Wednesday, June 6, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን በክርስቶስ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያምናል እንዴ?

በ1996 ዓ.ም በማኅበረ ቅዱሳን አሳታሚነት የታተመና በ30 ብር ሲሸጥ የነበረ፣ በአሁኑ ሰዓት ብዙዎች እየፈለጉት ያለ ግን ከገበያ ላይ የጠፋ፣ አሮጌ ተራ ከተገኘ ከ60 እስከ 80 ብር ድረስ እየተሸጠ ያለ አንድ መጽሐፍ አለ፡፡ መጽሐፉን ያዘጋጁት ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ ሲሆኑ፣ መጽሐፉን ያሳተመው ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ መቼም መጽሐፉ ከመታተሙ በፊት መጽሐፉን መርምሮ እንዲታተም የፈቀደው፣ ወደፊት ማኅበሩ ቤተክርስቲያኗን ሙሉ ለሙሉ ሲቆጣጠር (እንደ እርሱ ሐሳብ) የሊቃውንት ጉባኤን ተክቶ እንደሚሠራ በማኅበሩ የሚጠበቀው የማኅበሩ ኤዲቶሪያል ቦርድ ነው፡፡

መጽሐፉ ታትሞ ለገበያ የቀረበ ሰሞን በማኅበሩ አመራሮችና አባላት መካከል አንዳንድ ጭቅጭቅ ተነሥቶ ነበረ፡፡ ብዙዎቹ የማቅ አባላት “እንደዚህ ከሆነማ እኛ ከተሀድሶዎችና ከመናፍቃን በምን ተለየን? እንዴት እንዲህ አይነት ጽሑፍ ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ያሳትማል” የሚል ማጉረምረም ውስጥ ለውስጥ ነበረ፡፡ አንዳንዶቹም የማኅበረ ቅዱሳንን “የሊቃውንት ጉባኤ” ማለት ኤዲቶሪያል ቦርዱን ነበር ተጠያቂ ያደረጉት፡፡ ለዚያም ይመስላል፤ የታተመው ታትሟል ከዚህ በኋላ ግን አይታተምም የሚል አቋም ተወስዶ ይኸው መጽሐፉ ከገበያ ውጪ ሆኖ ሰዎች ከአሮጌ ተራ በውድ ዋጋ ለመግዛት የተገደዱት፡፡ መጽሐፉ እጅግ ተፈላጊ ሆኖና ነጋዴው ማቅም ጥሩ ገቢ የሚያጋብስበት ሆኖ እያለ፣ እንዴት አስችሎት መጽሐፉን ሳያሳትመው ቀረ? ቢባል፣ በዋናነት ከዚህ ቀደም የቤተ ክርስቲያን ልጆችን «መናፍቅ ሆነዋል» በማለት የሚከስበት ትምህርት በመጽሐፉ ውስጥ ስለሚገኝ እንዳይጠየቅበት በመሥጋት ነው፡፡

የመጽሐፉ አዘጋጅ ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ መጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት ራሱን ችሎ በአንድ ወገን ትውፊታዊው አመለካከትም ራሱን ችሎ በሌላ ወገን እንዲቀመጥ ማድረጋቸው፣ እግዚአብሔር አእምሮውን  የከፈተለት ሰው ወደ ወንጌል እውነት እንዲደርስ የሚያደርግ ስለሆነ መጽሐፉ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡ በመጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነቱን ያስቀምጣሉ፡፡ ደግሞ ትውፊቱን ለመጠበቅና ከቤተክርስቲያኒቱ ትምህርት ላለማፈንገጥ ትውፊታዊውን ነገር አስከትለው ያቀርባሉ፡፡ ለምን እንዲህ አደረጉ? መጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት ለብቻው ቢቀመጥና ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት ጋር የሚጣላው አንዳንዱ ትውፊታዊ ነገር ቢታለፍ ተቃውሞ ሊነሳባቸው ይችላል፡፡ ማቅም አያሳትምላቸው ይሆናልና ተቃውሞውን ለመቀነስ ነው ይህን ስልት የተከተሉት። ይሁን እንጂ በእውነቱ የጠገበ ሰው ከእውነቱ ጋር ወደሚጣላው ትውፊት እንዴት ሊሄድ ይችላል? ይህ ማለት ጣፋጭ መብል በልቶ የጠገበን ሰው በዚያ ላይ መናኛ ምግብ ጨምረህ ብላ፣ በሌላ አማርኛ በዶሮ ወጥ ላይ አሹቅ እንደማለት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስና ትውፊት መስማማት አለባቸው፡፡ ማለትም ትውፊት ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር መስማማት አለበት፡፡ ባይስማማ እንኳን መጣላት የለበትም፡፡ እንዲህ ከሆነ ብቻ ነው ቤተ ክርስቲያን ትውፊትን የምትቀበለው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን አባ ጳውሎስን በጥንተ አብሶ አስተምህሮ ለመክሰስና ይሉኝታ ለማስያዝ የጠቀሰውንና «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሥርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት» የተሰኘውን መጽሐፍ እዚህ ላይ እኔም ልጥቀስ፡፡ ስለ ትውፊት እንዲህ ሲል አስፍሯል። ‹‹ትውፊት ከቅዱሳት መጻሕፍት ምሥጢርና ትርጉም ጋር የሚቃረን አይደለም፡፡» (ገጽ 47) ይህ አባባል ቤተክርስቲያኗ ትውፊትን ብትቀበልም የምትቀበለው ትውፊት ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምርት ጋር የሚስማማ እንጂ የሚቃረን አለመሆኑን ይገልጻል። ስለዚህ ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ ከእውነቱ ቀጥሎ የጠቀሷቸው አንዳንድ ትውፊታዊ ነገሮች ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ጋር መስማማታቸውና አለመቃረናቸው መፈተሽ ይኖርበታል፡፡

