Sunday, June 17, 2012

ይድረስ በአባቶቻችን ላይ የስደብና የማዋረድ ዘመቻ ለከፈታችሁ ብሎጎች፡- አባቶችን ማዋረድ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር ማዋረድ ህልውናዋንስ መዳፈር እንደሆነ አታውቁምን…?!

በፍቅር ለይኩን
‹‹ደፋሮችና ኩሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፣ ዳሩ ግን መላእክት በኃይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ በጌታ ፊት በእነርሱ ዘንድ የስድብን ፍርድ አያመጡም…፡፡›› ፪ጴጥ ፪፣፲፩፡፡
መንፈሳዊ ድባብ ያላቸው የሚመስሉና ግን መንፈሳዊ ወዝና ሽታን የተራቆቱ በቤተ ክርስቲያን ስም በተከፈቱ መጦመሪያ መድረኮችና ድረ-ገጾች ዛሬ በእኛ ዘመን በአባቶች ላይ እየወረደው ያለው ስድብና እርግማን፣ እየተገለጸ ያለው ገመና ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነው፡፡ እንዲህ የቤተ ክርስቲያኒቱን ገበና ለአደባባይ በማብቃትስ የሚገኘው ትርፍና ጥቅም ምንድን ነው? እባካችሁ ቆም ብለን እናስብ፣ እናስተውል እንጂ ወገን፡፡ ምን ዓይነት ድፍረት ምን ዓይነት ዝቅጠት ነው ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የተባሉትን ሊቀ ጳጳስ- የአንተ ያለህ…! ‹‹ቀውስ እና ጦስ›› ናቸው ብሎ መጻፍና ማዋረድ፤ ሰውን ያህል ክቡር ፍጥረት ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ‹‹የጉድ ሙዳይ›› በማለት የመንፈሳዊነቱ ክብር ቢቀር ከሰብአዊ ክብር ማውረድ፣ ይህ በምንም ዓይነት መለኪያ፣ በምንም ዓይነት መንገድ ክርስቲያናዊነት ሊባል ይችላል፣ በምንስ መስፈርት ሞራላዊና ግብረ ገብነት ሊሆን ይችላል???
ምንም ከክርስቲያናዊ ጨዋነትና ግብረ ገብነት ብትፋቱም ይሄ አካሄዳችሁ ሕግ ወጥ እንደሆነ አስባችሁበት ታውቁ ይሆን?! እንዴት በቤተ ክርስቲያን ስም  ብሎግ ከፍቶ እንዲህ ዓይነቱ ተራና ወራዳ ሥራ ውስጥ ይገባል፡፡ አባቶችን ለማዋረድ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብርና ህልውና ለመድፍር ይህን መብት የሰጣችሁ ማነው? እናንተን በፍርድ ወንበር ላይ እንደትቀመጡ ያደረጋችሁስ ማነው? እናም እባካችሁ ምን እየሰራችሁና እያደረጋችሁ እንዳለ ቆም ብላችሁ ብታስቡ ደግ ነው እንላለን፡፡ ወይ ስማችሁ ከግብራችሁ ጋር ይስማማ አለበለዚያ ደግሞ ስማችሁን ቀይሩ፡፡
‹‹ሊቀ መልአክ ሚካኤል ከዲያቢሎስ ጋር ስለ ሙሴ ሥጋ በተከራከረ ጊዜ እንኳን ሚካኤል ዲያብሎስን የስድብ ቃል ሊናገረው አልደፈረም እግዚአብሔር ይገስጽህ አለው…፡፡›› እንጂ ነው የሚለን ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ፡፡ ታዲያ ቅዱሱ መልአክ የስድብንና የፍርድን ቃል ለመናገር ካልደፈረ እኛ ማን ነን በአባቶቻችን ላይ እንዲህ ዓይነቱን ለጆሮ የሚቀፍና የሚዘገንን ስድብና የድፍረት ቃል ለመናገር፣ ደግሞስ እንዲህ ዓይነቱን የፍርድ ቃል ለማስተላለፍ ማን መብት ሰጠን፡፡ የአንዳንዶች ድፍረት፣ እርግማንና ክስ ከራሱ ከክፋት አባትና ከጽኑ ከሳሽ ከጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ የማይተናነስና የሚልቅ ነው የሚመስለው፡፡
ለገባንበት መንፈሳዊ ክስረት፣ ውድቀትና ድቀት እርስ በርስ መካሰሱ፣ ማዋረዱና መዘላለፉ እንዲያም ሲል መረጋገሙና መወጋገዙ በምንም መንገድ የምንፈልገውን መፍትሔ ይዞልን ሊመጣ ይችላል፡፡  ይኸው ስንት ዘመናችን እርስ በርሳችን ስንፈራረድና ስንካሰስ ግን አሁንም መፍትሔያችን የሰማይ ያህል የራቀን ነው የሚመስለው፡፡ እናም እባካችሁ እንደ ባለአእምሮ እያሰብን እንደ ሰው እንስራ እንጂ፡፡
በመንፈሳዊነት ሽፋን በቤተ ክርስቲያን ስም የክፋት አንደበታቸውንና እኩይ ትንታግ የሆነ ብዕራቸውን ለዘረጉ ሰዎች ከዚህ ክፋታቻውና አመጻቸው ይመለሱ ዘንድ እባካችሁ ተመለሱ፣ አስተውሉ ልንላቸው እንወዳለን፡፡ የገዛ አባትን፣ ወንድምንና እህትን በማዋረድ ምን ትርፍ ይገኛል? ከእርግማን በስተቀር፣ ክርስቲያን ከሆናችሁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሆናችሁ እንዲህ ዓይነቱንስ ዓይን ያወጣ ድፍረት ከየት ነው ያገኛችሁት፣ ከየትስ ነው የተማራችሁት? ቅዱስ መጽሐፍ ‹‹ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናል፡፡›› ነው የሚለው፡፡ ምናለ ባልተረጋገጠና ባልተጨበጠ መረጃ ደግሞስ እንደው በአባቶቻችን ላይ የምንሰማው ገመና ሆኖስ ቢሆን የክርስትና ወግና ስርዓቱ እንዲህ ነው እንዴ…?! እንዴት እንደ ካም የአባቶቻችንን ገመና በመሸፈን ፈንታ በመግለጽ እርግማንና መዓትን በገዛ ፈቃዳችን ወደራሳችን እንጋብዛለን፡፡
እንደው የሆነውስ ሁሉ ሆኖ የአባቶቻችንንና የወንድሞቻችንን በደል፣ ኃጢአትና ገመና በፍቅር መሸፈን ቢያቅተንና ወደዛ የከበረ ታላቅ የመንፈስ ልእልና ላይ ካልደረስን ምናለ ዝም ማለት ማንን ገደለ፡፡ እንዴት በነጋ ጠባ አባቶቻችንና ወንድሞቻችን በማብጠልጠልና ኃጢአታቸውን በመግለጽ ሰው ከመሆን ክብር ራሳቸሁን ዝቅ ታደርጋላቸሁ የሌሎችንስ ኅሊና ለምን ታቆሽሻላችሁ፣ ታቆስላላችሁ…?
እንዴትስ በስማ በለው በአያችሁትም ባላያችሁትም እየገባችሁ አባቶቻችንና ወንድሞቻችንን ሰድቦ ለሰዳቢ በመስጠትና በሌሎች ድካም ላይ በመፍረድ ወደር የሌለውን ግብዝነታችሁንና ፈሪሳዊነታችሁን እንዲህ በአደባባይ ለመግለጽ ትሸቀዳደማላችሁ፡፡ ይህ በእውነቱ በእጅጉ የሚያሳዝንና ከዓለማውያን ከምንላቸው ሰዎች እንኳን የማይጠበቅ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱንስ ጹሑፍ በብሎጎቻችሁና በድረ ገጾቻችሁ የምታስተናግዱ ሰዎች መንፈሳዊነቱ ቢቀር ከክርስቲያናዊ ጨዋነት ብትሰደዱ እንደው ሰብአዊ/ሰው የመሆን ክብርና መብት ምን እንደሆነ አታውቁም ማለት ነው እንዴ… እናም እባካችሁ እንደ ባለ አእምሮ እናስብ እንደ ባለ ኅሊና እንደ ሰው እንስራ እንጂ ወገን!!! እንዴት ያለ ነገር ነው እባካችሁ…!!!
ሰላም! ሻሎም!
እግዚአብሔር አጥራረ ቤተ ክርስቲያንን ያስታግስልን!!!


