Thursday, July 26, 2012

የግንቦቱ ሲኖዶስ ካወገዛቸው ግለሰቦች መካከል ሦስቱ ውግዘቱን በመቃወም ጠቅላይ ቤተክህነቱን ይግባኝ ጠየቁ

Read in PDF
ክፍል 2
የዲያቆን አግዛቸው ተፈራ አቤቱታ
ህልውናውንና የሚመራውን መንፈስ ቅዱስን ወደጎን ትቶ ለማኅበረ ቅዱሳን በማደር በህሊና፣ በታሪክና በእግዚአብሔር ፊት አሳፋሪ ስህተት የፈጸመው የግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ እፎይ ብዬ ተቀመጥኩ ለማለት ቢሞክርም፣ እፎይ የማያሰኙ አቤቱታዎች እየቀረቡበት መሆኑን ከዚህ ቀደም ገልጸናል፡፡ እስካሁን ድረስ ባለን መረጃ ዲያቆን አሸናፊ፣ ዲያቆን አግዛቸው እና መምህር ጽጌ አቤት ያሉ ሲሆን፣ አቤቱታቸውን ሰምቶ ችግራችሁ ምንድን ነው ብሎ ሊያነጋግራቸው የቻለ አካል ይኑር አይኑር እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ ባለፈው ጊዜ የዲ/ን አሸናፊን አቤቱታ አቅርበንላችሁ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የዲ/ን አግዛቸውን አቤቱታ እናቀርባለን፡፡ ሙሉውን የዲያቆን አግዛቸውን ደብዳቤ ከዚህ ጽሑፍ በታች ያገኙታል . . .

Saturday, July 21, 2012

እግዚአብሔር አለን . . . ወይስ . . .? ካለስ ምን እየሰራ ነው. . .!?

       ‹‹Love is the Answer no matter what the Question! ለየትኛውም፣ ለማንኛውም ጥያቄዎቻችን ፍቅር መልስ ነው!!››
በፍቅር ለይኩን፡፡
አፄ ቴዎድሮስ ብዙ ከተባለለትና ከተጻፈለት አፍሪካዊው ‹‹ታላቁ ናፖሊዮን›› ካሰኛቸው ከጀግንነታቸው፣ ከጭካኔያቸው፣ ከፍርድ አዋቂነታቸውና ኢትዮጵያን ለማዘመን ከነበራቸው ታላቅ ራእይ ባሻገር በተለያዩ ጊዜያት ስለ ፈጣሪ ህልውና ከቤተ ክህነቱ ተጠሪዎች ነን ባዮች ደብተራዎችና ካሕናት ጋር ያደረጓቸው እንደ አንዳንድ የዋኃን አገላለጽ ‹‹ፈጣሪን መፈታተን›› ዓይነት ጥያቄዎችን እያነሱ ካሕናቱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሊቃውንቶች በጥያቄ በማጣደፍ ያስጨንቁ ነበር ይባላል፡፡ እናም በአንድ ወቅት ንጉሥ አፄ ቴዎድሮስ በዙፋናቸው በተሰየሙበት ግብር ገብቶ መኳንንቱና መሳፍንቱ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርሰቲያን፣ ካሕናት በታደሙበት ግብዣ ላይ ንጉሡ አንድ ጥያቄ አነሱ እንዲህ ሲሉ፡-

Wednesday, July 18, 2012

መንግስት ለማኅበረ ቅዱሳን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

(ምንጭ፦ አውደ ምህረት/www.awdemihret.blogspot.com)የበቀለውን እየነቀለ የታጨደውን እየበተነ ቤተክርስቲያንን የሁከት መንደር ያደረገው ማኅበረ ቅዱሳን አሰራሩን እንዲያስተካክል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው።
ማስጠንቀቂያው የተሰጠው በሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ ሲሆን የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች  የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጠርተው ውስጣቸውን እንዲያጠሩ፣ ሃይማኖቱ ከሚፈቅድላችሁ ወሰን ወጥተው ከሚፈጽሙት ድርጊት እንዲቆጠቡ፣ ከየትኛውም የአመጽ ሥራ በስተጀርባ ጥላቸውን እያጠሉ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲገቱ፣ ከሌላ ጽንፈኛ ሐይል ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቆሙ፣ ቤተክርሰቲያኒቱን በመበጥበጥና ስራዋን ሁሉ እቆጣጠራለሁ በማለት የሚያደርጉትን ሩጫ እንዲገቱ አካሄዳቸውን የማያስተካክሉ ከሆነ ግንከዚህ በላይ ሊታገሳቸው እንደማይችል እና መንግስት የሰበሰባቸው መረጃዎች ማኅበሩን ለማፍረስ እና በወንጀልም ለመጠየቅ በቂ  እንደሆኑ ተነግሯቸዋል።
ከአመሰራረቱ ጀምሮ እጁን በደም ነክሮ የተነሳው ማኅበር በተለያዩ ወንጀሎች እየተጠላለፈ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ እነ እሸቱ ለዛር እያደነከሩ የ8 ሴቶች ክብረ ንጽህናን ገፈው የመሰረቱት ማኅበር በደም አበላ እየተነከረ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሲፈጽማቸው የነበሩ የነብስ ግድያ የሙስና እና የተለያዩ ወንጀሎች በሙላት የሚታወቁ ሲሆን ያስጀመራቸው የዛር መንፈስ የደም ግብሩን በየአመቱ በተለያየ መንገድ እየተቀበለ ይገኛል፡፡ 

