Wednesday, May 9, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን በሲኖዶሱ ስብሰባ ሊያሳካቸው የሚፈልጋቸው ግቦች ዋነኛው የአቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካው አኅጉረ ስብከት መነሳት ነው።

ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት ብሎግ
የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ይጀምራል። በዚህ ስብሰባ ላይ ማኅበሩ ሊያሳካቸው የሚፈልጋቸው በርካታ አጀንዳዎች እንዳሉትና እነርሱንም ለማሳካት ማንኛውንም ጥረት እንደሚያደርጉ በተለያዩ መንገድ እየገለጹ  ይገኛሉ። በድረ ገጾቻቸው ከሚያሰሙት ኳኳታ በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስ አፋቸውን ከፍቶ ፊታቸውን ጸፍቶ በየሜዳው እያስለፈለፋቸው ዘንድሮ አሳባቸውን ለማሳካት እስከ ደም ማፍሰስ ድረስ የሚሄድ ዝግጁነት እንዳደረጉ በደብረ ብርሀን ከተማ እጁን በደም የታጠበው ማን ያዘዋል ነግሮናል። እራሱን ሳያዘጋጅና ሳያስብበትም ሰለፊያ ወካይ ስማቸው መሆኑን ነግሮናል። ሲኖዶሱ ለማኅበረ ቅዱሳን ሀሳብ የማይገዛ ከሆነ በ2001 ዓ.ም. ተከስቶ የነበረውን ሁኔታ እንደግመዋለን ሲል እግረ መንገዱን በ2001 ዓ.ም. የነበረውን ግጭትና የፓትርያርክ የማውረድ ሙከራ ከጀርባ ሆኖ ሲመራው የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን ነው ሲል ባልተራመ አንደበቱ፣ ጨዋነትን ባጣ ቋንቋና ትዕቢት ገልጿል።
 እንዲያውም ሲኖዶሱ የሚሰበሰበው ማኅበረ ቅዱሳን ሰርቶ የጨረሰውን ጉዳይ ለማጽደቅ ነው ሲል የመንፈስቅዱስን ቦታ ነጥቆ ለማኅበረ ቅዱሳን ሠጥቷል። ከታሪክ የማይማሩትና ተንኮልና ገንዘብ ብቻቸውን የምንፈልጋቸውን ነገር ለማድረግ በቂያችን ነው ብለው የሚያስቡት የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጸሎት ትተው እንደ ማራቶን ሩጫ የተንዛዛና እንደ ጀማሪ ማራቶን ሯጭ የተጎተተ ስብሰባ የሚያበዙትም ስለዚህ ነው። የነ ማን ያዘዋልን የታክሲ ላይ ውይይት እዚህ ላይ በመጫን ከደጀ ብርሃን ብሎግ ያንብቡ
ለዛሬ ማኅበረ ቅዱሳን ካልተፈጸሙ ሞቼ እገኛለሁ ከሚልባቸው ጉዶዮች አንዱን እናቀርባለን።
  1.  አቡነ ፋኑኤልን ከአሜሪካው ሀገረ ስብከት ማስነሳት
ለማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ ገንዘብ የሚያገኝበትንን የአሜሪካውን አገረ ስብከት ማጣት ባለፉት ስድስት ወራት የአጀንዳዎች ሁሉ እናት ሆኖበታል። ስለዚህም በቀንምም በማታም በህልሙም በእውኑም ይህን ጉዳይ ለማሳካት የማይፈነቅለው ድንጋይ አይኖረውም። ሰሞኑንንም በአቡነ አብርሃም አማካኝነት ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግበት የነበረና ከፍተኛ ገንዘብ የረጨበት ጉዳይ ነው። አሁን ደግሞ የሲኖዶሱ ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ለሽምቅ ውጊያ በከፈታቸው ብሎጎቹ የስም ማጥፋት ዘመቻውን ጀምሮዋል።
አንድ አድርገን ይህን ጉዳይ በሚመለከት በቅጡ ያልተጠናበትንና የጻፉትንን ደግሞ ለማንበብ እንኳ ጊዜ ያጡበትንን እንዲሁምም ለጉዳዩ በቂ ትኩረት ያልሰጡበትንና አንባቢያን እንኳ የማይሳሳቱትንን ስህተት በመፈጸም “እመኑኝ” ብሎ የማይታመንበት በቂ ማስረጃ  ያለው ዘገባ አስነብቧል።

ይህ “በእጅጉ ጥናት የተደረገበት ጥልቅ ዘገባ” አስመስሎ አንድ አድርገን ያቀረበው ዘገባ ስህተትን ሀ የሚለው ገና ከጅምሩ ነው። ዘገባውን የጀመረው አዲስ አበባ ላይ በቅጡ የማይታወቁትንን የሊቀስዩማንን ኃ/ጊዮርጊስን ታሪክ በመዘርዘር ነበር። የኃ/ጊዮርጊስን ታሪክ ሲጀምሩ አስከ 1989 ዓ.ም. ድረስ የማኅበረ ቅዱሳን አባል እንደነበሩና “ታድሰው መንፍቀው” ስለአስቸገሩና በመካሪና አስመካሪም ስለአልተመለሱ ከማህበሩ እንደተባረሩ ይገልጣል።
ዩንቨርስቲ ተማሪ በነበረበት ወቅት በስድስት ኪሎ ግቢ ጉባኤ ከተመረቀ በኋላ ማኅበረ  ቅዱሳን ማገልገል ጀምሮ የነበረ ቢሆንም 1989 . ያራምደው በነበረው ፕሮቴስታንታዊ የተሃድሶ አስተምሮ በወንድሞችና በአባቶች ቢመከርም በኑፋቄው ስለገፋባትም በማኅበሩ አባልነት ሊቀጥል እንደማይችል በሚገልጽ ደብዳቤ ከአባልነት እንደተሰናበተ በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡
የሚለን አንድ አድርገን ጹሁፉን ከለቀቀው በኋላ በአስተያየት መልክ ማስተካከያ የሚል ርዕስ ሰጥቶ ይህን ማስተካካያ ያቀርባል።
አቶ ኃይለጊዮርጊስ እስከ 1992 ዓም ድረስ በማህበረ ቅዱሳን የበግ ለምድ ለብሶ አባል ነበረ። በወቅቱ እሱም እንደተመረቀ ( 1990 ዓም AAU Psychology) ቀላል ለማይባል ጊዜ ስራ አላገኘም ነበረ። በዚያን ወቅት ከማህበሩ አባላት ወንድሞች ጋር ተጠግቶ የሚበሉትን እየበላ እነሱ በተከራዩት ቤት ይኖር ነበር። በወቅቱም በማቅ የዋናው ማዕከል ትምህርት ክፍል ውስጥ ሲያገለግል ነበር።
ይህ ቀላል ስህተት አይደለም። የአንድን ሰው “ክፋትና ስህተት”(ለዛውም አብረው ባልነበሩባቸው ሁኔታዎች ሆነ የሚሉትን) “እውነተኛ ማስረጃ” እኔ ልስጣችሁ የሚል ማኅበር የሚነቅፈው ሰው አብሮት  የነበረበትንን ሁኔታ በቅጡ መረዳት አቅቶትና እንደመሰለው የሚገልጽ ከሆነ  አብረው ባልነበሩበት ሁኔታ ሆነ የሚሉትንን ነገር ሲነግሩን እንዴት ልናምን እንችላለን?
