Wednesday, May 16, 2012

የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ለማኅበረ ቅዱሳን የአስር ቀናት የጊዜ ገደብ አስቀመጠ

በአልታዘዝ ባይነቱ የሚታወቀውና ለማደራጃ መምሪያውና ለጠቅላይ ቤተ ክህነት መመሪያና ትእዛዝ ተገዢ ከመሆን ይልቅ «እኔን ማንም አያዘኝም» በሚል አቋሙ ጸንቶ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን «ተዳፍኖ ቀርቶልኛል» ሲል ቸል ያለው የመስከረም 12/2002 ውሳኔ ዳግም ተቀስቅሶ በማኅበሩ ውስጥ ፍርሀትና ሽብር ማንገሱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች እየተናገሩ ነው። አንዳንድ ጳጳሳትን በልዩ ልዩ መንገድ እየደለለና እየሸነገለ እድሜውን ሲያራዝም የቆየው ማኅበረ ቅዱሳን፣ በተለይም በሟቹ አቡነ ይስሀቅ፣ እንዲሁም አሁን ባሉትና «ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል» በሚለው አገር አጥፊ ስልት ቤተክህነቱን በስጋ ዘመዶቻቸውና በወንዛቸው ልጆች ባጥለቀለቁት አቡነ ህዝቅኤል የስራ አስኪያጅነት ዘመን እጅግ ተጠቃሚ የሆነው ማቅ፣ አሁን ግን ጊዜ እንደከዳውና የቁርጥ ቀን እንደደረሰበት መታዘብ ተችሏል።
አንዳንድ የማኅበሩ አመራር አባላትም ልባቸው ከማህበሩ እየሸፈተ መሆኑን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረገጽ ዘግቧል። «ዓሠርቱ ቀናት ለማኅበረ ቅዱሳን» በሚል ርእስ በተጻፈው ደብዳቤ ዙሪያ ዜናውን ይፋ ያደረገው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረገጽ በጉዳዩ ላይ እንዳተተው «በዚህ የ20 ዓመት ጉዞ ውስጥ ማህበሩ በቤተክርስቲያን ስም እያመካኘ  ነገር ግን ለራሱ የሚሠራ ለቤተክርስቲያኒቱ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቱ እያመዘነ መምጣቱን አንዳንድ ለቤተክርስቲያኒቱ የሚቆሙ የማኅበሩ አመራር አባላት ይናገራሉ። ትተው እንዳይወጡ ደሞዝ፣ እንዳይሰሩም ጭንቅ የሆነባቸው ወንድሞች በማኅበረ ቅዱሳን ውሰጥ በርካታ ናቸው።» ብሏል።

አክሎም ለማቅ ወግነው በመቆማቸው «ሳይሾሙ ተሻሩ» ሲል የተቻቸው አባ ህሩይ «አምነውበት ተቀብለው ከፈረሙበት በኋላ ሁለት ቀናትን አሳልፈው በመምጣት ደብዳቤውን ስላላመንኩበት አይወጣም በማለት ከመዝገብ ቤት ክብ ማህተም ነጥቀው ተሰውረው ነበር። በወቅቱ ከማህበረ ቅዱሳን ጸሀፊ ከዲ/ን ሙሉጌታ ሀይለ ማርያም ባገኙት ምክር መልካም ነገር መስሏቸው አደረጉ። የማደራጃ መምሪያው ሠራተኞች ግን በወቅቱ እጅግ ተገርመው ጉዳዩን ይከታተሉ ነበር። ማህተሙ በተነጠቀበት ጊዜ ዲ/ን ሙሉጌታ ሀይለ ማርያም በማደራጃ መምሪያው መኪና ከአባ ህሩይ ጋር ቢሮ ገብቶ ሲያበረታታ ነበር። አባ ህሩይ በዚህ ጊዜ ነው የማህበሩ ቀኝ እጅ መሆናቸው በጥርጥር ውስጥ የገባው።» ብሏል ድረገጹ።

በመጨረሻም ማኅበረ ቅዱሳን አባቶችን በገንዘብ እየደለለ ከጎኑ እንዲቆሙ ማድረጉና አባቶችም በገንዘብ እየተደለሉ ማህበሩን መደገፋቸው፣ አምላክን ሳይሆን ገንዘብን መከተላቸውን እንደሚያሳይ ድረገጹ እንዲህ ሲል ጽፏል። «አባቶች ለማኅበራት ሳይሆን ለቤተክርስታያን ሲቆሙ ቤተክርስቲያንን በደሙ የዋጃት አምላክ አብሯቸው ይቆማል። ነገር ግን ከማህበራት ጋር ሲቆሙ ገንዘብ ብቻ አብሯቸው ይቆማል። ገንዘብ ደግሞ ህይወት አይሆንም»

