነበር;አምላኩ አሜሪካ ስለሆነ::እውነት ነው ብለህ ከተቀብክማ አፍህን ዝጋ::እግዚአብሔርን ለማይፈራ እንደ አንተ ላለው ሙሉጋኔን አሜሪካ አምላኩ ስለሆነ እነሱንም ፍራቸው::አንተ እንደሳልከውና እንደምትለው እንዲህ ጨካኝ ማኅበር ከሆነ እኮ አንተንም እንደ ገነት ቆጥረህ ከምትመጻደቅበት አሜሪካ እንዳያስወጣህ:መለስንም ከስልጣኑ እንዳያወርደው ተጠንቀቁ::

  ReplyDelete
 35. ይድረስ: በተለይ May 5-6/2012 ከእኔ አስተያየት በኋላ በተከታታይ በእኔ ላይ ብቻ ያነጣጠረ አስተያየት ለሰጣችሁ የሥጋ ወገኖቼ!!!

  1) Selam በማለት የጻፍከው:

  - ከራሴ ጋር እንድታረቅ ያቀረብከውን ሃሳብ ለተጣላ ሰው የሚሆን የእርቅ ምክር በመሆኑ ይህ ችግር ያለበት ሰው አንብቦ ሊጠቀምበት ስለሚችል ሳታውቀውም ቢሆን መልካም ሃሳብ ሰንዝረሃል::
  - ሌላው ያንች እምነት የእኛ አይደለም ያልከውም ሃሳብ እውነት ነው:: እኔ በመጽሐፍ
  ቅዱስ ላይ ብቻ የተመሰረተውንና ከማርቲን ሉተር በፊት የእምነት አባቶቻችን እነደቂቀ
  እስጢፋኖስ የሞቱላትን ቀጥተኛ የሆነችውን የቀደመቸውን (ሳትበረዝ)የኦርቶድክስ ክርስትና
  እምነት የያዝኩ ስለሆነ ከዚህ ውጭ ከሆናችሁት ጋር ሁሉ እምነቴ አንድ አይሆንም::
  - መልእክቱን የጻፍኩት እኔ ሆኜ ሳለ ስለ ፕሮቴስታንት እንዲህና እንዲያ በማለትህ የማያገባኝ
  ጉዳይ ቢሆንም ትንሽ ወደ ወንጌል ጠጋ ያለውን ሁሉ ጴንጤ/ፕሮቴስታንት በማለት መወንጀሉን
  ሁላችንም ያደግነበት ክፉና ያፈጀ ልማድ ስለሆነ አይደንቀኝም:: አንተ ግን እነሱ ጋ ዘለህ
  ገብተህ እንደወጣህ መግለጽህ ያንተን ያልሰከነ ባህሪ ሳታውቀው ከማጋለጥህ ባሻገር ጽኑ
  የሕይወት ውሳኔ የማድረግ አቅም እንደሚያጥርህ ነው የሚያመላክተው:: ምክናቱም ምን አይተህ
  ሄደህ ምን ዓይተህ ተመለስክ? ለሚለው ጥያቄ መልስ የለሕምና::
  - ሌላው አሁን ተመልሼ ሰላምና የዘላለም ህይወት አግኝቻለሁ! በማለት የጠቀስካቸውን ቃላቶች
  በሚገባ ተረድታሃቸው ከሆነ የሚጠቁሙት 'እኔ ህይዎት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸው መጣሁ'
  'ሰላሜን እሰጣችኋለሁ የእኔ ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም' ልጁ ያለው የዛላለም
  ህይውት አለው' በማለት የተናገረውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ነው:: ታዲያ መጀመሪያ
  ያላገኘኸውን ጌታ ስትመለስ እንዴት አገኘኸው???? አጻጻፍህስ የጌታ መሆንህንና በእውነት
  ሰላም ያገኘ ሰው ዓይነት ነውን? የጌታ ሰው ሌላውን አይኮንንም ብዬ ነውና በጥሞና
  ብታስረዳኝ???
  -ለአገርና ለሕዝብ በእንባ የታገዘ ጸሎት ሁሉን ወደ ሚችል አምላክ ማቅረብ የእውነተኛ ክርስቲያን
  ዋና ሥራ ስለሆነ ይህ መባሉ አንተን ምን አስከፋህ? ሰይጣን ብቻ ነው ሊከፋው የሚገባ::
  -በአጠቃላይ ይህና ሌሎች መድረኮችን ስለቤተ ክርስቲያናችንና ብሎም ስለህዝባችን ህይወት
  መሻሻል የሚጠቅሙ ሃሳቦችን የምንሰነዝርበትና ለመልካም ውጤት የምንመካከርበት ስለሆነ በግል
  ህይዎት ዙሪያና በእንካ ስላንትያ ላይ ጊዜህን ባታቃጥል በእህትነቴ እመክርሃለሁ::

