Tuesday, May 29, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ስውር አመራሮች እጅ በውጭ ያለውን ሲኖዶስ ሲፈታተን

ምስክር ከአሜሪካ (ጸሐፊው የአባት ስም ጨምረው አልላኩም)
በሃይማኖት ሽፋን የተሰባሰቡ ፖለቲከኞች ስብስብ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን የሲኖዶስ ስብሰባ በቀረበ ቁጥር የሲኖዶስ ስብሰባዎችን በማወክ ግብር መገለጥ ከጀመረ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው። በአገር ውስጥ ተወስኖ የነበረውን ይህን እኩይ ተግባሩን በውጭ አገር በሚገኘው ስደተኛው ሲኖዶስ መካከልም ተግባራዊ ለማድረግ መንቀሳቀሱንና በተወሰነ መልኩ የተሳካለት መስሎ እየታየ መሆኑን አንዳንድ ምንጮች እየገለጹ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን በስውር አመራሮቹ በኩል በአሁኑ ጊዜ በውጭ ያለውን ሲኖዶስ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ የቀረበው ለምን እንደሆነ በውጭ የሚገኙ አባቶች በሚገባ መረዳት አለባቸው የሚል እምነት አለኝ።ከዚህ ቀደም ከአገር ቤት ወደ አሜሪካ ተልከው እዚያ ተመድበው የነበሩትን የማኅበሩን ደጋፊ አባ አብርሃምን በመጠቀም ማኅበሩ የራሱን አቅም ይበልጥ ለማጠናከር በር ተከፍቶለት የነበረ ሲሆን፣ እርሳቸው ለቤተክርስቲያኒቱ ሳይሆን ለማኅበረ ቅዱሳን ጥቅም መቆማቸው በመረጋገጡ በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እንዲተኩ ተደርጓል። እርሳቸውም ቤተክርስቲያኒቱን ከማቅ ሕገ ወጥ አሰራር ነጻ ለማድረግ የጀመሩትን ጥረት ለማደናቀፍ የተንቀሳቀሱትን የዶ/ር መስፍንን «ክህነት» መሻራቸው በማኅበሩ ላይ ትልቅ ኪሳራ ማስከተሉን ከማኅበሩ ውስጥ አዋቂዎች እየተገለጸ ነው። ይህም የማኅበሩ ስውር አመራር በአገር ቤት ያለውን ብቻ ሳይሆን በውጪ የሚገኘውን ሲኖዶስም ቆርጦ ለመግባትና ለመከፋፈል የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል አድርጎታል። ለውጪው ሲኖዶስ እንደ እጅ መንሻ ይዞ የቀረበውም የዋልድባን ጉዳይ ሲሆን፣ ስውር አመራሩ ቀደም ብሎ የዋልድባን ጉዳይ በማንቀሳቀስና ህዝብን ለተቃውሞ በማነሳሳት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ በአሜሪካ የተቃውሞ ሰልፍና የሚዲያ ላይ ዘመቻ በመክፈትና አጀንዳውን ወደ አቡነ መልከጼዴቅ በሚያምኑት ሰው በኩል ይዞ ጠጋ በማለት የእርሳቸውን ትኩረት ለመሳብ ጥረት አድርጓል። በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲና በሎስ አንጀለስ በዋልድባ ዙሪያ ይካሄዳል የተባለው ሰላማዊ ሰልፍ እየተመራ ያለው በማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሏል። ማኅበሩ የዋልድባ ጉዳይ ጨንቆት ሳይሆን በጉዳዩ ቅር የተሰኘውን በስደት የሚኖረውን ኦርቶዶክሳዊ ለመጠቀም እና ሌሎች የራሱን አጀንዳዎች ለመፈጸም እንደሆነ በሚያካሂዱት የቴሌኮንፍረንስ ውይይት ውስጥ ገብቶ ለሚያዳምጥ ግልጽ ነው። አሁን እንደሚስተዋለው በዚህ ማኅበረ ቅዱሳን በሚመራው ቴሌኮንፍረንስ እና ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በስደተኛው ሲኖዶስ ታቅፈው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትም ሳያውቁ እየተሳተፉበት ነው። ይህ ሁኔታ በኋላ የሚያስከትለው ፈተና ለአብያተ ክርስቲያናቱና አገልጋዮች ካህናት የታያቸው አይመስልም።  ማቅ እያደረገች ያለችው የዋልድባን ጉዳይ ተጠቅማ፣ እውቅናን ለማትረፍ፣ ከዚያም በስደት ባሉ አብያት ክርስቲያናት ውስጥ ሰርጎ በመግባት በፊት ሞክረው ያልተሳካላቸውን የመከፋፈል ስራ ለማከናወን ነው።  ይህንንም ለመከላከል ካህናቱ፣ ምዕመናኑ እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ነቃ ነቃ እንዲሉ ለማሳሰብ እወዳለሁ።
የማኅበረ ቅዱሳን ስውር አመራር ስደተኛውን ሲኖዶስ ለፖለቲካ መሸሸጊያነት እንጂ ለሌላ እንደማይፈልገው ይታወቃል። በውጪ ያሉ አባቶች በአገር ውስጥ ካሉት አባቶች ጋር ታርቀው ቤተክርስቲያን አንድ እንድትሆንም ማኅበሩ አይፈልግም። የእነርሱ መታረቅና አንድ መሆን ለማኅበሩ ህልውና አስጊ ነውና። ምክንያቱም በውጪ ያለችው ቤተክርስቲያን ብዙዎቹ አገልጋዮች ማኅበሩ ከአገር ውስጥ «መናፍቅ» «ተሀድሶ» ወዘተ እያለ አለስማቸው ስም እየሰጠ በህገወጥ መንገድና በሌለው ስልጣን በጉልበት ያሳደዳቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ስለሆኑ፣ ሁለቱ ወገኖች ከታረቁ ኪሳራው ለማኅበሩ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ሁለቱ ወገኖች እንዳይታረቁ ጠንክሮ ይሰራል። በአገር ውስጥ የውጪውን፣ በውጪ ደግሞ የአገር ቤቱን ሲኖዶስ ሲነቅፍ የኖረውም ለዚሁ ነው። ይህ አካሄዱ ሁለቱም እንደተጣሉ ሳይታረቁ እንዲኖሩና ከሁለቱም ጋር ተስማምቶ ለመኖር የሚያደርገው ጥረት አካል ነው። 
ከዓመታት ሙከራዎች በኋላ የዘንድሮውን የሲኖዶስ ስብሰባ በተወሰነ መልኩ የተሳካ የተባለለትን ክፍፍል በውጪው ሲኖዶስ አባላት መካከል ለመፍጠር ምክሯል። ለዚህ ዋናው ተዋናይ የሆነው ደግሞ ዶ/ር ነጋ ዓለማየሁ የሚባለው ግለሰብ ሲሆን የማቅ ቀንደኛ አባላት ከሆኑት ከወንድሙ ቄስ ፋሲል እና ከሌላው ጓደኛው ጋር በመመሳጠር በጣዕመ ስብከታቸው የማኅበረ ቅዱሳንን መንደር ባዶ እያስቀሩት ያሉትን አባቶችና ወንድሞች ስም ማጥፋትና በውጪው ዓለም ተቀባይነት እንዲያጡ በማድረግ ስፍራውን ለማኅበረ ቅዱሳን መፈንጫነት እያመቻቸ ነው። እነ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ግን ሣሩን እንጂ ገደሉን አላዩም። ስለዚህ ከዚህ ከማቅ ስውር አመራር ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለውን ዶ/ር ነጋን በማቅረብ ሐዲስ ሐዋሪያ እያሉ ሲያሞካሿቸው በኖሩት በአባ ወልደ ትንሣኤ ላይ እስከ ማሳሰር የደረሰ እርምጃ ሲወሰድ መደገፋቸው ብዙዎችን አስገርሟል።
ዶ/ር ነጋ ጉዳዩን እዚህ ደረጃ ላይ ለማድረስ ውስጥ ውስጡን ልዩ ልዩ ሴራዎችን ሲሸርብ ቆይቷል። ወደ አባ ወልደትንሣኤ ከመሸጋገሩ በፊት የዲሲ ቅዱስ ገብርኤል ሰባኬ ወንጌል የነበረውን መምህር እንዳልካቸውን ያባረረ ሲሆን፣ በአባ ወልደ ትንሣኤ ላይም ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ውስጥ ውስጡን ከፍቶባቸው ቆይቷል። እነርሱን ከህዝበ ክርስቲያኑ እየነጠለ ለመሄድም ያልዋለበትን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማገልገል ራሱ ነጠላ እየለበሰ ልስበክ ማለት ጀምሯል። ከዚህ ቀደም በደብሩ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ሁለት ጳጳሳትና አንድ ካህን በሲኖዶሱ ተልከው ቢሄዱ ፖሊስ እጠራለሁ ብሎ ማባረሩ (በወቅቱ የነበረውን የቦርድ ሊቀመንበር አታሎ) የግለሰቡን ማንነትና በሃይማኖት ስም እያራመደ ያለውን ድብቅ ዓላማ አመላክቷል። ቤተክርስቲያን እንደ እነዚህ ባሉ ተንኮከኞች ቁጥጥር ስር መዋሏና አባቶቻችን በጨዋ ምእመናን እንዲመሩ የተደረገበትን አሰራር በውጪ ያለው ሲኖዶስ እንደገና ሊያጤነውና ሁሉም በየተጠራበት መጠራት እንዲመላለስ ሊያደርግ ይገባል። አንዳንድ ከካህናት ወገን የሆኑትም ከሃይማኖት ይልቅ በፖለቲካው ሰልፍ ውስጥ መቆማቸው ለእነ ዶ/ር ነጋ የልብ ልብ እንደሰጣቸው ይታወቃል።
በምድረ አሜሪካ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በቦርድ የሚመሩ ቢሆንም፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ስርአትና የቤተክርስቲያናችን የአመራር ስርአት መከበር አለበት። አሊያ ቤተክርስቲያንን የመምራቱን ቁልፍ እንደነዶ/ር ነጋ ያሉ ደፋሮችና ጮሌዎች ከነጠቁ ቤተክርስቲያን ተልእኮዋን በሚገባ መፈጸም አትችልም። ዛሬ እንደሚታየው ከክርስቲያኖች መካነ ጸሎትነት ወደፖለቲከኞች ጽ/ቤትነት መዛወሯ አይቀርም። በአባ ወልደትንሣኤ የደረሰው ነገ እንዳይደገም በውጭ ያለነው ኦርቶዶክሳውያን ከአሁን ልንነቃ ይገባል። ይህ አካሄድ ነገ በሌሎች አባቶች እንደማይደገም ምንም ዋስትና የለንም። ሁኔታዎች የሚጠቁሙትም ይህንኑ ነውና።
ይኸው ግለሰብ በአባ ወልደትንሣኤ የሞከረውና ጥቂት ውጤት ያገኘበትን አካሄድ እያጠናከረና ኔትዎርኩን እየዘረጋ መሆኑ ከጊዜ ወደጊዜ እየታየ ነው። ይኸው ጨካኝ ግለሰብ የሰራው ስራ አልበቃ ብሎት ጥፋቱን እጅግ በሚዘገንኑ ውሸቶች ለመሸፋፈን እና አባ ወልደ ትንሣኤ ላይ ጥላሸት ለመቀባት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው። በቅርቡ ሁለት አባቶችን ይዞ እነዚሁ አባቶች በኢትዮጵያን ሪቪዩ ድረ ገጽ ላይ በግልጽ እንዲዋሹ አድርጓል። የፈጸሙትን ተንኮል ሲፈጽሙ ሌላ ሰው የሌለ ይመስል አይን ያወጣ ውሸት እስከመዋሸት መደረሱ ብዙዎችን አስደንግጧል። ዶ/ር ነጋስ ለዓላማው ነው፤ አባቶች ግን በዓይናቸው ሳያዩ፤ ዶክተሩ በነገራቸው ብቻ ተመርኩዘው ውሸት አብረው ለመዋሸት መተባበራቸውና የአገልግሎት ወንድማቸውን ለመጣል መትጋታቸው ለአእምሮ የሚከብድ ነው። በውኑ እግዚአብሔር አያይምም፣ አይፈርድምም መስሏቸው ይሆን? አባ ወልደ ትንሣኤን በሚገባ በሚያውቃቸው ህዝብ ዘንድና በስፍራው ሁሉን ነገር ሲከታተሉ ለነበሩ የማይረሳ ትዝብትን አትርፈዋል። ይህን ሁሉ የሚያደርገው ጥንተ ጠላታችን ዲያቢሎስ ነውና እግዚአብሔር ይገስጸው።  ዶ/ር ነጋና ግብረ አበሮቹ በሌሎቹ አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ የውጪው ሲኖዶስ አካል የሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ወንጌል የሚሰብኩ አባቶችንና ወንድሞችን ስም ዘርዝሮ እነርሱን እንዳይጋበዙ ስልክ እየደወለ ለማሳደም እየሞከረ ነው። በአንጻሩ ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች እንዲሰብኩ በማድረግ ቤተክርስቲያንን ከወንጌል ወደ ማኅበሩ ተረታተረት የመመለስ ዕቅድ እንዳለው ከፍተኛ ግምት አለ። ለዚህም በውጪ ያሉ የአብያተ ክርስቲያናት ቦርድ አባላት ውስጥ የማኅበሩን ደጋፊዎችና ስውር አመራሮችን በስርዋጽ ማስገባት ማኅበሩ የያዘው አንዱ ስትራቴጂ መሆኑን በውጭ ያሉ አንዳንድ ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እየተናገሩ ነው። አላማቸውና ግባቸው ከላይ እንደተገለጠው ወንጌል በመስበክ የሕዝቡን ልብ ያሳረፉትንና በዚህ የተቀደሰ ተግባራቸው አለሙያው በቤተክርስቲያናችን የተሰማራውን ማኅበረ ቅዱሳንን ከጨዋታ ውጪ እያደረጉት የሚገኙትን ብርቅዬ የቤተክርስቲያን አባቶችንና ወንድሞችን ከሕዝቡ ጋር ማጋጨትና ሕዝቡ በአባቶቹ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርበትና ጥያቄ እንዲያነሣ መቀስቀስና የሐሰት ወሬ መንዛት ነው። ይህም በአሁኑ ጊዜ በውጪ ባለችው ቤተክርስቲያን ላይ የተጋረጠ ትልቅ አደጋ ነው።