ማቅ የዚህ መጽሐፍ አዘጋጅ ባይሆንም መጽሐፉን በማሳተሙ በመጽሐፉ ሐሳብ ሙሉ በሙሉ ተስማምቷል፡፡ ከዚህ በፊት አንዳንድ መንፈሳዊ መጽሐፍ ያሳተሙ የቤተክርስቲያን ሰዎች በዚህ መጽሐፍ ከሰፈረው እውነት እጅግ ያነሰ ይዘት ያላቸውንና ጥቂት እውነት ለአይነት ጣል ያደረጉበትን መጽሐፍ አልሸጥም ብሎ የመለሰባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ፡፡ የአባ አበራን መጽሐፍ ግን ራሱ ነው ያሳተመው፡፡ ማቅ እንዲህ ሲያደርግ በመጽሐፉ ያምናል ማለት ነው? ወይስ በማሳተሙ እንጂ በዝግጅቱ ውስጥ የለሁበትም ይል ይሆን? ወይስ ሳያስተውለው አምልጦት? መጽሐፉ ከገበያ እንዲወጣ የተደረገውስ ለምንድን ነው? ሰዎች ከትውፊት ጋር ተደባልቆም ቢሆን በያዘው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ተሐድሶ ሕይወት እንዳያገኙና የባህል ሃይማኖት ተከታይ ሆነው እንዲቀሩ በማሰብ ነው? የማቅ አባላትና ደጋፊዎች በአስተያየቶቻችሁ ብዙ እንደምትሉ እጠብቃለሁ፡፡

አንድ እውነት ግን አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል፡፡ ማቅ በመጽሐፉ የሚያምን ከሆነ የቤተክርስቲያን ልጆችን «መናፍቅ» እያለ ለምን ያወግዛል? በቅርቡ በእርሱ በተመራው «ሲኖዶስ» አስወገዝኳቸው ብሎ በልሳኖቹ በፍትህ ጋዜጣና በዕንቁ መጽሔት ላይ ዜናና ሀተታ ያሰራባቸው የቤተክርስቲያን ልጆች እኮ ሌላ ትምህርት አላስተማሩም፤ ያስተማሩት ትምህርት ተጠቃሎ ሲቀርብ በአብዛኛው ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ ተመስርተው «ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት» በሚል ርእስ በጻፉት መጽሐፍ ላይ የገለጹትን እውነት ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጨውን ትውፊት ካልሆነ በቀርም የተቃወሙት ነገር የለም፡፡ 
እስኪ ለዛሬ ሊቀ ጉባኤ አባራ በመጽሐፉ መግቢያ ገጽ 12-13 ላይ ያሰፈሩትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ልጥቀስና እስካሁን ያተትኩት እውነት ወይም ሐሰት መሆኑን አንባቢው ይፍረድ፡፡

ከጸጋ ታደለ
መግቢያ
የክርስትና ሃይማኖት የፍቅር[1] ሃይማኖት ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ለእኛ ያደረገው ሁሉ በፍቅር ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው፡፡ በመጀመሪያ ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ መፍጠሩ እግዚአብሔር ሰውን ከስነፍጥረት ሁሉ ለይቶ እንዳከበረውና እንደወደደው ያስረዳል፡፡ ዳግመኛም ከጥንተ ተፈጥሮ በበለጠ አኳኋን ሰው እግዚአብሔርን (እግዚአብሔር ሰውን ባለ በቀና ነበር) ምን ያህል እንደወደደው በልጁ በፈጸመው የማዳን ስራ በተጨባጭ ተገልጿል። ስለዚህ የሃይማኖታችን ታሪክ በፍቅር ተጀምሮ በፍቅር ሥራ ተፈጽሟል፡፡