36 comments:

 1. ጸሃፊው ይህን ቅዱስ ምክር በማዘጋጀትህ ፤ የብሎግ አዘጋጆችም ደግሞ ድፍረት አግኝታችሁ መልዕክቱ እንዲነበብ በማድረጋችሁ እግዚአብሔር ይስጣችሁ እላለሁ ፡፡

  ከመቅረዝ ድረ ገጽ ያነበብኳትን ቁራጭ መልዕክት ብታክሏት በማለት ይኸው፡-
  “የብዙዎቻችን ከንፈሮች ለሐሜት የተከፈቱ ናቸው፡፡ የራሳችንን ግንድ ትተንም ከሰዎች ጉድፍን ለማውጣት እንዳዳለን፡፡ በወንድሞቻችንም ላይ እንፈርዳለን፡፡ ተወዳጆች ሆይ! እንጠንቀቅ! የፍርድ ዙፋን ያለው ከእርሱ ጋር ብቻ ነውና የወልድን ሥልጣን እኛው አንያዘው፡፡

  መፍረድ ትፈልጋላችሁን? እንግዲያስ ምንም የማያስወቅስና በጣም ብዙ ጥቅም ያለው የፍርድ ችሎት አለላችሁ፡፡ አጥብቃችሁ በራሳችሁ ላይ ለመፍረድ ተቀመጡ፡፡ አስቀድማችሁ በደላችሁን ከፊታችሁ በመዝገብ አስቀምጡት፤ የነፍሳችሁም ወንጀል በሙሉ መርምሩ፤ ተገቢውንም ፍርድ አስቀምጡና ነፍሳችሁን “ይህንና ያንን በደል ያደረግሺው ስለምንድነው?” በሏት፡፡ ከዚህ ፈቀቅ ብላ የሌሎችን ሰዎች ኃጢአት መፈለግ ከጀመረች “የተከሰስሽበት ጉዳይ የእነዚያ አይደለም፣ አንቺም የመጣሽው ስለነዚያ ሰዎች ለመሟገት አይደለም፡፡ ስለምንድነው ክፋትን የሠራሽው? ስለምንስ ነው ያንንና ይህን ጥፋት ያጠፋሽው? የራስሽን ተናገሪ እንጂ ሌሎችን አትውቀሺ” በሏት፡፡ ሁል ጊዜም ይህን አስጨናቂ ፈተናን እንድትመልስ አቻኩሏት፡፡ ተሸማቅቃ ምንም የምትመልሰው ነገር ከሌላትም አስፈላጊውን ቅጣት (ቀኖና) ወሱንባት፡፡ ይህን ልዩ ፍርድቤት ሁል ጊዜ የምትቀመጡ ከሆነ የእሳት ሸሎቆው፣ መርዘኛው ትልና ሊመጣ ያለውን ስቃይ በአእምሮዋችሁ እንዲቀረፅ ይረዳችኋል፡፡
  ሐዋርያው “እኛ በራሳችን ብንፈርድ ኖሮ ባልተፈረደብም ነበር” እንዲል /1ቆሮ.11፡31/፡፡
  ይህን ሁሉ እንድናደርግ ሰውን በመውደድ ሰው የሆነው ክርስቶስ ይርዳን አሜን!!

