Monday, June 4, 2012

መምህር ዘበነ ለማ መመሪያ አክብሮ እንዲሠራ ደብዳቤ ተጻፈለት

(ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት)

የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነውንና ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተሰጠውን መመሪያ ጥሰዋል ያለፈቃድም ሰብከዋል በሚል ለመምህር ዘበነ ለማ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተጻፈ። ደብዳቤውን የጻፈው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሲሆን፣ ዘበነ መኖሪያውን በአሜሪካ ቢያደርግም በእናት ቤተክርስቲያን ውስጥ እያገለገለ ለመሆኑ የሚያስረዳ ደብዳቤ በአሜሪካ ከሚገኘው ሀገረ ስብከት ይዞ መምጣት ሲገባው እርሱ ግን ያለ ፈቃድ እየተዘዋወረ በመስበክ የስብከተ ወንጌል መምሪያ ውሳኔዎቹን ለማስፈጸም በሚያደርገው ጥረት ላይ አፍራሽ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ደብዳቤው ገልጾ፣ ከዚህ በኋላ ከሚኖርበት ሀገረ ስብከት በእናት ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ካላመጣና እንደለመደው እሰብካለሁ ቢል ለሚመለከተው አካል ሪፖርት በማድረግ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾአል።


መምህር ዘበነ ነዋሪነቱን በአሜሪካ አድርጎ ከሁለቱም ሲኖዶሶች ውጪ ነኝ በሚል በገለልተኛነት የሚኖር ሲሆን፣ እንዲህ ያደረገውም ወደ አገር ቤት ብቅ እያለ በስብከተ ወንጌል ስም ቢዝነሱን የሚሰራበት በር እንዳይዘጋበት ሲሆን፣ በሌላም በኩል በውጪ ያለው ዳያስፖራ ማህበረሰብ ደግሞ ከአገር ቤቱ ሲኖዶስ ጋር ነው የሚሰራው እንዳይለው በማሰብ ነው።

ዘበነ በአገር ውስጥና በውጭ አገር አክራሪነትን የሚሰብክና ክርስቲያኖች ተቻችለውና ተከባብረው እንዳይኖሩ የሚያደርጉ ርእሶችን በማንሳት፣ በስብከት ንግድ ለመክበር የሚሠራ ሰው እንደሆነ አሜሪካ ውስጥ በሬዲዮ ከሚያስተላልፋቸው ፕሮግራሞችና አልፎ አልፎ ከአሜሪካ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገባቸው ገበያ ተኮር ርእሶች፣ በአገር ውስጥም የሚያገኛቸው አንዳንድ በመለያየት ላይ የሚያጠነጥኑ ርእሶች ምስክር ናቸው። ዘበነ የወንጌልን ዓላማ ስላልተረዳና እንዲረዳም ስለማይፈልግ፣ ይሸጥልኛል ብሎም ስለማያስብ እስካሁን የወንጌልን እውነት የሚገልጥ የቪሲዲም ሆነ የካሴት ስብከት አላቀረበም።

ዘበነ በትምህርት ቤት ሳለ የስብከት ዘዴ የሚያስተምሩት የነበሩት የእህት አብያተ ክርስቲያን መምህር የትምህርቱ ይዘት ተማሪዎቻቸው ምን ያህል እንደገባቸው በሚገመግሙበት የሙከራ ስብከት ጊዜ ገና ስብከቱን ሲጀምር እየጮኸ ስለሚያስቸግራቸው ስብከት ጩኸት አይደለም እያሉ የሙከራውን ስብከት እያቋረጡ ያስቆሙት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። አዋቂ ነኝ ከሚል እሳቤ ውጭ መማር የሚፈልግ ማንነት ስለሌለው አሁንም ስብከት ካልጮኸ የማይደምቅ እንደሚመስለው የሚታይ እውነት ነው።

ዘበነ ከማን እንደተማረውና ከየት እንዳገኘው ባይታወቅም ክብርን ለራሱ በማከማቸት የሚታወቅ ሲሆን ከአሜሪካን ሲመጣ ለሚያውቃቸው ሰባኪያን እየደወለ ልመጣ ነውና ቀሚስ ለብሳችሁ ተቀበሉኝ በማለት እየደወለ በመጥራት የታወቀ ሰው ነው። ለስብከት ከቦታ ቦታ ሲዘዋወር ያለ አጃቢ የማይዘዋወር ሰው መሆኑ አላማው ምንድን ነው? የሚያሰኝ ነው። በአንድ ወቅት ከአሜሪካ ሲመጣ ከስብከት በኃላ እንደ ዘፋኝ እየፈረመ ረዥም ጊዜ ይወስድ እንደነበር የምናስታውሰው እውነት ነው።

አላማው ሕዝቡ እውነትን እንዲያውቅ ሳይሆን፣ እርሱ የሚያውቀውንና ሁሌ ከአፉ የማይለየውን “አውሬው” የሚለውን ስም ብቻ እንዲያጠናና በስጋት እንዲሞላ ለማድረግ ነው። ይህም ፍሬ አልባ ትምህርቶቹ የሚጠቀምበት እውነቱ ያልገባቸውና እንደዘበነ ያሉ ጆቢራዎች ያቀረቡላቸው ሁሉ እውነት የሚመስላቸው ወገኖች ገዝተው የእነዘበነን ኪስ እንዲሞሉና እነርሱ ግን የወንጌሉ ዓላማ ሳገባቸው እንዲሁ ስለ ልዩነት ብቻ በማሰብ በእነርሱ ጉንጭ አልፋ ክርክር ውስጥ ጠፍተው እንዲኖሩ ለማድረግ ነው።

የወንጌሉን ዓላማ ከተረዱ ግን የእነርሱን የተሳሳተ አስተምህሮ እንደማይቀበሏቸውና የስብከት ገበያቸው እንደሚቀዘቅዝ  ስለሚያውቁ፣ ሁሌ ስለመለያየት በሚሰብክ አመለካከት ስለተጠመዱ፣ የዕውር መሪዎች መሆንን መርጠዋል። በእውነትም ለሕዝቡ የወንጌል እውነት ማለትም «የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።» (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡4) ተብሎ እንደተጻፈው ሰይጣን ብቻ ሳይሆን ለሆዳቸው ያደሩ አንዳንድ ሰባኪዎችም ለጥቅማቸው ሲሉ ሕዝቡን ማሳታቸውን በመቀጠላቸው የስብከተ ወንጌሉ መመሪያ ተግባራዊ መሆኑ ጠቃሚ ነው።

67 comments:

 1. ይህ ደብዳቤ ስለምን ለፌደራል ፖሊስ በግልባጭ ሳይላክ? ረስተውት ስለሆነ እባካችሁ ንገሩልን። ለፌደራልፖሊስ፤ ለአዲስ አበባ መስተዳድር እና ለጠቅላይ ሚነስቴር ቢሮ ግልባጭ ቢደረግ ጥሩ ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ere lelam yikeral CC yemidereglachew le'Aba Fanuel, le'Hailegiorgis, le'Enqubahry, Aba Selama blog, Deje Selaaaaaaam mafia, Awdemihiret, Bete Paulos ena le'Bonke kiletamu sayilak bemekretu qir bilognal.
   Libeluat yasebuatin amora
   simuan yiluatal jigra

   Delete
  2. Ere lelam kertoal cc yemedereglachew: le "Seol", lemedrawiw geze Diabilos,le protestant churches, Wozete.

   Yegermal! beka hulun neger lemen bebego atayutem aba selamoch! Hulgezie kefu neger selemen tetsefalachehu? selemen yesewechen wudeket temegnalachehu? Egzeabehare Lebona yestachehu.

   Delete
 2. የምቀኛ ወሬ ነው እንደ ዘበነ የሚሰብክና ቤተ ክርስቲያንን የሚረዳ የለም አንተ ተመቅኝህተው እንጂ በትምህርት ቤትም ቢሆነ ጎበዝ ተማሪ ነው እንደ አበደ ውሻ እያነፈነፍክ ሰውን ትለክፋለህ እግዚአብሔር ይገስጽህ ያላወቅንህ አይምሰልህ አንድ ቀን እንደ ወዳጅህ ዲያብሎስ እራቁትን ትቆማለህ

  ReplyDelete
 3. የደብዳቤው ምልዕክት በትምህርትህ ላይ ህጸጽ ተገኝቶብሃል አይልም ፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክህነትን ጠብቅልንና አስተምር የሚል ነው ፡፡ አማርኛውም እንደ ባዕድ ቋንቋ የሆነባችሁ ይመስላል ፡፡ አንድ ወደሚጠበቅ መሥሪያ ቤት ሲገባ በዘበኛ ተፈትሾ ሁሉም ሰው ይግባ ቢባልና ቢታወጅ ፤ ሳይፈተሽ የገባ ቢገኝ ለወደፊቱ ህጋችንን ጠብቀህ እንድትገባ እንጅ አትግባ እንዳልተባለ ነውና ለመምህሩ የተጻፈለት ደብዳቤ ክፋት የለውም ፡፡ ያልሆነ ፣ ያልተባለ ነገር እየደመራችሁ ፣ የስሜታችሁን እየመረቃችሁ ወሬ አትፍጠሩ ፡፡

  ReplyDelete
 4. aye aba selama ahun zebenen yejemerachut tehadesochen magalete bemjemeru new!zebene,kidus sinodosen yemyakeber new!enante lematalate atmokru!!!

  ReplyDelete
 5. ግን አንተ - ባለ ብሎጉ ሰው ነህ (ኦርቶዶክስ ነህ አላልኩም)

  ReplyDelete
 6. Shame on deje selam..today you forgot mentioning about mahibere kidusan..elelelele

  ReplyDelete
 7. የነዘበነ ጊዜ እያከተመ ነው። የነ ፊደል ገደሉ ለብ-ለብ ሰባኪያን ጊዜ እያበቃ ነው። የዛሬ አያርገው እና በየስቴቱ እነሱ የሌሉበት ንግስ እማይታሰብ ነበር። ዛሬ ምእመኑ በካድሬዎችና በሊቃውንት መካከል ያለው ልዩነት እየገባው እሚጠሩበት ደብር በቁጥር ነው። አገር ቤት ሂዶ በእንተ ጳውሎስ እዚህ መጥቶ በእንተ ገለልተኛ እያሉ ለሁለት ጌታ ማደር ያሳፍራል። ክርስትና "ኦፕሽናል" የሚባል ነገር የለውም። "እመኒ እወ ወእመኒ አልቦ" ብቻ ነው። ሕርያቆስ

  ReplyDelete
  Replies
  1. የእናንተ ጊዜ ጊዜ እያከተመ ነዉ፡፡ ፈስ ያለበት ዝሊያ አይችልም እንዲሉ የምትረጨዉን የክህደት መርዝ ቀሲስ ዶ/ር ዘበነ ለማ እግዚአብሔር ብርቱ ኃይል በማድረግ ስላከሸፈ የሚትመልሰዉ መልስ ስለጠፋብህ በተቆረጠ ተስፋ ምላስህን ባታስረዝም ጥሩ ነዉ፡፡ ወሬ በመልቀምና ስም በማጥፋት የመቴ እንጂ የጸደቀ የለምና የሰዉን ሥም ዝም ብለህ አታጥፋ፡፡ ማህበራዊ ድረ ገጽህ ሥራ ካጣ የኮሜዲያን መጫወቻ አድርገዉ፡፡

   Delete
 8. እንዴት አንድ ወንጌላዊ ለ10 ዓመት ሙሉ በአሜሪካ ምድር ላይ ስለ ጴንጤና ስለ "አውሬው" በMediaና በመድረክ ላይ ቆሞ ይናገራል? የቤተክርስቲያንስ ዋና ዓላማዋ ስለ መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መመስከርና መስበክ አይደለምን?

  ጌታችን "ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ" እንዳለ it is so apparent the moment you walk in his weekly Monday sermon, no kind of spirituality exists. One person told me all the people at Zebene's program sitting on the front rows are the same people at Babylon nightclub at the dance floor. This is because his teaching is solely based on slandering Protestants and he is famous for attacking a straw man. I have stopped my own sister from attending his sermon because I realized he is committed with passion to brainwash people and to lead people astray; and eventually have asinine thoughts.

  Also about the Mother of Our GOD, the Virgin Mary. Those who attend his congregation say some non biblical stuff to come to their skewed conclusion concerning the Virgin Mary. He says, well before the annunciation, the Virgin knew she was going to bore the son of GOD. That is the most unbiblical and baseless teaching. I have asked church fathers and none of our fathers taught such dogma. This is Minfikina!!

  Off all the people Mahibere kidusan labeled "tehadiso", I wonder why they are so reluctant to label him so. In my personal opinion, Mk and Zebene are two complete opposites; Zebe is just fame starved individual unlike anyone else in our church. At least MK has good intentions; but we all know where good intentions lead to. "ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን የሞት መንገድ ነው።" ምሳሌ 16:25 እንደተለዉ ሆኖባቸው ነው።

  Anyway, lehulachinim mastewalun Yadilen

  ReplyDelete
 9. zebe yetert abat ye filifilu wondem zemnehe tefesem

  ReplyDelete
 10. menden new alamachu

  ReplyDelete
 11. ዓላማችሁ ምንድነው? ላልከው ጠያቂ!
  የዚህ ጽሁፍ ዓላማ ውሸታም ሰባኪያን ህዝቡን እንዳያሳስቱትና ገደል ይዘው እንዳይወርዱት ማንቃት ነው። እነ አይፈራም ጋሜና እነ ጭራቅ መጣልህ ሰባኪያን ወንጌሉን ለሚመግቡ መንፈሳዊያን መንገዱን እንዲለቁ ነው። በመሰረቱ ዘበነ ቅስና የተቀበለው በሌለው ዲቁና ሲሆን ያንንም ቅስና ከስንት ጉድ በኋላ የተቀበለው እዚሁ አሜሪካ ስንት ጳጳሳት እየነበሩለት ኢየሩሳሌም ወርዶ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በ112 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በቅርቡ ካረፉት ከአቡነ አብሳዲ እጅ ሲሆን ይህም ከእርጅናቸው የተነሳ ማን ምን እንደሆነ መርምረው በማያውቁበት ደረጃ ላይ አንድ የቅርብ ወዳጃቸውን በመንተራስ አሳስቶ እንደሆነ ይታወቃል። ከፈለጋችሁ የዘበነን ቅስና ወረቀት ተመልከቱ! የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ እያሉ በእርጅና ከደከሙ ጳጳስ መቀበል የፈለገው ለምድነው? የት ነህ? ምን ተምረሃል? ምን ታውቃለህ? ዲቁና ከማን ተቀበልክ? የት የት ቤተመቅደስ ቀደስክ? ስንት ዓመት አገለገልክ? «አሐዱ አብ ቅዱስ» «ለከ እግዚኦ ለገባሬ ኩሉ» በዜማ ሳይፈተን ሳይል ቅስና እንደሌለ ስለሚያውቅ ሳይፈተን ቅስናውን አወጀ። ለዘራፍ ትምህርቱ ደረቱን ነፋ።

  ReplyDelete
 12. http://www.wust1120.com/Audio/Demtse%20Tewahedo.mp3
  Please listen to ዘበነ about Male circumcision at 49 minutes 51 seconds. He said it is our religion and we must perform Male circumcision at the 8th day. He quoted from the bible and said it is God's commandment and he gave good examples like (people who don't believe Jesus as the son of God) are doing Male circumcision at the 8th day. Based on his teachings and answers to listener's question, our Tewahdo Haimanot still believes Male circumcision at the 8th day as one of the requirement to be a good Tewahdo Christians. He is not only against the current Holy Synod Decision but also he is against the first Holy Synod decision (that was attened by st. Paul, St. Peter, St. James and all the deciples.

  The bible teaches us

  "Some men came down from Judea to Antioch and were teaching the brothers: "Unless you are circumcised, according to the custom taught by Moses, you cannot be saved." Acts 15:1

  (please note that in our generation those "Some men" are ዘበነ and his followers. If you forgot the first synod's decision here it is read it. Sometimes it is good to learn as well.

