Tuesday, June 19, 2012

ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎቹን አስመረቀ

(ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት)
 • መምህር አሰግድ ሳሕሉም ከተመራቂዎቹ አንዱ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በስሯ ከምታስተዳድራቸው መንፈሳዊ ኮሌጆች መካከል አንዱና የ69 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ የሆነው አንጋፋው ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በተገኙበት አስመረቀ። የምረቃ ፕሮግራሙ ደማቅ የነበረ ሲሆን ተማሪዎቹ ቤተክርስቲያንን በቅንንነትና በመልካም ሥነ ምግባር ለማገልገል ቃል ገብተዋል። አዳራሹ በተመራቂዎችና በቤተሰቦቻቸው የተሞላ የነበረ ሲሆን በእያንዳንዱ ተማሪ ፊትም የሚታየው ደስታ ስሜት ልዩ ነበር። በዕለቱ አባታዊ ቡራኬ የሰጡት  ቅዱስ ፓትርያርኩም  “…ያለፉትን ዘመናት መሰናክሎችን እያለፍን መምጣታችን ስለምናውቅ ያለፉትንም ያለፍነው በራሳችን ስላልሆነ አሻጋሪውን አምላክ ከሁሉ በፊት እናመሰግናለን። እናንተ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በኃላፊነት ላይ ነው ያላችሁት እያስረከብናችሁ ነው። በዚህ የተመደበ ሌላ ሥራ የለውም የወንጌል ሥራ በትርፍ ጊዜ የሚሰራ አይደለም። ሁሉንም የምንማረው በጊዜ ነው። ከዚህ በፊት ተምረው የወጡ ብዙ ናቸው። በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ያሉ የገቡትን ኪዳን ይፈጽሙ አይፈጽሙ ተመልካቹ አምላክ ነው። መለኮታዊ አደራ ስለሆነ።….” በማለት አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አክለውም “…ከየትም ተነስቶ ለሃይማኖት ጠበቃ መሆን አይቻልም። ለሃይማኖት ጠበቃ ለመሆን ከእንደዚህ ካሉ መንፈሳዊ ኮሌጆች ተምሮ መውጣት ያስፈልጋል። በምድር ላይ ብዙ እውቀት ብዙ ትምህርት አለ። ያን እናከብራለን። ከየትም ተነስቶ ሃይማኖታዊ ነገር ለማድረግ አይቻልም። መንፈሳዊ እውቀት ከእንደዚህ አይነት ኮሌጆች ነው የሚወጣው።...
ከእንግዲህ በኃላ የዶግማችን የሥርዓታችን የቀኖናችን ምስክሮች አስተማሪዎች እናንተ ናችሁ። የሚጠበቅብን ትውልድ ማሳረፍ ነው። ከመንፈሳዊው ትምህርት ውጪ በሆነ እውቀት ፍልስፍናና ትምህርት የተራቀቀ ለእኛ ሃይማኖታዊውን እውነት የሚያብራራልን ሰው የለም። ከቤተክርስቲያናችን ሥርዓት ጋር አብሮ መታሰብ ያለበት አገልግሎታችንን የፍቅርና የሰላም ማድረግ ነው። በትዕዛዝ እኛ ያልናችሁን ፈጽሙ የሚል ግዳጅ አይሰራም።
ማኅበራችን አንዲት ናት ከዛ የተለየ ማኅበር የለንም። በርግጥ ታሪክ ራሱን ነው የሚደግመው የአጵሎስና የኬፋ ድሮም ነበር። ድምጽ ያላቸው ገንዘብ ያለቸው ሞንታርቮ ያላቸው ሲመጡ መደንገጥ የለም።
አሁን ልትሔዱ ነው። ወዴት? ልታስተምሩ። የእሱ ደቀ መዛሙርት ከመሆን ሌላ ሌላ መጠሪያ የማያስፈልጋችሁ ናችሁ።… ከኛ የተለየ ነው ብሎ ዝም ብሎ ማውገዝ ማሳደድ ከጌታ ትምህርት የተለየ አካሄድ ነው። መጀመሪያ ማስተማር መምከር አንዴ አይደለም። ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ ሲናገር የሰማናቸው ቁጥሮች አሉ። ደጋግሞ መምከር ዕድል መስጠት ያስፈልጋል። ከዛ በኋላ ነው መለየት የሚባለው ነገር የሚመጣው ዝርዝሩ አስፈላጊ አይደለም። ይገባችኋል የዘመናችን ሁኔታ ግን አንዲህ አይደለም ከጌታችን መመሪያና ከሐዋርያት ትምህርት አፈንግጠናል።
የመጣችሁት በአባቶች እግር ለመተካት ነው። ከሁሉ ጋር በአክብሮት ለመኖር የማይመሳሰሉን ቢኖሩ እንኳ ከእነርሱም ጋር ሀሳባችንን በአክብሮት ልንገልጽ የግድ ነው። መንፈሳዊ ሰው ከዚህ የተለየ መልክ የለውም።
ያልነኩንን አንነካም ቢነኩን እንኳ የምናስረዳ የምናስተምር ነን እንጂ። በአጠቃላይ አምላካችን የሚፈልገው ሁሉ በሰላም ሲኖሩ ማየት ነው። ስንተባበር ስንዋደድ ነው እርሱ ለማየት የሚፈልገው። ቤተክርስቲያን የራስዋ ሥርዓት አላት ዝምብሎ መዘርጠጥ መንቀፍ መሳደብ የቤተክርስቲያን ከመሆን የወጣ ነው። …ተርፎን አይደለም እንዲህ አይነቱን ተቋም ያቆምነው ትውልዱን የሚተካ ትውልድ ለማምጣት እንጂ።…” የሚል ሰፊ ትምህርት የሰጡት ቅዱስነታቸው ለምረቃው ዝግጅት ድምቀት ሰጥተውታል።
ከሞላ ጎደል በሁሉም ተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ የደስታ ስሜትን የፈጠረው ትምህርትህን አቁም አላቆምም በሚል ብዙ ውጣ ውረድና የህግ ክርክር ውስጥ የነበረው መምህር አሰግድ ሳህሉ ትምህርቱን ጨርሶ መመረቅ መቻሉ ነው።
መምህሩ በማኅበረ ቅዱሳን አጋፋሪነት ትምህርቱን እንዲያቆም ከፍተኛ ውጊያ ቢገጥመውም በእግዚአብሔር ሃይልና ቸርነት ትምህቱን ጨርሶ ተመርቋል። በተለይም ምርቃቱ የሕግ ክርክሩ እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ደርሶ ባልተቋጨበት ሁኔታ መሆኑና ባለፈው አርብም የፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበረው በመሆኑ የተማሪውን የይመረቅ ይሆን? ጥያቄ አርብ ስቅለት ነው እሁድ ደግሞ ትንሳኤ በሚል ንግግር የተደገፈ ነበር። ጉዳዩን በርካታ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች የጸሎታቸው ርዕስ አድርገው ይዘውት የነበረ ሲሆን አርብ ዕለትም የፍርድ ቤቱ ጉዳይ ምን ሆነ? በሚል አብዛኛው ተማሪ እርስ በራሱ ሲጠያየቅ እንደነበረ ታውቋል።
የሰበር ሰሚው ችሎት ቀጠሮ በሌላ ቀጠሮ እንደተተካ ሲሰማም፥  መምህሩ በእውነት በክርስቶስ ፍቅር የሚወዱት ብዙ ወገኖች አሉት በሚያሰኝ መልኩ ተማሪዎች በደስታ ስሜት ተውጠው ነበር። በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ መምህራን ውጤቱን እንዲያበላሹ ጫና ቢደረግባቸውም መምህራኑ ግን በፍጹም ጨዋነትና የሙያ ሥነ ምግባርን በጠበቀ መልኩ ለተማሪያችን የምንሰጠው ያገኘውን ትክክለኛ ውጤት ነው በማለት ተገቢውን ውጤት ሰጥተውታል።