  ReplyDelete
 2. haymanot yalew sew yazegajew tsihuf

  ReplyDelete
 3. እውነትን እውነት ማለት ስድብ አይደለም። የሰደቡትስ ራሳቸው እረሳቸውን በነውራቸው ሲሰድቡ እሱን መግለጥ በተለይም የራሳቸው ነውር አልበቃ ብሏቸው ሰውን ወደ ተሳሳተ መንገድ መምራት ለጀመሩ አባቶች ተገቢ ነው። እነርሱን ዝም ባለት በብዙ ሺኅ ንጹህ ወነወቸድሞች ደም ላይ መቀለድም ነው የሚሆነው። አባት አባት መሆን ካልቻለ ለዛ ያበቃው ነገር ምን እንደሆነ ሊገለጽ ይገባል። እነርሱ እዛ ቦታ ል የደረሱት የሁሉ አባት ሊሆኑ ነው እንጂ የተወሰነ ቡድን እና ግለሰብ አበት ሊሆኑ አይደለም። በዛ ላይ ለእውነት ለመቆም ሚዛን ያሳታቸው ነገር ምን እንደሆነ ህዝቡ ቢያውቅ ምን ይልሃል? ሌላኛው ወገን በነውራቸው እያስፈራራ ውሳኔዎችን በስጋ ሲያስፈጽም ተገቢ ድርጊት ነው ብለህ ትቀበለዋለህን? አጽራረ ቤተክርስቲያን የሚለውስ ቃል በትክክል ገብቶሃል ወይ? ከእነርሱ የተሻለ አጽራረ ቤተክርስቲያን የሚገን ይመስልሃል። የቤተክርስቲያን ጠላትነት እኮ የሚጀምረው እውነትን ከመጥላት ነው፡፡ ስለሰብዓዊ መብት ማንሳትህ ጥሩ ነው። ግን እኮ የእነርሱ ማንነት በሰብዓዊ መብት የሚዳኝ አየደለም የሚተዳደሩት በእግዚአብሔር ህግ ነው እንጂ በመንግስት ህግ አይደለም። ልጅ ወልዶ መጰጰስ ሕገ ቤተክርስቲያን ይከለክላል። እዚህ ጋር የእነርሱ ሰብዓዊ መብት ቤተክርሰቲያንን ለቆ በመውጣት እንደ አለማዊ በመኖር እንጂ የሚረጋገጠው ቤተክርስቲያን ላይ ተቀምጠው በእግዚአብሔር ልጆች ላይ የአመጽ ሥራ ሲሰሩ ቆሞ በማየት አይደለም።

  ReplyDelete
 4. ጥሩ እይታ ነው ግን ጽሁፍህ ትንሽ ድፍረት ይጎድለዋል። ለምን ከምሳሌዎችህ መካከል አባቶቻችንንም ሆነ ወንድሞቻችንን ለብዙ አመታት ስም ሲያጠፉ የነበሩ እንደ ደጀ ሰላም የመሳሰሉ ብሎጎች ላይ በርካታ ምሳሌዎች እያሉልህ አባ ሰላማ ላይ የወጡትን ጽኁፎች ብቻ በምሳሌነት ማንትህ የህሊና ባርነትህን ያሳይብሃል እንዲህ ያለ ጽሁፍ ሲጻፍ በቂ ጥናት በማድረግና ነውር እወጃውን ማን እንደጀመረው ለምን አላማ ከዛ ደግሞ ሌሎች እንዴት ተቀብለው አስኬዱት የሚለውን በማካተት እንጂ የአንድ ወገን ሀሳብ በሚመስል መንገድ አይደለም ፈቃዱና ዝግጁነቱ ካለህ በዚህ መንገድ ለማድረግ ሞክር። አባሳላማን በጣም አደንቃታለው ትችትዋን ለማውጣት በመድፈርዋ ድንቅ ምሳሌነት ነው። ሌሎች ብሎጎች የተጻፉትን ኮሜንት እንኳ ለማውጣት ሲፈተኑ እያየናቸው ነው። በርቺ አባ ሰላማ

  ReplyDelete
 5. Finally, someone has to be a grownup. This is something that I have been thinking lately. How the blogs, though providing news and information at times, are also creating more problems to the church than solving them by writing and reporting hearsay.

  ReplyDelete
 6. የእፉኝት ልጆች የተባሉት እንደነዚህ አይነት አባቶች ናቸው። እውነት ከሆነ እውነቱ ይገለጽ ሀሰት ካልጻፈችሁ አትጨነቁ እነርሱ ከዚህ ሁሉ ገመናቸው ጋር በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብን በፍትህ ዕጦት እያንገላቱት አይደለም ወይ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. እፉኝት ብሎ ለመውቀስ ብቀቱና ጽዳቱ ያለው ማን ነው ?
   ጌታ በአመንዝራ በተያዘችው ሴት ላይ እንዲፈርድ ሲያቀርቡለት የሰጣቸው ምላሽ ከእናንተ ኃጢአት የሌለባት ቀድሞ ይውገራት ብሏልና ፤ ለመውቀስም ሆነ ጣትን ለመቀተር መጀመሪያ ራሳችን የት እንዳለን መርምረነዋል ?

   Delete
 7. የጸሀፊውን ሀሳብ ብወደውም ሚዛናዊነት ግን በትክክል ይጎድለዋል። አባሰላማን እና አውረ ምህረትን ካነሳ በበርካታ አቡነ ጳውሎስን ጀምሮ በበርካታ አባቶችና ውንድሞች ላይ የስድብ አፉን የሚከፍተውን ደጀ ሰላምን ምነው ረሳ? አቡነ ጻውሎስንና አቡነ ገሪማን ክፉኛ ያብጠለጠለውን ገብርሄር ምነው ረሳ? አቡነ ጳውሎስንና አቡነ ሳዊሮስን እና በርካታ ወንድሞችን የሚሳደበውን አንድአድርገንን ምነው ረሳ? ወይስ እንደ አባቶቻችን እውነትም ቢሆን ማህበረ ቅዱሳንን መንካት አስጊ ሆኖበት ነው? ሀሳብህ ጥሩ ቢሆንም አስተሳሰብህ ግን ትክክለኛ አይደለም። በመጀመሪያ አንተ ንስሀ ግባና ማንም ምንም ቢልህም ለእውነት ስራ ሁሉንን ብሎጎች በትክክል ዳኝ? ከሁሉ ግን ያስጠላኝ አንተ የማህበረ ቅዱሳን ተቃዋሚ ብሎጎችን አጽራረ ቤተክርስቲን ማለትህ ወገንተኝነትህን በግልጽ ያሳይብሃል። አንዳንድ ጽሁፎችን ከዚህ በፊት አነብልህ ስለነበር በግሌ አደንቅሀለሁ ወደ ቀደመው ሚዛናዊ ማንነትህ መመለሱ ጥሩ ነው። ወገንተኝነት ለማንም አይበጅም።

  ReplyDelete
 8. well it is good but one sided. i thought u were a researcher then do z research in all blogs.

