Monday, July 9, 2012

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 2
በመጀመሪያው ክፍል ጽሑፋችን በግንቦት 15ቱ ውግዘት ዙሪያ የመግቢያ ሐሳብ አቅርበን የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ዛሬ ከዚያ የቀጠለውን ሐሳብ እናካፍላችኋለን፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በ30/1/2004 ዓ.ም በተጻፈ፣ የማኅበሩን አርማ የያዘና ማኅተሙ ያረፈበት 2 ገጽ ደብዳቤ ሸኚ በማድረግ በማኅበራት ላይ ማኅተምና ፊርማ አልባ 33 ገጽ፣ በግለሰቦች ላይም ማኅተምና ፊርማ አልባ 21 ገጽ በድምሩ 56 ገጽ የክስ መዝገብ ለፓትርያርኩ አስገባ፡፡ በግልባጭም ለሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለጳጳሳት በሙሉ፣ እንዲሁም ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አሳውቋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ስለማኅበራቱም ሆነ ስለግለሰቦቹ ያቀረባቸው ማስረጃዎች በራሱ መነጽር ያያቸው ናቸው እንጂ በእውነታ ላይ ያልተመሰረቱና የተዛቡ እንደሆኑ ካደረግነው ጥናት ለማወቅ ችለናል፡፡ ማቅ ሆነ ብሎ የሊቃውንት ጉባኤውንና በስሜት ነድቶ ስሜታዊ ያደረገውን ቅዱስ ሲኖዶስን  በማሳሳት የሌሉ ማኅበራትን ፈጥሯል፡፡ ፈጽሞ የማይተዋወቁና የማይገናኙ ግለሰቦችን በማገናኘትና አንድ ላይ በመደመር የተሳሳተ መረጃ ሰጥቷል፡፡ ሌሎች በብእር ስም የጻፏቸውን መጻሕፍት ላልጻፏቸው ለሌሎች በመስጠት ሊበቀላቸው የፈለጋቸውን ግለሰቦች ወንጀል ለማክበድ ጥረት አድርጎ ለጊዜው ተሳክቶለታል፡፡ አንዳንዶቹን በማኅበር ስም እና በራሳቸውም ስም በተመሳሳይ ነጥቦች ሁለት ጊዜ የከሰሳቸው ሰዎች አሉ፡፡ ለብዙዎች ማኅበራትና ግለሰቦች የሰጠው ሥዕልም የሌለና ምእመናንን ለማወናበድና ተሐድሶ ሲል በፈረጃቸው ላይ እንዲነሡ የቀሰቀሰበት ፕሮፓጋንዳው እንደሆነ ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡፡ ይህን አስመልክቶ ማቅ “ያስወግዛሉ” ብሎ ያቀረባቸውን የክስ ዝርዝሮች ስንመለከት ማኅበሩ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተሠረተ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተከታይ ሳይሆን በልማዳዊ አስተሳሰብ ላይ የቆመ ድርጅት መሆኑን ያሳየ ሆኖ አልፏል፡፡

ማቅ እንዲወገዙለት ክስ አቅርቦባቸው የነበሩት ማኅበራት 8፣ ግለሰቦች ደግሞ 9 ናቸው፡፡ የግንቦቱ ስሜታዊ ሲኖዶስ በጅምላና በጭፍን “አውግዣለሁ” ያላቸውን ግለሰቦች ግን 16 አድርሷቸዋል፡፡ ማቅ ካቀረባቸው ግለሰቦች መካከልም የተዋቸው አሉ፡፡ በእያንዳንዳቸው ላይ ማቅ እንደሃይማኖቱ “ኑፋቄ” ብሎ ያቀረባቸውን ነጥቦች ድምር፣ በሊቃውንት ጉባኤ ማጣራት “ኑፋቄ” ተብለው የተጣሩ ነጥቦችንና ሲኖዶሱ ያጸደቃቸውንና “ኑፋቄ” የተባሉ ነጥቦችን ድምር በንጽጽር ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡


ተ. ቁ.
የማኅበሩ ስም
ኑፋቄ የተባሉ ነጥቦች ብዛት
ምርመራ
በማኅበረ ቅዱሳን
በሊቃውንት ጉባኤ
በቅዱስ ሲኖዶስ
1
ከሣቴ ብርሃን
35
28
28
ማቅ ኑፋቄ ያላቸው 7 ነጥቦች በሁለቱ እንደ ኑፋቄ አልተወሰዱም
2
ማኅበረ ሰላማ
5
6
6
በማቅ ላይ 1 ተጨምሯል
3
የምሥራች አገልግሎት
12
4
4
ማቅ ኑፋቄ ያላቸው 8 ነጥቦች በሁለቱ እንደ ኑፋቄ አልተወሰዱም
4
የቅ/ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር
6
2
2
ማቅ ኑፋቄ ያላቸው 4 ነጥቦች በሁለቱ እንደ ኑፋቄ አልተወሰዱም
5
አንቀጸ ብርሃን
14
11
11
ማቅ ኑፋቄ ያላቸው 3 ነጥቦች በሁለቱ እንደ ኑፋቄ አልተወሰዱም
6
የእውነት ቃል አገልግሎት
8
9
9
በማቅ ላይ 1 ተጨምሯል
7
ማኅበረ በኩር
11
6
6
ማቅ ኑፋቄ ያላቸው 5 ነጥቦች በሁለቱ እንደ ኑፋቄ አልተወሰዱም
8
የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ማኅበር
-
-
-
በሁሉም ኑፋቄው አልተጠቀሰም

ከማኅበራቱ ባሻገር በግለሰቦች ላይ የተመሰረተው ክስ በዝርዝር ሲቀርብ የሚከተለውን ይመስላል
ተ. ቁ.
የግለሰቡ ስም
ኑፋቄ የተባሉ ነጥቦች ብዛት
ምርመራ
በማኅበረ ቅዱሳን
በሊቃውንት ጉባኤ
በቅዱስ ሲኖዶስ
1
መጋቤ ጥበብ ሰሎሞን
11
14
14
ማቅ ኑፋቄ ባለው ላይ 3 ተጨምሯል
2
ዲያቆን ጽጌ ስጦታው
30
10
10
ማቅ ኑፋቄ ያላቸው 20 ነጥቦች በሁለቱ እንደ ኑፋቄ አልተወሰዱም/ ተቀንሰውበታል
3
ዲያቆን አሸናፊ መኮንን
23
-
-
ማቅ በአንቀጸ ብርሃን ስር የዘረዘረውን ነውና የደገመው ሁለቱ አልደገሙትም
4
ዲያቆን ደረጀ ገዙ
8
6
6
ማቅ ኑፋቄ ያላቸው 2 ነጥቦች በሁለቱ እንደ ኑፋቄ አልተወሰዱም
5
ዲያቆን ደረጀ ገዙ እና በዛ ስፈርህ
10
-
-
ማቅ ኑፋቄ ያላቸው 10 ነጥቦች ሳይጠቀሱ ግለሰቦቹ ተወግዘዋል
6
ዲያቆን አግዛቸው ተፈራ
11
8
8
ማቅ ኑፋቄ ያላቸው 3 ነጥቦች በሁለቱ እንደ ኑፋቄ አልተወሰዱም
7
“አባ” ዮሐንስ ቢያዝን
1
-
-
በሁለቱ ስሙ አልተጠቀሰም፡፡ አልተወገዘምም
8
ዲያቆን ግርማ በቀለ
7
-
-
ማቅ በእውነት ቃል አገልግሎት ስር የዘረዘረውን ነውና የደገመው ሁለቱ አልደገሙትም
9
ዲያቆን በጋሻው ደሳለኝ
17
1
1
ሁለቱ 1 ነጥብ ብቻ አንስተው ወደፊት ተጠርቶ እንዲጠየቅና እንዲጣራ ተወስኗል
10
አባ ወልደትንሣኤ /ወልደ ሥላሴ አስገዶም
-
-
-
የማኅበረ ሰላማ መሥራች
11
አቶ መስፍን
-
-
-
የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር መሪ የተባለ
12
ዲያቆን አጥናፉ መኮንን
-
-
-
የየትኛው ማኅበር አባል እንደሆነ፣  ምን ኑፋቄ እንደተገኘበት አልተጠቀሰም
13
ዳንኤል ተሾመ
-
4
4
የዲያቆን አሸናፊ መኮንን ባልደረባ ተደርጎ ነው የቀረበው፤ ነገር ግን  ሁለቱ ፈጽሞ የማይተዋወቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል
14
ስዩም ያሚ
-
-
-
የእውነት ቃል አገልግሎት መሪ የተባለ
15
ስብሐት ለአብ
-
-
-
አለቃ መሠረት ስብሐት ለአብን ለማለት እንደ ሆነ ግልጽ አይደለም፤ ነገር ግን የተባለው “ስብሐት ለአብ” ነውና ምናልባት አባታቸውን አውግዘው እንዳይሆን የሚል ስጋት አለ፡፡
16
ተስፋ ተገኝ
-
-
-
ምን ኑፋቄ እንደተገኘበት አልተገለጸም
17
ብሥራት ጌታቸው
-
-
-
ምን ኑፋቄ እንደተገኘበት አልተገለጸም
18
መምህር ተስፋ ዓለም
-
-
-
ምን ኑፋቄ እንደተገኘበት አልተገለጸም
                                       
