Thursday, May 17, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ክፍል የዋልድባን ጉዳይ በተመለከተ የቤተ ክህነቱ አጣሪ ኮሚቴን ሪፖርት ያልዘገበበትን ምክንያት እንዲያብራራ ተጠየቀ

በ PDF ለማንበብ (ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት ብሎግ)
ህዝብ ሆይ ስማ!! ተነስ! ታጠቅ! ዝመት! ዋልድባ ገዳም ተተረማመሰ። እያለ በድረ ገጾቹ ግልጽ ፖለቲካዊ ቅስቀሳ እያደረገ ያለው የመንፈሳዊነት ጭላጩ እንኳ የሌለው ማኅበረ ቅዱሳን በዋልድባ ጉዳይ ከቤተክህነት የተሰጠውን መግለጫ ላለመዘገብ መወሰኑ የቤተክህነቱን ህዝብ ግንኙነት መምሪያ አስቆጣ።
የህዝብ ግንኙነት መምሪያው የሰንበት ማደራጃ መምሪያውን ማኅበረ ቅዱሳን ለምን ዜናውን እዘግባለሁ ካለ በኋላ ባሉት ህጋዊ ሚዲያዎቹ ሁሉ ላለመዘገብ መወሰኑን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጥበት በማዘዝ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው በደብዳቤ ጠይቋል።
ለዚህ ጥያቄ የራሱን መልስ መስጠት የማይችለው ሰንበት ማደራጃ መምሪያው ጉዳዩ የማህበሩን የሚዲያ ክፍሎች
 በተመለከተ ይሆናል በሚል ርዕስ ባወጣው ደብዳቤ ለምን ዜናውን ሳትዘግቡ ቀራችሁ የሚል ጥያቄን ጠይቆ ለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡበት አዟል። የሁልጊዜውም አላማው የፖለቲካ አየሩ ላይ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አቧራ ማቡነን የሆነው ማቅ ዋልድባን በተመለከተ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ ሲሆን ባለፉት 2 ወራት እንኳ ከ20 በላይ የግልጽ ተቃውሞና ህዝብን የማነሳሳት ዘገባዎችን አንዳችም መንፈሳዊ ባህሪ በሌለው መልኩ ማቅረቡ የሚታወስ ነው። እንዲያውም የማህበሩ ብሎጎች በሚያደርጉት ቅስቀሳ ጠብቀውት የነበረውን የአረቦች መነሳሳት አይነት አመጽ ሊያገኙ ባለመቻላቸው ስሜታውያን ህጻናት እንደፈለጉ እንዲቧችሩበት ፈቅዶ ማቅ ባቋቋመው አንድ አድርገን በተሰኘ ብሎግ እኛስ ሞተናል በሚል ርዕስ ምሬቱን መግለጹ አይዘነጋም።
ማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ በግልጽ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ በስውር ከፍተኛ የሆነና አልቃይዳ ተኮር ስልት ህዝብን በመንግስት ላይ ለማነሳሳት የሚያደርገው ቅስቀሳን ሽባ እንደሚያደርግበት ስለተረዳ በቤተ ክህነቱ የተሰጠውን መግለጫ የጋዜጠኛ ስነ ምግባርን በጣሰ መልኩ በህጋዊ የዜና ማሳረጫ መንገዶቹ  ላለመዘገብ ወስኗል።
ዳንኤል ክብረት እንደነገረን ከፍተኛ የአቅም ማነስ የሚታይባቸውና ሙያንና ስሜትን ለይተው የማያውቁት የማኅበሩ ጋዜጠኞች በይፋ የተዘገበን ዜና በይፋ እንዘግባለን ብለው ሄደው ውለው ሳያድሩ ግን በብሎጎቻቸው የቤተክህነቱን አጣሪ ኮሚቴ መግለጫ በከፍተኛ ሁኔታ እያጥላሉ ዘግበውታል።
