Friday, June 15, 2012

ዓለማየሁ ሞገስ ስለጥንተ አብሶ ይናገራሉ፤ በጥንተ አብሶ ዙሪያ ላነሡት ሀሳብ የሰጡት ርእስም የሚከተለው ነው

(ማርያም) ከጥንተ አብሶ ነጻ ናት ወይ?

በብሥራት ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለውን ይዘው እመቤታችንን ጥንተ አብሶ አልነካትም ከአዳም ጀምራ ስትወርድ ስትዋረድ የመጣች ንጹሕ ዘር ናት የሚሉ አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ጸጋን የተሞላች ከተወለደች በኋላም፣ መንፈስ ቅዱስ ካነጻት በኋላም ሊሆን ይችላል፤ ዘላለማዊ ድንግልናዋም በነቢያት ሲነገር ከጥንተ አብሶ ግን ነጻ ናት ያለ አንድም ነቢይ ስለሌለ፤ መልአክም መንፈስ ቅዱስ ይጸልልሻል ብሎ እንደሚያነጻት ተናገረ እንጂ እኔ ወንድ አላውቅም እንዴት ይሆንልኛል? ስትለው ሳለ ያለ ጥንተ አብሶ መወለዱን ለመናገር ምቹ ጊዜ ሳለው የመንፈስ ቅዱስን ማንጻት ተናግሮ ነው ያለፈው፡፡ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት መንፈስ ቅዱስ እንዳነጻት፣ «አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ ሥጋዋን አንጽቶ በላይዋ ላይ አደረ፡፡» ቅዱስ ያሬድ «ገሊላዊት ሐቀፈተከ፣ ነፍሳ ቀደስከ፣ ወሥጋሃ አንጻሕከ ገሊላዊት ታቀፈችህ፣ ነፍሷን ቀደስህ ሥጋዋን አነጻህ» መ. ቅ.ገ. 438፡21 እያሉ ስለሚናገሩና አብዛኛዎቹ አባቶችም እንደ ዳዊትና ሰሎሞን የመሳሰሉት ወንጀለኞችና አመንዝሮች ስለነበሩ በየት አልፋ ነው እሷ ከጥንተ አብሶ ነጻ የምትሆነው ይላሉ፡፡ ለሁሉም የቅዱሳት መጻሕፍትንና የቅዱሳን አበውን ትምህርት ከዚህ ቀጥለን አቅርበናልና አንባቢ በጥንቃቄ አንቦ እንዲከተለው አደራ እንላለን፡፡
ኢሳያስ ም. 61፡1-3 እግዚአብሔር ለድኆች የምሥራቹን ቃል እንዳበሥር ቀብቶ ስለላከኝ፣ የልዑል እግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፡፡ ልባቸው የተሰበረውን እንድፈውስ የተጨቆኑትን ነጻ እንዳወጣና፣ ለተሰበሩትም ነጻነትን እንዳበስር ልኮኛል፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር ጠላቶቻቸውን ድል ነሥቶ ሕዝቡን የሚያድንባት የጸጋ ዓመት መድረሷን እንዳውጅ ልኮኛል፣ ያዘኑትን እንዳጽናና በጽዮን ሐዘንተኞች ለሆኑት በሐዘን ፈንታ ደስታን እንድሰጥ በትካዜ ፈንታ የምስጋና መዝሙር እንዲዘምሩ አደርግ ዘንድ ልኮኛል፡፡ ይህን ጥቅስ ጌታም ቃል ለቃል ደግሞታል፤ ሉቃ. 4፡18-19፡፡ ይህም ትስብእትን ሲያይ የተነገረ መሆኑን ለሥጋ ለትስብእት የተነገሩ ቃላት በሚለው ምዕራፍ አስረድተናል፡፡
ነቢዩ ቀብቶ ላከኝ ያለውን ሊቁ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መንፈስ ቅዱስ ወዳንቺ ይመጣል በአንቺም ያድራል፣ ማለት ያነጻሻል ባላት መሠረት አምላክ እንዲፀነስ መንፈስ ቅዱስ በማርያም ላይ ወርዶ ሥጋዋን ባነጻ በመንፈስ ቅዱስ ይተረጎማል፤ ይችም የቅባት የማንጻት ትርጓሜ ናት፡፡ አምላካዊ ቃል ከሥጋዋ ጋር አንድ እስከሆነ ድረስ በእርሷ በሥጋ አድሮ ድል የነሣቻትንና ያረከሰቻትን የአዳምን ሥጋ አንጽቶአታልና ብሎአል (ግብረ ሕማማት ገጽ 205)
ቅዱስ ያሬድም፡- እመቤታችንና የድኅነታችን ምክንያት የሆነችው የአምላክ እናት ማርያም ከአዳም ሥር የተገኘች ናት፡፡ ነፍሷን አክብረህ ሥጋዋን አንጽተህ ልጅህን በርሷ እንዲያድር አደረግህ፡፡ (የጥር 21 ዝማሬ)
«ያማረ ኮከብ በማርያም አደረ
ሥጋዋን አንጽቶ በማርያም አደረ
ርስዋን ቀድሶ መለኮቱን ከሥጋዋ ጋራ አዋሐደ፡፡» (ነሐሴ 15 ቀን ዚቅ)
ያዕቆብ ዘሥሩግም፡- ከአብ የማይለይ ረጅም ፈትል ሰማይንና ምድር የፈጠረህ በፈቃድህ ከሰማይ ወረድህ የድንግል ማሕፀን ወሰንህ የድኆች ልጅ ትንሽ ብላቴና አቀፈችህ፣ ነፍሷን አከበርህ፣ ሥጋዋንም አነጻሕ፡፡ አጸናሃትም ባንተም አልደነገጠችም፡፡ (መ.ቅ. ቁጥር 21 ገጽ 438)
ጎርጎርዮስ ዘኑሲስም፡- ቃል በግብረ መንፈስ ቅዱስ ሰው ሆነ የሚለው ትርጓሜም ከሐድያንና መናፍቃን እንደሚያስቡት የመንፈስ ቅዱስ ሥጋ ኖሮት ወይም የተፈጠረ ሆኖ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ የማርያምን ሥጋ አነጻ ቀደሰ፣ የአብ አካላዊ ቃልንም ለመፀነስ የበቃች አደረጋት እንጂ ብሎአል፡፡ (ሃይ. አበ. ገጽ. 125 ቁ. 19)፡፡ በዘመናችንም አቶ ዐሥራት ገብረ ማርያም ትምህርተ መለኮት በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 95-6 የገብርኤልን አርኬ ጠቅሰው መንፈስ ቅዱስ ማርያምን ከጥንተ አብሶ እንዳነጻት አብራርተው፣ ገልጸው ጽፈዋል፡፡
«ሰላም ለከ ገብርኤል ለማርያም ኀይለ ልዑል ጸለላ መንፈስ ቅዱስ አንጽሐ ሥጋ አባላ ተፈሥሒ ሶበ ትቤላ፡፡ ገብርኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን ማርያምን ደስ ይበልሽ ባልሃት ጊዜ የልዑል ኀይል ጸለላት መንፈስ ቅዱስ ሰውነትዋን አንጽቷታል፡፡» ዝቅ ብለውም እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ባለች ጊዜ እምነትዋን በእግዚአብሔር ላይ ባሳረፈች ጊዜ ጌታን ከመውለድዋ በፊት መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን ቀድሶና አንጽቶ የጥንቱን የአዳምን ኃጢአት አስወግዶላታል ብለው ጥንተ አብሶ ወደ ጌታ ሳይተላለፍ ከማርያም ላይ መቅረቱን አስረድተዋል፡፡ እርሷም ያውም መንፈስ ቅዱስ ከአደረባት በኋላ በአምላኪየ ወመድኀኒየ በአምላኪየና በመድኀኒቴ ብላለች፡፡ ከጥንተ አብሶ ነጻ ብትሆን ኑሮ አዳኜና መድኀኒቴ ማለት አያስፈልጋትም ነበር፡፡ የቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ጥንተ አብሶ መወለድ በሮም ቤተክርስቲያን ለብዙ ዘመን ሲያጨቃጭቅ ኑሯል፡፡ አሁን ግን ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ የሮም ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ድንግል ማርያም ከጥንተ አብሶ ነጻ ናት ብላ ወስናለች፡፡ ይህ ክርክር በጣም ተባብሶ የነበረው በፎራንሲስካንና በዶሚኒካን መነኮሳት መካከል ነው፡፡ የፍራንሲስካን መነኮሳት ድንግል ማሪያም ከጥንተ አብሶ ነጽታ ተወልዳለች ሲሉ ዶማኒካን ደግሞ ይህን አይቀበሉም ነበር፡፡ ይህንም በተመለከተ በትሬንዴንተኒ በተደረገው ስብሰባ ላይ ከፓፑ ተልከው በሄዱት በሦስቱ ካርዴናሎች መካከል ልዩነት ነበር፡፡ ዲሞንቲ የተባለው ካረዴናል ያለ ጥንተ አብሶ ተወለደች ሲል ካርዴናል ሲቲናክሩስ ደግሞ ይህን ሐሳብ የሚቃወም ሲሆን ካርዲናል ጳውል ግን ከማንኛቸውም ወገን አልነበረም፡፡ ብሎም ካለ ኃጢአት ተወለደች የሚሉት ወገኖች በመብዛታቸው ከፒዮስ ዘጠነኛ ጀምሮ የቅድስት ማርያም ያለ ጥንተ አብሶ መወለድ በሮማ ቤተክርስቲያን ተወሰነ፡፡ እሱም እንደ ኤ. በ1854 ዓ.ም. የተደረገው የፓፓው ውሳኔ እንደሚከተለው ነው፤
በኢየሱስ ክርስቶስ ሥልጣን በብፁዓን ጴጥሮስና ጳውሎስ ሥልጣን በሥልጣናችንም ድንግል ማርያም ከተፀነሰችበት ደቂቃ ጀምሮ ከጥንተ አብሶ የነጻች መሆንዋን የሚያስተምረውን ትምህርት ወስነናል፡፡ ትምህርተ መለኮት 3ኛ መጽሐፍ ገጽ 556-557፡፡
ምንጭ፦ ሁሉም ሁሉን ይወቅ ገጽ 156-159

