Monday, June 25, 2012

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

የግንቦት 15/2004 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡ ውግዘት ያስተላለፈው በ7 ድርጅቶችና በ16 ግለሰቦች ላይ ነው፡፡ ሲኖዶሱ አውግዣለሁ ቢልም፣ የጉዳዩ አነሳሽ፣ ጥናት አቅራቢውና ውግዘቱ እንዲተላለፍለት ተግቶ ሲሰራ የቆየውና እቅዱን በተሳካ ሁኔታ ያስፈጸመው ማኅበረ ቅዱሳንና ደጋፊዎቹ በተላለፈው ውግዘት ደስተኛ ሆነዋል፡፡ ውግዘቱ በተላለፈባቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች፣ እንዲሁም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉ በነበሩት በርካታ ተመልካቾች ዘንድ ግን የጌታችንን ትምህርት ያልተከተለ፣ ህግ ቤተክርስቲያንን የጣሰ፣ ግብታዊነት የተሞላበት፣ ሥልጣንን አለአግባብ እንደመጠቀም የተቆጠረ፣ በአጠቃላይም ቤተክርስቲያኒቱ በምን አይነት ይዞታ ላይ እንዳለች ያመላከተና ውግዘት ዘበከንቱ ሆኖ ያለፈ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡  
የግንቦት 15ቱ ትእይንት በዚህ መልክ ይለፍ እንጂ፣ የተላለፈውን ውሳኔ ወደየአህጉረ ስብከት የማዛመቱ ስራ ቀጥሏል፡፡ ጉዳዩ እዚህ ላይ የሚያቆም አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ጉዳዩ የማኅበረ ቅዱሳንና የተሀድሶ ጠብ ሳይሆን፣ የክርስቶስ መንግሥትና የሰይጣን መንግስት ትግል፣ የእውነትና የሐሰት ትንቅንቅ፣ የወንጌልና የተረት ግብግብ ነው፡፡ በሐዋርያት ዘመን እንደሆነው የተጀመረው የክርስቶስን ወንጌል ለሰዎች ሁሉ የመስበክና በአዳኝነቱ የማሳረፍ የተቀደሰ አገልግሎት ሕገ ቤተክርስቲያንን ባልተከተለ ውግዘት አይቆምም፤ በከንቱ እርግማን አይገታም፤ በየሀገረ ስብከቱ በሚበተን ደብዳቤም አይሰናከልም፡፡ በጥሩ መሠረት ላይ የተጣለውና ማንም የማያቆመው የእግዚአብሔር መንግስት ስራ በሰይጣን መንደር ሽብርን፣ ፍርሀትንና ድንጋጤን እያሳደረ ብዙዎችን በክርስቶስ መውረሱን ይቀጥላል፡፡ ይህ ተራ ፉከራ አይደለም፡፡ የወንጌል አካሄድ ነው፡፡ ወንጌል ሲያፍኑት፣ ሲያወግዙት፣ ሲያሳድዱት ይብሳል እንጂ በተቃውሞና በአድማ ብዛት አይቆምም፡፡ በሐዋርያት ሥራ ውስጥ እንደተጻፈው «የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ።» ነው የሚለው (የሀዋርያት ስራ 6፡7)፡፡ እንደገናም «የእግዚአብሔር ቃል ግን ያድግና ይበዛ ነበር።» ይላል (የሀዋርያት ስራ 12፡24)፡፡    

ከታሪክ ማረጋገጥ የሚቻለው ውግዘት የሚጠቅመው ለአውጋዡ ሳይሆን ለተወጋዡ ነው፡፡ ይህ ማለት ለጊዜው በተወጋዡ ላይ አንዳንድ ችግሮችን ሊያስከትል አይችልም ማለት አይደለም፡፡ እያደር ግን የተወገዘው ክፍል ይበልጥ ተቀባይነት እያገኘና ትምህርቱ እየተስፋፋ መሄዱ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ሩቅ ሳንሄድ የግንቦቱ ሲኖዶስ በሕገ ወጥ አሰራር ካወገዛቸው ግለሰቦች ብዙዎቹ ከዚህ ቀደም በሲኖዶስ አይሁን እንጂ በያሉበት አካባቢ ባሉ በማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ቡድኖች፣ በሰበካ ጉባኤ አባላት፣ በሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮች እና  በቤተክህነት ሹማምንት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ባልተከተለ መንገድ የተወገዙ ነበሩ፡፡ በውግዘቱ ለጊዜው አንዳንድ ችግር አጋጥሟቸው ሊሆን ይችላል፡፡ እያደር ግን የተወገዙበትን እውነት በጽሑፍና በልዩ ልዩ መንገድ ይፋ በማድረጋቸው ብዙ የትምህርታቸው ተከታዮችን አፍርተዋል፡፡ ዛሬ በርካታ መነኮሳት፣ መሪጌቶች፣ ቀሳውስት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ተማሪዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ጭምር በቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ ሆነው እውነትን ከሐሰት ወንጌልን ከተረት ለይተውና በክርስቶስ ወንጌል ነጻ ወጥተው ይኖራሉ፡፡ ይህ እንዲሆን ውግዘት የተጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ የዘንድሮው ሕገን ያልተከተለ የጅምላ ውግዘትም የወንጌሉን አገልግሎት ወደበለጠ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው እሙን ነው፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት የአንድ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በማኅበረ ቅዱሳን አባላት በኩል «እነእገሌ ይወገዙ» በሚል ስም ዝርዝራቸው ስለቀረበ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች የሰጡት መልስ እዚህ ላይ ቢጠቀስ ለጉዳዩ ይበልጥ አስረጂ ይሆናል፡፡ እኚህ ጳጳስ እንዲህ ነበር ያሉት «እኔ ማንንም አላወግዝም ምክንያቱም እነአርዮስ ባይወገዙ ኖሮ ትምህርታቸው እንዲህ ባልተስፋፋም ነበር፡፡ ስለዚህ ከማውገዝ ይልቅ ሌላ መፍትሔ ነው መፈለግ ያለበት፡፡» ብለዋል፡፡ በዘንድሮው የጅምላ ውግዘት ላይ ይህን አስተያየት ደግመው ስለመናገራቸው ግን መረጃ የለንም፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን መስከረም 30/2004 ዓ.ም. እንዲወገዙልኝ ብሎ ለቅዱስ ፓትርያርኩና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ያሰራጨው ባለ 56 ገጽ የክስ መዝገብ፣ የሊቃውንት ጉባኤው 50 ገጽ ጥናታዊ መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ፣ 49 ገጽ የቅዱስ ሲኖዶስ የውግዘቱ ቃለ ጉባኤ በእጃችን ይገኛል፡፡ እነዚህን መረጃዎች መሠረት በማድረግ በውግዘቱ ዙሪያ ሂደቱን ይዘቱን ጠቅላላ አካሄዱን በተመለከተ የምናቀርበው ትንታኔ አለ፡፡ ለዛሬው ለመግቢያ የሚሆኑ ሐሳቦችን እናንሳ፡፡

