Friday, July 6, 2012

«አናኒመስ» ስለ ጥንተ አብሶ ምን እያለ ነው?

ክፍል ሁለት
«3. ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ወደ እመቤታችን በመጣ ጊዜ - “ደስ ይበልሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው ከሴቶች መካከል አንቺ የተባረክሽ ነሽ ፡፡በማለት አመስግኗታል (ሉቃ 1.28) ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ከእርሷ በፊት ይህን በሚመስል ምስጋና የተመሰገነ አንድም ፍጡር የለም ፡፡ ይኸ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእመቤታችን የተሰጠ ምስጋና ነው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!! እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጥንተ አብሶ ተይዛ ቢሆን ኖሮ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልጸጋን የተመላሽ ሆይሊላት አይችልም ነበር፡፡ ምክንያቱሳ ቢሉ ጥንተ አብሶ ጸጋዋን ጐደሎ ያደርግባት ነበርና ነው፡፡ አዳም በደልን እንደ ፈጸመ በቀጣዩ ያጋጠመው የመጀመሪያው ቅጣት ጸጋው መጉደሉ ወይም መገፈፉ ነው፡፡ ይኸ የአዳም በደል አለባት ከተባለ ጸጋዋ እንደ ቀደም አባቷ መጉደል ይገባው ነበርና ታድያ መልአኩ እንዴትና ስለምን ምልአተ ጸጋ በማለት ሊያወድሳት ይችላል 
መቼም በአለቃ አያሌው ታምሩ የሚመራ ሰው በሥጋውም በነፍሱም ገደል መግባቱ አይቀርም፡፡ እርሳቸው አስቀድሞ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የሚለውንና የጥንት አባቶችና የቅርቦቹም እነ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ፣ እነ ሊቀ ሊቃውንተ መሃሪ ትርፌና ሌሎችም ዓይናማ ሊቃውንት የሚያምኑትን ትምህርት ነበር የሚቀበሉት፡፡ ሊቀ ሊቃውንት መሐሪ ትርፌ መዝገበ ሃይማኖት በተሰኘው መጽሐፋቸው የኑሲስ ኤጲስ ቆጶስ የጎርጎርዮስን ቃል ጠቅሰው እንዲህ ጽፈዋል፡፡ «መንፈስ ቅዱስ የማርያምን ሥጋ አነጻ ቃልን ለመጽነስ የተዘጋጀች አደረጋት» (ገጽ 28)፡፡ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬም በመድሎተ አሚን ተመሳሳይ ነገር ጽፈዋል፡፡ አለቃ አያሌውም አስቀድሞ የኢትዮጵያ እምነት በሦስቱ ሕግጋት በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 205 ላይ ስለስግደት በጻፉበት ክፍል «… ይልቁንም መርጦ ከኃጢአት አንጽቶ በመንፈስ ቅዱስ ቀድሶ ሥጋዋን ነፍሷን ለተዋሀዳት ለእመቤታችን …» ብለው ነበር፡፡ በኋላ ላይ ግን ያንን አቋሜን አንስቻለሁ አሉና የለባትም ወደሚለው ጎራ ተቀላቀሉ፡፡ ይህንም ያደረጉት እነመጋቤ ብሉይ ሰይፈን ለመቃወም መሆኑን የሚናገሩ አሉ፡፡ መጋቤ ብሉይ ሰይፈና አባ መልከ ጼዴቅ በጻፉት መጽሐፍ ላይ ማርያም ጥንተ አብሶ ነበረባት የሚል አቋም ስላራመዱ እነርሱን የተቃወሙ መስሏቸው የቀደመ ትምህርታቸውን አልቀበለውም ሲሉ አስተባበሉ፡፡

አሁን «አናኒመስ» በዚህ ነጥብ ስር ያነሳው አለቃ አያሌው ወላዲተ አምላክ በኢትዮጵያ በተሰኘው መጽሐፋቸው ያስተላለፉትን ሐሳብ ነው፡፡ ነገር ግን «ጸጋን የተመላሽ ሆይ» የሚለው ጥንተ አብሶ እንደሌለባት እንዴት ያሳያል? በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እኮ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፏል፡፡ «ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።» (የሐዋ. 4፡33) እንዲሁም «እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር።» (የሐዋ. 6፡8)፡፡ በእነዚህ ክፍሎች ሐዋርያት ታላቅ ጸጋ ስለነበረባቸው፣ እስጢፋኖስ ጸጋንና ኃይልን ስለተሞላ ጥንተ አብሶ የለባቸውም ወይም ኀጢአት የለባቸውም ማለት ነውን? በፍጹም!

ጸጋ እኮ የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ነው እንጂ እንደ ደመወዝ የሚከፈል እዳ ወይም የድካም ዋጋ አይደለም፡፡ በማርያም ላይ ጸጋ ቢሞላባት ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ነው እንጂ በእርሷ ብቃት የተገኘ አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ «ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤» ይላል (2ቆሮ. 3፡5)፡፡ ይህን ያልተገነዘቡ ሰዎች ናቸው ሁሉ በእርሷ ብቃት እንደሆነ የሚናገሩት እንጂ፣ እመቤታችንም ለዚህ ሁሉ ምክንያቱና ምንጩ እርሷ ሳትሆን እግዚአብሔር መሆኑን ነው በጸሎቷ ገልጣለች፡፡ «የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።» (ሉቃ. 1፡48-49)፡፡

«አናኒመስ» «እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጥንተ አብሶ ተይዛ ቢሆን ኖሮ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ጸጋን የተመላሽ ሆይሊላት አይችልም ነበር፡፡ ምክንያቱሳ ቢሉ ጥንተ አብሶ ጸጋዋን ጐደሎ ያደርግባት ነበርና ነው፡፡ አዳም በደልን እንደ ፈጸመ በቀጣዩ ያጋጠመው የመጀመሪያው ቅጣት ጸጋው መጉደሉ ወይም መገፈፉ ነው፡፡ ይኸ የአዳም በደል አለባት ከተባለ ጸጋዋ እንደ ቀደም አባቷ መጉደል ይገባው ነበርና ታድያ መልአኩ እንዴትና ስለምን ምልአተ ጸጋ በማለት ሊያወድሳት ይችላልያለው በምንም ማስረጃ ሊደገፍ የማይችል የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው፡፡ በቅድሚያ እግዚአብሔር እኛን ኃጢአተኞችን ሊያድን ስለወደደ አንድያ ልጁን ወደ እኛ ወደኃጢአተኞቹ ላከው፡፡ እርሱም «ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ በእኛ አደረ» (ዮሐ. 1፡14)፡፡ እንዲያውም ብዙ ኃጢአት ባለችበት የእግዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች እንደተባለው ነው የሆነው (ሮሜ 5፡15-21)፡፡ ስለዚህ ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ ስላለባት ቃል ከእርሷ ሥጋ እንዳይነሳ አልከለከለውም፡፡ ምክንያቱም ጌታ ሰው ሆኖ ይወለድ ዘንድ አንዲት ሴት ታስፈልግ ነበር፡፡ ለዚህ ታላቅ ዕድል በእግዚአብሔር ጸጋ የተመረጠችው ደግሞ ድንግል ማርያም ሆናለች፡፡ ከላይ እንዳየነው መንፈስ ቅዱስ ወደ እርሷ መጥቶ ከእርሷ የከፈለውን ሥጋ በማንጻትና ከአካለ ቃል ጋር በማዋሐድ ኃጢአተኛ ባሕርይ ወደእርሱ እንዳይተላለፍ ጸልሏታል፡፡ ከዚህ የተነሣም ከእርሷ የተወለደው «ቅዱስ (ኃጢአት የሌለበት) የእግዚአብሔር ልጅ» ተባለ (ሉቃ. 1፡35)፡፡ ስለዚህ በአንተ አገላለጽ የአዳም ጸጋ መገፈፍ ከድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ ጋር አንዳች የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡    

«4.
ሌሎች ደግሞ ሉቃ 147 የተነገረውን ድንግል ማርያም በራሷ ላይ የምስክርነት ቃል እንደ ሰጠች አድርገው በማቅረብ ጥንተ አብሶ እንደነበረባት ለማስረዳት ይሞክራሉ ፡፡ ይኸን ቃል ለመናገር የሚገደደው ፍጡር የሆነ ሁሉ እንጅ አዳማዊ ኃጢአት ያለበት ብቻ እየተመረጠ አይደለም ፡፡ በአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አምሳል የተፈጠረ ፍጡር በሙሉ አምላኬ መድኃኒቴ በማለት አምላኩን ያወድሳል፡፡ ድንግል ማርያም በተለየ መድኃኒቴ የሚለውን የምስክርነት ቃል የሰጠችው ገና ኢየሱስ ሳይወለድና በመስቀል ላይ ሞቶ ሳያድናት ነው ፡፡ ሳይሞትና መስዋዕት ሳይሆን ደግሞ ስለድኀነት መናገር ስለማይቻል ከፍጥረት አስቀድማ ድና ነበር ያሰኘን እንደሁ እንጅ ገና ደሙን ያላፈሰሰና ያልሞተውን አምላኳንና ልጅዋን ሰው መሆኑን እንኳን አይታ ያላረጋገጠችውን የማህጸን የጽንስ ፍሬ መድኃኒቴ ብላለች በማለት ያልሆነ ትርጓሜም በመስጠት ወይም የትንቢት ቃል አስመስሎ መከራከር፣ የሚያስኬድ ሆኖ አላየሁትም ፡፡ ከመስዋዕትነት በኋላ የተነገረ ቃል ቢሆን እንኳን ያንን ተንተርሶ ትንሽ ለማደናገር ክፍተት ይገኝ ነበር፡፡ ቤዛነቱ ሳይፈጸም መድኃኒቴ ስላለች ከፍጥረት ሁሉ በፊት በተለየ መንገድ ድናለች ወይም ቀድሞውንም ከጥንተ አብሶ ጠብቆ አቆይቷቷል ለማለት እንደፍራለን እንጅ አዳማዊ በደል አግኝቷታል የሚለው በየትም በኩል ማስማሚያ የለውም፡፡ እግዚአብሔር ነቢይ ሊያደርግ የፈለገውን እንኳንበሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁእያለ የተናገረ / ኤር 15/ ለማደሪያውና እናት ትሆነው ዘንድ የመረጣትን ቅድስትና ብፅዕትማ ደግሞ ምን ያህል እንደ ሚጠበብላትና እንደ ሚያሰናዳት ባለ አእምሮ የሆነ ሰው ሁሉ ሊያጤነው ይገባል ፡፡ ከልማደ እንስትና ከሀልዮ (ሃሳብ) ከነቢብና (ንግግር) ከገቢር (ሥራ) ኃጢአት ነጻ ያደረጋት ፈጣሪ ጥንተ አብሶን አላስወገደላትም ማለት ፈጽሞ ቧልት ነው፡፡»

«አናኒመስ» የያዘው ይህ መከራከሪያ ብዙ የሚያዛልቅ አይመስለኝም፡፡ ማርያም እግዚአብሔርን መድኃኒቴ ያለችው እንደማንኛውም ፍጡር እንጂ ኃጢአተኛ ስለሆነች አይደለም ማለት እንዴት ይቻላል? ጌታ በወንጌል እንደተናገረው ባለመድኃኒትን የሚፈልጉት እኮ በሽተኞች እንጂ ጤነኞች አይደሉም (ማቴ. 9፡12)፡፡ ድንግል ማርያምም እግዚአብሔርን መድኃኒቴ ያለችው መዳን ከሚያስፈልጋቸው መካከል አንዷ እርሷ በመሆኗ ነው እንጂ አንተ ባልከው መንገድ አይደለም፡፡ ደግሞም ላቀረብከው ለዚህ ዋቢ የለሽ አመክንዮ የአንተን አስተያየት ብቻ እንጂ ማስረጃ የሚሆን ነገር ከመጽሐፍ አላቀረብክም፡፡ ኢየሱስ ሳይወለድ መድኃኒቴ ማለት እኮ በእርሷ አልተጀመረም፡፡ እርሱ ሳይወለድ ዳዊት በመዝሙሩ እግዚአብሔርን «መድኃኒቴ» ሲለው በብዙ ስፍራ እናነባለን፡፡ ስለዚህ ጌታ ሳይሠዋ መድኃኒቴ ማለት አዲስ የሆነው ለ«አናኒመስ» ይሆናል እንጂ ለማርያምም ሆነ ለሌሎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች የተለመደ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መድኃኒቴ የሚሉትም መድኃኒት ስለማያስፈልጋቸውና ፍጡር ስለሆኑ ሳይሆን ኃጢአተኞች ስለሆኑና የኃጢአት መድኃኒት ደግሞ እግዚአብሔር ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ በትንቢት የእርሱ መድኃኒትነት ተነግሯል፡፡ በወንጌል ተፈጽሞም ተሰብኳል፡፡ ስለዚህ አስቀድሞም ይነገር በኋላም ይነገር ሰው ሁሉ (ድንግል ማርያምን ጨምሮ) ኃጢአተኛ ስለሆነ መድኃኒት ስለሚያስፈልገው ኢየሱስን መድኃኒቴ ቢል ተገቢና ትክክል ነው፡፡

