Monday, May 21, 2012

ተወጋዦች አውጋዦች፣ አውጋዦች ተወጋዦች የሆኑባት ቤተክርስቲያን

ውግዘት ከእውነተኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርትና በእርሱ ላይ ከተመሰረተው እውነተኛ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ በተቃራኒ የቆመን የቤተክርስቲያን አባል (አገልጋይ/ምእመን) ቤተክርስቲያን መክራና ዘክራ አልመለስም ብሎ አቋሙን በግልጽ ሲያሳውቅና በእንቢተኛነቱ ሲጸና መጨረሻ ላይ ቤተክርስቲያን ያን አባሏን ከአንድነቷ ለመለየት የምትወስደው እርምጃ ነው። ይህም ሲሆን ቤተክርስቲያን ቅድሚያ የምትሰጠው ለውግዘት ሳይሆን አባሏን በንስሃ ለመመለስ ነው። ሁሉንም አማራጮች ተጠቅማና ሊያስወቅሳት የማይችለውን እድል ሰጥታ አባሏ አልመለስ ብሎ በኑፋቄው/በክህደቱ ሲጸና እያዘነች የምታስተላለፈው የከበረ ውሳኔዋ ነው። በዚህ መንገድ የተላለፈ ውግዘት ተቀባይነት አለው። ከዚህ ውጪ በቂም በቀል፣ በጥላቻ፣ አንዱን ወገን አስደስቶ ሌላውን ለመጉዳት የሚደረግ ውግዘት ግን ተቀባይነት የለውም። የማቅና እርሱ አእምሮአቸውን የተቆጣጠረው ጳጳሳት እንዱ ችግር ውግዘት ምን እንደሆነና በምን ምክንያት እንደሚተላለፍ አለማወቃቸው ነው። ውግዘት ለእነርሱ ቂምን መወጫ፣ ጠላትን ማጥቂያ መሣሪያ ነው።
ውግዘት እጅግ የተራከሰባት ቤተክርስቲያን ብትኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ናት። በገጠር ቀሳውስቱ በትንሽ በትልቁ «ገዝቼሃለሁ» እያሉ አርሶአደሩን ሲያስፈራሩ ነው የኖሩት። ዋና ምክንያታቸው ደግሞ በበአል አረስክ፤ ቆፈርክ ነው። ሊያስወግዝ በሚችል ለምሳሌ ጠንቋይ ቤት ቢሄድ ግን ቃልም አይናገሩትም። እነርሱም ወደዚያው ጎራ ማለታቸው አይቀርምና። ይኸው በትንሽ በትልቁ፣ በሆነው ባልሆነው የማውገዝ ልማድ ስር በመስደዱ ፈጽሞ ሊያስወግዝ በማይገባ ምክንያት ማውገዝ ስልጣን በሌላቸው አካላት ሁሉ ሲተላለፍ ነው የኖረው። በተለይም በየአጥቢያ ቤተክርስቲያን ብዙዎች የቤተክርስቲያን ልጆች «ተወግዘሃል» የተባሉት፣ ተገኘባቸው ስለተባለው የሃይማኖት ሕጸጽ ተጠርተው ሳይጠየቁና ምላሽ ሳይሰጡ፣ ሳይከራከሩና ሳይረቱ፣ ስሕተታቸው በሚገባ ሳይነገራቸውና ሳይቀበሉት፣ በማኅበረ ቅዱሳን ከሳሽነት ብቻ «ተወግዘሃል» ይባላሉ። ማኅበረ ቅዱሳንም የሚወገዙ ሰዎችን ሰልሎ ማቅረብን እንደጽድቅ ነው የሚቆጥረው። እንዲህ ባለ ግብር እነሆ 20 ዓመታትን አስቆጠረ እኮ።
