Wednesday, May 23, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ በታሪክ ፊት ተጠያቂ የሚሆንበትን ስህተት ፈጸመ

ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት
 • ውሳኔው አባ ሰረቀ ብርሃንና ዲ/ን በጋሻውን አይመለከትም
 • ማቅ ከሰንበት ማደራጃ ውጭ ሆኗል
 • የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመትንም በሐምሌ ሲሰባሰቡ እንደሚፈጸም ታውቋል፡፡
ማህበሩ በተሀድሶነት የከሰሳቸው ግለሰቦች ጉዳይ በተገቢው መንገድ ተጠንቶ ስላልቀረበና ግለሰቦቹም ተጠርተው ስላልተጠየቁ እንዲሁም ምላሻቸው ስላልተሰማ፣ ጉዳዩ በዚህ የህግ አግባብ ተሰርቶ ወደፊት እንዲታይ የተባለውን፣ አቅላቸውን በሳቱና የሚያደርጉትን በማያውቁ ጳጳሳቱ አማካኝነት ማኅበረ ቅዱሳን  አስገልብጦ ግለሰቦችንና ማኅበራትን የሚመለከተውን ውሳኔ ወሰነ፡፡ በዚህም ሲኖዶሱ በታሪክ የሚጠየቅበትን ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል፡፡
ምንም እንኳ ይወገዙ ከተባሉት ውስጥ ከዚህ ቤተክርስቲያን የተለዩ፣ ኦርቶዶክሳውያን ያልሆኑና እራሳቸውም ኦርቶዶክሳውያን አይደለንም ብለው አፋቸውን ሞልተው የሚናገሩ ማኅበራትና ግለሰቦችንን ቀላቅሎ ያቀረበ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም አላማው ያደረገውም በእነርሱ አስታኮ እውነተኞቹን የቤተክርስቲያን ልጆች መምታት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ቤተክርሰቲያኒቷ መኖርዋን እንኳ የዘነጉ ግለሰቦችና ማኅበራት ተወገዙ አልተወገዙ ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለው የሚያውቀው ማቅ እነርሱን አስታኮ አውነተኞቹን የቤተክርስቲያን ልጆች ለማስጠቃት ያደረገው ሙከራ ተሳክቶለታል፡፡
ጉዳያችንን በትክክለኛ መንገድ አልታየልንም፡፡ ተጠርተን እንኳ አልተጠየቅንም፡፡ ክሳችን ምን እንደሆነ እንኳ አናውቅም፡፡ ሲኖዶሱ የሊቃውንት ጉባኤው አካሄድ ፍትሀዊነት የጎደለው መሆኑን አውቆ ነገራችንን በማስተዋል ይይልን፡፡ ያሉ ሰዎችንም ጉዳይ ቸል በማለት የሲኖዶሱ ለእንዲህ ያለ ውሳኔ መፋጠን በታሪክ ፊት የሚኖረውን ተጠያቂነት ያጎላዋል፡፡  ማንም ይሁን ማን ቤተክርስቲያን ሊኖራት የሚገባው ድርሻ የመግፋት የማባረር ሳይሆን የማስተማርና የመምከርና መሆን ነበረበት፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ ተናግሮ የሚያሳምን መክሮ የሚመልስ አባት የሌላት መሆኑን መረዳቱም እጅግ አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ ሰው አጥፍቶዋል በሚል የሀሰት ምስክር ሳይሆን ማጥፋት አለማጥፋቱን በሚያረጋግጥ እውነተኛ ዳኝነት ጉዳዩ ታይቶ መወሰን ሲገባው እንዲሁ በደመ ነብስ በማቅ አሳሳች ባህሪ ተታለው እነርሱ ያጠኑት ይበቃል በማለት ሲኖዶሱ የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኖ መገኘቱ ያስተዛዝባል፡፡ 
