Tuesday, May 15, 2012

ዜና ቤተክርስቲያን በ«ቀሲስ» ዶ/ር መስፍን ላይ «የጤና ዶ/ሩ ከክህነታቸው ተሻሩ» በሚል ርእስ ዘገባ አወጣ

Read in PDF
·        «ዶ/ሩ የማኅበረ ቅዱሳን ቀንደኛ አባል፣ … በሥራ  ድክመትና ዛሬ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጃቸውን ግለሰቦች በድርጅቱ ውስጥ በመሰግሰጋቸው ተነቅቶባቸው የተባረሩ ናቸው» ብሏል
·        ማኅበረ ቅዱሳንን በሰይጣን መስሎታል
የዘገባው ሙሉ ቃል ከነትንታኔው ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል
«ዶ/ር መስፍን ተገኝ የተባሉት የማኅበረ ቅዱሳን ቀንደኛ አባል ያለ ሀገረ ስብከቱ ሊቀ  ጳጳስ ፈቃድ በሰሜን አሜሪካ ባሉ ስቴቶች በመዘዋወር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ባደረጉት ኢ-ቀኖናዊ እንቅስቃሴና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ባልጠበቀ ሁኔታ አባቶችን እርስ በርስ የሚያጣላና የሚከፋፍል፤ በማለት የታገዱበትንና ከዚህ ቀደም ድረገጻችን አውጥቶት የነበረውን ደብዳቤ አትሞታል።«ዶ/ር መስፍን ተገኝ ቀደም ሲል በኃላፊነት ይሠሩበት ከነበረው ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ በሥራ  ድክመትና ዛሬ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጃቸውን ግለሰቦች በድርጅቱ ውስጥ በመሰግሰጋቸው ተነቅቶባቸው የተባረሩ ናቸው፡፡
ምእመናንንም ለአድማ የሚያነሳሳ ትምህርት የሰጡ መሆናቸው በማስረጃ ስለተረጋገጠባቸው እንዲመከሩና በንስሐ እንዲመለሱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሰሜን አሜሪካና የካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢያደርጉላቸው ጥሪውን በመናቃቸው በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 6 በቁጥር 224 ሦስተኛ ረስጠብ በ22ኛው ድንጋጌ መሠረት ሊቀ ጳጳሱ ሥልጣነ ክህነታቸውን ሽረውታል፤ ከክህነታዊ አገልግሎትም አግደዋቸዋል፡፡»
«ዶ/ር መስፍን ከተጠቀሰው መሥሪያ ቤት ከተባበሩ በኋላም ለለጋሽ ድርጅቶች የተሳሳተ ኢንፎርሜሽን በመስጠት በብፁዕ ወቅድስ ፓትርያርኩ ጥረት ቤተ ክርስቲያናችን በሥራ ውጤት ከአሜሪካ መንግሥት ሽልማት ያገኘችበት የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ እንዲዘጋ በማስደረግ ሕሙማኑንም ሆነ የቢሮው ሠራተኞችን የበደሉ ከመሆናቸውም በላይ በሙያቸው የጀመሩት ሥራ አልሳካ ሲላቸው ‹‹ላም ካልዋለበት ኩበት ለቀማ›› እንዲሉ ፈተና የሌለበት መስሎአቸው የበለጠ ፈተና ወደአለበት ወደዚህ መንፈሳዊ ተግባር አምርተው በጅምራቸው ለዚህ ዓይነቱ መንፈሳዊ አደጋ የተጋለጡ ግለሰብ ናቸው፡፡» ብሏል።
በዶ/ሩ ላይ የተወሰደውን ክህነትን የመሻር ተገቢ እርምጃ ከግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ቀደም ብሎ ከሳምንታት በፊት በተደረገ የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን፣ በጊዜውም ሆነ ከዚያ ቀደም ብሎ ዶ/ሩ ቅሬታውን አላቀረበም። ይሁን እንጂ ዜና ቤተክርስቲያን ሁኔታውን መዘገቧን ተከትሎ ቅሬታውን እንዳሰማ የማቅ ድረገጾች ጽፈዋል። በዚህም ግለሰቡም ሆነ ማኅበሩ ከመጀመሪያው ጀምሮ ጉዳዩን ከድረገጾቻቸው ባለፈ አለመቃወማቸውና ተቀብለውት ከሰነበቱ በኋላ አሁን ለአቅጣጫ ማስለወጫነት ለመጠቀም እንደ ፈለጉ አንዳንድ ተንታኞች እየተናገሩ ነው። ይሁን እንጂ በዜና ቤተክርስቲያን አማካይነት የነፈሰውን ሀይለኛ ነፋስ መቋቋም የተሳናቸው አንዳንድ ጳጳሳት እንኳን ሌላ ጉዳይ መጥቶ አቅጣጫ ሊለውጡ ከቆሙበት መንቀሳቀስ ተስኗቸው ተስለውሏል።  
