Sunday, May 27, 2012

በእውኑ‘”ማህበረ ቅዱሳን” (ሰለፊያ) እየተዘጋ አይደለምን???

“ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር” እንዲሉ በግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የታዮ ክስተቶችን ትንታኔ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡
ሁላችንም እንደምናውቀው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራሱን በቅዱሳን ስም “ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል የሰየመው የፖለቲካ ድርጅት ለአለፉት ሁለት አሥርት አመታት በቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ይህ በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰው ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ሁሉም የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚያውቁት ሐቅ ነው፡፡
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳስነበብናችሁ ለመሆኑ ማቅን ማን መሠረተው? እነማንስ ስም ሰጡት የሚለውን እውነታ ስንመለከት ‹‹ማቅ›› የተሀድሶ ኮሚቴ ይባሉ በነበሩ የደርግ ደጋፊ አባላት የተመሠረተ ሲሆን ይኽ የጥፋት መልዕክተኛ ዘር ግንዱ እነኮሎኔል አጥናፉ አባተ ካቋቋሙት ”ጊዜያዊ የተሐድሶ ጉበኤ” ይነሳል። ጊዜያዊ የተሐድሶ ጉባኤ የማኅበረ ቅዱሳን አባቱ መሆኑ ነው። ይኽ አባቱ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ለማፍረስ እና በውስጥዋም ሥርዐት አልበኝነት በማንገስ ቤተ ክርስቲያን ደካማ እንድትሆን ለደርግ ያገለገለ ነው። አገልሎቱ ሁለት መልክ ነበረው - የሞተውን ሥርዐት ለመመለስ እና የየግል ጥቅማቸውን ማሳደግ እንዲሁም በሃይማኖት ሽፋን ስውር አላማን ማስፈጸም ነው፡፡
”ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል” እንደሚባለው ይኽ ጊዜጣዊ የተሀድሶ ጉባኤ የመንደረተኝነቱን ቂም ለማርካት ሲል ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ፓትርያርክዋን በገመድ አሳንቆ ያስገደለ የሠይጣን መልእክተኛ ነው። ስንኩዋን የቤተ ክርስቲያኒቱን አደረጃጀት ሊያድስ ቀርቶ የዕሪያ መፈንጫ አድርጓዋት አረፈው። የያኔው የጊዜያዊ ተሀድሶ ጉባኤ አባላት ግማሹም በሹመት ግማሹም በሞት ሲበታተኑ ያደረገው ቀለማቸውን ለውጠው ”ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል ሥያሜ ወራሹን ማደራጀት ነበር። ቤተ ክርስቲያኒቱን ተጠልሎ የወደቀ ሥርዐት ለማስመለስ ስለነበረ አባቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉልላት እየናደ ሲደልቅ ቆይቶ ልጁ ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ እንደሌሊት ሌባ መሠረቷን እንዲሰረስር ክህነት ሰጥቶ ባረከና አደራጀው።
”የአዛኝ ቅቤ አንጉዋች” እንዲሉ ለገዳማት ልማት ያሰበ በመምሰል የገዳማት ጉብኝት እያዘጋጀ ሀብት አካበተ፣ ንዋየ ቅድሳትን ዘረፈ፣ አስዘረፈ፣ ገዳማትን አስደፈረ፣ አንዳንድ ገዳማትን መርጦ ለ ”ትንቢት ተናጋሪ ባህታውያን ማሠልጠኛነት” አደራጀና በከተሞች ማሰማራት ጀምሮ ነበረ። ”ከጳጳሱ ምእመኑ -ቄሱ” እንዲሉ አባቱ ጊዜያዊ የተሀድሶ ጉባኤ ያተራመሰውን ቅዱስ ሲኖዶስ ተክቶ እንደ ብፁዕ አቡነ መርሀ ክርስቶስ (የቤተ ክርስቲያኒቱ መዝገበ ሃይማኖት በመባል የሚታወቁትን)፣ መጋቤ ብሉይ ሠይፈ ሥላሴ ያሉትን ሳይቀር ተሀድሶ ናቸው በማለት ስም ከማጥፋት አልፎ እስከማስወገዝ የደረሰ የዐይነ ደረቆች ቡድን ነው።  የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደር ለመጨበጥ አንዳንድ ጳጳሳትን በገንዘብ በመደለል፣ አንዳንዶችን ደግሞ በስነ ምግባር ጉድለታቸው ካርድ እመዝዛለሁ እያለ በማስፈራራት የሕይዎት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ቢሆንም እሰከ መሰዋት ድረስ የማሉለትን ሥልጣን የዚህን እኩይ ማኅበር ዓላማ ለማስፈጸም ሳያፍሩ ተሰለፉ። አስቀጥሎም የቅዱስ ሲኖዶስን የስብሰባ አጀንዳ የሚወስን፣ ማን ኤጲሲ ቆጶስ ሆኖ እንደሚሾም መመሪያ ቢጤ ሰጭ ሆኖ ተኮፈሰ።
መንገድህ የጥፋት ነው፣ አንተ ብቻህን ብትጠፋ ባልከፋ ግን ሊቃውንቷን በማሳደድ፣ ቀኖናዋን በማራከስ ቤተ ክርሰስቲንን ጤና አትንሳ ያሉትን የወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበራት ለክርስቶስ አገልግሎት ሳይሆን ለሱ እንዲያጎበድዱ፣ ይህን ያልተቀበሉትን በተቧደናቸው ጳጳሳት ተራዳኢነት ማስወገዝ፣ ደቀ መዛሙርትን ለመፍራት ያቋቋሟቸውን መንፈሳዊ ኮሌጆች የመናፍቃን መፈልፈያ ስለሆኑ ይወገዙ (ይዘጉ ለማለት ነው) እያለ ሲፏልል የቤተ ክህነቱ አስተዳደር ” ልጅ ያቦካው ለእራት አይበቃም” ቢልም አፍ በማዘጋት ጊዜና ገንዘብ እንዲባክን፣ በየመንፈሳዊ ኮሌጆች ያሉ ደቀ መዛሙርት እንዲተራመሱ በማድረግ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሁከት አውድማ አድረገዋታል፡፡
ማህበሩ ስሙን ያገኘው በቅዱስ ፓትሪያርኩ የሁል ጊዜ ጠላትነት የሚታወቁት፣ ገዥውን ፓርቲ በሰሜን አሜሪካ ባንዲራ በመያዝ ሲቃወም የነበሩት፣ አሁንም በምዕመናንና በመንግስት ትልቅ መቃቃርና ደም መፋሰስን እያበረታቱ ባሉት አቡነ ገብርኤል አመካኝነት ማህበረ ቅዱሳን የሚል ስያሜውን እንዳገኘ ይታወቃል፡፡
የማኅበሩ ስውር አላማዎች፣
1.      በቤተመንግስትም ይሁን በቤተክህነቱ የአፄው አሠራሮች እንደገና መመለስ፤ የሸዋን መሳፋንታዊ አገዛዝ ዳግሞ ለመመለስ የሚደረግ  ተግባር ነው፡፡
2.     ከፍተኛ ደረጃ ጥረት እየተደረገበት ያለውን የቤተክርስቲያን አንድነት እንዳይሳካና ተግባራዊ እንቅስቃሴው ላይ ተግዳሮት በማብዛት ቤተክርስቲያን አንድ እንዳትሆን ማድረግ፡፡ ይኸውም በውጭ ያሉ ሲኖዶስ አባላት ‹‹የጎንደርና የጎጃም ተወላጆች›› ናቸው ሲሉ በአገር ውስጥ ያለውን ሲኖዶስ  ደግሞ ‹‹የትግራይ ተወላጅ›› ናቸው በሚል የሁለቱ ሲኖዶስ አባላት አንድነት የሚፈጥረው ውህደት የሚያመጣውን የቤተክርስቲያን አንድነትና ሀገራዊ ስሜት ተጽዕኖ በመፍራት ለአጼው መንግስት በግጭት መካከል ቦታ ለማመቻቸት የሚደረግ ጥረት ነው፡፡
ይህንን ለማስፈጸም ማኅበሩ ከመጀመሪያው ጀምሮ የሚጠቀምባቸው የሸዋ ተወላጅ ሊቃነ ጳጳሳትን መሆኑ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የተነሱ ጳጳሳት ብንመለከት፤
1. ብፁዕ አቡነ ይስሀቅ በሕይወት የሌሉ
2. ብፀዕ አቡነ ቀውስጦስ
3. ብፀዕ አቡነ ገብርኤል
4. ብፀዕ አቡነ ቄርሎስ
5. ብፀዕ አቡነ ሕዝቅኤል
6. ብፀዕ አቡነ ፊሊጶስ
7. ብፀዕ አቡነ ኤልያስ እና ሎችም ሲሆኑከሊቃውንተ ቤተክርስቲናን፣

1. ሊቀ ጉባኤ አበራ
2. መ.ሰላም ዳኛቸው
3. ሊ.ካህናት ክንፈገብርኤል አልታና
4. ሊ.ትጉሃን ኃ/ጊዮርጊስ ዳኛ
5. ሊ.ካህናት ብርሃኑ ገ/አማኑኤል ናቸው፡፡

