Thursday, June 21, 2012

እውነት የተጨቆናባት ሐሰት የነገሠባት ቤተክርስቲያን

Read in PDF

ክብር ለስሙ ይሁንና ጌታ ኢየሱስ ከዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት ጀምሮ አነጋጋሪ ሆኖ ዘልቋል፡፡ የእርሱ ጉዳይ ዛሬም ዋና አነጋጋሪ ጉዳይ ነው፡፡ ኢየሱስ ዛሬ ለብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡ አንድ ቀንም ለጥያቄያቸው ሁሉ መልስ ይሆናል። እርሱ የእባቡን ራስ ይቀጠቅጣል ተብሎ ገና ከኤዶም ገነት ጀምሮ የተነገረለት አዳኝ ነው፡፡ በመሆኑም በጊዜው የሰይጣንን ራስ ቀጥቅጦ በዲያብሎስ ግዛት የነበሩትንና አዳኝነቱን ተረድተው በስሙ ያመኑትን ሁሉ ነጻ አውጥቷል፡፡ በዚህ ደስ የማይለውና የክርስቶስ የአዳኝነቱ ዜና የሆነው የክብሩ ወንጌል ብርሃን በሰዎች ልብ እንዳያበራ የማያምኑትን ሐሳብ በማሳወር እየሰራ የሚገኘው ሰይጣን በልዩ ልዩ ተንኮል እያሳተ ሰዎች በኢየሱስ አዳኝነት አምነው እንዳይድኑ ይተጋል፡፡ በሁሉም አቅጣጫ ሲንቀሳቀስ ዋና አላማው ሰዎች ከመዳን መንገድ እንዲወጡና መዳን በማይገኝበት ጎዳና ላይ እንዲነጉዱ ማድረግ ነው፡፡
ከጥንት ጀምሮ ሰይጣን በዋናነት ዘመቻ የከፈተው በኢየሱስ ላይ ነው፡፡ ይህን ስም ፈጽሞ ይጠላዋል፡፡ አስቀድሞ ይህ ስም በምኩራብ ውስጥ እንዲጠላ፣ ከቤተመቅደስም እንዲሰደድ አደረገ፡፡ ቤተክርስቲያን ግን ተቀበለችው፡፡ በዚህ የተበሳጨው ሰይጣን ቤተክርስቲያንን ማሳደዱን ቀጠለ፡፡ ይሁን እንጂ ስሙን የተሸከመችውን ቤተክርስቲያንን ማሸነፍ አልተቻለውም፡፡ ስለዚህ እርሷን በቀጥታ መዋጋቱን ትቶ ሌላ ስልት ነደፈ፡፡ ይኸውም በተንኮል መንገድ ስሙን ማስጠላት ነው፡፡ ስለዚህ በምኩራብ የጀመረውን ኢየሱስን የማስጠላት ክፉ ሥራ በጊዜ ሂደት ወደቤተክርስቲያንም በማስረጽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ኢየሱስን በረቀቀ ስልት እንድትቃወም እያደረገ ይገኛል፡፡ መቼም እንዲህ ሲባል ብዙዎች እንዴት ተደርጎ? ሊሉ ይችላሉ፡፡ ግን እውነታው ይህ ነው፡፡

እርግጥ ቤተክርስቲያኗ የኢየሱስን ስም ትጠራለች፤ እርሱ ፍጹም አምላክ ነው ፍጹም ሰው ነው ትላለች፤ ደግሞ ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይደለም የሚል ጠንካራ አቋም ታራምዳለች፡፡ ይህ ነው እንግዲህ በረቀቀ መንገድ የኢየሱስን አዳኝነት መቃወም፡፡ ኢየሱስ አዳኝ ነው ሲባል ጉዳዩ በቀጥታ የሚገናኘው ከአማላጅነቱ ጋር ነው፡፡ እርሱ ጌታችን ያዳነን ሰው ሆኖና በሰው ቦታ ተገብቶ በሊቀካህናትነቱ ስለኃጢአት ሁሉ የሚበቃውን መሥዋዕት ራሱን ቤዛ አድርጎ በማቅረብ እና የእርሱ ስለሆኑት ምልጃና ጸሎትን በማቅረብ ነው፡፡ ይህ የተከናወነው አንድ ጊዜ ነው፡፡ የአንድ ጊዜው ግን ለዘላለም ያገለግላል፡፡ በእርሱ አዳኝነት አምነው በእርሱ በኩል የሚመጡት ሁሉ እርሱ ባቀረበው መሥዋዕትና ምልጃ ከእግዚአብሔር ጋር ይታረቃሉ፤ የነፍስ እረፍትና ሰላም ያገኛሉ፡፡ ሰዎች በመሆናቸው ዳግም ኃጢአት መስራታቸው አይቀርምና ለወደፊቱም ኃጢአት ቢሰሩ ስለኃጢአት የሚቀርብ ሌላ መስዋእት እና ምልጃ ስለሌለ አንድ ጊዜ የሐዲስ ካዳን ሊቀካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ባቀረበው ፍጹምና ዘላለማዊ መሥዋእትና ምልጃ ዘወትር እየታረቁና የኃጢአታቸውን ስርየት እየተቀበሉ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ሕብረት ያድሳሉ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ የመታረቂያ መንገድ ከቶ የለም፡፡

ይህን እውነት መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወስደው የቤተክርስቲያን መጻሕፍትም ያስተምራሉ፡፡ ቤተክርስቲያኗ ግን ይህን እውነት በረቀቀ ስልት በትርጓሜ እያጠየመች፣ የክርስቶስን አዳኝነት ውስጥ ውስጡን እየሻረችና ለቅዱሳን እየሰጠች ትገኛለች፡፡ ለዚህ ስትል መጽሐፍ ቅዱስን እስከ ማሻሻል ደርሳለች፡፡ የግእዙ ገጽ ንባብ የማይለውንና ከእግዚአብሔር ሕያው ቃል ይልቅ ለአንድ ቡድን የትርጓሜ ስልት በማደር “ስለእኛ የሚማልደው” የሚለውን “ስለእኛ የሚፈርደው” በማለት ለውጣለች፡፡ ስለክርስቶስ ምልጃ የሚናገሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስትሸሻቸውና የሌሎች ጥቅሶች ተደርገው እንዲወሰዱ ስትወተውትና በሕዝቡ ልቦና ስታሰርጽ ኖራለች፡፡ የዚህም ውጤት “ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም” ወደሚል ትልቅ ክህደት አድርሷታል፡፡ (በዚህ ጉዳይ ላይ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ) ምናልባት ቤተክርስቲያኗ እንዲህ ብላ አታምንም፤ ይህ የታክሲ ላይ ጥቅስ ነው፤ ያልተማሩ ምእመናን ጥቅስ ነው፤ ወዘተርፈ ሊባል ይችላል፡፡ ቤተክርስቲያኗ ግን ይህን ስትቃወምና  እንዲህ አይባልም ስትል ግን አንድ ጊዜም አልተሰማችም፡፡ ዝምታዋ መስማማቷን ነው የሚያሳየው፡፡ የክርስቶስን የምልጃ ትምህርት ከላይ በተገለጸው መልኩ የሚያስተምሩት ልጆቿን ከአገልግሎት ለማገድና “መናፍቅ” “ተሀድሶ” የሚል የስድብ ስም ለማውጣት ግን የሚቀድማት የለም፡፡ ለዚህ ነው ቤተክርስቲያኗ ሐሰትን እያነገሠች እውነትን እየጨቆነች ትገኛለች የተባለው፡፡ ማን ነበር መወገዝ የነበረበት? ኢየሱስ ነው አዳኝ ያለ ወይስ ያለማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም የሚል?

አባቶቻችን ይህን ኑፋቄ ለምን አያወግዙም? ከዚህ ቀደም በዚሁ ድረገጽ ላይ እንዳነበብኩት ይህን ትምህርት በአደባባይ ያውም በጥምቀት በአል ላይ የተቃወሙት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ናቸው፡፡ በእውነት ሊመሰገኑ ሊደነቁ ይገባል፡፡ ሌሎቹስ ምነው ዝም አሉ? እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር በዚህ ትምህርት አያምኑም፡፡ ሲቃወሙትም አይታዩም፡፡ እርግጥ አይፈረድባቸውም፡፡ ደግሞ አንዱ ተነስቶ በተከበሩበት አገር እርስዎም መናፍቅ ሆኑ እንዴ ቢላቸውስ? ስለዚህ ትምህርቱን በልባቸው እየተቃወሙ በአፋቸው ግን ደግፈዋል፡፡ የብዙዎች አባቶቻችን ችግር ይኸው ነው፡፡ የሚያምኑት ሌላ የሚያስተምሩት ሌላ፡፡ የተጻፈው ሌላ ሕዝቡ የሚመራበት ሌላ፡፡ አንዳንድ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ከተጻፈው እያለፉ ያሻቸውን ኑፋቄ ሲዘሩና ሕዝብን ሲያሳስቱ ዝም ማለት ሰውን ደስ ለማሰኘት ካልሆነ በቀር እግዚአብሔር ግን ያዝናል፡፡ የዛሬዎቹ አባቶቻችን እንደሐዋርያት እግዚአብሔርን ሳይሆን ሰውን ለማስደስት የቆሙ ናቸው፡፡ የሚፈርዱት በተጻፈውና በሕገ ቤተክርስቲያን መሠረት ሳይሆን በሕዝብ ድጋፍ ነው፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያኗን የሐሰተኞች መፈንጫ አደረጓት፡፡ በእርግጥም ቤተክርስቲያኗ  እውነት የተጨቆናባት ሐሰት የነገሠባት ቤተክርስቲያን ናት፡፡      

ይህች ቤተክርስቲያን በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪና በረቀቀ ስልት የክርስቶስን አዳኝነት መቃወም ለምን አስፈለጋት? ቢባል የሚጠቀሱ ምክንያቶች ይኖራሉ፡፡ አንዱ ምክንያት ፕሮቴስታንቶችም የሚሉት እንደዚሁ ስለሆነ ከእነርሱ በትምህርት ለመለየት ነው፡፡ ሁለተኛውና ዋነው ምክንያት ግን በልዩ ልዩ መንገድ የክርስቶስን አዳኝነት የሚተኩ ሌሎች አዳኞች ሲሰበኩ ኖረዋልና እነዚህ አዳኞች በሕዝቡ ልብ ውስጥ ጠልቀው ስለገቡ ሊወጡ አይችሉም የሚል ፍራቻ ነው፡፡ ልክ ነው፡፡ በህዝቡ ሕይወት የሚንጸባረቀው ይኸው ክርስቶስን የተኩት የሌሎች አዳኞች  ትምህርት ነው፡፡ ብዙው ሰው በክርስቶስ በማመኑ እድናለሁ ብሎ አያስብም፡፡ እርሱ እድናለሁ ብሎ የሚያስበው ባንቀላፉ ቅዱሳን አማላጅነት ሲማጸን፣ በገድላትና በድርሳናት ስብከት መሰረት የታዘዘውን ሲፈጽም፣ ማለትም በቅዱሳን ስም ዝክር ሲዘክር፣ ገዳም ለገዳም ሲዞር፣ በበዓላቸው ቀን ስራ ፈቶ ሲውል ወዘተርፈ ነው፡፡ ክርሰቶስ አንድ ጊዜ በፈጸመውና አማራጭ በሌለው፣ ለዘለዓለምም በሚያገለግለው አዳኝነቱ ማመን ግን በራሱ ጥረት መዳን እንዳለበት ሲሰበክለት ለኖረ ሕዝብ ከባድ ነው፡፡ ይህን የኖረና በተለይ አፄ ዘርአ ያእቆብ ያስፋፋውንና ሃይማኖት ተደርጎ የተወሰደውን ልማድ ዛሬ ለማሻሻል ጊዜው ረፍዷል፡፡ ስለዚህ ይህን ልማድ ማደስ ስለማይቻል፣ አንዳንድ አባቶቻችን ባያምኑበትም ተስማምቶና ተከብሮ ለመኖር ሲሉ አለመቃወምና በዝምታ መደገፍ የመረጡት ስልት ሆኗል፡፡

ወንጌልን መስበክ በሰው ዘንድ ተቀባይነትን ያሳጣል የሚል አቋም ያላቸው አገልጋዮች፣ ለመኖር ሲሉ እውነተኛውን ወንጌል ሳይሆን በእነርሱ እምነት “የሚያበላውን” ልማዳዊ ትምህርት ማስተማርን ስራዬ ብለው ይዘዋል፡፡ ሕዝቡ እኮ በወንጌል የተገለጠው እውነት ቢገባው፣ ዛሬ ከሚያደርገው የበለጠ ያደርጋል፡፡ ታዲያ ምናለበት ሕዝቡ በቀራንዮ መስቀል ላይ የሞተለትን አዳኝ በትክክል እንዲያውቅ፣ እንዲያምነበትና እንዲድንበት ቢደረግ? ምናለበት እንደሞኝ ዘፈን ያንኑ ወንዝ የማያሻግር ተረት እየተረትን ከመዳን መንገድ ባናስወጣው?

ዛሬ ሃይማኖት የለሾች ቀሚስ ለብሰው በሚምነሸነሹበት አውደ ምሕረት ላይ እየታየ ያለው በዋናነት የክርስቶስን አዳኝነት የሚቃወም ክህደት ነው፡፡ ዘሪሁን ሙላቱ “ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት” በሚል ርእስ ለገበያ ባቀረበው ቪሲዲ ውስጥ በረቀቀ ስልት ያቀረበው ጥያቄና መልስ ሲፈተሽና ጀርባው ሲጠና “ኢየሱስ አያድንም” የሚል ነው፡፡ እርግጥ በፊት ለፊት እንዲህ አላለም፤ እንዲልም አይጠበቅም፡፡ ይህ የዝናውን መድረክ ለመቆጣጠርና ዝነኛ ሆኖ ለመውጣት እየታተረ ያለ ሰው በክርስቶስ ምልጃ ላይ ከተጻፈው በማለፍ፣ ትርጉም በማዛበትና መዛግብተ ቃላት ያላሰፈሯቸውንና ተሰምተው የማያውቁ የራሱን ተቀባይነት የሌላቸው ትርጉሞች በመስጠት ሕዝበ ክርስቲያኑን በማሳት ላይ ይገኛል፡፡ ለዛሬው በቪሲዲው ላይ አንድ የፕሮቴስታንት ቸርች አባል ስለሮሜ 8፡34 ላቀረበው ጥያቄ ሰጠሁ ያለውን በተግባር ሲታይ ግን ያልተመለሰውን ጥያቄና “ምላሹን” እንዳስሳለን፡፡

በቪሲዲው ውስጥ በመጀመሪያ የቀረበው ርእስ “የሚያፀድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኰንንስ…?” የሚል ነው፡፡ በዚህ ርእስ ስር ጠያቂው ሮሜ 8፡34ን ነው ያነበበው፡፡ አንብቦም በዚህ ክፍል “ስለእኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ይላል” ሲለው፣ ዘሪሁን ያቋርጠውና እዚሁ ላይ በመቆም ዳግም እንዲያነበውና እርሱ አቁም ሲለው በማቆም ምላሹን ከዚያው ከሮም 8፡34 እንደሚያገኘው ይነግረዋል፡፡ በዚሁ መሰረት “የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው” ሲል ያስቆመውና አጽዳቂ እግዚአብሔር መሆኑን መናገሩን ደግሞ ያስረግጣል። ከዚያ ጠያቂው “የሚኰንንስ ማነው?” ብሎ ሲያነብ አሁንም ያስቆመውና መልሱ እዚህ ጥያቄ ላይ እንዳለ ይናገራል - ዘሪሁን፡፡ የሚኰንንስ ማነው ብሎ አሁን “ኰናኙን ሊያመጣ ነው?” ካለ በኋላም ወደሌላ እንዳይሄድ በማገድ “የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” የሚለው ስለኰናኙ የተሰጠ መግለጫ ነው ይላል፡፡

ይህ ጥመት ካልሆነ በቀር ቃሉ ለማለት የፈለገው ይህን አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚል ነው ለዚህ ጥቅስ መነሻ የሆነው ሀይለ ቃል፡፡ ለዚህ መልሱ ማንም ሊከሳቸው አይችልም የሚል ነው፡፡ ከእግዚአብሔር በላይ ማንም ስለሌለ እግዚአብሔር ባጸደቃቸው ምእመናን ላይ ኰናኝ ሆኖ ሊነሣ የሚችል ማንም የለምና፡፡ ከሳሽ ቢኖርና እከሳቸዋለሁ ቢል እንኳን ክሱን ውድቅ የሚያደርግና እግዚአብሔር በልጁ ሞት ስላጸደቃቸው ሰዎች የሚከራከር አማላጅ ኢየሱስ አለና በእርሱ መካከለኛነት ታርቀው መዳናቸውን ያውጅላቸዋል፤ ክሱም ውድቅ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ጥቅሱ እግዚአብሔር ካጸደቀ ማንም ሊኰንን አይችልም የሚል መልእክት አለው እንጂ ስለኢየሱስ ፈራጅነት ለመናገር እንደመንደርደሪያ የገባ ሐሳብ አይደለም፡፡ በዚህ ክፍል የሚኰንነው ኢየሱስ ነው ተብሎም በፍጹም አልተነገረም፡፡ ግእዙም (“ይትዋቀሥ በእንቲአነ”) ቢሆን መከራከርን እንጂ መፍረድን አያሳይም፡፡

ይሁን እንጂ ዘሪሁን ግእዙም ይፈርዳል ነው የሚለው በማለት የአባቶቹን ስሕተት ደግሟል፡፡ በዚህ ቢያበቃ ግን መልካም በሆነ ነበር፡፡ እርሱ ግን ጠያቂ የለብኝም ውሸትን እስከፈለኩት ድረስ መለጠጥ እችላለሁ በሚል ክፋት “ማለደ ማለት ፈረደ ነው” ሲል በየትኛውም መዝገበ ቃላት ተመዝግቦ ያልተገኘ፣ በቋንቋችን ውስጥ ጥቅም ላይ ውሎ የማያውቅና ለመጀመሪያ ጊዜ ከእርሱ አንደበት የተሰማ ፍቺ ከኪሱ አውጥቶ ተናግሯል፡፡

ዘሪሁን “ማለደ ማለትና አማለደ ማለት ይለያያል ማለደ ማለት ፈረደ ማለት ነው” ብሏል፡፡ በቋንቋችን ስርአት “ማለደ” አድራጊ ግስ ነው፡፡ “አማለደ” ደግሞ አደራራጊ ግስ ነው፡፡ ማለደ አንድ ግለሰቡ በራሱ የሚያደርገው ተግባር ነው፡፡ “አማለደ” ደግሞ በሁለት ወገኖች መካከል ገብቶ ሁለቱ እንዲገናኙ አደረገ ማለት ነው፡፡ ይህ ሁለቱን ግሶች በቀጥታ ስንተረጉማቸው የምናገኘው ፍቺ ነው፡፡ ሁለቱ ግሶች በሰው አእምሮ ውስጥ በተለይም ከአማላጅነት ትምህርት ጋር በተገናኘ የሚሰጡት ፍቺ ግን ከሰው ሰው ሊለያይ ይችላል፡፡ ወይም ሁለቱንም አንድ አድርጎ የመመልከት ነገር ይኖራል፡፡ ነገር ግን ዘሪሁን እንዴት አድርጎ ቢያነበውና ቢረዳው ይሆን ማለደን ፈረደ ብሎ የፈታው?

