Monday, May 7, 2012

እያረፈበት ያለው ትችት እያደከመው ያለው ማኅበረ ቅዱሳን እባካችሁን ተውኝ ሲል ተማጸነ

ተማጽኖው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በማኅበሩ ላይ ለተናገሩት የተሰጠ መልስ ነው ተብሏል
የዘራውን በማጨድ ሥራ የተጠመደው ማኅበረ ቅዱሳን በስሙ በሚጠራው ድረገጹ ላይ “ማሩ አይምረር፤ ወተቱ አይጥቆር” በሚል ርእስ እባካችሁን ተውኝ የሚል አይነት ተማጽኖ አቀረበ። ድረገጹ ሚያዝያ 24/2004 ዓ.ም በሰቀለው በዚህ ጽሑፍ ላይ እንደወትሮው ሁሉ የተለመደውንና እንደሞኝ ዘፈን በየቆመበት ሁሉ የሚደጋገመውን አንድ አይነት ፈሪሳዊ ጽድቁን በማስተንተንና ራሱን እንከን የለሽ አድርጎ በማቅረብ ሐተታውን የጀመረው ድረገጹ፣ አክራሪ የሚል ስም የተሰጠኝ ለቤተክርስቲያን የድርሻዬን ስለተወጣሁ ነው ሲል ተከራካሪ ባጣበት በዚህ ሰአት ለራሱ ጠበቃ ሆኗል።ማኅበሩ ምንም እንኳን ማኅበሩን በራሳቸው ፈቃደኝነት የተሰባሰቡ ኦርቶዶክሳውያን ቢመሠርቱትም የማኅበሩ መሠረታዊ ዓላማ ግን ቤተ ክርስቲያን ተልእኮዋን ለማሳካት በምታከናውናቸው ተግባራት የልጅነት ድርሻውን” መወጣት ነው ብሎ በወረቀት ላይ የሰፈረ ደንቡን ቢያነበንብም፣ በተግባር እያደረገ ያለው ግን ከዚያ በተቃራኒው መሆኑን ከማኅበሩ ፍላጎትና አላማ፣ እንዲሁም ፍላጎቱንና አላማውን ለማሳካት ከሚያደርገው ግልጽና ስውር አካሄድ መገንዘብ ይቻላል። ማኅበሩ እንዳለው መሰረታዊ አላማው ቤተክርስቲያን ተልእኮዋን እንድታሳካ የድርሻውን መወጣት ነው ወይስ በቤተክርስቲያን ስም የራሱን ዝናና ክብር እየካበ ራሱን ከፍ ማድረግ? የሚለውን ከአባላቱና አመራሮቹ፣ እንዲሁም ከጭፍን ደጋፊዎች ይልቅ ትክክለኛ ማንነቱን በማስረጃ በተደገፈ ሁኔታ እየገለጡ ያሉት ወገኖች ቢናገሩ ይሻላል። መጽሐፍም “ሌላ ያመስግንህ እንጂ አፍህ አይደለም ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይደለም።” ይላል (ምሳ. 27፡2)።
 
በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ማኅበሩ ከሚታየው እውነታ ውጪ ለማደናገር የሞከረበት አንዱ ጉዳይ ስለገቢ ምንጩ የተናገረው ነው። በእርግጥ አንዱ የገቢ ምንጩ ከአባላቱ የሚሰበስበው መዋጮ ነው። እርሱ መዋጮ ይበል እንጂ ለቤተክርስቲያን ሊሰጡ የሚገባቸውን አስራታቸውን ጭምር ለማኅበሩ ገቢ እንዲያደርጉ እንደሚደረግ የታወቀ ነው። ይህም ማኅበሩ ለራሱ እንጂ ለቤተክርስቲያን ተልእኮ መሳካት የቆመ ነው አያሰኘውም። ከአስራት ሌላ ከልዩ ልዩ የንግድ ተቋማቱ የሚሰበስበው መጠኑ እንዲታወቅ የማይፈልገው ብዙ ገቢም አለው። በአገር ውስጥና በውጭ አገር ከሚገኙ ድርጅቶችና ግለሰቦች ጭምር “ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት ቅዱሳት መካናትና አብነት ት/ቤቶችን በዘላቂነት በልማት ራሳቸውን ለማስቻል” በሚሉ አማላይ ሰበቦች ፕሮፖዛል እየቀረጸ የሚሰበስበው ገቢም የትየለሌ ነው። ይህና ሌሎችም አገር ያወቃቸው የገቢ ምንጮቹን ደብቆ እርሱ ግን በአባላት መዋጮ ነው እየተንቀሳቀስሁ ያለው ይላል። መቼም የንግድ ተቋማትን የከፈተው ነግዶ ለማትረፍና የገንዘብ አቅሙን ለመገንባት እንጂ ለጽድቅ ብሎ አይደለም። ታዲያ ምነው እነዚህን የገቢ ምንጮች በዝምታ አለፋቸው? ነው ወይስ አልታወቀብኝም ለማለት ነው?