ባለፉት 20 ዓመታት ተወግዘው የተባረሩ ሁሉ በሕጋዊ አካል ተወግዘው የተባረሩ አይደሉም። በህገወጦችና በማያስወግዝ ምክንያት በህገወጥ መንገድ «የተወገዙ» ናቸው። የህግ የበላይነት ባልሰፈነባትና ሁሉም አዛዥ በሆነባት ቤተክርስቲያን ውስጥ መወገዝ የሚገባቸው ሰዎች መወገዝ የማይገባቸውን ሰዎች ሲያወግዙ ኖረዋል። ይኸው አሰራር አሁንም ቀጥሏል። ቤተክርስቲያኗ ምን ያህል እንደዘቀጠች፣ ምን ያህል አንቱ የሚባል ሰው እንደታጣባት፣ ምን ያህል ከክርስቶስና ከሐዋርያት፣ እንዲሁም ከሰለስቱ ምእት ትምህርት እንደራቀች ያሳያል። ወደዚህ ደረጃ እየወረደች የመጣችው፣ ጳጳሳትን በሃይማኖታዊ ዕውቀት ብቁነታቸውን፣ በመንፈሳዊነት ኑሯቸውን መዝና መሾም ካቆመችበት ዘመን አንስቶ ነው። የዛሬዎቹ እነአባ አብርሃም «የራጉኤልን ፎቅ ሰሩ» ተብለው የተሾሙ ዕለት ጵጵስና እጅግ መውረዱን ገምተን ነበር። እንደገመትነውም ይኸው ለተቀመጡበት መንበረ ጵጵስና በማይመጥን አኳዃን በማኅበረ ቅዱሳን ጭንቅላት እያሰቡ ማኅበሩ «እነእገሌን እንድታወግዙ» ሲል የሰጣቸውን ተልእኮ ለመፈጸም የሲኖዶሱን ስበሰባ ሲያውኩ ዋሉ።
ለመሆኑ የቅባት እምነት ተከታይ የሆኑትና ከትምህርተ ቤት በቅባትነታቸው ተባረው የነበሩት፣ ከቅባት ባህለ ትምህርት ያልወጡት አባ አብርሃም፣ ራሳቸውን በደብተራ ስራ በርቀት (በግዘፍ አይደለም) «ጃንደረባ» አድርገው የቆዩትና አዲስ አበባ ከመጡ በኋላ የአዲስ አበባ ጥቂት የማይባሉ መነኮሳት እንደ ሕጉ ከሴት ርቀው ንጽሕ ጠብቀው የማይኖሩ መሆናቸውን ሲገነዘቡ፣ ያን በርቀት ጃንደረባ ያደረጋቸውን ደብተራ ካለበት አስመጥተውና ዳጎስ ያለ ብር ከፍለው ያሰረውን እንዲፈታ አድርገው ከጃንደረባነት ወደ … መሸጋገራቸውን ድፍን የራጉኤል ቤተክርስቲያን ካህናት የሚያወራው እውነት ነው። ስሟን ለጊዜው መጥቀስ ከማያስፈልግ አንዲት ሴት ጋር ስለነበራቸው ግንኙነትም ቢጠየቁም የሚናገሩት ብዙ ምሰጢር አለ። ሙት ወቃሽ አያድርገንና በአጭሩ ከተቀጩት ከሟቹ አቡነ መልከጼዴቅ ጋርም ከዚህች «ቆብ አስጥል» ሴት ጋር ጦርነት ውስጥ ገብተው እንደነበርም አክለው መናገራቸው አይቀርም- ካህናቱ። ውግዘት ካስፈለገ ይህ የእምነትም የምግባርም ጉድለት አባ አብርሃምን ባስወገዛቸው ነበር። ከላይ እንደተገለጸው ግን ቤተክርስቲያናችን መወገዝ ያለባቸው አውጋዦች የሚሆኑባት የፍርደገምድሎች፣ የህሊናቢሶች መናኸሪያ ሆናለች።
አባ አብርሃም ማህበረ ቅዱሳን የከሰሳቸውን የቤተክርስቲያን ልጆች «እነርሱን ምን ማነጋገር ያስፈልጋል ማውገዝ ነው» ለማለት ያስደፈራቸው ምን ይሆን? ብለን ብንጠይቅ መልሱ አለመማራቸውና የሃይማኖት ሰው አለመሆናቸው ነው። እነዚህ ሰዎች ቀርበው ቢጠየቁ አባ አብርሃም አጥጋቢ ምላሽ የላቸውም። ዘለው ውግዘት ላይ ፊጥ እንበል የሚሉት መልስ ስለሌላቸው እንደሆነ ይታወቃል። መምህር ጽጌ ስጦታው በይነጋል እንዳስነበበን መምህር ግርማ በቀለና እርሱ የሲኖዶሱን አባላት ምን ያህል እንደተፈታተኗቸው አይዘነጋም። በክርክር እነጽጌ የረቱ ቢሆንም ለጳጳሳቱ ክብር ሲባል ግን ጥፋተኛ ባልሆኑበት ጉዳይ ላይ ጥፋተኛ ተብለው ቀኖና እንዲሰጣቸው ተደርጎ እንደነበር አይረሳም። ዛሬም እንዲወገዙ ማኅበሩ ያቀረባቸውን የቤተክርስቲያን ልጆች አቅርቦ ማነጋገር ያን ታሪክ መድገም ስለሆነ እነ አባ አብርሃም ፈጽሞ አይፈልጉትም።