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሊገነዘቡ የሚገባቸው ይህን እውነት ነው። ዶ/ሩ ከዚህ ቀደም ብሎ «ሊወገዙ የሚገባቸው ናቸው» ብሎ በማኅበረ ቅዱሳናዊ ጠባዩ በውጪ የሚገኙ የ12 እውነተኛ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ስም ዝርዝር ለብፁዕነታቸው አቅርቦ የነበረ መሆኑ ሲታወቅ፣ እርሳቸው ግን ቦታም ሳይሰጡት ወረቀቱን ወደ ቅርጫት ጨምረውታል ተብሏል። በዚህ ያልተሳካለት የቤተክርስቲያናችን ሳይሆን የማኅበረ ቅዱሳን ስውር አባል የሆነው ዶ/ር ነጋ አባ ወልደ ትንሣኤን የሚከስበትና የሚያሸንፍበት፣ በአቡነ መልከጼዴቅ ዘንድም ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው እርሳቸውን «ወያኔ ሆነዋል» ያለ እንደሆነ መሆኑን በሚገባ ተረድቷል። በተጨማሪም ካህናቱ አድመውበዎታል የሚል የሐሰት እና ያልተጣራ ወሬ ለአቡነ መልከጼዴቅ በመንገር ባጠቃላይ በታላቁ አባት እና በበርካታ ካህናት መካከል መተማመን እንዳይኖር ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ለዚህ ነው ይህንኑ የፈጠራ ወሬ በማቅረብ የብፁዕነታቸውን ልብ መማረክ የቻለው። ይሁን እንጂ ከጊዜያዊ ፖለቲካዊ ትርፍ ይልቅ የቤተክርስቲያናችን ህልውና ይበልጣል። ለቤተክርስቲያንም ከዶ/ር ነጋ በላይ አባ ወልደ ትንሣኤ ይበልጥ ይጠቅማሉ። በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያና በአፍሪካ የስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸው እጅግ የተባረኩና በሕይወተ ሥጋ እያሉ ዕረፍተ ነፍሳቸውን ያገኙ ምእመናን ለዚህ ምስክር ናቸው። ብዙዎች ከልማዳዊ ክርስትና ወደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክርስትና የተሸጋገሩት በተለይ በአባ ወልደትንሣኤ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መሆኑን እንኳን ወዳጅ ጠላትም ይመሰክራል።