ሌላው የተገለጸው አስቂኙ ሐሳብ “ስብከተ ወንጌል ባልተስፋፋባቸው አካባቢዎች ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት ቅዱሳት መካናትና አብነት ት/ቤቶችን በዘላቂነት በልማት ራሳቸውን ለማስቻል የሚሠሩ ኘሮጀክቶችን በጎ አድራጊ የቤተ ክርስቲያኗ ልጆች ከሆኑ ምእመናንና ማኅበራት ጋር በጋራ በመተባበር ይተገብራል፡፡ የሚለው ነው። ማኅበሩ መቼ ነው ከሌሎች የቤተክርስቲያን ልጆችና ማኅበራት ጋር ተባብሮ ሲሰራ የታየው? ባለፉት 20 ዓመታት ሁሉንም ለመጨፍለቅና በእርሱ ስር ለማስገባት አሊያ የትኛውም ግለሰብም ሆነ ማኅበር ጎልቶ እንዳይወጣ ልዩ ልዩ ስም እየሰጠ ሲታገላቸው ነው የኖረው። ከበርካታ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር ያለበት ትልቁ ችግርም፣ እኔ ልምራችሁ፣ በእኔ ስር ግቡ አሊያ ጥፉ የሚለው ራስ ወዳድ ጠባዩ ነው።

የቤተክርስቲያን ልጆች የሆኑትንና በስብከተ ወንጌልና በዝማሬ አገልግሎቶቻቸው የብዙ ኦርቶዶክሳውያንን ትኩረት መሳብ የቻሉትን እነ በጋሻውን፣ ትዝታውንና ከእነርሱ ጋር ያሉትን ሌሎች ወንድሞችና እህቶችን በሐሰት “ተሐድሶ ሆነዋል” የሚል ዘመቻ ከፍቶ ቤተክርስቲያንን ሲያውክ የከረመው ከሌሎች ጋር ተባብሮ በጋራ የመስራት ልምድም ማንነትም ስለሌለው ነው። እርሱ የቤተክርስቲያን ልጆችና ማህበራት የሚላቸው ለእርሱ እሺ ባይ ሆነው ያላቸውን ሁሉ ለመፈጸም ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡትን፣ በገንዘቡ እየገዛ ያሻውን የሚያስፈጽማቸውን ጀሌዎቹን ነው። ከእርሱ የተለየ አቋም ይዘው የመጡ የቤተክርስቲያን ልጆችን ግን እኔን ተቃወሙ፣ ከእኔ የተለየ አቋም ያዙ ሳይሆን የሚለው፣ “ተሐድሶ-መናፍቃን ሆኑ” ነው የሚለው። ስለዚህ ተባብሮ የመስራት ትልቅ ችግር ያለበት ማኅበር ነው ማቅ።

ድረገጹ ያነሳው ሌላ ነጥብ ማኅበሩ “በየጊዜው የሚገጥሙት ችግሮችና ፈተናዎች የተለያየ መልክ ያላቸው ቢሆኑም የፈተናዎቹ ምንጮች ግን ሁለት ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ማኅበሩ የቆመለትን ዓላማና የሚያከናውናቸውን በጎ ተግባራት በዓላማ ከመቃወም የሚመነጭ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት ወይም ቀርቦ ባለማየት ከሚፈጠር የተዛባ አመለካከት የሚመነጭ ነው፡፡” የሚል ነው።

የፈተናዎቼ ምንጮች ካላቸው የመጀመሪያውና “የመጀመሪያው ማኅበሩ የቆመለትን ዓላማና የሚያከናውናቸውን በጎ ተግባራት በዓላማ ከመቃወም የሚመነጭ” ያለው ያነጣጠረው፣ ተሐድሶ የሚል ስም ባወጣላቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ መሆኑ ግልጽ ነው። መቼም ማኅበሩ የሚያከናውናቸውን በጎ ተግባራት የተቃወመም ሆነ የሚቃወም አካል አለ ማለት ያስቸግራል። በማኅበሩ ላይ የተለያዩ ተቃውሞዎች የተነሡትና እየተነሱ ያሉት ለቤተክርስቲያን አሳቢና እውነተኛ አገልጋይ በመምሰል በስውር የሚሰራው ግን የራሱን ህልውና፣ ጥቅምና ስውር አላማ ለማስከበር መሆኑን በተጨባጭ ስለደረሱበት ነው። ይህን ማህበሩ የቆመለትን ግላዊና ድብቅ አላማ መቃወምና ለምእመናን ማሳወቅ በጎ ተግባራቱን እንደመቃወም ተደርጎ መወሰድ የለበትም።

በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጠውና “በተሳሳተ መረጃ ምክንያት ወይም ቀርቦ ባለማየት ከሚፈጠር የተዛባ አመለካከት የሚመነጭ ነው፡፡” የሚለው ደግሞ ተሀድሶ የተባሉት ክፍሎች ለመንግስት በሰጡት የተሳሳተ መረጃ መነሻነት መንግስት አክራሪ ሲል ሰየመን ወደሚለው ድምዳሜ የሚወስድ ምክንያት ነው። ቀጥሎ ያለውን ከተመለከትን ነገሩ ግልጽ ይሆናል። “ከዚህ አንጻር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የማኅበሩን አገልግሎት እየገጠሙት ካሉት ችግሮች አንዱ በዘመናችን መላው ዓለምን እያወከው ያለው የአክራሪነት አደጋ በአገራችንም ያለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለማሳየት በሚደረጉ ገለጻዎችና የውይይት መድረኮች ግልጽ ባልሆነና በማይወክለው መንገድ የማኅበሩን ስም በመጥቀስ በበጎ አስተዋጽኦው ላይ ጥላ የሚያጠላ ስሜት ይህ የተዛባ ሥዕል በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተለያየ መጠንና በተለያየ መንገድ ሲገለጽ መቆየቱና አሁንም እየተገለጸ መሆኑ በአባላቱም ሆነ በሌሎች ምእመናን ዘንድ መደነጋገርን መፍጠሩ አልቀረም፡፡ ምክንያቱም አባላቱም ሆኑ ሌሎች ምእመናን ከከተማ እስከ ገጠር የሚያውቁት የማኅበረ ቅዱሳን ማንነትና ምንነት አሁን እየተባለ ካለው ጋር ፍፁም የማይገናኝ በመሆኑ ነው፡፡” ሲል ያማርራል። ማቅ ስለራሱ ያለው አመለካከትና በተጨባጭ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ሌላው እርሱን የሚገልጽበት መንገድ ተቃራኒ መሆኑ የሚጠበቅ ነው። ለማቅ የተሰጠው የአክራሪነት ስያሜ ግን ትክክለኛ ማንነቱ እንጂ የተዛባ ሥዕል አይደለም። ከዚህ ቀደም ለማለት እንደሞከርነው በተለይ በሰሜኑ የአገራችን ክፍሎች በመንግስት ሥልጣን ውስጥ ያሉ አባላቱን በመጠቀም በርካታ ሕገወጥ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ይናገራሉ። ለምሳሌ በ”ተሐድሶነት” የጠረጠራቸውን የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን የማቅ አባላት የሆኑ ፖሊሶችን፣ የቀበሌ አመራሮችን፣ በመጠቀም ያለፍርድ ቤት ፈቃድ ድንገት ቤታቸውን መፈተሽና መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች ጽሑፎችን ካገኙ “ይኸው መረጃ ተገኝቷል” በሚል ከቤተክርስቲያን እንዲባረሩ ያደርጋሉ። ባሕርዳር ላይ የአንድ ቄስ ቤት፣ ደብረማርቆስ ላይም የአንድ መሪጌታ ቤት ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በእነዚሁ የማቅ አባላትና ደጋፊዎች መፈተሹንና መጽሐፍ ቅዱስና ተሀድሶአዊ ጽሁፎች በመገኘታቸው ቄሱ መናፍቅ ተብሎ በመከራ ውስጥ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያሳያል። ከመሪጌታው ቤት ግን የተገኘ ነገር ባለመኖሩ ለጊዜው ምንም ማድረግ አልተቻለም። ሰብአዊ መብታቸው የተጣሰባቸው ቄሱና መሪጌታው “ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ቤታችሁ ሲፈተሽ ለምን ዝም አላችሁ? የታለ የፍርድ ቤት ትእዛዝ ብላችሁ ለምን አልጠየቃችሁም?” ተብለው ሲጠየቁ፣ ይህን ሕገወጥ ተግባር የሚፈጽሙት ብዙዎቹ የማቅ አባላትና ደጋፊዎች ስለሆኑ እኛ ዘንድ ይህን መጠየቅ የማይታሰብ ነው ብለዋል። ማቅ ለዚህ እኩይ ተግባሩ ቅዱስ ስም ሊሰጠው ቢሞክርም፣ ይህ ፍጹም አክራሪነት ነው። ከእኔ አመለካከትና አስተሳሰብ በቀር ማንም ሊኖር አይገባም ማለት እኮ አክራሪነት ነው። ማቅ ከላይ የተጠቀሱትን የውንብድና ተግባራት እየፈጸመ ያለው ከእኔ በቀር ማንንም አልይ በሚለው አክራሪ አስተሳሰቡና ማንነቱ ነው።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ ማቅ ግን “አንድ ሰው ዛሬ በምድር ላይ ሲኖር የሕይወቴ መርሕ አድርጌ የምጓዝበት ከሞት በኋላም ዘላለማዊ ሕይወት የምወርስበት እምነት /ሃይማኖት/ ትክክል ነው ብሎ ማመኑ በምንም መስፈርት አክራሪነት ሊባል አይችልም፤ ምክንያቱም የእኔ ትክክል ነው ማለት የሌላው ትክክል አይደለም ወይም የእኔ ብቻ መኖር አለበት የሌላው መኖር የለበትም ማለት ሊሆን አይችልምና፡፡” ሲል ልብ አድክምና ጉንጭ አልፋ መከራከሪያ ያነሳል። እንዳለው እንዲህ ያለው አመለካከት አክራሪ አያሰኝም። ማቅም እንዲህ ስላለ አይደለም አክራሪ የተባለው። እንዲህ ቢሆንማ ኖሮ ማቅ ጥሩ ማኅበር ይሆን ነበር። እርሱ ግን የእኔ ትክክል ነው በማለት ብቻ ሳይወሰን፣ የሌሎችን አመለካከት በጭራሽ አያከብርም። ሌሎች ሁሉ ተሳስተዋል የሚል ግብዝነትም ያጠቃዋል። ስለዚህ አመለካከቱን ያልደገፉትንና በተሻለ ሃይማኖታዊ አመለካከታቸው የተቃወሙትን የቤተክርስቲያን ልጆች መብት በመጣስና የሀይል እርምጃ በመውሰድ የሚጓዝበት ኢመንፈሳዊ መንገድ አክራሪነት ነው። መንግስት ማቅን አክራሪ ካለበት ሁኔታ ይበልጥ የቤተክርስቲያን ልጆች በማኅበሩ እያረፈባቸው ያለው መከራና ስደት የአክራሪነቱ መገለጫ መሆኑን ጠንቅቀው ያውቃሉ።   

“ማኅበረ ቅዱሳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትክክል ናት ብሎ ያምናል፤ እንዴት ትክክል እንደሆነች በንግግርም በግብርም ይገልጣል፤ ይህ ትክክል የሆነው ሁለንተናዊ ማንነቷ ተጠብቆ እንዲኖርም የድርሻውን ይወጣል፡፡ ይህ አስተሳሰብ በምንም መንገድ ሌላውን የማጥፋት መንፈስን ያዘለ አክራሪነት ተብሎ ሊተረጎም አይችልም፡፡” ብሏል። ማቅ እንዲህ ማሰብ መብቱ ነው። ሌሎች የቤተክርስቲያን ልጆች ደግሞ ቤተክርስቲያናችን ትክክለኛ ገጽ ቢኖራትም ሊስተካከሉ የሚገባቸው በርካት ችግሮችም አሉባት ብለው ያምናሉ። ይህ በአንድ ቤት ውስጥ የተፈጠረ የሁለት ልጆች አመለካከት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፤ ይገባልም። እንዲህ ተቃራኒ ሐሳቦች በሚያጋጥሙበት ጊዜ፣ እኔ ያልኩት ብቻ ነው ልክ ከማለት ይልቅ በጉዳዩ እስኪ እንወያይበት ብሎ በመወያየት ትክክለኛነትን ማሳየትና የተሳሳተውን መመለስ ተገቢ ነው። ማቅ ግን እንዲህ እንዲህ ያለውን ጥያቄ እንደጦር ነው የሚፈራው። እንዲህ የሚያደርግ ማንነትም ልብም የለውም። ከዚያ ይልቅ እኔ ከማስበው ሌላ የሚያስብ ሰው በቤተክርስቲያናችን ካለ መወገድ አለበት ባይ ነው። ታዲያ ይህስ አክራሪነት አይደለምን?

