Wednesday, May 9, 2012

የዘንድሮው የግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ማኅበረ ቅዱሳን አንገት በደፋበት፣ ደጋፊው የነበሩት ጳጳሳት በተሻማቀቁበት ሁኔታ እንደሚካሄድ ይጠበቃል

ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የማኅበረ ቅዱሳን አንዱ ስራ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደውን የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በውጥረት ውስጥ እንዲካሄድ ማድረግ ነው። ለወትሮው ከሲኖዶስ ስብሰባ ቀደም ብሎ ማኅበረ ቅዱሳን በሚከፍላቸውና በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ጫና ለማሳደር በሚል በሚከፈቱት የግል ጋዜጦችና መጽሔቶች ብዙ ብዙ እያጻፈና እርሱ እንዲቀርብለት የሚፈልገውን አጀንዳ የቤተክርስቲያን አጀንዳ አስመስሎ በማስተጋባት፣ የሲኖዶሱን ስብሰባ አቅጣጫ ለማስለወጥና አባቶች እንዳይስማሙ፣ ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ውሳኔ እንዳይወስኑ በመከፋፈልና በገንዘብ በመደለል ሁሉ ቤተክርስቲያንን ሲያውክ ለመኖሩ ያለፈው የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ጥሩ ማሳያ ነው። በግንቦቱ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ግን ጋዜጦችና መጽሔቶች ይህን ዜና እንዳትዘግቡ የተባሉ ይመስል ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ዝምታን የመረጡ ይመስላል።ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የማኅበሩን ማንነት “አክራሪ” በሚል ከገለጹት ወዲህ በማኅበሩ ውስጥ ፍርሀት ነግሷል ነው የሚባለው። ሚያዝያ 30 ለንባብ የበቃው መፍቀሬ ማህበረ ቅዱሳን የሆነው “ፍኖተ ነጻነት” የተባለው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍተሕ ፓርቲ (አንድነት) ልሳን “የፖለቲካው ውጥረት ሩብ ጉዳይ።” በሚል ርእስ ስር ባቀረበው ጽሁፍ ውስጥ እንዲህ የሚል ሀሳብ ሰፍሯል። አንዳንድ የኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታዮችም የሃይማኖት መሪዎቻቸውን እንደ መንግሥት ‹‹ካድሬ›› ይቆጥሯቸዋል፡፡ ስሙን እንዳልጠቅስ ያስጠነቀቀኝ አንድ መምህር ግን የማህበረ ቅዱሳን ራሱን ነጻ አድርጎ ለመጓዝ ያደረገው ጥረት ለምእመናኑ መጽናኛ ሆኗቸዋል፡፡ ሰሞኑን አቶ መለሰ ለፓርላማ ባቀረቡት ንግግር ማህበረ ቅዱሳንን ከሙስሊም ጽፈኞች መሳ ለመሳ መፈረጃቸው ተዳፍኖ የቆየውን ተቃውሞ እንዲያገረሽ ምክንያት ሆኗል፡፡ ሆኖም ማህበሩን ወክለው ስሜታቸውን የሚያጋሩኝ ኃላፊዎችን ለማግኘት አልቻልኩም፡፡ መረጃ የሰጡኝ አካላትም ስማቸውንና ኃላፊነታቸውን ደብቀውኛል፡፡ የሚገርመው ሁሉም የጠቆሙኝ አደባባይ በተባለ የጡመራ መድረክ ላይ ኤፍሬም እሸቱ ያሰፈረውን ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ አባባል አልስማማም›› የሚለውን ጽሑፍ ነው፡፡ ‹‹የማህበሩን አቋም በድረገጻችን ላይ አስፍረናል፤ ተጨማሪ ነገር ለመናገር አልፈልግም›› ያሉኝ አንድ የማህበሩ ኃላፊ በደምሳሳው የአቶ መለሰ አስተያያት ስህተት ላይ የተመሠረተ መሆኑን በምክንያት አስደግፈው አስረድተውኛል፡፡ በኃላፊው ማብራሪያ መሠረት ማህበሩ የጥምቀት በአል አከባበርን በበላይነት አስተባብሮ አያውቅም፡፡ ስለዚህም በበአሉ ላይ የሚስተጋቡ መፈክሮች ይዘት ስህተት አይደለም፡፡ ቃሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡›› ካሉ በኋላ አክራሪነቱ ግን እንደማይመለከታቸውና ክርስትናም እንደማይፈቅደው አብራርተዋል፡፡ በኦርቶዶክሳውያኑ የሚነሳውን ጥያቄ ካባባሱት ክስተቶች መሀከል በዋልድባ ገዳም ላይ ተጀመረ የሚባለው ልማት በመነኮሳቱ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም በሃይማኖቱ ተከታዮች እና በመንግስት መሀከል የፈጠረው ውጥረት ሌላው የተቃውሞው አካል ነው፡፡ (ገጽ 14) ሲል ማቅ የሚገኝበትን ተጨባጭ ሁኔታ አስነብቦናል። የማኅበሩ ሰዎች የጠቆሙትን የኤፍሬም እሸቴን ጽሁፍና የማኅበሩን አቋም ድረገጻችን ሰፊ ምላሽ የሰጠበት መሆኑ ይታወሳል።

በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ያለው ማኅበሩ በራሱ ጉዳይ ስለተጠመደና ቀድሞ አብረውት የተሰለፉ አንዳንድ ጳጳሳት በመንግስት በኩል የተያዘውን አቋም በመፍራት ወደኋላ ሳያፈገፍጉ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው። ይህ ማለት ግን ማቅ የተለመደ የተንኮል ስራውን አይሰራም ማለት እንደልሆነ ከወዲሁ ግልጽ ሊሆን ይገባል።