መቼም የተማረ ሰው ያመዛዝናል። የሃይማኖት ሰውም በሌላው ላይ ከመፍረዱ በፊት ወደራሱ ይመለከታል። እግዚአብሔርንም ስለሚፈራ ፍርዱ ቅን መሆኑን ደጋግሞ ያረጋግጣል። ከዚህ ውጪ የሆነ ሰው ግን ለምንም ነገር ግድ ስለሌለው እንደፈለገው «ያዘው» «ቁረጠው» አይነት ፍርድ ይፈርዳል።
ስርአተ ቤተክርስቲያንን ባልተከተለና ህግን ባልጠበቀ መንገድ ይወገዙ የተባሉት ሰዎች ኃጢአት ከቶ ምን ይሆን? የሁሉም ጉዳይ ቢጨመቅ የሚወጣው በመጽሐፍ ቅዱስ እንመራ። መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን ትምህርትም ሆነ ስርአት ካለን በመጽሐፍ ቅዱስ እናስተካክለውና እግዚአብሔርን ብቻ እያመለክን እንኑር። ስለእኛ ኃጢአት በሞተው በክርስቶስ ኢየሱስ እንጂ መዳን በሌላ በማንም የለም ነው ያሉት። ይህ ያስወግዛል? ይህ እውነተኛ ሃይማኖት አይደለም? ይህን መቃረንስ ክህደትና መናፍቅነት አይደለም? መጽሐፍ ቅዱስ ያወገዛቸው እነማንን ነው? በወንጌል ከተሰበከው ውጪ ሌላ አዲስ ትምህርት የሚከተሉትን እኮ ነው? «በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ። ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።» (ገላትያ 1፡6-9)። ታዲያ ማነው ሐዋርያት ካስተማሩት ወንጌል የተለየ ወንጌል የሰበከው? ይወገዙ የተባሉት የቤተክርስቲያን ልጆች ወይስ ማኅበረ ቅዱሳን?  ስለዚህ ይህ ታይቶ ከሐዋርያት ትምህርት ያፈነገጠውና መመለስ ያልፈለገው ነው መወገዝ ያለበት።
ከውግዘት በቀር አፉ ላይ ሌላ ቃል የማይመጣለት ማቅ የሚታወቀው ኢየሱስ ክርስቶስን በመጥላት ነው። ኢየሱስን ስለማይወደው ነው ስለእርሱ ሲሰበክ የሚበሳጨው። ስለእርሱ ከመስበክም ተረታተረት ሲነግረን ነው የኖረው። ታዲያ ከዚህ የከፋ ክህደት ምን አለ? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እኮ በመልእክቱ «ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን።» ብሏል። (1ቆሮንቶስ 16፡22)። በቅዳሴ ላይ መልእክተ ጳውሎስ ከመነበቡ በፊት የሚታወጀውም ይኸው ሀዋርያዊ ቃለ ግዝት ነው። ቤተክርስቲያናችን እንደማቅ ያሉትንና መወገዝ የሚገባቸውን ፀረ ወንጌልና ፀረ ክርስቶስ ሃይላትን እየተንከባከበች፣ አጋንንታዊ ትምህርታቸውንም ሳትቃወም ተቀብላ መኖሯ ሳያንስ፣ በትምህርት ወልዳ አሳድጋ ለቁም ነገር ያበቃቻቸውንና ወንጌል ይሰብኩልኛል፤ ልጆቼን ያሳርፉልኛል ብላ ተስፋ የጣለችባቸውን እውነተኛ ልጆቿን አውግዢ ስትባል «እንዲህማ አይሆንም» የሚል አቅም ማጣቷ ክርስቶስን ከሚጠሉ ጋር መተባበሯን ያሳያል።             
