Thursday, June 7, 2012

አባ ቀውስ ጦስ እና አባ ፊልጶስ ለማኅበረ ቅዱሳን ያላቸውን አጋርነት አሳዩ

የማኅበረ ቅዱሳንን ሕንጻ ለማስፈጸም በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ላይ የተገኙትና ንግግር ያደረጉት አባ ቀውስ ጦስና አባ ፊልጶስ ለማኅበሩ ያላቸውን ተገዢነት ዳግም ማረጋገጣቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ግልጽ ድረገጽ ግንቦት 22/2004 ባወጣው ዘገባ አስታወቀ፡፡ ድረገጹ ከአባ ቀውስ ጦስ ንግግር ውስጥ የሚከተለውን ጠቅሷል። መንፈሰ ጠንካሮች ሁኑ፣ በማንኛውም በኩል እንዳትበገሩ፡፡ እኛ በእናንተ ልበ ሙሉ ነን፡፡ እምነታችሁ ጠንካራ ነው፡፡ ሃይማኖት ካለ ማንኛውንም ነገር መሥራት ይቻላል፡፡ እንመካባችኋለን፡፡ ከእኛ ይልቅ ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቃላችሁ፡፡ ይህ ቤት ለመሥራት የነበረው ውጣ ውረድ፣ የደረሰባችሁ መከራ ብዙ ነው፡፡ ብዙውን ፈተና አልፋችኋል፡፡ በዚህ ሳልፍ በጅምር ያለውን ሕንፃ እያየሁ ገንዘብ አጡ ማለት ነው? አቃታቸው እያልኩ ከራሴ ጋር እሟገት ነበር፡፡ ረዳት አጡ? መቼ ይሆን የሚፈጸመው? እነዚህ ልጆች ያሳፍሩን ይሆን እንዴ እያልኩ እሟገታለሁ፡፡ እኔ ተሸጬ ሁሉም ነገር በሆነ፡፡ ሽማግሌን ማን ይገዛል? እግዚአብሔር ሆይ እርዳቸው፣ ቅድስተ ቅዱሳን በደጅሽ ነው ያሉት በረድኤትሽ እርጃቸው እያልኩ ስጸልይ ነው የኖርኩት፡፡ ተስፋ አለን፡፡ ዛሬ የተሰበሰባችሁት ትጨርሱታላችሁአባ ቀውስ ጦስ «የተሐድሶ መናፍቃን»ን ጉዳይ እንዲያጣሩ በመጀመሪያ በአጣሪ ኮሚቴነት ከተሰየሙት ጳጳሳት መካከል አንዳንዶቹ ከሂደቱ ራሳቸውን በማግለላቸው በሞተከዳ በአጣሪነት የገቡ ሲሆን፣ በትክክለኛውንና ስርአተ ቤተክርስቲያንን በጠበቀ መንገድ እየሄደ የነበረውን የማጣራት ሂደት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በማበር አቅጣጫውን እንዲለውጥና ማኅበረ ቅዱሳን በሚፈልገው መንገድ እንዲካሄድ ያደረጉ አባት ናቸው። ውስጥ አዋቂዎች እንደሚናገሩት አባ ቀውስ ጦስ በማህበረ ቅዱሳን ትእዛዝ ሊቃውንቱ የጀመሩትን ትክክለኛ የማጣራት መንገድ እንዲቀለበስ ከፍተኛ ጫና ያሳደሩ ሲሆን፣ ዋና ተባባሪያቸው የሆኑትም ከዚህ በፊት በአንዱ ሊቅ «እርስዎ ዱሮም ቢሆን አምላክዎ ዘርአ ያዕቆብ፣ ቤተክርስቲያንዎ ማህበረ ቅዱሳን ነው» የሚል ተግሳጽ የደረሰባቸው ሊቀካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ መሆናቸው ታውቋል።
አባ ቀውስ ጦስ በጥቅምቱ ሲኖዶስ የተወሰነውን ውሳኔ ከማቅ በተሰጣቸው ትእዛዝ በማስቀልበስ ጉዳዩ ማቅ በሚፈልገው መንገድ እንዲሄድ ማድረጋቸው ታውቋል። የሊቃውንት ጉባኤ አባላትን ለማሸማቀቅም «እነ አለቃ አያሌው ያስከበሩትን የሊቃውንት ጉባኤ እናንተ ታዋርዱት! ማህበረ ቅዱሳን ብዙ ደክሞ ያጣራውንና ያቀረበልንን ይህን የመሰለ ጥናት እንዴት ወደ ጎን ብላችሁ ሌላ ማጣራት ይደረግ ትላላችሁ? ማህበረ ቅዱሳን ያጣራው በቂ ነው፤ ደግሞ ለእነርሱ (ተሐድሶ ለተባሉት) ማህበረ ቅዱሳን አነሳቸው» ብለው እንደነበር ምንጮቻችን ይናገራሉ። ከሊቃውንቱ በኩልም «ይህ እነርሱ የተከሰሱባቸው ብዙዎቹ ነጥቦች ሁላችንም በየቢሮው ተቀምጠን የምናወራውና የምንተቸው አይደለም ወይ? እንዴት የሚያስወግዝ ነው ይባላል? እኛ እኮ የቀረበውን አቤቱታ ሁለት ሦስት ጊዜ ተቀምጠን አይተነዋል፤ የብዙዎቹ ግን የሚያስወግዝ አይደለም።» ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ ቢሆንም፣ በአባ ቀውስ ጦስ ግፊትና ማህበሩ ከበስተ ጀርባ ሆኖ ያሳድር በነበረው ጫናና በገንዘብም ሀይል የሊቃውንት ጉባኤው ያጣራው ሳይሆን ማህበሩ «ያጠናው» የሊቃውንት ጉባኤ ድምዳሜ ተደርጎ እንደተወሰደ ታውቋል። ቅዱስ ሲኖዶስም በዚህ ላይ ተመስርቶ በግርግርና ስብሰባውን ሲበጠብጡ በነበሩ አንዳንድ ጳጳሳት ጩኸትና ሁካታ ተቃውሟቸውን ያሰሙ አባቶች ቢኖሩም የእነርሱን ድምጽ አፍኖ ውግዘቱን አስተላልፌያለሁ ብሏል።
የሲኖዶስ ስብሰባ በተጠናቀቀበት ዕለት በማቅ ተረቅቆ የመጣውን መግለጫ፣ በተለይም ስለማቅ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የተሰጠውን አስተያየት ለማስተባበል ሆን ተብሎ በማቅ የተረቀቀውንና የሲኖዶስ መግለጫ ተደርጎ እንዲነበብ የቀረበውን ጽሁፍ ቅዱስ ፓትርያርኩ አላነብም ብለው ሲቃወሙ አባ ቀውስ ጦስ እዬዬአቸውን እንዳስነኩትና እየጮኹ «ማህበረ ቅዱሳንን አትንኩት» በማለት እንዳለቀሱ ምንጮቻችን ተናግረዋል። በዚህም ለማህበረ ቅዱሳን ያላቸውን አጋርነት በእንባ ጭምር ገልጸዋል።
ለማህበሩ ህንጻ ማስጨረሻ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ላይም «እኛ በእናንተ ልበ ሙሉ ነን፡፡እንመካባችኋለን፡፡ ከእኛ ይልቅ ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቃላችሁ፡፡» ቢሉ ታዲያ ምን ይደንቃል? ለአባ ቀውስ ጦስ ቤተክርስቲያናቸው የክንፈ ገብርኤል አልታየ «ቤተክርስቲያን» ማህበረ ቅዱሳን መሆኑን መመስከራቸው ነው። ከዚህ ቀደም ብለውም «የሊቃውንት ጉባኤ ማለትም እናንተ ናችሁ» ብለው የሊቃውንት ጉባኤውን ተግባር በማሸማቀቅ ስልት ለማህበረ ቅዱሳን ሰጥተዋል፡፡ ምክንያቱም ለሲኖዶስ የቀረበው የአጣሪ ኮሚቴው «ድምዳሜ» ያው በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ማቅ ያቀረበው ክስ ነውና፡፡ ብይኑ የተሰጠውም ለስሙ በሲኖዶስ ነው ተባለ እንጂ ከበስተጀርባ ሆኖ አወገዝኩ ያለው ያው ማቅ ነው፡፡ ሲኖዶስ ቢሆንማ ኖሮ ጉዳዩ በዚሁ መንገድ ባልሄደም ነበር፡፡ ተቀባይነትም ባላጣም ነበር፡፡ ከውግዘቱ በኋላ አንዳንድ አባቶች በታላቅ ጫና ውስጥ ሆነው ውግዘቱ እንደተላለፈ እየተናገሩ ሲሆን፣ አውግዘናል ያሏቸውን ብዙዎቹን ሰዎች በስምም ይሁን በመልክ እንደማያውቋቸው፣ ጻፉ የተባለውን መጽሀፋቸውንም አንዳላነበቡት ይናገራሉ። አክለውም «እኛም እኮ በቤተክርስቲያናችን መታረም ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ እናምናለን» ማለታቸውን ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡  
የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅነታቸውን ዘመን በዋናነት የማህበረ ቅዱሳን ጉባኤ ባራኪ ሆነው ያሳለፉት አባ ፊልጶስም በገቢ ማሰባሰቢያው መርሀ ግብር ላይ ተገኝተው ያለ ይሉኝታና ያለሀፍረት ከአንድ መንፈሳዊ አባት የማይጠበቅ በመንፈሳዊ ሳይሆን በፖለቲካ ነክ ቃላት የተለወሰ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም « እነዚህ ልጆቻችን በትእግሥት ሁሉን አሳልፈው፣ ድል መትተው፣ ድል ተጎናጽፈው እዚህ በመድረሳቸው እግዚአብሔር ከእነሱ ጋር መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ሰው የሚታወቀው በሥራው በእምነቱ፣ በአቋሙ ነው፡፡ እነዚህ ልጆቻችን ካየናቸው ጊዜ ጀምሮ ወደ ኋላ ያላሉ እንደብረት ምሰሶ የሆኑ፣ አንድነታቸውን አጠናክረው አዋሕደው ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ የማይሉ፣ የመጣባቸውንና የሚመጣባቸውን ሁሉ ፈተና በጣጥሰው ያለፉና የሚያልፉ ለሁላችን አብነት የሚሆኑን ለቤተ ክርስቲያናችን መኩሪያና መመኪያዎች ናቸው፡፡ ታግለው ሩጠው እዚህ በመድረሳቸው እግዚአብሔርን ልናመሰግን ይገባል ብለዋል፡፡ ብፁዕነታቸው አያይዘውም ማኅበረ ቅዱሳን ልጆቻችን 20 ዓመታትን ታግላችሁ አልፋችሁ እዚህ ደርሳችኋል፡፡ ወደፊት ደግሞ የት እንደምትደርሱ እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ በርቱ ጠንክሩ፡፡ በርትታችሁ ከሠራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ ከእናንተ ጋር ይሠራል በማለት ማኅበሩን ያበረታቱ ሲሆን በጎ አድራጊ ምእመናን አስመልክቶም እግዚአብሔር በሰጣችሁ ለቤተ ክርስቲያናችሁ፣ ለእምነታችሁ ለታሪካችሁ፣ ለባሕላችሁና ለቅርሳችሁ ካላችሁ ላይ መስጠት፣ መለገስ እናንተን ብፁዓን ያሰኛችኋልና ስጡ ብለዋል፡፡