«አናኒመስ» ግን «ሰው መሆኑን እንኳን አይታ ያላረጋገጠችውን የማህጸን የጽንስ ፍሬ መድኃኒቴ ብላለች» ማለት ስሕተት መሆኑን ተናግሯል፡፡ ይህ በእውነቱ የድንግል ማርያምን ሰብእና ዝቅ ማድረግ ነው የሚሆነው፡፡ ድንግል ማርያም እኮ ካላየሁ አላምንም የምትል ሴት አይደለችም፡፡ ከጌታ የተነገረላት ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት ተብላ ከኤልሳቤጥ ሙገሳን ያገኘት የእምነት ሰው ናት፡፡ ስለዚህ መልአኩ ገብርኤል «ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ» (ሉቃ. 1፡31) ያላትን ቃል አምና ተቀብላለች፡፡ እንደቃልህ ይሁንልኝም ብላለች፡፡ ኢየሱስ ማለትም ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል ማለት መሆኑ ለዕጮኛዋ ለዮሴፍ ተነግሮታል (ማቴ. 1፡21)፡፡ እርሷም በቅዱሳት መጻሕፍት ዕውቀት የበረታች መሆኗ ከጸለየችው ጸሎት ይታወቃልና የስሙ ትርጓሜ ለእርሷም ግልጽ ነበር፡፡ ስለዚህም ይህንን አውቃ ነው መድኃኒቴ ያለችው፡፡ ወጣም ወረደ «መድኃኒቴ» ማለቷ መዳን ከሚያስፈልጋቸው ምእመናን መካከል አንዷ መሆኗን አመልካች ነው፡፡

ሌላው «አናኒመስ» ያነሣው ልማዳዊ አነጋገር ማርያምን ሰው አይደለችም ወደሚል አቅጣጫ የሚወስድ ነው፡፡ «እግዚአብሔር ነቢይ ሊያደርግ የፈለገውን እንኳን «በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ» እያለ የተናገረ / ኤር 15/ ለማደሪያውና እናት ትሆነው ዘንድ የመረጣትን ቅድስትና ብፅዕትማ ደግሞ ምን ያህል እንደ ሚጠበብላትና እንደ ሚያሰናዳት ባለ አእምሮ የሆነ ሰው ሁሉ ሊያጤነው ይገባል ፡፡ ከልማደ እንስትና ከሀልዮ (ሃሳብ) ከነቢብና (ንግግር) ከገቢር (ሥራ) ኃጢአት ነጻ ያደረጋት ፈጣሪ ጥንተ አብሶን አላስወገደላትም ማለት ፈጽሞ ቧልት ነው፡፡» የኤርምያስ በሆድ ሳለ መታወቅና ከማህፀን ሳይወጣ መቀደስ ኤርምያስ ለነቢይነት አገልግሎት አስቀድሞ መለየቱን እንጂ ከጥንተ አብሶ ነጻ መሆኑን አያሳይም፡፡ ስለዚህ ይህን ጥቅስ ወደድንግል ማርያም ማጠጋጋት አላዋቂነትን ነው የሚያሳየው፡፡ ከዚህ በኋላም የሰፈረው ስለእርሷ ያልተጻፈ ነውና በዚህ ላይ መከራከር አያስፈልግም ነበር፡፡ ነገር ግን ለድንግል ማርያም የተሰጡት እነዚህ መግለጫዎች ከምን የመነጩ ናቸው? ብሎ መጠየቅ የግድ ነው፡፡ እርሷ ሰው ናት ካልን ከእነዚህ ውጪ ልትሆን አትችልም፡፡ ማንም ሰው ከተፈጥሮ ሥርአት ውጪ ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን እርሷ ያለዘርአ ብእሲ ፀንሳ መውለዷ ተአምራዊ በሆነ መንገድ የተከናወነ በመሆኑ እርሱ የተለየ ነገር ነው፡፡ ከዚህ በቀር ግን ማንም ቢሆን (ሰው ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር) ከኃልዮ ከነቢብና ከገቢር ኃጢአት ንጹሕ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰው እኮ የኃልዮ የነቢብና የገቢር ኃጢአቶችን የሚሠራው ከአዳም በወረሰው ኃጢአተኛ ባሕርይ ምክንያት ነው፡፡ ምናልባት አንዳንድ ሊቃውንት ለእርሷ የሚሰጠውን ክብር መቀነስ ስለሚመስላቸውና ከሕዝብ ጋር እንዳይጣሉ ጥንተ አብሶ አለባት (ነበረባት)፤ ከኃልዮ ከነቢብ ከገቢር ኃጢአቶች ግን ነጻ ናት ይላሉ፡፡ ይህ ግን አንድ በጠብታ መርዝ የተበከለ ውሃን ንጹሕ ነው የማለት ያህል ነውና እንዳልከው ለእኔ ማርያም ጥንተ አብሶ የለባትም ማለት ነው ቧልት የሚሆነው፡፡

«5. ኢሳ 19 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር የሚለውን ስለይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ህዝብ እንደተነገረ አድርገው የሚተረጉሙ አሉ ፡፡ ከቁጥር 9 ንባብ አስቀድሞ በቁጥር 8 ላይ ስለ ጽዮን ሴት ልጅ የሚናገረውንስ እነዴት መንደርና ከተማ አድርጐ መተርጐም ይቻላል? ኢሳይያስ ነገሩን እያጠራልን ሲሄድ በምዕራፍ 2 ላይ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም እየተናገረ በቁጥር 2 ስለ ዘመን ፍጻሜ ክስተት ያወሳናል በቁጥር 3 ደግሞ ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል (አጽንኦት) ከኢየሩሳሌም ይወጣል ለአሕዛብ ሁሉ መንገዱን ያስተምራል በጎዳናውም እንደሚሄዱ ይናገራል ፡፡ እንዲያውም ዳግም አትታወሩ ብሎ ሊያሳርፈን ሲፈልግ፣ አለፍ ብሎ በምዕራፍ 714 ደግሞ ለዳዊት ቤት እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ይልና ትንቢቱን ያስቀምጥልናል ፡፡ በመቀጠልም በምዕራፍ 96 ደግሞ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል በማለት የምትወልድውን ህፃን ማንነት በግልጽ ያበሥራል ፡፡ ስለዚህም መጽሐፉ የሚነግረን መንፈስ ቅዱስ በምዕራፍ 19 22-3 ያስረዳውን ስውር ቃል በምዕራፍ 714 ግልጽ እንደ አደረገለትና ይህንኑ የተስፋ ቃል ደግሞ በማቴዎስ 118 በእውን እንደ ተረጐመው ነው፡፡ በመሆኑም ከመጀመሪያ ምዕራፍ አንስቶ በተደጋጋሚ በተለያየ ሥፍራ ስለ ድንግል ማርያም ተናግሯልና በኢሳ 19 የተገለጸውም እሷን የሚመለከት ቃል ነው እንጅ ስለ አገርና ህዝብ የተነገረ አይደለም ፡፡

በዚህ ነጥብ ስር «አናኒመስ» ያነሳው ሀሳብ አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ ነው የሆነበት፡፡ ስለኢሳያስ 1፡9 ከዚህ ቀደም በዚሁ ብሎግ ላይ የወጣ አንድ ጽሁፍ እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡ ስለእርሱ ያንን መመልከት መልካም ነው፡፡ «አናኒመስ» ግን ከቁጥር 8 ቢጀመር ግን ስለማርያም እንደሚናገርለት ጠቁሟል፡፡ «በቁጥር 8 ላይ ስለ ጽዮን ሴት ልጅ የሚናገረውንስ እነዴት መንደርና ከተማ አድርጐ መተርጐም ይቻላል ሲልም ለመሞገት ይሞክራል፡፡ ቁጥር 8 እንዲህ ይላል፡፡ «የጽዮንም ሴት ልጅ በወይን ቦታ እንዳለ ዳስ፥ በዱባ አትክልትም እንዳለ ጎጆ፥ እንደተከበበችም ከተማ ሆና ቀረች።» እሺ ይህ ቁጥር ስለ ማን ይናገራል፡፡ በንባቡ መሰረት ከሄድን የሚናገረው ስለጽዮን ሴት ልጅ ነው፡፡ እርሷ ምን ሆነች? ብንል ደግሞ አሁንም ምንባቡ እንደተከበበች ከተማ ሆናለች ይለናል፡፡ መቼም «አናኒመስ» ጽዮን ማርያም ናት ማለቱ አይቀርም፡፡ ጥቅሱ እየተናገረ ያለው ደግሞ ስለጽዮን ሴት ልጅ ነው፡፡ ታዲያ ማርያምን የምትወክለው ጽዮን ናት ወይስ የጽዮን ሴት ልጅ? የጽዮን ሴት ልጅ ከሆነች በዚህ ክፍል ስለእርሷ የተነገረውን ለማርያም መስጠት እንዴት ይቻላል? ደግሞስ በሴት ልጅ ከተገለጹት የከተማዋ ነዋሪዎች አልፎ ለድንግል ማርያም የሚተርፍ ምን ምስጢር አለ? ካለ «አናኒመስ» ሊነግረን ይችላል፡፡ ለመሆኑ «አናኒመስ»ና መሰሎቹ መጽሐፍ ቅዱስን ለክርክርም ቢሆን ሲያነቡት በሴት አንቀጽ የተነገረውን ጥቅስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የማይደግፈውን ከንቱ ሐሳባቸውን የሚደግፍላቸው እየመሰላቸው ለድንግል ማርያም ከመስጠት የሚታቀቡት መቼ ይሆን? ስለዚህ «አናኒመስ» ይህ ጥቅስ ከከተማና መንደር የሚያልፍ ትርጉም የለውም፡፡

«አናኒመስ» በዚህ ነጥብ ስር ከትንቢተ ኢሳይያስ አለፍ አለፍ እያለ ለመጥቀስ መሞከሩ ጥሩ ጅምር ቢሆንም፣ አካሄዱ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ይዞት የመጣውን ሐሳብ ለማጎልበት እንጂ በቃሉ መሰረት ወደ እውነት ለመድረስ ያለመ አይደለም፡፡ ስለዚህ ከምዕራፍ ወደ ምዕራፍ እየዘለለ ቃሉ የሚናገረውን ሳይሆን እርሱ የሚፈልገውን እየመረጠ የጠቀሳቸው ጥቅሶች ሁሉ ወደ ድንግል ማርያም እንደሚያመለክቱ ለመናገር ሞክሯል፡፡ ግን ፍጹም ስሕተት ነው፡፡ ከጠቀሳቸው ውስጥ በእርሷ ተፈጽሞ ያየነው ኢሳ. 7፡14 ብቻ ነው፡፡ ከእዚህ ውጪ ያሉት ግን ከእርሷ ጋር የተገናኙ አይደሉም፡፡