እግዚአብሔር የሰውን መዳን እንጂ መጥፋቱን አይወድም። የክርስቶስ ልብ ያላት ቤተክርስቲያንም በዚህ ምድር ያለችው ሰው እንዳይጠፋና እንዲድን ነው። ማቅ ግን ሃይማኖተኛ ስላልሆነ ማንም ወጣ ማንም ገባ ጉዳዩ አይደለም። ክርስቶስ የሞተለት አንድ ሰው ቢጠፋ ደስ ይለዋል እንጂ መመለሱን ፈጽሞ አይፈልግም። ያ ሰው እንዲወገዝ እንጂ ተመክሮ እንዲመለስ እንኳን ፈቃደኝነት የለውም። አሁን እነዚህ ይወገዙ የተባሉ ሰዎች “አታውግዙን እንመለሳለን” ቢሉ እንኳን ማቅ ሊመለሱ አይገባም እንደሚል ምንም አየጠራጥርም። ስለዚህ እርሱ በተሀድሶነት የጠረጠረው ሁሉ ተወግዞ እንስኪወገድ ድረስ እረፍት የለውም። እርሱ የጠረጠራቸው እስከሆኑ ድረስ የሞቱም ቢሆኑ እንኳ አጽማቸው መወገዝ አለበት እንጂ ያለውግዘት ዝም ሊባሉ አይገባም። እንዲህ ካለ ማኅበር ጎን ተሰልፎ ክርስቶስን የሰበኩትን ማውገዝ በየትኛው መንፈሳዊ ህግ ይደገፍ ይሆን?
አሁን ለውግዘት ከቀረቡት አንዳንዶቹ ከዚህ ቀደም በማቅ ሰላይነት በህገወጥ መንገድ ተገፍተው ከቤተክርስቲያን የተባረሩ ናቸው። ሁሉንም ለዚህ የዳረጋቸው ማቅ ነው። የተለያዩ መጻህፍት እንዲጽፉ ያደረጋቸውም በማቅ ተገፍተው ከእናት ቤተክርስቲያናቸው መባረራቸው ነው። መጻህፍቶቻቸው በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ያሳደሩት ተጽእኖ ግን ቀላል የሚባል አይደለም። ለብዙዎች ወደወንጌል እውነት መምጣት ምክንያት ሆነዋል። ቤተክርስቲያን ሳትወድ በግድ ገድላትና ድርሳናትን እንድታርም አስገድደዋታል።
አይሁድ ክርስቶስን ሰቅለው ከገደሉት በኋላ ይነሳል ብለው ሰግተው ነበርና መቃብሩን በወታደሮች አስጠብቀዋል። ነገር ግን ማቅና ተባባሪዎቻቸው የነበሩ የደብር ባለስልጣናትና አንዳንድ ጳጳሳት ያን ጊዜ እነዚህ ዛሬ ይወገዙ የተባሉ ሰዎች አንዳች ነገር ያመጣሉ ብለው አልገመቱምና ንቀዋቸው ነበር። የሆነው ግን ከሚገመተው በላይ ነው። ይኸው ዛሬ እንኳን የእነርሱ ነገር ራስ ምታት ሆኖበቸው ህጋዊ መሰረት ባይኖረውም ውግዘቱን ህጋዊ ለማድረግ እየተራወጡ ይገኛሉ። እንዳሰቡት እነዚህ ሰዎች አሁን ቢወገዙ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ማቅም ሆነ እርሱ የሚመራቸው ጳጳሳት አሁንም እንኳን የተገነዘቡት አይመስልም። እነዚህን ስማቸውን በሕዝቡ ውስጥ የተከሉ ሰዎችን ማውገዝ ለቤተክርስቲያን መፍትሔ አያመጣም። በያዙት መንገድ ይበልጥ እንዲገፉበት ያደርጋል። በዚህ አገልግሎት እንዲጠመዱ ያደረጋቸው የማቅ ተራ ውግዘት መሆኑ ፈጽሞ መዘንጋት የለበትም። በእርግጠኛነት ማቅ ገፋፍቶ ገፋፍቶ ባያስወጣቸው ኖሮ፣ ምናልባት የተረዱትን የወንጌል እውነት ላገኙት ሰው በቃል ከማስተላለፍ ባለፈ ደፍረው እውነቱን አፍረጥርጠው ባልጻፉትም ነበር። ስለዚህ እነዚህን ሰዎች በማውገዝ ቤተክርስቲያን ታገኛለች ተብሎ ከሚታሰበው ጥቅም ይልቅ የሚደርስባት ጉዳት እንደሚያመዝን መታወቅ አለበት። ውግዘት በማቅ ዘንድ እውቅናን መንፈግ ተደርጎ ቢወሰድም፣ እውነታው ግን ለዚያ ሰው እውቅናን መስጠት ነው።