25 comments:

 1. በርዕሱ ለቀረበው ጥያቄ የኔ መልስ ድንግል ማርያምን ጥንተ አብሶ አላገኛትም የሚል ነው ፡፡ ምናልባት ይኸ መልስ በተለያየ ጊዜ የተነሱትን ጥያቄዎች ሁሉ ለመመለስ ይሞክራል ብዬ እገምታለሁ ፡፡

  1. አንዳንዶች፡- ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ የጠፋላት መልአኩ ባበሠራት ጊዜ ነው በማለት ይጽፋሉ፡፡ ይህ አባባል ከዚህ በፊት መልአክ ያበሠራቸው ማኑሄና ሚስቱ ፣ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ለምን ጥንተ አብሶ አልጠፋላቸውም ያሰኛል ? መሳ 13.2-3 ፣ ሉቃ 1.13 ፡፡ ጥንተ አብሶ የሚጠፋው በብሥራተ መልአክ ቢሆንማ ፣ አካላዊ ቃል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ፣ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው በመሆን ፣ መከራ መቀበልና ፣ በመስቀል ላይ መሞት አያስፈልገውም ነበር ፡፡ በቀላሉ ውርደትንና ሞታችንን ሳይካፈል ፣ እልፍ አዕላፋት መላእክትን ልኮ ብሥራትን በመንገር ብቻ ጥንተ አብሶን ከሁላችንም ዘንድ ማጥፋት ይቀለው ነበር ፡፡ በሌላ በኩልም ፣ የቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ከጥንተ አብሶ ነጻ ማድረግ ከቻለ ፣ የአንድ መልአክን የብሥራት ቃል ከክርስቶስ ደምና ሞት ጋር እኩል አድርገነዋል ማለት ስለሚሆን ፈጽሞ የተሳሳተ መግለጫ ነው ፡፡

  2. አሁንም ሌሎች ደግሞ ጥንተ አብሶ የጠፋላት ፣ ጌታ በሚፀነሰበት ወቅት ፣ ከመቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ሲጸልላት ነው ይሉናል፡፡ ይህም ጌታ ሰው መሆን ያስፈለገውና ወደ እዚህ ምድር የመጣው አዳማዊውን በደል ማለትም ጥንተ አብሶን እንዴት አድርጐ ለማጥፋት ነው? የሚል ጥያቄ እንድናነሳ ያደርገናል ፡፡ መልሳችንም በመስቀል ላይ በሚፈጽመው ቤዛነትና በሚከፍለው መሥዋዕትነት ብቻ ነው የሚል ነው ፡፡ እንግዲህ እመቤታችን ጥንተ አብሶ ከነበረባት ፣ መድኃኒቴ ያለችውንም ቃል አጣምረን ደምረን ፣ እንደማናቸውም ሰው በመስቀል ላይ በሚፈጸም ቤዛነት ብቻ ከጥንተ አብሶ መዳን ነበረባት እንጂ ፣ አንዳንዶች እንደሚሉት መንፈስ ቅዱስ በጸለለባት ጊዜ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ ንጽህና ከሌለ ደግሞ ጌታ የተጸነሰው ጥንተ አብሶ በነበራት አንዲት ሴት ማህጸን ነው ስለሚያሰኝ ፍጹም ስህተት ይሆናል(1) ፤ በመቀጠልም የዳዊት መዝሙርን እንደሚተረጉሙት ጌታችንንም በኃጢአት ተወለደ ሊያስብል ነውና(2) ፡፡ በሌላው ወገን ደግሞ መንፈስ ቅዱስም በበኩሉ ጥንተ አብሶን አንጽቶ ድህነትን የሚያስገኝ ከሆነ ፣ በዚህ ዓለም ላለነው የአዳም ልጆች ሁሉ ፣ ሁለተኛ አማራጭ የመዳኛ መንገድ አለን ብለን ልንመሰክር ነው ማለት ነው(3) ፤ ማለትም በኢየሱስ ሞትና ደም ሌላም በመንፈስ ቅዱስ መጽለል በኩል፡፡ ሎቱ ስብሐት !!! የፈሰሰውን ደም ፣ ስለ እኛ የተቀበለውን ፍዳና መከራ መካድና ተደራራቢ ስህተቶችን ማምጣት ፡፡

