Wednesday, May 23, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪ ጳጳሳት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ባልተከተለ መንገድ መወገዝ የሌለባቸውን የቤተ ክርስቲያን ልጆች “አወገዝን” አሉ

ነውራችን ተሸፈነልን ብለውና ከማኅበሩ የሚከፈላቸውን ረብጣ ብር ከግምት በማስገባት፣ እንዲሁም ከማኅበረ ቅዱሳን ጎን ብንቆም ፓትርያርክነቱ ለእኛ ይሆናል በሚል ክፉ ምኞት ተይዘው ለአንድ ወንበር እርስ በርስ እየታገሉ፣ የቤተክርስቲያንን ሳይሆን የማኅበሩን አላማ ለማሳካት በግንቦቱ ሲኖዶስ ከመጠን በላይ ሲፋንኑ የነበሩት አባ አብርሃም፣ አባ ዲዮስቆሮስና አባ ሳሙኤል፣ እንዲሁም አባ ጢሞቴዎስ፣ “ምንም ቢሆን ማኅበረ ቅዱሳን የከሰሳቸውን ሰዎችና ማኅበራት ሁሉ ሳናወግዝ አንበተንም፤ ማኅበረ ቅዱሳን ያጠናው በቂ ነው፤ እነርሱን ጠርቶ ማነጋገር አያስፈልግም” በሚል የማኅበረ ቅዱሳንን ክስ ብቻ በመቀበልና ተከሳሾቹን ሳያነጋግሩ ፍትሀዊነት የጎደለውን ፍርድ በመፍረድ “አውግዘናል” ማለታቸው ተሰማ። እነዚህ በስም የተጠቀሱ የሰሙኑን የሲኖዶስ ስብሰባ ማኅበረ ቅዱሳን በአቡነ ጢሞቴዎስ ቤት ያገባላቸውን ግብር በምሳ ሰአት እየበሉ፣ የቀኑን ውሎ ለማኅበሩ አመራሮች ሪፖርት እያቀረቡና በቀጣዩ ስብሰባ ላይ ማድረግ ስለሚገባቸው መመሪያ ከማኅበሩ አመራሮች እየተቀበሉ ሲኖዶሱን ሲያውኩ መሰንበታቸው ይታወሳል።

በተለይም አባ አብርሃም ከአሜሪካው ሀገረ ስብከት መነሳታቸው ጥቅማቸውን ስላስቀረባቸው በግላቸውም በማኅበረ ቅዱሳንም በኩል አልተወደደምና፣ ይህን ቂም ለመወጣት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ “ክስ የቀረበባቸው ግለሰቦች ተጠርተው ሳይጠየቁ እንዴት ይወገዛሉ? ስለዚህ ተጠርተው ይጠየቁና ውሳኔ ይሰጥ” ሲሉ ያቀረቡትን ሐሳብ ለጊዜው ተቀብለው የነበረ ቢሆንም፣ በዚህ እጅግ የተከፋው ማኅበረ ቅዱሳን “ሰዎቹማ ካልተወገዙ ጤና አይሰጡንም። ስለዚህ ስብሰባው ከመዘጋቱ በፊት አውግዛችሁ መለያየት አለባችሁ ሲል ተላላኪ ጳጳሳቱን ባዘዘው መሰረት ተልእኮዋቸውን ተወጥተዋል። አንዳንዶቹ አረጋውያን ጳጳሳት ግን ውግዘት የተባለውን ህገወጥነት “ኧረ ተዉ ምንድነው ለውሳኔ መቸኮል? ተጠርተው ያልተጠየቁ ሁሉ ተጠርተው ይጠየቁ። አሊያ ይህ ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም ውሳኔ አይደለም” ቢሉም ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለግል ምቾታቸውና ለሥልጣናቸው ብቻ የቆሙት አባ አብርሃም፣ አባ ሳሙኤል፣ አባ ዲዮስቆሮስና አባ ጢሞቴዎስ አሻፈረን በሚል ማውገዛቸውን አውጀዋል። እነዚህ በቀሚሳቸውና በቆባቸው ካልሆነ በቀር አንድም የጳጳስ ሰብእና የሌላቸውና ሊወገዙ የሚገባቸው “ጳጳሳት”፣ መጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ ህገ ቤተክርስቲያንን እንደማያውቁ ካስተላለፉት ህገወጥ ውግዘት መረዳት ተችሏል። እንደክርስቶስ ትምህርት ቤተክርስቲያን ያጠፋውን ሰው ጠርታ መምከርና እንዲመለስ ማድረግ የመጀመሪያ ሥራዋ ነበር። ተመለስ የተባለው ሰው አልመለስ ብሎ ከጸና ግን ታወግዘዋለች። አሁን እነ አባ አብርሃም አስተላለፍን ያሉት ውግዘት ግን ይህን ስርአት ያልተከተለ፣ ከቤተክርስቲያን ፈጽሞ የማይጠበቅ፣ በእነርሱ መለኪያ የተሳሳተን ሰው ከስህተቱ ለመመለስ ሳይሆን በዚያው ጠፍቶ እንዲቀር ለማድረግ የተላለፈ የ“ጥፋ” አዋጅ ነው። በእውነተኛዪቱ ቤተክርስቲያንና በደጋጎቹ አባቶች አይን ሲታይ “ውግዘት ዘበከንቱ” ነው። መጽሐፍ ቅዱስም “እንደሚተላለፍ ድንቢጥ ወዲያና ወዲህም እንደሚበርር ጨረባ፥ እንዲሁ ከንቱ እርግማን በማንም ላይ አይደርስም።” (መጽሐፈ ምሳሌ 26፡2) ሲል የገለጸው አይነት ከንቱ መሆኑን ይናገራል።

ነገ የሚሆነው ባይታወቅም እነርሱ ግን ቤተክርስቲያኗን በእጅ አዙር በማኅበረ ቅዱሳን አመራር ስር መውደቋን በዚህ ስብሰባ ከወሰኗቸው አንዳንድ ውሳኔዎች መገንዘብ ይቻላል። እነዚህ ሃይማኖት የለሾችና ምግባረ ብልሹዎች ከቤተክርስቲያን ተወግዘው ሊለዩ የሚገባቸው መሆናቸውን ማንም ሊያውቀው ይገባል። ይህን ገበናቸውን ስናወጣ እያዘንን ነው። ቤተክርስቲያንም የእነዚህን ጳጳሳት ሳይሆኑ በቀሚስ ውስጥ ያሉ አቶዎች ጵጵስና መያዝና ራሷን ማጥራት አለባት። አሊያ ለሌሎች መሳቂያና መሳለቂያ መሆኗ አይቀርም።

ለግንቦቱ ሲኖዶስ መዶለቻነት ቤታቸውን የሰጡት አባ ጢሞቴዎስ “ዘአልቦ ዕውቀት” ምንም ያልተማሩና ቅዳሴ እንኳን በቅጡ የማያውቁ፣ ለአድማና ለሴራ ግን ማንም የማያህላቸው ሊቅ፣ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ግድያ ውስጥ እጃቸው ያለበት፣ በልማት ኮሚሽን ውስጥ ሳሉ ለእርዳታ የመጣውን ስንዴ አየር ባየር ሲቸበቸቡ የኖሩ፣ ኮንቴነር ሙሉ ዕቃ 4 ኪሎ በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ ያወረዱ ሰው ናቸው። ከዚህ በቀር በረድእ ስም ቤታቸው አስቀምጠዋት ከነበረችው ሚስታቸው ኢሳይያስ የሚባል ልጅ የወለዱ፣ ልጁም ሲያድግ “ጳጳስ እንዴት ይወልዳል?” በሚል ጴንጤ ሆኖ የነበረ፣ በኋላም አላስወጣ አላስገባ ሲላቸው ላዳ ታክሲ ገዝተውለት የነበረ ሲሆን፣ ከዚያም በወቅቱ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ከነበሩት ከሌላው ባለትዳር ጳጳስ ከአባ እስጢፋኖስ ጋር በመነጋገር ወደ አውስትራሊያ ልከውላቸዋል። የአባ እስጢፋኖስን ልጅ ደግሞ አባ ጢሞቴዎስ ሾፌራቸው አድርገውላቸው እርስ በርስ ያላቸውን አባታዊ መተሳሰብ አሳይተዋል። ሚስታቸው የነበረችውም ሴት «የእነዚህን ሃይማኖት ከምከተል ጴንጤ ብሆን ይሻላል» ብላ አሁን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሆናለች። እንዲህ ያሉት መወገዝ አለባቸው እንጂ ማውገዝ እንዴት ይችላሉ? መቼስ አለመማር ደፋር ያደርጋል።