በ6ኛው ነጥብ ስር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ሥርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነትተባለውን መጽሐፍ በመጥቀስ «ይህን 18 (፲፰) የቤተ ክርስቲያናችን አባቶችና ሊቃውንት የቀረበውን ቃል በአራት () የቤተ ክርስቲያን መምህራን የተፈተሸውንና ለኀትመት የበቃውን መጽሐፍ ወደጐን ገፍቶ የአንድ ሊቅን ጽሁፍ ብቻ መርጦ ማስነበብ ሚዛናዊነት ይጐድለዋል እላለሁ፡፡» ብሏል፡፡ ይህን ጽሑፍ ካዘጋጁት መካከል አንዳንዶቹ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የሚሉ መሆናቸው ከዚህ ቀደም ተጠቁሟል፡፡ ለምሳሌ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ እንግዲህ አቋማቸውን በጽሑፍ የገለጹ ናቸው፡፡ በጽሑፍ ያልገለጹና ይህንኑ አመለካከት የሚያራምዱ ሌሎችም ሊቃውንት እንዳሉበት ይታወቃል፡፡ ምናልባት እነዚህ ሊቃውንት በአደባባይ የለባትም፣ በጓዳ ደግሞ አለባት የሚሉ ስለሆኑ የቱ ጋ እንደቆሙ ለጊዜው መለየት አይቻልም፡፡ ለነገሩ የሰው ብዛት ሳይሆን የነገሩ እውነትነት ነው ትክክለኛው የቱ ነው የሚያሰኘው እንጂ በዚህ አቋም ዓለማየሁ ሞገስ አንድ ስለሆኑ ሐሰተኛ፣ የተጠቀሰውን መጽሐፍ 22 ሊቃውንት ስላዘጋጁት እውነተኞች ሊሆኑ አይችልም፡፡

በመጨረሻው ነጥብ ሥር የሰፈረው ሐሳብ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በጥንተ አብሶ አስተምህሮ ከሌሎቹ የኦርቶዶክስ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር የመለያየቷና ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር አንድ የመሆኗ ጉዳይ ብዙ ሊያነጋግር ይችላል፡፡ ቤተክርስቲያኗ ከጥንት ጀምሮ ከኦሪየንታል ኦርቶዶክስ ጋር በትምህርትም በሥርአትም ተመሳሳይነት አላት፡፡ እንዲህ ማለት ግን «አናኒመስ» እንዳለው በምድር ላይ ካሉ ከሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ጋርም ፈጽሞ የማትገናኝበትን ነገር እንደያዘችም ግልጽ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ትምህርት ከኦርቶዶክሳውያን ተለይተን ከካቶሊክ ጋር አንድ የሆነው በየትኛው ዓለም አቀፍ የሲኖዶስ ውሳኔ ነው? በአገራችንስ ጉዳዩ ለውይይት ቀርቦ ውሳኔ የተላለፈው መቼ ነው? እርግጥ የተባለው መጽሐፍ ተጽፏል፡፡ ነገር ግን መጽሐፉ የኖረውን ልማድ ያጸና እንጂ ቤተክርስቲያኗ አስተምህሮዋንና ሥርአቷን በመጽሐፍ ቅዱስ እንድትፈትሽ እድል የሰጠ አይደለም፡፡ ስለዚህ ጥንተ አብሶን በተመለከተ ሊቃውንቱ በሁለት ጎራዎች ተከፍለው መከራከራቸው ይቀጥላል እንጂ በተባለው መጽሐፍ እልባት አግኝቷል ብሎ ማመን አስቸጋሪ ነው፡፡ በመሆኑም ቤተክርስቲያኗ ስርአት ባለው መንገድ ሊቃውንቱ ተወያይተው፣ ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት አስተምህሮ ጋርም ተገናዝቦ ውሳኔ ባልተሰጠበትና የኖረው ልማድ በጸናበት በዚህ መጽሐፍ ዙሪያ ዳግም ውይይት መከፈት አለበት ባይ ነኝ፡፡

ጸጋ ታደለ

36 comments:

 1. በተራ ቁጥር ሦስት ላይ ለሐዋርያቱ በጸጋ መሞላታቸውን ምክንያት በመጥቀስ ከድንግል ማርያም ጸጋ ጋር ማነጻጸርህ አሁንም ስንፍናን እያመላከትህ ነው ፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያቱ እኮ በመልአክ ወይም በሌላ ሳይሆን ፣ በቀጥታ በጌታ በራሱ ተባርከዋል ፡፡ ስለዚህም የነሱ በጸጋ መሞላት ከድንግል ማርያም የጸጋ መሞላት ጋር አይነጻጸርም ፡፡ ክህሎቱን ለምንቀበል እሷን ያሰባትና ያቀዳት አዳም በደልን ከመፈጸሙ በፊት ነው ፡፡ ይኸ በረከት በራሷ ምርጫና ፈቃድ እንዳልሆነ እኛም እየተናገርን ነው ፡፡ ስለዚህም አምላክ ፈቀዳት ፣ መረጣት ፣ ከአዳም በደል ጠበቃት እንላለን እንጅ በራሷ ሥራ ባለጸጋ ሆነች ፤ ራሷን ከአዳም በደል አነጻች ማንም አላለም ፡፡

  በተራ ቁጥር አራት ላይ ደግሞ ንጽጽር ማድረግ የጀመርከው የፍየልና የኰርማ መስዋዕት እያቀረቡ ይቅር ከሚባሉትና መድኀኒትነቱን ከገለጹት ጋር እንጅ ፤ በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደም ስለመዳንና ከበደል ስለመጥራት የተናገሩ ሰዎችን ቃል አይደለም ፡፡ ዋቢ የለሽ አመክንዮ ላልከውማ በሉቃስ የተገለጸውን ከነባራዊው ሁኔታ ጋር እንድትመዝነው አቀረብኩልህ ፤ ረጋ ብሎ ለመረዳት መሞከር ብልህነት ነው ፡፡ አንተ እንዳልከው ሳይሆን መድኃኒቴ ያለችው ከመስቀል መስዋዕትነቱ ከመፈጸሙ አስቀድሞ ከአዳም በደል ስለጠበቃት ነውም እላለሁ ፡፡

  “ማንም ሰው ከተፈጥሮ ሥርአት ውጪ ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን እርሷ ያለዘርአ ብእሲ ፀንሳ መውለዷ ተአምራዊ በሆነ መንገድ የተከናወነ በመሆኑ እርሱ የተለየ ነገር ነው፡፡ ከዚህ በቀር ግን ማንም ቢሆን (ሰው ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር) ከኃልዮ ከነቢብና ከገቢር ኃጢአት ንጹሕ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰው እኮ የኃልዮ የነቢብና የገቢር ኃጢአቶችን የሚሠራው ከአዳም በወረሰው ኃጢአተኛ ባሕርይ ምክንያት ነው፡፡”

  ይኸን የኃጢአት ሰነድ ለአንተ ማን ይሆን ያስረከበህ ? ጥቅምህስ ምን ቢሆን ይህን ያህል ለማለት ደፈርክ ? ቤተ ክርስቲያናችን ከኃልዮ ከነቢብና ከገቢር ኃጢአቶች የጸዳች መሆኗን ታስተምራለች ፡፡ ያንተ መጽሐፍ ከየት ወገን ቢሆን ነው የቅድስት ድንግል ማርያምን በደልና ኃጢአት አለባት ለማለት የቻልከው ? ሠረቀች ፣ አመነዘረች ፣ ዋሸች ፣ …. እስቲ ያነበብከውን ድክመቷን በሙሉ ሳትቀናንስ አስነብበኝና እኔም እንዳንተው ምስክር እንድሆንላት ፡፡ በአንተ ከቀረበው “ሰው እኮ የኃልዮ የነቢብና የገቢር ኃጢአቶችን የሚሠራው ከአዳም በወረሰው ኃጢአተኛ ባሕርይ ምክንያት ነው” ከሚለው በሎጅክ ስንነሳ ድንግል ማርያም ከኃልዮ ፣ ከነቢብና ከገቢር በደል የጸዳች ስለነበረችና ስለሆነች ፣ አዳማዊው በደል ወደ ርሷ አልደረሰም ማለት ነው ብለን እንደመድማለን ፡፡

  ኤርምያስ በማህጸን ሆኖ ስለተቀደስ ጥንተ አብሶ ተወገደለት አላልኩም ፡፡ ስለ ተቀደሰ ግን በዘመኑ ለነበሩት ሁሉ ፣ ለእኔና ለአንተም ጭምር ነቢይ ሆኖ አገልግሏል ፡፡ ነቢይነት የጥንቆላ ሥራ እንዳይመስልህና እንዳታቃልለው ፡፡ ሓዋርያው ጳውሎስም በማኀጸን ገና ሳለሁ ለየኝ ብሎ ይመሰክራል ፡፡ ያም በመሆኑ ቀንበሩን ተሸክሞ በትጋት አገለገለ ፡፡ የድንግል ማርያምን ስንመለከት ደግሞ የተመረጠችው ለዚህ ዓለም ፈጣሪ ለሆነው አምላካችን እናትነት ነው ፡፡ ስለዚህም ቅዱስ የሆነው ፣ በቅዱስ ሥፍራ ማደርን መርጧልና ፣ ጥንተ አብሶ እንዳያገኛት ብቻ ሳይሆን ከሌሎችም በደሎች እስከ መጨረሻው ጠብቋታል ፡፡

  በተራ ቁጥር አምስት ላይ ኢሳይያስ ስለ ድንግል ማርያም የጻፈውን ሁሉ ጠቅልለህ በአንድ ኃይለ ቃል (ኢሳ 7፡14) ብቻ መገደብህ የሚያሳየው ቃሉን መካድህን ወይም ማጉደልህን ነው ፡፡ በእርግጥ ነቢዩ በአንድ ሥፍራ ሁሉንም ጠንቅቆ አላስቀመጠውም ፡፡ ነገር ግን በተገለጸለት ሰዓትና ቦታ የተረዳውን ከማስፈር አልቦዘነም ፡፡ ያንን የተበታተነውን አሰባስቦ መረዳቱ መጽሐፉን የሚጠቀምበት ሰው ፋንታ ነው ፡፡ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ ከማለት ጀምሮ እስከ ድንግል ትጸንሳለች ፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ያለውን ፣ ተበታትኖ ስለተቀመጠ ብቻ ፣ መካድ ግን ትክክል አይደለም ፡፡

  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 2. ክፍል ሁለት
  በስድስተኛ ተራ ቁጥር ጽሁፍህ “ነገር ግን መጽሐፉ የኖረውን ልማድ ያጸና እንጂ ቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮዋንና ሥርአቷን በመጽሐፍ ቅዱስ እንድትፈትሽ እድል የሰጠ አይደለም፡፡” የሚለው ስህተት ሆኖ አግኝቼአለሁ ፡፡

  በመጀመሪያ የሃይማኖት ዶግማና ቀኖና ወግ ፣ ባህል ፣ ልማድ እያሉ መጥቀስ ትልቅ ግድፈትን መፈጸም ነው ፡፡ ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረን ልማድን ሳይሆን በዶግማና በቀኖና የጸናውን ሃይማኖትን ነው ፡፡ ስለዚህም ይህ ገለጻ የቤተ ክርስቲያኗን ትምህርተ ሃይማኖት ፣ ቀኖናና ዶግማ የማይቀበሉ ቡድኖች አባባል መሆኑን ያስረዳኛል ፡፡ አንተ እንደምትፎክርበት ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በትውፊት ካልታገዘ ብቻውን የተሟላ መልስ አይሰጠንም ፡፡ ይህንኑ በተደጋጋሚ ፣ በተለያየ ጽሁፍ ለመግለጽና ለማስረዳት ሞክሬአለሁ ፡፡ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ፣ ዘመናዊ ሳትሆን ጥንታዊት ናት ፡፡ በብሉይም በሐዲስም የነበረውን ትምህርት አልፋበታለች ፡፡ ስለሆነም ከመጀመሪያው አንስቶ የቀረበው ትምህርት በትውፊትና በጽሁፍ ደርሷታል ፡፡ ስለዛም መጽሐፍ ቅዱሱን በትክክል እንድንረዳው ከትውፊትም እያገናኘች ፣ ብሉይን ከሐዲስ ሳታጋጭና ሳታጣላ (የተሻረውን ሽራ) ታስተምራለች ፡፡ ሌሎቹ ጋር ስንመለከት ግን ፣ ሐዋርያት ከተሰደዱ በኋላ የደረሳቸውን የወንጌል ትምህርትን ብቻ ነው የሚያነበንቡት ፡፡ የቃሉን ከየት መጣና ለምን የሚሉ ጥያቄዎችን ፈጽሞ አይመልሱም ፡፡ ስለዛም በትርጓሜ እየሳቱ ፣ ክርስትናን ለየራሳቸው እንዳ ፍርፋሪ መከፋፈል መርጠዋል ፡፡