ስህተቱ ጉልህ ነው። “ታቅዶበት ታስቦበት በእውነተኛ ማስረጃ ተደግፎ” ቀረበ የተባለው ዘገባ ኃ/ጊዮርጊስ ዩኒቨርስቲ በነበረ ጊዜ የማኅበሩ አባል የነበረ ሲሆን ነገር ግን ከየኒቨርሲቲ ከወጣ በኋላ በ1989 አበረርነው ይለናል። እንግዲህ “ብዙ ጥናት እንደተደረገበት ዘገባ” ከሆነ ኃ/ጊዮርጊስ ከዩንቨርሲቲ ከወጣ ከሆነ የተባረረው ቢያንስ ዩንቨርሲቲ የጨረሰው በ1988 ዓ.ም. ነው ማለት ነው። እንደማስተካከያው ከሆነ እውነታው ግን 1988 ዓ.ም. ገና የሁለተኛ ዓመት ተማሪ መሆኑ ነው። በዚህ ጊዜ ምን አልባት እንደ አገልጋይ አይደለም እንደ ተራ አባልም በማኅበሩ ላይታወቅ ይችላል። እንዲህ ያለው ስህተት “አሰራሬ በዘመናዊ መንገድ የተዋቀረና በማስረጃ የተደገፈ ነው” ከሚል ድርጅት የሚጠበቅ አይደለም። ለአመታት እንደ ብርቱ ጠላት የሚያየውንና ለማወቅም ቀላል የሆነውንን አንድ ግለሰብ ከማህበሩ ጋር የነበረውንን ቆይታ በተመለከተ ታሪኩን በቅጡ መረዳት አለመቻል ሌላው ዘገባ ሁሉ በስማ በለው የተዋቀረና ምንም አይነት በቂ ማስረጃ የሌለው ፍሬ ከርስኪ ነው ብለን እንድናምም ያስገድደናል።
ሌላው ሊቀስዩማንን ኃ/ጊዮርጊስን በሲአይኤ ኤጀንትነት መፈረጁ አስቂኝ ነገር ነው። usaid መስራት የሲአይኤ ኤጀንት ባያደርግምም ለአሜሪካንን መንግስት ወሬ አቀባይነት ግን የሲአይኤ ኤጀንት ያደርጋል። ምን አልባት የሲአይኤ ኤጀንት ለመሆን ሃሳቡ ካላችሁ ምን ምን መስፈርት ማሟላት እንዳለባችሁ ባያብል ሙላቱን ብትጠይቁት መልካም ነው።
በዚሁ አቡነ ፋኑኤልንን ከስልጣን ለማውረድ ይረዳኛል ብሎ ለከፈተው ዘመቻ እንደ ግብዓት እንዲያገለግለው በተጠቀመበት ጽፉፍ ሌሎች ጉልህ ስህተቶችም ይስተዋሉበታል።
2004 . የጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ብጹነታቸው ከሐዋሳ ወደ ሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ከሌጅ ሊቀጳጳስነት ተዛወሩ፡፡ በግንቦቱ ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ደግሞ ወደ የኪራይ ቤቶች አሰተዳደር መምሪያ ሊቀ ጳጳስነት ተዛወሩ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ብጹነታቸው ሀገረስብከት ባይሰጣቸውም በአወዛግቢነታቸው ገፍተውበት ነበር፡፡ 
2004 ዓ.ም. የጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ብጹዕነታቸው ወደ አሜሪካ ነው የተዘዋሩት። የግንቦቱ የርክበ ካህናት ስብሰባ ዛሬ ነው የሚጀምረው። እነዚያ በተባሉ ጊዜያት ሁሉ ደግሞ ብጹዕነታቸው አሜሪካ ነው የነበሩት። አንድ አድርገኖች እስኪ የጻፋችሁትንን መለስ ብላችሁ አንብቡት። ብጹዕነታቸው በአሜሪካ ቆይታቸውም ከማቅ ከፍተኛ የሆነ ነገር ግን ያልተሳካ የስም ማጥፋት ዘመቻ በቀር ሥራቸውን በአግባቡ ሲሰሩ ነው የነበሩት። እስካሁንም በእሳቸው አልታዘዝም ያሉት አብያተ ክርስቲያናት በብጹዕነታቸው አቡነ አብርሃም ፈቃድ ባለካንጋሮ እጆቹ የማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካው ቅርንጫፍ ከፍተኛ አመራር አካላት እነ አቶ መስፍን ብርሃኑ ጎበና ያሬድ ገ/መድህንን በላቸውና መሰሎቻቸው የሚያስተዳድሩዋቸው አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ናቸው።