ብዙዎች በአገልግሎታቸው እጅግ ደስተኞች ቢሆኑም፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ደጋፊዎች ግን ደስተኞች አይደሉም። አባ ወልደ ትንሣኤ በአንዳንድ ልማዶች ላይ የሰጧቸውን ስብከቶች፣ በተለይ ከኦሪት ልማዶች ጋር በተያያዘ የሰበኳቸውን ስብከቶች ለመቃወምና አባን በተሐድሶነትና በመናፍቅነት ለመፈረጅና ስማቸውን ለማጥፋት በአገር ቤትም በአሜሪካም ማኅበረ ቅዱሳንን የቀደመው የለም። አባ ወልደ ትንሣኤ ይህን ትምህርት ከቤተክርስቲያን እንጂ ከሌላ እንዳላመጡት በተለይም ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን አብነት አድርገውና የእርሳቸውንም መጻሕፍት እየጠቀሱ ቢያስረዱ እንኳን፣ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ፈጽሞ ሊቀበላቸው አልቻለም። በዚህም ከዚህ ቀደም በአባሰላማ ድረገጽ ላይ እንደቀረበው አንድ ጽሑፍ መልእክት፣ ማኅበረ ቅዱሳን በአቡነ ጎርጎርዮስ ስም የሚነግድ፣ ትምህርታቸውን ግን የማይቀበል መሆኑን አሳይቷል።

ለጊዜያዊ ፖለቲካዊ ትርፍ ሲባል የቤተክርስቲያን ዋና ተልእኮ የሆነውን ወንጌልን ከሚቃወሙ፣ በአገር ቤት እየከሰሩና ግብአተ መሬታቸው እየተፋጠነ ካሉትና ሀይላቸውን ለማጠናከር ወደአሜሪካና በአሜሪካ እየተጠራሩ ካሉት የማኅበረ ቅዱሳን ዋናዎች ጋር መተባበር ለአቡነ መልከጼዴቅ ትልቅ ውርደት ነው። ስለዚህ የተጠጓቸውና እውነተኛ የቤተክርስቲያን አባቶችን ስም በማጥፋት ከአገልግሎት ለማራቅና በውጭ ያለችውን ቤተክርስቲያን በማኅበረ ቅዱሳን ቁጥጥር ስር ለማዋል እየተደረገ ያለውን ሴራ ብፁዕነታቸውና በውጭ ያለው ኦርቶዶክሳውያን አባቶችና ምእመን ሁሉ ሊያውቁትና ሊቃወሙት ይገባል። በእነ አባ ወልደትንሣኤ ላይ እየተቀነባበረ ያለውን የማኅበረ ቅዱሳን ሴራም ለማክሸፍ ከአሁኑኑ ሊነሣ ይገባል። አሊያ ማኅበረ ቅዱሳን በአገር ውስጥ ላለችው ቤተክርስቲያንና ለቅዱስ ሲኖዶስ ትልቅ ፈተናና የጎን ውጋት እንደሆነባት ሁሉ፣ በውጪም ከዚያ የከፋ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም። ስለዚህ እንደነ ዶ/ር ነጋ ያሉትን ጨዋዎች ወደቦታቸው በመመለስ አባቶቻችን የስብከተ ወንጌሉን ሥራ እንዲያፋጥኑ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና በውጪ ያለችው ቤተክርስቲያናችንን ከማኅበረ ቅዱሳን ስውር አካሄድ ነቅቶ መጠበቅ የወቅቱ ትልቅ ጥሪ ነው።

ምስክር ነኝ ከአሜሪካ

41 comments:

 1. እና ም ይጠበስ ማህበሩም አዘጋጀው ማንም ይሁን በዋልድባ ጉዳይ የመጣ በ አይን መጣ ነው
  አንዴ ፖለቲከኛ አንዴ መናፍቅ አትሁኑ ማቅ እንደሁ በቅዱሳን ጸሎት በመቤታችን ምልጃ በአምላክ ቸርነት ተጠብቆ ይኖራል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማቅ የወሮ በላ ድርጅት ከመሆኑም በላይ ለአገርና ለቤተክርስቲያን ፍፁም ጠላት በመሆኑ ማቅ በጌታ ኃይል ማቅ ይለብሳል። የጨለማው ተባባሪ ነውና፣ ከስድብ አፍ በቀር ለአውሬው ማቅ የተሰጠው ነገር የለም። ድሮስ ከእናንተ ምን ይጠበቃል፣ በማጭበርበር 20 አመት ሞላችሁ አሁን ግን የተሰጣችሁን የንስሃ እድሜ እንኩአን ስላልተጠቀማችሁበት የጌታ ቁጣ በእናንተ ላይ መምጣቱ አይቀርም፣ ልጆቹን ከበረቱ በሐሰት በማስወጣታችሁ
   ዋጋችሁን ትቀበላላችሁ። እግዚአብሔር ተዋጊ ነው። የሚቀድመውም የለም። በከንቱ ግን ትደክማላችሁ አለቃችሁ ዲያቢሎስም ብቻውን መቃጠል ስለማይፈልግ በመጭረሻም ይዙአችሁ ይቃጠላል። ዳሩ ለሚያምን ነው እንጂ ለእናንተ የእግዚአብሔር ነገር እኮ አይገባችሁም። አይናችሁን ይግለጥላችሁና ተመልከቱ። ይቆየን።

   Delete
  2. ደጀ ብርሃን ብሎግ ፤ እንደ ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳን እንዲጠፋ ዓላማም፤ ፍላጎትም የለውም። ማኅበሩ ስለጠፋ የቤተክርስቲያኒቱ ችግር ሁሉ ይወገዳል ብለንም አናምንም። ስለ ማኅበሩ ያለን አቋም ስለቤተክርስርያኒቱ እኔ አውቃለሁ፤ እኔ ከሌለሁ ትጠፋለች፤ የኔ መኖር ወሳኝ ነው፤ እነ እገሌን አጥፉልኝ፤ አስወግዱልኝ አትበል። አንተ ባትኖርም ቤተክርስቲያን ትኖራለች። እንኳን አንተ ሲኖዶስ የሚባል ተቋም በሌላት 1600 ዘመን ሁሉ የጠበቃት በደሙ የመሰረታት ክርስቶስ ነው። መኖርህን ለበጎ እንጂ ለመከፋፈልና ለብጥብጥ አታውለው! አስቀድመህ ወንጌልን ተማር! በነጠላ መሸፋፈን እንደእውቀት አትውሰደው። ንግድህን አቁም። ወይም ከንግድ ሚ/ር ፈቃድህን አውጣ! መናፍቅ ይሁን ተሃድሶ ወይም ከሃዲ ቢኖር ለማሰደድ ስትል የኃጢአት ደብዳቤ እንደሰይጣን አትጻፍ። በሊቃውንቱ ደንብ እንዲናገር እድል ይሰጠው። በሊቃውንቱ ትክክለኛው ትምህርት ይነገረው! ከማባረር ይልቅ ለማስተማር ጣር ነው የምንለው። ማኅበሩ ሆይ ረጋ በል፤ ሽቅብ አትዝለል ነው አጥብቀን የምንነግረው። ሁሉ ነገር በአገባብና በሥርዓት አድርገው ነው የምንለው! ነውረኞች ጳጳሳትን ተሸክመው፤ ያልተስማሙህን ነውረኞች አትበላቸው ነው የምንለው! ምሰሶ ኃጢአት ዓይንህ ውስጥ ተሸክመህ የሌሎችን ጉድፍ ላውጣ አትበል ነው የምንለው! ማቅ ይህንን ካደረገ ከማንም ጋር አይጋጭም። ይህንን ጠርዝ ሲያልፍ ግን ከሰካራም ደጋፊዎቹ በስተቀር ሁሉም ይነሳበታል። ሰካራም ደጋፊዎቹ ማለት አልኮል የሚጠጡ ማለት ሳይሆን የእሱን ፖለቲካ ጠጥተው በእሱ ፍቅር የሚንገዳገዱ፤ የኅሊናቸው ምህዋር ግራና ቀኝ ከማየት የተከለከለ ማለት ነው።
   ገባህ!!!!!!!!!!!?????