በዘንድሮው የግንቦት ሲኖዶስ ስብሰባ የተላለፈውና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተለው ውግዘት እንዲደረግ ጉዳዩን ያነሳሳው ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ማኅበሩ ላለፉት 20 ዓመታት ራሱን ብቸኛ የቤተክርስቲያን ጠበቃ አድርጎ ሲመለከት፣ ከእርሱ ሐሳብ ጋር ያልተስማሙትን፣ የተቃወሙትንና እኩይ ተግባሩን የገለጡትን ማኅበራት የቤተክርስቲያን አባቶች፣ መምህራንና በየደረጃው ያሉ አገልጋዮችን በየጊዜው እንዲወገዙ ልዩ ልዩ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ስርአተ ቤተክርስቲያንን ባልጠበቀ ሕገ ወጥ መንገድም በርካቶች ከቤተ ክርስቲያን እንዲሰደዱ አድርጓል፡፡ በግንቦት ለተላለፈው ውግዘት ማኅበረ ቅዱሳን በተለይ ከ2002 ዓ.ም ወዲህ በተጠናከረ መልኩ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ በነሐሴ 2002 ዓ.ም «ሐመረ ተዋህዶ» የተሰኘ ልዩ እትም መጽሔት በማውጣትም ዘመቻውን መጀመሩን አበሰረ፡፡ ከዚያም ግንዛቤ አስጨብጣለሁ በማለት በየአዳራሹና በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ “ተሐድሶ” ሲል የፈረጃቸውን ወገኖች ማብጠልጠሉን ቀጠለ፡፡ አጋጣሚውንም ለዘመቻው በሚል ዳጎስ ያለ የገንዘብ ድጋፍ ለማሰባሰብ ተጠቅሞበታል፡፡ ማኅበሩ በግንዛቤ ማስጨበጥ ስም የጀመረው ስራ ህገ ወጥ መሆኑ በተለያዩ ጊዜያት ከጠቅላይ ቤተክህነት የሚመለከታቸው ክፍሎች ደብዳቤ እየተጻፈ ቢነገረውም በእንቢታው በመጽናት እየተሽሎከሎከ ዘመቻውን ገፋበት፡፡ ሐምሌ 26/2003 ዓ.ም በቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ [ስሙ ሳይጠቀስ] ማኅበሩ እየሄደበት ያለው መንገድ ሕገ ወጥና በስም ማጥፋት ወንጀል ከማስጠየቅ ያለፈ ፋይዳ እንደማይኖረው ተገልጾ ውግዘት እንዴት ባለ መንገድ ሊተላለፍ እንደሚችል የሚጠቁም ደብዳቤ ተበተነ፡፡ ማኅበሩ በስውር ድረ ገጾቹ ይህን ተቃውሟል፡፡ ያቀረበውን ክስም በጥቅምቱ 2004 የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በአጀንዳነት ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በኋላ ሊቃነ ጳጳሳት ያሉበት አጣሪ ኮሚቴ ከሊቃውንት ጉባኤ ጋር በመሆን ክስ የቀረበባቸውን ግለሰቦች ጠርተው በማነጋገር ጉዳዩን እንዲያጣሩና ለግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ እንዲያቀርቡ ተወሰነ፡፡

ይሁን እንጂ በውሳኔው መሰረት በማኅበረ ቅዱሳን የተከሰሱት ወገኖች ተጠርተው አልተጠየቁም፡፡ በአገር እያሉ እንደሌሉና እንደተሸሸጉ ተቆጥሮ ጉዳያቸው በሌሉበት ከታየ በኋላ በአጣሪ ኮሚቴው ሊወገዙና በሕግ ሊጠየቁ ይገባል የሚል አቋም ተያዘ፡፡ ተጠርተው የተጠሩና የተጠየቁ እንጀራቸው እዚያው የሆነው ቆሞስ አባ ሠረቀብርሃንና ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ፣ እንዲሁም መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ ብቻ ናቸው፡፡ ይኸው የውሳኔ ሐሳብ ተደርጎ ለሲኖዶስ ቀረበ፡፡ ፓትርያርኩን ጨምሮ አንዳንድ አባቶች አካሄዱ ተገቢ አለመሆኑን ቢናገሩም ሰሚ ሳያገኙ ሲኖዶሱ በድምጽ ብልጫ አውግዣለሁ አለ፡፡ የውግዘቱ መነሻ፣ ሂደትና ፍጻሜው ከሞላ ጎደል ይህን ይመስላል፡፡ 