ሌላው አውጋዥ አባ አብርሃም ሲሆኑ፣ እኚህ የጉድ ሙዳይ ከምንኩስና በፊት ባለትዳርና የደርግ ወታደር የነበሩ፣ ደርግ ሲወድቅ እንደአንዳንዶቹ ገዳም ገብተው ከመነኮሱ በኋላ ገዳም ውስጥ አንዷን እማሆይ አስረግዘው «ሀጢአቴ ፍሬ አፍርቶ ማየት አልፈልግምና አስወርጂው» ብለው እንድታስወርድ ያደረጉ፣ ወደ አዲስ አበባ ከመጡም በኋላ የራጉኤል አለቃ ሆነው የቤተክርስቲያኑን ሀብት እጥብ አድርገው የዘረፉ፣ ሰብለ የተባለች ሴት በገርል ፍሬንድነት ይዘው ከሟቹ አባ መልከጼዴቅ ጋር በእርሷ ምክንያት ሲጣሉ የነበሩ የማኅበረ ቅዱሳን የቁርጥ ቀን አባት ናቸው። እንዲህ ያለ ብልሹ ታሪክና ሰብእና ያለው ሰው መወገዝ አለበት እንጂ ማውገዝ ይችላል? ቢያወግዝስ ምን ለውጥ ያመጣል?

ስለአባ ሳሙኤል “የጳጳሱ ቅሌት” በሚል ርእስ በጻፈው መጽሐፍ የቅርብ ወዳጃቸው የነበረውና በቅርበት የሚያውቃቸው ዘሪሁን ሙላቱ ብዙ ነገር ነግሮናል። በቤት ስሟ “ሚጡ” ዋና ስሟ ኤልቤቴል መንገሻ የተባለችን ወጣት እንዲሁም ምሥራቅ የምትባል ቅድስት ማርያም ትሰራ የነበረች ሴት አግብተው ይኖሩ እንደነበረ አገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው እውነት ነው። ከእለታት አንድ ቀንም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በነበሩ ጊዜ ሁለቱም ሚስቶቻቸው አዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት ተገናኝተው በቅናት መንፈስ መደባደባቸውን፣ ጉቦ ካልሰጣችሁ አትቀጠሩም በሚል በቢሮአቸው ደጅ ሲያስጠኗቸው የነበሩ እጅግ በርካታ መነኮሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ መሪጌቶችና የቢሮውም ሰራተኞች ማየታቸውንና መገላገላቸውን ይናገራሉ። ይህን ጉዳይ የአባ ሳሙኤል ጆሮ ካልሆነ በቀር ሁሉ ሰምቶታል። ወዳጃቸው ዘሪሁን ሙላቱ እንደጻፈውም ሰውዬው ግብረሰዶማዊ ናቸው ይላል። በእርግጥም ይህን አባባል ለጊዜው መቀበል ቢከብድም ስለግብረ ሰዶማዊነት አንድ መጽሀፍ እንደልማዳቸው ሰዎችን አጽፈው በስማቸው ማሳተማቸው ጉዳዩን ይበልጥ አሳማኝ አድርጎታል። አሁን ድረስ ከቅድሰት ስላሴ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ መውጣትና ወደጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ መግባት የማይፈልጉት እንደዚህ ላለ ኑሮ ስለተመቻቸው ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው። በዚህ ላይ ደግሞ ዘጠኝ መለኮት ባይ በመሆናቸው በእምነታቸው ችግር ያለባቸው ናቸው። እስኪ አሁን ማን ይሙት አቡነ ሳሙኤል በመጽሐፍ ቅዱስ እንመራ ቤተክርስቲያናችንን ከነቀፋ ነጻ እናድርግ ያሉ ወንጌላውያን ልጆቿን ለማውገዝ ምን ሞራል አላቸው? ምን ብቃት አላቸው?

አባ ዲዮስቆሮስም ከእነዚህ የተለየ ታሪክ የሌላቸው የሁለት ልጆች አባት ናቸው። ልጆቻቸውን ለጊዜው በመደበቅ ነውሮትን እጠብቃለሁ ካላቸው ማኅበር ጋር ቢወዳጁም፣ የማይገለጥ የተሰወረ የለም። ከልጆቹ እናት በተጨማሪ ዘማሪዋን ማርታንም ወሽመዋል ይባላል። አሁን እነዚህ ናቸው ቤተክርስቲያንን እየመሩ ያሉት? እነዚህ መወገዝ ያለባቸው ሰዎች እናውግዝ ሲሉ ትንሽ አለማፈራቸው እጅግ ያስፈራል።

ይህ ሁሉ የምግባር ብልሽት የተከሰተው ከሃይማኖት ችግር ነው። ምግባር የሚገኘው ከቀና ሃይማኖት ነው። ሃይማኖቱ ችግር ያለበት ሰው 
ስርአተ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ በመሆኑ ውግዘቱ ተቀባይነት እንደሌለው ብዙዎች እየተናገሩ ነው። “ወልድ ፍጡር ነው” ላለው ለአርዮስ እንኳን ያልተነፈገውን እድል እነዚህ ጳጳሳት አሁን አወገዝናቸው ላሉት የቤተክርስቲያን ልጆች ነፍገዋቸው ጠርተው ሳያነጋግሯቸውና ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው ቢሆን እንኳን “ትመለሳላችሁ ወይስ አትመለሱም” የሚል የንስሃ እድል ሳይሰጧቸው በማኅበረ ቅዱሳን ክስ ላይ ብቻ ተመስርተው አውግዘናል ማለታቸው ቤተክርስቲያኗ ምን አይነት ሰዎች እጅ ላይ እንደወደቀች የሚያሳይ ነው።

መሰረተ ቢስ ውግዘት ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም እንዳልሆነ ከቤተክርስቲያን ታሪክ መማር ይቻላል። አንዲት የነበረችውን ቤተክርስቲያን እያለያየ እርስ በርሷ እንድትከፋፈልና በጠላትነት እንድትተያይ ከማድረግና ለጠላት ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር የዘለለ ምንም አላስገኘም። ስለ ቤተክርስቲያኗ ምንም ደንታ የሌላቸውና ያስቀደሙ አንዳንድ ጳጳሳትና ዛሬ እየዘወራቸው ያለው ማኅበረ ቅዱሳን የግል ጥቅማቸው እስካልተነካ ድረስ ምንም ባይመስላቸውም፣ ውሳኔው ግን ቤተክርስቲያንን ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍላት የተሳሳተ ውሳኔ ነው የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። ውግዘቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንመራ ባሉና ኦርቶዶክሳውያን ከእናት ቤተክርስቲያናቸው ሳይለዩ የወንጌልን እውነትና አዳኛቸውን አውቀው እንዲኖሩ በተጋደሉ፣ የተላለፈባቸው ውግዘት ህገወጥ በመሆኑ በጀመሩት መንፈሳዊ ጉዞ ላይ የሚያሳድረው አንዳች ተጽእኖ እንደማይኖረው ወንጌልን የሚያውቅ ሁሉ ያውቀዋል። እስካሁንም ቢሆን በህገወጥ መንገድ ከእናት ቤተክርስቲያናቸው በማኅበረ ቅዱሳን ተገፍተው የወጡ ስለሆኑ “ውግዘቱ” በእነርሱ ላይ ሌላ ዕውቅናን ከሚጨምርላቸውና ስራቸውን ይበልጥ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ከሚያበረታቸው በቀር ምንም ለውጥ አያመጣም እየተባለ ነው። ጠርተው ሳያነጋግሯቸው “አወገዝን” ያሉ ሃይማኖትና ምግባር የሌላቸውና፣ በልብሰ ጵጵስና ብቻ ጳጳስ መሆናቸው የሚለዩ አንዳንድ ጳጳሳትና ማኅበረ ቅዱሳን ግን ምንጊዜም በታሪክና በእውነት ፊት ተወቃሾች መሆናቸው የማይቀር ነው። በእነርሱ ውግዘት ወንጌል አይታሰርም። ይልቁንም ወንጌል ከቀድሞው የበለጠ እየሰፋ ይሄዳል። ወንጌል እኮ ሲቃወሙት የሚብስ ሰደድ እሳት ነው። ቀድሞም ቢሆን ወንጌል የሲኖዶስ ፈቃድ ተሰጥቶትና የእነአባን ይሁንታ አግኝቶ አልተሰበከም። በተቃወሞና በስደት፣ በውግዘትና በአድመኞች ሤራ ሳይገታ ነው እየተስፋፋ እዚህ ደርሷል። ነገም የሚያቆመው የለም።