ምንም እንኳን በከሳሹ፣ በአጣሪውና በወሳኙ አካላት “ኑፋቄ” ተብለው የቀረቡ ነጥቦች ቢኖሩም፣ ማቅ ያቀረባቸው በሊቃውንት ጉባኤውና በሲኖዶስ ከቀረቡት ይበልጣልና በአንድ በኩል ማቅ ሃይማኖትን ሃይማኖት ካልሆነው መለየት የማይችል የጨዋዎች ስብስብ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል የሊቃውንት ጉባኤውም ሆነ ስሜታዊው ሲኖዶስ በነቢያትና በሐዋርያት ትምህርት መሠረት፣ እንዲሁም በሊቃውንት ትምህርት መሰረት ሳይሆን፣ የኖረውን ልማዳዊ ትምህርት መሰረት ያደረገ፣ ህግንና ስርአትን ያልተከተለ «ውግዘት» በማሳለፋቸው በሃይማኖት ጉዳይ እነርሱም “ከእጅ አይሻል ዶማ” መሆናቸውን ያስመሰከሩበት ትልቅ አጋጣሚ ሆኖ አልፏል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን መቼም የጨዋዎች ስብስብ ስለሆነ ስለሃይማኖት ያሻውን ቢል፣ በማያገባው መግባቱ ቢያስጠይቀው እንጂ የሃይማኖትን ትምህርት ያልዋለበት በመሆኑ፣ ሃይማኖት ያልሆነውን ጉዳይ ሃይማኖታዊ አድርጎ ቢያቀርብ አይፈረድበትም ይሆናል፡፡ የሊቃውንት ጉባኤው ያጣራው ድምዳሜውና ስሜታዊው ሲኖዶስ ያንን አንብቦ ከላይ በተዘረዘሩት ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ የወሰነው ውሳኔና ያስተላለፈው ውግዘት በምን መስፈርት መሰረት የተከናወነ ይሆን? እንዲህ ያለ የጅምላ ውግዘት የተከናወነበት የታሪክ አጋጣሚስ ይኖር ይሆን ወይ? የተወገዙት ማኅበራትም ሆኑ ግለሰቦች ሕጋዊ የሆኑ፣ የየራሳቸውን መንፈሳዊ ተግባር የሚያከናውኑ ሲሆኑ በውግዘት ሊፈርሱም ሆነ የጀመሩት አገልግሎት ሊደናቀፍ እንደማይችል አለመገመት ከምን የመነጨ ይሆን? የእምነት ነጻነት በታወጀባት አገር ላይ ከእኔ በቀር ሌላው ተሳስቷልና አይኑር አይነት አካሄድ፣ ጊዜ ያለፈበት በኢትዮጵያ ላይ አሁን የማይሰራ ያረጀ ያፈጀ አስተሳሰብ ነው፡፡  