  እስቲ አንተም መጽሐፍ ቅዱሱን ብቻ በመጠቀም ምዕራፍን ከምዕራፍ በማጣቀስ ማስማማት ከሆነልህ ሦስት ጥያቄዎችን ከወንጌል ልበልልህ
  1. በሉቃስ ሦስትና በማቴዎስ አንድ ፣ የዩሴፍን አባት ማን ይሉታል ? አያቱስ ፣ ቅመ አያቱስ … ቀጥል ? ከዚህ መልስ በመነሳት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ አላነብም ፤ አልሰማም ፤ አልቀበልም የሚል ሰው ለድንግል ማርያም ሁለት ዕጮኛ ሊሰጣት ግድ ይላል ፡፡
  2. ዮሐ 4፡16 – 18 “ኢየሱስም። ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነዪ አላት። ሴቲቱ መልሳ። ባል የለኝም አለችው። ኢየሱስ። ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤ አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ አላት።” ፡፡ ባልሽን ጠርተሽ ነይ ካላት በኋላ ፣ መልሶ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም ስለምን ይላታል ፡፡
  3. ሰንበት ካለፈ በኋላ መቃብሩን ሊያዩና በድን ሥጋውን ሽቱ ሊቀቡ ስንት ሴቶች መጡ? ሦስት (ማር 16፡1) ፣ ሁለት (ማቴ 28፡1) ፤ ወይስ አንድ (ዮሐ 2ዐ፡1) ፡፡ ምርጫ ስለሆነ አንድ መልስ ብቻ ሊኖርህ ግድ ነው ፡፡

  ሦስት ካቀረብኩ ፣ ስለ ትውፊት አስፈላጊነት ለማስረዳት ይበቃ ይመስለኛል እንጅ ፣ መሰል ጥያቄዎችን በመቶዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡ ስለዚህም በትውፊት የደረሱንን ትምህርቶች ሳናጣጥላቸው ፤ የመጽሐፍን ቃልና ጽንሰ ሃሳብ እስካልተጻረሩ ፣ እስካላፈረሱ ወይም እስካልሻሩ ድረስ በአግባቡ መጠቀም አግባብ ነው ፡፡ እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ቃሉ በሙሉ አለመስፈሩን እየመሰከረ ፣ ይጻፍ ቢባል ፣ ዓለም ራሱ ባልበቃችውም ነበር በማለት ይገልጸዋልና ፣ ትክክለኛውን የትውፊት እውነታንም አሜን ብለን እንቀበል ፡፡
  ከዚህም በመነሳት ቅድስት ድንግል ማርያም ከጥንተ አብሶ ተጠብቃ ቆይታለች ቢባል የአምላክን ጠባቂነትና ቸርነትን ፣ ፈቃዱንና የምህረት መንገድን አስቀድሞ እንዳዘጋጀልን ይገልጻል እንጅ ፣ ከመጽሐፍ ቃል ማፈንገጥ አይሆንም ፤ ስለሆነም በተልካሻ የመጽሐፍ ማስማማት ብልሃት ትውፊትን መናዱ ይቁምልን ፡፡

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
  Replies
  1. kale hiwot yasamalin!

   Delete
 3. Tebarek Anonymous

  ReplyDelete
 4. ስለ ጸጋ ስጦታ ጥቂት ማብራሪያ ፡-
  ሐዋርያት የኢየሱስን ሞትና ትንሣዔ ከሁሉ አስቀድመው ያመኑ ስለሆኑ ፣ እምነታቸውን ተከትሎ ከአዳም በደል ሆነው ነበር እላለሁ ፡፡ ከዛ በኋላ ደግሞ ወንጌልን በአይሁድና በአሕዛብ መካከል እየተዘዋወሩ እንዲያስተምሩና ወደ ድኀነት መንገድ እንዲመልሱ ሲያሰማራቸው ባርኳቸዋል ፤ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ በማለትም አጽንቶአቸዋል ፡፡/ማር 16፡15-2ዐ/ ይኸ መባረክ ደግሞ የተለያየ ጸጋን አጐናጽፏቸዋል ፡፡ መጽሐፍም ይህንኑ የጸጋ ስጦታ ሲመሰክርልን “እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና” /ዮሐ 1፡16/ ፤ “ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።” /ሥራ 4፡33/ ይላል ፡፡

  ሐዋርያው የጸጋ መልዕክት መቀበሉን ሲመሰክር “ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።” /ሥራ 2ዐ፡24/ በማለት ይገልጸዋል

  ሐዋርያት በተሰጣቸው ጸጋ ምክንያት ድውያንን ፈውሰዋል ፤ ሙታንን አስነስተዋል ፤ እየተወገሩምና በመከራ መሃል በጽናትና በትዕግስት በጸሎት አምላካቸውን ሳያመነቱ አመስግነዋል ፤ “እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር።” /ሥራ 6፡8/ ብሏልና

  ስለ ተሰጣቸው ጸጋ መለያየትና መበላለጥም ጭምር ሲገልጽ “የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው” /1 ቆሮ 12፡4/ ፤ “ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ። ደግሞም ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ አሳያችኋለሁ።” /1 ቆሮ 12፡31/ ፤ “እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፤” /ሮሜ 12፡6/

  እናም ስለዚህ የሐዋርያት የጸጋ ሙላት ከአዳማዊው በደል ነጻ የመሆን አዋጅ ሳይሆን ፣ ከኢየሱስ የተሰጣቸው የተለያየ መንፈሳዊ ሃብት ነው ፡፡ ስለሆነም የድንግል ማርያም በመልአኩ “ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ /ሉቃ 1፡28/ መባል አዳም የተገፈፈው ጸጋ ፣ እንዳልጐደለባት መመስከሩ ነው እንጅ ሐዋርያተ በጌታ እንደተሞሉት መሞላት ዓይነት አይደለም እላለሁ ፡፡ ይኸም ቃል የተነገራት መድኃኒቴ እንዳለችው ሁሉ ለድኀነት የመጣው ወልድ ሳይጸነስ ፣ መስዋዕትነት ሳይፈጸም ነውና፡፡

  ReplyDelete
 5. አንተ እንዳልከው ሳይሆን መድኃኒቴ ያለችው ከመስቀል መስዋዕትነቱ ከመፈጸሙ አስቀድሞ ከአዳም በደል ስለጠበቃት ነውም enlalen

  ReplyDelete
  Replies
  1. How do you reason out that she was immuned from Adam's sin, you can subtantiate your statement by quoting from the bible. I totally disagree the reply given by Anonymous.

   Delete
  2. How do you reason out that she was immuned from Adam's sin, you can subtantiate your statement by quoting from the bible. I totally disagree the reply given by Anonymous July 6,2012 @4:31PM.

   Delete
 6. (የማክሠኞ ውዳሴ ማርያም)
  ለጊዜዉ ይሄን አንብቡት ከድረ ገፅ ያገኘሁት ነዉ
  (የማክሠኞ ውዳሴ ማርያም) ፡- “የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችንም መጀመሪያ፣ የንጽሕናችንም መሠረት መድኃኒታችንን በወለደችልን በድንግል ማርያም ሆነልን፡፡”እመቤታችን ከኢትዮጵያውያን ሕይወት ጋር የተቆራኘች ናት ፡፡ ነፍሰ ጡር ልጅ ልትወልድ ስታምጥ “ማርያም! ማርያም!”፣ ስትወልድ “እንኳን ማርያም ማረችሽ፡፡” “ማርያም ጭንሽን ታሙቀው፡፡” “ማርያም በሽልም ታውጣሽ፡፡” ትባላለች፡፡ በአራስነት ወራቷም “የማርያም አራስ” ተብላ ድንግል ማርያም በአደራ ትሰጣለች፡፡ ሕጻናት ለብቻቸው ሲስቁ “ማርያም እያጫወተቻቸው ነው፡፡” ይባላል፡፡ ሕጻናቱም አድገው ሲጫወቱ ማምለጫ ፍለጋ “የማርያም መንገድ ስጠኝ/ ስጪኝ፡፡” ይባባላሉ፡፡ አንድን ሰው አንዳች ነገር እንዲያደርግልን ሽተን ስንለምንም “እንደው ለእኔ እንደ ቆምህልኝ ማርያም ትቁምልህ” ብለን ስሟን ጠርተን እንማጸነዋለን፡፡ ሰማዩን ቀና ብለን ለኖኅ የተሰጠውን ውብ የቃል ኪዳን ምልክት ቀስተ ደመና ስናይም “የማርያም መቀነት”፣ ፈረስ የምትመስል በራሪ ፍጥረትንም “የማርያም ፈረስ” እንላለን፤ ወዘተ.፡፡አንዳንዴ ሳስበው በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ እንደማርያም ትልቅ ስፍራ ያለው ምንም ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ማርያምን ከቤት እስከ ቢሮ፣ ከትምህርት ቤት መታወቂያ ውስጥ እስከ ታክሲ ጋቢና ድረስ ታገኟታላችሁ፡፡ በቤተክርስቲያኗን ትውፊት ስንመለከትም እንደድንግል ማርያም ብዙ መልክእ የተደረሰለት በርካታ መጽሐፍ የተጻፈለት ፣ ቁጥሩ የበዛ በዓል የሚከበርለት አንድም ጻድቅ ወይም ቅዱስ አይገኝም፡፡ የዚህ ሁሉ ምክንያቱ ግን ሌላ አይደለም፡- ከላይ እንደጠቀስነው እውነተኛ የጽድቅ መብልንና እውነተኛ የሕይወት መጠጥን የወለደችልን ኃጢኣታችን ከክርስቶስ እንዳያርቀን የምትተጋ፣ እውነተኛ የክርስቲያኖች ረዳት፣ ርኅርኅተ ኅሊና መሆኗ ነው እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 7. ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል፥ የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና፤ መላእክት የሚፈሩትን፥ ትጉሆች በሰማያት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማኅፀንዋ ተሸከመችው። ይህች ከኪሩቤል ትበልጣለች፥ ከሱራፌልም ትበልጣለች፥ ከሦስቱ አካል ለአንዱ (ለወልድ) ማደሪያ ሆናለችና። (ኪሩቤል ቢሸከሙ የእሳቱን ዙፋን ነው፥ ሱራፌል ቢያጥኑ የእሳቱን ዙፋን ነው፥ እርሷ ግን እርሱን ባለቤቱን ተሸከመችው)። የነቢያት ሀገራቸው ኢየሩሳሌም ይህቺ ናት፥ ለቅዱሳን ሁሉ የደስታቸው ማደሪያ ናት፤ በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው፤ በቅዱሳን ላይ (በረድኤት) የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰው ሆኗልና፥ ኑ ይህን ድንቅ እዩ፥ ስለተገለጠልን ምሥጢር ምስጋና አቅርቡ፤ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና፥ ቃል ተዋሕዷልና፤ ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ፥ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት፤ የማይታወቅ ተገለጠ፥ የማይታይ ታየ፤ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በርግጥ ሰው ሆነ። ትላንት የነበረው፥ ዛሬም ያለው፥ መቼም የሚኖረው፥ ኢየሱስ ክርስ ቶስ እንሰግድለትና እናመሰግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው።» ኢሳ ፮፥፪፣ መዝ ፩፻፵፯፥፩፣ ኢሳ ፱፥፩-፪፣ ማቴ ፬፥፲፮፣ ዕብ ፲፫፥፰፣ ራእ ፩፥፰። (የረቡዕ ቁ. ፯)