ቅዳሜ ማታ የግቢው ደቀ መዛሙርት ተመራቂዎችን ለመሸት በግቢው የተማሪዎች የመመገቢያ ክፍል ውስጥ ባዘጋጁት የምስጋና ፕሮግራም በግቢው ታሪክ ተደርጎ የማይታወቅ የተባለ እና እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት የዘለቀ በውብ ዝማሬዎች የታጀበ የነበረ ሲሆን ተመራቂዎቹንም ሆነ የግቢውን ደቀ መዛሙርት በደስታ የሞላ ነበር። በዕለቱ የግቢው አካዳሚክ ዲን “…ያስተማርናችሁ የምናውቃችሁ እኛ ነን ህይወታችሁንም ሆነ ሃይማኖታችሁን በተመለከተ ሌሎች ምስክር ሊሆኑ አይችሉም። በየትኛውም ሀገረ ስብከት ሆናችሁ ለሚደርስባችሁ ፈተና ከጎናችሁ ነን። ከዚህ በፊት ተማሪዎች ነበራችሁ አሁን ግን መምህራን ናችሁ ቤተክርስቲያኒቱን የሚወክል ድምጽ ከእናንተ ነው የሚወጣው” ብለው የተናገሩ ሲሆን የዕለቱ መምህርም “---ጎሰኝነት ዘረኝነት እኔነት ጠባብነት መንደር ነው። ጌታ አይነስውሩን አይኑን ዳሶ ምን ታያለህ ሲለው ሰው እንደ ዛፍ ነው ብሎ የመለሰው ዛፍን ከስሙ በቀር አይቶ የማያውቅ ሰው አየሁ ብሎ የመሰከረው ውሸት ነው ሰው እንደ ዛፍ ሊሆን አይችልምና። ዛሬም ያላየቱን አየን ያልሰሙትን ሰማን እያሉ ውሸት የሚናገሩ ሰዎች አሉ። አጥርቶና አስተውሎ ማየት ካልተቻለ ዝም እናኳ ቢባል ምን አለ?” ብለው የጠየቁት መምህር በመቀጠል “…ሁለተኛ አይኑ ሲዳሰስ ግን አጥርቶ ማየት ችሏል። የእኛንም አይነ ልቦና መድሃኒዓለም ያጥራልን።” በማለት ድንቅ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከምረቃው ሥነ ስርዓት በኃላም ለመምህር አሰግድ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች በመመረቁ የተሰማቸውን ደስታ ሲገልጹለት ታይቷል። በግቢው ውስጥ በነበረውና በኮሌጁ መመገቢያ አዳራሽ በተዘጋጀው የተመራቂ ተማሪዎች ፕሮግራም በርካታ ቁጥር የነበራቸው ዘማሪያንና ሰባኪዎች የተገኙ ሲሆን በፕሮግራሙ፥ ለተማሪዎቹ ባደረገላቸው ድንቅ ነገር እግዚአብሔር የተመሰገነበት በከፍተኛ እልልታ የታገዘ እንደ ነበር ለመገንዘብ ተችሏል። በወቅቱ ያስተማሩት መምህርም ሰባተኛው ቀን በሚል ርዕስ ያስተማሩ ሲሆን ለተመራቂዎቹ እጅግ መልካም የሆነና በመንፈስ ቅዱስ የተመራ ምክር ሰጥተዋል። በግቢው ውስጥ በድንኳን ላይ የነበረው የማህበረ ቅዱሳን ፕሮግራም ግን ለቅሶ ቤት የመሰለ ከምስጋና ይልቅ አላማውን መብላትና መጠጣት የደረገ ነበር። አነርሱን አጅበው የነበሩ ዘማሪያን ጭምር በነመምህር አሰግድ ፕሮግራም በመሳባቸው ዝማሬውን መጥተው የተቀላቀሉ ሲሆን አለቆቻቸው መጥተው አንድ በአንድ እየጠሩ በማስወጣት አብረው እንዳይዘምሩ አድርገዋቸዋል።
ከሰዓት በኃላም መምህር አሰግድ ሳሕሉ በሥላሴ ኮሌጅ በድግሪ መርሃ ግብር ይከታተል የነበረውን ትምህርት ጨርሶ ለመመረቅ መብቃቱን ምክንያት በማድረግ በጓደኞቹ አማካኝነት የተዘጋጀ የምስጋና ፕሮግራም ተደርጎለታል። ዝግጅቱ የነበረውን ሰው ሁሉ በእጅጉ ያረካ  እና በእውነት እግዚአብሔር ትልቅ ነው ያሰኘ ነበረ። መልካም የሆነው ጌታ መልካምነቱን ለልጆቹ እንዲህ ያሳያል። ሥራው ክስና አሳዳጅነት የሆነውን ጠላት ዲያቢሎስንም እንዲህ ያሳፍራል ያስባለ እና የጠላት ጭካኔና ግፍ በበዛ ቁጥር አብረው የሚሰለፉ ወገኖችን እግዚአብሔር እንዲህ ይሰጣል ያሰኘ የምስጋና ፕሮግራም ነበር። የዕለቱ ፕሮግራም መሪ ለፕሮግራሙ ውበት በሆነ አቀራረብ ፕሮግራሙን የመራ ሲሆን በርካታ ሰዎችም በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው እግዚአብሔርን በዝማሬና ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት አመስግነዋል።
የዕለቱ መምህር ስለማዕዘኑ ራስ ክርስቶስ ያስተማሩ ሲሆን “…የመሰረቱ ድንጋይ ላይ ቆሞ አልነቀፍም ማለት አይቻልም። የምስክሩ አለት የማዕዘን ራስ የተባለው ክርስቶስ ነው።…” ሲሉ አስተምረዋል፡፡
የመኪና አደጋ በደረሰበት በዓመቱ ምርቃቱን ያከበረው መምህር አሰግድ በሰጠው ምስክርነት “…የዛሬው ዕለት ለሙት ዓመት እንጨት የሚሰበርበት ሊሆን የሚችል የነበረ ቢሆንም ከወገኖቹ ጋር አብሮ በመሆን እግዚአብሔርን እያመሰገነበት መሆኑን ተናግሯል። አራት ጊዜ ከተገለባበጠ መኪና ተርፎ ለእንዲህ ያለ ክብር መብቃት በራሱ ተዓምር መሆኑንም መስክሯል።
እንኳንስ እንዲመረቅ እንዲማርም የማይፈልጉ አካላት ትምህርቱን እንዳይቀጥል ምን ያህል ትግል እንዳደረጉ በማስታወስ ንግግር ያደረገው መምህር አሰግድ “የማያምን ሰው ወደ እኔ መጥቶ ሊማር ቢፈልግ እንዴት አድርጌ እንደማስተምረው እኔ ነኝ የማውቀው እንኳን እኔ ቤቴ ነው ብዬ መጥቼ ደግሞም ቤቴ ነው ከዚህ ሌላ ቤት አላውቅም፤ የለኝምም።…” ሲል ተደምጧል።
መምህሩ ነገሩን በማብራራትም “…ግቢው የራሱ የህግ ባለሙያ እያለው ማቅ ቀጥሮ ባቆመው ጠበቃ እንደሞገተው እና ባይነካኩን ኖሮ ምርቃቱ ይሔን ያህል ባላማረ ነበር። እየደቋቆሱ እንዲህ አስከበሩን ታሪካችንን አስጌጡት። ምርቃት ብርቅ አይደለም። ምርቃት ብቻ ቢሆን ኖሮ እኛ በዚህ ሆኔታ እዚህ ባልቆምን ነበር። ይህንን ፕሮግራም በቅንነትና በእልህ ያዘጋጁ ሰዎችም እንደዚህ ሆነው አይነሱም ነበር። አሳዳጆቻችን ከነክፋታቸው መቀጠላቸው እነርሱን የበለጠ ቢጎዳቸውም ይጥፉ ግን አንልም። እግዚአብሔር ይስጣቸው ለኛ ሞገስ ጨምረውናል።” ብሏል።
በመቀጠልም “…እኔም ወግ ደርሶኝ በስሙ ተነቅፌያለሁ። ከ18 ዓመት በፊት ጀምሮ የነበረው ትግል አምላካችንም አሁንም በድል ኣሻግሮናል። ከ18 ዓመት በፊት የከሰሰሱን ሰዎች መናፍቅ ይሆናል ጴንጤ ይሆናል እያሉ ቢጮሁም ያሉት ሳይሆን ቀርቶ እስከዛሬ ድረስ ቤተክርቲያንን ማገልገሌ የእግር አሳት ሆኖባቸው ከአባታቸው በተማሩት መሰረት ዛሬም ለክስ ዛሬም ለሀሰት ምስክርነት ሲሯሯጡ መመልከት እጅግ አሳዛኝ ነው።” ያለው መምህር እንዲህ ያለውን የክስና የጥላቻ መንፈስ “…ሳዖል ዕድሜውን ሙሉ ለዳዊት ጠላት ሆነው የሚለውን ቃል ያስታውሰናል።” በማለት የአንዳንድ ሰው የጥላቻ ባህሪ በቀላሉ የማይለወጥ መሆኑን ገልጿል።
ከዝግጅቱ በኃላ በርካታ ሰዎች የአበባ ጉንጉን ለመምህሩ ስጦታ የሰጡ ሲሆን በተለይም ውሾች ከበቡኝ በማለት መጽሐፍ የጻፉት መምህር ወንደሰን ለመምህሩ አበባ ሲሰጡ ያዩ ወገኖች በማኅበረ ቅዱሳን ከፋፋይ ሀሳብ ተከፋፍለው የነበሩ ወንደሞች “እንዲህ እንደገና መቀራረብ መቻላቸው አስደሳች ነው።” በማለት እግዚአብሔርን አመስግነዋል።
በአጠቃላይ ዝግጅቱ የነበረውን ሰው ሁሉ ያረካ በከፍተኛ ዝማሬ የተሞላ የማያቋርጥ እልልታ ያጀበው እጅግ ያማረና ውብ ነበር፡፡

