Saturday, July 14, 2012

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 3
ማኅበረ ቅዱሳን ከሶ፣ የሊቃውንት ጉባኤ አጣርቶ፣ የግንቦቱ ስሜት መራሽ ሲኖዶስ ያወገዛቸው ማኅበራትና ግለሰቦች የተገኘባቸው ኑፋቄ ምን ይሆን? ኑፋቄ ተብለው የቀረቡት ነጥቦች ሁሉ በእርግጥ ኑፋቄ ናቸው? ወይስ ኑፋቄ አይደሉም? ኑፋቄ ካልሆኑ እንዴት ሊያስወግዙ ቻሉ? ሲኖዶሱ ለማውገዝ መስፈርት ያደረገው፣ በመግቢያው ላይ እንደተናገረው የሐዋርያትንና የነቢያትን ትምህርት ነው? የሊቃውንትንስ ትምህርት መሠረት ያደረገ ነው? የሦስቱን ጉባኤያት ውሳኔዎችንስ ያገናዘበ ነው ወይስ ከዚያ ውጪ የተካሄደ ነው? የሚሉትና የመሳሰሉት ጥያቄዎች በግንቦቱ ሲኖዶስ ለተላለፈው ስሜታዊ ውግዘት ሊቀርቡ የሚገቡ ዋና ዋና ትያቄዎች ናቸው፡፡
የሲኖዶሱ ውሳኔ ቃለ ጉባኤ መግቢያ፣ ውግዘቱ ከላይ የተጠቀሱትን መሠረታዊ ነገሮች ያገናዘበ መሆኑን ቢናገርም፣ እውነታው ግን ከዚያ በተቃራኒ መሆኑን በዚህ ክፍልና በተከታታይ በምናቀርባቸው ግምገማዎች ለማሳየት እንሞክራለን፡፡ ምንም እንኳን ቀድሞም ቢሆን ለሃይማኖት ማስረጃነት ተአምረ ማርያምን የመሳሰሉ አዋልድ መጻሕፍትን እየጠቀሱ ለመከራከር የደፈሩ ገድል ጠቃሽ «ሊቃውንት» ባይጠፉም፣ ቤተክርስቲያኗ አራቱን ጉባኤ ብቻ ለሃይማኖት ትምህርት አስረጂ አድርገው የሚያቀርቡ ሊቃውንትና ነገሥታት ያለፉባት ቤተክርስቲያን ነበረች፡፡ አጼ ዮሐንስ በዘመናቸው በተደረገው ሃይማኖታዊ ክርክር ተአምረ ማርያምን ማስረጃ አድርገው የጠቀሱትን አንዱን ገድል ጠቃሽ «ሊቅ»፣ «ከአራቱ ጉባኤ አጣህና ስለሃይማኖት ተአምረ ማርያምን ትጠቅሳለህን?» ማለታቸውን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ መጽሐፋቸው ጽፈውታል፡፡  እንደእነዚህ ያሉ ደገግ ነገሥታትና ሊቃውንት የነበሩባት ቤተክርስቲያን ያን ሁሉ ክብሯን አጥታና ተጠያቂ ሊቅ የሌላት መስላ ስትታይና ሊወገዙ በሚገባቸው የአዋልድ መጻሕፍት ትምህርት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትንና እውነተኞችን ስታወግዝ ከማየት የበለጠ ውድቀት ያለ አይመስለንም፡፡

ሶስቱ ጉባኤዎች አርዮስን ንስጥሮስንና መቅዶንዮስን ያወገዙት ከሃይማኖት አንጻር ነው፡፡ ሃይማኖትም የሚባለው ትምህርተ ሥላሴ እና ትምህርተ ሥጋዌ ነበር፡፡ ዛሬ ግን የቱ ሃይማኖት እንደሆነ፣ የቱ እንዳልሆነ መለየት አልተቻለም፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ማኅበራትንም ሆነ ግለሰቦችን «አስወገዙ» የተባሉት ብዙዎቹ ነጥቦች ሃይማኖት ሆነው አልተገኙም፡፡ እንዲያውም በሃይማኖት ላይ የተደረቱ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የሚቃረኑ፣ በቤተክርስቲያን ውሳኔ ሳይሆን በልዩ ልዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በሀይል ወደቤተክርስቲያን የገቡና በሂደት ተቀባይነት አግኝተው እንደእውነተኛ ትምህርት የተወሰዱ ናቸው፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል ቢፈተሹ አስቀድመው በሀዋርያት ሥልጣን የተወገዙ፣ ዛሬም የሚወገዙ ናቸው፡፡

ይህን መስመር የሳቱት የሊቃውንት ጉባኤውና የጳጳሳቱ ጉባኤ ነገሮችን በእግዚአብሔር ቃል ከመፈተሽ ይልቅ፣ እስከ ዛሬ የያዝነው ሁሉ ምንም ይሁን ምን ጥያቄ ሊነሳበት፣ ሊተችም አይገባም የሚል አቋም ነው የያዙት፡፡ እንዲያውም በድፍረት «ትምህርተ ሃይማኖት ዘኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን መጠበቅ ድኅነትን ያስገኛል፤ በረከትንም ያሰጣል፡፡» (ገጽ 5) ተብሎ በጳጳሳቱ ቃለ ጉባኤ ላይ ሰፍሯል፡፡ እውን እንዲህ ይባላል? ሰው የሚድነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን እውነተኛ ትምህርት በመቀበል፣ በዚያው መሰረት በመኖር፣ ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመንና በእርሱ በመኖር እንጂ በአንድ ሃይማኖታዊ ተቋም አስተምህሮ ነው እንዴ? አሁን የተያዘው ውጥንቅጥና ወደ ሕይወት ሳይሆን ወደሞት የሚወስደው ትምህርት በእግዚአብሔር ቃል መስተካከል አለበት ነው እየተባለ ያለው፡፡ መቼም መንግስተ ሰማያት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ኖሮ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጓሮ መቀበር ነው ካልተባለ በቀር፣ አሁን ባለውና ሲኖዶሱ በውግዘቱ ውስጥ ባንጸባረቀው ትምህርት መሰረት ውድቀት እንጂ ትንሣኤ፣ ሞት እንጂ ሕይወት፣ ጥፋት እንጂ ልማት፣ ሲኦልና ገሃነመ እሳት እንጂ ገነትና መንግስተ ሰማያት እንደማይገኙ መጽሐፍ ቅዱስም በጎ ኅሊናም ምስክር ናቸው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ያቀረበው የክስ መዝገብ ውስጥ በማኅበራቱ እና በግለሰቦቹ ዙሪያ ያቀረባቸው ብዙዎቹ መረጃዎች በእውነታ ላይ ያልተመሰረቱ፣ የተጋነኑና የፈጠራ ናቸው፡፡ በዚያ ላይ ጊዜ ማጥፋቱ ግን ብዙ አልታየንም፤ የእኛም ጉዳይ አይደለም፡፡ አንዳንዶቹን ግን እንደአስፈላጊነቱ ኑፋቄ ከተባሉት ነገሮች ጋር አያይዘን ለማቅረብና ማቅ ሆነ ብሎ የሊቃውንት ጉባኤውንና ሲኖዶሱን ለማሳሳት እንደተጠቀመበት እናሳያለን፡፡ በዋናነት የእኛ ትኩረት ግን ኑፋቄ የተባሉት ነጥቦች ይሆናሉ፡፡ ከተወገዙት ግለሰቦች መካከልም ሊያስወግዝ የሚችል ኑፋቄ የጻፉም ሊኖሩ ስለሚችሉ የእነርሱንም ስሕተት ለማሳየት እንሞክራለን፡፡