ከዚህ አባዜው መውጣት ያልፈለገው ዘሪሁን ስለመንፈስ ቅዱስ ምልጃ ሮሜ 8፡26 የተጻፈውንም በተመሳሳይ መንገድ ነው የተረጎመው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል በሚለው ጥቅስ ውስጥ “ይማልድልናል” የሚለው ከሮሜ 8፡34 ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ከሁሉም የሚገርመው ግን እንደዘሪሁን ያሉ አንዳንዶች ተደናግረው የሚያደናግሩበትን ኤር 7፥25ን መጥቀሱና በዚህ ጥቅስ መሠረት እግዚአብሔር “እየማለድሁ” ያለውን “እየፈረድሁ” ማለቱ ነው ሲል መናገሩ ዘሪሁን ራሱን ትዝብት ላይ ከመጣሉም ባሻገር ፍጹም ጥመት እንዳለበትም አሳይቷል፡፡ ትንቢተ ኤርምያስ እንዲህ ነው የሚለው “አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ በየዕለቱ እየማለድሁ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር። ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።” እዚህ ላይ እየማለድሁ የሚለው ልመና ከሆነው ከምልጃም ሆነ ከፍርድ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ቃሉ በጠዋት መነሣትን በእግዚአብሔር አነጋገር ደግሞ ከጥንት ከመጀመሪያ አንስቶ መናገሩን ነው የሚያሳየው፡፡ በአማርኛችን ማለደ በጠዋት ተነሳ፣ ማለደ ለመነም ይሆናልና ቃሉ አሻሚነት ሊኖረው ቢችልም በዚህ ጥቅስ መሠረት መለመንን ሳይሆን በጠዋት መነሳትን ለማመልከት ነው የገባው፡፡ እንግሊዝኛው የሚለውን ብንመለከት ደግሞ ግልጽ ይሆንልናል። “Since the day that your fathers came forth out of the land of Egypt unto this day I have even sent unto you all my servants the prophets, daily rising up early and sending them” ግእዙም ቢሆን ተመሳሳይ ሐሳብ ነው ያለው፡፡ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልእ 36፡15 ላይ የተጻፈው ቃልም አንድ አይነት ሲሆን “እየማለድሁ” የሚለውን ቃል በማያሻማ መንገድ “ማለዳ ተነሥቶ” በማለት ግልጽ አድርጎታል፡፡ “የአባቶቻቸውም አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ስላዘነ ማለዳ ተነሥቶ በመልእክተኞቹ እጅ ወደ እነርሱ ይልክ ነበር።” መቼም ዘሪሁን የአማርኛው ትርጉም ሳይገባው፣ እንግሊዝኛውንም ሳያየው፣ የግእዙንም ትርጉም ሳያስተውለው አልቀረም፡፡ ነገር ግን የእርሱ አላማ የእግዚአብሔርን ቃል ማጣመምና ምእመናን ከልማድ ሳይወጡ እርሱና መሰሎቹ ያሏቸውን ሁሉ እየፈጸሙ የእግዚአብሔርን እውነት ሳያስተውሉ በዚሁ ጨለማ ትምህርት ውስጥ እንዲኖሩ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ተሳክቶለት ሊሆን ይችላል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ለሚቀር ጥቅምና ዝና ሲል ማጣመሙና ሕዝብን ማሳቱ ግን ታላቅ በደል ነው፡፡

ምእመናን ሆይ እናንተ ግን በዘሪሁን ስሕተት ሳትወሰዱ የጴጥሮስን የምክር ቃል ልብ ብላችሁ ስሙ እንዲህ የሚለውን፦ “በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ። እንግዲህ እናንተ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ፥ በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።” (2ኛ ጴጥሮስ 2፡16)

ይቀጥላል

ጸጋ ታደለ


75 comments:

 1. ጸጋ ታደለ መቼም የአንተና የዘሪሁን ፍቅር መቼም ቢሆን መቋጫ የለውም ፡፡ ጠፍተህ ነበር ፤ አሁን ብቅ ሲል ደግሞ እንደገና ተነሳህበት ማለት ነው ፡፡ ሙሉ ይሁን ጐደሎ አላውቅም ፣ በኢንተርኔት የተለቀቀውን ጥያቄና መልስ ተመልክቼ ፣ በአቀራረቡ ቅር የተሰኘሁበትን ምክንያት ለማስነበብ ሞክሬአለሁ ፤ ይድረሰው አይድረሰው አላውቅም ፡፡ ያው ቀለም ያቀለማችሁ ሰዎች እናሻሽል ስትሉ መሰለኝ ስህተትን የምትፈጽሙት /አባታችን እንዳቆጡ ብዙ አልልም/፤ ከሰዎች ለየት ያለ ለማድረግ ሲሞከር ፣ ነገሩ ፍልስፍና ይሆንና ፈር ይለቃል ፡፡ አንተም ያቀረብከው የማረሚያ አስተያየት ቢሆን ትክክል አይደለም ፡፡ ይኸው ጉዳይ ከዚህ ቀደም ተነስቶ ፣ በዚሁ ድረ ገጽ ብዙ ተባብለንበት ዘግተነው ነበር ፡፡ ሁሉንም ከምታፈራርስብን ስህተቱን ብቻ ለይተህ ብትጠቁመን ያስተምረን ነበር ፡፡ አለመታደል ሆኖ መማማርን አናውቅም ፡፡ ለማንኛውም በመንፈስህ እንኳን ደህና መጣህ ፡፡

  አሁን ወደ ዋናው ጉዳያችን
  ጽሁፉ ከሞላ ጐደል የተወሰደው http://www.abaselama.org/2012/03/4-read-pdf.html#more ከሚል መክፈቻ ነው ፡፡

  የሰው ልጅ አፈጣጠሩ እንደ ንጉሥ ቧለሟል ሆኖ ሁሉን እየተቆጣጠረና እያስተዳደረ ፣ ከአንዲት የዛፍ ፍሬ ከመብላት በስተቀር ፣ በሁሉም እንዲገለገልበት ተፈቅዶለት ነበር ፡፡ የፈጣሪን ዝግጅትና አደረጃጀት /አየሩ ፣ ውሃው ፣ ምግቡ ፣ ብርሃኑ ፣ ሙቀቱ ፣ ቅዝቃዜው ፣ ጸጋ ክፋኑ…./ ስናስብ እግዚአብጤር አዳምን /እኛን ይጨምራል/ ምን ያህል እንደወደደው ፣ ምን ያህል እንዳፈቀረው እንረዳለን ፡፡ ከሌሎች ፍጥረታቱ ለይቶ አዳምን በአርአያውና አምሳሉ ፈጥሮ ፣ የማትሞት ነፍስን መስጠቱም ሌላው የፍቅሩ መገለጫ ነው ፡፡ ይኸም ማለት ይወድና ያፈቅር የነበረው ገና ሳይፈጥረው ፣ ወደ እዚህ ምድር ሳያመጣው አስቀድሞ ነበር ያሰኛል ፡፡ እንደ አሁኑ ዘመነኛ ወላጆች ፣ ያልተወለደ ህጻን ልጃቸውን ለመቀበል በናፍቆት እንደሚዘጋጁት አልጋና ልብስ መግዛት ፣ ጡጦ ፣ ሳሙና ማሰናዳትና የመጨነቅ ዓይነት ማለት ፡፡

  እግዚአብሔር አዳምን ኃጢአት ከመሥራቱ በፊት ወዶት ነበር ብለንም አናበቃም ፡፡ ይልቁንም ይኸ ፍቅሩ አዳም አምላኩን ከበደለ በኋላም አልተለወጠም ፤ አልጠፋም ፤ እንዲያውም ይበልጥ ጠነከረ ፤ ይበልጥም ተገለጠ እንጂ እንላለን ፡፡ እግዚአብሔር ሰው አይደለምና ባህርዩን አይቀያይርም ፤ ቃሉንም አያጥፍም ፤ ዕቅዱንም አይሰርዝም ፡፡ እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ያለው ለዘለዓለም ቋሚ ነው ፡፡ ብርሃን ይሁን አለ ፣ እስከ ዛሬ ብርሃን አለ ፤ ፀሃይና ጨረቃም በብርሃን እነዲሠለጥኑ ታዘዘ ፣ ይኸው በቀንና በለሊት ሥርዓትን ሳያዛንፉ ይገኛሉ ፡፡ ስለዚህ ሰውን የወደደበትም ፍቅርም ዘለዓለማዊ ነው ፡፡ ለማዳንና እራሱን ፣ በራሱ በኩል ሊያስታርቅ በመፍቀዱ ፣ የፈጠረውን ሥጋ በአንድያ ልጁ ፣ በወልድ በኩል እስከመዋሃድ ደረሰ ፡፡

  ወልድም መንበሩን ትቶ በኃጢአት ወደ ረከሰው ሰው ሲመጣ አልተጠየፈም ፤ ይልቁንም መዋረዱን ተቀብሎ ርግማናችንን ርግማኑ ፣ ሞታችንንም በሞቱ አድርጐ ነጻ ሊያወጣን ፈቀደ ፡፡ ከዛም ሁሉን ሲያጠናቅቅ የተዋሃደውን ሥጋ ሳይተው ወደ ጥንት መንበሩ አረገ ፤ የኃጢአተኛው የአዳም /ባትወዱትም የድንግል ማርያም/ ሥጋም ፣ በወደደን በኢየሱስ በኩል ከበረ ፡፡ ለንጉሥ ባለሟልነት የተፈጠረው አዳም በወልድ በኩል ሆኖ ፣ ይበልጥ ማዕረግን ወይም ክብርን አገኘ እንላለን እንጅ ሥጋችንን ተዋህዶ ሰለሄደ ያማልዳል አንልም ፡፡

  ይህ ስጋችንን ተዋህዶ አርጓልና ያማልዳል ማለት የስድብ ቃል ነው ፡፡ ስለምን ቢሉ ፣ አምላክነቱን ሽሮ ወደ ሰውነቱ መልሶ አሁን ተኝቷል ፣ አሁን ደክሞታል ፣ ውሃ ይጠማዋል ፣ ምሳ አምጥተንልሃል ለማለት ስለሚያስደፍር ፤ አምላክነቱን ክዶ ፍጹም በሰውነቱ ባህርይ ማኖር ስለሚሆን ፡፡ ስለዚህም ስጋችንን በመዋሃዱ አከበረን ብቻ እንበል ፡፡ እርቅና አማላጅነቱን እስከ መስቀለ ሞቱ ድረስ ተጉዞ ፈጸመ ፡፡ ከፈጠረው ሥጋ ፣ ያልተፈጠረው አምላክ መዋሃድ ያስፈለገውም ፣ መስዋዕት በመሆን ካሳችንን ከፍሎ ፣ በአዳም ላይ ተጥሎ የነበረውን ፍርድን ፈጽሞ ሊያስታርቀን ነው እንጅ ፣ ዛሬም እንደ ቀደመው በሥጋው ሊወጣበትና ሊወርድበት ፣ ሊገለገልበት እና ሊያማልድበት አይደለም ፡፡ አንድ ጊዜ የተከፈለው መስዋዕት ፣ እንደ ፍየልና በግ ስላልሆነ ለዘለዓለም ያገለግላል ፡፡ ስለዚህም አንድ ጊዜ ያፈሰሰው ደሙ ፣ ዛሬም ካረገው ሥጋው ስለሚፈስ ፣ አዲስ አምነው ለሚጠመቁት የአማላጅነት ግልጋሎቱን ይሰጣል እንጅ ፣ እኛ አምነን የተጠመቅነውን መልሶ መላልሶ ያማልደናል አይባልም /ልዩነታችን እዚህ ላይ ይመስለኛል/ ፡፡

  ክርስቶስ ሞታችንን ሞቶ ፣ የጸጋ ልጅነታችንን ካስመለሰልን በኋላ እንደ ቀድሞው የነፍሳት ወደ ሲዖል መጋዝ ቀርቷል ሮሜ 5፡11 መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን ይለዋልና ። ክርስቶስ ወዶና ፈቅዶ ራሱን በማዋረዱ ፣ ተዋርደንና ተጥለን የነበርን እኛ ከንቱዎቹ ከብረናል+ ፡፡ ስለዚህ ስለዳንንበት ፣ ስለታረቅንበት ኢየሱስን አምነን ማመስገን ይገባናል ፤ በኢየሱስ ማዳን እንመካ ፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስንም ስለ ማዳን ኀብረታቸው ፣ ጥበባቸውና አሠራራቸው እናወድስ፡፡
  ይቆየን
  ክፍል ሁለት ይቀጥላል

  ReplyDelete
  Replies
  1. ay orthodox mistirish sitim:: endet menfes yarakal!
   Long live orthodox theology!

   Delete
  2. የፀጋ ትምህርት ከየትኛው ቤተ እምነት የመጣ ነው ? ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ግን አይደለም።

   Delete
  3. Aba markose is the one who support THEDSO
   So we never accept his preach

   Delete
 2. ክፍል ሁለት

  ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ 2 ፡ 4-5 ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥
  በቁጥር 8 ደግሞ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤

  13-17 አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤

  ከዚህም ቃል በመነሳት ካሳው ተከፍሎልን ድናችኋል ፣ ቀርባችኋል ፣ የጥል ግድግዳ ፈርሷል ፣ ጥልንም በመስቀሉ ገድሏል ስለተባለ የአስታራቂነት ሥራው ተፈጽሟል ይባላል እንጅ ዛሬም ያማልዳል አይባልም ፡፡ አንድ ጊዜ የተፈጸመው መስዋዕትነት የአዳም ዘር ለሆንነው በሙሉ ህያው ሆኖ ስለሚያገለግለን ዕብ 7፡25 ማለት ተቻለ ፡፡

  ለመዳንና የተገኘውን የማስታረቅ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን ፣ አምኖ መጠመቅ ያስፈልጋል ፤ በጅምላ መዳን ፣ በጅምላም መታረቅ የሚባል ነገር አይኖርም ፡፡ አምላካችን ሰው ሆኖ ስለእኛ ሞተልን ፣ እንደገናም በራሱ ሥልጣን ሞትን ድል አድርጐት ተነሣ ፤ አረገ ፤ በአባቱም ቀኝም ተቀመጠ ፤ ወደፊትም በሥልጣን ሆኖ ለመፍረድ ዳግም ይመጣል ፤ ብለን አምነን ከተጠመቅን በኋላ ግን አዲሱን የጸጋ ልጅነታችንን ስለምንቀዳጅ /ዳግም ስለምንወለድ/ ፣ አስቀድሞ የነበረብን ማንኛውም በዕውቀት ሆነ በስህተት የተፈጸመ ወይም ከአዳም በውርስ የተገኘ ኃጢአት /በግብርና በውርስ ማለት/ በሙሉ ይሻራል ወይም ይደመሰሳል ፡፡
  ስለዚህም አምነን በመጠመቃችን በክርስቶስ አስታራቂነት ይቅርታን አገኘን እንላለን ፡፡ አንድ ጊዜ ካስታረቀንና ድናችኋል ብሎ የምስራቹን ከአበሠረን ፣ ልጅነትንም ካገኘን በኋላ ሌላ አዲስ እርቅ እንደገና አንጠብቅም ፤ ሌላ ምልጃም ዳግም አይፈጸምም ፡፡

  ከተጠመቅን በኋላ በድክመት የምንፈጽመውን በደል በሙሉ ንስሐ በመግባትና የቤተ ክርስቲያን ቀኖና የሚያዘውን የጾም ፣ የስግደት ወይም ሌላ የንስሐ ማጠንከሪያና የማስተማርያ ቅጣት በመፈጸም ይቅርታን እናገኛለን ፡፡ በጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተገኘው እርቅ ፣ ምልጃና መዳን ፣ ያላመኑና ያልተጠመቁትን የአዳም ልጆች አይመለከትም ፡፡ አንድ ጊዜ የተፈጸመው አማላጅነት ዘለዓለማዊ ስለሆነ ፣ ወደፊት አምነው በመጠመቅ በክርስቶስ በኩል ዳግም ልጅነትን ሊያገኙ ዕድሉ አላቸው ፤ የታዘዘውን የአዲስ ኪዳን ሥርዓት ፈጽመው ዳግም ልጅነትን ሲያገኙ ፣ ከእኛው ጋር አንድ ወገን ይሆናሉ ፡፡

  በኢየሱስ በኩል እርቅና ምልጃ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት አዳም በአምላክ የተሰጠውን ትእዛዝ በመተላለፍ ፈጣሪውን በመበደሉና ዘለዓለማዊ ሞትን ስላመጣ ብቻ ነው ፡፡ ብዙ ጻድቃን ፣ ብዙ ነቢያት ተነሱ ፤ እምነታቸውን በእግዚአብሔር ጥለው ፣ ምግባራቸውንም አስተካከለው ጻድቅ ተባሉበት ፣ ሞገስን ተቀበሉበት እንጅ ያን በደል ደምስሰው እርቅ ሊፈጥሩ ፣ ክብርና ጸጋን ሊመልሱ ፣ ዘለዓለማዊ ሞትንም ሊያስታግሱ አልቻሉም ፡፡ ሌላውም የሰው መንገድና ብልሃት በሙሉ / ከአምላክ ፈቃድና ፍላጐት ውጭ ቢሆንም ልጆቻቸውን እስከ መሰዋት ደረሱበት/ ምንም መፍትሄ ስላላስገኘ ፣ የሚወደን አምላካችን ራሱን ከእኛ ስጋ አዋህዶ ፣ ዕዳችንን ለመክፈል ፣ ሞትን በሞት ድል ለማድረግና እኛን ለማዳን ወደ እዚህ ዓለም መጣ ፡፡

  ይህም ማለት ሊያድነን ያስፈለገው የአዳም በደል ካመጣው ዘለዓለማዊ የሞት ፍርድ እንጅ ከሌላው ድክመትና ኃጢአት አይደለም ፡፡ ከሌላው ስንፍናና ድክመት ሰዎች /ሄኖክ ፣ አብርሃም ፣ ሙሴ ፣ ኤልያስ …/ በጽናት ቆመው በራሳቸው የአምልኮ ትግል ከሌሎች የተሻለ ቅድስናንና ሞገስን አግኝተዋልና ፡፡ ስለዚህም ምክንያት ራሱን መስዋዕት በማድረግ ማንም ሊሽረው ያልቻለውን ፍርድ ፣ ለመደምሰስ ሲል በመስቀል ላይ ነፍሱን ሰጥቶ ዕርቅን ፈጸመልን ብለን እንመሰክራለን ፡፡ ያ ዕርቅ ከተፈጸመ ፣ ካሳውም ከተከፈለ በኋላ ፣ የሰው ልጅ ወደ ጥንት ክብሩ የመመለሱ ነገር ተረጋግጧልና ሌላ የአማላጅነት ሥራ ቀርቶታል ማለት አይቻልም ፡፡

  በ 2 ቆሮ 5 ፡16-20 ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው ፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃልን አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን /እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን/፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን /ስለ ክርስቶስ እንለምናለን/ በማለት ገልጿል ። ሐዋርያው በዚህ ባስተላለፈው ቃል ሁሉም የማዳንና የማስታረቅ ሥራ ተከናውኖ እንዳበቃ የሚያስረዳ ነው ፡፡ ኢየሱስ ዋናውን መንገድ ከፍቶልን ስለሄደ ፣ ቀጣዩ ሥራ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት /ጥምቀት ፣ ንስሐ .... / ሆኗል ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. wow, good job brother. But who r u?

   Delete
  2. "የእሱ ደቀ መዛሙርት ከመሆን ሌላ ሌላ መጠሪያ የማያስፈልጋችሁ ናችሁ።"
   አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ካስተማሩን የተወሰደ ነው ፡፡

   Delete
  3. `የእሱ ደቀ መዛሙርት ከመሆን ሌላ ሌላ መጠሪያ የማያስፈልጋችሁ ናችሁ።`
   አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ከተናገሩት የተወሰደ

   ስለዚህ ደቀመዝሙሩ በለኝ

   Delete
  4. hank you dear, you redeemed me. Endet bisil temihrit new:: I am really happy reading it and convenienced by this explanation, and I have been wrongly following the protestants, which I condemn now. I will learn the orthodox theology!

   Delete
  5. እባክህ ወንድሜ ጌታ ኢየሱስ የሞተው ከአዳም የሚተላለፈውን የውርስ ኃጢያት ብቻ ለመደምስስ ሳይሆን ከሁሉም ኃጢያት ሊያነጻን ነው፡፡ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነጻል ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ እለት እለት የምንበድለውም በደል የሚነጻው ለአንዴና ለሁልጊዜ በሚያገለግለው በጌታ በኢየሱስ መስዋዕት ነው፡፡ እርሱ መስዋዕታችን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ሌላ መስዋዕት ይዘን አንቀርብም፡፡ ይህንንም የምናደርገው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ነው፡፡ ለሁላችንም መንፈስ ቅዱስ ይህንን ታላቅ ፍቅር እንድንረዳው ያግዘን፡፡

   Delete
  6. Someone who hates theological debates from the heartJune 25, 2012 at 3:36 AM

   According to your logic, because we are already saved by Jesus we don't need the sacrifice of His Body and blood. Your premises derive a conclusion that says, "after being baptized we can be acquitted from our sins by our own works." That means we don't need the Holy Eucharist, the Body and Blood of Our Lord Jesus Christ, to be cleansed from our sin.

   If that is so, then what is the point of holding mass every day in the Church? What is the sacrifice for (if not for our sins)? If we agree that the works of mount Calvary are eternal for the remission of our sins, then comes the question "Don't we sin after baptism?" Don't we get back to our evil ways after baptism? If we answer this question negatively saying No, then the dialogue ends there for we are already in heaven where No sin can be thought of. But are we there? Are we in that non-sinning state of being? Don't we finish our days in filthy ways? Do we live as we are supposed to live as Christians: Looking like Christ? I really doubt, brother.

   Who then shall redeem us? I hope you will not dare to say Ourselves. By the way, how would you explain the words in the Book of Seatat "ሊቀ ካህናት ዘይቀውም ሎሙ ለቅዱሳን በደብተራ ስምዕ እንተ እግዚአብሔር ተከላ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ?" How about all the prayers of Litany "ሊጦን" "መስተብቁዕ" "ኪዳን" which closes with "በአሐዱ ወልድከ እግዚእነ ኢየሱስ"? If you look at the hermeneutics of the Ethiopian church you will find "በፍቁር ወልድከ፣ በቅንው ወልድከ" ብለን ብንለምነው ይሰማናል፡፡" Glory be to His Holy name, his intercession doesn't have any other equivalent or substitute. It is indispensable if we are to be saved.

   We need all the saints for we they are part of His one Holy family:Holy Catholic Apostolic Church. To learn from them. They are witnesses that Christianity is not something too ideal and impossible but a possible and redemptive way of life that we learn from our Lord. We need them to help our souls in our pilgrimage on our only way and our only end: Jesus Christ. May Glory be to His Holy Name.

   Delete
  7. Someone who hates theological debates from the heartJune 25, 2012 at 3:37 AM

   According to your logic, because we are already saved by Jesus we don't need the sacrifice of His Body and blood. Your premises derive a conclusion that says, "after being baptized we can be acquitted from our sins by our own works." That means we don't need the Holy Eucharist, the Body and Blood of Our Lord Jesus Christ, to be cleansed from our sin.

   If that is so, then what is the point of holding mass every day in the Church? What is the sacrifice for (if not for our sins)? If we agree that the works of mount Calvary are eternal for the remission of our sins, then comes the question "Don't we sin after baptism?" Don't we get back to our evil ways after baptism? If we answer this question negatively saying No, then the dialogue ends there for we are already in heaven where No sin can be thought of. But are we there? Are we in that non-sinning state of being? Don't we finish our days in filthy ways? Do we live as we are supposed to live as Christians: Looking like Christ? I really doubt, brother.

   Who then shall redeem us? I hope you will not dare to say Ourselves. By the way, how would you explain the words in the Book of Seatat "ሊቀ ካህናት ዘይቀውም ሎሙ ለቅዱሳን በደብተራ ስምዕ እንተ እግዚአብሔር ተከላ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ?" How about all the prayers of Litany "ሊጦን" "መስተብቁዕ" "ኪዳን" which closes with "በአሐዱ ወልድከ እግዚእነ ኢየሱስ"? If you look at the hermeneutics of the Ethiopian church you will find "በፍቁር ወልድከ፣ በቅንው ወልድከ" ብለን ብንለምነው ይሰማናል፡፡" Glory be to His Holy name, his intercession doesn't have any other equivalent or substitute. It is indispensable if we are to be saved.