የክርስትና ሃይማኖት ምሥጢር ያልገባቸው የጥንት አይሁድ ግን በኦሪት ሕግ ላይ ብቻ ተስፋቸውን ስለጣሉ በእርሱም ላይ ከፍተኛ እምነት ስላላቸው የጽድቅና የመዳን ሁሉ መሠረት የሕግ ሥራን በመሥራት ብቻ እንደሚገኝ በአጽንኦት ያስተምሩ ነበር፡፡ በመሆኑም የሐዋርያውን የቅዱስ ጳውሎስን የወንጌል ሃይማኖት ትምህርት አጥብቀው ይቃወሙ ነበር፡፡  ሐዋርያው ግን ሰው በሕግ ሥራ ሳይሆን እስከ ሞት ድረስ በወደደን በክርስቶስ በማዳን ሥራው በማመን የሚጸድቅ መሆኑን በልዩ ልዩ መንገድ በማስረዳት ለተቃሚዎች ተገቢውን ምላሽ ሰጥቷል፡፡ በታሪክም ሆነ በተመክሮ እንደምናውቀው ሰው በክርስቶስ ላይ ባለው እምነቱ ይጸድቃል ይድናል እንጂ የሙሴን ሕግ በመፈጸሙ ወይም በራሱ ጥረትና ሥራ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ ሰው ሕግን መፈጸም ስለተሣነው ሕጉም ሰውን ለማዳን ስለአልተቻለው ሰውን ወዳጅ እግዚአብሔር ሰው ሁሉ በእምነት የሚጸድቅበትንና የሚድንበትን መንገድ በልጁ አዘጋጀ፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔር ቸርነትና ፍቅር ሰው የመዳኑን ጸጋ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲሁ ያለ ዋጋ እንዲያገኝ ሆነ፡፡ ‹‹ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ›› በሰው ጥረትና ሥራ ስላልሆነ ማንም ሰው በሥራው ሊመካ አይችልም (ኤፌ. 2፣8-9)፡፡
‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥
በፍቅር የሚሠራ እምነት››
የመዳናችን መሠረት እምነት ነው ተብሎ ቢነገርም ‹‹እምነት›› ደግሞ ብቻውን እንዳልሆነ በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰከረ ነው፡፡ የክርስትና እምነት ከኦሪቱ ሥርዓትና ባሕል ከፈሪሳወያን ወግና የሕግ ሥራ ሁሉ የተለየ ይሁን እንጂ በክርስቶስ ከታዘዘው የፍቅር ሥራ የተለየ አይደለም፡፡ በክርስቶስ የተገኘው የመዳን እምነት ከኦሪት ሥራ እንጂ ከፍቅር ሥራ አልተለያየም፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና›› አለ (ገላ. 5፣6)፡፡ ይህ ቃል የክርስትና እምነታችንን ምንነትና ሁናቴ ይገልጻል፡፡
       
‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ›› የሚለው ቃል በፍቅር የሚሠራው እምነት ምን ዓይነት እንደሆነ ይገልጸዋል፣ ይወስነዋል፡፡ ይህ ቃል ባይኖር የእምነቱና የፍቅሩ ሁናቴና ምንነት አይታወቅም ነበር፡፡ አሁን ግን ከክርስቶስ ጋር አንድ በመሆናችን የእምነቱና የፍቅሩ ዓይነትና ይዘት ምን እንደሆነ? የማን እንደሆነ? እንዴት እንደሆነ? በይበልጥ እንዲታወቅ ሆኖአል፡፡ በክርስቶስ ከሆንን የክርስትናን ሃይማኖት ምስጢር ለማስተዋል እንችላለን፤ ካልሆንን ግን ዓላማውን ስተናል ከመንገድም ወጥተናል፡፡ ስለዚህ በክርስቶስ መሆን ወይም አለመሆን ጥያቄው እዚህ ላይ ነው፡፡ ለዚህም ጥያቄ ከሁላችንም የሚጠበቀው ምላሽና ውሳኔ አዎንታዊና ተግባራዊ እንዲሆን ጥረታችንና ጸሎታችን ነው፡፡
       
እንግዲህ በቅድሚያ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆነን መኖር ያስፈልገናል፤ ይህም ማለት ከእርሱ ጋር እንደ ወይን ግንድና እንደ ቅርንጫፎቹ በፍቅር በመተሣሠር እኛ በእርሱ እርሱም በእኛ በመኖር አንድ መሆን ማለት ነው፡፡ ከእርሱ ጋር አንድ ከመሆናችንም የተነሣ በእርሱ ያለን እምነታችን በፍቅር የሚሠራ እምነት ማለት በክርስቶስ ፍሬ የሚያፈራ እምነት ይሆናል፡፡ ምክንያቱም እምነታችንን የጣልንበት እርሱ ራሱ ፍቅር ስለሆነና እኛንም በፍቅር ሥራው ስላዳነን ብቻ ሳይሆን በእርሱ ያለ ፍቅር በእኛም እንዲሆንና እኛም እንደ እርሱ በፍቅሩ ኖረን እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ስለታዘዝን ነው (ዮሐ. 15፥1-17)፡፡ ፍቅር እንዲኖረን የታዘዝነው እግዚአብሔርን እንድናውቀውና በፍቅሩም እንድንኖር ነው፡፡ ‹‹ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፣ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና›› ተብሎ ተጽፏልና  (1ዮሐ. 4፥8)፡፡ እንግዲህ ይህ በፍቅር የሚሠራ እምነት ካለን ለሰውና ለእግዚአብሔር የሚያስፈልገውን በጐ ሥራ ሁሉ ለማከናወን እንችላለን፡፡ ስለዚህ የክርስትና እምነት ከፍቅር ሥራ ማለት ከበጐ ምግባር ጋር የማይለያይ እንደሆነ እንገነዘባለን (ያዕ. 2፥14-26)፡፡
        ‹‹በክርስቶስ …. ሆኖ›› ሃይማኖትንና ምግባርን ሳይለያዩ ሁለቱንም በአንድነት ማወቅና አውቆም መፈጸም ለክርስቲያን ሁሉ አስፈላጊ ነው፡፡ ከሁሉ በፊት ሃይማኖት ይቀድማል፡፡ ስለሆነም በዚህ መጽሐፍ መጀመሪያ «ትምህርተ ሃይማኖት» ቀርቧል። እሱን በቅድሚያ መማርና ማወቅ ይገባናል፡፡ ዳሩ ግን ክርስትናችን ስለ ሃይማኖት በመማርና በመመራመር፣ በማጥናትና በማወቅ ብቻ አያከትምም፡፡ ምክንያቱም ከላይ እንደጠቀስነው ‹‹እምነት›› ስንል ‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ›› እንዲያው እምነት በተናጠል ብቻውን በእውቀትና በትምህርት ደረጃ ብቻ የቆመ ነገር አይደለም፡፡
       
