Monday, May 7, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ከገቡበት አጣብቂኝ ለመውጣት ወደ ፓትርያርኩ ቢሮ እግር አብዝተዋል

 • የማቅ ተከፋዩ አባ ኅሩይ ማኅተም ይዘው ተሰውረው ሰነበቱ
 • ዘግየት ብሎ በዐውደ ምህረት ድረገጽ እንደተዘገበው አባ ኅሩይ (የሰንበት ማደራጃና መምሪያ ኃላፊ) ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደርገዋል
የማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ አመራሮች ሰሞኑን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጽ/ቤት ወጣ ገባ ማለት ይዘዋል። ምንጮቻችን እንደጠቆሙት የማቅ አመራሮች የሚመላለሱበባቸው ሁለት ዋነኛ ጉዳዮች አሉዋቸው። የመጀመሪያው ከአባ ሠረቀ ብርሃን ጋር በዋናነት ያጣላቸውና “ሂሳባችሁን አስመርምሩ። ያላችሁን የገንዘብ ዝርዝር አሳውቁ። ገንዘብ አጠቃቀማችሁ ግልጽና ተጠያቂነት ያለው ይሁን።” የሚለው አጀንዳ እንደገና ስለተቀሰቀሰ እሱ “አይሁን አይደረግብን” ለማለትና የቅዱስነታቸውን ልብ ለማራራት ነው። ሁለተኛውና ዋነኛው ደግሞ ቅዱስነታቸው የማህበሩ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጣቸው የግብር ስም ከሰለፊያ ዝቅ ያለ እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ፓትርያርኩ መንገድ እንዲያዘጋጁላቸው ለመጠየቅ ነው።
ሁልጊዜም “ለእውነትና በእውነት” እሰራለሁ የሚል ድርጅት ሊያስደነግጠው የማይገባ “ሂሳባችሁን አሳውቁ፤ አጠቃላይ የሂሳብ እንቅስቃሴያችሁን ኦዲት አስደርጉ” የሚለው ጥያቄ የማህበሩን አመራሮች ለምን እንደሚያስደነግጣቸውና ይህን ጥያቄ ለመጠየቅ የሚደፍረውን ሰው ሁሉ ደግሞ “ተሐድሶ” እያሉ ለመጥራት እንደሚያስቸኩላቸው ብዙዎችን ግራ እያጋባ ነው። እውነት በቀኝም አዩዋት በግራ፣ በፊት ለፊትም አዩዋት በጀርባ፣ አዙረውም አዩዋት ገልብጠው ያው እውነት ናት። ስለዚህ “እውነትን ይዣለሁ” የሚል ሁሉ ምንም ነገር አያስፈራውም። ሂሳብህን ኦዲት ላድርግ የሚል የበላይ አካል ሲመጣማ “የአሠራሬን ትክክለኛነትና እውነተኝነት ለማረጋገጥ የምችልበት መንገድ አገኘሁ ብሎ” በደስታ ነው የሚቀበለው።
ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ጥያቄ አጥብቆ ለምን ይፈራዋል? በግልጥ እንደታወቀው ማኅበሩ እንደ ጣልያን ማፍያ ዓላማውን ለማሳካት ሁለት ዓይነት መንገድ ይጠቀማል። የመጀመሪያው ሕጋዊ መንገድ ሲሆን በዚህ መንገድ ብዙም አይራመድም። አሠራሩ በአብዛኛው ሕጋዊነት ስለሚጎድለውና በብርሃን ከመመላለስ ይልቅ በጨለማ መሄድን ስለሚመርጥ በፍጥነት ከዚህ መንገድ ወጥቶ ወደ ዋናው መጓዣው ወደ ሕገ ወጥ መንገድ ይገባል። ማንኛውንም ነገር እንደ ክርስቲያን “የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ ይሳካል” ብሎ ሳይሆን “እኔ ከፈለኩት መሳካት አለበት” በሚል እምነት የሚንቀሳቀስ ድርጅት ስለሆነ ሀሳቡን ለማሳካት ሕጋዊው መንገድ አላዋጣ ሲለው ሕገ ወጡን መንገድ አጥብቆ ይከተላል። ይህም ጉቦ በመስጠት፣ ቁልፍ ቦታ ላይ አሉ የተባሉ ሰዎችን ከቦታቸው እስኪነሱ ድረስ ቋሚ ተከፋይ በማድረግና ዓላማው በሁለቱ መንገድ እንደማይሳካ ሲገባው ደግሞ ዱርዬ በገንዘብ ገዝቶ በማስፈራራት ሀሳቡን ለማስፈጸም የሚፈልግ ማፍያ ድርጅት ነው። ይህ አካሄድ ታዲያ ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ ስለሆነ የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነት ከሰፈነ ያሰበውን ማሳካት አይችልም። ስለዚህ ይህ የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖር የሚቀርብለትን የተቀደሰ ሐሳብ እያመከነ ጥያቄውን የሚያነሳበትን ሰው መርዞ በመያዝ ከቦታው እንዲነሣ እስከማድረግ የደረሰ እርምጃ በአመፅ መንገድ ከመውሰድ ወደኋላ አይልም። እንቅልፍም አይወስደውም። በአባ ሠረቀ ላይ የተከፈተባቸው የስም ማጥፋት ሥራ ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው።