   Delete
  3. Sure you are right. GOD bless you

   Delete
  4. Thank you anonymous!!

   Delete
  5. eyetahen neutral adregeh lemkreb mokerek enji befetsum wegentegna neh.... mabarer lalkew keyetegnawem betechristian belikawent sayteyek yetebarere yelem.... lememar yetezegajen mastemar gedeta new, gen ezih gar chegru lemastemar lemelewet yetezegaje aymero enji teyko lemeredat yehone aydelemena yihe linor yemichel yetenbit mefetsemiya selehone noro begochun kemiyasweta esu biweta aykelem telaleh??? ezih gar endatzenega yihe kesew feker wuchi ayadergem, miknyatum emnetu sisfafalet yemaywed sew yelemna..... gen menetek yelebet yewahu metebek selalebet new... yih degmo yerasu yeAmlak sera new!!!

   Delete
 2. Abba Selama,

  Your blind accusation of MK is shameful. If you've any sense of justice, and interest in mutual forgiveness within our church, you would not continue with your ceaseless attack on MK which is ignoring your useless accusations.

  Please cease your unchristian diatribe and focues on the reall challenges facing our beloved church: its desperate need for peace and reconciliation, support for the Debres and Gedams including our historic monastery in Jerusalem, evangelization, etc.

  I wonder if you realize that the Almighty is watching your completely negative and ill-considered campaign against others!!!!

  ReplyDelete
 3. Yih bemahibere kidusan Yetenesa guday sayhon bemelaw Chiristian bekul new.enanten gin Aychemirim...Because you don't want to preserve our ancient Monastry,WALIDIBA.Enante endehone Ke egna wegen Aydelachihum,Ke kidist Betekiristian aydelachihum.....Minim Enquan ende and qin asabi Ethiopiawi gid yemilachihu bihonim kilu......

  ReplyDelete
 4. ጽሁፉን ማቅረባችሁ ባልከፋንም ነበር ፡፡ ነገር ግን እውነት እንዲወጣና እንዲገለጥ አባ ወልደ ትንሣኤን በስልክም ሆነ በጽሁፍ ጠይቃችሁ ከቃላቸው ትንሽ ማቅረብ መልካም ነበር ፡፡ አባ ወልደ ትንሣኤ የኢትዮጵያ ጳውሎስ እንደሆኑ ክርስቲያን ነኝ የሚል በሙሉ ይመሠክራል ፡፡ እንደተነገረባቸው ስጋዊ ስህተትን ፈጽመው ከሆነም የንስሓ ቃል ለማሰማት የሚያፍሩ አባት አይደሉም ፡፡ ስህተት ከፈጸሙ ለመንፈስ ልጆቻቸው አይዋሹንም ፡፡ ወደ ሰማይ ያረጉ ሰው አስመስላችሁ ፣ የስማ በለው ዘገባ አቀረባችሁልን ፡፡ በሃሰት ስማቸው ተበክሎም እንደሁ ፣ እውነትን ከመናገር ወደ ኋላ አይሉምና የሚሉትን ካሰማችሁን እናምናለን ፡፡ ሰው ናቸውና ስህተት ካደረጉም በዚህ ማንም አይፈርድም ፤ እያንዳንዳችን ራሳችንን ብንመረምረው በሰዓት ሳይሆን በየደቂቃዋ ብዙ ድክመትን እንፈጽማለን ፡፡ ከአንድም ሁለት ሰው አሉ የተባለውን ንግግራቸውን ትተን /ፈረንጅ ብዙ ስለሚሰዳደብ ማለት/ በስመ አብ ብለው መስቀል የሚያወጡ መስለው በጡጫ ተማቱ ብሎ ሲናገር ሃሰት ለማለት ትንሽ ይከብዳል ፡፡ ስለዚህ አባ ወልደ ትንሣኤን ጠይቃችሁ ሃቅን አውጧት ፡፡ እኔ በበኩሌ መጽሐፍን ማገላበጥ የጀመርኩት በአባ ወልደ ትንሣኤ ትምህርት ተስቤ ነውና ለእኔ ትልቅ መምህሬና የመንፈስ አባቴ ናቸው ፡፡ እንዲያ መባላቸውን ባላምንም አንዳንዴ ሰይጣን የማይፈታተነው ፍጡር ስለማይገኝ ፣ ደክመውለት ይሆናል ፡፡ ያን እንደ ሰው ቢፈጽሙም ደግሞ ብዙ ነፍሳትን መልሰዋልና ፣ አባትነታቸው አይሻርም ፡፡

  ReplyDelete
 5. I think the author of this article is trying to take advantage of the EOTC division to furhter saw disocrd and animosity among EOTC followers.

  So what again? Whoever calls the peaceful protest, it does not matter? Abune Melkesedek and Aba WeldeTensae don't have differences regarding Waldeba. We support MK when it comes to Waldeba if they stand for the right and privilege of the Monastery. Mr. writer, it seems you are one of the enemies of EOTC. We may dislkie or hate MK for some of the wrongs that they may have done, but we don't dislike them for standing for the right of our ancient monastery and the fathers, who have made praying for us and Ethiopia their daily life...

  ReplyDelete
 6. Woldegiorgis MuluenehMay 29, 2012 at 6:17 PM

  IF this is what Aba Selama is standing for, I am starting to downgrade it, honestly. So far I was even thinking that this site was the work of God. But when I am being told what I know in a way that is somehow more of a conjecture than a truth, I started to bleed internally. Who is going to be trusted?

  It is true there is some misunderestanding, unfortunately, between the young monks and Archbishops and the senior ones. So what? IT should be because christianity is not a rose garden, it is full of ups and downs. Otherwise it is not going to be christianity. And, when ever such issues arise no matter how minor or major, we should work towards a peaceful resolution according to the word of God, not rushing to judgemnt and labeling one a vilan and the other a victim. Jesus has died both for Dr. Nega and Aba Woldetensae. In the eyes of the Lord, both souls are equal and much loved by our beloved creator. What else, both are serving the church to the best of their ability. Dr. Nega's efforts to preach the Gospel should have earned him praise, not otherwise. Aba's outstanding service too deserves applause for he has been nourishing starved sould around the world with the bread of the gospel. Both of them are our servants to keep and protect for our common good. Any divisive agend under any pretext sickens me to death. Why is it that some of us are acting like open graves poluting others smelling stenchy of death when we can be living examples of love, mercy and love. May The Good Lord have mercy upon all of us!!!