ከኔ ወዲያ ላሳር የሚለው ማቅ የራሱን አጣሪ ኮሚቴ ወደ ዋልድባ ልኮ አጣርተው መመለሳቸው ይታወቃል። ልኡካኑ ደረሱበት የተባለውም ድምዳሜም ፕሮጀክቱ ችግር የለውም የሚል ነው። ማኅበረ ቅዱሳን የውጭ አገር ደጋፊዎቹን መንግስት አስገድዶኝ እንዲህ ብለህ መግለጫ ስጥ ብሎኝ ነው መግለጫውን የሰጠሁት ብሎ ማሳመን እንደሚችል ቢያውቅም፣ የአገር ውስጦቹን ግን በምን እንደሚያሳምናቸው ማጣፊያው አጥሮታል። የማኅበሩ አባላት በሞባይል የጽሁፍ መልዕከት ለአባለት ብቻ ጥብቅ ምሥጢር ተባብለው በሚላላኩበት የ “ተነስ ወደ ዋልድባ” ቅስቀሳ ደማቸው የሞቀውን አባላቱን ቁጣቸውን ወደ እኔ እንዳያዞሩ ሲል ልዑካን ልኬ አጣርቼ ደረስኩበት ያለውን የስኳር ፕሮጀክት ምንም ጉዳት የለውም የሚለውን መግለጫውን እስካሁን ለማቅረብ አልደፈረም። የ “ተነሱ” የጹሁፍ መልዕክት ከደረሳቸው አባላቱ አንዳንዶቹ ይሁን ሁሉ ቅስቀሳ አድርገው የእኛን ልብ ወደ ሌላ አቅጣጫ ከገፉ በኋላ አሁን ችግር የለውም ቢሉ በቀላሉ አንላቀቃትም። የእነርሱ የፖለቲካ ፍላጎት ማርኪያ ሆነን መቀጠልም አንችልም ሲሉ ተደምጠዋል።
በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ምጥን ዘገባ" ከሀይማኖት ወዲያ ምን አለ፣ ለሀይማኖት መሞት ጽድቅ ነው።" የገዳሙ አባቶች፣ የዋልድባ ጉዳይ በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ዘገባ (ክፍል ሁለት)የስብሰባ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ መጋቢት ቀን ፳፻፬ ..የዋልድባ ገዳም አበምኔት ቤት በፌዴራል ፖሊስ ፍተሻ ተካሄደበት‹‹ስለ ዋልድባ ለመሰዋት ተዘጋጅተናል›› የገዳሙ መነኮሳት VOA ‹‹ራሳችንን ለሰይፍ አዘጋጅተን የተቀመጥን ሰዎች ነን›› የዋልድባ መነኮሳት እና በሌሎችም ርዕሶች ከፍተኛ ቅስቀሳ ያደረገው ማቅ ለምን በህጋዊ ድረ ገጹና ባለው ጋዜጣና መጽሔት እንደ ጋዜጠኛ የቤተክህነቱ አጣሪ ኮሚቴ የደረሰበትን ውጤት ለማስተላለፍ ሳይፈቅድ ቀረ የሚለው ጥያቄ መልስ የማህበሩን ጭፍን ፖለቲካዊ አቋም የሚያረጋግጥ ነው።
በቅርቡ እንኳ ቤተክርስቲያኒቱ የራስዋን አጣሪ ኮሚቴ ልካ የደረሰችበትን ውጤት ማሳወቅዋ እየታወቀ በአንድ አድርገን ብሎግ “የዋልድባ ገዳም ጉዳይ እንደ አጀንዳ አለመያዙ እያነጋገረ ይገኛል” በሚል ርዕስ ባወጣው ጹሁፍ ቅዱስ ሲኖዶስን ክፉኛ ወርፏል። በጽሁፉ ውስጥ “… በተጨማሪም እስከ አሁን ዝም ያሉት አባቶች አቋማቸውን ያንጸባርቃሉ ተብሎም ይጠበቃል ፤ ይህን ጉዳይ በዋና አጀንዳነት ይዘው መነጋገር ካልቻሉ የእነርሱም ሰልፍ ከወዴት እንደሆነ ይታወቃል ፤ ይህ ደግሞ ምዕመኑ ከእዚህ በፊት  በቋፍ ላይ የነበረውን ለአባቶች ያለውን እይታ እስከ ወዲያኛው ገደል ሊከት ይችላል ፡፡ ብሎ  እኛ ያልነውን ካላላችሁ እንደ አርዮስ የተወገዛችሁ ናችሁ የሚል አንድምታ ያለው ሰለፊነቱን የሚያስመሰክር የፍረጃ ዘገባ አውጥቷል። 
የማቅ ብሎጎች እየተቀባበሉ ከፍተኛና ግልጽ በሆነ ሁኔታ የ “ተነሳና ተፋለም” ቅስቀሳ እያደረጉ ባለበት በዚህ ወቅት አስተዋይ ልቦና ያለው ሰው ሁሉ በማቅ ፕሮፓጋንዳ እንደ መናጆ ከመነዳት ነገሩ እውነት ይሆንን? ብሎ በማስተዋል እንዲመላለስ የዝግጅት ክፍላችን በአጽንኦት ያስረዳል። እኛ ባለን መረጃ መሰረት ፕሮጀክቱ ቀጥታ ዋልድባን እንደማይነካና ከሚታይ ግልጽ ችግር ይልቅ ገዳሙ የተያያዥ ችግሮች ሰለባ ሊሆን እንደሚችል ያደረግነው ጥናት ያመለክታል። ተያያዥ ችግሩም ቢሆን ሊከሰት የሚችልበትን እድል አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ መቀነስ እንደሚቻል እናምናለን። በእውነት ቤተክርስቲያናችን የምትጎዳበት ትልቅ ችግር ቢኖር ኖሮ የማቅን ሃሳብ በመደገፍ እንቆም እንደነበር እንገልጻለን።