Monday, July 16, 2012

የሊቀ ጉባኤ አባ አበራን መጽሐፍ ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ ደጋግሞ የማያሳትመው ለምን ይሆን?

ማኅበረ ቅዱሳን መጽሐፉ በያዘው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ያምናል ወይስ አያምንም?
ከዚህ ቀደም ማኅበረ ቅዱሳን ከማያምንበት፣ ነገር ግን ካሳተመው፣ የወንጌል እውነት የተገለጠበትና ብዙዎች ወደመዳን እየደረሱበት መሆኑን ሲያውቅና እርሱ በሌላ በኩል እያወገዘውና እያስወገዘው ካለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ጋር አንድ መሆኑን ሲረዳ እንዳይታተም ካደረገው ከሊቀ ጉባኤ አባ አበራ «ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት» መጽሐፍ መግቢያ ላይ የወጣውን ድንቅ ጽሑፍ አስነብበን ነበር፡፡ ከዚያ ወዲህ አሮጌ ተራ አካባቢ ከተደረገው የዋጋ ማጣራት ለመረዳት እንደቻልነው፣ መጽሐፉ እስከ ብር 240.00 ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

Saturday, July 14, 2012

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 3
ማኅበረ ቅዱሳን ከሶ፣ የሊቃውንት ጉባኤ አጣርቶ፣ የግንቦቱ ስሜት መራሽ ሲኖዶስ ያወገዛቸው ማኅበራትና ግለሰቦች የተገኘባቸው ኑፋቄ ምን ይሆን? ኑፋቄ ተብለው የቀረቡት ነጥቦች ሁሉ በእርግጥ ኑፋቄ ናቸው? ወይስ ኑፋቄ አይደሉም? ኑፋቄ ካልሆኑ እንዴት ሊያስወግዙ ቻሉ? ሲኖዶሱ ለማውገዝ መስፈርት ያደረገው፣ በመግቢያው ላይ እንደተናገረው የሐዋርያትንና የነቢያትን ትምህርት ነው? የሊቃውንትንስ ትምህርት መሠረት ያደረገ ነው? የሦስቱን ጉባኤያት ውሳኔዎችንስ ያገናዘበ ነው ወይስ ከዚያ ውጪ የተካሄደ ነው? የሚሉትና የመሳሰሉት ጥያቄዎች በግንቦቱ ሲኖዶስ ለተላለፈው ስሜታዊ ውግዘት ሊቀርቡ የሚገቡ ዋና ዋና ትያቄዎች ናቸው፡፡

Thursday, July 12, 2012

የግንቦቱ ውግዘት መነሻ የሆነው የማኅበረ ቅዱሳን ክስ ዶሴ፣ የሊቃውንት ጉባኤው ጥናት ውጤትና የሲኖዶሱ ቃለ ጉባኤ

እነዚህን አራት ሰነዶች ስለሚከተሉት ምክንያቶች ለአንባቢያን አቅርበናል።
1ኛ) ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ፥ የእውነተኞች የቤተ ክርስቲያን ልጆችን አንገት ያስደፋና አሳፋሪ ታሪክ ቢሆንም ታሪክ ነውና ለቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች እና ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች እንዲሁም ፍላጎት ላላቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ በቀላሉ እንዲያገኙት ለማቅረብ ወደድን።
 
2ኛ) ውሸት እና ስህተት ዝም ከተባለ እንደ እውነት እና ትክክለኛ ነገር ስለሚቆጠር በክሱና በውግዘቱ ውስጥ «ኑፋቄ» በተባሉ ነጥቦች ዙሪያ ብዙ የምንለው ስላለን አስቀድመን ለአንባቢያን ጥሬ መረጃውን ማቅረቡ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። እነዚህን ሰነዶች ማንበቡ በሚቀጥሉት ቀናትና ሳምንታት የምናቀርባቸውን ጽሑፎች ለማገናዘብ ይጠቅማል።
  

 መልካም ንባብ . . .
  