   We need all the saints for we they are part of His one Holy family:Holy Catholic Apostolic Church. To learn from them. They are witnesses that Christianity is not something too ideal and impossible but a possible and redemptive way of life that we learn from our Lord. We need them to help our souls in our pilgrimage on our only way and our only end: Jesus Christ. May Glory be to His Holy Name.

   Delete
  8. you seem blindly commenting. The writer didn't argue as you say in the first lines of your argument. Please, re-read and understand the writers article line by line.

   Delete
  9. Someone who hates theological debates from the hear የሚለውን ለጻፍክ ወገን

   የቋንቋ ግርዶሽ እንቅፋት ካልሆነብን በስተቀር ፣ ስለ ተጠመቅን የክርስትና እምነት ጉዞአችንን ደምድመናል የሚል ቃል አልጻፍኩም ፡፡ ቢያንስ ንስሐ የሚል ቃልም አስከትያለሁ ፡፡ ክርስትና ደግሞ ጉዞ ነው ፤ ጥምቀት የዚሁ ጉዞ መጀመሪያችን እንጅ መደምደሚያችን አይደለም ፡፡

   ክርስቲያን ለመሆን በተቀዳሚ የሚያስፈልገው በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማመን ነው ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሰው እንደሆነ ፣ በመስቀል ላይ ስለ ኃጢአታችን እንደሞተልን ፣ ሞትንም ድል አድርጎ እንደተነሳና እንዳረገ ፣ በአባቱ ቀኝ እንደተቀመጠ ፣ ዳግም ለመፍረድም በሥልጣንና በክብር እንደሚመጣ መስክረን /ለመመስከር ብቃት ካለን ማለት/ በመጠመቅ /ለአንተ እንደሞተ ማመንህን ልብ በልልኝ/
   1 - የእግዚአብሔር የጸጋ ልጅነትን እናገኛለን ፣ ከክርስቶስ ጋር አንድነትንም እንመሠርታለን
   2 - ከአዳም የውርስ ኃጢአት ነጻ እንሆናለን
   3 - እስከ ተጠመቅንበት ዕለት /አጽንዖት/ ድረስ በዕውቀት ወይም በስህተት የፈጸምነው በደል በሙሉ ይደመሰስልናል ፡፡ እነዚህን የመጀመሪያ ግኝቶች ይዘን ፣ ራሳችንን ማነጽ እንቀጥላለን ፡፡

   ”ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ (አጽንዖት) ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።” ሮሜ 6:3-4

   ከላይ የጀመርነውን የመዳን መንገድ ይበልጥ ለማጽናት ፣ ሞቱን ለማሰብና ምሥክር ለመሆን ፣ ከክርስቶስ ጋር አንድነት ለመፍጠርምና ዘላለማዊ ህይወትን ለመውረስ ፣ ተአማኒ የሆነ ሥጋና ደሙን በማስከተል እንቀበላለን ፡፡ የመጀመሪያ አማኝ ከሆነ አንዱ ከሌላው /ጥምቀትና ቁርባን/ አይነጣጠሉም ፡፡ ጥምቀቱ እንደተፈጸመ የቁርባን ሥርዓቱ ይከተላል ፡፡ ይኸም በመጀመሪያው ቀን ብቻ የሚሆነው ጥምቀት አንዲት ብቻ ስለሆነች ነው ፡፡

   “ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።” 1 ቆሮ 11:26 ፤ (ምስክርነትን ይገልጻል)
   “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።” ዮሐ 6:53-56 እንዲል መጽሐፍ ፡፡ /የተሰጠንን ተስፋ ልብ ይሏል/

   ይህም ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ መሞቱን ፣ በሥጋና በደሙ መዳናችንን ይበልጥ እናጠነክራለን ፤ ሳናፍር በጽናት ቆመን እንመሰክራለን ፡፡ ስለዛም ቤተ ክርስቲያናችን ፣ አንድ ሰውን አጥምቃ ስታበቃ ፣ ቅዱስ ቁርባኑን በዚያው ዕለት ታስከትላለች ፡፡ ይህም በመሆኑ ሥርዓተ ጥምቀትና ቁርባን አብረው የሚፈጸሙ የቤተ ክርስቲያን ምሥጢር ናቸውና ስርየተ ኃጢአትን እንቀበላለን ፣ ዘላለማዊ ሕይወትን እንወርሳለን ፣ ለመንግሥተ ሰማያት ኗሪነትም እንበቃለን እንላለን ፡፡

   በሥርዓተ ቅዳሴው ካህኑ የሚያውጀው “ንጹሕ የሆነ ከቁርባኑ ይቀበል ፤ ንጹሕ ያልሆነ ግን አይቀበል ፤ ለሰይጣንና ለሰራዊቱ በተዘጋጀው እሳተ ገሃነም እንዳይቃጠል ፡፡ በልቡናው ቂምን የያዘ ፣ ልዩ ሐሳብና ዝሙትም ያለበት ቢሆን አይቅረብ” የሚለው ንስሐ ሳይገቡና ሳይናዘዙ አይቀበሉ ማለት ነውና ፣ ከኃጢአት ለመንጻት በማለት ከነበደል ሁኖ ሥጋና ደሙን መቀበል በራሱ ሌላ ቅጣትን ያመጣልና በዚህ መንገድ ካለህ አሁኑኑ በንስሐ ተመለስ ፡፡ ዛሬ ስላስነበብኩህ ዳግመኛም በድፍረት ሆነህ ከመሳሳት ተቆጠብ ፡፡

   ይህንንም ሁሉ ከፈጸምን በኋላ ቢሆን ፣ መቸም የሰው የመሸነፍ ባህርይ ይዞን ድክመትን ከፈጸምን በንስሐ ቀርበን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመፈጸም እንታደሳለን እንጅ ሥጋውን በመብላትና ደሙን በየሳምንቱ በመጠጣታችን የኃጢአት ሥርየትን አናገኝም ፡፡ ይልቁንም ለመቁረብ /ሥጋና ደሙን ለመቀበል/ ቀደም እንደገለጽኩት ራሳችንን መጀመሪያ ንጹህ ማድረግ ስለሚገባን ፣ ወደ አባቶች ቀርበን በምንገባው ንስሐና በሚሰጠን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ራሳችንን ስለምናጸዳ ፤ የበደል ሥርየቱ የሚፈጸመው ከመቁረባችን በፊት ነው ፤ ነገር ግን ያገኘነውን ዕድል በቁርባን እናጠናክረዋለን እላለሁ ፡፡ አንድ ሰው ከቆረበ በኋላ ፣ ለጌታ ስለተሰጠ ሃይማኖቱን መደበቅ አይገባውም ፤ ለወገን መመስከር ፣ ሌሎች እንዲድኑ የሚያውቀውን ያህል ማስተማር ይጠበቅበታል ፡፡

   እነዚህንም የሃሳቤ ማጠናከሪያ ይሆኑን ዘንድ ደምርልኝ
   - እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥ ሮሜ 3:25
   - ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን። ሮሜ 5:9
   - በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ኤፌ 1:7
   - ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ ራእይ 1: 5

   እነዚህ ኃይለ ቃሎች በሙሉ የሚናገሩት የኃጢአት ሥርየት የተገኘው በመስቀል ላይ በፈሰሰ ደሙ እንጅ እኔና አንተ በምንቀበለው ሥጋና ደሙ አይደለም ፡፡ ደሙ የፈሰሰው ስለ እኔ ድኀነት ነው ብሎ ማመን /መቀበል አላልኩም/ የኃጢአት ይቅርታን ያስገኛል ፤ እኛ እምነታችንን ለማጠንከርና ምስክሩ ለመሆን ሥርዓተ ቁርባንን እንፈጽማለን ፡፡ እሱ ግን እንዲያ ሲያገኘን ከሙታን መሃል ያስነሳናል ፣ ዘላለማዊ ህይወትንም ይሰጠናል ፤ በዚህ መንገድ ነው ቁርባንን የምረዳው ፡፡

   Delete
  10. ለባለዚህ አስተያየት ፡-
   “እባክህ ወንድሜ ጌታ ኢየሱስ የሞተው ከአዳም የሚተላለፈውን የውርስ ኃጢያት ብቻ ለመደምስስ ሳይሆን ከሁሉም ኃጢያት ሊያነጻን ነው፡፡ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነጻል ተብሎ እንደተጻፈ፡፡ እለት እለት የምንበድለውም በደል የሚነጻው ለአንዴና ለሁልጊዜ በሚያገለግለው በጌታ በኢየሱስ መስዋዕት ነው፡፡ እርሱ መስዋዕታችን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ሌላ መስዋዕት ይዘን አንቀርብም፡፡ ይህንንም የምናደርገው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ነው፡፡ ለሁላችንም መንፈስ ቅዱስ ይህንን ታላቅ ፍቅር እንድንረዳው ያግዘን፡፡”

   በእርግጥም እንዳልከው ጌታ ኢየሱስ የሞተው ከአዳም የሚተላለፈውን የውርሰ ኃጢአት ብቻ ለመደምሰስ አይደለም ፡፡ ይኸን እኛም እናምናለን ፡፡ ልዩነታችን ግን በምንገለገልበት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ነው ፡፡

   እኛ አምነን ስንጠመቅ ወዲያውኑ ያለ የሌለ ኃጢአታችን /ከአዳም የወረስነውም ሆነ በድፍረት አውቀን ፣ ወይም ባለማስተዋል በስህተት የፈጸምነው በደል ሁሉ/ ይደመሰስልናል እንላለን ፡፡ ይህን የመጀመሪያ ጸጋ ከተጐናጸፍን በኋላ በቀጣይ ለምንወድቅበት በደል ደግሞ ፣ ንስሐ በመግባት ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የሚያዘንን ፣ ጸሎት ፣ ጾም ፣ ስግደት ወይም ሌላ ማስተማሪያ ቅጣት በመፈጸም እንታደሳለን እንላለን ፡፡ ለቤተ ክርስቲያን አባቶቻችንም ይኸን ሥልጣን አስቀድሞ ሰጥቷቸዋል ፡፡ “የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።”ማቴ 16:19

   የእናንተን ስንመለከተው ደግሞ ከአዳም የወረሰውንም ፣ ማታ ያመነዘረውን ፣ ጧትም የሰረቀውን ፣ ቀንም የዋሸውን … ሌት ተቀን እየተከታተለ በየዕለቱ ሲያነጻና ሲያጸዳ ይኖራል ፡፡ ግለሰቡ ስለ ሃይማኖቱ አምኛለሁ ከማለት በላይ ምንም አይጠበቅበትም ባዮች ናችሁ ፡፡

   እንግዲህ ጌታ ሰው መሆን ያስፈለገው ስለምን ምክንያት ነው? ብለህ ራስክን ብትጠይቅ መልሱን የምታገኝ ይመስለኛል ፡፡ አብርሃም ፣ ሙሴ ፣ ኤልያስ በአዳም የውርስ በደል ምክንያት ነፍሶቻቸው ሲዖል ቢጠበቁም ህያው እንደነበሩ መጽሐፍ ይናገራል ፡፡ ማቴ 17፡3 ፤ ማር 9፡4ን ለአስረጅነት ተመልከት ፡፡

   ”ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን። እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።” ማቴ 22:31-32

   “አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም ነቢያትንም ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ባያችሁ ጊዜ፥ እናንተ ግን ወደ ውጭ ተጥላችሁ ስትቀሩ፥ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።” ሉቃስ 13:28

   “ድሀውም ሞተ፥ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት፤ ባለ ጠጋው ደግሞ ሞተና ተቀበረ። በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ።” ሉቃ 16:22-23 ፡፡ ይኸ የታየው የኢየሱስ ሞትና ትንሣዔ ከመፈጸሙ አስቀድሞ ነው ፡፡

   ስለዚህም ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣበት ተቀዳሚ ዓላማ ቤዛችን ሆኖ ዘላለማዊ ሞትን ለማስቀረትና ነፍሳችን በሲዖል ከመጠበቅ ትድን ዘንድ ነው ፡፡ ስለዚህም አምነን ስንጠመቅ የዚህ ዕድል ተካፋይ እንሆናለን ፡፡ ከዚያች ሰዓት በኋላ የምንፈጽመውን በሙሉ በንስሐና ሥርዓተ ቀኖናን በመፈጸም እናስወግዳለን ፡፡

   ይህንኑ ሲያጠናክርልኝም ዮሐ 17፡4 “እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤” በእዚህኛውም የጌታ ቃል የምንረዳው ፣ ጌታ ወደዚህ ዓለም የመጣው ለተወሰነ ተግባር ስለነበረ (በአዳም በደል ምክንያት የተፈረደውን ዘላለማዊ ሞት መሻር) ፈጸምኩ በማለት እንደ ትንቢት አስታወቀ እንጅ ፣ ዘወትር ለምንፈጽመው ኃጢአት ማለትም ለምንሠርቀውም ፣ ለምንሳደበውም ፣ ለምንዋሸውም ፣ ለምናመነዝረውም …. በየሰዓቱ እየተከታተለ ለመለመንና ለማማለድ የመጣ ቢሆንማ ፣ የሰጠኸኝን ሥራ ፈጸመኩ ማለት አይችልም ነበር እላለሁ፡፡

   እግዚአብሔር እንደ በለዓም ዓይኖችህን ይክፈት

   Delete
  11. አሜን !! ያንተንም ይክፈትልህ፡፡ እኔ የምለው ይህ የኦርቶዶክስ ትምህርት ነው ብለህ ስታቀርበው ይገርመኛል፡፡ እስቲ በደንብ አድርገህ ቅዳሴውን መርምር፡፡ ዛሬም ንስሐ የሚገባውና ጸሎት የሚደረገው ስለ ልጅህ ብለህ ማረን፣ ይቅር በለን፣ በፈሰሰው ደሙ ከኃጢያታችን አንጻን እየተባለ አይደለም አንዴ? ዛሬም የክርስቶስ የቀራንዮ ላይ ሥራ ህያው ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቀናል፡፡ ይህንንም የምናደርገው በእምነት ነው፡፡ ማንኛችንም ብንሆንም ዕለት ዕለት ከኃጢአት የጸዳን አይደለንም፡፡ በተግባር ባናደርገውም በሃሳባችን መበደላችን አይቀርም፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት በንስሐ የምንቆመው ልጁን ጌታ ኢየሱስን መስዋዕታችንን ይዘን ነው፡፡ እርሱ ጽድቃችን ነው፡፡ እግዚአብሔር እኛን ሳይሆን የሚመለከተው በኛ ውስጥ በእምነት ያለውን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡ አንድ ሰው ክርስትናን ሲቀበል በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አመነ ማለት ነው፡፡ ይህ እምነት ደግሞ እኛ ውስጥ የሚሰራው ከሀይል ጋር ነው፡፡ ብርታቱን ይሰጠናል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ለኃጢአት ባሪያ አንሆንም፡፡ ኃጢአትም ጠቅሎ አይገዛንም፡፡ ምክንያቱም በውስጣችን ያለው እምነት ያግዘናል፡፡ ነገር ግን ከላይ እንደገለጽኩት በሃሳብም ልንበድል ስለምንችል ከዚህ ኃጢያት ነጻ የምንወጣውም በጌታ ኢየሱስ ደም በመታጠብ ነው፡፡ ቃሉም እንደሚል …እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል፡፡ ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ህብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው፡፡ እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን፡፡

   Delete
  12. `ዛሬም ንስሐ የሚገባውና ጸሎት የሚደረገው ስለ ልጅህ ብለህ ማረን፣ ይቅር በለን፣`

   ይህን ከተቀበልክ እኮ ልዩነት የለንም ፡፡ ማረን ስንለው ኢየሱስ በራሱ ምሕረትን ያደርግልናል እንጅ ለምን እርቅና ማማለድን እናስባለን ? ለማስታረቅ የመጣው ከአዳም በደል እንጅ የየዕለት ድክመታችንንማ ፣ በእምነት ሆነን ስንቀርበውና ኃጢአታችንን ይቅር በለን ብለን ድምጽ ስናሰማ በራሱ ይሽረዋል ፡፡ ይኸን እኔ ማስታረቅ አልለውም ፡፡ ይቅር ባይ ነውና ምሕረት አደረገልኝ ብዬ እመሰክራለሁ ፡፡

   Delete
 3. ለዚህ ጽሁፍ ምንም ማለት አይቻልም። ለሰይጣን ምን ይባላል? ብቻ ያሳዝናል የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን አልሰበከችም ሲባል በ እርግጥ በተክርስቲያኗን ምን ያህል እንደማታውቃት ነው የሚገልጽው ። እንጂ የምታውቃት ቢሆን በእርግጠኝነት ይህን አትልም ። ኪዳኑን አታውቀውም፤ ቅዳሰውን አታውቀውም፤ ድጓውን አታውቀውም ፤የበተክርስቲያንን አገለግሎት አለማወቅህ ነው ለዚህ ክህደት ያደረሰህ ። አሁንም አልረፈደም ገባ ብለህ ብትማረውና ብታወቀው ይበጃል ። እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በተክርስቲያን 24 ሰዓት ወንጌል የሚነበብበት በተ ክርስቲያን የት አለ ? ካወከው። አንተን ቤተ ክርስቲያንን ከፈተኗት እንደ አንዱ እናይሃለን ..እንደነ አርዮስ እንደነ ንስጥሮስ ወዘተርፈ ። ከዛ ዉጪ ያልከው ሁሉ ሃሰት ነው ቤታችንን በደንብ እናቃታለን ።

  ReplyDelete
 4. Let the almighty God bless you.

  ReplyDelete
 5. እርግጥ ቤተክርስቲያኗ የኢየሱስን ስም ትጠራለች፤ እርሱ ፍጹም አምላክ ነው ፍጹም ሰው ነው ትላለች፤ ደግሞ ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይደለም የሚል ጠንካራ አቋም ታራምዳለች፡፡ ይህ ነው እንግዲህ በረቀቀ መንገድ የኢየሱስን አዳኝነት መቃወም፡፡ ኢየሱስ አዳኝ ነው ሲባል ጉዳዩ በቀጥታ የሚገናኘው ከአማላጅነቱ ጋር ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. kelay yalew melis yetesebetin tsehu degmeh degagmeh anbib

   Delete
  2. በኢየሱስ በኩል እርቅና ምልጃ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት አዳም በአምላክ የተሰጠውን ትእዛዝ በመተላለፍ ፈጣሪውን በመበደሉና ዘለዓለማዊ ሞትን ስላመጣ ብቻ ነው ፡፡ ብዙ ጻድቃን ፣ ብዙ ነቢያት ተነሱ ፤ እምነታቸውን በእግዚአብሔር ጥለው ፣ ምግባራቸውንም አስተካከለው ጻድቅ ተባሉበት ፣ ሞገስን ተቀበሉበት እንጅ ያን በደል ደምስሰው እርቅ ሊፈጥሩ ፣ ክብርና ጸጋን ሊመልሱ ፣ ዘለዓለማዊ ሞትንም ሊያስታግሱ አልቻሉም ፡፡ ሌላውም የሰው መንገድና ብልሃት በሙሉ / ከአምላክ ፈቃድና ፍላጐት ውጭ ቢሆንም ልጆቻቸውን እስከ መሰዋት ደረሱበት/ ምንም መፍትሄ ስላላስገኘ ፣ የሚወደን አምላካችን ራሱን ከእኛ ስጋ አዋህዶ ፣ ዕዳችንን ለመክፈል ፣ ሞትን በሞት ድል ለማድረግና እኛን ለማዳን ወደ እዚህ ዓለም መጣ ፡፡ ራሱን መስዋዕት በማድረግ ማንም ሊሽረው ያልቻለውን ፍርድ ፣ ለመደምሰስ ሲል በመስቀል ላይ ነፍሱን ሰጥቶ ዕርቅን ፈጸመልን ብለን እንመሰክራለን ፡፡ ያ ዕርቅ ከተፈጸመ ፣ ካሳውም ከተከፈለ በኋላ ፣ የሰው ልጅ ወደ ጥንት ክብሩ የመመለሱ ነገር ተረጋግጧልና ሌላ የአማላጅነት ሥራ ቀርቶታል ማለት አይቻልም ፡፡ እርቅና አማላጅነቱን እስከ መስቀለ ሞቱ ድረስ ተጉዞ ፈጸመ ፡፡ከፈጠረው ሥጋ ፣ ያልተፈጠረው አምላክ መዋሃድ ያስፈለገውም ፣ መስዋዕት በመሆን ካሳችንን ከፍሎ ፣ በአዳም ላይ ተጥሎ የነበረውን ፍርድን ፈጽሞ ሊያስታርቀን ነው እንጅ ፣ ዛሬም እንደ ቀደመው በሥጋው ሊወጣበትና ሊወርድበት ፣ ሊገለገልበት እና ሊያማልድበት አይደለም ፡፡ አንድ ጊዜ የተከፈለው መስዋዕት ፣ እንደ ፍየልና በግ ስላልሆነ ለዘለዓለም ያገለግላል ፡፡ ስለዚህም አንድ ጊዜ ያፈሰሰው ደሙ ፣ ዛሬም ካረገው ሥጋው ስለሚፈስ ፣ አዲስ አምነው ለሚጠመቁት የአማላጅነት ግልጋሎቱን ይሰጣል እንጅ ፣ እኛ አምነን የተጠመቅነውን መልሶ መላልሶ ያማልደናል አይባልም∷
   በ 2 ቆሮ 5 ፡16-20 ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው ፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃልን አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን /እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን/፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን /ስለ ክርስቶስ እንለምናለን/ በማለት ገልጿል ። ሐዋርያው በዚህ ባስተላለፈው ቃል ሁሉም የማዳንና የማስታረቅ ሥራ ተከናውኖ እንዳበቃ የሚያስረዳ ነው ፡፡ ኢየሱስ ዋናውን መንገድ ከፍቶልን ስለሄደ ፣ ቀጣዩ ሥራ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት /ጥምቀት ፣ ንስሐ .... / ሆኗል ፡፡

   Delete
  3. አያልቅብህ እስቲ ደግሞ ንስሐ እንዴት እንደሚገባ ጻፍልን፡፡ ስለ ልጅህ ብለህ ይቅር በለን አይባልም እንዴ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን?

