Sunday, May 13, 2012

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ስላለው የሲኖዶስ ስብሰባ ዙሪያ ሦስት ዋና ዋና ዘገባዎች

በትናንትናው ዕለት በአቡነ አብርሃም ቤት ልዩ ስብሰባ ተካሄደ
ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት ብሎግ
የዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ እና የአቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካ መነሳት አጀንዳዎች ነበሩ፡፡
በትናንትናው ዕለት አቡነ አብርሃም ቤት እስከ ምሽቱ የዘለቀ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን ስብሰባውም ሁለት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ታውቋል፡፡ የመጀመሪያው በዛሬው ዕለት በቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያ አጀንዳ የሆነውና አብዛኛዎቹን ጳጳሳት ያለልዩነት በአንድ ጎራ ላይ ያቆመው የዜና ቤተክርስቲን ጋዜጣ ዘገባ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሲኖዶሱ በአጀንዳነት አለመያዙ አቡነ አብርሃምንና ማኅበረ ቅዱሳንን እጅግ በጣም ያበሳጨው የአሜሪካ አኅጉረ ስብከት ጉዳይ እንደገና ወደ አጀንዳ የሚገባባት መንገድን ማመቻቸት ነው፡፡ 
የቅዳሜው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ባልጠበቁት መንገድ የሄደባቸው ማኅበረ ቅዱሳንና እና እንደ ሮብዓም “በልጅ” ምክር ተሳስተው “እርስዎ ካልፈለጉ ሌላ ሰብሰቢ መርጠን መቀጠል እንችላለን” ብለው ሲናገሩ በአቡነ ሙሴ እንደ ልጅ “ተው!! እንዲህ አይባልም” ተብለው የተገሰጹት አቡነ አብርሃም ከዚህ አጋጣሚ ሊገኝ የሚችለው ትርፍ ምንድር ነው? ብለው አስበውና መክረው ይሄን አጀንዳ በማብሰልና ስር በመስደድ ሰበብ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡ በዚህም መሰረት የዜና ቤተክርስቲያንን ጋዜጣ አዘጋጆች በዛሬው ዕለት ሲኖዶስ ስብሳባ ላይ ሲቀርቡ ምን ምን ጥያቄ እንጠይቃቸው? በሚለው ዙሪያ ሰፊ ጊዜ ወስደው የመከሩ ሲሆን ለቀጣዩ መወያያ በር ለማመቻቸትም የማቅ ሰዎች እዚህ አሳብ ላይ ደጋግመው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ሊቃነ ጳጳሳቱ “በነፃው ፕሬስ ጋዜጦች እንሰደብ እንጂ እንዴት በራሳችን ጋዜጣ እንሰደባለን?” በማለት እጅግ በጣም የተቆጡ ሲሆን አብዛኛዎቹ ዜናውንን ካነበቡበትና ከሰሙበት ከቅዳሜ ዕለት ስሜት ምንም ያልበረዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በዚህ በአይነቱ ልዩ በሆነው አጀንዳ የጋዜጣው አዘጋጅና ምክትል አዘጋጅ ምን መልስ ይሰጡ ይሆን? ጳጳሳቱስ ይህ ስሜታቸው በርዶ ወይስ በቁጣና በብስጭት ያናግሩዋቸው ይሆን የሚለው ትኩረት የሚስብ ሆኗል፡፡
በዚህ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ባመቻቹት የአቡነ አብርሃም ቤት ስብሰባ ለምን የእናንተ አጀንዳ ብቻ የእኛም አጀንዳ ይታይልን እንጂ በማለት  “ርስት ጉልቴ” ብለው አስበዋትና ለዘላለም ሊያስተዳድሩዋት የፈለጉት የአሜሪካው አኅጉረ ስብከት አጀንዳ አለመሆን ያንገበገባቸው አቡነ አብርሃም እና “አኁጉረ ስብከቱን የተደላደለ ዙፋኔና የገቢ ምንጬ አደርገዋለሁ” ብሎ አስቦ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካው ጉዳይ አጀንዳ ስለሚሆንበትና አቡነ ፋኑኤል ስለሚነሱበት መንገድ መምከራቸው ተነግሮዋል፡፡
የሮብዓምን መንገድ የመረጡትና ምክር ከሚያሳሳስቱ “ልጆች” ጋር ጊዜያቸውን የሚያጠፉት አቡነ አብርሃም የሚናገሩት ንግግር ሁሉ እውቀትና ማስተዋል የጎደለው እና ለእሳቱ የጭድ አቀባይነት ሚና ያለው ነው፡፡ የዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ዘገባ ከሚያካትታቸው ጳጳሳት መከከል እኚህ አቡነ አብርሃም የሚገኙበት ሲሆን ስብሰባው የተካሄደበት የግል መኖሪያ ቤታቸው የፈሰሰበት ገንዘብ እንኳን የጳጳስንን የኢንቨስተርንም አቅም የሚፈትን ከመሆኑ አንጻር አንዱ ተጠቃሽ ማስረጃም ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል፡፡
እስከ ዛሬ ድረስ የቅዳሜን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ለመዘገብ ያልደፈሩት የማቅ ብሎጎች እና አመራር አባለት በአቡነ አብርሃም በኩል አስነግረውት የነበረው ሰብሳቢ የመቀየር ምኞታቸው በአቡነ ሙሴ ተግሳጽ በቶሎ ስለተኮላሸ እና ስለአልተሳካ እንዲሁም የዜና ቤተክርስቲን ጋዜጣ ሰበር አጀንዳ ሆኖ መገኘት ከጣለባቸው ድንጋጤና ብስጭት በቅጡ እንዳላገገሙ የታወቀ ሲሆን የጋዜጣው አጀንዳ መሆን ሊፈጥርላቸው የሚችል ሌላ ዕድልም ካለ ለመጠቀም የትናንቱን ስብሰባ ማዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡  
  