የማቅ የቁርጥ ቀን አባታት ለመሆን ቆርጠው የነበሩት አባ ኅሩይ ለቀናት ማህተም ይዘው እስከ መሰወር የደረሰ ዋጋ ከፍለው ቢያዘገዩትም፣ ለማቅ እንዲጻፍ የተወሰነው ደብዳቤ በአዲሱ የማደራጃ መምሪያው ሀላፊ በመምህር ዕንቈ ባሕርይ ተከሥተ ፊርማ በቀን 6/9/2004 ወጪ ሆኗል። በደብዳቤው ማቅ በተደጋጋሚ ለጠቅላይ ቤተክህነት መመሪያና ትእዛዝ እንቢተኛ በመሆንና በሌለው ስልጣን ለመጠቀም ባደረጋቸው ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የቤተክርስቲያኒቱን ህልውና ሲፈታተን መቆየቱ ተገልጾአል። ስለሆነም የመስከረም 12/2004 ባለ 6 ነጥብ የስራ አፈጻጸም መመሪያ ተግባራዊ እንዲሆን ማቅ በደብዳቤው ታዟል። ደብዳቤው አመራሮቹን እነዚያን 6ቱን የስራ አፈጻጸም መመሪያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆናቸውም ለደረሰው ችግር ተጠያቂዎች አድርጓቸዋል። በመሆኑም ማቅ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አጣብቂኝ ውስጥ የገባ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ እርሱን እሹሩሩ የሚል አካልም ሆነ ግለሰብ  ይኖራል ተብሎ አይታሰብም። ደብዳቤው ማቅ አክራሪ መሆኑ በተበሠረ ማግስት መጻፉ ደግሞ ጉዳዩ ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ያስረዳል። ማቅ በዚህ በ11ኛው ሰኣት ላይ የተሰጠውን መመሪያ በ10ሩ ቀናት ውስጥ ተግባራዊ ካላደረገ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድበትም ማደራጃ መምሪያው አስጠንቅቆታል።

ለቤተክርስቲያን ህልውና መከበር በደከሙና የማቅን ስውር አጀንዳና በቤተክርስቲያናችን ላይ የጋረጠውን አደጋ በመረጃዎች አስደግፈው በመታገላቸው፣ በህገ ወጡ ማህበረ ቅዱሳን በህገወጥ መነገድ እስከ መከሰስ ደርሰው የነበሩትና በማቅ ቀንደኛ ደጋፊ ጳጳስ አቡነ ህዝቅኤል እንቢተኝነት ከማደራጃ መምሪያው እንዲነሱ የተደረጉት አበ ሠረቀ ብርሃን፣ ድካማቸው ሁሉ መና ሆኖ እንዳልቀረና ፍሬ እያፈራ መሆኑ ከተጻፈው ደብዳቤ መረዳት ይቻላል። እርሳቸው ከማደራጃ መምሪያው ቢነሱም እንኳ፣ ማቅ ሲያወራና ሲያስወራ እንደነበረው በማቅና በማደራጃ መምሪያው መካከል ችግሩ አባ ሠረቀ ሳይሆኑ፣ የራሱ የማኅበሩ ሕገወጥ አካሄድ መሆኑን መደበቅ አልቻለም።

ማህበረ ቅዱሳን በተጻፈው ደብዳቤ መሰረት መመሪያውን ተቀብሎ የታዘዘውን ይፈጽም ይሆን? ወይስ በእልከኛነቱ ይጸናል? የሚለው ብዙዎች የሚጠብቁት ነው። ለማንኛውም አሥሩ ቀናት እየነጎዱ ነው። ማቅ ግን በእንቢታው የሚጸና ይመስላል። ለዚህም ፍንጭ የሚሰጠው ግንቦት 7 ቀን በግልጽ ድረገጹ ፖስት ያደረገውና «በህገወጦችና በጨለማ የተዘጋጀው ደብዳቤ ተበተነ» ሲል ደብዳቤውን የተቃወመ ሲሆን አዲሱን የመምሪያ ሃላፊ ሹመትም ተቃውሟል። አባ ህሩይም ያለጠፋታቸው ተባረሩ ሲል ተከላክሏል። ለወጣበት መመሪያ መልስ ከመስጠት ይልቅም በጉዳዩ ላይ አቀረብኩት ላለው አቤቱታ ከሲኖዶስ ምላሽ እየጠበኩ ነው ሲል ለአስሩ ቀናት ትኩረት እንዳልሰጠ አሳይቷል።

6 comments:

 1. በእውነት በአገሩ ሕግ የለም ማለት ነው? በየትኛው አገር ነው አንድ ጋዜጠኛም ሆነ የሚዲያ ተቋም ስለዘገበው ሳይሆን ስላልዘገበው ነገር የሚጠየቀው? ስለጻፈው ሳይሆን ሳይጽፍ ስለቀረው የሚፈረድበት? ይህ በዓይነቱ በየትም ዓለም ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቀው ክስ መጨረሻው ምን እንደሚሆን ለማወቅ በጣም ያጓጓል። ደብዳቤው “የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባርን ማጉደል” ያለውን ይህንን ላልጻፉት ጽሑፍ የመወንጀልን ጉዳይ በዓለም የጋዜጠኝነት ታሪክ ውስጥ በብቸኝነቱ ሊያስመዘግብ የሚችለውን ጉዳይና ውጤቱን ወደፊት የምናየው ይሆናል።እናንተም እንግዲህ ትንሽነታሽሁን ገለጻችሁ ሃይማኖትማ እንደሌላችሁ ድሮም እናውቃችኋለን ዛሬ ደግሞ ገዳዮችም የዚህ ብሎግና ተባባሪዎቻችሁን ማለቴ ነው ደግሞ የሰላማን ሥም መጠቀማችሁ