26 comments:

 1. this is good.i like asgede and hid preaching. he is truely the son of God.

  ReplyDelete
  Replies
  1. you are right Dude , ASEGED has been serving Jesus for a long time before. he is a typical example of a true preacher & this is what we expect from all Ethiopian Orthodox Preachers.I do much respect for Memiher ASEGED SAHILU . Congrats Brother!! Geta Eyesus abzito yibarkih !! GOOD LUCK!!!!!!!

   Delete
  2. Tsegawin Yabsalit Wedu Yetemeretw Ewinetegna Sebaki New Egzaibher Yibarkih

   Delete
 2. አቡነ ጳውሎስ ቆንጆ ንግግር ነው ያደረጉት። ለራሳቸው ግን የሰሙት አልመሰለኝም። ምክንያቱም ያንን ሁሉ ህዝብ ሳያጣሩ አያወግዙም ነበር። ማንን አናግረው አወገዙ? ማንን ጠርተው መከሩ? ቢያንስ ከአሁን በኋለ በዚህ መንገድ ቢያስቡ ጥሩ ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድምዬ! አቀርቅሮ ወጊው ማኅበር፤ ያጠመዳቸው ጳጳሳት አንድን አጀንዳ እነሱን በሚጠቅም መልኩ ለማሳለፍ ሲፈልጉ በድምጽ ብልጫ ይወሰን ብለው ድምጻቸው ተቆጥሮ ሲኖዶስ ወሰነው ለማለት ይሽቀዳደማሉ። ፓትርያርኩ ሲቃወሙ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ የሚሰራውን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አልቀበልም ካሉ ከማን ጋር ሊሰሩ ነው ታዲያ? ብለው ይጮሃሉ! ፓትርያርኩ የሚያቀርቡት አጀንዳ የማይዋጥላቸው ከመሰላቸው ደግሞ አቀርቅሮ ወጊውን ማኅበር አማክረው እስኪመለሱ ይህ አጀንዳ በይደር ይቆይ ወይም በኮሚቴ ተጠንቶ ይቅረብልን ይላሉ። ፓትርያርኩም ላለመሸነፍ ባላቸው ሥልጣን የወጊውን ማኅበር አባላት ገትረው ይይዛሉ። የማኅበሩ አባላት ጳጳሳትም በተሰጣቸው የቤት ሥራ መሰረት የፓትርያርኩ የራስ ምታት እስኪነሳ በክርክር ወጥረውና በነገር ወግተው ድባቡን ጦር ሜዳ ያደርጋሉ። ውጥረቱ ያላማረው የሆነ ነገር ሊመጣ ይችላል ብሎ ያደፍጣል ወይም ጉባዔው ሳያልቅ ምክንያት ፈጥሮ ይጠፋል። ጎረምሶቹም ጳጳሳት የታባቱ ይሄ ሽማግሌ ይበድ እያሉ አብረው ያብዳሉ። ፈሪውም ጥጉን ይዞ ቅዱስነታቸው እንዳሉት ይላል። ወንድምዬ አመንክም አላመንክ፤ እነ አቡነ ሚካኤል(የጎንደሩ)፤ አቡነ መርሐ ክርስቶስ፤ አቡነ መቃርዮስ፤እነ አቡነ ማቴዎስ፤ ትላልቆቹ ከሞቱ በኋላ ሲኖዶሱ ብስለትና እርጋታ ያለው መሆኑ ቀርቶ እነእንትና የሚያፈጡበት ጠጅ ቤት መስሏል።

   Delete
  2. defar - kidus synodos'n Endih beleh lemenager tedefraleh. ye-menfes kidus gubae newu.