ለሁሉም ነጥቦቹን የምንመዝንበት መመዘኛዎቻችን የነቢያትና የሀዋርያት ትምህርት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሊቃውንት ትምህርቶች፣ የሦስቱ ጉባኤዎች ውሳኔ የሆነው ጸሎተ ሃይማኖት ናቸው፡፡ በዚሁ መሰረት በቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ጉባኤ ላይ በተቀመጡበት ቅደም ተከተል መሰረት የተወገዙት ማኅበራት ጻፏቸው የተባሉትን «ኑፋቄዎች» ከዚህ ቀጥሎ እንፈትሻቸዋለን፡፡

1.    ከሳቴ ብርሃን
በዚህ ማኅበር የተዘጋጀውና ገድል ወይስ ገደል ከተባለው መጽሐፍ ላይ ኑፋቄ ተብለው የተዘረዘሩት ነጥቦች፦
ሀ. «በሃይማኖት ላይ የተደረተ ሁሉ መፍረስ ሲያንሰው ነው» በማለት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናችንን በማጥላላት ተችተው ጽፈዋል፡፡ (ገጽ 6)” ስለተባለው፡፡
የሲኖዶሱ ቃለ ጉባኤ ከሣቴ ብርሃንን «ገድል ወይስ ገደል» በተሰኘው መጽሐፉ ሲያወግዘው፣ አገኘሁበት ያላቸው ኑፋቄዎች 6 ናቸው፡፡ አንዱም ግን የሚያስወግዝ ሆኖ አላገኘነውም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በሦስቱ ጉባኤዎች ውሳኔዎች ቢፈተሹም ኑፋቄዎች ሆነው አይገኙም፡፡ እንዲያውም ነገሮች በእውነት መሠረት ተከናውነው ቢሆን ኖሮ መወገዝ ያለበት ራሱ ሲኖዶሱ ነበር፡፡ ግን ምን ያደርጋል፤ የተወገዘው ኑፋቄ ሳይሆን እውነተኛ ትምህርት ሆነ፡፡

በቅድሚያ ገድል ወይስ ገደል «በሃይማኖታችን ላይ የተደረተ ሁሉ ግን መታደስ አይደለም መፍረስ ሲያንሰው ነው» ይላል፡፡ ስለዚህ ጥቀሱ በሊቃውንት ጉባኤውም ሆነ በሲኖዶሱ ቃለ ጉባኤ ላይ በትክክል አልተጠቀሰም፡፡ መውሰድ ያስፈለገው ቃለ ጉባኤው ያስፈረውን አረፍተ ነገር ቢሆን እንኳ ተቆርጦ የቀረውን የሚያመለክት ሦስት ነጥብ /…/ መካከል ላይ መቀመጥ ነበረበት፡፡ ነገር ግን የሊቃውንት ጉባኤውም ሆነ ሲኖዶሱ ለእውነት ያልቆሙና ግራ ቀኙን መስማት ያልፈለጉ በመሆናቸው፣ የሚፈልጉትን አረፍተ ነገር በሚያሳዝን ሁኔታ ቆርጠው በማውጣት፣ ጸሀፊው ያላለውን ነገር እንዲል አድርገው በሚፈልጉት መንገድ ለክስ አመቻችተዋል፡፡ በብዙዎቹ ተወጋዦች ላይ የተሠራው ይኸው ቆርጦ የመቀጠል ሥራ ነው፡፡ ዱሮስ ቢሆን የእግዚአብሔር መገለጥ በሆነው ሃይማኖት ላይ የተደረተ ነገር መፍረስ የለበትም ከሚል ሲኖዶስ ከዚህ ውጪ ምን ይጠበቃል!

ምንም ይሁን ምን፣ ጸሀፊው ለማለት የፈለገው ሌላ ነገር ቢሆን አንኳን፣ «በሃይማኖት ላይ የተደረተ ነገር ሁሉ መፍረስ ሲያንሰው ነው» መባሉ ለአንድ ሃይማኖተኛ ነኝ ለሚል ተቋም ጠቃሚ፣ ገንቢ፣ ተገቢ፣ ትክክለኛ እና እውነተኛ አስተያየት ነው እንጂ እንዴት ተደርጎ ቢነበብና ቢተረጎም ነው ኑፋቄ የሚሆነው? ለምንስ «… ሥርዓተ ቤተክርስቲያናችንን በማጥላላት ጽፈዋል፡፡» ብሎ ማከል አስፈለገ? ምክንያቱም አውጋዡ ክፍል በሚፈልገው መልኩ የመዘዘው አረፍተ ነገር ስለ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ሳይሆን ስለሃይማኖት ነው የሚናገረው፡፡ አንቀጹ ሲጀምር የሚለው «ታዲያ እግዚአብሔርን ማን ሊያርመው ይችላል?» በሚል ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ ሃይማኖት የእግዚአብሔር መገለጥ ከመሆኑ አንጻር ማንም ሊያርመው የማይችለው እውነት በመሆኑ ተቀብሎ መኖርና ለሕገ እግዚአብሔር መታዘዝ እንጂ፣ በራስ ወግና ልማድ እግዚአብሄርን ለማረም መሞከር ከባድ ሀጢአት ነው፡፡ ስለዚህ ቃለ ጉባኤው ኑፋቄ ብሎ ያሰፈረው «በሃይማኖት ላይ የተደረተ ነገር ሁሉ መፍረስ ሲያንሰው ነው» የሚለው አነጋገር ሃይማኖትን ለመጠበቅ የሚረዳ አስተያየት በመሆኑ ሊያስመሰግን እንጂ ሊያስወግዝ አይገባውም ነበር፡፡ በተቃራኒው ከታየ ግን እንዲያውም አውጋዡ «በሃይማኖት ላይ የተደረተ ነገር ሁሉ መፍረስ የለበትም» እያለ ነውና መናፍቁ ራሱ መሆኑን መስክሯል፡፡   