  Woldegiorgis Muluneh- Washington DC

  ReplyDelete
 7. እስኪ በናታችሁ የማህበረ ቅዱሳን ስም የለለበት አንድ ጽሁፍ አስነብቡን ብትችሉ ሙሉዉ ጽሁፍ ላይ ስሙ ባይኖር ካልቻላችሁ ግን at least ርእሱ ላይ ባይኖር የብእራችሁ ቀለም አስመሰላችሁት እኮ... ቀለም... ያለቀለም መጻፍ አይቻል አይደል... ፈጣሪን አመስግኑ የማያልቅ ርእስ ከማይጎድል ቀለም ጋር ሰጣችሁ

  ReplyDelete
 8. ውድ ወንድማችን ምነው ይህን ያህል ቤተ ክርስትያናችንን ለማፍረስ እና ህገ ቤተ ክርስትያን ለማፈለስ ተጋህ እንቅልፍም አጣህ ከቤተ ክርስትያን ነውን ወይስ ከሰው ጋር ነው ጠብህ!!!
  ሐዋሪያው ቅዱስ ማቴውስ እስመ ይመስሎሙ በአብዝኆ ንባቦሙ ይሰምዖሙ አብዝተው ጨኾው በመፀለያቸው የሚሰማቸው ይመስላቸዋል እንደለው ወንድሜ ምነው እንደዘንዶ እፉህን ወደ ቤተ ክረስትያን ከፈትክ ቀስትህን ለምን ወደ ቤተ ክረስትያን ወረወርክ እመሰ ኢተመየጥክሙ ሰይፎ ይመልህ ወቀስቶኒ ወተረ አስተደለወ በቅዱስ ዳዊት አድሮ የተናገረው እግዚአብሄር አምላካችን ምነው ዘነጋሀው፡፡
  እግዚአብሄር መኮንነ ጽድቅ ኃያል ወመስተዐግስ ብሎ የተናገረው እግዚአብሄር በነብዩ ቅዱስ ዳዊት የተናገረው መፈታተን አይሆንብህምን ወይስ አንተን አይመለከትህም በቅተህ ደርስ የሆነ እንደሆነ ብዬ ነው ምነው ተደፋፈርክ ፡፡
  ለክፉ ግብር አንዴ ቀይ አንዴ ጥቁር ሆንክ የዲያብሎስ አስፈፃሚ ለመናፍቃን ድልዲይ ሆንክን ቤተ ክርስትያን ያሳደገችህ ምነው ከዳሀት ምነው የስድብ ቃላት መሰንዘር ጀመርክ፡፡
  እግዚአብሄር አምላክ አስተዋይ ልብ የንስሀ ሕይወት ይስጥህ ይስጠን፡፡
  የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳኢነት ከሁላችን አይለየን፡፡

  ReplyDelete
 9. This information is uses regarding to walidiba. If you are the flower of the you should stand near to the church. Unless you may............................

  ReplyDelete
 10. bizu medkem ayasfelgachihum, Amlakn tektachu lemaseb lelawm endeziaw endiasb batitiru Yibejal. Yih Yetsidk Menged Wichi Mehonachihun Yedkam Guzoachihu Begilt Yasayal.Yemamesegnachihu Sile MK bedenb endawkew alemagezachihu!

  ReplyDelete
 11. ወይ ዘመንMay 30, 2012 at 6:23 AM

  ምን ዓይነት ሰይጣናዊ ሥራ እየሰራችሁ እንደሆነ ታውቃላችሁ ? እስኪ ቆም ብላችሁ አስቡ ::በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ :: ስለ ማህበረ ቅዱሳን ስተት መረጃ ካላችሁ ጻፉ:: ፍየል ወዲህ ቁዝምዝም ወዲያ የሆነ ነገር አትደርቱ:: አቡነ መልከጼዴቅ እንቅፋት ቢመታቸው : ማህበረ ቅዱሳን ያስቀመጠው ድንጋይ መታቸው አባ ወልደ ትንሳኤ ትን ካላቸው የማህበረ ቅዱሳን እጅ አለበት፣ ቅዳሴ ላይ ስፒከሩ ከተበላሸ ማህበረ ቅዱሳን ሆን ብሎ ያደረገው ነው:: ባራዳ ቋንቋ ይደብራል::
  ዲሲ ገብርኤል ላይ ለተከሰተው ችግር ለመናገር እፈልጋለሁ ለመሆኑ አንድ ሰው የሰበካ ጉባኤ ሊቀመንበር አይደለም አባል ለመሆን መስፈርት የለውም እንዴ? ወይንስ የውጪው ሲኖዶስ ቀይሮታል ? በዓለማዊ እውቀት ቤተ ክርስቲያን አትመራም:: ለምንድን ነው ምዕመናንን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለደረጃቸው ኃላፊነት በመስጠት ህይወታቸውን የምናበላሽ ቤተ ክርስቲያንንም ሰላም የምንነሳው ? እግዚኦ ማረነ ክርስቶስ!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 12. why are you not posting my several comments???

  ReplyDelete
 13. የዋልድባን ገዳም በአሜሪካ መንግስት አይደለም የተመሰረተው በእግዚአብሔር ፈቃልድ እንጅ። እግዚአብሐር ይስጣችሁ። ገና ገና ብዙ ጉድ ስለ ማቅ ይወጣል። አሁን ደግሞ በዋልድባ ስም ለመነገድ የፖለትካ ጥማቱን ለማሳካት ዛሬም ህዝቡን እያወከ ነው። በእውነት ከሆነ ለዋልድባ መኖኮሳት መፍተው ከእግዚአብዐሔር በጸሎት መጠየቅ ነው ወይስ ከተባበሩት መንስታት ነው?።

  ReplyDelete
 14. እውነቱ ስወጣ የማህበረ ቅዱሳን ደካማ ተከታዮች ለምን ይደነግጣሉ? ለመሆኑ ሐይማኖትና ፖለትካ ምን አገናኘው? ወይንስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ አማኝ የሃይማኖት ነግር አይገባውም የምል ንቀት ከት መጣ? ኢትዮጵያ እጆቹዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል እንደት አይዋጥላቸውም።
  እውርን የሚመራው እወር ነው። ማቅም በሥልጣን ጥማት የሰከረ ማህበረ ነው።

  ReplyDelete
 15. When are you going to stop your trash talk?

  "...በአንጻሩ ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች እንዲሰብኩ በማድረግ ቤተክርስቲያንን ከወንጌል ወደ ማኅበሩ ተረታተረት የመመለስ ዕቅድ እንዳለው ከፍተኛ ግምት አለ።"

  What does "ከፍተኛ ግምት አለ" mean?

  You are not writing the truth. You are assuming or wishing it will happen.

  This is definitely not expected from orthodox christians.

  May God guide us His way!

  ReplyDelete
 16. I fully support the project at waledba gedame. That is just piece of land , there is nothing special over there. if there is special, it is the school of Debetera. please let us focus in Bible.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለ ቁራሽ መሬት በማለት ማንም አይጨቃጨቅም ፡፡ ነገር ግን በዛች በቁራሽ መሬት ላይ ስለ ተፈጸመው ገድልና ተያይዞ ስለ ሚነገረው ታሪክ ፣ ቦታውን ከሌሎች ሥፍራዎች ለየት ያለ ዋጋ ያሰጠዋል ፡፡ ጌታችን የተወለደባት በረት ፣ የተሰቀለባት ጐልጐታ ታሪካዊ ሥፍራዎች ስለሆኑ ዛሬ የዓለም ክርስቲያን ሁሉ ከቦታው ደርሶ በረከትን ለማግኘት እየተተራመሰ ይገኛል ፤ በመሬትነት ጸባይ ከተፈተሹ ግን ከሌላው የእሥራኤል ምድር አንዳች የሚለያቸው አፈጣጠር አይታይም ፡፡ የዋልድባ ገዳምም እንደዛው እመቤታችን ድንግል ማርያም ከልጅዋ ጋር ተሰዳ ያረፈችበት ሥፍራ ነው የሚል የአባቶች ትውፊት ስላለንና ፣ ቅዱሳን አባቶችም የባረኩትና የቀደሱት ፣ አጽማቸውም ያረፈበት ስለሆነ እንዲከበር ግድ ይላል ፡፡ እንኳን ለአበሻ ለውጭ አገር ዜጋው የሚታደል መሬት ሳይጠፋ ፣ ለምን ገዳም ካልታረሰ ተብሎ ትግል ይጋጠማል ፡፡ ስለ አየር ጸባዩም ተብሎ ከሆነ ፣ ለምን ትንሽ አሸጋሽጐ ገዳሙን በማይጐዳ ዕቅድ ተለውጦ ተግባራዊ አይሆንም ፡፡ ጥናቱን ያደረገና ዕቅዱን ያወጣው የሰው አእምሮ ነው ፡፡ ልማቱን ስለመደገፍ ከሆነ ፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሃገር መልማትን ይደግፋል ፤ ልማቱ ሊሠራበት የተፈለገበት ቦታ ግን ከልማቱ በላይ የሆነ ታሪክና ዋጋ ስለ አለው ዕቅዱ ይሻሻል ፡፡

   Delete
 17. ማህበረ ቅዱሳን ያስቀመጠው ድንጋይ መታቸው አባ ወልደ ትንሳኤ ትን ካላቸው የማህበረ ቅዱሳን እጅ አለበት፣ ቅዳሴ ላይ ስፒከሩ ከተበላሸ ማህበረ ቅዱሳን ሆን ብሎ ያደረገው ነው::

  ReplyDelete
 18. I like say thank you guys for you doing great spiritual work. Our lord God may have bless you.

