Thursday, April 25, 2013

ክርስቶስ ሰምራ ዘብሔረ ቡልጋ በቀን ሦስት ሺህ ነፍሳት ከሲኦል ታወጣለች

«ወወሐባ ኪዳነ ከመ ታውጽእ ነፍሳተ እምሲኦል ሠለስተ እልፈ ነፍሳተ በበዕለቱ» ትርጉም "ጌታም በየቀኑ ከሲኦል ሦስት ሺህ ነፍሳትን እንድታወጣ ሥልጣን ሰጣት ወይም ቃል ኪዳን ሰጣት» ገድለ ክርስቶስ ሠምራ ዘጥቅምት ቁ 61.
ክርስቶስ ሠምራ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የታወቀች ቅድስት ሴት ናት። በየዓመቱ ግንቦት 12 መታሰቢያዋ ይከበራል። በዚህ ቀን በርካታ ምዕመናን እርሷን ከሲኦል እንድታወጣው ለመማጸን ወደ ቤተ መቅደሷ በመሄድ ሲሰግድ ይውላል። ንፍሮ በመቀቀል፣ ዳቦ በመጋገር፣ ጠላ በመጥመቅና ገድሏን በማንበብ ልመናና ጸሎት ያቀርብላታል። እርሷ የኖረችበት ነው በተባለው በጣና አካባቢ በሚገኘው ገዳሟ የሚሰበሰበው ሕዝብ ብዙ ነው። በዚያ ሰንጣቃ አለት የሚገኝ ሲሆን አንድ ሰው መጽደቅ እና አለመጽደቁን ለማወቅ በሰንጣቃው አለት በማለፍ እራሱን ይፈትናል። በዓለቱ ሾልኮ ካለፈ ጸድቋል ይባላል ካላለፈ ግን ተኮንኗል ይባላል። በብልሃት እንደምንም ያለፈ ሰው ጸድቄያለሁ ብሎ እራሱን አዘናግቶ ይኖራል።
ይህን ሁሉ በማደረግ የሚደክመው ሕዝብ ግን እውነተኛውን የነፍስ እረፍት ባለማግኘቱ በሌሎች ገዳማትም እየተንከራተተ አድርግ የተባለውን ሁሉ ያደርጋል። በግሸን ተራራውን ወዙ ጠብ ጠብ እያለ የወጣ ሰው ኃጢአቱ ተሠርዮለታል ይባላል። በዚህ የሰይጣን ትምህርት ምክንያት በባዶ እግሩ የሚኳትነው ሰው ብዙ እንደሆነ በሥፍራው ተገኝቼ ታዝቤያለሁ። ወደ ላሊበላ በባዶ እግር የሄደ ይጸድቃል ስለሚባል ያለጫማ እየደሙ ሄደው የተመለሱ ስዎች አሉ። ብቻ በኢትዮጵያ የጽድቅ መንገዶች ስፍር ቁጥር የላቸውም። የእግዚአብሔር ቃል «ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሏቸዋል በክርስቶስ ኢየሱስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ» የሚለውን መለኮታዊ ቃል ኪዳን በመሸፈን፤ በሰንጣቃ አለት፤ ተራራ በባዶ እግርህ በመውጣት፤ ንፍሮ በመቀቀልና ዳቦ በመጋገር ትጸድቃለህ ተብሎ ሲሰበክ የኖረው ወገናችን እንዲህ ሲንከራተት ስመለከት እጅግ ያሳዝነኛል። የክርስቶስን የመስቀል ሥራ በሰው ጥረት ለመተካት፤ የክርስቶስን ጽድቅ በሰው ጽድቅ ለመሸፈን የተጠነሰሰ የዲያብሎስ ወጥመድ ነው እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? የእርሱ ወዝ መንጠፍጠፍ መድማት መከራ መቀበል፤ እኛን ከእንዲህ ዓይነቱ ሥቃይ ለማዳን ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ንሥሐ የገባ ሁሉ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ እንደሚቆጠርለት መጽሐፍ ቅዱስ እየተናገረ (ሮሜ 4፥23) ወገኖቻችን ይህ የሥላሴ እውነት ባንድም በሌላም ነገር ተጋርዶባቸው በየተራራው ሲንከራተቱ እናያለን። አንዳዶች ይህን ለምን እንደሚያደርጉ ስንጠይቃቸው «በብዙ መከራ ወደ መንግሥተ ስማያት ልንገባ ይገባናል» የሚለውን የሐዋርያውን ቃል ይጠቅሳሉ። ይህ ቃል ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መከራ ስለመቀበል ከዓለም በሚደርስብን ጥላቻ ሳንሰቀቅ ጸንተን ተስፋችንን እንድንወርስ የሚያስረዳ እንጂ በባዶ እግር ተራራ ስለመውጣት፤ በሰንጣቃ አለት ስለማለፍ ወይም ደረትን በድንጋይ ስለመድቃት፤ እራስን ከሰው አግሎ ታፍኖ ስለመኖር የሚያስተምር አይደለም። ጌታ ወደ ዓለም ሂዱና ተናገሩ ነበር ያለው። ከዓለም ተደብቆ ዘግቶ ስለመኖር ያስተማረ ሐዋርያም ሆነ ነቢይ አናገኝም። በገዳም ተወስኖ መጸለይን የምንወደው ቢሆንም እንኳ ከሰው ተገልሎ በአፉ ድንጋይ ከቶ ሳይናገር ከሰው ሳይገናኝ ኖረ የሚለው ግን ከሃይማኖት የወጣ ነው፤ በገዳም የሚጸልዩትም እየወጡ እንዲያስተምሩ ሕዝብን እንዲመክሩ ያስፈልጋል።  
ወደ ክርስቶስ ሠምራ ቃል ኪዳን ልመልሳችሁና ክርስቶስ ሰምራ ማናት የሚለውን ላስቀድም። ክርስቶስ ሠምራ በሽዋ ክፍለ ሀገር በቡልጋ አውራጃ ጌየ በተባለች አገር ተወለደች። አባቷ በጊዜው ሀብታምና የተከበሩ ሰው ነበሩ፤ በአጼ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት በውበቷ የተደቀጆ ሴት ስለነበረች 174 ባሪያዎችን ከነጉሡ ተሸልማለች። በዚያን ጊዜ ሽልማቱ ባሪያ ነበር። ገድለ ክርስቶስ ሰምራ ዘመስከረም ቁ 17። ክርስቶስ ሰምራ ባለትዳርና የ 11 ልጆች እናት ነበረች፤ ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ባሪያዋ አበሳጨቻትና በእሳት ትንታግ ጉሮሮዋን ጠብሳ ገደለቻት። በዚህ ኃጢአቷ ተጸጽታ በጌታ ፊት ጸልያ ባሪያዋን ከሞት አስነስታታለች። ከዚያ በኋላ ግን ትዳሯን እና ልጆቿን ትታ ደብረ ሊባኖስ ገብታ መነኮሰች። ምንኩስናን በደረ ሊባኖስ ከተቀበለች በኋላ ወደ ጣና ሄዳ በጣና ባሕር ውስጥ ለ12 ዓመት ያህል ሳትነቃነቅ ጸልያለች። በዚህ ጊዜ ሰውነቷ አልቆ አጥንት ብቻ ቀርቷት ነበር። አሳዎችም ባጥንቶቿ ውስጥ መመላሻ መንግድ ጎጆና መዝናኛ ሠርተው ነበር።
ክርስቶስ ሰምራ በዲያብሎስና በክርስቶስ መካከል ያለውን ጠላትነት ዘንግታ ዲያብሎስን ለማስታረቅ ወደ ሲኦል ወርዳ ከዲያብሎስ ጋር ተነጋግራለች የተባለላት ሴት ናት። ዲያሎስ ግን በዚያው በሲኦል ሊያስቀራት ሲሞክር በሚካኤል ኃይል ከብዙ ነፍሳት ጋር ለጥቂት ያመለጠች ናት ተብሏል።
«ወ እምዝ ቦአት ውስተ ባሕረ ፃና ወቆመት ከመ አምድ ትኩል አሠርተ ወክልዔተ ዓመተ እንዘ ኢትወጽእ እስከ ያንሶሱ ማዕከል ሥጋሃ አሣ ባሕር» ትርጉም «ከዚያም ሰውነቷ ተበሳስቶ የባሕር አሣ መመላለሻ እስከሚሆን ድረስ እንደተተከለ ዓምድ ሆና ሳትወጣ ባባሕሩ ውስጥ አሥራ ሁለት ዓመት ስትጸልይ ኖረች» ገ/ክ/ ሰምራ ዘጥቅምት ቁ 4።
በዚህ ምክንያት ጌታ ተገልጦ በቀን በቀን ሦስት ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንድታወጣ ሥልጣን ሰጥቷታል። ይህ ማለት ከተነሳች እስከ አሁን (በ ስድስት መቶ ዓመት ውስጥ) ወደ ቢሊዮን የሚጠጉ ነፍሳትን ከሲኦል አውጥታለች ማለት ነው።  በቀን ሦስት ሺህ ነፍሳት ከማውጣቷ በተጨማሪ የአራት ወር ያህል በየቀኑ በዓለም ላይ የዘነበውን የዝናብ ጠብታ ያህል ነፍሳትን እንድታወጣ ቃል ኪዳን ተሰጥቷታል። ስለዚህ ሲኦል በክርስቶስ ሰምራ አማካኝነት ባዶ ሆናለች ማለት ይቻላል።
«ወሶቤሃ አውስአ  ወይቤላ ንስኢ ወሐብኩኪ ዓስራተ ብዙኃ ነፍሳተ መጠነ ነጠብጣብ ዝናም ዘ፬ቱ አውራኅ ለእለ አሐዱ ዕለት» ትርጉም «ጌታም ተናገራት እንዲህ አላት በአራት ወር ውስጥ በየቀኑ የሚወርደውን የዝናም ነጠብጣብ ያህል ነፍሳትን አሥራት ሰጥቸሻለሁ» ማለት ነው። የአራት ወር ያህል ዝናብ የሚያህሉ ነፍሳት ገና የተፈጠሩ አይመስለኝም። እነዚህ ሁሉ ከሲኦል ከወጡ የተኮነኑ ነፍሳት የሉም ለማለት ያስደፍራል።
 ታሪኩ በጌታ እና በሐዋርያቱ ቃል ሲመዘን፦
ለውሸታቸው ልክና መጠን የሌለው ያገሬ ደብተራዎች ይህን ያህል ለምን እንደሚጨነቁ ግልጥ አይደለም። ያነበብኋቸው ገድል ተብየዎች በሙሉ በሚያስቅ ተረት የተሞሉ ናቸው። በጣም የሚቆጨኝ ግን የዋሃን ምዕመናን ተረቶችንና ልብ ወለዶችን ሃይማኖት አድርገው መያዛቸው ነው። ከዚያም አልፈው በተረት የተሞላችውን ቤተ ክርስቲያን እንከን የለሽ አድርገው ስንዱ እመቤት እያሉ ሲመኩ እሰማለሁ። «የሚሉሽን ባልሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ» እንደተባለው አሁን የሚኮራበትን ሃይማኖት በጌታ ቃል ብንፈትሸው እሳት ፊት የወደቀ ገለባ ሆኖ ይገኛል።
የእግዚአብሔር ቃል «ኃጥአን ወደ ዘለዓለም ቅጣት ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ» ይላል ማቴ 25፥46። ይህ ቃል ክብር ምስጋና ይግባውና ከሰማይ ወርዶ እውነቱን የገለጠልን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ነው። ጌታ «እኔ መጥቼ ባልነገርኋችሁስ ኃጢአት ባልሆነባችሁም ነበር» ብሏል ዮሐ 15፥22። በእውነቱ በማያልፈው ቃሉ እውነቱን ነግሮናል፤ «የማይጠቅመውን ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት በዚያ ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል» ብሏል ማቴ 25፥30። ሰዎች ሲኦል ከገቡ በኋላ ተመልሰው በክርስቶስ ሰምራ አማካኝነት እንደሚወጡ ጌታም ሆነ ሐዋርያቱ አላስተማሩም፤ ሰው ሁሉ ንስሐ እንዲገባና በክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል ከሚመጣው ዘለዓለማዊ ፍርድ እንዲድን ነው ያስጠነቀቁት።
ነቢያት አልቦ ዘያድህን ወዘይባል፤ የሚያድንም ሆነ የሚታደግ የለም ብለዋል። ሰው ሁሉ ከሚመጣው የእግዚአብሔር ቁጣ ይድን ዘንድ አንድያ ልጁን ሰጥቷል። በእርሱ በኩል ንስሐ ገብተው የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። «በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም በ እርሱ በማያምን ግን  በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል» ይላል ዮሐ 3፥18። እውነቱ ይኸው በወንጌል የምናነበው ነው፤ የሐዋርያት እምነት የሚባለውም ይኸው ነው። በዚህ ትምህርት ጸንታ የምትኖር ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ትባላለች።
የቤተ ክርስቲያናችን ደብተራዎች ግን ሕዝባችንን የስሕተት ትምህርት አስተምረው ለእግዚአብሔር ቁጣ አዘጋጅተውታል። እግዚአብሔር በዘለዓለም መስዋእት ያቆመውን የጽድቅ መንገድ በማሳት ተራራውን ብትሳለም እንደ አርባ ቀን ሕጻን ኃጢአት ይሰረይልሃል፤ ክርስቶስ ሰምራን ስሟን ብትጠራ ከሲኦል ታወጣሃለች፤ ደብረ ሊባኖስ ብትቀበር እስከ ሰባት ትውልድ ትድናለህ ብለው እየሰበኩ ከእውነት አወጡት። ዛሬም የጥንት ደብተራዎችን ውሸት የአባቶቻችን እምነት እያሉ የሚመጻደቁ ሰዎች በማህበር ተደራጅተው የመዳን መንገድ እንዳይገለጥ እየተዋጉ ነው። እያወገዙ እያስወገዙም አሉ። እግዚአብሔር እንደ ሥራቸው የሚከፍላቸው መሆኑን ብናውቅም ሕዝባችን ከስኅተት መንገድ የሚመለስበትን ሁኔታ ከመፍጠር ሊያስቆሙን አይችሉም።
ሕዝቤ ሆይ ወደ እውነቱ ተመለስ
ተስፋ ነኝ

98 comments:

 1. Thank you, Tesfa. we should better to blame the holly Synods. I do not think most of the head of Orthodox church know Jesus. The solution probably come from Aba Paulos, I do not know when? Keep your contribution. I knew this tert tert when I was kid, I did not give any attention. The road to heaven is only through the Lord Jesus.

