Sunday, May 20, 2012

የ“ኢሳት” የዜና ማእከል እና “የማህበረ ቅዱሳን” ጊዜያዊ ጋብቻ!


ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

ሙሉውን የጽሑፉን ይዘት ከማንበብዎ በፊት÷ በPDF ለማንበብ
1.     ጸሐፊው በጽሑፋቸው ውስጥ የጠቀሱትን የዜና ማዕከል “ማህበረ ቅዱሳን” በመባል ስለሚታወቀው መንፈሳዊ ካባ ያጠለቀ ጸረ ቤተ-ክርስቲያን ጸረ ሀገርና ጸረ ትውልድ ማኅበርን በተደጋጋሚ ሽፋን በመስጠት ጽድቁን በዜና መልክም ሆነ በሐተታ ተጠቃሹ የዜና ማዕከል ለአድማጮች ያቀረባቸውን ፍጹም ሚዛኑን የሳተና የተንጋደደ ዘገባን ብቻ በማስመልከት ያነጣጠረ ለመሆኑ÷
2.    አሁንም በጽሑፉ ውስጥ የተካተቱ ማናቸውም ሂሶችና ጥያቄዎች “ማህበረ ቅዱሳን” በማስመልከት እጃቸውን የጨመሩ የክፍሉ ሰራተኞች/ግለሰቦች/ እንጅ የመደብሩ ባልደረባዎችን በመላ የማያጠቃልል ለመሆኑ÷
3.    የጸሐፊው ዓላማም ሆነ የጽሑፉ ግብ በማጣመም ሌላ አንድምታ በመስጠትም “በኢሳት” የመጣ በዓይኔ ብሌን” በማለት አካኪ ዘራፍ የሚልም ስለማይታጣ  “ኢሳት” “ማህበረ ቅዱሳንን” በተመለከተም ሆነ “ደጀ-ሰላም” በመባል የሚታወቀውበኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያንና በተከታዮችዋ ላይ ሁከትን ለመፍጠር ታጥቆ የተነሳ የማህበሩ (“የማህበረ ቅዱሳን’) በአንድ ራስ ላይ ተደራቢ ምላስ/ልሳን ሆኖ የበቀለ ድረ ገጽ ዋቢ እያደረገ የሚዘግባቸው ዘገባዎችና የሚያቀርባቸው ማናቸውም ዓይነት ሀተታዎች ፍጹም ከእውነት የራቁና ነጭ ሐሰት መሆናቸው ብቻ ሳይሆን በወንጀል የሚያስጠይቅ ስራ እየሰራ ለመሆኑ÷
4.    በተጨማሪም “ኢሳት” ጭራሽ “የማህበረ ቅዱሳን” ልሳን አስኪያስመስልበት ድረስ እየሄደበት ያለውን አካሄድ ማለት ነፍሰ ገዳይን የመታደግ ስራ ትክክል አለመሆኑ ለማሳየት ምንም በማያሻማ ግልጽ በሆነ አማርኛ የቀረበ ጽሁፍ ለመሆኑ÷
5.    በመጨረሻም “ለኢሳት” ለብቻ ተብሎ የሚታለፍ እውነት አለመኖሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ከአንደበት የሚወጣ ቃል የሰውን ልብ ከማሸፈት በላይ ህይወትም ይቀጫልና በተለይ የጉዳዩ ቀዳሚ ባለቤቶችና ሰላባዎች ሊሆኑ የሚችሉ/የምንችል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን እምነት ተከታዮችና ምእመን ሰላም ለመጠበቅ ሲባል ይህን ጽሑፍ ሊዘጋጅ ግድ ብለዋል። ደግሞም ሰው ይከበራል እንጅ ስጋ ለባሽ ሆኖ የሚፈራ፣ አምልኮም የሚገባው አንድ ስንኳ አለመኖሩን በሚያምን ልብ ተጻፈ። ጽሑፉ ልዩነትን የሚያሳይ እንጂ የክስ ደብዳቤም ሆነ የስሞታ ማመልከቻም አይደልም።
ከሰርጎ ገቦች የተነሳ በኢ/ኦ/ተ/ቤተ/ያን አስተዳደራዊ ማእከል ላይ ስለተፈጥረውና ስላለው ችግር በማስመልከት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት ዜናዎችን በማቅረብና ሰፊ ሐተታዎችን በመስጠት ይታወቃል። ይህ መቀመጫውን ሆላንድ አምስተርዳም ያደረገ እንዲሁም በአሜሪካን ክፍለ ግዛት ዋሽንግተን ዲሲ በመሆን ከሚያሰራጫቸው ሀገራዊ ዜናዎች በብዙዎቻችን ዘንድ የታወቀ ለመሆኑ አልጠራጠርም። ስለ መረጃው ማእከል ከማንም የተለየ የጠለቀ ቅርበትም ሆነ ስለ ጣቢያው የተሻለ እውቀት ባይኖረኝም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሚኖረኝ የጊዜ ክፍተት አልፎ አልፎ አድማጭ ነኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድ ሃሳብ የበላይነት ከሚንጸባረቅበት ብቸኛ መንግስታዊ የዜና ማሰራጫ ተገላግሎ አማራጭ እድል በማግኘቱም ደስታዬ ወሰን የለውም። ታድያ ይህ መቀመጫውን በምእራቡ ዓለም ያደረገ “ኢሳት” በመባል የሚታወቀው የዜና ማእከል በብዙ የአገልግሎት ዘርፎቹ ሁሉንም የሚያስማማና ሁሉንም ያቀፈ ስራዎቹን ውሃ የሚቸልስ ስራዎችን ሲያቀርብ አንዴ፣ ሁለቴና በተደጋጋሚ መፈፀሙ በተለይ ለጉዳዩ ቅርበት ባላቸው የቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ልጆችና ባለ አደራዎች ዓይን ሲታይ ነገሩ በቀላሉ የማይታለፍ ሆኖ በመገኘቱ ለመተራረምና እርስ በርስ ለመማማር ለማስታወሻም ያክል አንድ ማለቱ አስገዳጅ ሆኖ ተገኝተዋል። 