   Delete
  3. ሲኖዶስ ማለት እኰ «ስብሰባ» ማለት ነው? ምን መስሎሃል? ቃሉ የግሪክ ነው። በአማርኛ ደግሞ ፤ስብሰባ፤ ጉባዔ ተብሎ ይፈታል። አራት ነጥብ።
   ቅዱስ ማለት ደግሞ «በፍጹም ነፍሱ፤ በፍጹም ልቡና በፍጹም ሃሳቡ ለእግዚአብሔር የተለየ ማለት ነው። እንደዚሁ ሁሉ ወንድሙን የሚወድ ማለት ነው። እኔም ፤አንተም፤ እሷም፤ እሱም፤ ሁላችን ይህንን እንድንፈጽም ይገባል። ያኔም «ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ» 1ኛ ጴጥ 1፤15-16 የተባለው ሻሽ ላሰረ ወይም ኮፍያ ለደፋ የተለየ ሳይሆን ለሁላችን መሆኑን ይናገራል። ግንዱ ቅዱስ ስለሆነ እኛ የግንዱ ቅርንጫፎች ሁላችን ቅዱሳን ነን። «በኵራቱም ቅዱስ ከሆነ ብሆው ደግሞ ቅዱስ ነው፤ ሥሩም ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹ ደግሞ ቅዱሳን ናቸው» ሮሜ 11፤16
   ይሁን እንጂ ይህንን ቅድስና ለመጠበቅ መጠንቀቅ ይገባናል።
   «ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ» ኤፌ 5፤3 እንደሚለው ቅድስናችንን መጠበቅ ይገባናል። ከላይ «ደፋር» ላልከኝ ቃል የምሰጥህ ማጠቃለያ መልስ ቅድስናቸውን ልጅ በድብቅ ልጅ በመውለድ፤ ከደሃ ቤተክርስቲያን የሰበሰቡትን ገንዘብ አፓርትማ በመገንባት፤ በማከራየት፤ በዘርና በጎሳ፤ በአድማና በሁከት በዓመት ሁለቴ የሚሰበሰቡት ሰዎች አንድም የቅድስና ስምና ምልክት ስለሌላቸው ስብሰባቸው በመጣ ቁጥር ሽብር ስለሚሆን ይህ ደግሞ ከጠጅ ቤት ጋር ያመሳስለዋል። እውር ማብራትና ሙት ማስነሳቱ ቀርቶባቸው ገመናቸውን መሸፈን ከድመት ያልተማሩ ሰዎች ቅዱሳን ልንላቸው አይገባም። ፈሪሃ እግዚአብሔርና በመንፈስ የተቃኘ አስተምህሮ የሚሰጡትን የአክሱም ሊቀጳጳስ አቡነ ሰላማንና የጉድ ሙዳዩን ጳጳስ አባ አብርሃምን አንድ ላይ ማስቀመጥ በእውነት በመንፈስ ቅዱስ ላይ ማሾፍ ይሆናል። አባ መርሐ ክርስቶስ በአንድ ወቅት ለጵጵስና መታጨቱን ተቃውመው ብንድረው ይሻላል ያሉትን ቃል እኔም ተውሼ አባ አብርሃምና ወንድሞቹ ትዳር ቢይዙና አርፈው ቢቀመጡ ኖሮ ስብሰባው ጠጅ ቤት ከመምሰል፤ ህጋዊ ባልሆኑ ልጆች የተነሳ ከክርክር ቤተክርስቲያን ትገላገል ነበር።

   Delete
 3. የወንጌል ሥራ በትርፍ ጊዜ የሚሰራ አይደለም።

  አማን በአማን

  ReplyDelete
 4. አሰግድ ተመረቀቀቀቀቀቀቀ------ጉድ ነው እንዴት እባካችሁ?በሕይወት ነበር እንዴ??????????እንዲህ ነው በማቅ መቃብር ላይ ሐውልት መሥራት!!እንዴት ዓይነት ሃውልት>የወንጌል?ምን ይጻፍ ሐውልቱ ላይ?ነህ እንዴ?እዚያ መጽሔት ላይ ያንን ቃል በድፍረት ተናግረህ ከሆነ አሁን የተመረቅኸህ ከሆነ?ሀገሪቱ ተስፋ አላት ማለት ነው!
  የሚገርመው ደግሞ የብፁእ ወቅዱስ አባታችን ንግግር ጉደኛ ነበር እባካችሁ!ይህ ነው እንግዲህ የሰፋ አስተሳሰብ ያላቸው አባቶች አያሳጣ ማለት!እኒህን አባት እግዚአብሔር እድሜያቸውን ያርዝምልን!በእሳቸው ዘመን ቅድስት ቤ/ክርስቲያናችን በወንጌል ሙለሙሉ ትጥለቅለቅልን!ያነበብነው የሰማነው የተባረከ ይሁን!አይ አባ ሰላሞች እንደው እግዚአብሔር እናንተን አስነስቷልና በርቱ በርቱ እንዲህ እየተከታተላችሁ በርቱና ጻፉልን!

  ReplyDelete
 5. ስለልጁ መመረቅ ወይስ ስለተቋሙ አስባችሁ ይሆን ምርቃቱን የዘገባችሁት?እዉነት እና ንጋት እያደር ይጠራል እንደተባለዉ ሁሉም እያደር ይታወቃል?ልጁ በእዉነት ስህተት ከሌለበት እሰየዉ ግን እናንተ እነዴት ስለእርሱ ልትጨነቁ ቻላችሁ?መቸም ያለአንድ ነገር አልጮሃችሁም፤እናም የጮሃችሁበትን ምክንያት ባለቤቱ እግዚአብሔር አዉቆ መልሱን እርሱ ይስጣችሁ፡፡ማህበሩን አትፈታተኑ፤ በችግር እንዳትፈቱ፤አሉለት እና መላዕክቱ፡፡ (ዉብሸት)

  ReplyDelete
 6. Be Ewenet Egziabeher yetemesgene Yihun Betam Des Yilal Ahunem diyabilos kemewagat ayebozenem Enanete Tegtachehu Tseleyu Mahebre seyetanoch Ye Kinat Abaze Yeyazachew sewoch nachew masaded new serachew ensun atemleketuu wedesirachew yensu kersetna mesdeb,, bedebdeb, mekses new lelaw ensu tsuami, askedash tsadik, lelaw yemayetsom wezete ere sinetu yebetkersteyan amelak eyeferde new serachew be wechim be hager westim ende tsehay tegeltsoal ere genaaaa ayezoachehu bertu ye Egziabher lijoch

  ReplyDelete
 7. Congratulation Memhir Asegid may the blessing of our Lord JESUS CHRIST be with you all. Amen. Abba.