  T.G from Dallas

  ReplyDelete
  Replies
  1. ትዕግሥት ስለ ጌታ እልሻለሁ እስቲ የምታውቂውን ምሥጢር ትንሽ አብራርተሽ ጻፊው ፡፡ አባ ጳውሎስ ገዳም የሚያዘጋ አዋጅ አውጭ ናቸው ወይስ ሌላ የማናውቀው የሚጠበቅ ሥራ አላቸው ? መቸም ዘንድሮ ሴቶች የማትደርሱበት ቦታ ያለ አይመስልምና አባባልሽን ግልጽ አድርጊው ፡፡ ከዚህ አንቺ ከምትይው በመነሳት የምተረጉም ቢሆን አባታችንን የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ወይም ድብቅ የቤት ሥራ ያላቸው አስመስለሻቸዋል ፡፡ ምክንያቱም ገዳምንና የገዳም ህይወትን የሚያወግዙና የሚጠሉ እነማን እንደሆኑ ክርስቲያን ነኝ የሚል በሙሉ ስለሚያውቀው ማለቴ ነው ፡፡ የጽሁፉም መልዕክትና አጀንዳ ይኸንኑ ነው የሚተርከውና ፡፡

   Delete
  2. This comment has been removed by a blog administrator.

   Delete
  3. ስለ መልስሽ ቃለ ህይወት ያሰማልኝ ፡፡
   ካልኖሩበት መጽሐፍን ማወቅ ፣ ካለማወቅ በምንም አይለይም

   Delete
  4. Yene Paster Tolosa Betesewoch Gedamat Bsadebu Kidusan Bneqfu Aydenqenim Yaw Yegbr Abatachew Sira New Ena Yemserut. Paster Tolesa Be Egrachew Yale chama Lemin Yhedalu Eyale Sichoh neber Yaw Ahunim Temesasay neger new Yemyasaznew Gin Beaba Selam Sim Meshe fenachu new

   Delete
  5. ኪዳን የሚለው ቃል ‹‹ቃል›› ከሚለው ጋር እየተዛረፈ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲሰ ኪዳን ደግሞ ከ32 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ ‹‹ኪዳን›› ቃሉ ‹‹ተካየደ›› ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ምሕረት›› የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡

   ‹‹ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አድርጋለሁ›› ተብሎ በዳዊት መዝሙር እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደፊትም ያደርጋል፡፡ (መዝ88.3) ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡

   በቅዱሳን አበውና በቅዱሳት እማት እናቶች ታሪክ፣ ገድልና ድርሳን እንደምናነበው እግዚአብሔር ለቅዱሳን ከመሞታቸው አስቀድሞ ይገለጥላቸውና የምሕረት ቃል ኪዳን ይሰጣቸው ነበር፡፡ የእግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን በቅዱሳኑ ሕይወት ዙሪያ ብቻ የሚያተኩር አይደለም፡፡ ለስማቸው፣ ለመስቀላቸው፣ ለልብሳቸው ገድላቸውን ከትቦ ለያዘ መጽሐፍ፣ አልፎ ተርፎም ለረገጡትና አፈርና ለተጋደሉበት ቦታ ሁሉ ተርፎላቸዋል፡፡ ስለዚህ ልዩ ልዩ ቃል ኪዳን የተገባላቸው ቅዱሳት መካናት ሞልተዉናል፡፡

   ለቅዱሳን ከሞት አስቀድሞ የእግዚአብሔር መገለጥ ወይም የሚሞቱበትን ጊዜና የአሟሟታቸውን መንገድ ገልጦ መንገር በቅዱሳት መጻሕፍት የተለመደ ነው እንጂ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት ባለ አሟሟት እንደሚሞት ነግሮታል፡፡ (ዮሐ21.19 2ጴጥ1.14) ቅዱስ ጳውሎም ስለሚሞትበት ጊዜ ተነግሮታል፡፡ (የሐዋ20.25 የሐዋ21.10-13) ‹‹ከሞቱ አስቀድሜ እገለጥለታለሁ›› እንዲል፡፡ (ሰኔ ጎልጎታ)

   እግዚአብሔር ከሞታቸው አስቀድሞ በመገለጥ ለቅዱሳን የምሕረት ቃል ኪዳን የሚሰጣቸው በእነርሱ በጎ ሥራ ከእነርሱ በኋላ ያሉ የሰው ልጆችን ለመጥቀም ፈልጎ ነው፡፡ ተጠቃሚዎቹ ራሳቸው ናቸው እንዳይባል ወደ ሞት አፋፍ የተጠጉ ከመሆናቸውም ባሻገር ለቃል ኪዳን የበቁት የሚጠቀሙበት በጎ ሥራ በመሥራታቸው ነው፡፡ የሰው ልጆች ያለፉ ቅዱሳንን በመዘከር የቃል ኪዳናቸው ተጠቃሚ ሲሆኑ ቅዱሳኑ ግን ከመታሰብ በቀር በሰው በኩል የሚያገኙት ምንም ጥቅም የለም፡፡ ቅዱሳን የምሕረት ቃል ኪዳን ሲቀበሉ ለወገናቸው መትረፋቸውን ያመለክታሉ፡፡

   የምሕረት ቃል ኪዳን ለምን ያስፈልጋል ቢባል ሕግ መተላለፍ ካለ ሁልጊዜ ተጠያቂነት ወይም ቅጣት ይኖራል፡፡ ይህም በአዳም ይታወቃል፡፡ የሰው ልጆች ደግሞ ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርግ ፍጽምና ይዘው አይገኙም፡፡ በዚህ ምክንያት ቅጣት እንዳያገኛቸው የሚድኑበትን በርካታ መንገዶች እግዚአብሔር አዘጋጀ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡

   የምሕረት ቃል ኪዳን ሁሉ በጎ እንድንሠራ የሚያበረታታ ነው፡፡ ይህም ዘወትር ከቃል ኪዳኑ ጋር ተያይዘው በሚቀመጡ ግዴታዎች ይታወቃል፡፡ ለበጎ ሥራ ምክንያት የማይሆን ባዶ የምሕረት ቃል ኪዳን የለም፡፡ ‹‹ስምሽን (ስምህን) የጠራውን፣ ዝክር ያዘከረውን፣ የተራበ ያበላውን፣ የተጠማ ያጠጣውን፣ የታረዘ ያለበሰውን፣ እንግዳ በስምህ (በስምሽ) የተቀበለውን፣ ገድልህን ያነበበውን፣ የሰማውን፣ የተረጎመውን ወዘተ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ፣ እምረዋለሁ›› የሚሉ ቃል ኪዳናት በሙሉ ከባዱ መልካም ሥራ ባይቻለን እንኳን ቀላሉን መሥራት እንዳለብን ግዴታ የሚጥሉ ናቸው እንጂ አንዳንዶቸ እንደሚያስቡት መልካም እንዳንሠራ የሚያሳንፉ አይደሉም፡፡ ከዚህ ይልቅ ለበጎ ሥራ የሚያነሣሡና የታዘዙትን መሥራት ያልተቻላቸውን ሰዎች ተስፋ ሳይቆርጡ እስከመጨረሻው ሰዓት የሚድኑበት መንገድ እንዳለ አውቀው የተቻላቸውን እንዲያድርጉ የሚጠቁሙ ናቸው፡፡

   የእግዚአብሔር ቸርነት ከአእምሮ በላይ ነው፡፡ ይህም ሰዎች በእግዚብሔር ቸርነት ላይ በሚያነሡት ጥያቄ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ፡ እግዚአብሔር በዜና ገድላቸው እንደምናነበው ለብዙ ቅዱሳን ‹‹እስክ አሥር፣ ሠላሳ፣ ሃምሳ አምስት ወዘተ ትውልድ ድረሰ እምርልሃለሁ›› እያለ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን በማንበብ እምነት የጎደላቸው አንዳንዶች ‹‹ይህ እንዴት ይሆናል?›› እያሉ ይጠይቃሉ፡፡ ይህ ብቻ በራሱ የፈጣሪ ቸርነት ከሕሊና በላይ መሆኑን አያስረዳም?

   ፈጣሪ ስለ ፈራጅነቱና ስለ መሐሪነቱ ሲናገር ‹‹በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወዱኝ ትእዛዜን ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝ፡፡›› ይላል፡፡ (ዘጸ20.2-6) ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እስከ ሺህ ትውልድ የሚደርስ የእግዚአብሔርን ምሕረት በመናገሩ በአዋልድ መጻሕፍት ላይ ያለው የሠላሳና የሃምሳ ትውልድን ምሕረት የሚያወሳው ኃይለ ቃል ሊስተባበል አይቻልም፡፡ ያን ማክፋፋት ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደመቃወም ይቆጠራልና፡፡

   ዓለም ከተፈጠረች ሰባት ሺህ አምስት መቶ ዓመት ገደማ ሊሆናት ነው፡፡ የሰው ልጅን አማካይ እድሜ እጅግ አሳንሰን በመቁጠር የአንድ ትውልድ ዘመን ሠላሳ ዓመት ነው ብንል እንኳን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ያለው ትውልድ ከሁለት መቶ ሃምሳ አይበልጥም፡፡ በዚህ ዓይነት ደግሞ እስከ ዓለም ፍጻሜም ብንቆጥርና ብናሰላም የትውልድ ቁጥር እንኳን አንድ ሺህ ሊደርስ ወደ አምስት መቶም አይጠጋም፡፡ ነገር ግን ፈጣሪ የሚወደውና ትእዛዙን የሚጠብቅ እውነተኛ ሰው ከተገኘ ያን ያህል ትውልድ አይኖርም እንጂ ‹‹እስከ ሺህ ትውልድ›› ድረስ እንኳን ይቅር ሊል ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው የእግዚአብሔርን የቸርነት ስፋት ነው፡፡ ሺህ ትውልድ ስለሌለ እግዚአብሔር ሺህ ትውልድ ሊምር አይችልም አይባልም፡፡ ከዚህ አንጻር የፈጣሪን ቃል ኪዳን ከመሐሪነቱ አንጻር እንጂ ከተፈጻሚነቱ አንጻር ሊመለከቱት አይገባም፡፡

   ፈጣሪ ለቅዱሳኑ በየዕለቱ ብዙ ነፍሳትን ከሲዖል እንዲያወጡ የምሕረት ቃል ኪዳን ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ የተሰጣቸውም ቅዱሳን አሉ፡፡ ነገር ግን ተፈጻሚነቱን ስንመለከት በቀን የተባለውን ያህል ነፍሳት ከሲዖል ሊወጡ ወይም አንድም ነፍስ ከሲዖል ላትወጣ ትችላለች፡፡ ይህ ግን በተገባላቸው ቃል ኪዳን ላይ ምንም ዓይነት አሉታ የለውም፡፡ ምክንያቱም ለቅዱሳኑ ይህ ቃል ኪዳን ሲሰጥ ሲዖል ካለችው ነፍስ ደግሞ የሚጠበቅ ነገር ይኖራልና፡፡ ያን የምታሟላ ነፍስ ካልተገኘች ቃል ኪዳኑ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ ይህም በመሆኑ ቃል ኪዳኑ ከንቱ ነው አይባልም፡፡ ከላይ እንዳየነው ተፈጻሚ ሊሆን ባለመቻሉ ብቻ ለሺህ ትውልድ የተገባው ቃል ኪዳን ከንቱ ነው ሊባል አይቻልምና፡፡

   ‹‹ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ›› ባለው መሠረት ጌታ ከእመቤታችን ጋር ብዙ ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ እርሷ የተመረጠች ብቻ ሳትሆን ከተመረጡትም ሁሉ የተመረጠች ናትና፡፡ ከቅዱሳን ሁሉ እመቤታችን ድንግል ማርያም በሁሉም ረገድ እንደምትበልጥ ከተሰጣቸውም የምሕረት ቃል ኪዳን ለሷ የተሰጣት ኪዳን በእጅጉ ይበልጣል፡፡ በዚህም ምክንያት ድንግል ማርያም በተሰጣት ቃል ኪዳን ተለይታ ትታወቃለች፡፡ ማለትም ትጠራበታለች ኪዳነ ምሕረት ትባላለች፡፡ ስለዚህ የኃጥአን ሁሉ ዓይን የእርሷን የምሕረት ቃል ኪዳን ተስፋ ያደርጋል፡፡   ድንግል ማርያም በቃል ኪዳኗ አትለየን!


   አዘጋጅ ዲያቆን ኅብረት የሺጥላ
   hibretyes@yahoo.com

   Delete
  6. እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለ ህይወት ያሰማልን !!!

   Delete
  7. እውነት ነው :: ‹‹ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አድርጋለሁ›› ተብሎ በዳዊት መዝሙር እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደፊትም ያደርጋል፡፡ (መዝ88.3) ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡

   Delete
  8. እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለ ህይወት ያሰማልን !!!