የነገሩ ስር ተጠቃሹ የዜና ማዕከል ኢ/ት/ኦ/ተ/ቤ/ያን በተመለከተ ለሚያስተላልፋቸው/ለአድማጭ የሚያደርሳቸው/ በምስል የተቀረጹ ዘገባዎች በዋናነት “ደጀ ሰላም” በመባል የሚታወቀው ሰምዓ ሐሰት መካነ ድር እንደ ዋቢ መጠቀሙ አንዱ ነው። በነገራችን ላይ የዜና ማእከሉ እንደ አንድ የመረጃ ማሰራጫ ማዕከል ሚዛኑን በጠበቀ ሁሉንም በሚያንጽ መልኩ ዘገባዎችን ማቅረብ ሲገባው “ባለቤትነቱ በውል የማይታወቅ” የሰፈርተኞች አሉባልታ ማስተጋባት ምን ይሉት የሞያ ሃላፊነትና ግዴታ ነው ለማለት እንጅ “ኢሳት” ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በተመለከተ ለምን  ይዘግባል መዘገብ አይገባውም እየተባለ አይደለም ያለው። “ኢሳት” ድምጽ ሆኖ ካልዘገበ ሌላ ማን ይዘግብ!
የመረጃ ማእከሉ ነፃና ገለልተኛ ነኝ ሲል አላማው  የዘራውን እያጨደ ስለሚገኘው፣ በብዙዎች ደም ተጠያቂ የሆነው፣ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ጥንታውያንና ታሪካዊያን ቅርሶችዋ በማውደምና በመዝረፍም አቻ የማይገኝለት ሕጋዊ ሽፍታ፣ የሰው ለውጥና ዕድገት ደም የሚያስቀምጣቸው፣ ለሀገርና ለወገን ኪሳራ የሆነውን ትውልድ የሚፈለፍል ቆፍቁፎም የሚያሳድግ፣ እነሱ ያልተካፈሉበት ስራ ሁሉ ለመኮነንና ለማፍረስ የማይቀደሙ፣ የእግዚአብሔር እጅ የከበደችበት፣ በሞት አፋፍ ላይ ስለሚገኘው የሰው እባብ ስለ “ማህበረ ቅዱሳን” ጽድቅ መዘገብና ሽንጥን ገትሮ መከራከር ከሆነ÷
v ዋጋ በከፈልኩበት!
v እንደ ፌስታል እየተንጠለጠልኩ ወደ እስር በተወረወርኩበት፣
v ዜግነታዊ መብቴን ተግፎ ከትምህርት ገበታዬ በተፈናቀልኩበት፣
v በተወልድኩባት እትብቴም ተቆርጦ በተቀበረባትና በገዛ ሀገሬ በተገፋሁበት፣
v በተዋረድኩበት፣
v በተንገላሁበት፣
v በተደበደብኩበት፣
v በተረገጥኩበት፣
v በቆሳሰልኩበት፣
v አባት እንደሌለው በስደት ምድር ቁምስቅሌን ባየሁበት፣
v በኬንያ ጎዳናዎች በወደቅኩበትና በተጣልኩበት፣
v ወላጅ አባትእናቴ ወንድም እህቶቼ በትልቁም እናት ሀገሬ ጥዬ ለግዞት ህይወት በተዳረኩበት አጀንዳ ላይ እውነት የማይዋጥለትና ሲነገረውም ጆሮውን የሚያሳክከው ምንስ ቢሆን ማንም ሙሉጌታ ተኝቶ ያድራል ማለት ሲበዛ የዋህነት ነው። ደካማ መስዬ የታየሁት ግለሰብ ሆነ ድርጅትም ቢኖር መፅሐፍ ታናሹ ለሺህ የሁሉም ታናሽ ለብርቱ ሕዝብ ይሆናል እንዲል ጥጉ እንዲሁ ነው።የተደገፍኩትም እንደ ሸምባቆ የሚሰበረው ከሁኔታዎች ጋር የሚለዋወጠውን ሰው ሳይሆን ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ/የሚያደርግ/፣ ሰማያትን በብልሃት የሠራ፣ ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፣ ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው፣ ከበኵራቸው ጋር ግብጽን የመታ እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ፣ በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለ እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈፈርዖንንና ሠራዊቱን በኤርትራ ባሕር የጣለ፣ ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራታላላቅ ነገሥታትን የመታ፣ ለባሪያው ለእስራኤል ርስት የሆነውን እግዚአብሔርን ነው።