ማኅበረ ቅዱሳን መክሰስ መብቱ በመሆኑ ለምን ከሰሰ አይባልም፡፡ ጉዳዩን እንዲመለከት ሀላፊነት የተሰጠው ኮሚቴና የሊቃውንት ጉባኤው ግን ጉዳዩን በተወሰነው ውሳኔ መሰረት በሕጋዊና በተገቢው መንገድ ከማጣራት ይልቅ ማኅበረ ቅዱሳን ያቀረበውን የክስ መዝገብ «ኤዲት» አድርጎና ጥቂት አሻሽሎ ነው ያቀረበው ለማለት ይቻላል፡፡ የሊቃውንት ጉባኤው «ጋኖች አለቁና … » እስኪባል ድረስ በሊቃወንት ደንብ ሳይሆን በማኅበረ ቅዱሳን ደረጃ እንዲህ ወርዶ መታየቱ፣ ሃይማኖትን ሃይማኖታዊ ካልሆነ ነገር ሳይለይ ሁሉንም እንደ ኑፋቄ መውሰዱ፣ ለይምሰል የነቢያትንና የሐዋርያትን ትምህርት እከተላለሁ እያለ በተግባር ግን ሲያወግዛቸው መታየቱ፣ የእግዚአብሔርን ቃል እያወገዘ የሰውን ትምህርት ማጽናቱ ቤተ ክርስቲያኗ ሰው እንደሌለባት አሳይቷል፡፡ “አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር” ማለት ይህን ጊዜ ነው፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በአንድ ወቅት ግብጻውያን ያደረሱብንን በደል አስታውሰው «በእርግጥ ቤተክርስቲያናችን አልሞተችም ብለን አንዋሽም» ብለው ነበር (ትንሣኤ የሐዋርያዊ ድርጅት መጽሔት ነሐሴ 30/1963 ዓ.ም ገጽ 14)፡፡ ያቺ ብዙ ዓይናማና ተጠያቂ ሊቃውንት የነበሩባት፣ ፊት አይተው በገንዘብ ተገዝተውና ሰውን ፈርተው ሳይሆን ለእውነትና ለእግዚአብሔር ቃል ቅድሚያ የሚሰጡ ሊቃውንት ያለፉባት ቤተክርስቲያን፣ ሃይማኖትን ከትውፊት፣ የሚያስወግዘውን ከማያስወግዘው ለይተው የሚያውቁና እንደጌታችን ትምህርት ሰውን ለማዳን እንጂ ሰውን ለማጥፋት የማያድሙ እውነተኞች መምህራን ያለፉባት ቤተክርስቲያን፣ እውነትን በሚያወግዙና ሐሰትን በሚያነግሡ “ሊቃውንት” እጅ ስር መውደቋ ቤተክርስቲያኗ ሞታለች ከሚያሰኝበት ደረጃ ላይ መድረሷን አመልካች ነው፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ክስ የቀረበባቸውን መምህር ግርማ በቀለንና መምህር ጽጌ ስጦታውን ለማነጋገርና ለመከራከር የደፈረው ሲኖዶስ አሁን የት ሄዶ ነው ማንንም ሳያነጋግርና የተከሳሾቹን ቃል ሳይሰማ ከመሬት ተነስቶ አውግዣለሁ ያለው? ለማነጋገር ያልፈለገው ፈርቶ ነው ንቆ? ወትሮም ቢሆን በተገቢው መንገድና ሕገ ቤተክርስቲያንን ባልተከተለ አካሄድ የሚተላለፍ እንዲህ አይነቱ ውግዘት ቀልሎ እንደሚታይና ክብደቱ እንደሚቀንስና ተቀባይነት እንደማይኖረው እንኳ ማስተዋል እንዴት ተሳነው? የአባቶች ታላቅ ምክር በልጆች ስሜታዊ ሀሳብ እንዴት ተሸነፈ? ሥርአተ ቤተክርስቲያንን ያለተከተለ፣ የቤተክርስቲያንን ታሪክ ያላገናዘበውና ትልቅ ትዝብት ላይ የሚጥለው ይህ ውግዘት ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም አይሆንምን? የማኅበረ ቅዱሳኑ ዲያቆን ኅብረት የሺጥላ በጻፈውና «ትምህርተ ውግዘት» በተሰኘው መጽሐፍ ላይ እንደተጠቀሰው፥ ግዘት «እጅግ ስለታም የሆነ መንፈሳዊ ሰይፍ ትዕግስት በማጣት በየቦታው ያለአግባብ የሚመዘዝ መሆን የለበትም፡፡ ተእግስትና በቂ መንፈሳዊ እውቀት በሌለው ሰው እጅ ያለች ስልጣነ ክህነት በእብድ እጅ እንዳለች ሰይፍ ናት፡፡» (ገጽ 8)፡፡ በእርግጥም ውግዘቱ የተላለፈው እንዲህ ያለ ማንነት ባላቸው አባቶች አማካይነት በመሆኑ ማዘን የሚገባው ለቤተክርስቲያኒቱ ነው፡፡

ይህን የምንለው በሀቅ ላይ ተመስርተን እንጂ በስሜት ተነድተን እንዳይደለ በቀጣይ ከምናወጣው ዘገባ አንባብያን ይረዳሉ ብለን ተስፋ እንደርጋለን፡፡ የተወገዙትን ያስወገዟቸው ኑፋቄዎች ምን ምን ይሆኑ? ያስወግዛሉ አያስወግዙም? መወገዝ ያለባቸው ትምህርቶችስ የሉም?   