ማህበረ ቅዱሳን እዚህ የደረሰው በተጋድሎ ሳይሆን በትግል መሆኑን አባ ፊልጶስ በመናገራቸው የማህበሩ ጉዞ ፖለቲካዊ እንጂ መንፈሳዊ አለመሆኑን አረጋግጠዋል። ደጋግመው ያወሩት ስለትግልና ድል ነው። ጉዳዩ መንፈሳዊ ቢሆን ኖሮ ትግል ያሉትን ተጋድሎ ባሉት ነበር። ትግል በተለያየ የህይወት መስክ ውስጥ ቢጠቀስም በዋናነት ግን በፖለቲካ ውስጥ እያገለገለ የሚገኝ ቃል ነው፡፡ ማህበሩ በ20 አመታት ውስጥ የታገለውና ያለፈው ማንን ነው? የመጣበትንና የሚመጣበትን ሁሉ ፈተና በጣጥሰሶ ያለፈውና የሚያልፈው መቼ ነው? የማቅ ሰዎች ለእናንተ በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያኗን እያዋረዳችኋት ሌለችሁ አባቶች አብነት የሚሆኗችሁ እንዴት ነው? ይህ ብዙ ሳያነጋግር አይቀርም።
ደግነቱ በዚህ ትግላቸው «ሁሉን ያደረጉት እግዚአብሔር ረድቷቸው ነው» አለማለትዎትና ሁሉን በራሳቸው ማድረጋቸውን በዚህ መልክ በማቅረብዎት አበጁ ብለናል፡፡ ምክንያቱም በዚህ የማቅ ትግል ውስጥ የእግዚአብሔር አጀንዳ ስለሌለ የእግዚአብሔር ድጋፍ አይኖርም፡፡ ማቅ የክርስቶስ አዳኝነት እንዳይሰበክ የእግዚአብሔርን ወንጌል ሲቃወምና የዘላለም ሕይወት የማይገኝበትን የገድላ ገድል ተረት እንዲስፋፋ ሲያደርግ ነው የኖረው፡፡ በዚህም ጌታን የሚቃወም መሆኑን በተደጋጋሚ አሳይቷል፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር እርሱን ከሚቃወሙት ጋር አብሯቸው እንዴት ይሰራል?
ማቅ እንዴት እንደታገለና ለምን እንደታገለ ይታወቃል፡፡ በየጊዜው ድብቅ አላማውን ለማሳከት በገንዘብ፣ በጳጳሳቱ ላይ ይዣለሁ የሚለውን ነውር ማስፈራሪያ በማድረግና ብዙ ጀሌ ለማፍራት የሚረዳውን «መናፍቅ ተሀድሶ» የሚል ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ብዙ የአመጽና የስጋ ስራ ሰርቷል፡፡ ማቅ ለጥቅሙና ለሥልጣኑ እየታገለ ነው እንጂ መንፈሳዊ ገድል አልተጋደለም፡፡ እንዳሉት ስጋዊውን ትግል ግን ታግሏል፣ ድል ማድረግ አለማድረጉ ገና ባይለይለትም፡፡ የታገለውም የቤተክህነቱንም የቤተመንግስቱንም ሥልጣን በእጁ ለማስገባት ነው፡፡ በግንቦቱ ሲኖዶስ እድሜ ለእናንተ ቤተክህነቱን የተቆጣጠረ መስሏል፡፡ ስብሰባውን ለማቅ ጳጳሳት በየዕለቱ ከ500 - 1000 ብር ካርድ ተሞልቶላቸውና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የማቅ አመራሮችና የስውሮቹ ድረገጾች ጋዜጠኞች ስብሰባውን ቢሯቸው ሆነው በቀጥታ ሥርጭት እንዲከታተሉ መደረጉን ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ በዚያ ላይ ዋናዎቹ የማቅ ጳጳሳት በአባ ጢሞቴዎስ ቤት ማህበሩ ያገባውን ግብር እየበሉና የየዕለቱን ውሎ በመገምገምና መመሪያ በመቀበል በአባ ቀውስ ጦስ እንባ ታጅበው በሲኖዶሱ ላይ ጫና እንዲያሳድሩ የተሰጣቸውን ተልእኮ በሚገባ ፈጽመዋል፡፡     
ግን አባ ፊልጶስ እንደመሰከሩት ማቅ አገኘ ያሉት ድል እግዚአብሔር ከማቅ ጋር መሆኑን ያሳያል? ወይስ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኗን አሳልፎ መስጠቱን? ይህ ጉዳይ መንፈሳዊ በመሆኑና የእግዚአብሔርን አብሮነት በስጋዊና ሰይጣናዊ ሀይል በተገኘ ድል መለካትዎ የመንፈሳዊ ተጋድሎ ምንነት እንዳልተረዳዎ ይገልጻልና እንተወው! እግዚአብሔር ለረድኤት በሌለበት ነገር ውስጥ አለ ላሉት ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ «ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ።» እንላለን መዝሙረ ዳዊት ፷፭፥፫፡፡
ሌላው የብፁእነትዎ አስገማች ንግግር «እነዚህ ልጆቻችንለሁላችን አብነት የሚሆኑን ለቤተ ክርስቲያናችን መኩሪያና መመኪያዎች ናቸው፡፡» የእናንተ የአባቶች አርአያነት ሲጠፋ ታች ወርዳችሁ «ልጆች» ያሏቸውን አርአያ ማድረግዎት ያሳዝናል፡፡ ለመሆኑ ማቅ አርአያ የሚሆነው በበጎ ነው በክፉ? የገንዘብ ልመናውን ለማሟሟቅ ሲሉ ይህን አሉ እንጂ ማቅ የአልታዘዝ ባይነት ምሳሌ መሆኑን ከማንም በላይ እርስዎ ያውቃሉ። ከወራት በፊት ሒሳብህን ቤተክህነቱ በመደበልህ ኦዲተር አስመርምር ብለው በእርስዎ ፊርማ ለጻፉለት ደብዳቤ የሰጠዎ ምላሽ ምን ነበር? የእኔ ብቻ ሳይሆን የእናንተም መመርመር አለበት ሲል በማን አለብኝነት ሽቅብ አልተናገረም? ይህ ነው ለእናንተ አርአያ የሚሆነው? ሰው ቤተክርስቲያኑን ጥሎ አንዳይሄድ የሃይማኖት ጉዳይ ሆኖበት፣ እንዳይቀመጥም የእናንተ መጥፎ ምሳሌነት ችግር ሆኖበትነት አጣብቂኝ ውስጥ በሚገኝበት በዚህ ጊዜ በአልታዘዝ ባይነትና በአመጽ ስራ የሚታወቀውን ማቅን አርአያ ያደረጉት ለክፉው ነገር እንዳይሆን ግን ስጋት አለን፡፡ ከወንዝዎት ልጆች ጋር ለወጠናችሁትና እስካሁን ላልተሳካው የመፈንቅለ ፓትርያርክ ሴራ ከሆነ ልክ ነው ከማቅ በላይ አርአያ አይገኝም፡፡
«በርትታችሁ ከሠራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ ከእናንተ ጋር ይሠራል» ብፁዕ አባታችን አሁን እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ የኦርቶዶክስ ተከታይ ሁሉ ከማቅ ጋር ነው ብለው ያምናሉ? በዚህ ንግግርዎ ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖሩና የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ኢትዮጵያ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች አላወቁም ማለት ነው፡፡ ወይም ማቅ «አንድ አገር አንድ ሃይማኖት» በሚል ሲያራምድ የቆየው የአክራሪነቱ ሰለባ ሆነዋል ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ የተለያየ ሃይማኖት ያለው ህዝብ ነው፡፡ ሌላው ቢቀር እንኳን በሃይማኖቱ ምክንያት ሁሉም ከማቅ ጋር ሊሆን አይችልም፡፡ እንኳን የኢትዮጵያ ሕዝብ የኦርቶዶክስ ተከታዮችም ሁሉ ከማቅ ጋር አይደሉም፡፡ በኦርቶዶክሶች መካከልም ከጀሌዎቹና እውነት መስሏቸው በስማ በለው ከተከተሉት የዋሆች በስተቀር በገንዘብ የገዛቸውና ህሊናቸውን የሸጡ አገልጋዮቹና ብዙዎቹ አባላቱ ከማቅ ጋር ያለው በድናቸው እንጂ ልባቸውማ ከማህበረ ቅዱሳን ከሸፈተ እኮ ቆየ፡፡ እርግጥ «ሲኖዶስ» የተባሉት ጥቂት የማቅ ጳጳሳት ዘንድሮ ለማቅ በዋሉት ውለታ ከጎኑ መቆማቸውን ስላሳዩ በማንኛውም መንገድ ይሁን ሲኖዶሱ ከማቅ ጋር ነው ተብሎለታል፡፡ ፓትርያርኩን ከሲኖዶሱ ለይተው እርሳቸውም ከማቅ ጋር መሆናቸውን መናገርዎት ግን አልገባንም? ማቅን እየሸነገሉት ነው? ማቅ እኮ በስውር ድረ ገጾቹ እርሳቸው ናቸው ዋና ጠላት የሆኑኝ እያለ ነው፡፡  
በመጨረሻም አባ ፊልጶስ ለማቅ መስጠት ለቤተክርስቲያን መስጠት ነው የሚል ይዘት ያለው ቅስቀሳ አድርገዋል፡፡ «እግዚአብሔር በሰጣችሁ ለቤተ ክርስቲያናችሁ፣ ለእምነታችሁ ለታሪካችሁ፣ ለባሕላችሁና ለቅርሳችሁ ካላችሁ ላይ መስጠት፣ መለገስ እናንተን ብፁዓን ያሰኛችኋልና ስጡ» ማቅ እንዴት ቤተክርስቲያናችን ይሆናል? ማቅ እንዴት እምነታችን ይሆናል? ማቅ እንዴት ታሪካችን ይሆናል? ማቅ እንዴት ባህላችን ይሆናል? ማቅ እንዴት ቅርሳችን ይሆናል? የዚህችን ብዙ ዘመናት ያስቆጠረች፣ ጥንታዊትና ታሪካዊት ቤተክርስቲያን እምነት፣ ታሪክ፣ ባህልና ቅርስ እንዴት የ20 ዓመት ጎረምሳ ለሆነ ስጋዊ ማህበር ይሰጣሉ? ማህበረ ቅዱሳን እኮ እርስዎ ያሉትን ሁሉ አይደለም፡፡ ባይሆን ማቅ በእነዚህ ማንነቶቻችን እየነገደና እያተረፈ ያለ ለራሱ የቆመ ድርጅት ነው፡፡
 