አንድ አድርገን የአቡነ ፋኑኤል ይነሱልኝ ጥያቄውንን እንዲህ ሲል ይቀጥላል
የሁሉም አባት ነኝ” በሚል ሽፋን ከገለልተኛ አብያተክርስቲያናት ጋር ያለውን የቀኖና ቤተክርስቲያን ልዩነት ግምት ውስጥ ያላስገባ አካሄድ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መዋቅር ስር ያሉትን አብያተክርስቲያናት ካህናትን፣ምእመናን፣የአገረ ስብከት ኃላፊዎች፣ መምህራን ዘንድ ተቃውሞ ገጠማቸው፡፡በገለልተኛ አብያተክርስቲያናት በኩል ደግሞ የጠበቁትን ምላሽ ማግኘት አልቻሉም፡፡
የሁሉም አባት ነኝ ማለታቸው ምኑ ላይ ነው ጥፋቱ? ሁሉም የሚለው ቃል እናንተን አሳዳጆቻቸውንም እኮ ይጨምራል። ደግሞስ ተቀራርቦ ለመነጋገር ካልተሞከረ አንድነት እንዴት ሊመጣ ይችላል? ተጣሰ ያላችሁት የቤተክርስቲያን ቀኖና የትኛው ነው? እስኪ ተቃወሙ ያላችሁዋቸው አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ማህበረ ቅዱሳን ከሚያስተዳድረው ውጭ የሆነ አንድ ጥቀሱልን?  ለነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ እንደሌላችሁ ሁላችንንም እናውቀዋለን።
ሌላው ሀሳብ ደግሞ
ብጹእነታቸው በሊቀስዩማን /ጊዮርጊስ አቀነባባሪነትና ደብዳቤ አርቃቂነት ቀኖና ቤተክርስቲያን እንዲከበር ሲጠይቁ የነበሩትን የአገረስብከቱ ዋና ጸሐፊ የቀሲስ ዶክተር መስፍን ተገኝ ሥልጣነ ክህነት መያዛቸውን አሳወቁ፡፡ደብዳቤው የተሓድሶ መናፍቃን ልሳን በሆነ ድረ-ገጽ(አባ ሰላማ) በኃ/ጊዮርጊስ አማካኝነት እንዲወጣ ተደረገ፡፡ይህን ተከተሎ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መዋቅር ስር ያሉትን አብያተክርስቲያናት ቁጣ ቀሰቀሰ፡፡ ቅዳሜ መጋቢት 22/2004 .ም፤ ማርች 31/2012 የተሰበሰቡት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት፤ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት  የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፤ ምክትል ሰበካ ጉባኤ ሊቃነ መናብርት፤ የሰንበት /ቤት፤ የካህናትና የምእመናን ተወካዮች የተገኙበት ባወጡት የአቋም መግለጫ  ‹‹አብያተ ክርስቲያናቱ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ይጠበቅ›› በማለታችን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ነኝ የሚል አባት ሊደሰት ሲገባው፤ ይህንን አቋም በመጥላት፤ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ለማዳከም መነሳሳት ከብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በተግባር እያገኘነው ያለ ምላሽ ነው። ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በተደጋጋሚ ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤና አብያተ ክርስቲያናት የቀረበላቸውን "ወደ መንበርዎ ይመለሱየሚል ጥያቄ አልቀበልም በማለት፤ በተቃራኒ መልኩ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ጠብቀው የሚያገለግሉ ካህናትን በመደወልና በስሜታዊ ንግግር በመናገር የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት እንዲያከናውኑ የተሰጣቸውን ክህነት የፈለጉትን መፈጸም የሚችሉበት የግል ሥልጣን አድርገው በመውሰድ የቤተ ክርስቲያን መመሪያ ከሚፈቅደው ውጭ "እውነትን ይዘው የተከራከሩ ካህናትን ሥልጣነ ክህነት እይዛለሁበሚል መስመር በመጓዝ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

ይህንን ጹኁፋችሁን የአመቱ ምርጥ ውሸት ውድድር ላይ ብናቀርብላችሁ አንደኛ ይወጣ ነበር። አቶ መስፍን(በማንኛውም ሙያ ህግ መሰረት አንድ ሰው በተመረቀበት ሙያ ካልሰራበት  ያልሰራበት አመት ከተማረበት አመት እየቀነሰ ዕውቀቱ እየወረደ ይሔዳል። ዶክተሩ አሜሪካ ከሄደ ሰባት አመት ስላለፈውና የህክምና ትምህርቱን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የተማረው ለሰባት አመታት ስለሆነ ያልሰራበትን አመት ከተማረበት አመት ሲቀናነስ ከዜሮ ስላነሰ ከአሁን በኃላ የምንጠራው አቶ ብለን ይሆናል።) ሥልጣነ ክኅነቱ የተያዘው ቀኖና ቤተክርስቲያን ይከበር ስላላ አይደለም። ማኅበረ ቅዱሳን ሲገባ በሰለጠነበትና አሁን የክብር ዶክትሬት ቢያገኝበት ቅር በማያሰኘው የመሰሪነት ሙያው አሜሪካንን እየዞረ አብያተ ክርስቲያናትንን ለማሸበር ያልተሳካ ሙከራ ሲያደርግ ስለነበረ ነው። ይህንንም ነገር በትጋት ለማካሄድ የተነሳሳበት ዋነኛ እውነት ደግሞ ሌላ ሳይሆን የአቡነ ፋኑኤል አሜሪካ ውስጥ ተቀባይነት ማግኘት የማህበሩን የገቢ ምንጭ በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚያደርቀው ነው።
አዎን የአቶ መስፍን ስልጣነ ክህነት መሻር ከፍተኛ የሆነ ቁጣን ቀስቅሶዋል። የተቆጡት ግን በማህበሩ አባልነት ስር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው። እነርሱ ደግሞ ቁጣ የጀመራቸው ገና ሲኖዶሱ አቡነ ፋኑኤልንን የሾመ ጊዜ ስለሆነ ይህኛው ቁጣቸው ምንም አይገርምም።
የአገረ ስብከት ማህተም አልሰጥምም በማለት የመሰላቸውንና የገለባ ሸክም የሆነ ውሳኔ እየወሰኑ ማህተም እየረገጡ ውሳኔ ማሳለፍ ስራ መስሎዋቸው የሚሯሯጡት እነ መስፍን ኤፍሬምና ብርሃኑ ጎበና ህጋዊነቱ ያበቃለት ማህተም እጃቸው ላይ ስላላ ህጋዊ የሆኑ መስሎዋቸው የሚወስኑት ውሳኔን የብዙሀኑ ድምጽ ለማስመሰል ይደክማሉ እንጂ ብዙሀኑ ከአባታችንን አቡነ ፋኑኤል ጎን መሆኑ የተረጋገጠ እውነት ነው።