ላለፉት 20 ዓመታት ቤተክርስቲያኒቱ ብዙ የልማት ስራዎችን ሰርታለች። ብዙ ሰው ግን ገፍታለች። ብዙ ህንጻዎችን ገንብታለች። ብዙ ሰው ግን አጥታለች። ብዙ ጳጳሳትን ሾማለች። የአማኞቿ ቁጥር ግን እያሽቆለቆለ ነው። ሕዝበ ክርስቲያኑ ብዙ ገንዘብ ያስገባል። ነገር ግን የጥቂቶች መንደላቀቂያ ነው የሆነው። ተቆጣጣሪ የሌለበት ማኅበረ ቅዱሳንም በቤተክርስቲያን ስም እየዘረፈ ያለው የአንበሳውን ድርሻ የሚይዝ ነው። ህዝበ ክርስቲያኑ ግን በስጋም በነፍስም አንዳች ያገኘው አንዳች ጥቅም የለም። ቤቱ በአጠቃላይ ሰው የሌለበት የተበላሸ ቤት ሆኗል። ለዚህ መድሀኒቱ ደግሞ ጥቅምትና ግንቦት ላይ የሚሰበሰበው ሲኖዶስ ሳይሆን ቅዱስ ወንጌል ነው። ወንጌል ግን ተገፍቷል። የገድልና የድርሳን ተረቶች ተክተውታል። በማኅበረ ቅዱሳንና በእነዚህ ሊወገዙ የሚገባቸው ጳጳሳት ግፊት ቤተክርስቲያን ከዚህ ቀደም በስውር ያደረገችውን ዛሬ በይፋ ካወጀችው  ምን ይባላል? ጌታ ለኢየሩሳሌም እንዳለቀሰላት ለዚህች ቤተክርስቲያን ከማልቀስ በቀር ምንም ማድረግ አይቻልም። ስለዚህ በጌታ ቃል እንዲህ እንላታለን። “ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ ስንኳ ብታውቂ፤ አሁን ግን ከዓይንሽ ተሰውሮአል። ወራት ይመጣብሻልና፥ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኵሉም ያስጨንቁሻል፤ አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን ወደ ታች ይጥላሉ፥ በአንቺ ውስጥም ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተዉም፥ የመጐብኘትሽን ዘመን አላወቅሽምና።” (ሉቃስ 19፡42-44)።


35 comments:

 1. የሀራችንን ክርስትናና ክርስቲያን ለመስቀል ቆራጩና ለጨረቃ ተካዩ ስጡት በውድ እምቢ ብንል ሰይፍና ጎራዴ አንገት ሥር ስላለ የዚያን ጊዜ ይለያል::እስቲ ማን ይሙት?የቱ ይብሳል አሁን ጊዜው የመወጋገዣና የመገፋፊያ ነው ለክርስቲያኑ?ነውን?ነው አባቶቼነው ወዳጆቼ?ከእንግ ታሪክ እንማር ያን የመሰለ የክርስቲያን ሀገር የማን እንደሆነ አሁን እኮ እነሱ መስቀል ለማየት የሚጓጉበት ዘመን ላይ ደርሰዋል ምድራቸውን ጨረቃ እየወረሳት ስለሆነ ለምን ወደዚህ አጀንዳ አንመለስም?
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 2. haha.. eshi asteyayetachihu tikikil new enibel, Gin Ewnet "ወንጌል ግን ተገፍቷል። የገድልና የድርሳን ተረቶች ተክተውታል።" Gedill ena dirsan teret honoal? wechew gudd bilachihu bilachihu demo, Gedill ena dirsanat teret nachew tilun jemer. Endih new "kibbe anguach." Emebirhan libona tistachihu. Ahun asteyayeten kiberut eshi? mechem defrachihu, sihitetachihu sinegerachihu atawetutim. Menafik hula kehadi, kenantes yemayamin ahizab yishalalu, libb yagegnu elet, yikirta teyikew befitsum nisiha yimelesalu. Hulachinin yenisiha sewoch yargen. MedhaneAlem yitareken.

  ReplyDelete
 3. እናንተ ለመንግሥቱ ሥራ ጥሪ የደረሳችህ የቤ/ልጆች!!!

  የጠራችሁን ጌታ ድምጽ በጾም በጸሎት በመሆን ብታደምጡ ፈጣን መልስ ከላይ ይመጣል::

  ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማችሁን አቁሙና ከላይ ከሰማይ በእየለቱ የሚመጣውን ድምጽ በመስማት ሥራችሁን ወይም የተሰጣችሁን የመንግሥቱን አደራ ለመወጣት ሞክሩ:: ክርስትና ዋጋ ያስከፍላልና ዋጋችሁን ከወዲሁ ያልተመናችሁ ተምኑና በጋራ ተንቀሳቀሱ::

  ሰምቶ በእሳት የሚመልስ አምላክ ክብሩን እንደሚገልጥ እንመን

  በርቱ! በርቱ!! በጌታ መንፈስ በርቱ!! የዛሬ ሆሳእና ነግ ወደ ስቀለው
  ሞቱና ቀብሩ ደግሞ የትናሳኤው ኃይል እንደሚከተለው ሁላችንም ብንገነዘብ ከመንፈሳዊ ክስረት እንድናለንና እናስተውል::

  ጌታ በዙፋኑ ላይ ነው
  የዚችን ቤ/ክርስቲያን እድል ፋንታም በጻድቁ እጅ ነውና በርቱ::
  ተስፋን የሰጠው የታመነ ነው::

  ሰላም ሁኑልኝ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 4. ዛሬ የኦርቶዶክስ እምነት ተካታዮች ቁጥር እየቀነሰ የመጣው ከእድዚህ ክፉ መንፈስና የነዋይ ቀበኞች ጳጳሳት ስለ ተገኙባት ነው። ለመሆኑ ከአንድ መንፈሳዊ አባት እንድህ አይነት ሰጣናዊ ስራ ይጠበቃል? የፈሪሳዊያን ካህናት እርሾዎች ናቸው። ጌታ አምላካችንን የሰቀሉት የእነዝህ አይነት ደካማ አባቶች ባህር ያላቸው ናቸው። አሁንም አምላካችን በደሙ ያጸናትን ቤተ ክርስቲያን ያውካሉ። አትፊረድ ይፈረድብሃል። ማንም ሰው የሥራውን አያጣም ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. tew ante manehna silesew kidisina taweraleh, mereja amta inesunim mawgez yichalala

   Delete
 5. I think it is not unusual to be persecuted because of the true ወንጌል. It is a blessing for those brothers and sisters to have their name called and labeled. I think according to the bible ውግዘት is nothing. Our lord said even they might kill you because of the true ወንጌል. Let us not make a big deal out of this. Let us enjoy and praise the Lord for giving us the opportunity. Our Lord is in his throne, he watches everything that happens in this world, especially in his church. He loves those people who our fathers isolated them from the church.HE DIED FOR ALL OF US, HE DOES NOT LOOSE EVEN ONE CHRISTIAN. HE IS A TRUE FATHER. HE CARES. Ultimately all of us will answer for what we have done in this world, NO EXCEPTION.

  ReplyDelete
  Replies
  1. what is true my brother

   Delete
 6. የተገፋው ወንጌል እንጂ ሰው አይደለም። የተጠላው እውነት እንጂ ተሀድሶ አይደለም። የተወገዘው ክርስቶስ እንጂ ሰባኪያን አይደሉም። የሻገተ እንጀራ ይሻለናል እንጂ ቤተክርስቲያኒቱ የነበራትን ንጹህ እንጀራ አንበላም ያሉት የሻገቱ ጳጳሳት ናቸው። የኔሮን ጳጳሳት ውግዘት ክርስትናን እንደሰደድ እሳት ከማቀጣጠል አያቆምም። የነዚህ ጳጳሳት ግዝት ዘበከንቱ አንድ ነገር አስተምሮናል። ቤተክርስቲያኒቱን ለአዲሱ የሸዋ መንግሥት ለማኅበረ ቅዱሳን ማስረከባቸውን። ይሁን እንጂ የወንጌል አገልጋዮች ለክርስቶስ መንግሥት መስፋትና ለቤተክርስቲያን ቀደምት አስተምህሮ መጠናከር የበለጠ መደራጀት፤ መሰባሰብ፤ ኅብረት መፍጠር፤ መትጋትና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መፋጠን እንደሚገባ መልእክት ያስተላለፈ ሆኗል።
  10 እና 15 ሰው በማውገዝ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የተቀጣጠለው የወንጌል እሳት አይቆምም። አንድ እውነት በማስቀመጥ ልቋጭ። የወንጌል ጠላት ማቅ ይወድቃል፤ ወንጌል ግን እንደእሳት ይስፋፋል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. yihen sidib kemanew yetemarkew bakih