(ርእሰ አንቀጽ)የአባቶች ገበና በሕገ ቤተ ክርቲያን ሲጋለጥ
Source;- http://www.awdemihret.blogspot.com/
(በትናንትናው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶሱ በሰበር ያስተናገደው አጀንዳ በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ የተጻፈ ርዕሰ አንቀጽን የተመለከተ ነው። ርዕሰ አንቀጹ ለምን አወያየ የሚለው በብዙዎች ዘንድ መወያያ ስለሆነ ርዕስ አንቀጹን እንዳለ አቅርበነዋል። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ)
ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት፣ የካህናትና የምእመናን ድምር ውጤት ናት፤ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን ባልን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ማለታችን ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ብለን በጥቅሉ በምንናገርበትም ጊዜ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን ማለታችን ነው፡፡ በአጠቃላይ እነዚህ ሁሉ አካላት የተካተቱባት ቤተ ክርስቲያን አንዲት ተቋም ስለሆነችም ማኅበር ተብላ ትጠራለች፤ ራሷ ማኅበር ስለሆነችም ከዝክርና ከሰንበቴ ማኅበር በስተቀር በተቋም የተደራጀ ሌላ ማኅበር አያስፈልጋትም፡፡
ሆኖም ቤተ ክርስቲያናችን ቃለ ዓዋዲ የተሰኘ የመተዳደሪ ደንብ አውጥታ በሰበካ ጉባኤ ከመደራጀቷ በፊት የእርሷ ወኪልና ደጋፊ በመሆን ድምፅ የሚያሰሙላት አንድ አንድ የወጣት መንፈሳወውያን ማኅበራት እንደነበሩ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ በሰበካ ጉባኤ ከተደራጀች ወዲህ ግን ሕገ ልቡና እስከ ሕገ ኦሪት፤ ሕገ ኦሪትም እስከ ሕገ ወንጌል መዳረሻ ሆነው ወይም አገልግሎት ሰጥተው አንዳለፉ ሁሉ እነሱም አልፈዋል፡፡ ይህም ማለት በቃለ ዓዋዲው የመተዳደሪያ ደንብ በየድርሻቸው ተካትተዋል ማለት እንጅ ጨርሰው ወድመዋል ማለት አይደለም፡፡
ቤተ ክርስቲያን የምትመራበትና የምትተዳደርበት ሕገ ቤተ ክርስቲያን ዌም ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ሕገ ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት በቅዱሳን ሐዋርያት የተደነገገ ሕግ ሲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚመሩትና የሚተዳደሩት በዚሁ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የዓለም አብያተ ክርስቲያናት አካል እንደመሆኗ መጠን የምትመራውና የምትተዳደረው ወይም የምትዳኘው ከፍ ሲል በሕገ ቤተ ክርስቲያን፤ ዝቅ ሲል በቃለ ዓዋዲ የመተዳደሪያ ደንብ ነው፡፡
ይሁን እንጂ በ1991 ዓ.ም ተሻሻለ ተብሎ የወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ‹‹የብላጊ ዝናም ከላም ቀንድ ይለያል›› እንዲሉ ከሦስቱ አካላት አንዱን አካል ለይቶ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ምቾት ወይም መብት እንጂ የቤተ ክስቲያንን ምቾት ዌም መብት ሙሉ በሙሉ የጠበቀ አይደለም፡፡ አልፎ ተርፎም የቤተ ክርስቲያኒቱን ርእሰ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን መብት የሚጋፋ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የእርስበርስ መለያየትን እንጂ አንድነትን፤ ጠብ ክርክርን ወይም ሁከትን እንጂ ሰላምን፤ ጥፋትን እንጂ ልማትን ሊያመጣ አልቻለም፡፡
ለምሳሌ ያህል በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ በአድላዊነት ከተደነገጉት ጥቂቶችን መጥቀስ ቢያስፈልግ በሐተታዊ መግለጫው እንደተገለጸው ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ነጻ ምግብ፣ ነጻ ቤት፣ ነጻ ሕክምና አላቸው፤ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ካህናትና ለሠራተኞቹ ግን የላቸውም፡፡ እንደዚያም ሆኖ አንዳንደ ጳጳሳት በእግዚአብሔር ገንዘብ የግል ቪላ እየገነቡ ያከራያሉ፤ ቤተ ክርስቲያን ለሐዋርያዊ አገልግሎት ገዝታ ከሰጠቻቸው መኪናዎች ሌላ እንደዓለማዊ ሰው ለአባት የማይገቡ እጅግ ዘመናዊ የሆኑና ከፍተና ዋጋ ያላቸው መኪናዎችን በቤተ ክርስቲያን ስም በሚያገኙት ገንዘብ በግል እየገዙ ሲያሽከረክሩ ይስተዋላሉ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የተሠሩ ቤቶችንም እየሸጡ ለግል ጥቅማቸው ያውላሉ፤ በየአድባራቱ በቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ለሚፈጸመው ሕገ ወጥ ብልጽግና በር የከፈቱትም እንዲህ ዓይነቶቹ አባቶች ናቸው፡፡ ሐናንያን ሰጲራ ከዚህ የበለተ ሌላ ምን አደረጉ? በቫት ተይዘው የታሰሩት ባለሀብቶችስ ከዚህ ሌላ ምን ፈጸሙ?