  "Then the apostles and elders, with the whole church, decided to choose some of their own men and send them to Antioch with Paul and Barnabas. They chose Judas (called Barsabbas) and Silas, men who were leaders among the believers. 23 With them they sent the following letter:

  The apostles and elders, your brothers,

  To the Gentile believers in Antioch, Syria and Cilicia:

  Greetings.

  24 We have heard that some went out from us without our authorization and disturbed you, troubling your minds by what they said. 25 So we all agreed to choose some men and send them to you with our dear friends Barnabas and Paul— 26 men who have risked their lives for the name of our Lord Jesus Christ. 27 Therefore we are sending Judas and Silas to confirm by word of mouth what we are writing. 28 It seemed good to the Holy Spirit and to us not to burden you with anything beyond the following requirements: 29 You are to abstain from food sacrificed to idols, from blood, from the meat of strangled animals and from sexual immorality. You will do well to avoid these things.

  Farewell"

  Acts 1:51-29

  ReplyDelete
  Replies
  1. God bless you my friend for providing a source. I sometimes doubt if he even believes on the Gospel Of our Lord. He is always preaching about the Jewish dietary law and how it is a mandatory for Christians to follow it. But in doing so, he is rejecting the apostles' teaching and our church's dogma.

   Delete
  2. መምህሩ ስለ ግርዛት መልስ ከመስጠቱ በፊት ያስተማረው ፣ ማለትም ስለ ምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ፣ በተለይም ደግሞ ስለ መንፈስ ቅዱስ የገለጸው ፣ ርሱን ልንመዝንበት የሚገባ የእምነታችን መሠረት ነው ፡፡ በሰጠው ትምህርት ልሳን ተናገርን እያሉ ምንም በማያውቁ ወገኖች መሃል የራሳቸውን ልዩ ቅዱስነት ለማሳየት ፤ በባልደረቦችም መሃል ክብርን ለማግኘት በዝንጀሮ ዓይነት አንደበት የሚንተባተቡብንን በመቃወም ፣ በመንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው ልሳን ማለት ምን እንደሆነ አስረድቷል ፡፡ ይኸንኑ የመሰለ ትምህርትም ከዚህ ቀደም በአባ ወልደ ትንሣኤ ተሰጥቶ አድምጨ ነበርና የሁለቱም አንድ ዓይነት ትንታኔ በመሆኑ አስደስቶኛል ፡፡ ወዳጄንም ይህን የገጽ መክፈቻ አድራሻ በመለጠፍህ ፣ አንተንም በጣም አመሰግንሃለሁ ፡፡

   ከዛ በተረፈ ካስተማረው ርዕስ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ፣ የጠያቂውም ዜግነትና ሃይማኖት በግልጽ ባልታወቀ ሁኔታ ስለግርዛት በትውፊት ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ መገኘትና ከባህል አንጻር ለቀረበለት ጥያቄ ፣ የግርዛት ትእዛዝ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሚገኝ ለማስረዳት ምዕራፉን ጠቅሶ አንብቧል ፤ በመቀጠልም የአይሁድ ልማድ እንደሆነም ገልጿል ፤ ባህል መሆኑንም በአጭር ቃል ተናግሯል ፡፡

   ለራሴ ጠያቂውን እንዲያውም የቤተ እሥራኤል ሰው /ፈላሻ/ ፣ ወይም በእሥራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ አድርጌ ነው የገመትኳቸው ፡፡ ምክንያቱም መምህሩ በሚመልስበት ወቅት መውጫውን አያውቁ እንደሁ ለማሳየት በሚመስል ፣ አይሁዶችም ይህንን ትእዛዝ ስለሚጠብቁ የሚል ማስረጃ ጠቅሶላቸዋል ፡፡ እዚህ ላይ ለማስረዳትና ለመፍታት የሞከረው ማኀበራዊና ባህላዊ ችግርን ከእምነት በማጣመር ነው እንጅ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚታመነውን የትንታኔ ትምህርት በመስጠት አይዶለም ፡፡ ሰውየው የማስገረዝ ዓላማ ስለ አላቸው ይመስላል ፤ ያንን የተጠራጠሩትን ቃል ፣ ምን ማስረጃ ጠቅሰው መፈጸም እንደሚችሉ ለመርዳት እንደሞከረ ገምቻለሁ ፡፡

   በተረፈ መምህሩን ለመፈተን ታስቦ የተወረወረ ደንጊያ ከሆነ ፣ ጥያቄው እንደ ግለሰብ ችግር ሳይሆን ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስለ ግርዛት የምታምነውና የምታስተምረው ምንድር ነው ተብሎ በግልጽ መቅረብ ነበረበት ፡፡ መገረዝ አለመገረዝ የሚለውን ትምህርት ለምን አልሰጠም ከተባለ ፣ ሁሉን ለመተንተንና ለማስረዳት ከአንድ ደቂቃ በላይ ያስፈልግ ነበር እላለሁ ፡፡ ጠያቂው ጥርጣሬን ካዘለ አገላለጻቸው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ቃል መስሏቸው የጠየቁ ዓይነት መስሎት የመለሰ መስሎኛል ፡፡

   ይህን አስተያየት ልሰጥ የተገፋፋሁት የመጽሐፍን ቃል ከአንዳንዶቻችንም በእጅጉ የሚገነዘበውን ሰው ፣ ምንም መጽሐፍ እንደማያውቅና ይህን ቀላሉን ጥያቄ ተሳስቷል በመባሉ ነው ፡፡ የጳውሎስ ትምህርት ላልተገረዙት አሕዛብ ፣ የጴጥሮስ ደግሞ ለተገረዙት አይሁድ ማለትን እኔም ደካማው አውቃለሁ አንኳን ዝርዝሩን መስጠት የሚችለው ሊቅ ፡፡ እንዲያውም ከተረዳነው ስለመገረዝና አለመገረዝ ማስተማር የክርስትናችን ትምህርት መለኪያም አይዶለምና የእሱን የሃይማኖት ዕውቀት መመዘኛ ማድረግ አይገባም ፡፡ ወዶ ፈቅዶ የሚገረዝ እንደ አለ ሁሉ ፣ በተለያየ ምክንያት አለመገረዝን የሚመርጥም አለ ፡፡ ሃይማኖትን ሳይንተራሱ ከብዙ መገረዝን ከሚያስገድዱ ምክንያቶች በተጨማሪ ፣ እንዲያውም አሁን የብልት ካንሰርን ለመከላከልና ለንጽህና ሲባል ፣ ግርዛት በዘመነኞችም እየተደገፈ መጥቷል ፡፡ ስለተገረዙ ብቻ ክርስቲያን ሆነዋል ስለማይባል ፣ ያልተገረዘ ሰው ካገኘህ ከእምነት አንጻር ባይሆንም ምክርህን ለግሳቸው ፡፡

   ከሞላ ጐደል የውይይታቸው ቃል በጽሁፍ እንዲህ ይነበባል ፡
   የጠያቂ ቃል ፡- የኔ ጥያቄ ምንድ ነው ስለግርዛት ነው ፡፡ አይ ቲንክ ወንድ ልጅ ከተወለደ በኋላ በሰባተኛው ቀን እንዲገረዝ ትውፊታዊ ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት ነገር አለ መሰለኝ ፡፡ እና እዚህ አገር ግን ሲወለዱ ነው ግርዛት የሚደረገው ፡፡ እና ይኸ እንዴት ነው ከባህላችንና ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ?

   መምህር ዘበነ ፡- እሺ በመጀመሪያ ያው ቀኑ ሰባት ቀን ከተፈጸመ በስምንተኛው ቀን ላይ ነው ፡፡ ዘፍ 17፡ ከቁጥር 9 ጀምሮ ያለው ቃል እንዲህ ይላል …… ይነበባል
   ስለዚህ ይሄንን ቀኑ ስምንተኛው ቀን ነው ፡፡ በሆስፒታል በሚወለድበት ጊዜ ማነጋገር ይቻላል ፡፡ አይሁዶችም ይህንን ትእዛዝ ስለሚጠብቁ እነርሱም በዚህ ቀን ስለሚያደርጉ አነጋግሮ ማድረግ ይቻላል ፡፡ ያለው ጉዳይ የኢንሹራንስና የተለያዩ ነገሮች ነው ፤ ግን ባህላችንን ማስረዳትና ግን እምነት ነው ፡፡ እምነታችንንም መግለጽ ያስፈልጋልና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ፡፡ በዚህ መልክ እድርጎ ማድረግ ይገባልና በስምንተኛው ቀን ላይ ቢሆን ይገባዋል ፡፡
   ጠያቂ ፡- የግድ ነው ፤
   መምህር ፡- የግድ ነው ፡፡

   Delete
  3. ኧረ ጐበዝ ይሄ ቃል ስለምን ምክንያት ተብሎ ይታፈናል ? ለሦስተኛ ጊዜ እየተብራራ መቅረቡ ነው ፡፡
   "http://www.wust1120.com/Audio/Demtse%20Tewahedo.mp3"

   በተመለከተው የድረ ገጽ መስኮት መክፈቻ ፣ መምህሩ ስለ ግርዛት መልስ ከመስጠቱ በፊት ያስተማረው ፣ ማለትም ስለ ምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ፣ በተለይም ደግሞ ስለ መንፈስ ቅዱስ የገለጸውን ፣ ርሱን ልንመዝንበት የሚገባ የእምነታችን መሠረት ነው ፡፡ በሰጠው ትምህርት ውስጥ በልሳን ተናገርን እያሉ ፣ የልሳን ምንነትን በማይረዱ ወገኖች መሃል ፣ የራሳቸውን ልዩ ቅዱስነት ለማሳየትና ፤ በባልደረቦች መሃልም እንደ ትንቢት ተናጋሪዎች ያህል ፣ የልሳን ተናጋሪነት ክብርን ለማግኘት ሲሉ ፣ የዝንጀሮ አንደበትን ዓይነት በመሰለ (ቡክም ባኩም ቂርቅ ቃርቅ…በማለት) የሚንተባተቡትን በመውቀስ ፣ በመንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው ልሳን ምን ማለት እንደሆነ አስረድቷል ፡፡ ይኸንኑ የመሰለ ትምህርትም ከዚህ ቀደም በአባ ወልደ ትንሣኤ ተሰጥቶ አድምጨ ነበርና የሁለቱም አንድ ዓይነት ትንታኔ በመሆኑ አስደስቶኛል ፡፡ እግረ መንገዴን ወዳጄንም ትንሽ ስለተማርኩበት ይህን የገጽ መክፈቻ አድራሻ በማሳወቅህ ፣ አንተንም በጣም አመሰግንሃለሁ ፡፡

   ከዛ በተረፈም ካስተማረው ርዕስ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ፣ የጠያቂው ዜግነትና ሃይማኖትም በግልጽ ባልታወቀበት ሁኔታ ውስጥ ግርዛትን በተመለከተ በትውፊት ፣ የቃሉን በመጽሐፍ ቅዱስ መገኘትና ከባህል አንጻር በተዛመደ ለቀረበለት ጥያቄ ፣ የግርዛት ትእዛዝን የት መጣን ለመመለስ ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደሚገኝ ለማስረዳት መጽሐፉንና ምዕራፉን ጠቅሶ አንብቧል ፤ በመቀጠልም የአይሁድ ልማድ እንደሆነም ገልጿል ፤ በማከልም ባህል እንደሆነም በአጭር ቃል ተናግሯል ፡፡

   ለራሴ ጠያቂውን እንዲያውም የቤተ እሥራኤል ወገን /ፈላሻ/ ፣ አለያም የአይሁድ እምነት ተቀባይነት ባገኘበትና በተለመደበት አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ አድርጌ ነው የገመትኳቸው ፡፡ ምክንያቱም መምህሩ በሚመልስበት ወቅት ፣ መፍትሄውንና ስልቱን አያውቁ እንደሁ ለማሳየት በሚመስል ፣ አይሁዶችም ይህንን ትእዛዝ ስለሚጠብቁ የሚል ማስረጃ ጠቅሶላቸዋል ፡፡ እንደገባኝ እዚህ ላይ ለማስረዳትና ለመፍታት የሞከረው ፣ ግለሰቡ ህጻን ማስገረዝ ፈልገው ያጋጠማቸውን አካባቢያዊ ችግር እንዴት እንደሚያስወግዱ መፍትሄውን ከማኀበራዊ ፣ ባህላዊና ከእምነት ውስጥ በማፈላለግ ለመርዳት ነው እንጅ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚታመነውንና የሚሰጠውን ትምህርት ለመተንተን አይዶለም ፡፡ ማለቴም ሰውየውን የማስገረዝ ዓላማ እንዳላቸው በመቁጠር ፣ የህጻናት ግርዛት ባልተለመደበት የውጭ አገር /የአብዛኛው መጤዎች ችግር ስለሆነ/ በምን ብልሃትና ፣ ምንን ምክንያት በማድረግ ግርዛትን እንደሚያስፈጽሙ ፣ ምን ማስረጃ ጠቅሰው ማሰራት እንደሚችሉ መንገድ በማሳየት ለመርዳት እንደሞከረና የተጠራጠሩትንም ቃል ከመድሐፍ እንደገለጸ ገምቻለሁ ፡፡ ሌላው ማኀበራዊ ችግርን ለመፍታት የሚያስመስለውም ስለኢንሹራንስና ስለሌሎችም ችግሮች በማለት መጥቀሱ ነው ፡፡

   ከዚህ ባለፈ መምህሩን ስለሃይማኖት የሚያስተላልፈውን ቃል ለመመዘን ታስቦ የተወረወረ ፈተና ከሆነ ፣ ጥያቄው እንደ ግለሰብ ችግር ሳይሆን ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ወይም አንተ ራስህ ስለ ግርዛት የምታምነውና የምታስተምረው ምንድር ነው ተብሎ በግልጽ ቋንቋ መቅረብ ነበረበት ፡፡ መገረዝ አለመገረዝ የሚለውን ትምህርት በመምህርነቱ ስለምን ከራሱ አፍልቆ አልገለጸም ከተባለ ፣ ሁሉን ለመተንተንና ለማስረዳት ከተመደበለት ከአንድ ደቂቃ የአየር ጊዜ በላይ ስለሚያስፈልግ ነው እላለሁ ፡፡ ጠያቂው የግንዛቤ እጥረትን ካዘለ አነጋገራቸው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለ ቃል መስሏቸውም ለማጣራት የጠየቁም ዓይነት ስለሚመስል ፣ ከዚሁ አንጻር ብቻ የመለሰላቸው ይመስላል ፡፡

   ይህን አስተያየት ልጽፍ የተገፋፋሁት ፣ የመጽሐፍን ቃል ከአንዳንዶቻችንም በተሻለ የሚገነዘበውን ሰው ፣ ምንም መጽሐፍ እንደማያውቅና ይህን ቀላል ጥያቄ እንደ ተሳሳተ በመቁጠር ትችት በመቅረቡ ነው ፡፡ የጳውሎስ ትምህርት ላልተገረዙት አሕዛብ ፣ የጴጥሮስ ደግሞ ለተገረዙት አይሁድ ማለትን እኔም ደካማው ሰው እንኳን አውቃለሁ ፤ እንኳንስ ዝርዝር ምክንያትን መስጠት የሚችለው የመጽሐፍ ሊቅ ፡፡ እንዲያውም ከተረዳነው ስለመገረዝና አለመገረዝ ማስተማር ፣ የክርስትናችን ትምህርት ተቀዳሚ ርዕስ አይዶለምና ለሃይማኖት ዕውቀትና ግንዛቤ መመዘኛና መለኪያ ማድረግም ቀድሞውንም አይገባም ፡፡ ወዶ ፈቅዶ የሚገረዝ እንደ አለ ሁሉ ፣ በተለያየ ምክንያት አለመገረዝን የሚመርጥም አለ ፡፡ ሃይማኖትን ሳይንተራሱ ከብዙ መገረዝን ከሚያስገድዱ ምክንያቶች በተጨማሪ ፣ እንዲያውም አሁን በዚህ ትውልድ የወንድ ብልት ካንሰርን ለመከላከልና ለንጽህና አያያዝ ሲባል ግርዛት በዘመነኞችም እየተደገፈ መጥቷል ፡፡ ስለተገረዙ ብቻ ክርስቲያን ሆነዋል ስለማይባል ፣ ያልተገረዘ ሰው ካገኘህ ከእምነት አንጻር ባይሆንም ምክርህን ለግሳቸው ፡፡

   ከሞላ ጐደል የውይይታቸው ቃል በጽሁፍ እንዲህ ይነበባል ፡
   የጠያቂ ቃል ፡- የኔ ጥያቄ ምንድ ነው ስለግርዛት ነው ፡፡ አይ ቲንክ ወንድ ልጅ ከተወለደ በኋላ በሰባተኛው ቀን እንዲገረዝ ትውፊታዊ ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት ነገር አለ መሰለኝ ፡፡ እና እዚህ አገር ግን ሲወለዱ ነው ግርዛት የሚደረገው ፡፡ እና ይኸ እንዴት ነው ከባህላችንና ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ?