የሲኖዶሱ የውግዘት ቃለ ጉባኤ መግቢያ የቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት በነቢያትና በሐዋርያት ትምህርት የተመሠረተና በሊቃውንትም የተስፋፋና ከዘመናችን የደረሰ መሆኑን ያትታል፡፡ አክሎም “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዐራተኛው መቶ ዓመት በኒቅያና በቁስጥንጥንያ፣ እንዲሁም በአምስተኛው መቶ ዓመት በኤፌሶን በተደረጉት ጉበኤያት የተወሰኑትን ተቀብላ አጽንታ በመያዝ የምታስተምር ናት፡፡” ብሏል፡፡ ታዲያ ይህ መች ያጣላ ነበር? ቤተክርስቲያኗ የምትናገረው ሌላ፣ የምትኖረው ደግሞ ሌላ መሆኑ ከፋ እንጂ፡፡ በመሰረቱ የቤተክርስቲያኗ አቋም ይህ ከሆነና በነቢያትና በሐዋርያት ትምህርት፣ እንዲሁም በዚያ ላይ በተመሰረተው የሊቃውንት ትምህርት ላይ ከቆመች እኮ አውጋዡም ተወጋዡም ክፍል ያን ያህል ልዩነት የላቸውም፡፡ ያለያያቸው በነቢያት፣ በሐዋርያትና በሊቃውንት ትምህርት ላይ የተጨመሩና በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ ስሕተት ሆነው የሚገኙ ሐሰተኛ ትምህርቶች ናቸው እኮ!

ሰይጣን የሚመጣው የብርሃንን መልአክ መስሎ ነው፡፡ አሊያ ማንም አይቀበለውም፡፡ አስመሳዮችም የሀዋርያት ትምህርት ተከታይ ሳይሆኑ የሐዋርያት ትምህርት ተከታይ ነን በማለት ያወናብዳሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ የሐዋርያትን ትምህርት ሳትይዝና ከዚያ አፈንግጣ ሳለ ራሷን እንደሐዋርያት ትምህርት ባለአደራ ብትቆጥርና ከነቢያትና ከሐዋርያት ትምህርት፣ ከሊቃውንቱም ትምህርት አላፈነገጥሁም፤ የቆምኩት በዚያ ላይ ነው ብትል ተቀባይነት የለውም፡፡ ነኝ ብሎ መናገር ሌላ፣ ሆኖ መገኘት ደግሞ ሌላ ነው፡፡ እንዲህ ባለ አጋጣሚ ስትፋጠጥ ትምህርቷ የነቢያትና የሐዋርያት እንደሆነ፣ በዚያ ላይ ተመስርተው ሊቃውንቱ ያስተማሩትም እንደሆነ ትናገራለች፡፡ በተግባር ግን ያንን ተቃርና ነው የምትገኘው፡፡ እንዲያውም በአብዛኛው ያወገዘችው የነቢያትንና የሐዋርያትን፣ እንዲሁም የሊቃውንትን ትምህርት ነው፡፡ ስለዚህ ትክክለኛ ነኝ በማለት ብቻ ትክክለኛ መሆን አይቻልም፡፡ ትክክለኛነት በተግባር መፈተሽ አለበት፡፡

በተግባር ሲፈተሽ ቤተክርስቲያኗ ከቀደመው ትምህርት አፈንግጣ በስሕተት ትምህርቶች ተሞልታለች፡፡ ሊያስወግዝ የሚገባውን ስሕተት አጽድቃ፥ ሊያስመሰግን የሚገባውን እውነት አውግዛለች፡፡ መያዝ የሚገባትን እውነት ጥላ መጣል የሚገባትን ሐሰት ይዛለች፡፡ ሃይማኖትን ሃይማኖት ካልሆነው ነገር መለየት የማይችልና ገድል ጠቃሽ የሊቃውንት ጉባኤና ሲኖዶስ ያላት ቤተክርስቲያን መጨረሻዋ ምን ይሆን? ዛሬም የብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስን ንግግር ደግሞ መጥቀስ ያስፈልጋል «በእርግጥ ቤተክርስቲያናችን አልሞተችም ብለን አንዋሽም»