ስለዚህ ከሃይማኖት ጋር ክርስቲያናዊ ሕይወትና ምግባር በክርስቶስ ምን መሆን እንዳለበት በተግባር የሚገልጽ ትምህርት ተዘጋጅቷል፡፡


[1] እዚህ ላይ ፍቅር ማለት ሰው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅር ሳይሆን እግዚአብሔር ለሰው ያለው ፍቅር ነው። ይህ መለኮታዊ ፍቅር ነው። በክርስቶስ ለኃጢአታችን ስርየትን የሠጠን፥ ለመዳናችን መሰረት የሆነን (1ዮሐ. 4፥10 እና ከ14-16)። ክርስቲያኖች ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሰው የሚያሳዩት የፍቅር አይነት ለመለኮታዊ ፍቅር የሚሰጥ አዎንታዊ ምላሽ ነው። እንግዲህ የክርስቲያኖች ፍቅር ወይም የሚከተሉት የፍቅር አይነት በቋንቋችን ብዙ ጊዜ በተለምዶ  ፍቅር ከምንለው ተራ ነገር ጋር ወይም ከዚህ ዓለም ፍቅር ጋር የማይመሳሰል መሆኑን እናስተውል። እንግዲህ እግዚአብሔር ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት በመለኮታዊ ፍቅር ላይ የተመሰረተ ነው። የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስታን እግዚአብሔር ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት በራሱ በእግዚአብሔር አነሳሽነት የተጀመረ የፍቅር ታሪክ እንደሆነ ታስተምራለች። “God’s relation ship with Man is the story [‘history’] of love in which God took the initiative” H.H.Pop Shinoda III, God and Man. (Cairo, Dar EI Tebaa EI Kawmia, Desmber 2000), pp. 84 ff.

29 comments:

 1. በመግቢያ ርዕስ ሥር ስለሰፈረው ቃለ ህይወት በጣም አመሰግናለሁ ፡፡ ትንሽ የወንጌል ቃል እንዲህ ማከሉ ይልመድባችሁ ብያለሁ ፡፡

  ReplyDelete
 2. In case you post it, as you jammed several of my comments, including on Hailegiorgies's true accounts which I personal know as a heretic.

  You guys and Leke Gubae are completely different. Don't try to cover yourself and your likes of the heretics under the teachings of our beloved late father Leke Gubae. We know your teachings here in the website. Your teachings are protestant and Leke Gubae's is orthodox. Here is a simple analogy. You guys and we do believe in one Holy Bible, but does it mean that we belong to the same faith or follow the same biblical teachings? No and never in history. You see, by taking a common part we and you accept from Leke Gubae's book, don't try to assimilate yourself as if you are teaching the words alike Leke Gubae. You guys say Jesus, 'amalaj'; Leke Gubae maintained, Jesus's Godship and said TEMALAJ and FEREG. So, stick yourself there in your belief of protestantism and leave the words of Leke Gubae for us, the Orthodox.

  ReplyDelete
 3. Ahuns yenante alama men endehone mawek alchalkugnim enante ketadesowochi wegen satihonu atikerum. yemtitsifut batekalayi menfesu tiru ayidelem yemenfesawi ayimesilem timhrt alagegnewubetm 'just westing of time'
  balefew comment aderge alawetachiwutm betam endemtiwashu awekugni commentochin enanti endemtifelegut kalhone besteker atawetutim. Gen sew betekristiyanen yemiyagelegilew lemetsidek kehone enante lemen endezih ayinet sira layi tesemarachiw metsidek atifelgum malet new? betam new yemigermegni. Lemen yemiyatsedk sira atiserum eshi egna melkamen neger man yastemeren? yasazinal!

  ReplyDelete
 4. OMG what is wrong with you?. Apparently you haven't read the whole book or you just want to misinterpret a couple of pages of the book as you mistreatment verses of the bible. Why do you lie that this book is actually written to give answers to questions raised by people like you "tehadeso and menafikan"? To those of you who read this blog for "fun or to see how crazy and desperate this guy is to accuse MK" the book is a true teaching of the Ethiopian Orthodox church and it is about "tselote haimanot, ye-emebetachin milija, sebatu mistrate betekirstian and soon. I wish I can load the book online and make you stop visiting this page again.