እንግዲህ ይህ የመረጃ ማእከል ከተቋቋመበት ዓላማ በማፈንገጥ በተለይ “ማህበረ ቅዱሳን” በተመለከተ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በተደጋጋሚ ሽፋን በመስጠት የሚያስተላልፋቸው ዘገባዎች ፍፁም ከእውነት የራቀ፣ ጭብጥ የሌለው፣ተጠያቂነት በማይንፀባረቅበት፣ ሃላፊነት የጎደለበትና ሲበዛም የጋዜጠኝነት የሞያ ስነምግባር በሚያጎድፍ መልክ የቀረበ ለመሆኑ ልብ ብሎ ላስተዋለ ሰው ምንም አያጠያይቅም። ቁርጡ “ኢሳት” ለእኔ ለተገፊው ግለሰብ ስለ ሰላቢው ማህበር “ማህበረ ቅዱሳን” እንዲነግረኝ አይጠበቅበትም። (ደጀ ሰላምን በተመለከተ በሚቀጥለው ጽሑፌ እመለስበታለሁ)
ይህ በዋናነት “በኢሳት” ዜና ዘጋቢዎችና አንባቢዎች ሰፈር ዋቢ እየተደረገ የሚጠቀሰው መካነ ድር ፀሐፊው ማን ነው? ለዜናዎቹና ዘገባዎቹ ሐላፊነት የሚወስድ ግለስብም ሆነ ድርጅትስ ማን ነው? ለሚለው እጅግ ቀላል ጥያቄ “የኢሳት” ባልደረቦች በተለይ ማህበሩን በተመልከተ ጊዜያቸውን ሰውተው ብዙና ጥቂት የሚሉትን ለእነዚህ መሰል ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ይዘው እንደሚመጡ ተስፋ አደርጋለሁ። የሌሎቹን ባላውቅ እንደነ አበበ ገላውና ልጅ ተክሌ የመሳሰሉ በውጭ ዓለም የከፍተኛ ተቋማት ያለፉ ግለሰቦች የሚገኙበት ቤት አንዴት ነው እንዲህ ያለ ነገር በተደጋጋሚ ሊከሰት የሚችለው? ተጨማሪ ጥያቄ ነው (ስለማውቀው ተናገርኩ እንጅ ሌሎቹ አልተማሩም እያልኩ አይደለም)። ማንስ ይዘግበው ማንም የተገኘውን የማቅረብ መብት አለን ከተባለ ደግሞ ከዚህ በኋላ ሙግቱ ሞያ ነክ መሆኑ ነው። ያገኘኸውን ማግበስበስስ ተገቢ ነው ወይ ባይም ነኝ? ከሆነ ደግሞ የሌላውን ወገን ድምፅስ ለምን አይሰማም? ነፃ የመረጃ ማዕከል ተብሎ የሚነገርለት ፍትሃዊና ሚዛናዊ መሆን አይጠበቅበት? አንድ የመረጃ ማእከል የህዝብ አይንና ጆሮ ነው ሲባልስ የማን ጥቅም ማዕከል አድርጎ ሲሰራ ነው? የሕዝብና የሀገር ወይስ የጥቂት አማፅያንን?
እዚህ ላይ ቀለል ያለ ነገር ግን በቀላሉ የማይታለፍ ሞያዊ/101 ጥያቄ ማንሳት እወዳለሁ። ይኸውም ይቅር አንድ በተቋም መልክ የተደራጀና በምእራቡ የዓለማችን ክፍል መቀመጫው ያደረገ ቀርቶ ሃላፊነት ወስዶ ለሚሰራዎች ስራዎች አንድ በዋቢም ሆነ በምንጭ ደረጃ ለመጠቀም ቢያንስ ቢያንስ ቀዳሚው የመረጃ አካል ለሚያቀርባቸው ዘገባዎች በሕግ ሃላፊነት የሚወስድህጋዊነቱ የተረጋጋጠለትየሪፖርቱ ፀሐፊም ሆነ የዘገባው አጠናካሪ አካል በውል የሚታወቅሓላፊነት የሚወስድዓላማውና ግቡ በግልፅ የሚታወቅተአማኝነት ያለው መሆኑን ሳይረጋገጥ እንዲሁ እገሌ እንዳለው ተብሎ ዜና ማለትስ የማን ንቀት ነው? ታማኝ ምንጮች እንደዘገቡት፣ ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት፣ ሮይተር እንደዘገበው ማለቱ አይበቃም? አንድ በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ያለፈ ሰው ይቅር እንዲሁ ያደገውን የጋዜጠኝነትን መሰረታዊ ስልጠና የወሰደ ሰው ይህን መሰረታዊና አንኳር ስነ-ምግባር እንዴት ይስተዋል? በመረጃ የሚያምን ተብሎ የተነገረለት “የቃሊቲው መንግስት” የሚለውን መጽሐፍ የፃፈ ሰው ባለበት (መጽሐፉ ደርሶኝ እያነበብኩት ሰላለሁ ነው) እንዴት ነው እንዲህ ያለ ጉልህ የሆነ ስህተት የዜና ማሰራጫ ማእከሉ ሁነኛ መታወቂያ ሊሆን የሚችለው?
እንግዲህ በዚህ አጋጣሚ አንዳንድ የኢሳት ባልደረቦች ለማህበሩ እየዋሉት ያሉትን ውለታና እያደረጉት ያሉት ቅምጥል ህጻን ልጅ የማባበል ያክልም እሽሩሩ ማለቱ “ማህበረ ቅዱሳን” መሞቴ አይቀር አጥፍቼ ልጥፋ በማለት ፀሐይ ሳለ በቀን የታወሩት አባላቶቹ አሰልፎ ሊፈጥረው የሚችለውን ግርግር ወደ ምኒልክ ቤተ-መንግስት ሊያደርስ ይችላል ተብሎ ገና ለገና ከወዲህ ታምኖበትም እንደሆነ በዚህ አጋጣሚ ግምቱ ከቅዠት የማያልፍ ትልቅ ስህተት መሆኑን ለመግለፅ እወዳለሁ። ማህበሩም እንደሆነ የሚይዘው የሚጨብጠው በማጣት የተቃዋሚዎች ደጋፊ ስለሆንኩ ነው፣ ለቤተ-ክርስቲያን ስለቆምኩ ነው፣ በዚህ ስለመጣሁና በዛም ስለወጣሁነው፣ የሚለውም አጥቶ ብረት ስለዋጥኩ ነው ቢል ከተዘረጋች የጽድቅ እጅ የሚያተርፈው አንዳች ሃይል የለም። አሜን!!