  ReplyDelete
 8. የአባታችን አቡነ ጳውሎስ ፣ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ንግግር በእጅጉ የሚደነቅ ነው ፡፡ ብዙ ምክር ይዟል ፤ ሰላምን ይሰብካል ፡፡ በጥሞና ከተመረመረ ለሁሉም ወገኖች የሚያስተላልፈው መልዕክት አለው ፡፡

  አንድ ቦታ ላይ ብቻ ፣ የተመራቂዎችን ስሜት ለመጠበቅ ይሁን ስለምን ምክንያት ለሃይማኖት ጠበቃ ለመሆን የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተመራቂ መሆን ይገባዋል የሚል መልዕክት ማስተላለፋቸው እንደ ክርስቲያንነቴ መጠን አልተረዳኝም ፡፡

  እንደ እኔ አመለካከት ከሆነ እያንዳንዱ ክርስቲያን ለሃይማኖቱ አርበኛ ፣ ጠበቃም ነው ፡፡ ሃይማኖት የግል ተጋድሎን ስለምትፈልግ ፣ ማንኛውም ምእመን ላመነበትና ለተረዳው ነገር ባለበት ዘብ መቆም አለበት ፡፡ በየአውደ ምሕረትም የሚሰበከው በየአቅጣጫው እንዳይነዳ ለዚሁ ውትድርና ለማዘጋጀት ፤ በእምነትም ለማጐልበት ነው ፡፡ አባቶቻችንም ይህችን ቤተ ክርስቲያን ጠብቀው ያቆዩን ከኮሌጅ እየተመረቁ አይደለም ፡፡ እንዲያውም ቀለም ሲበዛ ስለሚያሰክር ፣ ምንፍቅናን ያመጡብን ተምረናል የሚሉ ሰዎች ናቸው እንጅ ተራው መደዴ አማኝ አይደለም ፡፡ በአሁኑ ዘመን ደግሞ ክርስትናን በየጽሁፋቸው የሚያብጠለጥሉት ግለ ሰዎች ፤ አንድ ሳይሆን ሁለትና ሦስት ዲግሪ የተሸከሙ ናቸው ፡፡ ስለዚህም ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃልን ስለተማረ ብቻ መንፈሳዊ ይሆናል ፣ ለሃይማኖትም ጠበቃ ይሆናል የሚል ድምዳሜ የለኝም ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ስናይ ደግሞ ፣ አንድም ሐዋርያ ወይም ደቀ መዝሙር ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የተመረቀ አናገኝም ፡፡ ለምን ይህን ለመናገር እንደፈለጉ ለእኔ ምክንያታቸው ግልጽ አይደለም ፡፡ በዚህ መልዕክታቸው የእግዚአብሔር ጸጋንም የዘነጉት መሰለኝ ፡፡ ኢየሱስ ጳውሎስን አንድ ቀን እንኳን አስተምሮት አያውቅም ፡፡ ከዕርገት በኋላ ግን በመገለጥ ብቻ የክርስትና አርበኛ አድርጎታል ፡፡ በእርግጥ ጳውሎስ እንዲያ በድፍረት የሚተነትነውን ክርስትና የተማረው መንፈሳዊ ኰሌጅ ገብቶ ነው ? መልሴ አይደለም ነው ፡፡ እናም መግለጫቸውን የተረዳችሁት ሰዎች ካላችሁ ብታብራሩልኝ ደስ ይለኛል ፡፡ ጥያቄዬን የማቀርብላችሁ በተንኰል መንገድ ተመልክቼው ሳይሆን ምናልባት ኰሌጅ ሳንገባ በምናውቀው አንዳንዴ መከራከራችን ስህተት ከሆነ ፣ ራሴን ለወደፊቱ ለማረም በማሰብ ነው ፡፡

  ከጽሁፍ የተወሰደ ቃላቸው እንዲህ ይላል “…ከየትም ተነስቶ ለሃይማኖት ጠበቃ መሆን አይቻልም። ለሃይማኖት ጠበቃ ለመሆን ከእንደዚህ ካሉ መንፈሳዊ ኮሌጆች ተምሮ መውጣት ያስፈልጋል። በምድር ላይ ብዙ እውቀት ብዙ ትምህርት አለ። ያን እናከብራለን። ከየትም ተነስቶ ሃይማኖታዊ ነገር ለማድረግ አይቻልም። መንፈሳዊ እውቀት ከእንደዚህ አይነት ኮሌጆች ነው የሚወጣው።..."

  ከምስጋና ጋር

  ReplyDelete
 9. አባ ጳውሎስ ትምሕርት ሳይሆን አመጽን ነው የሰበኩት

  ReplyDelete
  Replies
  1. መካድ የማንችለው ትምህርት ፡-
   - እግዚአብሔር ያጋጠማቸውን መሰናክሎች እንዲያልፉ ስለረዳቸው የምስጋና ቃል አሰምተውበታል ፤ የራሳችንንም አካሄድ እንድንመረምር እግረ መንገድ በማሳሰብ ፤ በምንሠራው ሁሉ የአምላክ ፍርድ ከበላያችን እንዳለ ጠቁመዋል

   - በኰሌጅ ላልተማሩና ለእኔ ብጤ መደዴ የሃይማኖት ተሟጋቾች የይበቃችኋል አዋጅ ነግረውበታል ፡፡ ሃይማኖትን ለመጠበቅ ትልቁ ትጥቅ የሚገኘው ከመንፈሳዊ ኰሌጅ በመመረቅ እንደ ሆነም መስክረዋል /በዚህኛው የራሳቸውን ምሁርነት ከመግለጽ ባሻገር ፤ በተመራቂዎችና በተለምዶ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ቀሳውስት መሃል ጐራ እንዲፈጠር የመሠረቱን ደንጊያ ያኖሩ ይመስላል ፡፡ ጉዳዩ በሂደት በሚያጋጥመው የሚፈተሽ ነው/፡፡

   - የሃይማኖት አገልግሎታቱ የፍቅርና የሰላም መሆን እንደሚገባው መክረዋል ፡፡

   - የክርስቲያኖች ማኀበር አንዲት መሆኗን ነግረዋል

   - ባለፈው የሲኖዶስ ስብሰባ የማይስማሙባቸው አንዳንድ ውሳኔዎች በመተላለፋቸው ምክንያት የተሰማቸውን ለመግለጽ “ከጌታችን መመሪያና ከሐዋርያት ትምህርት አፈንግጠናል” በማለት የንስሐ ቃል አሰምተዋል

   - በመጨረሻም ጐራ ፈጥረው አላግባብ ለሚወቃቀሱት ሲመክሩ ፣ ሃሳባቸው ከዓላማችን የማይስማማውን እንኳን ፣ በአክብሮት መወያየት ፣ በጨዋነት ማስተናገድ እንደሚገባ ፣ ቢበደሉ እንኳን በአግባቡ ማስተማር እንደሚገባ አስረድተዋል ፡፡ ስለሰላም ፣ ፍቅርና ትብብር ፤ በሥነ ምግባር መሆንንም መክረዋል ፡፡

