Wednesday, May 16, 2012

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያው ለማኅበረ ቅዱሳን ከባድ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጻፈ

ደብዳቤውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ


 • የ2002 ዓ/ም ውሳኔ በ 10 ቀን ውስጥ እንዲፈጸም ያዛል። ይህ ካልሆነ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።
 • ደብዳቤው ማህበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያንን ሕገ ደንብና የበላይ አካላትን ትዕዛዝ በመቃረን ላይ እንደሚገኝና ይህን ማስተካከል ለነገ የማይባል ጉዳይ እንደሆነ ያሰምርበታል።
ይህን ደብዳቤ አስመልክቶ የ ዐውደ ምህረት ዘገባ፦


የሰንበት ማደራጀና መምሪያ መምህር ዕንቁ ባሕሪን በዋና ኃላፊነት ካገኘ በኃላ ወሳኝ የሚባሉ አስተዳደሪያዊ ውሳኔዎችን መወሰን ጀምሯል። እንደሰናዖር ግንብ የማይደፈር መስሎት ሲኮፈስ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳንም ከሕግ በላይ ሊሆን እንደማይችል በግልጽ የሚረዳበት ዘመን መጥቷል። አመጸኛውና ሕግና ሥርዓትን ጠብቅ ያለኝ ሁሉ መናፍቅ ነው የሚለው ማሕበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ውጭ መሆን እንደማይችል የሚገልጸውን ደብዳቤ ለመዋጥ እየተናነቀው ይገኛል።
ከተመሰረትኩ 20 ዓመቴ ነው የሚለውና እንደ 20 ዓመት ጎረምሳ በትዕቢት የተወጣጠረው ማሕበር ቤተክርስትያን እኔ ነኝ የቤተክርስቲያን ዶግማ ቀኖናና ሥርዓት የኔ መተዳደሪያ ደንብ ነው። ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን ሲገቡ ሳይሆን ወደ ማሕበረ ቅዱሳን ሲገቡ ነው የሚድኑትና የቤተክርስቲያን ልጆች ቁጥር እጅግ ጨመረ የሚባለው። ህዝቡ ክርስትና ገባው የሚያባለው አሥራት በኩራቱን ለቤተክርስቲያን መስጠቱን አቁሞ ለማኅበሩ ሲሰጥ ነው። የማኅበረ ቅዱሳን አባል ያልሆነ ሁሉ መናፍቅ ነው። ከሲኖዶሱ በላይ ስለሆንኩ ሲኖዶሱ እኔ ያልኩትን መፈጸም አለበት እያለ እንደ ፊጋ በሬ ቤተክርስቲያንን እያመሰ ቢቆይም ዛሬ ልኩን የሚያውቅበት ቀን መጥቷል።
የማኅበሩ አልታዘዝ ባይነት ወሰን ከማጣቱም በላይ ሥርዓት እንዲይዝ የሚሞክሩትን የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች እያዋከበ አላስቆም አላስቀምጥ በማለት ማንም ሊያዘኝ አይችልም በማለት መሬት እርቆት በደመና ላይ እየተንሳፈፈ ቢቆይም አሁን እነርሱም ከሕግ በላይ መሆን እንደማይችል ያሳየና መሬት የሚያስረግጠው ደብዳቤ መጻፉ ተገቢ መሆኑ ታውቋል።

በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው የማደራጃ መምሪያው ደብዳቤውን ለመጻፍ የተገደደበትን ምክንያት ሲገልጽ “…ስለዚህ በሕገ ቤተክርስቲያኑ፤ በቃለ ዓዋዲው እና በማኅበሩ ውስጠ ደንብ የተቀመጠውን መብትና ግዴታን ባለማጤን የሥርዓት፤ የግብረ ገብነት እንዲሁም የዲስፒሊን መገኛ በሆነችው በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ውስጥ እየሰራችሁ መሆናችሁን በመዘንጋት የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ሕገ ደንብና የበላይ አካላትን ትዕዛዝ በመቃረን ላይ እንደምትገኙ የተደረሰበት ስለሆነ ይህን ማስተዋል የጎደለውን እንቅስቃሴ ማስተካከል ለነገ የማይባል ተግባር ሁኖ አግኝተነዋል።” በማለት ነው።
አክሎም በ2002 ዓ.ም. የተወሰነውን ውሳኔ በ10 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ያዛል።
በ2002 ዓ.ም. መስከረም ወር ላይ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንግስት ተወካዮችና የማኅበሩ አመራሮች በተገኙበት ተወሰነው ውሳኔና መምሪያ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለማስወገድ ሰላምና ፍቅር የሚሰጠውን ጠቀሜታ ለማጎልበት አንድነትና ኅብረት የወሳኝነት ሚና አለው፡፡ ተቻችሎ መሥራትና ተከባብሮ መኖር ከቤተ ክርስቲያኒቱ የአመራር መርሆዎች መካከሌ ተቀዲሚውን አጃንዲ ይዞ የሚገኝ ስለሆነ ታጋሽና ልበ ሰፊ ሆኖ መሥራት ብሩህ ተስፋን የሚያስገኝ ውጤት እንጂ ጠባብ አመለካከትን የሚያሰተናግድ ተልእኮ የለውም፡፡
ከዚህ አንፃር በድርጅቶቻችን ማለትም በመመሪያ ሰጭው በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና በመመሪያ ተቀባዩ በማኅበረ ቅዱሳን መካከል የተከሰተው የሥራ አለመግባባት ችግር ለዚህ ከፍተኛ የሰላም ጉባኤ ቀርቦ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን ከተፈቀደለት መተዳደሪያ ደንብ ሳይወጣ ከማደራጃ መምሪያው የሚተላለፍለትንን መመሪያ እየተቀበለ ይሠራ ዘንድ የሚከተለውን መመሪያ ሰጥተናል፡፡
መመሪያ
የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ዘርፍ በሆነው በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና በሥሩ በሚንቀሳቀሰው በማኅበረ ቅዱሳን ማኅበር መካከል በሚታየው አንዳንድ የሥራ አፈጻጸም ግድፈት ለመወያየትና ዘላቂ መፍትሔን ለማምጣት ዛሬ በተደረገው የሰላም ውይይትና ምክክር ብዘ ጠቃሚ ጉዳዮችን ለማየት ችለናል፡፡
ማኅበሩ ስለነበረው አጠቃሊይ ሥራና እንቅስቃሴም በሰፊው ተብራርቷል፡፡
ይሁንና ከዚሁ ከተገነዘብነው አንጻር የማኅበሩ ቀጣይ እንቅስቃሴ ምን መምሰል እንዲለበት የመፍትሔ መመሪያዎች ማስቀመጡ በጣም አስፈላጊ ይሆናል፡፡
ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመ እንደመሆኑ መጠን በሥራው ሁሉ መሰናከል እንዳያጋጥመው መጠበቅ ከቤተ ክርስቲያን ይጠበቃል፡፡
ከዚህ አንጻር ማኅበሩ በቀጣይ የሥራ እንቅስቃሴው የሚከተለውን ጠብቆ እንዲሠራ ያስፈልጋል፡፡

1. ማኅበሩ ከዚሬ ጀምሮ ግንኙነቱ በመተዳደሪያ ደምቡ መሠረት ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ጋር ብቻ ይሆናሌ፡፡ ከመምሪያው ዕውቅና ውጪ የሚፈጸመው ከሦስተኛ ወገን ጋር ግንኙነት ሕገ ወጥ መሆኑን እንዱገነዘብ፣
2. የቤተ ክርስቲያኒቱን የፋይናንስ አስተዳደር ማበልጸግ የሚቻለው ገቢውንና ወጭውንም በትክክል እየተቆጣጠሩ መሥራትና ማሠራት የሚቻለው በየሥራ ዘርፉ ያለት የባለድርሻ አካላት በማዕከላዊው አስተዳደር በታተመና አንዴ ወጥ በሆነ የገቢና የወጭ ካርኒ መሥራት ሲችሉ እንደሆነ ይታመናል፡፡