ይህ የግልጽነትና የተጠያቂነት አሰራር ተፈጻሚ እንዳይሆን የሚፈለግበት ሌላም ምክንያት አለ። የማህበሩ አመራር (ስውሩም ግልጹም) አባላትና አንዳንድ ለተንኮል ሥራ የሚፋጠኑ “ትጉህ” አገልጋዮቹ ለእንቅስቃሴያቸው መሳካት የሚያስፈልገውን ገንዘብና ለአንዳንዶቹ ከመሰረታዊ ፍልጎት አልፎ ኑሮ መደጎሚያ እንዲሆን በህገ ወጥ መንገድ ከማህበሩ የሚወጣውን ገንዘብ ግልጽነት ያለው አሰራር ስለሚያስቀርባቸው የሚያስፈልገውን ሁሉ ዋጋ መክፈል የህልውና ጥያቄ ስለሚሆንባቸውም ነው።
ታዲያ ሰሞኑን በአቡነ ገሪማ ፊርማ የሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃው ይህን ጉዳይ መልሶ እንዲያንቀሳቅስ ሲጠየቅ፤ አሜሪካ ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ በፍቅረ ንዋይ የሚታሙትና በቅርቡ ከስጦታና ከእጅ መንሻ ገንዘብ ተላቀው የማኅበሩ ቋሚ ተከፋይ ወደ መሆን የተሸጋገሩት አባ ኅሩይ ጉዳዩን ለማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ አመራሮች ሹክ ይላሉ። የማህበሩ አመራር አባላትም ይህ “እንቅልፍ የሚነሳ” ጉዳይ ካሉበት ቦታ አሰባስቦአቸው ወደ ቅዱስነታቸው በመግባት “ይህ አይሁንብን አይደረግብን” የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ። ቅዱስነታቸውም የሁሉም አባት እንደመሆናቸው በሚያጽናና ቃል ጉዳዩን መልሰው እንደሚያዩት ሲነግሩዋቸው ደስታው አላስቀምጥ ብሎአቸው ምክንያት ሲፈልጉ፣ ከተቀበሩ ሁለት ሳምንታት ያለፋቸውን የቅዱስነታቸውን ወንድም ሞት እንደጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው የእዝን እራት እናበላንን ብለው እራት አብልተው ነገሩን አብስለነዋል ብለው ሁለተኛ ጉዳያቸውን ደግሞ እንዴት እንደሚያሳኩት በማሰላሰል ይሄዳሉ።
ቅዱስነታቸውም ነገሩን ሲያስቡት ኦዲት የመደረጉና ሂሳብ የማሳወቁ ክፋት ስላልታያቸው ደብዳቤው እንዲወጣ ያዛሉ። ይህን ትዕዛዝ የሰሙት አባ ኅሩይ ከመዝገብ ቤት ማህተም ተቀብለው (በትክክለኛው አገላላጽ ሥልጣናቸውን ተጠቅመው በመስረቅ) ከግቢው ወጥተው ይጠፋሉ። ይህ እንደታወቀም ማህተሙ ሌላ ወንጀል እንዳይፈጸምበት በሚል ለፖሊስ ተነግሮ ፍለጋ ተጀመረ። ፖሊስ እንደሚፈልጋቸው የተረዱት አባ ኅሩይም አመሻሽ ላይ የጠፋሁት አቡነ ገሪማ ስላዘዙኝ አዝኜ ነው በማለት ማኅተሙን መለሱ።
ለመሆኑ ግን የብፁዕ አቡነ ገሪማ ሥልጣን አባ ኅሩይን ለማዘዝ ያንሳልን? ሌሎች ስልጣንና ኃላፊነታቸው ሣይጨመሩ የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ መሆን አንድ የሰንበት ማደራጃ ኃላፊ አልታዘዝም የሚለው ስልጣን ነው ወይ? የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ ለአባ ኅሩይና ለመካሪዎቻቸው እንተወዋለን?
ሁለተኛውና በእጅጉ ይፈልጉት የነበረው ጠቅላይ ሚኒስቲሩን የማግኘት ጉዳይ ለጊዜው ስለአልተሳካ “ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ ቢሆንም በበዓለ ሃምሳ (ጰራቅሊጦስ) ይዘነው የነበረው ጾም ጸሎት አልተሳካም።” በማለት ቁዘማ ላይ መሆናቸውን ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
አንዳንድ ወገኖች ከመንግሥት የተሻለ ሥራ እየሰራን ስለሆነ ነው መንግስት ጠምዶ የያዘን (አንድ አድርገን ሚያዚያ 17 ፤ 2004 ዓ.ም፤ መንግስት ለምን ‹‹ማህበረ ቅዱሳንን›› ጥምድ አድርጎ ያዘው?) በማለት በብሎጎቻቸው እየጻፉ ስለሆነ ለምን አሁን የገጠማቸውን ችግር ለመፍታት እራሳቸውን ባዩበት መነጽር ልክ አይሞክሩም እያሉ ይገኛሉ። ይኸውም “ካንተ የተሻለ ስራ እየሰራን ስለሆነ ይህን አለአግባብ የሠጠኸንን ስም በአስቸኳይ እንድታስተካክል እንደራደር አለበለዚህ ለአንድ ዓመት እጃችንን አጣጥፈን የምንመለከትህ ይሆናል ቢሉ መንግሥት ፈርቶና ደንግጦ በአስቸኳይ እሺ ይላል የምን በቅዱስነታቸው በኩል እየሄዱ መንገድ ማርዘም ነው” ሲሉ የማህበሩን አመራሮች  በስላቅ እየተቿቸው ይገኛሉ።