ይቀጥላል


25 comments:

 1. ሃሳባችሁ ግሩም ነው እንደእናንተ አይነት ለማቅ ተግዳሮት የሚገባ ሌላም ክፍል ያስፈልጋል ግን እንደው ለየሰንበት ት/ቤቱ የኢንተርኔት እድል ለሌላቸው ይህ መግለጫችሁ እንዴት ይድረስላቸው?ምን መንገድ ይኖራል?ይህ እኮ እቅጯን የምትናገሩትን ነገር እኮ የሰንበት ት/ቤቶች ቢያገኟት ማቆች አንድ ቀን የሚያድሩን አይመስለኝም!ለነገሩ ይህ ውግዘት ምን ያመጣል ብላችሁ ነው?ተወጋዦች እኮ ናቸው አሁንም ቤ/ክርስቲያኒቱን እያንቀሳቀሱ ያሉት እንደውም ተወጋዦች እየተፈለጕ ሌሎች ክፍሎች እየደወሉ እየጠየቋቸው ስለሆነ ጥሩ ነው ግን ይሄ ማቅ ያሰራጨው 56 ገጽ የክስ መዝገብ፣ የሊቃውንት ጉባኤው 50 ገጽ ጥናታዊ መግለጫና የውሳኔ ሐሳብ፣ 49 ገጽ የቅዱስ ሲኖዶስ የውግዘቱ ቃለ ጉባኤ በእጃችን ይገኛል፡ያላችሁት እኮ በቡልሌት መልክ ተባዝቶ ቢሰራጭ መልካም ነበርና እስቲ ሞክሩ እናንተ አባ ሰላሞችና ዓውደ ምህረቶች ምን ያቅታችኋል?እግዚአብሔር ይርዳችሁ!
  ኒቆዲሞስ ነኝ!

  ReplyDelete
 2. Enanite MK eko ayimetinachihum! Min awerachihu bilo yemiteyik yelem

  ReplyDelete
 3. afincha sineka ayin yaleksal new negeru.Aryos mewegez alneberebetim blo yemimuaget aryosawi kalhone lela lihon ayichilim. Haile seitan teregnaw tewegaj ante nehna tezegej

  ReplyDelete
 4. YES,they do not deserve the attention of MK! MK and sunday schools have a lot to do for the church. This group of TEHADISO should go to their homeland, Europe.

  ReplyDelete
 5. lenante, wongel malet wonjel new ende??? we know that insulting SAINTS is the highest crime, but the protestants( tehadiso) MENAFKAN consider these Crime ('wonjel) as 'wongel'. not surprising, dabilos is carecterized by such behaviour

  ReplyDelete
 6. to nekodimos, don't you know that almost all members of the sunday school students belong to MK????? even don't you know that the evidences accusing the menafkans including 'aba' serke was presented by the sunday school students???? hmmm you don't know as you are emmotional

  ReplyDelete
 7. አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል..........ጉድ በል የሀገሬ ሰው ከተከሳሾቹ ውስጥ ስላላችሁበት ከነከናችሁ..........እውነትናንጋት እያደር.......

  ReplyDelete
 8. እኔ የምላችሁ ይህ ውግዘት ያላችሁት ነገር የማቅን ነው ወይስ የእውነተኛውን ሲኖዶስ የማቅን ሲኖዶስ ነው ወይ የምታናፍሱላቸው?ሌላው ደግሞ በውግዝቱ እንደው የማቅም ሲኖዶስ ቢሆን በማቅ ድምጸ ስምዓ ጽድቅ ላይ አየነው እንጂ እንዚህ እነዚህ ይወገዙ የሚል ፊርማ ያለበትና ሸኚ ደብዳቤ የያዘ ጽሑፍ ከአውጋዡ ሲኖዶስና ከመንበረ ፓትርያርክ ጽሕፈት ቤት ወጥቷል ወይ?ከወጣ እስቲ እንደተለመደው አስነብቡን እባካችሁ!እኛም ተመልክተነው የምንለውን እንበል!ደግሞ የሃይማኖት ነጻነት ባለበት ሀገር ውግዘት ብሎ ነገር ምንድን ነው ማን አውጋዥ ማን ተወጋዥ ሊሆን ነው?
  የአርማትያሱ ዮሴፍ ነኝ

  ReplyDelete
 9. Yemejemriaw astayat sechi, Niqodimos neh weys Demas? ene demas temselngaleh