  3. ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ወደ እመቤታችን በመጣ ጊዜ ፡- “ደስ ይበልሽ ፣ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ፤ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው ፤ ከሴቶች መካከል አንቺ የተባረክሽ ነሽ ፡፡” በማለት አመስግኗታል (ሉቃ 1.28) ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ፣ ከእርሷ በፊት ይህን በሚመስል ምስጋና የተመሰገነ አንድም ፍጡር የለም ፡፡ ይኸ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእመቤታችን የተሰጠ ምስጋና ነው ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!! እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጥንተ አብሶ ተይዛ ቢሆን ኖሮ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል “ጸጋን የተመላሽ ሆይ” ሊላት አይችልም ነበር፡፡ ምክንያቱሳ ቢሉ ፣ ጥንተ አብሶ ጸጋዋን ጐደሎ ያደርግባት ነበርና ነው፡፡ አዳም በደልን እንደ ፈጸመ በቀጣዩ ያጋጠመው የመጀመሪያው ቅጣት ጸጋው መጉደሉ ወይም መገፈፉ ነው ፡፡ ይኸ የአዳም በደል አለባት ከተባለ ፣ ጸጋዋ እንደ ቀደም አባቷ መጉደል ይገባው ነበርና ፣ ታድያ መልአኩ እንዴትና ስለምን ኦ ምልአተ ጸጋ በማለት ሊያወድሳት ይችላል?

  4. ሌሎች ደግሞ ሉቃ 1፡47 የተነገረውን ድንግል ማርያም በራሷ ላይ የምስክርነት ቃል እንደ ሰጠች አድርገው በማቅረብ ጥንተ አብሶ እንደነበረባት ለማስረዳት ይሞክራሉ ፡፡ ይኸን ቃል ለመናገር የሚገደደው ፍጡር የሆነ ሁሉ እንጅ አዳማዊ ኃጢአት ያለበት ብቻ እየተመረጠ አይደለም ፡፡ በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አምሳል የተፈጠረ ፍጡር በሙሉ አምላኬ ፣ መድኃኒቴ ፣ በማለት አምላኩን ያወድሳል፡፡ ድንግል ማርያም በተለየ መድኃኒቴ የሚለውን የምስክርነት ቃል የሰጠችው ፣ ገና ኢየሱስ ሳይወለድና በመስቀል ላይ ሞቶ ሳያድናት ነው ፡፡ ሳይሞትና መስዋዕት ሳይሆን ደግሞ ስለድኀነት መናገር ስለማይቻል ፣ ከፍጥረት አስቀድማ ድና ነበር ያሰኘን እንደሁ እንጅ ፣ ገና ደሙን ያላፈሰሰና ያልሞተውን አምላኳንና ልጅዋን ፣ ሰው መሆኑን እንኳን አይታ ያላረጋገጠችውን የማህጸን የጽንስ ፍሬ መድኃኒቴ ብላለች በማለት ያልሆነ ትርጓሜም በመስጠት ወይም የትንቢት ቃል አስመስሎ መከራከር ፣ የሚያስኬድ ሆኖ አላየሁትም ፡፡ ከመስዋዕትነት በኋላ የተነገረ ቃል ቢሆን እንኳን ፣ ያንን ተንተርሶ ትንሽ ለማደናገር ክፍተት ይገኝ ነበር ፡፡ ቤዛነቱ ሳይፈጸም መድኃኒቴ ስላለች ፣ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በተለየ መንገድ ድናለች ወይም ቀድሞውንም ከጥንተ አብሶ ጠብቆ አቆይቷቷል ፣ ለማለት እንደፍራለን እንጅ አዳማዊ በደል አግኝቷታል የሚለው በየትም በኩል ማስማሚያ የለውም ፡፡ እግዚአብሔር ነቢይ ሊያደርግ የፈለገውን እንኳን “በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ” እያለ የተናገረ / ኤር 1፡5/ ፤ ለማደሪያውና እናት ትሆነው ዘንድ የመረጣትን ቅድስትና ብፅዕትማ ደግሞ ፣ ምን ያህል እንደ ሚጠበብላትና እንደ ሚያሰናዳት ባለ አእምሮ የሆነ ሰው ሁሉ ሊያጤነው ይገባል ፡፡ ከልማደ እንስትና ከሀልዮ (ሃሳብ) ፣ ከነቢብና (ንግግር) ፣ ከገቢር (ሥራ) ኃጢአት ነጻ ያደረጋት ፈጣሪ ጥንተ አብሶን አላስወገደላትም ማለት ፈጽሞ ቧልት ነው ፡፡
  ይቆየን

  ክፍል ሁለት ይቀጥላል

  ReplyDelete
  Replies
  1. wesobe REYE Nsihnach Lelhu Egzabher Abi Fenewe Habech Melako!!!!Brhanawie!! The Simu Gebriel Yalewun Lemin Tadya Atteqemubetim Ewunetengnoch Kehonach. Kemenfese Serf Beqer Lela Altadelachum malet new Beqa? we Erekuset In the Feteraha Digile Behlnaha wedingile Besigaha. watch yourself guys? I think you guys lost your mind.

   Delete
  2. መልስ እንድንሰጥ በሚያግባባን ቋንቋ ተጠቀሙልን ፡፡ በአማርኛ ፊደላት ባትጽፉም ፣ የምትሉትን እንድንረዳ ቋንቋችሁን አማርኛ አድርጉልን ፡፡ እግዚአብሔር በፈቀደ የምናውቀውን ለማስረዳት እንሞክራለን ፡፡