ቁርጣችንን እንወቅ። አይደለም የጥቂቶች ጩኸትና ሁካታ ስድስት ቢሊዮን ሕዝብ ሰልፍ ወጥቶ አይሆንም! ቢል የእግዚአብሔርን እጅ አይመለስም አይከለክልምም።  ታድያ በማወቅም ባለማወቅም ቢሆን በዚህ ሰልፍ መኸል የሚገባ ማንኛውም አካል ቢኖር በግብፅ ምድር የተገለጠውን መልአክ ሰለባ መሆኑን ሳይዘነጋ ያድርገው።
ለማጠቃለል ያክል የጸሐፍትና ፈሪሳውያን ገጽታ በከፊል ላውሳችሁ እወዳለሁ እነዚህ ሰዎች ጌታ ኢየሱስ በነበረበት ዘመን በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ መፈራት፣ ተቀባይነት ያላቸውና የላቀ የክብር ስፍራም የሚሰጣቸው ሰዎች ሲሆኑ በተመሳሳይ ትልቅ ትምክህትም የነበራቸው ሰዎች ነበሩ። በጥቂቱ የተመለከትን እንደሆነ  ኢየሱስ የመጣበት ዓላማ በሚያከናውንበት/እውነቱን በሚያስተምርበት ወቅት የአይሁድ ስርዓትና ወግ፣ በሙሴ ሕገ ኦሪት ላይ ያነጣጠረ በአጠቃላይ ብሉያት መፃሕፍትን በተመለከተ ቃል ከአፉ ያወጣ እንደሆነ እኛ ጋር ሳይደርስ ሕዝቡ ራሱ እንደተራበ አውሬ ቦጫጭቆ ይገድለዋል፣ ይውጠዋል በማለት ይታበዩና የልብ ልብ ይሰማቸው ስለነበር በዋለበት እየተገኙ ኢየሱስን ለማሳጣትና በወጥመዳችው ውስጥም ለማስገባት  ያላደረጉት ጥረት አልነበረም።
በተጨማሪም የእነዚህ አፅራረ ፅድቅ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ትልቁ መታመኛቸው ሕዝብ እኛ ያልነው ይሰማል ከእኛ እውቅና ውጭ ምንም የሚፈጠር ተአምር የለም አይኖርም! የሚል ፈሊጥም ስለነበራቸው ጊዜው እስኪደርስ ድረስ ደረታቸውን ገልብጠውና ምላሳቸውን አስረዝመው ለመዘባበት ተችሎአቸው እንደነበር ከቅዱሳት መፃህፍት ለመረዳት ይቻላል። ኢየሱስ ይህን እያወቀ በሕዝብ ፊት የተቃወማቸው እንደሆነ ግን ሊገጥመው የሚችለውን አደጋ ወደ ጆሮው ጠጋ በማለት ትሰማለህ ከእሳት ጋር አትጫወት! እንደማለት ይፎክሩበትም እንደነበር የታወቀ ነው። በተመሳሳይ “የማህበረ ቅዱሳን” ጉዳይም ሆነ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ጊዜያዊ አለመረጋጋት “ደጀ-ሰላም” በመባል የሚታወቀው ጋጠ ወጥ መካነ ድር ዋቢ በማድረግ እንዲሁ “ነጩን አጥቁረን ማሩንም አምርረን ሲፊ ጊዜም ሰጥተን ደግመን ደጋግመን ያሻን ብንዘግብ እስቲ በእኛ ላይ/በጣቢያው/ ላይ አፉን የሚከፍትም ሆነ ጣቱን የሚሰድ ማን ሱሪ የታጠቀ ወንድ ነው” በሚል አንድምታ ከሆነ በእውነቱ ነገር መጪው ሰፊ ጊዜ ሱሪ የታጠቀ ማን እንደሆነ ፍርዱ ለሕዝቡ የምንተው ይሆናል በማለት ለዛሬ ጽሑፌን በምስጋና ልቋጭ።
ከጽሑፉ እውነተኛነትና ቀጥተኛነት የተነሳ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ/በብዕር ስም በጹሑፉ አዘጋጅ ላይ ለሚሰነዘረው ማንኛውም ዓይነት የዓይን ቅንድብ ማነቃነቅ የማይቻለውን ዘለፋና መሰረተ ቢስ አሉባልታ ጨምሮ ደቀ- መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥምና ሊመጣ ያለውን ልክና ገደብ ያለው ሁሉ እንደ አመጣጡ በጸጋ እንደሚቀበሉ ሲገልፁ በአክብሮት ነው። በዚህና ተጓዳኝ በሆኑ ርእሰ ጉዳዮች ጸሀፊው በየትኛውም መድረክ ሃሳባቸውንና ተሞክሮአቸውን ለማካፈል ለሚቀርብላቸው ጥሪ ዝግጅነታቸውን እየገለጹ አስቀድመውም ለማመስገን ይወዳሉ።
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
United States of America