ከዚህ በሁዋላ የተዘገበ ሰበር ዜና:

የሰንበት ማደራጃና መምሪያ ኃላፊ የነበሩት አባ ኅሩይ ከሥልጣናቸው ተነሱ

አቀርቅሮ ወጊውና የማቅ ቀኝ እጅ መሆናቸውን በይፋ ያረጋገጡት የሰንበት ማደራጃና መምሪያ ኃላፊ የነበሩት አባ ኅሩይ ከሥልጣናቸው ተነሱ፡፡ በምትካቸውም መምህር ዕንቁባህሪ ተተክተዋል፡፡  እጅግ በሆነ መሰሪ አቀራረብ የሰንበት ማደራጃውን ሚስጢር ለማኅበረ ቅዱሳን አሳልፈው እየሰጡ ቤተክርስቲያንና ማደራጃውን ወደ ማቅ አቅጣጫ እየመሩ የነበሩት አባ ኅሩይ መነሳታቸው ለእውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች እጅግ አስደሳች ዜናና የጸሎታቸውምም ምላሽ ነው፡፡
ስልጣን ላይ ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ በድብቅ የማቅ ተላላኪ በመሆን የሰንበት ማደራጃውን አሰራር በሙሉ ለማቅ ለማስረከብ ተዘጋጅተው የነበሩት አባ ኅሩይ ከዚህ በፊት አብረውኝ የሚሰሩ ሰዎች ሁሉ በስራዬ ላይ እንቅፋት ስለሆኑ ይነሱልኝ ብለው ጠይቀው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በወቅቱ ጥያቄያቸው ምላሽ አግኝቶ ቢሆን ኖሮ በቦታው ላይ የሚተኩት ሰዎች በማቅ በኩል ተዘጋጅቶላቸው ነበር፡፡ 