  ReplyDelete
 5. MK still uses the book contrary to what you wrote. Here is the evidence:

  http://eotc-mkidusan.org/site/images/stories/pdfs/Temhirte_Hymanot_Meqidim.pdf

  They put it on their site so that every body benefit from the writing of the great writer.

  ReplyDelete
  Replies
  1. መጽሐፉ የሚገኝበትን አድራሻ በማቅረብህ አመሰግንሃለሁ ፡፡ ማቅ ይኸንን መጽሐፍ በነጻ እንዲነበብ በድረ ገጽ ማቅረቡ ስለ እነርሱ ትምህርት ምንነት የሚመሰክር ማስረጃ ነው ፡፡ ከገበያ አጠፉት የሚለውን አቤቱታንም ተራ ሃሜትና አሉባልታ ያደርገዋል ፡፡ አባ ሰላማዎች ግን በራሳቸው እንዲህ ዓይነት የሚያስተምር ጽሁፍ ማዘጋጀት ስለማይችሉ ወይም ከሊቃውንቱ መጽሐፍ በመንተራስ የማቅረብ ልምድ ስለሌላቸው ፣ እንደዚህ ክርስትናን የሚያስተምር ግልባጭ ጽሁፍ የሚያስነብቡበት ሲሶ ገጽ ቢመድቡልን ከወቀሳና ከሐሜት ባሻገር ትንሽ የቃሉን ፍሬ ነገርም እንቃርምበት ነበር ፡፡
   በድጋሚ አመሰግንሃለሁ

   Delete
  2. Anonymous @June 6, 2012 11:46 PM
   እግዚአብሔር ይባርክህ። አባ ሰላማዎችስ አይናቸው ማየት ለምን እንደተሳነው አላውቅም። እስኪ ምንጩን ብቻ ሳይሆን እራሱን አሳይተሃቸዋል ካነበቡትና ከተማሩበት።
   ግን እንዲህ አይነት ሰውን መክሰስና መውቀስ መንግሥተ ሰማያት ያስገባል ያላችሁ ማነ ነው አባ ሰላማዎች? አረ ልብ ይስጣችሁ፤ እራሳችሁን መርምሩ።

   Delete
  3. Thank you very much. I followed your reference and found four additional books (yekiristna meserete emnet 1-4). I am happy I am going to read those books now for free from MK website. Thank you Abaselama bloggers also. Even if you was raise this book to acquisition MK, you help me to dig and read it. You thought for bad, God change it for good. God used you to advertise about the book. Thanks again.

   May God help you to your true religion.
   Libona Yistachihu.

   Welete Amanuel

   Delete
  4. በእምነት ወንድሜ የሆንክ የሆንክ ወንድሜ ፦
   ማያያዣውን (link) ስላካፈልከን ጌታ ይባርክህ:: "ነጋዴው" ማህበርም ምስጋና ያስፈልገዋል:: መናፍቁም መመስገን አለበት:: አለማሰቡ እና መዋሸቱ ለኛ በአንድ ቀን እጅግ የበዛ የቤተክርስቲያናችንን የእምነት ፅሁፎች ስላስገኘልን::

   Delete
 6. በመረጃ የተደገፈ የማንነት ጥያቄ መልስ ሲያገኝ ያሳምናል!!!

  ማ! ማነው? ዓላማው ምንድነው? ለአገርስ ጠቀሜታው? የሚሉት ጥያቄዎች መልስ ያገኙ ቢሆንም በርካታ የዋህ ወገናችን በውሸት ያገር ፍቅርና በሃይማኖት ስም ናላው እስከሚዞር ድረስ የጥፋት ወንጌል ስለተሰበከ ሕዝቡ እውነተኛ የታሪኩን ጅማሬና አመጣጥ እንዴት እንደሆነ እንዲያውቅ እንደዚህ ያሉ መረጃዎች በግልጽ ሊቀርቡለት ይገባልና በርቱ!!!!!

  ከዚህ በተረፈ የእውነተኛ የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች (የተወገዛችሁትን ጨምሮ) መሰባሰብና ለወንጌል ሥራው በጸሎት በማስተማሩና እውነቱን ለሕዝቡ በማስረዳቱና የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የሚያስችል መንፈሳዊ ጉልበት መፍጠርና አብሮ በፍቅር መንቀሳቀስ የሚቻልበት ሁኔታ ለመፍጠር ሁሉን በሚችል አምላክ ታምናችሁ ብትጠናከሩ መልካም ይመስለኛልን ቢታሰብበት??

  የሰላም አምላክ አገራችንን/ቤተ ክርስቲያናችንን ይታደጋት!!!

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Demas hoy temeles hiwot yishalihal!