   Delete
 10. ብጹነታቸው የሰጡት ትምህርት እና አባታዊ ምክራቸው እጅግ ለተመራቅዎቸም ሆኑ ለሁሉ ህዝብ ሕይወትን የሚሰጥና የሚያበረታታ ነው። ለምን የማቅ ተከታዮች አባታቸውን እንደምቃወሙ አይገባኝም። የነቢዩ ኤልሳ እርግባን ለእነዛ ሀሰተኞች የነቢያት ልጆች አንድም አልጠቀመም ከጉዳት በስተቀር። ዛሬም የማቅ ልጆች ከሀሰተኞች ነቢያት ልጆች ምን ይማሩ ይሆን? የማቅ አባለት እራሳቸውን ብመረምሩ መልካም ነው ብጹዕ አባታችን ከመንቀፍም መቆጠብ ብችሉ ምንኛ ለነፍሳቸው ይጥቅማል።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ስለ ማቅ ጠንቅቆ የተረዳ ስለ ሆነ እባካችሁ ሐይማኖታችሁን ከማስወቀስ እራሳችሁን ጠብቁ። እግዚአብሔር የሾመውን የሚያነሰው እግዚአብሔር ብቻ ነው። የሰው ልጆች ከሳቸው ዲያቢሎስ ነው ። ት ኢዮ 1 ቁ 6

  ReplyDelete
 11. your brothers in U.S.AJune 20, 2012 at 3:36 PM

  Good job dn asged you win man through our lord Jesus christ . We know you your are prefect preacher mk always accuse people .

  ReplyDelete
 12. መቼም ለዚህች በእግዚአብሔር ቃል ተስፋ የተገባላት ሀገር እንዳያልፍላት ጠላቶቿ እኛው ነን መንገድና ሕንጻ ሲሰራ ምን ያደርጋል መንገድና ሕንጻ አይበላ እያልን የሀገሪቱን መሪዎች ተስፋ ማስቆረጥ!ደግሞ ኮሌጆች ሲበዙ ምን ያደርጋል ተምሮ የት ሊገባ!በማለት ማሟረት!ለመሆኑ ምን ይሆን የሚያስደስተን?ዛሬ በልቼ ልሙት እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች እንደሚባለው አህያ?ለምን ከታሪክ አንማርም!ዛሬ በሥልጣኔ እዚህ የደረሱት ሀገሮችና እነርሱ ሀገር ለመግባት የምንገበገብባቸው እኮ አባቶች ቆዳ በልተው ብርድ ፈጅቶአቸው ሙቀት ገድሏቸው ነው ታሪክ ማንበብ ይጠቅማል!ለነገሩ ታሪካቸውን እንኳን እኛ የውጭዎቹ የራሳቸው ልጆችም አያውቁም እነርሱ የደረሱት አልጋ በአልጋ ዘመን ነዋ!
  የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት መነፈሳዊ ኮሌጆች ቢከፈቱ የመናፍቃን መፈልፈያ አባት የሆኑት ቅዱስነታቸው በጎ ነገር በኮሌጁ ተማሪዎች ቢነገሩMሁል ጊዜ ልክ የማህበረቅዱሳን ሃሳብ ብቻ ነው አይደል?አሰግድ ቢመረቅ ምናችሁ ነው?እንደው ለመሆኑ እንዚህ ኮሌጆች የደናቁርት መሰብሰቢያና ተማሪዎቹ እኛ እንዳልናችሁ ሂዱ መመራመር መመርመር የለም ተብለው እንዲማሩ ነው እንዴ የሚፈለገው የዛሬ ወጣት እንኳን ተወልዶ ወደዚህ ምድር መጥቶ ይቅርና የሚጠይቀው ጥያቄ ከእናቱ ማሕጸን የሚጀምር ነው የሚመስለው ጠያቂ ተመራማሪ ትውልድ እንደመጣብን ካላወቅንና አብረን ካልተጓዝን ዳር እንደምንቀር መታወቅ አለበት::አሁን ይህ የቅዱስ አባታችን ንግግር ምን ችግር አለበት?ዛሬ ማቅ በግዳጅ የሚጭነውን ቀንበር ተብሎ ተሰብኮልን ዛሬ ደግሞ ኮሌጆች ውስጥ የሚደረገው የእውነት ጥያቄና የጥንት አባቶች አስተምህሮ ለምን ይደበቃል የሚል ጥያቄ መነሳቱ እንደወንጀል ተቆጥሮ ሲባረሩ ከረመ እነርሱ ቢወጡ ሌሎች ሲተኩ ሌሎች ሲተኩ ማቆም ሲያቅት ማህበረ ቅዱሳን ተብየው ማህበረ ሰይጣንየመናፍቃን መፈልፈያ ሆኗልና ለተወሰነ ዓመት መዘጋት አለበት እያለ ማስወራት ቀጠለ?የሰውን ስሜት ለማወቅ ከዚያ ቆራጦቹ የቤ/ክ ልጆች እስቲ ይዘጋና ይሞከር ሲሉ አቅጣጫ ለወጠ ይግረማችሁ ተብሎ በመቀሌ ከሳቴ ብርሃን ኮሌጅ ተከፈተ የባሰ አታምጣ ጉድ ፈላ መናፍቃን ተፈለፈሉ ተባለ ለሁሉም ስም ተሰጣቸው ትምህር ቤቱን ያጠናከሩትን አባት አሁን በሕይወት የሌሉትን የመናፍቃን መሪ ማጠናከሪያ እያለ ማስወራት ጀመረ ነገርን ነገር ያነሳዋልና እንደው የእርሳቸው አሟሟት ጉዳይ ሳይጣራ ምነው ቀረ?>ጥርጣሬው እኮ ብዙ ነው)እሼ ይህንን ትተን ወደ ዋናው ጉዳይ ስንገባ ታዲያ አሁን እነዚህ የሥላሴ ተማሪዎች ለሥላሴ ክብር ለምን ቆሙ ከሆነ ታዲያ ለማን ክብር ይቁሙ?እንደው እኒህን አባት ያቆይልን!!ቶሎ ብቻ ኮሌጁ ወደ ማስትሬቱ አድጎ ይህንን ቤተክርስቲያናችን ውስጥ የገባውን አረም ነቃቅለው ጥለውልን ተረጋግተን ሥራችንን በቀጠልን!እንዚያም ቤታቸውን እየጣሉ የሄዱት የተሻለ ቦታ አገኘን ብለው የሚያስቡት በተመለሱልን!ያነብነውን ይባርክልን ቃለ ንባብ ያስብበን!ይባል ይሆን?
  ኒቆዲሞስ ከባህር ወዲህ

  ReplyDelete
 13. Amelak Min Yesanehal Weladite Amelak Be Meljash Ateleyen Diyabilos kendu temata Ere Min Yibalal Abatachen yetnageruten mekawem? mahebre seytan tenekabhe kahun behuala gudachewen endatawetu yemeferuachehun abatoch eyesebesebachehu betmekiru Egziabeher betkitu abatoch wedk adergobachewal wengel tert tert sayehon ewenetegna wengel yemsebkebet kenu dersual Megabe Hadis Begashaw seyasetemr lemin yemareyam lij Selase atebelu yalewen tekawemew sikesut neber tadeya yeselasi lij man enbel wegen??? Eyesus yeselase lij new ende?? mahebre seyetan melsulegn??