3.     ማህበሩ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በመንፈሳዊ ጉባኤ ስም በመግባት መንግስት እያሰለጠናቸው ያለውን ሃገር ተረካቢ ወጣት ምሁራን የገዥውን ፓርቲ አስከፊነት በመግለጽ በሚሰማሩባቸው የሙያ መስኮች ሁሉ ሥውር የማኅበሩን ዓላማ ማስፈጸም እንዲችሉ ማዘጋጀት፤ከቀበሌ እስከ ከፍተኛ የመንግስት መዋቅር የሚገኙት የማህበሩ አባላት የተሰጣአውን የስራ ድርሻ ቸል በማለት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የማህበሩን ጽንሰ ሐሳብ በማስረጽ ከፍተኛ የሃገር ኪሳራ እያደረሱ ይገኛሉ፡፡
አንዳንዶች የማኅበሩ ቀደምት አመራር በሃገር ውስጥ ያላቸውን ተልዕኮ ካጠናቀቁና መንግስት እንቅስቃሴያቸውን መከታተል መጀመሩን ሲያውቁ የሃይማኖት ካባቸውን በማውለቅ የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ በሰሜን አሜሪካ የሚገኘውን ሕልመኛ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት ቡድን ተጠግተዋል።
 ከአመራሮች በጥቂቶች፤
ሀ. አቶ በላቸው ወርቁ፣ የማኅበሩ ሰብሳቢ የነበሩ፣ ባለው መንግስት የፓርላማ ፀኃፊ ደረጃ የደረሱ (ብዙ የመንግስት መረጃዎች አሉኝ እያሉ በሰ/አሜሪካ ቅስቀሳ የሚያደርጉ)፣ በአሁኑም ሰዓት የማኅበሩ የአሜሪካ ሰብሳቢ የሆኑ ከአ.አ.ዩ በአማርኛ የመጀመሪ ዲግሪ ያላቸውና የሸዋ ተወላጅ
ለ. አቶ ኤፍሬም እሸቴ የሚባሉ ከዚህ በፊት የማኅበሩ ጋዜጣ አዘጋጅ የነበሩ፣ በሰሜን አሜሪካ ኦነግ ነኝ በማለት የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው የማኅበሩ የአሜሪካ ፀሀፊ በመሆኑ $2500 እየተከፈላቸው dejeselam, ahati tewahido እና andadirgen የሚባሉትን blogs ላይ ከፍተኛ የሆነ propaganda በመፍጠር መንግስትንም ሆነ ቤተክርስቲያንን ለመበጥበጥ ዋና ሁነው የሚንቀሳቀሱና ጠቅላይ ሚኒስቴሩን በቀዳሚነት የተቃወሙ ሰለፊያ ሲሆኑ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከኮተቤ በአማርኛ አግኝተዋል፡፡
3ኛ/ አቶ ብርሃኑ ጎበና፣ በአሁኑ ሰዓት የጠየቁት የኦነግነት  ፖለቲካ ጥገኝነት አልሳካ ብሏቸው በአሜሪካ የሚገኙ ሲሆኑ፤ እኝሁ በመጀመሪያዎቹ አመታት የማኅበሩ ዋና ተቃዋሚ የነበሩና አሁን ተቀላቅለው ከማህበሩ ከላይ ለተገለጹት ብሎጎች( dejeselam, ahati tewahido እና andadirgen)  ተባባሪ ፀኃፊ በመሆን የሚያገለግሉ  ሲሆኑ ከአ.አ.ዩ. የኬሚስትሪ ዲግሪ ያላቸው ሰለፊያ መምህር ናቸው፡፡
4ኛ/ በሰሜን አሜሪካ የፖለቲካ ጥገኝነት ግንቦት ሰባት ነኝ ብለው ጠይቀው የሚኖሩ ሲሆን ባሳዩት ተሀድሶአዊ እንቅስቃሴ (ከትዳር በኋላ ክህነት መቀበላቸው) እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ በቤተክርስቲያኒቱ  የተወገዙ  ግለሰብ ሲሆን ይህንንም ውግዘት ሲኖዶስ አጽንቶታል፡፡
5ኛ/ አቶ ደጀኔ ሸፈራው (Denver) እና አቶ ያሬድ ገብረመድህን የሚባሉ ግለሰቦችና የሰሜን ሸዋ ተወላጆች በሰሜን አሜሪካ ምንም አይነት የቤተክርስቲያንም ይሁን የዘመናዊ ትምህርት የሌላቸው ሲሆኑ በተለይ ያሬድ ገብረመድህን 12ኛ ክፍል ሳይጨርስ ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲገባ ማኅበሩ ፎርጅድ ሰርቶለት በዲፕሎማ እንዲመረቅ ተደርጓል፡፡ ይህ ሰው አሁን አቶ ማንያዘዋል የሚባሉ የማህበሩ ጉዳይ አስፈጻሚ እያደረጉት እንዳለው ሁሉ በቤተ ክህነትና በማኅበሩ እንዲሁም በመንፈሳዊ ኮሌጅ ሰላይ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን በዳንኤል ክብረት አማካኝነት ከማኅበሩ ተባረው አንድ አግብታ የፈታች ምዕመን አግብተው  ወደ አሜሪካ በመዝለቅ ቄስ ነኝ በሚል ለሚያደርጉት ተሃድሶአዊ እንቅስቃሴ ባሉበት ስቴት ከፍተኛ ተቃውሞ እና ክስ ተመስርቶባቸው ሊቋቋሙት ባለመቻላቸው ሚስታቸውን ወደ ሎሳንጅለስ ልከዋል፡፡ እርሳቸውም በቅርብ ወደ ሎሳን ጀለስ እንደሚጓዙ ተገልጧል፡ ስለሆነም ተመሳሳይ ተቃውሞ በLA ይጠብቃቸዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡
በአጠቃላይ የማኅበሩ ሥራ አመራሮች በከፍተኛ የሞራል ዝቅጠት ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ ከመመስረታቸው ጊዜ ጀምሮ በተሃድሶአዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሚገኙ ቀደምት አባላት የሚያውቁትና በፖሊስና ርምጃው የኢቲቪ ፕሮግራም የቀረበ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ግለሰቦችን እና ዝርዝሩን እስከማስረጃው በቅርቡ እናወጣለን።
በዚህ እና በመሳሰሉት የማህበሩ ርኩስ ስራዎች ምክንያት ከማኅበሩ አዝነው ከተሰናበቱት አባላት መካከል ጥቂቱን ለመጥቀስ ያህል መድኃኒት ዘዋለ (የመለከት መጽሄት አዘጋጅ የነበረች)፣ ዳግማዊት የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን  ተመራጭ; ፈትለወርቅና ፋሲካ የሚባሉ የህግ ምሩቃን የማኅበሩ ቀደምት አመራር አባላት፣ ቅድስት የምትባል የህግ ባለሙያ (የአባይነህ ካሴ ሚስት)፣ ስመኝ የሞትባል ቀደምት አመራር በአሁኑ ሰዓት የፍትህ ሚኒስተር ባለስልጣን እንዲሁም ብዙ ንፁሀን ልጃገረዶች ከማኅበሩ ተለይተዋል፡፡ ማኅበሩም የሃይማኖት ካባውን እንዲያወልቅ በትግል ላይ ይገኛሉ፡፡
ሌላው በአባላቱ ላይ የተፈጠረው መፈራረስ ምንጩ የማኅበሩ የሥራ አስፈጻሚ አባላት የፖለቲካ ልዩነት ነው፡፡ ለምሳሌ፡-
ሀ. የኢህአዲግ ከፍተኛ አመራር ነን በሚል  ጳጳሳትንና ሊቃውንትን እንዲሁም የማኅበሩን አባላት የሚያስፈራሩ
-  አቶ ካሣሁን ኃ/ማርያም (መንገዶች ባለስልጣን)
                                      -   አቶ ባያብል ሙላቱ( ኮንስትራክሽን ባንክ ባለስልጣን)
                                     
የማኅበሩ አመራር አባላት በዋናነት - አቶ ሳምሶን ገብሬ (ደህንነት ቢሮ)
-  አቶ ደስታ በርሄ (ጠበቃ)
-  አቶ ሙሉጌታ ኃ/ማርያም
ለ. የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊነት በሚል ደግሞ የሚታገሉ ዋና አባላት
-   በላቸው ወርቁ አሜሪካ ኦነግ
-   ኤፍሬም እሸቴ አሜርካ ኦነግ
-   ያሬድ ገ/መድኅን አሜሪካ ግንቦት 7
-   ብርሃኑ ጎበና አሜሪካ ኦነግ
-   መስፍን ነጋሽ (አዲስ ነገር አዘጋጅ)
-   ማንያዘዋል ከአዲስ አበባ
-   እርገተ ቃል (አትላንታ)
ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት ማኅበሩን በከፍተኛ አመራር ይመሩ ከነበሩ አባላት መካከል ብዙዎቹ በፈቃዳቸው ማኅበሩን በመልቀቅ ለቅድስት ቤተክርስቲያናቸው አንድነትና ሉዐላዊት እየታገሉ ይገኛሉ፡፡ ጥቂቶችን ለመጥቀስ ያህል፡
Ø  ቀሲስ ሰለሞን ሙሉጌታ
Ø  ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
Ø  ወ/ሮ መድኃኒት ዘዋስ
Ø  ቀሲስ መንግስቱ ጎበዜ
Ø  ዲ/ን ቸሬ አበባ
Ø  መስፍን ነጋሽ (አቅርብ ጊዜ ወዲህ)
Ø  ቀሲስ ተስፋ እንዳለ
Ø  ዲ/ን ደረጀ ጅማ
Ø  ዲ/ን ዳንኤል ክብረትም ከነዚሁ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ጋር እየተቀላቀለ ይመስላል
Ø  ፈትለወርቅ፣ ፋሲካ፣ ቅድስትና ስመኝ የሚባሉ የህግ ባለሙያ ሴቶች እና ሌሎች አባላት ያሉበት ሲሆን አንዳንዶች በማህበሩ ውስጥ ያሉ አባላትንና አመራር አባላትን በቅርብ ሁሉንም መረጃ ስላገኘነው እናወጣዋለን፤ የወጡበትን ምክንያት ጭምር ትንታኔ በመስጠት እንገልጸዋለን፡፡
የማኅበሩ ስትራቴጅዎች