   Delete
  9. ወንድማችን ኣንብበህ ብትጽፍ ኣይሻልም። ''ከመረጥኩት ጋር'' ነው የሚለው። መዝሙር 89፡3

   Delete
 2. I think some of your points are fair enough. so, I say for that - keale hiwot yasemalign. However, your opposition against the monks, who have run from this world and hid in the desert dedicating themselves to God, is not acceptable. I persoanlly love the true monks.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያገባም መልካም አደረገ፤ ያላገባም የተሻለ አደረገ እንዳለው ጳውሎስ በድንግልና መኖር የተቻለው የበለጠ ተግባር ነው። ያ ማለት ግን ወንጌል ከማስተማር፤ ቃሉን ከማካፈል፤ ወደንስሐና ወደሕይወት መንገድ ሕዝቡን ከመጥራት ርቆ፤ የሴትን ዓይን እንዳያይ ተሸሽጎ፤ አንዳንዴም ፈቲው ሲጸናበት በቢላዋ ብልቱን እየቆረጠ፤ በበረሃ ይኑር፤ አፉንም ከማስተማር ድንጋይ ይወትፍበት፤ መስቀል ይጉረስበት የሚል የወንጌል ቃል የለምና ስህተት ነው። ከመጀመሪያው ከሴት ለመታቀብ ችሎታና የጸጋ ስጦታ የለውም ማለት ነው። የሌለውን ነገር ለማግኘት መታገል እግዚአብሔርን ጨካኝና አካላችንን ለፈተና የፈጠረ አድርጎ ፈጣሪን መክሰስ ይሆናል።
   ጳውሎስ ያለጋብቻ በድንግልና የኖረው የጸጋ ስጦታ ስለነበረው ሲሆን ያንንም ስጦታውን ቤቴን፤ ትዳሬን ሳይል ወንጌልን ለዓለሙ ሁሉ እንዲያዳርስ አስችሎታል። ዛሬ መነኰሳት ገዳም በረሃ የሚሄዱት በክርስቶስ ስለጸደቁ፤ ሳይሆን ለመጽደቅ ነው። እንደዚያ ከሆነ የክርስቶስ ሞትና ትንሳዔ ዋጋ የለውም ማለት ነው።
   ውድ ካሳ በድንግልና በንጽህና መኖር «
   1 ቆሮ 7፤7
   ሰው ሁሉ እንደ እኔ ሊሆን እወዳለሁና፤ ነገር ግን እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ለራሱ የጸጋ ስጦታ አለው፥ አንዱ እንደዚህ ሁለተኛውም እንደዚያ።
   እንዳለው በጸጋው ስጦታ እንጂ ያለጸጋው ሴትና ወንድ እየፈለጉ በመሸሽ አይደለም። ለዚያውም ለጽድቅ ሳይሆን «1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፥11
   ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።
   የሚል ቃል ስላለ ሰው ክርስቲያናዊ ምግባር የሚያደርገው በክርስቶስ ደም ስለጸደቀ እንጂ ለመጽደቅ አይደለም።
   ይህን የእውነት ቃል ማጣመም ትክክል አይደለም።

   Delete
  2. የተሰጠ መልስ
   ጌታ ራሱ ስለ ጃንደረባነት በማቴዎስ 19፡12 በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፥ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፥ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው። በማለት ይገልጽብሃል ፡፡
   አልተረዳኸው ከሆነ
   - በናታቸው ማኀፀን በተፈጥሮአቸው የሚጐድላቸውን
   - በሰዎች ያለፈቃዳቸው በአገራችን በነገሥታቱና መኳንንቱ ግቢ ለማገልገል የሚገቡ ወንዶች ዘር እንዳያበላሹ በሚል ወይም በደቡብ አካባቢ የጀግና አስረጅነት በመፈለግ የሚሰለቡትን ዓይነት
   - ስለ መንግሥተ ሰማያት ራሳቸውን የሰለቡ የሚለው ደግሞ ሥጋህን ስለ ሃይማኖት ጽድቅ ስትል መጐሸም እንደሚገባህ የሚያስረዳ ነው ፡፡ ታድያ ጌታ ያስተማረውን እንከተል ወይስ አንተ በየሥራቻው ለመንደፋደፍ እንዲያመችህ የምትለፍፈውን ?

   Delete
  3. የተሰጠ መልስ
   ጌታ ራሱ ስለ ጃንደረባነት በማቴዎስ 19፡12 በእናት ማኅፀን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ፥ ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ፥ ስለ መንግሥተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ። ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው አላቸው። በማለት ይገልጽብሃል ፡፡
   አልተረዳኸው ከሆነ
   - በናታቸው ማኀፀን በተፈጥሮአቸው የሚጐድላቸውን
   - በሰዎች ያለፈቃዳቸው በአገራችን በነገሥታቱና መኳንንቱ ግቢ ለማገልገል የሚገቡ ወንዶች ዘር እንዳያበላሹ በሚል ወይም በደቡብ አካባቢ የጀግና አስረጅነት በመፈለግ የሚሰለቡትን ዓይነት
   - ስለ መንግሥተ ሰማያት ራሳቸውን የሰለቡ የሚለው ደግሞ ሥጋህን ስለ ሃይማኖት ጽድቅ ስትል መጐሸም እንደሚገባህ የሚያስረዳ ነው ፡፡ ታድያ ጌታ ያስተማረውን እንከተል ወይስ አንተ በየሥራቻው ለመንደፋደፍ እንዲያመችህ የምትለፍፈውን ?

   Delete
  4. I would agree with the verse on በማቴዎስ 19፡12. Even if I agree that preaching the Bible should be given priority over aanything else in any church mission, not all people are chosen to preach the Bible. We have different gifts. Thus, we should serve God according to our gift. The monks praying in monasteries are serving God according to their gift. However, our culture of ignorance should be changed with knowledge and fervent desire to spread the word of God. Yes, our monasteries need to improve in that aspect. When I visited the Tsadkane Mariam monastery in Sela Dingay last year, people told me that the people inhabiting around the monastery live a life full of supersition or TINKOLA. If our monasteries had the capacity to reach out the community and teach the true word of God, we would not have seen this kind of lost souls at least around monasteries. So, we need to change how we think about holiness and the roles of our monasteries in our church.

   Delete
  5. በስንዴው መሃል የሚዘሩ እንክርዳዶች ብሎ ያስተማረው እንደነዚህ አንድ ወጥ መናገር እንዳንችል የሚያደርጉንን ደካሞች ለመጥቀስ ነው ፡፡ እኔ ደግሞ ስለ ገዳም የማውቀው ያበቁ ፣ ዓለምን የናቋት ፣ ለሥጋ ማደርን ችላ ያሉ ሰዎች መሰብሰቢያ ፤ ትምህርተ ሃይማኖት የሚካሄድበት ፣ ጾም ፣ጸሎት ፣ ስግደት ያለማቋረጥ የሚከናወንበት ለየት ያለ ሥፍራ አድርጌ ነው የምቆጥረው ፡፡ የጥንቶቹ አባቶቻችን የወጡትም ከእንደነዚህ ካሉ ሥፍራዎች ነበር ፡፡ የሃይማኖት መጽሐፍት የሚደረሱትና ለቤተ ክርስቲያን ማስተማሪያ የሚቀርቡት ከነዚሁ አሁን በእንክርዳድ ከተወረሩት ሥፍራ ነበር ፡፡ ጥንታዊ የገዳም ታሪካችንን ብታነበው ፣ ለማውደም ሳይሆነ ለማደስ ወደሚለው ዓላማ ትዛወራለህ ፡፡

   Delete
  6. ስለ ምንኲስና መገንዘብ ስለሚያስፈልገን ትንሽ ልበል ፡-
   የምንኩስናን ትርጉምና ዓላማ በሥርዓቱ ካለማወቅ የተነሳ የመነኑ ሰዎችን ፣ የሐዋርያነትን ሥራ ወይም ሐዋርያዊ ተግባራትን ለምን አይፈጽሙም ? የሚል አቤቱታ በተደጋጋሚ ይነሳል፡፡ ለሃይማኖት ግልጋሎት ካልሰጡስ ፣ የነሱ ክርስቲያን መሆን ጥቅሙ ምንድር ሊሆን ነው ? በማለት ምንኩስናን የሚተቹ በዘመናችን ብዙ ሰዎች አሉ ፡፡ እንዲያውም አንዳንዶቹ ካለመረዳት በመነጨ መልኩ ፣ ከመተቸት አልፈውም የማያስፈልግ ሥርዓት ነው በማለት እንዲወድም የሚፈልጉ አሉ ፡፡

   - መነኲሴ ፡- መናኝ ድኻ ፣ ለማኝ ፣ ከዓለም ከዘመድ ፣ ከሕዝብና ከገንዘብ የተለየ ፡፡
   - መነኰሰ ፡- በራሱ ላይ የተጸለየበትና የተባረከ ቆብ አደረገ ፤ ጫነ ፤ ሳይሞት በሰሌን ተገነዘ ፤ ፍታት ተፈታ ፡፡ ዓለም በቃኝ አለ ፤ መነነ ፤ ገዳም ገባ ፤ አስኬማ ለበሰ ፤ ቃል ኪዳን ገባ ፤ ደኸየ
   - መመነን ፡- መናቅ ፣ መጥላት ፣ ማኰሰስ ፣ ማርከሰ ፣ መንቀፍ ፣ ማጸየፍ ፣ መካድ መጣል
   - ገዳም ፡- የመናኞች ባሕታውያንና መነኮሳት መኖሪያ ፤ ዓለማዊ የሌለበት ስፍራ ፤ ዱር ፤ በረሐ ፤ ደን ፡፡ መሸሻ ፤ መደወያ ፤ መማጠኛ ሥፍራ
   - ገዳም ገባ ፡- ዓለምን ናቀ ፤ ተወ ፣ መነነ ፣ ከዓለም ተለየ

   ከዚህ ከላይ በተዘረዘሩት የቃላት ትርጉሞች ውስጥ ሐዋርያዊ ሥራን የሚያካትት ፍቺ በአንደኛውም ቃል ውስጥ አልተጠቀሰም ፡፡ በደፈናው ምንኲስና በቅድሚያ ራስን ለማዳን ብቻ የሚደረግ ለየት ያለ በእምነት የመታገል ልምምድ እንጅ ፣ አውቆ ማሳወቅን ፣ ለሌሎች መትረፍን አይጨምርም ፡፡ ለዓለማውያን እየተዘዋወሩ ማስተማርን ግቡ አያደርግም ፡፡ ምክንያቱም ቀዳሚ ዓላማው ከዓለም መለየት ስለሆነ ነው ፡፡

   ሆኖም ግን በአገራችን የነበሩት የታወቁ የጥንት ገዳማት የሃይማኖት ትምህርት ቤት እንደነበሩና ፣ ለመመንኰስ በመፈለግ ብቻ ሳይሆን የሃይማኖትን ምሥጢርንም ለመማርና ለማጥናት ሲሉ ሰዎች ሁሉ የሚሄዱባቸው ሥፍራዎች ነበሩ ፡፡ በገዳም የሚጻፉ መጽሐፍትንም እስከ አሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያናችን እየተገለገለችባቸው ትገኛለች ፡፡ ሁሉም መነኰሳት ባይሆኑም አልፎ አልፎ ደግሞ ከነርሱ መሃል እጅግ የበቁት ወደ ዓለማውያን ተሰደው እንዳንክድ አስተምረዋል ፤ ሌላ ቀርቶ እስከ ጳጳስና ፓትርያርክነት ደረጃ በመድረስ ንጹህ ሃይማኖታዊ ግልጋሎትን ፈጽመዋል ፤ እየፈጸሙም ያሉ አሉ ፡፡

   አንተ እንዳወሳኸው በገዳም ዙሪያ የሚኖሩ ሰዎች ዓለማውያን ስለሆኑ ፣ የአካባቢቸውን ነውሮች ይፈጽማሉ ፡፡ ይኸ ማለት ግን የአካባቢው ጥፋት ከመነኰሳቱና ዓላማና ተግባር ፤ ከገዳም መኖር አለመኖር ጋር ይዛመዳል ማለት አይደለም ፡፡ በአጠቃላዩ ግን በአቅራቢያ ያን የመሰለ ሥፍራ መኖር በስብዕናህና በወደፊቱ ዓለማዊ ጉዞህ ላይ የራሱን መንፈሳዊ አስተዋጽዖ ሊያደርግ ይችል ይሆናል የሚል ግምት አለኝ ፡፡ አንተነትህን በበጎ በመቅረጽ በኩል ዶሮ ማነቂያ ከማደግ ፣ ደብረ ሊባኖስ አካባቢ መኖር ሳይሻል አይቀርም እላለሁ ፡፡

   Delete
 3. Essey, kehadi hula, chirash endih sirachihu hulu gitit bilo weta eko. demo yemigermew, yenanten billo Eyesusn awakinet? uute alekerebachihu. Fetari libona yistachihu, ahunim kirstos semra tamaldachihu. Lela minim alilim, yekihedet libachihun amlak yimelsilachihu. weyine ortodox yenewa, tehadiso endih hono tenseraftoalina lekka? eshi, esu fetari betun yatseda yele? yane yasteyayenal. tinish tinish tsihufachihun aneb neber ahun gin lekihidet bota yelegnim. Hasawiyan hulu tesebisibachihu.

  ReplyDelete
 4. to tesfa, I would like you explain the bible foolish story about Yonas? how could a man be alive living three days inside Whale,and inside the water. yih yemetsihaf kidus tera worie new. enante kirsitianoch teret teret tiwodalachihu.
  second, God, told to Abrham, your seeds will be like a sand of a sea or as many as the stars. tesfa, how many are the number of sand and of stars on the sky?
  oh! God is wrong! how could a persons generation be as many as the number of stars may be 1,000000000000000000000000000000000000000000000....this much! please dear ask God and give the answer.
  Meku

  ReplyDelete
  Replies
  1. መኩ
   አባቶች በሬ ሆይ ሣሩን አየህና ገደሉን ሳታይ ይላሉ
   አንተም እነሱን ተከትለህ ወደ ሚፈልጉት ክህደት እያመራህ ነው ፡፡ ይኸ ለሌሎች ክርስትናን ለማይፈልጉ ቋንቋ ያስተምራቸዋል ፡፡ ዓላማህ ገብቶኛል ፤ ነገር ግን የማያምኑ ቢያነቡት ልክ እንዳልከው ይሞግቱናል ፡፡
   መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም እውነት ነው ብለን እንቀበላለን ፡፡ ሌሎቹንም በእግዚአብሔር ፈቃድ የተፈጸሙትን ገድላት እናምናለን ፡፡ በሰው ህሊና ይሆናል ተብሎ የማይገመተውን መፈጸም የእግዚአብሔር ክህሎቱ ነው ፡፡ ለማያምኑት ተረትና እንቆቅልሽ ይሆንባቸዋል ፡፡

   Delete
  2. Dear sir/ madam,

   The Holy Bible, even though it is the Book of eternal truth, it is not a book of facts. If one is looking for facts it is better to read a newspaper than the Bible.