  ReplyDelete
 14. እንኳን ከቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ከእርሱ ከባለቤቱ መድኃኔዓለም እግር ስር የተማረው ይሁዳ ተለይቷል፡፡ የኢትዮጵያና የኢት/ቤ/ክ ልጆች ሆነው ከቀጠሉ እሰየው ያለዚያ ክርስቶስ በመንሹ ይለያቸዋል፣ የምን ስሜታዊ መሆን ነው፡፡ አባ ፓትርያርኩም በዚያ ያጡትን በዚኛው ማካካስ የፈለጉ ይመስላሉ፣ የእሳቸውም ልብና ኩላሊት ከቤ/ክ ተዋህዶ ጋር መሆኑ እየተመረመረ ነው ፤ ልባቸውና መንፈሳቸው የሰው ግቢ እየቀላወጠ ነው፤ ነገሩ ቆየ፤ ግን አሁን………..አሁን ግን አሁን…………እግዚአብሔር ጥናቱን ይስጣቸው?

  ReplyDelete
 15. Yes, the speech of Aba Pawulos is fantastic! But, the very essnce of the matter is not delivering colorful and great rhetoric. It is a question of being keeping the words we speak out practical . I do not think we have problems of talking for the sake of talks. I do not think we have a problem of highly selective and inspiring bibilical and philosophical citations or qoutations . The challenge is : the more we claim that we are educated,the more we become more arrogant and disingenous. That is what we are witnessing as far as the very behavior and action of Aba Pawulos. It is really very absurd if those graduates did not ask themselves; ' Is the Aba Pawulos really speaking his real sense of mind or just something else??" If those students are really beieving that they were andare blessed by a religious leader who lives up to the expectation of the real sense of beief and believers , I am sorry to say but I have to say that they are good for nothing, if not disingenous and dishonest .

  ReplyDelete
 16. If you are fan of MK, you had better visit their website( Deje Selam) your comments are irrelevant here

  ReplyDelete
 17. C O N G A T U L A T I O N S Asegid, the truth is revealed by the time, let them talk, but you have to preach the true gospel of Jesus Christ as you are called for it.

  ReplyDelete
 18. I do not know what else would be relevant if telling the very known fact about what Aba Pawulos has done and still is doing is irrelevant. Yes, I understand very well that to those of you who are neither interested nor genuinely concerned about the serious absence of true spiritual leadership in our country, calling the apade spade ( telling about religious scandal in the name of religion ) is not relevant . Do you have any convincing hard fact to tell the innocent people of the followers of th Church that the two palaces ("Aba Pawulos' in Amisit kilo and Ato Meles' in Arat Kilo ) are different as far as what they practically did for the last quarter of a century and what they have continued to do so is concerned?? I am sorry to say but I have to say that unless we tell the truth ( which I believe is the essence of true Christianity) , I am afraid that we will cause more seriouse damage to the very image of the Church iteslf, and consequently the religious values of this generation. I am not saying that it is not great to see young gradutates of theology accomplishing something good . I am one of the followers of the Church ( not conservative) who want to see more and more people who are qualified in any field of study. However, I strongly believe that the Curch in particular and the country in general desperately need to produce sincerely principled and honest generation . For this desirable situation to be true ,it is absolutely necessary to have genuine and credible leadership,not a very disingenous and dysfunctional one such as Aba Pawulos and those around his circle. I am very well aware that this remark of mine sounds harsh and impolite. But, that is the way how we are witnessing day in and day out.And there is no any other way to express the very hard fact the innocent followers of the Church are experiencing. I strongly argue that if we continue pretneding that nothing wrong is happening and calling "His or Their Holiness " while the reality on the ground is quite the contrary, we are doomed to fail. That is what it is!! Please let's not try to deny what is undeniable !

  ReplyDelete
 19. እውን እናንተ እንደዘገባችሁት አባታችን ተናግረዋል ወይስ እንደዚህኛው ከመቅረዝ እንደተወሰደው ?

  "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
  የዘማናችሁን ዐሥራት ሳይሆን መላ ዕድሜአችሁን ለወንጌል አገልግሎት የሰጣችሁ፣ ዘመናዊውን ዓለም ተላምዳችሁ ዘመናውያን ሰዎች ለመሆን ሳይሆን መንፈሳዊውን ዕውቀት ቀስማችሁ የዓለም ብርሃን ለመሆን በመንፈሳውያን ኰሌጆች ውስጥ እየተማራችሁ የምትገኙና የትምህርታችሁን የመጀመርያው ምዕራፍ አጠናቃችሁ በእግዚአብሔር ስም ልትመረቁ የበቃችሁ የተወደዳችሁ ልጆቼ! በፍቅሩ ቅመም አልጫውን ምድር ባጣፈጠው፣ ጨለማውን ዓለም በቃሉ ባበራው በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም እላችኋለሁ፡፡

  የተወደዳችሁ ልጆቼ! እግዚአብሔር አምላካችን የአንድ ቀንን መታመን የማይረሳ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለማገልገል ብቁዎች መሆን አለብን ብላችሁ ወደ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት የመጣችሁበትን የአንዷን ቀን ፍቅራችሁን የሚያስብ አምላክ ነው፡፡ ምንም እንኳን የጓዳውና የቤቱ ሥራ አስፈላጊና የማይታለፍ ቢሆንም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከማርታ ይልቅ በማርያም ደስ ተሰኝቷል፡፡ ማርታ ያላትን ለትልቁ እንግዳ ልታቀርብ ባለቤቱን ጌታ እንደ እንግዳ ቆጥራ መባረክን ጀመረች፡፡ ማርያም ግን በቤቷም የሚያስተናግዳትን፣ የታዛዋ ብቻ ሳይሆን የሕይወቷም ራስ የሆነውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልታደምጥ ከእግሩ ሥር ቁጭ አለች /ሉቃ.10፡38-42/፡፡ ጌታችን ለእርሱ ከማድረጋችን በፊት ያደረገልንን፣ ስለ እርሱ ከመናገራችን በፊት የነገረንን እንድናስተውል ይፈልጋል፡፡ የማርታ እኅት ማርያም ይህን የተረዳች ትመስላለች፡፡ እናንተም ደቀ መዛሙርት ያሳለፋችኋቸው ዓመታት ከጌታችን እግር ሥር ቁጭ ብላችሁ ድምፁን የሰማችሁበት ዓመታት ናቸውና ደስ ይበላችሁ! ምንም እንኳን የዘወትር ትካዜአችን እንደ ቃሉ መኖር አለመቻል ቢሆንም በቃሉ የመኖርን ኃይል በንስሐና በጸሎት ልንለምን ይገባናል፡፡