   Delete
  4. “አያልቅብህ እስቲ ደግሞ ንስሐ እንዴት እንደሚገባ ጻፍልን፡፡ ስለ ልጅህ ብለህ ይቅር በለን አይባልም እንዴ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ?” ብለህ የጠየቅሀ ወገን

   እስከ ዛሬ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነ አንቀበልም እያላችሁ ስትሞግቱ ፣ በመጽሐፍ ስትያዙ ወደ ቅዳሴ ቤት ገብታችኋል ፡፡ ለመመለስ አስባችሁ ከሆነ መልካም አካሄድ ነው ፡፡

   ቅዳሴ የጋራ ውትወታና ጸሎት ስለሆነ ለሁሉም ቋንቋ በሚስማማ ወይም በሆነ መልኩ ይቀርባል ፡፡ ሰለዚህም ለአዲስ አማኞችም ፣ ላበቁትም ባጠቃላዩ ይቅር በለን ይባላል ፡፡ ይህ ማለት ግን ኢየሱስ ከመንበሩ ተነስቶ እየለመነ ፣ እንደ ሥጋው ዘመን እየጸለየ ያማልዳል ወይም ያስታርቃል ማለት እንዳልሆነ ሊገነዘቡት ያስፈልጋል ፡፡ ስንጸልይና ይቅርታን ስንጠይቅ ኢየሱስ ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አብሮ ምህረትን አድራጊና ይቅር ባይ ነው ፡፡

   አሁን አዙራችሁ ከቅዳሴ ጋር በማቆላለፍ ለማምታታት ሞከራችሁ እንጅ በቅዳሴ የሚባለውን ብትቀበሉትማ እንዲህም እንላለን ፡፡ “አማላጅቱ ሆይ እሊህንም ሁሉንም ከልጅሽ ዘንድ አማልጂ ፤ የጳጳሳትንና የሊቃነ ጳጳሳትን ፣ የኤጲስ ቆጶሳትንም ሁሉ ነፍስ ያሳርፍ ዘንድ የቀሳውስትንና የዲያቆናትንም ፤ እውነተኛውን የቃል ጐዳና የሚያቀኑ ፡፡ ነገሥታቱንና መኳንንቱን ፣ መሳፍንቱንም ፣ በሥልጣን የሚኖሩትን ፣ ወራዙትንና ደናግልን ፣ መነኰሳትንም ፣ ባለጠጋውንና ድሃውን ፣ ታላቁንሃ ታናሹን ፣ ባልቴቱንና አባት እናት የሞቱበትን መጻተኛውንና ችጋረኛውን ፡፡ አስቀድሞ ከቤተ ክርስቲያን ማኀበር ተለይተው ያረፉትን የክርስቲያንንም ወገኖች ሁሉ ይልቁንም በዚች ቦታ ስለ ሞቱ አንቺ ስለነርሱ ተግተሽ አማልጅ ነፍሳቸውን ዕረፍትን ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ” ፡፡

   ስለ ምሥጢረ ንስሐ ምንነት በአጭሩ፡-
   ምሥጢረ ንስሐን የመሠረተ ራሱ ጌታችን ነው ፡፡ ለሰው ልጆች አዛኝ የሆነው መፍቀሬ ሰብእ ክርስቶስ የኛን ኃጢአት ሁሉ በሰውነቱ ተሸክሞ በሕማምና በሞቱ አንድ ጊዜ አድኖናል ፡፡ ይህንንም ጸጋ በምሥጢረ ጥምቀት አግኝተነዋል ፡፡ ከዚያም በኋላ ለምንፈጽመው በደል ማስተሥረያ እንዲሆነን ለሐዋርያቱና እነርሱንም ለሚተኩት ካህናት ሥልጣንን በመስጠት ምሥጢረ ንስሐን መሥርቶልናል ፡፡ ኃጢአትን የማስተሥረይ ሥልጣን የእግዚአብሔር ብቻ ሲሆን ፣ ለእኛ ጥቅምና ደኀንነት ሲል ይህን ሥልጣን ለቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ለጴጥሮስና ለሐዋርያት ተከታዮች ሰጥቷል ፡፡ ማቴ 16፡19

   “እውነት እላችኋላሁ በምድር የምታሥሩት ሁሉ በሰማይ የታሠረ ይሆናል ፤ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል” ማቴ 18፡18 ፡፡ “ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል ፣ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል” ዮሐ 2ዐ፡21-23

   ንስሐ የሚገባ ሰው በቅድሚያ ንስሐ በመግባት ኃጢአት ሁሉ እንደሚሠረይና እንደሚደመሰስ ማመን አለበት ፡፡ “ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ፤ ተመለሱም “ ሥራ 3፡19 ፡፡ እግዚብሔር ንስሐ በሚገቡ ሰዎች ደስ ይለዋል ፡፡ ክርስቶስ ኃጥአንን እንጂ ጻድቃንን ለመጥራት እንዳልመጣ እርሱ ራሱ ተናግሯል ማቴ 9፡13 ፡፡ “ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል” ሉቃ 15፡1-7 ፡፡ “የአንድ ኃጢአተኛ መመለስ በእግዚብሔር መላእክት ፊት ታላቅ ደስታን ያስከትላል” ሉቃ 15፡1ዐ ፡፡

   ለንስሐ መፈጸም የሚያስፈልጉ ሦስት ነገሮች፡-
   - የንስሐ ኃዘን ማለትም እውነተኛና ልባዊ ጸጸት 2 ቆሮ 7፡9-1ዐ
   - ኑዛዜ - ማለትም በደልን ምንም ሳያስቀሩ መናገር ያዕ 5፡16
   - ስለ ኃጢአታችን የሚሰጠንን የንስሐ ቅጣት የሚመለከት የቀኖናን ሥርዓት መፈጸምና በካህኑ የሚሰጠን የፍትሐት ጸጋ ገጽ 268 -269

   ለኃጢአታችን ሥርየት እንደዚህ ዓይነቱን ቀላል መንገድ ስላዘጋጀልን ክርስቶስን ማመስገን ይገባናል ፡፡
   ምንጭ ፡- ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት በሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ 1996

   Delete
 6. ጌታ ይባርክህ

  ReplyDelete
 7. ለማህበረ ቅዱሳን የተሰጡ የምስክርነት ቃል፤
  መለስ ዜናዊ ፡- ማህበረ ቅዱሳን አሸባሪ ነው
  ዳንኤል ክብረት፡- ማህበረ ቅዱሳን ዘረኝነት ይንጸባረቅበታል፡፡
  ዳንኤል ክብረት፡ ማህበረ ቅዱሳን ስውር የፖለቲካ አጀንዳ ያራምዳል፡፡
  አባይ ጸሐዬ ፡ ማህበረ ቅዱሳን ህገ መንግስቱን በመካድ ይጠረጠራል፡፡
  ስብሐት ነጋ ፡ ማህበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አፍራሽ ሚና እየተጫወቱ ነው
  ሰንበት ት/ማ/መምሪያ ፡ ማህበረ ቅዱሳን በህገወጥ ተግባር ተሰማርታል፡፡
  ዲያቆን በጋሻው፡- ማህበረ ቅዱሳን ሌቦች ናቸው፡፡
  ወንድሞቼ እና እህቶቼ ከዚህ ሁሉ የምስክርነት ቃል ምንድ ነው የምንረዳው እባካችሁን ማህበረ ቅዱሳን ካልፈረሰ ለቤተክርስቲያናችን አደጋ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. seyetane eko hule gezeam eweneten ayewedem ezihe laye mesekerenete kesetute wesete andem sewe hayemanote yelewem leteqeme becha yaderena menafeqane nachewe gebahe ...bemechereshawe zemene hulume eweneten yewegal negere gene ayashenefatem.....

   Delete
  2. ጌታ ይገስጽህ፡፡ይህ እማ ከሆነ አንተ/አንቺ ስንት ጊዜ በሰፈር ሰዎች፤በጓደኞችህ፤በመምህራኖችህ፤--- አፈር ብላ፤ሙት፤ እንደወጣህ አትግባ፤--- ወዘተ ተብለህ እንደተሰደብክ ታስታዉሳለህ?ግን ያ ሁሉ ሳይሆን ቀርቶ ነዉ ቢያንስ ይህን የእርግማን ስራህን ለመጻፍ የተነሳህዉ፡፡እናም ማንም ምን ቢል፤ሰጥጣን ዝናሩን ቢፈታ ማህበሩ ምንም እንደማይሆን በእርግጠኝነት ልታዉቀው ይገባል፡፡እንዲህ ስልህ በትምክህት እንዳልሆነ ልብ በል፡፡አንተ እና መሰሎችህ ጥፋቱን እንደምትመኙት ሁላ እድገቱ የተፋጠነና ዘላቂነት ያለዉ እንዲሆን፤ለቤተክርስቲያን ያለዉ ቀረቤታ ከበፊቱ ይበልጥ እንዲጎለብት የሚመኙት ስንቶች ስንተ በርካታ ምዕመናን እንደሆኑ ቤቱ ይቁጠረዉ፡፡ ልፋ ያለዉ ሙቅ ያኝካል አሉ፤ልፋ ብሎህ ማህበሩን ለማጥላላት የማትፈነቅለዉ ድንጊያ፤የማትቆፍረዉ ጉድጓድ የለም፡፡ግን ጥረትህ ሁሉ ዉሃ እንደማይዝ ልታዉቀዉ ይገባል፡፡እንደት በአለት ላይ የተሰራ ነገር በአሉባልታ ሊፈርስ ይችላል፡፡ለመሆኑ ስንቱ ልብ ዉስጥ ገብተህ ይሆን ስለ ማህበረ ቅድሳን ፍቅር ልታስረሳዉ የምትችለዉ?ለበርካታ ወጣት ከአለማዊ እስከ መንፈሳዊ/ሰማያዊ/ ህይዎት መሻሻል መሰረት የሆናቸዉ እኮ ማህበሩ ነዉ፡፡wubshet

   Delete
  3. Mahbibere Kidusan should be happy as it is tested by a lot of allegations and allegations are the signs of true Christianity, as Jesus taught. Allegations are always from the spirit of the devil.

   Delete
  4. Yalebotahi gebitehi atikebatir anitena aniteni yemeselu sewochi iyalu meche selamtagenyalechi. Lemehonu le betekirisitiyan asibehi/shi new le dabachu silalitemechachihu inji.

   Delete
 8. እንዲህ ነው እንጂ የበግ ለምዳችሁን ወዲያ ጣሉት እና ማንነታችሁን በግልጽ አሳውቁን ፡፡ ስለ ፕሮቴስታን ዶግማ ለመስበክ ለምን በኦርቶዶክስ ካባ ትታጀላላችሁ፡፡ ሉተር ይህን የአማላጅነት ትምህርት ማስተማር ሳይጀምር አባቶቻንን ከሐዋርያት ተረክበው የቆዩልንን ትምህርተ ሃይማኖት አማናዊት እንደሆነች እናማናለን፡፡

  እስቲ ተመልከቱ በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን ከተነሳው የሉተር ትምህርት በስተቀር ቀደምት አብያተ ክርስቲያናት በኢየሱስ ክርስቶስ የባህርይ አምላክነት ላይ ጥያቄ የሚያነሳ የለም፡፡ ከቀደምት አብያተ ክርስቲያናት መካከል ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ነው በማለት የሚያስተምር የለም፡፡

  በኃለኛው ዘመን የተነሳችሁት መፍቀሬ ፕሮቴስታንት ግን ይህን ትምህርት እንደምታስተምሩ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን ቦታችሁን እዛው አዳራሻችሁ ውስጥ አድርጉት፡፡ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን እምነት ዶግማ ግን ለአማኞቿ ተውት፡፡

  ReplyDelete
 9. kewunet yaraqe ewnet mesay

  ReplyDelete
 10. From your messages, it is very simple to guess from which side you are placed. Please don't waste your time to take people to the enemy. Our people know the good and the bad things. Don't work with enemy to get money or other things. Everything will over. Truth will win.

  ReplyDelete
 11. ማህበረ ቅዱሳን በደጀ ሰላም ብሎግ እያወጣው ያለ የመነኮሳትን ስም ማጉደፍ ምን ይሉታል?

  ReplyDelete
 12. ማህበሩ ስም ማጉደፍ ከጀመረ ኮይቶአል፤ የጀመረው ከመዘምራን ይሄው አለባበሱ፤ ከሚለው ተነስተው ጳጳሳቱን አልፈው የማይመስላቸውን ተሀድሶ እያሉ ካህናት ዲያቆናቱን ብሎም መነኮሳቱን[ቆሞሳቱን]ጳጳሰቱን ፓትርያሪኩ ደረሱ፤ ይሄው ቤተ ክርስቲያን ሊያፈርሱ፥

  ReplyDelete
 13. ሰው ሁሉ በአንዱ በአዳም በደል ተጠያቂ ሆኖ፣ ባሕርይው ጎስቁሎ፣ ሕያውነትን አጥቶ፣ ባለ ዕዳ ሆኖ በኖረበት ዘመን የካህናቱ ጸሎት፣ የነቢያቱ ምልጃ፣ የቅዱሳኑ ልመና የሰውን ልጅ ከሲኦል ማውጣት፤ ገነትን መክፈት፤ ጎስቋላ ባሕርይውን ማደስ፤ የሰውን ጥንተ ተፈጥሮ ሳይወድቅ በፊት ወደ ነበረበት ንጽሕና መመለስ አልቻለምና ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ «በክርስቶስ በተገኘው እርቅ ካልሆነ በቀር» አለ፡፡
  ጌታችን መገለጥ ያስፈለገበት መንገድ እንደ ነቢያቱና ካህናቱ ምልጃና ጸሎት አይደለም፡፡ ዕርቁ ኃጢአት የተዋሐደውን የሰው ልጅ ከኃጢአት ነጻ ማውጣት የተፈረደበትን የሞት ፍርድ በደሙ መፍሰስ፣ በሥጋው መቆረስ ማስወገድ፣ ገነትን መክፈትን ባሕርይውን ማደስ ነው፡፡ ለዚህም ደግሞ ከሰው ወገን ይህንን ሊፈጽም የሚችል አልተገኘም ፤ ራሱ የሰው ልጅ ገነትን መክፈት አልቻለም፤ ገነት ተዘግታበታለችና፡፡ ሞትን ማስወገድ አልቻለም፤ ሕያውነትን አጥቷልና፡፡ ከኃጢአት ነጻ አይደለም፤ ባለዕዳ ነውና፡፡ ታዲያ ለዚህ የሚያስፈልገው ሰው ሆኖ የሚክስለት ሰው የሆነ በሐዲስ ተፈጥሮ ይቅር ብሎ የሚታረቀውም አምላክ መሆን አለበትና ይህንን የሚያሟላ ቢጠፋ «የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ» አለ፡፡ ስለሆነም «የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት» እንዲል ክንዱ የተባለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለየ አካሉ ተገልጦ እንደ ነቢያቱ «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል» እያለ ሳይሆን « እኔ ግን እላችኋለሁ» በማለት ተገለጠ፡፡ ነቢያት ምሳሌውን እየመሰሉት ትንቢት እየተናገሩለት ሱባኤ እየቆጠሩለት ኖሩ ጌታችን ግን እርሱ መሆኑን ስለ እርሱ መነገሩን... እንደ ተፈጸመ እየነገረን መጣ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም «በአምላካቸው በእግዚአብሔር አድናቸዋለሁ» ይላል፡፡ /ሆሴ 1÷3/ የተገለጠው እግዚአብሔር ነው፤ ያለ እግዚአብሔር ይህ ሁሉ ሊሆን አይችልምና፡፡ በትምህርታቸው እየገሠጹ በኃይለ ቃላቸው እየመከሩ መጻኢያቱን እየተናገሩ በጸሎትና በምልጃ ሕዝቡን እየተራዱ የኖሩት ነቢያት /ቅዱሳን/ ይህን ፍጹም እርቅ ማምጣት አልተቻላቸውምና continue...

  ReplyDelete
 14. በአዳም የሞት ፍርድ የፈረደው እግዚአብሔር ነውና እግዚአብሔር የፈረደውን እንዴት ፍጡራን ያነሣሉ? የነቢያት፣ የካህናት፣ የቅዱሳኑ ጸሎትና ምልጃ ፍጹምን ዕርቅ አምጥቶ ሰውንም አድኖ ከሲኦል ወደ ገነት ማግባት የማይቻለው በመሆኑ ለሰው ልጅ ደጋግመው መጸለይ ዘወትር መሥዋዕት መሠዋት ሲያገለግሉ መኖርን ጠይቋቸው ነበር፡፡ ደጋግመው በማድረጋቸውም ድካም ስላለባቸው ፍጹም መፈወስ /ማዳን/ አለመቻላቸው ይታወቃል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ድካም የሌለበት የባሕርይ አምላክ በመሆኑ አንዴ ሠርቶ የሚያድን አንዴ ተናግሮ የሚያጸና በመሆኑ እንደ እነርሱ ዘወትር ምልጃን ሲያቀርብ አይኖርም፡ደጋግሞ መሥራት ከፍጡራን የሚጠበቅም እንጂ ከፈጣሪ የሚጠበቅም አይደለምነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር እንመካለን፡፡» ከሚለው /ሮሜ. 5÷11/ መታረቁን አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ አግኝተናልና «..በልጁ ሞት ታረቀን» እንዲል፡፡ /ሮሜ. 5÷10/
  ዳግመኛም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ «ብርቱ መድኃኒት አንድ ጊዜ በመደረጉ ጽኑውን ደዌ ያድናል፡፡ ብዙ ጊዜ የሚደረግ መድኃኒት ደካማ እንደሆነ ይታወቃልና፡፡» እንዳለው /ድርሳ 17 ቁ 96 -97/ የቀደሙት /የነቢያቱ ጸሎት የካህናቱ መስዋዕት /ደካማ ነበሩና/ በኃጢአት በባለዕዳነት/ ብዙ ጊዜ መሥዋዕት እየሰሠዉ ምልጃ እያቀረቡ ኖሩ፡፡ ጌታችንን ግን «ብርቱ መድኃኒት» ነውና አንድ ጊዜ ባደረገው የመስቀል ዕርቅ ጽኑ ደዌአችንን አስወገደልን፡፡ አሁን /መታረቁን ካገኘን በኋላ/ «አማላጅ ነው» ማለት በየትኛውም አቀራረብ ጌታችንን ያለ ጥርጥር «ደካማ መድኃኒት ማድረግ» ነው፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ልጠይቅህ
   1/ዛሬ በቅዳሴ ላይ የሚቀርበው መስዋእት አንዴ ቀራንዮ ላይ የተፈጸመው መስዋእት፤ እለት እለት እየቀረበ አይደለም እንዴ? እስከዓለም ፍጻሜ እየተሰዋ ይቀርብልን የለምን?
   2/ የሚቆርቡ ሰዎች በዚህ የክርስቶስ መስዋእት ኃጢአታቸው ተደምስሶ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እየታረቁበት አይደለምን?
   3/ ዛሬ ኃጢአት ሰርተው ንስሀ የሚገቡ ሰዎች የእርቅን ስርየት የሚያገኙት በቁርባን አይደለምን? በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት መስራት በደል ነው። በደል ደግሞ ጥል ነው። ሰው በኃጢአት ከእግዚአብሔር ጋር ሲጣላ ዳግመኛ ለመታረቅ በንስሀ በኩል ያለክርስቶስ ስጋና ደም የመዳን እርቅ አለ ወይ? ካለ እስኪ ንገረኝ!
   ቀራንዮ ላይ የፈጸመው ምልጃ አንዴ የተከናወነ፤ ነገር ግን ሕያውና ዘላለማዊ ስለሆነ ዛሬም ከኃጢአትና ከበደል ወጥተው የሚታረቁበት መንገድ አይደለምን?
   ቅዳሴ ሲቀደስ ማለትም በቅዳሴ ሐዋርያት ላይ፤
   «ወናሁ ደመ መሢህከ ይኬልህ ህየንቴየ» «እነሆ የልጅህ ደም ስለእኔ ይጮሃል» በማለት ካህኑ ወደአብ ዘንድ የሚያቀርበው ጸሎት፤ ጌታችን ቀራንዮ ላይ የጮኸውን «አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ያለውን ምልጃ በመጥቀስ በኢየሱስ ምልጃ አድነን እያለ አይደለምን?

   Delete
  2. ይህን አስተያየት የጻፍኩት ተጠያቂው ሰው አይደለሁም

   ጠያቂው እስቲ አንተም ተጠየቅ ፡-
   - ይኸ ሁሉ ራሱን የሉተር እምነት ተከታይ ያደረገና ፣ ኢየሱስ በየቀኑ እየለማነ ያማልደኛል ፣ ያስታርቀኛል እያለ ለእኛም ያደረሰን ወገን ፣ ስጋወ ደሙን እየተቀበለና ምሥጢረ ቁርባንን እየፈጸመ ነው እርቁን የሚፈጽመው ?
   - የቁርባን ሥርዓት ካላቸው ምን እንደሚሉ ታውቀዋለህ ? ቁርባን ተአማኒ ሳይሆን ምሳሌው ነው ስለሚሉ ማለቴ ነው ፡፡
   - የእምነትና የንስሐ ጥቅምንስ ምን ብለን እንለፍና ቁርባንን እንደ መጀመሪያ የኃጢአት ሥርየት መንገድ አድርገን እንውሰደው ?