እንዲሁም ጳጳሳቱ ለራሳቸው ብቻ በሚመች ሁኔታ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ በደነገጉት መሠረት የየሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያች ሲፈልጉ ይሾሟቸዋል፤ ሳይፈልጉ በሾሟቸው ማግስት እንደ ቤት ሠራተኛ ያለ ፍትሐ ያባርሯቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር የጡረታ ሕግ በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ካህናትና በሠራተኞቿ ዘንድ የተከበረ ነው፤ ጳጳሳቱ ጡረታ የሚወጡት ግን ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ በሚለዩበት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ሌላው ጳጳሳት ዕድሜ ልክ ያከማቹትን የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት መልሰው ለቤተ ክርስቲያን ማውረስ ሲገባቸው የሚያወርሱት ለቤተሰብ ነው፡፡
ከዚህም ሌላ በጳጳሳት ምርጫ ጊዜ የካህናትና የምእመናን ተሳትፎ የለም፤ እንደ ስም ኦን ቀሬናዊ ቆሞሳቱን ከመንገድ እየጎተቱ ለጵጵስና የሚመርጧቸው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብቻ ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ ምርጫው ብቃትና ጥራት ስለሌለው ከሢመተ ጵጵስና በኋላ በአንድ አንድ ብፁዓን አባቶች ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር ዝቅ የሚያደርጉ ዓላማዊ የሆኑ አሳፋሪና ድርጊቶች እየተከሰቱ ነው፡፡ በቀድሞው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ግን በጳጳሳት ምርጫ የካህናትና የምእመናን ተሳትፎ ነበረበት፤ ይህም በመሆኑ የቀድሞቹ ጳጳሳት በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ምንም ዓይነት እንከን ስለአልነበራቸው የራሳቸውንም ሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር አስጠብቀው ነው ያለፉት፡፡
በአሁኑ ሕገ ቤተ ክርስቲያን እጅግ አስገራሚና አስደናቂ የሆነው አዲስ ጉዳይ ደግሞ ጥንታውያኑ ግብፃውያን ‹‹ኢትዮጵያውያን ከአዋቂዎቻቸው ጳጳሳትን አይሹሙ›› በማለት በሥርዋጽ ያስገቡት ቃል ከተሻረ ከዘመናት በኋላ ሙሉ ኢትዮጵያዊ ሳይጠፋ ግማሽ ዜግነት ያለፈው ኢትዮጵያዊ ወይም የውጪ ዜጋ ጳጳስ ሆኖ እንዲሾም በራሳችን አባቶች ዛሬ መደንገጉ ነው፡፡ በዚህ ክፍተት ሳይሆን አይቀርም ጥቂት ጳጳሳትም በአገሪቱ በሌለ ሕግና ከመንፈሳውያን አባቶች በማይጠበቅ ሁኔታ የውጭ ዜግነት አግኝተው አንድ እግራቸውን ኢትዮጵያ፣ አንድ እግራቸውን አሜካሪ አድርገው የሚኖሩት፡፡
ከሁሉም በላይ ‹‹ጳጳሳቱ ፓትርያርኩ የሁላቸውም የበላይ ስለሆነ እንደንጉሥ ይፍረት፤ እንደአባት ይውደዱት፣ እንደ እግዚአብሔርም ይመኑት›› ተብሎ በዲድስቅልያ በአንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 27 የተደነገገው ተሸሮ በአንዳንድ ተጨባጭ ችግሮች ምክንያት ጳጳሳቱና ኤጲስ ቆጶሳቱ በተሾሙባቸው ሀገሮች ውስጥ የሚሠሩትን ሥራና የሚሰጡትን ትእዛዝ ፓትርያርኩ ይመለከታል፣ ይመረምራል፤ እነሱም ማናቸውንም የማይገባ ሥራ ሲሠሩ ቢገኙ ይለውጣቸው (ያዛውራቸው)፣ እርሱ ለሁሉም የበላይ ነውና፣ ወይም አባታቸው ነውና፣ እነሱም ልጆቹ ናቸውና›› ተብሎ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 39 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጳሳቱን ከአንዱ ሀገረ ስብከት ወደ ሌላው ሀገረ ስብከት በሚያዛውሩበት ጊዜ ጳጳሳቱ ‹‹አንዛወርም፣ አሻፈረን›› በማለት ሽቅብ መልስ ይሰጣሉ፡፡
ከዚህም አልፈው በነጻ ፕሬሶች ውዝግብ በመፍጠር የራሳቸውንም የቤተ ክርስቲያኒቱን ገበና ያጋልጣሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተከታይ የሆነው ወጣት ትውልድም ተቀናንቶና አንጃ ለይቶ በሆነ ባልሆነው በነጻው ፕሬስ መወዛገብ የጀመረው ከእነዚሁ አባቶች ተምሮ ነው፡፡ ይህም ማለት ፓትርያርኩ ከሕግ በላይ የፈለገውን ያድርግ ማለት ግን አይደለም፡፡
ለዚህ ሁሉ ክፍተት መነሻውና ለአባቶች ገበና መጋለጥም ዋና ምክንያት ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ስለሆነ ከቤተ ክርስቲያናችን ዕድገት አንጻር ዓለም አቀፋዊ ይዘት ሊኖረውም ስለሚገባ ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም፣ ለአባቶችም ክብር ሲባል በ1991 ዓ.ም የወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲሻሻልና እንዲታረም በቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ውሳኔ ሊሰጥበት ይገባል፡፡ ውሳኔውም ከአሁኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ማለፍ እንደሌለበት ዜና ቤተ ክርስቲያን ሳይጠቁም አያልፍም፡፡