  ReplyDelete
 9. once a human being is under the control of satan, how can he think good! how can he/she respect Saits, humanity, ...or GOD? how can that be possible? if that be possible, it implies that satan has stopped its work and/or canged its mission. had that been happenned, all things would have been okey. but it is to the end of the world that satan is working hard, with its maximum effort to get more with it in the hell. more and more people have been engaged in its mission, becoming best and well trained servants...if we observe every thing happening wisely, it is the critical time for us to defend ourselves, our Holly Church...Thank you Fikir Leykun for advising them wisely! but what we are observing from their work is that they are trying to use other more harmfull methods to accomplish the mission of diablos. they didn't understand the fact that they are moving at a very high speed away from the Kingdom of God, as when satan fell.

  ReplyDelete
 10. o!i doubt is it aba selama?

  ReplyDelete
 11. Yetesadebachihu enante sithonu ahun lemanew yemititsifut.Lemanegnawum lib yistachihu.

  ReplyDelete
 12. መልስ ለበፍቅ ለይኩን ለመሆኑ የማህበረ ቅዱሳን ልሳን የሆነው ደጀ ሰላም የፓትራርኩን የአቡነ ጳውሎስን ስም በሌልትና በቀን በድህረ ገጾቻቸው የመሳደብ መብት ለመሆኑ ማን ሰጣቸው? የሊቃነ ጳጳሳት አባት ናቸው። እነርሱ እሳቸውን ሲያዋርዱና ስሳደቡ ወንድማችን የት ነበረክ? ስድብ የተጀመረው ከማህበረ ቅዱሳን የተገኘ ነው። በመጀመሪያ የጠቀስካቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ለማህበረ ቅዱሳን ልሳን ለሆነው ለደጀ ሰላም ይፈቅድለታልን? አቡነ ጳውሎስትን ለመሳደብ መብት ማን ስጣቸው? ገንብ ሀሳብና ምዛናዊ የሆነ አስተያየት ጥሩ ነው ነገር ግን እንድህ አይነቱ አቡነ ጳውሎስ ይሰደቡ እነ አቡነ አብራሃም ግን ይከበሩ። እንድ ልሆን ይችላል? የእነ አቡነ አብርሃም አባት እኮ እሳቸው ናቸው። አባ ሰላማዎች እውነቱን ከማውጣት ዝም አትበሉ።የአየነውና የሰማነውን ከመናግር ዝም ማለት አንችልም። የሐዋርያት ሥራ ም 4፤20

  ReplyDelete
 13. "አጥራረ ቤተ ክርስቲያን" mindinewu?
  However, the point you (the writer) have raised seems fine on one hand. On the other hand, it seems to me you are trying to pull the trigger to bring the already hated articles those are posted earlier in this blog and other "sister" blogs. However, if you initiated this idea from the bottom of your heart, the mercy of Lord may be with you all those who raised those shamefull imoral words on our religious fathers.If not, may the mercy of Lord be with you for your transgration on your mind and hand and mouth (may be).

  ReplyDelete
 14. ሊቀ መልአክ ሚካኤል ከዲያቢሎስ ጋር ስለ ሙሴ ሥጋ በተከራከረ ጊዜ እንኳን ሚካኤል ዲያብሎስን የስድብ ቃል ሊናገረው አልደፈረም እግዚአብሔር ይገስጽህ አለው…፡፡››

  ReplyDelete
 15. Egziabher Yibarkih Wendime!!!!!!!

  ReplyDelete
 16. God bless you Befikir Leykun. Jero yalew mesimatin Yisma. It is also a blessing to Aba selama blog to post such kind of logical, correct and impressive comment. I hope they will learn more and retreat from their bad work by insulting our fathers. By the way I don't think like Befikir that the bloggers are religious people rather they are probably politicians sent by some body to distract the church b/c I haven't seen in their post something that seems spiritual rather than insulting our fathers and brothers struggling for the church. Anyways well said and I want to ask those bloggers to stop their distinctive movement.

  ReplyDelete
 17. sidibu endalawatachihu sitawuqu aqitacha mekeyer jemerachihu malet new? yih yishalal. belu bertu.

  ReplyDelete
 18. Oh this is a nice article . yes why you blame our fathers even if there are a lot of problems is there. why you blogers follow your fathers(protestantawi tehadiso to full time protestant)

  ReplyDelete
 19. ውድ ፍቅር ለይኩን፣
  እጅግ በጣም ጥሩ ምክር ነው፣ የሚሰማ ቢገኝ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድሜ። አዎ ማስተዋል፣ መተዛዘን፣ መከባበር ከብዙዎች ዘንድ ተሠወረ፤ እናም እግዚአብሔር ፊቱን ከኛ አዞረ። ኹልጊዜ ስደት፣ ኹልጊዜ ችግር በወገናችን ላይ ጠነከረ፤ ...
  እስቲ ማስተዋሉን ያድለን

  ReplyDelete
 20. ለይኩን ጥሩ ብለሃል በዛም ክርስትናና አስተማርካቸው ልብ ካላቸው እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይህንን አላስተማረችም ያሳዝናል ጌታ እውነቱን ያመላክታችሁ ምስኪን ወንድሞቻችን

  ReplyDelete
 21. Egzer yistelen wondimachen chigiru mine meselek hulunime mokirewu silakatacheewu neewu wede sideb yeteshegagerut wondime emenegne enze sewoche aemiro yalachewu sewoch ayidelum

  ReplyDelete
 22. በመጀመርያ አንተን ይገስፅህ፡፡
  ለመሆኑ ለምን አፍህን ወደ ቤተ ክርስትያን ከፈትክ !!!
  የአባቶችን ስም የምታጠፋ እንተ እራስህ ከዚያ ደግሞ ጠበቃ ትሆናለህ!!!
  ለምን የዲየቭሎስን ተባባሪና አስፈፃሚ ተሆናለህ!!!
  ከክህደት ይጠብቅ እግዚአብሔር እንጂ እሷስ ጥንተ አብሶ አያገኛትም
  አንተ ግን በደልክ በክፋትም ተሞላህ!!!
  እግዚአብሔር ልቦናህ ይመልስልህ!!!