እኝህ ሰው እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ ዜግነት እስተቀበሉባት አሜሪካ ድረስ መፍቀሬ ንዋይነታቸው በእጅጉ የታወቀ ስለነበር በሰንበት ማደራጀው ላይ በተሾሙ ጊዜ፤ ሹመታቸው ብዙዎችን የቤተክርስቲያን ልጆች አሳዝኖ  ነበር፡፡ የሰውየውን የባህሪ ክፍተት አሜሪካ ባሉ ባልደረቦቻቸው የሰሙት የማቅ አመራር አባላት አባ ኅሩይ አዲስ አበባ በገቡ ጊዜ በቀላሉ በማግኘትና የንዋይ ፍቅራቸውን በማርካት ከጎናቸው እንዲቆሙ አድርገዋቸዋል፡፡ ከዛም ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበር ይታወቃል፡፡
በቅርቡ እንኳ ማቅን በሚመለከት የአሰራርን ግልጽነት ለማስረጽ የሚረዳ ደብዳቤ እንደይወጣ ማህተም ይዞ እስከመሰወር የደረሰ አሳፋሪ ድርጊት የፈጸሙ ሰው ናቸው፡፡ ከዛ ጊዜም በኋላ በስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ ሲሆን ከሰዎች ጋር ያላቸውም ግንኙነት በስልክ ብቻ የተወሰነ ነበር፡፡ የእለት ዕለት የስራ ዕንቅስቃሴ የሚያስፈልገው የማደራጃ መምሪያው የስራ ገበታ ክፍት ስለሆነና የሰውየውም አካሄድ አደገኛ በመሆኑ መነሳታቸው አስፈላጊ ሆኗል፡፡
በአባ ኅሩይ ቦታ የተሾሙት መምህር ዕንቁባህሪ ሲሆኑ እሳቸውም ከዚህ ቀደም በመምሪያው ኃላፊነት የሰሩና እስካሁንም ድረስ ደግሞ በምክትል ኃላፊነት የቆዩ ሰው ናቸው፡፡ ለመምህር እንቁባህሪም የሹመቱ ደብዳቤ የደረሳቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡


11 comments:

 1. pls check the link: http://eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=976:2012-05-04-09-25-45&catid=1:-&Itemid=18

  Why Aba Hiruy is fired?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ነው አንዴ? አልገባንም ነበር እኮ? ሚጢጢ ማቅ

   Delete
 2. Egziabehere andit Tewahedo emnetachenen yetebekelen kesew yemenetebekew neger yelem.

  ReplyDelete
 3. ሰዎች በሁለት ምክንያት እንቅልፍ ያጣሉ እንደኛው መልካም በሆነ ስራ ሲተጉ ሲሆን ሌላኛው መልካም ላልሆነ እኩይ ግብር ነው፡፡ አሁን በዚህ አስገራሚ ዜና ላይ ‹‹ስለዚህ ይህ የአሰራር ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲኖር የሚቀርብለትን የተቀደሰ ሐሳብ እያመከነ ጥያቄውን የሚያነሳበትን ሰው መርዞ በመያዝ ከቦታው እንዲነሣ እስከማድረግ የደረሰ እርምጃ በአመፅ መንገድ ከመውሰድ ወደኋላ አይልም። እንቅልፍም አይወስደውም። በአባ ሠረቀ ላይ የተከፈተባቸው የስም ማጥፋት ሥራ ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው›› የሚለውን ማንበቤ ነው ይህን እንድል ምክንያት የሆነኝ፡፡ ማኅበሩ ስሜና ስራዬ መልካም ነው እንቅልፍ ባጣም ለበጎ ነው እያለ ሊደሰኩር ይሞክር እንጂ መንግስት እንኳ ጤናማ ያልሆነ አካሄዱን አውቆ ማንነቱን ሚሊዮኖች እየሰሙት ሲያውጅ አሁንም ካፈርኩ አይመልሰኝ የሚለው ማኅበር እንዴት ሲኮን ክብሬ ይነካል በሚል ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይቅርታ እንዲጠይቁት እንደሚፈልግ በልሳኖቹ አስነብቦናል፡፡ አሁን ደግሞ ነገሮች ከጠበቀው ውጪ እየሆነበት እንደሆነ ሲያይ በጽድቅ ሳይሆን እንደለመደው በጉቦ ነገሮች ለማፈን ጥረት ማድረጉ ማንነቱን አጉልቶ የሚያሳይ ምስክር ነው፡፡ እናንተዬ በዚህ አጭር ጊዜ እየተያ ያለው ነገር ነገን እንድናፍቅ አደረገኝ እኮ፡፡ በሉ ቸር ይግጠመን
  ደቂቀ አቡዬ ነኝ

  ReplyDelete
 4. aba Hiruy balege sew new. Lezih shumet aybeqam neber. Qidus patryarkun ameseginachewalehu. betekirstiyanin lemetebeq wesagn ermija mew.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I think you don't know Aba Hiruy or you are a 'menafik' because he doesn't need 'menafik'. He is open person and doesn't afraid to say 'lieba' when he got 'lieba.' That is why your kind of people dosn't need him.

