Tuesday, June 12, 2012

ይድረስ ለመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው ዴንቨር ኮሎራዶ - ክፍል ሁለት

ባለፈው መልእክቴ ያቀረብሁለዎት አስተያየት ይድረስዎት አይድረስዎት አላውቅም። እስከ አሁን ድረስ መልስ ስላላገኘሁ ስሕተትዎንም ሊያርሙ ባለመቻልዎ አስተያየቴን እቀጥላለሁ።
የእግዚአብሔርን የአምላክነት ሥራ ለመላእክትና ለሌሎች ፍጡራን እየሰጡ ምስጋናውን ለማጋራት ወይም ለመንጠቅ እየተሸረበ ያለውን ሴራ ከማጋለጥ ወደ ኋላ አልልም። ቤተ ደጀኔ በሚለው ብሎግዎ ላይ የሚያስተላልፉትን የስሕተት ትምህርት ቢያርሙ መልካም ነው፤ አለባለዚያ በዚህ ምድር ምንም ባያገኝዎት በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት ግን ቀርበው ይጠየቁበታል። ጌታ «በእኔ ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል የወፍጮ ድንጋይ ባንገቱ ታሥሮ ወደ ጥልቁ ቢሰጥም ይቀልዋል» ያለውን የማያልፍ ቃል መፍራት ጥበብ ነው። በእኔ ከሚያምኑ አለ እንጂ በሚካኤል ከሚያምኑ አለማለቱን ልብ ይበሉ።እርስዎ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑትን ምእመናን እያስኮበለሉ(እያሰናከሉ) በመላእክትና በፍጡራን እንዲያምኑ እያደረጉ ነው።
ልምሳሌ፦
«ለሕንብርትከ» በሚለው ርእስ ሥር እንዲህ ብለዋል «ሚካኤል ሆይ! . . . በነጋ በጠባ ትኲስ መናን በማዝነም የእስራኤልን ልጆች በበረሀ እንደመገብካቸው እኔንም ባሪያህን እውነተኛውን ኅብስተ ሕይወት መግበኝ፤» ብለዋል። ሰማይና ምድርን በውስጡ ያለውን ሁሉ ፈጥሮ የሚመግብ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እውነት እውነት እላችኋለሁ እውነተኛ እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው እንጂ ከሰማይ መና የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና» በማለት በእርሱ ዘመን ለነበሩ የእሥራኤል ትውልዶች ተናግሯል። ዮሐ 6፥33። እርስዎና ከርስዎ በፊት የነበሩ ሐሰተኛ ወንድሞች ግን በጠባ በነጋ ትኩስ መና በማዝነብ የእሥራኤልን ልጆች በበርሃ የመገባቸው ሚካኤል ነው በማለት የእግዚአብሔርን ምስጋና ለሚካኤል በመስጠት አስተምራችኋል። እንግዲህ የጥንቱንም ያሁኑንም የሚያውቀውን ጌታ እንመን ወይስ እርስዎንና ሐሰተኛ ወንድሞችን? የእግዚአብሔር መንግሥት ታሪክ በሆነው በታላቁ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሚካኤል ለእሥራኤል መና ያወረደ መሆኑን የሚናገር አንድም ቃል አናገኝም። እርስዎ ከየት አመጡት?
ለእሥራኤል መና ያወረደው ሚካኤል ነው ብለው ስላመኑ እንዲህ ብለው ጸልይዋል አስተምረዋልም «እኔንም ባሪያህን እውነተኛውን ኅብስተ ሕይወት መግበኝ» በሌላ በኩል ጸልዩልን ብለን እንጠይቃለን እንጂ ወደ እነርሱ አንጸልይም ብለዋል። እዚህ ላይ ግን ህብስተ ሕይወትን መግበኝ ብለው እግዚአብሔር የሚሠራውን ሚካኤልን ጠይቀዋል። ይህ ጸሎት አይደለምን?
 ምን ዓይነት እንጀራ ነው መብላት የሚፈልጉት? ጌታ እውነት እውነት እላችኋለሁ እውነተኛ እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው ብሎ እየነገረዎት ሚካኤልን ለምን ይጠይቃሉ? ሚካኤል አብ ከሚሰጠው የበለጠ እንጀራ አለውን? መጽሐፉ እንደሚለው ኅብስተ ሕይወት (የሕይወት እንጀራ) እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ይህንም የሕይወት እንጀራ እንዲሁ በነጻ ለዓለም የሰጠ አብ ነው። ሰው ከእርሱ በልቶ በሕይወት ይኖራል።
«ኢየሱስ እንዲህ አላቸው የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም.. የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ አባቶቻችሁ በምድረ እዳ መና በሉ ሞቱም ሰው ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ከሰማይ አሁን የወረደ እንጀራ ይህ ነው። ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው» ብሏል ዮሐ 6፥41-51። እንግዲህ ይህ ኅብስተ ሕይወት(የሕይወት እንጀራ)በአብ ፈቃድ አጠገብዎ ቀርቦልዎታል። የአብ ስጦታ እንዲህ ለዘለዓለም የሚበቃ ዓለምን ሁሉ የሚያጠግብ ቅዱስ እንጀራ ነው። እርሱም ኢየሱስ ነው። 
 ታዲያ ኢየሱስን የሰጠን ሚካኤል እንዳልሆነ እያወቁ እንዴት እርሱን ይጠይቁታል? ስለምድራዊ ምግብ ጸሎት እየጸለዩ ከሆነ ግን «የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ ተብሎ የሚጠየቀው» እግዚአብሔር ብቻ ነው። ጌታ ነው እንዲህ እንድንል ያስተማረን። ሚካኤልን ምን አድርግ ነው የሚሉት? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው ብሏል። ስለዚህ የጌታችንን ሥጋ እራሱ ኢየሱስ ይሰጥዎታል። ሚካኤልን መለመን አይጠበቅብዎትምና ንስሐ ይግቡ። በዚያው ስለሚካኤል በጻፉት ላይ የፈጸሙትን ታላቅ ክህደት ደግሞ ላሳይዎት፦
 የተቸገረን ሁሉ ጸሎትና ልመና ያዳምጣሉ።
          የእግዚአብሔር መልአክ ቆርኔሌዎስን፦ «ጸሎትህም ምጽዋትህም መልካም መታሰቢያ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ዐርጓል።» ያለው ስላዳመጠው ጸሎትና ልመና እንጂ እንዲያው በግምት አይደለም። ካዳመጠውም በኋላ ወደ እግዚአብሔር አድርሶለታል። የሐዋ ፲፥፬። ብለዋል።
ቆርኔሌዎስ የተባለው ሰው በሐዋርያት ሥራ እንደምናነበው ይጸልይ የነበረው ወደ እግዚአብሔር ነው የሚያመልከውም እራሱን እግዚአብሔርን ነበረ።
«በቂሳርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ። እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ» ይላል የሐዋ 10፥1-2
ጸሎቱን የሰማውም እራሱ እግዚአብሔር ነው። አዎ ቆርለኔዎስ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰሚነት ማግኘቱን ለመናገር ተልኮ የመጣው ግን መልአኩ ነው። የተቸገረን ሁሉ ጸሎትና ልምና የሚሰማውና የሚያዳምጠው እግዚአብሔር ሆኖ እያለ መላእክት የተቸገረን ጸሎትና ልመና ያዳምጣሉ ብለው የስሕተት ትምህርት አስተምረዋል። ለዚህ ማስረጃ አድርገው ያቀረቡት ደግሞ ወደ ቆርኔሌዎስ የተላከውን መልአክ ነው። ይህ ማንኛውም መናፍቅ ያላስተማረው ትልቅ ክህደት ነው። እራሱ መልአኩ እንኳ ጸሎትህን ሰምቻለሁ አላለም «ጸሎትህና ምጽዋትህ ለመታሰቢያ እንዲሆን በእግዚአብሔር ፊት አረገ» ብሎ መሠከረ እንጂ። በእግዚአብሔር ፊት አለ እንጂ በእኔ ፊት አላለም። እርስዎ ግን «ካዳመጠው በኋላ ወደ እግዚአብሔር አድርሶለታል» ብለው ዋሽተዋል ቃሉን አጣመዋል። አወይ ውሸት መላከ ሰላም እስኪ ቆም ይበሉ! በሐዋርያት ሥራ የምናነበው የቆርኔሌዎስ ታሪክ እርስዎ እንደሚሉት አይደለም። መልአኩ አዳምጦ ጸሎቱን ወደ እግዚአብሔር አደረሰለት አይልም። ከእግዚአብሔር ተልኮ ጸሎትህ ተስምቶልሃል ነው ያለው። ከመጀመሪያው ቆርኔሌዎስ ወደ መልአኩ አልጸለየም። ስለዚህ እግዚአብሔር ልኮት መጣ እንጂ እርሱ ስላዳመጠ አይደለም። ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ብቻ ይጸለያል። በታላቁ መጸሐፍ፦  
«አቤቱ በጽዮን ለአንተ ምስግና ይገባል ለአንተም ጸሎት ይቀርባል ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል» መዝ 64፥1-2 ተብሎ ተጽፏል።
ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደ ሚሰማ ወደ እግዚአብሔር ሲመጣ እርስዎ ግን ወደ መናፍስትና ወደ ሥጋ ለባሽ ይሮጣሉ። ይህ ጽሑፍዎት የማህበረ ቅዱሳን የፈጠራ ትምህርት ስንቱን እንደበከለ ያመለክታል። በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስም አዲስ ሃይማኖት ተፈጥሯል፤ ኦርቶዶክሳውያን የሆናችሁ ሁሉ ከዚህ የስሕተት ትምህርት ተጠንቀቁ።
ማጠቃለያ
ብዙ የምጽፈው ነበረኝ ነገር ግን የስተት ትምህርቱ ታርሞ የሚያልቅ አይደለም። እሺ ብሎ እራሱን የሚመረምር ንስሐ የሚገባ አስተማሪም አልተገኘም። ዘመኑ የማፍያ ዘመን ነው። ሀይማኖት በጌታ ቃል መሆኑ ቀርቶ በፊርማ ማሰባሰብ በአድማ በሰላማዊ ሰልፍ በቲፎዞና በገንዘብ ሆኗል። እኔ ይህን የምጽፈው አንዳንድ ነፍሳትን ከእሳት ነጥቄ አወጣ እንደሆነ ብዬ ተስፋ ስላደረግሁ ነው እንጂ ነገሩ አድካሚ ነው። ሆኖም ሰዎች የፈጠራቸውን አምላክ ብቻ እንዲያመልኩ እርሱን ብቻ ተስፋ እንዲያደርጉ ተሰቅሎ ያዳናቸውን እንዲወዱ የተቻለኝን ሁሉ ከማድረግ ግን አልቆጠብም። ወንድሞቼ ሁሉ እኔ ያገኘሁትን እንዲያገኙና እንዲድኑ ምኞቴና ናፍቆቴ ነው። የማህበረ ቅዱሳን አባላትም ሀይማኖት ያገኘን መስሏቸው እግዚአብሔርን ሳያገኙት በተሳሳተ መንገድ እየሄዱ ሳይ እጅግ ያሳዝኑኛል። በዚህ ብሎግ ላይ የምጽፈው እነርሱንና የዋሑን ወገኔን ለመርዳት አስቤ ነው። እግዚአብሔር በዚህች ትንሽ መልእክት ስንቱን ያድን ይሆን? ብቻ ተስፋ ሳልቆርጥ እጽፋለሁ። እግዚአብሔር ይግለጥልን አሜን
መርጌታ ገረመው ነኝ  