  ReplyDelete
 10. እጃችሁ በደም ጣቶቻችሁ በበደል ረክሳለች ከንፈራችሁ ሐሰትን ተናግሮዋል ምላሳችሁም ሐጢአትን አሰምቶዋል። ኢሳ 59 ቁ 3
  ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻው ቀርቦአል።እንግድህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ።1ኛ ጴጥ 4 ቁጥር 7።በቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘንድ እውነተኛ ፍርድ ቅን ሀሳብ ከጠፋ ፍጻመው እንደ ደረሰ ማወቅ እጅግ በጣም ቀላል ነው። ስለዚህ የማቅ በቅዱሳን ስም የሚሰራው ክፉ ሥራ ገና ይጋለጣል። ብዙ ወጣቶች ጥለውት እየሄዱ ነው። ሃየማኖት ይበልጣል ማህበር ? ይህ ዓይነቱ ጥያቄ በብዙ ሰዎች ዘንድ መልስ እያገኘ ያለው። በፊት ብዙ ሰዎች የማቅ ስውር ደባ ሳይገባቸው ተከትለውትና ብዙ ገንዘብም አስራት ገብረው ነበር። ይህ ሁሉ ስህተት እንደነበረ አሁን ሁሉም እየተረዳ ነው። በእውነት ከሆነ አስራት መሰጠት ያለበት ለቤተ ክርስቲያን እንጅ ለማህበረ ቅዱሳን አይደለም። ከአንድ መንፈሳዊ ሰው የምጠበቀው እንደ ቅዱስ ቃሉ መኖር እንጅ ለነጋደ ማህበር ክስ ማዳበር የእግዚአብሐርን ሰማያዊ መንግስት አያዋርስም።በቅዱሳን ስም ሥር ተደብቆ የመናፍቅ ሥራ እየሰራ ያለው ማህበረ ቅዱሳን ነው።

  ReplyDelete
 11. kkkkkkk,,hahahhahahahahha.....kkkkkkk....ppppppppppp.........you guys you are so disappointed because of the begining of the destruction of your conispiracy......the two aged sword is going to cut off all who have destructive motives on the whole religious values and identity of our golden church and those who sings for them like you guys. Go and beg your lords in Europe to give you a space because they are changing the european churchs into museums....they might be compassionate to give you one.....Morons.

  ReplyDelete
 12. ውግዘቱን የፈጸሙት አባቶች ስተት መፈጸማቸው በእርግጥ ሳይጸጸቱ አይቀርም የቅድስት ቤተ ከርስቲያን ልጆች በሊነ ጳጳሳቱ ትክክለኛና ምዛናዊ ያልሆነ ዉሳነ በእግዚአብሔር ወንበር ላይ ተቀምጠው ዓለማዊያን እንኳን ያመያደርጉት በመስራታቸው። አንዳንድ እንደ ፈርዖን ልባቸውን ለነዋይ ያደነደኑት ትምክትና ጭካነ ስራ ከመሰራት አሁንም እንደማይቆጠቡ እያየን ነው። እግዚአብሔር ግን በግዜውና በሰዓቱ መልስ ይሰጣል። ለሁሉም ትግስቱን ይስጠን።አባ ሰላማዎች በርቱ ተበራቱ አምላክ ይጠብቃችሁ።

  ReplyDelete
 13. Bezih meder lay sent amet letenoru new yehe hulu weshet yemecheresha mengedachehus wedet mehonun asbachehubetal Amlak lebona yestachehu enes selnante aferku gezew saymesh mengedachehun leyu.

  ReplyDelete
 14. hahahahahahah ayi abaselam:)

  ReplyDelete
 15. በጣም የሚያሳዝን ጊዜ ላይ ለመድረሳችን አንዱ ምልክት ይሄ ነዉ፡፡ ጎበዝ ሰይጣን እኮ 24 ሰዓት በስራ ላይ ነዉ፡፡ ሰይጣን ከማይፈልጋቸዉ ነገሮች የመጀመሪያዉ የክርስቶስ አዳኝነት መነገር ነዉ፡፡ ቀላል ምሳሌ ልንገራችሁ በየትኛዉም ቦታ ይሁን አንድ ሰዉ ስለማርያም፣ ተክለ ሐይማኖት ፣ ገብርኤል ወዘተ ሲያወራ ዉሎ ቢያድር ነገሬ የሚለዉ አይኖርም፡፡ ኢየሱስ የሚል ቃል ከአፉ ቢወጣ ግን አይደለም ሰዉ፣ ሳር ቅጠሉ ይነቃነቃል፡፡ ይህንን የሚፈልግ ሰዉ ሞክሮ ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡ ለምን ብትሉ ሰይጣን ይህንን ስም እጅግ አድርጎ የሚፈራዉ ከመሆኑም በላይ ማንም ሰዉ እንዲጠራዉ አይፈልግም፡፡ አንግዲህ በስብከታቸዉ፣ በንግግራቸዉም ሆነ በጽሑፎቻቸዉ ይህንን ስም የሚጠሩ ክርስቲያኖች ሁሉ ናቸዉ በማህበረ ቅዱሳን ተብየዉ መርዛማ ማህበር ስማቸዉ እየጠቆረ አንዴ ተሐድሶ፣ አንዴ መናፍቅ እየተባሉ አበሳቸዉን የሚያዩት፡፡ በመሰረቱ መናፍቅ ማን ነዉ የክርስቶስ ስም ሲጠራ የሚያመዉ ወይስ የክርስቶስን አዳኝነት የሚመሰክር? ያለድንግል ማርያም ክርስትና የለም የሚል አንድ ሰዉንና ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል የሚል ሌላ ሰዉን አስቡና እስኪ የቱ ነዉ መናፍቅ? በማቅ አስተምህሮና ተልዕኮ ያለድንግል ማርያም ክርስትና የለም የሚለዉ ሰዉ እዉነተኛ ኦርቶዶክስ ሲሆን ስለክርስቶስ አዳኝነት ተናጋሪዉ ግን ጀርባዉ ይጠና ወይ ተሐድሶ አሊያም ጴንጤ ነዉ ይባላል፡፡ አያችሁ ኪሳራ! በመሰረቱ ኢየሱስ የሚለዉ ስም ለጴንጤ ብቻ በኮፒራይት የፈቀደዉ ማነዉ? ጎበዝ እባካችሁ መጽሐፉን እንመርምር፡፡ ክርስትና ማለት ሰኔ ጎለጎታ በመድገምና ነጠላ ለብሶ ቤ/ክ በመመላለስ አይደለም ቃሉን በመማርና በሕይወትም በመተግበር እንጅ፡፡ ለማንኛዉም የተወገዘ ሁሉ የተሳሳተ ስላልሆነ አዉጋዦቹ ልቦና ካላቸዉ ዉሳኔያቸዉን እንደገና ቆም ብለዉ ይመርምሩ፡፡ አለበለዚያ በሰፈሩት ቁና መሰፈሩ አይቀርምና አንድ ቀን በዉሳኔያቸዉ ይጸጸታሉ፡፡
  ወስብሀት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
  Replies
  1. You are really a layer. How could Orthodox Christians refuse the name of Jesus? There are so many churches named Eyesus.Don't you know the meaning of Eyesus? Eyesus means Medicine( Medhanit). we Ethiopians are calling our lord as Medhanealem. Didn't you hear any body who said Medhanealem. If I said Jesus or Medhanealem or Amanueal or Egzeabehare, do you believe that I am wrong unless I said only Eyesus. Please think and see things in different directions.Please think beyond different languages since Americans or other countries do not know what the word Eyesus means but they know what Jesus means. But the meaning of the word Jesus and Eyesus is the same as Medhanealem. don't confuse. Come to our church and get lessons on trinity and other doctrines.