   Even though it is a collection of divinely inspired books, we don't have to forget that, it is a collection of books that had been written by human beings, who were conditioned by culture, sociopolitical issues, historical events, etc.

   The Bible is the Word of the Lord yet that doesn't mean that the Lord had spoken each and every word we find in the Bible. Rather, it is written by human beings according to their understanding of the Sacred. These human beings are always liable to errors and mistakes and misunderstandings despite the fact that they will always be instruments of the Lord's eternal truth.

   The Bible is not a simple book or a news paper to be taken literally. No! If we try to take the Bible literally there will be a lot to loose.

   Never forget that, the Lord didn't dictate each and every word to the writers.

   If we want to understand the Bible first, we should learn about its historical, cultural, sociopolitical backgrounds. Before judging them as bad or good we need to understand why the writers wrote each and every particular book in the Bible the way they wrote it from cultural, historical, political factors. We need to understand what the situations that conditioned their minds.

   Second, we need to have a good knowledge of symbolism. For instance, if we want to understand the Book of Jonah (Yonas) we need to ask what number three represents in the Hebrew culture. Why three days of fasting? Why three days in the belly of the whale? What is the meaning of fasting? What does the number three represents here?

   Third, we need to understand what the purpose of the writer was when he wrote that particular book. We don't have to forget that none of the Books in the Bible were written to report an event like a simple newspaper. For example, the main objective of the writer(s) of Genesis is to tell us that the Universe didn't come from the blue. It has a creator who willed to bring it to being. How did he created it is not the concern there. The issue is to tell us that we are not meaningless. There is God in whom "we live, move and have our being." Why are we created? Not to be educated. Not to be rich. Not to be poor. Not to exploit whomsoever and whatsoever around us. Neither to be kings nor to be slaves. But to praise Him in Whom we live, move and have our being.

   Delete
  3. Dear Meku,

   The Holy Bible, even though it is the Book of eternal truth, it is not a book of facts. If one is looking for facts it is better to read a newspaper than the Bible.

   Even though it is a collection of divinely inspired books, we don't have to forget that, it is also a collection of books that had been written by human beings, who were conditioned by culture, sociopolitical issues, historical events, etc.

   The Bible is the Word of the Lord; yet that doesn't mean that the Lord had spoken each and every word we find in the Bible. Rather, it is written by human beings according to their understanding of the Sacred. These human beings are always liable to errors and mistakes and misunderstandings despite the fact that they will always be instruments of the Lord's eternal truth.

   The Bible is not a simple book or a news paper to be taken literally. No! If we try to take the Bible literally there will be a lot to lose.

   Never forget that, the Lord didn't dictate each and every word to the writers.

   If we want to understand the Bible first, we should learn about its historical, cultural, sociopolitical backgrounds. Before judging them as bad or good we need to understand why the writers wrote each and every particular book in the Bible the way they wrote it from cultural, historical, political factors. We need to understand what the situations that conditioned their minds.

   Second, we need to have a good knowledge of symbolism. For instance, if we want to understand the Book of Jonah (Yonas) we need to ask what number three represents in the Hebrew culture. Why three days of fasting? Why three days in the belly of the whale? What is the meaning of fasting? What does the number three represents here? The people who wrote and translated the Bible were not idiots not to think what everyone can think. How could a human being stay in a whale’s belly without being digested? Why didn’t you think they left it as it is now?

   Third, we need to understand what the purpose of the writer was when he wrote that particular book. We don't have to forget that none of the Books in the Bible were written to report an event like a simple newspaper. For example, the main objective of the writer(s) of Genesis is to tell us that the Universe didn't come from the blue. It has a creator who willed to bring it to being. How did he created it is not the concern there. The issue is to tell us that we are not meaningless. There is God in whom "we live, move and have our being." Why are we created? Not to be educated. Not to be rich. Not to be poor. Not to exploit whomsoever and whatsoever around us. Neither to be kings nor to be slaves. But to praise Him in whom “we live, move and have our being.” (Acts 17: 28). That is why as St. Augustine said “[Oh, Lord,] for you have created us for yourself our heart shall never rest until it rests in you.”

   Are you sure that your heart has got its resting place?
   Why do you think that the world and such a messy place to live?
   Why do each and everything we do bring consequences?
   What does that tell you?
   What is the meaning of your life? Richness? Knowledge? Pride? Pleasure?...?

   Life: when it is purposeless, it is meaningless, when it is meaningless it is worthless. So do you think that you are worthless? Why are you reading my message to you then? What made you to write your comment? How would you define yourself? What is the difference between you and a dead dog?

   Most of us get it “Unbearably Light” that the meaning of our lives is one: God who is Love. Quite a simple answer! Try to look at your surrounding isn’t everything a miracle? Isn’t everything amazingly amazing? There are two ways to live in this world one seeing everything as a miracle and considering that nothing is a miracle at all.

   Lastly, if you would like to understand the Bible, start with this (although there are plenty of books on the area this one is very concise): “A Catholic Guide to the Bible”.

   Thank you,

   Delete
  4. በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ፊቴንና መላ አካሌን አማትቤአለሁ ፡፡ እኔ እንደዚህ አልልም ፤ ስለዚህም የለሁበትም ፤ ከደሙ ንጹህ ነኝ

   Delete
  5. My question is just to "menafik Tesfa and Ababa Selama Blogers" I know everything very well. I believe in God,the absolute perfect,I believe in Kiristos Semira.
   Le Awurew Menfes Melikitegnoch new tiyakeye yeneberew, le Egiziabher lijoch alineberem.
   Meku

   Delete
  6. መለየትህ መልካም ፡፡ እግዚአብሔር ይባርክህ

   Delete
 5. «ጌታም ተናገራት እንዲህ አላት በአራት ወር ውስጥ በየቀኑ የሚወርደውን የዝናም ነጠብጣብ ያህል ነፍሳትን አሥራት ሰጥቸሻለሁ» ማለት ነው። የአራት ወር ያህል ዝናብ የሚያህሉ ነፍሳት ገና የተፈጠሩ አይመስለኝም። እነዚህ ሁሉ ከሲኦል ከወጡ የተኮነኑ ነፍሳት የሉም ለማለት ያስደፍራል»
  ያልከውን ቃል ከዓመታት በፊት ምንም ስለወንጌል እውቀት ሳይኖረኝ በልጅነት አእምሮዬ እንዲህ ብዬ ነበር። የዓለሙ ሁሉ የአራት ወራት የዝናብ ነጠብጣብና በዚህ ምድር ላይ ኖሮ ያለፈውን የሰው ቁጥር በምን ሂሳብ ሊመጣጠን ይችላል? ብዬ ገርሞኝ ነበር። በኋላ ላይ ወንጌልን እያነበብኩ ስሄድ ግን ልብ ወለድና የእግዚአብሔር ቃል እንዳልሆነ ተረዳሁትና ይህን ልብ ወለድ መጽሐፍ አውጥቼ ጣልኩት። አሁን እዚህ ላይ ጽፈህ ሳየው ጊዜ ትዝ ብሎኝ ረጅም ሳቅ ሳቅሁኝ። የሚገርምህና የሚያሳዝነው ለሰዎች ይህንን ተረት ስትነግራቸው ፍጹም የማይቀበሉህና እውነት ነው ብለው የሚከራከሩ መሆኑ ነው።
  ይታይህ እስኪ! የዓለም ሁሉ የአራት ወራት ዝናብ ነጠብጣብና የሰው ልጆች ቁጥር ሲመዛዘን!!! የሚገርመው ደግሞ ይህ ከሲኦል የማዳን ስራ ለዓለሙ ሁሉ የሚተርፍ መሆኑ ነው። ካቶሊክ፤ ጴንጤ፤ እስላም፤ ጄሆቫ፤ ቡድሃ፤ ጌይ፤ ሌስቢያን፤ ከሃዲ፤ አረሚ፤ ወዘተ ሁሉን የሚያድን መሆኑ ነው። ታዲያ ምን እምነት ያስፈልጋል? እድሜ ለክርስቶስ ሰምራ ገድል!!
  ለተረትና ለልብ ወለድ ልቧን ክፍት ያደረገች ቤተክርስቲያን ዋጋ መክፈሏ አይቀርም!!! ዋጋውም ይኼው እውነቱ ሲገለጥ የደነቃቸው ይጠይቃሉ፤ የታወሩ ያብዳሉ!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማስተካከያ ቃሌ
   ማለት ፈልጌው የነበረ ጌታም የሚያድነው በስሙ የሚያምኑትን ነው እንጅ የአዳም ፍጥረትን በሙሉ በጠቅላላው አይደለም ፡፡ ነገር ግን በሃይማኖት ትምህርት ፣ የዓለም መድኀን ተብሎ ይገለጻል ፡፡ ክርስቶስ ሰምራም በተሰጣት ቅድስና ካመንክባት ስለድኀነትህ ትራዳሃለች ፡፡ ያላመነባት ደግሞ ለራሱ የሚሆነውን አዳኝ ይፈልጋል ፡፡

   Delete
 6. "...bezan zemen wushoch yiweledalu!!" yetebalew yifetsem zendi enante teweledachihu...
  Minalibat Geta yikir yilachihu zendi ...Ye kalun tirgum teyiku !! setan beseletenebet ayimiro yihin meredat atichilumina !!

  ReplyDelete
  Replies
  1. tenesh ataferum saytan yetetenawetachew hula lemn bega sem kemtematu ymensabkaw lik naw kalachew be rasachew atmetum ye saytan zeraywech amelak yeferdebachew

   Delete
 7. ተስፋ በመጣጥፎችህ ስመዝንህ የምታመልከው እንዳንተ ትንሽ ፣ ጠበብ ያለች ጭንቅላት ያለውን አምሳያ ሰውን እየመሰለኝ መጥቷል ፡፡ እግዚአብሔር የምታደርገውን ሳይሆን በማህጸን ሆነህ በእርጅና ዘመንህ የምትደርስበትን ፣ ወደ ተግባር ከመግባትህ በፊት በሃሳብህ ያለውንም ሁሉ ይገነዘባል ፡፡ ወገኖችህ የሆኑት የዋህ ምእመናን ዳገት በመውጣት ፣ ቁልቁለት በመውረድ የሚደክሙት ፣ በተጣበበ ድንጋይ ለማለፍ የሚታገሉት እሱን በንጽህና ለማምለክ መሆኑን በደንብ ይረዳል ፡፡ አያውቅም ብለህ መቼም አትከራከረኝም ፡፡

  እነዚህ በሃገራችን ቅዱሳን ተብለው የሚዘከሩት ጻድቃንና ቅዱሳን ደግሞ ቢያንስ አገልግለው ያለፉት ፣ አንተ አመልከዋለሁ እያልክ ስሙን የምትጠራውን አምላክ ነው ፡፡ ክርስቲያን ወገኖችህ ደግሞ ለዚህም ተጋድሎ ሲሰማሩ የሥጋ ምቾታቸውን አስበውት አያውቁም ፡፡ ጭንቀታቸው ስለ ነፍሳቸው መዳን ብቻ ስለሆነ ድካምና ረሃባቸውን አያሰሉትም ፡፡ አንተና መሰሎችህ ወንጌልን በቃል ፣ የድኀነት መንገድንም በምን እንደሚሆን እናውቃለን የምትሉት ፣ ይኸው ሰው ለደከመበት እንኳን ትቸገራላችሁ ፡፡ ስቃይና መከራን ትመዝናላችሁ ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ቃሉን ለማዳረስ በማለት አምስት ኪሎ ሜትር እንኳን የእግር ጉዞን አትሞክረውም ፡፡ የዋሁ አማኝ ግን ቀን ከሌሊት ስለ እምነቱ ሲል መከራን እየተደሰተበት በጾም በጸሎት አምላኩን በተቀደሰው ቦታ ሁሉ እየተዘዋወረ ያመሰግናል ፡፡

  እንደ ሁናቴውማ ለእኔ በድንጋይ መሃል መሹለኩ አልነበረም የሚያስጨንቀኝ ፡፡ ደብረ ዳሞ ያለው የአቡነ አረጋይን ገዳም ጉዞ እንዴት ተመለከትከው ወይስ ወደዛ ማለፍ ክልክል ነው ? መጫኛን አምነህ ስትንጠላጠል ቢበጠስ ፣ ወይም እጅህ ወይም እግርህ ዛል ቢልብህ ፣ መድረሻህን አስበከው ታውቃለህ ? እንዲያው ንባብ ነገርን ያነሳዋል በማለት ነው እንጅ አንተ እምነት ካለህ በመጫኛ ታስረህ ሳይሆን በንፋስ ተገፍተህም ትወጣዋለህ ፡፡ ደግሞ ትግራይ ወስዶ ደነቀረኝ እንዳትለኝ ፡፡ እዚሁ ሸዋ ውስጥ የአቡነ መልከጸዴቅ ገዳምንስ ታሪክና ተዓምርስ ለምን ለአንባቢ አታቀርብም ፡፡ ማለቴም አጽም ሳይፈርስ ፣ ማተብ ሳይበጠስ ፣ ጸጉር ሳይረግፍ ፣ ጥፍር ሳይነቀል የሚቆይበትን ቅዱስ ስፍራ /ገዳም/ ማለቴ ነው ፡፡ እንደዛ ዓይነቱን ትንግርት የሆነውን የሚያሳየው እንዳንተ እምነትን ለመካድና ለማስካድ የሚታገሉትን ፣ ዓይታችሁ ትመለሱ እንደሁ በማለት ይመስለኛልና ዕድሉን ተጠቀምበት ፡፡