  - « ሰለ ሔዋን የገነት ደጅ ተዘጋ፥ ዳግመኛም ስለድንግል ማርያም ተከፈተልን፥ ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ አደለን፥ ይኸውም እኛን ስለመውደድ መጥቶ ያዳነን የክርስቶስ ክቡር ሥጋው ክቡር ደሙ ነው።» ዮሐ ፮፥፶፫ ( የሐሙስ ቁ.፫)።

  ReplyDelete
 8. ... ንፁህ ዘርን በአዳም ልጅ በሴት በኩል ጠብቆ ሊያቆይልና ለአሕዛብና ለሕዝብ መድኃኒት የሚሆን አምላክን በማሕፀኗ የምትሸከም ንፅህት ዘርን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊያስተላልፍልን ወዶ የእግዚአብሔርን ሕግጋት የሚጠብቁ ሕዝቦችን በምድር ለየልን፡፡ ዓለም ሁሉ በበደለበት በዘመነ ሰባትካት ይህች ንፅህት ዘር በደል ባልተገኘበት በኖኅ አብራክ ነበረች፡፡ ዓለም ሁሉ እግዚአብሔርን በመርሳት በጣኦት አምልኮ በጠፋበት በአብርሃም ዘመን ይህች ንፅህት ዘር የጣኦትን አምልኮ በመጥላት እግዚአብሔርን በፍጥረቱ ተመራምሮ ያገኘ በአብርሃም አብራክ ውስጥ ነበረች፡፡ እንዲሁም ብኩርናን እጅግ በመሳሳትና በጉጉት ከኤሳው ከወንድሙ በእምነቱ ብዛት በተቀበላት የእግዚአብሔርን ጸጋ በናፈቀ በያዕቆብ አብራክ ውስጥ ነበረች፡፡ በዚህ ሁኔታ ለእግዚአብሔር እራሳቸውን የበለጠ ባስገዙ በሕሊናቸውም በስጋቸውም የተሻለ ንፅህና በነበራቸው ውስጥ ከዘመን ዘመን ያች ንፅሕት ዘር ተሸጋገረችልን፡፡ ለዚያ ነው ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር” (ኢሳ. ፩፥፱) ያለው...from orthodox for africa blog

  ReplyDelete
 9. ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕና
  “በቅዳሴ ማርያም በእንተ ብፅዕት ወፍሥሕት ወስብሕት በኲሉ ወቡርክት ወቅድስት ወንጽሕት እግዝእትነ ወላዲተ አምላክ ማርያም ድንግል” ትርጉም “ብፅዕትና ፍሥሕት በሁሉ ዘንድ የተመሰገነች ቡርክትና ቅድስት ንጽሕትም ስለሆነች ስለ አምላክ እናት ስለ እመቤታችን ድንግል ማርያም” የሚልና “ወሶበ ርእየ ንጽሕናኪ ለሊሁ እግዚአብሔር አብ ፈነወ ኀቤኪ መልአኮ ብርሃናዌ ዘስሙ ገብርኤል ወይቤ ለኪ መንፈስ ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ ወኃይለ ልዑል ይጼልለኪ” ማለትም “እርሱ ቅሉ እግዚአብሔር አብ ንጽሕናሽን ባየ ጊዜ ፣ ስሙ ገብርኤል የሚባል ብርሃናዊ መልኣኩን ወደ አንቺ ላከ ፣ መንፈስ ቅዱስ በላይሽ ይመጣል ፣ የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል አለሽ” በማለት ንጽህናዋና የሚገልጽ ቃል አለ ፡፡

  እንደዚሁም ደግሞ “እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ፤ በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ ፤ ” የሚለው ዘወትር ከአባታችን ሆይ ቀጥሎ የሚጸለየው ጸሎትም ፣ ድንግልና በማለት የሚገልጸው ከሀልዮ (ሃሳብ) ፣ ከነቢብና (ንግግር) ከገቢር (ሥጋ) በደል ንጽሕት መሆኗን ነው ፡፡ ወንድም ጸጋ ታደለ ከአባቶች ተቀብሎ ካስተማረን ቃል ደግሞ ፣ የአዳም በደል በውጤቱ ወደ ሥጋዊና መንፈሳዊ ኃጢአት ስለሚመራ ፣ ከዚህ ሥጋዊና መንፈሳዊ ኃጢአት ነጻ የሆነ ቅዱስ ሰው /ቅድስት ድንግል ማርያም/ አዳማዊው በደል አልነበረበትም ቢባል ትክክል ስለሚሆን አያከራክርም ፡፡

  ድንግል ማርያም በነገረ ድኀነት
  ስለ ነገረ ድኀነት ሲተነትኑም ቅድስት ድንግል ማርያም ከፍጡራን በላይና ከፈጣሪ (ሥላሴ) በታች የሆነች የአምላክ እናት ፣ ስለ ድኀነታችን ታላቅ አስተዋጽዖ ያደረገች ለእኛም የመንፈስ እናታችን ናት በማለት አባቶች ያስተምራሉ ፡፡ ይኸንኑም በዚሁ ድረገጽ ምስላቸው ከተደረደረው መሃል ያሉት አንዱ አባት በሚከተለው ቃል በመጽሐፋቸው አስፍረውታል ፡፡

  “የሰውን ልጅ የመዳን ቀን ከሰው ልጆች በቅድሚያ ያወቀች ፣ ለእግዚብሔር የማዳን ሥራ መሣሪያ በመሆን አዳኙን መሲሕ የወለደች ፣ ለእግዚአብሔር ታማኝ የምሥጢር መዝገብ ናትና ነው ፡፡ በመዳን ትምህርት የእምቤታችን ሕይወት ከእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ጋር የተዋሐደ ነው ፡፡ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያናችን ድንግል ማርያም ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ሆና ትከበራለች ፡፡ በመዝሙራችንም ሆነ በቅዳሴያችን ከስመ ሥላሴ ቀጥለን የምንዘምረው የድንግል ማርያምን ውዳሴ ነው ፡፡ አምላክ ሰው በመሆኑ ለሰው ልጆች የዋለውን ውለታ ፣ ስደቱን ፣ መንከራተቱን ፣ ስቅለቱንና ሞቱን በምናስታውስበት ጊዜ ድንግል ማርያምን ለመለየት አይቻልም ፡፡ ወልዳ ያስገኘች ናት ፤ አዝላ የተሰደደች ናት ፤ በማስተማር ጊዜው አብራ ተንከራትታለች ፤ በተሰቀለበት ዕለት ከመስቀሉ ሥር አልተለየችም ፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየው እመቤታችን የሰውን ልጆች ለማዳን ከተደረገው አምላካዊ ጉዞ አለመለየቷን ነው ፡፡”

  “በአዲስ ኪዳንም ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም በቀር በመላእክት ቃል “ቡርክት አንቲ እምአንስት ፣ ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ ፣ መንፈስ ቅዱስ የመጽእ ላእሌኪ ወኃይለ ልዑል ይጼልለኪ “ ተብሎ የተመሰገነ አልነበረም ሉቃ 1፡48 ፡፡ እርሷም ናሁ እምይእዜሰ ያስተበፅዑኒ ኩሉ ትውልድ ፡፡ ከእንግዲህስ ወዲህ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል ብላ በተናገረችው መሠረት በልጅዋ ያመኑ ክርስቲያኖች ሁሉ መመኪያ ዘውዳችን ፣ ጥንተ መድኃኒታችን ፣ የንጽሕና መሠረታችን ድንግል ማርያም ናት እያሉ ይዘምራሉ ፡፡”
  ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በአቡነ ጎርጎርዮስ ገጽ 155 – 156

  ይኸንኑ የአባቶች ትምህርት መልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው ሲያብራሩትም “ስለ ነገረ ድኅነት ስንናገር ጌታ ድኅነታችንን በመስቀል ላይ ፈጸመ የምንለው የዕለት ፅንስ ሆኖ በእመቤታችን ማኅፀን የጀመረውን ነው ፡፡ ሥጋውን ቆረሰልን ደሙን አፈሰሰልን ነፍሱን አሳልፎ ሰጠልን ብንል ከእርሷ የነሳውን ነው፡፡ ከእርሷ ነሥቶ በመስቀል ላይ የፈተተውን ሥጋውን እና ደሙንም የሕይወት ማዕድ አድርጎ ሰጥቶናል፡፡ መለኰታዊውን ፍህም በማኅፀን ከመሸከም ጀምሮ ይህ ታላቅ ምሥጢር የተፈጸመባት በመሆኑ መልዕልተ ፍጡራን መትሕተ ፈጣሪ ሆና ትመሰገናለች ፡፡ በመዝሙራችንም ሆነ በቅዳሴአችን ከስመ ሥላሴ ቀጥሎ የምንዘምረው የእመቤታችንን ምሥጋና ነው ፡፡ ቅዱስ ዳዊት « መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው ፤ ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል፤ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው ነገር ድንቅ ነው ፡፡» ያለው ለዚህ ነው ፡፡ መዝ 86.1-3 ፡፡ እርሷም እሳተ መለኰትን በማኅፀንዋ ተሸክማ ፣ « ሰውነቴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች ፡፡ ልቡናዬም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች ፡፡ የባርያውን ትሕትና ተመልክቷልና ፡፡ (ትንቢተ ኢሳያስን ተመልክቼ አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ከምትወልደው እመቤት ዘመን ቢያደርሰኝ ገረድ ሆኜ አገለግላታለሁ የሚለውን የልቤን አሳብ አይቷልና፡፡) እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብዕፅት ይሉኛል፡፡ ታላቅ ሥራን ሠርቶልኛልና ስሙም ቅዱስ ነው ፡፡ » ብላለች ፡፡ ሉቃ 1.46 ፡፡

  ለእመቤታችን የተደረገላት ታላቅ ሥራ ፡-
  1ኛ ከጥንተ አብሶ ነፃ ሆና መፈጠሯ ነው ፤
  2ኛ ፡- ከሀልዮ ከነቢብ ከገቢር ኃጢአት ነፃ መሆኗ ነው ፤
  3ኛ ከልማደ አንስት ነፃ መሆኗ ነው ፤
  4ኛ ሰማይና ምድር የማይችሉትን ኪሩቤል እሳታዊ መንበሩን የሚሸከሙለትን ፣ ሱራፌል መንበሩን የሚያጥኑለትን ፣ መላእክት የሚንቀጠቀጡለትን በማኅፀኗ መሸከሟ ነው፡፡
  በመሆኑም እንደ ቅዱስ ዳዊት « ሀገረ እግዚአብሔር ድንግል ማርያም ሆይ ለአንቺ የተደረገው ነገር ዕፁብ ድንቅ ነው ፤» እያልን እናመሰግናታለን ፡፡”
  ይቆየን
  ክፍል ሁለት ይቀጥላል

  ReplyDelete
 10. ክፍል ሁለት
  እምቅድመ ዓለም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአምላክ ኀሊና ታስባ እንደኖረች በመግለጽ በትምህርተ ሃይማኖት ዕውቀትም ሲመግቡን እንደሚከተለው ይገልጹታል ፡፡ “ሊቁ ቅዱስ ያሬድ « ዘእንበለ ይትፈጠር ሰማይ ወምድር ወዘእንበለ ይሣረር ምድረ ገነ ሀለወት ስብሕት ቅድስት ወቡርክት ይእቲ ማርያም እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ፣ ጽዮን ፣ ቅድስት፣ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት፡፡ ትርጉም የመላእክት እህታቸው፣ የሰማዕታትና የጻድቃን እናታቸው፣ ጽዮን ፣ ቅድስት፣ የክርስቲያን ሰንበት የተባለች የተመሰገነች በንጽሕና በድንግልና የተለየችና የተባረከች እርሷ ማርያም ሰማይና ምድር ሳይፈጠር የገነት ምድርም መሠረት ሳይጣል ነበረች፡፡ » ብሏል ፡፡