13 comments:

 1. Who is Mulugeta WeldeGebriel?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል ማነው ለሚለው ጥያቄ?
   በአካል አላውቀውም ፤ ከሚያቀርባቸው ጽሁፎች ጽንሰ ሃሳብ በመነሳት ግን ፣ ስለ ግዙፍ አካሉም ባይሆን ስለ አስተሳሰቡ ጥቂት ማለት ይቻላል ፡፡

   መጀመሪያ ይኸን ስም ያነበብኩት በተለያዩ ድረ ገጾች አዜብ ለተባለ ሰው ደጋግሞ በሰጣቸው አስተያየቶች ነው ፡፡ በወቅቱ ለማንበብ የፈቀድኩትም ስለ ቀዳማዊ እመቤት የሚያትት ስለ መሰለኝ ነበር ፡፡ ኋላም ደግሞ የጻፈውን መጽሐፍ በማግኘቴ በማንበብ ስለ አመለካከቱ ለመረዳት ሞከርኩኝ ፡፡ በሁሎችም የሚያንጸባርቀው ብሶቶቹን ነው ፡፡ እነዚያ ምናምንቴዎች እንዴት እንዳጠቁት በዝርዝር አልገለጸም እንጅ በደል እንደተፈጸመበት በመጣጥፉ ሁሉ ያላስነካው ገጽ የለም ፡፡ ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነውና አልተበደልክም ማለት አልችልም ፡፡ ነገር ግን እንደዛ የተካረረ ደረጃ ስለምን ምክንያት ተደረሰ ነው የኔ ጥያቄ ? በእርግጥ የኢየሱስን ጌትነት መግለጽ ያሰወግዛል ወይስ ኢየሱስና ሰይጣን ቁማር ሲጫወቱ ተሸዋወዱ ማለት? ኢየሱስ የዓለም መድኀን ነው ብሎ መመስከር ወይስ አካሉ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንና ሃይማኖትን በአንዲት ዕድሜ በሚቆጠርላት ሴት መስሎ አሮጊት ማለቱ ? እያንዳንዱን ስለ ድንግል ማርያም ፣ ስለ ቅዱሳንና ጻድቃን ፣ ስለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና አምልኮአችን ያለውን ዝርዝር ልዩነታቸውን ሙሉ በሙሉ ጠንቅቄ መዘርዘር አልችልም ፡፡ መግባባት ያልቻሉባቸው ይህን የመሳሰሉ የእምነት አገላለጽ ግድፈቶችና ልዩነቶች ናቸው እንጅ አባቶች እንዳስተማሩት በሥርዓት ስላስተማሩ ወይም ኢየሱስን ስላመለኩ ብቻ አይደለም ፡፡

   ወንድም ሙሉጌታም በጻፈው መጽሐፍ እንኳን የተጠላበትን ፣ የተወገረበትን ፣ የተጠቃበትን ምክንያት ዝርዝር አድርጐ አላቀረበም ፡፡ በደፈናው በእሱ አባባል ማቅ ወይም ማሰ ቤተ ክርስቲያንን ይከፋፍላል ፤ እርስ በእርስ ያጣላናል ፤ አባቶችን ይዘልፋል …. ይላል፡፡ ባጠቃላዩ ከመጽሐፉ የተረዳሁት ፣ አንድ በግልጽ እኔ ነኝ ያላለ ኃይል ከጀርባው እንዳለና ፣ የድርጅታዊ አሠራር መገለጫ መሆኑን ነው ፡፡ ምክንያት ቢሉ በመጽሐፉ ውስጥ ለአስረጅነት ያቀረባቸው ናሙናዎች ምስክሮቼ ናቸው ፡፡ አንድ የኘሮቶኮል ቁጥርን የያዘ የመሥሪያ ቤት ደብዳቤ ፣ ዘመኑ ቢያበቃ እንኳን ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ለግለሰብ እንዲታደልና እንደ ተፈለገ መሉ በሙሉ እንዲገለገልበት አይፈቅድም ፡፡ ህጋዊ ማስረጃ ስለሆነ ለማንም ሳይተላለፍ በአግባቡ ተጠብቆ ይቀመጣል ፤ ዘመኑ ካበቃ በኋላም ለመማማሪያና ለመመራመሪያ ይሆን ዘንድ ለሁሉም ይገኝና ይፈተሽ ዘንድ ይፋ ሆኖ በታወቁ መጽሐፍት ቤቶች በጥብቅ ትእዛዝ ተራብቶ ይበተናል፡፡ ይኸ ሥርዓትና ደንብ ስላለ ፣ ከሥርዓት ውጭ የኘሮቶኮል ቁጥርና የግለሰቦች ፊርማ ያረፈበትን ጽሁፍ በግል ማግኘቱ ከበስተ ኋላው ሌላ ሥውር ኃይል እንዳለ ያሳብቃል ፡፡

   ሌላ የታዘብኩበት ሁኔታ ባለፈው ሰሞን በዚሁ ድረ ገጽ ላይ አንድ የማኀበረ ቅዱሳን አባል የሲአይኤ አባል መሆኑ ተረጋገጠ የሚል ዘገባ ይዞ መቅረቡ ነው ፡፡ ቢያንስ አንብቦ መረዳት የሚችለው ወገን ከእንደዚህ ከተሳሳተ ገለጻ ይድን እንደሁ እንጅ ፣ በስማ በለው የሚነዳውን ለማሳሳት ሞክሯል ፡፡ ያም ስለ ዲያቆን ሙሉጌታ ማንነት ትንሽ የምናውቅበት ሁለተኛው ማስረጃ ነው ፡፡