በቀጣይ ከላይ በተዘረዘሩት ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ ኑፋቄ ተብለው በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰኑትን ነጥቦች ኑፋቄ መሆን አለመሆናቸውን በነቢያትና በሐዋርያት ትምህርት፣ እንዲሁም ቤተክርስቲያኗ እመራበታለሁ ስትል በፎከረችባቸው በሶስቱ ጉባኤዎች ውሳኔዎች በቅደም ተከተል እየፈተሽን እናቀርባለን፡፡

ይቀጥላል       

  

18 comments:

 1. the protestants said so!!!!but your dream/vision will be practical IF AND ONLY IF THE LOGIC (PROTESTANT = ORTHODOX) WORKS, WHICH IS LIKE SAYING PARALLEL LINES MEET EACH OTHER.

  ReplyDelete
 2. የኢትዮጵያ ህዝብ አብዛኛው የኢንተርኔት ተጠቃሚ አይደለም፡፡ ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ጠቃሚ ጽሁፎችን በቡክሌት ወይም በአነስተኛ መጽሄት እያዘጋጃችሁ ለህዝቡ ብታቀርቡ ጥሩ ነው፡፡ ሌላው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ብታሳውቁን ለአገልግሎቱ የአቅማችንን ያህል ልናዋጣ እንችላለን፡፡ ጥሩ አቀራረብ ነው በርቱ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለሕዝብህ መርዝ አሰራጩ የምትል አንተ ማነህ
   አርዮስ ልበልህ ወይስ ንስጥሮስ ይሁዳስ ልበልህ
   እንዴዉ ወደር የለሽ እራሱን ሰይጣን ነህ።