1.      በቤተክርስቲያኖች ሁሉም ተቋማት ውስጥ አባላትን በማስገባት/በማስቀጠር ቤተክርስቲያናችን ውስጥ የማህበሩን ዓላማ ማስረጽ፡፡ ለምሳሌ፡-
·        ጠቅላይ ቤተክህነት
·        አህጉር ስብከት
·        ልማት ኮሚሽን
·        መንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
·        ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
2.     በከፍተኛ ት/ት ተቋማት ውስጥ የቤተክርስቲያን አባላት ለማኅበሩ እኩይ ተግባራት ማዘጋጀት፤
3.     በሰ/ት/ቤቶች ውስጥ ተለጣፊ ማኅበራትን በመፍጠር በቀጥታ አመራር ከማኅበሩ እንዲቀበሉ በማድረግ የማኅበሩን አኩይ ተግባር እንዲሳካ ብጥብጥ መፍጠር፤
4.     በስብከተ ወንጌል ስም ‹‹ፀረ-ተሃድሶ›› ጥምረት በሚል አንዳንድ ሲሞናዊ የገንዘብ አገልጋዮችን በገንዘብ በመደለል የእኩይ ተልኮአቸው አስፈጻሚ ማድረግ
5.     ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶችን እንረዳለን በሚል ሰበብ የዋህ መነኮሳትንና የአብነት መምህራንን በማግባባት የአላማቸው ማስፈጸሚያ አካላት ማድረግ፤
ምሳሌ፡- ዋልድባ ገዳም ከመምህራን መጋቢ ሀዲስ እሸቱ
6.    የአንዳንድ ጳጳሳትን የስነ ሞግባር ጉድለት እንደ ማስፈራሪያ በመጠቀም የአላማቸው ማስፈፀሚያ አካላት ማድረግ፡፡
ምሳሌ፡-
ሀ. አቡነ አብርሃም (ሰብለ የምትባል ሚስት ያላቸው)፡፡ የማኅበሩ የአሜሪካ ብሎግ ጽሑፍ ማዘጋጃ እንዲሁም ሀ/ስብከት ጽ/ቤት የሰጣቸው፣ ግንቦት 7 በማጠናከር በአሜሪካ የሚታወቁ ሲሆን በሲኤምሲ እና በአስኮ ፎቅ ቤቶች ያላቸው ስለፊያ አስላፊ ናቸው፡፡
ለ. አቡነ ሳሙኤል፡- ከዚህ በፊት የጳጳሱ ቅሌት በሚል በሚገባ የተገለጹና  የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን ተገን በማድረግ የጨለማው ንጉስ ከሚባለው ማንያዘዋል ጋር በመሆን የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን የሚያምሱ ፕትርክና ናፋቂ የ6ኛ ክፍል ተማሪ ናቸው፡፡
ሐ. አቡነ ሉቃስ፡- የደርግ ኢሀፓ አባል የነበሩ፣ ምንም አይነት እምነት ሳይኖራቸው ለጵጵስና  የተሾሙ፣ በአሁኑ ሰዓት ሐዋሳ ያለው ቤታቸው ለማኅበሩ አከራይተው የሚጠቀሙ፣ የአቡነ በርተለሜዎስ ሠራተኛን ወሸመው በፍርድ ቤተ ተከሰው የነበረ ሥራ አስኪያጅ የነበሩ፣ በአሁኑ ሰዓት ለሐዋሳው ብጥብጥ ዋና ተጠያቂ የሰለፊ ደጋፊ ናቸው፡፡
በቀጣይ የሁሉንም መረጃ የምናቀርብ ይሆናል፡፡
የማኅበሩ ወቅታዊ ሁኔታ
1.      የማኅበሩ እኩይ አላማ እና ተግባር በቤተ መንግስት አመራር አባላት ጭምር ታውቆ በይፋ በፖርላማ ተገልጾል፡፡ መንግስትም በቀበሌና በወረዳ ደረጃ የማኅበሩን እኩይ አላማ ገልጾአል፡፡ ምዕመናንም በቂ ግንዛቤ አግኝተዋል፡፡
2.     በማኅበሩ የአገር ውስጥም ይሁን የውጭ አገር ተባባሪ የነበሩ አባላትና ድርጅቶች ተለይተው ታውቀዋል፡፡ የተወሰኑ አካላት ላይም እርምጃ ተወስዷአል፡፡
ሀ. ስብከተ ወንጌል፤ ቀሲስ ሳሙኤል እሸቱ ከም/መምሪያ ኃላፊነት ተወግደዋል፡፡
ለ. ሰንበት ት/ቤት መምሪያ፡- አባ ህሩይ ወንድይፍራው የተባሉ የመምሪያ ኃላፊ ተወግደዋል፡፡
ሐ. የገዳማት መምሪያ፡- ንቡረዕድ ገብረ ማርያም ከኃላፊነታቸው ተወግደዋል፡፡
መ. በልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሰራተኛ የነበሩ 18 የማኅበሩ እኩይ ተግባር አስፈጻሚዎች ተሠናብተዋል፡፡ ምሳሌ አቶ ማንያዙዋል የተባሉት የማኅበሩ ካድሬ ሲሆን ይህ ጉዳዩ እንደሚቀጥል ተገልጾአል፡፡
3.     የጳጳሳት ያልተገባ የገንዘብ ዝርፊያ፣ ጥቅመኛነትና እንዲሁም የፖለቲካ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት እንዲጠና ኮሚቴ ተቋቋሞል፡፡ ይህ ጉዳይ አገራዊም ሆነ ቤተክርስቲያናዊ ፋይዳ ስላለው መንግስትም ሆነ ምዕመናን በቅርብ ክትትል ላይ ናቸው፡፡
4.     ማኅበሩ በሁሉም የቤተክርስቲያን ተቋማት ጣልቃ እየገባ የሚያደርጋቸው እኩይ ተግባራት እንዲያቆም ለጊዜው (እስኪፈርስ) እንደ አንድ መምሪያ እንዲቀሳቀስ ተደርጎል፡፡ የዚህ አንድምታ፡-
ሀ. ማኅበሩ በሰ/ት/ቤት ሥም የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ያቆማል፡፡
ለ. በአዲስ የስብከተ ወንጌል መመሪያ መሠረት በየትኛውም ቦታ የፈለገውን ፖለቲካዊ ጉባኤ ማድረግ አይችልም
ሐ. ማኅበሩ በገዳማት፣ አብነት ት/ቤቶችና ሰበካ ጉባኤ ነክ ጉዳዮች ያለው እንቅስቃሴና ገንዘብ ማካበት ያቆማል፡፡
መ. የማኅበሩ አመራር እንደሌሎች መምሪያዎች በቅዱስ ፓትርያርኩ ይሾማሉ፡፡ ይሻራሉ፡፡
ሠ. ማኅበሩ ሀብቱን አዲት ያስደርጋል፡፡ወጭውን በፋይናንስ ህግ መሠረት በቤተክርስቲያን በኩል ብቻ ያደርጋል፡፡ በሁሉም አካውንቱ ላይ ብፁዕ ሥራ አስኪያጅ ፈራሚ ይሆናሉ፡፡ እንደሁሉም መምሪያዎች ማለት ነው፡፡
ረ. ጥገኝነት አገልግሎት ያቆማል፡፡ በውጭ ሀገርም ምንም አይነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስለሌሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ይዘጋሉ፡፡
ሰ. በሐሞሌ የማኅበራት ጥናት መሠረት የሚወስነው የመጨረሻ ውሳኔ በማኅበሩ ላይ ይወስናል፡፡ በቀጣይ ዝርዝር መረጃዎች ጋር እንልካለን፤፤
ታዲያ ይህ ሆኖ እያለ ሰሞኑን ለምን ማኅበሩ እና የማኅበሩ ልሳናት ጮቤ ረገጡ፡፡ ምክንያቱ ይህ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው በአሁኑ ሰዓት ነፃ የHIV/AIDS ህክምና/ እድሜ ማርዘሚያ ተጠቃሚ ነው፡፡ ART ማረዘሚያ መውሰድ ማለት ግን ከቫይረሱ ሙሉ ለሙሉ መላቀቅ አለመሆኑን ሊቃውንት ያረጋግጣሉ፡፡ በተመሣሣይ መንገድ ለማኅበሩ ሰሞኑን በአቡነ ገሪማ አማካኝነት የተደረገው የዕድሜ  ማራዘሚያ አንድምታው፤ በሥነ ስርዓት የማኅበሩን ንብረት የቤተክርስቲያን ለማድረግ የሚያመቻች ሂደት እንጂ ሰለፊያ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለማስፋፋት አለመሆኑ በሁሉም የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞች ግንዛቤ ተፈጥሮል፡፡
ይቀጥላል፡፡

35 comments:

 1. This is a wonderful article. So good and truth.
  Aba Selama please continue, what you are doing is the best. God Bless you, more, more and more.

  your Sister in Christ.

  ReplyDelete
 2. አባ ሰላማዎች በእውነት እግዚአብሔር ይስጣችሁ፡ ይህን የመሰለ ሰፊና ለእያንዳንዱ የኦርቶዶክስ ምዕመናን ሁሉ ጥልቅ እውቀት ልሰጥ የምችል የማህብረ ቅዱሳን ስዉር ደባ በማጋለጥ ያቀረባችሁት ጽሁፍ ደስ ይላል። በርቱ ጠንክሩ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን።

  ReplyDelete
 3. ኃይለ ጊዮርጊስ ከሁሉ አስቀድሜ የሰማይና የምድር ጌታ በጎ የሆነውን ሁሉ እንዲያመላክትህ እጸልያለሁ:: ወንድሜ ሆይ መቸም ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን ያደረገውንና እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ ልቡናህ ያውቀዋል :: አንድ ነገር ልጠይቅህ ? መልካም :: ትዝ ይልሃል ? ለመጀመሪያ ጊዜ እንጀራ የቆረስክበትን ሥራ ስትጀምር ? ቤተ ክህነት/ልማት ኮ ሚሽን/:: እንዴት ነበር የገባህ ? በኔ ሙት አንድ ጊዜ ወደ ልብህ ተመለስና አስብ ::አስታውሳለሁ በጣም ተቸግረህ ሰው ቤት ተጠግተህ /እነ ደምስ ..../ይገባሃል ብየ ነው::ማኅበረ ቅዱሳን አባሌ ነው የቤተ ክርስቲያን ልጅ ነው ብሎ ጽፎልህ ተቀጠርክ ከቤተ ክህነት /በወቅቱ የማኅበሩ ጸሐፊ በነበረው በዳንኤል ፊርማ /ወንድማለም ሁሉም ያልፋል :: ካንዳን የማኅበሩ አባላት ጋር ስላልተገባባህ ማኅበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ አካፋና ዶማ ማቀበል ፍጹም የሚያዋጣ አለመሆኑን ስገልጽልህ በማኅበር ስሜት አለመሆኑን በፍጹም እርግጠኛነት በእግዚአብሔር ስም እምልልሃለው::ማኅበረ ቅዱሳን ከነ መዋቅሩ ሥራው ሳይቋረጥ የቤተ ክርስቲያኗን ሥራ እየሰራ ከቀጠለ "ማኅበረ ቅዱሳን " የሚለው ስም ኖረ አልኖረ ለኔ ትርጉም አይሰጠኝም:፡ እውነታው ግን ማኅበሩ በትክክል ለቤተ ክርስቲያን እየደከመ መሆኑን ማመን ነው::
  ወድ ወንድሜ ኃይለ ጊዮርጊስ አንድ ነገር ብየ ልሰናበትህ ከእግዚአብሔር ጋር አትጣላ::
  ወዳጅህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. It is very interesting and matured response. Wondome zim belachew...nothing will happen since they write their wish here and there. Libona yisetachew....