   መምህር ዘበነ ፡- እሺ በመጀመሪያ ያው ቀኑ ሰባት ቀን ከተፈጸመ በስምንተኛው ቀን ላይ ነው ፡፡ ዘፍ 17፡ ከቁጥር 9 ጀምሮ ያለው ቃል እንዲህ ይላል …… ይነበባል
   ስለዚህ ይሄንን ቀኑ ስምንተኛው ቀን ነው ፡፡ በሆስፒታል በሚወለድበት ጊዜ ማነጋገር ይቻላል ፡፡ አይሁዶችም ይህንን ትእዛዝ ስለሚጠብቁ እነርሱም በዚህ ቀን ስለሚያደርጉ አነጋግሮ ማድረግ ይቻላል ፡፡ ያለው ጉዳይ የኢንሹራንስና የተለያዩ ነገሮች ነው ፤ ግን ባህላችንን ማስረዳትና ግን እምነት ነው ፡፡ እምነታችንንም መግለጽ ያስፈልጋልና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ፡፡ በዚህ መልክ እድርጎ ማድረግ ይገባልና በስምንተኛው ቀን ላይ ቢሆን ይገባዋል ፡፡
   ጠያቂ ፡- የግድ ነው ፤
   መምህር ፡- የግድ ነው ፡፡

   Delete
  4. I am glad you defended መምህር ዘበነ (or yourself, I feel like he is defending himself), but it better to defend the truth. The truth sets you free. This is a minor mistake መምህር ዘበነ did. I have a lot of false teachings he presented regarding our beloved church. It will be compiled and presented to the public in books or audio, in time God willing. Enough is Enough. By the way he is a generous man for providing a lot of false teaching in one radio program. He thinks everyone is like him and he thinks he is the only one for the church. Regarding the above argument, you still didn't get it and you wrote
   መምህር ዘበነ said "እምነታችንንም መግለጽ ያስፈልጋልና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ፡፡ በዚህ መልክ እድርጎ ማድረግ ይገባልና በስምንተኛው ቀን ላይ ቢሆን ይገባዋል ፡፡
   ጠያቂ ፡- የግድ ነው ፤
   መምህር ፡- የግድ ነው ፡፡

   when he said "እምነታችንንም መግለጽ ያስፈልጋልና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው"
   "እምነታችን" is it JUDASIM OR CHRISTIANITY?


   በዚህ መልክ እድርጎ ማድረግ ይገባልና በስምንተኛው ቀን ላይ ቢሆን ይገባዋል

   If you understand the word ይገባልና and በስምንተኛው ቀን ላይ ቢሆን ይገባዋል, it is a must according to እምነታችንንም መግለጽ ያስፈልጋልና.

   and he was given another chance ጠያቂ ፡- የግድ ነው? ፤
   መምህር ፡- የግድ ነው

   I am sorry መምህር you said again የግድ ነው. So when I wrote

   "Some men came down from Judea to Antioch and were teaching the brothers: "Unless you are circumcised, according to the custom taught by Moses, you cannot be saved." Acts 15:1

   (please note that in our generation those "Some men" are ዘበነ and his followers. If you forgot the first synod's decision here it is read it. Sometimes it is good to learn as well.

   I was not accusing ዘበነ falsely, I was just defending the truth and my mother church from false preachers like ዘበነ who doesn't even care about the word coming from their mouth. Next time try to think twice before you answer the questions and try to learn the truth with open mind and if you don't know the answer say I don't know (I know it painful for you) but try. By the way i don't listen to your radio unless i am in the car driving somewhere, I stopped listening when you said "our lady saint Mary already knew that she is going to be the mother of God before ark Angel st. Gabriel told her". i don't know where you get it. and That was it for me. It was too much.

   Delete
  5. for the writer it is good to defend someone but i don't know what you are trying to say
   Most of your points are irrelevant to the issue discussed for example
   ከዛ በተረፈም ካስተማረው ርዕስ ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው ፣ የጠያቂው ዜግነትና ሃይማኖትም በግልጽ ባልታወቀበት ሁኔታ ውስጥ (why you need የጠያቂው ዜግነትና ሃይማኖት)


   "መምህሩን ስለሃይማኖት የሚያስተላልፈውን ቃል ለመመዘን ታስቦ የተወረወረ ፈተና ከሆነ ፣ ጥያቄው እንደ ግለሰብ ችግር ሳይሆን ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ወይም አንተ ራስህ ስለ ግርዛት የምታምነውና የምታስተምረው ምንድር ነው ተብሎ በግልጽ ቋንቋ መቅረብ ነበረበት" If you really understand clear amaharic the question is simple and easy let me write it to you again, HERE YOU GO

   አይ ቲንክ ወንድ ልጅ ከተወለደ በኋላ በሰባተኛው ቀን እንዲገረዝ ትውፊታዊ ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት ነገር አለ መሰለኝ ፡፡ እና እዚህ አገር ግን ሲወለዱ ነው ግርዛት የሚደረገው ፡፡ እና ይኸ እንዴት ነው ከባህላችንና ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር

   NOTE THE WORDS "ትውፊታዊ ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት ነገር አለ መሰለኝ" THE answer was in the question and was simple and YES ትውፊታዊ ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት ነገር አለ.

   or ከባህላችንና ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር. It is መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት to Christians, it is not a must. I don't have to do it. I get baptized instead. so he made clear error and don't try to say ይህን አስተያየት ልጽፍ የተገፋፋሁት ፣ የመጽሐፍን ቃል ከአንዳንዶቻችንም በተሻለ የሚገነዘበውን ሰው ፣ ምንም መጽሐፍ እንደማያውቅና ይህን ቀላል ጥያቄ እንደ ተሳሳተ በመቁጠር ትችት በመቅረቡ ነው. He is a human being after all and makes mistake and as i promised when you get more evidence you will enjoy him how his teachings contradicts from TRUE TEWADHO'S teachings.
   peace

   Delete
  6. ማስገረዝ የሚያስችሏቸውን በቂ ምክንያቶች ፣ አሳማኝ ዝርዝሮችን ለመግለጽ ካልሆነ በስተቀር ፣ ግርዛት የክርስትናችን ሥርዓት ነው በሚል አልተረዳሁትም ፡፡ ግለሰቡ አልሞተምና ምናልባት ስለ ግርዛት ማወቅ ካስፈለገ ጥያቄ ሊቀርብለት ይችላል ፡፡ የመጽሐፍን ቋንቋና ትርጉም የሚረዳውን ሰው ይህን ግድፈት ፈጸመ ብዬ አልቀበልም ፡፡ ጠያቂውን ለመርዳት በማሰብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ፣ አይሁዳዊ እምነትና ሥርዓት መሆኑን ሁሉ ዘርዝሯል ፡፡ እምነታችንን መግለጽ ያስፈልጋል ብትባልና በክፍተት ቢተውልህ ከእምነትህ አኳያ አግባብ መልስ መስጠት የሚገባው አንተ ባለጉዳዩ ነህ ፡፡

   Delete
  7. God bless you my friend. Thanks for providing a source; and I can't wait to read the book or cd when it finally comes out.

   Delete
 13. geleltegnan maqreb yihe new ende. Teyakiew Papasun yimeleketal ayimeleketm?

  ReplyDelete
 14. በደብዳቤው የምትቆጡት በሙሉ ሕገ እንዳይከበር የምትፈልጉ ናችሁ፣ የሚገርመው እንዴት እንዴት እንደምታስቡ ለመረዳት አለመቻላችን ነው፡፡ ሕግ አክብሩ እምቢ፣ ሕገ ወጥ ናችሁ የሕግ ባለቤትና ምንጭ ከሆነችው ከቤተ ክርስቲያን ውጡና እዚያው በመለዳችሁበት ዝለሉ እምቢ እሽ ምን ትደረጉ፣ ወደ እስሳነት እንድትለወጡ መጸለይ አለበት እንደባሕርያችሁ፡፡ ጠቕላይ ቤተ ክህነቱ በርቱ ሕግ አስከብሩ

  ReplyDelete
 15. ዘበነ ጎበዝ ሰባኪ ነህ ግን ሕግ አክብር፣ ቤተ ክርስቲያን የምገድ ወንዝ አይደለችም ማንም እየመጣ ዘው ብሎ የሚጨፍርባት፣ እስከ አሁን የተጨፈረው የተዘረፈው ገንዘብ ይበቃል

  ReplyDelete
 16. don't bother he will preach us ( the 'geleltegna' churches ) until aba pawulos dies.

  ReplyDelete
 17. lezebene yemekere agelgelot yasfelegewal. zebaraki new

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ባለብሎግ አምላክ ይቅር ይበልህ እባክህ ቤ/ክያንን አትበጥብጥ ወሬህ ሁሉ የመናፍቅ ነው ተው ተው ...................

   Delete
 18. የማቅ ስም ያልተነሳበት የመጀመሪያ ክስ። አሁን ሰልፉ በመ/ር ዘበነ ላይ ነው። ምን ይሆን ባለሳምንት?

  ReplyDelete
 19. Hope you will share this to your readers:

  http://www.dejeselam.org/2012/06/blog-post_2818.html

  ReplyDelete
 20. ዘበነ በጣም አጸያፊ ንግግር ለመምሪያው እንደተናገርክ ታውቀዋለህ
  አሁን በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ የሕግና የሥርዓት መከበር ተምሳሌትና ተባባሪ ልትሆን ይገባል

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኢክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ተፈጽሞ ከሆነ ወይም ከተደረገ ትክክለኛ መልዕክት እንዲህ ነው ፡፡ በአካባቢው ኑረህ የታዘብከው ስህተትን ለራሱ ለባለ ጉዳዩ ከደረሰው ነግረኸዋል ፡፡ ለንስሃም መጋበዝህ ደግሞ ክርስቲያናዊ ነው ፡፡
   መልካም መንገድ ፡፡

   Delete
 21. ለመሆኑ ዘበነ አሜሪካን ሀገር ገለልተኛ ነኝ ብሎ እንደ ጴንጤ ቤተ ክርስያን የከፈተ ሰው አይደለም ወይ፡፡ ምን ሊሠራ ነው ኢትዮጵያ መጥቶ የሚሰብከው

  ReplyDelete
 22. ህግ ማስከበሩ መልካም ነው:: የብዙሃኑን ድጋፍም ያገኛል:: ነገርግን ሕጉ ለመምህር ዘበነ ብቻ መሆን የለበትም ከፓትርያርኩ ጀምሮ እስከጳጳሳቱ ጭምር እንጅ::

  ReplyDelete
 23. የደብዳቤው መልዕክት በትምህርትህ ላይ ህጸጽ ተገኝቶብሃል አይልም፡፡ ብለህ ላሰፈርከው ወገኔ ዘበነ የሃይማኖት ህጸጽ እንዳለበት ማወቅ ትፈልጋለህ? ከየትኛው ስብከቱ እንዳሳይህ ትፈልጋለህ? የፈለከውን የእሱን የስብከት ስራ ጻፍልኝና ህጸጹን ላስነብብህ
  ደቂቀ አቡዬ ነኝ

  ReplyDelete
 24. ደቂቀ አቡዬ በተዓምር ያልተጻፈ ወይም ለሰው የማይታይ ጽሁፍ ማንበብ ትችል ካልሆነ በስተቀር ፣ ተጻፈለት ተብሎ የቀረበልን ደብዳቤ ላይ ስለ ሃይማኖት ህጸጽ ምክንያት የሚናገር የለውም ፡፡ ከእኛ የተሰወረውን ረቂቅ ነገር ከራስህ ልትፈጥርልንና ልታስነብበን የፈለከው ድርሰት ካለ መጻፍ ትችላለህ ፡፡ የምናነብና የምንረዳውንም ፣ በቋንቋችን የተጻፈ ደብዳቤ መልዕክት እንደምን ልትለውጠው ወይም ልታሻሽለው እንደምትችል በትክክል ግልጽ አይደለም ፡፡ ደብዳቤውን ደግመህ አንብብና ስለሃይማኖት የሚያስረዳው ጉዳይ ካለ ይዘህ ብቅ በልልኝና ልረዳው ፡፡ ልብ ካልከው ደብዳቤው እንዲያውም በተመላላሽ የሚሰጠውን ግልጋሎት ያወድሳል ፡፡ የተወቀሰው የቅዱስ ፓትርያርኩን መመሪያ አላከበርክም ፣ ሳታስፈቅድ ስብከት አካሂደሃል ፣ ከሀገረ ስብከትህ ደብዳቤ ይዘህ አልመጣህም በሚል ነው ፡፡ ከዛ ውጭ ስላስተማረው ትምህርቶች መከራከርና ማስረዳት ከፈለግህ ከባለጉዳዩ በቀጠሮ ብትገናኝ በተሻለ ያስተናግድህ ይሆናልና በዛው በኩል ሞክር ፡፡ በተረፈ ከዚህ ቀደም ከፓስተር ቶሎሳ ጋር ያደረገውን ጥያቄና መልስ ፣ ስለ ድንግል ማርያም እመቤታችን በሚል ርዕስና ማን አስተዋለ የሚል በዩ ቲዩብ የተለቀቀ ትምህርቶቹን አድምጫለሁ ፡፡ በነዚህ ስብከቶች ውስጥ የጐደለ ወይም የጐደፈ የምትለውና ልታስተምረኝ የምትሻው ካለህ እጠብቃለሁ ፡፡

  ReplyDelete
 25. የትዝታው መዝሙር በሚያገለግልበት በድሃኒአለም ቸርች እንዳይሸጥ የከለከለ አባወኦልደትንሳዔ ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ በተገኙ ጊዜ እርስዎ ማስቀደስ ይችላሉ ነገር ግን እሰብካለሁ ብላው እንዳይነሱ በማለት ማስጠንቀቂያን የቻራቸው የማህበረ ቅዱሳን አባል ያልሆነ ነገር ግን የማህበሩ መንፈስ የሞላበት ባለጸጋ ነው! አስፈላጊ ከሆነ ሌላም መጨመር ይጫላል። አባሰላማ በርቱ

  ReplyDelete
 26. በመጀመሪያ እኔ ያሰፈርኩትን በሚገባ ሳታብ ምላሽ ለመስጠት በመሞከርህ የጻፍክልኝ ከእኔ ሐሳብ ጋር የማይገኛን መሆኑን ላሰገነዝብህ እወዳለሁ፡፡ እኔ ያሰፈርኩት ‹‹የደብዳቤው መልዕክት በትምህርትህ ላይ ህጸጽ ተገኝቶብሃል አይልም›› የሚል ሐሳብ ላሰፈረው ሰው (ምናልባትም አንተ ልትሆን ትችል ይሆናል) ዘበነ ህጸጽ እንዳለበት ማየት ከፈለክ ከየትኛው ስብከቱ ማየት ትፈልጋለህ? የሚል እንጂ ስለደብዳቤው ምንም ያሰፈርኩት ነገር የለም፡፡