የነገው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በቅዱስ ፓትርያርኩ ሰብሳቢነት ይቀጥላል።
ምንጭ፡- ዐውደ ምሕረት
·         በትናንትናው ዕለት የዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ርዕሰ አንቀጽ ሰፊውን ጊዜ ወስዶ ሲያወያይ ነበር ሰኞም ይቀጥላል
(የማሕበረ ቅዱሳን ብሎጎች ይህን መርዝ ሳንረጭ አያስተኛን አያሣድረን በማለት /ሲኖዶስ ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ጉባኤውን ለመቀጠል ወሰነ የሚል ነጭ ውሸት በሰበር ዜናነት አስነብበውናል ሲኖዶሱ እንዲህ ያለ ውሳኔ እንዳልወሰነ የተረጋገጠ ሲሆን እነዲያውም ቀኑ ያልታሰበና ያልተጠበቀ አጀንዳ የተስተናገደበት ቀን ነበር፡፡ ዝርዝሩን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡)
በትናንትናው ዕለት የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በጠዋቱ ውሎ አጀንዳቸው ተቀባይነት እንዲያገኝ የከረረ አቋም ይዘው የሚገኙት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲኖዶሱ ሃሳባቸውን ይቀበል ዘንድ ግድ እያሉ የነበረ ቢሆንም የአብዛኛው ጳጳሳት ፍላጎት አጀንዳዎቹን አለመቀበል ስለሆነ ጉዳዩ መክረር ጀምሮ ነበር። ከሰዓቱን ግን የዜና ቤተክርስቲያን ዘገባ እጃቸው ላይ በገባ አባቶች ጉዳዩ ይታይልን ተብሎ ስለተጠየቀ ሲታይ ሁሉን አጀንዳ አስጥሎ ፊታውራሪ ሆነ።