   Delete
  2. አባቶች በጉባዔ ለምን እንዳወገዙ ዝርዝሩን አላውቅም ፡፡ ኢየሱስን ስለሰበከ በሚል ብቻ ግን ማንም አይወገዝም ፡፡ ምክንያቴ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ ትምህርት በሙሉ ኢየሱስን የሚመለከት ስለሆነ ነው ፡፡ አንተን ካልደከመህና ካላቋረጥህ በየቀኑ ረጅሙ የኢየሱስ ምስጋናና ጸሎት የሚደረገው በኢኦተቤ ብቻ ነው ፡፡ ከስሙ ጋር ጸብ እንደሌላት ለዓይነት እንዲሆንህ የሚከተለውን አንብበው ፡፡ እግረ መንገጽህን ጸሎቱን ታደርሳለህ ፡፡

   ከኪዳን ጸሎት ተቀንጭቦ የተወሰደ ፡፡

   እግዚብሔር ቅዱስ ኃያል ፤ ቅዱስ ሕያው የማይሞት ፡፡
   ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደ ፡፡ አቤቱ ይቅር በለን ፤
   በዮርዳኖስ የተጠመቀ በመስቀል ላይ የተሰቀለ አቤቱ ይቅር በለን ፤
   በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ፤ በምስጋና ወደ ሰማይ ወጣ ፤ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ ዳግመኛም በጌትነት ይመጣል ፤ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ አቤቱ ይቅር በለን ፡፡ ልዩ ሦስት ሕያው እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለን

   የሁሉ ዕውቀት ኃያል የምትሆን ፣ ይቅርታህ የበዛ አምላክ ፣ ነፍስን የፈጠርሃት ከዓለም አስቀድሞ ፣ ከአብ የተወለድህ አንተን እናመሰግንሃለን ፡፡

   ወልድ ዋሕድ አንተን እናመሰግናለን ፤ ቀዳሜ በኲር የምትሆን የአብ ቃል ለምንጠራህ ለእኛ ለሁሉ የሚሆን የአንተን ጸጋ የሰጠኸን ፡፡

   ከጨለማ ወደ ብርሃን አወጣኸን ፤ ከሞት አድነህ ሕይወትን ሰጠኸን ፡፡ ከመገዛት ነፃ አወጣኸን ፡፡ በመስቀልህ በሰማይ ወዳለው ወደ አባትህ ያቀረብከን አቤቱ በወንጌል መራኸን ፡፡ በነቢያት አረጋጋኸን ፡፡ ያቀረብከን አምላክ አንተ ነህ ፡፡

   ከሁሉ በላይ የምትሆን የእግዚብሔር ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ጌትነትህ ለዘላለም ከሚሆን መንግሥትህ ጋራ በቃላችን ይህንን ምስጋና ለአንተ እናቀርባለን ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በመራድ ፣ በመፍራት ያመሰግንሃል ፡፡ ነፍስ ሁሉ የሚፈራው የሚያመልከው ፡፡ የጻድቃን ነፍሳት በአንተ ጸንተው ይኖራሉ ፡፡ መናፍስት ያመጡትን የጐርፉን ፈሳሽነት ከእኛ ጸጥ ያደረግህልን ፣ ከጥፋት አድነህ የሕይወት ወደብ የሆንከን ፣ የዘላለም ደኀንነት አለኝታ ፣ ያለበት መሸሻ የሆንከን በባሕር የተጨነቁትን የምታድን ፣ በምድረ በዳም ያሉትን የምታድን ፣ በጽኑ እስራት ካሉትም ጋራ አብረሃቸው የምትኖር ፣ ከሞት ማሰሪያ የፈታኸን ችጋረኞችንና የሚያለቅሱትን የሚያረጋጋቸው ፡፡ የደከሙትን በመስቀሉ የሚያድን ከአመንበት ከእኛ መዓቱን ሁሉ የሚያርቀ ፤ ነቢያትና ሐዋርያት በኀቡእ ያመሰገኑህን አንተን አቤቱ እናመሰግናለን ፡፡ ለአንተ ምስጋና እናቀርባለን ፡፡ አንተን አምነን በመንግሥተ ሰማያት እናርፍ ዘንድ ፡፡ ፈቃድህንም እየሠራን በትእዛዝህ እንድንሄድ አድርገን ፣ ሁሉንም በቸርነትህ ጐብኝ ፡፡ትንንሾችንም ፣ ትልልቆችንም ፡፡ ገዢውንና ሕዝቡን ፣ ጠባቂውንና መንጋውን ፡፡

   አቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቊርጥ ልመናችንን ስማን ፡፡ ድዳ ለነበሩት ቃል ፣ ለተሰበሩት ምርኩዝ ፣ ለዕውራን ብርሃን ፣ ለአንካሶች መሔጃ ፣ ለምጻሙን የሚነፃ ሆናቸው ፡፡ በደዌ የተያዙትን አቤቱ አዳንህ ፤ ደንቆሮችን ፈወስህ ፤ ሞትን ዘለፈው ፤ ጨለማንም ማቀየው ፤ ብርሃንን የፈጠረ ኀልፈት የሌለበት ፣ ፀሓይ የማይጠፋ ፋኖስ በቅዱሳን ላይ ዘትር የሚያበራ ፀሓይ በተወሰነ በቁርጥ ፈቃድ ለዓለም ጌጥ ፣ ሁሉን የፈጠረ ፡፡ ሰውን ለማዳን ለሁሉ ተገለጽህ ፤ ነፍስን ለመለስሃት አንተ ነህ ፡፡ ሁሉን እንደሚገባ ማሰብን አስቀደምህ ፡፡ መላእክትን የፈጠርህ ፤ የሁሉ አባት ፣ የሁሉ ጌታ ፣ የዓለም ጌጥ ፣ ምድርግ የፈጠርሃት ፡፡

   ከጠላታችን ማታለል እንጠበቅ ዘንድ የዘላለም ንጉሥ ሆይ ስማ ፤ ባልቴቲቱን አረጋጋት ፤ አባት እናት የሞቱበትን ልጅ ተቀበል ፡፡ የታለሉትን በቸርነትህ አንጻ ፤ ሰነፎችን አስብ ፤ አዋቂ አድርጋቸው ፤ የጠፉትን መልስ ፤ በግዞት ያሉትን አድናቸው ፤ ለሁላትንም መጸጊያ ሁነን ፡፡ አቤቱ አምላካችን ክቡር መንግሥት ያንተ ነውና ፡፡

   ይህን የምታስተምርና የምታሳትፍ ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስን ... ብሎ ለመውቀስ ራሱ ውሸታም መሆን ነው ፡፡ ስለ ቤተ ክርስቲያኗ ምንም የማያውቁትንም ወገኖች በሩቅ ማስደንበር ነው ፡፡ ከዚህ በተረፈ ውግዘቱ ትክክል ነው አይደለም ለማለት ፣ ሰነዱ ለሕዝብ ይፋ በሚሆንበት ጊዜ የምንነጋገርበት ነው እንጅ ፣ አሁን አንዳንድ የተጐዱ ግለ ሰዎች ቅሬታቸውን በመግለጻቸው ብቻ ፣ አባቶች የወሰዱት ርምጃ ስህተት ነው ለማለት ማንም አይደፍርም ፡፡ እናም ሁሉ እስኪገለጽ ድረስ ትንሽ ታገሱ ፡፡

   ወስብሀት ለእግዚአብሔር

   Delete
  3. በእውነቱ እንደው አፍ የተፈጠረው ለመናገር ነው ብሎ ብቻ መናገር ያስጠይቃል። እነዚህ የኢየሱስን ስም ይፈራሉ የምትላቸው ሰዎች እኮ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እያሉ በተገቢ ቦታ እና ሰዓት በክብር ነው የሚጠሩት። ከእርሱ ጋር ደግሞ የእርሱ የሆነውን ሁሉ ይቀበላሉ እንደ ቃሉ። ማቴ.10፥40
   ለመሆኑ ኢየሱስ ኢየሱስ ማለት የሚያድን ወይም የእውነተኛነት ምልክት ከመሰለህ ጠፍተሃል ተመለስ መጽሐፍ ቅዱስን በትህትናና በማስተዋል አንብብ። አሳሳቾች የሚመጡት ኢየሱስ በሚለው ስም ነው። ማቴ. 24

   ማቴ.7፥21-23 'የአባቴን ፈቃድ የሚፈጽም እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።....በዚያን ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህ አጋንንትን አላወጣንንምን በስምህ ብዙ ተአምራት አላደረግንምን? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ አመጸኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።'

   Delete
  4. You are fool
   Planting church in the name of Jesus differs from worshiping him in truth and spirit.

   Delete
 16. You guys please don't write this kind of evil messages which will make you to stand on the left side of Jesus when he comes. You know what you are doing and which religious path you are following.I know from which religion you are as I was a protestant before 10 years. As far as I know LYING is forbidden in your protestant church so, why do you write as if you are member of Ethiopian Orthodox church? Do you believe that Jesus will reward you by confusing the true Christians like Satan who is tempting Christians day and night.