  2)የሁለተኛው ጸሐፊ ሃሳብ/ጥያቄ ደግሞ:

  እውነተኛ ሰው እራሱን አይደብቅምና ማንነትሺን አጋልጭ ፎቶግራፍሺንም አውጪውና እንከታተልሻለን የሚል ነው::
  በመሰረቱ Anonymous በማለት እራሱን የደበቀ ማነው? እኔ በስሜ ነው እየጻፍኩ ያለሁትና በምትለው ነገር እራስህን መልሰህ እያጋለጥክ መሆንህን እስቲ ቆም ብለህ አስብበትና መልሱን እራስህ መልሰው?
  ፎቶ ግራፍሺን አውጪ ለሚለው ጥያቄህ ግን መልሱ ባጭሩ 'ለጥላ ወጊ' ደጋሚ ደብተራ እንዳልመች 'እምቢዮ' ነው:: ደግሞስ እንከታተልሻለን የሚለው አባባልህ ትንሽ ማንነትህና የማን ወገን መሆንህን አያመላክትም ትላለህ? 'የክፉን ሃሳብ አንስተውም' የሚለው የጌታ ቃል ትዝ አይልህም? ነው ወይስ መጽሐፍ ቅዱስን ነክተኸው አታውቅም?? ብዙዎቻችንም እኮ በጴንጤዎች ጥቅስ ጠቃሺነት እልህ ተጋብተን መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ነው በጌታ ፍቅር የተለከፍነውና አንተም/እናንተም ወገኖቼ ቃሉን ለማንበብ እልህ ቢይዛችሁ ብዬ ነው ይህን ሁሉ የምልህና ወገኔ/ወገኖቼ እባካችሁ ፍቅር ያለበትን በጎ የሆነውንና ለሁላችንም የሚበጀውን እናስብ እንጻፍ እናድርግ? ከዚህ ውጭ ግን ዓለማውያን ሴት ወገኖቼ እራሳቸውን ለገበያ እንደሚያቀርቡት ዓይነት ነገር ፎቶ ግራፍሺን አውጪ የሚለውን ጥያቄህ ግን ማን ያውቃል አንድ ቀን የጌታ መንፈስ ወደ ሙሽራው አካል ሲጨምርህ በፎቶ ብቻ አይደለም በእውን እንደምንተያይና ለቤተ ክርስቲያናችን የወንጌል ሥራ አብረን እንጠመድ ይሆናል:: ለነገሩ ጌታ በምድር በነበረበት ወቅት 'አብ ካልሳበው በቀር ወደ እኔ ማንም ሊመጣ አይችልም' የሚለውን ሕያው ቃል አስረግጦ ስለተናገረ በመስቀሉ የፍቅር ገመድ ይሳብህ/ይሳባችሁ እላለሁ:: የዘወትርም ጸሎቴ ነው::

  በ 3ኛውና በ 4ኛው አስተያየት ጸሓፊዎች ላይ ይ ቀ ጥ ላ ል......


  የጌታ ምህረት ያግኛችሁ!!

  የጌታ ሰላምም ያግኛችሁ!!

  የተቃወምኩት ለክፉው መጠቀሚያ የሆነውን ሃሳባችሁን ነው!!!

  እናንተን ግን በጌታ ፍቅር በእውነት እወዳችኋለሁ!!!!

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለ አባ እስጢፋኖስ ዘጉንዳጉንዲ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ፡-