  ዳግመኛም « በቤተልሔም ተወሊዶ መድኅን ክብረ ቅዱሳን ፍስሐ ለኵሉ ዓለም ወሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ወይቤላ እግዚአብሔር ለማርያም ፡- አዝማንየ አዝማንከ አምጣንየ አምጣንኪ ማርያም ሐቀፍኪዮ ወአነ ዮም ወለድኩዎ ፡፡ ለዓለሙ ኹሉ ደስታ የሚሆን የቅዱሳን ክብር መድኃኔዓለም በቤተልሔም ተወልዶ ፡- ለሰው ልጅ ዕረፍት ሰንበትን ሠራ እግዚአብሔር ማርያምን ፡- ዘመኖቼ ዘመኖችሽ መጠኖቼ መጠኖችሽ ናቸው ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩት፤ ማርያም ሆይ አንቺ ታቀፍሺው ፡፡ » የሚል አለ ፡፡

  ቅዱስ ያሬድ በድጓው እንደገለጠው እግዚአብሔር እመቤታችንን « ዘመኖቼ ዘመኖችሽ ናቸው ፤» ማለቱ ዓለም ከመፈጠሩ ዘመን ከመቆጠሩ በፊት በእርሱ ኅሊና መኖሯን የሚያስረዳ ነው፡፡ « መጠኖቼ መጠኖችሽ ናቸው ፤ »ማለቱ ደግሞ እርሱ ቅድመ ዓለም አካላዊ ቃል ወልድን ያለ እናት ወልዶት አባት እንደሆነው እርሷም ድኅረ ዓለም አካላዊ ቃል ወልድን ያለ አባት ወልዳው እናት እንደሆነችው የሚያመለክት ነው ፡፡ ምሥጢራዊ መልእክቱም « ወላጆች (አባትና እናት) ለወለዱት ልጅ እኩል እንደሆኑ ሁሉ ወልድን በመውለድ በወላጅነት መሰልሽኝ ተስተካከልሺኝ ፤ » ሲላት ነው ፡፡ ይህም ፈጣሪን እና ፍጡርን የማነፃፀር የማስተካከል ሳይሆን የተሰጣትን ክብርና ልዕልና የማሳየት ነው፡፡ ለምሳሌ ጌታ ደቀመዛሙርቱን ፡- « እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል ፤ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፡፡» ብሏቸዋል ፡፡ ዮሐ 14 .12 ፡፡ ይህም በማስተማርና ተአምራት በማድረግ እንደሚመስሉት ሲነግራቸው ነው ፡፡ «የሚበልጥ ያደርጋል፤» ማለቱም ፡፡ እርሱ ያስተማረው ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ነው፡፡ እነርሱ ግን ከዚህ በላይ ሃያ ሠላሳ ዓመት የሚያስተምሩ ስለሆነ ነው፡፡ እርሱ ለአብነት ሁለት ሦስት ሙት ቢያነሣ እነርሱ ደግሞ በስሙ ከዚያ በላይ ብዙ ስለሚያስነሡ ነው፡፡ እንዲሁም ሐዋርያው ጴጥሮስ በጥላው ፤ በጳውሎስም የልብስ ቁራጭ ከደዌአቸው ይፈወሱ እንደ ነበር ልብ ይሏል፡፡ /ሥራ 5፡15 ፣ 19፡12/

  « ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸአዳ፤ እመቤታችን ማርያም ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች ፤ » ይላል ፡፡ ይህንንም በድጓው የተናገረው ቅዱስ ያሬድ ነው ፡፡ እመቤታችን በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ማብራቷ ከጥንተ አብሶ ነፃ ሆና መፈጠሯን የሚያመለክት ነው፡፡ አዳም ይኽንን ስለሚያውቅ ነው እመቤታችንን ተስፋ ያደረገው ፡፡ ምክንያቱም በውስጡ እንደ ነጭ ዕንቁ ስታበራ ይታወቀው ነበርና ነው ፡፡ አባ ሕርያቆስ ይህ ምሥጢር ተገልጦለት « ከገነት በተሰደደ ጊዜ የአዳም ተስፋው አንቺ ነበርሽ ፤» እያለ እመቤታችንን አመስግኗታል፡፡ ይህም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትእዛዝን በመተላለፍ በአዳም ላይ ከመጣ ጥንተ በደል በአምላካዊ ምሥጢር ተጠብቃ ከአዳም ወደ ሴት ከሴት ወደ ኖኅ ከኖኅ ወደ ሴም ከሴም ወደ አብርሃም ስትቀዳ የኖረች ንጽሕት ዘር መሆኗን ያስረዳል ፡፡ ከላይ እንደተገለጠው ነቢዩ ኢሳይያስ « እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ » ያለው ይኽንን ነው ፡፡

  በክብረ ነገሥት ገጽ 71 የተጻፈውም ይኸንኑ የሚያጠናክር ነው ፡፡ “አዳኙ ከዚህ እንደሚመጣና ከአባቶቻችሁ ከአንተና ከዘርህም ጋር እንደሚያድንህ ምልክት ይሆንልሃል ፡፡ በመምጣቱም ከሄዋን በፊት መድኃኒታችሁ እንደ ባህር እንቁ ከአዳም ሆድ ውስጥ ተፈጠረች ፡፡ ሄዋንንም ከአዳም ከጎኑ አጥንት በፈጠራት ጊዜ ወደ ቃየንና ወደ አቤል አልወጣችም ፡፡ ከአዳም ሆድ ወጥታ ወደ ሶስተኛው ወደ ሴት ሆድ ገባች እንጂ ፡፡ ከእሱም ይህች እንቁ በኩር ወደ ሆኑት ስትሄድ እስከ አብርሃም ደረሰች ፡፡ ከአብርሃም ወደ ንፁህ ይስሃቅ ገባች እንጂ ወደ በኩሩ ወደ እስማኤል አልወጣችም ፡፡ ከይስሃቅም ወደ ያእቆብ ገባች ፤ ከያዕቆብም ወደ የዋሁ ይሁዳ ፣ ወደ ትእግሥተኛው ፋሬስ ፣ ከዛም እስከ እሴይ ድረስ በየበኩሩ ተላለፈች ፡፡ ቀጥሎም ወደ ዳዊት ከዛም ወደ ሮብአም ሄደች ፡፡ እነሱ በክህደታቸውና በክፋታቸው ይሰቅሉታልና ፤ ባይሰቀል ኑሮ መድሃኒታችሁ ባልሆነ ነበር ፡፡ ያለ ኃጢአቱ ይሰቀላል ፤ ያለጥፋትም ይነሳልና ፡፡ …..”

  “በዚህችው እንቁ የነፁ ይሆናሉና ፡፡ እሷ የተቀደሰችና የነፃች ናትና በእሷ ትቀደሳላችሁ ፡፡ ትነፃላችሁም ፡፡ ዓለሙን ሁሉ ስለ እሷና ስለ ፅዮን ፈጥሯታልና ፡፡ ፅዮን ግን በበኩርህ ነበረች ፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝቦችም እስከ ዘላለም መድኃኒታቸው ትሆናለች ፡፡” “ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ይህችው እንቁ ከዘርህ ትወለዳለች ፡፡ ከፀሃይ ሰባት እጅ የነፃች ናትና ፡፡ አዳኙም ከመንበረ መለኮቱ ይመጣል ፡፡ በላዮም ላይ ያድራል ፡፡ ስጋዋንም ይለብሳል /ይዋሃዳል/” በማለት ይገልጻል ፡፡

  ቤተ ክርስቲያናችን ለምን ስለ እመቤታችን ዘወትር እንደምታስተምር አንዳንድ ሰዎች ግር ሲላቸው ይታያል፡፡ እንዲያውም ‹‹አላዋቂ ሳሚ...›› እንዲሉ ስለ እመቤታችን በማስተማሯ ስለ ጌታችን እንዳታስተምር አድርጓታል ብለው የሚናገሩም አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ግን ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የምታስተምረው ለርሷ ካላት ልዩ ፍቅር ብቻ ወይም ስለጌታችን የምታስተምረው ለርሷ ካላት ልዩ ፍቅር ብቻ ወይም ስለጌታችን የምታስተምረው አልቆባት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ከኢትዮጵያ ሊቃውንት በላይ ለነገረ መለኰት ምሁርና ጥንቁቅ ከማግኘት የሰማይን ስፋት ልክ ማግኘቱ ሳይቀል አይቀርም፡፡

  በቅዳሴያችን፣ በዘወትር ጸሎታችን፣ በመዝሙራችን፣ በሥርዓታችን፣ በትውፊታችን፣ በአለባበሳችን ሳይቀር የነገረ ድኀነት ትምህርት የሌለበት የለም፡፡ ሰዎች ዐረፍተ ዘመናቸው ደርሶ ወደ መቃብር ሲሸኙ በምናደርግው ጸሎተ ፍትሐት ለክርስቲያኑ በሚደረገው የቀብር ሥነ ሥርዓት ሁሉ ነገረ ድኀነት ይሰበካል ይገለጣል፡፡
  ቤተ ክርስቲያን ነገረ ማርያምን ዘወትር ለምእመናን የምታስተምረው ከነገረ ድኀነት ጋር የተያያዘ ጥልቅ ምሥጢር ስላለው ነው፡፡ ነገረ ድኀነትን ለመማር፣ ለመረዳትና ለማመን ነገረ ማርያም መሠረትና መቅድም ነው፡፡ ያለ ነገረ ማርያም ነገረ ድኀነት፣ ያለመሠረት ቤት ማለት ነው፡፡

  ወስብሐት ለእግዚብሔር

  ReplyDelete
 11. የነገረ ማርያመ ዕውቀት በእንደዚህ ያለ ቁራጭ ጽሁፍ ተተንትኖ ያበቃል ማለት ዘበት ነው ፡፡ ነገር ግን ምእመንን ለማናወጥ የሚራወጡትን ፣ እያወቁ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን ለመናድ የሚታገሉትን ለማስረዳትና ለመመለስ ቢረዳ በማለት የቀረበ ፣ የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረቱን ለማስቀኘት የተመረጠ ጽሁፍ ነው ፡፡ ሰው ሺህ ዓመት ከሚያስተምረው እግዚአብሔር በደቂቃ የሚገልጸው እጅግ ይበልጣል ያስተምራልምና እሱ ምሥጢሩን ለሁሉም እንዲገልጽ እጸልያለሁ ፡፡

  ReplyDelete
 12. I think the issue is whether እመቤታችን ከጥንተ አብሶ ነፃ ሆና መፈጠሯ or አለመፈጠሯ ነው፡፡ Answering this question with true evidence is the most important thing. We can write 2 or 3 pages or a book, but if we don't really give good convincing true answer, it will be a waste of time. I think we all agree that with the quote ቅድስት ድንግል ማርያም ከፍጡራን በላይና ከፈጣሪ (ሥላሴ) በታች የሆነች የአምላክ እናት. Not with this

  በዚህችው እንቁ የነፁ ይሆናሉና ፡፡ እሷ የተቀደሰችና የነፃች ናትና በእሷ ትቀደሳላችሁ ፡፡ ትነፃላችሁም ፡፡ ዓለሙን ሁሉ ስለ እሷና ስለ ፅዮን ፈጥሯታልና ፡፡ ፅዮን ግን በበኩርህ ነበረች ፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝቦችም እስከ ዘላለም መድኃኒታቸው ትሆናለች ፡፡” “ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ይህችው እንቁ ከዘርህ ትወለዳለች ፡፡ ከፀሃይ ሰባት እጅ የነፃች ናትና ፡፡ አዳኙም ከመንበረ መለኮቱ ይመጣል ፡፡ በላዮም ላይ ያድራል ፡፡ ስጋዋንም ይለብሳል /ይዋሃዳል/” በማለት ይገልጻል

  If this በዚህችው እንቁ የነፁ ይሆናሉና ፡፡ እሷ የተቀደሰችና የነፃች ናትና በእሷ ትቀደሳላችሁ ፡፡ ትነፃላችሁም true, why he came and died after all