  ReplyDelete
 2. Abba Selama Minew Tedebekish ? Min Wesedesh? weyis Yesinodosi Abal Sinebersh Sibseba Gebash ?Negeroch Mezegeb yalebachew ahun Ayidelem wey ?Sinodosu Beyekenu Yewesenewin Teketatilo Masawk neberbsh Leloch Kewashi behala Menageru Min tsikim alew Kedimo yeemidersew wshet kehone Lemaswetsat bizu yadekimal Abba Sereke -D Begashaw- Leke Kahinatt Getachew Doni Min Tebalu ?Man Tewgeze ? Man Terefe ?Kidus Sinodos Ahun Mahibere Kidusann Semitona Amino Sewn Kawgeze Ariyosina Mekidenyos Yetewgezut bekelalu neber malet new Yasblal Kihidet yetegegebet Sew keale yimar -yimeles -yimeker Alimeles kale yiley biye aminalehu Gin Abba Selam Tedebekish Minew ?

  ReplyDelete
 3. ማኅበረ ቅዱሳንን ከሚያስወግዙ ነጥቦች ውስጥ ዐሥሩ

  1. ሃይማኖታዊ፡ አንደኛ፡ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ማኅበር ናት ይህ ዶግማ ነው፡፡ ማንም ማኅበር በማኅበር ላይ አይዋቀርም፡፡ ዓለምም፣ መንግሥትም፣ አምላክም የሚያውቃት እንደ አንድ ማኅበር ነው፡፡ በዚህች ማኅበር ውስጥ ሌላ ማኅበር ሠርቶ፣ ለብቻው መተዳደሪያ ቀርጾ መዋቅር ዘርግቶ እስብካለሁ፣ ካህን እቀጥራለሁ፣ .አባላት እመዘግባለሁ… ካለ ዶግማ አፈረሰ፡፡ ከሐዲ ነው፡፡
  ሁለተኛ፡፡ የማህበሩ የሕትመት ውጤቶች በሙሉ በከፍተኛ የሃይማኖት ሕጸጽ የተሞሉ ናቸው፡፡ የአሁን የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ተመልክተን ወደ ፊት እንደአስፈላጊነቱ፡፡ ከ68 የሕትመት ውጤቶች ውስጥ በ23 ጸሐፊያን የተጻፉ ከፍተኛ የትምህርተ ሃይመኖት ስሕተቶች ለቅዱስ ሲኖዶስ ይቀርባሉ፡፡
  ሦስተኛ፡ አሁንም በሕትመት ውስጥ ለገንዘብ ብለው ማን እንደጻፋቸው በሚገባ ሳይውቁና ሳይጠይቁ ኦርቶዶክሳውን ያልሆኑ የውጭ ሀገር ሰዎች የጻፏቸውን ተርጉመው በማቅረብ እና የሀገር ውስጥ ጸሐፍያን የጻፏቸውን የራስ አስመስሎ በማቅረብ፡፡ ፍቅር የለሽ፣ ገላትያ 5፡22 አድመኛ፣ ቡድነኛ፣ ጠባብ በመሆን ምእመናንን ቢያንስ ማኅበረ ቅዱሳን የሆነና ያልሆነ ብሎ በመከፋፈል፣ አንድ የክርስቶስ አካል የሆነች ቤተ ክረስቲያንን በማወክ፡፡
  2. ቀኖናዊ፣ ከቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውጭ፣ ምእመናን ለካህናተ፣ ካህናት ለጳጳሳት፣ ጳጳሳት ለቅዱስ ሲኖዶስ ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ለመንፈስ ቅዱስ፣ የሆነውን ቀኖናዊ ሥርዓት በመሻር ራሳቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ተጠሪ አድርገዋል፣ ካህናትን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ በመቅጠር፣ ያልተሰጣቸውን የቤተ ክርስያን የስብከተ ወንጌል፣ የገዳማት፣ የትምህርት ቤቶች ሥራ በመሥራት፣ ዐሥራት በኩራት በመሰብሰብ፣ ቅዱስ ሲኖዶስት በማታለል አባላቱ አንድ ፐርሰንት መዋጮ ይክፈሉ ብለው ከሰበካ ጉባኤ መዋጮ በላይ በመሰብሰብ፡፡ (ማለትም፡ የሰበካ ጉባኤ መዋጮ ሁለት ብር ሲሆን፣ ማቆች ግን በፐርሰንት 1000 ብር ደመወዝ ያለው ዐሥር ብር በወር እያዋጣ ለቤተ ክርስቲያን መሰጠት የሚገባው ብር ከምእመናን በማጭበርበር በመውሰድ)፣ ለቤተ ክርስቲያን መከፈል ከፍተኛ ሥጋት መሆን፣ አሁን አንዳንድ የቴዎሎጅ ዕውቀት የሌላቸው ሰዋች የቤ/ክ ታሪክና ቀኖናን ለይተው ባለማወቅ ይናገራሉ ነገሩ ግን ከፉኛ የከበደ መሆኑ አልታያቸውም፡፡ ማቅ የቀረው እኮ በይፋ ጳጳሳቱን ቀጥረቶ ሲኖዶስ ማቋቋም ነው ከዚያ በደጋፊዎቹና ፡፡