የጉዳዩ ባለቤት ተጠርቶ ባልተጠየቀበትና ስለተከሰሰበት ጉዳይ ድምጹ ሳይሰማ በአለማዊ ፍርድ ቤት እንኳ ተደርጎ የማያውቅ የስህተት አሰራር ላይ ቅዱስ ሲኖዶሱ ወድቋል፡፡ በዚህም የመንፈስ ቅዱስን የመሪነት ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ለማኅበረ ቅዱሳን ሰጥቷል፡፡ ሲኖዶሱ የቤተክርስቲያንንም ውድቀት በዛሬው ዕለት በይፋ አውጇል፡፡አንዳንድ እንደ መንፈሳዊ ሰው ማሰብና ነገሮችን መመልከት ያቆሙትና ራሳቸው የሃይማኖት ሕጸጽ ያለባቸው ጳጳሳት ውሳኔው ካልጸደቀ እያሉ ቤቱን እያመሱት የዋሉ መሆኑ ሲታወቅ ትላልቆቹ ጳጳሳት እነ ብጹዕ አቡነ ፊሊጶና እነ ብጹዕ አቡነ አረጋዊ አረ ተዉ ምንድን ነው ተሸቀዳድሞ ለውሳኔ መቸኮል ተጠርተው ያልተጠየቁ ሁሉ ተጠርተው ይጠየቁ ቢሉም በጎረምሶቹና ጊዜያቸውን ቤተክርስቲያንን በማገልገል ሳይሆን በነውር በሚያጠፉ ጳጳሳት ግፊት ሰነዱን አጽድቀው ወጥተዋል፡፡
ከ1000 አመት በፊት የተወገዘው አውጣኪ የተወገዘው ትክክለኛ ዳኝነት ሳያገኝ ነው ብለው የሚከራከሩት የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎችም ዋናው ዳኝነተ ሳይሆን ውግዘት ነው ብለው ለውግዘት ተፋጥነዋል፡፡ በርግጥ ማቅ ነገሮችን የሚያየው ከንግድ ህግና ከጥቅም አንጻር ስለሆነ በሚታይም በማይታይም መንገድ ነጋዴ ባህሪውን ያቀጨጩበትን ወገኖች ቀላቅሎ ሰነዱን ማስጸደቁ ከባህሪው አንጻር ባያስገርምም ለትክክለኛ ዳኝነት የተዘጋጀ ልብ ከአባቶች ዘንድ መጥፋቱ አስገርሟል፡፡
መቼ ይሆን ቤተክርስቲያን ልጆችዋን ከመግፋት ተቆጥባ ስህተት አለባቸው የምትላቸውን መክራና ገስጻ ጌታችን በቃሉ ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ ባለው መሰረት የሚድኑት እንዲበዙ መፋጠን የምትጀምረው?መቼ ይሆን ከሌላው በረት ለመንጠቅ የጠፉትን በእውነት መንገድ የመምራት ልብ የሚኖራትስ? መቼ ነው የራስን በረት እያራቆቱ ያንን ደግሞ በድል ዜማ ማስነገር የሚያበቃው? እንዲህ ያለው ድርጊት ህሊና ላለው ሰው አሳፋሪ ነገር ነው፡፡
ባለፈው የህዝብ ቆጠራ ቤተክርሰቲያናችን ከስምንት ሚሊየን ህዝብ በላይ አማኝ ማጣትዋ ሳያስደነግጠንና መፍትሔ ለመፈለግ ሳያንቀሳቅሰን እንደገና ያለበቂ ምርመራ ልጆችዋን መግፋትዋ አስተዛዛቢ ጉዳይ ሆኗል፡፡
ቤተክርስቲያን በታሪክዋ ኑፋቄ ስታወግዝ ብቻ አይደለም የኖረችው፡፡ አጠፉ የተባሉትን ጉዳይ አጥንታ መክራ መመለስ ዋና አጀንዳዋ ነበር፡፡  ማቅ ራሱ ለወሬ ማድመቂያ ከጨመራቸው በቀር የከሰሳቸው ሰዎች ትክክለኛ ዳኝነት ቢያገኙ ምንፍቅና እንደማይገኝባቸው ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ አባቶች የማቅን ቂምና ጥላቻ አክብረው ትክክለኛ ዳኝነት ሳያሳዩ የወሰኑት ውሳኔ በምድራዊ መንግስት ትዝብት ላይ ሲጥላቸው በሰማያዊው መንግስት ደግሞ ያስጠይቃቸዋል፡፡ ለመንጋው የማይጠነቀቁ ሙያተኞች ሆነው በእግዚአብሔር መንግስት ላይ የሀሰተኛው ክርስቶስ መንገድ ጠራጊ በሆነው ማኅበረ ቅዱሳን እጅ ላይ መውደቃቸው በእጅጉ የሚያሳፍርና የሚያሳዝን ነው፡፡ ቤተክርስቲያን የእውነት ወገን ሆና በእውነተኛ ዳኝነት ልጆችዋን መጠበቅ ሲገባት ለመንጋው በማይራሩ እረኞች ስር መውደቅዋ በታሪክዋ ትልቁ ውድቀትዋ ነው፡፡
ውሳኔው አባ ሰረቀብርሃንንና ዲ/ን በጋሻውን እንደማይመለከት ታውቋል፡፡
በሌላ ዜናም ማኅበረ ቅዱሳንም ከሰንበት ማደራጃ ሥር ወጥቶ እንደ ልማት ኮሚሽን ራሱን ችሎ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡ ማቅ በዚህ ውሳኔ ጮቤ ቢረግጥም ሲፈራውና ሲሸሸው የነበረው ሂሳቡ በውጭ ኦዲተር የመፈተሹ ጉዳይ አይኑን አፍጥጦ መጥቶበታል፡፡
የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመትንም በሐምሌ ሲሰባሰቡ እንደሚፈጸም ታውቋል፡፡