ለነገሩ ቤተክርስቲያን ልክ ነች አይደለችም ለማለት ማቅ ማነው? እርሱ ቤተክርስቲያንን የት ያውቃታል? የትምህርቷንና የስርአቷን ትክክለኛነትና ስሕተት ለመመዘን የሚያስችልስ ምን ሃይማኖታዊ እውቀት አለው? ያው ሲባል የሰማውን ከነአሰስ ገሰሱ አግበስብሶ ደርሶ ያገሳብናል እንጂ። የማህበሩ ፍሬዎች የሆኑትን እነዳንኤል ክብረትን አየናቸው እኮ? እነርሱ ገድልና ወንጌልን በተመሳሳይ ደረጃ አስቀምጠው ቤተክርስቲያንን የሚሸነግሉ ጥራዝ ነጠቆች ናቸው እኮ? በእነርሱ ፍትሻ ነው እንግዲህ ከዚህ ድምዳሜ ላይ የተደረሰው?

ማኅበረ ቅዱሳን እኔ ፍጹም እንጂ ጉድለት አለብኝ ብሎ አስቦ አያውቅም። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ እንኳን ፍጹም እንደሆነና ስሙ በአክራሪነት የተነሳው በተሳሳተ መንገድ መሆኑን እንጂ ከእርሱ ጉድለት ተገኝቶ አለመሆኑን በድፍረት ነው የተናገረው። በዚህም እየተቀበለ ያለው መከራና ስደት ከዘራው ያጨደው የስራው ውጤት መሆኑን ለመቀበል ከብዶታል። ይሁንና በመዝጊያው ላይ እየተናነቀውም ቢሆን እንደህ አለ። “በመጨረሻም ማኅበረ ቅዱሳን ጉድለት ካለበትም ስለ ጉድለቱ በምድራዊም ሆነ በሰማያዊ ሕግጋት ሊጠየቅ የሚችል ሕጋዊ መንፈሳዊ ተቋም እንጂ ምንም የተሠወረ ነገር እንደሌለ አምነን አባላቱም ሆነ ምእመናን ዛሬም እንደ ትላንቱ አገልግሎታችንን አጠናክረን እንድንቀጥል አደራ በማለት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ማኅበሩን በማይገልጸው ማንነት እየሣልን ያለን አካላት ደግሞ ማሩን ባለማምረር ወተቱን ባለማጥቆር የማኅበሩን አገራዊ አስተዋጽኦ እናበረታታ ዘንድ ማኅበራችን መልእክቱን ያስተላልፋል፡፡”

በዚህ ተማጽኖ ውስጥ በአንድ በኩል አባላቱ እንዳይከዱት እየተማጸነ ነው። ምንም የተሰወረ ነገር እንደሌለ አምነን ስራችንን እንቀጥል ይላቸዋል። ከዚህ በፊት ዳንኤል ክብረት ስለስውር አመራሩ ሲናገር ማኅበሩ የተገለጸ ብቻ ሳይሆን የተሰወረ ስራም እንዳለው እግረመንገዱን ጠቁሟል። ይህም በሌሎች በበርካታ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ሀቅ ነው። እስካሁን እንኳን በድረገጻችንና በሌሎችም ድረገጾች ላይ ማህበሩን በተመለከተ እየወጡ ያሉ ዘገባዎች ይህን ያሳያሉ። አባላቱም እንደድሮው አብረውት ከመቆም ይልቅ ሸርተት ማለት የጀመሩ ይመስላል። ከዚህ ቀደም እርሱ ተናግሮ የማይሰሩት የሌላቸው አባላቱ፣ ለሚያዝያ 27 አዘጋጅቶት የነበረውንና ቢዝነሱን ሊሰራበት ያቀደውን የእግር ጉዞ “ከ40 ሺህ ባላይ ናቸው” የሚላቸው አባላቱን ጨምሮ ተመዝጋቢ ባለማግኘቱ ለመሰረዝ ተገዷል። ገንዘቡ ቢቀርብኝም “ጠላት ደስ እንዳይለው” በሚል እንኳን አባላቶቼን አሰልፌም ቢሆን 20ኛ አመቴን ማክበር አለብኝ አላለም። ቢልም አይሳካለት ይሆናል። ከገንዘብ የሚበልጥበት ስለሌለ ግን ለጉዞው የተለያየ ሰበባሰበብ በመደርደር፣ ጉዞውን ለግንቦት 26 አራዝሜዋለሁ ሲል ማስታወቂያውን መሰረዝ መደለዝ ግድ ሆኖበታል። ምክንያቱ ግን ከላይ የተገለጸው ነው። በተጨማሪም ከቢሮዬ ተነስቼ መዳረሻዬ አድርገዋለሁ ያለው አዲሱ ገበያ አካባቢ ካለው የሚካኤል ቤተክርስቲያን አዎንታዊ ምላሽ እንዳላገኘ አንዳንድ ምንጮች ይናገራሉ።