  ስለሆነም ቀናውን ነገር ሁሉ እያጣመምክ ከመመልከትና ያልተባለ ከመተርጎም ፣ በቀናነት ብታየው ፣ በተክለሃይማኖትም ሆነ በክርስቶስ ሰምራ ወይም በሌላው ስም የሚመለከው አንድ እግዚብሔር ነው ፡፡ እነሱን የረዳ ፣ ያገዘ ፣ ያጸና አምላክ ፣ እኛንም እንዲለመነን ፣ እንዲረዳን ፣ እንዲምረን በማለት ያለመጠራጠር በእምነት ሆነን ጸሎት እናደርሳለን ፡፡ መጽደቅና መኮነን ከእኛ ምድራዊ ልፋት ወይም በእምነታችን ጥንካሬ አለመሆኑም እንዳይዘነጋን ሐዋርያው ሲያስረዳ “ምሕረት ለወደደ ወይም ለሮጠ አይደለም፥ ከሚምር ከእግዚአብሔር ነው እንጂ። /ሮሜ 9፡16/” ብሏልና አንተም በእምነት እንደሆንክና እንደምትጸድቅ የሚሰማህ ሰው እንኳን ለመዳንህ ምንም አስተማማኝ ደረሰኝ የለህምና የሌላውን የሲዖል ጉዞ አትተርክ ፡፡ ይልቁንም ሳትንከራተት እንደ እምነትሀ አርፈህ በአንድ ሥፍራ ጸልይ ፡፡

  ለማጠቃለል አንድ ጥያቄ ላቅርብ ፡፡
  እንዲህ የምታስነብበንን ታሪክ ከመጽሐፍ ወይስ በየገዳማቱ እየተዘዋወርክ ነው መረጃህን የምትቃርመው ? ስለእምነቴ ብሎ የሚደክመውስ እንደምንም በማለት በዓመትም ሆነ በሁለት ዓመት ዕቅድ አውጥቶ ይዘጋጃል ፣ ለአንተ ግን እንዲህ በየሥፍራው እንድትነቀሳቀስ ወጭህን ማን ወይም የትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የሚሸፍንልህ ? ከዚህ ቀደም ትዝ የሚልህ ከሆነ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብተህ የቤተ መቅድስ አገልግሎታቸው እንኳን ሳይቀር አስነብበኸን ነበር ፡፡ የተቀጣጠለው እንዳይጠፋ ብለው የሚሯሯጡትን ስለማውቃቸው በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ብር ይዘንብልኛል ብለህ እንዳትዋሸኝ አደራዬን አሰቀድማለሁ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Aye MK. I am sorry for you. Still you closed your heart. Betam tasazinaleh.I want to encourage you, what do you do, before pray and read it again and again please! Geta yaberalihal. please I beg you that is good for you. Abba.

   Delete
  2. ጸሐፊው ከሌሎች ገንዘብ ተቀብሎ የሚሰራ ይሁን አይሁን ከግምት በስተቀር እርግጠኞች መሆን አንችልም። እንዲያው ለነገሩ እየተከፈለው የሚሰራ ነው ቢባል እንኳን የክፍያው ቦታና ሁኔታ የቀረበውን ጽሁፍ ማንነት ይወስነዋል እንዴ? ስላልተከፈለው እውነት፤ ስለተከፈለው ደግሞ ውሸት ሊባል ይቻላል? ይህ የጅል አስተሳሰብ ነው። ቁም ነገሩ የቀረበው ጽሁፍ እንደመጽሐፍ ቅዱስ የሕይወት መንገድ ገላጭ ቃሉ ትክክለኛ ነው ወይስ አይደለም በሚለው ነው መነገር ያለበት! መልስ መስጠት ሲያቅትህ ወደግለሰብእ ታሪክ ጥናት ትወርዳለህ።
   እስኪ ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ ስጥ፤
   1/ የዓለሙ ሁሉ የ4 ወራት የዝናብ ነጠብጣብ ምን ያህል ነው?
   2/ በሲኦል ያሉ ነፍሳትስ ምን ያህል ናቸው?
   3/ በዝናብ ነጠብጣቡ ቁጥር የሚድኑት ሰዎች የየት ሀገር ዜጎች ናቸው?
   4/ የዓለሙ ዝናብ ያህል ነፍሳት ከሲኦል የሚወጡ ከሆነ ኩነኔ ለማነው?
   5/ እንደዚህ የሚዳን ከሆነ እምነት ምን ያደርጋል?

   Delete
  3. እንደ የዋሁ ምዕመን ጽድቅን ፍለጋ ለመድከም ካልሆነ ገዳም ለገዳም ለምን ይንከራተታል ? ስለሁለት ነገር ጥያቄን አነሳሁ ፤ አንድም አሳዝኖኝ ሌላውም እንዴት እንደሞላለት ለማወቅ በማለት ? እኔም እንደ ርሱ መጐብኘትና ጸሎቴን እንዳደርስ በማለት ነው እንጅ በሌላ የተንኰል አካሄድ አይደለም ፡፡ ግና ምነው ታመመክ ? ውስጥ አዋቂ ትሆን እንዴ ?

   ለጥያቄዎችህ ይህን መልስ ከሌላ ቦታ ገልብጨ አምጥቼአለሁ ፡፡
   ጌታም የሚያድነው በስሙ ለሚያምኑ ነው እንጅ የአዳም ፍጥረትን በሙሉ በጠቅላላው አይደለም ፡፡ ነገር ግን በሃይማኖት ትምህርት የዓለም መድኀን ተብሎ ይገለጻል ፡፡ ክርስቶስ ሰምራም በተሰጣት ቅድስና መሠረት ካመንክባት ስለድኀነትህ ትራዳሃለች ፡፡ ያላመነባት ደግሞ የራሱን አማላጅ ይፈልጋል ፡፡

   በአምስተኛ ተራ ቁጥር ላስቀመጥከው
   እንድን ብንሆን በማለት እንደክማለን ፡፡ ይኸ ቢባልም እንድንድን በክርስቶስ ሰምራ ማምለክ አይገባም ፡፡ ነገር ግን እንደማንኛውም ጻድቅ ከፈጣሪአችን ይቅርታን ጠይቂልን ፣ ተራጂን ፣ አማልጂን ማለት ክፋት የለውም ፡፡

   Delete
 8. ተስፋ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ እዉነተኛዉ የእግዚአብሔር ቃል መጻፍ ግን ይህንን አያስተምርም ይልቁንም፣
  1. “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” የሐዋርያት ሥራ 4 12
  2. “ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” የዮሐንስ ወንጌል 146
  3. “በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል።”የዮሐንስ ወንጌል 109
  4. “የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።” የሐዋርያት ሥራ 221
  ይላል እንጅ፡፡ ተስፋ ገብረስላሴ ዘብሔረ ቡልጋ የሚባሉ ማተሚያ ቤት የነበራቸዉ ሰዉ( አሁን በሕይወት የሉም) እነዚህን መሰል ተረት የተሞሉ ገድሎች በማሳተምና በማሰራጨት ሐብት ሲያካብቱ የኖሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባሉለታም እየተባሉ ሲሞካሹ ነበር፡፡
  እንግዲህ እንዲህ ያለዉን የጅል ተረት የማትቀበልና አዳኙና የዘላለም ሕይዎት ሰጪዉ ስለ ሰዉ ልጆች ሐጢያት በመስቀል ላይ የሞተዉ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነዉ ብለህ የምታምን ከሆነ መናፍቅ ትባላለህ፡፡ ይህንን ተረት አምኖ ከመቀበልና፣ “አንድ ሰው መጽደቅ እና አለመጽደቁን ለማወቅ በሰንጣቃው አለት በማለፍ እራሱን ይፈትናል ፣በዓለቱ ሾልኮ ካለፈ ጸድቋል ካላለፈ ግን ተኮንኗል ።”፤ ” ጌታም በየቀኑ ከሲኦል ሦስት ሺህ ነፍሳትን እንድታወጣ ሥልጣን ሰጣት ወይም ቃል ኪዳን ሰጣት”፤ “የአራት ወር ያህል በየቀኑ በዓለም ላይ የዘነበውን የዝናብ ጠብታ ያህል ነፍሳትን እንድታወጣ ቃል ኪዳን ተሰጥቷታል።” ፤ “ክርስቶስ ሰምራ ዲያብሎስና እግዚዘብሔርን ለማስታረቅ ወደ ሲኦል ወርዳ ከዲያብሎስ ጋር ተነጋግራለች ።“ ብሎ ከማስተማር የበለጠ ክደትም ሆነ መናፍቅነት ግን ሊኖር አይችልም፡፡ እኔን የሚገርመኝ የተክለ ሐይማኖት አድናቂ የሆነ ገድል ጸሀፊ የሁሉ ነገር መፍትሔ እሳቸዉ መሆናቸዉን ሲተርክ፣ የአቡዬ ገድል ጸሀፊም በመሰለዉ መንገድ ድርሰቱን ሲቀጥል፣ የክርስቶስ ሰምራዉ ተረኛ ገድል ጸሀፊም በበኩል የመዳን ተስፋችንን በክርስቶስ ሰምራ ላይ ይጭነዋል፡፡ የዚህ ሁሉ አላማ ግን አንድ ነዉ እሱም የክርስቶስን አዳኝነት መሸፈን፡፡ አቤቱ እብክህን አንተዉ አይናችንን አብራልን፡፡
  ማስረሻ ይዘንጋዉ

  ReplyDelete
  Replies
  1. የአምላክን ችሎታ እየተጠራጠርክ ነው ያለኸው ፡፡ ለአህያ ያለ ተፈጥሮዋ ልሳን ሰጥቶ የሚያናግር አምላክ ከቶም የሚሳነው የለምና ፣ ተረት ከማለት የማያምን ሰው አስተያየት ሳይሰጥ ቢቀመጥ መልካም ይመስለኛል ፡፡

   Delete
  2. ወቸ ጉድ የክርስቶስ ሳምራ ገድል ከተፈታተነው አልፎ
   ጻድቃኔ ሄጀ ጥንቆላ አየሁ ያለው ገረመኝ። በለፈለፉ ይጠፉ ይላሉ አባቶች። ወዳጀ እኔ ምስክር ነኝ። በዛ በተቀደሰ ቦታ የሚታየው ሰው በርድ አይል ሙቀቱን ተቋቁሞ ደጅ እያደረ አምላክን የሚማጸንበት ገዳም ስሆን ክፉው መንፈስ የሚረገጥበትነው። ገዳማት ለምን አስፈለጉ ይሚሉ መናፍቃን እንኳን አምነው የሚሄዱበት
   የሰው ልጅ መተሳሰብን ፍቅርን የሚያሳይበት ልዩ ቦታ ነው። ክዚህ በላይ አንተ የምታቃልላቸው መነኮሳት ዘወትር ቀኑን ሙሉ ሳይበሉ ስለህዘበ እግዚአብሄር ስለሃገር እየጸለዩ መልስ የሚገኝበት ቦታ ነው፡፡ ወንጊልን መስበክ መጽሃፉን በመዘርጋት በመድረክ ላይ ሆኖ የምስራቹን ቃል ማብሰር ብቻ ሳይሆን እንደየስጦታው በድርጊት እንዴት ወደአምላክ መቅረብ እንደሚቻልና በሚከናወኑት በረክቶች ሰው ሲመለስ የእግዚአብሂርን ፍቅርና ደግነት ለአለም እንዲመሰክር ነው። ቅዱሳን አበው ወደህዝብ ሲሄዱ አምላክ ሃጣተኞችን እኛን ታግሶ ልመናችን ምህላችን እንደሚሰማን ከውደቅንበት እንደሚያነሳን ለዚህም ምን ማደረግ እንደሚገባን ነው። ጥንቆላን ምን አመጣው፡፡

   Delete
 9. thank you for this post.

  ReplyDelete
 10. ተስፋ ላቀረብከው ጽሁፍ አመሰግንሀለው፤
  ግን እኔን ያልገባኝ ነገር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆኑ ብዙ የተማሩ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ታዲያ ለምንድ ነው ቤተክርስቲያን በእንደዚህ አይነት ተረት ተረት ተሞልታ፤ ህዝቡ በተሳሳተ መንገድ ሲሄድ እያዩ ዝም የሚሉት ? ይገርማል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Because those they're called educated also they can read it in Ge'ez perfectly but they can't understand what it says. Or they can't understand what the word of God in the Holy Bible says. when I was in the monastery I know many monks, priests, deacons,... church servants they can't quiet one word from the Bible. Abba.

   Delete
  2. wendemea terete teretema yemiyawerawe tsehafiwe enji yeqedusane gedele menu newe terete teret? esiti leaberehame yetegebawen qale kidane endihume leqedusan yetegebawen kalkidan metsehafe kidus kefetehe anebebe...keza terete teret yeminagerewe ma endehone egizihare yegeletselehale bego lebona kalehe..kalehone gene hulea eyechelemebehe eweneten kemenagere ende tesfu bewerea tetemedalehe

   Delete
  3. leabraham yetegebalet kalkidane nefsatin silemadan aydelem. lekidusan tegebalachew yemibalew kalkidane gin yemadan sira new. medan degmo bekirstos enji belela bemanim ayhonim.

   Delete
 11. you will never understand this spiritual story unless u change your heresy attitude.