ለ. «ለእመቤታችን እና ለመስቀል ስግደት አይገባም»
ስግደት ከእግዚአብሔር ውጪ ለሌላ ፍጡር ይገባል ተብሎ የታወጀው መቼ ነው? በየትኛውስ ጉባኤ ነው? ጌታ ኢየሱስ በሰይጣን በተፈተነ ጊዜ አንዱ የቀረበለት ጥያቄ «ስገድልኝ» የሚል ነበር፡፡ የጌታም መልስ «ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፏል» የሚል ነበር፡፡ ሰይጣን ያን ጊዜ በፊት ለፊት ያጣውን ስግደት ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ የማርያምን ስም ተውሶና በዕንጨት መስቀል ውስጥ ተሰውሮ በአጼ ዘርአ ያዕቆብ በኩል አገኘው፡፡ እርሱ ማርያምና መስቀል ከፈጣሪ ጋር በክብር እኩል ናቸውና ስግደት ይገባቸዋል ሲል አወጀ፡፡ ይህ ትምህርት በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይደገፍ ይሆን?

በወቅቱ «ስግደት ለፈጣሪ እንጂ ለሌላ አይገባም፤ ተው!» ያሉትን እነ ደቂቀ እስጢፋኖስን አወገዛቸው፤ ብዙ መከራና ስቃይ አደረሰባቸው፡፡ «አጼ በጉልበቱ» ዘርአ ያእቆብ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውጪ አምልኮ ባእድን በሀይል ወደቤተክርስቲያን ሲያስገባ፣ ከደቂቀ እስጢፋኖስ በቀር ማንም ተው አላለውም፡፡ በኋላም ቤተክርስቲያን ያለማንገራገር ተቀብላ ስግደትን በማርያምና በእፀ መስቀል ስም ለራሱ ለሚያደርገው ለሰይጣን ማቅረቧን ቀጥላለች፡፡ እንዲህ የምንለው ዝም ብለን አይደለም፤ ዛሬ በማርያም ስም የሚደረገው ሁሉ የሚደርሰው ወደ ማርያም አይደለም፤ እመቤታችን አታውቀውም፤ በዚህ ነገር ውስጥም እጇ ፈጽሞ የለበትም፡፡ ነገር ግን በስሟ የሚነግደው ያው የቀድሞው እባብ ሰይጣን ነው፡፡ ታዲያ በማርያም እና በዕንጨት መስቀል ስም ስግደት ለሰይጣን መቅረብ የለበትም ማለት ሊያስመሰግን እንጂ ሊያስወግዝ ይገባል ወይ? በፍጹም!! ስግደት ብቻውን አምላክ ለሆነ ለእግዚአብሔር ብቻ እንጂ ለምንም ለማንም መቅረብ የለበትም፡፡ ታዲያ መናፍቁ ማነው?
 
ሐ.«የቅዱሳን አጽም ተአምር ለማድረግ ኀይል የለውም» በማለት ከጌታችን የተሰጣቸውን የቃል ኪዳን ኀይል አቃለዋል፡፡ ገጽ 66» 
ገጽ 66 ላይ እንደዚህ የሚል ቃል አልሰፈረም፡፡ እንዲህ አድርገው የጻፉት አውጋዦቹ ናቸው እንጂ መጽሐፉ እንዲህ አላለም፡፡ ይህ አይነቱ አቀራረብ የሊቃውንት ጉባኤው የሚከስበት ነጥብ ሲያጣና በጥቅስ መልክ የተቀመጠ መክሰሻ ሲጠፋ የራሱን ሐሳብ ጸሀፊዎቹ እንደጻፉት አስመስሎ በጥቅስ ውስጥ ያስቀምጣል፡፡ ዲ/ን አሸናፊን ጨምሮ ብዙዎቹን የከሰሰው በዚህ መንገድ ነው፡፡

«ገድል ወይስ ገደል» በገድለ ተክለ ሃይማኖት ላይ የተጻፈውን የማይመስልና የተጋነነ ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በመመዘን ተችቶታል፡፡ «አጥንቴንና ስጋዬን ዳስ» በሚለው በዚህ ርእስ ስር ስለተክለ ሃይማኖት አጽም የተነገረውን የማይመስል ነገር ተችቶ መጻፉ፣ ለቅዱሳን ተሰጠ ከተባለው ቃል ኪዳን ጋር ምን እንደሚያገናኘው ግልጽ አይደለም፡፡ ዛሬ ቤተክርስቲያኗ ልማዳዊ አሰራሮችን እውነተኛ አስመስላ ለማቅረብ በምታደርገው ጥረት ለቅዱሳን ቃል ኪዳን ተገብቷል ትላለች እንጂ፣ የሚባለው አይነት ቃል ኪዳን የለም፡፡ የመጨረሻው ቃል ኪዳን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ በዚያ ላይ የሚጨመር ሁሉ የክርስቶስን ሞት ከንቱ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ያልሆነ ቃል ኪዳን ነው፡፡

ደግሞስ የቅዱሳን አጽም ተአምር ለማድረግ ሀይል አለው ማለት ከየት የመጣ ትምህርት ነው? በቅዱሳኑ አድሮ ቢሰራ ሀይሉ የእግዚአብሔር እንጂ የቅዱሳኑ አይደለም፡፡ በኤልሳዕ መቃብር ላይ የተጣለው አስከሬን መነሳቱ፣ የቅዱሳን አጽም ሁሉ ተአምር ለማድረግ የተሰጠ ፈቃድ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡ እንዲህ ያደረገው ሀያሉ እግዚአብሔር ነው፤ መመስገንም መወደስም ስሙ መጠራትም ያለበት እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ የተክለ ሃይማኖት አጽም ጉዳይ የሃይማኖት ጉዳይ ተደርጎ ሊወሰድም ሆነ ሊያስወግዝ የሚችልበት ምክንያት የለም፡፡