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ፣ አቡነ አብርሃም አሜሪካ ተልከው ሳለ ባልተላኩበት ተልእኮ ተጠምደው የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪ በመሆን አፍራሽ ስራ ሲሰሩ መቆየታቸውንና ይኸው በመረጋገጡ አቡነ ፋኑአል በምትካቸው መላካቸውን የሚገልጽ ዜና ያስነበበ ሲሆን፣ ከአዋሳ ጀምሮ አላሰራ ያላቸውንና እስከ አሜሪካ ተከታትሎ የተፈታተናቸውን በሰይጣን የመሰላቸውንና «የቤተክርስቲያናችን ፈታኞች» ሲል የጠራቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎችን ድል መንሳታቸውን እንዲህ ሲል አብራርቷል። «በእውነቱ ብፁእ አቡነ ፋኑኤል እንደሌሎቹ ያልተላኩበትን ስራ ሳይሰሩ ወይም እንደ አንዳንዶቹ የቁራ መልእክተኛ ሆነው ሳይቀሩ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የሚገኙትን የቤተክርስታናችን ፈታኞችን በትእግስትና በቆራጥነት ተቋቁመው «ካልጾማችሁና ካልጸለያችሁ ዘመዳችሁ ሰይጣን ከእናንተ ዘንድ ለቅቆ አይወጣም» የተባለውን አምላካዊ ቃል በተግባር በመተርጎም ከአዋሳ ጀምሮ ተከትሏቸው የሄደውን ሰይጣን በጾም በጸሎት ድል ነስተው በባዕድ አገር ለቤተክርስቲያናችን አንድ የታሪክ እመርታ በማሳየታቸው ምስጋና ሊቸራቸውና የሞራል ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል።»
በዚህ የተበሳጩ የመሰሉትና ከዚህ ቀደም፣ የ60 ዓመቱ ሽማግሌ በ10 አመቱ ሕጻን ተዘለፈ» በሚለው ጽሁፋቸው የማኅበረ ቅዱሳንን እኩይ ተግባር በተባ ብእራቸው በመተቸታቸው ከፍተኛ ዘለፋና ስድብ ያደረሱባቸውን፣ ባለፈው ለዘመን መለወጫ የተሀድሶ እንቅስቃሴን በቅኔ አጋለጡልን በሚል ደግሞ ሲያሞካሿቸው የነበሩትን መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒን፣ አሁን ፊታቸውን አዙረውና ጀርባቸውን ሰጥተው መኮነንና መውገዝ መጀመራቸውን ከድረገጾቻቸው መረዳት ተችሏል። በዚህ ጽሁፍ ማኅበሩን በትክክለኛ ዘገባዎቻቸው ያጠቁትን የጋዜጣውን አዘጋጆች፣ በተለይም ዋና አዘጋጁን ደጀሰላም የተባለው የማኅበሩ ድረገጽ ከፍተኛ ቅስቀሳ እያካሄደባቸው ይገኛል።
በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ አጀጋጆቹ ቀርበው ሳይጠየቁና ሳይመልሱ፣ ጥፋተኛ ሳይባሉም ማኅበሩ እንደለመደው በተጠናወተው በባዶ ሜዳ የማውገዝ አባዜው፣ ሲኖዶሱ ስለሚወደው እርምጃ ተወያይቶ የእርምጃ አማራጮችን አስቀምጧል ሲል መዘገቡ፣ የደጀሰላም አንባቢዎች ምን አይነት ይሆኑ? እንዴት? ለምን? ወዘተ ብለው የማይጠይቁና የተሰጣቸውን ብቻ የሚቀበሉ በድረገጹ አነጋገር «ዘገምተኞች» እና «ደመነፍሶች» ናቸው ወይ? አሰኝቷል። «ስለ ውሳኔው ምንነት በተደረገ ውይይትአስተዳደራዊ ይኹን” “የለም፣ በቀኖናዊ ቅጣት እንለፈውየሚሉ አማራጮች መነሣታቸው የተገለጸ ሲኾን በአመዛኙ የተያዘው ስምምነት ወደ አስተዳደራዊ ውሳኔ ያጋደለ መኾኑ ተጠቁሟል፡፡ አስተዳደራዊ ርምጃ ይወሰድ የሚለው አማራጭ ከታየ 1950ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ከጋዜጣው ሪፖርተርነት እስከ ዋና አዘጋጅነት ያገለገሉት መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ከሓላፊነታቸው የመሰናበት ዕጣ ፈንታ እንደሚገጥማቸው ተመልክቷል፤እስኪ እርሱም ይብቃውይላሉ ስለ ውሳኔው ከወዲሁ ሐሳብ የሚሰጡ የጉዳዩ ተከታታዮች፡፡» ሲል ማኅበሩ በዋና አዘጋጁ ላይ ከፍተኛ ዘመቻ መክፈቱን አውጇል።
አክሎም «ከጋዜጣው መውጣት በኋላ ዜና ቤተ ክርስቲያን ስም ብቻ ይዞ ቢቀር በሚል ባለ ዘጠኝ ገጽ ጽሑፍ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ቅጽር እየተሠራጨባቸው የሚገኙት ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ 1967 . አንሥቶ በያዙት የዋና አዘጋጅነት ሓላፊነት የጋዜጣውን ዓላማ በመለወጥ የግል ሰዎች ስም ማወዳሻ፤ የስድብና የሐሜት መናኸርያ፤ የባለሥልጣናት ማጥመጃና መደለያ” የሚል ክስ እየቀረበባቸው ይገኛል፡፡» በማለት ዋና አዘጋጁን ማጥቃት መጀመሩን ጠቁሟል። ምንም መፈየድ ያልቻሉና በድረገጾቹ ላይ ከመነበብ ውጪ በጠቅላይ ነቤተክህነት አካባቢ ፈጽሞ ያልታዩ ጽሁፎችን እየጻፈ «ተበተነ» ማለትን ስራዬ ብሎ የያዘው ማቅ፣ በግንቦቱ ሲኖዶስ ራሱ እየበተነና በሌሎች እየላከከ «ተበተኑ» ያላቸው ጽሑፎች ሁለት መድረሳቸው ታውቋል። ከስም ማጥፋት የዘለለ ተጨባጭ ውጤት ግን እንዳልተገኘ እየታየ ነው።