   Delete
 7. እውነታችሁን ቢሆን እና ስለ ቤተክርስቲያን በውነት የቆማችሁ ብትሆኑ ኖሮ ይህንን መረጃ ቀድማችሁ ባወጣችሁ ነበር። አሁን ተወገዝን ብላችሁ የጻፋችሁት እና ከጥላቻ ላለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለን? ሌሎቹስ አባቶች ነውር የለባቸውም? ፓትርያርኩ ነውር የለባቸውም? የደገፈንን ሸፍለንለት የተቃወመንን ጥላሸት ቀብተን ክርስትናን መስበክ አይቻልም።

  ReplyDelete
 8. Hulachininm ykir ybelen yegna hatiyat ejig silebeza new betecristian endih yemititamesew

  ReplyDelete
 9. ዘመኑ ከፍቶዋል መጸለይ ሲግባ መወጋገዝ ምንዋጋ አለው ተወጋዦች ሆኑ አውጋዦች የዚች በተክርስቲን ልጆቸ ናቸው ለሀይማኖት እንጂ ለስምና ለዝና አታዳሉ ወደነፈሰው አታጋድሉ እውነትና ንጋት እደር ነወና ወሬ ፈጣሪዎች ግን ሀማኖተኛና ሐቀኛ ሁኑ
  አምላክ ሆይ ቤተክርስቲያንን ጠብቃት!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. በጣም ደስ የሚለው ነገር እምነትን ከልብ አውጥቶ የሚወስድ ማንም የለም። ተወገዙ አልተወገዙ ምንም ትርጉም
   አይሰጥም። ምክንያቱም ለእውነተኛ ክርስቲያኖች እንዲህ ተበሎ ተፅፉአልና፤ በኔ ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ክፉውን
   ሁሉ በውሸት ቢናገሩባችሁ፣ መከራም ቢያበዙባችሁ፣ የምታምኑትን ታውቃላችሁና እንዲሁም እኔ ዓለሙን ሁሉ
   አሸንፌዋለሁና አይዙአችሁ፣ በመከራም ደስ ይብላችሁ እስከ መጨረሻው የፀና እርሱ ይድናል ብሎ ጌታችን አምላካችን
   መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ አስቀድሞ አስጠንቅቆናልና ከምንም አንቆጥረውም። ድሮም እኮ ማቅ የግብር አባቱን
   የዲያቢሎስን ሥራ ለመስራት ነው የሚሩሩጠው ይህ እኮ የታወቀ ነው። ነገር ግን ድሉ የኛ የተገፋነው ክርስቲያኖች ነው።

   ማቅና ግብረአበሮቹ እንኩአን አሁን ጌታችንንም ሰቅለው ሲሳለቁና በትዕቢት ተወጥረው ሲሳደቡ የነበሩ ናቸው። ታዲያ
   ማቅ ያልገባሽ ነገር ቢኖር ድሉ ማታ ነው ድሉ ሲባል ሰምተሻል አይደል\ የኛ ጌታ እኮ የአሸናፊዎች አሸናፊ ነው።
   እንኩአን በክርስትናቸው የበሰሉትን ወንድሞቻችን ቀርቶ ገና ወተት የሚመገቡ በክርስትና ያልበሰሉትን እንኩአን ከእጁ
   ማንም ፈልቅቆ ሊያወጣቸው አይችልም። አሜን። ማፈሪያው ማቅ ኪ...ኪ....ኪ.................

   Delete
 10. አቤት፣ አቤት፣ አቤት ክርስቲያን፣ እናንተን ብሎ ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ፤ እስኪ መጀመሪያ ክርስቲያን ምሰሉ ማለት ከክርስቶስ ተማሩ።
  ማውግዝ የሚቻል ቢሆንስ ጎግል ይህን ክፉ ቃል ስትናገሩ፣ ስትዋሹ፣ ዓለምን ለመበጥበጥ ደፋ ቀና ስትሉ ቢያወግዛችሁ ምን ነበረበት? ግን ምን ይሆናል መቼ ማውገዝ ጀመረና ግን አይቀርም....

  ልብ ይስጣችሁ!!! ቅድስት ንጽሕት ከሆነች ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ኑ! ኑ! ኑ! ንስሓ ግቡ ተመለሱ ትላችኋለች። እግዚኦ መሃርነ ክርስቶስ!!!

  ReplyDelete
 11. የገረመኝን አንድ ነገር ልበላችሁ
  "ኢየሱስን የማያውቅ ያወግዛል
  ኢየሱስን የሚያውቅ ይወገዛል" ለካስ ነገሩ ሁሉ ኢንዲግ ተገለባብጧል? ለመሆኑ የማያምን ውግዘትን እንዴት ተማረ? ይገርማል

  ReplyDelete
 12. ሰደበኝ የደገመኝ እንዲሉ ፣ ይህን ጽሁፍ ብታወጡና ቃላቸውን እናንተም ብታስተጋቡት ፣ መልካም አይመስለኝም ፡፡ ምናልባት አንድ ቀን ህዝብ ማወቅ የሚገባው ማስረጃ ሊሆን ስለሚችል በማለት ብቻ ጽፌላችኋላሁ ፡፡

  የኘሮቴስታንታዊ ተሃድሶ ጠበብቶች ስውር ሴራ ፣ በአንቀልባ ሸፋፍነው ያዘሉት ድብቅ ትምህርትና ዓላማ ፣ በብስጭት ምክንያት በራሳቸው ደጋፊ ገሃድ ወጣ ፡፡ በአባ ሰላማ ድረ ገጽ አንድ ብሶተኛ አስተያየት ሰጭ የክርስቶስ ቤትንም እንደ ፖለቲካው በጐጥና በጐሳ ለማድረግ አስበው እየተንቀሳቀሱ እንደነበር በሰጠው አስተያየት ገለጸ ፡፡ አዘጋጆቹም የሃሳቡ ተጋሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጠው ፣ እንዲህ ዓይነቱን ከፋፋይ ርዕስ ለህዝብ አቅርበው ማስነበባቸውና ፣ አብሮ እንዲነበብ እኔ የጻፍኩትን መልስ አፍነው መያዛቸው ነው ፡፡ ምን ያህል የቆሸሸ ሥራ እየሠሩ እንደነበር ፤ በምን ተጠምደውና በማን አለኝታ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ አንድ ማስረጃ ነው ፡፡ አባ እስጢፋኖስ ዘጉንዳጉንዲን እያወደሱ ፣ አንዴ አቡነ ተክለሃይማኖትን ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ አፄ ዘርዓ ያዕቆብን እያወገዙ የሚጽፉት ሁሉ ከዚሁ የጎሣ እምነታቸው የተነሳ መሆኑን ዛሬ በንዴት ካወጡት ቃል ተረዳሁ ፡፡ በድረ ገጻቸው የተለጠፈው አስተያየት እንደሚከተለው ይነበባል፡፡

  "የተገፋው ወንጌል እንጂ ሰው አይደለም። የተጠላው እውነት እንጂ ተሀድሶ አይደለም። የተወገዘው ክርስቶስ እንጂ ሰባኪያን አይደሉም። የሻገተ እንጀራ ይሻለናል እንጂ ቤተክርስቲያኒቱ የነበራትን ንጹህ እንጀራ አንበላም ያሉት የሻገቱ ጳጳሳት ናቸው። የኔሮን ጳጳሳት ውግዘት ክርስትናን እንደሰደድ እሳት ከማቀጣጠል አያቆምም። የነዚህ ጳጳሳት ግዝት ዘበከንቱ አንድ ነገር አስተምሮናል። ቤተክርስቲያኒቱን ለአዲሱ የሸዋ መንግሥት ለማኅበረ ቅዱሳን ማስረከባቸውን። ይሁን እንጂ የወንጌል አገልጋዮች ለክርስቶስ መንግሥት መስፋትና ለቤተክርስቲያን ቀደምት አስተምህሮ መጠናከር የበለጠ መደራጀት፤ መሰባሰብ፤ ኅብረት መፍጠር፤ መትጋትና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መፋጠን እንደሚገባ መልእክት ያስተላለፈ ሆኗል።
  10 እና 15 ሰው በማውገዝ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የተቀጣጠለው የወንጌል እሳት አይቆምም። አንድ እውነት በማስቀመጥ ልቋጭ። የወንጌል ጠላት ማቅ ይወድቃል፤ ወንጌል ግን እንደእሳት ይስፋፋል።"

  ወዳጅ መሳይ ጠላትህን የምታዳምጠው አንድም ሲደሰት ወይም ሲበሳጭ አለበለዚያም ሲሰክር ነው ፤ ደብቆ የያዘውን ሁሉ ይዘረግፍልሃል ፡፡ "ቤተክርስቲያኒቱን ለአዲሱ የሸዋ መንግሥት ለማኅበረ ቅዱሳን ማስረከባቸውን" የሚለው ቃል መልዕክቱ ምንድር ነው ? አሁን ማን ይሙት የማኀበረ ቅዱሳን አባሎች በሙሉ የሸዋ ሰዎች ብቻ ሆነውባቸው ነው ወይስ የዘርዓ ያዕቆብ ዝርያ አድርገዋቸው ?