የትናንትና ጠዋቱ አጀንዳ ከአርብ የቀጠለ ሲሆን አርብ ዕለት የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች የቅዳሜ አስመስለው የዘገቡት መንግስት ይካተትና የማይሆን ከሆነ ሌላ ሰብሳቢ እንመርጣለን የሚሉ ሀሳቦች ቢቀርቡም እነዚህ ሀሳቦች እንደማያዋጡ ሲታወቅ በትናንትናው ዕለት እነዚህን ሀሳቦች ትተው ስሜት ሰጪ በሚመስለው ሀሳብ ማለትም ወደሀገረ ስብከታችን ሄደን ለህዝቡ እምቢኝ አሉ ብለን እናስረዳለን ወደሚል ቀይረውት ነበር።
በዋነኛነት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ያልተግባቡባቸው አጀንዳዎች       
·         ተጨማሪ ጳጳሳት ይሾሙ እና
·         ሕገ ቤተክርስቲያን ይሻሻል የሚሉ ሲሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን ለፖለቲካ ፍጆታ ሊጠቀምበት የፈለገው የሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ ጉዳይ ምንም ተቃውሞ ያልገጠመው መሆኑ ታውቋል። 

ክርክሩ በቅዱስነታቸው እና ሀሳባቸውን በሚቃወሙ ጳጳሳት ዙሪያ ቀጥሎ ውሎዋል። ይልቁንም  ሲመኘው የነበረው ፍላጎት የሚሳካበት ዕድል የገጠመው የመሰለው ማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ጳጳሳቱን በምሳ ዕረፍት ጊዜ በከሰዓት በኋላው ስብሰባ በተጠናከረ ሁኔታ ሌላ ሰብሳቢ መምረጥ ላይ አተኩረው እንዲሰሩ ቢቀሰቅስም፤ ከሰዓት በኃላ በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ሌላ ሰበር አጀንዳ ብቅ ብሏል።

ሰበሩ አጀንዳ ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ በርዕሰ አንቀጹ ያወጣው “የአባቶች ገበና በሕገ ቤተ ክርቲያን ሲጋለጥ” የሚልጽሁፍ ሲሆን በውስጡም “…እንዲሁም ጳጳሳቱ ለራሳቸው ብቻ በሚመች ሁኔታ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ በደነገጉት መሠረት የየሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያች ሲፈልጉ ይሾሟቸዋል፤ ሳይፈልጉ በሾሟቸው ማግስት እንደ ቤት ሠራተኛ ያለ ፍትሐ ያባርሯቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር የጡረታ ሕግ በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮች ካህናትና በሠራተኞቿ ዘንድ የተከበረ ነው፤ ጳጳሳቱ ጡረታ የሚወጡት ግን ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ በሚለዩበት ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ሌላው ጳጳሳት ዕድሜ ልክ ያከማቹትን የቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት መልሰው ለቤተ ክርስቲያን ማውረስ ሲገባቸው የሚያወርሱት ለቤተሰብ ነው፡፡…”የሚሉና ሌሎች ጠንካራ ጉዳዮች የተስተናገዱበት ነው። 

የዜና ቤተክርስቲያኑን ርዕሰ አንቀጽ አብዛኛዎቹ አባቶች የተቃወሙት ሲሆን  “እንዴት እንዲህ ያለ ርዕሰ አንቀጽ ይጻፋል?” በሚል ሙሉውን ከሰዓት በኃላ የነበረው ጊዜ ሁሉ ለዚህ ጉዳይ ተሰጥቶ ሲወያዩበት የነበረ መሆኑ ታውቋል።

ይህ አጀንዳ ሰኞ ዕለትም የሚቀጥል ሲሆን የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ መጋቤ ሚሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒና ምከትል አዘጋጁ ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር ሰኞ ዕለት ቅዱስ ሲኖዶሱ ፊት ቀርበው ለምን እንዲህ ያለ ጽኁፍ ጻፋችሁ ተብለው እንደሚጠየቁ ታውቋል።  

በተለይም “…እንደዓለማዊ ሰው ለአባት የማይገቡ እጅግ ዘመናዊ የሆኑና ከፍተና ዋጋ ያላቸው መኪናዎችን በቤተ ክርስቲያን ስም በሚያገኙት ገንዘብ በግል እየገዙ ሲያሽከረክሩ ይስተዋላሉ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የተሠሩ ቤቶችንም እየሸጡ ለግል ጥቅማቸው ያውላሉ፤ በየአድባራቱ በቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ለሚፈጸመው ሕገ ወጥ ብልጽግና በር የከፈቱትም እንዲህ ዓይነቶቹ አባቶች ናቸው፡፡…”ብለው ለጻፉት ጽሁፍ ምን አይነት መልስ ይሰጡ ይሆን እንዴት ያለ ውሳኔስ ይወሰንባቸው ይሆን የሚለው ጥያቄ የነገውን ስብሰባ በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።

ሌላው ሳይጠቀስ ሊታለፍ የማይገባው፥ የሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ ጉዳይ ነው። የዕርቁ ሁኔታ ሂደቱን በቅርበት ለምናውቅና አሜሪካን ሀገር በሁለቱ ሲኖዶሶች ክፍፍል ምክንያት ያለውን ችግር በቅርበት ለሚረዱ ሰዎች ይህንን በቅዱስ ሲኖዶሱም ሆነ በቅዱስ አባታችን ተቃውሞ ያልቀረበበትን አጀንዳ ለምን ማኅበረ ቅዱሳን ተቃውሞ እንደቀረበበት አድርጎ ለማቅረብ ፈለገ? የሚለው ጥያቄ መልስ የሚያስፈልገው  ነው። 