  3. አስተዳደራዊ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቱ መዋቀር የገዳማት መምሪያ፣ የትምህርትና ማሰልጠኛ መምሪያ፣ የስብከተ ወንጌል መምሪያ፣ የቅርስና ቱሪዝም መምሪያ፣ የሰበካ ጉባኤ መምሪያ፣ የሊቃውንት ጉባኤ፣ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ፣ የውጭ ግንኙነት መምሪያ፣ የሕግ አገልግሎት መምሪያ፣ የምህንድስና የቴክኒክ አገልግሎት መምሪያ፣ የልማትና ዕቅድ መምሪያ፣ የልማት ኮሚሽን፣ የንዋየ ቅድሳት ምርትና ማከፋፈያ ድርጅት፣ የአልባሳት ማደራጃ፣ የትንሣኤ ማተሚያ ቤት፣ የትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፣ የካህናት መንፈሳዊ አገልግሎት መምሪያ፣ ምነፈሳዊ ፍርድ ቤት የመሳሰሉት ሲሆን በእነዚህ ልክ ራሱን በማደራጀት የቤተ ክህነት እንቅፋት በመሆን፡፡ አስተዳደሩን በማወክ፣ ቤተ ክህነቱን በመሳደብ፣ በማጥላላት፣ በየመመሪያው እየገቡ መምሪያዎችን ማዳከም፣ ለመምሪያዎች የሚወሰነው የሥራ ድርሻ በል ልዩ ስልት እንዳይፈጸም ማድረግ፣ ስም ማጥፋት…
  4. ንግድ፣ ሲቋቋም የተሰጠው መመሪያ ወጣቶች በሰለጠኑበት ሙያ በትርፍ ጊዜያቸው የበጎ አድራጎት ነጻ የሙያ እገዛ ማድረግ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳን በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ንብረትና ገንዘብን በማንቀሳቀስ፣ ከዐራባ በላይ ሱቆች በመክፈት፣ መዎጮ በመሰብሰብ፣ የቅዱሳን አክሲዮን ማኅበርን ለመመስረት በቅቷል፣ አንዳንድ መሪዎችን እና አባላቱም የአክሲዮን ከፍተኛ ባለድርሻ ናቸው፡፡
  5. አለመታዘዝ እና ውሽት፣ ማቅ ለማንኛውም መመሪያን ትእዛዛ ተገዥ አይደለም፡፡ የወጣቶች ማኅበር ነው፡፡ ከቀሲስ ሙሉጌታ፣ ዲ/ን ሙሉጌታ፣ ሁሉም አባላቱ የእድሜ ልክ አባል የሆኑ ናቸው፡፡ ይህ በሕግ የተወሰ ነው፡፡ ማቅ የተወሰኑ ሰዋች የአክሲዎን ርስት የፖለቲካ አንጃ መሆኑ በዚህ ይታወቃል፡፡ እንደሚታወቀው አሁን ሃያ አመቴን አከብራለሁ ሲል መሥራቾቹ ከማኀበሩ ጋር እነሆ ሃያ ዓመታቸው፡፡ እነሱ ሲመሠረቱ የዐሥር ዓመት ልጂ የነበረ አሁን ከሰንበት ት/ቤት እነሆ ወደ ሰበካ ጉባኤ ተዛወረ፡፡ ማቆች ግን አሁንም የንግድና የፖለቲካ፣ የመንደር አንጃ፣ የቡድን ርስታቸውን እንደያዙ ናቸው
  6. አጥፊነት፡ ማቆች በዞሩበት ቦታ ሁሉ ምቅኝነት፣ ቧልት፣ ሐሜት፣ ስም ማጥፋት፣ ንብረት ማጥፋት፣ ሃይማኖት ማጥፋት፣ ሥርዓት ማጥፋት አብሮ አለ፡፡
  7. ሽርተኛነት፡ በገሃድ እንሚታየው አባቶችን በደጋፊ፣ በለዘብተኛ/ዘገምተኛ/ነውረኛ፣ በተቃዋሚ ከፍለው ያሸብራሉ፣ መምህራንንና ሊቃውንትን ተሐድሶ እያሉ፣ የቤተ ክህነት ሠራተኞችን ሴተኛ አዳሪ/ዱርየ/ ጆቢራ እያሉ፣ ያለተሠራ ተሠራ ያልወሰነ ተወሰነ እያሉ ያውካሉ፣ ያሸብራሉ… ምእናንና ሠራተኞችን የግልህ መረጃ አለኝ እያሉ ያስፈራራሉ፣ ያሸብራሉ
  8. ዓለማዊነት/ ሥጋዊነት፣ መንፈሳዊ ፍቅርና ዕውቀት የላቸውም፣ ሁሉም ይወገዝ ባዮች ናቸው፣ ገንዘብ ይወዳሉ፣ በሰው ሥራ ለመወደስ የሰው ሥራ ይወስዳሉ በ18 ዓምት የሕትመት ታሪክ ለመቁጠር የሚያዳግት ጽሑፍ በሕትመቶቻቸው ተዘርፏል በራሳቸው ስም የሰው ሥራ ሰርቀው ለጥፈዋል (በቅርቡ ሁሉም ገሀድ ይወጣል)፣ ታይታ ይወዳሉ፣ ምእመናን ሠሩ ከማለት ማቅ ሠራ ለማስባል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፣ ይህ ዐለማዊነት ነው፡፡
  9. ፖለቲካ፣ ማቅ ውስጥ የነበሩ በርካታ አባላትና አመራሮች ፍጹም ፖለቲከኞች ነበሩ፣ ማኀበሩ በእነዚህ ሰዎች የተቃኘ ከሆነ ከፖለቲካ አይጸዳም፣ ስለዚህ በሃይማኖት ካባ የተሸፈን የፖለቲካ ፓርቲ ነው፡፡ ከንግድ፣ ከመዋጮ፣ ከአሥራት፣ ከልመና ከሚያገኘው ገንዘብ በተጨማሪ ከዐራባ በመቶ በላይ የፖለቲካ ፓርቲዋች የሥልጣን ባለ ባዶ ተስፈኞች ድጎማ ነው፡፡
  10. ቤተ ክርስቲያን አልባ ሃይማኖታዊ ማኅበር፣ መንፈሳዊ አባላትን በአንድ መዝገብ ጥላ አስፋራ መዝግባ ማስተዳደር፣ መምራት፣ ማዘዝ፣ አገልግሎት መስጠት፣ ዐሥራትና ምጽት መሰብሰብ የምትችለው ማኅበር ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት፡፡ ማቅ የራሱ መተዳደሪያ አለው፣ መዋጮ ይሰብስባል፣ የማኅበር ሥርዓት አለው፣ ምዝገባ እና ፎርም አለው፣ ግን ቤተ ክርስቲያን የራሱ የለውም፡፡ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን አልባ ማኀበር ቢባል ልክ እንደ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይሻላል፡