  ለኔ የቤተ ክርስቲያን በትረ መንግሥት ግልበጣ ተፈጽሞ መቆየቱንና ማኀበረ ቅዱሳንን ለማጥፋት የሚታገሉት በጎጥ ጭንብል ዓይናቸውን ሸፍነው እንደሆነ አላወቅሁም ነበር ፤ ዛሬ ተማርኩኝ ፡፡ እንደ እነሱ ሃይማኖትን በጎጥ የሚያምን ካለ እነሱኑ መከተል ይችላል ፤ ነገር ግን ይህን ተንኰላቸውን ሳያውቅ አብሮ የሚያጫፍር የኔ ብጤ ገልቱውን ግን እንዲገነዘብ ለማስተማር መንገዱ ሁሉ መቃኘት አለበት ፡፡ ሌላው የተደጋገመ ግድፈትም ክርስቲያን ነን እያሉ አባቶችን መዝለፋቸው ነው ፡፡ ይኸኛው የእምነት ጎደሎነት ብቻ ሳይሆን የአስተዳደግ በደልም ጭምር ነው ፡፡ የክርስትና ትምህርት በሰፈራቸው እንኳን ተሰብኮ የሚያውቅ አይመስለኝም እንኳንስ ክርስቲያን ሊሆኑና ሊባሉ ፡፡ ለወደፊቱ ይህን ዓይነቱንም ዓላማ ጭምር መዋጋት ያስፈልጋልና ከወዲሁ እንዲታሰብበት በማለት ተጻፈ

  ReplyDelete
 13. እውነታችሁን ቢሆን እና ስለ ቤተክርስቲያን በውነት የቆማችሁ ብትሆኑ ኖሮ ይህንን መረጃ ቀድማችሁ ባወጣችሁ ነበር። አሁን ተወገዝን ብላችሁ የጻፋችሁት እና ከጥላቻ ላለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለን? ሌሎቹስ አባቶች ነውር የለባቸውም? ፓትርያርኩ ነውር የለባቸውም? የደገፈንን ሸፍለንለት የተቃወመንን ጥላሸት ቀብተን ክርስትናን መስበክ አይቻልም። since they are protestants and they are supporting those persons that represents themselves.

  ReplyDelete
 14. መወገዝ የሌለባቸው እነማን ናቸው? ለምን? የሚለውን ብታስታውቁን የተሻለ ነው ምክንያቱም ሲኖዶሱ ከስድስት ወር በላይ በሊቃውንት የተጠና ማስረጃ ላይ ተመርኩዞ መሰለኝ ውሳኔውን ያሳለፈው።

  ReplyDelete
 15. በኢትዮጵያ የሲኖዶስ ታሪክ ውስጥ ( ባለፉት 54 ዓመታት ) ቅዱስ ሲኖዶስ ታሪክ የማይረሳው ታላቅ ስህተት ተሳሳተ ። የእግዚአብሐየርን ቤተክርስቲያን ይጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ጳጳሳት አድርጎ ሾሞናል የሚሉ አባቶች « ማኅበረ ቅዱሳንን ፍራቻ » ሾመን ያሉትን መንፈስ ቅዱስን የሚያሳዝን ውሳኔ አስተላልፈዋል ።
  የክርስቶስን ሞት በሚያክፋፋ መልኩ ጽሑፍ የሚጽፈውን፡ ለእግዚአብሔር ኃሳብ ጀርባውን ሰጥቶ የቆመውን ፡ ፍጡራኖና መላዐክትን በእግዚአብሔር ተተክተው እንዲመለኩና እንዲወደሱ የሚሰብከውን፡ ሰቀው በክርስቶስ የመስቀል ሥራ ሳይሆን በድካምና በጥረቱ እንዲጸድቅ የሚያለማምደውን የመናፍቃንን ትምህርት የሚያስፋፋውን ማኀበር ፈርተው፡ ድነት በክርስቶስ የመስቀል ላይ ሥራ በማመንና ይህን እምነትን በመልካም ክርስቲያናዊ ሥራ በመተግበር መኖር በቂ ነው ያሉትን፡ስግደት ለፍጡራን ሰዎችና ለመላዕክትም ቢሆን ተገቢ አይደለም ፡ መጽሐፍ ቅዱስ የክርስትናችን መሠረትና ብቸኛ መመሪያ መሆን አለበት ብለው የተነሱትን ፡ በክርስቶስ በማመመን የሚገኘውን ጽድቅ ና የዘላለም ሕይውት እንስበክ ብለው ጥያቄ ያቀረቡትን የቤተክርስቲያኒቱን ልጆችና ማኅበራት አውግዘናል በሕግም እንጠይቃለን በማለት ለመወሰን( ውሳኔ ለማስተላለፍ ) መፈለጋቸው እነዚህ አባቶች ለቤተክርስቲያኒቱም ሆነ ለሀገር ደንታ ቢስ መሆናቸውን የሚያሳይ ውሳኔ ነው። እላለሁ። አሁን አባቶች ወሰነው ያሉት ውሳኔ ማኅበረ ቅዱሳን በድልለና አንዳዶችንም በስህተታቸው ማስረጃ በመሰብሰብ ባስደነገጣቸው ጥቂት « ጳጳሳት » ድጋፍ አዘጋጅቶ ያቀረበው ወረቀት ግልባጭ ነው። አሁን ወሰነው ባሉት ጉዳይ እረፍት የሚያገኙ መስሏቸው ከሆነ ዓለምን የሚያስገርም ስህተት እንደፈጸሙ ማን በነገራቸው። ለመሆኑ ሲኖዶስ የሚባለው ማኅበረ ቅዱሳን ነው ወይስ ...?

  ReplyDelete
 16. አውጋዥም ተወጋዥም ካሥር በታች ዘጠኝ ቁጥር ቅዝቃዤ ደርሰዋል፤
  ምክንያት (ክፉ ካልሆንህ ክፉ አያገኝህም )ይላልና ሢራክ፤ አውጋዦቹ ቤተ ተ/ሀይማኖት ተወጋዦቹ ቤተ እስጢፋኖስ ሁለቱም ወገኖች ከማለፋቸው በፊት ክፋይ( ጥንሽ )ሙቀተ መንፈስ ቅዱስ ሊያገኙ ይገባል፤
  ወትዋች አስወጋዦቹ ግን ለመጨረሻው የፍርድ ቀን ተጠብቀዋል፤

