Thursday, May 17, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ የስድስተኛ ቀን ውሎ እንዴት ነበር?

·        ማኅበረ ቅዱሳን የመፍረስ አደጋ ያሰጋዋል
·        ውግዘቱ ሥርአተ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ ነው፤ ይወገዛሉ የተባሉት ግለሰቦች ተጠርተው አልተጠየቁም
·        አባ ሠረቀብርሃንና ዲ/ን በጋሻው ስማቸው ይወገዙ ከተባሉት ውስጥ የለም  
በ PDF ለማንበብ (ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት) 
በትናንትናው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶስ በስድስተኛ ቀን ውሎው ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ያነሳ ሲሆን የጠዋቱ የማኅበራት ጉዳይ ነው። ከሰዓት በኋላ ደግሞ የተነሳው የሃይማኖት ህጸጽ አለባቸው ስለተባሉ ግለሰቦችና ማኅበራት ጉዳይ ነው።
በጠዋቱ ውሎ በማኅበራት ጉዳይ ላይ የተሰናዳው ጥልቅ ጥናት የቀረበ ሲሆን ጥናቱም በሃይማኖት ጸሎት ላይ ያለውን “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” በሚለው መሰረት ጉባኤ የሚለው አንዲት ቤተክርስቲያንን ነውና ሌሎች ማኅበራት አያስፈልጉም። አንዲቷ ቤተክርስቲያን ራስዋ ማኅበር ናትና የሚል ጥቅል ይዘት ያለው ጥናት ቀርቦዋል። ጥናቱ ሁሉንም አባቶች ያስደሰተ ሲሆን፣ አንዳንድ አባቶች ከውሳኔ በፊት ጥናቱ ለሁላችንም ይሰጠንና እናንብበው ብለው ሲጠይቁ አቡነ ቄርሎስ ጥናቱ በጥሩ ሁኔታ ቀርቦአል። ትክክል የምንለውን ውሳኔ መወሰን ነው እንጂ ጽሁፉን እንደገና ወስደን የምናነበው ለምንድን ነው? ብለው በመጠየቃቸው ተባዝቶ ይሰጠን የሚለው ሀሳብ ቀርቶ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ለመወሰን ቀጠሮ ተይዟል። ማኅበሯን ትልቅ ስጋት ውስጥ የከተታትም ይኸው ውሳኔ ነው ተብሏል።
ማኅበራት እስካሁን ባላቸው አሰራርና ባደረጉት እንቅስቃሴ ራሳቸውን እንጂ ቤተክርስቲያንን የጠቀሙበት ሁኔታ ያን ያህል ነው። ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳታቸው አመዝኖ እንደታየ ያመለከተው ጥናቱ፣ እንዲያውም በአባቶች መካከል የሚነሱትን መጠነኛ የሀሳብ ልዩነቶች በማስፋትና በራሳቸው መንገድ ነገሩን በመጠምዘዝ እየተጫወቱት ያለው አፍራሽ ሚና ይበልጣል ማለቱ ተነግሮአል። ስለዚህ ከዚህ የከፋ ጉዳት ሳያስከትሉ በማኅበራት ላይ ውሳኔ መተላለፍ እንዳለበት ግንዛቤ ተወስዷል። የተሻለውም አማራጭ ማኅበራትና ማፍረስ ነው ሲል ጥናቱ የመፍትሔ ሀሳብ አቅርቧል።
ማኅበራትን በተመለከተ የቀረበው ጥናት ድምዳሜው ከአንዲት ቤተክርስቲያን ውጭ ማኅበራት ኣያስፈልጉም የሚል መሆኑን የሰሙት የማኅበረ ቅዱሳን ግልጽ አመራሮችና ጀሌዎቻቸው፣ ትናንትና ከሰዓት በኋላ ግቢውን ወረውት የነበረ መሆኑ ሲታወቅ፣ ገቢ ወጪው ሁሉ ማኅበሩን ሊያፈርስ የመጣ ግብረ ኃይል እየመሰላቸው አይናቸውን ሲያጉረጠርጡበትና ሲደናበሩ መዋላቸውን በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ተናግረዋል።