   Delete
 5. አቤት ውሸት ስትችልበት

  ReplyDelete
 6. semonun yemideregewn ye cinodos sibseba teketatlachihu ewnetegawn neger zegibuln Mechem deje Selam yerasun Filagot & Hasab saydebalk ayimezegibim Adre

  ReplyDelete
 7. አይ ማቅ ከወደቁ በኅላ መፈራገጥ ለመላላጥ እንዳይሆንባችሁ በቀረው ጊዜ እንኩአን \በአሥራ እንደኛ ሰዓት እንኩአን እስቲ ወደ ነፍሳችሁ
  ተመለሱ፣ እስከመቼ ነው በሐሰትና በቅናት የምትኖሩት \ እስከመቼስ ነው የክርስቲያኖችን ሥም ስታጠፉና ጥላሸት ስትቀቡ የምትኖሩት
  \ አንድ ቀንም እንኩአን የህይወት ማግኛ ሥራ ሳትሰሩ እንዲሁ የሰይጣንን ወሬ ስታቀባብሉ 20 ዓመት ሞላችሁ።

  የቀድሞ ስሙ ሳዖል በሚባልበት ጊዜ እንደሚያደርገው የአይሁድን ሥርዓትና ቤተመቅደስ የጠበቀ መስሎት ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ እንደነበረው በኅላም ክርስቶስ ተገልጦለት ሳዖል ፣ ሳዖል ስለምን ታሳድደኛለህ \ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሃል ብሎ አይኑን በታላቅ ብርሃን እንዳወረውና ሃይሉን ክርስቶስ እንዳሳየው፤ የቀድሞ ስሙ ተቀይሮ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተባለ ከዚያም በኊላ አምኖ
  ክርስቲያን ሆኖ የክርስቶስ ወታደር በመሆን እስከ መጨረሻው ድረስ የሚገባውን የክርስቲያን ሥራ ፈፅሞ የድል አክሊል ከአምላኩ የተቀበለ መንፈሳዊ ጀግና ነው። ታዲያ እናንተም አሁን ለቤትክርስቲያን ያገለገላችሁ መስሎአችሁ ይሆን የክርስቶስና የክርስቲያኖች ጠላት ወይም አሳዳጆች የሁናችሁት ያሳዝናል።
  ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ እኮ እያንዳንዳችን የምንጠየቀው የማህበረ ቅዱሳን አባል ነበርክ \ ክርስቲያኖችን አሳደሃል\ ቤተክርስቲያንን
  ከፋፍለሃል\ እገሌን መናፍቅ እግሌን ደግሞ ተሐድሶ ብለህ አጋልጠሃል\ ወይስ ደግሞ እርስ በርስ ፍቅር እንዳይኖር አጣልተሃል\
  እኔ ብቻ ክርስቲያን ሌላው በሙሉ ሌላ ነው እያልክ አጣልተሃል እንዲሁም ሌላም ሌላም---------- አይደለም የምንጠየቀው።

  ክርስቶስ ሲመጣ የምንጠየቀው ፤ ብራብ አብልታችሁኛል \ ብጠማስ አጠጥታችሁኛል \ ብታረዝ አልብሳችሁኛል \ታስሬስ
  ጠይቃችሁኛል \ ታምሜስ አይታችሁኛል \ እውነት እውነት እላችሁአለሁ ከኔ ለሚያንሱ ለታናናሽ ወንድሞቼ ካደረጋችሁ ለኔ
  አደረጋችሁ ማለት ነው። ታዲያ ለፍርዱ ጥያቄ ከራሴ ጀምሮ ያደረገነው የትኛውን ነው \ የሚፈረድልንስ በየትኛው ሥራችን ነው \
  በማህበረ ቅዱሳን ጭፍን ተከታይነታችን \ መልሱን ለህሊናችሁ\ን\ ትቸዋለሁ። እናስተውል፣ እናስተውል፣ እናስተውል።። አሜን።
  ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስም ሆነ አቡነ ፋኑኤል የእናንተ ደጋፊ ካልሁኑ ስማቸውን ማጥፋት አለባችሁ \ ከእናንተ የጥፋት ድርጅት
  በቀር ፤ እኛ ሁለቱንም ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፍቅር እጅግ እድርገን እንወዳቸዋለን። ክርስቶስ ያስተማረን ፍቅርን ነውና። አሜን።
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 8. selimone lazeche bitekiresetiyane essoe eriso yamitawei