   Delete
  2. ታማኝ አገልጋያችሁ ለማድረግ እንጂ እንደአንድ ኢትዮጵያዊ ሊደረግለት የሚገባው እንደሆነ ባለማመንህ ቀኑ ካለፈ በኋላ የያኔውን ውለታ በመቁጠር ዛሬ ኅሊናውን ወደ ማቅ ባርነት እንዲመልስ መሞከርህ ይገርማል! ሰው በዘመኑ ሊቸግረው፤ ሊደኸይ ይችላል። እድሉ ያላቸው መልካም ነገር ቢያደርጉለት ያስመሰግናቸዋል እንጂ ባደረጉለት ውለታ እየተኩራሩ ይህንን አድርጌልህ እያሉ ጠፍንገው የኅሊናቸው ተገዢ ለማድረግ ሲመኙ እጅግ ያሳፍራል። ደግሞም አንድ ወቅት ውለታ የዋለ ማኅበር ከውለታው በስተጀርባ ጠላት ሆኖ ሊቀርብ እንደሚችል ባለመገንዘብ የጥንቱን እያሰብክ ክፋቴን ቻለው ማለት ጅልነት ነው። በዚያ ላይ አለመግባባት ሲከሰት ማኅበሩ ጡንቻውን ተማምኖ ኃይለ ጊዮርጊስን ለመምታት የሚችለውን ሁሉ ጉድጓድ ሲቆፍር በተቃራኒው የመልስ ምት አይመጣም ብሎ ማሰብ ኅሊና ቢስነት ይሆናል። እኔ ስደበድብህ የድሮውን እያሰብክ ዱላዬን ቻለው የሚል ግብዝነት ምን ይባላል?
   ደግሞም ይህ ጽሁፍ የኃይለ ጊዮርጊስ ይሁን፤ አይሁን በምን አወቅህ? ምናልባት በቅርበት ያውቀን ስለነበረ ይህንን ሁሉ ጉድ የሚያወጣ ከእሱ ሌላ ማንም የለም ከሚል ግምት የተነሳ እንጂ የጽሁፉ ባለቤት ኃ/ጊዮርጊስ ስለመሆኑ በስም አልተገለጸም። የጸሀፊዎችን ማንነት ለማወቅ ብዙ ከማሰላሰል ይልቅ ለምን በመጠን ለመኖር አትፈልጉም? መጠናችሁ ከመስፈሪያው መፍሰስ ሲጀምር ግጭቱ ግራና ቀኝ ሲሆን እናንተ ግን በመልካም ስራችሁ የሚመጣባችሁ ፈተና እንጂ ስለክፋታችሁ የደረሰባችሁ እንዳልሆነ ትቆጥሩታላችሁ። በኃይለ ጊዮርጊስ ላይ የነበራችሁን ክፋት በውለታችሁ የደግነታችሁ ልክ ማስላታችሁ በሚዛናዊ ኅሊናችሁ ውስጥ እንደሌላችሁ አረጋጋጭ ነው። ዛሬ ኃ/ጊርጊስን እንደጠላችሁት ነገ ደግሞ አንዱን፤ሌላውን፤ ሁሉን ታጣላችሁ!!!!!!!!!!!!

   Delete
  3. ደጀ ብርሃን
   ስለ አስተያየቱ በኢትዮጵያዊ ወግ አመሰግናለሁ:;
   እባካችሁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኝዎች ከሆናችሁ ሥራችሁ ይግለጻችሁ ::
   /በዚህ ብሎግ ላይ የሚወጡት በሙሉ የኦርቶዶክስ ባለመሆናቸው ይህን ልናገር ችያለሁ/
   ይሁንና በዚህ ብሎግ የግድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ይውጣ ለማለት መብት የለኝም::
   ወደተነሳሁበት ስመጣ :ኃይለጊዮርጊስን በተመለከተ የጻፍኩለት " ተርበህ ነበር ተቸግረህ ነበር...." ለማለት እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባዋል ለምን ቢሉ ኢትዮጵያውያን ነንና ሁላችንም ያለፍንበት ህይወት ተመሳሳይ ነው::
   ወንድሜ ኃይለ ጊዮርጊስ
   አሁንም እልሃለሁ ከእግዚአብሔር ጋር አትጣላ ደግሜ እላለሁ ከእግዚአብሔር ጋር አትጣላ::
   ደጀ ብርሃን :ብታምኑም ባታምኑም አንድ ነገር ልንገርህ የማኅበረ ቅዱሳን አይደለሁም ማኅበረ ቅዱሳን ለሚሰራው በጎ ነገር ግን ደጋፊ ነኝ ::
   ወዳጅህ

   Delete
  4. እድሜዎ ምን ያህል ነው? ትክለኛውን ባላውቅም በትንሹ 6 ነገሥታት ወይም ገዥዎችን ያዬ ዕድሜን አያጡም ብል ተሳሳትክ አይሉኝም፤ (ጄ/ል አማን፣ ኮ/ል መንግሥቱ፣ ሻ/ል ፍሰሐ፣ ታጋይ ታምራት፣ ታጋይ መለስ እና ፓስተር ኃይለማሪያም)። ባይሆን ሁለት ጨምር አንድ ቀንስ ይሉኝ ይሆናል። ያለ ምክንያት ቋሚንም ሟችንም አላነሳሁም እናም ሁሉም ሥራቸው የሚገለጠው አበረዋቸው በመጥፎም በጥሩም ከተሳተፈው ነው። ታዲያ እኝህም ሰው ካጋለጧቸው ጋራ ተባበሩ አልተባበሩ ወይም መረጃን አስደግፈው ትክክለኛውን በማስረዳት ታርመን እንድንድንበት ማድረጋቸው ምን ያስነቅፍባቸዋል? በእኔ በኩል ግን ለኖኅ እውነተኛውን የውሃ መጉደል አብስራ ነጻነቱን እንደጠቆመችው እርግብ እመስላቸዋለሁ። ይልቅስ ይቀጥላል ያሉትን እንዲነግሩን እንቅፋት አይምታብን።

   Delete
 4. የምትገርሙ ሰዎች ናችሁ! አባቶችን በመሳደብ የሚገኝ ክብርና ካለ ቀጥሉበት፡፡ የእናንተ የመጨረሻ ግባችሁ የት ለመድረስ እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. Am MK! Why is everything so confusing? May be am out of my mind....

  ReplyDelete
 6. Ere eyetezega new......

  ReplyDelete
 7. ማቅ በሃያ ዓመቱ ክርስቲያን የሆነበትን (ክርስትና የተነሳበትን) ከንዑስ ክርስትና ወደ ክርስትና የመጣበትን ሃያኛ ዓመት በቅርቡ ያከብራል፡፡ ለዚህም የመረጥንለት ርዕስ

  ማቅ በሃያ ዓመቱ ተጠመቀ ወደ ቤተ ክህነት ወደ ቤተ ክርስያንም ገባ ወይም ሊገባ ነው

  እስከ ዛሬ የምናውቀው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ሰብስቦ ቤተ ክርስቲያን ያገባል በሰበካ ጉባኤ አስመዝግቦ የቤተ ክርስያን አካል ያደርጋል ሲባል ሲኖዶስ ለራሴ መተዳደሪያ ሰጠቶኛል ዐሥራት በኩራት እንደሰበስብ ፈቅዶልኛል በማለት ወጣቶቹን የማቅ አባል፣ ሀብታቸውን ወደ ማቅ ባንክ፣ ሃይመኖታቸውን የማቅ ሃይማኖት፣ ሥርዓታቸውን የማቅ ሥርዓት በማድረግ ስብሰባው በየሆቴሉ፣ በየአዳረሹ፣ ገንዘቡን በየ አባላቱ ኪስ፣ የራሳቸው መዝሙር፣ የራሳቸው ዩኒፎርም፣ የራሳቸው አርማ፣ የራሳቸው መተዳደሪያ በመያዝ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ሆነው ነበር፡፡

  አሁን ግን በሃያ ዓመቱ ወደ ቤተ ክህነት ሊገባ ነው መሰል ምናልባት እምቢ ካላለ በቀር አሁንም ያላመሁ አባላት ስላሉ፡፡

  ለዚህ ከፍተኛ ስኬት የሐዋርያነት ሥራ ለሠራችሁ ለእነ አባ ሠረቀ፣ ለማኅበራት ጉዳይ አጥኒ ቡድን እንኳን ደስ ያላችሁ፣ ማቅን ከሐጢአትና፣ ከኑፋቄ፣ ከዝርፊያና ከአሸባሪነት አውጥታችሁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስለመለሳችሁ፡፡ ልትመሰገኑ ይገባል እንላለን፡፡

  እስኪ ምእመናን ማቅ በሃያ ዓመቱ የንዑሰ ክርስቲያን ጉዞው ምን ሠራ እንዴት አሳለፈው፣ በሚለው ጉዳይ እየተወያየን ማቅን እንኳን ደህና መጣህ እንበለው፣ ሰብሰብ ብለን እስከ አሁን ከሰበሰቡት ወይም ከዘረፉት ገንዘብ ከወጭ ቀሪ ሰንት አስገባችሁ፣ ወደ ማኅበር መዝገብ ከሰበሰባችሁት ዓባል ስንቱን ለክርስቶስ አመጣችሁ እንበላቸው፡፡

  ግጥም እነሆ ለማቆች ሃያኛ ዓመት

  ወንዙ ወርዶ ወርዶ
  ሲሔድ ገደል ንዶ
  ደንጋይ ጋር ተጋጨ
  እያሙለጨለጨ
  ቀጠለ እያፏጨ
  ዛፉንም ገንድሶ
  ሜዳውንም አርሶ
  ገስግሶ ገስግሶ
  ስንቱን አተራምሶ
  ይደርሳል ከባሕር
  ከዚያ ላይሻገር
  ማቅ የሚሉት ቡድን
  ቢጽ ሐሳዊ ሰይጣን
  ስንቱን ሰው አታሎ
  የሰው ክብር አቃሎ
  የዋሁን ደልሎ
  የሰው ሥራ ሟጦ
  የስንቱን ኪስ ልጦ
  ስንቱን በቃል ወግቶ
  የስንቱን ቤት ፈቶ
  መቆሚያው ሊገታ
  የማታ የማታ
  ሊገባነው መሰል
  ከባሕሩ ወለል
  ሊካፈል ከማዕድ
  ከአቅሌስያ አጸድ

  ReplyDelete
  Replies
  1. selam, sew mechem ke haymanot sirek tesadabi new yemihonew mesel lenegeru kezih wechi min mehon yichilal endemibalew yezih blog azegaj Hilegiorgis kehonik and wekit gibi gubae beneberikubet gize astemirogn neberena yasetemaregnin kene kedimo keresaw yigermal...manim yetsafew man yehenin tsehuf ketsafew behwala letinesh dekika wede libu temeliso lemanibeb edil kagegne erasunim endemayasaminew yigebawal "yesideb af tesetew" tewu egziabeher yayal yisemalem ::Tamitrat

   Delete
 8. wey gud mk meslotal ahun yebase yemayeweta cheger west wedekee gud mayet new ruk ayedelem abaselamawoch egziabher yisetachehu yihen hulu tarik endenawek aderegachehun lelaw yekehenet neger zim malet new le mk zim tebelo yemitadel new Eperm eshete, ke usa.. abrham belete ke Germen,... wendosen yewhalashet, kegermen minem sayaweku wetader yehonu ahun kihenet bekihenet egzioooo enesun belo ye hayemanot tekorekuari neseha gibuna kihenetun melesu

  ReplyDelete
 9. we are in 21 centure,peple what are u doing, we have a lot of information to filter out truth or false but u are doing a crazy thing.please go back to your mind.you are posses with evil sprite

  ReplyDelete
 10. ይድረስ ለዚህ አርቲክል ጸሐፊ??????