  ለማንኛውም ግን አንተ የጠቆምከኝን የዘበነን ስራዎች በመጥቀስ ከሁለቱ ላይ አንዳንድ ነገሮችን ብቻ ላሳይህ ይህቺን አጭር ማሳተወሻ ጻፍኩልህ፡፡

  ከዛ በፊት ግን ‹‹ከዛ ውጭ ስላስተማረው ትምህርቶች መከራከርና ማስረዳት ከፈለግህ ከባለጉዳዩ በቀጠሮ ብትገናኝ በተሻለ ያስተናግድህ ይሆናልና በዛው በኩል ሞክር ›› ላልከኝ አስተያየትህን ከታላቅ አክብሮት ጋር ተቀብዬ ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ ጋር እንጂ ከተረት አባት ጋር ስለመንፈሳዊ ነገር ለመነጋገር ፍላጎት እንዳሌለኝ ላሳወቅህ እወዳለሁ፡፡

  በቅድሚያ ከትውልዱ ማን አስተዋለ ብሎ ከለቀቀው ላይ ተቀበለኝ፡፡ ቀደም ብዬ ዘበነ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህር ሳይሆን የተረት አባት ነው ማለቴን አልዘነጋሁትም ምናልባትም በዚህ ሐሰቤ ግር ተሰኝተህ ከሆነ ከራሱ ስብከት ላይ አንድ ተረት ላስነብብህ፡- ‹‹ተራራ ወጥቶ ኢየሱስ ልብሱ ተለወጠ ነጭ ሆነ አብረቀረቀ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ ደነገጡ ምድር ላይ ምን ሰምተዋል እነሱ? ሙሴ ነህ ኤልያስ ነህ ሲባል ነበር ኢየሱስ... ሙሴና ኤልያስ መጥተው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መነጋገር ጀመሩ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ ደነገጠው ወደቁ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ ደነገጠው በወደቁ ጊዜ ሙሴና ኤልያስ ኢየሱስ ክርስቶስ ያነጋገሩት ነበር፡፡ ሙሴም አለ፡- ጌታዬ ሆይ አምላኬ ሆይ የኔን ጌታ አንተን ምን ብለው ይጠሩሃል? እንዴት ሙሴ ይሉሃል? እኔ ሙሴማ ሙሴ እንጂ ደመና ብጋርድ መና ባወርድ ባህር ብከፍል ጠላት ድል ብመታ በአንተ አይደለም እንዴ አምልኬ ሆይ...›› ይህን ንግግሩን ማንበብም ብቻ ሳይሆን መስማትም ከፈለክ ቀደም ብዬ የጠቀስኩትን የስብከት ቪሲዲውን ተመልከት፡፡ ይህ ንግግር መነሻ ያደረገው ማቴዎስ ምዕራፍ 17ን ቢሆንም ማቴዎስ ባሰፈረው ላይ ግን ‹‹ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ሲነጋገሩ ታዩአቸው›› ከሚለው ያለፈ ነገር የለም፡፡ ዘበነ ግን በራእይ ተገልጦለት ይሁን ወይም ምስጢሩን ሹክ ያለው ሰው ኖሮ ግልጽ ባይሆንም ይሄን የመሰለ ቆንጆ ተረት አውርቷል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ሰበብ አድርጎ ግን በመጽሐፉ የሌለን ነገር መናገርን የመሰለ ሕጸጽ ምን እንዳለ ልትነግረኝ ብትችል ደስ ይለኛል፡፡

  ሌላው ከዶክተር ቶሎሳ ጋር ያደረገው ውይይትን ነው የጠቀስክልኝ፡፡ ከእርሱም አንድ ነገር ብቻ በማቅረብ ዘበነና መጽሐፍ ቅዱስ ላይገናኙ በየራሳቸው እየተጓዙ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ እዚህ ጋር ለማሳያነት የማቀርበው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰፈረውና ዘበነ እንደሚል አስመስሎ ያቀረበውን ነገር በማነጻጸር ነው

  በዕብ 11÷35 ላይ የመምህር ዘበነ መልእክት
  ዕብራዊያን ምዕራፍ 11ን እንመለከተው ከቊጥር 35 እንጀምር ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተገረፉ በወህኒ እየታሰሩ እየተጣሉ የበግና የፍየል ቆዳና ሌጦ ለብሰው ተንከራተቱ ዓለም አልተገባቻቸውምና የዓለምን ነገር ትተው የዓለምን ምግብ ትተው የጣመን የጣፈጠን ትተው በገዳም ገብተው ድምፀ አራዊትን ግርማ ለሊትን ታግሰው ድንጋይ ተንተርሰው ጤዛ ልሰው እነሆ እምነታቸው እግዚአብሔር ስለነበረ ዓለምን ንቀው የእግዚአብሔር ሆኑ ይላል፡፡


  በዕብ 11÷35-40 ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት
  ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፡፡ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ÷ ተፈተኑ÷ በመጋዝ ተሰነጠቁ÷ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ÷ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቻቸውምና በምድረ በዳና በተራራ÷ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ፡፡ እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም÷ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለእኛ አንዳች የሚበለጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና፡፡


  ዕውን ዘበነ እንደተናገረው መጽሐፉ ይላል? እራስህ ፍረድ

  ሌላውና ‹‹ስለ ድንግል ማርያም እመቤታችን›› የሚለውን ስላላየሁት በእርሱ ዙሪያ ምንም ለማለት አልቻልኩም፡፡ ይህ የማይበቃ ከሆነ በቀጣይ በሲዲ ከለቀቃቸውና ለገበያ ካቀረባቸው ውስጥ ከየትኛው ላይ እንድጽፍልህ እንደምትፈለግ ንገረኝ ከእንከን የጸዳ ስብከት ስለሌለው አሳይሃለሁ፡፡
  ደቂቀ አቡዬ ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. here is ዘበነ's twin brother
   http://www.youtube.com/watch?v=kJ1wuJWYp9A

   Delete
  2. ያካፈልከኝ ትምህርቶች በአጠቃላዩ በጽንሰ ሃሳብ አልተራራቁብኝም ፡፡ ቃል በቃል የመውረድ ነገርን ከሆነ የምትፈትሸው ፣ በንባብ እየታገዝን ካልሆነ በስተቀር አይቻልም ፡፡ በስብከት ላይ የማስፋትና የማጥበብ ፣ የማብራራትና የማጉላት ነገር ስለሚታከልበት ፣ በመሥመር ላስተያይ ብለህ ብትታገል ለዚህ ዓለም ሰባኪዎች ለአንዳቸውም አይመጣላቸውም ፡፡ ሁሉም በራሱ የአነጋገርና የማስተማር ዘዴ መሠረቱን ባላናጋ አስፍቶ ይናገራል ፡፡ ለምሳሌም እንዲሆንህ ርዕሳቸውን ከአንድ ኃይለ ቃል /ግፋ ቢል ቢበዛ አምስት መስመር/ ይወስዱና ከግማሽ እስከ አንድ ሰዓት ያላነሰ ያስተምራሉ ፡፡ ታድያ ከምን አምጥቶ ለሰዓት ለፈለፈብን ትለዋለህ ? ለእኔ በክፋትና በተንኰል ተሞልተን ከተመለከትን ቀና ነገርን በየትኛውም ትምህርት ፣ በማንኛውም አስተማሪ ዘንድ አናገኝም ፡፡ ሰው ሁል ጊዜም በጐደሎ የሚንቀሳቀስ ፍጡር ነው ፡፡ ምንም ጉድለትና በቃሉ ሁሉ ስህተት የሌለበት አስተማሪ አንድ ኢየሱስ ብቻ ነው ፡፡ ስለዚህም ከላይ የጐደሉብህን ቃሎች አንተ በግልህ በመጽሐፍ ብታሟላቸው መልካም ይሆኑልሃል ፣ ከሚቆጠርና ከሚደመረው ኃጢአትም ትድናለህ ፡፡ እኔ የአጠቃላይ መልዕክቱን ፍሬ ነገር እንጅ የምፈትሸው እየነጣጠልኩ አይደለም ፡፡ ስለዛም ሲያስተምሩኝ ዋና መልዕክታቸው በቶሎ ይደርሰኛል ፡፡

   በእምነት ሆነህ መታገልን/መጋደልን ለማስረዳት ከነምሳሌው የተጻፈው የመጽሐፍ ሙሉ ቃል፡-
   "ዕብ 11፡ 32 -4ዐ እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና። እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ። ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና። "
   ወዳጅህ

   Delete
  3. ወዳጄ የጻፍክልኝን ወዳጃዊ መልእክት አንብቢያለሁ፡፡ አንተ እንዳልከው መምህራን በአንድ ጥቅስ ተነስተው ሰፋ ያለ ትምህርት ያስተላልፋሉ፡፡ ያ ማለት ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ውጪ የሆነ ትምህርት ቢያስተምሩ ምንም ችግር የለውም ማለት እንዳልሆነ እንግባባለን፡፡

   ዘበነ ግን እያደረገ ያለው እንደዛ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰፈሩትን እውነቶች መነሻ በማድረግ እርሱ የሚፈልገውን ነገር መጽሐፍ ቅዱሱ ይደግፈውም አይደግፈው በነጻነት ያስተላልፋል፡፡ እኔም ትክክል አይደለም ለማለት የሞከርኩት ይህን ድርጊቱን ብቻ ነው፡፡

   አሁን አንተ ያነሳኸውን ምንባብ መመለከቱ ብቻ ዘበነ ምን ያህል ከመጽሐፍ ጋር የማይገናኝ መልእክት ለማስተላለፍ ‹‹የጀገነ›› ሰው መሆኑን ለመረዳት ያስችላል፡፡

   አንተ እንዳሰፈርከው ዕብራዊያን 11ኛው ምዕራፍ ላይ ስለገዳማዊ ኑሮ የሚናገረው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱ ግን ስለገዳም እንዲናገርለት በሚል ምን ያህል ምንባቡን እንዳጣመመው ቀደም ሲል ያሰፈርኩትን መለስ ብለህ ተመለከተው፡፡ ይህ ታዲያ ጥቅሱን መነሻ በማድረግ ማስተማር ነው ወይስ ከጥቅሱ መልእክት ውጪ የሆነ ሐሳብ ማስተላለፍ?
   ደቂቀ አቡዬ ነኝ

   Delete
 27. ውድ ወዳጄ በቅንነት ስለሰጠኸኝ ወዳጃዊ ሐሳብ እያመሰገንኩ ያለተረዳኸኝ የመሰለኝን ነገር እንዲህ ላስረዳህ አሰብኩ፡፡ አንድን ምንባብ መነሻ በማድረግ ማስተማር ምንም ችግር የሌለበት የሁሉም መምህራን አካሄድ ነው፡፡ እኔም እርሱን አልተቃወምኩም፡፡ ዘበነ እያደረገ ያለው መጽሐፍ ቅዱሱን መነሻ በማድረግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት መስጠት ሳይሆን የራሱን የልቡን መሻት ማሰራጨት ነው፡፡ አሁን አንተ ሙሉ ቃል ብለህ ያሰፈረከው የዕብራዊያን መልእክት ምዕራፍ 11 ስለገዳምና ስለገዳማዊያን ምንም የሚለው ነገር የለውም፡፡ ዘበነ ግን ለገዳማዊ ትምህርት እንዲሆን በሚል ሆነ ብሎ አጣሞ ‹‹ይላል›› በሚል ሊያቀርበው ችሏል፡፡ እኔ ትክክል አይደለም ያልኩት እሱን ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እንድታውቀው የምፈልገው መጽሐፉ የማለይውን ቃል እየተናገሩ ‹‹ይላል›› ብሎ ማቅረብ ከመጽሐፉ ቃል አትርፎ መናገር በሌላ አማርኛ ከእግዚአብሔር ቃል እውነት ማፈግፈግ መሆኑን ነው፡፡ ዘበነ ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ሰው መሆኑን አሁን አንተ ያነሳኸው ጥቅስ ብቻ ያስረዳል፡፡ ከዚህም በላይ ትንሽ ብጨምርልህ ቅር አይለኝም፡፡ ይህን የማደረገው ግን አንተ እንዳልከው በክፋትና በተንኮል ተመልክቼው ሳይሆን የእግዚአብሔር ቃል ከምንም ነገር ጋር ሳይሸቃቀጥ ይነገር የሚል እምነት ስላለኝ ብቻ መሆኑን እንድትረዳልን እፈልጋለሁ፡፡

  ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን በሰጣቸው ምሽት ስርዓት ቁርባንን የሰራው በታቦት ላይ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ይህን ስርዓት የሰራውም የአንድ ሰውን ቤት በመጠቀም እንጂ ቤተ መቅደስ ገብቶ እንዳልነበረም ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ዘበነ ‹‹በብሉይ ኪዳን እነሆ 10ቱ ትህዛዛት ያሉበት ታቦተ ህግ በክብር ከሆነ አሁን ደግሞ ያለው የመንፈስ አገልግሎት አዲስ ኪዳን ደሙና ስጋው የሚፈተትበት በማቴ 26፡26 ስጋውና ደሙን የተናገረበት ምስጢሩን የሰራበት ይሄ የሚፈተትበት ደግሞ የአሁኑ አገልግሎት ድንቅ ነው›› ሲል አስተምሯል፡፡ ልብ አድርግልኝ ዘበነ ማቴ 26፡26ን የጠቀሰው ክርስቶስ በታቦቱ ላይ ነው ስርዓተ ቁርባንን የሰራው ለማለት እንደሆነ ንግግሩን መመልከቱ ብቻ በቂ ነው፡፡ እኔ የተቃወምኩትም ይህንን ነው ምክንያቱም አልተጻፈምና፡፡ ‹‹ምንም ጉድለትና በቃሉ ሁሉ ስህተት የሌለበት አስተማሪ አንድ ኢየሱስ ብቻ ነው›› ያልከኝን ግን በሙሉ ልብ ተቀብያለሁ፡፡
  ደቂቀ አቡዬ ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዴት አላችሁ አባ ሰላማዎች ጽሁፋችሁ ተመችቶኛል

   Delete
  2. የቀደመው ስላልወጣ ዳግም ከትንሽ ማብራሪያ ጋር የተጻፈ

   ደቂቀ አቡዬ አሁን ለአንተ የራስ ምታት ሆኖ ቀኖና የፈረሰ ያህል ያስቆጣህ ማለቴም የረበሸህ በተሰጠው ትምህርት መሃል ገዳም የሚል ቃል ስለተደባለቀ ብቻ ነው ፡፡

   "መዘበቻ ከመሆንና ከመገረፍም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ÷ ተፈተኑ÷ በመጋዝ ተሰነጠቁ÷ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ÷ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቻቸውምና በምድረ በዳና በተራራ÷ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ፡፡"

   ስታስበው ይህን ከላይ የሰፈረውን ሐዋርያትና የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ያለፉበትን ገድል ለዘመናዊ ሰው በትክክለኛ ምሳሌ ለማስረዳት መምህሩ በምን ቋንቋና ቃላት መግለጽ ይችላል? መቸም እርግጠኛ ነኝ ሰው ስለ ሃይማኖት ምክንያት ተሰዶ የሚኖርበት ዋሻና ጉድጓድ በከተማ ውስጥ አይገኝም ፤ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሶ የሚዞርም መንፈሳዊ ሰው ፒያሳና አራት ኪሎ አይታይም ፡፡ ያ በመጽሐፍ የተዘረዘረውን የህይወት ገጠመኝ ለዚህኛው ትውልድ በሚገባን ቋንቋ ማስረዳቱ ፣ በቤተ ክርስቲያናችንም የሚታመንበትን ሥርዓት ማካተቱ ስህተት አይደለም እላለሁ ፡፡ እንደተጠቀሰውም ስለ እምነት ጉዳይ የፈተናና የመከራ ህይወት በአሁኑ ዘመን በግልጽ የሚታየውና የሚገኘው በገዳም ብቻ ነው ፡፡ ማክያቶና ኬክ እየበላ ፣ ጥብስና ክትፎ እያገሳ እንደ መንደር ውሻ በየሰፈሩ እየተልከሰከሰ የተባረርኩ ፣ ከአውደ ምህረት በምንፍቅና ስለተባረረ ፣ የተሰደድኩ መምህር ነኝ የሚለውን መቸም እዚህ ወግ እንደማታደርሰው እርግጠኛ ነኝ ፡፡