   Delete
  2. ስድብን እያበረታታሽ ያለሽ እህት ፣ ከጽሁፉ ውስጥ አንድ መስመር የወንጌል ቃልና ሥራን እስቲ ፈልገሽ አንብቢ ፡፡ ታድያ ክርስቲያን ነኝ እያልሽን እንዴት ወገኖች ወደ ጥፋት መንገድ ሲሄዱ ፣ ከኋላ ሆነሽ በርቱ ለማለት ትደፍሪያለሽ ፡፡ ይኸ የተላጋ ስብዕና ይባላል ፡፡

   Delete
 7. Wud Aba selama, and tyakie alegn? Mariam tamaldalech woise Atamaldim? adera yezewotr anbabiachihu negn melsun baschequay efelgewalehu.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አማላጅ የሚባል ነገር የለም ፤ የእነሱ አምላክም አማላጅም አንድ ነው ፡፡

   Delete
  2. ውድ የአባ ሰላማ የዘውትር አንባቢ እርስዎ ምን ብለው እንደሚያምኑ ማወቅ ይቻል እንደሆነ እስኪ ይንገሩን ማርያም ታማልዳለች ወይስ አታማልድም?
   ደቂቀ አቡዬ ነኝ

   Delete
 8. ማቆች በጣም የምትገርሙ ፍጥረቶች ናችሁ? ጥያቄው እኮ ማቅ ይህን መጽሐፍ አላሳተመም፣ ፖስት አላደረገም አይደለም፡፡ ጥያቄው ማቅ መጽሐፉ በያዘው እውነት ያምናል? አያምንም? የሚል ነው፡፡ እውነተኞች ከሆናችሁ ይህን መልሱ፡፡ ማቅ ግን በተደጋጋሚ እንዳሳየን ቆመው ከዚህ ትምህርት በተቃራኒው ነው፡፡ ለማቅ እኮ አዳኝ ስለኃጢአታችን የተሰቀለውና ስለጽድቃችን የተነሣው ጌታችን መድኃችንና አምላካችን ኢየሱስ ብቻ አይደለም፡፡ ማርያም፣ ተክለ ሃይማኖት፣ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ፍታት፣ ዝክር፣ ገዳም ለገዳም መንከራተት፣ ... ሁሉ የመዳኛ መንገዶች ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም እንደውም የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በተሰኘው መጽሐፉ ግልጽ እንዳደረገው ተሐድሶዎች ከቤተክርስቲያን አስተምህሮ ውጪ የወንጌል አስኳሉ ክርስቶስ ነው ብለዋል ሲል ነበር የከሰሳቸው፡፡ እንዲህ ያለ ፀረ ክርስቶስ ማኅበር የአባ አበራን መጽሐፍ ቢያሳትምም ፖስት ቢያደርግም እንደማያምንበት ግን ግልጽ ነው፡፡ ቢያምንበትማ ወንጌልን የሰበኩትንና ከወንጌል ውጪ የሆነውና ሌላ የመዳኛ መንገድ የሚሰብኩትን መጻሕፍት አንደ ወንጌል ቃል አይናገሩም ብለው የተቃወሟቸውን ተሀድሶ መናፍቃን ባላላቸውም ነበር፡፡ ስለዚህ አሁንም አስተያየት ሰጪዎች በማሳተምና ፖስት በማድረጉ ላይ ሳይሆን ትምህርቱን ማቅ በመቀበል ባለመቀበሉ ላይ ብንወያይ መልካም ይሆናል፡፡ አሊያ ምሰሶውን ትቶ ጉድፍ እንደማውጣት ይሆናል፡፡ አባ ሰላማዎችም የሊቀ ጉባኤ አባ አበራን መጽሐፍ በተከታታይ ብታወጡት ብዙዎች እውነቱን ሊረዱት ይችላሉና በዚሁ ቀጥሉ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ..... ለዚያም ይመስላል፤ የታተመው ታትሟል ከዚህ በኋላ ግን አይታተምም የሚል አቋም ተወስዶ ይኸው መጽሐፉ ከገበያ ውጪ ሆኖ ሰዎች ከአሮጌ ተራ በውድ ዋጋ ለመግዛት የተገደዱት፡፡ መጽሐፉ እጅግ ተፈላጊ ሆኖና ነጋዴው ማቅም ጥሩ ገቢ የሚያጋብስበት ሆኖ እያለ፣ እንዴት አስችሎት መጽሐፉን ሳያሳትመው ቀረ? ቢባል፣ በዋናነት ከዚህ ቀደም የቤተ ክርስቲያን ልጆችን «መናፍቅ ሆነዋል» በማለት የሚከስበት ትምህርት በመጽሐፉ ውስጥ ስለሚገኝ እንዳይጠየቅበት በመሥጋት ነው፡፡ .....

   ማንበብ ትችላላህ???? ከቻልክ የቤተክርስቲያናችንን እና የማቅን እምነት ካንተ ተመልከተው:: ከዛ ካንተ የጴንጤ አስተምህሮ ጋር ልዩነቱን ተመልከት::

   Delete
  2. ጌታ ይባርክ

   Delete
 9. ማርያም ታማልዳለች ወይስ አታማልድም በሚል ጥያቄ በእውነትና በቅንነት ለተቸገራችሁ ወገኖቼ በሙሉ!!!