  ReplyDelete
 17. ድንገትም ባይሆን በወቅቱ የሚናፈሰው የአስወጋዦችና የተወጋዦች ወሬ እንዳይልፈኝ ካመቸኝም እኔም ለማውራት ብዬ ወደ ብሎጎች ጎራ አልኩ፡፡ በስንት ልመድበው እንደምችል ባይገባኝም የተጻፈውና የሚነበበው ሁሉ ጎጠኝነት፣ ፖለቲከኛነት፣ እኔነት፣ ስሜታዊነት፣ ድንፋታ፣ ተማጽኖ ምኑቅጡ ድብልቅልቅ ያለ ሆነብኝና ራሴን ጠየቅሁት? የሰው ፍላጎት ምንድነው? ግጭት ወይስ ሰላም? ልዩነት ወይስ አንድነት? እውነት ወይስ ውሸት? ታማኝነት ወይስ ሽንገላ? ለጥያቄዬ መልስ አላገኘሁለትም፡፡ ሁሉም እኔ ነኝ እውነተኛ፣ እኔ ነኝ ትክክል ነዋ የሚለው! ማንን በምን ልመዝነውና እውነት ሃሰቱን ልለየው፡፡
  ግን አንድ ነገር አስተውያለሁ፡፡ ይህ ሁሉ ውጣ ውረድ ‹‹ተሃድሶ›› እና ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› በሚባሉ በሁለት ታላላቅ ጎራዎች አለመስማማት የተነሳ የተፈጠረ ግብግብ መሆኑንና እውነቱን ለሚፈልግ ከወገንተኛ ስሜት ነጻ ሆኖ ቀጣዩን የአገሪቱንና በተለይም የኦርቶዶክሳዊው ሕዝብ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል በስጋትም በጉጉትም የሚጠብቀውን ሰው የሚያበረታታ የችግሩን መንስኤ አሳይቶ መፍትሔ ሊሆን የሚችል ሃሳብ የሚያመነጭ አቅጣጫ የሚመራ የሰከነ ሰው አላየሁም፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳኖቹም ሆኑ ተሃድሶዎቹ አንዱ አንዱን ሲያጥላሉን ሲነቅፉ እንጂ የእኔ አስተምህሮ ይኸ ነው ብለው በግልጥ ሲያቀርቡ አላስተዋልኩም፡፡ ነገሩ እነርሱ እንደሚሉት ሕዝቡ ስለ እምነቱ በቂ ግንዛቤ ስለሌለው ማን ይዳኘናል ብለው ሰግተው ይሁን ወይም ሁለቱም የሚያስተምሩት በቂ ትምህርት ስሌለላቸው አላውቅም፡፡ ብቻ አንዱ አንዱን ጸረ ምንትስ እያሉ እውነተኛ መስለው ለመታየት የሚያደርጉትን ፍትጊያ መስማትና መመልከት የሰለቸ ነገር ሆኖብኛል፡፡
  እናንተ ሁለት ጎራ ውስጥ ያላችሁ ቡድነኞች፤ የምትሰሙኝ ከሆነ እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን የማይበጀውን እልህ መገባባት ትታችሁ አለን የምትሉትን ማስረጃ ያለው ሃሳባችሁን (ትምህርታችሁን) በዝርዝር አስነብቡንና እንመዝናችሁ ዘንድ ፍቀዱልን፤ ምናልባት እንደ እናንተ በየኮሌጆቹ ውስጥ እየገባን በነገረ መለኮት ባንመረቅም የሚቀርቡልንን መረጃዎች መዝነን እውነት ሃሰቱን ለመለየት ብዙም አንቸገር ይሆናል፡፡
  እናንተ የእኔ መሰሎቹ ምእመናን ክርስትና አስተዋይነት እንጂ ስሜታዊነት፣ እውነተኝነት እንጂ ሸንጋይነት፣ ዓለም አቀፋዊነት እንጂ ኢትዮጵያዊነት … አይደለምና ረጋና ሰከን ብላችሁ የግራ ቀኙን ሃሳብ ለማዳመጥ ዝግጁ ሁኑ፡፡ እኔ እንደማውቀው እውነት የሚለካው በያዘው እውነት እንጂ በሕዝብ ብዛት አይደለም፡፡ በተለይም ክርስትና የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡት ግን ጥቂቶች መሆናቸውን ስለሚናገር ምናልባት ብዙነታችን እንዳያስታብየንና ከተጣሉት መሃል እንዳያደርገን ማሰብ ያለብን መስለኛል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያነበብኳቸው ታሪኮች ጥቂቶቹን እውነተኞች እያደረጉ ብዙዎቹን ጥፋተኞች የሚሉ መሆናቸው አሳስቦኝ ነው ይህንን ያልኩት፡፡
  ሰለስቱ ደቂቅ የምንላቸው ሶስቱ ሰዎች ለናቡከደነጾር ምስል አንሰግድም ብለው ወደ እሳት ሲጣሉ የእግዚአብሔር ክንድ እስኪታደጋቸው ድረስ ማንም እውነታቸውን ነው ያለ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ሶስት ብቻ ነበሯ፡፡ ሶስት ለእልፍ አእላፋት፤ እናም ጥቂትነትና ብዙነት ለእውነት መለኪያና ማረጋገጫ እንደማይሆን እናስተውል ዘንድ ይገባናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ደግሞም ጨምር ካላችሁኝ ጌታ ኢየሱስ በከሰሱትና በሰቀሉት አይሁድ መካከል አንድ ነበር፡፡ ዙሪያውን ከብበውት ይጠይቁትና ያዋርዱት የነበሩትን ሰዎች ደግሞ እናንተ ቁጠሯቸው፡፡ ንጽጽር ብንሰራ 1፡ለቆጠራችሁት ሕዝብ መሆኑን አስተውሉ፡፡ እነርሱ ብዙ ስለ ነበሩ የጌታችንንና የመድኃኒታችንን እውነተኛነት አልቀለበሱትም፡፡ እርሱም አንድ ስለሆነ ሃሰተኛ አልሆነው፡፡ ዛሬም እንዲሁ ይመስለኛል ለክርስትና! ምናልባት ድምጽ ብልጫ የሚያገለግለው ለፌዴራላዊ መንግሥታት እንጂ ለክርስትና አይደለምና ልናስተውል ይገባል፡፡
  ዘመናችን የሥልጣኔ ነጸብራቆች ሊታዩበት የሚገባ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ውሻና ድመት፣ አይጥና ድመት፣ አንበሳና ሰው በጥቅሉ አጥፊና ጠፊ የምንላቸው ፍጥረታት እየተሻሹ መዋል ማደራቸውን በምናይበት በዚህ ዘመን አንድ ቋንቋ ተናጋሪ የአንድ ቤተ ክርስቲያን ሰዎች መነጋገርና መደማመጥ ካቃታችሁ፣ ለቤተ ክርስቲያናችሁ የሚያስብና ለሕዝባችሁ የሚራራ ልብ ካጣችሁ … ዓላማችሁ እምነት ነወይ? ብዬ እንድጠይቅ ያስገድደኛል፡፡ ስውር ዓላማ ከሌላችሁ ስለ አላማችሁ አስተምሩን፤ የተለያያችሁበትን ነጥብ በግልጽ ንገሩንና እኛ እንመዝነው፡፡ በተረፈ ማንኛችሁም ስለ እኛ ወሳኝ ከመሆን ተቆጠቡ፡፡
  እናንተ እድሜ ጠገብ አባቶችም ይህንን ስሙኝ፡፡ አንድ እለት እለት ትነዘንዘው የነበረችውን ሴት የፈረደላትን ዳኛ ታሪክ ታውቁት የለ? ግብሩን አይደለም ታሪኩን ነው ያልኩት! ምንም እንኳ ሰውን ባትፈሩ ማንም ምንም ሊያደርግባችሁ እንደማችል ብትተማመኑ ነገር ግን ለሁሉ እንደ ሥራው ሊያስረክበው በክብር የሚገለጠውን ጌታ ትፈሩት ዘንድ ሰማይንና ምድርን እማኝ አድርጌ እናገራችኋለሁ፡፡ ሥልጣን የተሰጣችሁ ለሰው ፊት ሳታደሉ ሁሉን በአንድ ዓይን አይታችሁ እውነት ልትናገሩና ልትፈርዱ ስለሆነ አድሎ የሰራችሁበትንና ሁለቱን ጎራዎች እርስ በርስ እያናከሳችሁበት ያለውን ቸልተኛነታችሁንና አድሎኛነታችሁን በንስሃ ከእናንተ ታርቁት ዘንድ አሳስባችኋለሁ፡፡ ሁለት ተከፋላችሁ አንደኛችሁ ላንዱ ዱላ እያቀበላችሁ እርስ በርስ ማፋጀታችሁ የክብር ሽልማት እንደማያስገኛላችሁ አበክሬ ላሳስባችሁ ግድ ሆኖብኛል፡፡ በተለይም በሰሞኑ ወሰናችሁት እየተባለ የሚሰማው የማውገዝና የማስወገዝ ተግባር ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ መሆኑ ሲነገር ይሰማልና አሳዝኖኛል፡፡ ይህንን ሳስብ ኒቆዲሞስ የሚባለው የህግ መምህር በሸንጓቸው የተናገረው ቃል ትዝ አለኝ፡፡ ሰው ምን እንዳደረገ ሳይነገረው የህጉንም ቃል ሳይሰማ ይፈረድበታልን? እናንተም እንዲሁ እንዳደረጋችሁ ይነገራልና እውነት አድርጋችሁት ከሆነ የሚያሳፍር ነው፡፡ አባቶቻችን የምንላቸው ሰለስቱ ምዕት፣ ከዚያም በኋላ በቁስጥንጥንያና በኤፌሶን መናፍቃንን ያወወገዙ ምሳሌዎቻችን የተከሳሾቹን ቃል ሰምተው አስተምረውና መክረው አልመለስ ያሉትን አውግዘው መለየታቸው የታወቀ ነው፡፡ እናንተም እንዲሁ አድርጋችሁ ስህተቱን ለይታችሁ ከሆነ አበጃችሁ! ሃይማኖት የሚጠበቀው በዚሁ መንገድ ነው፡፡ እንዲህ ሳታደርጉ የአንድ ወገንን አቤቱታ ሰምታችሁና ወግናችሁ ከሆነ ግን አሳዛኝ ነው፡፡ ታሪክ ሲዘጅረው የሚኖረው አሳፋሪ ተግባር፡፡
  ለማንኛውም ለዛሬው በዚሁ ልሰናበታችሁ፡፡ ለሁለቱ ጎረኞች ግን አንድ ነገር ደግሜ ላስታውስ፤ እውነት ይዘናል ካላችሁ የማያሳፍር መረጃ ካላችሁ ሜዳው ይኸው ፈረሱም ይኸው እንያችሁ! እውነቱን አቅርቡልን፤ እንድንፈርድ ዕድል ስጡን፡፡ ዳር ላይ ቆመን የምናሽቃብጠውም ታግሰን እንከታተላቸውና ከእውነተኞች በኩል ለመቆም እንዘጋጅ፡፡

  ReplyDelete
 18. ለሰላም መፍትሔው መዘላለፍ ሳይሆን መማማር ነው!