   እንደ መጽሐፍ ቃል ከሆነ ፣ ለድኀነታችን መጀመሪያ እምነት ይቀድማል ፤ ያመነ ደግሞ ይጠመቅና ዳግም በመወለድ የጸጋ ልጅነትን ይቀበላል ፡፡ በዚህም የኃጢአት ሥርየትን ያገኛል ፡፡ ዳግም በበደል የወደቀ እንደሁ በንስሐና በቀኖና ይመለሳል ፤ በቁርባንም የተገኘውን ሥርየትና አንድነቱን ያጠናክራል ፡፡ ከምታውቀው በደል ራስህን በኃጢአት ኑዛዜ ሳታስተካክል ፣ ቁርባን የኃጢአት ማስተስርያ ይሆናል ብለህ ብትዳፈር ፤ አቀባዩም እኔ ከደሙ ነጻ ነኝ ብሎ ስለሚያውጅ ፣ ከድኀነት ይልቅ ሌላ በደልን በራስህ ለራስህ ትፈጽማለህ ፡፡

   ቁርባን የመጨረሻው ደረጃ የእምነት ፍጻሜ ነው ፤ ምክንያቱም ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ በማለት አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሥጢረ ቁርባን መፈጸም ምክንያት አንድነትን እንደሚፈጥር ተናግሯልና ነው ፡፡ ቁርባን የኃጢአት ሥርየትን ማስገኘቱን ብናምንም ፣ ከዛ በፊት የሚቀድሙ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች ለመዳረሻ የግድ ይፈጸማሉ ፡፡ ሳታምንና ሳትጠመቅ ፣ ቢያንሰ ህሊናህ ከሚያውቀውም በደል በንስሐ ሳትስተካከል ፣ ከኃጢአት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመገላገል በሚል ቋንቋ ዘለህ ቁርባን አትፈጽምም ፡፡ ስለዚህም በጥምቀትና በንስሐ የተጀመረው ሥርየት በቁርባን ይጠናከራል እላለሁ ፡፡

   - ሌላው ከበድ የሚለኝ ጥያቄ በየዕለቱ እስከዓለም ፍጻሜ እየተሰዋ ይቀርብልን የለምን ? የሚለው ጥያቄ ነው ፡፡ መፈተት የሚል ቃል መቁረስ የሚል እንጅ በየዕለቱ መሰዋትን አያመለክትም ፡፡ አንድ ጊዜ በቀራንዮ ከቀረበው መስዋዕት መካፈልን ይናገራል ፡፡ ኀብስትና ወይኑ በየጊዜው ስለሚዘጋጅ ፣ በየጊዜው ኢየሱስ ተሰቀለ ማለትም አይሆንም ፡፡ አንድ ጊዜ በመስቀለ ሞት የቀረበው መስዋዕት ፣ ዘለዓለማዊ ስለሆነ ፣ ካህኑ ኀብስትና ወይኑን በጸሎትና በቅዳሴ ወደ ተዓማኒ የቀራንዮ መሥዋዕት ሥጋና ደም የሚቀየርበትን ምሥጢር እንናገራለን እንጅ በየዕለቱ ኢየሱስን እየሰዋ ለህዝብ ያቀብላል ማለት አንችልም ፡፡

   - የሚቆርቡ ሰዎች ኃጢአታቸው ተደምስሶ ከአብና ከመንፈሰ ቅዱስ ጋር እየታረቁበት አይደለምን ? ለተባለው ጥያቄ መጀመሪያ በአዳምና በእግዚአብሔር መካከል ጸቡን የፈጠረው ኃጢአት የትኛው ነው ? በማለት ጥያቄህን በጥያቄ እመልሰዋለሁ ፡፡ ከአዳም በደል የምትለኝ ከሆነ ፣ በመጀመሪያው ጥምቀት ተደምስሷል ፡፡ ከተቀረው የዕለት በደል ከሆነ በንስሐና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በመፈጸም ይከናወናል ፡፡ ይህም ማለት ቅዱስ የሆነው በእኛ ሲያድር ኃጢአት ስለማይስማማው ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል እንጅ ፣ ከአብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ዕርቅማ ቀደም ተፈጽሞ አብቅቷል ፡፡

   - ዛሬ ኃጢአትን ሰርተው ንስሃ የሚገቡ ሰዎች የእርቅን ስርየት የሚያገኙት በቁርባን አይደለምን ? ንስሐ የሚገቡ ሰዎች የሚያገኙት የእርቅን ስርየት ሳይሆን የኃጢአት ምሕረትን ነው ፡፡ ምሕረቱን የሚቀበሉት ደግሞ የታዘዙትን ጾም ፣ ጸሎት ፣ ስግደት … ሌሎች ካህኑ እንደ አስፈላጊነቱ የሚያዛቸውን ማስተማሪያ ቅጣቶች በመፈጸም ነው ፡፡ ዛሬ በአመንዝራ ወድቄአለሁ በማለት ለመንፈስ አባቴ ብናዘዝ ምሕረት እንድታገኝ በቀጥታ ቁረብ አይሉኝም ፡፡ ቁርባን ምሳሌ ወይም ተራ ነገር ስላልሆነ ለመፈጸም ብዙ ጥንቃቄ ይደረጋል ፡፡ ብቃትህ ፣ ጽናትህ በሚያውቁህ አባት ይፈተሻል ፡፡

   Delete
  3. እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ይሄ የኔም ጥያቄ ነው፡፡ የቤተክርስቲያኒቱን እምነት ምን እንደሆነ በደንብ ሳይመረምሩ አንዳንድ አሳቾች የጻፏቸውን ጽሑፎች ከኢንተርኔት ላይ እየለቃቀሙ ልክ የኦርቶዶክስ እምነት ነው ብለው ያወጣሉ፡፡ ዛሬም ቢሆን የእኛ ቤተክርስቲያን እምነቷ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አስታራቂነት ማመን ነው፡፡ አምልኮ ሁሉ የሚፈጸመው በጌታ በኢየሱስ ስም ነው፡፡ ኪዳኑን፣ ቅዳሴውን መመርመር ነው፡፡

   Delete
  4. "በአዳምና በእግዚአብሔር መካከል ጸቡን የፈጠረው ኃጢአት የትኛው ነው?"
   The question is not intended to me but I would like to give what I think I know from what I have read somewhere.
   Sin is trying to rule by your own ways rather than His way. Adam was created to rule over the world through protection, admiration and nurture. Not through sheer dominance and exploitation. Don't we do that every day? Don't we sin like Adam every day? Don't we try to build our own kingdom instead of our Lord's? That is why our Lady Holy Virgin Mary said "ታዐብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር". She doesn't take the pride of being the mother of the Lord of the Universe to herself rather she glorifies the Lord for what He has done to her: making her His mother. How amazing is this! St. Ephraim said "The Virgin gave birth to her creator and He created His mother."
   Sin is not letting God be your God. Sin is trying to block His light from shinning on the earth through you. Sinning is denying access to shine through you the Lord who created you. For you are created to shine His Light to everyone around you- essentially for the second time through the sacrifice of our Lord. When Adam tried to shine himself by blocking the Lord's light away he sinned. Don't you do that every day? Do all people around you see the light of the Lord through you? The story of Genesis may not be an historical fact. Yet, it is a general truth that works every day in every one of us. We sin everyday means we sin everyday like Adam. We try to stand for ourselves as gods instead of letting the Lord to be God to us whose light of love and compassion we are created to shine.
   Are not you tempted everyday with self importance? Are not you tempted every hour with pride? That is why the Lord said "Blessed are those who are poor in spirit." Thus, you shall know that whenever you sin you sin like Adam. Our Lord in His flesh was tempted with this: to build a humanly kingdom instead of His Heavenly One, to feel self importance rather than His Father’s will, to avoid the cross rather than being crucified. But He said, “Abba, let your will be done not mine” when He was praying in the garden.
   And hence, you shall be redeemed like Adam through the sacrifice of the Body and Blood of Our Lord. Yet the Lord cannot redeem you if you are not willing to be redeemed. The first thing to be healed is to admit that you are sick. Repentance is: to admit that I have sinned. The Greek word for repentance is Metonoia which means changing way. Yes, repentance is changing your dead- end way of sinning to Life giving way of Christianity: following Christ, being one with His saints, who look like Him. God cannot save us without our “help”. That is why St. Augustine said, “He converts thee not without thy help.” We first need to believe that we need to be changed.
   When we believe that we need to be changed we will come to Him Like the adulterer woman who came to Him and Kissed His feet, washed it with her tears and dry it with her hair. This is repentance. Why did she do this? Because she believed that she had been sinning against Him. So He took her sin and for all the kisses of sin she accepted He was kissed by Judah the Iscariot; for all the tears she cried He cried bloody tears wearing the crown of thorns and died, for she needed to die by stoning as she was adulterer.

   Delete
  5. Now, let’s check ourselves. Are not we sinners like her? Are not we sinners like Adam? Are not we sinners like Cain? Look in to your heart. Shut up and be silent and let God speak to you. You will find who you really are, beneath what everyone tells you or what you think you are. Who shall then redeem you? You have sinned like Adam you are no better than Adam. You are even worse for Adam had no example before Him while you have Christ. Thus you shall be redeemed like Adam. When Adam sinned He lost his originality. So Christ came to give his originality back. The same happens to you when you sin. You throw away the grace which you were given by His coming. But now you don’t have to wait for the Christ to be born for you to be saved (For He was born). Rather, you are only needed to go to Him who waits for you on the altar being sacrificed for you.
   This is why the Mass is held every day. That is why the Church prays in Jesus name. That is why every prayer in the church closes with “በአሐዱ ወልድከ እግዚእነ ኢየሱስ”. By doing this, the Church follows what the Lord instructed her to pray in His name: “አብ በስሜ የምትለምኑትን ኹሉ ይሰጣችኋል፡፡” (ዮሐ. 16:23) Otherwise, how would you explain why the Church's liturgy uses “in Jesus Name” at the end of all the prayers?
   Neither your confessions in the ears of the priest nor your penances of fasting and prayer and alms shall redeem you unless they are presented to Holy Trinity in Jesus name. Even the absolution you get from the priest is not done by anything else but in His name. Look at “ፍትሐት ዘወልድ”.
   This however doesn’t mean that Jesus has not finished the work of salvation. Indeed He has accomplished it on mount Calvary. Yet it is up to us whether we prefer to see the one crucified as our savior or as a simple criminal. When you believe Him to be the messiah then that means He is your redeemer, by whose works of salvation you shall be saved from your sins. How? By believing that you are a sinner, confessing your sins and approaching to the Bread of Life by considering that everything He did on the Cross was to compensate for my sins. I eat His Holy Body and drink His Inebriating Blood to be cleansed from my sins because neither my penances nor my confessions can save me without His sacrifice: the eternal sacrifice of mount Calvary that always stands for me.
   I don’t think this is Protestantism. I know no protestant church that believes in the need of the sacrament of Eucharist for the salvation. This is what our forefathers put in their writings. One cannot be Orthodox by giving the label to him/herself. Rather it is what you believe in.
   By the way, the Protestants do not believe in the need of most of the sacraments, particularly the Holy Eucharist, for salvation. To them it is just symbol. So what I tell you cannot be Protestantism at all.
   I have never heard anywhere in the world among the Christian communities that pray in Jesus name at the same time denying the intercession He did on mount Calvary. Neither in east nor in west.
   However, the problem of most Ethiopians is, I think, the Word “ምልጃ፣ ያማልደናል”. Most of the time, they take it to be equalizing the Lord to the saints. But it is not that. The world has been saved by His Blood. His Blood intercedes for us then and now and forever until the end of the world.
   When someone says that the Eucharist is an eternal sacrifice then does it not mean that it is a sacrifice for my sin?

   Delete
  6. ohh thanks brother, i grew in the orthodox church. i red bible and most church books. but my belief some times donot much with either protestants or orthodox believers.

   Delete
 15. ቅዱስ ፓትርያሪኩ ከሆኑ ሰው አይወጣላቸውም ዛሬ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባውን ሲጀምር በ አድማና በብጥብጥ የተካኑትን አባ ሳሙኤልንና አባ አብርሃምን ብዙ የጉድ ሙዳይ እንዳለባቸው እየታወቀ ቅዱስነታቸው ልሹማቸው ፍቀዱልኝ ብለው ስለተየኩ የፓትርያሪኩን ጥያቄ በምሁራኑ አበው ጳጳሳት ዘንድ ተቀብለው ብዙ እያወቁ ካለእድሜያቸው የአበውን ጵጵስና ተሸክመው ይንገዳገዳሉ አሁንም ቆይ ጵጵስናውን ላግኝ እያሉ የሚዝቱትና የሚፎክሩት አፈ ቀላጤው ገብረ ስላሴ ጉበና ብዙ የጉድ ሙዳይ ያለበት አሁንም ሹሙኝ በማለት ካውስትራልያ ኢትዮ በመመላለስ ላይ ይገኛል ነገር ግን ቤተ ክርስቲያንን ለመበዝበዝ ለማወክ ካልሆነ ምን ይሆን ጥቅሙ እነዚህ የጉድ ሙዳዮች እንደ ቀደሙት አባቶች ለሀገር ለወገን ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ይጸልዩ ይሆን አለመጸለያቸውን ለማወቅ ግን ቀላል ነው በራሳቸው ሰላም ማጣት ይታወቃልና፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

  ReplyDelete
 16. አባቶችን አለመሳደብ ጥሩ ነው ነገር ግን አባቶችም በአባቶች ቦታ ተገኝተው የቤተ ክርስቲያናን ሰላም ሊያስተብቁ ይገባል አለያ ግን የታሪክ ቦታ የሆነችዋን ብቅዱሳን ስም ማህበር መስርተው የሚንቀሳቀሱት ማቆች በእየ አጥቢያ ተሰግስገው ማህበሩን በማይደግፉ ከዲ እስከ ፓት ድረስ ክርስቶስ ቀርቶ እኛን አልሰበኩም በሚል መናፍቅ እያሉ እንደ ሚቀጥሉ አይጠራጠሩ፧ ስለዚህ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች ዘብ ይቁሙ ማቅ ማቅ ማለቱን ይተው

  ReplyDelete
 17. enante "abaselamawoch" tadia emnetachehu endezih kehone semachehun meqeyer yenrbachual, endihum yenzehen talalq abatoch foto letanesu yegebach-hual, meknyatum semach-huna emnetachihu selmaygenang. degmom enezih abatoch eko netsuh yebetekrestianua abatoch nachew, kenesu men guday alach-hihu?

  ReplyDelete
 18. ወንድሞቻችን ዓላማችሁ የታወቀ ነው ቀንዷ የተመታች ላም ያቀብዘብዛታል እንዲሉ እናንተ ደግሞ የዲያብሎስ አስፈፃማዎች ቀንዳችሁ ስለተመታ ይህን ሀሳብ በየጊዜው ትፅፋላችሁ ግን አይሆንላችሁም፡፡
  መሪር አፉሆሙ ወሙሉእ መርገመ እንዳለው ቅዱስ ዳዊት ሰዎች መስላችሁ ግን የበግ ለምድ የለበሳችሁ!!!
  እግዚአብሔር ልቡና ይስጣችሁ!!!

  ReplyDelete
 19. ቆይ ያለገባኝ ነገር… ስለ እናት ቤተ ክርስቲያናችን ማወቅ ያለብን ማህበረ ቅዱሳን የሚለንን ነው ወይስ ተሃድሶ የሚለንን? ማህበረ ቅዱሳንም ሆኑ ተሃድሶዎች የየራሳቸውን ፍላጎት እና አጀንዳ የሚያራምዱ እኛ ምዕመናንን መሳሪያቸው አድርገው ፍላጐታቸውን ለመፈጸም ደፋ ቀና የሚሉ ናቸው፡፡ የዘላለም ንጉስ፣ አልፋ እና ኦሜጋ፣ በአካል ሦስት የሆነ በአገዛዝ፣ በሥልጣንና በመለኮት አንድ የሆነ ቅድስት ሥላሴ አብ ፣ ወልድ ፣ መንፈስ ቅዱስ ፡፡ አብ ከወልድና መንፈስ ቅዱስ አይበልጥም አያንስም፣ ወልድ ከአብና መንፈስ ቅዱስ አይበልጥም አያንስም፣ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ወልድ አይበልጥም አያንስም ሦስቱም በሥልጣን ፣ በአገዛዝ ፣ በመለኮት አንድ ሲሆኑ በግብር እና በአካል ሶስት ብለን እያመንን አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ ብለን በአንድነታቸውና በሦስትነታቸው የምናምን እንዲሁም ወልድ ክርስቶስ እየሱስ መድህነ አለም እኛን ለማዳን የአዳም ኃጢአት ያልነበረባት፣ የሌለባት ፍፁም ድንግል ከሆነች ከእመቤታችን ድንግል፣ ቅድስት፣ ብጽዕት ማርያም ያለ ተራክቦ ተወልዶ በእሱ ሞት እኛ ኃጢአተኞቹን መስቀል ላይ ተሰቅሎ አዳነን ከዛም የምድር ሥራውን ፈጽሞ ወደ ቀደመው የአምላክነት ክብሩ አረገ እንደ ነበረው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሥላሴ በፀወተ መንበሩ በኪሩቤል ዙፋን ተቀመጠ አሁንም ቅዱሳን መላዕክት ያለ እረፍት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አሸናፊ እግዚአብሔር እያሉ ሥላሴን ያመሰግኑታል፡፡ አለም ሲፈጸም እኛን እንደ ሰው ተወልዶ ያዳነን ጌታችን እየሱስ በክብር በመላዕክት ታጅቦ ለፍርድ ይመጣል፡፡ በዛን ጊዜ ለሁላችን እንደየ ሥራችን ይከፍለናል፡፡ አምላክነቱን አዋርዳችሁ አማላጅ ላላችሁት ወዮላችሁ እግዚአብሔር ለአምላክነቱ ለሥልጣኑ ለመለኮቱ ፍፁም ቀናኢ ነውና እባካችሁ ክርስቶስ አማላጅ ነው እያላችሁ ክብሩን የምታዋርዱት ሰዎች ተመለሱ፡፡ እግዚአብሔር ልቡና ይስጣችሁ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ

   Delete
  2. አምላክነቱን አዋርዳችሁ አማላጅ ላላችሁት ወዮላችሁ እግዚአብሔር ለአምላክነቱ ለሥልጣኑ ለመለኮቱ ፍፁም ቀናኢ ነውና እባካችሁ ክርስቶስ አማላጅ ነው እያላችሁ ክብሩን የምታዋርዱት ሰዎች ተመለሱ፡፡ እግዚአብሔር ልቡና ይስጣችሁ ፡፡

   Delete
 20. I am happy to read all the discussion and it helps a lot to see how EOTC is well versed, righteous and firm in the belief of Jesus Christ, our Lord. I really understood how the protestant theology is self defeating, ill-articulated and extremely short of deep understanding about Jesus Christ, our Lord.

  I thank you abaselama. While you posted for spreading protestant ideas, this discussion rather served to preach the true belief and strengthen our understanding and belief in EOTC. It really answered a number of critical questions. Thank you once again. Of all, thank you for those who gave us the answers.

  ReplyDelete
 21. bemeskel lay erek tefetseme. leman ke adam esk mechereshaw sew dres.tadya yehulu sew yidnal? pentewoch endemilut yetenatel dehnet tedemero yealem dehnet ayhonem HONOM GEN EYANDANDU SEW LEALEM KETEDREGEW DEHNET ASFELAGIWOCHUN MESFERT BEMAMUALAT YIDNAL.EYESUS YADANEN BEMAMALED BECHA NEW? BEFTSUM DEHNET BEMESWATAWI KASSA NEW YETFESEMEW.TADYA LEMEN AMALEDE? BEMESKEL LAYE YAMALEDEW LIKE KAHN ENDEMEHONU ABATU ERSUN ENDIMELEKET, KASA KEFYALEHU BEZIH KASA MESEET YIKER BELACHEW NEW YALEW , YIHN YADEREGEW MESWATUN (RASUN) YIMIKEBEW KAHNE ERSU BEMEHONU NEW.YEHEM MALET BEMESKEL LAY (BEKIDESTE KIDUSANU)WEST DEMUN YITHO LEABATU EYETAYE NEBERE.SO HE IS BOTH HIGH PRIEST AND SACRIFICE ON THE CROSS .Christ had to be the sacrifice Who was slain or standing FOR INTESSION at the same time, They did not break His legs when they found that He had already DIED SO BEGROCH KOMO LEGHA TAYELEN ,YET? BEKIDSTE KIDUSAN MESKEL LAY. SO CROSS IS SUFFICIENT FOR OUR SALIVATION BECAUSE THE MOST HOLY PLACE IS CROSS NOT LITERAL HEAVEN.SO AHUN GETACHIN SELEGHA EYETAYE (EYAMALEDE)AYDELEM.