  ReplyDelete
 4. ቅዱስ ሲኖዶስ በሃይማኖትና በቀኖና ጉዳዮች አይሳሳትም፣ በአስተዳደር ጉዳዩች ግን ስሕተቶችን ያርማል፣ መተዳደሪያዎችን ያሻሽላል፡፡

  የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ ያለ አግባብ የጸደቀ አባቶች በየዋሐት በደርግ ዘመን በየዩኒቨርስቲው በፖለቲካና በጥላቻ የተወሰዱ ወጣቶችን ወደ ቤተ ክርስቲያን ለማምጣት ብለው የሠሩት አስተዳደራዊ ውሳኔ ሲሆን አሁን ሊታረምና በሰንበት ትምህርት ቤቶች መተዳደሪያ ሊተካ ይገባዋል፡፡

  1. ቅዱስ ሲኖዶስ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ቃለ ዓዋዲንና ለወጣቶች ሰንበት ትምህርት ቤትና የማኅበራት መተዳደሪያን ደንብን መስጠቱ ሊስተካከል ይገባል፡፡ ወጣቱ በማንኛው ይካተት (ከቤ/ክ ውጭ በማኅበር ወይስ ቤ/ክ ውስጥ በሰንበት ት/ቤት)ስለዚህ ሁሉም ምእመናን በቃለ ዓዋዲ የሚተዳደሩ ሲሆን ወጣቶች በሰንበት ትምህርት ቤት ብቻ ይታቀፋሉ፡፡ መተዳደሪያቸው የአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤት መተዳደሪያ ይሆናል፡፡
  2. የማኅበራት አደረጃጀት በኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ፈጽሞ የለም በሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት ያልተለመደ ሕገ ወጥ አሠራር ነው፡፡
  3. ማቅ የራሱን አባላት ለማበራከት ከቤተ ክርስቲያን አባላት አባላትን ይመርጣል፣ ጉዳዩ ምንድን ነው ሌላ ቤተ ክርስቲያን ለመመሥረት ነው
  4. የማቅ ንብረቶች አዛዥ የላቸውም፣ ሂሳቡ ተቆጣጣሪ የለውም፣
  5. የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ሲመረቱ መሥፈርቱን ቅዱስ ሲኖዶስ አያውቀውም
  6. ቅዱስ ሲኖዶስ ደንቡን አጸደቀ እንጅ የአባልነት ፎርም አላጸደቀም
  7. አባላት በማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ለስንት ጊዜ አባል እንደሚሆን ድንጋጌ የለም
  8. ማኅበረ ቅዱሳን ከሰበካ ጉባኤ፣ ከወረዳ፣ ከሀገረ ስብከት እና ከጠቅላይ ቤ/ክ በላይ ገንዘብ ይሰበስባል
  9. የማኅበረ ቅዱሳን አመራር አባላት ከሰባ በመቶ በላይ ፖለቲከኛዎች ናቸው
  10. ማኅበረ ቅዱሳን ከሙስሊም አሸባሪዎች ጋር ከፍኛ ተመሳሳይነት አለው
  11. ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክህነትና ለሊቃውንት ከፍተኛ ጥላቻ አለበት
  12. ማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ከቃለ ዐዋዲ ይበልጣል
  13. ማኅበረ ቅዱሳን ለበርካታ ሰንበት ትምህረት ወጣቶች መዳከም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው
  14. የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ከቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አደረጃጀት ጋር ከፍተኛ ተቃርኖ አለው
  15. ማኅበረ ቅዱሳን የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን እየመረጠ የራሱ አባል ያደርጋል