ይሁን እንጂ አጭበርባሪው ማኅበር ወዲያው ታጥፎ 20ኛ ኣመቱን በመጻሕፍት ምረቃ አከብራለሁ ብሎ
ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ጋር ተቀላቅሎ መጻህፍቱን አራት ኪሎ ማለዳ ካፌ አካባቢ በጣለው ድንኳን አልሸጥ ያሉትን መጻሕፍት ተመጣጣኝ ባልሆነ ዋጋ ለሽያጭ አስጥቷል። ይመረቃሉ የተባሉት መጻሕፍት ግን አዲሶች ሳይሆኑ ብዙዎቹ የከረሙና በሱቁ ውስጥ አልሸጥ ያሉት ናቸው። ለዚህም ነው እንደጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ገበያ ፍለጋ ከተለመዱት ሱቆቹ ወጥቶ አደባባይ ላይ በድንኳን ለመሸጥ የተገደደው።

ከዋጋ አንጻር ካየነም ከፍተኛ ትርፍ ለማጋበስ ቆርጦ እንደተነሳ አንዳንዶቹ ዋጋዎች ምስክር ናቸው። ለመጥቀስ ያህል፥ በቤተክህነት ሱቅ 180 ብር የሚሸጠውን የግእዝና አማርኛ ሀዲስ ኪዳን ነጋዴው ማቅ በ200 ብር ለሽያጭ አቅርቧል። በ8/9 (?) ብር ሲሸጥ የኖረውን የአቡነ መልከጼዴቅን “ትምህርተ ክርስትና 2ኛ መጽሀፍ” በ15 ብር፣ በ15 ብር እየተሸጡ ያሉትን የአቡነ ጎርጎርዮስን መጻሕፍት በ25 ብር እየሸጠ ነው። በዚህ አጋጣሚ እርሱ ከጥቃቅንና አነስተኛ ያለፈ “ዲታ” ማኅበር ስለሆነ ከሚመስሉት ጋር ቢወዳደር መልካም ነው እንላለን። ካልሆነም ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ወጥቶ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ኢንተርፕራይዝ ስር ቢመዘገብልን እኛም እናርፍ ነበር።
  
ማቅ እየተነገረብን ባለው ነገር ሳትደናገጡ የጀመርነውን ጉዞ አብረን እንቀጥል ሲል አባላቱን ከተማጸነ በኋላ “በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ማኅበሩን በማይገልጸው ማንነት እየሣልን ያለን አካላት ደግሞ ማሩን ባለማምረር ወተቱን ባለማጥቆር የማኅበሩን አገራዊ አስተዋጽኦ እናበረታታ” ሲል በእኔ ላይ ተነስተዋል ያላቸውን አካላት ከ “ተሀድሶ” እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ ያሉትን ሁሉ ተማጽኗል። እስካሁን ለማሳየት የተሞከረውና ማቅ የተገለጸበት ስዕል ፈጠራና ውሸት ሳይሆን በገሃድ የሚታይ የእርሱ ትክክለኛ መግለጫ ነው። ስለዚህ ከመማጸን ባሻገር ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል። ወዴት እየተጓዘ እንደሆነና ጉዞው ወዴት እንደሚያደርሰውም፣ ለምን ሁሉ ጠላት ሆኖ እንደተነሳበት በጥሞና ማሰብ አለበት እንጂ በ “ጽድቄ” ምክንያት የተነሳብኝ የሰይጣን ፈተና ነው ብሎ ራሱን መሸንገል የለበትም። ከዚህ በኋላ በዚህ አክራሪ አካሄዱ ቤተክርስቲያንም ሆነች አገር ማቅን የሚሸከሙበት ትእግስት አይኖራቸውምና።      


21 comments:

 1. ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ጉደለት ካለበት›› ማለት ምን ማለት ነው; ማኅበሩ በሰዎች የሚመራ መሆኑን ዘነጋው ልበል; ወይስ ‹‹ቅዱሳን›› የሚለው ተለጥፋ እውነትም ቅዱሳ የሆኑቱ ብቻ የተሰበሰቡበት እንደሆነ እንዲሰማቸው አደረገ; በሰው እንደሚመራ እንደማንኛውም ማኅበር (እንደውም እጅግ በከፋ ሁኔታ) ስህተት (ምናልባት ስህተት የሚለው ይገልጸው ይሆን;) ይሰራል፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ የሚሰራቸውን ስህተቶች እንደገድል እየቆጠራቸው ነው መሰለኝ ከስህተቱ ለመታረምና ይቅርታ ለመጠየቅ አልቻለም፡፡ አቤቱ የይቅርታ ልብን ፍጥርለት
  ደቂቀ አቡዬ

  ReplyDelete
 2. Selam Egiziabiher Ayileyachu,Yesew hiwot yemiyanitsi neger Lemin Atakerbum weyim sertachu aserun yemiseran bich mewikes tiru Ayidelem
  E/z Yikir Yibelashu
  Erisu Yibarcachu Amen

  ReplyDelete
 3. ሠው ለሠው በተባለው የቴሌቪዢን ድራማ ላይ አስናቀ የሚባለውን ገጸ ባህሪ የሚመስል ሠው በዚህ ዓለም ያለ አይመስለኝም ነበር፡፡ ብዙም ሳልጠብቅ እናንተን በማየቴ በጣም ገርሞኛል፡፡ ሰይጣኖች!!

  ReplyDelete
 4. enkuan. gin min haymanotawi hitsetse tegegnebet?
  lemin silezih atnegrunim?

  ReplyDelete
 5. ሰላም ተሃድሶውያን አንድም ቀን አንኳ ቅን ነገር አታስተምሩንም? ለነገሩ ከየት ታመጡታላችሁ!!