38 comments:

 1. When do you speak honest and put yourself infront of Lord?

  ReplyDelete
 2. ahun lzih tsehufachu mene Yigebachwal? wanca weys . . . ? ene seticachualehu "as you deserve". mikniatum Ytsafachut yebetekiristiyanacin xbatocin weqsachu new. yihe degmoi altelmedem. bertu gin andande ymititeqemut atsatsaf gir yasegnal. lemisale . . . MAK "gedla gedln" kemesbek wici... malet min malet new? ene kenante belay balaqim ... lela ewnet xbatocacin maseb tesenoacew new le MAK yetegezut weys mak metet asnekito? yihem tinish gir yaasegnal. bicha khulum tsehufacihu yezareq altemecegnim. mecem bimecih bayimecih atilugnim biye basib altesasatkum.
  Cer were asemun

  ReplyDelete
 3. abaselamawoch are jealous of mahibere kidusan.

  ReplyDelete
 4. I know this website is from TIGRAY.

  ReplyDelete
 5. አባቶች ስለማኅበረ ቅዱሳን የተናገሩትን እየጠቀሳችሁ ማሳየታቸሁ ተገቢ ነው፡፡ ይህም እውነት እና እውነት እንደሆነ እናንተው መሰከራችሁ፡፡መንፈስ ቅዱስ አፍን ፀፍቶ ሲያናግር እንዲህ እንደሆነ ወንጌል ነግሮናል፡፡ ክፉዎችና በከንቱ ነገር ደካሚዎች ስትሆኑ የማትፈልጓትን እውነት በግድ ስተናገሩ ስመለከት በስንፍናችሁ ውስጥ እግዚአብሔር እንዳለ እረዳለሁ፡፡ ሩጡ አታሸንፉም ሀሰት እንጂ እውነት ከእናንተ ጋር አይደለችምና፡፡ አውሩ ወሬ የማያልቅባችሁ የወሬ ፋብሪካዎች ናችሁና፡፡ መቸም እንደ በሬ ቆዳ ለልፋት የፈጠራችሁ ናችሁና አይዟችሁ ለመልፋት በርቱ¡ በርቱ¡ ተበራቱ¡

  ReplyDelete
 6. እግዚአብሔር እውነቱን ያውጣ ታዲያ ማን ይታመናል በጽሁፋችሁ ውስጥ የጠቀሳችሁት ቃል ተመልከቱ‹‹ማቅ የክርስቶስ አዳኝነት እንዳይሰበክ የእግዚአብሔርን ወንጌል ሲቃወምና የዘላለም ሕይወት የማይገኝበትን የገድላ ገድል ተረት እንዲስፋፋ ሲያደርግ ነው የኖረው፡፡ በዚህም ጌታን የሚቃወም መሆኑን በተደጋጋሚ አሳይቷል፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር እርሱን ከሚቃወሙት ጋር አብሯቸው እንዴት ይሰራል?››
  ምን ማለት ነው እግግዚአብሔር ያከበራቸውን የቅዱሳን አባቶችን ገድል ተረት ያልክ እግዚአብሔር ያከበራቸውን ያልከበርክ አንተስ ከማቅ ግብር በምን ተለየህ እንዲህ ለካ ተቦርቡረናል የዘመኑ ፍጻሜ መሆኑን አሁን ተረዳሁ ገና ብዙ ክፍፍል ይኖራል……….

  ReplyDelete
 7. mene yegere tiru lesera biyasayu...menafeqane ayedelu enesu..lebetekerstiyane lefu enji...


  enanete gene weshoche ezawe adarashachehu betechohu ayeshaleme ...ezawe seyetane zeqezeqo eyetechawetebachehu tiru neger ayetayachehum


  menafeqe wesha!!!