  Please I would like to forward my advice from my deep heart in the name of Jesus that you need to confess your sins especially on this kinds of issues, stop writing on untruth stories by blaming our brothers in Jesus and read the holy bible so as to get the truth. 'Mawenabed' or 'matalel' is totally unacceptable in front of Jesus. If you are against Ethiopian Orthodox church, refuse it directly. But, you are doing what Satan is doing , Satan changes his character according to the environment. Some times you wrote by supporting some Archbishops, on other days you criticize them and you start insulting our fathers and our church.
  As you know you do not have any thing that makes you Orthodox christian. Orthodox Christianity is not by birth, it is by FAITH. There are Christians in Egypt, Syria, India, Armenia, Eritrea but they are not Ethiopians. Since you are an Ethiopian you might not be an Orthodox christian since you need to accept the DOCTRINES of Orthodox Church.
  Please stop writing unnecessary literature on your blog and let alone our church and our fathers in the name of Jesus Christ, our Lord.
  Zemekane Eyesus

  ReplyDelete
 17. ኧረ ተው!ምነው ዕኮ? መስተዋል ያለበት ሊስተዋል ይገባ ነበር ያም ባይሆን ለማስተዋል መሞከር ጨርሶ ግን
  (ሾላ በድፍኑ)ባልሆነ መንገድ መደናበር፤ እናም ማቅን ከሰይጣን ጋር ማነጻጸር የማይሆን ነገር ነው፤
  ሰይጣን ዕኮ ሥርዓት አለው በፈጣሪ ቁጥጥር ውስጥ ነው ሲንቀሳቀስም ፈቃድ ተቀብሎ ይንቀሳቀሳል፤
  ኢዮ 1.6---13 ማቅ ለባሾች ግን ከጨለማው ዓለም ገዥ አራት ኪሎ የንግድ መሠረቱን 1.ጢሞ 6.5-6 ጥሎ በቅዱሳን ስም በራሱ የሥልጣን ጥም የሚንቀሳቀስ ምድራዊ ኃይል ነው እና ምኑን ከምን
  ሰዎችን ከመናፍስት መናፍስትን ከስዎች መለየትና ማተት ይገባል አለዚያ ግን ገደል ይከታል፤

  ReplyDelete
 18. ayi paster lemehonu enanten sile ethiopia bete kirstiyan men tawukalachuna new yemtawerut sile erasachiw atawerum ende yigermal

  ReplyDelete
 19. የወንጌል ተከታዮች የሆናችሁ በያላችሁበት በርቱ ምንጊዜም የሚድኑ ወገኖች አንድ አንድ እያሉ ስለሚገኙ ተስፋ ሳንቆርጥ ስለእውነተኛው አዳኝ በመንፈስ እንትጋ እንደአእውነቱ ከሆነ ወንጌል በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተቀብሯል ምንኩስና እና ጵጵስና ነግሷል እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ እናነግሣለን

  ReplyDelete
 20. Let me first make clear myself that although I am one of the followers of the Church (not conservative), I do not have any detail and credible information you people are writting and discussing about.But, I am one of the very genuinely concerned followers about the very serious challenges the Church faces. And I want to argue that even if the level of wrong doings considerably varies , I do not believe that there is an individual or group especially of the clergy is blameless and totally free from responsibility and accountablity. Yes, I strongly argue that the Synod in Addis Ababa led by Aba Pawulos has the biggest and the worst share of religious scandal. I do not think I need to go far or do some research to proof this as the terrible wrong doing committed for the last 20 years speak for themselves. And I am not convinced by an arguement which praises some members of the Synod as if they are not part of the notorious problem simply because they might have been personally attacked by the very inner circle of Aba Pawulos.

  As far as Mahibere Qedusan ( I do not know if there is such kind Mahiber in the real sense the term) concerned, I am sorry to say but I have to say that it sounds that the very trend of this type of move is creating its own religious mini-empire led by junior princes or big fishes aspiring the occupation and omination of small pool. This grouping is trying to promote the very introverted interest of its top leaders and their submissive subordinates ( not the majority) under the pretext of preserving major religious traditions and making some sort of reformation. I do not believe the very idea of this grouping which preaches the very ugly theory of making itslef the rescuer of the Church ,or the tendency that has no room for tolrerance and reconcliation is desirable. Let me hope anyway that things will change for the better!!

  Concerning the Synod in exile, I want to say that although there are credible reasons to have some level of sympathy to its cause, it is wrong and undesirable not to be critical about mistakes it makes, especially its terrible weaknesses in handling the problems among the clerymen under its structure, if not with in itself.

  Another grouping which claims being nuetral (very absurd riligious identity ) is one of the distructing and misleading factors. It is absolutely nonsensical to try to convince the innocet followers of the Church that this group does not agree with Aba Pawulos and his inner circle but it does accept the Synod .This really sounds very silly and disingenous .

  Tha last but not least important factor for the problem the Chucrch is experiencing is the followers themselves . I do not know how it is possible to get a real sense of spiritual satifaction if the followers contiune to go Church regulary or wotherwise and OK with the culture of considering beibg critical not only wrong or taboo but serious sin punishable with serious consequences.

  Simply put, the challenges the Church is contiuning to encounter cannot be atributed to a particualr individual or grouping .It is more complex and multi-facated . Does the degree of contribution vary ? Absolutely yes!! What I AM SAYING IS THAT OUR ANALYSIS OF THE PROBLEM AND SUBSEQUENTLY OUR SEARCH FOR SOLUTION DESPERATELY NEEDS HOLISTIC OR COMREHENSIVE APPROACH!!!

  May God help us!!

  ReplyDelete
 21. Behold,wolves in sheeps'clothing are tending to make the pure values of ethiopian orthodox tewahido church vanish in to air.the truth is that MK is realy devoted to put a kibosh on the bad plans of tehadiso menafikans.thanks to God who organize MK.

  ReplyDelete