በትናንትና የከሰዓት በኋላ ውሎ የሃይማኖት ህጸጽ አለባቸው የተባሉ ግለሰቦችና ማኅበራት ጉዳይ የታየ ሲሆን፣ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የተወሰነው በተለይ ግለሰቦቹ በህጋዊ መንገድ ተጠርተው እንዲጠየቁ፣ አቋማቸውን እንዲያሳውቁና በዚያ ላይ ተመስርቶ አጣሪ ኮሚቴው የደረሰበትን ድምዳሜ ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀርብና ውሳኔ ይሰጣል የሚል ነበር። እስካሁን ባለን መረጃ ማኅበረ ቅዱሳን ከአባ ሠረቀ ብርሃንና ከሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ በስተቀር፣ ይወገዙልኝ ያላቸው ግለሰቦች በሙሉ ከሊቃውንት ጉባኤ ጥሪ እንዳልተደረገላቸውና ቀርበው የሰጡት ሐሳብ እንደሌለ ታውቋል። ስለሆነም ጳጳሳቱ በዚህ መንገድ በማኅበረ ቅዱሳን ተቀነባብሮ የቀረበላቸውን ክስ ብቻ ተቀብለው ግለሰቦቹን ሳያነጋግሩና ሀሳባቸውን ሳይጠይቁ ውግዘት ቢያስተላልፉ ይህችን ታላቅ ቤተክርስቲያን ትልቅ ውርደት ላይ የሚጥልና ራሳቸውንም የሚያስገምት ውሳኔ እንዳስተላለፉ ይቆጠራል የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ምክንያቱም በሃይማኖት ሕጸጽ የተጠረጠረ ሰው ከመወገዙ በፊት ተጠርቶ ሊጠየቅና በእርሱ ሐሳብ ላይ ተመስርቶና ህገ ቤተክርስቲያንን መርምሮ ውሳኔ መስጠት ተገቢና ተቀባይነት ያለው አሰራር ነው።
ቤተክርስቲያን የተሳሳቱ ካሉም ቅድሚያው መስጠት ያለባት መክሮ ለመመለስ እንጂ ለማውገዝ እንዳልሆነ የኖረ የቤተክርስታያኒቱ አቋም ነው። ከዚህ ቀደም ቅዱስ ፓትርያርኩ የጻፉትና በመላው ኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የበተኑት ደብዳቤም ይህንኑ የሚያስረዳ ነው። ይህን መንፈሳዊ አሰራር ወደጎን በማለት በማኅበረ ቅዱሳን ግፊት የከሳሽን አቤቱታ ብቻ ሰምቶና ተከሳሽን ሳያነጋግር ህግን ባልተከተለ መንገድ ማውገዝ ፈጽሞ ተቀባይነት እንደሌለው አእምሮ ያለቸው አባቶችና ምእመናን ሁሉ የሚገነዘቡት እውነት ነው። በቤተክርስቲያን ላይ የሚያስከትለውም አደጋ ዛሬ ባይታያቸውም ከፍተኛ መሆኑ አይጠረጠርም። 
ጳጰሳቱ የውግዘቱን ጉዳይ ለማጣደፍ የተነሱበት ዋናው ምክንያት በዜና ቤተክርስቲያን የቀረበባቸውን ፍጹም አለማዊነት የተሞላ ሕይወት ለመሸፋፈንና ስብሰባውን አቅጣጫ ለማስለወጥ እንደሆነ ተገምቷል። አንዳንድ አላዋቂዎች ሃይማኖትንና ምግባርን ለያይተው ከምግባር ህጸጽ የሃይማኖት ሕጸጽ ይከፋል ይላሉ። ግን ፍጹም ስህተት ነው። ምግባር የሚበላሸው ሃይማኖት ሲበላሽ ነው። ከቀና ሃይማኖት በጎ ምግባር ይገኛል። ህጹጽ ሃይማኖት ግን ብልሹ ምግባር እንጂ በጎ ምግባር አይገኝበትም። በዜና ቤተክርስቲያን የተዘረዘረውና ያልተዘረዘረውም በብዙዎች ዘንድ የታወቀው እንደዚያ ያለ ከጳጳሳት የማይጠበቅ ምግባረ ብልሹነት ከቀና ሃይማኖት እንደማይገኝ የታወቀ ነው። የቀና ሃይማኖት በጎ ምግባርም ይከተለዋልና። እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ጳጳሳት ሳይጠይቁና ሳይመረምሩ ሌላውን ለማውገዝ ብቃትም ሞራልም የላቸውም። ጳጳስ ስለሆን ብቻ እንችላለን ካሉም ውግዘቱ ዖፈገዝት ከመሆን አያልፍም ይላሉ እነዚሁ አስተያየታቸውን የሚሰጡ ወገኖች።  
ይህ በእንዲህ እንዳለ ማኅበረ ቅዱሳን ከሌሎቹ ይልቅ እነርሱ ቢወገዙልኝ የሚላቸው አባ ሠረቀብርሃንና ዲ/ን በጋሻው በውግዘቱ ላይ ስማቸው እንዳልተካተተ ታውቋል። ሲኖዶሱ በዛሬው ውሎው በእነዚህ ሁለት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።