  ReplyDelete
 8. የአባ ቀውስጦስን ስም ስትጽፍ ፊደላቱን አጠጋግተህ «ቀውስጦስ» ማለት ስትችል አንተ ግን «ቀውስ ጦስ» በማድረግ ቀውስ እና ጦስ ብለህ ያለያየኸው ለምንድነው?
  ሰውዬው «እኔን ሽጡኝና ህንጻውን ጨርሱ» ስላሉ ይሆን? አዎ ከድንጋይ ቤት እሳቸው ሊቀጳጳሱ ቢያንሱና ይህንንም ክብራቸውን ከማቅ የድንጋይ ቤት አሳንሰው ቢገኙ እውነትም «ቀውስ»ጦስ የሚያሰኝ ነው። ከእኛ እናንተ ትሻላላችሁ ካሉ ምነው ወደሚሻለው የጽድቅ ስራ ወደማቅ አባልነት ድስታቸውን ትተው የማይሄዱና ሲኖዶሱን የማይለቁ? እውነትም «ቀውስ» ጦስ! ቤተክርስቲያኒቱ ስንት ስራ እያላት እሳቸው ግን ዘወትር የሚያሳስባቸው የማቅ ህንጻ ነበር። እውነትም «ቀውስ»ጦስ! የኢትዮጵያ ህዝብ ከእናንተ ጋር ነው አሉ? እኔም ጭምር? ባይሆን እኔ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አንዱ ነኝ እንጂ ከማቅ ጋር እንደሌለሁ አስረግጬ እነግራቸዋለሁ። እውነትም «ቀውስ» ጦስ!!! እንደዚያ ብለህ በመጻፍህ ገርሞኛል። ሰውዬው ትልቅ ነበሩ። ሲያስቡ ግን እንደትልቅ ሰው ሳይሆን ልክ እንደ ቀውስ ያደርጋቸዋል። ይህ ደግሞ ለእኛ «ጦስ» ነው። እውነትም «ቀውስ»ጦስ ስምን መልአክ ያወጣል እንዲሉ!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ke 12 tu hawariyat mekakel yihuda nebere. ena ye ante kihidet ke 50 million kiristian wust minm ayidelem. erirrrrrrrrrrr kitilllllllllll belu ayisakalachihum

   Delete
  2. ባታውቀው ነው እንጂ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ውጪ ከ50 ዓመት በፊት ፈረንጅ ካልሆነ በክርስትና የሚጠራ ሌላ አንድም ኢትዮጵያ አባል ያለው ድርጅት አልነበረም። ባለፉት 30 እና 20 ዓመታት ብቻ የወንጌላውያን ተቋማት ብቻ ቁጥር ወደ 16 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ከኦርቶዶክስ ወጥቶ ተቀላቅሏል።
   የአንተ ዓይነቱ ካልቀረ በስተቀር ማስተማርን ሳይሆን ማባረርን ስራዬ ብላችሁ እንደያዛችሁት አካሄድ ወደፊት 30ውና 40ው ሚሊዮን ከወንጌላውያን መቀላቀላቸው አይቀርም።
   ግብረ በላ ጳጳሳት እንደቀፎ ቆራጭ ተሸፋፍነው ሲያንቀላፉ በጎቹን ማየት ስላልቻሉ እየተሰረቁ አልቀዋል። ማቅ ደግሞ ንግዱን እያጧጧፈ ያስቸገረውን ሁሉ እንደ ደርጉ «ፈጣን ነው ባቡሩ፤ ፈጣን ያልሆናችሁ ባቡሩ፤ እንዳትሳፈሩ» እያለና ያልተስማማውን እያገለለ ዘፈኑን ቀጥሏል። «ገንፎ እየሞተ አለሁ ሊል ይተነፍሳል» እንዲሉ እየሞትክ ነገር ግን ያለህ ይመስልህና 50 ሚሊዮን፤ ምናምን፤ ተቃጠሉ፤እርር በሉ ወዘተ አፍንጫህ ተይዞ በአፍህ ትተነፍሳለህ!!!!!!

   Delete
  3. Am not an MK but would like to say this being reading the main report and your comment.

   Egziabhear ahunis yiferid!!!

   Sima Getan ayihud betekawemut gize dingayoch endamesegenut semteh atwakimin? rasun ziq yemyadirg hulu be geta fit kef endil tenegroh ayawikimin? Ayeh kidusan ena lijochachew rasachewin ednet ziq endemiyadrigu! Ayeh lebetu kenae yehonu sewich rasachewin restew meshet enkoua bichil, le Geta kibir lishet silu! Geta ke endenezi kalu sewoch gar enji sim atfiwoch gar ayhonim::

   Ye sew sim sitbetatis yegeza hiwotih ke Geta gar endayibetes fira::

   Delete
 9. ማህበረ ቅዱሳን በመንግስት መ/ቤቶች ውስጥ የራስን አባላት እያደራጀ የሚገኝ ስለሆነ መንግስት ቢጠነቀቅ ጥሩ ነው፡፡

  ReplyDelete
 10. I think God brings his grace aba Kewostewos to stand for the truth. I see from your writing that God always doesn't leave us alone and defends for HIS house.

  We know ab kewostewos - whos is a senior father and respected by the excel synod members, and by many EOTC children.

  Sometimes the true comes out from the other way.

  Selam

  ReplyDelete
 11. 'እኛ ከጨለማ የተነሣ በሥርዓት መናገር አንችልምና የምንለውን አስታውቀን::' (ኢዮብ 37:19)

  በሥጋና በደም(በእድሜ)ከኢዮብና ከሦስት ባልደረቦቹ እጅግ የሚያንሰው ወጣቱ ኤሊሁም በጌታ መንፈስ ተሞልቶና ተመርቶ የተናገርው ምክር አዘል ግሳጼ ወደ ልቤ ስለመጣ ነው ይህን ለሚሰማና ለሚቀበለው ህይወትን ሊሰጥ የሚችለውን የሁላችንም ፈጣሪ ቃል የጠቀስኩት::

  ለነገሩ እነዚህ እንደ አስቆሮቱ ይሁዳ ስፍራ የማግኘት እድል የገጠማቸው ባለረጅም ቀሚሶች በእጃቸው የያዙትን መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ ሳይሆን ለመድገምና ለማስመሰል ሲገልጡት ይህን ቃል በጨረፍታ ሳያዩት እንደማይቀሩ እገምታለሁ:: ነገር ግን በእምነት ስለማያነቡት/ስለማይሰሙት አልጠቀማቸውም እንደተባለው ሆኖባቸው ይኸው ለዚህ ማንነታቸው በቁ::

  ቢሆንም 'አንቺ በንጉስ ቤት ስለ ሆንሁ ከአይሁድ ሁሉ ይልቅ እድናለሁ ብለሽ በልብሽ አታስቢ'(አስቴር 4:13) እንደተባለችው አስቴር ይህን አባ አባ አሳልሙኝ እየተባሉ ቃሉን ባልመገቡት የዋህ ሕዝብ በኩል የሚያገኙት ሥጋዊ ከበሬታ ከቁጣው የሚያስመልጣቸው መስሏቸው ከሆነ አሁንም ቃሉ በቀጣይነት እዚያው ክፍል ላይ እንደሚነግረን 'በዚህ ጊዜ ቸል ብትይ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ' ስለሚል እግዚአብሔር ማስተዋልን እንዲሰጣቸው የምህረትን አምላክ ከመለመን በቀር ምን ይባላል??

  አሁንም እናንተ ሕዝባችንን ያልተበረዘና ያልተከለሰውን የጌታ ኢየሱስን ወንጌል በማስተማር ከሞት ፍርድ እንዲድን ለማድረግ ይህን ሰማያዊ እድል ያገኛችሁ ጳጳሳት! የእግዚአብሔር ቃል 'ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሺው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?'(አስቴር 4:14) ተብሎ የተጻፈው ለአስቴር ብቻ ሳይሆን ለእናተም ለሁላችንም ለጥቅማችን ነውና ማስተዋልን ይስጠን::

  እኔን እጅግ የሚያሳዝነኝ ግን በምድራችን በተለይ በዚች ባለውለታችን በሆነች ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ጠላት መሳሪያ አድርጎ በሚጠቀምባቸው ሰዎች በኩል እያደረገ ያለውን ጠፍቶ የማጥፋት ሥራውን በመንፈስ ተረድተው በቃ! በቃ! በቃ! የሚሉ የዘመኑ ጳውሎሶች አለመኖራቸው ነው:: ጳውሎስ እንኳን እንደማህበረ ቅዱሳንን ያሉ ጎረምሶችን ይቅርና 'ዋኖች ግን መስለው ለሚታዩ ለብቻቸው አስታወቅኋቸው::'(ገላ 2:2) 'አለቆች የመሰሉት ግን በፊት ማን እንደ ነበሩ አይገደኝም' (ገላ 2:6) የተሰጠኝን ጸጋ አውቀው አዕማድ መስለው የሚታዩ ... (ገላ 2:9) በማለት በተሰጠው የጸጋ ጉልበት በድፍረት ይገስጽ ይመክርና ያስተምር እንደነበር ቃሉ ይመሰክርልናል:: ታዲያ ይህን የመሰለ ኃላፊነት ይዘውና (እንደ ጳውሎስ በጥሪ ባይሆንም)ከፍተኛውን የሲኖዶስ አደራ ተሸክመውና አባት የሚለውን መጠሪያ ተሸክመው እንዴት በስሜቱ ለሚነዳና ያየውን ሁሉ ለማድረግ ለሚቋምጥ ወጠምሻ ልጅ ይህን የመሰለ ያባትነት አደራቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ? ይህ ድርጊታቸው የሚያመለክተን ሕዝቡ እረኛ የሌለው መንጋ መሆኑንና በተኩላ እንዲበላ አልፎ የተሰጠ መሆኑን ነው:: እግዚአብሔር በመልኮታዊ ስልጣኑና አሠራሩ እንዲታደገው ከመጸለይ በቀር ሌላ ምን ይባላል??