50 comments:

 1. Ay merigeta Gere! what you wrote is not bad as compared to many article that I read on this blog. at least you argue reasonably. Yichin Mahbere kidusan minamin yemtilewun gin tewowu. They are doing great... especially to keep the church from pretender. Even if few of you hate them millions are their supporters either directly or indirectly. E,G. I am not belonged to MK but I think they are good and I like them. so no matter if you and your friends hate them or not.

  ReplyDelete
 2. Aba selama bolg yemenafikan bloge mehonun sayawkew erasun berasu eyeglete new. Yeorthodox eminet tektay mesilo gin bezu orthodoxawiyann yikonnin neber.

  ReplyDelete
 3. ውድ “መርጌታ ገረመው” በቅድሚያ የጻፉት ጽሑፍ በየዋህነትና ባለመማር ከሆነ በትህትና ሆነው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት፣ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ቅዱሳን መላዕክት፣ ስለ ጻድቃንና ሰማዕታት.... በአጠቃላይ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የክርስትና እምነት አስተምህሮ ቢማሩ መልካም ነው፡፡ በስተቀር ሌላ ቦታ ሄደው እየተማሩ የቤተክርስቲያንን ትምህርት ላስተካክል ማለት ተገቢ አይደለም እርስዎ ያስገጠሙት/የሚመለከቱበት ክርስትናና የቤተክርስቲያን ትምህርት የተለየ ነው፡፡ በርግጥ ያመኑበትን መከተል ይችላሉ፡፡ ግን መረጌታ ነኝ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያን ነኝ በማለት አያደናግሩ፡፡ የቤተክርሲያኒቱን ትምህርት ካልተቀበሉ የሚቀበሉበትና የሚስማዎት ቦታ ሂደው ያምልኩ፡፡ ለነገሩ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ አይደል የሚለው መጽሐፉ፡፡
  ለመሆኑ “ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደ ሚሰማ ወደ እግዚአብሔር ሲመጣ እርስዎ ግን ወደ መናፍስትና ወደ ሥጋ ለባሽ ይሮጣሉ።” ሲሉ ምን ማለትዎ ነው:: ወደ ቅዱስ ሚካኤልና ወደ ቅዱሳኑ መሮጥ ነው የሚሻለው ወይስ ከእነሱ መሸሽ? ጸሐፊው ወይም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚያመልኩትን አያውቁም መስሎት ነው? ተሳስተዋል፡፡ በመንፈሳዊ ህይወት ውስጥ የመላዕክትን ድርሻና አገልግሎት ለማሳየት እንጂ ገነት የተከፈተው የሰው ልጆች የዘላለም ህይወት ያገኘነው ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ በቆረሰው ቅዱስ ሥጋው ባፈሰሰው ክቡር ደሙ መሆኑን አስረግጠው ያምናሉ ያሳምናሉ፡፡
  ለመሆኑ ወደ ቅዱስ ሰው እባክህን ጸልይልኝ ሲባል ወይም ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩልን ሲል ሲል ከእግዚአብሔር ፈቃድና አሠራር ውጪ የሆነ ይመስሎታል፡፡ ቅዱሳኑን የመረጠ/ያከበረ እርሱ ባለቤቱ ነውና ወደ እነሱ መሮጥ ጥፋት አይደለም፡፡ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ የሚገርመው ከእርስዎ ብሶ “የስተት ትምህርቱ ታርሞ የሚያልቅ አይደለም።” ይላሉ ይልቁንም እውነተኛውን የቤተክርስቲያን ትምህርት ከፈለጉ ታርሞ የማያልቀውን ኢየሱስ ጌታና አማላጅ፣ ቅዱሳን ሰዎች ከሞቱ በኋላ በዚህ ምድር ላይ ምንም አገልግሎት የላቸውም መታሰቢያቸው ተረስቷል፣ ቅዱሳን መላዕክት አገልግሎታቸው አንድ ወገን ብቻ ነው.... የሚሉትን የእርስዎ ትምህርት ጥለው ነው የቤተክርስቲያኗን ትምህርት ይማሩ፡፡ አለበለዚያ ደግሞ ከቤተክርስቲያኗ ውጪ ሆነው የመረጡትን ይከተሉ፡፡ በተረፈ “ኦርቶዶክስ ነኝ/መረጌታ ነኝ” እያሉ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሆኖ አማኙን ማደናገር ሓጢአት ነው፡፡
  ለእርስዎና እርስዎን ለሚመስሉ ሁሉ ቅን፣ ታዛዥ፣ ትሁትና አስተዋይ ልቦና እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ እውነተኞቹንም ከሀሰተኞች መምህራን ይጠብቅልን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከባለቤቱ ያወቀ ምንድን ነው የሚባል ተረት አለ፡፡ እርሶ እንደዚህ ነው የሆኑብኝ፡፡ ጽሑፍዎን ቀስ ብዬ አነበብኩትና አንድን ኦርቶዶክሳዊ መሪጌታ ‹‹ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የክርስትና እምነት አስተምህሮ ቢማሩ መልካም ነው›› ለማለት ሲሞክሩ አይቼ ገረመኝ፡፡ መሪጌታ የሚለው ከሱቅ ገዝተው ያመጡት መሰለዎ እንዴ? በአባቶች እግር ስር ቁጭ ብለው ተምረው ያልገባቸው ጠይቀው ቆሎ ቆርጥመው ብዙ ዋጋ ከፍለው ነው፡፡

   ‹‹እርስዎ ያስገጠሙት/የሚመለከቱበት ክርስትናና የቤተክርስቲያን ትምህርት የተለየ ነው›› ያሉትስ ምን ለማለት ነው? ቀደም ሲል እንዳልኩት መሪጌታ የተሰኙት ፓስተር ማን ጋር ሄደው ነው ብለው ገምተው ነው፡፡ እርስዎ ወላጆችዎ እጅ ላይ ሆነው የፈለጉት እየተደረገልዎ ሲያድጉ እርሳቸው ግን ከውሻ ጋር ተናጥቀው መንደር ለመንደር ዞረው ለምነው የቤተሰብ ናፍቆት እያነገላታቸው ችለው ተቀምጠው ተምረው ነው፡፡ እርሳቸውን እንዲህ ለማለት የሚያስችለው የእርስዎ ትምህርት ምንጩ ምን ይሆን? እንኳን እርስዎ የማህበረ ቅዱሳን የአመራር አካላት እንኳ ከአንድ መሪጌታ እኩል በዚህች ቤተ ክርስቲያን እምነትና አስተምሮ ላይ የመወያየት አቅም የላቸው፡፡ ከየት ተምረው ያወቁትን ሊያስረዱ ይችላሉና ነው ከተማረው ጋር ፊት ለፊት የሚቆሙት? ለዚህ አይደል እንዲህ ለክስ የሚሆን መረጃ ፍለጋ ውስጥ ለውስጥ መሹለክለክን የሚመርጡት? አይደለም እነርሱ የእነርሱ ሰዎች የሆኑት ጳጳሳትም እንኳ ዲያቆን አሸናፊ መኮንን ተጠርቼ ልጠየቅ ብሎ ደብዳቤ ሲያስጋባ አይሆንም ብለው የተከራከሩት ምክንያቱም ለሚያቀርባቸው ምላሾችና ለሚጠይቃቸው ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የሚያስችል አቅም የላቸውምና ነው፡፡

   ምንም ትምህርት የሌለው አንድ አርሶ አደር አንድን ዶክተር አንተ ደደብ ብሎ ሰደበው አሉ እንደተባለው እርስዎም ማንነቱን በሚገባ የማያውቁትን አንድን የተማረ ኦርቶዶክሳሳዊ ላይ ‹‹መረጌታ ነኝ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያን ነኝ በማለት አያደናግሩ›› ብለው ለመጻፍ እጅዎን ሲያበረቱ ትንሽ አልከበደዎትም? እንዲህ ከሆነ ችግር አለበዎትና እባክዎ ወደህክምና ስፍራ አሁኑኑ ያዝግሙ፡፡

   ‹‹ወደ ቅዱስ ሚካኤልና ወደ ቅዱሳኑ መሮጥ ነው የሚሻለው ወይስ ከእነሱ መሸሽ?›› ብለው ያቀረቡት ደግሞ የማደናገሪያ ጥያቄ ነው እንጂ ጸሐፊው እንዲህ ዓይነት ቃል አላሰፈሩም፡፡ የእርሳቸው መልእክት ለእርስዎ ካልተመቸዎት ይህ ሌላ ጉደይ ነው፡፡ ነገር ግን እሳቸው ያላሉትን ብለዋል ብሎ ማቅረብ አግባብ አይደለም፡፡