ከዚህ አንፃር የማኅበረ ቅደሳን አባላት እንደሌሎቹ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሥሪያ ቤቶች ሁለ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እያሳተመ በሚያሰራጫቸው የገቢና የወጭ ካርኒ እንዲሠሩ
3. ማኅበሩ ከመምሪያው በሚሰጠው መመሪያ መሠረት በእጁ የሚገኘው የሀብትና የንብረት እንቅስቃሴ ሁኔታ በዝርዝር ኦዲት እንዲደረግ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱም ከመምሪያው በሚቀርብለት ጥያቄ መሠረት ሕጋዊ ኦዲተር በመሰየምና በማቅረብ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት እንዲፈጽም
4. ከዚህ በፊት ከመተዳደርያ ደንቡ ድንጋጌ ውጭ የተደረገው በቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና በፖለቲካ ጉዳዮች ጣሌቃ የመግባት እንቅስቃሴ ከቤተክርስቲያኗ ፍላጎትና ከመተዳደሪያ ደንቡ ውጭ በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ ማኅበሩ በፖለቲካ ጉዳዮችና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ጣልቃ የመግባት አዝማሚያ ማቆም አለበት፡፡
5. የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ የማደራጃ መምሪያውና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያናችን ተቅዋማት የማኅበሩን መተዲደደርያ ደንብ ማዕልድ ባደረገ ሁኔታ ማኀበሩ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የሚያቀርብላቸውን ጥያቄ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ማስተናገድ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ዛሬ በስፋት የተገነዘብነው ነገር ቢኖር በሁሉም አቅጣጫ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በወጣው መተዳደሪያ ደንብ ያልተሠራ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ከመተዳደሪያው ደንብ ውጭ መሥራትና መንቀሳቀስ ሕገ ወጥ መሆኑን ሁሉም ተገንዝቦ በመተዳደሪያ ደንቡ ብቻ እንዲሠራ ይህን መመሪያ አስተላልፈናል፡፡

ይህን ውሳኔ ማቅ 10 ቀን ውስጥ ካልፈጸመ የሚፈጸምበት አስተዳደሪያዊ ውሳኔ ምን ይሆናል የሚለው ከወዲሁ አጓጊ ሆኗል።

8 comments:

 1. የዘንድሮ ዓመት ዓመተ ጸጸት ነው ማለት ይቻላል፤
  ማቅም የኀፍረት ማቅ ይከናነባል (ዋርካ ምድር ነካ ደረሰ ንግሬ፤ እንግዲህ ልመለስ ልግባ ወዳገሬ፤ እንደ ተባለው በማቅ የተገፉ ሁሉ ደስ ይበላቸው፤

  ReplyDelete
 2. መቆየት ደግ ነው ልክ ዓመጽ በተጀመረ በ 21 ዓመቱ እግዚአብሔር ሰማያትን ቀዶ ወረደ ማለት ነው!ለካ ነቢዩ ምነው ሰማያትን ቀደህ ብትወርድ ያለው ይህንን ይሆንን?ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስስ ጅራፍ ይዞ ወደ ቤተመቅደስ የገባው በዚህ ዓይነት ሁኔታ ላሉት ይሆንን?
  ጎረቤትህ ሲታማ ነግ ለኔ ብለህ ስማ እንዳሉት አበው ይህ ጅራፍ ለ ሰለፊያው ማህበረ ቅዱሳን ብቻ ነው ብለን እንዳንታለል::ልክ እንዲሁ የሚቀጥልባቸው በክርስትና ስም የሚነግዱ በእግዚአብሔር ስም የሚነግዱ ሁሉ በየቦታው ሊቀጥል ስለሚችል ጌታችን<ንስሐ ባትገቡ እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ አላለለምን?ታዲያስ ጎበዝ ወደ ንስሐዋ በር ብንጠጋ ምን ይመስላችኋል::አባቶች ካህናት ዲያቆናት መጋቢዎች ጳጳሳት ሊቃነጳጳሳት ሁሉ ይህች መልክት ለማህበረ ቅዱሳን ብቻ እንዳይመስለን::እግዚአብሔር ወደ ምድራችን እየወረደ መሆኑን እያየንበት ያለ ስለሆነ ብናስብበትስ???
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 3. so what? is there any danger here? nothing new!u ll see it!u ll see it the result soon.