  ለሚያስተውሉ ወገኖቼ ሁሉ ግን አሁንም:-

  'መንፈስን ሁሉ አትመኑ...መርምሩ' (1ዮሐ 4:1)

  'ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ'(ሐዋ17:11)

  'ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ' (1ተሰ 5:20)

  'አሕዛብ(የዋሁ ሕዝባችን) እንዲድኑ እንዳንነግራቸው ይከለክሉናልና:: ነገር ግን ቁጣው ወደ እነርሱ ፈጽሞ ደርሷል::'(1ተሰ 2:16)

  'በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም'(2ዮሐ:9)

  'ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል የተሻረ አይደለም:: እነዚህ ከእስራኤል የሚወለዱ ሁሉ እስራኤል አይደሉምና...'(ሮሜ 9:6)

  'መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል' (1ቆሮ 2:15)

  'እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን' (1ቆሮ 2:16)

  ወዘተ ወዘተ ወዘተ....

  የማይለወጠውና የማይሻረው የአምላካችን ቃል አስረግጦ ስለሚመክረንና ስለሚያስተምረን ዓይኖቻችንን ከሰው ላይ ወይም ከአስመሳይ ጳጳሳት ላይ አንስተን ምትክ በማይገኘለት በመስቀሉ ቃል ላይ እንድናደርግ ከልቤ አሳስባለሁ::

  ደግሞም ይህ በቤተ ክርስቲያናችን ጥላ ስር በተሰባሰበው ወገናችን ላይ እናውቅልሃለን ወይም እንመርሃለን በሚሉ የሥጋ ብቻ ወገኖቻችን እየተፈጸመ ያለው አሳዛኝ ተግባር:-

  1) ቴዎዳስ - እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ አራት መቶ ሰዎችን በማስተባበር ተነስቶ
  እሱም ጠፋ የሰሙትም/የተባበሩትም ተበተኑ(ሐዋ/ሥራ 5:36)

  2) የገሊላው ይሁዳ ተነሣ ብዙ ስዎችንም አሸፍቶ አስከተለ እርሱም ጠፋ
  የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ (ሐዋ/ሥራ 5:37)

  3) አሁንም እላችኋለሁ ከእነዚህ ሰዎች (የእግዚአብሔር ከሆኑ) ተለዩ ተዋቸውም
  ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከስው እንደ ሆነ ይጠፋልና ከእግዚአብሔር
  እንደ ሆነ ግን ታጥፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም በእርግጥ ከእግዚአብሔር
  ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ (ሐዋ/ሥራ 5:38-39)

  ከሚለውና ለጥቅማችን ከተጻፈልን የአምላካችን ቃል ጋር የሚመሳሰል ስለሆነ በእውነት ለሚያየውና ለሚፈርደው አምላካችን በጾምና በጸሎት ሳንታክት እንድናቀርብ እያሳሰብኩ የቤተ ክርስቲያናችን የዋህ ምእመን ግን ከተጫነበት የክፉዎች የሞት አገልግሎት እንዲያመለጥ መሥራት የሚገባንን የጊዜውን የመዳን ወንጌል ሥራችንን ለሰከንድ ያህል ሳንዘነጋ መሆን አለበት::

  ከዚህ በተረፈ የያዝነውና የምንሰብከው እውነት ተብሎ የሚጠራውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስንና ተከታይ የሆኑት ሁሉ እንዲናገሩት/እንዲያስተምሩት የተቀበሉትን የወንጌል አደራ ስለሆነ አናፍርበትምና በርቱ!!! በርቱ!!!

  እግዜአብሔር ሕዝባችንን ይጎብኝ!!!!

  አሜን::

  እህታችሁ

  ሰላም ነኝ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. Lemehonu anchi MK wetemisha new yalishiw anchi man nesh?Abatochis lelijochachew ayzuachihu maletachew min yaskenal Yasidesital Enji.Ende ene kehone degin lemisera Abatoch bertu kalalu yemiatefawun degmo mekirew zekirew,gesitsew memeles yelebachewum bay nesh?Wengelun yizew yemayanebut eyalish lemesadeb yemidadash anchi man nesh?
   Mk eko gedamatun ena abinet timihirt betun bemerdatu,chigirachewun lemimenu masaweku,Ye University ena college temariwochun mastemaru,Yebetekiristian kenona kene sereate amlikotu enditebek yebekulun tiret madiregu lemin yikefashal?Lemehonu Chiristian kehonish,are you ready to know the facts?Eski hulie ene bicha tikikil aydelehum yemil tibit aynurish.Degmos bihon,lene wengelin bemeshemided aydanim,ende kalu sininor enji.Tilachan sayhon fikirin yemizera enji.....

   Delete
 12. Ena min yedereg? You are one poor soul who want to see hatred spread against MK. Your body aches from top to bottom when you see love, respect and support towards MK. Do you have any thing else to talk/write? why don't you preach the bible even in your own "tehadeso" way.

  ReplyDelete
 13. እሰይ አባቶቻችን አኩርታችሁናል:: በዚሁ ቀጥሉ:: እነዚህን ግራ የተጋቡ መናፍቃን ከቤተክርስቲያናችን አስወጡልን:: የቀሩትን ግልገል መናፍቆች በማቅ ጥናት መሰረት ካልተመለሱ ሳታመነቱ አስወጡልን:: ተከሰስን ያሉት ተከሰስን ብለው ከማላዘን ከተሳሳቱ ተሳስተን ነበር፤ ካልተሳሳቱ ደሞ እምነቴ ትናንት፥ ዛሬም ሆነ ነገ ይህ ነው ብለው ማስረዳት መፃፍ እየቻሉ አታካራ የሚገቡት መናፍቅ ስለሆኑ ብቻ ነው:: 
  > ማቅ ለአንድ ጳጳስ "200ሺ ብር ይከፍል" የለ እንዴ? ምነው የሺ ብር ካርድ ገረመህ????
  > እናንተ በተነቀላችሁ ጥቂት ቀን የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ በግለሰቦች ተደረገለት:: ከዚህ ምን ትማራለህ:: የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ላንተ ይብስብሀል::

  ReplyDelete
 14. Ye MK memesgen endet atikenekenachihu. Besme Ab.Surprising.

  ReplyDelete
 15. Always MK, MK, MK, MK, MK...full of MK post. it seems MK blog.

  ReplyDelete
 16. በራችሁ ያለሁለቴና ሶስቴ ማንኳኳት አልከፈት ፣ አላስገባ እያለ መጥቷል ፡፡ ይህም ሁለተኛ ሙከራዬ መሆኑ ነውና ድካሜ ይቆጠርልኝ ፡፡

  መርሆአችን ወንጌልን ማስተማር ነው ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መስበክ ነው ይላል ፡፡ ዘወር ብለን ሥራችሁን ስንመለከት ግን ፣ አዳም ካወረሰን በደልና በራሳችን ከምንፈጽመው ኃጢአት ተጨማሪ የናንተንም ድክመት እየደረባችሁ በጭንቅላታችን ልታሸክሙን ትታገላላችሁ ፡፡ ወንጌልን ከማስተማር ይልቅ በግለሰዎች ማንነትና ምንነት ላይ ያነጣጠረ የአሉባልታና የሐሜት ዝንጠላ ፤ የስድብም ቃል ፣ ለእናንተ ቃል ያልተንበረከኩትን ትላልቅ አባቶችንም ቀንድ ተክላችሁ ጭራ ቀጥላችሁ ያልሆነ ገጽና መልክ በመስጠት ስማቸውን ማበላሸት ሥራዬ ብላችሁ ተያይዛችሁታል ፡፡