   Delete
 2. ክፍል ሁለት
  5. ኢሳ 1፡9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር የሚለውን ስለይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ህዝብ እንደተነገረ አድርገው የሚተረጉሙ አሉ ፡፡ ከቁጥር 9 ንባብ አስቀድሞ በቁጥር 8 ላይ ስለ ጽዮን ሴት ልጅ የሚናገረውንስ እነዴት መንደርና ከተማ አድርጐ መተርጐም ይቻላል ? ኢሳይያስ ነገሩን እያጠራልን ሲሄድ በምዕራፍ 2 ላይ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም እየተናገረ በቁጥር 2 ስለ ዘመን ፍጻሜ ክስተት ያወሳናል ፤ በቁጥር 3 ደግሞ ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል (አጽንኦት) ከኢየሩሳሌም ይወጣል ፤ ለአሕዛብ ሁሉ መንገዱን ያስተምራል ፣ በጎዳናውም እንደሚሄዱ ይናገራል ፡፡ እንዲያውም ዳግም አትታወሩ ብሎ ሊያሳርፈን ሲፈልግ ፣ አለፍ ብሎ በምዕራፍ 7፡14 ደግሞ ለዳዊት ቤት እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ይልና ፣ ትንቢቱን ያስቀምጥልናል ፡፡ በመቀጠልም በምዕራፍ 9፡6 ደግሞ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል በማለት የምትወልድውን ህፃን ማንነት በግልጽ ያበሥራል ፡፡ ስለዚህም መጽሐፉ የሚነግረን መንፈስ ቅዱስ በምዕራፍ 1፡9 ፤ 2፡2-3 ያስረዳውን ስውር ቃል በምዕራፍ 7፡14 ግልጽ እንደ አደረገለትና ፤ ይህንኑ የተስፋ ቃል ደግሞ በማቴዎስ 1፡18 በእውን እንደ ተረጐመው ነው፡፡ በመሆኑም ከመጀመሪያ ምዕራፍ አንስቶ በተደጋጋሚ በተለያየ ሥፍራ ስለ ድንግል ማርያም ተናግሯልና በኢሳ 1፡9 የተገለጸውም እሷን የሚመለከት ቃል ነው እንጅ ስለ አገርና ህዝብ የተነገረ አይደለም ፡፡

  6. ኢትዮጵያውያን አባቶች “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ፣ ሥርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት” በተባለ መጽሐፍ ገጽ 49 ላይ ስለ ጥንተ አብሶ የጻፉልን እንዲህ ይነበባል ፡፡

  “አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአዳም ዘር የተላለፈ ኀጢአት /ጥንተ አብሶ/ ያላገኛት መርገመ ሥጋ ፣ መርገመ ነፍስ የሌለባት ገና ከመወለዷ አስቀድሞ በአምላክ ኀሊና ታስባ ትኖር የነበረች በሰው ልማድና ጠባይ ከሚደርሰው ሥጋዊ አሳብና ፈቃድ ሁሉ የተጠበቀች ከተለዩ የተለየች ንጽሕት ፣ ቅድስተ ቅዱሳን ናት” መሓል 4፡7 ፡፡ “ምልዕተ ፀጋ ምልዕተ ክብር ሆይ ደስ ይበልሽ” ተብላ በቅዱሳን መላእክት አንደበት በቅድስናዋ ተመስግናለች ፤ ትመሰገናለችም” ሉቃ 1፡28-3ዐ ፡፡ “እመቤታችን በውስጥ በአፍኣ በነፍስ በሥጋ ቅድስት ስለሆነች ፣ እግዚአብሔር ለልጁ ማደሪያ መርጧታል ፤ ማኀደረ መለኮት እንድትሆን አድርጓታል ፡፡ አምላክን ለመውለድ ያስመረጣትና ያበቃት ፣ ድንግልናዋ ፣ ንጽሕናዋ ነው ፡፡ /ሕርያቆስ ቅዳሴ 45 ፤ መዝ 132 ፡13/ ፡፡ ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና ለእመቤታችን ገንዘቦቿ ናቸው፡፡”

  ይህን በ18 (፲፰) የቤተ ክርስቲያናችን አባቶችና ሊቃውንት የቀረበውን ቃል ፣ በአራት (፬) የቤተ ክርስቲያን መምህራን የተፈተሸውንና ለኀትመት የበቃውን መጽሐፍ ወደጐን ገፍቶ የአንድ ሊቅን ጽሁፍ ብቻ መርጦ ማስነበብ ሚዛናዊነት ይጐድለዋል እላለሁ ፡፡

  7. ክርስቲያኖች ኦርየንታል ኦርቶዶክስ የሚለውን መለያ ስም ለራሳቸው ያስገኙት /የሰጡት/ የኬልቄዶንን ጉባዔ /እኤአ 451 ዓ.ም./ ውሳኔ አንቀበልም በማለታቸው ምክንያት ብቻ ነው ፡፡ ይኸውም

  - አንደኛው ወገን መለኮትንና ሥጋን አልተዋሃዱም ፤ በዚህም ምክንያት ኢየሱስ አንድ ጊዜ በሥጋው ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በመለኮቱ ፣ እንደ ፈለገ እያፈራረቀ ሥራዎቹን አከናውኗል ፤ ሥጋ የሥጋን ፣ መለኮት ደግሞ የመለኮትን ድርሻ ፣ ለየግላቸው በመሆን ፈጽመዋል በማለት ፤ የአባ ልዮንን አንድ አካልና ሁለት ባህርይ ፍልስፍና ስለሚያራምዱና ፣ በመስቀልም ላይ ደግሞ ተለያይተዋል በማለታቸው ነው ፡፡

  - የኦርየንታል ኦርቶዶክሶች ደግሞ መለኮትና ሥጋ ተዋህደው ፍጹም አንድ አካል ሆነዋል (ንብረትና ሃብት ተወራርሰዋል ፤ ማለትም አንድ አካልና አንድ ባህርይ ሆነዋል) በማለት ተለይተዋል፡፡ ይኸም ማለት የኦርቶዶክስነት ስያሜ የተገኘው የድንግል ማርያምን ከጥንተ አብሶ ነጻ መሆንና አለመሆንን ጉዳይ አክሎ በመግለጽ አይደለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህም በጥንተ አብሶ ትርጉም ከሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያናት መለየት ከማኀበሩ ውጭ ነን አያሰኘንም ፡፡ እንደዚህ በምንለይበት ሁሉ ከአካልነት የምንከፈል ቢሆንማ ፣ የኢኦተቤክ ከሌሎች ተለይታ ለታቦት ክብር ሰጥታ በየአደባባዩ ስትታይበት ፣ ጥምቀትዋን እየዘከረችና ለዓለም እየመሰከረች ስታስተዋውቅ ፣ ደመራዋንም በያመቱ ደምረነ ምስለ እለ ይድኀኑ በማለት እያቀጣጠለች ስትዘምር ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎቿንም ቁጥር ሰማንያ አንድ ነው ብላ ስታስነብብ … አውግዘው መለየት ነበረባቸው ፡፡ ከዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኒቅያ 318ቱ ሊቃውንት ፣ ኋላም በኤፌሶን 2ዐዐው ሊቃውንት የወሰኑትን ትምህርተ ሃይማኖት ስለተቀበለችና ስለያዘች ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትባላለች ወደፊትም በዚሁ ትቀጥላለች፡፡