   ‹‹ጸሐፊው ወይም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚያመልኩትን አያውቁም መስሎት ነው?›› ላሉት እኔ በበኩሌ ያለኝ መለስ አዎ አያውቁም የሚል ነው፡፡ ከክፉ ሊጠብቅ በመልካም ሊሞላ የሚችለው አንድ አምላክ ብቻ ሆኖ ሳለ መልካም የሆነለትም ቢሆን ምስጋና ሊያቀርብ የሚገባው ለአምላክ ብቻ ነው፡፡ እርስዎና መሰለችዎ ግን ጸሎትን ወደሚሰማው ወደእግዚአብሔር ከመጸለይ ይልቅ ወደፍጡራን እርዳኝ ጠብቀኝ ይህንና ያንን አድርግልኝ ብላችሁ እየጸለያችሁ አይደለምን? ከዚህ በላይ አምልኮ ምን አለ? ይሄ እኮ የጸጋ እና የአምልኮ በሚል ይከፈላል በለው ሊያደክሙኝእንዳይሞክሩ ለዚህ የሚሆን የሚረዳዎ አንድም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምንባብ ሊያወጡ አይችሉምና፡፡

   ‹‹ታርሞ የማያልቀውን ኢየሱስ ጌታና አማላጅ፣… የሚሉትን የእርስዎ ትምህርት ጥለው›› የሚለው ጽሑፍዎን ሳነብ በትክክል እርስዎ ከማን ወገን እንደሆኑ ገባኝ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ የማያምንና እንዲህ ብለውም ሰዎች እንዳያመኑ እያደረገ ያለው ማን እንደሆነ ግልጽ ስለሆነ የእርስዎን ማንነት ለማወቅ ብዙ ማሰብ አስፈላጊ አልሆነብኝም፡፡

   ደቂቀ አቡዬ ነኝ

   Delete
  2. Dekike Abuyee? Ere simna sew! Ante Abuyen eyesedebik degmo besimachew? assasach.tekula mehonih bezih yitawqal.

   Delete
  3. dekike Abyee sayehone dekike wesheya nehe

   Delete
 4. zoreh zoreh mk.

  ReplyDelete
 5. Kesis Dejene Shiferaw Melikam Astemari Nachew
  1 Mahibere Kidusan Bihonum Lemetsekemiya new enj Ayaminubetim yihinin Awkalehu Lerasachew negireachewalehu
  2 Wendim Bemekises -sebakin bemekawem -zemarin bemekawem -Like Kahinat Hayile Silasen Bemekawem -D Daneil Kibretin Bemekawem-Yinoralu Betsam zerega
  3 Canada Honew Yelemenut America simetsu yekedut wndimachin ahun bete kirsityan ayidersim
  4 Kesis Dejene Wongal Sebkew ayawkum Dirsan -Gedil -Teret Teret-fiezina Balit-Bicha yasazinal
  5 .Abune Abirhami Gojam Bemehonachew Bicha Yikawemu Nebere YeJimaw Neger Endayinesa silefelegu Tesimamu
  6 Kesis Degene Begenzeb Kehone Andega Nachew Denber yeminorubetin yekiray bet Akatsilew Berkata Genzeb Sebesebu -Ragueil Honew Keseratega Gubae sebesebu Awropa Hedew Kekefelg gar Tesimamtew sebesebu-Ahun Beyesamintu Las vegas Eiyehedu yisebesbal Aba Gebire Kidan Yetebalutin Sebaki Lemasnesat Kekefele Gar honew yimekiralu Wongail yelem neger bicha Masmesel bicha yasazinal

  ReplyDelete
 6. ድሉ ዘእግዚአብሔርJune 13, 2012 at 10:48 AM

  ሰአል ለነ=ለምንልን ማለትና ተሰአለነ እግዚኦ=አቤቱ ይቅርበለን አዎ ልዩነት አላቸው። እኛ እንደ እኛ ፍጡራን ለሆኑ ጻድቃን ፣ ሰማዕታትና መላእክት ለፈጣሪያችን እንዲለምኑልን ''ሰአሉ ለነ'' ብለን ብንማጸናቸው እንደ አምልኮት ይቆጠራል ? ''ቅዱስ ሚካኤል ተሰአለነ'' ካልን ግን ሚካኤልን እንደማምለክ ይቆጠራል። እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የጻድቃንን፣ ሰማዕታትንና መላእክትን አማላጅነታቸውን እንቀበላለን። ስንጸልይም ሰአሉ ለነ= ለምኑልን እያልን ነው። ታድያ በዚህ ላይ ማኅበረ ቅዱሳንና አባ ሰላማውያን ልዩነታችሁ ምንድን ነው ? ቀሲስ ደጀኔ ቅዱስ ሚካኤል የእግዚእብሔር መልክተኛ ሁኖ ለእስራኤላውያን በሲና በርሃ መና ማውረዱን እንዴት አይተውት ነው? የመናው ባለቤት እራሱ እግዚአብሔር ሳይሆን መላኩ ቅዱስ ሚካኤል ነው የሚሉት? መሪጌታውስ ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር መናውን እንዲያደርስ መላኩን እያስተባበሉ ነው? ልዩነታችሁ የቃላት አገላለጽ ነው ወይስ መሠረታዊ የሆነ የዶክትሪን ልዩነት ? እባካችሁ የሌለ ልዩነትን እንዳለ እያደረጋችሁ ጥላቻንና መከፋፈልን በወንጌል ስም አትስበኩብን። በፖለቲካ ፖለቲከኞች በጎሳና በቀጠና የሚከፋፍሉን ይበቃል። ማን የአንድነትና የፍቅር አራያ ይሁነን ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ENDYA ENDYA NEW ENGY KEZELABEDU AYQER DEHINA ADRGO MEZELABED NEW. DEGMOM EKO ALEMAFER MERGETA GEREMEW TEBALE WEY GUDI YEMAYAMESHUBET BET AYADRUBETIM SIBAL ALSEMAHIM WEY? MINEW SAY MESHBIH WEDEBETH BTIHED AYSHALIM BLEHI NEW. MANIM SEW YEFELEGEWUN MEHON MEBTUNEW NEGER GEN BE ETHIOPIA ORTHODOX TEWAHEDO SIM MENEGEDU GIN MINALE BTAQOMU. ABASELAMAWOCH. ANDQEN QUMNEGER BTAWERUS YKEBDACHUWAL WEY? MENAFQNETACHU AGER YAWEQEW TSEHAY YEMOQEW NEW. ENDAW ALTAWEQNEM KEHONE MEGAGAL NEW. MAQACHUN TEQLLACHU WEDE GBIR ABROCHACHU BET LEMIN ATHEDUM. ENDAW BESEW BET GTIR YGERMAL. MECHEM ENANTEN YEMNEKA NEGER LEHIZIBOFCIALLY ONE ENDE MATADERGU AWUQALEHUNGNE ENANTEW ANBBACHU ENDTREDUT LEMALET NEW ENGNE. EST EWEQUT MIN YAKIL SEW ENDETELACHU. EWUNETENOCH KEHONACHU MIN ASFERACHU BE EMNETACHU TEHADSONETACHU LEMIN BEGIS BEADEBABAY ATNAGERUM BENEGERACHIN LAY AHUN YESAFKUT ENDE MATAWETU AWQALEHU

   Delete
 7. እስመ ለሊሁ :'': ይትሜሰል ከመ መልአከ ብርሃን የጨለማው ገዥ ራሱ የብርሃን መልክተኛን
  ይመሰላል ለመሆኑ በቤተ ክርስቲያን የሚሠየሙ ሰዎች ራሳቸውን ሳያውቁ ግዙፉን ዓለም ሳይጠይቁ
  ወደ ረቂቁ ዓለም እየጠለቁ ለምን ይሆን ኅሊናቸውን የሚያማቅቁ?እናም አንድ ሰው ሌላውን
  የሙሴን ታሪክ ንገረኝ ስትነግረኝም ደኅና ደኅናውን አለው ይባላል፤ ምን አለ የሰው ልጅ መልካሙን ቢናገር

  ReplyDelete
 8. In my opinion, both the writer and the so-called MK or the fanatic blind Orthdox groups are mistaken.

  One of the mistakes of the group represented by the writer is the complete denial of the blessings that we can receive through the saints. I believe that St Mary and all the rest of the saints are the good helpers that God has assigned for us. They deserve veneration and praise as they are holy and the hosts of God.

  On the other hand, MK and the group represented by Kesis Dejene Shiferaw have exaggerated the place of the saints and have made the veneration of the saints equivalent to worship. This needs to be corrected. I love and believe in the helping power of St Michael, but I believe we need to be careful not to cross the line and offer him a worship like veneration. Even if we do, St. Michael won't accept it as he knows that the devil fell just becase he sought worship from the rest of the angels.

  I believe the question should not be whether the Saints can intercede for us or not. Of course, they can intercede for us and even save us from evil. What the question should be whether our veneration practices need to be cleaned up or corrected in light of the word of God that we read in the Bible. I love Jesus Christ; I love His Mother; I love all His saints and rely on them as intercessors. But again, we need to revisit our veneration practices, the melka-melkoch written by some monks or debteras; the Mesehafe Zik that some people cticize. I think those of you who love the EOTC church should be prepared and willing to consider or accept constructive criticisms and clean up our church. This is not to mean all the writerls comments are constructive.

  ReplyDelete
  Replies
  1. God bless you friend, I completely agree with your comment. The problem is, people in our church are quick to pick up stone for any kind of critique; even if it's reasonable. We are living in the 21st century where criticism is by all means welcomed because it reduces the chances of misunderstanding and confusion. But for most people in the church, their thinking process is no different from people in the Middle Ages. I guess ignorance is truly bliss. On the other hand, there are those who are orthodox by appearance but heretic by heart. These people need to join other Christian denomination groups where it suits their view.