   - በአባቶች ትምህርት የሥላሴን አንድነትና ሶስትነት ለማስረዳት በፀሐይ ክበብ ፣ በብርሃኗና በሙቀቷ መመሰላቸውን አይቀበልም ፤ ምናልባትም እንደ ሞርሞን ሃይማኖት ፣ አንድነት የሌላቸው የተለያዩ ሶስት አካላት የመሰለ ግንዛቤ ያለው ይመስላል
   - ድንግል ማርያምንና የጌታ መስቀልን ማክበርና መስገድ ይቃወማል ፡፡ መጽሐፍ ግን መልአክ ሳይቀር ድንግል ማርያምን እንዳወደሳትና እንዳከበራት በሉቃስ ወንጌል ይናገራል ፤ ሌላውም አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መረገጫ ስገዱ።/መዝ 99:5/ ይላል ፡፡ ለምናምን መስዋዕት በሆነበት ወቅት ፣ ደሙን ያፈሰሰበትና የእግሩ መረገጫ የነበረው መስቀሉ ነውና መስገድ ይገባናል ፡፡
   - ለስዕል ሲሰገድ ፣ በስዕሉ ላይ ለተመለከተው መላእክት ወይም ቅዱሳን አምላክ መሆኑን ባለመገንዘብ ለስዕል መስገድንም ይቃወማል ፡፡
   - መላእክትንና ቅዱሳንን ማክበርና ለእነሱም መስገድ አይገባም ይላል ፡፡ አግዚአብሔር ያቀረባቸው ዳንኤልና ዮሐንስ ግን አይገባም ፣ አታድርጉት እስኪባሉ ድረስ ሲሰግዱ ተስተውሏል ፡፡
   - ለሞቱ ቅዱሳንና ለመላእክት መጸለይን ይቃወማል ፡፡ መጽሐፍ ግን እንኳንስ ለቅዱሳኑ እኛ በቁማችን በበደል ለሞትነውም አንዱ ለአንዱ እንዲጸልይ ያስተምራል
   - ንጉስን አክብሮ ሰላምታ መስጠትን ይቃወማል ፡፡ መጽሐፍ ግን ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ ፣ ለንጉሥም ቢሆን ከሁሉ በላይ ነውና ፣ ለመኳንንትም ቢሆን ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ ፡፡ 1 ጴጥ 2፡13 – 14 የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ተጋፍቷል
   - ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ፣ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አባቶች የተቀበሉትን የሐዋርያትና የአርድእት የትውፊት ትምህርትና መጽሐፍት ተቃውሟል
   - መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን /ያዕቆብ 2፡14 – 26/ በመቃወም ፣ ያለ ምግባር በጸጋ ብቻ እንደሚዳን አስተምሯል ፡፡ ይህም አቋሙ ሉተር ከመነሳቱ ሰባ ዓመት በፊት የኘሮቴስታንት ትምህርት ዓይነት እምነት ሊመሰርት የሞከረ አባት ነው ያስብላል ፡፡

   ይኸ ሁሉ ከመጽሐፍ ጋር የማይስማማ አቋሙ እየታወቀ ፣ የውጭ ጸሃፊዎች ሳይቀሩ ከሉተር በፊት ሊመሠረት የነበረ የኘሮቴስታንት ሃይማኖት መሆኑን እየመሰከሩ ፣ ተሃድሶ ነን የሚሉ ወገኖች ለምን ዘወትር የአባ እስጢፋኖስን ትምህርተና እምነት እንጋራለን ብለው ይመሰክራሉ ቢባል ፤ አጭሩና ቀጥተኛው መልስ ፣ የኘሮቴስታንት ትምህርት ተከታዮች መሆናቸውን ቢናገሩ ማንም እንደማያዳምጣቸው ስለሚያውቁ ሽፋን ፍለጋ ነው የሚል ነው ፡፡ አባ እስጢፋኖስ የኦርቶዶክስ እምነታችንን ሊበርዝ የታገለ ለመሆኑ ከላይ የተዘረዘሩት አቋሞቹ ያስረዱናልና ፣ አባ እስጢፋኖስ ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ስለሆነ ብቻ አልተሳሳተም ፣ አይሳሳትም የሚል ግምት እንዳይያዝ በማለት ይህን ጽፌአለሁ ፡፡ አርዮስና ንስጥሮስም የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ነበሩና የማይሳሳት አይኖርም ፤ ስለዚህም በተለይ በአሁኑ ሰዓት ሁሉንም በሚያስተምረውና በሚከተለው እምነት መመዘን ተገቢ ነው እላለሁ ፡፡
   መልካም ንባብ

   Delete
 36. የ ቀ ጠ ለ......

  3)ሶስተኛው ጸሐፊ:
  'ሰው ይገላል' የሚለውን ውሸት ለጌታ ብለሽ ነው የምትዋሺው:: 'አይ ግብዟ ሰላም'
  >ሌባው ሊሰርቅ ሊያርድ ሊገድል መጣ< የተባለው እኮ እውነተኛ ገዳይ ስለሆነ ነው:: አሁንም ማቅ እንደ እነ ዲያቆን ሙሉጌታ ያሉትን የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች በነጭ ለባሽ እያፈነና እያሳፈነ ከአገር እንዲሰደዱ ሲያደርግ አልገደለም ነው የምትለኝ? እስቲ 'ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን' የሚለውንና ሌሎች በማቅ ላይ የተጻፉትን መጽሐፍትን አንብብ:: ታዲያ ጌታ ጴጥሮስን 'ሒድ አንተ ሰይጣን' ሲለው በንግግሩ የተጠቀመውን ክፉ መንፈስ አልነበረምን? አሁንስ ይህን የመሰለ ሥራ የሚሰሩትንና የክፉው መንፈስ ፈረስ በመሆን የቤተ ክርስቲያናችንን 'ዓይናማ ልጆች' ያዘው ልቀቀው በለው ውገረው እሰረው 'የማርያም ጠላት' ወይም ፕሮቴስታንት' ወይም 'ጴንጤ' የሚል ጥላሸት እየቀባ የሚያሳድደውን ምን እንበለው? እስቲ ይህን ለሚያደርግ አካል እራስህ ስም አውጣ ብትባል ደጉ! ምንተስኖት! በማለት ታወጣለት ይሆንን??