  ድንገትም ባይሆን በወቅቱ የሚናፈሰው የአስወጋዦችና የተወጋዦች ወሬ እንዳይልፈኝ ካመቸኝም እኔም ለማውራት ብዬ ወደ ብሎጎች ጎራ አልኩ፡፡ በስንት ልመድበው እንደምችል ባይገባኝም የተጻፈውና የሚነበበው ሁሉ ጎጠኝነት፣ ፖለቲከኛነት፣ እኔነት፣ ስሜታዊነት፣ ድንፋታ፣ ተማጽኖ ምኑቅጡ ድብልቅልቅ ያለ ሆነብኝና ራሴን ጠየቅሁት? የሰው ፍላጎት ምንድነው? ግጭት ወይስ ሰላም? ልዩነት ወይስ አንድነት? እውነት ወይስ ውሸት? ታማኝነት ወይስ ሽንገላ? ለጥያቄዬ መልስ አላገኘሁለትም፡፡ ሁሉም እኔ ነኝ እውነተኛ፣ እኔ ነኝ ትክክል ነዋ የሚለው! ማንን በምን ልመዝነውና እውነት ሃሰቱን ልለየው፡፡
  ግን አንድ ነገር አስተውያለሁ፡፡ ይህ ሁሉ ውጣ ውረድ ‹‹ተሃድሶ›› እና ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› በሚባሉ በሁለት ታላላቅ ጎራዎች አለመስማማት የተነሳ የተፈጠረ ግብግብ መሆኑንና እውነቱን ለሚፈልግ ከወገንተኛ ስሜት ነጻ ሆኖ ቀጣዩን የአገሪቱንና በተለይም የኦርቶዶክሳዊው ሕዝብ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል በስጋትም በጉጉትም የሚጠብቀውን ሰው የሚያበረታታ የችግሩን መንስኤ አሳይቶ መፍትሔ ሊሆን የሚችል ሃሳብ የሚያመነጭ አቅጣጫ የሚመራ የሰከነ ሰው አላየሁም፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳኖቹም ሆኑ ተሃድሶዎቹ አንዱ አንዱን ሲያጥላሉን ሲነቅፉ እንጂ የእኔ አስተምህሮ ይኸ ነው ብለው በግልጥ ሲያቀርቡ አላስተዋልኩም፡፡ ነገሩ እነርሱ እንደሚሉት ሕዝቡ ስለ እምነቱ በቂ ግንዛቤ ስለሌለው ማን ይዳኘናል ብለው ሰግተው ይሁን ወይም ሁለቱም የሚያስተምሩት በቂ ትምህርት ስሌለላቸው አላውቅም፡፡ ብቻ አንዱ አንዱን ጸረ ምንትስ እያሉ እውነተኛ መስለው ለመታየት የሚያደርጉትን ፍትጊያ መስማትና መመልከት የሰለቸ ነገር ሆኖብኛል፡፡
  እናንተ ሁለት ጎራ ውስጥ ያላችሁ ቡድነኞች፤ የምትሰሙኝ ከሆነ እንዲህ ለቤተ ክርስቲያን የማይበጀውን እልህ መገባባት ትታችሁ አለን የምትሉትን ማስረጃ ያለው ሃሳባችሁን (ትምህርታችሁን) በዝርዝር አስነብቡንና እንመዝናችሁ ዘንድ ፍቀዱልን፤ ምናልባት እንደ እናንተ በየኮሌጆቹ ውስጥ እየገባን በነገረ መለኮት ባንመረቅም የሚቀርቡልንን መረጃዎች መዝነን እውነት ሃሰቱን ለመለየት ብዙም አንቸገር ይሆናል፡፡
  እናንተ የእኔ መሰሎቹ ምእመናን ክርስትና አስተዋይነት እንጂ ስሜታዊነት፣ እውነተኝነት እንጂ ሸንጋይነት፣ ዓለም አቀፋዊነት እንጂ ኢትዮጵያዊነት … አይደለምና ረጋና ሰከን ብላችሁ የግራ ቀኙን ሃሳብ ለማዳመጥ ዝግጁ ሁኑ፡፡ እኔ እንደማውቀው እውነት የሚለካው በያዘው እውነት እንጂ በሕዝብ ብዛት አይደለም፡፡ በተለይም ክርስትና የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡት ግን ጥቂቶች መሆናቸውን ስለሚናገር ምናልባት ብዙነታችን እንዳያስታብየንና ከተጣሉት መሃል እንዳያደርገን ማሰብ ያለብን መስለኛል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያነበብኳቸው ታሪኮች ጥቂቶቹን እውነተኞች እያደረጉ ብዙዎቹን ጥፋተኞች የሚሉ መሆናቸው አሳስቦኝ ነው ይህንን ያልኩት፡፡
  ሰለስቱ ደቂቅ የምንላቸው ሶስቱ ሰዎች ለናቡከደነጾር ምስል አንሰግድም ብለው ወደ እሳት ሲጣሉ የእግዚአብሔር ክንድ እስኪታደጋቸው ድረስ ማንም እውነታቸውን ነው ያለ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም ሶስት ብቻ ነበሯ፡፡ ሶስት ለእልፍ አእላፋት፤ እናም ጥቂትነትና ብዙነት ለእውነት መለኪያና ማረጋገጫ እንደማይሆን እናስተውል ዘንድ ይገባናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ደግሞም ጨምር ካላችሁኝ ጌታ ኢየሱስ በከሰሱትና በሰቀሉት አይሁድ መካከል አንድ ነበር፡፡ ዙሪያውን ከብበውት ይጠይቁትና ያዋርዱት የነበሩትን ሰዎች ደግሞ እናንተ ቁጠሯቸው፡፡ ንጽጽር ብንሰራ 1፡ለቆጠራችሁት ሕዝብ መሆኑን አስተውሉ፡፡ እነርሱ ብዙ ስለ ነበሩ የጌታችንንና የመድኃኒታችንን እውነተኛነት አልቀለበሱትም፡፡ እርሱም አንድ ስለሆነ ሃሰተኛ አልሆነው፡፡ ዛሬም እንዲሁ ይመስለኛል ለክርስትና! ምናልባት ድምጽ ብልጫ የሚያገለግለው ለፌዴራላዊ መንግሥታት እንጂ ለክርስትና አይደለምና ልናስተውል ይገባል፡፡
  ዘመናችን የሥልጣኔ ነጸብራቆች ሊታዩበት የሚገባ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ውሻና ድመት፣ አይጥና ድመት፣ አንበሳና ሰው በጥቅሉ አጥፊና ጠፊ የምንላቸው ፍጥረታት እየተሻሹ መዋል ማደራቸውን በምናይበት በዚህ ዘመን አንድ ቋንቋ ተናጋሪ የአንድ ቤተ ክርስቲያን ሰዎች መነጋገርና መደማመጥ ካቃታችሁ፣ ለቤተ ክርስቲያናችሁ የሚያስብና ለሕዝባችሁ የሚራራ ልብ ካጣችሁ … ዓላማችሁ እምነት ነወይ? ብዬ እንድጠይቅ ያስገድደኛል፡፡ ስውር ዓላማ ከሌላችሁ ስለ አላማችሁ አስተምሩን፤ የተለያያችሁበትን ነጥብ በግልጽ ንገሩንና እኛ እንመዝነው፡፡ በተረፈ ማንኛችሁም ስለ እኛ ወሳኝ ከመሆን ተቆጠቡ፡፡
  እናንተ እድሜ ጠገብ አባቶችም ይህንን ስሙኝ፡፡ አንድ እለት እለት ትነዘንዘው የነበረችውን ሴት የፈረደላትን ዳኛ ታሪክ ታውቁት የለ? ግብሩን አይደለም ታሪኩን ነው ያልኩት! ምንም እንኳ ሰውን ባትፈሩ ማንም ምንም ሊያደርግባችሁ እንደማችል ብትተማመኑ ነገር ግን ለሁሉ እንደ ሥራው ሊያስረክበው በክብር የሚገለጠውን ጌታ ትፈሩት ዘንድ ሰማይንና ምድርን እማኝ አድርጌ እናገራችኋለሁ፡፡ ሥልጣን የተሰጣችሁ ለሰው ፊት ሳታደሉ ሁሉን በአንድ ዓይን አይታችሁ እውነት ልትናገሩና ልትፈርዱ ስለሆነ አድሎ የሰራችሁበትንና ሁለቱን ጎራዎች እርስ በርስ እያናከሳችሁበት ያለውን ቸልተኛነታችሁንና አድሎኛነታችሁን በንስሃ ከእናንተ ታርቁት ዘንድ አሳስባችኋለሁ፡፡ ሁለት ተከፋላችሁ አንደኛችሁ ላንዱ ዱላ እያቀበላችሁ እርስ በርስ ማፋጀታችሁ የክብር ሽልማት እንደማያስገኛላችሁ አበክሬ ላሳስባችሁ ግድ ሆኖብኛል፡፡ በተለይም በሰሞኑ ወሰናችሁት እየተባለ የሚሰማው የማውገዝና የማስወገዝ ተግባር ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለ መሆኑ ሲነገር ይሰማልና አሳዝኖኛል፡፡ ይህንን ሳስብ ኒቆዲሞስ የሚባለው የህግ መምህር በሸንጓቸው የተናገረው ቃል ትዝ አለኝ፡፡ ሰው ምን እንዳደረገ ሳይነገረው የህጉንም ቃል ሳይሰማ ይፈረድበታልን? እናንተም እንዲሁ እንዳደረጋችሁ ይነገራልና እውነት አድርጋችሁት ከሆነ የሚያሳፍር ነው፡፡ አባቶቻችን የምንላቸው ሰለስቱ ምዕት፣ ከዚያም በኋላ በቁስጥንጥንያና በኤፌሶን መናፍቃንን ያወወገዙ ምሳሌዎቻችን የተከሳሾቹን ቃል ሰምተው አስተምረውና መክረው አልመለስ ያሉትን አውግዘው መለየታቸው የታወቀ ነው፡፡ እናንተም እንዲሁ አድርጋችሁ ስህተቱን ለይታችሁ ከሆነ አበጃችሁ! ሃይማኖት የሚጠበቀው በዚሁ መንገድ ነው፡፡ እንዲህ ሳታደርጉ የአንድ ወገንን አቤቱታ ሰምታችሁና ወግናችሁ ከሆነ ግን አሳዛኝ ነው፡፡ ታሪክ ሲዘጅረው የሚኖረው አሳፋሪ ተግባር፡፡
  ለማንኛውም ለዛሬው በዚሁ ልሰናበታችሁ፡፡ ለሁለቱ ጎረኞች ግን አንድ ነገር ደግሜ ላስታውስ፤ እውነት ይዘናል ካላችሁ የማያሳፍር መረጃ ካላችሁ ሜዳው ይኸው ፈረሱም ይኸው እንያችሁ! እውነቱን አቅርቡልን፤ እንድንፈርድ ዕድል ስጡን፡፡ ዳር ላይ ቆመን የምናሽቃብጠውም ታግሰን እንከታተላቸውና ከእውነተኞች በኩል ለመቆም እንዘጋጅ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ድንቅ ብለሃልና ይበል ብያለሁ ፡፡