   Delete
 3. የክርስቶስ ሰምራና ሌሎች መሰል ገድል በሚል ስም የተደረቱ ታሪኮች የብዙ ሊቃዉንትን አንገት የሚያስደፉና የቤተ ክርስቲያኗን ገጽታ ያበላሹ መሆናቸዉ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ እያለ ዛሬም ድረስ ለዚህ ድርሰት ጠበቃ ሆናችሁ የቀረባችሁ ሰዎችን በማየቴ በእጅጉ ተገርሜአለሁ፡፡ አንዳንዶች ይባስ ብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ የተነገሩ ተአምራቶችን እየጠቀሱ እግዚአብሔር የሰራዉን እዉነት የክርስቶስ ሰምራ ግድል ደራሲ ከደረተዉ ድሪቶ ጋር ለማነጻጸር ሞክራችኋል፡፡ እዚህ እየተባለ ያለዉ፣ እግዚአብሔር ለሰዉ የማይቻልና ከአዕምሮ በላይ የሆነ ነገርን መስራት አይችልም ሳይሆን፣ ማንኛዉም አይነት ገድልም ሆነ መንፈሳዊ ይዘት ያለዉ ጽሑፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ከተቃረነ ተቀባይነት ሊኖረዉ አይገባም ነዉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምህሮ መሰረት አድርጎ ብዙ አስተማሪ የሆኑ መጻህፍትን ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ የበሬ ወለደ ተረትና ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለዉ ከሆነ ግን አይጠቅምም ነዉ የጸሐፊዉ አላማ የሚመስለኝ፡፡ በተረፈ ግን ብዙ የዋሆች፣ ሁሉ ነገር ኢትዮጵያዊ እንዲሆን አትፈልጉ( አንዳንዴ ክርስትና ራሱ ከየት እንደተጀመረ ድሮ በታሪክ ትምህርት የተማራችሁትንም አስታዉሱ)፡፡ ክርስቲያኖች እኮ በሌላም አገር አሉ( ኢትዮጵያዊ የሆኑትን እነ ክርስቶስ ሰምራም ሆነ እነ ተክልዬን የማያዉቁ) ታዲያ እነዚህ እንዴት የሚድኑ ይመስላችኋል? አጼ ዘረ ያዕቆብ ከገዳም ወጥቶ ንጉስ ሲሆን ስሙን ለማስጠራት በየገዳሙ ሰዎችን ቀጥሮ ያስደረሳቸዉን የፈጠራ ታሪኮች አዉጥተን መጣል አቅቶን ገድል በሚል ስም ሸፋፍነን ይዘን እነሱን ብቻ በመተረክ እዉነተኛ የሆነዉን የአምላካችንን ቃል መጽሐፍ ቅዱስን ወደጎን ስንገፋ መኖራችን ትልቅ ኪሳራ መሆኑ ተዘንግቶ ዛሬም ለዚህ ድሪቶ ታሪክ ዘብ መቆማችን የሚያሳየዉ ሰይጣን በዚያ ዘመን የዘራዉ ክፉ ስራ ፍሬ አልባ ሆኖ ያልቀረ መሆኑን ነዉ፡፡
  “ክርስቶስ ሰምራ ሰይጣንንና እግዚአብሔርን ለማስታረቅ አስባ ሐሳቧን ለእግዚአብሔር ስትነግረዉ፣ ‘’እሺ ይላል ብለሽ ነዉ? እሺ ካለ ምን ቸገረኝ” ብሎ እግዚአብሔር ተስማማ፤ ከዚያም ክርስቶስ ሰምራ ወደ ሲኦል ሔዳ ሳጥናኤል.. ሳጥናኤል ብላ ስትጠራዉ ”ማነዉ በድሮ ስሜ የሚጠራኝ ?” ብሎ በመዉጣት ክርስቶስ ሰምራን አገኛት፣ ከእግዚአብሔር ጋር ልታስታርቃቸዉ እንደምትፈልግ ስትነግረዉ ሰይጣን ተበሳጭቶ ክርስቶስ ሰምራን ወደ ሲኦል ገፍትሮ ጣላት ከዚያም እግዚአብሔር መልአክ ላከላትና መልአኩ ከሲኦል ሲያወጣት ብዙ ነፍሳትን ከሲኦል አዉጥታ ወደ መንግስተ ሰማያት አስገባች” የሚል ታሪክ አሁን በእዉነት ድሮ ልጆች ሆነን ከምንሰማዉ ተረት በምን ይለያል? በእዉኑ ሰይጣንና እግዚአብሔርን ማስታረቅ ይቻላል? የገድሉ ደራሲ ግን ሰይጣን ነዉ እንጅ ያልተስማማዉ እግዚአብሄር ግን ለመታረቅ ተስማምቶ እንደነበረ ሳያፍር ጽፏል፡፡ በእዉነት አንዴ በሰራዉ ስራ ተመዝኖ ወደ ሲኦል የወረደን ነፍስንስ በዚህ መልክ ወደ መንግስተ ሰማያት ገባ ማለት በእግዚአብሔር ስራ ላይ መዘባበት አይሆንም? እግዚአብሔርን በጠባብ አዕምሮአችን እንደምናስበዉ አንወስነዉ፡፡ እርሱ የዩንቨርስ ሁሉ ፈጣሪ ነዉ፡፡ ሁሉን ነገር ኢትዮጵያዊ እያደረግን አሁንማ እግዚአብሄርም በኢትዮጵያ ምድር ብቻ የሚኖር እያስመሰልነዉ ነዉ፡፡ ለዚያም እኮ ነዉ በየትም አለም ተስምቶ የማያዉቅ ጉድ፣ ሰዉ እግዚአብሔርን ከሰይጣን ለማስታረቅ ሞከረ ተብሎ ለመናገር የተቻለዉ፡፡ ተስፋን ለማመስገን እወዳለሁ፡፡ ወደፊትም በርታ ፣ሌሎች ተጨማሪ የህዝባችንን ትክሻ ያጎበጡ ገደል ተብዬ የሐሰት ድሪቶዎችንም በማጋለጥ እንደምታስነብበን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
  ማስረሻ ይዘንጋዉ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድም ማስረሻ ያቀረቡት አስተያየት በጣም ተገቢና አጥጋቢ ነው፡፡

   Delete
 4. The Ethiopian Orthodox Church is to be honored for the Christian legacy it has maintained in Ethiopia across the centuries but this legacy needs to be ignited once more with the truth of the gospel, and the fire of the Holy Spirit. We all pray for revival in this church to reach and renew all corners of Ethiopia!