  ReplyDelete
 6. ወገኖቼ ለምን ተው ትሏቸዋላችሁ? ሁሉም እኮ ዓላማቸ አለው!! የእነ አባ ዮናስን ዕጣ ያየ ከማ/ቅ ጋር አይቀለድም!!ማ/ቅ መጥፋት አለበት። ይህ ካልሆነ ያን የመሰለ "ትምህርታቸውን፡ ይዘው ወደ ቤ/ን እንዴት ይገባሉ? በሚያነኳኩት በር ሁሉ እየደረሰ እንደ ሳይረን እየጮኸ አላስገባ አላቸው እኮ!! ምን እንደ ሳይረን ብቻ...እንደ ጥላ እየተከተለ መተንፈሻም አሳጣቸው እኮ!! በሃገር ውስጥም በውጭም!! ካለገቡ ደግሞ "አሮጊቷ ሳራ" እንዴት ትታደስ? ግን እኮ ተሐድሶንም ማደስ ይቻላል እኮ..ቤ/ንን ማደስ ካልተሳካ ማለቴ ነው!!
  ታ.ው

  ReplyDelete
 7. "ተማጽኖው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በማኅበሩ ላይ ለተናገሩት የተሰጠ መልስ ነው ተብሏል":: ማን ነው ደግሞ እንደዚያ ያለው? አሁን እናንተ መጻሀፍ ቅዱስን ታውቁታላችሁ? ምን አልባት አንተ የያዝከው በመሰለኝ መናገር የጌታ ልጅ ያደርጋል ይል ይሆን?

  ReplyDelete
 8. pleas letus work together orthodox people:

  ReplyDelete
 9. Marum Ayimrer Wetetum Ayitkor!

  ReplyDelete
 10. አባ ሰላማ ሰላምን እጡ ፤ ይህን ጠብቁ ። ማርያም ከግንድ የሚያላጋ ልጇን በቅርብ ቀን ትልክባችኋለች። የተክለ ሃይማኖት አጽም አይናችሁን ያወጣዋል። እናንት የተረገማችሁ ርጉሞች ናችሁ ። ድረ ገጻችሁም ወንጀልኛ ሁኖ ይገኛል፤ ይዘጋል። ይህን በድረ ገጻችሁ ባታወጡትም ግድ የለኝም ፥ ዋናው ቁም ነገር እናንተ መልእክቱን እንድታገኙ ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. you are non sense! what is wrong with this guys? As far as I know about this web site, they are not anti Christ, do you know what you are talking? you said that virgin Mariam gonna send her son to punish this them. please do not be idiot and chicken head!

   Delete
  2. typical MK Cheerleader

   Delete
 11. አይ ማቅ ከወደቁ በኅላ መፈራገጥ ለመላላጥ እንዳይሆንባችሁ በቀረው ጊዜ እንኩአን \በአሥራ እንደኛ ሰዓት እንኩአን እስቲ ወደ ነፍሳችሁ
  ተመለሱ፣ እስከመቼ ነው በሐሰትና በቅናት የምትኖሩት \ እስከመቼስ ነው የክርስቲያኖችን ሥም ስታጠፉና ጥላሸት ስትቀቡ የምትኖሩት
  \ አንድ ቀንም እንኩአን የህይወት ማግኛ ሥራ ሳትሰሩ እንዲሁ የሰይጣንን ወሬ ስታቀባብሉ 20 ዓመት ሞላችሁ።

  የቀድሞ ስሙ ሳዖል በሚባልበት ጊዜ እንደሚያደርገው የአይሁድን ሥርዓትና ቤተመቅደስ የጠበቀ መስሎት ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ እንደነበረው በኅላም ክርስቶስ ተገልጦለት ሳዖል ፣ ሳዖል ስለምን ታሳድደኛለህ \ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሃል ብሎ አይኑን በታላቅ ብርሃን እንዳወረውና ሃይሉን ክርስቶስ እንዳሳየው፤ የቀድሞ ስሙ ተቀይሮ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተባለ ከዚያም በኊላ አምኖ
  ክርስቲያን ሆኖ የክርስቶስ ወታደር በመሆን እስከ መጨረሻው ድረስ የሚገባውን የክርስቲያን ሥራ ፈፅሞ የድል አክሊል ከአምላኩ የተቀበለ መንፈሳዊ ጀግና ነው። ታዲያ እናንተም አሁን ለቤትክርስቲያን ያገለገላችሁ መስሎአችሁ ይሆን የክርስቶስና የክርስቲያኖች ጠላት ወይም አሳዳጆች የሁናችሁት ያሳዝናል።
  ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ እኮ እያንዳንዳችን የምንጠየቀው የማህበረ ቅዱሳን አባል ነበርክ \ ክርስቲያኖችን አሳደሃል\ ቤተክርስቲያንን
  ከፋፍለሃል\ እገሌን መናፍቅ እግሌን ደግሞ ተሐድሶ ብለህ አጋልጠሃል\ ወይስ ደግሞ እርስ በርስ ፍቅር እንዳይኖር አጣልተሃል\
  እኔ ብቻ ክርስቲያን ሌላው በሙሉ ሌላ ነው እያልክ አጣልተሃል እንዲሁም ሌላም ሌላም---------- አይደለም የምንጠየቀው።