  የፓለቲከኞቻችን ታሪክ አንድ በስልጣን ያለ መንግሥት ወይም የሚጠሉት ተቀናቃኝ የፓለቲካ ድርጅት የፈለገውን ዓይነት መልካም ነገር እንኳ ቢሰራ ሁልጊዜ የሚያስወሩበት ደካማ ጎኑን ብቻ ነው:: የሚጠቀሙበት ስልትም ማሕበረ ሰቡ በቀላሉ ሊቀበለው የሚችል ዘመን ያለፈበት ውንጀላ በማንሳት ነው:: ለዚህ ነው 'የጠላትህ ጠላት ወደጅህ ነው' የሚለውን ያረጀ አባባል የዛሬ ፓለቲከኞቻችን በመከተል በዓላማ ከማይገናኙ የዘር ፓለቲከኞች ጋር ሳይቀር የማያዛልቅ አንድነት እየፈጠሩ ያሉት:: ተራራ የሆነባቸውን የጋራ ተቀናቃኝ ጠላታቸውን ድል ካደረጉ በኋላ ግን አብሮ የመሄዳቸውና የሚፈለገውን እውነተኛ ለውጥ የማምጣታቸው እድል ግን እጅግ ያሰጋኛል:: አሁን ያለው መንግሥትም በለስ ቀንቶት አሁን ላለበት ሁኔታ በቃ እንጂ እያደረገ የመጣው እንደዚህ ነው:: አሁንም ቢሆን ላለመጠቃት የአብዛኛውን ሕዝብ ልብ የያዘው በዚህ ዓይነት ስልት ነው::

  ለመንደርደሪያ ይህን ካልኩ አርቲክሉን የጻፈው ሰው ወደ አነሳቸው ነጥቦች ልምጣና የማህበረ ቅዱሳንን ማንነት ከተግባሩ በመነሳት ከማጋለጥ ይልቅ የወንጌል ጠላትነትን በአካባቢ ወይም በተወላጅነት ወይም በፓለቲካ ድርጅት አባልነት የተወሰነ እንደሆነ አድርጎ አቅርቦታል:: እኔ መችም እንደዚህ ዓይነት አካሄድ የንጹህ ወንጌል መንፈሳዊ ውበትን የሚያበላሽና ሥጋዊ ስሜት ላይ ያነጣጠረ አጻጻፍ ነው የሆነብኝ::

  ወንጌሉ ገብቷቸው ለእውነት የሚሰለፉ ሰዎች ከየትኛውም አካባቢና ዘር ሊመጡ እንደሚችሉ እየታወቀ የማቅ መሪዎች ከሸዋ በመሆናቸው ብቻ ሸዋው ሁሉ አብሮ ተጨፍልቆ እንዲታይ የሚጋብዝ ልዩ መልእክት ማስተላልፍ ጥሩ አልመሰለኝም:: እንዲያውም ነፍሴ ተጸይፈዋለች:: አመራሩ ሸዋ ጳጳሳቱ ሸዋ የሊቃውንት ጉባኤ አባላቱ ሸዋ ...ወዘተ ማለቱ የሌላውን አካባቢ ተወላጅ በስሜት ለማነሳሳት ነው ወይስ መንግሥት በሸዋ ላይ ባለው የተለየ አመለካከት ምክናያት ዱላውን በማቅ ላይ እንዲያነሳ ለማድረግ? የጽሑፉ ዓላማ ይህ ከሆነ እጅግ ነው የሚያሳዝነው:: ምክናያቱም በታሪክ እንደታየው የወንጌል ጠላቶች ወይ በወንጌል ፍቅር ተማርከው ይመጣሉ ወይም በራሱ በቃሉ ሰይፍ ይወድቃሉ እንጂ በሥጋና ደም ውጊያ ፈጽሞ ድል አይመቱም::

  ስለሆነም እንደዘመኑ ፓለቲከኞች በዘር ወይም በአንድ በተወሰነ አካባቢ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ የወንጌል ጠላትነት ፈጽሞ ሊኖር ስለማይችል ይህ ዓይነቱን ትንተና የሸዋ ተወላጅ ባልሆንም በበኩሌ ከመጸየፍ ሌላ ፈጽሞ አልቀበለውምና ይታረም:: የማህበረ ቅዱሳን አመራር አባላትም ሆናችሁ ተራ አባላት በመንፈሳዊነት ስም እየሄዳችሁበት ያለው አካሄድ መዳረሻው ቦቶምለስ ፒት እንጂ ሌላ እንዳልሆነ አውቃችሁ ብትመለሱ ጌታ ሊመልሳችሁ የታመነ ነውና ቆም ብላችሁ ብታስቡበት ለራሳችሁም ለጋራ ጊዜያዊ አገራችንም ይጠቅማል:: ማስተዋል ለሁላችንም!!!

  'እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል በዚያም የግሪክ ሰው አይሁዳዊም የተገረዘም ያልተገረዘም አረማዊም እስኩቴስም ባሪያም ጨዋ ሰውም መሆን አልተቻለም ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው በሁሉም ነው::' (ቆላ 3:9-11)

  ሕያው ቃሉ ስለሚል:

  የመንግሥቱ ጠላትነትም ሆነ
  የመንግሥቱ ወራሽነት/አገልጋይነት

  በዘር ወይም በአካባቢ ፈጽሞ አይወሰንምና ሸዋ ወይም ወሎዬ ወይም ጎጃሜ ወይም ጎንደሬ ወይም ትግሬ ወይም ወለጌ ወይም ሶዶ ወይም ሐረሬ ወይም ከምፓቴ ጉራጌ ሃድያ አፋር ኡርጂ ከፋ ሲዳማ ባሌ አርሲ.... ወዘተ ማለቱ ይቁምና እንደቃሉ እንጻፍና እንናገር ማለት እወዳለሁ:: ደግሞም ሸዋ የሚባል የተለየ የወንጌል ጠላት አጋንንት አይኖርም::

  ማስተዋልን ጌታ ይስጠን!!!

  የጌታ ሰላም ለሁላችን ይሁን::

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 11. don't be irritated,how do you know all the above silly points before the improvement of the rules by the assigned persons ,

  ReplyDelete
 12. የማይ መስል ነገር አትንገር እንኳን አባላቱ ጸሃፊውም ቢጠየቅ አያምንበትም አልሞት ባይ ተጋዳይ እንደ ይሁዳ። የሰሜን ወሎው የልማት ኮምሽን ሌባው ዋነኛው የተሃድሶ አቀንቃኝ አንተ ውሸት ትፈጥራለህ እኔ እውነቱንና የአንተን ማንነት በመረጃ ወደፊት የማቀርብ መሆኔን አትጠራጠር ኃይለ ጊዮርጊስ የተደበቀ ሁሉ በጊዜው ይገለጣል።

  ReplyDelete
 13. bizega des yilachehu neber Egziabher gen kezih Maheber gar nebere lezelealemem yinoral! Amen! YeKidusan Girma Yekelilewal kendenante ayinet afe kelate. Egziabher libona yestachehu. Amen! Eme Amlak mechem rehrytelib natena enantenim menem Amalajinetuan bitiniku tamalidachehualech. Betifatachehu timotu zend atifelegimna. Amen Tamaldachehu!

  ReplyDelete
 14. lemin weshet yiweral ! bekerb yemakachewn sewoch sem metekesu yebelete endeteraterachihu adergonial ! huliem gin egeziabhier ethiopian kenetaki tekulawochi selemitebekat bizum ayidenkenim !!

  ReplyDelete
 15. ለሰላም

  እግዚአብሔር ሰላሙን ያብዛለህ ካልኩ በሃላ

  አቡነ አብርሃም ሣሙኤል ጢሞቴዎሰ ቄርሎስ ሉቃሰ ገብርኤል ናትናኤል ሕዝቅኤል ዲዮስቆሮስ ሸዋ አየደሉም
  ጸሐፊ ሆይ ትንተናህን በተጨባጭ መረጃ እንጂ በጭፍኔ አታድርገው
  አንድ ወዳጄ ምን አለ መሰለህ
  ስለቤክ ጉዳይ ሙሉ እውነት የሚነግር በሎግ የለመ
  ግማሽ እውነት ከአባሰላማ ግማሸ እውነት ከደጀሰላም ያለው ትዝ አለኝ
  ለካስ እንዲሀ አየነቱ ግርድፍ ጽሁፍ ነው አባሰላማን የሚያስነቅፈው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጸሀፊው እነዚህን ሁሉ ሸዌ አላለም። አንዳንድ ሰዎች በትምህርት ብቻ ሳይሆን በተፈጥሮ እንኩዋን ልብ ብለው አንብበው ይቅርና አንዴ ቢወርዱት ከጸኃፊው የበለጠ ሃሳቡን ለሌላው በደንብ ማስረዳት ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ ሦስቴም አንብበው በራሳቸው ይተረግሙትና እሄ ነው ብለው ድርቅ ብለው ይከራከራሉ። ጥቂቶች ደግሞ በሰውየው ወይም ርዕሱን ብቻ አይተው ብዙ ሰዎችን ያሳስቱበታል። እርሶ ከየትኛው ኖት?