  ReplyDelete
 12. ከዚህ በታች የተጻፈው የወንጌል ቃል ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ካህናት የተጻፈ ይመስለኛል፡፡
  እናንተ ፈሪሳውያን የመንግስተ ሰማያትን መግቢያ ቁልፍ ይዛችኃል፤
  ነገር ግን እናንተም አትገቡም ሌሎች እንዳይገቡበት እንቅፋት ትሆናላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 13. ወንድሞቼ ና እህቶቼ ቤተክርስቲያናችን ተሀድሶ ያስፈልጋታል ፤ እንዲህ አይነቱን ተረት ተረት ነቅለን በመጣል ብዙ ነፍሳትን ማዳን እንችላለን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. በሽፍን የያዛችሁት አጀንዳ ተጋልጧል ፣ በዚህ እንደገና ለመሸፋፈን አትሞክር

   Delete
  2. መታደስ ያለበት የአንተ ሃሳብ እና አንተ ነህ። ቤተ ክርስቲያን አንዴ በክርስቶስ ደም የተመሰረትች፣ በሐዋርያት የጸናች ናትና አትታደስም። ሰዎችን ግን ታድሳለች። አንተም ለመታደስ ያብቃህ።

   ቆይ ይህን ተረት ተረት ያልከውን ነቅለህ ስትጥለው፤ አንተ ማነህና ነው ብዙ ነፍሳትን የምታድነው?

   የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ በረከት ይደርብን፣ አምላከ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!!!

   Delete
  3. ሕንጻ ቤተክርስቲያን ከሆነ ሲፈርስ ይታደሳል፤ ሲሰነጠቅ ይጠገናል፤ ሲያፈስ ይከደናል፤ ሲጠብ ይሰፋል። ይህ እውነት ነው። ስለህንጻው የምታወራ ከሆነ መታደሱን በገሃድ እናውቃለን። ስለሰው የምታወራ ከሆነ ሰው ይበድላል፤ ያጠፋል፤ኃጢአት ይሰራል። በንስሃ ይታደሳል። ከውድቀቱ ይነሳል፤ በመንፈስ ቅዱስ ይለወጣል፤ ጸጋውን ያገኛል። እንግዲህ ቤተክርስቲያን ሲባል አንድም ክርስቶስ የሞተለት የሰው ልጅ ነው። አንድም ክርስቲያን ጸሎት የሚያደርስበት ህንጻ ነው። እነኚህ ሁለቱ መታደሳቸው የግድ መሆኑን ካየን ቤተክርስቲያን አትታደስም ስትል ምኑን ለማለት ፈልገህ ነው?
   እግዚአብሔር ውላጤና ኅልፈት የሌለበት፤ ዘመን የማይቆጠርለት ስለሆነ ለእሱ የሚነገርለት መታደስ የለም። ታዲያ አንተ አትታደስም የምትለው ቤተክርስቲያን ምኑን ነው?

   Delete
  4. ለመደነቋቆር ካልሆነ በስተቀር ፣ ይኸን ያህል መግለጽ ከቻልህ መታደስ አያስፈልጋትም ያለው ትምህርተ ሃይማኖቷን ማለትም ዶግማና /እምነቷና/ በቀኖናዋ የተወሰኑትን የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ትምህርቶቿን ማለቱ እንደሆነ አይጠፋህም ፡፡

   Delete
  5. ቤተ ክርስቲያን ተሀድሶ ያስፈልጋታል በማለት ሀሳብ ያቀረብኩት እኔ ነበርኩ፤ ይህን ያልኩት ቤተክርስቲያን ትፍረስ ለማለት አይደለም፤ ተዋህዶ ፈርሳ ከማየት ዓይኖቼ ቢፈሱ እመርጣለሁ፡፡ ነገር ግን ለሐዋርያት የተሰጠው መሰረታዊ የወንጌል ቃል ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልን ስበኩ ህዝቡንም በአብ ፤በወልድ ፤በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኃቸው ደቀመዛሙርቴ አድርጉዋቸው የሚል ቢሆንም እኛ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ የመኑትን ነገር ግን በአንዳንድ ሰማዕታት ገድል ላይ ጥርጣሬ አለን የሚሉትን መናፍቃን በማለት ስናሳድዳቸው ኖረናል፡፡ ኢህአዴግ እንካን ህገ መንግስቱን የሚቃረን ማንኛውም ህግ ተቀባይነት የለውም ይላል፤ ታዲያ መጽሀፍ ቅዱስን የሚቃረን ገድል እንዴት ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል ?? የኔ ሀሳብ ሁላችንም መጽሐፍ ቅዱስንና ገድላትን እናንብብ ዕውነቱንም እንወቅ የሚል ነው፡፡ አመሰግናለሁ

   Delete
 14. Thank very much. please! continue to forward the truth. we have to fight with such gossip or 'teret teret'. GOD may bless you.

  ReplyDelete
 15. ሰለስተ እልፈ ማለት ሦስት ሺህ ማለት አይደለም። 30 ሺህ ማለት እንጅ። ወይስ ከግእዙ ላይ ችግር ይኖርብሽ ይሆን። ኣንድ እልፍ እኮ 10 ሺህ ነው። ለነገሩ ቁጥሩ አይደለም ቁም ነገሩ በእየቀኑ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ነፍሳት ከሲኦል መውጣታቸው ነው ታምር የሚሆነው።30 ሺህ ቀርቶ ሦስት ነፍሳት በየቀኑ ከሲኦል ከወጡ የሚደንቅ ነው፡፤

  ReplyDelete
 16. ante mengiste semayt enquan litgeba beruq enkan atayatim, yemigebutin tasuitaleh enj, !!!

  ReplyDelete
 17. I wonder how many of you understand what mysticism is or how it is expressed or how we better understand it. I am neither judging you nor defending the Ethiopian writers of hagiography.

  However, I am trying to put everything in perspective.

  Just take a perspective of mysticism and try to understand what it means, what its pitfalls are and how mystics experience the sacred. These are words from scholastic fields of Religion Studies. If you would like to understand what mysticism is you need to refer books from that particular field of study.Otherwise your judgments will be a lay person's judgement who doesn't distinguish between mysticism and mistake.

  I would also like to demarcate that there is a huge difference about believing in saints and believing in whatsoever is written about them. After all, as of my knowledge no one in the EOC will dare to say you will go to hell if you do not believe Gedle Krstos semra.

  ReplyDelete
 18. engidihe yemenefeqena mechereshawe metsehafe qedusen meqawem silehone ayegerememe ..lemehonu endante ende tsehafiwe tesfu ababal...egiziabehere leaberehame yegebawe qale kidane sihetete endehone eyenegerekene newe silezihe mene yegeremale tadiya yeqedusanenen gedile mananaqehe? derome bihone ye menafeqane mecheresha adarashe wesete mechohe bechan yeseyetan mechawecha mehon enji lela fayeda yelewem....


  egiziabehere gene lebona yesetachehu enanete menafeqan!!!

  ReplyDelete
 19. «ወሶቤሃ አውስአ ወይቤላ ንስኢ ወሐብኩኪ ዓስራተ ብዙኃ ነፍሳተ መጠነ ነጠብጣብ ዝናም ዘ፬ቱ አውራኅ ለእለ አሐዱ ዕለት» ትርጉም «ጌታም ተናገራት እንዲህ አላት በአራት ወር ውስጥ በየቀኑ የሚወርደውን የዝናም ነጠብጣብ ያህል ነፍሳትን አሥራት ሰጥቸሻለሁ» ማለት ነው። የአራት ወር ያህል ዝናብ የሚያህሉ ነፍሳት ገና የተፈጠሩ አይመስለኝም። እነዚህ ሁሉ ከሲኦል ከወጡ የተኮነኑ ነፍሳት የሉም ለማለት ያስደፍራል።

  ahune mane yemute tesfa deneqoro mehonehe enji egiziabehere leaberehame kalekidane sigeba zerehen endebahere asewa abezawalehu yelale ...ante dedebe menafeqe selehoneke yehe ayegeletselehem.......kemenafeqe kezihe belaye ayetebekime

  ReplyDelete
  Replies
  1. deneqoro ነው ያልከው? ይህ ፍርድ ደርሶብሃልና ደንቆሮ ላልከው ቶሎ ንስሐ ግባ!!
   ማቴዎስ
   5፥22
   እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።

   Delete
  2. ቆንጆ ሃሳብ ነው ፤ ቀድሞ በደል የፈጸመ አስቀድሞ ይጀምር ፡፡

   Delete
  3. ቀድሞ የበደለው ማን እንደሆነ እስከምታውቅ ድረስ ንስሐ አትገባም ማለት ነው?
   ቂቂቂቂቂቂ! ክርስቲያን ማለት እንደዚህ ነው።

   Delete
 20. Imagine we are saying God said this by invoking his name "ጌታም ተናገራት እንዲህ አላት".
  Ok let us assume this is true "ጌታም ተናገራት እንዲህ አላት በአራት ወር ውስጥ በየቀኑ የሚወርደውን የዝናም ነጠብጣብ ያህል ነፍሳትን አሥራት ሰጥቸሻለሁ". Is the selection of those to be saved random or those who believes in her while they are in hell. If so, OH, there is salvation and redemption in hell. (please note that I am absolutely happy if hell is empty of human generation". What about God's word which says God "will give to each person according to what he has done" Romans 2:6. I always wonder why at least one of the disciples do not have such writings. If this is false "ጌታም ተናገራት እንዲህ አላት" it will be sin with out any proportion for the writer and for those who believed him and followed him. because we falsely invoked God's name to say that he said this but he never did. So we have to be extra careful whenever we invoke God's name.

  ReplyDelete
 21. የክርስቶስ ሰምራና ሌሎች መሰል ገድል በሚል ስም የተደረቱ ታሪኮች የብዙ ሊቃዉንትን አንገት የሚያስደፉና የቤተ ክርስቲያኗን ገጽታ ያበላሹ መሆናቸዉ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ እያለ ዛሬም ድረስ ለዚህ ድርሰት ጠበቃ ሆናችሁ የቀረባችሁ ሰዎችን በማየቴ በእጅጉ ተገርሜአለሁ፡፡ አንዳንዶች ይባስ ብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ የተነገሩ ተአምራቶችን እየጠቀሱ እግዚአብሔር የሰራዉን እዉነት የክርስቶስ ሰምራ ግድል ደራሲ ከደረተዉ ድሪቶ ጋር ለማነጻጸር ሞክራችኋል፡፡ እዚህ እየተባለ ያለዉ፣ እግዚአብሔር ለሰዉ የማይቻልና ከአዕምሮ በላይ የሆነ ነገርን መስራት አይችልም ሳይሆን፣ ማንኛዉም አይነት ገድልም ሆነ መንፈሳዊ ይዘት ያለዉ ጽሑፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ከተቃረነ ተቀባይነት ሊኖረዉ አይገባም ነዉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምህሮ መሰረት አድርጎ ብዙ አስተማሪ የሆኑ መጻህፍትን ማዘጋጀት ይቻላል፡፡ የበሬ ወለደ ተረትና ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለዉ ከሆነ ግን አይጠቅምም ነዉ የጸሐፊዉ አላማ የሚመስለኝ፡፡ በተረፈ ግን ብዙ የዋሆች፣ ሁሉ ነገር ኢትዮጵያዊ እንዲሆን አትፈልጉ( አንዳንዴ ክርስትና ራሱ ከየት እንደተጀመረ ድሮ በታሪክ ትምህርት የተማራችሁትንም አስታዉሱ)፡፡ ክርስቲያኖች እኮ በሌላም አገር አሉ( ኢትዮጵያዊ የሆኑትን እነ ክርስቶስ ሰምራም ሆነ እነ ተክልዬን የማያዉቁ) ታዲያ እነዚህ እንዴት የሚድኑ ይመስላችኋል? አጼ ዘረ ያዕቆብ ከገዳም ወጥቶ ንጉስ ሲሆን ስሙን ለማስጠራት በየገዳሙ ሰዎችን ቀጥሮ ያስደረሳቸዉን የፈጠራ ታሪኮች አዉጥተን መጣል አቅቶን ገድል በሚል ስም ሸፋፍነን ይዘን እነሱን ብቻ በመተረክ እዉነተኛ የሆነዉን የአምላካችንን ቃል መጽሐፍ ቅዱስን ወደጎን ስንገፋ መኖራችን ትልቅ ኪሳራ መሆኑ ተዘንግቶ ዛሬም ለዚህ ድሪቶ ታሪክ ዘብ መቆማችን የሚያሳየዉ ሰይጣን በዚያ ዘመን የዘራዉ ክፉ ስራ ፍሬ አልባ ሆኖ ያልቀረ መሆኑን ነዉ፡፡
  “ክርስቶስ ሰምራ ሰይጣንንና እግዚአብሔርን ለማስታረቅ አስባ ሐሳቧን ለእግዚአብሔር ስትነግረዉ፣ ‘’እሺ ይላል ብለሽ ነዉ? እሺ ካለ ምን ቸገረኝ” ብሎ እግዚአብሔር ተስማማ፤ ከዚያም ክርስቶስ ሰምራ ወደ ሲኦል ሔዳ ሳጥናኤል.. ሳጥናኤል ብላ ስትጠራዉ ”ማነዉ በድሮ ስሜ የሚጠራኝ ?” ብሎ በመዉጣት ክርስቶስ ሰምራን አገኛት፣ ከእግዚአብሔር ጋር ልታስታርቃቸዉ እንደምትፈልግ ስትነግረዉ ሰይጣን ተበሳጭቶ ክርስቶስ ሰምራን ወደ ሲኦል ገፍትሮ ጣላት ከዚያም እግዚአብሔር መልአክ ላከላትና መልአኩ ከሲኦል ሲያወጣት ብዙ ነፍሳትን ከሲኦል አዉጥታ ወደ መንግስተ ሰማያት አስገባች” የሚል ታሪክ አሁን በእዉነት ድሮ ልጆች ሆነን ከምንሰማዉ ተረት በምን ይለያል? በእዉኑ ሰይጣንና እግዚአብሔርን ማስታረቅ ይቻላል? የገድሉ ደራሲ ግን ሰይጣን ነዉ እንጅ ያልተስማማዉ እግዚአብሄር ግን ለመታረቅ ተስማምቶ እንደነበረ ሳያፍር ጽፏል፡፡ በእዉነት አንዴ በሰራዉ ስራ ተመዝኖ ወደ ሲኦል የወረደን ነፍስንስ በዚህ መልክ ወደ መንግስተ ሰማያት ገባ ማለት በእግዚአብሔር ስራ ላይ መዘባበት አይሆንም? እግዚአብሔርን በጠባብ አዕምሮአችን እንደምናስበዉ አንወስነዉ፡፡ እርሱ የዩንቨርስ ሁሉ ፈጣሪ ነዉ፡፡ ሁሉን ነገር ኢትዮጵያዊ እያደረግን አሁንማ እግዚአብሄርም በኢትዮጵያ ምድር ብቻ የሚኖር እያስመሰልነዉ ነዉ፡፡ ለዚያም እኮ ነዉ በየትም አለም ተስምቶ የማያዉቅ ጉድ፣ ሰዉ እግዚአብሔርን ከሰይጣን ለማስታረቅ ሞከረ ተብሎ ለመናገር የተቻለዉ፡፡ ተስፋን ለማመስገን እወዳለሁ፡፡ ወደፊትም በርታ ፣ሌሎች ተጨማሪ የህዝባችንን ትክሻ ያጎበጡ ገደል ተብዬ የሐሰት ድሪቶዎችንም በማጋለጥ እንደምታስነብበን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
  ማስረሻ ይዘንጋዉ