  ReplyDelete
 4. Do you think that this is end of the world.No,God start his work now.He will show you every think.MK is the real church/tewahedo/ maheber,so don't worry God will save mk.That is better to cry for your self.our lord is not let you to control the church. believe me he will show you soon. wolfs don't expect this is the time to eat the sheep's.This is the time to know who is who in the church.then .....

  ReplyDelete
 5. አሁንስ የአንዳንድ የማቅ አባል ወገኖቻችን አእምሮ ትክክል አልመሰለኝም!!!
  'ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም' ነው የሚባለው?

  እኛ ግን በእውነት ጥፋታችሁን ሳይሆን ደህንነታችሁን ስለሆነ የምንፈልገው ሳይመሽባችሁ እውነተኛ ንስሃ እንድትገቡ ሁሉን ቻይ በሆነውና ምህረቱ በበዛው ጌታ ስም እጠይቃችኋለሁ????

  በእውነት ጌታ ማስተዋልን ይስጣችሁ!!!

  ሰላም ይብዛላችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 6. Hey Mahebere Erkusan I think this is a good time to run before you caught.Unfortunately it look like your time is up. This is a wake up call for you Erkusan! No more violence ,grand theft . . . you name it ( because you know what you did ) hey why dont you run to somewhere with all the money before the audit ( ke ke ke ke . . . )Go enkubahri go for it get them and brought them to the court

  ReplyDelete
  Replies
  1. Both of the letter written to MK are written by Enkubahri as both of the are same letter evidenced by one with out ref number and date is the one which is written on behalf of the prevous one and the second one is by him self. any way he started his work with accusation because the issue of the chrch is not his issue just he is making the mission of the church delaying back through political issues.

   Delete
 7. የቤተክርስቲያናችንና የሐገራችን የካንሰር በሽታ የሆነው እራሱን ማህበረ ቅዱሳን እያለ የሚጠራው የማፊያ፣ የወሮበላ፣ የአሸባሪ፣ የመሰሪ ድርጅት የተሰጠው ደብዳቤ ብጣም አስፈላጊ መሆኑ ፍፁም ጥርጥር የለውም። ሆኖም ግን ቤተክርስቲያናችንን ሐያ አመት ሙሉ የገዘገዛትና ምዕመኑን በእምነትና በቤተክርስቲያን ሥም ሲዘርፍ ለኖረ የሠይጣን ድርጅት በአሁኑ ጊዜ ግን በቃህ ሊባል ይገባው ነበር እንጂ የማስተካከል ደብዳቤ ብቻ መቀበል የለበትም። ማህበሩ ባጠቃላይ ለቤተክርስቲያናችንና ለሐገራችን ፈፅሞ አስፈላጊ አይደለም። ማቅ ካልተዘጋ በቀር በየጊዜው የማፊያ ስትራቴጁን እየቀያየረ የቤተክርስቲያንን ደምና የክርስቲያኖችን ደም ሲመጥ ለመኖር አላማ ስላለው እባካችሁ የቤተክህነትና የሲኖደስ አባቶች ይህንን መሰሪ የሰይጣን ማህበር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከካንሰሩ እንድትታደጉት በህያው እግዚአብሔር ሥም እንለምናችኁለን።

  ReplyDelete