   Delete
 16. አንድ ያነበብኩት ጽሁፍ “መንፈሳዊ /ኦርቶዶክሳዊ/ ሥነ ጽሑፍ የሚባለው ዓላማው ነገረ እግዚአብሔርን ማስተማር ምግባረ ሃይማኖትን መስበክ ነው ፡፡ የሥነ ጽሑፉ ግብ እግዚአብሔር ለሰዎች ያደረገውን ቸርነት ፣ የሰውንና የእግዚአብሔርን ግንኙነት ፣ የቅዱሳንን ገድል ፣ የጠላት ዲያብሎስን ግብር ወዘተ በማሳየት ሰውን በእምነቱ ጸንቶ እንዲኖር መምከር ነው ፡፡” ይላል ፡፡ ይህ ያስነበባችሁን ጽሁፍ ግን ከመንፈሳዊነት ያፈነገጠ ፣ ነገረ እግዚአብሔርን የረሳና በምድራዊና በዓለማዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ፡፡ ሆኖም ግን ስለቀረበው ጽሁፍ ያለኝን አስተያየት ለማስነበብ ጫጭሬአለሁ ፡፡

  - ጽሁፉ ገና ከመጀመሩ ማኀበረ ቅዱሳንን የሚመድበው የፖለቲካ ድርጅት አድርጎ ነው ፡፡ ቀጠል በማድረግ ይህንኑ አባባሉን ለማጠናከር ሲያብራራም የተሃድሶ ጉባዔ ኮሚቴ በሚባሉት በእነ ኮሎኔል አጥናፉ አባተ እንደተመሠረተ ያትታል ፡፡ ኋላ ላይ ሌላ ስም ካልወጣለት እስከዚህ በተነበበው እንግዲህ የደርግ አባላት ድርጅት ነበረ ለማለት እንደፍራለን ፡፡ በሎጅክ ደግሞ ኢህአዴግ ሲፋለም የኖረው ከደርግ እና ከርዝራዦቹ ጋር ስለነበረና ስለሆነ የውጊያ ቀጠናውን ወደዚሁ ማኀበር ማነጣጠር እንደሚገባው የማንቃት ጥሪም ይመስላል ፡፡ የማህበሩ አገልሎትን ም አጠቃልሎ ሲያስረዳን ሁለት መልክ እንደ ነበረው - አንድም የሞተውን ሥርዐት መመለስ እና የየግል ጥቅምንን ማሳደግ እንዲሁም በሃይማኖት ሽፋን ስውር አላማን ማስፈጸም መሆኑን ይገልጻልል ፡፡ ይህም ከመንዳዮችን ለማነካካት የታቀደ አባባል ነው ፡፡ ደርግ የሚከተለው ርዕዮተ ዓለም እግዚአብሔር የለም የሚያስብለው ሲሆን ፣ ማንን ለማምለክ ብሎ የሃይማኖት ድርጅት ፈጠረ ብለን ሃሳቡን እንመን ?

  - ስለ ማኀበረ ቅዱሳን አመሠራረት ማስረጃና ምስክር አለን በማለት ፣ ከአንድም ሁለት መጽሐፍ የጻፉት ሌሎች ግለሰቦች /አቶ ጽጌ ስጦታውና ዲያቆን ሙሉጌታ ወ/ገብርኤል/ ደግሞ ማኀበሩ የዛርና የጥንቆላ መንፈስ በሠፈረባቸው አሥራ ወጣቶች ፣ እንደ ቀልድ ሰፈር ውስጥ እንደ ተመሠረተና ፣ ወንጀልን ከመጀመሪያው ሥራዬ ብሎ በመያያዙ እስከ ህግ ድረስ እንደደረሰ ጽፈው አንብበናል ፡፡ ማኀበረ ቅዱሳን ደግሞ ለራሱ የራሱን አመሠራረት ሌላ ታሪክ ይናገራል ፡፡ ይህም ማለት ማኀበሩ የተመሠረተበት የተለያዩት መንገዶች ፣ ለጊዜው አንድም ሦስት ናቸው ማለት ነውና አንባቢ የማንን ዕውነት እንደሚከተል ለራሱ ይምረጥ ፡፡ ምናልባት አራተኛውና አምስተኛው የማኀበሩ የሥነ ፍጥረት ታሪክ ደግሞ በሂደት ወደፊት መምጣቱ አይቀርምና ለመጠበቅም ይቻላል ፡፡

  - በወቅቱ ፓትርያርክ የነበሩትን ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስን አሳንቆ ያስገደለም ይኸው ጨቅላ የጨለማ ማኀበር እንደሆነ ይናገራል ፡፡ ነገሩን ለማገጣጠም ይረዳ ዘንድ ማኀበሩ ተመሠረተ የተባለበትንና (የሞተውን ሥርዓት ለመመለስ) ፓትርያርኩ የተገደሉበትን ምክንያት እንዴት ተደርጎ እንደሚገጣጠም ብልሃት የሚገኝለት አይመስለኝም እንጂ ፣ ጥቆማው ለታሪክ ጸሃፊዎች ደግ ነበር ፡፡ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የሕይወት ታሪክ በአጭሩ የሚል ጽሁፍ ግን ለመሞት ያበቃቸውን ምክንያቶች ሲዘረዝር እንዲህ እንደተነበበው ማኀበሩ ነው ብሎ አላስቀመጠውም ፡፡ ለጊዜው በመንግሥት የተወነጀሉባቸው ምክንያቶች ሲጠቅስ

  o የተሾሙት በንጉሥ ወዳጅነታቸው በመሆኑ (ለሞተው ሥርዓት ባለሟልነታቸውንና ቀረቤታቸውን ልብ ይሏል) ፤ የተመረጡትም በሚቀርቧቸው ሰዎችም መሆኑ ፤
  o የካፒታሊዝም ሥርዓት በመከተል ለንግድ የሚሆን ሕንጻ በቤተ ክርስቲያን ስም እያስገነቡ ስለሆነ ፤
  o የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ በግል ስማቸው በተለያየ ባንኮች ስለአከማቹ ፤
  o ሦስት ጳጳሳትን ከሥርዓት ውጭ በግላቸው ስለሾሙ ፤
  o ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አፍርሰው በራሳቸው አካሄድ ስለተመሩ የሚሉ ናቸው

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 17. ሁለተኛው ክፍል
  - ሌላው የማኀበሩ ስውር ሥራ ነው ብሎ የተጠቀሰውም ጳጳሳትን በገንዘብ መደለሉንና ፣ የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸውን ደግሞ በድክመታቸው በማስፈራራት የራሱ ዓላማ ፈጻሚ አድርጎ እንደያዛቸው ነው ፡፡ ለዚህ አባባል ቀደም ማስረጃ ከነበረ እስከ ዛሬ ድረስ ማን ስለምን ምክንያት ይጠበቅ ነበር ? መረጃውስ ያላችሁ ሰዎች እስከዚህ ቀን ምን እያደረጋችሁ ቆያችሁ የሚል ጥያቄን ያስነሳል ፡፡ የቃል ማደነባበር ወይስ ሌባ የሚጣላው መከፋፈል ሲጀምር በመጨረሻዋ ሰዓት ነው ብለን ራሳችንን እናንቃና እናንተም የጉዳዩ ባለቤቶች ናችሁ እንበል ፡፡

  - የማኀበሩ ሥውር ዓላማ ናቸው ከተባሉት ውስጥ የአፄው አሠራርን ለመመለስና የሸዋን መሳፍንታዊ አገዛዝ ለመመሥረት የሚል ይገኝበታል ፡፡ እዚህ ጋርም የማነሳው ጥያቄ ከላይ በደርግ አባላት ተመሠረተ የተባለ ማኀበር እንደምን ከአፄው ጐራ ከተፈረጁ ሰዎች ሊወዳጅ ይችላል ? ከመግቢያ የተቀመጠው የደርግ ንክኪን እንደ ምን አድርገን እንሠርዝና ይህኛውን እንቀበል ? የምናነበው የቤተ ክርስቲያን ያለፈ ታሪክ ከሞላ ጎደል ነገሥታቱ በሙሉ ፈሪሃ እግዚአብሔር እንደነበሩ ፣ ቤተ ክርስቲያን እንድታድግና እንድትጠናከር ሳይሰለቹ ይሠሩም እንደነበርና የተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንደነበሩም ነው ፡፡ ሃይማኖት መድከምና መርከስ የጀመረው ፣ የማይሳለምና የማያስቀድስ መሪም የታየው ፣ ቤተ ክርስቲያንም ፈተና ውስጥ የወደቀችው ፣ ከደርግ አንስቶ በተነሱ መሪዎቻችን እንደሆነ ማንም ሊክደው አይችልም ፡፡ ትውልዱ አላለፈምና ሽፍጠት እየተደረገ እንደሆነ በቀላሉ ይታወቃል ፡፡

  - ከወደ ሃምሳ ከሚጠጉ የሲኖዶስ ጳጳሳት መሃከልም ተመርጠው ሰባቱን ከሸዋ እንደሆኑ ይገልጻል ፡፡ ይኸ ጠባብ የመንደርተኝነተ ትምህርት ፣ የተቀሩትን ጳጳሳት የጐሳ ስብጥር እንዴት እንደሆነ አሟልቶ አይገልጽም ፤ ወይስ ከዚህ ቀደም ከሸዋ ጳጳስ እንዳይሾም የሚል ውግዘት ነበር ማለት ይሆን ፡፡ ነገ ደግሞ የጐንደር ጳጳሳትን ቀጥሎም የጎጃምና …. ጳጳሳት እየተባለ የማይፈለገውን በተናጠል ለመምታት ዕቅድ ተይዞ እንዳይሆን እሰጋለሁ ፡፡ የጎሳ ጥናቱ ለቤተ ክርስቲያን ጥንካሬ ፣ ለወንጌልም መስፋፋት የሚረዳ መሆኑ ከታመነበት ጠቅላላ የጳጳሳቱን ዝርያ ዝርዝር አለፍም ብሎ በየቢሮው ቁልፍ ቦታዎች ላይ የተሰገሰጉትን ኃላፊዎች ሁሉ መዳስስና ማስነበብ ያስፈልግ ነበር ፡፡ ክርስቶስ ግን እንዲህ በዓይነታችሁና በመልካችሁ ተሰለፉልኝ ብሎ አላስተማረንምና ፣ ስለሃይማኖት ብቻ ከሆነ የምንነታረከው ጠቃሚ ርዕስ አይደለም ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ሁሉን ተረድቶ ፣ ሌላው ቀርቶ የሁለት አገር ዜጎች የተደረጉት ፣ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን እንኳን በአንድ ቤተ ክርስቲያን እየተሰበሰቡ ማስቀደስና ጸሎት ማድረስ ጀምረዋል ፡፡ ታድያ ይኸ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለመሸንቀር የተፈለገ የጐጠኝነት ተስቦ ከወዴት ፣ ስለምንስ የተነሳ ነው እንበለው ?