Wednesday, July 11, 2012

የግንቦቱ ሲኖዶስ ካወገዛቸው ግለሰቦች መካከል ሦስቱ ውግዘቱን በመቃወም ጠቅላይ ቤተክህነቱን ይግባኝ ጠየቁ

(ደብዳቤ የጻፉት ዲ/ን አሸናፊ መኮንን፣ ዲ/ን አግዛቸው ተፈራ እና መምህር ጽጌ ስጦታው መሆናቸው ታውቋል)
የግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ቤተክርስቲያንን የዓለም መሳቂያና መሳለቂያ በማድረግ ያዋረደበትን ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ ይህን የራሱን ክብር የቀነስበትን፣ በታሪክ ተወቃሽ የሚያደርገውንና ብዙዎችን ያሳዘነውን፣ የቤተክርስቲያንን ሕግና ስርአት ባልተከተለና፣ በየትኛውም መስፈርት ሲመዘን ሕገ ወጥ ሆኖ የተገኘውን ውግዘት፣ «ተወጋዦቹ» እየተቃወሙት ነው፡፡ አንዳንዶቹም ይግባኝ እየጠየቁበት መሆኑ ተሰምቷል፡፡ እስካሁን ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ለጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤትና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት በጻፏቸው ደብዳቤዎች ተቃውሟቸውን ያሰሙትና የተላለፈባቸው ሕገወጥ ውግዘት እንዲነሳና ጉዳያቸው እንደገና እንዲታይ የጠየቁት ዲ/ን አሸናፊ መኮንን፣ ዲ/ን አግዛቸው ተፈራ እና መምህር ጽጌ ስጦታው መሆናቸው የታወቀ ሲሆን ለዛሬው የዲ/ን አሸናፊ መኮንንን ደብዳቤ እናቀርባለን (ሙሉውን ደብዳቤ ከዚህ ጽሑፍ በታች ያገኙታል)፡፡
እንደሚታወቀው ዲ/ን አሸናፊ መኮንን  እስካሁን 16 መንፈሳዊ መጻሕፍትን በመጻፍ ለበርካታ ምእመናን መጽናናትን ያመጣና እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ያስነሳው እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጅ ነው፡፡ መጻሕፍቱ በአብዛኛው መንፈሳዊ ሕይወት ላይ ያተኮሩ፣ እየጣፈጡ የሚነበቡ፣ ሕይወትን የሚፈትሹና ለብዙዎች የመንፈስ እርካታን ያመጡ በመሆናቸው በየቤተክርስቲያኑ ደጅና የኦርቶዶክስ መጻሕፍት በሚሸጡባቸው የመጻሕፍት መደብሮች ውስጥ እየተሸጡ ለምእመናን በቅርበት የሚደርሱ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥም በስፋት የሚነበቡና የማኅበረ ቅዱሳንን የተረት መጻሕፍት ከገበያ እያስወጡ ያሉ መጻሕፍት መሆናቸውን ብዙዎች የሚመሰክሩት ሐቅ ነው፡፡

Monday, July 9, 2012

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 2
በመጀመሪያው ክፍል ጽሑፋችን በግንቦት 15ቱ ውግዘት ዙሪያ የመግቢያ ሐሳብ አቅርበን የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ዛሬ ከዚያ የቀጠለውን ሐሳብ እናካፍላችኋለን፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በ30/1/2004 ዓ.ም በተጻፈ፣ የማኅበሩን አርማ የያዘና ማኅተሙ ያረፈበት 2 ገጽ ደብዳቤ ሸኚ በማድረግ በማኅበራት ላይ ማኅተምና ፊርማ አልባ 33 ገጽ፣ በግለሰቦች ላይም ማኅተምና ፊርማ አልባ 21 ገጽ በድምሩ 56 ገጽ የክስ መዝገብ ለፓትርያርኩ አስገባ፡፡ በግልባጭም ለሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለጳጳሳት በሙሉ፣ እንዲሁም ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አሳውቋል፡፡

Friday, July 6, 2012

«አናኒመስ» ስለ ጥንተ አብሶ ምን እያለ ነው?