   Delete
 9. አስተያየቴን በድረ ገጻችሁ ለማስነበብ በጣም አስቸጋሪ መሆኑን ባውቅም አሁንም ይህችን አቅርቤአለሁ ፡፡ ብዙ ትግል እያስፈለገ በመምጣቱ ላለመጻፍ ወስኜ ነበር ፤ ለዲያብሎስ እጅ ላለመስጠት በማለት ከራሴ ጋር ተሟግቼ አቀረብኳት ፡፡

  አስቀድሞ ማሳሰቢያዬ ፡-
  ምእመኑን የሚያደናግሩና መልሰው ቤተ ክርስቲያንን የሚሞግቱ ፣ በቃላት ድርዳሮሽ የሚወጓትም ፣ የሰጠቻቸውን ስምና ማዕረግ በመጠቀም ስለሆነ ፣ ከዛሬ ጀምሮ ሳይጠየቁ ፣ በራሳቸው ስላሳወቁኝ ብቻ መልሼ ሹመታቸውን ስጠራ አልገኝም ፡፡ ምክንያቱም መሐንዲሱ በተመረቀበት ሥራ ተሰማርቶና አገልግሎ ፣ በሠለጠነበት ሙያው ሳይጠቅምበት ወደ ግብርና ከተሰማራ ፤ በገበሬነቱ ነው እንጅ መጠራት ያለበት ቀለምን ስለቆጠረበት ብቻ መሐንዲስ በሚለው አይደለም ፡፡ ፍሬ ባላፈሩበት ሙያና ማዕረግ ራሳቸውን እየጠሩ ፣ ከበሬታቸውን በእኛ ላይ ማሸከማቸውም ለጊዜው አግባብ ሆኖ አልታየኝም ፡፡ ስለዚህም በራሴ ትክክል የመሰለኝ ፣ ዲያቆን ይበል መሪጌታ ወይም ሌላ ፣ ለኔ ከጸሃፊነቱ የተለየ ሹመቱ አይታየኝምና ፣ ሁላችንንም በሚያግባባን ቃል ፣ ጸሐፊ ወይም ጣፊ ብየ ብጠራ ጣፎች ሁሉ እንደ ማይቀየሙኝ እርግጠኛ ነኝ ፤ ምክንያቱም የተሰጣቸውን የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን በራሳቸው እያፈረሱ ፣ አንባቢን ለማስፈራሪያ ይሆናቸው ዘንድና ፣ መማራቸውን ለመገለጽ ምንም ማዕረጋቸውን ቢደረድሩትም ከምላሴ ሊንጠለጠልል ፣ ከአንጀቴም ጠብ ሊል አልቻለም ፡፡ ቢቻል እነሱም ይህን አግባብ ያልሆነ የስም ሸክም ባይጭኑንና ፤ ደፍረን ሃሳባችንን እንዳንገልጽ የሚያስፈራራ ደንቃራቸውን ከሚያስነብቡን ፤ ቤተሰብ የሰጣቸውን አለበለዚያም የብዕር ስም ወይም ስም አልባ ሆነው መልዕክታቸውን ብቻ ቢያስተላልፉልን ለኛ ይበቃናል ፤ ተቀጽላቸው ስለማያስጨንቀንም መልስ ለመስጠት መልካም ይሆንልናል፡፡ እኔ ከአደግንበት ባህላችን አንጻር ማዕረጋቸውን እየጠራሁ ፣ አንቱዬ እባክዎ ተሳስተዋል ብዬ ለመናገር ከህሊናየ ጋር ብዙ ትግል ማድረግ አስፈልጐኛል ፡፡

  እንግዴህ ቃሌን ከይቅርታ ጋር እጀምራለሁ ፡-
  ጣፊ ገረመው ለራሳቸው እግዚአብሔርን የሰነፈ አስመስለው ጥብቅና ቆመውለታል ፤ ውክልና ሳይሰጥዎትም ይናገሩለታል፡፡ እኛ ይህን ዓለም የፈጠረ አንድ እግዚአብሔር አለን ፤ ሁሉ በርሱ ሆኗል ፤ ያለርሱ የተከወነ አንዳች የለም እንላለን ፡፡ በእኛና በእግዚአብሔር መሐል ደግሞ የሚራዱን ፣ የሚያማልዱን ድንግል ማርያም ፤ መላእክትና ቅዱሳን አሉ ፡፡ እርሱ በጸጋው ስለመረጣቸውና ስላከበራቸው ከኃያሉ ፈጣሪ ቸርነትን ያስገኙልን ዘንድ እንማጸናቸዋለን ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ከመረጠው ህዝብ ጋር ያደርግ የነበረውን ግንኙት እንዴት እንደነበር ተዘንግቶዎት እንደ ሆነ ወይም አዲሱን ትምህርት ከሰፈር መቀበልዎን ለመመስከር ብቅ ማለትዎ ግልጽ አይደለም ፡፡ ከላይ እንደ ገለጽኩት የእንጀራው /መና/ ባለቤት እግዚአብሔር መሆኑን ማንኛውም የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኝ ያውቃል ፤ ነገር ግን ደካሞችና በኃጢአት የተጨማለቅን ስለሆነ ግንኙነታችን በመልአክ ፣ በቅዱሳን በኩል እንዲሆንልን እንለምናለን ፡፡ እስኪ ከዚህ በታች ከመጽሐፍ የወሰድኳቸውን ቃሎች በቀጥታ ያንብቡልኝ ፡፡

  “እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። ሂድ፥ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም። ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ወደ ማልሁባት ምድር፥ ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው ምድር አንተ ከግብፅ ምድር ካወጣኸው ሕዝብ ጋር ከዚህም ውጣ። አንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለ ሆንህ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ እኔ በአንተ መካከል አልወጣምና በፊትህ መልአክ እሰድዳለሁ፤ ከነዓናዊውን አሞራዊውንም ኬጢያዊውንም ፌርዛዊውንም ኤዊያዊውንም ኢያቡሳዊውንም አወጣልሃለሁ።” ዘጸ 33:1-3 “ትኩረት አንድ - በአንተ መካከል አልወጣምና በፊትህ መልአክ እሰድዳለሁ”


  “በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት ፡፡” ዘጸ 23:20 -21 “ ትኩረት ሁለት - በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ ፤ ቃሉንም አድምጡ”

  “ወደ እግዚአብሔርም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ሰድዶ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።” ዘኍል 20:16 “ትኩረት ሦስት - እግዚአብሔር እንዳወጣቸው ቢታወቅም መልአክንም ሰድዶ ከግብፅ ምድር አወጣን ይላሉ” ፡፡ እንግዲህ ሦስት ቃል ካስነበብኩዎት የመጽሐፍ ምስክርነቱ የሚጸና ይመስለኛል ፡፡

  ይኸን የብሉይ ዘመን ብቻ አድርገው ፣ የእህልና የውኃ ነገርም አስመስለው እንዳያቀሉብኝ ከአዲስ ኪዳን ትምህርትም አንድ የማያንቀሳቅስ ኃይለ ቃል ልበልልዎት ፡፡ እግዚአብሔ ረሃብን ለማስታገስና ከርስን ለመሙላት የሚያገለግል እንጀራ ወይም መና ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ለመላእክቱ የበለጠ ስልጣንም ሰጥቷቸዋል ፡፡ ማቴ 13:49 “በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኃጢአተኞችን ከጻድቃን መካከል ይለዩአቸዋል፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤” ይላል ፡፡ ይኸን ከቃሌ ፈጥሬ የደረስኩት ሳይሆን እግዚብሔር መንፈስ ቅዱስ እንዳስነብብዎት እየረዳኝ ያዘጋጀሁት ስለሆነ መጥኃፍዎን ፈትሸው እርሶም ንስሐ ይግቡና ወደ ጥንት ሃይማኖትዎ ይመለሱልን ፡፡

  ReplyDelete
 10. የመጀመሪያውን አታወጡትም ብዬ ስለሰጋሁ የተደገመው

  አስተያየቴን በድረ ገጻችሁ ለማስነበብ በጣም አስቸጋሪ መሆኑን ባውቅም አሁንም ይህችን አቅርቤአለሁ ፡፡ ብዙ ትግል እያስፈለገ በመምጣቱ ላለመጻፍ ወስኜ ነበር ፤ ለዲያብሎስ እጅ ላለመስጠት በማለት ግን ከራሴ ጋር ተሟግቼ አቀረብኳት ፡፡

  አስቀድሞ ማሳሰቢያዬ ፡-
  ምእመኑን የሚያደናግሩና መልሰው ቤተ ክርስቲያንን የሚሞግቱ ፣ በቃላት ድርዳሮሽ የሚወጓትም ፣ የሰጠቻቸውን ስምና ማዕረግ በመጠቀም ስለመሰለኝ ፣ ከዛሬ ጀምሮ ሳይጠየቁ ፣ በራሳቸው ስላሳወቁኝ ብቻ መልሼ ሹመታቸውን ስጠራ አልገኝም ፡፡ ምክንያቱም መሐንዲሱ በተመረቀበት ሥራ ተሰማርቶና አገልግሎ ፣ በሠለጠነበት ሙያው ሳይጠቅምበት ወደ ግብርና ከተሰማራ ፤ በገበሬነቱ ነው እንጅ መጠራት ያለበት ቀለምን ስለቆጠረበት ብቻ መሐንዲስ በሚለው አይደለም ፡፡ ፍሬ ባላፈሩበት ሙያና ማዕረግ ራሳቸውን እየጠሩ ፣ ከበሬታቸውን በእኛ ላይ ማሸከማቸውም ለጊዜው አግባብ ሆኖ አልታየኝም ፡፡ ስለዚህም በራሴ ትክክል የመሰለኝ ፣ ዲያቆን ይበል መሪጌታ ወይም ሌላ ፣ ለኔ ከጸሃፊነቱ የተለየ ሹመቱ አይታየኝምና ፣ ሁላችንንም በሚያግባባን ቃል ፣ ጸሐፊ ወይም ጣፊ ብየ ብጠራ ጣፎች ሁሉ እንደ ማይቀየሙኝ እርግጠኛ ነኝ ፤ ምክንያቱም የተሰጣቸውን የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን በራሳቸው እያፈረሱ ፣ አንባቢን ለማስፈራሪያ ይሆናቸው ዘንድና ፣ መማራቸውን ለመገለጽ ምንም ማዕረጋቸውን ቢደረድሩትም ከምላሴ ሊንጠለጠልል ፣ ከአንጀቴም ጠብ ሊል አልቻለም ፡፡ ቢቻል እነሱም ይህን አግባብ ያልሆነ የስም ሸክም ባይጭኑንና ፤ ደፍረን ሃሳባችንን እንዳንገልጽ የሚያስፈራራ ደንቃራቸውን ከሚያስነብቡን ፤ ቤተሰብ የሰጣቸውን አለበለዚያም የብዕር ስም ወይም ስም አልባ ሆነው መልዕክታቸውን ብቻ ቢያስተላልፉልን ለኛ ይበቃናል ፤ ተቀጽላቸው ስለማያስጨንቀንም መልስ ለመስጠት መልካም ይሆንልናል፡፡ እኔ ከአደግንበት ባህላችን አንጻር ማዕረጋቸውን እየጠራሁ ፣ አንቱዬ እባክዎ ተሳስተዋል ብዬ ለመናገር ከህሊናየ ጋር ብዙ ትግል ማድረግ አስፈልጐኛል ፡፡