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ደጀ ሰላም ጉዳዩን በሚመለከት በጻፈው ጽሁፍ እንዲህ ሲል የተጻፈበትን ደብዳቤ ይዘት አጣጥሏል። “በእውነት በአገሩ ሕግ የለም ማለት ነው? በየትኛው አገር ነው አንድ ጋዜጠኛም ሆነ የሚዲያ ተቋም ስለዘገበው ሳይሆን ስላልዘገበው ነገር የሚጠየቀው? ስለጻፈው ሳይሆን ሳይጽፍ ስለቀረው የሚፈረድበት? ይህ በዓይነቱ በየትም ዓለም ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቀው ክስ መጨረሻው ምን እንደሚሆን ለማወቅ በጣም ያጓጓል። ደብዳቤውየጋዜጠኝነት ሥነ ምግባርን ማጉደልያለውን ይህንን ላልጻፉት ጽሑፍ የመወንጀልን ጉዳይ በዓለም የጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ በብቸኝነቱ ሊያስመዘግብ የሚችለውን ጉዳይና ውጤቱን ወደፊት የምናየው ይሆናል።” እኛም ደጀ ሰላምን በየትኛው ሃገር ሕግ ነው የማኅበር አቋም ጋዜጠኝነት ላይ የሚንጸባረቀው? በየትኛው ሃገር ሕግ ነው ጋዜጠኛ የሚፈልገው ነገር ሲነገር ብቻ የሚዘግበው? በየትኛው ሀገር ህግ ነው ሚዲያን ለተንኮልና ሸፍጥ ተግባር የሚውለው? ብለን እንጠይቀዋለን። መግለጫው ላይ የተገኛችሁት እኮ እናንተ የምታምኑትበትን ልትዘግቡ ሳይሆን የቤተክህነትን አቋም ልትነግሩን ነው? ይሔ የእናንተ አቋም እስካልሆነ ድረስ ምን ያስፈራችኋል? ነገሩ ምን ያለበት ምን አይችልም ሆኖ ነው እንጂ በጉዳዩ ላይ የቤተክህነትን አቋም መግለጽ ምን አስፈርቷችሁ ነው ለመዘገብ ያልፈለጋችሁት? ሕዝቡ የቤተክርስቲያንን ድምጽ ከሰማ የአሰባችሁትን የአመጽ መንገድ አይሳካም ብላችሁ አይደለምን? ስለዚህ በጉዳዩ ላይ መልስ መስጠት አለባችሁ።
 ማቅ ጉዳዩን በትክክል ሳያጣራ ዳንኤል ክብረት እንደነገረን ወሬንና መረጃን ለይተው የማያውቁ የመረጃ ክፍል ሰራተኞቹ “ተባለን” “ሆነ” ብለው ቸኩለው ስላስወሩ ካፈርኩ አይመልሰኝ በሚል ስልት ተቃውሞውንና የ “ተነሱ” ቅስቀሳውን አጠናክሮ በመቀጠል ላይ ይገኛል። በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ገንዘብ ላይ ዘሎ ፊጥ የሚለው ማቅ በውጭ አገር በሚኖሩ አባላቱ አማካኝነት ዋልድባን እናድን የሚል የገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገድ የቀየሰ ሲሆን፣ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ዋልድባን ለማዳን የገንዘብ መዋጮ ያስፈልጋል ወይ? ብሎ መጠየቁ አግባብ ነው። ይህ ጉዳይ ስህተት ነው ብሎ የሚያምን ክርስቲያን ከመንግስት ጋር በስነ ስርዓት ተነጋግሮ ፕሮጀክቱ የሚቀየርበትን መንገድ ከመቀየስ የተሻለ አማራጭ እንደሌለው ገልጽ ሲሆን ለዚህም ደግሞ የገንዘብ መዋጮ እንደማያስፈልገው የታወቀ ነው። አንዳንድ ወገኖች ማቅ ዋልድባን እናድን በሚል ሰበብ ገንዘብ እያሰባሰበ ያለው ምናልባትም በሰበሰበው ገንዘብ ዋልድባን ለማዳን ሲል መሳሪያ ለመግዛት አስቦ ነው በማለት እየተሳለቁ ይገኛሉ። ለነገሩ እንተዋወቅ የለ! መሳሪያውስ ቢኖር ልቡ ከየት ይመጣል? በተንኮል በመሰሪነትና ጉቦ በመስጠት ውጊያ እንደሁ የለ!!