  ReplyDelete
 22. Somebody በሚል ለቀረብክ ወገን

  ኃጢአት ትንሽና ትልቅ ፣ ቀላልና ከባድ ተብሎ በክፋት ደረጃው አይከፈልም እንጅ በደላችንን ከአዳም የማነጻጸር ጉዳይ ከሆነ ፣ በከረምን ቁጥር የበደሉም ዓይነትና መልክ እየተቀያየረና እየረቀቀ ፣ እየበዛና እየተወሳሰበ ስለመጣ ፣ የኛ ኃጢአት አዳም ከፈጸመው ጋር ሊነጻጸርና ሊቀራረብ ከቶም አይቻልም ፡፡ ግን በደፈናው ወሲብ የፈጸመም ፣ ዓይቶ የተመኘም እኩል በደል አድርገዋልና ፣ ሁላችንም በበደል ሚዛን ላይ ስንወጣ በአንድ ስሙ ኃጢአተኛነታችን ብቻ ይነበባል ፡፡

  ድኀነትን ለማግኘት የእኔ ግንዛቤ
  1.እምነት - ይኸም ማለት ወልድ ፍጹም አምላክ ሆኖ ሳለ ፣ እኔን ለማዳን በማለት በልዩ አካሉ ከሥጋ ተዋሕዶ ፍጹም ሰው በመሆን ፣ በደሌን ሁሉ ተሸክሞ በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ ፣ ሥጋውን በመቁረስና በመሞት ያዳነኝ መሆኑን መቀበል ፤ በሦስተኛውም ቀን በራሱ ሥልጣን ሞትን አሸንፎ መነሳቱን ማመን ፤ ከዛም ለሐዋርያት መመሪያውን ሰጥቶ ሲያጠናቅቅ ማረጉንና በአባቱ ቀኝ መቀመጡን ፤ ወደፊትም ደግሞ በኃይልና በክብር ሆኖ በሁሉም ላይ ለመፍረድ ይመጣል ብሎ ማመን ነው ፡

  2.ጥምቀት - እምነትን በተግባር ለመተርጐም የመጀመሪያው መግቢያ በር ነው ፡፡ ቢያምኑም እንኳን ካልተጠመቁ ምንም ዋጋ የለውም ፣ አጋንንትም ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል ተብሏልና ፡፡ በዚሁ በሚፈጸመው ጥምቀት ፣ ከአዳም የወረስነው በደልና ፣ እስከ እዚህች ዕለት ከአዳምም የከፋ ሆነ የቀለለ የፈጸምነው በደል በሙሉ ይደመሰሳል ፤ የእግዚብሔር የጸጋ ልጆችም እንባላለን

  3.ቁርባን - ከጥምቀት በኋላ በማስከተል የቁርባን ሥርዓት ይፈጸማል /በመጀመሪያው ቀን ስለማይነጣጠሉ ማለቴ ነው/ ፡፡ በዚህም በጥምቀት ያገኘነውን ድል እናጠነክራለን ፤ አካላችንን መቅደሱ አድርጐ በእኛ ስለሚኖር ከክርስቶስ ጋር አንድነትን እንፈጥራለን ፤ በሄድንበት ሁሉ ምስክሩም እንሆናለን ፡፡ ከዚህ ከመጀመሪያው ቀን ሥርዓት በኋላ እምነታችንንና አንድነታችንን ለማጽናት ፣ ራሳችንን ከሚታወቅ በደል በመጠበቅና ንስሐ በመግባት የቁርባን ሥርዓትን በተደጋጋሚ እንፈጽማለን ፡፡

  4.ንስሐ - እስከተጠመቅንበት ያለውን በደል በእምነትና በጥምቀት ብናስወግድም ፣ የዚህ ዓለም ሰው በመሆናችን ፣በድፍረትም ሆነ በስህተት ኃጢአትን መፈጸማችን ስለማይቀር ፣ በኑዛዜና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመፈጸም የጥፋታችንን ይቅርታ /ፍትሐት/ ከካህኑ እናገኛለን ፡፡ የሚታወቅ በደል በህሊና አስቀምጦ ቁርባን አይወሰድም ፡፡ አስቀድሞ በንስሐ መታደስ ያስፈልጋል ፡፡

  ይኸን የድኀነት መንገድ ያስገኘልን ፣ በቀራንዮ በመስቀል ላይ ያለበደሉ ስለ እኛ የሞተልን ኢየሱስ ነው ፡፡ ይህን የምልጃ ሥራ በመፈጸሙም ፣ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ፣ ከራሱም ጋር አስታረቀን ብለን እንመሰክራለን ፡፡ ይህ አንድ ጊዜ የተፈጸመው ዘለዓለማዊ መስዋዕታችን ስለሆነ ፣ ትውልድ አልፎ ትውልድ ሲተካ ይህንኑ የድኀነት መንገድ በመከተልና በማመን ሁሉ እንዲድን ሆኗል ፡፡ ይኸን የመዳናችንን መንገድ ከከፈተና ከመራን በኋላ አርጐ በአባቱ ቀኝ ተቀምጧል ፡፡ በዚህም ለእኛ ሲል ተዋረዶ የነበረው የኛን ሥጋ ተዋሕዶ ወደ ጥንት ክብሩ ተመለሰ እንላለን ፡፡

  - ዕብ 1፡3 “ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤” ስለዚህም ኃጢአታችንን በመስቀል ሞት ደምስሶ ወደ ጥንት ክብሩ ተመለሰ እንላለን
  - ዕብ 4፡16 “እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።” በእምነት መቅረብን ልማድ ስናደርግ ምሕረት ያደርግልናል እንጅ አንድ የሃይማኖት ምሁር እንደሚሉት ለምልጃና ለዕርቅ ዳግም ቆሞ እየተከራከረ አይለምንም ፡፡

  - ዕብ 7፡25 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። ይህም ማለት ካህናቱ የሞት ተሸናፊ ስለሆኑና ፣ ኢየሱስ ደግሞ ሞትን ድል በማድረጉ ምክንያት የዘለዓለም ካህን ሆኖ ፣ በመስቀል ላይ በፈጸመው መስዋዕትት በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን /የሚመጡትን ሲል አዲስ አማኞችን ያመለክታል/ ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል
  - 1 ጴጥ 2፡24 ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ
  የማስታረቅ ሥራው በመስቀል ላይ መፈጸሙንና አሁን ግን በክብሩ መሆኑን ያስረዳል ፡፡

  - ዕብ 1ዐ፡10 በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።
  - ዕብ 1ዐ፡12 እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ ስለዚህም አሁን የሚገኘው በማዳኑ ሥራ አምነው ለሚቀርቡት በደለኞች ምሕረትን በሚያደርግበት ስልጣኑ ነው እንጅ እየለመነ በሚያስታርቅበት ሁኔታ አይደለም ፡፡

  - ዕብ 1ዐ፡14 አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።
  - ዕብ 1ዐ፡15-18 መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ ፤ ብሎ ከተናገረ በኋላ፥ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል። የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም። /ኤር 31፡33-34 ተመሳሳይ ንባብ/

  “ስለ እርሱም የምንናገረው ብዙ ነገር አለን፥ ጆሮቻችሁም ስለ ፈዘዙ በቃል ልንተረጕመው ጭንቅ ነው። ዕብ 5፡11”

  እነዚህ ለንባብ ያህል አቀረብኳቸው እንጅ እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቃል የሚነግረን ፣ ኃጢአታችንን እስከ መስቀል ድረስ እንደተሸከመና ዕርቅን እንደ ፈጸመ እንጅ ዛሬም በመንበሩ ለምሕረትና ለይቅርታ ባለበት ሁኔታ እኛን እያስታረቀ እንዳልሆነ ነው ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Now I understand. As Somebody said above,your problem is the word "ምልጃ". None of you deny the works of mount Calvary are eternal. That means you both believe that Jesus has sacrificed Himself to redeem us. So whenever one sins, it is only through the works of the Son that he shall be saved. I think, you guys are talking the same thing in different words. But some of you try to avoid the word "ምልጃ" for it looks to you that it stands for "ለምልጃና ለዕርቅ ዳግም ቆሞ እየተከራከረ". Nevertheless, the guys who favor to use the word "ምልጃ" do not put it that way; instead they are saying the works He accomplished on the cross are eternally capable of saving any sinner who believes in Him and confesses his sins and receives the Body and Blood of Jesus Christ.

   Anyway, may the Lord bless us all.

   Delete
  2. እንደ ባቢሎን ቌንቌችን ካልተደባለቀ በስተቀር ክርስቶስ አሁንም በመውደቅና በመነሳት ይለምንልናል ያለ ማንም የለም፡፡ የቀደመ ሥራው ሕያው ነው፡፡ የሚናገር መሥዋዕት ስለሆነ ዛሬም በእግዚአብሔር ፊት የምንቀርበው እሱን መስዋዕታችን አድርገን በእምነት ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት አቅራቢ ሊቀ ካህናችን፣ እራሱ መስዋዕቱም፣ መስዋዕት ተቀባይ (ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር) ነው፡፡ ዛሬም በእግዚብሔር ፊት ስለልጅህ ብለህ ይቅር በለን፡፡ በደላችንን ባፈሰሰው ደሙ እጠብልን ብለን እለት እለት በንስሐ በፊቱ እንወድቃለን፡፡ በእርሱ የጽድቅ ሸማ በደላችን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተሸፈነ ይሆናል፡፡ ቃሉም እንደሚል እንግዲህ ‹‹እርሱንም (ክርስቶስንም) እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስረያ እድርጎ አቆመው..›› (ሮሜ 3፡25) የእግዚአብሔር ቁጣ በሰው ላይ እንዳይወርድ ልጁን ለሰው የሚመክት መከታ እንዳደረገው ይገልጣል፡፡ የፋሲካ በግ ደም ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ ነው፡፡ እግዚአብሔር በእስራኤል ቤቶች ላይ ስለተቀባው ስለበጎች ደም ‹‹ደሙንም ባየሁ ጊዜ ከእናንተ አልፋለሁ….መቅሰፍቱ ለጥፋት አይመጣባችሁም በሎ ተስፋ ሰጠ ዘጸ 12፡13 በተጨማሪም በስርየት መክደኛው ላይ የተረጨው ደም ሕግን የተላለፉትን ከእግዚአብሔር አይን እንደሚከድን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ለኀጢአት ሌላ ማስተስረያ የለም፡፡ ኀጢአተኛ በክርስቶስ ቃል አምኖ ተስፋውን ሁሉ በክርስቶስ ደም ላይ ማድረግ አለበት፡፡ …የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ!! ዩሐ 1፡29-30

   Delete
  3. አሁንም እየወደቀና እየተነሳ አይለምንም ይል እንደሁ ፣ ይህን እነርሱ ክሚጠቀሙበት መጽሐፍ የተወሰደ ቃል መርምርልኝ “ማስታረቅና ማማለድ ከሁለት ተጣዮች መሃል ገብቶ በመገላገል ሁለቱም አንድ ናቸው ፡፡ የሚለያዩት ግን በማስታረቅ ሦስቱም ሰዎች እኩል ሲሆኑ በማማለድ ግን አማልዱኝ ባዩ ያንሳል ፡፡ …. በማማለድ ደግሞ አማላጅና ተማላጅ አሁንም እኩል ናቸው ፡፡ … አዳም ንስሓ ገባ ፣ ተጠጠተ ፣ ፈጣሪውን በመበደሉ አዘነ ፤ ወልደ እግዚብሔር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተለየ አካሉ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ፣ ሥጋ ለብሶ በመለኮቱ እኩያው ከሚሆን ከባሕርይ አባቱና ከራሱ ከመንፈስ ቅዱስም ሕይወቱ አማልዶ ለምኖ ፣ ጸልዮ ራሱን ሠውቶ አስታርቆታል ፡፡ በመስቀሉ አዳም የሠራውን ጥንተ አብሶ አስወግዷል ፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ በአባቱ ቀኝ ቁሞ የሰው ልጅ እያንዳንዱ በሚሠራው በደል ሲያማልድ ፣ ሲከራከር ይኖራል ፡፡” ምንጭ ፡- ሁሉም ሁሉን ይወቅ ገጽ 47-48

   ወገኖች ኢየሱስ አማላጅ ነው ብለው የሚከራከሩን ከዚህ በላይ በተጠቀሰው መንፈስ ሁነው እንጅ እስከ መስቀል ተጉዞ በሞቱ ዕርቁን ፈጽሞ ደምድሞታል በማለት አይደለም ፡፡ ተቀምጦ ማለት እንኳን እኩልነቱን እንዳያማለክትባቸው /ስለእኛ ድኀነት ሲል የፈጸመውን የቀደመ ውርደቱን ላለመሻር / በአንድ ሥፍራ የተገለጸውን ቁሞ የሚል የሰማዕቱ እስጢፋኖስን ቃል ነው ለመጠቀም የመረጡት ፡፡ ስለዚህም አማላጅ የሚለውን ቃል በሥርዓቱ ካላብራሩት በቀር ሁልጊዜም መቀበል ያስቸግረኛል ፡፡ በቀራንዮ መስቀል የፈጸመው ለሁልጊዜም ቤዛችን ሆኖ ያገለግላል ፡፡ በመንበሩ ፣ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ሲጠብቀን ግን አማላጅ ሆኗል አይባልም ፡፡ እንደ አብና መንፈስ ቅዱስ ምሕረትንና ይቅርታን ይፈጽማል ፡፡

   Delete
 23. ወንድሞች ሆይ ሐዋርያው ጴጥሮስ በመንፈስ ቅድሱ ሐይል እንድህ የሚል ቃል ጽፎልናል "ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን እንደ እግዚአብሄር ቃል ይናገር" 2ኛ ጴጥ 4፡11። ጌታ አምላካችን አሁን በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ይማልዳል ማለት ስህተት ነው።ምክንያቱም ምልጃን ለአንደና ለዘላለም በመስቀል ላይ ፈጽሞአል። ሉቃ 23፤34 አባት ሆይ የምያደርጉት አያውቁምና ይቅር በላቸው በማለት የሐጢአትን ግድግዶ በሞት አጥፍቶ የማስታረቅን አግልግሎት በእርሱ አዳኝነት ለሚያምኑና ለሚከተሉት ሰጥቷዋል።"የማስታረቅን አገልግሎት በእኛ አኖረ።እንግድህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልዕክተኞች ነን። ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ አንለምናለን" 2ኛ ቆሮ 5፤20።ከእርገቱ በሗላ የማስታረቅ አገልግሎት የእኛ የአማኞች አገልግሎት ነው። ራሱ ጌታችን በዮሐንስ ወንጌል ም 14 ቁጥር 26 ላይ እንድ ብሎ ተናግሮዋል "በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ እኔም አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለም" በማለት ተናግሮዋል።ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን በአባቱ ቀኝ ተበርክኮ ያመልዳል ማለት የአይሁድ እምነት ነው። ስለ መልካም ስራህ አንወግርህም ስለ ስድብህ ነው አንተ ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስላመድረግ ነው። ዮሐ 10 ቁ 33 እና ዮሐ 5 ፤ 18 ።እግዚአብሔርነቱን አልተቀበሉም ነበር(አያምኑበትም) ።በመጨረሻም ለማከል የሚፈልገው ሰማዕቱ እስጥፋኖስ ሰዎች በድንጋይ እየወገሩት መንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ሰማያት ተከፍተው ጌታችንን በአባቱ ቀኝ ቆሞ አየ ቀጥሎም ጌታ ሆይ ነፍሰን ተቀበላት ሐጢአታቸውን አትቁጥባቸው ብሎ አንቀላፋ እንጅ አማልደኝ አላለውም ሐዋ ሥራ ም 7 ቁ 55 እስከ 60። እግዚአብሐር አስተዋይ አእምሮ ይስጠን ። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው 1ኛ ዮሐ መል 5 21። ጌታ አምላክና አዳኝ ወንድም ይልቁ በተሰጠህ ጸጋ ወደ እርሱ ስለ ሌሎች ደካማ ወንድሞችና እህቶች አማልድ ጌታ አምላከችን ምህረቱን ይሰጣቸዋል።ይህ ነው የድህነት መንገድ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህን ያስተማርከኝን ቃለ ሕይወት ያሰማልን

   Delete
  2. ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ

   Delete
 24. አሁን ጌታ ኢየሱስ አማላጂ አይባልም ፩ በምድር ላይ ተርቧል ግን ርሀብተኛ እንደማይባል ፪ ሊቀ ካህን መሆኑም አማላጂ አያስብለዉም አሁን በሰማይ ያለዉ ሊቀ ካህንነቱ መስዋት ይዞ ለአባቱ ምልጃ ማቅረብ አይደለምና የኦሪት ሊቃነ ካህናት ወደ ለእግዚአብሔር መስዋት በመስዋት ሐጢያትን ያስተሰርዩ ነበር። በተለይም በአመት አንድ ጊዜ ካህኑ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ደም ይዞ በመግባት ስለህዝቡና ስለራሱ በእግዚአብሄር ፊት ይታይ ነበር ይሁንና ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤ ዕብ ፱፡፯ አሁንጌታ ኢየሱስ አማላጂ ነዉ ካልን አሁን ደም ይዞ እየታየ መሆን አለበት ሆኖም ጌታችን ደሙን ያፈሰሰዉ በመስቀል ላይ በሰማይ አይደለም ዕብ ፯፤፪፯ እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና። ዕብ ፩፤፫፫ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤ ብ ፱፤፪፮፡፪፯ ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል። ለበለጠ ማስረጃ የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ስርዐተ መሠዋት እንመልከት 1. Once a year, on the Day of Atonement, the following ceremony took place.

  2. Two perfect male goats were chosen by the priests.

  3. Both were presented to God.

  4. Lots were cast( ዕጣ ይጣላል,) and the sacrificial goat was chosen.

  5. The sacrificial goat was kept to be sacrificed as a blood sacrifice for sin.

  6. None of its bones were broken

  7. The other goat, the scapegoat, was sent into the wilderness, with a red cord tied around its horns.

  8. The throat of the sacrificial goat was cut outside the Temple, and its blood collected in a special basin(ሳህን)

  9. The high priest then entered the Holy of Holies, wearing special priestly garments, and carrying the basin of blood from the sacrificial goat.

  10. The high priest remained in the Holy of Holies, in pitch darkness, for a total of three hours.

  11. The high priest then prayed before the Ark of the Covenant, asking God to forgive the Jewish people for their sins over the previous 12 months.

  12. The high priest then poured the blood of the sacrificial goat onto the Eastern or right hand side of the Mercy Seat.

  13. God then appeared in Shekinah Glory between the two Cherubim over the Mercy Seat.

  14. God forgave the sin of the Jewish people.

  15. The high priest then stood up, and cried out, "It is finished".

  16. The Old Covenant was fulfilled, by the sacrifice of the sacrificial goat, the prayer of repentance by the high priest on behalf of the Jewish people, and the appearance of God in Shekinah Glory over the Mercy Seat. continue...

  ReplyDelete
 25. ያዳነን ጌታችን እየሱስ ፥ግን የሀዲስ ሊቀ ካህናችን በምትበልጠውና በምትሻለው በእጆችም ባልተሠራች ማለት ለዚህ ፍጥረት ባልሆነች ድንኳን፥የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።as there was a high priest every year who celebrated the Old Covenant *** Jesus Christ is The High Priest of the New Covenant for Eternity
  ***The priests chose two perfect adult male goats Jesus Christ and Barabbas were chosen by Pontius Pilate
  ***The two goats were presented by the priests outside the Temple *** Jesus Christ and Barabbas were presented to the crowds outside the Praetorium***
  The scapegoat was chosen by lots*** Barabbas was chosen by the crowds***
  The scapegoat later received the Rite of Atonement, and was set free *** Barabbas was set free, which is a picture of the Gospel***
  The sacrificial goat was then sacrificed, and the High Priest then entered the Holy Place with the blood of the sacrificial lamb *** Jesus Christ was the High Priest, and the Crucifixion Site became the Holy Place of the New Covenant. Jesus Christ was sacrificed by God on the Cross, as the Lamb of God.***
  The High Priest was completely alone in the Tabernacle Jesus Himself was the only High Priest of the New Covenant once and for all in Eternity***
  The High priest spread blood on the horns of the altar in the Holy Place *** The Blood of Jesus Christ was smeared all over the Cross
  The High Priest prayed to God to forgive the sins of the people *** Jesus Christ prayed for God to forgive the sins of the people
  There was a confession of sin by the high priest over the scapegoat *** Jesus Christ, the High Priest of the New Covenant, did NOT confess sin, because He was without sin. Instead, Jesus Christ became the Blood Sacrifice to take away sin.
  The scapegoat bore all the sins of the people to an uninhabited land *** In the New Covenant, "The blood of Jesus Christ His Son cleanses us from all sin," I John 1, 7
  The blood of the sacrificial goat was sprinkled onto the Mercy Seat of the Ark of the Covenant, in the Holy of Holies The high priest then removed his ceremonial linen garments*** When Jesus Christ was crucified all four of his priestly garments were removed
  The Temple Sacrifice happened every year on the Day of Atonement ** Jesus Christ was crucified on Passover, AD 33, on one occasion only***
  On the Day of Atonement the high priest made atonement for the Jewish people *** On the Day of Crucifixion, Jesus Christ died for the sins of the whole world***
  By Rabbinic tradition, the high priest spent 3 hours in the Holy of Holies, in the pitch darkness*** Jesus Christ spent 3 hours in total darkness on the Cross, and the darkness was world wide***
  During this 3 hour period, God appeared in Shekinah Glory between the Cherubim, over the Mercy Seat*** During this 3 hour period, Jesus Christ was rejected by God the Father, and atoned for the sins of the world***
  By Rabbinic tradition, at the end of this period of 3 hours, the high priest stood up and said, "It is finished" ***At 3 pm, after 3 hours of darkness all over the world, Jesus Christ stood up on the Cross to announce His 7th announcement from the Cross. He said, "It is finished".

  ስለዚህ በዚህ ንፅፅር መሰረት መስዋትና ምልጃ የተፈፀመዉ በመስቀል ላይ ነዉ ንዲህ ባ ይሆንስ ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር ሆኖምአሁንም ጌታ ኢየሱስ ሊቀ ካህናችን ነው፥፥ ሊቀ ካህንነቱ ግን በእግዚአሄር በሆነው ነገር ሁሉ ይቅር ለማለትና ለመማር እንጅ ለመለመን አይደለም፥፥ዕብ ፱፤፪፮፡፪፯ ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባምና፤
  ፩ ሃጢያትን ለማስተረይ ነው ፥አንድ ጊዜ ያፈሰሰው ደሙ ፣ አዲስ አምነው ለሚጠመቁት የአማላጅነት ግልጋሎቱን ይሰጣል
  ፪ ለመማር፨የ
  ፫ የሚፈተኑትን ለማገዝ new..