4 comments:

 1. ሕቱ ርእሰክሙ(ራሳችሁን መርምሩ)
  ለመሆኑ ውግዘት ውግዘት የሚሉ ወገኖች የንባቡ ትርጉም ተቀላቅሏችዋል ወይ?
  የቤ/ክርስቲያኒቱስ ጉልላት የሆነው ጉባኤስ ውግዘትን እንዴት ያይዋል፤ለእመ ረከብከ
  ቀለመ ጸዋገ ተመያየጥ ዓሠርተ ወክልኤተ ጊዜያተ አስቸጋሪ ነገር ባጋጠመህ ጊዜ ጉዳዩን
  መላልሰህ ተመልከተው ይላልና ሊመለከትው ይገባል፤አለዚያ ግን ማን አውጋዥ ማን ተወጋዥ
  (የበላችው ያገሳታል በላይ በላይ ያጎርሳታል)ሁለቱ ወገኖች በከንቱ ተወጋግዘው መቀራረቢያ
  ጠፍቶ ዓለም እየተጨነቀ እንደ ገና ውግዘት( የማይመስል ነገር ለምንህ አትንገር)ነው.

  ReplyDelete
 2. Abba Selama MAhibere Kidusan Yemefires Adega Yasegawal Bilachihu Nebere Ahat Tewahedo Dedimo Sinodos Yewesenew Ye Mahiberat Guday Mahibere Kidusann Ayimeleketim Tebale Yilal Ewnetu yemanew ? Abba Selama Zegebachihu Wishet Alebet Malet New ?Weyis Ahat Tewahedo Yetenagerew Belbu Yasebewn YIhon ? Melsun befitsinet Mezigubu

  ReplyDelete
 3. አባ ሰላማዎች አትሳሳቱ፡፡ ሲኖዶሱ እየተወያበት ያሉት ማኅበራት ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት እና አነዚህን መሰሎች ላይ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን በቤተ ክርስቲያን ስር (በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ) የተዋቀረ እንደ አንድ ሰንበት ት/ቤት የሚቆጠር ነው፡፡

  እንደ እናንተ አባባል በቤተ ክርስቲያን መኖር ያለበት አንድ ማኅበር ብቻ ከሆነ ያደግንባቸው የተማርንባቸው ሰንበት ት/ቤቶች ሁሉ ሊፈርሱ ነውን፡፡ ሰው ለማሳሳት እና ውዥንበር ለመፍጠር ብላችሁ ብቻ የራሳችሁን ፍላጎት ብቻ አትጻፉ፡፡

  ዛሬ በሲኖዶስ ፊት የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በማጣመም ጉዳያቸው እየታየ ያሉት ሰዎች ዝርዝር መረጃ በማቅረብ የታገሉትን ማኅበረ ቅዱሳንን እና የሰንበት ት/ቤቶች ኅብረት ለቤተ ክርስቲያን የልጅነታቸውን ተወጥተዋል፡፡ እናንተ ግን ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ ብቻ ትሯሯጣላችሁ፡፡ በዚህ ስራችሁ በነፍስም በስጋም ፍርዱ ይጠብቃችኃል፡፡

  ReplyDelete
 4. please donot histate our church and our saint fathers.

  ReplyDelete