Friday, May 18, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ሰባተኛ ቀን ውሎ

በ PDF ለማንበብ (ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት)
 • አንዳንድ ግለሰቦችን ሊቃውነት  ጉባኤ ጠርቶ ስላላነጋገራቸው ጠርቶ እንዲያነጋግር ታዘዘ
 • አቡነ ገብርኤል ከአዋሳ አይነሱም
 • የሰንበት ማደራጀውና የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ ታየ
 • ዲ/ን አሸነፊ መኮንን ይወገዝ ተብሎ አልቀረበም
በትናንትናው ዕለት በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ከተነጋገረባቸው ጉዳዮች አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን እንዲወገዙ ከቋመጠባቸው ግለሰቦች አንዳቸውም ሳይወገዙ እንደ ገና መታየት ያለባቸው ነገሮች እንዲታዩና ሲኖዶሱ ሊቃውነት ጉባኤው ሰዎቹን ጠርቶ በጥንቃቄ መርምሮ ይወሰን የሚለውን ባለማሟላቱ እንደገና ያላነጋገሩዋቸውን ሰዎች እንዲያነጋግሩ ታዘዘ።አባ ሰረቀ እና ዲ/ን በጋሻው የውግዘት ሀሳብ እንዳልቀረበባቸውም ታውቋል። በጋሻው በትናንትናው ዕለት ሊቃውንት ጉባኤ ሊያነጋግረው ፈልጎ ተጠርቶ የነበረ ቢሆንም ሊቃውንት ጉባኤው ራሱ በሲኖዶሱ በመጠራቱ ሳያነጋግሩት ቀርተዋል። ደጀ ሰላም ዲ/ን በጋሻው ሊለማመጥ ሄደ ያለው ከሀቅ የራቀ ሲሆን ሊቃውንት ጉባኤው ስለጠራው መሄዱ ታውቋል።
“አቡነ አብርሃም ምንድንነው መልሶ መልሶ ነገር ማየት መናፍቁን ሁሉ ማውገዝ ነው። ለእነኚህ ደግሞ የማሕበረ ቅዱሳን ጥናት አነሳቸው?” ብለው የደነፉ ሲሆን በዛን ወቅትም ቅዱስ ፓትርያርኩ አቅማቸውን እንዲያውቁና ለማንበብ ለመጻፍ ዝግጁነት ሳይኖራቸው ይወገዙልኝ እያሉ ወመወራጨታቸውን እንዲያቆሙ አዝዘዋል። እኛ ለእውነት እንጂ ለማንም ማድላት የለብንም ድጋፍ ድምጽ ሰብስበን ሳይሆን የነገሩን እውነትነትና በጥንቃቄ መታየቱን መርምረን መፍረድ ነው የሚገባን አሊያ የሁሉ አባት መሆናችን በምን ይታወቃል? የተቀመጥንበት ወንበርም ይኼን ነው የሚያዘን በማለት ተናግረዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን የመጽሐፍ ገበያውን ለብቸኝነት ለመቆጣጠር ባለው ፍላጎት የኔ መጽሐፍ እንዳይሸጡ አድርጓል ያለውን ዲ/ን አሸናፊ መኮንንን እንዲወገዝለት ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረውም ሊቃውንት ጉባኤው ግን ውግዘት አይገባውም ምክር እንጂ ሲል ሪፖርት አቅርቧል። ይህንን ገልብጦ ያነበበው ደጀ ሰላምም በትናንትናው ዕለት ይወገዛል ሲል የዘገበ ሲሆን ትላንትናም እንደሌላው ቀን ማንም ሳይወገዝ አልፋለች።
አባ አብርሃም ሊቃውንት ጉባኤው የውጭ ተጽዕኖ አለበት ሲሉ እንደተናገሩ ታውቋል። እኛም ይህ የሲኖዶስ ስብሰባ ከተጀመረ ከአባ አብርሀም የሰማነው አንድ ቁምነገር ይኼ ነው እንላለን። አባታችን ሊቃውንት ጉባኤው አዎን ተጽእኖ አለበት፤ ተጽዕኖውም ከማኅበረ ቅዱሳን የመነጨ ነው እንልዎታለን። አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ እንደሚባለው የሊቃውንት ጉባኤው አባል በሆኑ የማኅበረ ቅዱሳን አባቶች እና የማኅበሩ ተጽዕኖ በከፍተኛ ደረጃ እንዳለበት የሚታወቅ ነው። 
ሌላው የአዋሳው ጉዳይ የተነሳ ሲሆን በሁለት ወገን የተወጠሩት አቡነ ገብርኤል ከቦታቸው እንዳይነሱ ተወስኗል። ማኅበረ ቅዱሳን የምፈልገውን ሥራ አልሰሩልኝም በማለት በአባ አብርሃም ሊተካቸው ቢፈልግም ሳይሳከለት ቀርቷል። የማኅበረ ቅዱሳንና የሰንበት ማደራጃ ጉዳይ የተነሳ ሲሆን ሁሉም ባለህበት እርጋ ተብሏል።