  እንግዴህ ቃሌን ከይቅርታ ጋር እጀምራለሁ ፡-
  ጣፊ ገረመው ለራሳቸው እግዚአብሔርን የሰነፈ አስመስለው ጥብቅና ቆመውለታል ፤ ውክልና ሳይሰጥዎትም ይናገሩለታል፡፡ እኛ ይህን ዓለም የፈጠረ አንድ እግዚአብሔር አለን ፤ ሁሉ በርሱ ሆኗል ፤ ያለርሱ የተከወነ አንዳች የለም እንላለን ፡፡ በእኛና በእግዚአብሔር መሐል ደግሞ የሚራዱን ፣ የሚያማልዱን ድንግል ማርያም ፤ መላእክት ፣ ቅዱሳንና ጻድቃን አሉ ፡፡ እርሱ በጸጋው ስለመረጣቸውና ስላከበራቸው ከኃያሉ ፈጣሪ ቸርነትን ያስገኙልን ዘንድ እንማጸናቸዋለን ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ከመረጠው ህዝብ ጋር ያደርግ የነበረውን ግንኙት እንዴት እንደነበር ተዘንግቶዎት እንደ ሆነ ወይም አዲሱን ትምህርት ከሰፈር መቀበልዎን ለመመስከር ብቅ ማለትዎ ግልጽ አይደለም ፡፡ ከላይ እንደ ገለጽኩት የእንጀራው /መና/ ባለቤት እግዚአብሔር መሆኑን ማንኛውም የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኝ ያውቃል ፤ ነገር ግን ደካሞችና በኃጢአት የተጨማለቅን ስለሆንን ግንኙነታችን በመልአክ ፣ በቅዱሳንና በጻድቃን በኩል እንዲሆንልን እንለምናለን ፡፡ እስኪ ከዚህ በታች ከመጽሐፍ የወሰድኳቸውን ቃሎች በቀጥታ ያንብቡልኝ ፡፡

  “እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። ሂድ፥ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም። ለዘርህ እሰጣታለሁ ብዬ ወደ ማልሁባት ምድር፥ ወተትና ማርም ወደምታፈስሰው ምድር አንተ ከግብፅ ምድር ካወጣኸው ሕዝብ ጋር ከዚህም ውጣ። አንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለ ሆንህ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ እኔ በአንተ መካከል አልወጣምና በፊትህ መልአክ እሰድዳለሁ፤ ከነዓናዊውን አሞራዊውንም ኬጢያዊውንም ፌርዛዊውንም ኤዊያዊውንም ኢያቡሳዊውንም አወጣልሃለሁ።” ዘጸ 33:1-3 “ትኩረት አንድ - በአንተ መካከል አልወጣምና በፊትህ መልአክ እሰድዳለሁ”

  “በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት ፡፡” ዘጸ 23:20 -21 “ ትኩረት ሁለት - በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ ፤ ቃሉንም አድምጡ”

  “ወደ እግዚአብሔርም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ሰድዶ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።” ዘኍል 20:16 “ትኩረት ሦስት - እግዚአብሔር እንዳወጣቸው ቢታወቅም መልአክንም ሰድዶ ከግብፅ ምድር አወጣን ይላሉ” ፡፡ እንግዲህ ሦስት ቃል ካስነበብኩዎት የመጽሐፍ ምስክርነቱ የሚጸና ይመስለኛል ፡፡

  ይኸን የብሉይ ዘመን ብቻ አድርገው ፣ የእህልና የውኃ ነገርም አስመስለው እንዳያቀሉብኝ ከአዲስ ኪዳን ትምህርትም አንድ የማያንቀሳቅስ ኃይለ ቃል ልበልልዎት ፡፡ እግዚአብሔር ረሃብን ለማስታገስና ከርስን ለመሙላት የሚያገለግል እንጀራ ወይም መና ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ለመላእክቱ የበለጠ ስልጣንም ሰጥቷቸዋል ፡፡ ማቴ 13:49 “በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኃጢአተኞችን ከጻድቃን መካከል ይለዩአቸዋል፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤” ይላል ፡፡ ይኸን ከቃሌ ፈጥሬ የደረስኩት ሳይሆን እግዚብሔር መንፈስ ቅዱስ እንዳስነብብዎት እየረዳኝ ያዘጋጀሁት ስለሆነ መጥኃፍዎን ፈትሸው እርሶም ንስሐ ይግቡና ወደ ጥንት ሃይማኖትዎ ይመለሱልን ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድማችን እገዜር ይባርክ.

   Delete
  2. እዚህ ጋር ጥያቄው ማለትም ጸሐፊው ያነሱት ጥያቄ ሚካኤል መናን ሳያወርድ እንዳወረደ ተደርጎ መቅረቡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም የሚልና የቆርኔሌዎስ ጸሎት በእግዚአብሔር ፊት አረገ ተብሎ ተጽፎ ሳለ መልአኩ ወደ እግዚአብሔር አድርሶለታል መባሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም የሚል እንጂ አሁን እርስዎ ያቀረቡት አይደለምና አስተያየት ለመስጠት ከመነሳትዎ በፊት በቅድሚያ ጽሑፉን በሚገባ ያንብቡት፡፡
   በተረፈ እስከ አሁን የሕይወትን ቃል ስላልሰሙ ቃለ ሕይወትን ያሰማዎ
   ደቂቀ አቡዬ ነኝ

   Delete
  3. ደቂቀ አቡዬ
   ጽሁፉን ደጋግሜ አንብቤ ፣ ስለ ጣፊው እውቀትና ማዕረግም ተጨንቄ ፣ ከራሴም ብዙ ተሟግቼ ነው የወሰንኩት ፡፡ እኔ ማተኰር የፈለግሁት አጠቃላይ ግንዛቤ ላይ እንጅ በተጸውዖ ስም ላይ አይደለም ፡፡ ስለዛም ነው ሚካኤል ሚካኤል ከማለት ስለ መላእክት በጠቅላላ የተነገረውን ለማስነበብ የሞከርኩት ፡፡ በዘጸአት የሚናገረው በመልአክ ስም ስለነበረ እኔ ለጊዜው በውል ለይቼ ማንነቱን የማነብበት መጽሐፍ ስለሌለኝ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር የሚያስኬደኝን አቀረብኩ ፡፡ በደፈና ከተመለከትነው ግን ስለ አንድ ነገር ሲነገር ፣ ሁልጊዜም አለቃውና ተወካዩ ነው ተጠሪ የሚሆነው ፤ ለሐዋርያቱ ጴጥሮስ እንደ ሆነው ዓይነት ፣ ለመላእክቱ ደግሞ ሚካኤል ፡፡

   እንዲያውም ምኑ ሰው ነህ ካላልከኝ የይሖዋ ምስክሮች እንኳን የሚካኤልን ክብር አሳድገው ኢየሱስ ነው እስከ ማለት ደርሰዋል ፡፡ ትክክል ናቸው ማለቴ አይደለም ፡፡ ቢሆንም ሚካኤል በአለቅነቱ የሰማይ እንጀራ /መና/ አደለ ቢባል ለኔ ትልቁ ሥራ አይደለም ፡፡ ከዛ የበለጠ ስለ እርሱ በመጽሐፍ የተጻፈው ሥራው እንዲህ ይላል ፡፡ "በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥" ራዕ 12፡7 ፡፡

   በመሠረቱ ከዘንዶው ይዋጋል ተብሎ በዘፍጥረት 3፡15 የተጻፈው ግን ከሴቷ የሚወለደው ነበር ፡፡ ነገር ግን እንዲያ ቢባልም ፣ ለአምላክ አገልጋይ በመሆኑና አለቅነትም ስላለው ይህንን የመጨረሻውን ጦርነት ሚካኤል እንደሚዋጋና ለድኀነታችንም ሊራዳን እንደተዘጋጀ ተጽፎልናልና በጥቃቅኑ ነገር አንጨነቅ ፡፡

   Delete
  4. Kele hiwot yasemalin melis yesetu wendme weym ehite

   Delete
  5. Melkam new, but the war between the holy angels and bad evil angels already happened thousands of years ago when the devil rebelled against God. Again, you are misinterpreting this.

   The verse that you quoted "በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥" ራዕ 12፡7" refers to a past event, not to the great war between Christ and the Beast, which is expected to happen around the end of this world.

   Please don't mix up things. thanks.