በስሜትና በጥላቻ ለማውገዝ ከመራወጥ ይልቅ እነዚህን ሁሉ ጉዳዮች በጥሞና መፈተሹ ለቤተክርስቲያን ይበጃል። ለነገሩ በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ላይ በመረጃ የተደገፈ ገበናቸው መገለጡ አበሳጭቷቸውና በስሜት ተነድተው «የጋዜጣው አዘጋጆች መወገዝ አለባቸው» ካሉ የዘመናችን ጳጳሳት ምን ይጠበቃል? አባቶች ሆይ እባካችሁ ማኅበረ ቅዱሳንን ለማስደስት ብላችሁ ሳይሆን፣ ለቤተክርስቲያን የሚበጀውን ውሳኔ ወስኑ። እናንተም አንድ ቀን የሁላችን ዳኛ በሆነው በአለቃችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት እንደምትቆሙና በምትፈርዱበት ፍርድ  እንደሚፈረድባችሁ አትዘንጉ።

4 comments:

 1. mewegz alemwegz aydelem wanaw guday. bergt mk mulu orthodoxawi yehonu wendemochen enkuan yawegezebet geze neberena.wanaw gudaye. .mk lemen bezu degafi afera? enen chemro endegfewalen.b/c .1. kewste gemro wede wuchi yemiy new.tehdsowoch gen kewch gemrew wede weste yemiyayu nachew.lemsale NEBURE ID ARMIAS KEBEDE BETMHRTACHEW KENANTE GAR BETEWSENE DEREGA YEMESASELALU GEN BEZU SEWOCH WEBSITACHEWN ENDE AND TEWAHDOWI KOTRO YEKETATELEWAL LEMEN?KEWESTE GEMREW WEDE WUCH YAYALU.ENANTE GEN HULGEZE YETEWAHDO MESAHFT TERET YEMOLABACHEW YEMSLOCHHOAL END MESHAFE MISTER YALU YESENEMELEKOT MESAHFT BETEWAHDO YEMIDERSU AYMESAYEMSLACHIHUM.TEWAHDO SELE AND TARIK BETNAGER, TATLALACHIHU YEWCH SEWOCH SINAGERU EWNET NEW TLALACHIHU.LEMSALE TEWAHDO BEMHALEY SOLOMON LAY ERGEBE ANDIT NAT YETEBALECHIW MARYAM NAT SETELE YEHE YETEWAHDO TERET YETELETEFE TRGUM NEW TLALACHIHU. CATHOLICAWYAN GEN YEHNENU HASSAB BINEGRUACHIHU BIANS BATEDGFUT ATATATLUTEM.TEWAHDOWYAN YEMESLUACHEWN MESALEWOCH TATLALACIHU,YANENU MESALE LELAW KERTO BEHT ABYATE KIRSTIANAT BETSEMUT GEN KEBDET TSETULACHIHU.MK