  ReplyDelete
 5. እስቲ ጨርሱትና እንመልከተው!ይህንን ማህበር በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት በህግ ፊት የሚያቆመው ጠፍቶ ነው እኮ እነዚህ ተሀድሶ የሚባሉትም ልብ የላቸውም እኮ ወሬና መጻፍ ብቻ ነው::ቢተባበሩ እንኳን ጸጥ ያሰኙት ነበር እኮ:ፈጽሞ በህግ መቀመቀም የሚከተውን ሥራ እየሰራ ነው ያለውና!ዋጋውን ያገኛል::
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ ካንተ ጀምሮ የትኛው ጴንጤ ነው ሲተባበር ያየኸው? እንደ አሜባ በየቀኑ ከመበጣጠስ ውጪ ስለዚህ እነዚህም ቀጣሪዎቻቸው የተለያዮ የማይስማማሙ ስለሆኑ መተባበር አይችሉም መቼም። አንድ የሚያስማማቸው ነገር ቤ/ያኗን ለማፍረስ በተለያየ አቅጣጫ መጣራቸው ብቻ ነው እንጂ አንድ አይነት አመለካከት ኖሯቸው አያውቅም ወደፊትም አይኖርም።

   Delete
 6. አባ ሰላማዎች፤ የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ወደ ቀድሞ ስፍራዋ(ቅድስናዋ) እንድትመለስ የምንፈልግ ብዙዎች ነን፡፡ ስለዚህ በቤተክርስቲያን ውስጥ ተሀድሶ እንዲደረግ ወይም ለክርስትና ባዕድ የሆኑ ነገሮች እንዲወገዱ የምንጥር ሰዎች በአንድ መድረክ የምንሰባሰብበትን ሁኔታ ብታመቻቹልን መልካም ነው፡፡ ከአሁን በኃላ በጎ ሀሳባችንን በድብቅ ሳይሆን ፊት ለፊት መግለጽ ይኖርብናል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምን እያልክ ነው ደግሞ ? ጉባዔ አርድዕት የሚባለው እንኳን በህቡዕ እንደሚሠራ አላነበብክም ? የምን አደባባይ ታወራለህ ? ሃሳቡ ካለህ ከሁለት ሳምንት በኋላ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት ይሰበሰባሉና ቀድመህ ጠብቃቸው ፡፡

   Delete
 7. aklabat BETEKERSTIANUAN KEBEBEUAT NEGERGEN YE GEHANEM DEGOCH AYCHELUATEM MK MAN YAKOMEWE NEWE YEMIMESLACHU KIDUSU EGEZEABEHER NEWE (ENE MARTIN LUTER EKO AYDELUM) ENANT YEKhADI LEGOCH)ke diabilos KEMAN YEWERESACHUT NEWE YE diabilos WEGENOCH MEONACHUN EKO GELETSACHUAL: diabilos ENDEMAYETNGA ENAWEKALEN

  MK ENDEHON YE MENEFES KIDUSEN YOTER LEBES LEBESUAL

  ReplyDelete
 8. You guys are working hard to destroy our church. ይበላኝ ለእናንተ እንጂ አለት በሆነዉ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስለተመሰረተች ቤተክርስቲያን ምንም አትሆንም
  እናንተም ታልፋላቸሁ ኑፋቄያችሁም አብሮአችሁ ያልፋል
  ባይሆን ልቦና ሰጥቶአችሁ በንስሃ ለመመለስ ያብቃችሁ

  ReplyDelete
 9. አስመሳዮችም የሀዋርያት ትምህርት ተከታይ ሳይሆኑ የሐዋርያት ትምህርት ተከታይ ነን በማለት ያወናብዳሉ፡፡---
  ነኝ ብሎ መናገር ሌላ፣ ሆኖ መገኘት ደግሞ ሌላ ነው፡፡
  ደግ ብላችዃል!!!!!!!!