  ይህንን መሠረታዊ ልዩነት ለማስረዳት ያመጣሁት ቅድስት ድንግል ማርያምን ጥንተ አብሶ አላገኛትም ማለት የካቶሊክ አባልነት መታወቂያን አያሰጥም ለማለት ነው ፡፡ ምክንያቱም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከላይ የተጠቀሰውን የኬልቄዶን ጉባዔ ውሳኔ ትቀበላለች ፤ ማለትም የተዋህዶን ዶግማ አታምንበትም፡፡ ከዛም አልፎ መንፈስ ቅዱስን ከአብና ከወልድ ይሠርጻል በማለት ከእኛ ዶግማ ትለያለች (እኤአ 1ዐ54 ዓ.ም. ከምሥራቅ ኦርቶዶክስም የተለዩበት ዋነኛ ምክንያትም ይኸው ነው) ፡፡ እነዚህ መሠረታዊ የክርስትና ልዩነቶች በመሃከላችን ስላሉ ፣ በጥንተ አብሶ ዶግማ ከነሱ በመስተካከል ብቻ ካቶሊክ ሆነናል ማለት አይቻለንም ፡፡ በተረፈ ግን በሌሎቹ የነገረ ማርያም ዶግማዎች በሙሉ ከካቶሊኮቹ እንደምንመሳሰል ማወቅ አለብን ፤ ማለትም ዘላለማዊ ድንግልናዋን ፣ ከግብረ ኃጢአት ነጻ መሆኗን ፣ እመ አምላክ መባሏንና ድኀረ ሞተ ሥጋ ማረጓን እንደ ሮማዋ ካቶሊክ የእኛም ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች ፡፡

  ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን -አሜን
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 3. I sincerely believe that it is better to accepot faith as faith or religious belief as religious belief as though some big religious stories are beyond our sphere of knowledge. Because if we engage in serious arguement and reasoning ,it won;t be as simple as anything .Well; we can argue the great religious people such as Saint Yared ,Jacob, Gorogious and other followers of Jesus Christ had taught us . That is fine! If we are intended to argue that all what had been said is absolutely uncontrovercial, I do not think it works that way. Why? even if those great religious people , had taught and had written gided by the Holy Spirit, ,it is possible to argue that as they are human beings they might have not been absolutely free from human errors in their teachings.
  I hope my opinion is healthy as all Mighty God created me in that way.

  ReplyDelete
 4. why you Guys care about her ? she is our mather for those who believe. if a Boy start question him self my mather taking care of him from her womb to the age he start taking care of him , that is most of her life she spend with , she did all this because she suppose to do that, i am not asking to be Born....you see how you question your self. For Us she is really Deserve all as a mather and specially for her to give for as food the world is cured from ..not only from Hunger , even for that is forever. we Love her ,we say she is in adams mind when he is out of all that Hope. she is cleared from all those Adam and his childrens experiance.... God is good boy not like you Guys speaks and shows two faces. May God give you all the wisdom...please u can call me or any person what ever you like , that is from your father Davil....even those u have right to say ... but say something about me at list u know me as human with errors

  ReplyDelete
 5. ሰርጸ ድንግልJune 16, 2012 at 12:33 AM

  እዉቀት አጠር ናችሁ መተም!! በደንብ አንብቡ እንጅ ለራሳችሁ ህይወት ይሆንላችሁ ዘንድ፡፡ ያጠራችሁን እዉቀትም እግዚብሄር ይገልጽላችሁ ዘንድ ያለነቀፋ ጸልዩ፡፡ ካልሆነ ግን ጉንጭ አልፋ ክርክር አታድርጉት እኛ እንደሆንን አንሸወድም መሰረታችን ክርስቶስ ነዉ እሱ ያከበራቸዉን እናከብራለን ከአፋችንም የስድብ ነገር አይወጣም፡፡ እግዚብሄርንና ማደሪያዉን የሚሳደብ አዉሬ እንዲመጣ ተነግሮናል ደግሞም በክበር እንኳን የሚበልጧቸዉን የሚሳደቡ እንዳሉም ቃሉ ያስጠነቅቀናል፡፡ እግዚብሄር ይቅር ይበላችሁ ደግሞም በንስሃ ተመልሳችሁ የመንግስቱ ወራሾች ትሆኑ ዘንድ እንጸልያለን፡፡ አምላከ እስራኤል ፍቅር እና ማስተዋል ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 6. ሰርጸ ድንግልJune 16, 2012 at 1:41 AM

  ደግሞም ወንደ አላዉቅም አለች እንጂ ጥንተ አብሶ ስላለብኝ እንዴት ይሆንልኛል አላለችም፡፡ መልአኩም እንደምትጸንስ የልኡል እግዚብሄር ልጅ እግዚአብሄርን እንደምትወልድ እርሱም ታለቅ እንደሆን በዳዊት ዙፋ እንደሚቀመጥ ለመንግስቱም ፍጻሜ እንደሌለዉ ሲነግራት እንደሰዉ ልማድ ስለመሰላት ወንድ አላዉቅም አለችዉ በዚህም እንኳንስ በስጋዋ በሃሳቧም ንጽህት እንደሆነች እንረዳለን ባጠገቧ ያለዉን ዮሴፍን እንኳን አላሰበችምና፡፡ ከዚህ በኋላ ነዉ እንግዲህ መንፈስ ቅዱስ በአንች ላይ ይመጣል የልዑል ሃይልም ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ካንች የሚወለደዉ ቅዱስ የእግዚበሄር ልጅ ይባላል ያላት ፡፡ ወንድ አላዉቅም ማለት ያለወንድ ዘር መዉለድ አይቻልም እኔ ደግሞ እንዲህ የማድረግ ሃሳብ ፈጽሞ የለኝም የሚል ትርጉም የሚሰጥ እንጂ ሃጢያተኛ ነኝ የሚል ትርጉም የለዉም፡፡ ለዚሀም ነዉ የምትወልደዉ ያለወንድ ዘር እንደሆነ ‹‹ መንፈስ ቅዱስ ባንችላይ የመጣል የልዑል ሃይልመ ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንች የሚወለደዉ ቅዱስ የእግዚብሄር ልጅ ይባላል ያላት፡፡
  ለመሆኑ መንፈስ ቅዱስ ስራዉ ማንጻት ብቻ ነዉ እንዴ ሃዋሪያት እኮ መንፈስን ቅዱስን እስክልክላችሁ ድረስ ከእየሩሳሌም እንዳትወጡ የተባሉት ቅዱሱ መንፈስ ካላጸናቸዉ በቀር የእዉነትን ቃል መሸከም ስለማይችሉ ነዉ፡፡ ማርያም ደግሞ ልትሸከም የተመረጠችዉ የቃሉን ባለቤት ነዉ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ ያጸናጽ ዘንድ እንጅ ያነጻት ዘንድ እንዳልሆን አስተዉል፡፡ ደግሞም የልኡልም ሃይል ይጸልልሻል(ይጋርድሻል) በማለት የተጋረደች የንጉስ መንበር እንደምትሆን ነገራት እንጅ ፈጽሞ ስለ ሃሚያት መንጻት መልአኩ አልተናገረም፡፡ ያልተጻፈ አታንብ እንዲህ ያደረጉ ብዙዎች ተገስጸዋልና የመልአኩን ቃል አታጣም፡፡
  ማንም ነብይ ይህንን አልተናገረም ላልከዉ በነብዩ ኢሳያስ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በጠፋን እንደገሞራም በሆንን ነበር ያለዉን ለማን አድርገኸዉ ነዉ፡፡ መቸም እንደ ፕሮቴስታንቶች(አንተም የነርሱ መሆንህ ከንግግርህ ታስታዉቃለህ) ለኢየሱስ ነዉ ልትለኝ እንደምትችል አዉቃለሁ፡፡ ግን እየሱስ ስጋን የወሰደዉ እግዚአብሄር ካስቀራት ዘር ላይ መሆኑን አስተዉል፡፡ ከሃጢያት የተጠበቀች ዘር ድንግል ማሪያም ተዘራች የህይወት ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስን አፈራች እርሱም በርሱ ላመኑት ሁሉ የዘላለም የህይወት እንጀራ ሆነላቸዉ፡፡ መቸም የአሮን በትር ያፈራችዉ የለዉዝ ፍሬ እንጅ በትሩ የክርስቶስ ምሳሌ ነዉ አትለኝም አእምሮህ ጨርሶ ካልታወረ በቀር፡፡ የአሮን በትር( ድንግል ማሪያም) ለመለመች ለዉዝ(የጽድቅ ፍሬ እየሱስ ክርስቶስ) አፈራች አበቃ እንዲህ ነዉ ቃሉ ያስተማረን እኛም የምናምነዉ ይህንን ነዉ፡፡
  ጥያቄየ፡- እግዚአህሄር ኤልሻዳይ ነዉ ያድርበት ዘንድ የወደዳትን ዘር ማስቀረት አይችልምን ደግሞስ አምላክ ከመጀመሪያዉ ማደሪያዉ ትሆን ዘንድ ለይቶ ያለሃጢያት የጠበቃትን ጉድፍ የሌለባትን የሰርግ ቤት አድፋ ነበር ማለት የሚቻለዉ ማን ነዉ፡፡ ከዘሯ የቀሩትን የእየሱስ ምስክርነት ያላቸዉን ሊዋጋ በባርህ አሽዋ ላይ ከቆመዉ በቀር ይቃወማት ዘንድ ማን ይደፍራል ?ለሁላችንም ማስተዋሉን አምላካችን ያድለን