ግንቦት 2/2004 ይጀመራል ተብሎ ከሚጠበቀው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በፊት ቅዱስ ፓትርያርኩ በጥቅምቱ ሲኖዶስ ወቅት በነፍስ ወከፍ ከማኅበሩ 2 መቶ ሺህ ብር ተቀብለዋል ተብለው የሚታሙ አንዳንድ ጳጳሳትን ለምሳሌ አቡነ ሉቃስንና አቡነ ዲዮስቆሮስን በግል እንዳነጋገሯቸው አንዳንድ ምንጮች ይናገራሉ። በጉዳዩ ላይ ምን እንደተነጋገሩና ጳጳሳቱ “አዎን ተቀብለናል” ብለው ይመኑ፣ ወይም “አልተቀበልንም” ብለው ይካዱ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቡነ ዲዮስቆሮስ ከአንዲት ሴት የወለዱት ልጃቸው አባቴን እያለ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እየተናገሩ ነው። ከሰሞኑ በዚህ ጉዳይ ላይ በፎቶ የተደገፈ ሀተታ ለማቅረብ እንሞክራለን።

ጳጳሳቱ እንዲህ ባለ የራሳቸው ጉድ ተይዘው ሳለ፣ የማቅን ጉዳይም መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየተመለከተው ባለበት ሁኔታ ጳጳሳቱ እጃቸውን በማቅ ጉዳይ ላይ ያስገባሉ ተብሎ አይጠበቅም። ይልቁንም መንግስት አክራሪ ሲል በፈረጀው በማኅበረ ቅዱሳን ላይ አንዳች መፍትሔ መስጠት አለባቸው የሚል እምነት አለ። እኛ የአሸባሪ ያህል የምንመለከተውን ማቅን መንግስት ለዘብ አድርጎ አክራሪ ማለቱ፣ ቤተክርስቲያን በውስጧ አክራሪዎችን ይዛለች ስለሚያሰኛት ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያንን ስም ለማደስ በማቅ ላይ የማያዳግም አቋም መያዝ እንዳለበት ለማንም ግልጽ ነው። በእርግጥም ቀደም ሲል ብፁዕ አቡነ ገሪማ ለተሰናባቹ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማዳረጃ መምሪያ ሃላፊ ለአባ ኅሩይ የጻፉትና በ5 ቀናት ውስጥ ከዚህ ቀደም በማቅ ላይ እነ አቶ አባይ ጸሀዬ በተገኙበት የመስከረም 12/2002 ዓ.ም ውሳኔዎች በ5 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆኑ ማዘዛቸውና መነኩሴውም፣ አልፈርምም በማለት ትእዛዙ እንዳይፈጸም ማዘግየታቸው በቤተ ክህነት በኩል የማቅ ጉዳይ ትኩረት እንደተሰጠው ያሳያል የሚሉ ተንታኞች አሉ። ለማቅ እንጂ ለቤተክህነት አልታዘዝ ባዩ የመምሪያ ሃላፊም ከቦታው እንዲነሱና የመምሪያው ምክትል ሃላፊ ቦታውን እንዲይዙ መደረጉ በማቅ ላይ ጀንበር እየጠለቀች ነው የሚያሰኝ ሆኗል። በቀጣዩ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የሚሆነውን ነገር እየተከታተልን ለመዘገብ እንሞክራለን።     
    
  


3 comments:

  1. aba hiruye come back U.S.A THERE IS A LOT OF DOLLARS OVER HERE .

    ReplyDelete
  2. SELAM LE ENANETE YIHUN WEGENOCHE BE EWENET BETAM ASEDESETACHEHUGNN BERTU AND NEGER LAKAFELACHEHU BE GERMEN FRANKFURT MAREYAM BETEKERESETEYAN BETAM ME EMENUN BEMATEMED MAHEBERE SEYETANOCH BOTAWEN BE KUTETERACHEW LEYADERGU HASEBEW QUAMETEW NEBER MIN YADEREGAL TADEYAA DERO ETHIOPIAM EAYLU YAWEKUACHEW SELENEBER TENKOLACHEWEN ASETDADARIEW ABA SIRAK NIKINK ALADERG SILUACHEW MK TEDEBEKO NETSU YEHONEWEN TEKIT MEMEN EYASADEME SEREWEN JEMERE KETELOM ASTEDADARIWEN LEGERMEN POLIC ASALEFEW ASETU ALHONELACHEWEM KISUM FERESE KESASHUM HAGER TELO USA TEFA AHUN TESFA SIKORTU SIDEB JEMERU MIGEREMEW DEGEMO BE MK CHEFEN YALU 1-10 MEMENAN YINEDALU EGNA KALSEBEKIN; KALZEMERN BEMALET ENSUN YEBELETE SIGEGN TEADESO; YEBTEKERESTEYAN TELAT; BEAWEDEMIHERT SEW MESADEB MIN AYENET BELGENA NEW KEHAHUN BEHUALA BE FRANKFURT MAREYAM EHEL WEHACHU ABEKETUAL MITEHEDUBET HEDU MIGEREMEW DEGIMO SEW TENSIHU SAYECHEL QES MEHON YECHELAL WEY?? minem yemayawek chew Ato Shabel Aberham Ebakhe nesha gibana kisenawen mels ato wendesen anetem wetader yenberk dikunawen meles dn henok anetem ti ebit ena memenanen masadem akum enanete fetoch ribka, misirak, tigest, genet arfachehu tekemetu ye tewahedo lijochen ataweku bemiketelew tshufe ye mk gud asnbebachehualhu lezare yibeka beretu abaselamawoch

    ReplyDelete