   እንዲያውም በአዲስ ኪዳን ስንመጣ ደግሞ ምድረ በዳ የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሁን በገዳምነት የሚያገለግሉትን ሥፍራ ሆኗል ፡፡ ለምሳሌም ዮሐንስ አስተዳደጉ በገዳም መሆኑ ባይዘነጋም ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክበት የነበረ የይሁዳ በረሃ ከ483 ዓ.ም. ጀምሮ የቅዱስ ሳባ ገዳም ተብሎ ይጠራል ፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ በመንፈስ ወደ ምድረ በዳ ተወሰደ የሚለውን ሥፍራ ገዳመ ቆሮንቶስ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምራናለች ፡፡ ከላይ ከገለጽኩልህ በተጨማሪ በዚህም ምክንያት በዕብራውያን መልዕክት ትምህርት ላይ ገዳም ምድረ በዳን ተክቶ መጠቀሱ አግባብነት ይኖረዋል ፡፡

   የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ለማስተማር የቀመሱትን መከራ ፤ በፈቃዳቸው ዓለምን ክደው ፣ ገዳም ገብተው ፣ ሥጋቸውን የሚቀጡ ምእመናን አሉንና ፤ ትውልዱ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰውን መገንዘብ ይችል ዘንድ መጠቀሱ ኢ-መጽሐፋዊ አይደለም ፡፡ ምናልባት የውጭው ስሜት ኖሮህ ከሆነ ፣ ሉተር ገዳምን የጠላው መከራው ስለበረከተበት ፣ ሰው የለመደ ሰው ስለሆነ ፣ ከሰው ተለይቶ የመኖር ፈተናውም ስለጠነከረበት ነው ፡፡ እኛ አገር ግን ገዳማቱ እንደ ዘመናችን ኮሌጆች ፣ የሃይማኖት ትምህርት መማሪያዎች ነበሩ ፤ መምህር የሚወጣው ፣ መጽሐፍ የሚጻፈው ፣ የሚመሠጠረው ሁሉ በነዚሁ በገዳማቱ ነበር ፡፡ በዛ የሚሰባሰቡት ግለሰዎች ሙሉ ኃይላቸውንና ዕውቀታቸውን የሚያውሉት የሃይማኖትን ነገር በመማር ፣ ጾምና ጸሎትን በዓለም ላለነው በመፈጸም ፣ ቤተ ክርስቲያናችንንም የሚያገለግሉ መጽሐፍትን በመድረስ ነው ፡፡ ይኸ አሁን የተዳከመውን አገልግሎት ተመልሶ የሚጠናከርበትን መንገድ መፈተሽ እንጅ ፣ የገዳም ስም በስብከት መሃል ስለተጠቀሰ ብቻ ሊታመሙበት አይገባም ፤ ሰውም ይታዘበናል ፡፡ ዛሬ የምንባላባትን ቤተ ክርስቲያን አቆይተው ያስረከቡ ከገዳም ተምረው የወጡ ሊቃውንት መሆናቸውንም አንዘንጋው ፡፡ ተጽፈው ዛሬ እያንዳንዱ የሚነበንባቸውም መጽሐፍት የገዳም ውጤቶች ናቸውና ጥቅሙ ከጽድቅም ባለፈ እኛ ለማስተማሪያነት ጠቅመዋል ፡፡

   Delete
  3. ደቂቀ አቡዬ አሁን ለአንተ የራስ ምታት ሆኖ ቀኖና የፈረሰ ያህል ያስቆጣህ ማለቴም የረበሸህ በተሰጠው ትምህርት መሃል ገዳም የሚል ቃል ስለተደባለቀ ብቻ ነው ፡፡

   "መዘበቻ ከመሆንና ከመገረፍም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ÷ ተፈተኑ÷ በመጋዝ ተሰነጠቁ÷ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ÷ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቻቸውምና በምድረ በዳና በተራራ÷ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ፡፡"

   ስታስበው ይህን ከላይ የሰፈረውን ሐዋርያትና የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ያለፉበትን ገድል ለዘመናዊ ሰው በትክክለኛ ምሳሌ ለማስረዳት መምህሩ በምን ቋንቋና ቃላት መግለጽ ይችላል? መቸም እርግጠኛ ነኝ ሰው ስለ ሃይማኖት ምክንያት ተሰዶ የሚኖርበት ዋሻና ጉድጓድ በከተማ ውስጥ ይገኛል አትለኝም ፤ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሶ የሚዞርም መንፈሳዊ ሰው ፒያሳና አራት ኪሎ አይታይም ፡፡ ያ በመጽሐፍ የተዘረዘረውን የህይወት ገጠመኝ ለዚህኛው ትውልድ በሚገባን ቋንቋ ገዳም ብሎ ማስረዳቱ ፣ በቤተ ክርስቲያናችንም የሚታመንበትን ሥርዓት ማካተቱ ስህተት አይደለም እላለሁ ፡፡ እንደተጠቀሰውም ስለ እምነት ጉዳይ የፈተናና የመከራ ህይወት በአሁኑ ዘመን በግልጽ የሚታየውና የሚገኘው በገዳም ብቻ ነው ፡፡ ማክያቶና ኬክ እየበላ ፣ ጥብስና ክትፎ እያገሳ እንደ መንደር ውሻ በየሰፈሩ እየተልከሰከሰ የተባረርኩ ፣ ከአውደ ምህረት በምንፍቅና ስለተገፋ ፣ የተሰደድኩ መምህር ነኝ የሚለውን መቸም እዚህ ወግ እንደማታደርሰው እርግጠኛ ነኝ ፡፡

   እንዲያውም በአዲስ ኪዳን ስንመጣ ደግሞ ምድረ በዳ የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሁን በገዳምነት የሚያገለግሉትን ሥፍራ ሆኗል ፡፡ ለምሳሌም ዮሐንስ አስተዳደጉ በገዳም መሆኑ ባይዘነጋም ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክበት የነበረ የይሁዳ በረሃ ከ483 ዓ.ም. ጀምሮ የቅዱስ ሳባ ገዳም ተብሎ ይጠራል ፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ በመንፈስ ወደ ምድረ በዳ ተወሰደ የሚለውን ሥፍራ ገዳመ ቆሮንቶስ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምራናለች ፡፡ ከላይ ከገለጽኩልህ በተጨማሪ በነዚህም ምክንያቶች በዕብራውያን መልዕክት ትምህርት ላይ ገዳም ምድረ በዳን ተክቶ መጠቀሱ አግባብነት ይኖረዋል ፡፡

   የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ለማስተማር የቀመሱትን መከራ ፤ በፈቃዳቸው ዓለምን ክደው ፣ ገዳም ገብተው ፣ ሥጋቸውን የሚቀጡ ምእመናን በሃገራችን አሉንና ፤ ትውልዱ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰውን መገንዘብ ይችል ዘንድ መጠቀሱ ኢ-መጽሐፋዊ አይደለም ፡፡ ምናልባት የውጭው ስሜት ኖሮህ ከሆነ ፣ ሉተር ገዳምን የጠላው መከራው ስለበረከተበት ፣ ሰው የለመደ ሰው ስለሆነ ፣ ከሰው ተለይቶ የመኖር ፈተናውም ስለጠነከረበት ነው ፡፡ እኛ አገር ግን ገዳማቱ እንደ ዘመናችን ኮሌጆች ፣ የሃይማኖት ትምህርት መማሪያዎች ነበሩ ፤ መምህር የሚወጣው ፣ መጽሐፍ የሚጻፈው ፣ የሚመሠጠረው ሁሉ በነዚሁ በገዳማቱ ነበር ፡፡ በዛ የሚሰባሰቡት ግለሰዎች ሙሉ ኃይላቸውንና ዕውቀታቸውን የሚያውሉት የሃይማኖትን ነገር በመማር ፣ ጾምና ጸሎትን በዓለም ላለነው በመፈጸም ፣ ቤተ ክርስቲያናችንንም የሚያገለግሉ መጽሐፍትን በመድረስ ነው ፡፡ ይኸ አሁን የተዳከመውን አገልግሎት ተመልሶ የሚጠናከርበትን መንገድ መፈተሽ እንጅ ፣ የገዳም ስም በስብከት መሃል ስለተጠቀሰ ብቻ ሊታመሙበት አይገባም ፤ ሰውም ይታዘበናል ፡፡ ዛሬ የምንባላባትን ቤተ ክርስቲያን አቆይተው ያስረከቡ ከገዳም ተምረው የወጡ ሊቃውንት መሆናቸውንም አንዘንጋው ፡፡ ተጽፈው ዛሬ እያንዳንዱ ሰው እንደ ሊቅ የሚያነበንባቸውም መጽሐፍት የገዳም ውጤቶች ናቸውና ፣ አገልግሎቱ ከጽድቅም ባለፈ እኛን ለማስተማሪያነት ጠቅሟል ፡፡ ስለዚህ ገዳም በኢትዮጵያ ክርስትና ውስጥ ትልቅ አስተዋጽዖ ስላለው ስሙን መጥቀስ ብቻ ሳይሆን ፣ ገዳም ግቡ ብሎ ቢሰበክም ስህተት አይደለም ፡፡ ዓላማው የጽድቅን መንገድ ለማስተማር ስለሆነ ከክርስትናውም ዓላማ ጋር አይጋጭም ፡፡

   Delete
  4. ይህንን መልስ ለማስነበብ አራተኛ ሙከራዬ ነው ፡፡ ይኸኛው አካሄዳችሁ ተሳትፎአችንን የማትፈልጉት ይመስላልና ለመጨረሻ ጊዘ ለማየት ጽፌዋለሁ ፡፡

   ደቂቀ አቡዬ አሁን ለአንተ የራስ ምታት ሆኖ ዶግማና ቀኖና የፈረሰ ያህል ያስቆጣህ ማለቴም የረበሸህ በተሰጠው ትምህርት መሃል ገዳም የሚል ቃል ስለተደባለቀ ብቻ ነው ፡፡

   "መዘበቻ ከመሆንና ከመገረፍም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ÷ ተፈተኑ÷ በመጋዝ ተሰነጠቁ÷ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ÷ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቻቸውምና በምድረ በዳና በተራራ÷ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ፡፡"

   ስታስበው ይህን ከላይ የሰፈረውን ሐዋርያትና የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ያለፉበትን ገድል ለዘመናዊ ሰው በትክክለኛ ምሳሌ ለማስረዳት መምህሩ በምን ቋንቋና ቃላት መግለጽ ይችላል? መቸም እርግጠኛ ነኝ ሰው ስለ ሃይማኖት ምክንያት ተሰዶ የሚኖርበት ዋሻና ጉድጓድ በከተማ ውስጥ ይገኛል አትለኝም ፤ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሶ የሚዞርም መንፈሳዊ ሰው ፒያሳና አራት ኪሎ አይገኝም ፡፡ ያ በመጽሐፍ የተዘረዘረውን የህይወት ገጠመኝ ለዚህኛው ትውልድ በሚገባን ቋንቋ ገዳም ብሎ ማስረዳቱ ፣ በቤተ ክርስቲያናችንም የሚታመንበትን ሥርዓት ማካተቱ ስህተት አይደለም እላለሁ ፡፡ እንደተጠቀሰውም ስለ እምነት ጉዳይ የፈተናና የመከራ ህይወት በአሁኑ ዘመን በግልጽ የሚታየውና የሚገኘው በገዳም ብቻ ነው ፡፡ ማክያቶና ኬክ እየበላ ፣ ጥብስና ክትፎ እያገሳ እንደ መንደር ውሻ በየሰፈሩ እየተልከሰከሰ የተባረርኩ ፣ ከአውደ ምህረት በምንፍቅና ስለተገፋ ፣ የተሰደድኩ መምህር ነኝ የሚለውን መቸም እዚህ ወግ እንደማታደርሰው እርግጠኛ ነኝ ፡፡

   እንዲያውም በአዲስ ኪዳን ስንመጣ ደግሞ ምድረ በዳ የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሁን በገዳምነት የሚያገለግሉትን ሥፍራ ሆኗል ፡፡ ለምሳሌም ዮሐንስ አስተዳደጉ በገዳም መሆኑ ባይዘነጋም ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክበት የነበረ የይሁዳ በረሃ ከ483 ዓ.ም. ጀምሮ የቅዱስ ሳባ ገዳም ተብሎ ይጠራል ፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ በመንፈስ ወደ ምድረ በዳ ተወሰደ የሚለውን ሥፍራ ገዳመ ቆሮንቶስ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምራናለች ፡፡ ከላይ ከገለጽኩልህ በተጨማሪ በነዚህም ምክንያቶች በዕብራውያን መልዕክት ትምህርት ላይ ገዳም ፣ ምድረ በዳን የሚለውን ተክቶ መጠቀሱ አግባብነት ይኖረዋል ፡፡

   የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ለማስተማር የቀመሱትን መከራ ፤ በፈቃዳቸው ዓለምን ክደው ፣ ገዳም ገብተው ፣ ሥጋቸውን የሚቀጡ ምእመናን በሃገራችን አሉንና ፤ ትውልዱ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰውን መገንዘብ ይችል ዘንድ መጠቀሱ ኢ-መጽሐፋዊ አይደለም ፡፡ ምናልባት የውጭው ስሜት ኖሮህ ከሆነ ፣ ሉተር ገዳምን የጠላው መከራው ስለበረከተበት ፣ ሰው የለመደ ሰው ስለሆነ ፣ ከሰው ተለይቶ የመኖር ፈተናውም ስለጠነከረበት ነው ፡፡ እኛ አገር ግን ገዳማቱ እንደ ዘመናችን ኮሌጆች ፣ የሃይማኖት ትምህርት መማሪያዎች ነበሩ ፤ መምህር የሚወጣው ፣ መጽሐፍ የሚጻፈው ፣ የሚመሠጠረው ሁሉ በነዚሁ በገዳማቱ ነበር ፡፡ በዛ የሚሰባሰቡት ግለሰዎች ሙሉ ኃይላቸውንና ዕውቀታቸውን የሚያውሉት የሃይማኖትን ነገር በመማር ፣ ጾምና ጸሎትን በዓለም ላለነው በመፈጸም ፣ ቤተ ክርስቲያናችንንም የሚያገለግሉ መጽሐፍትን በመድረስ ነው ፡፡ ይኸ አሁን የተዳከመውን አገልግሎት ተመልሶ የሚጠናከርበትን መንገድ መፈተሽ እንጅ ፣ የገዳም ስም በስብከት መሃል ስለተጠቀሰ ብቻ ሊታመሙበት አይገባም ፤ ሰውም ይታዘበናል ፡፡ ዛሬ የምንባላባትን ቤተ ክርስቲያን አቆይተው ያስረከቡ ከገዳም ተምረው የወጡ ሊቃውንት መሆናቸውንም አንዘንጋው ፡፡ ተጽፈው ዛሬ እያንዳንዱ ሰው እንደ ሊቅ የሚያነበንባቸውም መጽሐፍት የገዳም ውጤቶች ናቸውና ፣ አገልግሎቱ ከጽድቅም ባለፈ እኛን ለማስተማሪያነት ጠቅሟል ፡፡ ስለዚህ ገዳም በኢትዮጵያ ክርስትና ውስጥ ትልቅ አስተዋጽዖ ስላለው ስሙን መጥቀስ ብቻ ሳይሆን ፣ ገዳም ግቡ ብሎ ቢሰበክም ስህተት አይደለም ፡፡ ዓላማው የጽድቅን መንገድ ለማስተማር ስለሆነ ከክርስትናውም ዓላማ ጋር አይጋጭም ፡፡

   Delete
 28. I really have no any idea about the very motive of the article . But one thing is very true as far as my observation about the teachings of Zebene. I am not a conservative follower of the Church . But I am one of the follwers who try to listen to the approaches and actual preachings of peachers either by attending or through various media of communication. To my understanding , it is not uncomon to observe that there are considerable problems in every single Church. What is good for those preachers is that the system has no any space for any comment or opinion. When it comes to Zebene, it is not difficult to sense his deep- rooted ulterior motive . The way he crafts or prepare his "teachings"deeply sound very exploitative or synically manipulative . His mentality and tendency is very cily if we do take the meaning and the implication buried under his his words and expressions. I want to say that he sounds a very "smart"guy who knows very well the weaknesses of our Church (EOC) that has a lot to do with its tradition of taking so many things as taboo or sinful.