  - በሌላም ቦታ በፖለቲካ ቀለም አቅልሞ ማኀበሩን ለማስመታትና ለማጥቃት አልሞ እንደሆን አይታወቅም “ለሃገር ተረካቢ ወጣት ምሁራን የገዥውን ፓርቱ አስከፊነት በመግለጽ” የሚል ቃል አስነብቧል ፡፡ ከላይ እንዳቀረብኩት አሁንም ይኸ መረጃ ቀድሞ ከነበረ ሲኖዶስ ተሰብስቦ እስከሚወስንና በብስጭት ተገፋፍታችሁ መርዝ እስከ ምትረጩ ለምን በዝምታ አለፋችሁት? ወይስ እናንተም በስውር እንዲያ እያላችሁ ታስተምሩ ነበር ? ሃይማኖትን ከማይረባት ሥፍራ ወስዶ መቀላቀል ዳፋው የሚተርፈው ለራስም ጭምር ነውና አስቡበት ፡፡ መንግሥትንም በሃይማኖት መካከል የፖለቲካ ምዕራፍና አምድ ለማስያዝ መቀስቀሱ ዘላቂ የቤተ ክርስቲያንን ሰላምን አያስገኝም ፡፡

  - በመጨረሻው ገለጻ ደግሞ በውጭ በስደት ላይ የሚገኙትን ወገኖችና የመንግሥት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችንም ህልመኛ በማለት ይገልጻቸዋል ፡፡ እንግዲህ ጸሃፊው ሃይማኖትን እየሰበኩ ወይስ አቋም ወስደው የመንግሥትን ቃል እየተቀበሉ እንደ ፖለቲከኛ እየተናገሩን ነው ይባላል ፡፡ እንግዲህ ይህን ጽሁፈ ያነበበ ፣ የሚያስተምሩት ስለ መስቀሉ ላይ መስዋዕት እንጅ ስለ ነፍጥ አይደለም ብሎ እንዴት ደፍሮ ይከራከራል ? እያደር ብዙው የተደበቀው ማንነታችሁን እያሳወቃችሁን ነው ፡፡ ይኸ ለማንም ስለማይረባ ወደ ወንጌል ትምህርት ብትመለሱ ይሻላል እላለሁ ፡፡ ዓለማዊ ንጉሥን መከተልና ማገልገል ፣ ዓላማው ምድራዊ ነው ፤ ሁሉም ሥራው በሰዎች ዕድሜ የተወሰነ ስለሆነ ቀጣይነትም አይኖረውም ፤ ሰማያዊውን በረከትም አያስገኝም ፡፡ መንግሥት የሚገባውን ሃገር የመምራት ሥራውን ያከናውን ፤ የሃይማኖት መሪዎችም ስለሃይማኖት ብቻ ያስተምሩ ፡፡

  ReplyDelete
 18. are you foulish? Don't fight with God...if you do it you will pay the price ....

  ReplyDelete
 19. wenidm keshi,

  yegeta selam yibizalih
  kelay yezerezerikachew menekosat(nen yemilu) shewa baihonum hodachew amilakachew silehonu begenizeb shewa honewal. wanaw neger gin egnan yemiyasasiben yekilil guday ayidelem keziya balefe agerachin besemay new bilen beketero yalen sewochi yihe yezer guday ayasichenikenim. neger gin bezih yetamemu sewoch bebetekirisitiyanachin lay yemiyderisutin tifat abiliten enimeliket. manibebachin kewere balefe yihun. kezi gimash keziya gimash eyalin kehone yasaseben yewere guday new yemihonew. anigebigabiwu guday enidekidus paulos yemiyasicheniken guday yebetekirisitiyan yihun.

  ReplyDelete
 20. I think you have gone out of mind. You seem very mad and for that you seem writing a baseless report. How come that some of the mentioned Bishops are from Shewa? I am afraid and sorry for you. Please come to true senses. Think of well what you will answer when you stand in God's justice, just in front of Him!

  ReplyDelete
 21. God bless YOU!

  ReplyDelete
 22. May God forgive both groups, what do you get out of accusing each other instead of preaching the gospel of our Lord. Is this how you want the e.o.c to be represented?
  This is the internet. Everyone sees it (not only members).
  Please take a minute to realize the weight of what you post.

  ReplyDelete
 23. EGZIABHER YEMSERETEWN MAN YAFERSEWAL?

  ReplyDelete
 24. በአባቶች ስም የተከፈተው ብሎግ የለበሰው ለምድ ቢወልቅ ምን ሊመስል እንደሚችል ለሁሉም ግልጽ ሆነ በራሱ አንደበትና ምግባር ለምን ይሆን ሁል ጊዜ አንድን ማኅበር በመኮነን የሚጽፈው እኔ መጠራጠር ጀመር ምክየቱም የሁለቱንም ብሎግ ሳነብ የማገኘው ነገር በአቡነ ሰላማ ስም የተከፈተው ብሎግ የሚጽፈውና ለሰው ልጆች እንዲያነቡት የሚጋብዘው ዘረኝነትን፣ ፖለቲካንና መለያየትን ነው እኔ ወንጌልን ጠለቅ ብዬ ባልውቀውም ከአባቶች እንደምሰማው መወንጀል ሰው ባልዋለበት ማንሳት የክርስትና ምግባር አይደለም ስለዚህ ምንድነው ዓላማችሁ ለማንኛውም ለእኔ አሁን ገብቶኛል፡፡ ማለቴ ለሆዳችሁ ለሚከፍላችሁ እንደ ቱቦ አስተላላፊ መሆንችሁ

  ReplyDelete
 25. የዚህ ጥሁፍ ማንም ሆነ ማን ምን ለማለት እንደፈለገ ግልፅ መሰለኝ… ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያነጣጠረ መሆኑ..እባካችሁ እግዚአብሔርን ፈርታችሁ ከዚህ ውዳቂ ተግባራችሁ ሽሹ፡፡ ከዚህ ይልቅ መልካም ስራ የሚሰሩትን ከህዝብ አታጣሉ..ለነገሩ ለሁላችንም ተመልካች አለን በእርሱ ፊት ምናልባት መቆም ከቻልን ምን እንላለን፤please don’t try to be loved with foolish and arrogant ideology. Let God help and keep healthy Ethiopia

  ReplyDelete
 26. አንድ ያነበብኩት ጽሁፍ “መንፈሳዊ /ኦርቶዶክሳዊ/ ሥነ ጽሑፍ የሚባለው ዓላማው ነገረ እግዚአብሔርን ማስተማር ምግባረ ሃይማኖትን መስበክ ነው ፡፡ የሥነ ጽሑፉ ግብ እግዚአብሔር ለሰዎች ያደረገውን ቸርነት ፣ የሰውንና የእግዚአብሔርን ግንኙነት ፣ የቅዱሳንን ገድል ፣ የጠላት ዲያብሎስን ግብር ወዘተ በማሳየት ሰውን በእምነቱ ጸንቶ እንዲኖር መምከር ነው ፡፡” ይላል ፡፡ ይህ ያስነበባችሁን ጽሁፍ ግን ከመንፈሳዊነት ያፈነገጠ ፣ ነገረ እግዚአብሔርን የረሳና በምድራዊና በዓለማዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ፡፡ ሆኖም ግን ስለቀረበው ጽሁፍ ያለኝን አስተያየት ለማስነበብ ጫጭሬአለሁ ፡፡

  - ጽሁፉ ገና ከመጀመሩ ማኀበረ ቅዱሳንን የሚመድበው የፖለቲካ ድርጅት አድርጎ ነው ፡፡ ቀጠል በማድረግ ይህንኑ አባባሉን ለማጠናከር ሲያብራራም የተሃድሶ ጉባዔ ኮሚቴ በሚባሉት በእነ ኮሎኔል አጥናፉ አባተ እንደተመሠረተ ያትታል ፡፡ ኋላ ላይ ሌላ ስም ካልወጣለት እስከዚህ በተነበበው እንግዲህ የደርግ አባላት ድርጅት ነበረ ለማለት እንደፍራለን ፡፡ በሎጅክ ደግሞ ኢህአዴግ ሲፋለም የኖረው ከደርግ እና ከርዝራዦቹ ጋር ስለነበረና ስለሆነ የውጊያ ቀጠናውን ወደዚሁ ማኀበር ማነጣጠር እንደሚገባው የማንቃት ጥሪም ይመስላል ፡፡ የማህበሩ አገልሎትን ም አጠቃልሎ ሲያስረዳን ሁለት መልክ እንደ ነበረው - አንድም የሞተውን ሥርዐት መመለስ እና የየግል ጥቅምንን ማሳደግ እንዲሁም በሃይማኖት ሽፋን ስውር አላማን ማስፈጸም መሆኑን ይገልጻልል ፡፡ ይህም ከመንዳዮችን ለማነካካት የታቀደ አባባል ነው ፡፡ ደርግ የሚከተለው ርዕዮተ ዓለም እግዚአብሔር የለም የሚያስብለው ሲሆን ፣ ማንን ለማምለክ ብሎ የሃይማኖት ድርጅት ፈጠረ ብለን ሃሳቡን እንመን ?