መ. «ዐሠርቱ ቃላተ ኦሪትና ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን መጠበቅ አያስፈልግም» ብለዋል (ገጽ 92 እና 93)           
ገድል ወይስ ገደል በምዕራፍ አራት ተአምረ ማርያምን እየተቸ ጽፏል፡፡ ሲተችም ተአምረ ማርያም የጻፈውን ኑፋቄና ክህደት በምእራፉ ውስጥ ለተነተናቸው ሐሳቦች ርእስ አድርጎ ነው የተጠቀመባቸው፡፡

በትንሹ ተአምረ ማርያም ተአምር 12 ቁጥር 52-54 የሰፈረው ክህደት እንዲህ ይነበባል፡፡ «እንደእኔ ያላችሁ ኃጥአን ወንድሞቼ ሆይ! ከእንግዲህስ ወዲህ 16ቱን የህግ ትእዛዛት በመፈጸም የእግዚአብሔር ባሪያዎች ለመሆን አንሻ፤ እርሱ … እርሷን ሰጥቶናልና፡፡ ስለዚህ እላችኋለሁ የእናታችንና የእመቤታችን የማርያም ባሪያዎች ለመሆን እንሽቀዳደም … ይህችውም ማርያም ከልጇ ጎን በፈሰሰው ደሟ ንጹሐን ታደርገናለችና፡፡» ይላል፡፡

በዚህ ጥቅስ ላይ ተመስርቶ «ገድል ወይስ ገደል»፣
1.     «ከእንግዲህ ወዲህ»፣
2.    «፲ወ፮ቱ ቃላተ ወንጌል መጠበቅ አያስፈልገንም» … እያለ ጥቅሱን ይተቻል፡፡
ስለዚህ ከሳቴ ብርሃን በዚህ ነጥብ የተወገዘው አባባሉ የእርሱ ተደርጎ ቀርቦበት እንጂ የእርሱ ሆኖ አይደለም፡፡ የተአምረ ማርያም ነው፡፡ የሊቃውንት ጉባኤውና ሲኖዶሱ በዚህ ነጥብ እርሱን መክሰስ የሚችሉበት ጥቅስ ቢያጡ ከተአምረ ማርያም ቃል በቃል የወሰደውንና ሊተቸው ርእስ ያደረገውን አረፍተ ነገር «ዐሠርቱ ቃላተ ኦሪትና ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን መጠበቅ አያስፈልግም» ብለዋል ብለው አወገዟቸው፡፡ እንዲህ ማለት የሚያስወግዝ ቢሆንማ መወገዝ የነበረበት በመጀመሪያ እንዲህ ብሎ የጻፈውና ያስተማረው «ተአምረ ማርያም» የተባለው ልቦለድ መጽሐፍ፣ ደራሲውና አስደራሲው ዘርአ ያእቆብ ናቸው፡፡ ዛሬም ይህን ተአምር በቤተክርስቲያን የሚያነቡ፣ መወገዝ አለባቸው፡፡

ነገር ግን እውነትን አውጋዡ ሐሰትን አንጋሹ የሊቃውንት ጉባኤና ሲኖዶስ ከላይ የተጠቀሱትን ክፍሎች በማውገዝ ፋንታ ተአምረ ማርያም የያዘውን ኑፋቄ ያጋለጡትን ወገኖች አወገዙ፡፡ እንዲህ ሲባል ከዚህ በፊት ተአምረ ማርያም ላይ እርምጃ አልወሰዱም ማለት አይደለም፡፡ ውስጥ ለውስጥ ይህ ያፈጠጠ ስሕተት እንዲታረም ተደርጓል፡፡ የታረመ ተአምረ ማርያምም ታትሟል፡፡ እንዲታረም ካደረጉት መጻህፍት መካከልም ገድል ወይስ ገደል የተሰኘው መጽሐፍ አንዱ ነው፡፡ ተአምረ ማርያም የታረመውም «እስከ መቼ ያሰድበናል?» ተብሎ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ በሌላ በኩል የአጼ ዘርአ ያእቆብን ልቦለድ ማረም ነውና በኮፒ ራይት ሕግ የሚያስጠይቅ መሆን አለመሆኑ በሕግ ባለሙያዎች ቢታይ ጥሩ ነው፡፡ ማን የማንን ድርሰት ያርማል! ባይሆን እንደከሳቴ ብርሃን መተቸት (ሂስ መስጠት) ይቻላል፡፡ ታዲያ በዚህ ሂደት ውስጥ «ተአምሯ ለምን ታረመ? እንዳለ ነው መቀመጥ ያለበት» ባዩን ማኅበረ ቅዱሳንን አወድሶ፣ ይታረም ባዩን ከሳቴ ብርሃንን ማውገዝ ግን «ፌይር» ነው ትላላችሁ?

«ሠ. በራዕየ ዮሐንስ 12 ላይ «ብእሲት እንተ ትለብስ ፀሐየ ወወርኀ ታሕተ እገሪሃ» የሚለውን ገጸ ንባብ ቤተ ክርስቲያናችን ለእመቤታችን ሰጥታ የምትናገረውን አስተምህሮ በመቃወም ጽፈዋል፡፡ ገጽ 99»
እናንተ ይህን ገጸ ንባብ ለእመቤታችን የሰጣችሁት በምን መሰረት ነው፡፡ ትልቁ ችግራችሁ እኮ የእግዚአብሔርን ቃል ለተነገረለት አካል ሳይሆን ለምትፈልጉት መስጠታችሁ ነው፡፡ በተለይም በሴት አንቀጽ የተጻፈና በውብ ቃላት ያሸበረቀ ጥቅስ ከሆነ ዘላችሁ «ማርያም ናት» ማለት ይቀናችኋል፡፡ ራእይ 12 ውስጥ የተጠቀሰችው ሴት እንዴት ማርያም ትሆናለች? አንዳንድ የሚመስል ነገር ቢጠቀስ እንኳ ማርያም ልትሆን አትችልም፡፡ በራእይ 12 ላይ መጻፍ አስፈላጊ ከሆነ በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን፡፡

የሆነው ይሁንና ይህን ክፍል ቤተክርስቲያኗ ለማርያም ሰጥታ ተረጎመች፡፡ ሌላው ደግሞ ማርያምን አይወክልም ቢልና ቢቃወም፣ ጉዳዩ እንዴት ኑፋቄ ይሆናል? እንዴትስ ያስወግዛል?