  ክርስቶስ ሲመጣ የምንጠየቀው ፤ ብራብ አብልታችሁኛል \ ብጠማስ አጠጥታችሁኛል \ ብታረዝ አልብሳችሁኛል \ታስሬስ
  ጠይቃችሁኛል \ ታምሜስ አይታችሁኛል \ እውነት እውነት እላችሁአለሁ ከኔ ለሚያንሱ ለታናናሽ ወንድሞቼ ካደረጋችሁ ለኔ
  አደረጋችሁ ማለት ነው። ታዲያ ለፍርዱ ጥያቄ ከራሴ ጀምሮ ያደረገነው የትኛውን ነው \ የሚፈረድልንስ በየትኛው ሥራችን ነው \
  በማህበረ ቅዱሳን ጭፍን ተከታይነታችን \ መልሱን ለህሊናችሁ\ን\ ትቸዋለሁ። እናስተውል፣ እናስተውል፣ እናስተውል።። አሜን።
  ሊቀ ስዩማን ኃይለ ጊዮርጊስም ሆነ አቡነ ፋኑኤል የእናንተ ደጋፊ ካልሁኑ ስማቸውን ማጥፋት አለባችሁ \ ከእናንተ የጥፋት ድርጅት
  በቀር ፤ እኛ ሁለቱንም ወንድሞቻችን በእግዚአብሔር ፍቅር እጅግ እድርገን እንወዳቸዋለን። ክርስቶስ ያስተማረን ፍቅርን ነውና። አሜን።
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 12. የመንፈሳዊ ኮሌጅ ማታ ተማሪ ከሆንኩ በኋላ በተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በአማኒነት በነበርኩባቸው ዓመታት ያላወኩዋቸውን እውነታዎች ለማወቅ ችያለሁ፡፡ ለእኔ ዋናውና ትልቁ የተረዳሁት እውነታ ማህበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ስም የተለጠፈ መሰሪና ኪራይስብሳቢ አመራር ያለው ማህበር መሆኑን ነው፡፡ በየዋህነት ዘመኔ ከማገኛት ደመወዜ 10ፐርሰንት እየቀነስኩ ለማህበሩ ስድስት ዓመታት ሙሉ መገበሬ ያሳዝነኛል፡፡ አመራሮቹ አክስዮን አቋቋሙበት፤ባንክ፤ ኮንስትራክሽን ድርጅትና ሌሎችንም የንግድ ድርጅቶች ከፈቱ፡፡ አሁንም አይን ባወጣ መንገድ የምንሰራው ለበተ ክርስቲያን ነው እያሉ የቤተክርስቲያንን ሀብት እያጋበሱት ይገኛሉ፡፡
  ማህበሩ የሰበሰበውን ሀብትና ንብረት ለበተክርስቲያን መልሶ መፍረስ አለበት፡፡ ይሕ እሰከሚሆን ድረስ የመደበኛም ሆነ የማታ ቲኦሎጂያን ትግላችን ይቀጥላል፡፡

  ReplyDelete
 13. 'እናንተ የእፉኝት ልጆች'

  መጥምቁ ዮሐንስ እንደዚህ ያለ ግልጽ ስብከት በመስበኩ ቃሉ ከሰሚዎች ጋር ስለተዋሃደ እንዴት እንዲህ ይለናል? ሳይሉ ብዙዎች በንስሃ ጥምቀት ከክፋታቸው ተመለሱ:: ታዲያ 'መልአኩ ገብርኤል' 'ሰይፈ ገብርኤል' እያላችሁ በመላእክት ስም የምታላግጡ 'የዚህ ዘመን የእፉኝት ልጆች' መቼ ይሆን ወደ ማስተዋል የምትመጡትና ከስንፍና ሥራችሁና ስድባችሁ የምትፈወሱት? ደግሞስ ማቅ ሰዎችን እባካችሁ ተውኝ ብሎ ከመማጸን ፊቱን ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው የምህረት ጌታ ቢመልስና ንስሃ ቢገባ አይሻለውምን?? የሚለመን ማን እንደሆነ እንኳ ጠፋበት ወይስ ከጅምሩም የሚያደርገውን አያውቀውም ማለት ነውን??

  ስለዚህ የተማጽኖ ልመና የሚገባው ጌታ እንጂ ሰው አይደለምና እባካችሁ አቅም የሌለውን አፈር የሆነውን ሰው ከመማጠን ፊታችሁን ወደ ሰማይ አምላክ አቅኑ!!! ሌሎቻችንም ትክክለኛ ንስሃ እንዲያደርጉ/እንዲገቡ በጸሎት እንርዳቸው? 'ከፍቅር ሌላ እዳ አይኑርባችሁ' ይላልና የዘላለም ቃሉ::

  ማቆች ወይም ተሳዳቢ የሆኑት እነ'መላኩ ገብርኤል' 'የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው' በማለት እንደ ዲያቆን እስጢፋኖስ/እንደ ራሱ እንደ ጌታ ኢየሱስ እንቃትትላቸው?? ምንስ ቢሆን የሥጋ ወገኖቻችን አይደሉ?

  ለሁላችንም ማስተዋልን ይስጠን!!!

  ሰላም ሁኑልኝ

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሠይፈ ገብርኤልMay 9, 2012 at 11:54 AM

   በመላእክት ስም አታላግጡ ብሎ ለመናገር አግባብ የሚሆንለት በመላእክት አማላጅነት የሚያምንና የአክብሮት ስግደትን የሚፈጽም እንጅ የሉተር ትምህርትን በጉንዳጉንዲው እስጢፋኖስ ስም ወደ ቤተ ክርስቲያን ለማስገባት በሚሯሯጥ ሰው አይደለም ፡፡ ቃሉን ቢቻል ከመጽሐፍ ለማጥፋት የምትመኝውን ገብርኤልን በማይገባው ቦታ ሁሉ አትደንቅሪው ፡፡ ዛሬ ራስሽን በራስሽ አጋለጥሽ ፡፡ ከዚህ ቀደም በሰይፈ ገብርኤል ስም "እናንተ የእፉኝት ልጆች" በሚል ርዕስ መልዕክት የጻፍሺው አንቺ ነበርሽ ማለት ነው ፡፡ ለሁሉም እግዜአብሔር ይመስገን ፡፡ ትዕግስቱን ሰጥቶ ጩኸቴን ሰምቶ ሁሉንም በፈቀደ ጊዜ መልስ ሰጠኝ ፣ በዓይኔም አሳየኝ ፡፡ በሰው ስም ከመጠቀምና ከአሉባልታ ተላቀቂና ወደ ፍሬ ነገር ተመለሽ ፡፡ ትንሽ ብንማማር ሃይማኖት ላይ ብቻ ትኩረት አድርጊ ፡፡