  16. ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ (ከያሬዳዊ መዘምራን መሪጌቶች፣ ለሰንበት ትምህርት ቤት) ለመጀመሪያ ጊዜ የመዘምራን ኳየር ያዋቀረ ሕገ ወጥ የፕሮቴስታንት ተምሳሌት
  17. ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ጸሎት ይልቅ ለራሱ የቡድን ጸሎት ቅድሚያ ይሰጣል
  18. የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሳይምሩና ሳይመረመሩ ሹመትን ይቀበላሉ
  19. ማኅበረ ቅዱሳን ሳይፈቀድለት በበጎ ፈቃድ ማገልገል ሲገባው እጅግ ከፍኛ ደመወዝ እየከፈለ ሰዎችን ያሠራል
  20. ማኅበረ ቅዱሳን ሳይፈቀድለት ከሦስተኛ ወገን ጋር ውል ይገባል በቅርቡ የዐራት ሚሊያን ብር የኮንስትራክሽን ውል ገብቷል፣ ጉዳዩን ጠቅላይ ቤጸ ክህነት አያውቀውም
  21. ማኅበረ ቅዱሳን በርካታ ትናንሽ ማኅበራትን አጥፍቷል፣ ጠቅልሏል፣ ሥራቸውን ወርሷል
  22. ማኅበረ ቅዱሳን ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውጭ በርካታ ነጋዴዎችን፣ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ አባላቱ እንዲያደርግ ማን ፈቀደለት (ዕውነተኛ ከሆነ ለምን ከማኅበር ይልቅ ለቤ/ክ አገልጋይ አያደርጋቸውም)
  23. የማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ ባለቤት ማነው
  24. ማኅበረ ቅዱሳን በከፍተኛ ደረጃ የግለሰቦችን መረጃ ይሰበስባል፣ ትውልዳቸውን ያጠናል…. ለምን
  25. የማኅበረ ቅዱሳን የመረጃ መረቦች ግልጽነት የሌላቸው እና የዋናው አንጃ ውክልና ያላቸው የማኅበረ ቅዱሳን የፖለቲካና ዓለማዊ ጥላቻ ማስተላለፊያ ድረ ገጾቹ የማኅበረ ቅዱሳን ትክክለኛ መልክ ሲያሳዩ ይፋዊ ሆነው የእኔ የሚላቸው ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳንን በጭምብል ያሳያሉ
  26. ማኅበረ ቅዱሳን እጅግ ዘርፈ ብዙ በሆነና በጣም በተስፋፋ የንግድና የልመና፣ የፕሮጀክት መረብ ለምን ኖረው
  27. ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ በጀት መድቦ፣ መምህራን ቀጥሮ በሚያቋቁማቸው ገዳማትና፣ አብነት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጨማሪና መጠነኛ ድጎማ እየሰጠ መምህራኑንና ተማሪዎቹን አባላት ወይም ደጋፊ ያደርጋል፡፡ ይህም ማለት በሰው ቤት ውስጥ ለሠራተኛዎ ተጨማሪ ብር ባለ ድርብ ተልዕኮ ማድረግ ነው
  28. ማኅበረ ቅዱሳን በርካታ ማኀበራትን በአርአያው ፈጥሯል ለምሳሌ (ደጆችሽ አይዘጉ፣ የቴዎሎጅ ምሩቃን ማኅበር፣ የአቡነ ሐራ ማኅበር፣ ማኅበረ ሰላም፣ … )
  29. ማኅበረ ቅዱሳን ለብዙ አባላቱ ከፍተኛ የኑሮ ድጎማን በቤ/ክ ስም ሰጥቷ፣ መኪና ገዝተዋል፣ ቤት ሠርተዋል…
  30. ማኅበረ ቅዱሳን ሁለት የመንደር ቡድኖች አሉ የጎንደሮች ቡድን አቡነ መርቆሬዮስን ፓትርያርክ ለማድረግ የሚንቀሳቀስ፣ እና የሸዋ ቡድን የሸዋ ፓትርያርክ ለመሾም የሚንቀሳቀስ ሌላው አጫፋሪ ነው፡፡