6 comments:

 1. shame on you... for fact i was there when dr. Mesfin was apponinted to be the

  ReplyDelete
  Replies
  1. to be what? Get out of that man? Read this tip:
   መልሱ አዎ ነው። የተንኮልን ጉድጓድ አትቆፍር፣ ከቆፈርክም አታርቀው፣ የሚገባበትን አታውቀውም እና።
   አቶ መስፍን ያልተሰጠውን ስልጣነ ለምድ ለብሶ በእግዚአብሔር እያላገጠ ሲቆፍር በደከመበት ጉድጓድ እራሱን ገፍትሮ ከተተው። አንተ ግን ከእንደዚህ አይነቱ እራቅ።

   Delete
 2. እናት ትውለድ የሚያሰኝ ሥራ በዚህ ዓመት ተሠራ(በሬ በጅራፍ ሰው በጽሑፍ ካልተገረፈ/ካልተወረፈ/ፈር ተላለፈ) እንደሚባለው መን/መሪዎቹ ራሳቸውን አንድ ሳይሉ
  እደ ማቅ ያሉትን እየፈለፈሉ ቤተ ክርስቲያንን ስላጎሳቆሉ ሲያንሳቸው ነው መጎነታተሉ
  ዜና ቤ.ክርስቲያን አዘጋጁም በዚህ ዓመት ይህን ጽሑፍ ማውጣት ንስሓ ገብቶ እንደመሞት
  ይቆጠርለታል(ትንሽ ምስጋናም ይገበዋል ትንሽ እውነት ስላወጣ)

  ReplyDelete
 3. Yemiserutin ayawkumina amlakoy yikir belachew... libona yistachihu... (mico libuna)

  ReplyDelete
  Replies
  1. ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው፣
   አቶ መስፍንን መሆኑ ነው፣
   እውነት ነው፣
   ጉድጓዱን ሲቆፍር ያራቀው እርሱ እራሱ ነው፣
   ግን ትርጉሙ ብዙ ነው፣
   ሲመክሩት ካልሰማ እራሱ ይዝለቀው፣
   መሀላ ካለብህ አንተም ተከተለው፣
   ድሮም የመከርንህ እሄንን አውቀን ነው፣
   መቼም እርም አትልም ልብህ ደንዳና ነው፣
   ሽማግሌን ንቀህ ሰድበህ ያባረርከው፣
   ጊዜው እንኳን አልራቀም ምነው እረሳኸው፣
   የማቴዎስ ወንጌልን በሙሉ አንብበው።

   Delete
 4. l hulum Egiziabher selamun yabizalen

  ReplyDelete