6 comments:

 1. Mahibere Kidusann Yetseyekew Yebete Kihinetu Yehizib Gigunet New Neger gin yetesedebew Mr Enkobahiriy new Yehizib Gingunet Halafiw Manachew ? Mr Enkobahirin -Aba Sereken _D Begashawn Ato Eyalu Mezegeb Degimo Mekom Alebet Kinet Mestsetna Mawgez yepapasna yesinodos Dirsha New Deje Selam -Ahat Tewahedo- Andi Adirgen yetebalut bilogoch Dr Kesis Mesifin Papas siyawegzew Ayihonim Papasu Mawgez aichilum yilunal enersu degimo Kahinun -Menekusewn Diyakonun Ato eyalu Yitseralu ebakachihu siltsane Kihinet yemiyazew Beman ende Hone giletsulin

  ReplyDelete
 2. ማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ በግልጽ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ በስውር ከፍተኛ የሆነና አልቃይዳ ተኮር ስልት ህዝብን በመንግስት ላይ ለማነሳሳት የሚያደርገው ቅስቀሳን ሽባ እንደሚያደርግበት ስለተረዳ በቤተ ክህነቱ የተሰጠውን መግለጫ የጋዜጠኛ ስነ ምግባርን በጣሰ መልኩ በህጋዊ የዜና ማሳረጫ መንገዶቹ ላለመዘገብ ወስኗል።
  ሰለፌ ማለት አልቃይዳ ተኮር ነው ወይስ ይኸኛው ደግሞ ለየት ያለ መለዮ ይሆን
  ክርስትናን ከእስልምና ጋር ምን አቆራኘውና አልቃይዳ ተኰር ተባለ
  ማለቱን በሉ ነገር ግን ለአንባቢውም እዘኑለት

  ReplyDelete
 3. በየትኛው ሃገር ሕግ ነው የማኅበር አቋም ጋዜጠኝነት ላይ የሚንጸባረቀው? በየትኛው ሃገር ሕግ ነው ጋዜጠኛ የሚፈልገው ነገር ሲነገር ብቻ የሚዘግበው? በየትኛው ሀገር ህግ ነው ሚዲያን ለተንኮልና ሸፍጥ ተግባር የሚውለው?

  ReplyDelete
 4. SELAM LENANETE YIHUN ABASELAMAWOCH ERE MIN YISHALENAL MK EKO BEDEBIK MEWAGATUN TITO BETAGEL MINALEBET 1 SEW ENE LEBETEKERSETEYAN NEW YEKOMEKUT KALE RASUN SEMAET MADERG ALEBET TEDEBEKO SEMAET YELEM yigermal BEMINOREBET AKEBABI BE GERMEN FRANKFURT Q MAREYAM BETEKERESETEYAN egna kaletekotaterenew mekidesun, MEdrekun, senbet temhert betun BEMALET YAZUGN LEKEKUGN SIL ASETEDADARIEW ENDEZHI YEWAZA AYEDELUM YE GERMEN HEZBEM MEMENUM SELAWEKEBACHEW LIKEBELUACHEW BALEMECHALACHEW 1-10 yemihonu netsuhan miemenanen bemasadem wengel tekelekeln bemalet asetdadariw lemasadem felgew neber gin tenkara mimen selal keshefebachew Ahunema Tenketobachewal MANIM AYESEMACHEWEM BEGENZEB GEZETEW YAMETUT KIHENET GUD AFELA TENEKIRU ABASELAMAWOCH EGNAM KE GONACHEW NEN BERTUU YENESU SERA TAWEKUAL BEMENGESETEM DEREJA