   Delete
 19. Hahahahahahahaha..... u always shouting when ur pros are cursed.

  ReplyDelete
 20. በስመአብ . . . የዘንዶው አፍ እንዴት የሸታል፡፡ ያም ዘንዶ እናንተ ናችሁ፡፡ ስለመደሀኒአለም የብሎጋችሁ ራስ ላይ ያደረጋችኋቸውን አባቶች ፎቶ አንሱት፡፡ በፍጹም ለእንዲህ አይነት ርካሽ ስድድብ መግቢያ ሊሆኑ አይገባም፡፡ አፍሬባችኋለሁ . . . . አፍሬባችኋለሁ . . . . አፍሬባችኋለሁ . . . . እግዚአብሄር የስራችሁን ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 21. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 22. አሁን ተወገዛችሁ። ባለማወቅ የደገፏችሁም ፓትርያርክ አረፉ። አሁን ለምዳችሁ ተገፎ ተኩላ መሆናችሁ ስለታወቀ የሞት ሽረት ትግል ላይ ናችሁ። ደህና ሁኑ። ወደ አማኑኤል ቸርቻችሁ ሂዱ። መቼም ጌታ ይከተላችሁ አልላችሁም። ይቅር ይበላችሁ እንጂ ።

  ReplyDelete
 23. እውነታችሁን ቢሆን እና ስለ ቤተክርስቲያን በውነት የቆማችሁ ብትሆኑ ኖሮ ይህንን መረጃ ቀድማችሁ ባወጣችሁ ነበር። አሁን ተወገዝን ብላችሁ የጻፋችሁት እና ከጥላቻ ላለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለን? ሌሎቹስ አባቶች ነውር የለባቸውም? ፓትርያርኩ ነውር የለባቸውም? የደገፈንን ሸፍለንለት የተቃወመንን ጥላሸት ቀብተን ክርስትናን መስበክ አይቻልም

  ReplyDelete
 24. TEHADSO!! GETA,IYESUS, LEMALET YMIYAFREW TWLD MTADES YASFELGEWAL SMUN SHESHGWALNA
  KDMIYA MEKBER YALEBET YKBER

  ReplyDelete
 25. WUD YE ABA SELAMA AZEGAJOCH. KENTU NEGERACHIHUN TITACHIHU NISEHA GIBUNA EGZIABHEREN BITAGELEGILU TIRU NEW. ESKEZARE YADEREGACHIHUN NEGER LEFAT BICHA NEW YEHONEBACHIHU ENJI MINIM LEWT ALAMETACHIHUM MANINIM MASASAT ALCHALACHIHUM.

  EGZIABHER MASTEWAL YISTACHIHU

  ReplyDelete
 26. እናንተ መናፍቃን እውነታችሁን ቢሆን እና ስለ ቤተክርስቲያን በውነት የቆማችሁ ብትሆኑ ኖሮ ይህንን መረጃ ቀድማችሁ ባወጣችሁ ነበር። አሁን ተወገዝን ብላችሁ የጻፋችሁት እና ከጥላቻ ላለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለን? ሌሎቹስ አባቶች ነውር የለባቸውም? ፓትርያርኩ ነውር የለባቸውም? የደገፈንን ሸፍለንለት የተቃወመንን ጥላሸት ቀብተን ክርስትናን መስበክ አይቻልም።

  ማውግዝ የሚቻል ቢሆንስ ጎግል ይህን ክፉ ቃል ስትናገሩ፣ ስትዋሹ፣ ዓለምን ለመበጥበጥ ደፋ ቀና ስትሉ ቢያወግዛችሁ ምን ነበረበት? ግን ምን ይሆናል መቼ ማውገዝ ጀመረና ግን አይቀርም....

  ልብ ይስጣችሁ!!! ቅድስት ንጽሕት ከሆነች ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ኑ! ኑ! ኑ! ንስሓ ግቡ ተመለሱ ትላችኋለች። እግዚኦ መሃርነ ክርስቶስ!!!

  ReplyDelete
 27. እውነታችሁን ቢሆን እና ስለ ቤተክርስቲያን በውነት የቆማችሁ ብትሆኑ ኖሮ ይህንን መረጃ ቀድማችሁ ባወጣችሁ ነበር። አሁን ተወገዝን ብላችሁ የጻፋችሁት እና ከጥላቻ ላለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለን? ሌሎቹስ አባቶች ነውር የለባቸውም? ፓትርያርኩ ነውር የለባቸውም? የደገፈንን ሸፍለንለት የተቃወመንን ጥላሸት ቀብተን ክርስትናን መስበክ አይቻልም

  ReplyDelete
 28. yesedeben kale lisadeb zedowen afun kefete yetebalelachu (protestant)enante natchu.atasemeslu,yebeg lemedachun aweleku betam yasazenal

  ReplyDelete