  ReplyDelete
 23. ሰርጸ ድንግልJune 18, 2012 at 5:32 AM

  በፍቅር ለይኩን እግዚብሄር ይባርክህ፡፡ ባንተ አድሮ የተናገረንና የገሰጸን የአባቶቻችን አምላክ ስሙ ከምድር መሃል እስከ አርያም ጫፍ የተመሰገነ ይሁን፡፡ እኛም ደግሞ ድምጹን ከመስማት ወደኋላ እንዳንል በንስሃም ተመልሰን በቤቱ ለመኖር በጽድቅ እንድንመላለስ መንፈስ ቅዱስ ልቦናችንን ይከፍትልን ዘንድ ተግተን እንጸልይ፡፡

  ReplyDelete
 24. ኦ አባ ሰላማ ፈታኅከ በርእስከ
  ዛቲ ጽፋት ለአባ ሰላማ ወአውደ ምህረት
  እግዚአብሔር የሃውክሙ ልበ

  ReplyDelete
 25. 'ወንድሜ' ፍቅር ለይኩን
  እንደምን ሰነበትክ
  ከብዙ ጊዜ በኋላ በዚህ ብሎግ ድምጽህን በመስማቴ ደስ ብሎኛል::

  አዎ! እኔም በእንደዚህ ያለ ጨዋ የክርስትና ሕይወት እጅግ እጅግ እስማማለሁ:: በእርግጥ ሓጢአተኛን እንደ እግዚአብሔር ቃል መገሰጽና እንዲመለስ ማድረግን ቃሉ ይደግፈናል:: ጳውሎስ አእማድ የሆኑትን እንደ ጴጥሮስ ያሉትን እንደተቃወማቸው ማለት ነው:: ሆኖም ግን የእውነተኛ ክርስቲያኖች ቃል ሰሚን በሚያንጽ መልኩ እንጂ እንዳልከው ሊጎዳ በሚችል መልኩ መሆኑ የለበትም::

  እኔ እንደ ገባኝ ክርስትና ፍቅር እውነት ሕይወትና በአጠቃልይ በጎ የሆነውን ሁሉ በማድረግ (ለክፉ ሰዎች ሁሉ) የሚኖሩት እንጂ ክፉን በክፉ አጻፋውን በመመልስ አይደለም:: እንዳልከው እንዲህ ከሆነ የውድድርና የፉክክር ይሆንና የማይደግፉንን ሁሉ(እንደ ፓለቲከኞቻችን) ከስም ማጥፋት ጀምሮ እስከ መግደል የሚያደርስ የጠላትነት ሥራ ይሆናል ማለት ነው::

  የሃይማኖት ሰዎቻችንና ፓለቲከኞቻችን ባለፈው እንደጻፍከው ካለው ከኒልሰን ማንዴላ የሚማሩት መቼ ይሆን????????

  *** ጥያቄ ግን አለኝ:

  አባ ያልካቸውም ሆኑ (ቃሉ ባይደግፍህም) የማይደፈር በሚመስል ስልጣን ተሸፍነው ያሉ ሰዎች እንደ እኔ ያለ ተራ ሰው እንኳ ያደርገዋል ተብሎ የማይገመትና ሕዝብን ወደ ሞት እንዲፈጥን የሚያደርግ ዘግናኝ ሥራ ሲሰሩ ብታይና ሙሉ መረጃ ቢኖርህ ምን ታደርጋለህ? (እንዲመለሱ በጥንቃቄ ካሳሰብክና አልመለስ ሲሉ ማለቴ ነው)

  *** ሌላው በዚች ቤተ ክርስቲያን ስም አሁን እየሆነ ላለው የተሃድሶና የማቅ ትርምስ መፍትሄው ምን ይመስልሃል?? ይህ ትርምስስ ምንጩ ምን ይመስልሃል??

  *** ቤት ክርስቲያኒቷ ባለውለታ የሚያደርጋት ብዙ ቁም ነገር ለአገር የሠራች ቢሆንም አሁን ያለችበት የተደበላለቀ አስተምርዋ ክርስቲያን ያሰኛታል ብለህ በእውነት ታምናለህ?????

  ለምትሰነዝራቸው ገንቢና ጥንቃቄን የተሞሉ አስተያየቶችህ አድናቆት አለኝ:: ነገር ግን ካለህ የታመቀ የታሪክ እውቀትህ አኳያ ብዙ ልታሳውቀን የምትችለው የምድራችን መንፈሳዊ ታሪክ እንዳለህ ስለማምን በበኩሌ በማንኪያ እንኳ አላቀመስከንምና ብታስብበት???

  የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ይብዛልህ!!!

  እህትህ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 26. አባቶችን መዝለፍና መውቀሳችሁን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አድርጋችሁ ለምትመለከቱ ሁሉ ፡-

  1 - ጴጥሮስና ጳውሎስ ፣ ሌሎቹም ሐዋርያት ቢሆኑ የተወቃቀሱት በደረጃቸው የሚቀራረቡና ቅድስናቸውም የተመጣጠነ ስለሆኑ ነው ፡፡ አርድዕቱ ሐዋርያቱን አልወቀሱም ፡፡ ሐዋርያቱም ቢሆን አግባብ ባለው መንገድ ቅሬታቸውን አሰሙ /ተወቃቀሱ/ እንጅ በየመንደሩ የተማረና ያልተማረው ህዝብ ወሬው እንዲደርሰው አልበተኑትም ፡፡ ታድያ የእኛ አፍ መፍታት ፣ በምግባርና በእምነታችን ጳውሎስን ወይስ ጴጥሮስን ሆነናል ማለት ነው ? አሻቅቦ ድንጋይ መወረወርስ ከየትኛው ሐዋርያ ትምህርት የተቀዳ ነው ? የቤተ ክርስቲያን ሥርዓታችሁስ ይኸን የተያዘውን አካሄድ ይደግፍላችኋል ?
  2 - ዮሐንስ እፉኝት /ብዙ አማኞች የሚወዱት ቃል/ ብሎ ቢወቅስ ፣ ጌታ ሳይቀር የመሰከረለት ታላቅ የሃይማኖት መልዕክተኛ ነው ፡፡ እኛ ታድያ የማን ምስክርነትን ይዘን ፣ የትኛው የእምነት እረከን ላይ ደርሰን ይሆን ሌሎችን ለመውቀስና ለመሳደብ የደፈርነው ? አስቀድመን ራሳችንን በውል እንወቀው ፡፡ ሰው ራሱን ሳያውቅ ነው ፣ ወደ ሌሎች የሚያተኩርና የሌሎች ኃጢአትን የሚያነበንበው ፡፡

  በተረፈ የሐዋርያው ያዕቆብን መልዕክት በጥሞና ደጋግማችሁ አንብቡት ፤ እጅግ ያስተምረናል ፡፡
  “ 1፡2-3 ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት” ፡፡ በደል ደረሰብን የምትሉን ግለ ሰዎች ፣ ይህ አሁን ያጋጠማችሁ መፈተኛችሁ ሊሆን ሲችል ፣ የሰጣችሁት መልስ ግን መጽሐፉ ከሚለው እጅግ የራቀ ነው ፡፡

  “ 1፡22 ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።” አማኝነታችሁን ካረጋገጣችሁልን ፣ በተግባርም እንደ ክርስቶስ ምርጥ ልጆች መረማመድ ያስፈልጋችኋል እንጅ ፣ ሃይማኖት እንደ ሌለው መንገደኛ መሳደብ ትክክል አይደለም ፡፡

  “ 1፡26 አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።” ይኸን ደግማችሁ አንብቡት ምንም ማብራራት አይፈልግም ፡፡

  “ 3፡ 1 ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ብዙዎቹ አስተማሪዎች አይሁኑ፥ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃላችሁና።” ፡፡ አባቶች ማንንም ቢበድሉ እግዚአብሔር ይበልጥ ይቀጣቸዋልና ወደ እግዚአብሔር ማመልከቱ ብቻ ይበቃን ነበር ፡፡ እንዲያውም ተሳሳቱ ብለን ካመንን ፣ እንደ ክርስቲያንነታችን መጠን ለተሳሳቱበት ጉዳይ ፍርድ እንዳያገኛቸው መጸለይና ማልቀስ ፤ ስህተታቸውን እንዲረዱትና እንዲያርሙ ፣ መንፈሰ ቅዱስ እንዲያግዛቸውም መለመን እንጅ ፣ ለህሊና የሚከብድን ቃል ማስነበብ ክርስቲያናዊ ልምምድ አይደለም ፡፡

  ሌላው በአብዛኞች የተጠቀሰው ፣ የተሰጠው አስተያየት አንድ ወገንን ብቻ የወቀሰ ነው ስለሚል ፣ ትንሽ ቃሎች አስተካክሎ በግልባጭ ሌሎቹም ራሳቸውን እንዲመረምሩ ማድረግ መልካም ነው ፡፡ ምናልባት የሰላም መንገድ በዚሁ ይከፈት ይሆናል ፡፡

  ReplyDelete
 27. ክቡራን አንባቢዎቼ ለሰጡኝ አስተያየት፣ ጥቆማ፣ ምክር ስለ ሌላውም ስለሌላውም ነገር በኢትዮጵያ ጨዋነትና ባሕል ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ የመጻፋችን ዓላማ እርስ በርስ ለመተናነጽና ለመማማር እስከሆነ ድረስ ምልካም ነው እላለሁ፡፡ በጹሑፌ በነሳሁት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከተሰጡ አስተያየቶች በመነሳት ጥቂት ነገሮችን ልበል፡

  በቤተ ክርስቲያናችን አንዳንድ ማኅበራትና ግለሰቦች ዘንድ በእጅጉ በሰፈነው የመወጋገዝ፣ የጽንፈኝነትና የፍረጃ አባዜ የተነሳ አንዳንዶች ማኅበረ ቅዱሳን አንዳንዶች ደግሞ በተቃራኒው ያሰቡኝ ወይም የፈረጁኝ የሚመስሉ አስተያየቶችን ታዝቤያለሁ፡፡ ይሄ ጽንፈኝነትና ፍረጃ የ66ቱ አብዮት ከፈጠራቸው ግራ ዘመም (Marxists’) ፖለቲካኞቻችን ዘንድ ተላልፎብን ይሆን እንዴ ጎበዝ! ለማንኛውም ስለ ራሴ ብዙ ነገሮችን ለማለት አልደፍርም፤ ግን አንድ ነገር ግን በድፍረት ለመግለጽ እገደዳለሁ፣ ስለ ተዋህዶነቴ፣ ስለ ፍቅርና እውነት ግን እስከ መጨረሻዋ ህቃታዬ ድረስ እመሰክራለሁ፣ እጽፋለሁም፣ ጥብቅናም እቆማለሁ!!!


  በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ድረ-ገጾችና ብሎጎች ላይ በሀገሬና በሀገሬ ታሪክ፣ ፖለቲካ/ስነ መንግሥት፣ ህግና ፍትህ፣ ፍልስፍና፣ ተፍጥሮና የአካባቢ ጥበቃ፣ ስነ ጹሑፍ፣ ኪነ ሕንጻ፣ ማኅበራዊ መስተጋብርና ኢኮኖሚ ላይ ደማቅና በጎ አሻራን ስላሰረፈች ስለ ቅድስት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያምን አቅሜ በፈቀደ መጠን ስጽፍ ነበር፣ አሁንም እጽፋለሁ፡፡ እናም በቤተ ክርስቲያኔ ጉዳዮች ላይ በተለያዩ ጊዜያት በጥቂቷ ካለችኝ እውቀቴ አልፎ አልፎም ቢሆን ወርወር ማድረጌ አልቀረም፡፡ ይህን የማደርገው ደግሞ ለአንድ ድረ ገጽና ብሎግ ብቻ ለይቼ አይደለም፡፡


  ለአባ ሰላማ የምጽፈውን ያህል በዓይነ ቁራኛ ለሚተያዩትና በቃላት ጅራፍ ለሚሸነቋቆጡት ለደጀ ሰላምና ለሎችም ብሎጎችና ድረ ገጾች ላይም እጽፋለሁ፤ ጽፌያለሁም፡፡ ይህን የአሁኑን ጹሑፍ በተመለከተ ግን ለሁሉም ብሎጎች ማለት ይቻላል በተለይ በአባቶች ላይ እንደዛ ያሉትን ጹሑፎች ለመጻፍ ለደፈሩ ብሎጎች ሁሉ ለመላክ ሞክሬያለሁ፣ ያወጡታል ብዬ በሚል ግን አልነበረም፡፡ ያ ቢሆን ደግሞ ከዚህ በተሻለ መረጃና ታሪካዊ እውነቶችን በማከለ ሁናቴ ለመጻፍ ይቻል ነበር፡፡ ቢያንስ ግን እነዚህ ብሎጎች ይህ አጭር መጣጥፍ እንዲህ ለተጠመዱበት ጸያፍ ስራቸው ቆም ብለው እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል በማለት ስስ ስሜት ነው የዚህ ጹሑፍ ጽነሰትና ውልደት፡፡