9 comments:

 1. የማኅበረ ቅዱሳን ኃጢአት ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር፣
  ከዚህ በታች ተዘረዘሩትን መጽሐፍ ቅዱስ ያወግዛት ማኅበረ ቅዱሳን በይፋ ይሠራቸዋል

  ስድብ
  አድማ
  ጥላቻ
  ቡድነኛነት (እኔ የኬፋ እኔ … አትበሉ)
  ራስ ወዳድነት
  ውሸት
  ቧልት፣ ሐሜት
  የሃይማኖት ሕጸጽ
  የቀኖና ጥሰት
  ክፉ ዝንባሌ
  ውንጀላ
  ፍቅር ማጣት
  ገንዘብ መውደድ
  ዓለማዊነት
  ሥጋዊነት (የሥጋ ባለ ፍሬ)
  ማስመሰል
  መንደርተኛነት
  የቤተ ክርስቲያንን ሐብት ለቡድን ማድረግ

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
  Replies
  1. alkerebihim...eko ante man honeh new sewin hatiyategna yemitadergew...wedesew sayhon mejemeriya terasachinin hatyat temelkiten new mefred yeminichilew...

   Delete
  2. Ere yene wendim betam tigermaleh,"Kenante wist hatiyat yelelebet be dingay yiwgerat" Yemilewin Ye Getachin ye Amlakachin ena Yemedhanitachin Ye Iyesus Kiristosin Kale tastawisaleh? Erasihin Mermir yene wendim elay ketekeskachew wist lelawin hulu enquan batifesim be huletu maletim BE KENONA TISET ENA BE HAYMANOT HITXES gin ante Mahbere Kidusanin endemitbeltachew tiritir yelengim.

   Delete
 2. YEMAHEBERE KIDUSAN ( yedejeselam) WESHETENA WERE AYALIKIM BERE WELEDE NEW SERACHEW MIKINEYATUM ENEM BALEMAWEK YE MK ABAL NEBERKU LE 4 amet Medehaniyalem bekine tibebu adanegn gibezoch asmesayoch EGZIABHER AMELAK GELETSACHEW MIDERE WETADER HULU NETSU YEHONUTIN YEBETEKERESTEYAN LIJOCH TEADESO EYALE SIM ATFI EGZIABHER GENA YIFERDAL TEBIKU LEHULUM GIZE ALEW KE GERMEN FRANKFURT NEGN EHETACHU BERTU ABASELAMAWOCH

  ReplyDelete
 3. Egziabher yesethi ye mk hateyat belehe yetsafekew(shew) tekikelegna serachew new leka hulum bebetu belibu yizot kuch belo neber yetkemetew yigermalllllll yenezhi sewoch sera egzioooooo ere mafereyawoch nachew mahebre kidusan belew siteru yemayaferu egzioooooo

  ReplyDelete
 4. "የተቀመጥንበት ወንበርም ይኼን ነው የሚያዘን በማለት ተናግረዋል።" ,yetignaw wonber ? is it chair.wonber degmo yazal inde? sew malet yalamenebtn alemetsaf,alemenager....new.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንበር ማለት ሥልጣንና ኃላፊነት ነው። አመዛዝነን ትክክለኛውን ነግር እናድርግ ማለት ነው። በደመ ነብስ ማቅን እየደገፉ ማዶዝደዝ ይቅር ለሁሉም እኩል እንፍረድ ማለት ነው። ገባህ? i hope u understood it.

   Delete
 5. የኔ ወንድም ይቅርታ ወንድሜ ያልኩህ በጌታ ነው ምክንያቱም ሃሳብህን ስለተረዳሁት ነው ወንበር የሚለው አነጋገር ግራ ያጋባህ ወንድሜ የሚለውማ....አንተው ተርጉመው። ወደመጣሁበት ጉዳይ ልመለስና እንደዚህ እያሰብክ እንዴት ሆነህ ነው የምትኖረው? መቼ ኖርኩና ብትለኝ ሃሳብህን አልቃዎምህም! እንደዚህ ካለ የማህበረቅዱሳን ሰው ጋር ነበር የምነጋገረው? አበስኩ ገበርኩ ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ? ምኑህ ነገር አሳየሕኝ

  ReplyDelete
 6. አይጣል! ማቅ ምን አገኘው?እንደ ከፋ ከልብ(እንስሳ)ሁለት ጀሮዎችን አዘንብሎ ይበርግጋልሳ
  በፊቱ ያገኛቸውን እንዳይለክፋቸው ጤና አዳም ይዘጋጅላቸው ባለመድኃቱም ይምከራቸው መርዙን
  እንዳያሰራጭባቸው፤

  ReplyDelete