  ReplyDelete
 10. እለቀቁ ነው የተባላቹህት። ዉግዘቱም ይሄው ነው ። እንጂ የፈለጋችሁትን አታምልኩ አይደለም ።አሁንም ቢሆን ነቅተናል አውቀናችኋል ማንንም አታስቱም ዝምብላቹህ አትድከሙ ።የእኛንም መብት አትጋፉ ። መናፍቃን ናቹህ ተጠራጥራቹህ /ክዳቹህ/ ከ ኦርቶዶክስ የወጣችሁህ ናቹህ ስለዚህ መወገዝ ይገባችኋል።ምንፍቅናችሁንም ከሥራቹህ እያየን ነው ። ሌላ ምስክር አንሻም ። ዝም ብላቹህ ማቅ ማቅ አትበሉ እሱንም ማህበር እናውቀዋለን ።የራሱ ችግር ቢኖርበትም ቢያንስ ማቅ የምግባር እንጂ የሃይማኖት ችግር እንደሌለበት እናውቀዋለን። ማቅን በምንም መንገድ በሃይማኖት አትከሱትም።እናንተ ግን ዋናውን አጣችኋል ሃይማኖት የላችሁም የተከተላችሁት ሃይማኖት ስህተት ነው ። ትክክል አይደለም ።እግዚአብሔር ወደ ልባችሁ ይመልሳችሁ

  ReplyDelete
 11. እኔ ያልገባኝ ነገር እዉነተ መናገር ሀጢያት ነዉ እንዴ አባ ሰላሞች በርቱ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሁሉ ከእናንተ ጋር ነዉ ማቅን ርሱት የበሄርተኞችና አና የፖሎቲከኞች ስብስብ ነዉ ቢይመሽም መንጋቱ አይቀርም ደብተራሁንና መተተኛሁን ጠንቆያሁን ተረት ተረት ሚያዉራሁን ከምኩራብ ማበረር ወይም ልቡን ለክርሰቶስ እንዲይሰጥ ማድርግ ያስፈልጋል አባቶቻችን ላይ የቀለዱት ይበቃል እኛ እንሸዉድም ነቅተናል አድሚዩ ለቅዱሱ ቃሉ እና ለእምላካችን ይሁን

  ReplyDelete
 12. አባ ሰላማዎች ምነው ዕኮ ጌታ ኢየሱስ ክርቶስን ለማወቅና ስሙን ለመጥራት ለተሳነው በባልቴት ተረታተረት ለተካነው ማቅ ድጋፍ ይሆን ዘንድ ዕውነተ ገፍ ገድላገድልን አየጣጣፋችሁ ታስነብባላችሁ
  ይገርማል ይህን ያነበበ ሁሉ ሊጸደቅ ወደ ባሕር ልጥለቅ፤በከንቱ ለመሞገስ ወደ ከንቱ መወደስ፤
  ልገሥግስ ልድረስ ይላልና ለሚነበበው ትኩረት በመስጠት ፈንታ ለማይነበበው አንክሮ መስጠት እናንተና እነርሱ ልዩነታችሁ የት አለ??እስመ አይሁድኒ ተአምረ ይሴአሉ ወጽርዕኒ ጥበበ የኀሥሡ(አይሁድ ታምራትን ግሪኮች ጥበብን ይፈልጋሉ ይጠይቃሉ)እንደተባለው 1.ቆሮ 1.22.የዚያኛው ደጋፊዎች እነዚያን ሲሆኑ የዚህኛው ደጋፊዎች እነዚህን መሆናቸው አይቀርምና እውነት ያለው ትምህርት በመካከል
  ሳይነገር ባልሆነ ትምህርት ተውጦና ዘቅጦ እንዳይዘገይ ያሰጋል በመሆኑም እናስብበት!

  ReplyDelete
 13. wonderful continue

  ReplyDelete