  የተወደዳችሁ ደቀ መዛሙርት ልጆቼ! እስከ ዛሬ የሚታሰብላችሁ ልጆች ነበራችሁ፡፡ ዛሬ ግን የምታስቡ ወላጆች እንድትሆኑ ለወንጌል ሙሽራይት ቤተ ክርስቲያን ትድራችኋለች፡፡ በዘመናት ሁሉ እንደታየው ወንጌል ዝም ማለት የማትወድ ናት፡፡ ወንጌልም መክና አታውቅም፡፡ የወንጌል የማጌጫ ዘውዷ አክሊለ ሦክ፣ የሥልጣን ዘንጓም መስቀል፣ መገለጫዋም መገፋት ነው፡፡ የማትገድለው ወንጌል ለሰማዕትነት የጨከነች ናትና አዲሱ ኑሮአችሁን ቤተ ክርስቲያን ትመርቃለች፡፡

  የተወደዳችሁ ልጆቼ! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ለሦስት ዓመታት ከሦስት ወራት ያህል ካስተማራቸው በኋላ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ከልሎ ወደ ዓለም ልኳቸዋል፡፡ እናንተም ላለፉት ዓመታት የደቀ መዝሙርነት ትምህርታችሁን ተከታትላችኋል፡፡ ትምህርታችሁን በሞገስ ለሕዝብ እንዲደርስ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል የምታገኙት በጽሞናና በጸሎት በመቆየት ነው /ሉቃ.24፡49/፡፡ ቤተ ክርስቲያን እናንተን መምህራን አድርጋ ሳይሆን ደቀ መዛሙርት አድርጋ መርቃለች፡፡ ስለዚህ የሁል ጊዜ ተማሪዎች እንደሆናችሁ፣ ትምህርቱም የማያልቅ መሆኑን ልትገነዘቡ ይገባችኋል፡፡

  የተወደዳችሁ ልጆቼ! ምንም ብታስተምሩ፣ ምንም ብትጽፉ ዓለም አበባ ይዛ እንደማትቀበላችሁ እወቁ፡፡ ይህ በእናንተ የተጀመረ ሳይሆን የዓለም መገለጫዋ መሆኑን አትዘንጉ፡፡ ልዩ ልዩ ነቀፋና ስደት ሲመጣባችሁ ከዓለም እንደተጣላችሁ አትቁጠሩት፡፡ እንዲያውም ከዓለም ጋር እንደተዋወቃችሁ ቁጠሩት፡፡ ዓለም እንደዚህ ናትና፡፡ ጎበዝ የሚባለው ሳይቀር በመገፋት ውስጥ በኀዘን ይጐዳል፡፡ የሚታይ ተስፋ እያጣም በብቸኝነት ይንገላታል፡፡ ይሁንና ሰው መተማመኛ የማይሆን የሸምበቆ ምርኩዝ መሆኑን ቃሉ ይነግረናል /ኢሳ.36፡6/፡፡ ስለዚህ በሁሉም ነገር ውስጥ የጠራችሁን ጌታ ክርስቶስን ተመልከቱ /ዕብ.3፡1/፡፡ የተቀበላችሁትን ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ያልተቀበላችሁትንም ለመስጠት ፈቃደኞች ሁኑ፡፡ ፍቅርን አላያችሁ ከሆነ ከእናንተ ይልቅ የፍቅርን ረሀብ የሚያውቅ የለምና ፍቅርን ስጡ፡፡ የሚያዝንላችሁ አባት አላገኛችሁ እንደሆነ ለሚጠጓችሁ እናንተ ደግሞ አዛኝ አባቶች ሁኑ፡፡ ተራራውን ስትጨርሱ መስክ እንደሚያጋጥማችሁ እያሰባችሁ በተራራው አትዘኑ፡፡ እናንተ ዱር መንጣሪዎች ናችሁና የተመቸ ቦታን ፍጠሩ እንጂ ምቹ ቦታን አትጠብቁ፡፡ የደረሰባችሁ ችግርም እስከ ዕድሜአችሁ ፍጻሜ የምትናገሩትን ትምህርት ይሰጣችኋልና አትበሳጩ፡፡ ከምትፈልጉት ነገር ይልቅ ያገኛችሁት ይበልጣል፤ እርሱም የሰማይ ዜጐች መሆናችሁ ነውና ደስ ይበላችሁ!

  የተወደዳችሁ ልጆቼ! እግዚአብሔር የሚባርከው አሳባችሁን ሳይሆን ቃል ኪዳናችሁን ነውና አገልግሎታችሁን በቃል ኪዳን ያዙ፡፡ መጽናናትን የሚሹ ብዙዎች ኀዘንተኞች፣ በማዕበል የሚንገላቱ ብዙዎች ደካሞች እየጠበቋችሁ ነውና ፍጠኑ፡፡ እናንተን ኑ ለማለት አቅም የሌላቸው ብዙ አሉና ሳይጠሯችሁ ሂዱ፤ ወንጌል ሀገሯ እስከ ምድር ዳርቻ ነውና፡፡ ዘመናዊነትና ሥልጣኔ የማይሞላው የሕይወትን ክፍተት በወንጌል የምትሞሉ እናንተ ናችሁ፡፡ የያዛችሁት እንደ ቀላል አትቁጠሩት፡፡ የዓለምን ኃይልና ዕውቀት ሁሉ የምትማርኩ የዕውነት ዘማቾች ናችሁ፡፡ እንደማይፈለግ ሰው ራሳችሁን አትቁጠሩት፡፡ የሞተላችሁ ጌታ ውበቱ የማያረጅ፣ ዛሬም ያደመቃችሁ እርሱ ነው፡፡

  የተወደዳችሁ ልጆቼ! ዋጋችሁ በሰማያት እንደሆነ እያሰባችሁ በትንንሽ የምድር ዋጋ ክብራችሁን እንዳትጥሉ ተጠንቀቁ፡፡ እኔም በጸሎትና በአባታዊ ፍቅር ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን በሰማያዊና በምድራዊ በረከቱ ይባርካችሁ! ዛሬ እንደ ያዕቆብ በሌጣ ወጥታችሁ፣ ለከርሞ ግን በብዙ ፍሬ ይመልሳችሁ! እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክ! የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አገራችን ኢትዮጵያን ይባርክ!”

  የነገር አወላግዶ እንደዚህ ማቀናበሩ ትርፉ ምንድር ነው ? ማንን በሃሰት አስደስቶ ማንን ለማሳዘን ?

  ReplyDelete
 20. PLEASE POST ON YOUTUBE MORE PREACHING FROM MEMHIR ASEGED SHILUE.AND IF IT IS POSSIBLE SHOW US WHEN HE GRADUAT. WE ARE VERY HAPPY ABOUT HIM. WE THANK YOU THE LORD JESUS WAS WITH HIM ALL THE WAY.

  ReplyDelete