  ReplyDelete
 29. ወዳጄ ወንድምህን ለመምከር ካለህ ቅን ፍላጎት የተነሳ በተደጋጋሚ የላከውን መልእክት ለማንበብ በመታደሌ እግዚአብሔርን አመስግኛለሁ፡፡ ከአንተ ቀድም ብዬ እኔም ልኬው የነበረው መልእክት ስላልወጣ ደግሜ ለመላክ ተገድጄ ነበር፡፡

  ከመልእክትህ ለመረዳት እንደቻልኩት የአንዲት ቃል መግባት ምንም አይደለም የሚል ስሜት እንዳለህ ነው፡፡ ግን ምናልባት ይሄን ያደረጉት አንተ መናፍቃን የምትላቸው ሰዎች ቢሆኑ በልና አስበው፡፡ አይደለም የአንዲት ቃል የአንዲት ፊደል መጨመር ምን ያህል እንደሚያናግረን ስለምንተዋወቅ የቃሉን ትንሽ ወይም ብዙ መሆኑን ሳይሆን መጨመሩ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የሚለው ነው ትኩረት ሊሰጥበት የሚገባው የሚል እምነት አለኝ፡፡

  አሁን እያየነው ያለነው ክፍል ላይ ስለገዳም የሚናገረው ምንም በሌለበት ሁኔታ ዘበነ ክፍሉ ስለገዳም እንደሚናገር አስመሰሎ ለማቅረብ ስለፈለገ የሌለ ቃል መጨመሩ ምንም አይደለም እያልከኝ መሆኑን ልብ በል፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ይጨምር ዘንድ እሱ ማን ነው? የሚለውን ግን ልታስተውለው የፈለክ አይመስልም፡፡

  ሌላው ደግሞ ‹‹መቸም እርግጠኛ ነኝ ሰው ስለ ሃይማኖት ምክንያት ተሰዶ የሚኖርበት ዋሻና ጉድጓድ በከተማ ውስጥ አይገኝም ፤ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሶ የሚዞርም መንፈሳዊ ሰው ፒያሳና አራት ኪሎ አይታይም… ማክያቶና ኬክ እየበላ ፣ ጥብስና ክትፎ እያገሳ እንደ መንደር ውሻ በየሰፈሩ እየተልከሰከሰ የተባረርኩ ፣ ከአውደ ምህረት በምንፍቅና ስለተባረረ ፣ የተሰደድኩ መምህር ነኝ የሚለውን መቸም እዚህ ወግ እንደማታደርሰው እርግጠኛ ነኝ›› ያልከኝን ዘበነ አሁን እያደረገ ካለው አንጻር እንዴት እንደተረዳኸው አልገባኝም፡፡ እሱ ምን የሚባለው ገዳም ውስጥ ሁኖ ነው እኛን እየጠራን ያለው? የሚለውን እንድትመልስልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ምነው እሱ የሌለበትን እንድናደርግ ሊመክረን ሞከረሳ?

  እንደገናም ደግሞ ‹‹የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ለማስተማር የቀመሱትን መከራ ፤ በፈቃዳቸው ዓለምን ክደው ፣ ገዳም ገብተው ፣ ሥጋቸውን የሚቀጡ ምእመናን አሉንና ፤ ትውልዱ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰውን መገንዘብ ይችል ዘንድ መጠቀሱ ኢ-መጽሐፋዊ አይደለም ›› የሚል ነገር አስፍርህልኛል፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት አሁን እኔና አንተ ጊዜያችንን እያበከንበት ያለውን ገዳም የሚባለውን ነገር አያውቁትምና የውይይታችን አካል ሊሆኑ የሚችሉበት ምንም መነሻ የላቸውም፡፡

  ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሐዋርያት አሁን እኛ በክብር ይዘነው ያለነውን ቅዱስ ወንጌል እንዲደርሰን ያደረጉት ገዳም በመግባታቸው ሳይሆን በሰው ሁሉ ፊት በመቆም የጽድቁን ወንጌል በመስበካቸው ነው፡፡ ገዳማዊትን መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ቃል ይቃወማል፡፡ እርሱም እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ በሚለው ነው፡፡ አንድ ሰው ብርሃን የሚሆነው የሆነ ስፍራ ላይ ራሱን ሸሽጎ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ ብርሃናችሁ በሰው ሁሉ ፊት ያብራ ብሏልና፡፡

  ገዳማዊነት ኃጢአት አይደለም፡፡ ግን ደግሞ ለጽድቅ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ በአፉ መስክሮ ብዙዎችን ሊያድን የሚችለው ሰው ሸሽጎ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ባይ ነኝ፡፡ ዘበነ ይህን ጠቃሚ ያልሆነ ነገር እንዲደግፍለት ነው የዕብራዊያን መልእክትን የጠቀሰው፡፡ ታዲያ ይህን የዘበነን ስራ ስህተት አይደለምን ትለኛለህ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያላነበብከው ክፍል ያለ ስለመሰለኝ

   እንዲያውም በአዲስ ኪዳን ስንመጣ ደግሞ ምድረ በዳ የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሁን በገዳምነት የሚያገለግሉትን ሥፍራ ሆኗል ፡፡ ለምሳሌም ዮሐንስ አስተዳደጉ በገዳም መሆኑ ባይዘነጋም ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክበት የነበረ የይሁዳ በረሃ ከ483 ዓ.ም. ጀምሮ የቅዱስ ሳባ ገዳም ተብሎ ይጠራል ፡፡ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ በመንፈስ ወደ ምድረ በዳ ተወሰደ የሚለውን ሥፍራ ገዳመ ቆሮንቶስ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምራናለች ፡፡ ከላይ ከገለጽኩልህ በተጨማሪ በነዚህም ምክንያቶች በዕብራውያን መልዕክት ትምህርት ላይ ምድረ በዳ የሚለውን ቃል ገዳም በማለት ተክቶ መጠቀሱ አግባብነት ይኖረዋልም ብያለሁ ፡፡

   በሃገራችን ቀደም ገዳማቱ እንደ ዘመናችን ኮሌጆች ፣ የሃይማኖት ትምህርት መማሪያዎች ነበሩ ፤ መምህር የሚወጣው ፣ መጽሐፍ የሚጻፈው ፣ የሚመሠጠረው ሁሉ በነዚሁ በገዳማቱ ነበር ፡፡ በዛ የሚሰባሰቡት ግለሰዎች ሙሉ ኃይላቸውንና ዕውቀታቸውን የሚያውሉት የሃይማኖትን ነገር በመማር ፣ ጾምና ጸሎትን በዓለም ላለነው በመፈጸም ፣ ቤተ ክርስቲያናችንንም የሚያገለግሉ መጽሐፍትን በመድረስ ነው /የዓለም ብርሃንነታቸውን እንድታይላቸው ለማጉላት እንደገና ታነበው ዘንድ ገለበጥኩት/፡፡ ይኸ አሁን የተዳከመውን አገልግሎት ተመልሶ የሚጠናከርበትን መንገድ መፈተሽ እንጅ ፣ የገዳም ስም በስብከት መሃል ስለተጠቀሰ ብቻ ሊታመሙበት አይገባም ፤ ሰውም ይታዘበናል ፡፡ ዛሬ የምንባላባትን ቤተ ክርስቲያን አቆይተው ያስረከቡ ከገዳም ተምረው የወጡ ሊቃውንት መሆናቸውንም አንዘንጋው ፡፡ ተጽፈው ዛሬ እያንዳንዱ ሰው እንደ ሊቅ የሚያነበንባቸውም መጽሐፍት የገዳም ውጤቶች ናቸውና ፣ አገልግሎቱ ከጽድቅም መንገድነት ባለፈ እኛን ለማስተማሪያነት ጠቅሟል ፡፡ ስለዚህ ገዳም በኢትዮጵያ ክርስትና ውስጥ ትልቅ አስተዋጽዖ ስላለው ስሙን መጥቀስ ብቻ ሳይሆን ፣ ገዳም ግቡ ብሎ ቢሰበክም ስህተት አይደለም ፡፡ ዓላማው የጽድቅን መንገድ ለማስተማር ፣ ቤተ ክርስቲያንንም ለማገዝ ስለሆነ ከክርስትና ዓላማ ጋር አይጋጭም ፡፡

   በተረፈ ሃሳብክን በቁም ነገር ስላካፈልከኝ አመሰግንሃለሁ ፡፡

   Delete
 30. ‹‹ገዳማዊነት ኃጢአት አይደለም›› ይሄን ቃል ደገምኩት ልበል? አዎ ደግሜዋለሁ፡፡ ለምን መድገሙ አስፈለገ? ቢባል የገዳም መኖር የሚጠቅም ከሆነ እሱን ለመቀበል ችግር ስለሌለብኝ ነው፡፡ ጥቅሙን ግን እንድታሳየኝ እፈልጋለሁ፡፡ ገዳማት ውስጥ ለቁጥር የሚከብዱና ለብዙዎች የሚጠቅሙ እውቀቶች መኖራቸውን፣ በርካታ ቅርሶችን በክብር ማስቀመጣቸውንና እንደግራኝና እንደዮዲት ያሉ እምነት የለሾች ሲመጡ ከእነሱ ጥፋት ለታሪክ የሚቀር ነገር ሸሽገው ማቆየታቸውን በታላቅ አክብሮት እቀበላለሁ፡፡ እነዚህ ሁሉ ግን ምድራዊ እንጂ ሰማያዊ አይደሉም፡፡ አንተ እንድታሳየኝ የምፈልገው ሰማያዊውን ነው፡፡ በነገራችን ላይ የመነሻ ነጥባችን ይሄ እንዳልሆነ ግን በፍጹም አልዘነጋሁትም፡፡ አንተ አቅጣጫዬን እንዳስቀየርከኝም ሳላስታውቅህ ማለፍም አልፈልግም፡፡

  ዘበነ ያልተጻፈ ነገር ማንበቡን አንተም ሳትክድ ግን ቢል ምን አለበት በሚል መንፈስ እየጻፍክ ያለኸው ነገር አልሞት ባይ ተገዳይ የሆንክ አስመስሎብሃል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ የሆነ ነገር የተናገረን ሰው ደግፎ ሐሳብ ማቅረብ አስቸጋሪ ይመስለኛል፡፡

  ኢየሱስ ወደምድረ በዳ ሄዶ ነበር ለተባለው አዎ፡፡ ነገር ግን አሁን አንተና መምህርህ ልትሉ እንደምትፈልጉት ዓይነት ሕይወት ፍልጎ ነው ወይ? አይደለም፡፡ ዮሐንስ በምድረ በዳ ነበር አዎ፡፡ ነገር ግን አሁን አንተን መሰሎችህ እንደምትሉት ለጽድቅ ነው ወደዛ የገባው? በፍጹም፡፡ ዮሐንስ በስደቱ እዛ ሄደ እዛው አደገ ከዛ በኋላ እየሰበከ ‹‹ሰው ወዳለበት ቦታ መጣ›› እባክህ በትምህርተ ጥቅስ ያሰፈርኩትን ደግመህ አንብበው፡፡

  ሌላው ‹‹በዕብራውያን መልዕክት ትምህርት ላይ ምድረ በዳ የሚለውን ቃል ገዳም በማለት ተክቶ መጠቀሱ አግባብነት ይኖረዋልም ብያለሁ›› ያልከኝን ሳነብ መጽሐፍ ቅዱሱ ላይ ለምን ‹‹ምድረ በዳ›› የሚለው እንደሰፈረ ስላልተረዳኸው ከሆነ በሚል ሐሳቡን በሙሉ ለማስፈር ተበረታትቻለሁ፡፡ ‹‹ሴቶች ሙታናቸውን በትንሳኤ ተቀበሉ፡፡ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሳኤ እስኪያገኙ እስከሞት ድረስ ተደበደቡ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወህኒ ተፈተኑ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ ተፈተኑ በመጋዝ ተሰነጠቁ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የፍየል ሊጦ ለብሰው ዞሩ ዓለም አልተገባቻቸውምና በምድረ በዳና በተራራ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ›› እንግዲህ ይህ ክፍል እንደሚለው እነዚህ ሰዎች ወደምድረ በዳ (አንተ እንደምትለው ወደገዳም) የሄዱት ጽድቅን ተርበው ወይም ለመጸለይ ሳይሆን በህዝብ መሃል ለመኖር የሚያስችል ሁኔታ ስላጡ ማለትም መከራና ስቃይ ስለበዛባቸው ሰው የሌለበት (መከራ የሌለበት) ቦታ ስለፈጉ ብቻ ነው፡፡ አዲሱ ሰማንያ አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ሐሳብ እንዲህ ሲል ያስቀምጠዋል፡- ‹‹ዓለም የማይገባቸው እነዚህ ናቸው ዱር ለዱርና ተራራ ለተራራ ዋሻ ለዋሻና ፍርኩታ ለፍርኩታም ዞሩ›› (ገዳም ለገዳም እንዳላላ ልብ በልልኝ) ምክንያቱ ከላይ ስለተዘረዘረ እዚህ ጋር መድገሙ የሚያስፈልግ አይመስለኝም፡፡ ታዲያ ይህ ክፍል አንተ እንደምትለው ስለገዳም ምን አለበት በሚል ሊቀርብ ይችላል? አንተ እንዳልከው ‹‹ሰውም ይታዘበናል››ና አስቦ መጻፍ ብልህነት ነው፡፡

  ደቂቀ አቡዬ ነኝ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ መልካም አእምሮ ያለህ ሰው ነህ ፡፡ በብዙው ጉዳዮች ላይ የተግባባን መስሎኛል ፡፡ "በህዝብ መሃል ለመኖር የሚያስችል ሁኔታ ስላጡ ማለትም መከራና ስቃይ ስለበዛባቸው ሰው የሌለበት (መከራ የሌለበት) ቦታ ስለፈጉ ብቻ ነው" ላልከኝ ክርስቲያኖች በካታኮምብ /ከርሰ ምድር/ የተሸሸጉት ሰላም ለማግኘት ብቻ አይደለም ፤ ወደ ምድረ በዳም የተሰደዱት ከግድያ ለማምለጥ በመፈለግ ብቻ አይደለም ፡፡ በተጓዳኝ የፈጸሙትን ገድልና ሥራ መርሳት የለብንም ፡፡ በጥሻና ጉድባ ሆነው አምልከዋል ፣ ጾመዋል ፣ ጸልየዋል ፣ ከትበዋል ፣ ክርስትናን አስተምረዋል / እንዲያውም የክርስትና ትምህርት በአደባባይ ከመሰበኩ በፊት የተስፋፋው በዋሻና በጉድባ በመሰጠቱ እንደ ነበር ታሪክ ይናገራል/ ፡፡ ወደ አገራችንም ስንመጣ ፤ ከገዳም የሚገባው ሁሉ ሃይማኖት በሥርዓት የሚያውቅ ሊቅ ስላልሆነ ክርስትናን በጥልቀት ይማራል ፤ አምልኮውንም ሳያቋርጥና ሳይሰንፍ ይተገብራል ፡፡