  አባ ሰላማ ጹሑፍ እንደደረሳቸው በኤሜይል አድራሻዬ መልእክት ላኩልኝ፡፡ በትትክከልም እንዲህ ዓይነት የአባቶችንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክበር የሚነካ ጹሑፍ ማውጣታችን ተገቢ አይደለም በማለት ጹሑፍን ለማስተናገድ ወሰኑ፡፡ ለዚህም ምስጋና ይገባቸዋል እላለሁ፡፡ እስቲ አሁን ጹሑፍ ከተስተናገደ በኋላ በተሰጡት አስተያየቶች ላይ ጥቂት ነገሮችን ልበል፡፡ አንድ አስተያየት ሰጪ ከየት አምጥቶ እንደሆነ ለጊዜው ባይገባኝም እንዴት ስንት ‹‹የስድብ አፍ የሆኑ ብሎጎች›› የሆኑ ደጀ ሰላም፣ አንድ አድርገንና ገብረ ኄር የመሳሰሉ ብሎጎች እያሉ አባ ሰላማና አውደ ምሕረትን ለመውቀስ ተነሳህ የሚል አስተያየት አስነብቧል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር ያሳያችሁ እኔ የማንንም ግለሰብም ሆነ ብሎግ ስም አልጠቀስኩም፡፡

  በዚህ ጉዳይ ላይ በማኅበረ ቅዱሳንን ይወግናሉ የተባሉትም ሆኑ በተቃራኒው የቆሙ ብሎጎች ሁሉ በዚህ ዓይነት የማይገባ ስራ ውስጥ ካሉ ሁሉንም የሚመለከት እንጂ ስም ጠቅሼ ለይቼ የጻፍኩት ነገር አይደለም፡፡ ይህን ለማረጋገጥ ጹሑፍን በጽሞናና በሰከነ ልብ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡ በመሰረቱ እኔ አነሳሴ ክርስቲያናዊ ጨዋነት ይኑረን የክርስትና ትልቁና ዋና ባሕርይ የሆነው ፍቅር እንዲህ አያደርግም፣ ፍቅር ይሰደባል፣ ይሰደዳል፣ ይንገላታል… እንጂ በተቀቃራኒው አያደርግም ከሚል ከመሠረታዊው የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ/የክርስትና አስተምህሮ በመነሳት ይህን ጹሑፍ ልጽፈው ወደድሁ እንጂ ለአንዳንዶች እንደመሰላቸው አንዱን አጥላልቶ ሌላውን በመደገፍ በሚል ተራ ቁማር ለመጫወት አይደለም፡፡


  የማስታውሰው በአንድ ወቅት በሌላ አንድ ጹሑፌ የዓባይን ልማትና የቤተ ክርስቲያን አስተዋእፆ በተመለከተ በደጀ ሰላም ላይ በተስተናገደ ጹሑፌ ብዙዎች የአባ ጳውሎስ ካድሬና ኢአህአዴግ እንደሆንክ ሊፈርጁ የሞከሩ አስተያየቶችን በገፍ ተቀብያለሁ ደጀ ሰላምም እንዲህ ዓይነቱን አፍቃሪ አባ ጳውሎስና ካድሬያዊ የሆነ ጹሑፍ ለወደፊቱ እንዳታስተናግድ ማሳሰቢያ ጭምር የሰጡ ሰዎች ነበሩ፡፡ እንግዲህ በዛም አለ በዚህ ከመፈረጅና የዚህ ወገን ነህ ከመባል የሚያድን አማራጭ ጠፍቷል ልክ እንደ ፖለቲካችን ሁሉ ወይ ከእኛ ጋር ሁን ካለበለዚያ ግን ከጠላቶቻችን ወገን ጋር ነህና ሰስም አጠራርህ ይጥፋ! በቆምክበት የጨው ሀውልት ሁን! ዓይነት እርግማንና ውግዘት ከአየአቅጣጫው የበዛ ይመስላል፤ በአሁኑ ጹሑፌም ላይ የአንዳንድ ወገኖቼም አስተያየት ይኸው መንፈስ የሚንጸባረቅበት ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡


  ግና እንዲህ ዓይነቱ ከእኔ ወዲያ ለአሳር የሚል ጭፍን አካሄድ ወዴት ሊያደርሰን እንደሚችል ሳስብ እሰጋለሁ፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የእኔነት መንፈስ ደግሞ ወዴት ይዞን ሊዘልቅ እንደሚችልና ፍጻሜያችን ምን ሊሆን እንደሚችል ሲታሰብ ልብ ቀጥ ይላል፣ ነፍስም ትደክማለች፡፡ ትናንት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ስም በተለያዩ ጎራዎች የተሰለፉ ወንድሞቻችን የተማዘዙትን ሰይፍ፣ ያወረዱትን የድንጋይ ውርጅብኝ፣ የተለዋወጧቸውን ስድብ፣ ውግዘትና እርግማን ለታዘበ ነገ ደግሞ በዚህ አካሄዳችን የመስቀል ጦርነት ላለማወጃችን ምን ዋስትና ይኖረናል… እረ ወዴት ነው እየሄድን ያለነው ጎበዝ…ቆም ብለን ብናስብ መልካም ነው…እርስ በርሳችን ከመበላላታችንና ከመጠፋፋታችን በፊት፡፡
  በመጨረሻም የጹሑፌ መንፈስ በገባችሁና በተረዳችሁት መጠን

  አስተያየታችሁንና ጥቆማችሁን ያደረሳችሁትን ሁሉ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ በአጭር ቃል የጹሑፌ ዓላማ በፍቅርና በክርስቲያናዊ ጨዋነት እርስ በርስ እንድንመካከርና እንድንወያይ ስለሆነ በዚሁ መንፈስ ለመጻፍ ለመወያየት እንችል ዘንድ የፍቅር አምላክ ፍቅሩን አብዝቶ ያድለን!!!
  ሰላም! ሻሎም!
  በፍቅር ለይኩን ነኝ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. This comment has been removed by a blog administrator.