  ReplyDelete
 7. ሰላም ለሁላችሁ ይሁን የእግዚአብሄር ቤተሰቦች። ድንግል ማርያም ከጥንተ አብሶ ነፃ አይደለችም ቢባል በድኅነታችን ምሥጢር ላይ የሚጨምረው ነገር ምንድነው? ለእርስዋስ ከምንሰጠው ክብር ምን ይቀንሳል?

  ReplyDelete
  Replies
  1. 1.there must be enemity[telatnet] between her and satan as god said in pardise in genesis 3:15 [THEFETRET 3:15] 2.God is holy OF HOLIES and he cant unite with womb with orginal sin. 3.bible say in revealation13;8 god knows christ will be cruicefied befor creation so in the same way he can protect her from fall 4. she died she is not immortal but she has no orginal sin ,christ also not immortal even if he died for us he is mortal when he was on earh as he truly human ,we also die but we have no orginal sin therfore death doesnt indicate she has orginal sin

   Delete
 8. ይህን እውነት አለመቀበል። የእግዚአብሔርን እውነት አለመቀበል ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. adam yetefeterew mereat satiregem new .adam tizaz siyafers teregeme. besu mikinyat yetefeterbat mereat teregemech. tadiya yihin kezer wede zer yemitelalefewin yewiris hatiyat lemasiweged kasa mekefel neberebet kasa degimo mebilet alebet. tadyia geta yeteweledew erigiman kalitelalefebat mariyam/mereat/ new.alebelzya be mariyam tinte abiso/mergem/ alebat telalifobatal yeminil kehone ke geta yilik adam yibelital malet new.

   Delete
 9. ""አይሁድ በሴቶች ሁሉ ልማድ ገምተዋት እንዲህ አሏት እንጂ ድንግል ማርያም ግን የሴቶች ልማድ የሌለባት ቡርክት የአዳም ሀጥያት ያላገኛት ንጽህት ባህርይ ናት::( ስርወ ሃይማኖት ገጽ 61 ::በሊቀ ሊቃውንት ሃይለ መስቀል ገብረ መድህን :: ከዛሬ 44 አመት በፊት በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት የታተመ::)

  ReplyDelete
 10. she become pure because 1.there must be an enmity between the serpent and her as a prophesy 2.there mustnot be enmity between her and her son but if she has orginal sin there will be enmity between her and her almighty son and there will be relation between her and satan[protestant,tekawami] 3.God can protect HIM ONLY from orginal sin but he didnt [why?] because HE DIDNT WANT TO MAKE ENMITY B/N THE FEMALE[MOTHER]AND HER SEED[THE SON]4.EARLY IN FALL OF ADAM THE FIRST TO FALL IS EVE[HEWAN]SO NOW ON SALIVATION THE FIRST TO BE SAVED FROM ORGINAL SIN BECOME OUR BELOVED MOTHER MARY 5.SOME PEOPLE ASK IF SHE IS ON BACK OF ADAM HOW CAN SHE SVED FROM ORGINAL SIN WE SAY NOT ONLY SHE IS ON THE BACK OF ADAM BUT JESSUS ALSO WAS IN BACK OF ADAM SINCE HE IS HUMAN 6.IF SHE DIED HOW CAN SHE SAVED FROM ORGINAL SIN WE SAY WE ALSO DIE BUT WE HAVE NO ORGINAL SIN. JESSUS DIE FOR US BUT HE HAS NO ORGINAL SIN EVEN IF HE DIED FOR US HE HAS ABEHAVIOR LIKE ALL HUMAN IMEAN HE IS NOT IMMORTAL SINCE HE FULLAND TRUE HUMAN.CONTINUED....

  ReplyDelete
 11. Abune Fanueil Yawgezut Dr Yikedisal Abune Eliya Yawgezut Menekuse Mahibere Kidusann Tekaweme Tebilo Mekerawn Eyaye New Ahun Yemishalew Mahibere Kidusan Mehon Bicha New Abune Fanueil & Abune Eliyas Liyunetachew Mindinew ?Deje Selam Ye Gibi Gebreil Astedadar Yehonutn Menekuse Asmelkito Yezegebewn temelketu