  This is laughable ለኢትዮጵያ ህዝቦችም እስከ ዘላለም መድኃኒታቸው ትሆናለች, is Christianity for Ethiopians only. I she is really መድኃኒታቸው why the need አዳኙም ከመንበረ መለኮቱ ይመጣል ፡፡ በላዮም ላይ ያድራል ፡፡ ስጋዋንም ይለብሳል /ይዋሃዳል/ since she can save them. It is full of contradiction. Please come up with a good reasoning and argument and let us learn the truth. It is religion it is not a joke.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጥንተ አብሶ እንዳልነበረባትማ ከላይ በተለያየ ቦታ ተገልጿል ፡፡ ማመንና መቀበል ወይም አለመቀበል ብቻ ነው ቀጣዩ ጥያቄ መሆን ያለበት፡፡ የተቀረው ተጨማሪ ጽሁፍ የሚያትተው ከጥንተ አብሶ ነጻ ሆኖ ፣ ተጣጥፎ መቀመጥ ብቻ ሳይሆን ፣ ከዛም ባለፈ በነገረ ድኀነት ውስጥ ያላትን አስተዋጽዖ ለመግለጽ ነው ፡፡ ጭንቅላታችን በጐደሎ እየተንቦጫቦጨ እንዳያስቸግረን ፣ በማለት የታከለ የአባቶች ትምህርት ነው ፡፡ ነጻ ስለሆነች ምን ይጠበስ ታድያ እንዳይሉን ለማለት ፡፡ ክርስቶስ በተጠራበት የሷም ስም አብሮ ይጠራል ፡፡ ምክንያቱም ሥጋው ከሷ ሥጋ ስለሆነ ፡፡ ደሙ ከሷ ደም ስለሆነ ፡፡

   Delete
 13. የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።የዚህ ጥቅሥ ትርጉም እንዴት ይተረጎማል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. መፍጨርጨሬ ዕውቀት በመትረፉ ሳይሆን የተጣለውን ጥያቄ የሚነሳው ስላልተገኘ የምረዳውን ያህል ለጠያቂው ለማስረዳት ነው ፡፡ ለጎደለው እግዚብሔር ይርዳህ ፡፡

   አበበ ይኸን የጠቀስከውን ቃል በኢሳይያስ 61፡1 ላይ ታገኘዋለህ ፡፡ በ 42፡1 ላይም ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ ፣ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል የሚለውም ተቀራራቢ ስለ ኢየሱስ የተነገረ ትንቢት ነው ፡፡

   - የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው ፡- የሚለው መንፈስ ቅዱስ ለአብም ለወልድም የጋራ እስትንፋሳቸው ወይም መንፈሳቸው መሆኑንና በማቴ 3፡16-17 ለተገለጸው ጥምቀት የትንቢት ቃል መንገሩ ነው
   - ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ፡- /ወንጌል ትርጉሙ መልካም ዜና ፣ የምሥራች ማለት ነው/ ወንጌልን ማለትም የድኀነት መንገድ መገኘቱን ለማስተማር እንደሚመጣ ሲናገር ነው ፡፡ በማቴ 11፡6 ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል ይለዋልና ፡፡
   - እግዚብሔር ቀብቶኛልና ፡- በትንቢት ንጉሥነቱን ለመግለጽ ፣ ክርስቶስ እንደሚባል ሲያውጅልን ፤ የቀደሙ ነገሥታት የሚቀቡት በካህናት አለቃ ነበር ፤ የዚህኛው ሹመት ግን ምድራዊ አለመሆኑን ይናገራል
   - ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ ፣ ለተማረኩትም ነጻነትን ፣ ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ - በማቴ 5፡4 እና 11፡5 እንደተገለጸው የሚያዝኑ ይጽናናሉ ፣ ዕውሮች ያያሉ ፣ አንካሶችም ይሄዳሉ ፣ ለምጻሞችም ይነጻሉ ፤ ደንቆሮችም ይሰማሉ ፤ ሙታንም ይነሳሉ ለሚለው የትንቢት ቃል ሲሆን ፣ ሌላው ደግሞ በ 1 ጴጥ 3፡19 እንደተገለጸው በሲዖል በምርኮና በእስራት ያሉ ነፍሳትን የሚመለከት ነው

   ይኸን ለመተንተን የሞከረልህን ሰው እንድትመዝነው እነዚህን ሁለት እውነታዎች ልብ በልለት ፡-
   - በጣም አዋቂ የሆነው ሊቅ ፣ እንዳይሳሳት በመጨነቅ አንዳች አይናገርም
   - እጅግ ደደብ የሆነውም ደግሞ ፣ ምንም ስለማያውቅ ሃሳብ አይመጣለትምና አይተነፍስም እናም እኔ ግን ተንፍሻለሁ ፡፡

   በተረፈ የሃይማኖት ሊቃውንቱ ጥያቄ ሲቀርብላችሁ ሳትፈሩ ብቅ በሉና አስተምሩን ፣ ድኀነት ባይገኝበትም ፣ ለዕውቀት ያህል ያግዘናል ፡፡

   በተረፈ "የእግዚአብሔር መንፈስ" የሚለውን ቃል በአንድ ቃል ከመተርጐም ይልቅ እንደ አገባቡ መረዳት ያስፈልጋል ፡፡
   (ባል ስለሞተባት ሴት ሲናገር) እንደ ምክሬ ግን እንዳለች ብትኖር ደስተኛ ናት፤ እኔም ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ያለ ይመስለኛል። 1 ቆሮ 7፡4ዐ
   የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። 2 ጢሞ 3፡16-17
   ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ። 1 ጴጥ 4፡14
   የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ። ኢዮ 33፡4
   …….

   Delete
  2. በሦስቱ ሕግጋት በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 205 ላይ ስለስግደት በጻፉበት ክፍል «… ይልቁንም መርጦ ከኃጢአት አንጽቶ በመንፈስ ቅዱስ ቀድሶ ሥጋዋን ነፍሷን ለተዋሀዳት ለእመቤታችን …» ብለው ነበር፡፡sle sigdet tamnalachu ende??????

   Delete
 14. ስለ መመካከር
  ይኸኛው ጽሁፍ ባለፈው ያልተካተተው ትኩረት ሁሉ በትምህርተ ሃይማኖት ላይ ብቻ ስለነበር በመዘንጋቱ ነው ፡፡ ጸጋ ታደለ ካስነበበን መግለጫው ውስጥ እንዲህ የሚል ቃል ይነበባል ፡- “መቼም በአለቃ አያሌው ታምሩ የሚመራ ሰው በሥጋውም በነፍሱም ገደል መግባቱ አይቀርም፡፡ እርሳቸው አስቀድሞ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት የሚለውንና የጥንት አባቶችና የቅርቦቹም እነ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ፣ እነ ሊቀ ሊቃውንተ መሃሪ ትርፌና ሌሎችም ዓይናማ ሊቃውንት የሚያምኑትን ትምህርት ነበር የሚቀበሉት፡፡ ….”


  ጸጋ ታደለ በዚህ ገለጻው ላይ የአለቃ አያሌው ታምሩን ዓይነ ሥውርነት (አካለ ስንኩልነት) መከራከሪያ ወይም ማሳፈሪያ እንዲሆነው በማሰብ ሊሆን ይችላል ፣ “መቸም በእሳቸው የሚመራ ሰው በሥጋውም ገደል መግባቱ አይቀርም” በማለት ይገልጻል ፡፡ ይኸ አባባሉ ስለ ሃይማኖት ትምህርታቸው ብቻ አለመሆኑን የሚያስረዳው ፣ የእምነት ማጉደል ቅጣትን ወይም የበደል ፍርድን የምንጠብቀው ከሞትን በኋላ በነፍስ ብቻ መሆኑን ስለሚገነዘበው “በነፍሱም” ብሎ አክሎታል ፡፡ አሁንም ይኸንኑ ስውር ትርጉም ይበልጥ እንዲገልጽለት የተጠቀመው ሌላው ቃል ደግሞ፣ ሌሎች የእሱን ሃሳብ ዓይነት የሚጋሩትን ትጉሃን አባቶች “ዓይናማ ሊቃውንት” በማለት ማሞካሸቱ ነው ፡፡ ወንጌል አዋቂ ከሆነ ሰው ፣ ማቴዎስ 5፡22 የሠፈረውን ቃልም ያነበበና የተረዳ ምሁር ፣ ይኸን የመሰለ አገላለጽ መጠቀሙ ትክክል ስላልሆነ ይህችን ጠቋሚ መልዕክት አብሮ ቢያነባትና ለወደፊቱ ሃሳቡን ሲገልጽ ቢታረም በማለት ጽፌአታለሁ ፡፡ እኛ ብንወቃቀስ ምንም አይከብደኝም ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር እጅ በወደቀ ሰው ፣ በድክመቱ መናገር ኃጢአትም ስለሚሆን ነው ፡፡

  ReplyDelete
 15. ድኀነት ባይገኝበትም ፣ ለዕውቀት ያህል ያግዘናል ፡፡በመንፈስ ቅዱስ ተቀባ የሚለዉን ኢሳይያስ ፮፩፡፩ን አባ ጊዬርጊስ ሲተረጉም በማቴ ፫፡፩፮፡፩፯ ለተገለጸው በጥምቀት ክርስቶስ ጊዜ ለወረደዉ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ተናግሯል ይህም ለአገልግሎት ነዉ ሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ፡፡ ፨ወንጌል ትርጉሙ መልካም ዜና ፣ የምሥራች ማለት ነው፨ ወንጌልን ማለትም የድኀነት መንገድ መገኘቱን ለማስተማር እንደሚመጣ ሲናገር ነው ብሏል አገልግሎት የጀመረዉ ከተጠመቀ በኋላ ነዉና but.......

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምንድር ነው እንደ ፊልም ጉዞ ላይ ማንጠልጠል ፡፡ ወንድሜ ምናለ የተረዳኸውን አጠቃለህ ብታስረዳን ፡፡ ጀምረህ ሳትቋጨው ተውክብን ፡፡ ለማንኛውም እግዜር ይስጥህ ፡፡

   Delete
 16. ነገር ግን ክርስቶስ(የተቀባ) የሚለዉ ስሙ የተዋሕዶ ስሙ እንደ ሆነ ይሕም ማለት መለኮት ሥጋን ተቀባ(ተዋሐደ)ማለት እንደሆነ ተናግሯል ማለትም ሥጋ መለኮትን በመቀባቱ ....

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምንድር ነው እንደ ፊልም ጉዞ ላይ ማንጠልጠል ፡፡ ወንድሜ ምናለ የተረዳኸውን አጠቃለህ ብታስረዳን ፡፡ ጀምረህ ሳትቋጨው ተውክብን ፡፡ ለማንኛውም እግዜር ይስጥህ ፡፡

   Delete
  2. betam ygermal gn tekatel egn enakebratalen!!!