   ከዛ ያለፈውን መንፈሳዊ ግልጋሎታቸውን የምትረዳና የምትቆጥርላቸው ከሆነ ደግሞ የነሱ የልፋት ውጤት የሆነው መጣጥፉ ፣ መምህሩና ሊቃውንቱ ለቤተ ክርስቲያናችን በየጊዜው ደርሰዋታል ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ያንን ከነሱ የተቀበለችውን በመጠቀም እንደ እኔና አንተ ያሉ ዓለማውያን ፣ ፈጣሪያቸውን አውቀው እንዲያመልኩ ፣ ወደ መንፈሳዊ ህይወት እንዲመለሱ ትታገልበታለች ፡፡ ይኸም እንግዲህ በቀና ለተገነዘበው የገዳም መንፈሳዊ ወይም ሰማያዊ ግልጋሎት ወይም አስተዋጽዖ የሚንጸባረቅበት መንገድ ነው ፡፡ ሌላው መዘንጋት የሌለበት ጥቅማቸው ደግሞ እኛ እርስ በርስ ስንናቆር የአገር ዳር ድንበር ያለ አንድ ሠራዊት ተጠብቆ የኖረው ፣ እኛ በዓለም የምንገኘውም በበረከት ያለነው በልመናና በጸሎታቸው መሆኑ ነው ፡፡

   Delete
  2. እየተግባባን እንደሆነ አድርገህ ያቀረብከው ሐሳብ ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም፡፡ እኔ የሚታየኝ እየተግባባን እንዳልሆነ ነውና፡፡ እኔ ለማስተላለፍ የምፈልገውና አንተ የምትረዳኝ አንድ እንዳልሆነ አሁን ያሰፈርከውን ብቻ መመልከቱ በቂ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በነበረኝ ሐሳብ እኔ ለማለት የፈለጉት ‹‹ወደምድረ በዳ (አንተ እንደምትለው ወደገዳም) የሄዱት ጽድቅን ተርበው ወይም ለመጸለይ ሳይሆን በህዝብ መሃል ለመኖር የሚያስችል ሁኔታ ስላጡ ማለትም መከራና ስቃይ ስለበዛባቸው ሰው የሌለበት (መከራ የሌለበት) ቦታ ስለፈጉ ብቻ ነው፡፡›› የሚል ቢሆንም አንተ ግን ‹‹በህዝብ መሃል ለመኖር የሚያስችል ሁኔታ ስላጡ ማለትም መከራና ስቃይ ስለበዛባቸው ሰው የሌለበት (መከራ የሌለበት) ቦታ ስለፈጉ ብቻ ነው›› የሚለውን ብቻ ነጥለህ በማውጣት ከእኔ ሐሳብ የተለየ መልክ በመስጠት የራስህን ሐሳብ አሰፈርክ፡፡ እኔ ለማለት የፈለኩት ገዳም ወደምትለው ስፍራ የሄዱት በተጓዳኝ ገድል ለመፈጸም ነው አይደለም፡፡ አንተ ግን …

   ሌላው ‹‹በጥሻና ጉድባ ሆነው አምልከዋል ፣ ጾመዋል ፣ ጸልየዋል ፣ ከትበዋል ፣ ክርስትናን አስተምረዋል / እንዲያውም የክርስትና ትምህርት በአደባባይ ከመሰበኩ በፊት የተስፋፋው በዋሻና በጉድባ በመሰጠቱ እንደ ነበር ታሪክ ይናገራል›› ብለህ ላልከው እንዲያመልኩ፣ እንዲጾሙ፣ እንዲጸልዩ ክርስትናቸውን በቻሉት መንገድ ሁሉ እንዲያስተላልፉ ክርስትናቸው ያስገድዳቸዋል፡፡ እነዚህን ነገሮች ለማድረግ የግድ በገዳም መግባት አያስፍልግም፡፡

   ‹‹ከዛ ያለፈውን መንፈሳዊ ግልጋሎታቸውን የምትረዳና የምትቆጥርላቸው ከሆነ ደግሞ የነሱ የልፋት ውጤት የሆነው መጣጥፉ ፣ መምህሩና ሊቃውንቱ ለቤተ ክርስቲያናችን በየጊዜው ደርሰዋታል ›› የሚለውን ሐሳብህን እኔ የማይበት መንገድ ለየት ያለ ነው፡፡ እውነት ነው ብዙና ብዙ ጽሁፎች ከገዳምና ከገዳማዊያን ወጥተዋል፡፡ ከእነዚህ ጽሁፎች ውስጥ ምን ያህሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ናቸው? ምን ያህሉስ እግዚአብሔርን እንድናከብር ምክንያት ይሆኑናል? የሚለው ነገር ቢነሳ ምናልባት ከመቶ አንድ ለማግኘት ሳንቸገር አንቀርም የሚል እምነት አለኝ፡፡ አንድ አባት ተናገሩ እንደሚባለው ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደጉም የሸፈኗትን እነዚህን መጻሕፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ የሚያይ ትውልድ ባለበት በዚህ ዘመን ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ማን እንደደረሳቸው እንኳ የማይታወቁት መጻሕፍት ከፍተኛ ተቀባይነት አላቸው፡፡

   ለስሙ (ለአንደበት ያህል) እነዚህ መጽሐፎች አዋልድ ማለትም የመጽሐፍ ቅዱስ ልጆች ናቸው ይባል እንጂ ጸረ መጽሐፍ ቅዱስ ናቸው፡፡ እንደዚህ ዓይነት መጽሐፎች በገዳም በመሰራታቸው ገደም ለቤተ ክርስቲያን እድገት አስተዋጽኦ አደረገ ተብሎ ሊነገር አይገባም፡፡ እዚህ ጋር ግን ታሪክን በተመለከተ እንዲሁም አንደንድ እግዚአብሔር የበረካቸው ሰዎች የጻፏቸው መልካም ሐሳብ የያዙ ጽሑፎች መኖራቸውን አልዘነጋሁም፡፡

   በነገራችን ላይ በሕዝብ መሃል ሆኖ ስለ ማገልግልና ተለይቶ ስለማገልገል መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል የሚለውን ልታስረዳኝ ብትችል ደስ ይለኛል፡፡ እኔ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ ብርሃናችሁ በሰው ሁሉ ፊት ያብራ ይላል ብዬ ባልኩት ላይ ምንም አስተያየት ያልሰጠህበትም ለምን እንደሆነ ባውቅም ደስ ይለኛል፡፡ አንተ ሳላስበው ብዙ ጻፍኩ ከስራ ድክም ብሎኝ ስለገባሁ ይሄን ያክል እጽፋለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር በል ሳለም ሁን፡፡

   ደቂቀ አቡዬ ነኝ፡፡

   Delete
  3. እኔም አሁን ከጠቀስክልኝ በመነሳት የተስማማንባቸው ሃሳቦች የምላቸው ፡-
   - ምድረ በዳ ማለት ገዳም መሆኑን ከላይ ባሰፈርካቸው ቃሎች ስለ ገዳመ ቆሮንቶስ ፣ አይሁድ በረሃ በጠቀስኩት ምክንያት መሠረት አልተቃወምክብኝም
   - አሁንም “ክርስትናቸውን በቻሉት መንገድ ሁሉ እንዲያስተላልፉ ክርስትናቸው ያስገድዳቸዋል” ስትለኝ በገዳም ፣ በዋሻና በጢሻ አላስተማሩም ማለትህ አይደለም ፡፡ አገላለጻችን ይለያይ እንጅ አጠቃላይ ሃሳባችን አንድ ነው ፡፡
   - አንድም ሆነ ሁለት መጽሐፍ ተጽፎ ለቤተ ክርስቲያን መተላለፉን አልካድክም ፡፡ አስረጅ የምቆጥረው “አንደንድ እግዚአብሔር የባረካቸው ሰዎች የጻፏቸው መልካም ሐሳብ የያዙ ጽሑፎች መኖራቸውን አልዘነጋሁም” የሚለውን ቃልህን ነው

   ለጥያቄህ መልስ ይሆነኝም ዘንድ ደግሞ እንዲህ ጽፌአለሁ ፡-
   - በሕዝብ መሃል ሆኖ ስለ ማገልገልና ተለይቶ ስለማገልገል ፣ መጽሐፍ ብርሃናችሁ በሰው ሁሉ ፊት ያብራ ይላል ስላልከው ፡፡ አዎ ይላል ፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ እንደ ስጦታው ብቻ ማገልገል አለበት እላለሁ ፡፡ ትንቢት ተናጋሪ ፣ ሰባኪ ፣ መጽሐፍ ተርጓሚ ፣ የደዌ ፈዋሽ … ብሎ የእግዚአብሔር ሥጦታው የተለያየ መሆኑን መጽሐፍ በተለያየ ቃል ይነግረናል ፡፡ ሰባኪው ጸሃፊ መሆን አይችልም ፡፡ በልሳን ተናጋሪም ባለ ትንቢት መሆን አይችልም ፤ ስጦታው አይደለምና ዘማሪው መምህር መሆን አይችልም ፡፡ የእኛ አገር ግን ከትምህርቱ ይልቅ የግል ጥቅሙና ከርስ መሙላቱ ፣ ኑሮን ማደላደሉ ስለሚያመዝንብን ፣ በስጦታችንም ፣ ያለ ስጦታችንም ሁሉን እንያዝ ፣ ሁሉንም እናዳርስ ስንል ስጦታችንን በውል ሳንገነዘበው በከንቱው እንደክማለን ፡፡ በመሆኑም ገዳም ያሉትም ግለ ሰዎች በተሰጣቸው ስጦታ እያገለገሉን እንደሆነ እመሰክሪለሁ ፡፡ ከገዳም ወጥተው ጳጳስ የሆኑ አውቃለሁ ፤ ከገዳም ወጥተው ወንጌልን የሰበኩ በዕድሜዬ በተደጋጋሚ አጋጥመውኛል ፤ ሁሉን አግኝቼ ባላነበውና በቋንቋ ልዩነት /ግዕዝ ስለሆነ/ ባልረዳውም ካነበብኳቸውና ከተረዳሁዋቸው ውስጥ መንፈሳዊ ይዘት እንዳላቸው አውቃለሁ ፡፡

   Delete
  4. በቅድሚያ የተስማማሁባቸው የመሰሉህን ሐሳቦች ለማቅረብ ብሞከር የተሻለ ነው ብዬ አሰብኩኝ፡፡ ምክንያቱም አንተም በመጀመሪያ ያሰፈርከው እሱኑ ነውና፡፡

   ‹‹ምድረ በዳ ማለት ገዳም መሆኑን ከላይ ባሰፈርካቸው ቃሎች ስለ ገዳመ ቆሮንቶስ ፣ አይሁድ በረሃ በጠቀስኩት ምክንያት መሠረት አልተቃወምክብኝም›› ስላልከው አለመቃወም መስማማት ሆኖ የሚታሰብህ ከሆነ አንተም እኔ ካቀርብኳቸው ሐሳቦች ውስጥ ብዙና ብዙ ነገሮችን አንስቼ በእነዚህ ነገሮች ላይ ተመሳሳይ ሐሳብ አለን ማለት ነው ወይም ሐሳቤን ተቀብለሃል ማለት ነው ብዬ ብተረጉም ትክክል ነኝ ማለት ነው?

   ‹‹አሁንም “ክርስትናቸውን በቻሉት መንገድ ሁሉ እንዲያስተላልፉ ክርስትናቸው ያስገድዳቸዋል” ስትለኝ በገዳም ፣ በዋሻና በጢሻ አላስተማሩም ማለትህ አይደለም ፡፡ አገላለጻችን ይለያይ እንጅ አጠቃላይ ሃሳባችን አንድ ነው›› ላልከኝ እኔ እንዲያስተምሩ ክርስትናቸው ያስገድዳቸዋል ያልኩት አንተ በገዳም ያሉት ወንጌልን ማስተማራቸውንና በገዳም መሆናቸውን አስተሳስረህ ታላቅ ገድል እንደሆነ አድርገህ ልታሳየኝ ስትሞከር ነው፡፡ ይሄማ የመብት ጉደይ ሳይሆን ግዴታ ነው የሚለውን እንድታየው ለማድረግ ነው የሞከርኩት፡፡ አንድ ሰው የትም ሆነ የት ስላዳነው ጌታ እንዲመሰክር ክርስቲያን መሆኑ ብቻ ያስገድደዋል ነው ለማለት የሞከርኩት እንጂ በዚህ መልኩ ልክ ነህ ማለቴ አይደለም፡፡

   ‹‹አንድም ሆነ ሁለት መጽሐፍ ተጽፎ ለቤተ ክርስቲያን መተላለፉን አልካድክም ፡፡ አስረጅ የምቆጥረው “አንዳንድ እግዚአብሔር የባረካቸው ሰዎች የጻፏቸው መልካም ሐሳብ የያዙ ጽሑፎች መኖራቸውን አልዘነጋሁም” የሚለውን ቃልህን ነው›› ስላከው ደግሞ ሰዎች በአንድም በሌላም መንገድ ገዳም ይገባሉ፡፡ ነገር ግን ገዳም መኖራቸው ሳይሆን የሚያድናቸው በክርስቶስ ኢየሱስ ማመናቸው መሆኑን ሲረዱት በገዳም ቆይታቸው ያወቁትን ታላቅ የጽድቅ መንገድ ሁሉም እንዲያውቅላቸው በቃል ሊያስተምሩ በጽሑፍ ሊያስተላልፉ ይሞክራሉ፡፡ ምስክር ጥራ ካልከኝ አቡነ አስጢፋኖስንና ልጆቻቸውን እጠራልሃለሁ፡፡

   ሌላው ላቀረብኩት ጥያቄ የሰጠኸኝ መልስ ነው፡፡ በመልስህም ስጦታ ልዩ ልዩ መሆኑን አስፍረኽ ‹‹በመሆኑም ገዳም ያሉትም ግለ ሰዎች በተሰጣቸው ስጦታ እያገለገሉን እንደሆነ እመሰክራለሁ›› የሚል ሐሳብ አስቀምጠኻል፡፡ ይህን አባባልህን ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ በሚለው በተለመደው ብሂል ብተቸው ቅር ይልህ ይሆን? ምክንያቱም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው ብለህ የጳውሎስን መልእክት መነሻ በማድረግ ልትሞግተኝ ስትሞክር በጳውሎስ መልእክት ውስጥ ገዳም መግባት የሚል ነገር በስጦታ መልኩ እንዳልሰፈረ ስላላወክ ነው ብዬ ለመቀበል ተቸግሬአለሁና ነው፡፡ ገዳም መግባት መንፈሳዊ ሆኖ በቅዱስ መጽሐፍ የተጠቀሰበት ምንም ዓይነት ስፍራ ስለሌለ ከመጽሐፍ ቅዱስ ምንም ስፍራ ጠቅሰህ ልታሳየኝ አትችልም፡፡ ስጦታ ያልከውም ቢሆን አንድ ሰው በሰው መካከል ሆኖ በሚያገለግልበት ወቅት ስለሚኖረው ሁኔታ እንጂ ከሰው ተለይቶ በበረሃ መኖር እንደ ስጦታ አድርጎ ያስቀመጠበት ምንባብ አይደለም፡፡ ‹‹በዓለም ዘጅም እድሜ አለው ተብሎ የሚገመተው ሃይማት በዓለም የተለዩ የእመነት ክፍሎች ከቤተሰብ ተለይቶ መመነን ወይም የባህታዊነት ኑሮ ወደ ሁሉም ሃይማኖቶች ተሰራጭቶ ኑሮ በበረሃ የሚል ትምህርት የጀመሩትና የስርዓቱ ጀማሪዎች ናቸው›› ብሎ ቡድሂዝምን በመጥቀስ የባቢሎን ምስጢር በተባለው መጽሐፍ በገፅ 194 ላይ የሰፈረውን እንዴት ታየዋለህ? በሚለው ጥያቄ ነገሬን ልቋጭ፡፡
   ደቂቀ አቡዬ ነኝ