እንደሚታወቀው የሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ ቢሳካ ከማንም በላይ የሚጎዳው ማቅ መሆኑ ግልጽ ነው። ማኅበሩ ባለፈው በአሜሪካን አገር የእርቁ ስብሰባ በሚካሄድበት ጊዜ በአቶ መስፍንና በተባባሪዎቹ እነ ብርሃኑ አማኻኝነት እርቁ ለምን መካሄድና መሳካት እንደሌለበት ከእስቴት እስቴት እየተዘዋወሩ ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ የነበረ መሆኑን በቅርብ የሚያውቁ ወገኖች አይዘነጉትም። ለዚህም ዋና ምክንያት የሚሆነው ማኅበሩ በአሜሪካው ሲኖዶስ ተቀባይነት የሌለው መሆኑ ነው። በአሜሪካ ባለው ሲኖዶስ ስር የሚተዳደሩ አብያተ ክርስቲያናት እንዲህ ያለውን ሳይነጋ የመሸበትን ማኅበር እንደ አሸባሪ በመግለጽ ምንም አይነት ግንኙነት የማያደርጉ ሲሆን፤ ሁለቱ ሲኖዶሶች ከታረቁ ይህ እጣ ኢትዮጵያ ውስጥም ይገጥመኛል ከሚል ስጋት የመነጨ መሆኑ ግልጽ ነው።

ይህንን እርቅ ለማስቀረትም ከሚጠቀሙበት ዘዴ አንዱ የፕሮፓጋንዳ ጦርነት ነው። አሜሪካ ያሉ አባቶችና ወንድሞች የማኅበሩ ብሎጎች የሚጽፉትን አምነው ከእርቁ ሀሳብ ላይ ልባቸውን ዞር እንዲያደርጉ የታቀደ ደካማ አስተሳሰብ ውጤትም ነው። ማኅበሩ አሜሪካ ላሉ ወገኖች እኔን ለቀቅ ፓትርያርኩን ደግሞ አብረን ጠበቅ እናድርግ ብሎ ለማስተላለፍ የፈለገውን መልዕክት ለማያቅሽ ታጠኝ በማለት ልንመልስለት ይገባል። ስለዚህ በዕርቁ ጉዳይ ላይ ያሉ ወገኖች ሁሉና የአሜሪካው ሲኖዶስ አባቶች፤ የእርቁ ጉዳይ በተያዘው አጀንዳ ቅደም ተከተል መሰረት የሚታይና በቅዱስ ፓትርያርኩም ምንም አይነት ተቃውሞ ያልቀረበበት መሆኑን አውቀን መሰሪውን ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳንን ነቅተንብሀል ልንለው ይገባል።

 ይህ በእንዲህ እንዳለ ማኅበረ ቅዱሳን የሲኖዶሱ ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ጀምሮ በግልጽም በስውርም ቅስቀሳ ሲያደርግበት የነበረው ፓትርያርክ የማውረድ ሀሳብ ደጋፊዎቹ ጳጳሳት በምሳ ሰዓት ላይ አጠንክረው እንዲቀጥሉበት አሳስቦ ስለነበረ ብቻ ለወሬ ጓጉቶ ጉዳዩ እንደተፈጸመ  ቆጥሮ  /ሲኖዶስ ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ጉባኤውን ለመቀጠል ወሰነ  በሚል ርዕስ የዕለቱ  የሲኖዶሱ ስብሰባ ከማለቁ በፊት አዘጋጅቶት የነበረውን ጽሁፍ እኔ ከመከርኩ ማን ያስቆመኛል ብሎ በስብሰባው ሰዓት ምን እንደተፈጠረ ሳያጣራ ጉዳዩን በሰበር ዜናነት ለማጮህ መሞከሩ በእጅጉ አስተዛዝቦዋል።

በጣም የሚገርመው በርዕስነት ሰበር ዜና ብሎ ማቅ የጻፈውን ሀሳብ ፈጽሞ ያላብራራና አፈጻጸሙ እንዴት እንደነበር ያላስረዳ ሲሆን፥ ሀሳቡ ስለተነሳ ብቻ ተፈጸመ ብሎ ማስወራትም ለአንድ ቀን እንኳ በድል ሙቀት ልደር በደጋፊዎቼ ዘንድ ደስታ በሚቃወሙኝ ዘንድ ደግሞ ሽብር ልንዛ ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ መሆኑ ተነግሮዋል። 

የሰኞ ዕለቱም የሲኖዶስ ስብሰባ በቅዱስ ፓትርያርኩ ሰብሳቢነት እና የዜና ቤተክርስቲያንን ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠት የሚቀጥል መሆኑ ታውቋል።4 comments:

 1. እውነቱ ይህ ነው ለአዳሙ ዘር
  ቀጥ ብሎ ሚሄድ ፊቱን ሳይዞር፤
  የማይደለል ማይርበደበድ ጳጳስ ቢያብርም
  ዛሬም ነገም ሁሌም ለኦርቶዶክሶች ይኑር አብረሃም ።
  የአቡነ አብርሃም አቋም ሰውን በማክበር፣ በትሕትና በመውደድ፣ በእውነትና ከሁሉም በፊት እግዚአብሔርን በማስቀደም ጋር ነው፡፡ ዝቅ ብለውም ለአረያነት መጋረጃ ለመትከል፣ ዕቃ ለማሰናዳት ሲነሡ ለሰው ጳጳስነታቸውን የረሱት እስኪመስለው ድረስ ነው እግዚአበሔርን የሚያገለግሉት፡፡ አገልግሎቱ እንጂ ክብሩ የማይታያቸው ጀግና ግዚአበሔር ወታደር፡፡ አዲስ አበባ ለቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጥተው እያለ በፓትርያርኩ እግድ የትም ቤተ ክርስቲያን እንዳያስቀድሱ፣ በኋላም ከሀገር እንዳይወጡ ብዙ ጫና ነበረባቸው፡፡ ከዚህም ሌላ እርሳቸው የሚያውቁት ብዙ ፈተና ደርሶባቸዋል፡፡ ይህም ሆኖ ግን «የፓትርያርኩን ስም ካልጠራችሁ ከእናንተ ጋር ኅብረት የለኝም» የሚለው አቋማቸው አልተቀየረም፡፡ ሲፋጅ በማንኪያ፣ ሲበርድ በእጅ እንደሚሉት እንዳንዳንዶቹ ጊዜ እና ሁኔታ አይተው ቢለዋወጡ ኖሮ ተለዋዋጮቹ ያገኙትን ሁለት ሀገረ ስብከት አያጡትም ነበር፡፡አቋም አቋም ነው፡፡ በችግሮች እና በሁኔታዎች አይለወጥም፡፡ አቋም የሌለው ሃይማኖት ሊኖረው አይችልም፡፡ ከአሥር አብያተ ክርስቲያናት በላይ በእናት ቤተ ክርስቲያን ስም እንዲጠቃለሉ ያደረጉት በዚህ አቋማቸው ነበር፡፡ «ከሕዝብ ከሚጣሉ ይህንን አቋምዎን ይተውት» ሲባሉ «ከእግዚአብሔር ከመጣላት ከሕዝብ መጣላት ይሻላል» ይሉ ነበር፡፡ በአሜሪካን ሀገር ታላላቅ ሥራዎች እየሠሩ የሚገኙ ሦስት ታላላቅ ማኅበራት አሉ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን፣ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እና ማኅበረ በዓለ ወልድ፡፡ በተለይም የኋለኞቹ ሁለቱ በራሳቸው መዋቅር ነበር የሚጓዙት፡፡ እነዚህን ማኅበራት ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መሥመር ለማስገባት ከወጣቶቹ ጋር በመከራከር፣ በማሳመን እና አብረውም በመሥራት ያደረጉትን ተጋድሎ ሳስበው አቋም እና ሃይማኖት ያለው አባት ካገኘ ወጣቱ የት ሊደርስ እንደሚችል ይታወሰኛል፡፡በተገኘው አማራጭ ሁሉ እየተጓዙ በጉባኤያቸው ላይ ይገኛሉ፡፡ መሥመር ያልያዘ መስሎ በተሰማቸው ነገር ሁሉ ሃሳብ ይሰጣሉ፡፡ ጉባኤያቱ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ የመውጫ መንገድ ያመለክታሉ፡፡ ራሳቸውን እንደ አንድ ተሰብሳቢ ቆጥረው ይከራከራሉ፣ እንደ አባት ይመክራሉ፣ እንደ ወንድም ያበረታታሉ፡፡ትዝ ይለኛል የዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ሲቋቋም እርሳቸው የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ዴንቨር ተደርጎ በነበረው የሰንበት ት/ቤቶች ጉባኤ ላይ የወጣቱ መንገድ ምን መሆን አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ ሁላችን እንፈራው የነበረውን አቋም ሠነዘሩ፡፡ ክርክር ተፈጠረ፡፡ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ሆነው መጓዝ እንዳለባቸው በድፍረት ተከራከሩ፡፡ ከጉባኤው መልስ በዘማሪት ፋንቱ ወልዴ ቀስቃሽነት የተሰባሰቡ ወጣቶች የአቡነ አብርሃምን ሃሳብ ይዘው ተነሡ፡፡ በተለይም ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ የዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እያሉ ከፍተኛው ችግራቸው ማረፊያ ነበር፡፡ ይህ ነበር ወጣቶቹን ያንገበገባቸው፡፡ አባቶቻችን በልመና ቤት አያርፉም፡፡ መንበረ ጵጵስና ያስፈልጋቸዋል አሉ፡፡ ሌላም ችግር ነበር፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ እና በአካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የተሠራ ቤተ ክርስቲያን አልነበረም፡፡ በዚህም ምክንያት ሊቃነ ጳጳሳቱ የሚቀድሱበት ቤተ መቅደስ አልነበራቸውም፡፡ አንዳንዶቹም ፖለቲካውን ፈርተው እንዳይመጡብን ብለው ወስነው ነበር፡፡ ይህንን የወጣቶች ሃሳብ ሲሰሙ አቡነ አብርሃም ከኒውዮርክ ወደ ዲሲ በአውቶቡስ መጡ፡፡ በወይዘሮ ሐረገ ወይን ቤት ከወጣቶቹ ጋር ውይይት አደረጉበት፡፡ መቼም ወጣት የያዘው ነገር ኃይል እንጂ አቋም ለማግኘት ጊዜ ይፈጅበታል፡፡ ወጣቶቹ በልዩ ልዩ ሃሳብ ሲላጉ ከኒውዮርክ በአውቶቡስ እየተመላለሱ መክረዋል፣ አስተምረዋል፣ አሠርተዋልም፡፡ ጉባኤያት በተደረጉ ቁጥር ሳይሰለቹ ይገኙ ነበር፡፡ በአንድ በኩል ከገለልተኞች፣ በሌላም በኩል ከስደተኞች፣ ሲብስ ደግሞ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ነን ከሚሉ ዘረኞች የደረሰባቸውን ጫና ሁሉ ተቋቁመው በስም ብቻ የነበረውን ሀገረ ስብከት በሕግ እንዲቋቋም፣ መንበረ ጵጵስና እና የመንበረ ጵጵስና ቤተ ክርስቲያን እንዲኖረው አድርገዋል፡፡ከኒውዮርክ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከመጡ በኋላ አናጺ ሆነው መንበር እየሠሩ፤ እንደ ልብስ ሰፊ መጋረጃ እያዘጋጁ፣ እንደ አካውንታት ሂሳብ እየሠሩ፣ እንደ ፕሮግራም መሪ ገንዘብ እንዲዋጣ እያደረጉ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል፡፡ የአሜሪካ አውሮፕላን ማረፊያዎች ጳጳሳትን ሲፈትሹ ክብር በሚነካ ሁኔታ ነው፡፡ ይህንን የፈታሾች ሥርዓት አልበኛነት ሊታገሡት ባለመቻላቸው የአንድ ቀን መንገድ ያህል በመኪና እየተጓዙ ነው አያሌ ሥራዎችን ያከናወኑት፡፡አቡነ አብርሃም ከዋሽንግተን ዲሲ ሀገረ ስብከት ወደ ሐረር እንዲዛወሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢኖርበትም ዋናው ምክንያት ግን የአቋም ሰው መሆናቸው ነው፡፡ የአበው ሊቃነ ጳጳሳት በር ሲደበደብ እና፣ አቡነ ሳሙኤል ከሥርዓት ውጭ ሲታገዱ «ይህ ከሥርዓት ውጭ ነው መታረም አለበት» ብለዋል በድፍረት፡፡ ተሐድሶ የለም የሚል ደብዳቤ ከመንበረ ፓትርያርኩ ሲደርሳቸው «ተሐድሶማ አለ፤ በዓይናችንም አይተነዋል» ብለው ነው በአደባባይ የተናገሩት፡፡ ከሀገረ ስብከት በላይ የውጭ ግንኙነት ቢሮ ሲቋቋም ከማንም ቀድመው ነው ስሕተት ነው ያሉት፡፡ በመጨረሻም «የሲኖዶሱን ውሳኔ ባልስማማበትም አክብሬ ወደ ታዘዝኩበት እሄዳለሁ» ያሉትም የአቋም ሰው በመሆናቸው ነው፡፡አሜሪካ አቡነ አብርሃምን አጣች እንጂ አቡነ አብርሃም አሜሪካን አያጧትም፡፡ ለአንድ ሐዋርያ ሀገሩ ሁሉም ነው፡፡ ምናልባትም ሰው ካልሄደ አይመሰገንምና ከእርሳቸው በኋላ የሚመጣው ሰው እርሳቸውን የሚያስመሰግን ይሆናል፡፡ «ትሻልን ሰድጄ.....» አይደል የሚባለው፡፡አሁን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕድገት ሊቀለበስ ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ከአቡነ አብርሃም ይልቅ ከባዱ ቀጣይ ዕዳ ያለው በሲኖዶሱ እጅ ነው፡፡ አቡነ አብርሃምማ ከአሜሪካኖች ይልቅ የሐረሮች ጸሎት በልጧልና ሐረር ሄደውም ሥራ ይሠራሉ፡፡

  ReplyDelete
 2. silebetekrstian woys slemahbere kdusan?

  ReplyDelete
 3. Dr Kesis Mesifin Betirufat yemagelegil sew sihon Abune Fanueil Debdabe Setsitewgal yalut Min Malet new ? Nashivel tenes Kidane Mihiret yeminorubet Bet Yetekerayut Beman Genzeb new Beyeweru yeminkeflachew Dollar Betirufat sertew new ? Beyebotaw sihedu Yemikefelachew Abel Ayitasebim Malet New ?

  ReplyDelete
 4. Abba Selama Kidus Sinodos Manday (May 6 2004 ) Min Wesene?

  ReplyDelete