  - ስለ ማኀበረ ቅዱሳን አመሠራረት ማስረጃና ምስክር አለን በማለት ፣ ከአንድም ሁለት መጽሐፍ የጻፉት ሌሎች ግለሰቦች /አቶ ጽጌ ስጦታውና ዲያቆን ሙሉጌታ ወ/ገብርኤል/ ደግሞ ማኀበሩ የዛርና የጥንቆላ መንፈስ በሠፈረባቸው አሥራ ወጣቶች ፣ እንደ ቀልድ ሰፈር ውስጥ እንደ ተመሠረተና ፣ ወንጀልን ከመጀመሪያው ሥራዬ ብሎ በመያያዙ እስከ ህግ ድረስ እንደደረሰ ጽፈው አንብበናል ፡፡ ማኀበረ ቅዱሳን ደግሞ ለራሱ የራሱን አመሠራረት ሌላ ታሪክ ይናገራል ፡፡ ይህም ማለት ማኀበሩ የተመሠረተበት የተለያዩት መንገዶች ፣ ለጊዜው አንድም ሦስት ናቸው ማለት ነውና አንባቢ የማንን ዕውነት እንደሚከተል ለራሱ ይምረጥ ፡፡ ምናልባት አራተኛውና አምስተኛው የማኀበሩ የሥነ ፍጥረት ታሪክ ደግሞ በሂደት ወደፊት መምጣቱ አይቀርምና ለመጠበቅም ይቻላል ፡፡

  - በወቅቱ ፓትርያርክ የነበሩትን ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስን አሳንቆ ያስገደለም ይኸው ጨቅላ የጨለማ ማኀበር እንደሆነ ይናገራል ፡፡ ነገሩን ለማገጣጠም ይረዳ ዘንድ ማኀበሩ ተመሠረተ የተባለበትንና (የሞተውን ሥርዓት ለመመለስ) ፓትርያርኩ የተገደሉበትን ምክንያት እንዴት ተደርጎ እንደሚገጣጠም ብልሃት የሚገኝለት አይመስለኝም እንጂ ፣ ጥቆማው ለታሪክ ጸሃፊዎች ደግ ነበር ፡፡ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የሕይወት ታሪክ በአጭሩ የሚል ጽሁፍ ግን ለመሞት ያበቃቸውን ምክንያቶች ሲዘረዝር እንዲህ እንደተነበበው ማኀበሩ ነው ብሎ አላስቀመጠውም ፡፡ ለጊዜው በመንግሥት የተወነጀሉባቸው ምክንያቶች ሲጠቅስ

  o የተሾሙት በንጉሥ ወዳጅነታቸው በመሆኑ (ለሞተው ሥርዓት ባለሟልነታቸውንና ቀረቤታቸውን ልብ ይሏል) ፤ የተመረጡትም በሚቀርቧቸው ሰዎችም መሆኑ ፤
  o የካፒታሊዝም ሥርዓት በመከተል ለንግድ የሚሆን ሕንጻ በቤተ ክርስቲያን ስም እያስገነቡ ስለሆነ ፤
  o የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ በግል ስማቸው በተለያየ ባንኮች ስለአከማቹ ፤
  o ሦስት ጳጳሳትን ከሥርዓት ውጭ በግላቸው ስለሾሙ ፤
  o ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አፍርሰው በራሳቸው አካሄድ ስለተመሩ የሚሉ ናቸው

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 27. ሁለተኛው ክፍል
  - ሌላው የማኀበሩ ስውር ሥራ ነው ብሎ የተጠቀሰውም ጳጳሳትን በገንዘብ መደለሉንና ፣ የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸውን ደግሞ በድክመታቸው በማስፈራራት የራሱ ዓላማ ፈጻሚ አድርጎ እንደያዛቸው ነው ፡፡ ለዚህ አባባል ቀደም ማስረጃ ከነበረ እስከ ዛሬ ድረስ ማን ስለምን ምክንያት ይጠበቅ ነበር ? መረጃውስ ያላችሁ ሰዎች እስከዚህ ቀን ምን እያደረጋችሁ ቆያችሁ የሚል ጥያቄን ያስነሳል ፡፡ የቃል ማደነባበር ወይስ ሌባ የሚጣላው መከፋፈል ሲጀምር በመጨረሻዋ ሰዓት ነው ብለን ራሳችንን እናንቃና እናንተም የጉዳዩ ባለቤቶች ናችሁ እንበል ፡፡

  - የማኀበሩ ሥውር ዓላማ ናቸው ከተባሉት ውስጥ የአፄው አሠራርን ለመመለስና የሸዋን መሳፍንታዊ አገዛዝ ለመመሥረት የሚል ይገኝበታል ፡፡ እዚህ ጋርም የማነሳው ጥያቄ ከላይ በደርግ አባላት ተመሠረተ የተባለ ማኀበር እንደምን ከአፄው ጐራ ከተፈረጁ ሰዎች ሊወዳጅ ይችላል ? ከመግቢያ የተቀመጠው የደርግ ንክኪን እንደ ምን አድርገን እንሠርዝና ይህኛውን እንቀበል ? የምናነበው የቤተ ክርስቲያን ያለፈ ታሪክ ከሞላ ጎደል ነገሥታቱ በሙሉ ፈሪሃ እግዚአብሔር እንደነበሩ ፣ ቤተ ክርስቲያን እንድታድግና እንድትጠናከር ሳይሰለቹ ይሠሩም እንደነበርና የተዋህዶ እምነት ተከታዮች እንደነበሩም ነው ፡፡ ሃይማኖት መድከምና መርከስ የጀመረው ፣ የማይሳለምና የማያስቀድስ መሪም የታየው ፣ ቤተ ክርስቲያንም ፈተና ውስጥ የወደቀችው ፣ ከደርግ አንስቶ በተነሱ መሪዎቻችን እንደሆነ ማንም ሊክደው አይችልም ፡፡ ትውልዱ አላለፈምና ሽፍጠት እየተደረገ እንደሆነ በቀላሉ ይታወቃል ፡፡

  - ከወደ ሃምሳ ከሚጠጉ የሲኖዶስ ጳጳሳት መሃከልም ተመርጠው ሰባቱን ከሸዋ እንደሆኑ ይገልጻል ፡፡ ይኸ ጠባብ የመንደርተኝነተ ትምህርት ፣ የተቀሩትን ጳጳሳት የጐሳ ስብጥር እንዴት እንደሆነ አሟልቶ አይገልጽም ፤ ወይስ ከዚህ ቀደም ከሸዋ ጳጳስ እንዳይሾም የሚል ውግዘት ነበር ማለት ይሆን ፡፡ ነገ ደግሞ የጐንደር ጳጳሳትን ቀጥሎም የጎጃምና …. ጳጳሳት እየተባለ የማይፈለገውን በተናጠል ለመምታት ዕቅድ ተይዞ እንዳይሆን እሰጋለሁ ፡፡ የጎሳ ጥናቱ ለቤተ ክርስቲያን ጥንካሬ ፣ ለወንጌልም መስፋፋት የሚረዳ መሆኑ ከታመነበት ጠቅላላ የጳጳሳቱን ዝርያ ዝርዝር አለፍም ብሎ በየቢሮው ቁልፍ ቦታዎች ላይ የተሰገሰጉትን ኃላፊዎች ሁሉ መዳስስና ማስነበብ ያስፈልግ ነበር ፡፡ ክርስቶስ ግን እንዲህ በዓይነታችሁና በመልካችሁ ተሰለፉልኝ ብሎ አላስተማረንምና ፣ ስለሃይማኖት ብቻ ከሆነ የምንነታረከው ጠቃሚ ርዕስ አይደለም ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ሁሉን ተረድቶ ፣ ሌላው ቀርቶ የሁለት አገር ዜጎች የተደረጉት ፣ ኤርትራውያንና ኢትዮጵያውያን እንኳን በአንድ ቤተ ክርስቲያን እየተሰበሰቡ ማስቀደስና ጸሎት ማድረስ ጀምረዋል ፡፡ ታድያ ይኸ በቤተክርስቲያን ውስጥ ለመሸንቀር የተፈለገ የጐጠኝነት ተስቦ ከወዴት ፣ ስለምንስ የተነሳ ነው እንበለው ?

  - በሌላም ቦታ በፖለቲካ ቀለም አቅልሞ ማኀበሩን ለማስመታትና ለማጥቃት አልሞ እንደሆን አይታወቅም “ለሃገር ተረካቢ ወጣት ምሁራን የገዥውን ፓርቱ አስከፊነት በመግለጽ” የሚል ቃል አስነብቧል ፡፡ ከላይ እንዳቀረብኩት አሁንም ይኸ መረጃ ቀድሞ ከነበረ ሲኖዶስ ተሰብስቦ እስከሚወስንና በብስጭት ተገፋፍታችሁ መርዝ እስከ ምትረጩ ለምን በዝምታ አለፋችሁት? ወይስ እናንተም በስውር እንዲያ እያላችሁ ታስተምሩ ነበር ? ሃይማኖትን ከማይረባት ሥፍራ ወስዶ መቀላቀል ዳፋው የሚተርፈው ለራስም ጭምር ነውና አስቡበት ፡፡ መንግሥትንም በሃይማኖት መካከል የፖለቲካ ምዕራፍና አምድ ለማስያዝ መቀስቀሱ ዘላቂ የቤተ ክርስቲያንን ሰላምን አያስገኝም ፡፡

  - በመጨረሻው ገለጻ ደግሞ በውጭ በስደት ላይ የሚገኙትን ወገኖችና የመንግሥት ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችንም ህልመኛ በማለት ይገልጻቸዋል ፡፡ እንግዲህ ጸሃፊው ሃይማኖትን እየሰበኩ ወይስ አቋም ወስደው የመንግሥትን ቃል እየተቀበሉ እንደ ፖለቲከኛ እየተናገሩን ነው ይባላል ፡፡ እንግዲህ ይህን ጽሁፈ ያነበበ ፣ የሚያስተምሩት ስለ መስቀሉ ላይ መስዋዕት እንጅ ስለ ነፍጥ አይደለም ብሎ እንዴት ደፍሮ ይከራከራል ? እያደር ብዙው የተደበቀው ማንነታችሁን እያሳወቃችሁን ነው ፡፡ ይኸ ለማንም ስለማይረባ ወደ ወንጌል ትምህርት ብትመለሱ ይሻላል እላለሁ ፡፡ ዓለማዊ ንጉሥን መከተልና ማገልገል ፣ ዓላማው ምድራዊ ነው ፤ ሁሉም ሥራው በሰዎች ዕድሜ የተወሰነ ስለሆነ ቀጣይነትም አይኖረውም ፤ ሰማያዊውን በረከትም አያስገኝም ፡፡ መንግሥት የሚገባውን ሃገር የመምራት ሥራውን ያከናውን ፤ የሃይማኖት መሪዎችም ስለሃይማኖት ብቻ ያስተምሩ ፡፡

  ReplyDelete
 28. እናንተ የናንተ የሆነ ሀሳብ የላችሁም ሁሌ ከ ማክ ጋ ነዉ ጠባችሁ ምንድን ነዉ ላማችሁ ነዉ አላማ የላችሁም አላማ የለሾች

  ReplyDelete