  ReplyDelete
  Replies
  1. የምንከራከረው የቤተ ክርስቲያናችንና የአባቶች ትምህርት ስለሆነ ነው ፡፡ እስከ መጨረሻም ቢሆን የአባቶችን ትምህርት በአንዳንድ አወቅን ፣ ደረስን በሚሉ ዲያቆንና መሪጌታ ቃላት አንሽረውም ፡፡ ምናልባት እኒህ በየሥርቻው የሚጭሩ ሰዎች ዕድሜ ሰጥቷቸው ፣ በዕውቀጥትና በጥበብ አድገው ፣ በሃይማኖት ትምህርቱም ጐልምሰው ፣ አባትም ተብለው በአደባባይ ካስተማሩን ልንቀበላቸው እንገደድ ይሆናል ፡፡ ከዛ ውጭ ያለው ግን ቤተ ክርስቲያንን ማድማት ፤ ሃይማኖቷን ለመናድ የሚደረግ ትግል ፣ ለሆድ አዳሪነትን ነው የሚያመላክተው ፡፡ የጸሃፊዎችና የተመራማሪዎች የገቢ ምንጭ ከየት እንደሆነ በቅርቡ ከነማስረጃ በድረ ገጽ ቀርቦ አይተነዋልና ስለ ወንጌል ቃል መቆርቆር የሚለው ፣ የማደናቆሪያ ዘፈን ነው ፤ ወይም እናቱ ገበያ የሄደችበትን ህጻን እንደ ሞተችበት ያህል እንባ ማድረግ ነው ፡፡ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭው እንዲሉ አባቶች ፣ ስለ ሃይማኖት በመቅናት ሳይሆን ስለ ግል ጥቅማቸው የሚሯሯጡ ከርሳሞች በዘመናችን በዝተዋል ፡፡ በየትም ፣ እንደምንም ብሎ ብቻ ገቢን ማግኘትና ማሳደግ ነው ዓላማቸው ፤ ይኸኛው ደግሞ በተለይ ግዕዝ ቀመስና የቤተ ክርስቲያንን ምሥጢር በሚያውቁት ቀለማውያን ይብሳል ፡፡ ትምህርት ከላይ ወደ ታች መፍሰስ አለበት እንጅ በግልባጩ ከታች ወደ ላይ አያስኬድም ፡፡ ወጋችንም እምነታችንም ይኸን አካሄድ አይደግፈውምና በሁሎችም ዘንድ ሊታረም ይገባል ፡፡ ሃይማኖቴ ያገባኛል የሚል ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቷንና ዶግማዋን ጠብቆ ፣ መልዕክቱን ለሚመለከታቸው ብቻ ማቅረብ አለበት እንጅ ሃይማኖት በአድማና በቡድን ፍላጐት የተመሠረተች ይመስል ለማስተባበር መታገሉ ፈጽሞ አይሠራም ፡፡ በተረፈ ኢትዮጵያዊ የሆኑትን ቅዱሳን ለማያውቁ ፈረንጆች ላልከው ፣ እኛ የነሱን እንዳወቅንላቸው የኛንም ቢያውቁ የሚጠቀሙ ይመስለኛል ፡፡ አንተ የፈረንጆቹን “saints” ሰማያዊ አካላት አድርገሃቸዋል እንዴ ለመሆኑ ?
   እናም አልፎ አልፎ የጠቃቀስካቸው ሃሳቦች አንተም የእነርሱው ክፍል እንደሆንክ ይጠቁማሉ ፡፡ ለአጠቃላይ መልዕክትህ ግን ያለኝ አመለካከት ይኸን ይመስላል ፡፡

   Delete
  2. ኪዳን የሚለው ቃል ‹‹ቃል›› ከሚለው ጋር እየተዛረፈ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲሰ ኪዳን ደግሞ ከ32 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ ‹‹ኪዳን›› ቃሉ ‹‹ተካየደ›› ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹‹ምሕረት›› የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡

   ‹‹ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አድርጋለሁ›› ተብሎ በዳዊት መዝሙር እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደፊትም ያደርጋል፡፡ (መዝ88.3) ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡

   በቅዱሳን አበውና በቅዱሳት እማት እናቶች ታሪክ፣ ገድልና ድርሳን እንደምናነበው እግዚአብሔር ለቅዱሳን ከመሞታቸው አስቀድሞ ይገለጥላቸውና የምሕረት ቃል ኪዳን ይሰጣቸው ነበር፡፡ የእግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን በቅዱሳኑ ሕይወት ዙሪያ ብቻ የሚያተኩር አይደለም፡፡ ለስማቸው፣ ለመስቀላቸው፣ ለልብሳቸው ገድላቸውን ከትቦ ለያዘ መጽሐፍ፣ አልፎ ተርፎም ለረገጡትና አፈርና ለተጋደሉበት ቦታ ሁሉ ተርፎላቸዋል፡፡ ስለዚህ ልዩ ልዩ ቃል ኪዳን የተገባላቸው ቅዱሳት መካናት ሞልተዉናል፡፡

   ለቅዱሳን ከሞት አስቀድሞ የእግዚአብሔር መገለጥ ወይም የሚሞቱበትን ጊዜና የአሟሟታቸውን መንገድ ገልጦ መንገር በቅዱሳት መጻሕፍት የተለመደ ነው እንጂ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት ባለ አሟሟት እንደሚሞት ነግሮታል፡፡ (ዮሐ21.19 2ጴጥ1.14) ቅዱስ ጳውሎም ስለሚሞትበት ጊዜ ተነግሮታል፡፡ (የሐዋ20.25 የሐዋ21.10-13) ‹‹ከሞቱ አስቀድሜ እገለጥለታለሁ›› እንዲል፡፡ (ሰኔ ጎልጎታ)

   እግዚአብሔር ከሞታቸው አስቀድሞ በመገለጥ ለቅዱሳን የምሕረት ቃል ኪዳን የሚሰጣቸው በእነርሱ በጎ ሥራ ከእነርሱ በኋላ ያሉ የሰው ልጆችን ለመጥቀም ፈልጎ ነው፡፡ ተጠቃሚዎቹ ራሳቸው ናቸው እንዳይባል ወደ ሞት አፋፍ የተጠጉ ከመሆናቸውም ባሻገር ለቃል ኪዳን የበቁት የሚጠቀሙበት በጎ ሥራ በመሥራታቸው ነው፡፡ የሰው ልጆች ያለፉ ቅዱሳንን በመዘከር የቃል ኪዳናቸው ተጠቃሚ ሲሆኑ ቅዱሳኑ ግን ከመታሰብ በቀር በሰው በኩል የሚያገኙት ምንም ጥቅም የለም፡፡ ቅዱሳን የምሕረት ቃል ኪዳን ሲቀበሉ ለወገናቸው መትረፋቸውን ያመለክታሉ፡፡

   የምሕረት ቃል ኪዳን ለምን ያስፈልጋል ቢባል ሕግ መተላለፍ ካለ ሁልጊዜ ተጠያቂነት ወይም ቅጣት ይኖራል፡፡ ይህም በአዳም ይታወቃል፡፡ የሰው ልጆች ደግሞ ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርግ ፍጽምና ይዘው አይገኙም፡፡ በዚህ ምክንያት ቅጣት እንዳያገኛቸው የሚድኑበትን በርካታ መንገዶች እግዚአብሔር አዘጋጀ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡

   የምሕረት ቃል ኪዳን ሁሉ በጎ እንድንሠራ የሚያበረታታ ነው፡፡ ይህም ዘወትር ከቃል ኪዳኑ ጋር ተያይዘው በሚቀመጡ ግዴታዎች ይታወቃል፡፡ ለበጎ ሥራ ምክንያት የማይሆን ባዶ የምሕረት ቃል ኪዳን የለም፡፡ ‹‹ስምሽን (ስምህን) የጠራውን፣ ዝክር ያዘከረውን፣ የተራበ ያበላውን፣ የተጠማ ያጠጣውን፣ የታረዘ ያለበሰውን፣ እንግዳ በስምህ (በስምሽ) የተቀበለውን፣ ገድልህን ያነበበውን፣ የሰማውን፣ የተረጎመውን ወዘተ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ፣ እምረዋለሁ›› የሚሉ ቃል ኪዳናት በሙሉ ከባዱ መልካም ሥራ ባይቻለን እንኳን ቀላሉን መሥራት እንዳለብን ግዴታ የሚጥሉ ናቸው እንጂ አንዳንዶቸ እንደሚያስቡት መልካም እንዳንሠራ የሚያሳንፉ አይደሉም፡፡ ከዚህ ይልቅ ለበጎ ሥራ የሚያነሣሡና የታዘዙትን መሥራት ያልተቻላቸውን ሰዎች ተስፋ ሳይቆርጡ እስከመጨረሻው ሰዓት የሚድኑበት መንገድ እንዳለ አውቀው የተቻላቸውን እንዲያድርጉ የሚጠቁሙ ናቸው፡፡

   የእግዚአብሔር ቸርነት ከአእምሮ በላይ ነው፡፡ ይህም ሰዎች በእግዚብሔር ቸርነት ላይ በሚያነሡት ጥያቄ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ፡ እግዚአብሔር በዜና ገድላቸው እንደምናነበው ለብዙ ቅዱሳን ‹‹እስክ አሥር፣ ሠላሳ፣ ሃምሳ አምስት ወዘተ ትውልድ ድረሰ እምርልሃለሁ›› እያለ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን በማንበብ እምነት የጎደላቸው አንዳንዶች ‹‹ይህ እንዴት ይሆናል?›› እያሉ ይጠይቃሉ፡፡ ይህ ብቻ በራሱ የፈጣሪ ቸርነት ከሕሊና በላይ መሆኑን አያስረዳም?

   ፈጣሪ ስለ ፈራጅነቱና ስለ መሐሪነቱ ሲናገር ‹‹በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወዱኝ ትእዛዜን ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝ፡፡›› ይላል፡፡ (ዘጸ20.2-6) ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እስከ ሺህ ትውልድ የሚደርስ የእግዚአብሔርን ምሕረት በመናገሩ በአዋልድ መጻሕፍት ላይ ያለው የሠላሳና የሃምሳ ትውልድን ምሕረት የሚያወሳው ኃይለ ቃል ሊስተባበል አይቻልም፡፡ ያን ማክፋፋት ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደመቃወም ይቆጠራልና፡፡

   ዓለም ከተፈጠረች ሰባት ሺህ አምስት መቶ ዓመት ገደማ ሊሆናት ነው፡፡ የሰው ልጅን አማካይ እድሜ እጅግ አሳንሰን በመቁጠር የአንድ ትውልድ ዘመን ሠላሳ ዓመት ነው ብንል እንኳን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ያለው ትውልድ ከሁለት መቶ ሃምሳ አይበልጥም፡፡ በዚህ ዓይነት ደግሞ እስከ ዓለም ፍጻሜም ብንቆጥርና ብናሰላም የትውልድ ቁጥር እንኳን አንድ ሺህ ሊደርስ ወደ አምስት መቶም አይጠጋም፡፡ ነገር ግን ፈጣሪ የሚወደውና ትእዛዙን የሚጠብቅ እውነተኛ ሰው ከተገኘ ያን ያህል ትውልድ አይኖርም እንጂ ‹‹እስከ ሺህ ትውልድ›› ድረስ እንኳን ይቅር ሊል ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው የእግዚአብሔርን የቸርነት ስፋት ነው፡፡ ሺህ ትውልድ ስለሌለ እግዚአብሔር ሺህ ትውልድ ሊምር አይችልም አይባልም፡፡ ከዚህ አንጻር የፈጣሪን ቃል ኪዳን ከመሐሪነቱ አንጻር እንጂ ከተፈጻሚነቱ አንጻር ሊመለከቱት አይገባም፡፡

   ፈጣሪ ለቅዱሳኑ በየዕለቱ ብዙ ነፍሳትን ከሲዖል እንዲያወጡ የምሕረት ቃል ኪዳን ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ የተሰጣቸውም ቅዱሳን አሉ፡፡ ነገር ግን ተፈጻሚነቱን ስንመለከት በቀን የተባለውን ያህል ነፍሳት ከሲዖል ሊወጡ ወይም አንድም ነፍስ ከሲዖል ላትወጣ ትችላለች፡፡ ይህ ግን በተገባላቸው ቃል ኪዳን ላይ ምንም ዓይነት አሉታ የለውም፡፡ ምክንያቱም ለቅዱሳኑ ይህ ቃል ኪዳን ሲሰጥ ሲዖል ካለችው ነፍስ ደግሞ የሚጠበቅ ነገር ይኖራልና፡፡ ያን የምታሟላ ነፍስ ካልተገኘች ቃል ኪዳኑ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ ይህም በመሆኑ ቃል ኪዳኑ ከንቱ ነው አይባልም፡፡ ከላይ እንዳየነው ተፈጻሚ ሊሆን ባለመቻሉ ብቻ ለሺህ ትውልድ የተገባው ቃል ኪዳን ከንቱ ነው ሊባል አይቻልምና፡፡
   ክርስቶስ ሳምራ በቃል ኪዳኗ አትለየን!!!