GEN LELAW KERTO ANGET YEMISDEFUN MESAHFT MEKAKEL ENDE MESEHAFE ZIK YALUTEN ENKUA MESTEKAKEL ENDALEBACHEW EYAWEKEM BETENEKAKE YEMEREMRACHAL ENJI YETFU BELO LESAT AYEZEGACHEWEM.KENANTE YELEK PROTSTANTU BELEHU DESSALEGH TESHLO SELETMEHRTE HAYMANOTACHIN MIZANAWI TENTANE BEHULET MESHAFTU SETTOAL.ENANTE GEN ALLEGORICAL TREGUAME ENKUAN BIHON PROTESTANTOCH KASSEDEKUT TATSEDKALACHIHU. ANCIENT ABATOCHEN MESEHFTEN KE ENGLISH WEDE AMRHARIC EYEMELESE YEMISNEBBEN ENKUAN MK NEW.2. CHIKUL NACHIHU.LEMESALE AUROPAWYAN BAHUNUGEZE LEDERESEBACHEW HAYMANOTAWI WEDKET MESERTU CHIKULE MEHONACHEW NEW.PROTESTANTWI DOGMAN TEKEBLEW GEN TENTAWIWUN SERAT SAYTLU MEKETEL YITCHLU NEBER.BEWKTU GEN ASSABACHEW CATHOLIKAWYANEN MEMAREK BICH SILHONE NAKUT .BEMECHERESHA LEZIH AYNET YEAMLKO SERAT ALBEGHNET DERESU.MK GEN LELA KERTO BEORGAN YEMIZEMERU YAREDAWI ZEMAWOCHIN ENKUAN TEKAWMOAL MIKNYATUM YERUKUN ASSEBOALENA.YEHEM CHKUL ALEMHONUN BEMZMURAT MEMSET KESSE BLO YEMIMTA MEHONUN BEORGAN MEZEMERU GEN BEHIDET LELA TATA YAMTAL BELO NEW. YEKOYEN/////////

  ReplyDelete
 2. ሓጢያት ሠሪውን አያድንም!!!

  ወገኖች ጌታ በህያው ቃሉ እንዳስቀመጠልን 'ልትድኑ ብቻ ሳይሆን ስለስሙ መክራም ልትቀበሉ እንጂ' ስለሚል አጋንንት አጋንንትን ያወግዛል ብላችሁ አትጠብቁ:: ይልቁንም ጌታን እራሱን በክፉ ሰው ተጠቅሞ ብኤልዜቡል አለበት ያስባለ እናንተንማ እንዴት???

  ስለዚህ ከማቅ እና አጋሮቹ ከሆኑት ከነ አባ አብርሃም የጽድቅ ፍርድ ወይም ክፉውን የማውገዝ ሥራ መጠበቅ ሊያርድና ሊሰርቅ ከመጣው ሌባ ምህረትን ወይም ቸርነትን መጠበቅ ነው የሚሆነውና ከዚህ ይልቅ እጅግ የሚሻለውና ቃሉም የሚደግፈን ሁሉን ወደ ሚችለው አምላካችን (ማድረግ ያለብንን ሥራ ሳንዘነጋ) እንደ ቃሉ አጥብቀን ለዚህ እረኛ ላጣ የቤተ ክርስቲያናችን ምእመንና ጠቅላላ አገራችን ማልቀስ ነውና ሁላችንም በዚህ እንበርታ::