8 comments:

 1. እውነትን ይዞ መጓዝ እንዲህ ነጻ ያወጣል።
  እስቲ እናንተም ከዚህ ተማሩ።
  ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ድካማቸውን አይቶ ነው።
  እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አይደል የሚለው ቃሉ


  የሐሰተ አባታችሁ መምሰል ትታችሁ እውነትን አውሩ።
  ናቡከደነጾር ላይ የደረሰው ረሳችሁት እንዴ????????

  you will be next like him

  ReplyDelete
  Replies
  1. The same thing happened to lord jesus is happening to his children. is this a liberation? God was preparing away to escape the dead work of evil people, but devil is closing that way. as written in the gospel the Lord will save people of His own.The Father loves whoever loves the Son

   Delete
 2. ተባለ ምን እንላለን!!! ሆነ ምን እንላለን!!! የሁላችን ህይወትና ኑሮ ግን አምላክ ያየዋል። አንድ ነገር ላስታውሳችሁ በዚህ ዓለም ማን ነው ጻዲቅ ቢባል ደፋር ካልሆነ በቀር እኔ ወይም እገሌ ማለት አይችልም። ሀጢአት ቢያደርግም በዚህ ምድር እያለ ሀጢእ ነው ብለን መደምደምያ መስጠት የጢጦስን ታሪክ አለማጥናት ነው። ሆኖም ለክርስቲያኖች፡- ወንድሞች ተሳስተውም ከጉባኤ ሲለዩ ያሳዝናል እንጂ የሚያስደስት አይመስለኝም። "አንባቢው ያስተውል"ማቴ 24

  ReplyDelete
  Replies
  1. መቼም ወንድማችን አባቶቻችን ህጻን ናቸው ብለህ እንደማታስብ አምናለሁ፡፡ አንተ የምትለውን ከሁላችንም በላይ ያውቁታል ስለዚህም አስበው አብሰልስለው ያመኑበትን አድርገዋል፡፡ ይህንን ደግሞ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጅ ከሆንን እንዳለ መቀበል ግድ ይለናል፡፡ ምክንያቱም ይሄ የሰው ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ውሳኔ ነውና፡፡ እግዚአብሄር ሀገራችንን እና ህዝባችንን ይጠብቅ፡፡ አባ ሰላማዎቸም ምንም ብንወዳችሁ የአባቶቻችንን ውሳኔ በዚህ መልኩ ማጣጣል እንዳለባችሁ አናምንም፡፡ ስለዚህ ልቡናችሁን መለስ አድርጉና ለቤተክርስቲያን የሚሆነውን አስቡ፡፡ እውነት ጊዜ ብትወስድ እንጂ ተዳፍና አትቀርምና፡፡

   Delete
 3. ስለሁሉም ነገር ኢየሱስ ይባረክ! እምነትን ይጨምርልን! መወገዝ መባረር ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ድርጅት መሆኑ የበለጠ የኢየሱስን ክብር እንድናውቅ ይረዳናል ነገር ግን ኢየሱስን ትቶ ወደኦርቶዶክስ መቀላቀል የገሃነም እርስት ተካፋዮች ያደርገናል! እውነት መንገድ ህይዎትን (ኢየሱስን) ከያዝን ሌላው ገደል ይግባ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኢየሱስን አንተ እኮ አማላጅ ብለህ ነው የምታምነው አንተደግሞ ፈራጅ ኮናኝነት ሆነህ ቦታውን ለመውሰድ ምንፍቅናህን ትነዛለህ ትሳደባለህ
   ኢየሱስ ክርስቶስ የኛ ፈራጅ ነው አማላጅ አይደለም አቅም ካለህ ማስተማር ንጂ መፍረድ የአንተ አይደለም ተስፋህን ቁረጥ ተነቅቶብሃል

   Delete
 4. kefuwen kemekakelachehu leyu BEMALET METSHEF KIDUS YAZENAL BEMEHONUM ABATOCHACHEN BADEREGUACHEW GUBAYAT KEFUWEN ENA ALEMELES YALEWEN LEYETEW NEW TEKEKELEGNA ASTEMEHERO LEGNA YADERESUN...AHUNEM YETESERAW KEZIH AYELEYEM

  ReplyDelete
 5. yehe blog yemahbere selama blog neaw?

  ReplyDelete