   Delete
 28. ፍቅር ለይኩን!!!!

  ምነው በእኔ ጥያቄዎች ላይ ቅንባ ደፋህባቸው???

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 29. ወንድሜ እባክህ እውነታውን ቆም ብለህ ለመመልከት ሞክር። ሁሉንም ብሎጎች ሳይሆን የጠቀስከው አባ ሰላማን እና አውደ ምህረትን ብቻ ነው። ምሳሌዎችህን በጥንቃቄ ተመልከታቸው። ቀውስ ጦስ ማን ላይ የወጣ ጽሄፍ ነው? የጉድ ሙዳይ ማን ላይ የወጣ ጽሁፍ ነው? ሁሉንም ለመውቀስ ብትፈልግ ሳይሳደቡ ውለው ከማያድሩት ከደጀ ሰላምና ከአንድ አድርገን የሚጠቀስ ምሳሌ አጣህ? ቢያንስ እንድንረዳህ ስህተትህን እመን። ፍላጎትህ ግልጽ ነው። አላማህ የማቅ ተቃዋሚ ብሎጎችን ማብጠልጠል ነው። ልብ ካለህና ድፍረቱ ካለህ ስንት ነገር ማንሳት ትችል ነበር። ግን አሁንም እንኳ ስህተቶችህን ለማረም አለመፈለግህ ያሳዝናል። አስተዋይ ልቦና ይስጥህ የሚመጥንህ ቃል ነው።

  ReplyDelete
 30. ፍቅር ሊቀየምህ ይሆን? አጥፍችለሁ አንድ ወገን መያዜ ስህተት ነው ብትል ምን አለበት? ለምን መካከለኛ ነኝ ለማለት ትሞክራለህ? ምክንየቱም አይደለህምና። አስሳደቡ ያልክ ሰው ራስህስ ጽሁፍህን በስድብ መዝጋትህን ትክደዋለህን። በምን ሞራልህ ነው የማቅ ተቃዋሚ ብሎጎችን ብች ነጥለህ ምሳሌዎችን ከነሱ ብቻ ወስደህ ስታበቃ እንደገና አጽራረ ቤተክርስቲያን ለማለት የደፈረከው? እነ አባ ሰላማስ ቢዘገንነንም አውነት ነው የጻፉት ዋሻዎቹንና ሆነው ብለው በአላማ የሰውን ስም ለማጥፋት የፈጠራ ታሪክ ዘጋቢዎቹን እነ ደጀ ሳላም ምን ነው ረሳክ? ከእነርሱ የሚጠቀስ ምሳሌ አጥተህ ነው? ከጽሁፍህ በመልስህ አዝኛለሁ። ይቀርታ የማደርግልህም በእውነተኛ ዳኝነት ሁሉንም ብሎጎች በዚህ ርዕስ የመተቸት ድፍረት ያለህ ከሆነ ብቻ ነው። ከአንተ የማይጠበቅ ስህተት ተሳስተሀል። ይህም ሚዛናዊነት ማጣትህ ነው።

  ReplyDelete
 31. አዛኝና ተቆርቋሪ መሳይ፤ ባንተ ቤት አባቶች ለምትላቸው ተቆርቁረህ ሞትሃል ስንኳን ዕሩቅ ብእሲ(ምድራዊ ኃይል)መለኮት(ሰማያዊ ኃይል)ዕንኳ የተባለበት ቦታ ነገርና ጊዜ አለ፤ እናም
  በውነት ለሰው መብት ተቆርቋሪና ለሰው አዛኝ ከሆንህ በወሬ አመልክዋለሁ ለምትለው ምነው አልተቆረቆርህ?ለመሆኑ መጽሐፍ ታነባለህ? ከሆነ ይኸውና መላልሰህ አንበው(ሀመይዎ ለእግዚአብሔር ወይቤሉ ይክልኑ ሠሪአ ማእድ በገዳም) ብለውታልና ስለሆነም በሰሌዳው ላይ እውነተኛ ሓሳባቸውን
  የሚያሠፍሩትን ሰዎች ቅሥማቸውን አትስበር፤ በሐሰት የሐሰት ቀምበር በሰው ትክሻ ላይ የሚጭኑትን ግን
  እኔም እንዳንተ አልቀበልምና በርታ!

  ReplyDelete
 32. Fikir Leikun,

  your idea is very good even if it is too late. Already there have been strong wars between blogs that support MK (Dejeselam, andadrgen, gebrher) and the others who are labeled as 'Tehadsio'. Don't be surprised if some pops are insulted by either group as this grouping goes to the pops themselves who are member of the 'Holly Synods'. As you rightly said, we have my way or the high way sort of thinking or if you you like you can call it the zero sum game which is reflected in our social, political and religious thinking. Hence, both groups will continue the fighting until the other group is defeated. The pbm is both groups dont understand in such wars no one will win. rather both of them will lose. In such complex war do you think one should worry about religious, moral or legal issues considering the Ethiopian way of thinking ? I don't think so. For me the solution should come from the pops in the Synod who are expected to be more spiritual than these groups. They should solve their differences and help their sons and daughters to stop the fight. I am not sure whether we have such fathers. Otherwise, i afraid that your idea will not hold water.

  ReplyDelete
 33. Dear commentator Fikir,

  I do not know why you are worried about being critical about" religious leaders". Yes, I agree that our comments need be reasonably rational,not unnecessarily emotional and personal attack. However, this depends on the personality and behavior of those clergymen such as Aba Qostos or any other .... If those clergymen disqualify and undermine themsleves with all kinds of unacceptable pratices, there is no reason for them to expect respect and dignity at all. Yes, we have to be selective in expressing our views. But,do not tell us that harsh but objective criticism is a "religious or cultural taboo ."

  So, the question is not why somebody calls Aba Qostos "qewus and Tos" . The question is whether Aba Qostos behave that way or not. If he does crazy things ,yes he is crazy; and if he does somthing cynical,yes he is synical. There is no any other way to tell the truth. Do not try to scare people with your selected bibilical quotaions. To call the spade spade has nothing to with being sinful or unethical .

  Have a wonderful time buddy!!

  ReplyDelete
 34. Yemigerm afetate new ewunete new kkkkkkkk

  ReplyDelete