  4) አራተኛ አስተያየት ሰጪ:
  'በፊት የኦርቶዶክስ ጠላት ትመስይኝ ነበር አሁን ግን ጸረ ኢሕዴግ አቋም ያለሽ ቅንጅት ነሺ'
  አሁንም በእኔ ማንነት ላይ ያጠነጠነ ጉዳይ ነው:: ለነገሩ ሁሉንም አስተያየቶች አንድ ሰው ቅርጹን ለወጥ እያደረገ የጻፋቸው ይመስላሉ: የሚገርመው ግን እኔ ምንም ልሁን ምን ቁምነገሩ ከመልእክቱ ምን እንማራለን? የጽሑፉ አቀራረብ ህጸጽ ምንድነው? የሚለውን የሳተን ሊያስተምር በሚችል መልኩ እነዚህ 4 አስተያየቶች አለመቅረባቸው ነው::
  አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ ዓይነት አስተያየት የሚያቀርቡ ሰዎች ሳይኮለጂስቶች ሊመስሉ ይቃጣቸዋል:: ለእነሱ የማይመስል ሃሳብ ያቀረበ ሁሉ ስምና ድርጅት ይሰጥዋል:: መንግሥት አንድ ጥሩ ነገር ከሰራና ይህንኑ እውነት የተናገረ ሁሉ የኢሕዴግ አባል ነው ተብሎ ይፈረጃል:: ተቃዋሚ ድርጅቶች ባዘጋጁት ስብሰባ ላይ ደግሞ መገኘትና ፕሮግራማቸውን ማዳመጥ ደግሞ ተቃዋሚ የሚል የቅጽል ስም ከሌላኛው ወገን ይሰጠውና ቁምስቅሉን ያያል:: እንግዲህ ይህ ዓይነቱ ልማድ ተጠናውቶት ነው 4ውን አስተያየት የሰጠው ሰው ለእኔ ጸረ መንግሥት አቋም በማደል የቅንጅት አባል አድርጎ የሾመኝ:: በእውነት ከእንደነዚህ ያሉ አስተያየት ሰጪዎች የምንማረው ምን ይሆን? አንባቢ ሁሉ ይፍረድ::
  'እርሱ በሰው ውስጥ ያለውን ያውቅ ስለነበር::ስለሰዎች ማንነት ለጌታ ማንም ሊነግረው አያስፈልግም ነበር: እርሱ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበርና' የሚለውና በዮሐንስ ወንጌል ያለው ቃል ትዝ አለኝና እነዚህ ሰዎች እንደ አምላክ በሰው ውስጥ ያለውን ሁሉ እናውቃለን ሊሉ እየከጀላቸው ይሆንን?? የሚል ጥያቄ አጫረብኝ::

  እናንተ ጸሐፊዎች!
  እስቲ እንመማርና የሰነዘራችሁትን ሃሳብ ፍሬ ነገር ለአንባቢ አስረዱ? ለእኔም አስረዱኝ? ሕሊና የሚባል ነገር ጠፋ እንዴ? ትልቅ ሃብት ነበር እኮ እንደሚገባ በሥራ ላይ ብናውለው??
  እስቲ ብዙ የሚሠራ ሥራ እያለ:-
  እራሳችሁን አጋልጡ
  እንከታተላችኋለን
  ቅንጅት ነው/ናት
  ጸረ ቤተ ክርስቲያን/ኦርቶዶክስ ናት
  ፕሮተስታንት/ጰንጤ ናት/
  ወ ዘ ተ..... በሚል ዝባዝንኬ ጌዜ አንግደል?

  የጌታ ምህረት ያግኛችሁ!!

  የጌታ ሰላምም ያግኛችሁ!!

  የተቃወምኩት ለክፉው መጠቀሚያ የሆነውን ሃሳባችሁን ነው!!!

  እናንተን ግን በጌታ ፍቅር በእውነት እወዳችኋለሁ!!!!

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሠይፈ ገብርኤልMay 7, 2012 at 10:22 PM

   በሠፈሩት ቁና መሠፈር አይቀርም

   Delete