   Delete
  6. ስለ ማረሚያህ አመሰግናለሁ ፤ መፈጸሙን በግልጽ ተጽፎ ስላላነበብኩ ተሳስቼ ይሆናል ፡፡ ያለፈም ሆነ የወደፊት ቅዱስ ሚካኤል ተሳትፎ ማድረጉን ለማሳየት ብቻ ነው ለማስረዳት የፈለግሁት ፡፡
   አመሰግናለሁ

   Delete
 11. ኧረ ተው ጸሓፊ! መላ'እክት እኮ ለፈጣሪ ተላላኪዎች እንጂ ላኪዎች፤ አምላኪዎች እንጂ ተመላኪዎች
  አይደሉም ምን የቀትር እባብ ይመስል ታፏጫለህ እንደ ቀትር ጋኔንስ ለምን ትጠቃቅሳለህ? ይልቁንስ
  አንድነትን በሦስትነት ሦስትነትን ባንድነት ተቀብለህ ብታዘግም አይሻልም፤ በኔ በኩል ይሻላል እላለሁ፤

  ReplyDelete
  Replies
  1. ባለዚህ ጉዳይ መላእክት ለፈጣሪ ተላላኪዎችና አምላኪዎች ናቸው በማለትህ መልካም ብለሃል እልሃለሁ ፡፡ ለጠየቋቸው አግባብ ያለው መልስ ይሰጣሉ ብትል ደግሞ ግንዛቤህ የተሟላ ይሆንልህ ነበር ፡፡ ለዘካርያስና ለድንግል ማርያም ከመቅጽበት ገብርኤል ከራሱ መመለሱ የሰውን ነገር ማዳመጡና ማስተናገዱ አይመስልህም ? እንዲያውም ሊያረጋጋ ፣ ሊያስተምር ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ደግሞ በራሱ ሊገስጽህ እንደሚችል ከዚሁ ከወንጌል ቃል አንብበሃል ፡፡ ስለሆነም እኛም አማልዱን ፣ እርዱን ብንል ጥፋት የለብንም ፤ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ መልስ ይሰጡናል ፤ ይራዱናል ፤ ጸሎትና ልመናችንን ያደርሱልናል ፤ ያሰሙልናል ፡፡

   በተረፈ ከጋኔን ጋር ለምትኖረው ሰው እግዚብሔር ይርዳህ ብዬ እጸልያለሁ ፡፡ ከመጽሐፍ መጥቀስ ለጋኔን ብቻ የተሰጠ ስልጣን ካደረግኸው ፤ ከእንግዲህ አይጠቅምህምና መጽሐፍ ቅዱስህን /ምናልባት ከቤትህ ካለ/ አውጥተህ ጣለው ፡፡ ማጠፊያው ሲያስቸግርህ ይህን የደካማ አነጋገር ተገለገልክበት ፡፡ አሁንም እግዚአብሔር በመላእክቱ በኩል ያግዝህ ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱን የቀትር ጋኔን መሣሪያ አድርጐ ከሚያሳይህ መጥፎ መንፈስም ይፈውስህ ዘንድ በጸሎት አስብሃለሁ ፡፡ ሳናውቀው በየቤቱ ስንት እስረኛና የታመመ ወገን ኖሯል ለካስ ? ከመጽሐፍ ቅዱስ ሲጠቀስልህ የጋኔን ፣ ከአዋልድ ሲባል ተረት የምትሉ ከሆነ ሃይማኖታችሁን አንተና መሰሎችህ በጥልቀት ፈትሹት የሚል መልዕክትም ስለ አለኝ ዛሬውኑ ተጠቀምበት ፡፡

   ሌላ ቀርቶ ወንጌልን ሊያስተምርህ የሚመጣው መልአክ እንደሆነም “በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤” ራእይ 14:6

   ባትቀበለውም ዓይንህ እንዲያየውና መልአክ እንደሚመለክ እንድታነብ በማለት ደግሞ ”የእርሱ የምሆንና ደግሞ የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ /የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ/ በዚች ሌሊት በአጠገቤ ቆሞ ነበርና፥ ” ሥራ 27:23 ይልብሃል ፡፡ ይህን ምሥክርነት የሚተርክልህ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምኖ ፣ ህይወቱን እንኳን ቢሆን አሳልፎ ሊሰጥ የተዘጋጀው ታላቁ ሐዋርያ ነው ፡፡

   ሙግትህን ማንሳትህን አሳውቀኝ

   Delete
  2. ገብርኤል ማርያምንና ዘካሪያስን በነበሩበት ስፍራ ስለነበረ ሰማቸው፡፡ አሁን ግን ገብርኤል እግዚአብሔርን በማመስገን ስራ ላይ ብቻ በመሆኑ እኛን ሊሰማ የሚችልበት ሁኔታ ውስጥ አይደለምና ይህን እንዴት ታየዋለህ?
   ደቂቀ አቡዬ ነኝ

   Delete
  3. Even if I agree with on most of your statements and analysis, I would like to disagree with the following statement at the strongest term:

   "ባትቀበለውም ዓይንህ እንዲያየውና መልአክ እንደሚመለክ እንድታነብ በማለት ደግሞ ”የእርሱ የምሆንና ደግሞ የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ /የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ/ በዚች ሌሊት በአጠገቤ ቆሞ ነበርና፥ ” ሥራ 27:23 ይልብሃል ፡፡ ይህን ምሥክርነት የሚተርክልህ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምኖ ፣ ህይወቱን እንኳን ቢሆን አሳልፎ ሊሰጥ የተዘጋጀው ታላቁ ሐዋርያ ነው ፡፡"

   Kesis Dejene or X, you have made a grave mistake with the above statement. In the verse at Acts 27:33, the word "yemamlkew" qualifies "Egziabehere", not the angel. You have completely misinterpreted the phrase and hence the meaning of the verse. STOP IT!!! YOU HAVE MADE A GRAVE MISTAKE WITH THE ABOVE STATEMENT!!! I personally CONDEMN AT THE STRONGEST TERM any form of worship of Angels. The holy person who said those words never referred to the angel as "yemamelkew." Again, "yemamelkew" refers to "Egziabehere" Which follows right after it.

   Delete
  4. እንግሊዝኛው ከቀናህ ፣ ይህን የአምልኮ ቃል የሚመሰክረው የአማርኛው ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ኤቫንጀሊካል ነን ብለው የሚጠሩት የሚያነቡትን መጽሐፍ ቅዱስም ጭምር መሆኑን እንድትመለከተው ይኸውልህ
   Acts 27:23 For there stood by me this night an angel of the God to whom I belong and whom I serve
   NKJV Bible

   Acts. 27:23 Last night an angel of the God whose I am and whom I serve stood beside me
   NIV Bible

   Acts 27:23 For there stood by me this night an angel of the God to whom I belong and whom I serve,
   The Billy Graham Training center Bible

   Acts 27:23 For there stood by me this night the angel of God, whose I am, and whom I serve,
   KJV Bible

   Delete
  5. ደቂቀ አቡዬ
   ራሳችሁን ከፍ ከፍ የምታደርጉና ጻድቅ ነን ፣ ቅዱሳን ነን ለምትሉና ለምታነጻጽሩ ሰዎች እንደ ወገን ተጠንቀቁ እላለሁ ፡፡ ምላሳቸውን ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ ህይወታቸውንና ኑሮአቸውን እንኳን አሳልፈው ሰጥተው ፣ በእምነታቸውና በምግባራቸው በመመካት አልተመጻደቁበትም /ለምሳሌም አቡነ ተክለ ሃይማኖት/ ፡፡

   እኔና መሰሎቼ ደግሞ ኃጢአተኞች መሆናችንን እንረዳለን ፡፡ የቱንም ያህል እምነትና አምልኮ ቢኖረን ፣ እሱ በቸርነቱ ይምረን እንደሁ እንጅ እያልን የምንደክም በደለኞች ነን ፡፡ ጽድቃችን እንኳንስ ከዘካርያስና ከድንግል ማርያም ሊነጻጸር ቀርቶ ያንተንም ያህል ይሆንልኛል ብዬ አላስብም ፡፡ መላእክትን ለማየት እኮ ፣ ቢያንሰ አንተም በመንፈስ አድገህ ፣ ጻድቃንና ቅዱሳኖቹ ከደረሱበት ደረጃ መድረስ አለብህ ፤ ያንንም ፈጽመህ እንኳን ካልተፈቀደልህ ደረቅ ግንባር ይዘህ ነው ይምትኖረው ፡፡ በራሱ ስትመረጥ ደግሞ እንደ ጳውሎስ አንደፋድፎም ቢሆን ራሱን ይገልጥልሃል ፡፡

   እናም እኔን ኃጢአተኛውን እንደ ድንግልና ቅድስት ማርያም የአምላክ እናትን ያህል አድርገህ ፣ መላክ አላናገርክም ብለህ አትሞግተኝ ፡፡ መላእክት መንፈሳዊ አካላት ስለሆኑ የሚገለጡላቸው ጻድቃን አሉ ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በእቅድ በፈቃዳቸው ይቀርባሉ ፡፡ አላየሁም ብሎ መካድ ክርስቲያናዊ አካሄድ አይደለም ፡፡ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው ተብሏልና ፣ እኛም ሳናይ በመንፈስ ሆነን እንጸልያለን ፡፡ አንተም አያምልጥህ ፡፡ ለመሆኑ አንተ ጌታን የት ቦታ አይተኸው ነው ያድነኛል ብለህ የምትጸልየው ? ክፉ አጻፍከኝ ፡፡ አየህ ነገር ነገርን ይወልዳል ፡፡
   በጌታ መመካቱ አግባብ ቢሆንም ፣ ያሉበትን ጠንቅቆ ማወቅ ግን ፣ በድፍረት ከሚፈጸም ስህተት ያተርፍሃልና እኔን በደለኛውንና ኃጢአተኛውን ማረኝ እያልክ መጸለይ አትዘንጋ ፡፡

   Delete
  6. ካሳ ሃይማኖትን ትተን አማርኛም ልንማማር መሰለኝ
   ለአንድ ወገኔ አማርኛውን ከማስረዳት በእንግሊዝኛ እንድትረዳ ማድረጌ ስህተት ሆኖ ስለተሰማኝ ይህችን ታግዝህ እንደሁ በማለት ሞጫጨርኳት ፡፡

   አየህ ካሳ ፡-
   የአበበ እናት ሲባል የሚያወሳው ስለ እናትየዋ እንጅ ስለ ልጃቸው አበበ አይደለም ፡፡
   የከበደ ልብስ ሲባልም ፣ የሚነግረን ስለ ልብሱ ነው እንጅ ስለ ከበደ አይደለም ፡፡ አስከትሎ ቆንጆ ፣ ቀዳዳ ወይም ሌላ ነው ሊለን ይችላል ፡፡ በሰዋሰው ትምህርት ባለቤት ምናምን የሚሉት ነገር አለ /ከአሃምሳ ዓመት በፊት የተማርኩት ነገር ነውና በትክክል ባለመግለጼ አትፍረድብኝ/፡፡

   የእግዚአብሔር መልአክም ብሎ ሐዋርያው ሲናገር ፣ የገለጸው ስለ አናገረው መልአክ ነው እንጅ ስለ እግዚብሔር አይደለም ፡፡
   አሁንም አልገባ ካለህ በዚህኛው ደግሞ እስቲ
   የድንጋይ ኳስ ቢልህ ኳሱ ከምን እንደተሰራ የጨርቅ ወይም የላስቲክ አለመሆኑን ሲያስረዳ መግለጹ ነው ፡፡ ስለ ድንጋዩ እያወራ አይደለም ፡፡ የዓይን መነጽር ሲልም ስለ መነጽሩ እንጅ ስለ ዓይን እየተናገረ አይደለም ፡፡ ይህን ያህል ከሞከርኩልህ በተረፈ ሰዋሰው የሚያውቅ ምሁር አናግር ፡፡
   በተረፈ ቀሲስ ደጀኔ አይደለሁም ፤ የቀሲስን ያህል አዋቂ ካደረግኸኝ እግዚአብሔር አንተንም ከፍ ከፍ ያድርግልኝ ፤ ባለህ ላይ ይጨምርልህ ፡፡

   Delete
 12. በእውነትቀሲስ እግዚአብሄር ይስጥዎ ስለመልካምትምርትዎ. አንተ ይሄን የፃፍከው መናፈቅ መሆንህ እንድንረዳ ፈልገህ ከሆነ እናውቅሀለን አዛኝ ቅቤ አንጐች አርፈህ ለሆዴ ነው አትልም አትሸቃቅጥ የዚህምድር ነገር ሀላፊ ነውና.