   በመጨረሻም ስለ ኢሳት የተሰማውን ቅሬታ ገልጿል ፤ ኢሳት ሁሉም እንደሚረዳው በምጥ የተገኘ የዜና አውታር ነው ፡፡ ዕድል ተነፍገው ያሉ ህዝቦች ድምጽ እንዲወጣ ፣ የተበደሉ ወገኖችን አቤቱታ ለማሰማት ፣ አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦችን የሚያስተዋውቅ ድርጅት ነው ፡፡ ለማቅ ወገናችሁ ብሎ ለመኰነን ቢያንስ ሃሳቡን በአካል ፣ ያ ካልሆነ ደግሞ በስልክና በደብዳቤ ለማቅረብና ለማሰማት እስከ መጨረሻ ተሄዶ ፣ ሳይሳካ ሲቀር ፣ ወደ ህዝብ ለማድረስ ሌላ አማራጮችን መጠቀሙ አግባብ ነው ፡፡ ኢሳትንም ለሁለትና ከሦስት ለመክፈል ያለመ ይመስል የተወሰኑ ሙያተኞችን ስም በመጥቀስ አሞጋግሷል ፡፡ ለእኔ ይህኛውም ከኋላው የሚያሠሩት አካሎች ዕቅድ ፣ አንድ ድርጅትን ለማዳከም የሚዘረጉት ወጥመድ አካል ነው ፡፡ በየትም ይሁን በምን ከማኀበረ ቅዱሳን ጋር ንክኪ ከፈጠርህ እንደ ዲያቆን ሙሉጌታ አስተሳሰብ ከሆነ ሃቅ ባይሆንም የምትወቀስ ነህና ተዘጋጅ ፡፡

   Delete
  2. “ስለ አስተሳሰቡ ጥቂት ማለት ይቻላል” ምን አለፋዎት አስተሳሰቡማ ከእኔና ከእርስዎ የላቀ ችሎታ ያለው ለመሆኑ ስራዎችሁ ምስክሮች ናቸው።
   “መጀመሪያ ይኸን ስም ያነበብኩት በተለያዩ ድረ ገጾች አዜብ ለተባለ ሰው ደጋግሞ በሰጣቸው አስተያየቶች ነው” እኔም እጅ በአፍ የሚያስጭን የወረኛ ቅስም የሚሰብርና አንጀት የሚያርስ የማያዳግም መልሳቸውን አንብባለሁ። ታድያ የመምህሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስራዎቻቸውን ትተው የአዜብ መጥቀስዎን ሰው ሊመዝኑ ወጥተው እራስዎ መመዘንዎ ሆኖ ተሰማኝ።
   “ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነውና አልተበደልክም ማለት አልችልም፡፡ ነገር ግን እንደዛ የተካረረ ደረጃ ስለምን ምክንያት ተደረሰ ነው የኔ ጥያቄ?” ዝርዝሩን በተመለከት ባለቤቱ ቢያስረዳዎት ነው የሚሻለው። ነገር ግን አንድ ያልገባኝ ነገር ሁሉን ነገር ማወቅ አለብኝ እውቅና ያገኝም ዘንድ በእኔ ማለፍ አለበት ባዩ እርስዎ ማን ኖት? እርግጠኛ ባልሆንም አድራሻዎትንና ማንኖትዎን ቢያውቅ ይህን ሳያደርግ አይቀርም ነበር። መምህሩ ከአያያዛቸውም ብዙም የሰው ጭብጨባ የሚፈልጉ አይደሉም።
   “ወንድም ሙሉጌታም በጻፈው መጽሐፍ እንኳን የተጠላበትን ፣ የተወገረበትን ፣ የተጠቃበትን ምክንያት ዝርዝር አድርጐ አላቀረበም፡፡” ከዚህ ቅደም በሶፍት ኮፒ የተለቀቀው ክፍል ሁለት በቃኝ እስኪሉ ድረስ ጽፈውታልና መጽሐፋቸውን ፈልገው ያንብቡ ያነበብን ስነነግሮት ደግሞ ድርቅ ከማለት ይልቅ ይስሙን።
   “ባጠቃላዩ ከመጽሐፉ የተረዳሁት ፣ አንድ በግልጽ እኔ ነኝ ያላለ ኃይል ከጀርባው እንዳለና ፣ የድርጅታዊ አሠራር መገለጫ መሆኑን ነው ፡፡” ይቅር ሌላ ተጨምሮ ብቻቸውም አልተቻሉም። የሚያቁት ድርጅት ካለ ደግሞ አይደብቁን!
   “ሌላ የታዘብኩበት ሁኔታ ባለፈው ሰሞን በዚሁ ድረ ገጽ ላይ አንድ የማኀበረ ቅዱሳን አባል የሲአይኤ አባል መሆኑ ተረጋገጠ የሚል ዘገባ ይዞ መቅረቡ ነው ፡፡ ቢያንስ አንብቦ መረዳት የሚችለው ወገን ከእንደዚህ ከተሳሳተ ገለጻ ይድን እንደሁ እንጅ ፣ በስማ በለው የሚነዳውን ለማሳሳት ሞክሯል ፡፡ ያም ስለ ዲያቆን ሙሉጌታ ማንነት ትንሽ የምናውቅበት ሁለተኛው ማስረጃ ነው፡፡”
   አሁን ነገር መጣ! “የምናውቅበት” አንድ ከቅንነት የተነሳ ሳያውቅ የሚያቀውን አየተናገረ ያለ መስለውኝ ነበር ለካ … ኖት! ልፋ ያለ መጫኛ ይጎትታል! እንዲህ ያለ ነገርማ ኩምትር ኩምትር ማድረግ የሚችሉበት ራሳቸው መምህሩ ናቸው። ይህን አስተያየት አንብበውም የሚሉትን አብረን እናነባለን።
   “በመጨረሻም ስለ ኢሳት የተሰማውን ቅሬታ ገልጿል ፤ ኢሳት ሁሉም እንደሚረዳው በምጥ የተገኘ የዜና አውታር ነው ፡፡ ዕድል ተነፍገው ያሉ ህዝቦች ድምጽ እንዲወጣ ፣ የተበደሉ ወገኖችን አቤቱታ ለማሰማት ፣ አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦችን የሚያስተዋውቅ ድርጅት ነው ፡፡” በደፈናው በዚህ አስተያየትዎን እስማማለሁ ባይሆን ግን “ለማቅ ወገናችሁ ብሎ ለመኰነን ቢያንስ ሃሳቡን በአካል ፣ ያ ካልሆነ ደግሞ በስልክና በደብዳቤ ለማቅረብና ለማሰማት እስከ መጨረሻ ተሄዶ ፣ ሳይሳካ ሲቀር ፣ ወደ ህዝብ ለማድረስ ሌላ አማራጮችን መጠቀሙ አግባብ ነው ፡” ያሉትን እኛ የምናውቀው ነገር የለም! ይህን ጽሑፍ በይፋ ከማውጣታቸው በፊት ለኢሳት ቴሌቪዥን ስልክ ይደውሉ አይደውሉ ደብዳቤ ይፃፉ አይፃፉ እርስዎ እንዴት ሊያውቁ ቻሉ? አስተያየት ሰጪው ከኢሳት ኖት እንዴ? ስለ ሕጋዊ ሰነዶች እያወሩ እርስዎ በመም ሙሉጌታና በኢሳት መካከል ቀድሞ የተካሄደ ሰጣ ገባ ነፋስ ካልሆኑ በስተቀር እንዴት ሊያቁ ቻሉ? ይህ ሁሉ አስተያየት ሰጪ መስለው የለቀለቁትን የቅናት የሚያስመስሉቦት ለካ የተወጉ ወገን ሆኖው ኖረዋል።
   “በየትም ይሁን በምን ከማኀበረ ቅዱሳን ጋር ንክኪ ከፈጠርህ እንደ ዲያቆን ሙሉጌታ አስተሳሰብ ከሆነ ሃቅ ባይሆንም የምትወቀስ ነህና ተዘጋጅ ፡፡” ሌባን ሌባ ማለት እንካን የመምህር ሙሉጌታ ግዴታ ብቻ ተደርጎ ባይወሰድ እኔም በአቅሜ የድርሻዬን አበረክታለሁ።
   ዘጭ ዘሊባኖስ