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዕውቀታችን ሰፋች
   ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ

   Delete
  2. ‹‹ሃጢያትን ለማስተረይ ነው ፥አንድ ጊዜ ያፈሰሰው ደሙ ፣ አዲስ አምነው ለሚጠመቁት የአማላጅነት ግልጋሎቱን ይሰጣል››
   አሁን ጥሩ አመጣኋው፡፡ እኛም የምንለው ይህንኑ ነው፡፡ አንድ ጊዜ የፈጸመው ለሚያምኑት እስከ ዓለም ፍጻሜ ያገለግላል፡፡ የጌታ የኢየሱስ አማላጅነት እንደ ቅዱሳንና ጻድቃን አይደለም፡፡ የእርሱ አማላጅነት ኀጢያትን ያስተሰርያል፡፡ ያጸድቃል፡፡ የቅዱሳን የጻድቃን አማላጅነት ግን የንስሐ ጊዜ ያሰጣል እንጂ ኀጢያትን አያስተሰርይም፡፡ አያጸድቅም፡፡

   Delete
  3. “የቅዱሳን የጻድቃን አማላጅነት ግን የንስሐ ጊዜ ያሰጣል እንጂ ኀጢያትን አያስተሰርይም፡፡ አያጸድቅም፡፡” ይህን ያልክ ሰው ፈጣሪንና ፍጡርን በእኩል ሚዛን ላይ አድርገህ በማወዳደርህ ስንፍናህን ተናገርህ ፡፡ በየትም ሥፍራና ቦታ መላእክትም ሆኑ ቅዱሳንና ጻድቃን በራሳቸው ያደርጋሉ ወይም ይፈጽማሉ አልተባለም ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ስለፈቀደላቸው ፣ በርሱ ጸጋ ለድኀነታችን ይራዳሉ ፣ ለጽድቃችን ይሠራሉ ነው የተባለ ፡፡ ስለማንኛውም ትንሽ ግንዛቤ ብታክል የመጽሐፍ ቃል ይኸውልህ

   ስለ መላዕክት ሲናገር ፡-
   -ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን። ተነሣ፥ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፤ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፋ እያሉ ያስቸኵሉት ነበር። ዘፍ 19፡15

   -ያዕቆብም አለ “ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤” ዘፍ 48፡16

   -የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል። መዝ 34፡7

   -በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው። ኢሳ 63፡9

   -የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ። አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? ዘካ 1፡12-13

   -ስለ መላእክት ሲናገር "ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?" ዕብ 1፡14

   ስለ ጻድቃንም ደግሞ ፡-
   -የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው። 1ጴጥ 3:12

   -የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና። መዝ 34፡15

   -አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ፤ ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፤ ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ። መዝ 142፡7

   -እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሣል፤ እግዚአብሔር ዕውሮችን ጥበበኞች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ጻድቃንን ይወድዳል፤ መዝ 146፡8

   -እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች። ያዕ 5፡16

   Delete
 26. አባ ሰላማዎች እምነታችሁ ምንድን ነው እንዴ? ግራ ተጋባሁ እኮ ፡፡ ክርስቶስ አማላጅ ነው ብላ ስትሰብክ የነበረው አውንም በመስበክ ላይ የምትገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ (ፕሮቴስታንት) ናት እኮ፡፡ እናንተን ማን ይሏችኋል ጃል? በፊትስ ተሀድሶዎች ኦርቶ ጴንጤዎች ናቸው ብዬ አስብ ነበረ አሁን ግን 99.99% ጴንጤዎች ናችሁ 0.1% ቱም ቢሆን የስማችሁ ሽፋን ኢ.ኦ.ቤ/ክ ስለሚል ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንን እናድስ ካላችሁ እንኳን የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ሥርዓቷን ቢሆን እንኳን መልካም ማለቴ ጾምና ፀሎት ላይ ያለንን አመለካከት ፣ ቅድስት ቤ/ክ የምትመራበት መመሪያዎች ሥርዓቶቿ ላይ እንኳን ቢሆን መልካም እንላለን፡፡ ነገር ግን አይደፈሬውን ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ላይ እጃችሁን ትቀስራላችሁ ? ከአይሁድ ፈሪሳውያን በምን ተሻላችሁ ታዲያ? እነሱ ከናንተ የባሰ ምን ክፉ ተናገሩ? እግዚአብሔር አይደለህም የቀራጩ የዮሴፍ ልጅ ነህ፣ ምንም የአምላክነት ሥልጣን የለህም ብለው አይደለም እንዴ እንደ ወንበዴ በቀራንዮ መስቀል የሰቀሉት፡፡ እናንተስ ክብሩን ዝቅ አድርጋችሁ አማላጅ አይደለም እንዴ እያላችሁት ያለው፣ ጌታ ክርስቶስ ከማንስ ያማልዳችሁ ፡፡ ኧረ ጐበዝ ምን እየሰራችሁ እንደሆነ ለደቂቃ አሰብ አድርጉ፡፡ ለማንኛውም ሰማይና መሬትን የፈጠረው አምላክ ወደ ቅድስት ተዋህዶ እምነት ይመልሳችሁ፡፡

  ReplyDelete
 27. I am proud of my ETHIOPIAN brothers specially the EOC believers. I don't expect such kind of biblical knowledge.engdih pente min tihon? tinish tiliku ye metshaf kidus anbabi hone. machiberber atchilum.

  THANKS ABA SELAMAS for giving us such opportunity.

  ReplyDelete
 28. ልባችሁ በደስታ አዕምሮም በዕውቀት ይሞላ ዘንድ ስለ ንስሐና ቁርባን የሚባለውን የማታውቁ ካላችሁ አንብቡት

  በቅዳሴ ማርያም 139 -141 “ይህ መለኮታዊ ኀብስት እነሆ ተቆረሰ ፡፡ ይህ ማኀየዊ ጽዋም እነሆ ተዘጋጀ ፡፡ የሚቀበል ይምጣ ፤ አስቀድሞ ራሳችሁን መርምሩ ፣ ሰውነታችሁንም አንጹ ፡፡ ንጹሕ ያልሆነ ሰው ቢኖር ይወገድ ፤ በኃጢአት የወደቀ ሰው ቢኖር አይርሳ ፤ የማይረሳ ነውና ፡፡ ይህን ቁርባን የሚያቃልል ሰው ቢኖር አይቅረብ ፤ ይከልከል እንጂ ፤ ይህ ኀብስት እንደምታዩት እንደ ምድራዊ ኀብስት ብላሽ አይደለም ፤ እሳተ መለኮት ነው እንጂ” ይላል ፡፡

  ሌላውም “ሰው ወዳጅ ሆይ ያንተ በሚሆን በዚህ በመንፈሳዊ ታቦት ላይ ባኖርነው በዚህ እማሬ ኀብስት ላይና በዚህ እማሬ ጽዋ ላይ ፊትህን ግለጽ ፡፡ ይህንን ኀብስት ባርከው ፤ ይህንንመ ጽዋ አክብረው ፤ ሁለቱንም አንጻቸው ፡፡ ይህ እማሬ ንጹሕ ሥጋህን ይሆን ዘንድ ለውጠው ፡፡ በዚህ እማሬ ጽዋ ውስጥ የተቀዳውም ወይን የከበረ ደምህን ይሁን ፤ ለሁላችንም ያረገ ፣ ለነፍሳችንና ለሥጋችን ለልቡናችንም ፈውስ ይሆን ዘንድ ፡፡” ይላል ፡፡

  በሌላም ጸሎት “አቤቱ እንለምንሃለን ፣ እንማልድሃለንም ፤ በዚህ እማሬ ኀብስት ላይ ቅዱስ መንፈስን ኃይልንም ታሳድር ዘንድ በዚህም እማሬ በጽዋው ላይ የጌታችንና የአምላካችን የመድኀኒታችን ሥጋና ደም ያደርገው ዘንድ ለዘለዓለሙ ፡፡” ይባላል ፡፡ (ኀብስትና ወይኑን ወደ ንጹሕ ሥጋህና የከበረ ደምህ ለውጠው በማለት ይለመናል ፣ ይጸለያል ፡፡ በመጽሐፍ ደግሞ “እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል።” /ማር 11:24/ ይላልና ኀብስቱና ወይኑ ወደ ተአማኒ የጌታ ሥጋና ደሙ ተለውጧል ብለን ተጠንቅቀን እንቀበላለን እንጅ እንደ ከሃድያን ምሳሌው ነው አንልም)

  ከቅዳሴ ዘሐዋርያት የተወሰደ
  94 – 96 በንስሓ ውስጥ ያላችሁ ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ ፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ በንስሓ ውስጥ ወዳሉት ወገኖች ተመልከት ፡፡ እንደ ይቅርታህም ብዛት ይቅር በላቸው ፡፡ እንደ ቸርነትህም ብዛት በደላቸውን አጥፋላቸው ፤ ከክፉ ነገርም ሁሉ ጠብቃቸው ፤ ሰውራቸውም ፡፡ የቀደመ ሥራቸውን ይቅር ብለህ በሰላም ነፍሳቸውን አድን ፤ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ አንድ አድርጋቸው ፤ ተቀዳሚ ፣ ተከታይ በሌለው ባንድ ልጅህ በጌታችንና በአምላካችን በመድኃኒታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ በይቅርታውና በምሕረቱ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ ጨምራቸው ፡፡ በርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ለአንተ ይገባል ፤ ከርሱ ጋራ ፤ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን ፡፡

  98 - 1ዐዐ በእውነት ክቡር የሚሆን የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ይህ ነው ፡፡ አምነው ከርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትና መድኃኒት ፣ የኃጢአት ማስተሥረያም ሊሆን የሚሰጥ ፡፡ በእውነት አምነው ከርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትና መድኃኒት የኃጢአት ማስተሥረያም ሊሆን የሚሰጥ የጌታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም ይህ እማሬ ነው ፡፡ በእውነት የአምላካችን የአማኑኤል ሥጋውና ደሙ ይህ እማሬ ነውና

  1ዐ3 አምናለሁ ፣ አምናለሁ ፣ አምናለሁ ፡፡ የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውና ደሙ ይህ “እማሬ” እንደሆነ እታመናለሁ ፡፡ ክብርና ምስጋና ስግደትም ፣ ቸር ከሚሆን ከሰማያዊ አባቱ ጋራ ፣ ማሕየዊ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ የሚገባው ይህ ነው ፡፡ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን ፡፡

  11ዐ – 113 አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርኲሰት ከሆነች ከቤቴ ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለም ፡፡ እኔ አሳዝኜሃለሁና ፤ በፊትህም ክፉ ሥራ ሠርቻለሁና ፤ በአርአያህና በአምሳልህ የፈጠርኸው ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌአለሁና ፤ ሥራም ምንም ምን የለኝምና ፡፡ነገር ግን ስለ መፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ስለ መሆን ፤ ስለ ክቡር መስቀልህም ማኀየዊት ስለ ምትሆን ስለ ሞትህ በሦስተኛው ቀን ስለ መነሣትህም ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመርገም ሁሉ ከኃጢአትና ከርኲሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ ፤ እማልድሃለሁም ፡፡ የቅድስናህንም ምሥጢር በተቀበልሁት ጊዜ ለወቀሳ ለመፈራረጃ አይሁንብኝ ፤ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ ፡፡ የዓለም ሕይወት ሆይ በርሱ የኃጢአቴን ሥርየት የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ እንጂ ፡፡ በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን በወለደችህ በእመቤታችን በቅድስት ማርያም በመጥምቁ በዩሐንስም አማላጅነት ክቡራን በሚሆኑ በመላእክትም ፣ በሰማዕታትና ለበጎ ነገር በሚጋደሉ በጻድቃንም ሁሉ ጸሎት እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን ፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይህ ምሥጢርህ በእኔ በደል አይሁንብኝ ሥጋዬንና ነፍሴን ለማንጻት ይሁንልኝ እንጂ ፡፡ (ጌታ ኢየሱስን ማረኝ ፣ ይቅር በለኝ እንጅ አስታርቀኝ ወይም አማልደኝ አይባልም)

  115 ሥጋንና ነፍስን ደመ ነፍስንም ለማክበር የሚሆን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ይህ ነው ፡፡ ከሰማይ የወረደ የሕይወት ኀብስት የሚሆን የክርስቶስ ክቡር ሥጋ ፡፡ ከሁላችን እመቤት ከማርያም የነሣው እውነተኛ የሚሆን የአምላካችን የአማኑኤል ሥጋ

  117 – 121 የማይነገር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሦስት የምትሆን ይህን ሥጋና ደም ሕይወት ሊሆነኝ ሳይፈረድብኝ እቀበል ዘንድ ስጠኝ ፡፡ በጌትነትህ እንድገለጽ ደስ የሚያሰኝህን ፍሬ እሠራ ዘንድ ስጠኝ የአንተንም ፈቃድ እየሠራሁ እኖርልህ ዘንድ ስጠኝ ፡፡ በማመን አባት ብዬ እጠራሃለሁ ፤ መንግሥትህንም እጠራለሁ ፤ አቤቱ ፡፡ ስምህ በኛ ላይ ይመስገን ፤ ምስጉን ክቡር የምትሆን ኃያል አንተ ነህና ለአንተ ክብር ይገባሃል ፤ ለዘላለሙ ፡፡ ሰውን ለማዳን ሰው ከሆነ ከአምላካዊ ምሥጢር በተቀበልሁ በእኔ በአንደበቴ ምስጋናህን በልቡናዬ ሐሤተን በሰውነቴም ደስታን ምላ ፡፡ ይህ የሕይወት ጽዋ ከሰማይ የወረደ የክርስቶስ ክቡር ደሙ ነው ፡፡ አሜን ወአሜን

  ጌታዬ አምላኬም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ንጹሕ ሥጋህንና ክቡር ደምህን እነሆ ተቀበልሁ ፤ ለኃጢአቴ ማስተሥረያ ይሁነኝ ስለ በደሌም ሁሉ ፡፡

  ReplyDelete
 29. መቅረዝ -Mekrez
  Pages

  Monday, July 2, 2012

  የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት- ክፍል ሦስት!


  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

  በክፍል ሁለት ትምህርታችን ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እግዚአብሔር ሥርዓት ከሰዎች ተመርጠው ከሚሾሙት የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናት ፍጹም የሚለይባቸውን ነጥቦች ማሳየት ጀምረን ነበር፡፡ የሚምር ነው፤ የታመነ ነው፤ በሰማያት ያለፈ ነው፤ በድካማችን የሚራራልን ነው ብለን አራት ነጥቦችን አይተናል፡፡ ለዛሬም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ካቆምንበት እንቀጥላለን፡፡ ቢችሉ አስቀድመው ይጸልዩ!

  1. በመሐላ የተሾመ ሊቀ ካህናት ነው፡፡ መሐላ የማይለወጥ ነገርን ያመለክታል፡፡ አንድ ሰው ይህን አላደርግም እንዲህም አላደርግም ብሎ ከማለ የነገሩን ሓቅነት ያመለክታል፡፡ “ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው (ሎሌ በጌታው፣ ገረድ በእመቤቷ፣ ደቀ መዝሙር በመምህሩ፣ ልጅ በአባቱ) ይምላሉና ለማስረዳትም የሆነው መሓላ የሙግት (የክርክር የጸብ) ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል፤ ስለዚህም እግዚአብሔር የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደማይለወጥ አብልጦ (አብዝቶ) ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ እግዚአብሔር ሊዋሽ (ሊፈርስ፣ ሊታበል) በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ በመሐላ (በሥጋዌው) በመካከል ገባ፤ ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን (ተስፋችንን አጽንተን ለያዝን ለእኛ ልቡናችን እንዳይነዋወጥ እንደ ወደብ የሚያጸናን ፍጹም ደስታ አለን)፤ እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ (እንደ መልከ ጼዴቅ ባለ ሹመት ተሹሞ ወደ ውሳጤ መንጦላዕት የገባ የዘላለም አስታራቅያችን ፊተውራርያችን ኢየሱስ ክርስቶስ) ነው” እንዲል /ዕብ.6፡16-19/፡፡ እንግዲያውስ ከሌዋውያን ክህነት በሚበልጥ ክህነት፣ እንደ መልከ ጼዴቅ ክህነት ዘላለማዊ በሆነ ክህነት የተሾመ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ የዘመነ ብሉይ ሊቃነ ካህናት ምንም እንኳን በእግዚአብሔር ጥሪ የተመረጡ ቢሆኑም አገልግሎታቸው ጊዜአዊ ስለ ነበረ ያለ መሓላ የተሾሙ ነበሩና፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከኦሪት ለምትበልጥ ለወንጌል መምህር ለመንግሥተ ሰማይም አስታራቂ ሆኖአልና በመሓላ የተሾመ ዘላለማዊ ሊቀ ካህናት ነው፡፡ ሐዋርያውም ስለዚሁ ሲናገር እንዲህ አለ፡- “እነርሱም ያለ መሓላ ካህናት ሆነዋልና፤ እርሱ ግን፡- ጌታ፡- አንተ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ማለ አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት ከመሓላ ጋር ካህን ሆኖአልና ያለ መሓላ ካህን እንዳልሆነ መጠን እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል” /ዕብ.7፡20-22/፡፡ በዚህም ኦሪት ሥርየተ ኃጢአትን ማሰጠት ስላልቻለች እንደተሻረች ወንጌል ግን ማዳን ስለቻለች፣ ሥርየተ ኃጢአትን ማሰጠት ስለቻለች ሕልፈት ሽረት እንደሌለባት አወቅን፤ ተረዳን፡፡ ካህኑም አገልግሎቱም እንደዚሁ፡፡ ለምን ቢሉ ያለ መሓላ ከተሾሙት የብሉይ ኪዳን ሊቃነ ካህናት ይልቅ በመሓላ የተሾመ ሊቀ ካህናት ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኢየሱስ ይበልጣልና፡፡

  ReplyDelete
 30. መቅረዝ -Mekrez.... የማይለወጥ ክህነት ያለው ሊቀ ካህናት ነው፡፡ የቀደሙት ሊቃነ ካህናት ያለ መሓላ ተሠራችው ሕገ ኦሪት የተሾሙ ስለ ነበሩ አንድም መዋትያን ስለ ነበሩ ካህናት የሆኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በመሓላ ለተሠራችው ወንጌል የተሾመ ስለሆነ አንድም ሞትን በሞቱ ገድሎ ተነሥቶ በሕይወት የሚኖር ሥግው ቃል ስለሆነ ወራሽ የሌለው አንድ ነው፡፡ ክህነቱም (ኃጢአት የማሥተስረይ ችሎታውም) የባሕርዩ ስለ ሆነ በሞት (ሞት ሊያሸንፈው ስላልቻለ) አይለወጥም፡፡ የባሕርዩ የሆነውን ለእነዚያ በጸጋ ሰጥቷቸው ነበርና ሥጋ ለብሶ በክህነት ሲገለጥ ባሕርያዊ ሥልጣኑ የማይሻር ሆነ፡፡ ሐዋርያውም ይህን አስመልክቶ ሲናገር፡- “እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘለዓለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው” አለን /ዕብ.7፡23-24/፡፡

  3. ሞትን አሸንፎ በሕይወት የሚኖር ሊቀ ካህናት ነው፡፡ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፡- “የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና፡፡ ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል” /ዕብ.7፡25/፡፡ ካቶሊክ ሳትታሰብ ፕሮቴስታንትም ሳትታለም ከ325 እስከ 389 ዓ.ም የነበረውና የቀጰዶቅያ አውራጃ ለምትሆን የቂሳርያ ሊቀ ጳጳስ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ ይህን ሲተረጕመው እንዲህ ይላል፡- “ይህ ቃል የሚያመለክተን የጌታችን አስታራቂነቱን ነው፡፡… ምክንያቱም መጽሐፍ እንደሚል አንድ እግዚአብሔር አለና፣ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው (ሰው ሆኖ ሰውና እግዚአብሔርን ያስታረቀ) ደግሞ አንድ አለ፣ እርሱም (ለሁሉ ቤዛ አድርጎ ራሱን አሳልፎ ለሞት ለሕማም የሰጠ) ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው /1ጢሞ.2፡5-6/፡፡ አሁንም ይህ ሥግው ቃል ከመቃብር በላይ ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ “በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን” እንላለን /1ኛ ዮሐ.2፡1/፡፡ ሆኖም ግን ይህን በአብ ፊት በመውደቅና በመነሣት የሚያደርገው አይደለም፤ በዕለተ ዐርብ በተቀበለው መከራ ባደረገው ተልእኮ እንጂ” /On The Son, Theological Oration, 4(30):14/፡፡ ከ347 እስከ 407 ዓ.ም የነበረውና የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እንዲህ ይላል፡- “የቀደሙት ሊቀነ ካህናት መዋትያን ስለ ነበሩ ብዙ ናቸው፡፡ እርሱ ግን የማይሞት ሕያው ስለሆነ አንድ ነው፡፡ የማይሞትም ስለ ሆነ እርሱን አምነው የሚመጡትን ሁሉ ሊያድናቸው ይቻለዋል፡፡ እንደምንስ ያድናቸዋል? የሚል ሰው ካለም “በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ ነው” ብለን እንመልስለታለን፡፡ በሃይማኖት በንስሐ ወደ እርሱ የሚቀርቡትን የሚያድናቸው በዕለተ ዐርብ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚያ በኋላም ጭምር እንጂ፡፡ በወደደበት ጊዜም ለመነላቸው፡፡ ሁል ጊዜ ይለምናል ብሎ የሚያስብስ ከቶ እንደምን ይኖራል? ጻድቃንስ እንኳ አንድ ጊዜ በለመኑት ልመና የሚሹትን የሚያገኙ አይደሉምን?… ሐዋርያውም ሁል ጊዜ ቁሞ የሚያገለግል እንዳያስመስሉት በማሰብ በመትጋት መሥዋዕት አንድ ጊዜ እንደሠዋ አስረዳ፡፡ አንድ ጊዜ ሰው እንደ ሆነ አንድ ጊዜ ተሾመ፤ አንድ ጊዜ እንደ ተሾመ አንድ ጊዜ አገለገለ፡፡ ሰው በሆነ ጊዜ የሰውነትን ሥራ በመሥራት ጸንቶ እንዳልኖረ ሁሉ ባገለገለ ጊዜም በማገልገል ጸንቶ አልኖረም፡፡ አሁን ቢያገለግል ኖሮ ሐዋርያው ቆመ እንጂ ተቀመጠ ባላለ ነበርና፡፡ መሥዋዕቱ ቁርጥ ልመናውን አንድ ጊዜ ወደ እዝነ አብ (በአብ ጀሮ) ወደ ገጸ አብ (በአብ ፊት) የደረሰች ስለሆነች እንደ ቀደሙት ሊቃነ ካህናት ሁል ጊዜ ሊያገለግል አያስፈልገውም” /Homily on the Epistle of Hebrews, Hom.13/፡፡ የኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ትርጓሜም ተመሳሳይ ነው፡- “በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ እስከ ምጽአት ድረስ ሲያድንበት የሚኖር ስለ ሆነ በእርሱ አስታራቂነት ወደ እግዚአብሔር የቀረቡትን ማዳን ይቻለዋል” /የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡ ከነ ትርጓሜው፣ ገጽ 434/፡፡ እንግዲያውስ ተወዳጆች ሆይ! “ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል” የሚል ጥሬ ምንባቡን ብቻ በመያዝ እንዳይሳሳቱ ይጠንቀቁ፡፡ ይህ ማለት አስቀድመን እንደነገርንዎት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ የዕለተ ዐርብ የማስታረቅ አገልግሎት ከአዳም መፈጠር ጀምሮ እስከ ዕለተ ዐርብ ላሉት ሁሉ ብቻ ሳይሆን እስከ ዕለተ ምጽአት የሚፈጠረው ፍጥረት ሁሉ በዚሁ የዕለተ ዐርቡ የማስታረቅ አገልግሎት እያመነ እንደሚድን ደሙም የማስታረቅ ችሎታ እንዳለው የሚገልጽ ነውና /ዮሐ.17፡20-21/፡፡ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ የሠዋው መሥዋዕት እንደ ብሉይ ኪዳን ሊቃነ ካህናት መሥዋዕት ተረፈ ኃጢአት (ያልተደመሰሰ ኃጢአት) አስቀርቶበት አሁን ያንን ለማስተስረይ የሚወድቅ የሚነሣ አይደለምና፡፡ ጸሎቱና መሥዋዕቱ ምልአተ ኃጢአትን (ኃጢአትን ሁሉ) ለመደምሰስ አንድ ጊዜ ተፈጽሟልና /ዮሐ.19፡30/፡፡ ስለዚህ ይማልድልናል ስንል “የዕለተ ዐርቡ ቤዛነት፣ ካሣ፣ ሞት፣ ደም መፍሰስ አዲስና በየዕለቱ ንስሐ የሚገቡትን የሚያቀርብ የሚያድን ነው” ማለት መሆኑን ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህም ነው ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች “ከእርሱ ውጪ ሌላ ሊቀ ካህን የለንም፤ ከቅዱስ ሥጋዉና ከክቡር ደሙ ውጪ ሌላ በየቀኑ የምናቀርበው መሥዋዕት የለንም” የምንለው፡፡ ክህነቱ የማይለወጥ፣ መሥዋዕቱም አንድ ጊዜ ቀርቦ በጊዜ ብዛት የማይበላሽ ሕያው አሁንም ትኵስ ነውና፡፡ ትኵስ መባሉም ነፍስ ስላለው ሳይሆን መለኰት የተዋሐደው ስለሆነ ነው፡፡