  በጌታ ፍቅር ከልቤ ይህን ልበላችሁ:-

  የጌታ ቃል የሚለውን አውቀን በዚያ ብቻ መመራቱ እንጂ ሰው እንዲሆንለት ከራሱ ልብ እያፈለቀ በሚለው ድርሰት ማተኮሩ ከቃሉ ባለቤት ጋር መጣላት ስለሆነ የጌታ ቃል የሚለንን እነሆ:-

  1) እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በህይዎት ይኖራልና::(እብራ7:23-25)

  *** ሞት ስለከለከላቸው የሚለውን ቃል ያስተውሏል (በክርስቶስ የንጉስ ካህናት የሆኑት(ራእይ 1:6)እና(1ጴጥ 2:9) በክርስቶስ የሆኑት ካህን ስለመሆናቸው ያስተውሏል::
  አሁን ግን የክህነት(የመማለድ) ሥራቸውን ለማገልገል በሥጋ እንዳይኖሩ ሞት የከለከላቸው

  2) ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንባሳ ይሻላልና ሰው ..... ከጸሐይ በታችችም በሚሰራው ነገር (ምልጃንም ጨምሮ ማለት ነው) ለዘላለም እድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ (ከሥጋ ሞት በኋላ) የላቸውም:: (መክብብ 9:4-6) የሚሉትንና ለሎችንም የመጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ሁነህ በጾምና በጸሎት አጥናቸው::

  ከሰው ከመጠበቅ ደግሞ ከመንፈስ ቅዱስ ለመማር ሞክር::

  ጌታ ይርዳህ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለዚህ ዝብዝቡን ትተሽ
   ማርያም ታማልዳለች ወይስ አታማልድም??? ከሁለቱ ምረጭ::

   Delete
  2. በሚከተለው አድራሻ ከተገለጸው ትዕግሥቱ ካለህና ካነበብክ መልሱን ታገኛለህ

   http://www.abaselama.org/2012/03/4-read-pdf.html#more

   Delete
  3. የተሰጠው መልስ የጭንቀትና የጥርጣሬ ነው ፤ አላልኩም ብሎ ለመከራከር ያመች ዘንድ የታለመም አመላለስ ነው ፡፡ ምክንያቱም ከዚህ ቀደም በዚሁ ርዕስ መውጫና መግለጫ ያጠራቸው በመሆኑ ጭምር ነው ፡፡ ለማንኛውም የተሰጡትን አስተያየቶች ለማንበብ ትዕግሥቱ ካለህ ፣ ስለ አማላጅነት የሚያምኑትን ለመረዳት በዚህ መክፈቻ ያለውን ተመልከት ፡፡
   http://www.abaselama.org/2012/03/4-read-pdf.html#more

   Delete
 10. ሰላም ለናንተ ይሁን ጄታ ይባርካችሁ

  ReplyDelete
 11. በትክክል ታማልዳለች!!!!!!

  ReplyDelete
 12. ወገኔ!

  ማርያም እንደሆነች የምድር ሩጫዋን በድል አጠናቃ የሥጋን ሞት እንደማንኛም የአዳም ዘር በመሞት ከቅዱሳን ሁሉ ጋር የነጩን ዙፋን ፍርድ አብራ በመጠባበቅ ላይ ስለሆነች ያንተን የግልህን ሩጫ እንደቃሉ በመሮጥ በድል ለመፈጸም ብትሞክር እንደሚሻልህ በጌታ ፍቅር እያሳሰብኩ ለጠየከው ማብራሪያ እንሆ:-

  1)እብ 7:23-25 ያለው ካህናት እንዳይኖሩ ሞት ስለከለከላቸው ማለት የክህነት ሥራቸውን ወይም የምልጃ ሥራቸውን የሥጋ ሞት ስለከለከላቸው አያማልዱም ማለቱ ነው:: ይህ አባባል ካልገባህ ደግሞ ማርያም (የጌታ እናት) አዳኟ እንደሆነ ጌታን 'አምላኬ መድሃኒቴ' በማለት በመጥራት ከዘላለም ሞት እንደዳነች በሉቃስ1:47 የተናገረችውና ከሴቶች መካከል የተባረከች ብትሆንም የሥጋን ሞት ስለሞተች ከዚያች እለት ጀምራ አታማልድም ነው::

  2) ማስረጃ ደግሞ እያለህ ያለው (የምታስተውል ከሆነ) ሃጢያተኛም ሆነ ጻድቅ የሥጋን ሞት ከሞተ በኋላ ከሰማይ በታች በሚሠራው ነገር ለዘላለም እድል የላቸውም ነው የሚልህ (መክብብ 9:4-6) ስለዚህ የወንጌል እና የምልጃ ሥራ ደግሞ በዚች ምድር ወይም ከሰማይ በታች ብቻ የሚሰራ በመሆኑ ማርያምም ሆነች የሥጋ ሞት የሞቱ ቅዱሳን ሁሉ አያማልዱምና እባክህ ዘበዘብሽ የሚለውን ስድብ ትተህ እውነቱን አውቀህ ተጠቀምበት::

  ተጨማሪ መረጃ ከፈለክ ደግሞ ሉቃስ 16:19-31 ያለውንና ስለ አንድ አልዓዛር ስለሚባል ድሃና ስለ ሃብታሙ ሞት ከዚያም ሃብታሙና አብርሃም የአደረጉትን ንግግር ተመልከት::