  በእውነት እራሳችንን በእግሮቹ ስር አዋርደን ያባቶቻችን የአብርሃም የይሳቅና የያእቆብ አምላክ ወዴት ነህ? በማለትና እንደ ቃሉ በቃሉ በመያዝ ይህን ይዋሽ ዘንድ ሰው ያልሆነውን የድሃ አደግ አባት አጥብቀን መጠየቅ ነው ያለብንና በዚህ እንበርታ:: አንድ ቀን ጣቶቹ 'ማኔል ቴቄል ፋሪስ' በማለት በአመጸኛው ላይ ትጽፋለችና:: የተስፋ ቃሉን የሰጠ ደግሞ የታመነ ነው:: ደግሞም 'ለመንጋው የማይራሩ እንደሚመጡ' አንዘንጋ::

  ከዚህ በተረፈ ይህን እረኛ የሌለውን መንጋ በቃሉ ኃይልና ስልጣን ወደ እውነተኛው የበጎች እረኛ ለመመለስ የወንጌሉ ትምህርት በሁሉም መልክ ይጧጧፍ ይንደድ:: እያንዳንዳችንን ከነበርንበት ድቅድቅ ጨለማ አውጥቶ በጌታ ብርሃን ውስጥ እንድንሆን ያደረገን ይሄው የወንጌሉ ቃል ነውና::

  ስለዚህ ሰይጣን ሰይጣንን እንዲያወግዝ መጠበቁ ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውና ይስተካከል???

  ቤተ ክርስቲያኒቱን እግዚአብሔር ያስባት!!! አሜን::

  ለማቅ አባላትና ለአንዳንድ ጉዳይ አስፈጻሚ ጸለምተኛ ጳጳሳቱ ማስተዋል ይብዛላቸው!!

  ሰላም ሁኑልኝ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 3. እውነት እናወራ ከተባለ መወገዝ የሚገባው ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ እስከዛሬ የጻፈቸውና ሕዝብን እንዲሳሳቱ ያደረገባቸውን ጽሑፎች ብንመለከት ምን ያህል ጸረ ወንጌል ጽሑፎች እንደነበሩ ለመረዳት ይቻላል፡፡ እርሱ ሳይወገዝ ሌላውን ለማውገዝ መሞከር መጽሐፍ ቅዱሳዊም መንፈሳዊም አይደለም፡፡
  ወልደ አቡዬ ነኝ

  ReplyDelete
 4. To all who write and read this!

  I have 5 questions which you must answer first
  1) Do you accept the the saints and matryts of teh church? Do you beleive taht the saint virhgin marry is the way to life?
  2)Are you planning to introduce what you belive to the church or you are fighting to preserve what the church beleives in?
  3) How do you see yours' ralation with othewr churches like the protestants? Do you beleive that they are in the wrong way? or you favour some or all of thier teachings?
  4) How do evlauate your teaching intermes of the oriental orthodoc chrches? Is the EOTC unique from this? If so, you can rais those differences
  5) What is your final goal? r u sure you are serving purely the Jesus crist?

  Give me answer to this questions... Please bothers you are not in the right way... lemein besew imnet wust gebtachihu tekebekleun tilalachu... tewegezu sibal yagna new tikikil tilalachihu... beyetignaw mesferet. yeinate astemhiro tikikil bihonim ye EOTC zare kemitamnew keleteleye yerasachihun imnet bebetachu indatakenawunuyekelekelachu yelem beyifa rasachun leyitachu astemiru... yane yemikebelachu ketegegna beka... keza wuchi kidusanin, agegay papasatn, kahinatin iyawaredachu yekirstos misrkroch nen sitilu.. ire bakachihu... kirstos inkuan tesadbo sewn asazino ayawkim... legenzeb kehone imebrhanin belela sira yishala. lebnet yishalal bcs leba yesigan bicha new yemiserkew inate gin legenzeb bilachu nebs kalserekin tilalachu.... ire tinish betam tinish libona yistachu... begid.... yehualawun isat asibut... agiz tebyew wenbede asela lay min sertio inde hede inena isu inawkalen... behudade wetet tetito kidase mekedesun isuna inenen yemeinawkew... begid iko yazezew yelem yeneger aklu sitefabet gin beka....

  ReplyDelete