  ReplyDelete
 31. 4. በእርሱ በኵል (እርሱን አምነው) ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሊያድን የሚችል ሊቀ ካህናት ነው፡፡ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፡- “የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል” /ዕብ.7፡25/፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ጌታችን ራሱ እንዲህ ብሏል፡- “እውነት እውነት እላችኋለሁ እኔ የበጎች በር (ደጅ) ነኝ… በሩ እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ (በእኔ ያመነ) ቢኖር ይድናል ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል (ክብረ ሥጋን ክብረ ነፍስን ያገኛል፤ መንግሥተ ሰማያትንም ይወርሳል)” /ዮሐ.10፡7፣9/፤ “እኔ መንገድና እውነት ነኝ (የሕይወትና የጽድቅ መንገዷ እኔ ነኝ) በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም (እኔን ልጅ ካላለ በቀር አብን አባት የሚለው የለም አንድም በእኔ የማያምን ከአብ ጋር መታረቅ አይችልም)” /ዮሐ.14፡6-7/፡፡ እውነት ነው! የሕይወት መሥመር ክርስቶስ ነውና ክርስቶስን አምኖ የሚኖር ሰው ሕይወትን ያገኛል፡፡ ማንም ይሁን ማን ክርስቶስን ካላመነ ቢጾምም ቢጸልይም ያለ ክርስቶስ ዋጋ የለውም፤ በክርስቶስ ካልሆነ በቀር ዓለም በራሱ ሕይወት የለውም፤ በክርስቶስ ቤዛነት የማያምን በሌላ በምንም መንገድ አይድንም፡፡

  5. ድካም የሌለበት ፍጹም ሊቀ ካህናት ነው፡፡ የዘመነ ብሉይ ሊቃነ ካህናት ድካምን የሚለብሱ እንደነበረ መጽሐፍ የሚሰክረው የታወቀ የተረዳ እውነት ነው፡፡ ይህም በጣም የተገለጠ ድካም በታየባቸው በኤሊ ልጆች መረዳት እንችላለን፡፡ አፍኒንና ፊንሐስ የተባሉ የኤሊ ልጆች በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለመሥዋዕት ከሚቀርበው ሥጋ ለግል ጥቅማቸው በማዋል እግዚአብሔርን ያሳዝኑ ነበር፡፡ ይህም ሳይበቃቸው በመገናኛው ድንኳን ከሚያገለግሉ ሴቶች ጋር ያመነዝሩ ነበር /1ሳሙ.2፡12-22/፡፡ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ጻድቅና ቅን፣ ነቀፋ የሌለበት እውነተኛ፣ ከኃጢአት ሁሉ ፈጽሞ የራቀ የተለየ ከሰማያትም ከፍ ያለ ነው /ዕብ.7፡26/፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትም ይህን ሲመሰክሩ እንዲህ ይላሉ፡- “በአፉም ተንኰል አልተገኘበትም” /ኢሳ.53፡9/፤ “ኃጢአት ያላወቀው” /2ቆሮ.5፡21/፤ “እርሱ ኃጢአትን አላደረገም” /1ጴጥ.2፡22/፤ “በእርሱ ኃጢአት የለም” /1ዮሐ.3፡5/፡፡ ጌታችንም ራሱ እንዲህ ብሏል “ከእናንተ ስለ ኃጢአት (ኃጢአት ሠርተሃል ብሎ) የሚከሰኝ ማን ነው?” /ዮሐ.8፡46/፡፡ ለሞት አሳልፈው የሰጡት ተቃዋሚዎቹም ሳይቀሩ ይህን መስክረዋል፡- “ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ” /ማቴ.27፡4/፤ “በዚህ ሰው አንድ በደል ስንኳ አላገኘሁበትም” /ሉቃ.23፡4/፡፡

  6. ስለ ራሱ መሥዋዕት የማያሻው ነውር የለሽ ፍጹም ሊቀ ካህናት ነው፡፡ የዘመነ ብሉይ ሊቃነ ካህናት ዕሩቅ ብእሲና እንደ ማንኛውም ሰው ኃጢአተኞች ስለነበሩ ሕዝቡን ከእግዚአብሔር ጋር በመሥዋዕት በጸሎት ከማስታረቃቸው በፊት ስለ ራሳቸው ቁርባን መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር /ዘሌ.9፡7፣ ዘሌ.16፡6፣ ዕብ.5፡3-4/፡፡ ሊቀካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን አስቀድመን እንደተናገርነው በባሕርይው ድካም የሌለበት ቅዱስ፤ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለበት ንጹሕ፤ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን ሳይጐድልበት የሚያድል ባዕለ ጸጋ፤ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን የሚያርቅ ቡሩክ፤ ከኃጢአተኞችም የተለየና ነውር የሌለበት ፍጹም ስለሆነ “እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈለገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና” /ዕብ.7፡27/፡፡

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር (ሳምንት ይቀጥላል)!

  Geplaatst door መቅረዝ-Mekrez op 10:22 PM

  ReplyDelete
 32. መቅረዝ -Mekrez.... የማይለወጥ ክህነት ያለው ሊቀ ካህናት ነው፡፡ የቀደሙት ሊቃነ ካህናት ያለ መሓላ ተሠራችው ሕገ ኦሪት የተሾሙ ስለ ነበሩ አንድም መዋትያን ስለ ነበሩ ካህናት የሆኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በመሓላ ለተሠራችው ወንጌል የተሾመ ስለሆነ አንድም ሞትን በሞቱ ገድሎ ተነሥቶ በሕይወት የሚኖር ሥግው ቃል ስለሆነ ወራሽ የሌለው አንድ ነው፡፡ ክህነቱም (ኃጢአት የማሥተስረይ ችሎታውም) የባሕርዩ ስለ ሆነ በሞት (ሞት ሊያሸንፈው ስላልቻለ) አይለወጥም፡፡ የባሕርዩ የሆነውን ለእነዚያ በጸጋ ሰጥቷቸው ነበርና ሥጋ ለብሶ በክህነት ሲገለጥ ባሕርያዊ ሥልጣኑ የማይሻር ሆነ፡፡ ሐዋርያውም ይህን አስመልክቶ ሲናገር፡- “እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘለዓለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው” አለን /ዕብ.7፡23-24/፡፡

  3. ሞትን አሸንፎ በሕይወት የሚኖር ሊቀ ካህናት ነው፡፡ ሐዋርያው እንዲህ ይላል፡- “የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና፡፡ ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል” /ዕብ.7፡25/፡፡ ካቶሊክ ሳትታሰብ ፕሮቴስታንትም ሳትታለም ከ325 እስከ 389 ዓ.ም የነበረውና የቀጰዶቅያ አውራጃ ለምትሆን የቂሳርያ ሊቀ ጳጳስ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ ይህን ሲተረጕመው እንዲህ ይላል፡- “ይህ ቃል የሚያመለክተን የጌታችን አስታራቂነቱን ነው፡፡… ምክንያቱም መጽሐፍ እንደሚል አንድ እግዚአብሔር አለና፣ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው (ሰው ሆኖ ሰውና እግዚአብሔርን ያስታረቀ) ደግሞ አንድ አለ፣ እርሱም (ለሁሉ ቤዛ አድርጎ ራሱን አሳልፎ ለሞት ለሕማም የሰጠ) ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው /1ጢሞ.2፡5-6/፡፡ አሁንም ይህ ሥግው ቃል ከመቃብር በላይ ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ “በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን” እንላለን /1ኛ ዮሐ.2፡1/፡፡ ሆኖም ግን ይህን በአብ ፊት በመውደቅና በመነሣት የሚያደርገው አይደለም፤ በዕለተ ዐርብ በተቀበለው መከራ ባደረገው ተልእኮ እንጂ” /On The Son, Theological Oration, 4(30):14/፡፡ ከ347 እስከ 407 ዓ.ም የነበረውና የቁስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳስ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም እንዲህ ይላል፡- “የቀደሙት ሊቀነ ካህናት መዋትያን ስለ ነበሩ ብዙ ናቸው፡፡ እርሱ ግን የማይሞት ሕያው ስለሆነ አንድ ነው፡፡ የማይሞትም ስለ ሆነ እርሱን አምነው የሚመጡትን ሁሉ ሊያድናቸው ይቻለዋል፡፡ እንደምንስ ያድናቸዋል? የሚል ሰው ካለም “በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ ነው” ብለን እንመልስለታለን፡፡ በሃይማኖት በንስሐ ወደ እርሱ የሚቀርቡትን የሚያድናቸው በዕለተ ዐርብ ብቻ አይደለም፡፡ ከዚያ በኋላም ጭምር እንጂ፡፡ በወደደበት ጊዜም ለመነላቸው፡፡ ሁል ጊዜ ይለምናል ብሎ የሚያስብስ ከቶ እንደምን ይኖራል? ጻድቃንስ እንኳ አንድ ጊዜ በለመኑት ልመና የሚሹትን የሚያገኙ አይደሉምን?… ሐዋርያውም ሁል ጊዜ ቁሞ የሚያገለግል እንዳያስመስሉት በማሰብ በመትጋት መሥዋዕት አንድ ጊዜ እንደሠዋ አስረዳ፡፡ አንድ ጊዜ ሰው እንደ ሆነ አንድ ጊዜ ተሾመ፤ አንድ ጊዜ እንደ ተሾመ አንድ ጊዜ አገለገለ፡፡ ሰው በሆነ ጊዜ የሰውነትን ሥራ በመሥራት ጸንቶ እንዳልኖረ ሁሉ ባገለገለ ጊዜም በማገልገል ጸንቶ አልኖረም፡፡ አሁን ቢያገለግል ኖሮ ሐዋርያው ቆመ እንጂ ተቀመጠ ባላለ ነበርና፡፡ መሥዋዕቱ ቁርጥ ልመናውን አንድ ጊዜ ወደ እዝነ አብ (በአብ ጀሮ) ወደ ገጸ አብ (በአብ ፊት) የደረሰች ስለሆነች እንደ ቀደሙት ሊቃነ ካህናት ሁል ጊዜ ሊያገለግል አያስፈልገውም” /Homily on the Epistle of Hebrews, Hom.13/፡፡ የኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ትርጓሜም ተመሳሳይ ነው፡- “በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ እስከ ምጽአት ድረስ ሲያድንበት የሚኖር ስለ ሆነ በእርሱ አስታራቂነት ወደ እግዚአብሔር የቀረቡትን ማዳን ይቻለዋል” /የቅዱስ ጳውሎስ መጽሐፍ ንባቡ ከነ ትርጓሜው፣ ገጽ 434/፡፡ እንግዲያውስ ተወዳጆች ሆይ! “ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል” የሚል ጥሬ ምንባቡን ብቻ በመያዝ እንዳይሳሳቱ ይጠንቀቁ፡፡ ይህ ማለት አስቀድመን እንደነገርንዎት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ የዕለተ ዐርብ የማስታረቅ አገልግሎት ከአዳም መፈጠር ጀምሮ እስከ ዕለተ ዐርብ ላሉት ሁሉ ብቻ ሳይሆን እስከ ዕለተ ምጽአት የሚፈጠረው ፍጥረት ሁሉ በዚሁ የዕለተ ዐርቡ የማስታረቅ አገልግሎት እያመነ እንደሚድን ደሙም የማስታረቅ ችሎታ እንዳለው የሚገልጽ ነውና /ዮሐ.17፡20-21/፡፡ ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ የሠዋው መሥዋዕት እንደ ብሉይ ኪዳን ሊቃነ ካህናት መሥዋዕት ተረፈ ኃጢአት (ያልተደመሰሰ ኃጢአት) አስቀርቶበት አሁን ያንን ለማስተስረይ የሚወድቅ የሚነሣ አይደለምና፡፡ ጸሎቱና መሥዋዕቱ ምልአተ ኃጢአትን (ኃጢአትን ሁሉ) ለመደምሰስ አንድ ጊዜ ተፈጽሟልና /ዮሐ.19፡30/፡፡ ስለዚህ ይማልድልናል ስንል “የዕለተ ዐርቡ ቤዛነት፣ ካሣ፣ ሞት፣ ደም መፍሰስ አዲስና በየዕለቱ ንስሐ የሚገቡትን የሚያቀርብ የሚያድን ነው” ማለት መሆኑን ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህም ነው ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች “ከእርሱ ውጪ ሌላ ሊቀ ካህን የለንም፤ ከቅዱስ ሥጋዉና ከክቡር ደሙ ውጪ ሌላ በየቀኑ የምናቀርበው መሥዋዕት የለንም” የምንለው፡፡ ክህነቱ የማይለወጥ፣ መሥዋዕቱም አንድ ጊዜ ቀርቦ በጊዜ ብዛት የማይበላሽ ሕያው አሁንም ትኵስ ነውና፡፡ ትኵስ መባሉም ነፍስ ስላለው ሳይሆን መለኰት የተዋሐደው ስለሆነ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይኸ የአዋቂዎች መግለጫ ነው
   ብዙ ለመማር የሚፈልግ መልሶ መላልሶ እንዲያነበው እመክራለሁ
   አቃንተው ፣ አሰማምረው ፣ አጣቅሰው በዕውቀት ሲያቀርቡት ቃሉ ሥንቅ ነው ፡፡
   ያስነበበንና ጸሐፊውን ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ
   መከሩና መከራው ብዙ ስለሆነ አትጥፉ ፤ ብዙ እንማራለን

   Delete
 33. hello Dear Brothers and Sisters in Christ!
  A lot of Reformers here in Ethiopia used to misinterpret this verse of the Apostle Paul in Hebrews 7:25 & Rome 8:34. But what does it mean in its Orthodox meaning? What does the Ancient Fathers say about it? Let’s hear its interpretation from one of our Oriental Orthodox Holy Fathers, St. John Chrysostom
  For as there were many priests, because they were mortal, so [here is] The One, because
  He is immortal. “By so much was Jesus made a surety of a better covenant,” inasmuch as He sware to Him that He should always be [Priest]; which He would not have done, if He were not living. “Wherefore He is able also to save them to the uttermost, that come unto God by Him, seeing He ever liveth to make intercession for them.” Thou seest that he says this in respect of that which is according to the flesh. For when He [appears] as Priest, then He also intercedes. Wherefore also when Paul says, “who also maketh intercession for us” ( Rom. viii. 34 ), he hints the same thing; the High Priest maketh intercession. We have clearly seen this when Our Lord was saying ‘’Father, forgive them; for they know not what they do’’ (Luk.23:34).
  The question is that for He “that raiseth the dead as He will, and quickeneth them,” ( John v. 21 ), and that “even as the Father” [doth], how [is it that] when there is need to save, He “maketh intercession”? ( John v. 22.) He that hath “all judgment,” how [is it that] He “maketh intercession”? He that “sendeth His angels” ( Matt. xiii. 41, 42 ), that they may “cast” some into “the furnace,” and save others, how [is it that] He “maketh intercession”?
  Wherefore (the Apostle says) “He is able also to save.” For this cause then He saves, because He dies not. Inasmuch as “He ever liveth,” He hath (he means) no successor: And if He have no successor, He is able to aid all men. For there [under the Law] indeed, the High Priest although he were worthy of admiration during the time in which he was [High Priest] (as Samuel for instance, and any other such), but, after this, no longer; for they were dead. But here it is not so, but “He” saves “to the uttermost.” What is “to the uttermost”? He hints at some mystery which is the Holy Eucharist. Not on the day of the Good Friday only (the Apostle says) but there also He saves them that “come unto God by Him” through confession and this Holy Communion. If you asketh How does He save? I say unto you “In that He ever liveth” (the Apostle says) “to make intercession for them.” Thou seest the humiliation? Thou seest the manhood? For he says not, that He obtained this, by making intercession once for all, but continually, and when so ever it may be needful to intercede for them.

  ReplyDelete
 34. To the uttermost.” What is it? Not for a time only, but there also in the future life. ‘DOES HE TEHEN ALWAYS NEED TO PRAY? Yet how can [this] be reasonable? Even righteous men have oftentimes accomplished all by one entreaty, and is He always praying? NO! If He need to pray always why then is He throned with [the Father]?’ Thou seest that it is a condescension. The meaning is: Be not afraid, nor say, Yea, He loves us indeed, and He has confidence towards the Father, but He cannot live always. For He doth live always. “For such an High Priest also became us, who is holy, harmless, undefiled, separate from the sinners.” Thou seest that the whole is said with reference to the manhood. (But when I say ‘the manhood,’ I mean [the manhood] having Godhead; not dividing [one from the other], but leaving [you] to suppose what is suitable.) Didst thou mark the difference of the High Priest? He has summed up what was said before, “in all points tempted like as we are yet without sin.” (Heb. iv. 15.) “For” (the Apostle says) “such an High Priest also became us, who is holy, harmless.”
  “Harmless”: what is it? Without wickedness: that which another Prophet says: “guile was not found in His mouth” ( Isa. liii. 9 ), that is, [He is] not crafty. Could anyone say this concerning God? And is one not ashamed to say that God is not crafty, nor deceitful? Concerning Him, however, in respect of the Flesh, it might be reasonable [to say it]. “Holy, undefiled.” This too would anyone say concerning God? For has He a nature capable of defilement? “Separate from sinners.” Does then this alone show the difference, or does the sacrifice itself also? How? “He needeth not” (he says) “daily, as the High Priest, to offer up sacrifices for his sins, for this He did once for all, when He offered up Himself” ( Heb.7: 27) .“This,” what? Here what follows sounds a prelude concerning the exceeding greatness of the spiritual sacrifice and the interval [between them]. He has mentioned the point of the priest; he has mentioned that of the faith; he has mentioned that of the Covenant; not entirely indeed, still he has mentioned it. In this place what follows is a prelude concerning the sacrifice itself through the Holy Eucharist.
  Do not then, having heard that He is a priest, suppose that He is always executing the priest’s office. For He executed it once, and thenceforward “sat down.” ( Heb. x. 12.) Lest thou suppose that He is standing on high, and is a minister, he shows that the matter is [part] of a dispensation [or economy]. For as He became a servant, so also [He became] a Priest and a Minister. But as after becoming a servant, He did not continue a servant, so also, having become a Minister, He did not continue a Minister. For it belongs not to a minister to sit, but to stand.
  Glory be to God Amen!
  ( Source:-
  ü St. John Chrysostom: Homily on the Epistle of Hebrews, Homily 13:6-9, English Version).
  ü ድርሳን ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን 13፡123-191(Dirsan zekidus Yohans Afewerk)- which is the Ethiopic Version of the above reference.)


  Geplaatst door መቅረዝ-Mekrez op 9:47 AM

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዕውቀት ስላካፈልከን ጌታ ይባርክህ
   Now we are a little bit better than yesterday.
   Thanks to Almighty God

   Delete