«ረ. አብ በከንቱ ደከመ ኀጢአት የተሰረየው በኢየሱስ ሞት ብቻ ነው» በማለት በህልውና በአድኅኖት የማይለያዩ አብና ወልድን ይለያያሉ፡፡ ገጽ 104»
ይህን ነጥብ ኑፋቄ ብሎ የፈረጀው ማኅበረ ቅዱሳን ነው? ወይስ የሊቃውንት ጉባኤ? ወይስ ሲኖዶስ? ሳያሰኝ አይቀርም፡፡ «ገድል ወይስ ገደል» የተሰኘው መጽሐፍ «አብ በከንቱ ደከመ» በሚለው ርእስ ስር የጻፈው የእግዚአብሔር የማይቀለበስ ሐሳብና ውሳኔ በኢየሱስ ሞት እንድንድን ነው፡፡ ይህን ወደ ጎን ትቶ ሰው ስሙንና የልጁን ስም በቅዱሳን መላእክት፣ በጻድቃንና በሰማዕታት ስም ዘርፍነት ቢጠራ ይጸድቃል የሚለው ትምህርት ልጁን ለአድኅኖት የላከውን አብን በከንቱ ደከመ ያሰኘዋል የሚል መንፈስ አለው፡፡

እንዲህ መባሉ ስሕተቱ የቱ ላይ እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ የሊቃውንት ጉባኤው ይህን እውነት መጋፈጥ ስለማይሆንለት በቃላት ወደመዋጋት ነው ፊቱን ያዞረው፡፡ ገድል ወይስ ገደል መጽሐፍ አብና ወልድ በአድኅኖት ስራ ይለያያሉ የሚል አንድም ቃል ሆነ ሐሳብ ፈጽሞ ሳያሰፍር፣ የሊቃውንት ጉባኤው እንዳሰፈረ አስመስሎ ነው የራሱን ሐሳብ ያቀረበው፡፡  «ኀጢአት የተሰረየው በኢየሱስ ሞት ብቻ ነው» የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊና የማይለወጥ እውነት ኑፋቄ አድርጎ ማቅረቡ ግን ይህች ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበትን ዋና መሰረት ከስሩ እንደናዳችሁት የሚቆጠር ነው፡፡ ከኢየሱስ ሞት በቀር ኀጢአት የሚሰረይበት ሌላ መንገድ አለ ወይ? በፍጹም የለም!!!!!!!!!!! አለ የምትሉ ከሆነ ግን እናንተ ክርስቲያን አይደላችሁም፡፡

በገድል ጠቃሾቹ ሊቃውንት ዘንድ ግን አይኖርም አይባልም፤ ብዙዎቹ ገድሎች በጻድቃንና በሰማዕታት ስም በሚደረጉ ልዩ ልዩ ነገሮች ሀጢአት ይሰረያል ይላሉና «በኢየሱስ ሞት ብቻ ኀጢአት አይሰረይም» የሚል አቋም ነው ያላቸው፡፡ እኛም እኮ ገድል ጠቃሽ ያልናቸው በከንቱ አይደለም፡፡ ይህ ትምህርታቸው ግን በሐዋርያት ሥልጣን የተወገዘ ነው፡፡  እኛ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የተለየ ወንጌል ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን ነው የሚለው ቃሉ፡፡ እነርሱ የሰበኩት ወንጌል ምንድን ነው? ኢየሱስ ስለ ሀጢአታችን ሞተ ስለመጽደቃችንም ተነሳ የሚል አይደለምን?
·        ኢየሱስ «እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።» ተብሏል (ዮሐ. 1፡29)
·        «እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።» (1ዮሐ. 1፡2)
·        «እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥» (ዕብ. 10፥12)
·        «የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም።»
·        «የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥» የሚሉትንና ከተነሳንበት ሐሳብ ጋር የተያያዙትን ቃላተ መለኮት በገድል ስብከት ልትለውጡት ትፈልጋላችሁን? ለነገሩ «ኃጢአት የሚሰረየው በኢየሱስ ሞት ብቻ ነው» የሚለውን የማይቀለበስ መለኮታዊ ውሳኔ ለማውገዝ ካልፈራና ካላፈረ፣ ካወገዘም ሲኖዶስ ምን ይጠበቃል?

ይቀጥላል

14 comments:

 1. Abune Basiliyos 12 years Neberu Min seru ?
  Abune tewofilos 4 years Neberu Min seru ?
  Abune tekile hayimanot 12 years mini sreu ?
  Abune Merkorewos 4 years neberu Min seru ?
  Abune Pawlos 20 years Koyu Mini seru ?
  sefa yale zegeba mezigibulin zerzirulin bertu