   Delete
 31. ዘበነ ማለትኮ እድሜልኩን ስለጴንጤ ብቻ እንደለፈለፈ የኖረ ሰዉ ነዉ፡፡ ስብከት ማለት ጴንጤን ማብጠልጠል ብቻ ይመስል ነጋዴዉ ዘበነ ልክ ዳንኤል ክብረት ስለ ተሀድሶ ካልተናገረ ያልሰበከ እንደሚመስለዉ ሁሉ መምህር ተብዬዉ ዘበነም ስለጴንጤ እያቀነቀነ የአድማጭ ጆሮ ፍለጋዉን ቀጥሎበታል፡፡ አንድ ሰዉ መምህር ተብሎ ሲሰየም ወንጌልን ሊሰብክ፣ ሊያስተምርና ሊመክር እንጅ አነድን የእምነት ተቋም በማብጠልጠል ብቻ ዘመኑን ይጨርሳል? ነጋዴዉ ዘበነ ግን ከ10 ዓመታት በላይ ሲያደርገዉ የነበረዉ ይህንኑ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከእሱ በቀር ሌላ ተቆርቋሪ የሌላት የሚመስለዉ ዘበነ ለራሱ ቢዝነስና ካሴት ማሻሻጫ ሲል ብቻ የሰዉ ጆሮ ይኮረኩራሉ ያላቸዉን ርዕሶች እየመዘዘ ከመዘባረቅ በቀር ከእሱ ትምህርት አንድም ፍሬ ያለዉ ነገር ተገኝቶበት(ሰዉን የሚያስተምርና የሚያንጽ ስራ ሰርቶ) አያዉቅም፡፡

  ReplyDelete
 32. ዘበነ ማለትኮ እድሜልኩን ስለጴንጤ ብቻ እንደለፈለፈ የኖረ ሰዉ ነዉ፡፡ ስብከት ማለት ጴንጤን ማብጠልጠል ብቻ ይመስል ነጋዴዉ ዘበነ ልክ ዳንኤል ክብረት ስለ ተሀድሶ ካልተናገረ ያልሰበከ እንደሚመስለዉ ሁሉ መምህር ተብዬዉ ዘበነም ስለጴንጤ እያቀነቀነ የአድማጭ ጆሮ ፍለጋዉን ቀጥሎበታል፡፡ አንድ ሰዉ መምህር ተብሎ ሲሰየም ወንጌልን ሊሰብክ፣ ሊያስተምርና ሊመክር እንጅ አነድን የእምነት ተቋም በማብጠልጠል ብቻ ዘመኑን ይጨርሳል? ነጋዴዉ ዘበነ ግን ከ10 ዓመታት በላይ ሲያደርገዉ የነበረዉ ይህንኑ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከእሱ በቀር ሌላ ተቆርቋሪ የሌላት የሚመስለዉ ዘበነ ለራሱ ቢዝነስና ካሴት ማሻሻጫ ሲል ብቻ የሰዉ ጆሮ ይኮረኩራሉ ያላቸዉን ርዕሶች እየመዘዘ ከመዘባረቅ በቀር ከእሱ ትምህርት አንድም ፍሬ ያለዉ ነገር ተገኝቶበት(ሰዉን የሚያስተምርና የሚያንጽ ስራ ሰርቶ) አያዉቅም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. የአንተን በመጠኑ የምደግፈው መልዕክት ነው ፡፡ መውቀስና መወቃቀስ ብቻ አያስተምረንም

   Delete
 33. ገዳም ትርጉሙ ሰው የማይኖርበት ፣ ምድረ በዳ ፣ ጭው ያለ ቦታ ማለት ነው

  በገዳም መኖር አልሆንለት ሲለው ፣ ምንኩስናን ሉተር ስለተቃወመ ብቻ ፣ ተከታዮቹ ታሪክን ያበላሹ መስሏቸው ከሂንዱይዝምና ከቡድሂዝም የተወረሰ ልማድ ነው በማለት እየተናበቡ ይጽፋሉ ፡፡ ለእኔ ይኸኛውን አባባል ከታሪክ አኳያ ከታየ አያስኬደንም እላለሁ ፡፡ ምክንያቱም አይሁዳውያን በተጋዙበት ዘመን ቀስመው መጡ እንዳንል ፣ የእሥራኤላውያን ስደት ከፋርስ አላለፈም ነበርና ነው ፡፡ በማራኪዎቻቸው ተግዘው የሄዱ ሰዎች ወደ ህንድና ቻይና አልፈው የሚሻገሩበት ምንም ምክንያት የለም ፤ ነጻነቱም የላቸውም ፤ ታሪኩም በመጽሐፍ አልተጠቀሰም ፡፡ ከሌላ ጐኑ ሲፈተሽ ደግሞ አይሁዳውያን በእምነታቸው የሚኮሩ ፤ መከራና ፈተና ቢጸናባቸው እንኳን የእግዚአብሔር ምርጥ ዘር ነን ብለው የሚታበዩ ስለሆኑ ፣ የሌላውን ሃይማኖት መውረስ ቀርቶ ከመጽሐፋቸው ጥቂት ወጣ ያለውን ትርጓሜ እንኳን አይቀበሉም ፣ ሌላው ቀርቶ ከጐሳቸው ውጭም ጋብቻን አይፈጽሙም ፡፡ ስለዚህም ነው አሁን እሥራኤል ዝርያዋን ከያለበት መለቃቀም የቻለችው ፡፡ በግብጽ ለአራት መቶ ዓመታት ሲኖሩ ፣ ከሞላ አምልኮ አንድም ልማድ ወደ ባህላቸውና አምልኳቸው እንዳላቀላቀሉ መመልከቱ ብቻ በቂ ነው ፡፡ ለሃይማኖታቸው ቀናዒነታቸውን የሚያስረዳን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰፈረው የፈሪሳውያንና የሰዱቃውያን ወግና እምነትም ጭምር ነው ፡፡ በሌላ በኩልም ደግሞ ህንዶችና ቻይናውያን ወረራ ፈጽመው መጥተው ይሆናል እንዳንል ፣ ያን የመሰለ ታሪክ የለም ፡፡ የግዛት አስተዳደራቸው እንዲያውም ከአካባቢያቸው አላለፈም ፡፡ ይባስ ብሎ ጃፓን እንደወረራቸው ተጽፏል ፡፡ ስለዚህ ከታሪክ አንጻር ሁለቱም መንገዶች የተዘጉ ናቸው ፡፡

  ከእምነት አኳያም ከቃኘነውም ለመቀበል ይከብደኛል ፡፡ በዘመን መቀዳደም ከሆነ አወረሰና ወረሰ የሚባለው ፤ ቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ በቀጥታ አይጠቀስ እንጅ ልምምዱ የተጀመረው በሙሴ ዘመን ነው ፡፡ በሲና ተራራ ለአርባ ቀናት ሰው ከሌለበት በጾምና /ያለ ውሃና ምግብ/ በጸሎት ያሳለፈው ጊዜ ለእኔ የገዳም ህይወት ነው /ዘጸ 24፡12 ፤ 34፡28/፡፡ ላክርረው ካልኩ ደግሞ አዳም ጥፋትን አጥፍቶ ቅጠልን ለብሶ ከፈጣሪ የተሸሽገበት ዳዋ /ይጸልይ እንደነበር ትውፊት አለ/ የገዳም ገጽታ አለው ፡፡ ጸጋው በመገፈፉ ምክንያት የሚመገበውም ከአካባቢው ያገኘውን እንደ ፍየል እየለቃቀመ ነበር ፡፡

  ወደዚህ እየቀረብን ስንመጣ ደግሞ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ኤልያስ የተሸሸገበት ፈፋ ፣ የተመገበው የቁራ ትራፊ የገዳማዊ ህይወት ማሳያ ነው /1 ነገ 17፡2-7/ ፡፡ በነቢያቱ ዘመንም ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ተጥሎ ከአራዊት ጋር ተፋጦ ያደረበት የፈተና ዕለት የገዳም ህይወት ምን እንደሆነ የሚያመላክት ነው /ዳን 6፡16-22/ ፡፡ በሐዲስ ዘመን ስንመጣም ዮሐንስን ያሳድጉ የነበሩት ፣ በገዳም ይኖሩ የነበሩ መነኮሳት ናቸው ፡፡ ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ በመንፈሰ የተወሰደው ቀድሞ ወደ ተመሠረተ ገዳም ነው ፡፡ መቃወም የሚያስፈልግ ቢሆንማ ፣ ጌታ አንድ ቃል ሳይነግረን ወይም ሳያስጠነቅቀን አይቀርም ነበር ፡፡ ስለዚህም ኢየሱ ክርስቶስን መምሰልና መከተል ማለት ቅሌን ጨርቄን ሳይሉ ዓለምን ክዶ እንደርሱው በየጢሻውና በተራራው ሲጸልዩ ማደርን ይጠይቃል ፡፡ ለምግብ ፣ ለልብስ ፣ ለማደሪያ ፣ ስለኑሮ አለማሰብን ይፈልጋል ፡፡ የተስፋ ቃሉም በማቴዎስ 19፡29 ሰፋሯልና ማየት ይቻላል ፡፡ የአገራችን የምንኩስና ምንጭ እንግዲህ ግብጾችና የቀደሙት የሃይማኖት አባቶች ናቸው ፡፡ ይኸንን የምታውቀው ስለሚሆን በዚሁ ላብቃ ፡፡
  ገዳማዊነት ኃጢአት አይደለምና በሌሎች ችግሮች ላይ እናተኩር ፡፡ ሰላም ሁንልኝ ፡፡

  ReplyDelete
 34. ዛሬ ያነበብኩት የአንተ መልእክት ‹‹ገዳማዊነት ኃጢአት አይደለምና በሌሎች ችግሮች ላይ እናተኩር ፡፡ ሰላም ሁንልኝ›› በማለት በመልካም ምኞት የሚያበቃ ነው፡፡ እኔም ሰላምህ ይደረሰኝ ብዬአለሁ፡፡ ከሰላምታው በፊት ግን ገዳማዊነት ሃጢአት እንዳልሆነ እኔ ያሰፈርኩትን መነሻ በማድረግ በዚህ ጉደይ ላይ መነጋገራችን አስፈላጊ እንዳልሆነ ልታሳየኝ እና ውይይታችንን ወደተሻለ ነገር እንዲዞር መፈለግህን ተረድቻለሁ፡፡ ከዚህ በፊት የተነሳንበትን ነጥብ ትተን መሄዳችንን በመንገር አሁን ያለንበት ነጥብ ውስጥ በአንተ ገፋፊነት መግባታችንን አስፍሬ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን ወደሌላ ርዕስ በመሄዳችን የሚከፋኝ አይደለሁም፡፡ ግን ደግሞ ሁለት ስጋቶች አሉኝ፡፡ አንደኛው የብሉጎ ባለቤቶች በእኔና በአንተ ግላዊ ውይይት ምን ያህል ደስተኛ ናቸው የሚለው ሲሆን ሁለተኛው አሁንስ በምንጀምረው ውይይት እስከመደምደሚያው መዝለቃችንን በምን እርግጠኞች መሆን እንችላለን የሚለው ነው፡፡ አሁን ባሰፈርካቸው ነጥቦች ዙሪያ ለማለት የምፈልገው ነገር ቢኖርም ግን ደግሞ የመወያያ ርዕሱ የማይቀጥል ከሆነ በእርሱ ላይ ሐሳብ መስጠቱ ምንም ስሜት አይሰጥም በሚል ላዘገየው ወደድኩ
  እስኪ እባክህ ከላይ በነሳኋቸው ሁለት ስጋቶቼ ላይ ምን ዓይነት አስተያየት እንዳለህ አሳውቀኝ፡፡ ከዚህ መልስህ በኋላ አሁን በይደር ባስቀመጥኳቸው ነጥቦች ዙሪያ የምልህ ሊኖረኝ ይችል ይሆናል፡፡
  ደቂቀ አቡዬ ነኝ

  ReplyDelete
 35. ይህን ጽሁፍ ሳነብ አንድ ነገር ትዝ አለኝ። መምህር ዘበነ አሜሪካ እንደመጡ ..ገና ማስተማር በጀመሩ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የመናፍቃን አዳራሽ ርቃኑን ቀረ። ሰዉ ሁሉ ተገልብጦ ወደ ኦርቶዶክስ መጣ። ያን ጊዜ የመናፍቃኑ ፓስተሮች "ዘበነ የሚባል ጥቁር ሰይጣን መጥቶብናል - ጸልዩ" ሲሉ አወጁ። ያቺ ነገር ዛሬ እዚሁ መናፍቃን ብሎግ ላይ መደገሙ .. አሁንም ሰይጣን በመምህር ዘበነ ኦርቶዶክሳዊ ስብከት እንቅልፍ እንዳጣ ይመሰክራል። የራሳችሁን መናፍቅነት ጠበቅ . የኛ የኦርቶዶክሱን ለቀቅ ብታደርጉትስ?

  ReplyDelete
 36. YASAZNAL
  ETHIOPIAWIN YE ETHIOPIA ORTHODOX TEWAHDO TEKETAYOCH MNEW YIHIN YAKIL ERS BERSACHUHU YEMTWEKAKESU : YGERMEGNAL HULACHU ORTHODOX NEN TLALACHUHU ENIEM ENDA MEHONACHU NEBER YEMIASBEW:GIN MIN ALEBET LEGNA BERUKU TMHRTACHUHUN LEMNKETATEL ERITRAWIAN LBACHIN AWDKEN LEMISETEW TMHRT BNKETATEL: AWO YEGNAM ALEN TECHEMARIM YENANTEN : SLEZI LEMENAFKANU MESALEKYA ATHUNU EBAKACHU

  ReplyDelete
 37. "ማኔ ቴቄል ፋሬስ"

  ReplyDelete
 38. zebene seytan new yetsfew etdenaget

  ReplyDelete
 39. በጣም ያሳዝናል እንዲያውም እናንተ እራሣችሁ ከ መ/ር ዘበነ ለማ ብዙ መማር ይጠበቅባችኃል.
  በተቻለ ራሳችሁን መርምሩ……………………….

  ReplyDelete
 40. ደንቆሮ ሰው ቢነግሩት ስለማይገባው ጥሩ መምህርን አይችልም አያውቅም ከማለት ወደኋላ አይሉም፡፡አባ ሰላማ ማለት ሰላም የሌለው የሐሜት የሽንገላ ብሎግ ነው!!!

  ReplyDelete
 41. የተማረን የሚያውቅ በአብዛኛው የተማረ ሰው ነው። መምህር ዘበነ አስተምህሮታቸው ስሜት የተሞላበት እንጂ ፍሬ ነገሩ ብዙ ህጸፅ አለበት። ለምሳሌ ስለ መልከፄዴቅ ባስተማሩት ትምህርት ላይ … መልከፀዴቅ ኢትዮጵያዊና የእዳም አፅም ጠባቂ ነው ብለዋል። ግን እኔ አንድ ሰው ተው የሚለው የለም? ለጴንጤዎቹ እኮ መሳቂያ አደረገን። በምን ሂሳብ ነው … ከየትኛው መፅሐፍ ነው መልከፄዴቅ ኢትዮጵያዊ የሆነው? እንዴ ምነው…ይኴን ያህል እኮ ደንቆሮ አይደለንም። መሃይም ሴቶችን ሰብስቦ ምሁር መምሰል እኮ ራሱን የቻለ መሃይምነት ነው። አንድ ዶ/ር የተባለ የቤ/ክ ሊቅ እንዲህ አይነት ገለባ ትምህርት ያስተምራል። ምን በወጣኝ ቁጭ ብዬ አፈታሪክ እሰማለሁ? በቅዱሳት መፅሐፍት ያልተጻፈን ማስተማር መናፍቅነት ነው። ከውጪ መናፍቅ እያለ እያወገዘ ራሱ መናፍቅ ሆኖ ቁጭ አለ አይደል እንዴ? ምነው ጃል መካሪ አበጁለት እንጂ። መምህር መሆን ሃላፊነት አለበት…ብሄራዊነት ስሜት መጥፎ ባይሆንም ቅዱስ ቃሉ ውስጥ ቀላልቅሎ ማስተማር ግን ነውር ነው። ምነው ጃል!

  ReplyDelete