  ተጨማሪ ሠላሣ ጉዳዩችን በቀጣይ ይጠብቁ

  ReplyDelete
 5. የቤተክርስቲያናችንና የሐገራችን የካንሰር በሽታ የሆነው እራሱን ማህበረ ቅዱሳን እያለ የሚጠራው የማፊያ፣ የወሮበላ፣ የአሸባሪ፣ የመሰሪ ድርጅት የተሰጠው ደብዳቤ ብጣም አስፈላጊ መሆኑ ፍፁም ጥርጥር የለውም። ሆኖም ግን ቤተክርስቲያናችንን ሐያ አመት ሙሉ የገዘገዛትና ምዕመኑን በእምነትና በቤተክርስቲያን ሥም ሲዘርፍ ለኖረ የሠይጣን ድርጅት በአሁኑ ጊዜ ግን በቃህ ሊባል ይገባው ነበር እንጂ የማስተካከል ደብዳቤ ብቻ መቀበል የለበትም። ማህበሩ ባጠቃላይ ለቤተክርስቲያናችንና ለሐገራችን ፈፅሞ አስፈላጊ አይደለም። ማቅ ካልተዘጋ በቀር በየጊዜው የማፊያ ስትራቴጁን እየቀያየረ የቤተክርስቲያንን ደምና የክርስቲያኖችን ደም ሲመጥ ለመኖር አላማ ስላለው እባካችሁ የቤተክህነትና የሲኖደስ አባቶች ይህንን መሰሪ የሰይጣን ማህበር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከካንሰሩ እንድትታደጉት በህያው እግዚአብሔር ሥም እንለምናችኁለን።

  ReplyDelete
 6. በእግዚአብሔር ፈቃድ የተመሠረተች የቅዱሳን ማኅበር አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንጅ ሌላ የንግድ፣ የመዋጮ፣ የአሸባሪ፣ የአሉባልታ፣ የቡድነኛ፣ አንጃ አይደለም፡፡

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷን፣ ክብሯን፣ ሃይማኖቷ ጠብቃ የቆየችው በል ልዩ ቡድን ተከፋፍላ፣ ከራስዋ ውጭ ለልዩ ልዩ ቡድኖች ዕወቅና ሰጥታ ምእመናኖችዋ ተለያያ የቡድን መተዳደሪያ አጸድቀው አይደለም፡፡ ከጥንት ጀምሮ ሳትከፈል የቆየችው አንድ ማኅበር ሆና ነው እንጅ የተለያ ማኅበር አደራጅታ አይደለም፡፡ የተወሰኑ ማኅበራት ተዋቅረው ቡድን መሥርተው ምን ያህል ችግር እንደፈጠሩ አሁን የሚታየው ልዩነት መሠረታዊ ማስረጃ ነው፡፡ በብቁ መረጃና ያለመሳሳት ግማሹ መናፍቅ፣ ግማሹ ፖለቲከኛ፣ ግማሹ አሸባሪ፣ እሆነ ምእመኑን መከፋፈሉ እየታወቀ አንዱን ለመከልከል ሌላውን ለመፍቀድ መፈለጉ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ትልቅ ጠባሳ ትቶ ማለፍ ነው፡፡

  ምናልባት ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያን ጠቅሟል ብለው የሚያምኑ ጥቂት አባቶች አንዳንድ በሰንበት ትምህርት ቤት ተኮትኩተው ያደጉ ወጣቶች በየሆስፒታሉና በልዩ ልዩ ቦታዎች ሲረዷቸው ተመልክተው ሊሆን ይቻላል፡፡ እነሱ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ወደ ማኀበሩ ወሰዳቸው እንጅ ወጣቶቹ ያደጉት በቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ወደፊትም ጥሩ ከመሆን የሚያግዳቸው የለም፡፡