  ReplyDelete
 5. ሪፖርቱ በጣም ያስቃል፡፡ ማቆች ትክክለኛ ገልባጮችና አደናጋሪዎች መሆናቸውን ያጋልጣል፡፡ ግን ለመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን የመንግሥት ፕሮጀክቶችን የሚተችና ሚገመግም ለመሆኑ በሕገ ደንቡ ተቀምጧል ወይ፡፡

  መ/ር ዕንቆባሕርይ በጣም ዘዴኛና አስደናቁ ሰው መሆኑ መታየት ጀመረ፡፡ ማቆችን በራሳቸው ጥርስ ራሳቸውን እጅ እንዲነክሱ አደረገ፡፡ ማቅ ሁለት የመረጃ እጅ አለው አንዱ የዋናው ማዕከል ሲሆን በጎ የማይሠራ የታጠፈ ትሑት መሳይ፣ የሚለምን፣ ገንዘብ የሚሰበስብ፣ የሚሰርቅ፣ መረጃ የሚሰበስብ ስርክርክ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ደጀ ሰላም፣ አደባባይ፣ አሐቲ ተዋሕዶ … ምናምን የሚባሉ ብዙ ጣቶች ያሉት የሚራገም፣ ሚሳደብ፣ አድማ የሚቀሰቅስ፣ የሚዋሽ፣ የሚበጠብጥ፣ የፖለቲካና የሽብር የመረጃ እጅ ነው፡፡ መ/ር ዕንቆሕርይ ጀግና፣ ጀግና፣ ጀግና፣ በርታ በርታ፣ በርታ ገና ትመሰገናለህ ግን በጣም ጠንቃቃ ሁን፣ የማቅን እጆች ርስ በርሳቸው አስተሣሰርካቸው፣ በአንዱ እጁ ሌላውን እጁን እንዲያሥር አደረግከው፡፡ ወንድ እናት ወልዳለች፡፡

  ReplyDelete
 6. ሪፖርቱ በጣም ያስቃል፡፡ ማቆች ትክክለኛ ገልባጮችና አደናጋሪዎች መሆናቸውን ያጋልጣል፡፡ ግን ለመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን የመንግሥት ፕሮጀክቶችን የሚተችና ሚገመግም ለመሆኑ በሕገ ደንቡ ተቀምጧል ወይ፡፡

  መ/ር ዕንቆባሕርይ በጣም ዘዴኛና አስደናቁ ሰው መሆኑ መታየት ጀመረ፡፡ ማቆችን በራሳቸው ጥርስ ራሳቸውን እጅ እንዲነክሱ አደረገ፡፡ ማቅ ሁለት የመረጃ እጅ አለው አንዱ የዋናው ማዕከል ሲሆን በጎ የማይሠራ የታጠፈ ትሑት መሳይ፣ የሚለምን፣ ገንዘብ የሚሰበስብ፣ የሚሰርቅ፣ መረጃ የሚሰበስብ ስርክርክ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ደጀ ሰላም፣ አደባባይ፣ አሐቲ ተዋሕዶ … ምናምን የሚባሉ ብዙ ጣቶች ያሉት የሚራገም፣ ሚሳደብ፣ አድማ የሚቀሰቅስ፣ የሚዋሽ፣ የሚበጠብጥ፣ የፖለቲካና የሽብር የመረጃ እጅ ነው፡፡ መ/ር ዕንቆሕርይ ጀግና፣ ጀግና፣ ጀግና፣ በርታ በርታ፣ በርታ ገና ትመሰገናለህ ግን በጣም ጠንቃቃ ሁን፣ የማቅን እጆች ርስ በርሳቸው አስተሣሰርካቸው፣ በአንዱ እጁ ሌላውን እጁን እንዲያሥር አደረግከው፡፡ ወንድ እናት ወልዳለች፡፡

  ReplyDelete