  ይህ ግልጽ የሆነ የአምላካችን ቃል ካልግባህ ግን እግዚአብሔር ዓይኖችህን እንዲያበራ በሉቃስ 24:45 ባለው ቃል መሰረት አጥብቀህ ጸልይ::

  በተረፈ 'በእርሱ(በቃሉ= ወልድ)ሕይወት ነበረች
  ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች
  ብርሃንም በጨለማ ይበራል
  ጨለማም አላሸነፈውም (ዮሐ 1:4-5)

  የሚለው ቃል ያግኝህ ይፈውስህም:: አሜን::

  ሰላም ይብዛልህ

  እህትህ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዕብ 7፡23-25 የተናገረው የአይሁድ ካህናት በሙሉ ለሞት ተሸናፊ ስለሆኑ ፣ ህዝቡ የሚያመጣውን መስዋዕት ዘወትር ማቅረብ አይችሉም /ዘለዓለማዊነት የላቸውም ፤ ሲሞቱ መስዋዕት የማቅረብ አገልግሎታቸው ይተጓጎላል/ ለማለት ነው እንጅ ጻድቃንና ቅዱሳን ሲሞቱ እንደ ሸክላ ተሰባብረው ወደቁ ፣ ፈረሱ ፣ ተረሱ ፣ አበቃ ፣ ተደመደመ ማለት አይደለም ፡፡ እግዚአብሔር የህያዋን አምላክ ነው ይባላልና ፡፡ ከርሱ የተገኘ እስትንፋስ ህያው አድርጎ ይጠብቃቸዋል ፡፡ ስለዛም ነው በደብረ ታቦር ከዘመናት በፊት ሙተው የተረሱትን ሙሴና ኤልያስ ለሦስቱ ሐዋርየት የታዩዋቸው ፡፡

   በመክብብ 9፡4-6ም የሚገልጸው ሙታን ተመልሰው እንደ ዓለማውያን ዓይነት ኑሮን መለማመድ አይችሉም ፤ አይጋቡም ፤ አይዋለዱም ፤ አይበሉም ፤ አይጠጡም ለማለት ነው ፡፡ ማፍቀርና መጥላት የህያዋን ብቻ ባህርይ ናቸውና ፡፡ ይህንኑ መልዕክት ሲያጠናክርም የዚህን ዓለም ገጠመኝ ለመቅመስ ከሙታን ፣ ህያዋን የተሻሉ ናቸው በማለት የውሻና የአንበሳን ነገር ተናግሮልናል ፡፡ በአጭር አገላለጽ ከሞቱ ወዲያ ወደዚህ ዓለም መጥቶ መስተናገድ አይቻልም ለማለት ነው ፡፡

   በሉቃስ 16፡19-31 የሚተርከው በአጸደ ነፍስ የሚናገሩ የሙታንን ውይይት ነው ፤ ጻድቃንና ኃጥአን ከሞቱም በኋላ እንደሚነጋገሩ /ከላይ እንደገለጽኩት ሙታን ህያዋን ለመሆናቸው/ ማስረጃ ማለትም ሞት የሰዎችን ነፍስ ፣ በመቃብር እንደሚጣለው ሥጋ ፣ በድን እንደማያደርግ የሚያስረዳን ነው ፡፡ ይኸ ከድንግል ማርያም ማማለድ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም ፡፡ አብርሃም የምድሩን ጐስቋላ መታቀፍና መንከባከብ ከቻለ ፤ የጌታ እናት ፣ ለእኛም በስጦታ እናታችን ስለሆነች ልታደርገው የምትችለውን በንጽጽር ማሰብ ይገባል ፡፡ ኢየሱስ መከራን ተቀብሎ ድኀነታችንን ያስገኘበትም ክቡር ሥጋ ከድንግል ማርያም በተዋሕዶ ንብረቱ ያደረገው መሆኑንም መቀበልና ከስህተት መቆጠብ ይፈልጋል ፡፡

   አምላኬ መድኃኒቴ ያለችው ፣ ዓለምን በመስቀል ላይ ታግሶ ፣ የኛን ሞት ሞቶ ከማዳኑ በፊት ነው ፡፡ እሷን ያዳነበትን መንገድ ስለማታውቂው ይህን ቃል ያለቦታው አታምጭው ፡፡ የተናገረችው ሞቶ ከተነሳ በኋላ ቢሆን መልካም ፡፡ ነገር ግን ገና በማህጸን እያለ የተናገረችውን ቃል በመስዋዕትነቱ ደም ድኀነትን ካገኘነው ጋር አብሮ መደመርና መቀላቀል ግድፈት ነው ፡፡ ገና ወደዚህች ዓለም ያልመጣውን የማህጸኗን ፍሬ ስለምን መድኃኒቴ ትለዋለች ??? መልስሽን እጠባበቃለሁ ፡፡

   Delete
 13. BERTU TEBERATU! ENANETE SETEKERAKERU EGNA MEMAR ENECHELE YEHONALE! MANE YAWEKALE GETAME BEFEREDU YASETEMERENE YEHONALE!

  ReplyDelete
 14. MARIAM ATAMALEDIM TEWEDEDEM TETELAM!

  ReplyDelete
 15. yih yemaryam tselot tinbitm misganam new

  ReplyDelete