ባለጌ ሰድቦ ተሰደብኩ ይላል እንደሚባለው መንበሩ ርስታችን ነው አንሰጥምም እያሉ ከአቡነ አብርሃም ጋር ወግነው እያስቸገሩ ያሉት የማቅ ሰዎች ወደ መንበርዎ ተመለሱ ብንላቸው እንቢኝ አሻፈረን አሉ በማለት መጻፋቸው አሳፋሪ ድርጊት ነው። ሌላው ቢቀር ለብጹዕነታቸው አቡነ አብርሃም የተጻፈው እና መንበሩ የግሌ ነው ማለት አቁመው ለትክክለኛው ጳጳስ ያስረክቡ የሚል ድበዳቤ መውጣቱ ለትዘብት እንደሚዳርጋቸው አለማወቃቸው የሚያሳፍር ነገር ነው።       
  ሌላው አቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካ እንዲነሱ እንደማስረጃ ያቀረቡት አስቂኙ ነገር የአባ ኀሩይ ከሰንበት ማደራጃው ኃላፊነት መነሳት ነው። አባ ኅሩይ የተነሱት አለአግባብ ነው ለማለት ፍሬ አልባ “ፍሬዎቹን” ድረ ገጹ እንዲህ ሲል አስቀምጧል።
“ …ለዚህ የተመረጠው “ስስ ርእሰ ጉዳይ” (sensitive issue) የማኅበረ ቅዱሳንን ህልውና ላይ አደጋ መጋረጥ ነው፡፡ ለአሁኑ በኃ/ጊዮርጊስ አስተባበሪነት ተቀነባብሮ በቆሞስ መልዓከ ጽዮን አባ ሕሩይ ወንድይፍራው የሠንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ አማካኝነት የከሸፈውን ሴራ እናቀርባለን፡፡”
በማለት “በሴራው ላይ ተካፈሉ የሚላቸውንን ሰዎች ስም ዝርዝር ዘርዝሮ ሀሳባቸው በአባ ኅሩይ አማካኝነት ከሸፈ ይለናል። በዚህም ምክንያት አባ ኅሩይ ተነሱ በማለት ያስከትላል።
መቸም ምንም ይሁን ምን ሂሳባችሁ ኦዲት ይደረግ ግልጥነት የሰፈረበት አሰራር ይኑራችሁ። ገቢ ወጪያችሁ በግልጥ ይታወቅ የሚለው ሃሳብ ሴራ የሚሆነው እንዴት ነው?
ጉዳዩን ካነሳችሁት በዝርዝር እንነጋርበት። አዎን አባ ኅሩይ ተጠርተው የመስከረም 2002 ውሳኔ እንዲፈጸም ያድርጉ ተብለዋል። አሳቸውምም ምንም እናኳ በቅርቡ ደረጃቸውንን አሻሽለው የማኅበሩ ቋሚ ተከፋይ ወደ መሆን ቢያድጉም ገና የማኅበሩ አሰራር በቅርበት ስላልገባቸው ይህስ ምን ክፋት አለው በማለት ደብዳቤው ላይ ይፈርማሉ። ከዛም በገንዘባው ለገዙዋቸው አዲስ የማይጨበጡ አለቆቻቸው የሆነውን ነገር ቀለል አድርገው ያስረዳሉ። ከዛኛው በኩል የሰሙት ምላሽ ግን አስደንጋጭ ነበር። ይህ ጉዳይ የህልውና ጉዳይ ስለሆነ በአስቸኳይ ደብዳቤ ጽፈው ደብዳቤው እንዳይወጣ ያድርጉ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ሲደርሳቸው እርሳቸውም እየተርበተበቱ ደብዳቤውን ወደ ማዘጋጀት ይገባሉ።
በዚህ መሀልም የማቅ አመራሮች በአስቸኳይ ተጠራርተው ቅዱስነታቸው ጋር ይመጣሉ። እንገዲህ ይሔ ነው “…በዚህ መሃል የማኅበሩ አመራሮች አካባቢው ደርሰው ብጹእ አቡነ ገሪማ ሲያናግሯቸው ጉዳዩን እንደማያውቁት ጆቢራዎቹ እንዳሳሳቷቸው ይናጋራሉ…”
የተባለው። አካባቢው ያለ መረጃ እንደማይደረስ የታወቀ ነው። በወቅቱ ድንገት ተሰብስበው የሚመጡበት ሌላ ጉዳይ የላቸውም።
የሆነው ሆኖ ትዕዛዙ እንደማይቀለበስ በነጋታው  ሲታወቅ ግን የማኅበሩ አመራሮች ደብዳቤውን እንዲህ እንዲህ ብለው ጻፉ እና አስገብተው ማህተም “ይዘው ይጥፉ ሲኖዶሱ ሳምንት ስለቀረው በደጋፊ ጳጳሳቶቻችን አማካኝነት ሲኖዶሱ ላይ አስነስተነው ጉዳዩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እናዘጋዋለን።” በማለት የሞኝ ምክር ይሞክሩዋቸዋል። እሳቸውም ነገሩን አዙረው ሳያስቡ የተመከሩትን ያደርጋሉ። ደብዳቤውንም አስገቡ። ማህተሙንም ይዘው ተሰወሩ።