ክፍል ሁለት
«3. ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ወደ እመቤታችን በመጣ ጊዜ - “ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው ከሴቶች መካከል አንቺ የተባረክሽ ነሽ ፡፡በማለት አመስግኗታል (ሉቃ 1.28) ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ከእርሷ በፊት ይህን በሚመስል ምስጋና የተመሰገነ አንድም ፍጡር የለም ፡፡ ይኸ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእመቤታችን የተሰጠ ምስጋና ነው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!! እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጥንተ አብሶ ተይዛ ቢሆን ኖሮ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልጸጋን የተመላሽ ሆይሊላት አይችልም ነበር፡፡ ምክንያቱሳ ቢሉ ጥንተ አብሶ ጸጋዋን ጐደሎ ያደርግባት ነበርና ነው፡፡ አዳም በደልን እንደ ፈጸመ በቀጣዩ ያጋጠመው የመጀመሪያው ቅጣት ጸጋው መጉደሉ ወይም መገፈፉ ነው፡፡ ይኸ የአዳም በደል አለባት ከተባለ ጸጋዋ እንደ ቀደም አባቷ መጉደል ይገባው ነበርና ታድያ መልአኩ እንዴትና ስለምን ምልአተ ጸጋ በማለት ሊያወድሳት ይችላል 

Thursday, July 5, 2012

«ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ»

(ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት)
ማኅበረ ቅዱሳን ደጀ ሰላም በተባለው አሸባሪ ብሎጉ ጉባኤ አርድእት የተባለ ማኅበር ተቋቋመብኝ ይህ ማኅበር ደግሞ አያያዙ በሞኖፖል ይዠው የነበረውን የቤተክህነት ሥልጣን ሊነጥቀኝ ነው። የተሰበሰቡት ሰዎችም ከኔ ጨዋና ጥራዝ ነጠቅ አመራሮች የተሻሉ ስለሆነ ግርማ ሞገሳቸው አስፈርቶኛል የሚል አንድምታ ያለው ባለ 9 ገጽ ጽሁፍ ከለቀቀ በኃላ ይህ ገና ከመቋቋሙ ማኅበሩን በጥላው ያሸበረው ጉባኤ አለማው ምንድን ነው? በማለት በቤተክህነት አካባቢ ያለውን ነገር እያጣራን ሳለ gubae ardiet የሚል የፌስ ቡክ ገጽ ላይ አላማውን የሚያስረዳ ጽኁፍ ስላገኘን አላማውን ታውቁት ዘንድ ልናቀርብላችሁ ወድደናል።ማኅበረ ቅዱሳን በአንድ እግሩ ፖለቲካ በሌላኛው እግሩ ሃይማኖት እየረገጠና በሁለት ሀሳብ እያነከሰ ያለ እኔ ቤተክርሰቲያን ዋጋ የላትም እያለ ቤተክርስቲያንን ለዘመናት ሲጠብቅ የነበረውን መንፈስ ቅዱስን ስፍራ ልቀቅ በማለት ያለአቅሙ እየተውተረተረ በየአቅጣጫው አቧራ በመበተን ቤተክርሰቲያንን እየረበሸ በመገኘቱ ያሳዛናቸው የቤተክህነት ሠራተኞች የመምሪያ ኃላፊዎችና የደብር አለቆች የተሰባሰቡበት ጉባኤ አርድእት አላማው በጽሁፉ እንደሚነበበው ቤተክርስቲያንን ከምንደኞችና ከእበላ ባዮች ለመታደግ እና አባቶችን በሚያስፈልገው ሁሉ ለመርዳት ነው።

Sunday, July 1, 2012

«አናኒመስ» ስለ ጥንተ አብሶ ምን እያለ ነው?

ክፍል አንድ፦
Read in PDF
ባለፈው በጥንተ አብሶ ላይ የዓለማየሁ ሞገስን ጽሑፍ አስነብባችሁን ነበር፡፡ በጽሑፉ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች ነበሩ፡፡ ብዙዎቹ አስተያየቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ያፈነገጡ ወይም በማያስኬድ ሎጂክ ላይ የተመሠረቱ ሆነው አግኝቼአቸዋለሁ፡፡ በተለይም «አናኒመስ» በ 7 ነጥቦች ስር ያቀረባቸው ሀሳቦች ምክንያታዊ አይደሉም፡፡ የጥንተ አብሶን ምንነት በትክክል ያልገለጹ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት የሚያዛቡ፣ የተሳሳተ አስተሳሰብን ትክክለኛ ለማስመሰል ጥረት የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ለዛሬው በዚህ ላይ ጥቂት ማለት ፈለግኩ፡፡