  ዛሬ ደግሞ ይባሱኑ ከርዕሱ አንስቶ ግድፈት /ስድብ / ፈጽማችኋል ፡፡ በጠራችሁት ስም የሚጠራ አባት የለም ፤ እንዲያውም ከመግቢያው ጀምሮ ለመሳደብ ያቀዳችሁና ያለማችሁ ይመስላል ፡፡ ይኸ እንግዲህ ዓላማችንና መርሆአችን ነው ያላችሁትን “በዚህች መድረግ የሰውን ስም ከማጥፋት እና ከስድብ ነጻ በሆነ ሥነ ጽሑፋዊ ጨዋነት መሳተፍ እና አስተያየት መስጠት ይቻላል። የግለሰብን ስም ያለ እውነተኛ መረጃ በመጥፎ የሚያነሱ ሥነ ጽሑፍም ሆነ አስተያየት ብሎጓ ፈጽሞ አትቀበልም” ቃል አፍርሷል ፤ ጥሰቱንም እናንተው በገሃድ እያሳያችሁን ነው ፡፡ ህግን ማውጣት እንጅ ማክበር አይመለከተንም ከሆነ ግፉበት ፡፡ አባ ቀውስ ያላችሁት ግን ለመሳደብ አስባችሁ ስለሆነ የተጠቀማችሁበት ፣ በትክክል አርማችሁ ጻፉት ፡፡ አባ ቀውስጦስ ለማለት የፈለጋችሁ መስሎኛልና አሁኑኑ አስተካክላችሁ የእናቧልት ተልዕኮአችሁን ቀጥሉ ፡፡

  እስከ ዛሬ የነፍስ ወከፍ አሉባልታ ያቀረባችሁባቸውና ያስነበባችሁን ግለሰዎች የስም ዝርዝር እንግዲህ ልቁጠርላችሁ ፡፡
  ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
  መምህር ምህረተ አብ አሰፋ
  አባ ገብርኤል
  ዘመድኩን
  አቶ ደስታ
  አባ ሳሙኤልና ሟቹን አቡነ ሚካኤልን በጥምረት
  አቡነ ሳሙኤል ከዋልድባ ገዳም ችግር ጋር በተጣመረ
  ቀሲስ ዶ/ር መስፍን
  መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው
  ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ንግግር ጋር በተያያዘ
  ከ2ዐዐ4 የሲኖዶስ ውሳኔ ወዲህ ደግሞ ይበልጥ ሥራችሁን በማፋፋም ፡-
  አባ እስጢፋኖስ
  አባ ጢሞቴዎስ
  አባ ሳሙኤል
  አባ አብርሃም
  አቡነ ዲዮስቆሮስ
  መምህር ዘበነ ለማ
  አቡነ ቀውስጦስ
  አባ ፊልጶስ
  ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዮ

  *****ታድያ ጐበዝ ከዚህ ዝርዝር ምን አተረፋችሁ? ስለእነዚህ ሰዎች አሉባልታ ለመጻፍ ያጠፋችሁትን ጊዜና ጭንቀት ወንጌልን ለማስተማር ብታውሉት ኖሮ ፣ እንደ እኔ ግምት ከሆነ ቢያንስ የሐዋርያው ጳውሎስን መልዕክታት በሙሉ አስፋፍታችሁ አስረድታችሁን እንጨርሰው ነበር ፡፡

  አሁንም ጊዜው ገና ስለሆነ ተውትና ተመለሱ እላለሁ ፤ መንገዱ ጠፍቶባችኋል ፣ በጨለማ አገዛዝ ውስጥ ናችሁ ፤ የምትሠሩትም የጨለማውን ሥራ ነው ፡፡ ሰይጣን በሰዎች አድሮ ነው ዓላማና ግቡን የማያስፈጽመው ፡፡ ካዱትና ወደ ወንጌል ሥራ ተመለሱ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ አላወቅክም መሰለኝ ማኅበረ ቅዱሳን እኮ ከመቶ በላይ የሞቱና ያሉ ሊቃውንትን ምእመንን ይወገዙልኝ ብሎ አቅርቧል አልሰማህም

   Delete
  2. ከላይ ስም ለዘረዘረው ሰው

   አንተ አላወቅክም መሰለኝ ማኅበረ ቅዱሳን እኮ ከመቶ በላይ የሞቱና ያሉ ሊቃውንትን ምእመንን ይወገዙልኝ ብሎ አቅርቧል አልሰማህም

   Delete
 17. MK is Anti christ.It preaches "Gedla gedel" rather than the true Gospel.

  ReplyDelete
 18. Abune Fanuailn Asinestew endimetsu Abba Gebre wolid- Abba Zelibanos-Kesis Ergete Kal yetebalu lieukan Ke America Addis Abeba dires Kefitega Genzeb Sebsiben Lakinachew Sinodosun Sayanegagiru -Hager Ayitew _Beteseb Tseykew -Tezinantew Temelesu
  Abune Fanueiln Yasinesalu yalnachew Lieukan D Hayile Giyorigisn 3 Hagere Sibket Sira Asikiyaj Asdergew Temelesu Negerun Bezirzir Zegibulin

  ReplyDelete
 19. ከዛሬ 10-30 ዓመት በፊት ባለው ጊዜ ውስጥ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች (ካህናቱን ጨምሮ) የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች የሆኑትን ኢየሱስ ጌታ ነው ብለው ስለመሰከሩ ብቻ ያሳድዳቸው ነበረ፡፡ ዛሬ ደግሞ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በተራቸው እየሸሹ ነው፡፡ ይህ እኛ በዓይናችን ያየነው በጆርአችን የሰማነው ዕውነት ነው፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ዓይን ካለህ ተመልከት ጆሮ ካለህ ስማ ኢየሱስ ክርስቶስን መቃወም ይቅርብህ ምክንያቱም የቀድሞ አባቶቼ ጻፉት የምትላቸው አንዳንድ አዋልድ መጽሐፍት ኢየሱስን የሚቃወሙ ናቸውና አስተውል፡፡

  ReplyDelete
 20. Shame on Aba Selama for doing nothing but to spread hatred against MK. I'm not a member of MK but am disgusted by your un-christian behaviour in fomenting such a deep animosity against another member of the church.

  Is this the way Christ taught us to resolve our conflicts? What about the Lord's prayer. Are we not supposed to exercise forgiveness 7x70? Who do we benefit by spreading such a hatred except our church's enemies including the fundamentalist moslems and the Pentes?

  For God's sake, think again because you will otherwise incur his wrath!!!!!!!

  ReplyDelete
 21. የተወገዘና የታሰረ ተሐድሶ መናፍቃን ሌላ ልጅ ያለው ጳጳስ የለም እንዴ? ፓትርያርኩም ይታሙ አልነበር? ከበሰበሱ አይቀር ………
  መንግስት ከደደቢት በረሃ ጀምሮ ሴሎች አሉት፣ የረሳ እየመሰላችሁ ደህንነት መሆን ይቅርባችሁ በእናንተ የሚያምረው የጳጳሳትን ሚስቶች ማሳወቅ ነው፡፡ ወንዱ ሴቱ ከሊስትሮ ሰራተኛ እስከ ጄነራል/ መከላከያ/ ውስጥ ሳይቀር ኢንተለጅንስ አለው፡፡ እናንተም ማን እንደሆናችሁም በዝርዝር ተይዟል፡፡

  ReplyDelete
 22. እረ አባሳላማዎች አሁን ማን ይሙት አቡነ ቆስጦስ የምሰደቡ አባት ናቸው? እኔስ የናንተ አላማ ነው ያልገባኝ ልቦና ይስጣችው።