ከሁሉ የሚያስቀው በጨለማ ፈረምኩ የሚለው ምክንያታቸው ነው። በዚህ ዘመን ጨለማ የሚያሰናክለው ፊርማ ምን አይነት ይሆን? 24 ሰዓት መብራት እሱ ባይኖር ጄኔሬተር እሱ ባይኖር ደግሞ በርካታ ሻማ ባለበት ቦታ ጨለማ እንደምክንያት መቅረቡ አሳዛኝም አስቂኝም ነው።
የሆነው ሆኖ የአባ ኅሩይ መሰወር በመታወቁ ለፖሊስ ተነግሮ ፖሊስ ፍለጋ መጀመሩን ስለሰሙ አመሻሽ ላይ መጥተው ማህተሙን መልሰው “ማህተሙን ብመለስ ፊርማዬን የት ያገኛታል” ብለው ተመልሰው እብስ ይላሉ። አንድ ሠራተኛ በሥራ ገበታ ላይ ካልተገኘ ሊወሰድ ከሚገባው እርምጃ አንዱ በስራ ገበታው ላይ ሌላ ሰው መተካት በመሆኑ መምህር ዕንቁባህርይ በቦታው ላይ ተተክተዋል።
እነዚህንና ሌሎች ምክንያቶችን በመደርደር አቡነ ፋኑኤልን ከአሜሪካ ሀገረ ስብከት ማስነሳት የማኅበረ ቅዱሳን ዋነኛ አጀንዳ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን ማቅ አቡነ ፋኑኤልን የጠመደበት ምክንያት ምንድን ነው? ለሚል ጠያቂ አጭሩ እና ግልጹ መልስ፡- ብጹዕነታቸው በስራቸው ማንንም ጣልቃ ማስገባት ስለማይፈልጉና የማኅበሩን አጀንዳ ከቤተክርስቲያን አጀንዳ አስቀድመው ለመቆም ስለማይፈልጉ ነው። የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ አባቶች መሰረታዊ ችግርም ቤተክርስቲያንን ለማኅበሩ አጀንዳ ለማስገዛት መፈለጋቸው ነው።
ሌሎች በሲኖዶሱ ስብሰባ ለማስፈጸም የሚፈልጉትንን አጀንዳቸውንን ደግሞ በቀጣዩ ጽሁፍ እንመለስበታለን።

1 comment:

  1. Overall, a well-balanced article even though it is biased against MK. One major comment I have for the writer of this article and for readers is please target your criticism of Dr. Mesfin for his work against the bishop that was assigned by the Holy Synod (Aba Fanuel)and his close association towards Aba Abrham who is partly responsible for EOTC problems in the U.S. However, it is really disingenuous to consider Dr. Mesfin's hard earned medical degree as irrelevant. You could certainly question his priesthood, as it was revoked recently, but you do not have the authority to revoke his degree that he obtained from an accredited university. Just being honest.

    ReplyDelete