   Delete
 2. Dear Dn Mulugeta,

  Thank you so so much. This is also my quastion for ESAT. We love ESAT for alternative news and some information but please don't mention about MK. or try to mention news about MK from other sourses.

  Everyone knows currently MK's statege is goooon to distracted it is not like religous association.All the time read from MK sourses accusation, hatrate, how to kill your brother........ not how to returen to God.

  ESAT please don't interfer in such matters do your best as you started before. If you knows the aouthers of dejeselam tel to people.

  ReplyDelete
 3. In majority of your posts you explain the suffering of you due to MK. B/c of this it is difficult to believe what you write, since we couldn't identify whether the writing is real or it comes from revenging mind.I am so surprised in many occasions which people say MK,MK,MK... MK is the name of an association, MK can be deleted from associations list.But can you delete value,attitude,thinking... of persons? Try to focus on changing persons mind rather than focusing on association. you have to know I am orthodox christian, but not member of MK.It is difficult for us to learn from Deje selam,Aba selama & Awude mihiret. All are the same in their content of writing.Insulting people, association etc.As to me you all are "Ashebari" for the believers. please go & observe other sites like Daniel Kibret views. He focuses on changing person's mind. I feel peace when I visit his site rather than this. Really You don't believe in God since your mind is obsessed with MK, MK, MK.

  ReplyDelete
 4. ይድረስ ለኢሳት:

  አዎ! እውነት ነው ዲያቆን ሙሉጌታ በጥልቀት እንዳብራራው እኔም በዚህ ሚዛናዊነት በጎደለውና መረጃ ቢስ በሆነው ዘገባችሁ እጅግ ካዘኑት ዋና ደንበኞቻችሁ መካከል አንዷ ነኝ:: ሊሞት እያጣጣረ ያለን ያገር ነቀርሳ መልሶ እንዲያገግም ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለማድረግ የተነሳችሁ ነው ያስመሰለባችሁ:: እዚህ ላይ የማንንም መብት አታክብሩ አይደለም:: ወይም አታስተናግዱ አይደለም እያልኩ ያለሁት:: ማን ምን እየሠራ ነው? እየሄደበት ያለው መንገድስ (በሃይማኖት ስም) ለሃገርና ለወገንስ ዘለቄታ ጥቅም አለው ወይ? ሌላውስ ወገን ምን እያለ ነው? ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች በቅድሚያ ተገቢ መልስ መሰጠት የለባቸውምን?? ይህን የመሰለ ነገር ስታቀርቡ ሰፊ የሆነው ታዳሚያችሁ ላይስ ምን ዓይነት ስሜት ያስከትል ይሆን የሚል አስተማማኝ የሆነ ሙያዊ መልስ አግኝታችሁበትና ተስማምታችሁበት ነውን?