  ከባለፈው የቀጠለ ሌላ ሠላሳ ምክንያት ማኀበረ ቅዱሳን የሚወገዝበት ለሁሉም መረጃ አላቸው በሄደት ይቀርባል፡፡

  1. የማንኛውም ሰንበት ትምህርት ቤት አመራር ሲመረጥ፣ የደብሩ፣ የሀገረ ስብከቱ… ተወካይ ይገኛል አስመራጭ ኮሚቴም ይዋቀራል የማኅበረ ቅዱሳን አማራሮች ያለመሥፈርት በጡረታቸውም የወጣቶ ማኅበር አባልና አመራር ሆነው ይገኛሉ መራጩም፣ አስመራጩም፣ ተመራጩም ራሱ ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡
  2. የማኅበረ ቅዱሳን አባልነትና የአባልነት የዕድሜ ገደብ፣ የአመራር እድሜ ገደብ የእድሜ ደረጃ ምንም አይከተልም እንደፈለገው አጎራ ዘለል፣ ነው
  3. አገልግሎቱ በበጉ ፈቃድ ሲሆን ልክ እንደ ሰንበት ትምህርት ቤት እነሱ ከፋይና ተከፋይ ናቸው፣ የቀጠሩትን ሰው ዋና የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አያውቅም ለብቻው ቤተ ክርስቲያን አልባ ድርጅት መሆኑ እታወቀ ነው
  4. የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን ያለፈቃድና ያለ ምርመራ እያሳተመ አትርፎ በመሸጥ
  5. ያልተሰጣቸውን ውክልና አለን በማለት ሳይወከሉ ወይም መወከል ሳያስፈልጋቸው መሪዎችን በማታለል ደብዳቤ እያጻፉ በልዩ ልዩ የመንግሥት4 መሥሪያ ቤቶች የስለላ ሥራ መሥራት፣ ሳይወከሉ ራሳቸውን በመወከል የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ማደናገር
  6. ቤተ ክርስቲያን የማታቀው በርካታ ሲምፖዚሞችን፣ ዐውደ ጥናቶችን ወርክሾፖችን ስብሰባዎችን በቤተ ክርስቲያን ስም ማካሄድ
  7. በቤተ ክርስቲያን ስም ፖለቲካዊ መልእክቶቸን ማሰራጨት
  8. ራሳቸው ሳይላኩ፣ አገልጋይ መዳቢ በመሆን በልዩ ልዩ ቦታዎች አገልጋዮችን ልከናል በሚል ያልተፈቀደላቸውን መሥራ
  9. በገዳማት ስም ተወክለናል በማለት በልዩ ልዩ ዓለማት እየተዘዋወሩ መንደላቀቅ፣ ገንዘብ መሰብሰብ፣ መነገድ ራብ ማስተዋወቅ
  10. በአብነት ትምህርት ቤቶችም እንዲሁ
  11. የሃይማኖት ትምህርት ስሕተት ብቻ ሳይሆን ለቁጥር የሚያዳግት የታሪክ ስሕተት በሕተመቶቻቸው ማሰራጨት
  12. ኢክርስቲያናዊ በሆነ መንገድና ደረጃውን ባልተበቀ መንገድ ሰዎች ይወገዙልን በማለት የቕዱስ ሲኖዶስን ሥራ ጊዜ መሻማት እንደ ክርስቲያን መጀመሪያ መምከር፣ በጥንቃቄ በፍቅር ማቅረብ፣ ከዚያ አልመከር አልመለስ ሲል ማውገዝ
  13. በራሱም ሆነ በቤተ ክርስቲያን ስም ሳይገባው፣ ማደራጃ መምሪያውን ሳይስፈቅድ መግለጫዎችን መስጠት
  14. ወጣቶችን ከቤተ ክርስቲያን ውጭ መሰብሰብ፣ ከቤተ ክርስቲያን አባልነታቸው በተጨማሪ የማኅበር አባል ማድረግ
  15. ማደምና ማሳደም
  16. አባቶችን መዝለፍ፣ መሳደብ፣ ማስፈራራት፣ መረበሽ፣ መደለል፣ ማሳሳት፣ ሊቃውንት መዝለፍ ካህናትን ማሳጣት
  17. ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ምስጢር ማጋለጥ
  18. የምእመናን ገንዘብ ያለ ዋጋ ያለ ዕሴት፣ በሕንጻ፣ በእርዳታ ስበብ መሰብሰብ፣ ቤተ ክርስቲያን ሳታውቅ
  19. ጥላቻንና ጠብና መንዛት
  20. ያልተማሩ አስተማሪዎችን ማባዛት
  21. የሰዋችን ጥፋት እንደ እኩይ ፍልስጣ መከታተል መክሰስ፣ ሳይገባ መፍረድ
  22. በሙያቸው አገልግሉ የታባሉት ሁሉ ባለ አክሲዮች በመሆን መዝባሪወችና ቤተቨክርስያን የትርፍ ጥገት ላም ማድረግ
  23. የሰው ገመና ማጋለጥ
  24. የተደራጀ የውንብድና እና ሙስና ሥራ መሥራት
  25. የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ትርፍ ጊዜ ሥራ ማድረግ
  26. ከቡድኑ ዓላማና ግብ ውጭ መረጃ ማሰባሰብ ለምን
  27. በየቦታው መመሪያ ሰጭ በመሆን ከእነሱ ጋር ጥሩ ግንኙነት ሌላቸው አገልጋዮች ሥራን ማሰናከል
  28. ከፍተኛ ንብረት ያለ ሕግና አዛዥ ማሰባሰብ
  29. ቅዱስ ፓትርያርኩን መዝለፍ፣ የቤተ ክርስቲያንን መንበር መዳፈር
  30. የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ለመናድ መሞከር

  ይቀጥላል

  ReplyDelete