  ReplyDelete
 13. ...ምስጋናውን ለማጋራት ወይም ለመንጠቅ እየተሸረበ ያለውን ሴራ....!!! ante le AMLAK tekorkuari!!! AMLAKACHIN indante yalle dekama, yemminnetekibet!!!mesloh yemitasib minigna dekama astesaseb yizehal bakih! Be Cherinetu Yifewwusih! Amen!!

  ReplyDelete
 14. “በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት ፡፡” ዘጸ 23:20 -21

  Read and re-read "My name is on him, if you sin,he has no mercy" Who has no mercy? the Angel. Look, while a merciful character is the behavior attached only to God, doing a merciful thing is given to Angels. How? God gave them (the Angels) to punish those who sin and protect those who obey God.

  What word would I need other this? For me and believers of Tewahido Orthodox, this is verse is enough than millions of broken verses quoted by the protestants and tehadisos to justify their false arguments.

  Geta Hoy Ewedihalehu Yetewahido Lij Adrgeh Silanorkegn!

  ReplyDelete
 15. “በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት ፡፡” ዘጸ 23:20 -21
  Read and re-read "My name is on him, if you sin,he has no mercy" Who has no mercy? the Angel. Look, while a merciful character is the behavior attached only to God, doing a merciful thing is given to Angels. How? God gave them (the Angels) to punish those who sin and protect those who obey God.
  What word would I need other than this? For me and believers of Tewahido Orthodox, this verse is enough than millions of broken verses quoted by the protestants and tehadisos to justify their false arguments.
  Geta Hoy Ewedihalehu Yetewahido Lij Adrgeh Silanorkegn!

  ReplyDelete
 16. ድሉ ዘእግዚአብሔርJune 14, 2012 at 8:13 PM

  ማዳንና ማማለድ አንድ አይደለም ። ድኅነት በመኃኔዓለም ክርስቶስ ብቻ ነው ! ምልጃ ግን በናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ፣ በቅዱሳን መላእክት ፣ በጻድቃንና ሰማዕታት ነው ። አለቀ በቃ ፥ ጠጉር ስንጠቃ ይብቃ !

  ReplyDelete
  Replies
  1. አመሰግናለሁ ፡፡ በዚሁ ይብቃ ፡፡

   Delete
  2. መዳን በክርስቶስ ያልከው ያስማማናል። አራት ነጥብ።
   ሰው ሲበድልና ኃጢአት ሲሰራ ደግሞ ወደክርስቶስ ንስሐ መግባት!!! ከዚያ ውጪ ቅድስና የለም። አራት ነጥብ!!!!! ከዚህ በክርስቶስ አምኖ በመመለስ ከመዳንና ሲበድሉ ደግሞ ንስሐ ከመግባት ውጪ የዘላለማዊ ሕይወት መንገድ አለ? የለም!!!!!!!!!!
   7 ትውልድ፤ 12 ትውልድ፤ 30 ትውልድ፤ አቧራ መላስ፤ ፍርፋሪ መቅመስ፤ እባብ መግደል፤ ወዘተ ሰይጣን ያስቀመጣቸው እንቅፋቶች እንጂ በወንጌል የተጻፉ አይደሉም።

   Delete
  3. For us who believe in God's miracle and grace on his saints, not only 30 generations possible to redeem thousands of generations. Is there anything impossible for God? Just leave for us for the true believers, and you stay with your heresy which you inherited from the 16th century Lutherans. Tell me where was your teaching before the 16th century. Do you think that a belief that emerged after 1550 years after Jesus Christ would tell the truth.

   You say 'wengel', but how crooked your mind is just to assume the acts of saints to be included in the Holy Bible, while the Bible itself was assembled hundreds and thousands of years before the saints themselves. Your suggestion is just a silly argument which is ridicules after all. I am always happy that our God counts everyone of us and at the end of the day He will pay us accordingly. But, the same time am extremely sad for those lives that are lost by heretics.

   Delete
 17. እግዚአብሔር ብቻውን የሚመለክ አምላክ ነው። ከእርሱ ጋር ማንም ልስተካከል አይችልም። መለኮት መለኮት ነው። መልአክት ግን ከእግዚአብሔር ለተለያዩ አገልግሎቶች የምላኩ ናቸው። ማክበር ይቻላል ነገር ግን ማምለክ አይቻልም ። አምልኮት የሚገባው ለአንድ አምላክ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። መለኮት ወይም እግዚአብሔር ሦስትነቱና አንድነቱን ማመን ነው። የመልአክት ትርጉሙም ተላክ ማለት ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ማንም እኩል ልሆን አይችልም። ለእግዚአብሔር አምላክ የሚገባውን ምስጋና ለሌላ ማድረግ አይቻልም።ይህም እውነተኛ የኦርቶዶክስ ዶግማ ነው።አንዳንድ ሰባክያን ለራሳችው ጥቅም እንድመች ተከታይ ለማግኘት የሚያደርጉት አግልግሎት የስጋ በሆኑ ህይወት አይሰጥም።የሚወደኝ ብኖር ቃለን ይጠመብቅ ዮሐ 14 ቄ 13

  ReplyDelete
  Replies
  1. Your comment is a kind of vague which has been waxed by sheep's clothing. No one said Angles should be divine like God, but they intercede. Don't take away the discussion to your intention of sabotaging the word of God. It's your choice if you believe they intercede, if not leave the judgment to God.

   Delete
  2. "አምልኮት የሚገባው ለአንድ አምላክ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።"

   ወንድሜ ቃልህ ጥሩ ነበር ፤ ነገር ግን የጐደሉብህን አብና መንፈስ ቅዱስን አክልበት ፡፡ ጥቆማዬ ዛሬ የአንተን ጽሁፍ ያነበበ መንገደኛ ፣ ደግሞ ነገ ተነስቶ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አብና መንፈስ ቅዱስን አታመልክም እንዳይለን ስለሰጋሁ ነው ፡፡ አስበህ ያደረግኸው ከሆነ ግድፈት ፈጽመሃል ፤ እንደ አንተ አብንና መንፈስ ቅዱስን ትተን ወልድን ብቻ አናመልክም ፡፡ በጽሁፍህ ላይ ብቻ የሚለው ቃል መግባት አይገባውም ፡፡

   በተረፈ ሐዋርያው ጳውሎስ የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ ቢለንም ፣ እኛ የተዋሕዶ አማኞች መላእክትን ከአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያማልዱናል ፣ ደካሞች ስለሆንን ይራዱናል ፣ ኃጢአተኞች ስለሆንን ጸሎታችንን ከፍ ያደርጉልናል ፣ ያሰሙልናል ብለን የአክብሮት ስግደትን ብቻ እንፈጽማለን እንጅ ስለአምልኮ አይደለም ፤ አትጠራጠረን ፡፡

   Delete
 18. የአምልኮት ነገር ከተነሳማ «በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ አድባር ኮኑ ሕብስተ ሕይወት» የሚለው ተለውጦና ክርስቶስ ተወርውሮ «በእንተ ልደቱ ለተክለ ሃይማኖት አድባር ኮኑ ሕብስተ ሕይወት...» ተክለሃይማኖት በተወለደ ጊዜ ተራራዎች ሁሉ የሕይወት ሕብስት ሆኑ የተክለሃይማኖት ዚቅ፡- ተብሎ ለሰው ተለውጦ የክህደት አምልኮ ይፈጸምበታል፡፡ ስለዚህ እውነት የምትጽፉ ሰዎች በጣም በርቱ
  ቀሲስ ደጀኔ ለድህነት እንድትበቃ እንጸልይልሃለን