  ReplyDelete
 12. ሰርጸ ድንግልJune 18, 2012 at 4:54 AM

  ጥንተ አንሶ አለባት ብንል በድህነታችን ላይ ክህደት እንጨምራለን ለምን ክርስቶስ የነሳዉ ስጋ ከሃጢያት ያልነጻ ከሆነ እንዴት ልንድን እንችላለን መንፈስ ቅዱስ አነጻት ስንል የምናመጣዉን ክህደት ደግሞ ከላይ በ 2 ክፍል ያስተማረን/ችን ወንድም/እህት ጥሩ አድርገዉ ስላስቀመጡት በደንብ ከተነበበ አጥጋቢ ትምህርት ይገኝበታል፡፡ ለእርሷ ከምንሰጠዉ ክብር ምን እንቀንሳለን ለሚለዉ ግን የሌለባትን ሃጢያት አለባት ነዉና እያልን ያለነዉ የእግዚብሄርን ማደሪያ እንሰድባለን ደግሞም እግዚአብሄርን እራሱ ከሃጢያተኛ ስጋ ነሳ ብለን እንሰድበዋለን፡፡ ባጠቃላይ እግዚብሄርንና ማደሪያዉን እንሳደባለን ማለት ነዉ፡፡ ለድንግል ማሪያም የምንጨምርላትም ሆነ የምናጎድልባት ነገር የለም አንድ ግዜ እግዚብሄር አክብሯታልና፣ የስድብን ቃል በመናገራችንና ለድህነታችን የተቆረሰዉ ስጋና ደም የተነሳዉ ጥንተ አብሶ ከነበረባት እናት ነዉ በማለታችን ግን እግዚብሄር ከህይወት መጽሃፍ እኛን ያጎድለናል፡፡ከላይ የእዉነትን ቃል ሳታዛንፍ/ፊ ያስተማርከን/ሽን ግን እግዚብሄር ጸጋዉም ያብዛልህ/ሽ እያልኩ እንዲሁ እንደኔ አይነት ሰዎች ከምንጽፈዉ ይልቅ ለሁሉም የተሰጠዉ ጸጋ አለና ሁሉንም ተንትናችሁ የማስረዳትና የመምህርነት ጸጋዉ የተሰጣችሁ ሰዎች ብቅ እያላችሁ ብታስተምሩን በማይሆን ትምህርት የሚወሰደዉን ሰዉ ወደ አባቱ ቤት በመመለስ ሃዋሪያዊ ተልእኮአችሁን ፈጽሙ በእግዚብሄር ፍቅር እለምናለሁ፡፡ ለሁላችንም አምላካችን ማስተዋልን ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 13. አዘጋጅ ክፍሉን ወይም ይህን ጽሁፍ ላቀናበረ ሰው የሚመለከት ምክር ፡-
  ይህንን ምክር ፣ ቀደም ካቀረብኩት መግለጫ ጋር በአንድነት ከማቅረብ የተቆጠብኩት የነቢዩን መጽሐፍ አግኝቼ እስከ ምፈትሸው ነበር ፡፡ እናንተ በሰው የተሰጠ ማዕረጋችሁን ዲያቆን ፣ መሪጌታ ፣ ሌላ ሌላም እያላችሁ ስታስነብቡን ፣ ሁሉም ቢቀር እንኳን መልአኩ ገብርኤል የገለጸላትንና የመሰከረላትን ፣ እሷም የተቀበለችውን መለያ ማዕረጓ የሆነውን ስለምን መግለጽ ከበዳችሁ ? ጸሃፊው በተለያየ የእምነት መግለጫቸው ከተዋሕዶ እምነታችን ቢለዩንም ፣ የድንግል ማርያምን ስም ግን ከእኔም በተሻለ መንገድ በጥምር ክብሯ ፣ ቅድስት ድንግል ማርያም በማለት ነው የራሳቸውን ግንዛቤ የሚያተቱት ፡፡ በአባቶች የተጀመረው ዝርጠጣ እንግዲህ እየተለመደ ሲሄድ ፣ አድጎ ያልሆነ ቦታ ሁሉ ያርፋል ብዬ የፈራሁት ፣ ይኸው አንደኛውን ወር ሳይሞላችሁ አስነበባችሁን ፡፡

  በመልአኩ ገብርኤልና በኤልሳቤጥ ከተገለጸው በመነሳት ማለት የሚገባን
  - ጸጋ የተሞላሽ ማርያም /መልአኩ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ በማለት ሰላምታውን ስለጀመረ/
  - እመ አምላክ ወይም ወላዲተ አምላክ /ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ስላላት/
  - ድንግል ማርያም /በድንግልና እንደምትወልድ ስላስረዳትና ስለመሰከረላት/
  - ብርክት ፣ ቅድስት ማርያም /አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ በማለቱ ፤ ይኸንን ኤልሳቤጥም ደግማዋለች/
  - የጌታ እናት /ከኤልሳቤጥ ምስክርነት በመነሳት/
  - ብፅዕት ማርያም /ከራሷ የምስክርነት ቃል በመነሳት/

  ReplyDelete
 14. ahun Geta Amlakachen limeta beqerebebet seeat seleMariyam netsehena menegageru meen yetekmal? yelekes Neseha gebu hatiyatachwu yeserey zened eyandandachu be Eyesus krstos seem tetemeku yemenfes kidusenm setota tekebelalachu Act.2/38 yalewun ye Egziabheren kal mefetsemena tezegajeto metebeku newu yemiyawatawu.

  ReplyDelete
 15. The Geez word "Tselele" means kelele in amharic. If you look at the English version of the Bible, it says " ... The power of the Highest shall OVERSHADOW thee ...". So "Tselele" means overshadow. which means cover. It doesn't mean cleanse.

  So just don't get confused, St Mary is free of the Original sin.

  ReplyDelete
 16. god word dont rejected even after destruction of sky and earth so , bible say Mary is sinlessness in Genesis 3:15 “I will put enmity between you and the woman, and between your offspring and hers; He speaks of an enmity between woman’s offspring and satan. If you have sin in you, can you say that there is enmity between you and Satan? If you are a sinner, aren’t you actually on Satan’s side. Jesus is this offspring. The enmity between Jesus and Satan is complete and total opposition, because of Jesus never sin, the same must be true for the enmity between woman and the serpent. So for Mary is New Eve, she must be sinless and free from original sin and its effects.

  Mary is the new Ark of the Covenant. In order for Mary to carry God in her womb, like the Ark used to carry the tablet of the Ten Commandments, she would have to be sinless and pure. This Ark was the holiest object in the Old Testament. God gave careful and precise instructions on how to make the Ark. It was to be kept free from all impurity . The Ark carried the written Word of God, and for Mary to be the Ark carrying the living Word of God, she became without original sin.Eve was created without sin, and if Mary is greater than Eve, then it makes sense for Mary to be created without sin

  ReplyDelete
 17. መደበኛ ጸሓፊዎችና አስተያየት ሰጮችም የኅሊና ድጋፍ ይገባችኋል፤ስለናቱ ብዙ ተባለ ብዙ ተተረከ ያም
  ይሁን ይህም ይሁን ወሳኙ አንድ አካል ብቻ ነው፤ወደ ልጇ ዘወር እንበልና እንመልከት ዮሓ.፲/ ፴፮
  ወዘሰ ቀደሶ አብ ወፈነዎ ውስተ ዓለም(አብ ቀድሶ ወደ ዓለም የላከው) ዮሓ 10/36.ይላልና በዚህም
  መጻጽፍ ዕውቀትን ያሰፋል ስንኳን መልካሙን ክፉውን ብንጽፍ እንደ ክፉ፤ ክፉ አይደለምና አይከፋብንም
  እንዲያውም የሰው ልጆች በሚሉትና በሚጽፉት ቢሳሳቱም ዕንኳ አቤቱ የሚሠሩትን አያቁምና ይቅር በላቸው የሚለውን ቃል ያሳስበናል፤