  ReplyDelete
 19. Look what MK is doing when you guys are writing trash... and false accusation.

  ለገዳማት የመብዐና አልባሳት ድጋፍ ተደረገ
  በእንዳለ ደምስስ
  ግንቦት 18/2004 ዓ.ም.
  በቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል በየወሩ እየተዘጋጀ የሚቀርበው የዜና ገዳማት መርሐ ግብር ግንቦት 7 ቀን 2004 ዓ.ም. ተካሔደ፡፡ በዋነኛነት ከየካቲት 24 እስከ መጋቢት 4 ቀን 2004 ዓ.ም. ድረስ በቆየው የመብዐ ሳምንት በሚል በችግር ላይ ለሚገኙ 400 አድባራትና ገዳማትን ለመርዳት ከምእመናን የተሰበሰበን መብዐ እና አልባሳት /ልብሰ ተክህኖ/ ስርጭት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ 800 ሺህ ብር ለመሰብሰብ የተቻለ ሲሆን እስከ 750 ምእመናን ተሳትፎ አድርገዋል በማለት የገለጹት የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ መሠረት ናቸው፡፡ በተገኘው ገቢ መሠረት ስርጭቱን በ4 ዙር ለማከናወን የታቀደ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር በትግራይ 7 ሀገረ ስብከቶች ውስጥ ለሚገኙ 50 አድባራትና ገዳማት እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናት ለአንድ ዓመት የሚሆን የመብዐ ስጦታ ተሰጥቷል፡፡  ስጦታው የተከፋፈለው ለአንድ ሳምንት የቆየ ጉዞ በማከናወን በየአድባራቱና ገዳማቱ በመገኘት ሲሆን ስርጭቱ ካካተታቸው ሀገረ ስብከቶች መካከል በደቡብ ትግራይ አርማጭሆ፤ እንደርታ፤ አዲግራት፣ አክሱም፣ ሽሬና ሁመራ ይገኙበታል፡፡ ከገዳማቱ መካከል ደብረ ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያ፣ ደብረ በንኮል አቡነ መድኀኒነ እግዚእ፤ አባ ዮሃኒ ዘቆላ ተንቤን፣ አባ ቶማስ ዘደብረ ማርያም ዘሃይዳ፣ ፀአዳ አምባ አቡነ መርአዊ ክርስቶስ፣ እንደቆርቆር ቅድስት ማርያም ገዳማት ይገኙበታል፡፡

  አድባራቱና ገዳማቱ ሰው የማይደርስባቸው ሊባሉ የሚችሉ በረሃማና ጠረፋማ አካባቢዎች ሲሆኑ እቅዱን ለማሳካት አስፋልቱንና ኮረኮንቹን በመኪና፤ ተራራውንና ተዳፋቱን በግመል በመጫንና በማከፋፈል ምንም መቀደሻ እጣን፣ ጧፍ፣ ዘቢብ እንዲሁም ልብሰ ተክህኖ ለሌላቸው ለማዳረስ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡ ስርጭቱን የተቀላጠፈ ለማድረግ በየሀገረ ስብከቱ የሚገኙ የማኅበሩ ማእከላት አባላት ድርሻ ከፍተኛ ነበር፡፡  በስጦታው ወቅት አባቶች ያሉባቸውን የመብዐ እጥረት ገልጸው “ዛሬ ዐይናችን እንደበራ እንቆጥረዋለን” በማለት የተደረገላቸውን ስጦታ ውዳሴ ማርያም እየደገሙና የኪዳን ጸሎት እያደረሱ መብዐውን ለሰጡ ምእመናንና ማኅበረ ቅዱሳን በጸሎት በማሰብ ተቀብለዋል፡፡  በተያያዘም በዋነኛነት ትኩረት ከተደረገባቸው ገዳማት ውስጥ ትግራይ ፀአዳ አምባ አቡነ መርአዊ ክርስቶስ ገዳም ይገኝበታል፡፡ ታላላቅ አባቶችን ያፈራ ገዳም እንደሆነና በረሃብና እርዛት፤ እንዲሁም ሆድ በሚነፋ በሽታ ምክንያት አባቶች በችግር ላይ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን እውነታውን በፊልም በማስደገፍ ለምእመናን ቀርቧል፡፡ በሽታው በጥናት ሊደረስበት እንዳልተቻለ መነኮሳቱ የሚገልፁ ሲሆን የአካባቢው ምእመናን በበሽታው ምክንያት ወደ ሰፈራ በመሄዳቸው ገዳማውያኑ ብቻቸውን ቀርተዋል፡፡ ከገዳሙ የሁለት ሰዓት የእግር ጉዞ በኋላ የእርሻ ቦታ ያላቸው ቢሆንም የገዳሙ አባቶች በእርጅናና በጤና መታወክ ሳቢያ ማረስ አልቻሉም፡፡ ከዚህ ቀደም የአካባቢው ምእመናን ያርሱላቸው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ “አበው ያቆዩልንን ቅርስና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ጥለን አንሄድም” በማለት ጸንተው ቆይተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት 52 መነኮሳት ብቻ የሚገኙ ሲሆን በአልባሳትና በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ምክንያት የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ትኩረት አድርጎ ለእነዚህ አባቶች ምእመናን እንዲደርሱላቸው ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ እስከ ነሐሴ 2004 ዓ.ም. ድረስ ለአልባሳት 15.600 ብር እንዲሁም ለቀለብ 20.800 ብር እንደሚያስፈልግ በመርሐ ግብሩ ወቅት በመገለጹ በእለቱ ከተገኙ 2 በጎ አድራጊ ምእመናን ከላይ የተጠቀሱትን ወጪዎች እንደሚሸፍኑ ቃል ገብተዋል፡፡ ዋና ክፍሉም ምስጋናውን በማቅረብ ምእመናን ድጋፋቸውን እንዳይለይ አጽንኦት በመስጠት “እናንተ ሁል ጊዜ ስጡ፣ ከቅዱሳን በረከትን ታገኛላችሁ፣ እጃችሁ ከምጽዋት አይጠር፣ እኛም አደራችሁን ተቀብለን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ነን” በማለት የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዓለም ፀሐይ መሠረት ገልጸዋል፡፡  በዜና ገዳማት ወርሐዊ መርሐ ግብር ከተዳሰሱት መካከል ለዝቋላ ገዳም በቃጠሎው ምክንያት ጊዜያዊ ድጋፍና የፕሮጀክት ጥናት መደረጉ ተገልጿል፡፡ በቃጠሎው ወቅት የቀለብ እጥረት በመከሰቱ ማኅበረ ቅዱሳን ምእመናንን በማስተባበር 50 ኩንታል ስንዴ፣ 20 ኩንታል ጤፍ፣ 40 ሺህ ብር የሚገመት ውኃ፣ በሶ፣ ስኳርና ዳቦ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ከማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ከበጎ አድራጊ ምእመናን የተሰበሰበ ለድጋፍ የሚሆን 125 ሺህ ብር ተሰብስቧል፡፡ ወደ ዝቋላ ገዳም ባለሙያዎችን በመላክ ለገዳሙ የሚሆን የእርሻ ቦታ፣ የመጠጥ ውኃና የመንገድ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል ጥናት ተደርጓል፡፡ የደብረ ዘይት ማእከል አባላት የዝቋላን ገዳም አስቸጋሪ መንገድ ለመጠገንና ለማስተካከል ምእመናንን በማስተባበር ከፍተኛ ርብርብ ላይ እንደሚገኙ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡ የጎንደር ወደብረ ጥበባት በዓታ ለማርያም ገዳም የአብነት ተማሪዎች ማደሪያ ቤት ግንባታ መጀመሩም በሪፖርቱ ከተካተቱት አበይት ክንውኖች አንዱ ሆኗል፡፡  በቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ዳይሬክተር በዲ/ን አእምሮ ይሄይስ በክፍሉ የተከናወኑ ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ የ10 ዓመት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በሪፖታቸውም በእርሻ ፤ንብ ማነብ፤ግንባታ፤ የወተት ላምና ከብት ማድለብ እንዲሁም ሰው ኃይል ማፍራት ላይ ያተኮሩ ፕሮጀክቶች ተሠርተዋል፡፡ ከፕሮጀክቶቹ መካከል በአብዛኛው የአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ፣ የመምህራንና የተማሪዎች መኖሪያ፤ የጉባኤ ቤትና የካህናት ማሠልጠኛ፣ የካህናትና መነኮሳት መኖሪያ ግንባታ ፕሮጀክቶች ሰፊውን ድርሻ እንደሚይዙ በስፋት አብራርተዋል፡፡ በጥናት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በሂደት ላይ ሲሆኑ ከእቅድ ውጪም እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶች ይገኛሉ፡፡በተጨማሪም 145 የአብነት ትምህርት ቤቶች፣ 136 መምህራን፤ 865 ተማሪዎች በየወሩ እየተደጎሙ እንደሚገኙ ዲ/ን አእምሮ ይሔይስ ገልጸዋል፡፡  በመርሐ ግብሩ ላይ በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ትምህርተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን የ3 ወራት የሒሳብ ሪፓርት ቀርቧል፡፡ ከምእመናን በክፍሉ እንቅስቃሴና በገዳማት ዙሪያ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡ ከ800 በላይ ጥሪ የተደረገላቸው በመብዐ ሳምንት ድጋፍ ያደረጉ ምእመናንና በጎ አድራጊዎች በመርሐ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል፡፡  ዜና ገዳማት በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል በየወሩ እየተዘጋጀ የገዳማትንና አድባራትን ነባራዊ ሁኔታ፣ የክፍሉን እቅዶችና ተግባሮች እንዲሁም የተተገበሩና በዝግጅት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች የሚተዋወቁበት መርሐ ግብር መሆኑ ይታወቃል፡፡