   ሲቻል በአውደ ምህረትና በወንጌል ፣ ሳይሳካ ያልሆነ ስም በመለጣጠፍና አርማ በመስጠት ፣ አልሆን ሲል ደግሞ በመንግሥት ላይ ታዝሎ የቤተ ክርስቲያንን ችግር ፣ ከፖለቲካ ጋር አቆላልፎ ለመፍታት በስውር መሥራቱ ፣ ያረጀ የዘመነ መሳፍንቱን ታሪክን ነው የሚያስታውሰን ፡፡ አካሄዱ ለቤተ ክርስቲያናችን ዕድገትና መሻሻልን አያመጣም ፤ እምነትንም አያጠነክርም ፡፡ ከእግዚአብሔር ይልቅ የምንመካው በሰዎች ላይ ይሆንብናልና ፡፡ በሁኔታው ግለሰቦች ሥጋዊ ፍላጐታቸውን ሊያደላድሉና ሊጠቅሙበት ይችሉ ይሆናል ፡፡ እግዜር ግን ይህን ዓይነቱን ሥራ አይፈልገውም ፡፡

   እንደ ወንድም የምሰጠው ምክር የሃይማኖት ትምህርት ግድፈት ተፈጽሞ ከሆነ በዛ ዙሪያ መማማር ነው እንጅ ፖለቲካንና ሃይማኖትን አታደበላልቁት ፡፡ እንደ ወንጌሉ ቃል ለሁሉም የሚገባውን ብቻ አድርጉ ፡፡

   ለሁሉም ልቦና ይስጥልን

   Delete
 14. LE"MELAKU GEBRIEL":-EYESUS YADNAL ENJI KEGIND GAR YALAGAL YEMIL KAL YETGNAW BIBLE NEW BAKIH YASTEMAREH?ST'MARRY EYESUSIN TILIKEWALECH YALEWUS YETGNAW NEW?BIBLE ANBIBEH ENDEMATAWUK TEBANENEBIH.YEMELAK SIM MEYAZ MELAK AYADERGIM ESHI!DINKEM CHRISTIAN.YESELAM ALEKA YEHONEWUN EYESUSIN SILEMISEBKU ANTE ENDALKEW SELAM LIATU AYCHILUM.GIN 1 NEGER LINGERIH CHRISTIAN YEMITELUTIN YEMIWED,YEMIMERIK ENJI YEMISADEB AYDELEM EGZIABHER MASTEWAL YISTEN."ማርያም ከግንድ የሚያላጋ ልጇን በቅርብ ቀን ትልክባችኋለች። የተክለ ሃይማኖት አጽም አይናችሁን ያወጣዋል።"LEMEHONU LEZIH KAL MASREJA MAKREB TICHIL YIHON ESKI NIGEREGN?BENATIH......PLZ.ABA SELAM ENANTE GIN EWNETUN AWUTU YEMIKEBEL YIKEBEL YEMAYKEBEL THAT IS UP TO HIM.STAY BLESSED.JESUS IS LORD.(BORN AGAIN CHRISTIAN.)

  ReplyDelete
 15. አሳፋሪ ብሎግ ስለ ማቅ ብቻ
  ለምን ስለተሓድሶ መናፍቃን የሚሰብኩትን “ወንጌል” / ወንጀል አትፅፉም፡፡

  ReplyDelete
 16. እኔስ በአንዲስ ቤተክርስቲያን / ኃይማኖት (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ) አማኝ ነኝ፡፡ የማህበረ ቅዱሳን ደጋፊም ተቃዋሚም አይደለሁም፡፡ ግን ምነው ማ/ቅ ላይ እንዲህ ችክ አላችሁ? ሌላም ወሬ የላችሁ? እስኪ ኢአማኒ የሆነው እንዲያምን፣ ኃጢአተኛው ንስሀ እንዲገባ በአጠቃላይ የሚያንጽ ነገር በመድረካችሁ ብታወጡ፤ ሌላው በጣም የሚገርመኝ እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳንን ጻድቃንን ባታዋርዱ (ጻዲቁን የሚቀበል የጻዲቁን ዋጋ ያገኛል) የሚል በቅዱሱ መጽሐፍ ሠፍሯል፡፡ ስለዚህ ወገኖች እባካችሁ ከዚህ አዘቅጥ ውስጥ ራሳችሁን አውጡ ቅዱሳኑን ባታከብሩም ቢያንስ አምላከ ቅዱሳን ያከበራቸውን ዝምምምምምም በሉ፡፡ በእየለቱ ኃጢአት አታከማቹ እንደ እህት የናንተ መጥፋት ያሳስበኛል፡፡ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ለማደስ ከሆነ የተነሳችሁት ያለ ዘለፋና ንቀት ወይም ያለ ስድብ ይሁን፡፡ የቅዱሳን አምላክ ይቅር ይበላችሁ

  ReplyDelete
 17. ስማ! አንተ እኮ ደንበኛ ማቅ ነህ። በየት በኩል ያልከውን ያድርጉ። እንዲህ እንዳያደርጉ የከለከለው እኮ ማቅ ነው። ማቅ አስቀድሞ ከቤተክርስቲያናችን ሳይወገድ ይህን ስራ መስራት አይቻልምና አስቀድሞ ማቅ መመታት አለበት። ከዚያ ሕዝባችን ነጻ ይወጣል

  ReplyDelete
 18. makn lemetagel wust wstun tenestenal hulachinm 1 yebetekiristiyan lijochi inihun bemileyay mahber anderaji.gondere na gojame ,weloyena shewa eyaln anbetbit.lelochi bizu ethiopiyawyan alu.mak ene tsadik ene nitsuh zer ene yetemarku....aresintun meglets yichalal? silazih eyihe yekiristiyan parti akuakume kiristinan tebikalehu yemilewn tsinfena betechalen hulu taglen enatifaw !!! tederajitewal akim fetrewal anibel tiglun zare enjamer gobez tenes !!!!!
  G/wold

  ReplyDelete