   Delete
 17. ስለክርስቶስ መቀባትን የሚመለከቱ ጥቅሶች የሚከተሉት ናቸው፤
  ሉቃ. 2፥26 በጌታም የተቀባውን ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ
  ነበር።
  ሉቃ. 4፥17-20 የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ
  ጊዜ። የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤
  ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ
  ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን
  ስፍራ አገኘ። መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም
  የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር።
  ሉቃ. 9፥20 እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦
  ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ አለ።
  ሐዋ. 4፥26-27 የምድር ነገሥታት ተነሡ አለቆችም በጌታና በተቀባው ላይ አብረው
  ተከማቹ ብለህ የተናገርህ አምላክ ነህ። በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ
  ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ
  እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።
  ሐዋ. 10፥38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥
  እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥
  እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤
  ዕብ. 1፥9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ
  ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ ይላል።
  ከእነዚህ ክርስቶስን የሚመለከቱ ጥቅሶች ናቸው። ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስ
  ብለን ነው የምንጠራው። ኢየሱስ የዕብራይስጥ ስሙ ሆኖ አዳኝ ማለት
  ሲሆን ክርስቶስ የግሪክ ቃል ሆኖ ከላይ የተመለከትነው መሢሕ ማለት
  ነው። ቅቡዕ ወይም የተቀባ ማለት ነው። ጌታን ስሙን በአማርኛ
  ተርጉመን የምንጠራው ቢሆን ኖሮ “የተቀባው አዳኝ”Ύ ብለን ነበር
  የምንጠራው። በብሉይ ኪዳን መቀባት መሾምን፥ ሥልጣንን፥ ማዕረግን፥
  አብሮት የተያያዘውንም ክብር የጨበጠ ነው። የጌታ ቅቡዕነት የተለየ
  ነው። ቅባት ያካተተውን ክብርና ምማዕረግ ሁሉም የያዘ ነው። በአይሁድ
  ይጠበቅ የነበረው መሢሕ፥ ሰው የሆነ አምላክ፥ ሥጋ የሆነ ቃል፥
  ለዘላለም የሚኖር ሊቀ ካህናት፥ ቃልን የገለጠ ነቢዩ ኢየሱስ
  እርሱ ሰማያዊው ሹም ነው።ahun tshufu yene bayhonem selasnebebkoachehu እንደ ፊልም ጉዞ ላይ ማንጠሌን yiker belugh

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጌታ ይባርክህ !!! እግዜር ሁላችንንም ይቅር ይበለን ፡፡ ትንሽም ይሁን ብዙ ፣ የምናውቀውን ማካፈል ሃይማኖታችንን በሥርዓቱ ለመረዳት ያግዘናል ፡፡ በተዘዋዋሪ ካየነው ደግሞ በአዳዲስ ቃልና ወፍ ዘራሽ ትርጉም እንዳንናወጥ ፣ ስንጠየቅም መልስ ለመመለስና ለማስረዳት ያግዘናል ፡፡ ዕውቀት መቀባበሉ መልካም ነውና ቀጥሉበት

   Delete
  2. ke mekrez .org yewetsedkut new

   Delete
  3. yiker belugh...ማለትም ሥጋ መለኮትን በመቀባቱ ....yihchn bemecheresha yamatahoat latefahut tfat kitat kenona sefi mabrarya lemtsaf sel new.. bemetshaf kal legemer የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረየሐዋርያት ሥራ 2 ,24እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፤

   31 ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ፥ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገውየሐዋርያት ሥራ5,31

   Delete
 18. bedegami yikrta liteyek kelaym yikerta teyekealehu tshufoch yemikoraretut yegele computer sayhon yehizb computer selemtekem new yehizeb computer degmo besat bewerfa yemisera silhone leweta sil bechikola yetsafkuachew silhone new ....መቀባትን አባ ጊዬርጊስ ሲተረጉም በሁለት መልኩ ነዉ ይህዉም ፩ ከስጋና መለኮት መዋሐድ ጋር አያይዞ ነው ፩መለኮት በስጋ ተቀባ ስለዚህም ሰዉነትን እና ለሰዉ ልጆች በፀጋዉ ያድላቸዉ የነበሩትን ፫ቱን ግብራት ማለትም ካህንነትን ነቢይነትን እና መሲሓዊን ሰለሞናዊ ዙፉንና ንግስና ከስጋ ወደራሱ ገንዘቡ አደረጋቸዉ(አምላካዊ ዙፉን የወደፊቱን ማወቅና ይቅር ማለትና መማር ግን የባህሪ ገንዘቦቹ ናቸዉ) እነዚህ ፫ቱን ግብራት ግን ክርስቶስ ለሰዎች የሚሰጣቸዉ እንጂ ቅድመ ተዋሕዶ በባህሪዉ የሚሰራባቸዉ አይደሉም ስለሆነም እርሱም ካህን ነቢይና ንጉስ ለመሆን የግድ በስጋ መቀባት ነበረበት ስጋም ደግሞ መለኮትን ተቀባ ተዋሐደ ስለሆነም ስጋ መለኮትን በመቀባቱ ደግሞ እነዚህ ፫ቱን ግብራት ከአርያም እዝነ አብ (የአብ ጀሮ) ገጸ አብ (የአብ ፊት)ለመድረስ ኃይል አገኙ ...

  ReplyDelete
 19. yiker belugh...ለዚህ ትርጉም የትኛዉ መጽሓፉዊ ቃል ይደግፈዋል ብትሉኝ እንደእኔ ሉቃ። ፱፥፳ እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ፧ አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ፦ከእግዚአብሔር የተቀባህ ነህ አለ።የሚለዉ ነዉ ምክንያቱም ይህ መልስ ከክርስቶስ ማንነት ጋር ተያይዞ መነገሩ ብቻ ሳይሆን ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ። አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ የማቴዎስ ወንጌል ፲፮፣፲፮ ከሚለዉ መልስ ጋር ተያይዞ መነገሩም ጭምር እንጂ ይሁንና አባ ጊዬርጊስ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው የሚለዉን ሲተረጉም በጥምቀት ክርስቶስ ጊዜ ለወረደዉ መንፈስ ቅዱስ መሆኑንም ተናግሯል ( beknef yalew tshuf mekrez .org kemil website yetegegh new.. በመጀመሪያ ቃሉና አሳቡ በብሉይ ኪዳን እንዴት እንደተገለጠ እንይ። በብሉይኪዳንግዑዛንቁሳቁሶችም ይቀቡ ነበር። የተቀቡት ነገሮች ግዑዛን ቁሳቁስ ከሆኑ የተቀቡት ነገር ዘይት ወይም ቅባት፥ ደም ወይም ቀለም ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ፥ ጋሻ፥ መሠዊያ፥ ቤት፥ ሐውልት፥ የመስዋዕት ቂጣ፥ እንዲሁም በማደሪያው ድንኳን ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች ከተቀቡ ነገሮች መካከል ይገኛሉ።የመገናኛውን ድንኳን ንዋየ ቅድሳት በተመለከተ ይህ ቅባት ወይም መቀባት የሚያመለክተው እነዚህ ነገሮች የተለዩ፥ የተቀደሱ ለእግዚአብሔር የተሰጡ መሆናቸውን ነው። ግዑዛን ከሆኑት ነገሮች ሌላ የተወለደ ሕጻን፥ የታመመ ሰው፥ እንዲሁም የሞተ በድን እንደተቀቡ ወይም እንደሚቀቡ ተጽፎአል።)ስለዚህ በዚህ ትርጉም መሰረት ለአገልግሎት ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርጧል ተቀብቷል ተመስክሮለታል ( beknef yalew tshuf mekrez .org kemil website yetegegh new.. ቅባትና ሰዎች አብረው የተጠቀሱት ከሹመትና ሥልጣን ጋር ሆኖ ይገኛል። በዚህ ሁኔታ በብሉይ ኪዳን በብዙ ቦታዎች ‘የተቀቡ’ተብለው ሲጠሩ ወይም ሲቀቡ የምናያቸው ነገሥት ናቸው፤ 1ሳሙ. 2፥4፤ 10፥1፤ 12፥3-5፤ 16፥13፤ 24፥6-10፤ 26፥9-23፤ 2ሳሙ. 1፥14-16፤ 19፥21፤ 1ነገ. 1፥39፤ 19፥15-16፤ 2ነገ. 11፥12፤ 23፥30፤ 2ዜና 29፥22 ወዘተ። ንጉሥ ከተቀባ በኋላ ‘በእግዚአብሔር የተቀባ’ተብሎም ይጠራል። ሹመቱ ከላይ ከእግዚአብሐር ዘንድ የመነጨ የመሆኑምልክትነው። ምንም ሥልጣን ከላይ ካልተሰጠ በቀር እንዲያው የሚቀዳጁት አይደለምና ይህ ቅባት
  የዚህ አመልካች ነው። የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናትና ካህናት ሲካኑ ይቀቡ ነበር፤ ዘጸ. 29፥7፤ 30፥22-33፤ 40፥15፤ ዘሌ. 8፥12፤ 16፥32፤ 21፥10-12፤ ወዘተ። ነቢይ
  ሲቀባ ግን ከአንድ ጊዜ በቀር አናይም፤ ያም ነቢዩ ኤልሳዕ የተቀባበት
  ነው፤ 1ነገ. 19፥16።) .....

  ReplyDelete
 20. yiker belugh...አባ ጊዬርጊስ ከዚህ በተጨማሪ ክርስቲያኖች ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ(በሜሮን) የተቀባን መሆናችንን ተናግሯል እንዲያዉም ክርስቲያኖች ሁሉ በናዝራዊዉ ኢየሱስ ናዝራዉያን እንደምንባል በዚሁ መፅሐፈ ሚስጥር ላይ ፅፏል ስለዚህ ናዝራዉያን ካልሆን በመንፈስ ቅዱስ ያልተቀባን ከሆን ቀድሞም ክርስቲያኖች አልነበርንም።( beknf yalew tsehuf ke mekerez.org yetewsede new ብሉይ ኪዳን በተጻፈበት የዕብራይስጥ ቋንቋ ቅባትና ዘይትን ለግል ጉዳይ መቀባትና መለኮታዊ ለሆነጉዳይ መቀባት በተለያዩ ቃላት ተገልጠዋል። ለግል፥ ማለትም፥ ለመውዛት፥ ለጌጥ፥ ወዘተ፥ መቀባት ሱቅ (סוּך) ሲሰኝ ለእግዚአብሔር መቀባት ደግሞ ማሻኽ (משׁח) ይባላል። በዚህ ቋንቋ መሺያኽ የሚባለው መሢሕ የሚለውስያሜየመጣውከዚህነው።እንግዲህ እነዚህ የብሉይ ኪዳን ቅባቶችና የተቀቡ ሰዎች ወደ አዲስ ኪዳን የሚጠቁሙ አመልካቾች ናቸው። ያም አንድ ቀን ነቢይም፥ ሊቀ ካህናትም፥ የነገሥታት ንጉሥም የሆነው
  መሢሕ ክርስቶስ እንደሚመጣ የሚያመለክት የናፍቆት ገላጭ ነው።)

  ReplyDelete
 21. ሁላችንንም እግዜር ይቅር ይበለን ፡፡ እግዚአብሔር የበለጠውን ዕውቀትም ያድልህ !! ድንቅ የሆነውን ፣ የተሟላ ትምህርት አስነበብከን ፡፡ ይኸ ነበር እስከ አሁን ሲፈለግ የነበረ ፡፡
  ቅሬታዬን መግለጼ ፣ ተጐርዶ የቀረ እንዳለ በመገመት ነው እንጅ አንተን ለመኮነን ወይም በተንኰል አድርገኸዋል በማለት አይደለም ፡፡ የጠቆምከን ችግር ደግሞ ሁላችንም ያለንበት ወይም ያለፍነበት ስለሆነ እንገነዘበዋለን ፡፡ ክርስትና በመከራ ውስጥም ማስተማርን ይጋብዛልና ተስፋ አትቁረጥ ፡፡
  የምታውቁትን በየአጋጣሚው ሁሉ ማካፈልን አትዘንጉ ፤ ቢያንስ የሚተላለፈውን ትምህርት ያላገኙ ወይም የማያውቁ ከእኔ ጀምሮ አያሌ ወገኖቻችን ይኖራሉና ጥቅሙ ቀላል አይሆንም ፡፡ እምነት በዕውቀት ሲታገዝ ጽናቱ ይበልጥ ይጐለብታል ፡፡ እንዲህ በጥበብም ከተሞላን እንኳንስ በቃላት ውበት ፣ በኃይልም ቢሉን መሸርሸር አይገኝብንም ፡፡

  ReplyDelete
 22. Royal Priesthood of Israel and the Aarnoic institutional priesthood have become one in Jesus Christ the Eternal High Priest. The people of the New Covenant constituted in Him possess His Royal Priesthood, and are called after the Old Testament fashion, “an elect race, a royal priesthood, a holy nation, a people for God’s own possession” (I Pet. 2:9). All those who are properly baptized within the Church are members of this priestly community.After the pattern of Jesus’ baptism and anointing with the Spirit the Church has the washing of regeneration, baptism, and the granting of the Spirit, Chrismation, (cf. Tit. 3:5). Following the ancient custom of the Church, the two are administered together in the Ethiopian Church. fromhttp://www.ethiopianorthodox.org/english/ethiopian/hierarchy.html

  ReplyDelete
 23. Let me tell u, It is really very simple ur next question is who is God? You r possed by spiritual demon.

  ReplyDelete