  ReplyDelete
 20. Be hager bet kalew kidus sinodos gar Mahibere Kidusanin lematalat mokerechihu alisaka silachihu ahun degmo wede wichim synodos zorachihu:: Betam tazebokuoachihu!!!

  Be hager wistim hone bewichiw synodos lemenafikan bota endelelachew tenkikachihu mawek alebachihu::

  Hulutum synod anid ken yitarekalu; MKem le betekrstian melkam sirawin yiktilal; yetim wedkachihu yemtikerut enante ena nufakechihu new::

  ReplyDelete
 21. Why don't you post my comments?

  ReplyDelete
 22. እግዚአብሔር ተዋጊ ነው። የሚቀድመውም የለም። በከንቱ ግን ትደክማላችሁ አለቃችሁ ዲያቢሎስም ብቻውን መቃጠል ስለማይፈልግ በመጭረሻም ይዙአችሁ ይቃጠላል። ዳሩ ለሚያምን ነው እንጂ ለእናንተ የእግዚአብሔር ነገር እኮ አይገባችሁም። አይናችሁን ይግለጥላችሁና ተመልከቱ

  እስኪ በናታችሁ የማህበረ ቅዱሳን ስም የለለበት አንድ ጽሁፍ አስነብቡን ብትችሉ ሙሉዉ ጽሁፍ ላይ ስሙ ባይኖር ካልቻላችሁ ግን at least ርእሱ ላይ ባይኖር የብእራችሁ ቀለም አስመሰላችሁት እኮ... ቀለም... ያለቀለም መጻፍ አይቻል አይደል... ፈጣሪን አመስግኑ የማያልቅ ርእስ ከማይጎድል ቀለም ጋር ሰጣችሁ

  ReplyDelete
 23. Sitazazinu! Bizu lefachihu, kesesachihu, Ahunim tikesalachihu. Please comeback to your mind. Your writings say a lot about your Christianity. Christianity cannot carry HATE. Christianity is LOVE. GOD IS LOVE. You always tell us HATE. MK doesn't say anything, just doing its job. May God help MK!!

  Christian from NY

  ReplyDelete
 24. ማን ብሎጉን ሊያነበው በውሸት የታጠረውን ክሳቸውን ካላነሱ በማህበሩ ላይ ካላነሱ። ወንድሜ ጽሁፋቸውማ ገባ ብለህ ብታነበው በገድል የተዋደቀትን ቅድስናን የተጎናጸፉት እነ ቅዱስ ጊዮርጊስን ጻድቁ ተክለሃይማኖት የተዳፈሩ ናቸው የሚያደርጉት የማያውቁ ናቸው

  እስኪ በናታችሁ የማህበረ ቅዱሳን ስም የለለበት አንድ ጽሁፍ አስነብቡን ብትችሉ ሙሉዉ ጽሁፍ ላይ ስሙ ባይኖር ካልቻላችሁ ግን at least ርእሱ ላይ ባይኖር የብእራችሁ ቀለም አስመሰላችሁት እኮ... ቀለም... ያለቀለም መጻፍ አይቻል አይደል... ፈጣሪን አመስግኑ የማያልቅ ርእስ ከማይጎድል ቀለም ጋር
  ሰጣችሁ

  ReplyDelete
 25. አቡነ መልከጼዴቅ እንቅፋት ቢመታቸው : ማህበረ ቅዱሳን ያስቀመጠው ድንጋይ መታቸው አባ ወልደ ትንሳኤ ትን ካላቸው የማህበረ ቅዱሳን እጅ አለበት፣ ቅዳሴ ላይ ስፒከሩ ከተበላሸ ማህበረ ቅዱሳን ሆን ብሎ ያደረገው ነው:: ባራዳ ቋንቋ ይደብራል::

  ReplyDelete
 26. አቡነ መልከጼዴቅ እንቅፋት ቢመታቸው : ማህበረ ቅዱሳን ያስቀመጠው ድንጋይ መታቸው አባ ወልደ ትንሳኤ ትን ካላቸው የማህበረ ቅዱሳን እጅ አለበት፣ ቅዳሴ ላይ ስፒከሩ ከተበላሸ ማህበረ ቅዱሳን ሆን ብሎ ያደረገው ነው:: ባራዳ ቋንቋ ይደብራል::

  ReplyDelete
 27. እንዲህ የሚያባላን ነገር እውነት ስለ ሀይማኖት ቀናት ‹እስመ ቅንዓተ ቤትከ በልዓኒ!!!› እንዳለ ልበ አምላክ አሳስቦን ነው ወይስ ሌላ ከጀርባ ስውር ተግባር አለ ካለስ ማንን እንመን እባካችሁ እንዲህ ስንወቃቀስ ጊዜያችን አይለቅ ስለ ፖለቲካ አታውሩ ስለ ዋልድባ ገዳሙን አይጎዳም ብትሉም አናምንም እናንተም የፖለቲካ አራማጅ ናችሁና እውነት እውነት እላችኋለሁ በቤተክርስቲያን በአንድ ቤት፣አንድ ዓላማ እያለን ያውም ለጽድቅ ይህን ያህል አለመግባባት የተፈጠረና መናቆር ካለ ፖለቲካችማ ውስጡን ለቄስ……….ሟርት አይደለም፡፡አንድ ነገር ሲኖር ቀርቦ ከማማከር ይልቅ ወደ መካነ ድር (ዌብ ሳይት) መነቋቆር ምን ማለት ነው እናንተ አሁን ለምዕመን አርዓያ ትሆናላችሁ ነገርን ቢያበዙት በአህያ አይጫንም ይላሉ አባቶች ሲተርቱ‹ለጠቢብ ሰብእ አሐቲ ቃል ትበቅኦ› እንዳለ መጽሀፍ፡
  እግዚአብሔር እውነተኛውን መሪና አስተካካይ ይስጠን
  አሜን!!!