  ወገኖቼ! እንደ እኔ ሃሳብ ምንም እንኳ ለመተቸት ሁላችንም ብርቱዎች ብንሆንም እጅግ ታላቅ የሆነው አገርን የመታደግ ዓላማችሁ እንዳይሰለብ እጅግ ጥንቃቄ ብታደርጉ ለማት ነውና ጆሮአችሁን አንቅታችሁ ስሙ :: ሁላችንም ብንሆን ያገራችንን ትንሳኤ ነውና የምንናፍቀው እንደማመጥና እንተራረም??????
  'ትንሿ እርሾ ትልቁን ሊጥ ልታቦካ ትችላለች' የሚለው የጌታ ትምህርት ትዝ ይበላችሁና በመረጃ ላይ የተመሠረተና ሚዛናዊነትን የጠበቀ ሥራ ለመሥራት ቢሞከር መልካም ነው በማለት የዲያቆኑን የጠለቀ አስተያየት እጋራለሁ::

  የምህረት አምላክ የሆነው እግዚአብሔር
  የብርሃን መልአክ ከሚመስል ጠላት ይጠብቀን::
  አሜን::

  ዲይቆን ሙሉጌታን ግን እጅግ በርታ 'እውነትን በፍቅር ለመግለጥ' አትቦዝን እናንተን ከመሰሉ ልጆቿ አገሪቱ ብዙ ትጠብቃለችና ማለት እወዳለሁ::

  ሰላም ሁኑልኝ

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 5. ጉድ ሳይሰማ አይታደርም!!እኔ የምለው ይህ ምነው እሳት ሆኖ ማቃጠል ጀመረ ደግሞ?ስለማህበረ ቅዱሳን ምንአገባው?ምናለ የማያውቀው ውስጥ ባይገባ?በዚህ የነፈሩ የተቀቀሉ የተጠበሱ አሉና ለምን ቁስላችንን ትነካኩታላችሁ ይህን መዘገብ ከፈለጋችሁእየተባሉ በማህበረ ቅዱሳን ምክንያት ከሀገር የተሰደዱትንም ቀርባችሁ መጠየቅ ነው!አይመስላችሁም?አለበለዚያ ያንንም ይህንንም አትነካኩ!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 6. “በመጨረሻም ስለ ኢሳት የተሰማውን ቅሬታ ገልጿል ፤ ኢሳት ሁሉም እንደሚረዳው በምጥ የተገኘ የዜና አውታር ነው ፡፡ ዕድል ተነፍገው ያሉ ህዝቦች ድምጽ እንዲወጣ ፣ የተበደሉ ወገኖችን አቤቱታ ለማሰማት ፣ አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦችን የሚያስተዋውቅ ድርጅት ነው ፡፡” በደፈናው በዚህ አስተያየትዎን እስማማለሁ ባይሆን ግን “ለማቅ ወገናችሁ ብሎ ለመኰነን ቢያንስ ሃሳቡን በአካል ፣ ያ ካልሆነ ደግሞ በስልክና በደብዳቤ ለማቅረብና ለማሰማት እስከ መጨረሻ ተሄዶ ፣ ሳይሳካ ሲቀር ፣ ወደ ህዝብ ለማድረስ ሌላ አማራጮችን መጠቀሙ አግባብ ነው ፡”

  ያሉትን እኛ የምናውቀው ነገር የለም! ይህን ጽሑፍ በይፋ ከማውጣታቸው በፊት ለኢሳት ቴሌቪዥን ስልክ ይደውሉ አይደውሉ ደብዳቤ ይፃፉ አይፃፉ እርስዎ እንዴት ሊያውቁ ቻሉ? አስተያየት ሰጪው ከኢሳት ኖት እንዴ? ስለ ሕጋዊ ሰነዶች እያወሩ እርስዎ በመም ሙሉጌታና በኢሳት መካከል ቀድሞ የተካሄደ ሰጣ ገባ ነፋስ ካልሆኑ በስተቀር እንዴት ሊያቁ ቻሉ? ይህ ሁሉ አስተያየት ሰጪ መስለው የለቀለቁትን የቅናት የሚያስመስሉቦት ለካ የተወጉ ወገን ሆኖው ኖረዋል።

  ReplyDelete
 7. ወያኔ ማህበረ ቅዱሳንን( ሰለፌን ) ይጠላል
  ማህበረቅዱሳን ደግሞ ኢየሱሳዉያንን ያሳድዳሉ
  ኢሳት ደግሞ ወያኔን ይጠላል ስለዚህ ወያኔን ለመጥላት ማህበረሰይጣንን መውደድ አለበት ምክንያቱም መህበሩን ከጠላ ወያኔን የደገፈ ስለሚመስለው። የሚገርመው ግን ለኢየሱስ ቦታ ማጣት! ይች ናት ጨዋታ

  ReplyDelete
 8. Please post it, and once again please post it.

  You the so called mulugeta, you are an opportunist like a hyena. You are thoughtless like a donkey. You are shameless like a goat.
  A big failure, sooner or later, trying to connect MK (in my view, who have nothing hidden agenda other than serving the true church) with ESAT so that EPRDF put them behind bars. But, EPRDF is more clever than you, an opportunist. EPRDF truly knows MK, but the interest of EPRDF is not in the way you think of MK rather it's a different one.
  Don't waste your time. I am not a member of MK but an EPRDF member who have a close eye on MK. BZW, what have you done for the church or the country other than waging wars of words and animosity, sometimes in religious websites, sometimes in political websites. Count your day, it will come soon!!!

  About ESAT - I don't care what it is and for what it talks about as far as we are able to halt it at home.
  About mulugeta: he is a protestant (formerly a tehadiso), otherwise how come that his views are top flights in anti orthodox blogs like, aba selama, deje birhan, awide mihiret, deje selaam etc.

  ReplyDelete
 9. ከማህበሩ ላይ እጃችሁን አንሱ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህን ለማድረግ፤ ማህበሩ ከእኔ ቤተ ክ/ን አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነቱ ላይ እጁን ያንሳ !!

   Delete
  2. ይህን ለማድረግ፤ ማህበሩ ከእኔ ቤተ ክ/ን አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነቱ ላይ እጁን ያንሳ !!

   Delete