  ReplyDelete
 19. አያ ጸሓፊ ሆይ የቀትር ጋኔን ይሉሃል ሌላ አለ ይኽው ዕኮ ነው፤ ብለህ ብለህ ራስህንና መሰሎችህን
  ለመደለል ጳውሎስን መልአክ አምላኪ አልኸው ይገርማል!እስቲ ልብህን ከፍርኀት ኅሊናህን ከብክነት
  አ'አምሮህን ከጭንቀት መልሰህ ቆላስይስ ፪ ፲፰(ቆላ 2/ 18.ያለውን ተመልከተው ማንም ሰው ሰው መስሎ መላእክትን ታመልኩ ዘንድ እንዳያሳንፋችሁ(እንዳያታልላችሁ)እያለ ያስተማረ ጳውሎስን ከፈጣሪ
  አምልኮት ለማውጣት መሞከርህ ተጃጅልሃና ባጭሩ ፊደል ቁጠርና ንስሓ ግባ!በተረፈ መደዴውን በመደዳ
  ለመሸንገል በሓ ሥራ ፳፯/፳፫(27/23 ስንኳንስ ትርጉሙን ንባቡንም አላየኸው በምንስ ዓይን?
  አዋቂዎችን ጠይቀህ እንድትረዳ ያስባልኸውን መጀመሪያ በግእዝ እስመ ቆመ ኀቤየ በዛቲ ሌሊት መልአከ
  እግዚአብሔር ዘአነ ሎቱ ወኪያሁ አመልክ እኔ ለርሱ የሆንሁና እርሱን የማመልከው እግዚአብሔር አለ እንጂ ለመላኩ ነኝ መላክ አመልካለሁ አላለም፤የማመልከው እግዚአብሔር የላከው መልአክ በዚች ሌሊት በኔ ዘንድ ቆሟልና በማለት ከፈጣሪ ተልኮለት እንደ መጣ ተናገረ እንጂ አምልከው ብሎ እንደ ላከለት አልተናገረም ያሁኑን ትውድ ስም ማጥፋት አልበቃችሁ ብሎ ወደ አለፈው ትውልድ መዞራችሁ ይገርማል እላለሁ እናም አስቡበት አለዚያ ግን ወይዘሮ ስመኝ ለማያውቁሽ ታጠኝ ነውና ሰው የማይገባውን ጥቅስ ካመጣ ጋኔን ማለት ያ ነው፤ ለመማር ያብቃህ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንደ አልከውማ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰት ጽፏል ወይም እርስ በርሱ ይጋጫል ማለት ነው ፡፡ አንዱ መጽሐፍ ሁለት ዓይነት ንባብ ካቀረበልን ደግሞ እየመረጥን ፣ አንተም ለራስህ ፣ እኔም ለራሴ ፣ ሌሎቹም ለራሳቸው የሚስማማቸውን ትርጉም ይከተሉ ማለት ነው ፡፡

   የወይዘሮ ስመኝ ልጅ ቃሉን ከመጽሐፍ ገልብጨ ያስቀመጥኩት መሆኑን ለማስረዳት በአማርኛ ብቻ ሳይሆን በእንግሊዝኛ የተጻፈውንም አሳይቼአለሁ /ግዕዙን ስለማልረዳው ቢኖረኝም አላነበውም ፤ ይኸም ድክመቴ እንደሆነ አምናለሁ/ ፡፡ እንግዲህ እንዲህ ሐዋርያው በአዋጅ ለተሳፋሪዎች ተናግሮ የተጻፈውን ቃል ልታሻሽለው ወይም በትርጉም ልትቀይረው አስበህ እንደሆነ ድርሰትህን ጻፍልን ፡፡ ትንሽ እብደቱን የሚቀንስልህ ቢሆን ግን በመጽሐፍ ሙሴ ፣ የዕብራዊቷ ልጅም እንኳን አምላክ ተብሎ ተጽፎልሃል /ዘጸ 7፡1/፡፡

   ሐዋርያው ጳውሎስ የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ ማለቱ የአንተን ያህል የምድር ጥበብና ዕውቀት ጐድሎት እንዳይመስልህ ፤ የቋንቋ ደሃም አልነበረም ፡፡ በመመርመር ከሆነ ፣ ጳውሎስ መጽሐፍን ከማንም በላይ እንደሚያውቃትና እንደተረጎማት ማለትም እንደተገበራት በፊልጵስዩስ 3፡2-6 መልዕክቱ መስክሯል ፡፡ እናሳ ሥራ 27፡23 የሚናገረውን ከአንተ ቆላ 2፡18 እንደምን አድርገህ ታስታርቅልኛለህ ? በመካድና በመሸምጠጥ ከሆነ ክርስትናን ነው የምታራክሰውና ፣ አይሆንም እላለሁ ፡፡

   እኔ የተረዳሁት ምናልባት ትንሽ የሚያግዝህ ቢሆንና ፣ በአካል የማታውቀውን ሰው ከመዝለፍም ትቆጠብ ዘንድ በማለት ይኸው ፡፡ አምላክነት ማለትም ፈጣሪነት ፣ ገዢነት ለአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የባህርያቸው ነው ፤ ተነጻጻሪ ፣ ተወዳዳሪ የለባቸውም ፡፡ ለፈጠሯቸው ለሌሎች ፍጥረታት ደግሞ ሲመርጧቸውና ሲፈቅዱላቸው የጸጋ አምላክነት ያጐናጽፏቸዋል ፡፡

   ከዚህም ግንዛቤ በመነሳት ፣ በፈጣሪ ክብር ያህል ማለትም መስዋዕት ሆኖ ያዳናቸውን ኢየሱስን ክደው *** መልአክትን የሚያመልኩትንና እንደ እግዚአብሔር አድርጋችሁ አምልኩ የሚሉ መምህራንን በቆላስያስ መልዕክቱ ገሰጸ ፤ የመላእክትን የጸጋ አምላክነታቸውን በመቀበሉ ደግሞ የሐዋርያት ሥራ ምስክርነቱን ሰጠ ፡፡ ያው አንዱ ባለ መልካም አእምሮ ሰው ሁለቱንም ዓይነት ትርጓሜ የሚያስጨብጠንን ቃል በመናገር አስረድቷል እላለሁ ፡፡ እኔም ለአስረጅ እንዲሆን የመጽሐፍን ቃል አስነበብኩ እንጅ አምልኩ የሚል ትእዛዝ አልሰጠሁም ፡፡

   ከላይ ለሌላ ሰው በሰጠሁት አስተያየት አላነበብከው እንደሁ እንጅ "በተረፈ ሐዋርያው ጳውሎስ የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ ቢለንም ፣ እኛ የተዋሕዶ አማኞች መላእክትን ከአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያማልዱናል ፣ ደካሞች ስለሆንን ይራዱናል ፣ ኃጢአተኞች ስለሆንን ጸሎታችንን ከፍ ያደርጉልናል ፣ ያሰሙልናል ብለን የአክብሮት ስግደትን ብቻ እንፈጽማለን እንጅ ስለአምልኮ ብለን አይደለም ፤ አትጠራጠረን ፡፡" ብያለሁ ፡፡

   *** (በቆላ 2፡18ን የገለጽከው በግሪክኛው መጽሐፍ ቃሉ καταβραβεύω ንባቡ ካታብራቤው ሲሆን ተቀራራቢ ትርጉሙም የአሸናፊውን ድል ለተሸነፈው ወይም ለማይገባው ወገን አሳልፎ መስጠት ማለት ነው)

   በተረፈ እግዚአብሔር ይማርህ

   Delete
  2. ባለጉዳዩ ሰው አንተ ከሆንክ ፣ ለአንተ ከሰጠሁት አስተያየትም እንዲህ የሚል ይነበባል ፡፡
   "ስለሆነም እኛም አማልዱን ፣ እርዱን ብንል ጥፋት የለብንም ፤ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ መልስ ይሰጡናል ፤ ይራዱናል ፤ ጸሎትና ልመናችንን ያደርሱልናል ፤ ያሰሙልናል ፡፡"
   ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ጸጋ የሚለውን እንድትመለከተው ነው የፈለግሁት ፡፡

   Delete
 20. የማያውቁትንና ያልተማሩትን ፣ አላውቅም ፤ አልተማርኩም ማለት ማንንም አላስገደለም ፡፡ እኔ ደግሞ ግዕዝ አምላኪ አይደለሁም ፡፡ በግዕዝ በመጻፉ ብቻ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ነው ለማለት አስበህ እንደሁ የሰፈር የድርሰት ትርጉም ያመጣህልኝ ፣ እጅ ከፍንጅ ያዝኩህ ማለት ነው ፡፡ በተለይ አሁን ደግሞ አንዳንድ ከቤተ ክርስቲያን የኰበለሉ ግዕዝ ተናጋሪዎችም በግዕዝ መጻፍ ስለሚችሉ ጥርጣሬዬን ከፍ አድርጌአለሁ ፡፡ አንተ በወፍ ዘራሽ እንዳጐለደፍከው ሳይሆን አባቶቻችን ግዕዙን በሥርዓቱ ተርጉመው ያስቀመጡልን እንዲህ ይነበባል ፡፡

  ወይ እዜኒ እብለክሙ ኢትፍርሁ እስመ አልቦ ዘይትኀጐል አሐዱ ነፍስ እምኔነ ዘእንበለ ዳእሙ ሐመርነ ፡፡ እስመ ቆመ ኀቤየ በዛቲ ሌሊት መልአከ እግዚአብሔር ዘአነ ሎቱ ወኪያሁ አመልክ ፡፡ /"መልአከ እግዚአብሔር ዘአነ ሎቱ ወኪያሁ አመልክ" የሚለውን ልብ በልልኝ/
  ትርጉም ፡- አሁንም መርከባችን እንጂ ከመካከላችን አንድ ሰው እንኳን የሚጠፋ የለም ፡፡ እኔ የሱ የምሆንና የማመልከው የእግዚብሔር መልአክ /እንድታርፈው የማመልከው የእግዚብሔር መልአክ የሚለው እዚህም ጋ ተደገመልህ/ በዚያች ሌሊት ወደኔ መጥቶ ነበርና ፡፡
  ምንጭ ፡- http://ethiopianorthodox.org/amharic/yeqolotbet/addiskidantitle/addiskidan/gebrehawariat.pdf

  ReplyDelete
 21. Look carfeully! Man has free will.I and my church worship God
  please, come to worship Him, but be humble and open your eyes before you try to come to the home of Trinity. We do not want to worship other creatures.

  ReplyDelete
 22. all of you stop your none sense!! God does not judge us by our theological knowledge, skill of hair splitting biblical verses...or by the love we have for our sect or denomination... He judge us by the purity of our heart, motive and action....let us use the blog to preach love, harmony, forgiveness, compassion, unity.....the essence of the teachings of our Lord Jesus The Christ!!!!

  let us not judge our brothers, let us leave the judgement for God, let us have sin covering eyes....let us focus on our short comings than our brothers....

  ReplyDelete
 23. AnonymousJune 19, 2012 at 5:31 PM...Egzeabher edmena tena yesteh min yibalal.

  ReplyDelete
 24. denkoro menafikkkkkkkkkkkkkkkkkkkk

  ReplyDelete
 25. aye merigtea enkwan elalwen erasehenem alemrah

  eskidekmegn sakubeh

  kentu
  ayenehn yaberaleh

  ReplyDelete
 26. merigeta: enkuwan meri teketayim athon

  ReplyDelete