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጸሃፊው ማረም ከቻሉ ፡- የሃይማኖት ዶግማ ታሪክ ስላልሆነ ተተረከ ተብሎ መገለጹ አግባብ አይደለም ፡፡

   በተረፈ ደሙን አፍስሶ ፣ የእኛን ኃጢአት ተሸክሞ ፣ የፍርድ ሞታችንን በመሞት ያዳነን ወልድ ፣ በሥጋ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነውና ስለፈጣሪነቱ ፣ ስለካህንነቱ ፣ የእግዚአብሔር የመስዋዕት በግ ሆኖ በመቅረቡ እናመልከዋለን ፡፡ በተጨማሪም ደግሞ ወልድ በተለየ አካሉ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከስጋዋ ሥጋ ፣ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ፣ የዚህ ዓለም ሰው እንዲሆን ላገልግሎት ስለተመረጠች ፣ እሳተ መለኮትን በአምላክ እርዳታ በጠባብ ማህጸኗ ስለተሸከመች ፤ በትንቢት የተነገረው ሊፈጸም አብራው ስለተንከራተተችና ስለደከመችልን ፣ ከተፈጠሩት ፍጥረታት ሁሉ በላይ ምስጋና ይገባታልና በተደጋጋሚ ጥንተ አብሶ አለባት የሚለው ሐተታ ፣ ምንም ትርፍ ስለማያስገኝልን በዚሁ ይደምደም ፡፡

   እግዚአብሔር ለእናትነት የመረጣትን ቅድስት ፣ እኛ በመናገራችን ወይም በመጻፋችን ፤ አእምሮአችንን እናረካው ካልሆነ በስተቀር ፣ በርሷ ላይ ቅንጣት ለውጥ አናመጣም ፡፡ አቅማችንና ሥልጣናችንም ቢሆን ከማውራትና ከመጻፍ አያልፍም ፡፡ የአምላክ እናት አማላጃችን ናት ስንልም በተሰጣት ጸጋ ማለታችን ነው እንጅ በሥልጣኗ እያልን አይደለም ፡፡ የነገሮቻችን ሁሉ መደምደሚያ የአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ቸርነት መሆኑን አስረግጠን እናውቃለን ፡፡

   ፈቃደኛ ከሆኑ አንድ የተማሪነት ጥያቄዬን ላቅርብልዎ ፤ ወዘሰ ቀደሶ አብ ወፈነዎ ውስተ ዓለም ማለትም አብ ቀድሶ ወደ ዓለም የላከው /ዮሓ 10/36/ ያሉት ምን ለማለት እንደሆነ አልገባኝምና ቢያብራሩልን እግረ መንገዱንም የወንጌል ጥናት ስለሆነ መማር እችላለሁ ፡፡

   Delete
 18. ሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።” ስለወለደችው ልጅም፦ “አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች” ። አሕዛብን ሁሉ የሚገዛ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱን የወለደች ደግሞ ቅድስትና ድንግል ማርያም ናት። ስለዚህም ምክንያት “ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።” ወደ ግብጽ ስለመሰደዷ። በመጨረሻም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቁትን፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች የሆኑትን እንደሚያሳድድ ሲገልጽ፦ “ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤” ከዘርዋ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሴቲቱን ዘር ነው፤ ይህች ደግሞ የመመኪያችን ዘውድ ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ዘርዋ ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች የሆኑትን ነው። ንዋየ ኅሩይ ቅዱስ ጳውሎስም፦ “በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።” ብሎ፣ በእርሱዋ የደረሰ በዘሮቿም እንደሚደርስ አስረግጦ ተናግሯል። (2ጢሞ3፥12)
  በአብርሃም ልጅ በይስሐቅ ደም ዓለም እንደማይድን ተነገረ፤ በእመ አምላክ ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ግን ክብርን አገኘን። በሥጋ ተወልደው የአብርሃም ዘር የሆኑት ከነዓንን ለመውረስ ተስፋ አደረጉ፤ እኛ በመንፈስ ከአብርሃም ተወልደን የድንግል ማርያም ዘር የሆንነው ደግሞ መንግስተ ሰማያትን ተስፋ እናደርጋለን። እነርሱ ከነዓንን ለመውረስ ብዙ ሰልፍ አደረጉ፤ እኛ መንግስተ ሰማያትን ለመውረስ መንፈሳዊ ውጊያ እናደርጋለን። እነርሱ በመገረዛቸው ይመካሉ፤ እኛ ግን በጥምቀት ባገኘነው የጸጋ ልጅነት እና የድንግል ልጅ በመስቀል ላይ ባደረገልን ውለታ እንመካለን። እነርሱ ማመን ለሥጋ ዘመዶቻቸው ብቻ እንደሆነ ያስባሉ፤ እኛ መዳን ለሁሉ እንደተሰጠ እናምናለን። እነርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት መሲህ ወደ ዓለም አልመጣም ይላሉ፤ እኛ የነቢያት እውነተኝነት ይገለጽ ዘንድ ሰውን ለማዳን የመጣውን ኢየሱስ ክርስቶስን ድንግል ማርያም ወልዳልናለች ብለን እንመሰክራለን። እነርሱ በሥጋ የአብርሃም ዘር ነን እያሉ ይመካሉ፤ እኛ በመንፈስ የአብርሃም ልጆች፣ የድንግል ማርያም ዘር በመሆናችን we are the off springs of immaculatly without orginal sin conceived mary

  ReplyDelete
 19. ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ፡፡ የአባ ሰላማ ብሎግ መከፈቱ በምንፍቅና ሕይወት ላሉት ወንድሞችና እህቶች መመለስ በር ከፋች ነው፡፡ ምክንያቱም እንደው በግርድፍ /ለብ ለብ/ ያለውን እውቀታቸውን የሚፈትሹበት እና ጥርጣሬያቸውን ወደ ፍጹም እምነት /ኦርቶዶክስ ተዋህዶ / የሚመልሱበት ስለሆነ ደስ ብሎኛል፡፡

  ReplyDelete
 20. የተዋህዶ ልጆች ኮራሁባቹህ ለካስ በ አባቶች ፈንታ ብዙ ልጆች ተወልደዋል በርቱልን
  እናንተ አባሰላማዎች በጣም አዘንኩባችሁ ነገረ ሥራችሁም አሳቀኝ ።በጣም ነው የሚያስቀው ደሞ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት ግን ከሷ የንሳውን ስጋ የለበትም ምን ማለት ነው ? አያስቅም ግን ነገሩ ? አሁንስ በጣም ወረዳችሁ ወይ እመኑ ወይ ደሞ ካዱ ምንድነው ማደናገር ከየት የመጣ ነው እንዲህ አይነት ምንፍቅና ደሞ ወይ ጉድ

  ReplyDelete