  ReplyDelete
 2. 1/መስተብቍእ ዘመስቀል «ለእሉ ክልዔቱ ፍጡራን/ለማርያም ወለመስቀል/ ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ፤ እስመ ተዐረዮሙ በክብሮሙ»
  ለሁለቱ ፍጡራን ማለትም ለማርያምና ለመስቀል የፈጣሪ ምስጋና ይገባቸዋል። በክብር ፈጣሪያቸውን ተካክለዋልና!
  እንደዚህ ዓይነት ክህደት ከሰይጣን ካልሆነ በመንፈስ ቅዱስ እመራለሁ ከምትል ቤተክርስቲያን የሚመነጭ አይደለም። ፍጡር ከፈጣሪው ጋር እኩል የሆነው መቼ ነው?
  ፍጡርስ የፈጣሪውም ምስጋና እኩል የሚቀበለው እንዴት ሆኖ ነው? በአጭሩ ማርያም ጌታን ስለወለደች፤ መስቀሉም ስለተሰቀበለበት አምላክ ሆነዋል ይሉናል። ስለዚህ ሥላሴ የሚባል ነገር ወደ አምስት የፈጣሪ ደረጃ ተቀይሯል ማለት ነው። ይህንን ሲሉ ጥቂት አያፍሩም። ደግሞ ከእኛ ወዲያ ክርስትና ላሳር ይሉናል። በእግዚአብሔር መለኮታዊ ሥልጣን ላይ የተገዳደሩትን የእነዚህን ፍጻሜ ያሳየን ዘንድ እንጸልይ። ሰይጣንን በእግዚአብሔር ስም እየተመከ ስለሆነ ይህ ለሀገሪቱ ትልቅ መንፈሳዊ ውድቀትና ጩኸታችንም ከአምላክ መንበር ደርሶ ለመከራችን ሁሉ ምላሽ የተከለከልንበት ነው ብዬ አስባለሁ።
  2/ ተአምረ ማርያም ዐሥርቱ ቃላትንና ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን ለመጠበቅ አትፈልጉ፤ ይልቁንም ተአምሯን ለመስማት እንጂ! እንደሚል ይታወቃል።
  በአንድ በኩል ህግንና ነብያትን ለመሻር አልመጣሁም ሲል በክርስቶስ የተነገረውን ቃል እንደማስረጃ የምትጠቀም ቤተክርስቲያን በተአምረ ማርያም በኩል ዐሥርቱ ትእዛዛትን ለመጠበቅ ሳይሆን ተአምሯን ለመስማት ነው መሽቀዳደም ያለባችሁ ብላ ስትሽረው ከዚህ ወዲያ ኑፋቄና ክህደት ከየት ሊመጣ ነው?
  በፍርድ ቀን ክርስቶስ በጎቹን በቀኝ ሲያቆማቸው « ብራብ አብልታችሁኛል፤ ብጠማ አጠጥታችሁኛል፤ ብታረዝ አልብሳችሁኛል፤ ብታመም ጠይቃችሁኛል፤ ብታሰር ዋስ ሆናችሁ አስፈትታችሁኛል፤ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛል» የሚለው ቃል ለሰዎች መዳንን ሆነ መጥፋት ዋና ምክንያት ሆኖ ሳለ ይህንን ለመጠበቅ አትጨነቁ፤ ይልቅስ ይህንን ከመጠበቅ ይልቅ ለተአምረ ማርያም ተሽቀዳደሙ የሚል ድምጽ እውነትን ከሚያጣምም ከሰይጣን እንጂ እንዴት ከመንፈስ ቅዱስ ሊሆን ይችላል?
  ከሁሉ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህንን ያፈጠጠ ክህደት እንዳለ እንዲቆይና ሰዎችን ከእግዚአብሔር ሃሳብ እንደለያየ እንዲቀጥል የሚደረገው የመከላከል ዘመቻቸውን አስገራሚ ያደርገዋል። ሰይጣን ቅዱስ መስሎ የነገሰበት ቦታ ቢኖር ተአምረ ማርያም ውስጥና ኑፋቄን የሚዘሩ አዋልድ መጻሕፍት ውስጥ ነው። ይህ ሁሉ እንዳይወገድ ደግሞ ለኑፋቄዎች ሁሉ ተከራካሪ የሆነውን ግራ ክንዱ ማቅን በአምሳሉ አዋቀረው።
  ሲኖዶስ የሚባለው መስሪያ ቤት እንደዚህ ያሉ ከእግዚአብሔር ሃሳብ ጋር የሚጋጩ ስርዋጽ የገቡ አስተምህሮዎችን ማረምና ማስተካከል ሲገባው ራሱ ይህንን ኑፋቄ ሳይነካ እንዲቆይ መፈለጉ እግዚአብሔር ለቃሉ የሚቆም ሰው ሲያጣ እግዚአብሔር የሰሎሞንን ቤተመቅደስ መፍረስና የሕዝቡን መከራ አይቶ እንዳለቀሰው ዓይነት በእኛም ዘንድ ለቃሉ ቀናተኛ በማጣቱ ያንን የመሰለ ዘመን መቅረቡን ያሳያል።
  ምክንያቱም፤
  «በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው» ራእ 3፤15

  ReplyDelete
 3. ‹‹Shame on you! Shame on you!!›› እነዚህ ቃላት አሜሪካዊው የሆሊውድ ፊልም ዳይሬክተር ጆርጅ ሙር እ.ኤ.አ በ2003 የወቅቱ መራሄ-መንግሥት ጆርጅ ቡሽ በኢራቅ ላይ ያደረጉትን ወረራ ለመቃወም የሰነዘራቸው ነበሩ፡፡ ጆርጅ ሙር የሞያውን እጅግ ከፍ ያለ ሽልማት በሚቀበልበት መድረክ ላይ በከፍተኛ ስሜት ተውጦ የተሳሳተ ዘመቻ ነው ብሎ ያመነውን አሜሪካ መራሽ ጦርነት አውግዞአል፡፡ የጦርነቱ ጠቅላላ ሁኔታ ከአሜሪካም ሆነ ዴሞከራሲያዊ ከምትላቸው መርሖዎችዋ አይጠበቅም ነው መልእክቱ፡፡ እለዚህ ቃላት ዛሬም በኦርቶዶከሳዊት ቤተክርስቲያናችን ሲኖዶስ ላይና በተለይም ‹‹የሊቃዉንት ጉባኤ›› ተብዬው ላይ ሊሰነዘሩ ይገባል፡፡ shame on you! የሊቃውንት ጉባኤ!!! የአንዲት ታሪካዊት፤ ብሔራዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ‹‹ሊቃውንት›› ተብላችሁ ተራና ጨዋ የሚባሉ ሰዎች እንኩዋ ሊሰሩት የማይቻላቸውን ስህተት ለመስራት በቃችሁ፡፡ ከስሞቻችሁ ፊት የተዘረዘሩት ማዕረጎችና የኃላፊነት ብዛት ከተሠራው የህጻን ስህተት ጋር ሲነጻጸር ለሰሚም ለተመልካችም እጅግ ግራ የሚያጋባና አስደንጋጭ ነው!! የተጻፉ መጻሕፍትን ስህተት ሊገመግምና ሊተች የተቀመጠ ጉባኤ መጻሕፍቱን ሳይዝና ሳያነብ እንደው ወፍ ባመጣለት ድምጽ ይፈርዳል እንዴ? ታዲያ ምንድን ነው የናንተ ‹‹ሊቃውንትነት››? ነው ወይስ መጻሕፍቱን እያነበብን ብንገመግማችው እኛንም አሳምነውን ማህበረ ቅዱሳን የተባለ ድርጅት ከሰጠን ተልዕኮ ያዘናጋናል ብላችሁ ፈራችሁ? አይ የሊቃውንት ጉባኤ!! ሊቅ ማለት አብራርቶ የሚናገር፣ አፍታቶ የሚያስተምር፤ ከዕውቀት የተዛነፈውን አስተካክሎ የሚያርም መሆኑ ቀርቶ ለሆዱ የሚያድር እበላ ባይ ሲሆን ማየት እጅግ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ shame on you!! ‹‹ሊቃውንት ጉባኤ››!! አሁንም ቢሆን ለእውነት ያደሩ፣ ህሊናቸውን የሚያደምጡ ሊቃውንት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ጨርሶ የሉም የሚል ደፋር ድምዳሜ የለኝም፡፡ ሆኖም ግን ድምጻቸው ተውጦአል፤ አይሰሙም! ታሪካዊትዋን ተቋም እንዲህ ሳያነቡ የሚፈርዱ፤ ከተለመደው የአዋቂነት መሥፈርት በተጣላ ሁኔታ የልጆች ማህበር በሚያቀርቡለት ተረት ተረት የሚነዳ ተራ ድርጅት ያስመሰላችኋት አባቶችም ሆነ ‹‹ሊቃውንት›› ተብዬዎች መጠየቃችሁ አይቀርም፡፡ ፊደላትን ቀርፃ፤ ታሪክ አደራጅታ፣ ዘመናዊው መሥሪያ ቤት ባልነበረበት ጊዜ የትምህርት ሚኒስቴር ሆና ያገለገለችውን ይህችን የአገራችንን ባለውለታ ታላቅ ተቋም እንዲህ የልጆች እንቶ ፈንቶ ስታደርጉዋት ህሊና የሚያቆስል ነገር ነው! ከዩኒቨርሲቲ ተመረቅን ለሚሉ የመንፈሣዊ ነገር ሕፃናት ታላቂቱን ቤተክርስቲያን እንዲህ ልጅ ያቦካው ሊጥ ይመስል በፈቃደኝነት አሳልፋችሁ በመስጠታችሁ ከመጠየቅ አታመልጡም፡፡ ነገሥታትን ወቅሰው፣ መጽሐፍ ጠቅሰው የሚመክሩ የሚዘክሩ ፤ የሚፈሩ የሚከበሩ ታላላቅ ሊቃውንትን ያፈራች ታላቂቱ ተቋም ቤተክርስቲያን እንዴት ተደርጎ ነው እንዲህ በቀላሉ ለአንድ ወፍ ዘራሽ ድርጅት እውቀት አልባ አሠራር መስዋዕት ተደርጋ የምትቀርበው? Shame on you ‹‹የሊቃውንት ጉባኤ››!!