  ReplyDelete
 23. thank you abba selama

  ReplyDelete
 24. እኔ የማውቃቸው የጳጳሳት አለቃ

  መጽሐፍ በቅድስናው ስፍራ ርኩሰትን የሚያደርግ በተቀመጠ ግዜ የጌታ የመምጨው ምልክት መሆኑን ነግሮናል ። ከዚህ ቃል መነሻነት ቤተ ክርስቲያኒቱ የዚህ ትንቢት ቃል የደረስባት መሆኑን የሚያሳዩ እውነቶች ይስተዋላሉ ። መገለጫውም ፓትርያሪኩ ናቸው። ቀጥዬ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ እውነቶችን አሳያለሁ።
  አባ ጰውሎስ በድርጊታቸው ሁሉ ቅድስና የራቃቸው በመሀላ የተቀበሉትን እምነት/ቤተ ክርስቲያን/ ለማፍረስ ከሚያሴሩ ተሀድሶዎች ጋር የሚያብሩ/የሚተባበሩ/ ፤በዋዛ ፈዛዛ የተሞሉ፤ በምድራዊ ነገር እና ክብር የተጠመዱ ፤ሀውልታቸውን በህይወት እያሉ ያሰሩ፤ በቤተስብ ፍቅር ተጠምደው ከ500 በላይ የቅርብ ቤተስቦቻቸውን ያለ ስራ ቤተ ክርስቲያን እንድትቀልባቸው የሚያደርጉ ። በምዝበራና በሥነ ምግባር ከዘቀጡት ሰዎች ጋር ከነአባ እዝራ፤ ሰሎሞን በቀለ፤ዳዊት እጅጋየሁ ሀይሉ ወዘተ ጋር የሚያብሩ ናቸው ። ከዚህምጋር በዙሪያቸው ይህ ነው የሚባል ስብእና በሌላቸው ሰዎች እየተመሩ አመራር የሚሰጡ ። ማሰናከያነታቸው የበዛ ከመሆናቸው የተንሳ በቤታችው ሴት በማሳድር የሚታሙ ናቸው እማሆይ ሮማን ለዚ ታላቅ ማሳያ ናት ። ከወይዘሮ እጅጋየሁ ጋር ያላቸው ግኑኝነት መስመሩን የለቀቀ የሀይማኖት አባትነታችውን የዘነጉና በተላላቅ ድግሶችና መሰል ዝግጅቶች የተወጠሩ ሲሆን በተለይም በገንዘብ ወዳድነታችው ምክንያት የመንፍስ ቅዱስን ስጦታ በገንዘብ የሚሸጡ በዚህም ምክንያት የደብር አስተዳዳሪነት ፣ የውጭ ሀገር ጉዞ ፤ጵጵስናና መሰል ሹመቶችን በገንዘብ ይሸጣሉ፣
  የእግዚአብሄር ቃል በሙላት የሌለባቸው በመሆናቸው ለአንድም ቀን የወንጌል ቃል ጠቅሰው ሲያስተምሩ አይታይም ፣ በዚህም ምክንያት ለአገልግሎቱ የማይቀኑ ና የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪክና ተዓምራት ለመናገር የማይፈቅዱ በገዳማት ሱባኤ ለመያዝና ከመናንያን ጋር ለመወያየት ምኞቱ ብቻ ሳይሆን የማያምኑበትም አባት ናችው ።
  ከሁሉም በላይ ከጥንቆላ ጋር የተያያዝ ስብእና እንዳላቸው የሚታሙ እኝህ አባት ታንከኛና መድፍኛ በሚባሉት ጠንቅዮቻቸው በእነዲበ ኩሉ ፤ቃለ ወንጌልና አይመረ አሸብር አማካኝነት ቤተ ክህነቱን በጠብና በጭቅጭቅ ጊዜውን እንዲፈጅ የሚያድርጉ ናችው ። በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ እጅግ አሳዛኝ የሆነው የጳጳሳት ድብደባ በእኝሁ ሰው ዘመን ነው የተከናወነው ። ፕሮጀክቶቻቸው ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን ለመጥቀም ሳይሆን እንደ መፍያ ቢዝነስ ከሚሰሩበት ጉዳይ ጋር ነው የሚያስተሳስሩት ለምሳሌ የአክሱም ሙዝየም 11 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚያወጣ ነግረው ዝርፊያውን ተያይዘውታል ቤተ ክርስቲያኒቱ ክፉ ቀንቢመጣ ለመጠባበቂያ ያስቀመጠችውን ወርቅ ሰቀር መሸጣቸው ሰያንስ አበው የስሩትን መተዳደሪያ ህንጻዎቓን ለዘመዶቻቸውና በልዩ ጥቅምለተወደጁትበመስጠት ጨርሰውታ። ታዲያ እኝህን አባትብለን እንጥራ እነሺኖዳ የሙስሊምንና የጵሮቴስታንትን ተጽእኖ በመመክትየአመኒያኑን ቁጥር በየአመቱ ሲያበዙ የእኘው አባት ግን መንጋውን በማስነጠቅ የአመኒያኑ ቁጥር በየጊዜው ከመውረዱም በላይ በአሁን ሰኣትቁጥሩ ከፍ እያልየሚግኝው በከር ስትናው እስታቲክስ ፕሮቴስታንት ነው ። ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊ ሁሉ ዘር ፖሎቲካና ወገን ሳይለይ ጌታ ለዚህ ሰው ለቡና እንዲሰጥ እልያም ፍርዱን እንዲስጥ መጸለይ ይገባናል።

  ReplyDelete
 25. ለወልደ ሰንበት???????????????

  ከስምህ ጀምረህ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ሲገባህ አባትህ ሰንበት በመሆኑ ገና ከጅምሩ የማን ልጅ እንደሆንክ የእግዚአብሄር ቃል በግልጽ ስለሚያስረዳህ በመጀመሪያ ለሕይወትህ መትረፍ ፈጥነህ የራስህን እርምጃ መውሰድ እንድትችል:-

  1)ዮሐ 1:13 ን
  2)ማቴ 23:በሙሉ(ክብር ስለሚፈልጉ አባዎች)በተለይ አንተ የማን ልጅ መሆን ስላለብህ ቁ.9 ን

  በመንፈስ በመሆን አጥናና ዘርህን አዲስ ፍጥረት አድርገው:: እንዲሁም (2ቆሮ 5:17;1ጴጥ 1:3,23 እና ያዕቆብ 1:18 ን) ለራስህ ብለህ አንብብ:: ያልዳነና የእግዚአብሔር የልጅነት ስልጣን ያላገኘ ሰው ስለ እግዚአብሔር የመንግሥቱ ሥራ መሥራት ይቅርና ምን መናገር እንዳለበት ስለማያውቅ ዝም ማለቱና ስለመዳኑ ቢያስብ ይሻላልና (2ጴጥ 2:12) ቃሉን በማወቅና በመዳንህ ላይ ብታተኩር ይሻላል:: ይህን ካደረክና ያባትህን ስም ቀይረህ መንገድህን ካስተካከልክ በኋላ ስለ እኔ ማንነት የጠየከው ጥያቄ ባይጠቅምህም ተገቢ መልስ ታገኛለህ::

  ምናልባት 'የክርስትና ስምህ' ከሆነ ደግሞ ዘሌዋውያን 12:1-5 ላይ ያለውንና ገና ክርስትና ከመጀመሩ ከብዙ ዓመታት በፊት አምላካችን እግዚአብሔር ስለ ሴቷ መንጻት ያዘዘውን ትእዛዝ በተወለድክ በ40 ቀንህ በማታውቀው ነገር በቀዝቃዛ ውሃ በመንከር አስለቅሰው ሳትፈልግ የሰጡህ መሆኑን አስተውል:: 'ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል'(ሆሴዕ 4:6) የሚለው ሕያው ቃል ይህ ዓይነቱን አለማወቅ አይመስልህምን??? እስቲ አስተውለን ወደዚህ የመስቀሉ ቃል ብቻ እንመለስና አምልጠን ይህን የዋህ ወገናችንን በቃሉ ብርታት ብቻ እናስመልጥ???

  ስድብ ስላልከው ነገር እንዲገባህ ማንንም ሰው አልሰደብኩም ደግሞም ቃሉ አይደግፈኝም ነገር ግን ክፉው መንፈስ የዓላማው ማስፈጸሚያ የሚያደርጋቸውን ሰዎች በክፉው ተይዘው እራሳቸውን መሆን ስላላስቻላቸው ሙሉ ማንነታቸው የመንግሥቱ ወንጌል ጠላት ስለሆኑ ከግብራቸው/ከሥራቸው በመነሳት ማንነታቸውን የሚገልጽ ቃል ሰነዘርኩ እንጂ ስድብ አይደለምና አስተውል:: ለምሳሌ አንተ የሰነበት ልጅ ስለሆነክ በቃሉ ውስጥ ከእግዚአብሔር ሌላ አባት ዲያብሎስ ስለሆነ (ሁለት መንፈሳዊ አባት ብቻ ስላሉ) 'የዲያብሎስ ልጅ' ነህ ብልህ ስህተት አይደለምና አስተውል!! አንተ ግን የእግዚአብሔር እጅ ውብ አድርጎ የሠራህ ነህና በመስቀሉ ላይ ደሙን እስከማፍሰስ ድረስ ለመዳንህ የህይወት ዋጋ ስለተከፈለብህ ብትቀበለው ብቸኛ አባትህ እንደሆነ ቃሉ ያረጋግጥልሃል ዓይተኸው የማታውቀው ሰላምም ይበዛልሃልና እኔም በዚህ የሁላችንም ጌታ ፍቅር ስለመዳናችን ግድ የሚለኝ እህትህ እንጂ በማያድንና ሰይፍ አንስቶ የጌታን ባሪያዎች ለማሳደድና ለመግደል በሚመክር ሃይማኖት የታሰርኩ አይደለሁም::

  ጌታ ማስተዋልን ለአንተና ለመሰሎችህ ይስጥ::

  አሜን::

  በሰማያዊ ፍቅር

  እህትህ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አስቀድሜ መስተንግዶአችሁ እጅግ ክፋት በመሰለ እየተበላሸ መጥቷል ፡፡ ለዚህ አስተያየት ማስተካከያ ወይም መማማሪያ ይሆን ዘንድ የጻፍኩት ተደጋጋሚ ጽሁፍ አልወጣም ፡፡

   በቅድሚያ የተጠቀሰው ግለሰብ አይደለሁም ፡፡ መልስ ልሰጥ የተገደድኩት የቤተ ክርስቲያናችንን ሥርዓት አስመልክቶ “ስለ ሴቷ መንጻት ያዘዘውን ትእዛዝ በተወለድክ በ40 ቀንህ በማታውቀው ነገር በቀዝቃዛ ውሃ በመንከር አስለቅሰው ሳትፈልግ የሰጡህ መሆኑን አስተውል” የሚል የተዛባ ቃል ስላነበብኩኝ ነው ፡፡ ስለ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በማለት ይነበብ ፡፡

   ትምህርቱ የማያልቅብሽ እህት ፣ አንድ ይሄ እንኳን እንዳይቀርብሽ ደግሞ ጥምቀትንም ነካሽው ፡፡ ምኑ ላይ ነው እንግዲህ የአንቺ የኦርቶዶክስ እምነት? መቼ ነው መጽሐፉን በቀና አንብበሽ የምትረጅው ፡፡ ሐዋርያት የተለያዩ ቤተሰቦችን በተለያየ ቦታ አጠመቁ ሲል /ሥራ 1ዐ፡48 ፣ 16፡15፡33 ፣ 2፡38፤ 1 ቆሮ 1፡6 ፣ 1ዐ፡1-2/ ህፃናትን እየለዩ ተው ማለት ይሆን ወይስ አዲሱን የወንጌል ሃይማኖት ትምህርት ከተለየ የግል መጽሐፍ እያመጣሽልን ነው ?

   ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ህፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዋቸው ፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና ብሎ ካስተማረን /ሉቃ 18፡16/ ፤ አንቺ የማንን ትምህርት ተንተርሰሽ ከድኀነት መንገድ ህፃናቱን ልትነጥያቸው ትሰብኪያለሽ ?

   ህፃናትስ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ወገኖች /ሉቃ 15፡7/ እንደሆኑ ስለምን መረዳት ያስቸግርሻል ?

   እግዚአብሔር የመዳን መንገድንና ሥርዓትን ሲመሠርት በየትኛው ቦታ ላይ ህፃናትን ከልክሎአቸዋል ? አብርሃም ሸለፈታቸውን እንዲቆርጥ /እንዲገርዝ/ ሲታዘዝ ፣ ህፃናት ተለይተው እንኳን እንዲቀሩ አላደረገም ፡፡ /ለአዲሱ ሥርዓት ግርዛት ያስፈልጋል እያልኩ አይደለም ፤ ምሣሌውን ማለቴ ነው/ ፡፡

   ህዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል የምትይን የእግዚአብሔር ልጅነትን ለማግኘት በጥበብ የመግቢያ ፈተና ይሰጣል ያለ የቱ ነቢይ ነው ? ሃይማኖት የምታስተምረው ሳይመረምሩና ሳይጠራጠሩ አንድ አምላክን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው ብሎ በየዋህነት ማመንን እንጅ ፣ በጥበብማ መንገድ ተጉዘው ብዙዎቹ ተሰናክለውበታል እልሻለሁ ፡፡ ህፃናትን ማጥመቅ እግዚብሔርን አለማወቅ ወይም መካድ አይደለም ፡፡ ይልቁንም የጸጋ ስጦታውን እየመረጠ እንደማያድል መገንዘብ ፤ ለልጆቻችንም የጸጋ ልጅነት እንደሚሆንላቸው በይበልጥ ማመን ፤ በአባትነቱ መመካት እንጅ ፡፡

   እስቲ ተጠየቂልኝ ፤ አንድ ማስተማርና ማሳመን የማትችይውን የአእምሮ ዘገምተኛ (IQ 30%) ችግር ያለበትን ጐልማሳ /ህፃን አላልኩሽም/ በአንቺ ሃይማኖት ስለ ጥምቀቱ ምን ታደርጊያለሽ ? መጽሐፉ የእግዚአብሔር ልጅነትን ለማግኘት ከመንፈስና ከውሃ ዳግም መወለድ ያስፈልጋል ይለናልና ፡፡

   ማቴ 8፡5-8 የመቶ አለቃው ልጅ ስለምን ምክንያት ተፈወሰ ?
   ማር 2፡4-5 ኢየሱስ የሽባውን ልጅ ስለምን ምክንያት ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው?
   ይህን የመሳሰሉ በቤተ ሰብ ውክልናና ኃላፊነት የተፈጸሙ አያሌ ጉዳዮች በመጽሐፍ ቅዱስ ተወስተዋል ፡፡

   ለዕውቀት ይሆንሽ ዘንድ ፡- ወላጆች ኃላፊነትን ወስደው ለልጆቻቸው ጥምቀትን ካስፈጸሙ ፣ በሂደት ተከታትለውም ክርስትናውን በራሳቸው ኃላፊነት ያስተምራሉ ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንንም ያስፈጽማሉ /እንዲያው አላደግሽበት እንደሁ ወላጆች ህፃናት ልጀቻቸውን ቤተ ክርስቲያን ይወስዳሉ ፣ አብረው ያስቀድሳሉ ፣ ያቆርባሉ/ ፡፡ ስለዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችን የእግዚብሔር የጸጋ ልጅነት የማግኘትን ዕድል ለህፃናትና ልጆች ነጥላ አትከለክልም ፡፡ የእግዚአብሔር በረከትም በቤተሰብ ስለሚሆን ህፃናቱም ይደርሳቸዋል ፡፡

   እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጐም አንድ ሰው ሙሉ ሰው ሆኗል የሚባለውና ቃሉን መስጠት ፣ መመስከር የሚችለው ፣ ሠለሳ ዓመት ሲሞላው ነው ፡፡ የአንቺን ትምህርት እውን ብሎ ተከትሎ ፣ ከሠላሳ ዓመት ልደቱ በፊት ሳይጠመቅ ቢሞት ፣ ይህ ብዛቱ የዓለምን 70% የሆነ ወገን ምን ይጠብቀዋል ? አየሽልኝ ትምህርትሽ የሚመለምለውና የሚያግዘው ለማን ጥቅም እንደሆነ ?

   Delete
  2. እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ በዚህ ብሎግ ብዙ የዋህ ወገኖች እዉነት የተዋህዶ እምነት ያለ እየመሰላቸዉ ሊታለሉ ይችላሉ፡፡ ሰላም የተባለችዉ እህቴ ግን ግልጽ የሀይማኖት ልዩነት እንዳለ የሚያረጋግጥ ነገር በማንሳቷ እና አንተ ደግሞ ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ እና ጥያቄም በማቅረብህ ብዙ ሰዉ አባ ሰላማ የተባለዉ ብሎግ የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን እምነት የማይከተሉ እና ደጋግመዉ በሚያወግዙት ማኅበር የተነቃባቸዉና ማኅበረ ምዕመናኑም ከእንዲህ አይነቱ አታላይ ራሳቸዉን እንዲጠብቁ ስለሚደረግ የሚበሳጩ “ተሀድሶ” በሚባል ስም የፕሮቴስታንት እምነትን በኦርቶዶክሳዉያን ዉስጥ ለማስረጽ የሚዋሹ በከንቱ የሚደክሙ ወገኖቻችን ሀሳብ የሚተላለፍ መሆኑን አንባቢ ይረዳ፡፡

   Delete
 26. The guy who commented as "Anonymous June 9, 2012" at 5:27 AM,

  I agree with you, but you should also tell the same to MK, which is the main propagtor of hateful, defamatory, and divisive propoganda.

  ReplyDelete
 27. ከላይ ስም ለዘረዘረው ሰው

  አንተ አላወቅክም መሰለኝ ማኅበረ ቅዱሳን እኮ ከመቶ በላይ የሞቱና ያሉ ሊቃውንትን ምእመንን ይወገዙልኝ ብሎ አቅርቧል አልሰማህም

  ReplyDelete
 28. I thank Aba Selama for having posted my remarks calling for a more christian way of resolving conflicts instead of fomenting hatred! I also thank "anonymous" above asking me to address my proposal to MK as well. I'd like to inform him/her that I did call on MK to cease completely its war on what it calls "tehaddeso" but rather resort to our church's mechanism for dealing with conflicts including differences of opinion.

  Therefore, please allow me, with all my utmost respect, to suggest to Aba Selama, to extend its christian hand of friendship and peace to MK so that the contending entities will meet under neutral/objective circumstances in the context of our church to resolve their problems and use their respective energies for the benefit of our beloved church.

  I feel sure that you realize that the Almighty God is watching you and that He does not appreciate vehement attacks that only result in the weakening of our church!!

  ReplyDelete
 29. In the name of the Father and the Son and the Holy Spirit One God Amen.

  You tried to exploit the misunderstanding between the late Abba Pauos and MK , Abba Paulos and members of the synods, the Government and MK to gate a legal ground to steer division within church to protestantize EOTC. You have failed! God will protect EOTC. It is time to repent and stop your statnic deeds. You are Daemas of the end times!

  Amen


  ReplyDelete