  ReplyDelete
 9. በልማት ሰበብ ዋልድባ ገዳም፤ ባቦጋያ መድኃኔዓለም ጌታቸው ዶኒን በመሰሉ መናፍቃንና እሱን የመሰሉ ሆዳሞችን በሚሾሙ በተላላኪ ሆዳም ሰዎች ኃይማኖታችንን ቅርሳችንን ታሪካችንን. . .ሁሉ እንዳናጣ እሰጋለሁ፡፡
  በባቦጋያ መድሃኔዓለም ምክንያት ብዙ ሕዝበ ክርስቲያን እየታሠረ፤ካህናት እየተንገላቱ ምዕመናን ቤተክርስቲያን እንዳይስሙ እየተደረገ ነው፡፡ በቅርቡም ቄሰ ገበዙን አሠሩት፡፡ ብዙዎቸን እያሳደዱ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የሚመራው ደግሞ በመናፍቁ ፤ ሆዳሙና ቦክሰኛው ጌታቸው ዶኒ ነው፡፡
  የዋልድባው ምኑ ተነግሮ ምኑ ይቀራል…..?
  ይህን ሁሉ ከማየት ደግሞ ሞት ሳይሻል አይቀርም፡፡
  “አባቶቻችን” ሆዳሞችን፤መናፍቃንን መሾም ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ የሲሞን መሠሪን ሕይወት መኖርም ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥሯል፡፡
  የቅዱስ እንጦስ ሕልም እውን ከሆነ ቆየ መሰለኝ፡፡
  በመጨረሻው ዘመን የሚሾሙ መነኮሳት እንደቁራ ጠቁረው ቢያያቸው አዝኖ ትርጉሙን ሲረዳ፤
  1. ከክርስቶስና ከመስቀሉ ፍቅር ይልቅ ለራሳቸው፤ለዘራቸው፤ለማንነታቸው የሚተጉ
  2. ከመሳፍንት (ከካድሬዎች) ጋር በጠዋት ማዕድ የሚበሉ ሆዳሞች
  3. ርካሽ ፖለቲካ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚዘሩ
  4. ከኃይማት ይልቅ ቢዝነስ፤ገንዘብ፤ሕንጻ የሚመርጡ አዋልደ ይሁዳዎች ሆነዋል፡፡
  በንሥሐ መጠራታቸውንም እኔ እንጃ . . .
  መንግሥትም ከዚህ ነገር ዳር ላይ ቆሞ የሚቀላውጥ ከሆነ ሕዝብ እየባሰው ነውና ችግሮች ተባብሰው ከመገንፈላቸው በፊት ሕዝቡ ቁጣውን መግለጥ ሳይጀምር የማይሳሳት የለምና ቢመለስ ጥሩ ነው፡፡ ይህን ሕዝብ ሳይሆን እየገጠማችሁ ያላችሁት ስልጣንን የሠጣችሁ እግዚአብሔርን ስለሆነ ተጠንቀቁ!!!!
  ካልሆነ ግን እንደ ምርጫ 97 በምርጫ 2007 የምርጫ ካርዱን በመጠቀም የመንግሥት ለውጥ ማድረግ ግድ ሳይል አይቀርም፡፡ እስከዛሬ ወገቤን አስሬ ለኢህአዴግ መከራከሬ ስህተት መሆኑ የገባኝ አሁን ነው፡፡
  የስኳር ልማቱ ለአዜብ መስፍንና ለዘመዶቿ ከሆነ እነርሱ እምነታቸውን እንደሚመርጡ አልጠራጠርም፡፡ ምክንያቱም እምነታቸውን፤ባህላቸውን፤ማንነታቸውን ሽጠው ስኳርን አይመርጡምና ምክንያቱም እኔም የተዛመድኩ በመሆኔ ሁሉን አውቀዋለሁ፡፡
  መቸም የኢትዮጵያ ሕዝብ ክርስቲያኑም ሙስሊሙም በእነዚህ ዐመታት ያስተዋለው ብዙ ነገር እንዳለ አያጠራጥርም፡፡ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ከሕዝብ አይሰወርምና መንግሥት ረጋ ብሎ ነገሮችን ቢያስተውል መልካም ይሆናል እንላለን፡፡ እየባሰ ከሆነ ግን ይህ ሕዝብ ከምንም በላይ ራሱን ስለኃይማኖቱ፤ስለሐገሩና፤ስለማንነቱ መስዋዕት በማድረግ የመለስ ቀዮ አድዋ ራሷ ትመሰክራለች፡፡
  ፈጣሪያችነ ለሃይማኖትና ለአገር መሪዎቻችን ልቦና ይስጥልን!

  ReplyDelete