  ReplyDelete
 4. ይህን ፅሁፍ የቤተክርስቲያን ልጆች ሁሉ ሊያነቡት ይገባ ነበር፤ ግን ምን ያደርጋል ድህነት ሆነና… ደጀ ሰላሞች ከ Internet በተጨማሪ ሌላ መስተማሪያ መንገድ ብትፈልጉ ጥሩ ነው እንላለን፡፡

  ReplyDelete
 5. ኃኃኃኃ.....በርቱ ጥሩ ነው፣ ላላወቅን ስህተታቸውን እና የዘሩትን ምንፍቅና በግልጽ ለይታችሁ አሳይታችሁናል።

  ReplyDelete
 6. ant5e rasu bekentu dekemk, sint hon emikefelh? amlak libehn ymelsew? esti ra'eye yohanes lay yalechiw set man nat litel yhon degmo lemesmat mechem guaguchalehu. ere taw bekidusan lay afehn mekfet ybkah? koy sira serteh genzeb magegnet eyechalk lemn bekentu tdekmaleh. ay seytam meche yhon kezihech kidest betekrestian lay ejun yemianesaw?

  ReplyDelete
 7. betekiristianua kemitaminew wuchi eskehone dires yaswogizal. egna yeminaminew enanite bemitilut melku ayidelem. medemidemiaw yihe new. eslimina bekirisitina ayine sihitet new. andi eslam kiristian bihon gin yigedelal. mikiniatum ye esliminan mesfert silalamuala. andi orthodox protestant bihon yiwogezal mikiniatum ye orthodoxin memeria silaliteketele. yaligebachihuna hul gizie bedinkurian enditiguazu yaderegachihu yine new. ye enanetena ye egna astemiro yileyal. silezih enawogizachihulen.

  ReplyDelete
  Replies
  1. "ቤተክርስቲያናችን ከምታምነው ውጪ ከሆነ ያስወግዛል ብለሃል፡፡" እርሷ ግን እያለች ያለችው የእኔ ትምህርት የሐዋርያትና የነቢያት እንዱሁም የሊቃውንት ነው የሚል ነው፡፡ እንደዚያ ከሆነ አሁን ያወገዘችው በቀጥታ ይህንን ትምህርት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ስለዚህ ከነቢያት ከሐዋርያትና ከሊቃውንት ትምህርት ወጥቻለሁ ብላ በይፋ ማወጅ አለባት እንጂ በነቢያትና በሐዋርያት በሊቃውንትም ስም መነገድ የለባትም፡፡ ደግሞስ የእስልምናን መንገድ ለክርስትና ማሳያ አድርገህ ታቀርባለህ? ውግዘት ተቀብነት የሚኖረው በአግባቡ ሲሆንና የሚያስወግዝ ኑፋቄ ሲገኝ ነው፡፡ የአንተ ሃይማኖት የለሽ ጳጳሳት ያወገዙት ግን እውነትን ነው፡፡ የኒያትና የሐዋርያትን ትምህርት ነው፡፡ አቀርበው እንዳይጠይቁ ዕውቀት የላቸው፡፡ ዝም ብለው እንዳይቀመጡ ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን በገንዘብ ገዝቷቸዋል። በነውራቸው ሸብቧቸዋል፡ ስለዚህ አድርጉ ያላቸውን ነው የሚያደርጉት። እንደዚች ያለች በገድላገድል የምትመራ ቤተክርስቲያን አስቀድማ የተወገዘች ናት፡፡

   Delete
 8. Even if I don't agree with some of your points, I believe you guys are doing the work of God in the sense that your crticism and cries have helped the church to clean some of the dust like the one you mentioned. EOTC has certainly a better truth compared to many other churches, but dust has covered some of the truth we have.

  Therfore, I think you should continue to criticize the church so we and the next generation can drink a clean life giving water. Your criticism should not be aimed at aligning our faith/belief with the Protestantism, which I think has more fundamental problems than EOTC.

  If you truely care about the Gospel and are not hired by anyone to destablize, you should compare the EOTC teaching with other ancient Orthdox churches. While I think your criticism is good, I am also afraid that you may take some folks and/or the church to the direction of protestantism, which is much worse!!!!

  ReplyDelete
 9. የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር መንፈስ ቅዱስ የሚለውን ሰምቶ ይታረም!!!

  የሚሰማ አስተዋይ አምልጦ ያስመልጣል!

  የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰምቶ ለሚመለስ ጌታ ሩኅሩኅ ነው!!

  ለምድራዊ/ለሥጋዊ ክብር በላችሁ የማያልፈውን ሕይወት በሚያልፍ አትቀይሩት!!!