  ReplyDelete
 28. Yetabatachihu enante menafikan, Mahibre Kidusan Egiziabiher yemeseretew Mahiber silohone andachim neger ayhonim errrrrrrrr belu.

  ReplyDelete
 29. The objective of "Abba Selama" is not to inherit the new Jerusalem nor to attract follower, but to carry suicidal mission to destroy MK by making alliance with satan ( lying, information distorting). They tried to instigate the "Synod in Exile" claiming MKs are children of Abba Paulos and members of EPRDF, they were partially successful.They have tried to arise the Holy Synod against MK, but failed. Now , they are trying hard to use the Government arm against MK. Although you are heretic, at least pretend to be Christians. Th Bible says do not oppose evil by evil let alone to oppose true with false.

  Please repent!

  Let God Keep the Holy Synod of Ethiopian Orthodox Church which made the right decision!

  ReplyDelete
 30. እንዲህ የሚያባላን ነገር እውነት ስለ ሀይማኖት ቀናት ‹እስመ ቅንዓተ ቤትከ በልዓኒ!!!› እንዳለ ልበ አምላክ አሳስቦን ነው ወይስ ሌላ ከጀርባ ስውር ተግባር አለ ካለስ ማንን እንመን እባካችሁ እንዲህ ስንወቃቀስ ጊዜያችን አይለቅ ስለ ፖለቲካ አታውሩ ስለ ዋልድባ ገዳሙን አይጎዳም ብትሉም አናምንም እናንተም የፖለቲካ አራማጅ ናችሁና እውነት እውነት እላችኋለሁ በቤተክርስቲያን በአንድ ቤት፣አንድ ዓላማ እያለን ያውም ለጽድቅ ይህን ያህል አለመግባባት የተፈጠረና መናቆር ካለ ፖለቲካችማ ውስጡን ለቄስ……….ሟርት አይደለም፡፡አንድ ነገር ሲኖር ቀርቦ ከማማከር ይልቅ ወደ መካነ ድር (ዌብ ሳይት) መነቋቆር ምን ማለት ነው እናንተ አሁን ለምዕመን አርዓያ ትሆናላችሁ ነገርን ቢያበዙት በአህያ አይጫንም ይላሉ አባቶች ሲተርቱ‹ለጠቢብ ሰብእ አሐቲ ቃል ትበቅኦ› እንዳለ መጽሀፍ፡
  እግዚአብሔር እውነተኛውን መሪና አስተካካይ ይስጠን
  አሜን!!!

  ReplyDelete
 31. Yes,it is ok to express our concerns and views about any issue (rligious or secular) we believe it desreves exchange of our various angles of thoughts . From this perspective, the article or comment above should be treated as normal and healthy reflection of the writer.

  What is ridiculous and unhealthy is the way we express our concern or arguement ,or diagreement . Are we willing and able to control our wild emotion and try to put our views in a rational, credible and constructive manner or we are victms of uncontrolled and highly inflamable attitudes ? Do we try our best to get credible information about the very reason for a conflict from both sides and make genuine effort to resolve it or we just take side and come with condemnation after condemnation? Yes, it is very wrong if the board or Dr.Nega Alemayehu has done something bad to Aba W/Tensai without any convincing justification . On the other hand, if Aba W/Tensai has done somthing inappropriate to the board or to Dr, Nega, it is equally very wrong . Well; we may extend our arguement by raising the question of who was and is expected to be much more tolerant and great example from the point of view of having huge religious responsibility. But,I think that has to be taken as an advantage to be more wise and solution-oriented.

  I have read letters from Los Angles and South Africa adressed to the Synod. That is well and good. But, as far as some expressions of the letters are concerned, I want to say that we are victms of very emotional,poor, and undesirable judgements. And this kind of attitudes will never take us to the direction we desperately aspire.

  Let us express our concerns based on the right information about the very cause of the problem and come up with ideas which are helpful in the process of resolving our conflicts.

  ReplyDelete
  Replies
  1. የጻፍኩትን ስላላወጣችሁት ዳግም እንድታነቡት የተጻፈ
   አንተ ምራቅህን የዋጥክ ሰው ስለሆንክ /ጨዋ ለማለት/ ይህንን የአስተዋዮች አስተያየት ጻፍህ ፡፡ አዘጋጆቹ ግን እንዲያ የተረጋጋና የሚያመዛዝን አእምሮ የላቸውም ፡፡ ማቅን በቅዝምዝምም ይሁን በቀጥታ የሚመታላቸው ከመሰላቸው የሆነ ያልሆነውን ፣ ልብ ወለዱንም ፣ ቁም ነገሩንም ለጥፈው ዓይናችንን ያፈዙታል ፡፡ የሌሎች ግለሰቦችን አስተያየቶችና የተለያየ አመለካከት ከመሰብሰብና ከማስተናገድ ፣ እንደ እኔ ሃሳብ ቢሆን ፣ ይህ መረጃ እጃቸው እንደገባ መቅደም የነበረበት ፣ ነገሩን ለማጣራት አቅማቸው እስከሚፈቅድ መጓዝና ፣ ትክክለኛውን ዘገባ ማቅረብ የተሻለ መንገድ ነበር ፡፡ የሆነለት ለቅድስናና ለጽድቅ ተመርጦና ተጠርቶ የሚሠራ ወገን ደግሞ ከዛም አለፍ ብሎ ፣ የስማ በለው ዜናውን ቅንብር ተወት አድርጎ ፣ ግለ ሰዎቹን ይቅር ለእግዚአብሔር አባብሎ ፤ እንዲህ ዓይነት ስህተት በክርስቲያን ወገኖች መሃል ተፈጥሮ ፣ በቤተ ክርስቲያናችንም ውስጥ የሚያሳፍር ችግር ተፈጽሞ ነበር ፡፡ እግዚአብሔር ረድቶን ግለሰዎቹን አወቃቅሰን አስታረቅናቸው ፤ እገሌም ስህተት እንደፈጸመ አምኖ ይቅርታ ጠየቀ ፤ ንስሐም ገባ ፡፡ እገሌም ደግሞ ጥያቄውን ተቀብሎ ከልብ ይቅር አለው ፡፡ ቢሉን እውነትም እኒህን ሰዎች የሰይጣን ዘንግ ስናደርጋቸው ፣ ሳናውቅ ለካስ ቅዱሳን ነበሩ በማለት ክርስትናን ከነሱም ተምረን ፣ አመለካከታችንን ለወደፊቱ እናስተካክል ነበር ፡፡ ይህን አጋጣሚ አግኝተው እንኳን ማንነታቸውን ለማሳየት አልተጠቀሙበትም ፡፡ አሁን እያደረጉ ያለው ፣ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ከመሥራት ይልቅ ፣ የተለኰሰችዋን ትንሽ ክብሪት ሰደድ እሳት እንድታስነሳ ማራገብ ፣ ነዳጅ ነገርም ጠብ ማድረግና ማፋፋም ፣ ከወዲያ ወዲህ ነገርን በማመላለስ አንዱን ከሌላው ማቆላለፍ ነው ፡፡ ምናልባት ወደፊት ሌላ አጋጣሚ ቢያገኙ ፣ ከዚህ ተምረው በረከትን ወደሚያስገኝላቸው ሥራ እንዲሠማሩ በማለት እንደ ማሳሰቢያ ይሆናቸው ዘንድ እመክራለሁ ፡፡

   Delete
 32. Ayi "Aba Selamawochi"... Min yeshalachihal.... dekiki ariyos nachihu.... Minim Betenchrechru... MK endeh Y'Kidusan Amelak Yemseretew selehone mimim ayihone ... kidusan hulu gezie yetseleyuletal

  ReplyDelete
 33. why we hide the turth,why we think two time before we speak.aba welde tensae and dr.nega ,they know each other any body else.
  i donot know the metion of this.aba welde tensae is very closest to all bishops.so aba welde tensae knows what he is doing so he does not need any help.so stop talking our falsful talk.

  ReplyDelete
 34. why we hide the turth,why we think two time before we speak.aba welde tensae and dr.nega ,they know each other any body else.
  i donot know the metion of this.aba welde tensae is very closest to all bishops.so aba welde tensae knows what he is doing so he does not need any help.so stop talking our falsful talk.

  ReplyDelete