  ወገኔ በሙሉ! በሥጋ ለባሽ ላይ አትደገፍ! የሞተልህን ጌታ ላይ በማተኮር እንደ ቤሪያ ክርስቲያኖች በቃሉ ላይ ሌት ተቀን በማተኮርና በማጥናት ከዘላለም ፍርድ አምልጥ:: ደግሞም እውነተኛ የነፍስ አባትህ የዘላለም አምላክ እግዚአብሔር ብቻ እንጂ ቆብ የደፋ ሥጋ ለባሽ መሆን የለበትም እሱ ለራሱም በጌታ እስካልሆነ ድረስ አይገባትምና በልምድና በባህል አትታለል::

  እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያናችንን ተከታይ በምህረቱ ይጎብኝ!!!!

  አሜን::

  የጌታ ሰላም ለምድራችን በሙሉ!!!

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 10. ለመስቀል ክብር መስጠት ፣ በመስቀል ሰውነትን ማማተብ የተጀመረው በማን ነው? የማይቀበሉትና የማያከብሩትስ የየትኛው እምነት ተከታዮች ናቸው ? መልካም ንባብ
  Part one
  During the first two centuries of Christianity, the cross may have been rare in Christian iconography, as it depicts a purposely painful and gruesome method of public execution and Christians were reluctant to use it. A symbol similar to the cross, the staurogram, was used to abbreviate the Greek word for cross in very early New Testament manuscripts, almost like a nomina sacra. The extensive adoption of the cross as Christian iconographic symbol arose from the 4th century.

  However, the cross symbol was already associated with Christians in the 2nd century, as is indicated in the anti-Christian arguments cited in the Octavius of Minucius Felix, chapters IX and XXIX, written at the end of that century or the beginning of the next, and by the fact that by the early 3rd century the cross had become so closely associated with Christ that Clement of Alexandria, who died between 211 and 216, could without fear of ambiguity use the phrase τὸ κυριακὸν σημεῖον (the Lord's sign) to mean the cross, when he repeated the idea, current as early as the apocryphal Epistle of Barnabas, that the number 318 (in Greek numerals, ΤΙΗ) in Genesis 14:14 was interpreted as a foreshadowing (a "type") of the cross (T, an upright with crossbar, standing for 300) and of Jesus (ΙΗ, the first two letter of his name ΙΗΣΟΥΣ, standing for 18), and his contemporary Tertullian could designate the body of Christian believers as crucis religiosi, i.e. "devotees of the Cross". In his book De Corona, written in 204, Tertullian tells how it was already a tradition for Christians to trace repeatedly on their foreheads the sign of the cross. It is important to note that the crucifix, that is a cross upon which an image of Christ is present, is not known to have been used until the 6th century AD.

  The Jewish Encyclopedia says:

  The cross as a Christian symbol or "seal" came into use at least as early as the second century; and the marking of a cross upon the forehead and the chest was regarded as a talisman against the powers of demons. Accordingly the Christian Fathers had to defend themselves, as early as the second century, against the charge of being worshipers of the cross, as may be learned from Tertullian, "Apologia," xii., xvii., and Minucius Felix, "Octavius," xxix. Christians used to swear by the power of the cross

  ReplyDelete
 11. Part two contd.
  In contemporary Christianity

  In Christianity the cross reminds Christians of God's act of love in Christ's sacrifice at Calvary—"the Lamb of God who takes away the sin of the world." The cross also reminds Christians of Jesus' victory over sin and death, since it is believed that through His death and resurrection He conquered death itself. They venerate it not as a material object seen in isolation but as the symbol of the sacrifice by which Christ saved them, as the instrument of Christ's triumph, according to Colossians 2:15 ("Having disarmed the powers and authorities, he made a public spectacle of them, triumphing over them by the cross"), and "as the instrument of our God's saving Love".

  Roman Catholics, Eastern Orthodox, Oriental Orthodox, members of the major branches of Lutheranism, some Anglicans, and other Christians often make the Sign of the Cross upon themselves. This was already a common Christian practice in the time of Tertullian.

  The Feast of the Cross is an important Christian feast. One of the twelve Great Feasts in Eastern Orthodoxy is the Exaltation of the Cross on September 14, which commemorates the consecration of the basilica on the site where the original cross of Jesus was reportedly discovered in 326 by Helena of Constantinople, mother of Constantine the Great. The Catholic Church celebrates the feast on the same day and under the same name (In Exaltatione Sanctae Crucis), though in English it has been called the feast of the Triumph of the Cross.

  Roman Catholic, Eastern Orthodox and Anglican bishops place a cross [+] before their name when signing a document. A cross [†] may also be placed before the name of a departed Christian when their name appears in print.
  Jehovah's Witnesses do not accept the use of the cross as a symbol of Christianity. They do not see Biblical support for doing so and associate devotion to that symbol with idolatry. They believe that the cross was widely used by worshipers of Tammuz, a Babylonian god, as his symbol. Jehovah's Witnesses believe that Jesus died, not on a two-beam cross, but on an upright stake, in accordance with their interpretation of the Greek word σταυρός (stauros). In classical Greek, of the period about four centuries before Christ, this word meant merely an upright stake, or pale. Later it also came to be used for an execution stake having a crosspiece. Although formerly, the Watchtower Society's publications stated that Christ was crucified on a cross, after further research was done, they concluded that the belief had no scriptural basis and was actually false.

  Members of the Church of Jesus Christ of Latter Day Saints believe that Jesus died on a cross, however "For us the cross is the symbol of the dying Christ, while our message is a declaration of the living Christ... the lives of our people must become the only meaningful expression of our faith and, in fact, therefore, the symbol of our worship." Latter Day Saints do not place the cross on their buildings because the Bible does not mention the cross as a symbol for Christianity. Most temples will usually decorate one spire of the temple with a symbol of the Angel Moroni as an expression that the heavens have been reopened to man on earth.

  ምንጭ፡- http://en.wikipedia.org/wiki/Christian_cross

  ReplyDelete
 12. ከላይ የተጻፈውን ዲስኩር እንዳልቀበል ከቅድሳት መጻሕፍት አንድም ያስቀመጣችሁት ማስለጃ የለም፤ ለነገሩ ተውት መጽሐፍስ ‹‹ ከዘርዋ የቀሩትን ይዋጋ ዘንድ የስድብ አፍ ተሰጠው›› ይል የለ……

  ReplyDelete
 13. ከላይ የተጻፈውን ዲስኩር እንዳልቀበል ከቅድሳት መጻሕፍት አንድም ያስቀመጣችሁት ማስለጃ የለም፤ ለነገሩ ተውት መጽሐፍስ ‹‹ ከዘርዋ የቀሩትን ይዋጋ ዘንድ የስድብ አፍ ተሰጠው›› ይል የለ………

  ReplyDelete