   Delete
  3. girum ena dink meleekit new. Amilak yabertachihu.tekawamiwochachihun atitilu.yeenesu menor leenanite birtat newina.God bless u!!

   Delete
 22. ለአባታችን አብርሃም ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ክዋክብት አበዛሃለሁ፤ ስንት ማለት ይሆን?
  ጉደኛው ተሐድሶ መናፍቃን

  ReplyDelete
  Replies
  1. የአብርሃም ዘር ቢሊየን ጊዜ ቢሊየን ሊሆን ይችላል። ልክ እንደዚሁ በቁጥር ስሌት የክርስቶስ ሰምራን የዓለማቱን ዝናብ ያህል ሰው ከሲኦል እንድታወጣ ሲፈቀድ መቀበል ይገባችኋል ማለትህ ነው። አንተ ያቀረብከው ሎጂክ ወይም ሥነ አመክንዮ፤ ቨርባል ፋላሲ/ verbal fallacy/ እድሜ በመመዘን እና የኮንቨርስ ፋላሲ /converse fallacy/ ሁሉን በአንድ የመጠቅለል ስሌታዊ ውጤት ለማሳመን የመሞከር አባዜ ነው።
   ለአብርሃም እንደአሸዋ አበዛልሃለሁ ያለውን ቃል የምንቀበል ከሆነ ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ሃሳቦች ባገኘን ቁጥር ሁሉ መቀበል አለብን። ምክንያቱም ለአብርሃም የተነገረው ቃል ለሁሉም ጽሁፍ ማረጋገጫ መሆን ይችላልና ነው እያልክ የምትከራከረው።
   የሰው ልጆች በሁለት እጆቻቸው ላይ አስር ጣት እንደሚኖራቸው ይታመናል። ስለዚህ የሰው ልጆች ሁሉ አስር ጣት በሁለት እጆቻቸው ላይ አላቸው። /ይህ ሁሉን በአንድ የመጠቅለል ስሌት «አብርሃም እንደአሸዋ ቁጥር ዘሩ እንደሚበዛለት ከተነገረ፤ ለክርስቶስ ሰምራም እንደዚሁ ተነግሯል ማለት ነው» ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ለአንዱ ሰው የተናገረውን ለሁሉ ሰው እንደተነገረ ማሰብ ትክክል አይደለም።
   እንደዚሁ ሁሉ ለምሳሌ « አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 1000 ዓመት እድሜ ያለውና የትምህርት ጥራቱም አስተማማኝ ነው» ብንል እንደዚሁ ሁሉ 1000 ዓመት ያላቸው ዩኒቨርሲቲዎች በጠቅላላው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጥራት እኩል ናቸው» ማለት እንዴት ይቻላል?
   ስለዚህ እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ቃል ኪዳን የእግዚአብሔርን ቻይነት ስለሚያሳይ በተመሳሳይ መልኩ ለክርስቶስ ሰምራ የተሰጠውም ቁጥር ትክክል ነው ብለህ መቀበል አለብህ የሚል ስነ ሞገት መቅረቡ አስገራሚ ይሆናል።
   የማይነጻጸረውን ለማነጻጸር የመሞከር ኢ- ተነጻጻሪ ስነ ሞገት ከላይ ባቀርባናቸው ሎጂክ መሰረት ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው።
   አብርሃም በምድር ላይ ስለሚወለዱ የዘሩ ብዛት የተነገረውን ቁጥር ክርስቶስ ሰምራ ከሲኦል ከምታወጣቸው ሰዎች ጋር እንዴት ሊነጻጸር ይችላል? በምድርና በሲኦል፤ በመውለድና በማዳን፤ በሕይወትና በሞት መካከል ምንም ዓይነት ዝምድና የሌለውን ነገር በቁጥር ተጠግቶ ማመሳል እብደት ነው።
   ስለዚህ ለአብርሃም ዘር መብዛት ለክርስቶስ ሰምራ ከሲኦል ማውጣት በቃሉ፤ በይዘቱ፤ በሃሳቡና በትርጉሙ መካከል ምንም መመሳሰል ሳይኖር «አበበ ሰው ነው፤ በሁለት እጆቹም ላይ አስር ጣት አለው፤ ስለዚህ ሰው ሁሉ በሁለት እጆቹ ላይ አስር ጣት አለው» ብለህ ማመን የግድ ይሆናል» ማለት የጤንነት አይደለም። ምክንያቱም የጣት ቅጥያም ይሁን በየምክንያቱ የጣት መጉደል ያላቸው ብዙ ሰዎች ስላሉ ሎጂኩ ተቀባይነት የለውም። ስነ ሞገቱን ተከራካሪዎች የሚያቀርቡት ያነሱትን ሃሳብ ለማሳመኛ ሲጠቀሙ ይሄ ትክክል ከሆነ፤ ያኛውም ትክክል መሆን አለበት ከሚል የተቃርኖ ንጽጽር ስለሚነሱ ነው። አበበ ሰው ከሆነ፤ በእጆቹ ላይ ዐሥር ጣት ካለው፤ ከሰዎች ሁሉ ዘንድ እንደአበበ መጠበቅ አንጻራዊ ነው። ተቃርኖው ግን ሌሎች ልክ አበበን መሆን አለመቻላቸው ነው።
   እንደዚሁ ሁሉ ለአብርሃም የተነገረውን ዓይነት ቃል እግዚአብሔር ለሌሎች የማይናገርበት ምክንያት እንደሌለ ይታመናል። ይህንን የታመነ ቃል ይዘህ በምትፈልገው ሃሳብ ውስጥ በመጠቀም እግዚአብሔር ተናገረው ልትል አትችልም።
   አንዳንዶች ሎጂካል ፋላሲን ወደ ሃይማኖት በማምጣት መጠየቅ ሳይሆን እንዳለ «አዎን» ብሎ ማመን ነው ይላሉ። ግን ይህም ውሸት ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ሥነ አመክንዮን /ሎጂክ/ በመጠቀም ያስተምር እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
   ፈሪሳውያን፤ ክርስቶስ ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ሲል ለመስማትና ለመክሰስ ፈልገው በማድነቅ ስሜት «በምን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ?» ሲሉት ያቀረበላቸው ሃሳብ እኔ ለጥያቄአችሁ እንድመልስ አስቀድማችሁ «የዮሐንስ ጥምቀት ከምድር ናት ከሰማይ?» ለዚህ መልስ ስጡኝ! ሲላቸው ከምድር ናት ብንል የዮሐንስ ደጋፊዎች ይገድሉናል፤ ከሰማይ ናት ብንል ታዲያ ለምን አላመናችሁትም ስለሚለን አናውቅም እንበለው በማለት ተመካክረው በተናገሩት ጊዜ «ኢየሱስም በማን ስልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም» እንዳላቸውና ወደመጡበት እንደመለሳቸው ወንጌል ይናገራል።
   ሎጂኩ፤ 1/ ለመጡበት የክፋት ሃሳብ ምላሽ ማሳጣት
   2/ የማያምኑ መሆናቸውን መግለጥ ሲሆን
   የመለሰላቸው ግን ሃሳባቸውን ወደ ዮሐንስ የሕዝብ ቁጥር ውስጥ በመክተት ነበር።
   /የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ወይስ ከምድር?/ ሲል ፈሪሳውያኑ ሊከራከሩ የሚችሉትና በክፋት ሃሳባቸው ግጭት ውስጥ የሚገቡት ከክርስቶስ ጋር ሳይሆን ከዮሐንስ ደጋፊዎች ጋር ነው። አዎ ከሰማይ ናት ብለው ከዮሐንስ ደጋፊዎች ጋር መቀላቀል ወይም ከምድር ናት ብለው ከዮሐንስ ደጋፊዎች ጋር መጋጨት ነበር ያላቸው አማራጭ።
   ይህም /naturalistic fallacy/ ይሰኛል። በአጭሩ የመንፈሳዊ ሕይወት ህክምና ዶክተር የሆነው ዮሐንስ እየሰጠ ያለው የመድኃኒት ቃል ያድናል፤ አያድንም? ነበር ጌታ የጠየቃቸው። ያድናል ካሉ መታከም፤ አያድንም ካሉ ደግሞ ከዳኑት ታካሚዎች ጋር መቃረን ስለሚሆን ያድናልም ፤ አያድንምም ሳይሉ በሽተኞቹ ፈሪሳውያን ተመልሰዋል።
   ስለዚህ ስነ አመክንዮ የወንጌል ቃል ስለሆነ አንዳንድ ፈሪሳውያን ሰዎች ጠማማ ሃሳብ ይዘው በመምጣት በመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ውስጥ ለመደበቅ ሲፈልጉ በመንፈሳዊ ስነ አመክንዮ እንደፈሪሳውያኑ ልናሳፍራቸው መብቱ አለን።
   ከዚህ አንጻር ከላይ ያለው ፈሪሳዊው ሰው በአብርሃም የዘር ብዛት ያህል፤ የክርስቶስ ሰምራን የማዳን ብዛት ለመሸሸግ ሲፈልግ የአብርሃም ዘርን ምድርን ስለመሙላት ተነግሯል። የዚያኑ ያህል ነፍሳት በክርስቶስ ሰምራ በኩል ከሲኦል ማዳን ከተቻለ ሲኦል ለምን ታስፈልጋለች? የጌታስ ፍርድ ለማን ይሆናል? የሚኮነንስ ማን ሊሆን ነው? እምነትስ ጥቅሙ ምንድነው? ለሚሉ መጠይቆች መልስ መስጠት የግድ ይላል።
   ሌላው የማጠቃለያ ነጥብ የሚነሳው ደግሞ እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረው ቃል የሚገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው። ቃሉን የእግዚአብሔር እስትንፋስ መሆኑን የሚያምን የዓለሙ ሁሉ ክርስቲያን፤ በክርስቶስ ሰምራ ገድል ላይ ያለውን የዓለሙ ሁሉ ማንኛውም ሰው ከሲኦል እንደሚወጣ ሳያውቀው ለአብርሃም ከተነገረው ቃል ጋር እንዴት የእግዚአብሔር እስትንፋስ ነው ይቀበለዋል? ልክ ለአብርሃም እንደተሰጠው ቃል ፤ ዓለሙ ሁሉ ከክርስቶስ ሰምራ ገድል ጋር መተዋወቅ አለበት። ምክንያቱም ለአብርሃም ከተሰጠው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል በላይ ከሲኦል የሚታደግና ዋስትና መስጠት የሚችል ገድል ማጣት ስለሌለበት። ለአብርሃም የተነገረው ምድራዊ ብዛትን ነው። ገድሉ ግን ከሲኦል የሚታደግ ስለሆነ መታወቅ ያለበት ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ መሆን ሲገባው እስካሁን በኢትዮጵያ እንኳን እስላምና አረሚው፤ ኦርቶዶክሱም ብዙ አያውቀውም።
   ስለዚህ መንፈሳዊ ኃይልና ከመጽሐፍ ቅዱስ በላይ መከበር የነበረበት ከሲኦል የሚታደግ መጽሐፍ ለምን ይሆን እንደመጽሐፍ ቅዱስ ቦታውን በዓለም ውስጥ ያላገኘው? ይህም መልስ ያሻዋል።
   ምክንያቱም ከሲኦል ከመዳን የበለጠ ነገር ለፍርድ የተገባቸው ሰዎች ተስፋ የሚሆን ነገር ስለሌለ። ገድሉ የሚሰራው ለዓለሙ ሁሉ ነው ወይስ ለአበሻ ብቻ?

   Delete
  2. የተስፋን ጽሁፍ ጠቅለል አድርገን ስንመለከት የሚያስረዳን ፣ በእምነታችን ስንጸና የሚያስገኝልን ትሩፋት እንደሚኖር ነው ፡፡ ክርስቶስ ሰምራ በፈጣሪዋ ታምና ሥጋዋ እስከሚበሰብስና የዓሣ መተላለፊያ ቦይ እስከሚሆን መታገሷን /ፈተናዋን በጽናት እንዳጠናቀቀች/ ካስረዳን በኋላ ፣ እግዚአብሔር ደግሞ ቅድስናዋንና ተጋድሎዋን ለሚያምኑ ወገኖች ምህረትን እንደሚሰጥላት ቃል እንደ ሰጣት አስተምሮናል ፡፡

   የቁጥሩ ሂሳብ ወይም ስሌቱ የሚነሳው ፤ በዛ አነሰ ፣ ትክክል ነው ወይስ አይደለም የሚባለው በተራዳዒነቷ ስንት ሰው እንደ አመነ ሲታወቅ ነው ፡፡ ያላመነባት የሰው ዝርያ ሁሉ ከዚሁ ከቃል ኪዳኑ ውጤት ተቋዳሽ ስለማይሆን ሊቆጠር አይችልም ፡፡ እንደ ተረዳሁት ይኸ ለአንባቢ ያስጨንቀ ቁጥር መጠቀሱ በጥሞና ስንመለከተው እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ የሚሰጠው የጸጋ በረከት ጥቂት እንዳልሆነ ፣ ተሰፍሮ ፣ ተቆጥሮ ፣ ተለክቶ አለመሆኑንና ፣ ያልቅባቸዋል ወይም እስከ አሁን ጨርሰውት ይሆናል የሚል ፍርሃትና ጥርጣሬ በአማንያን መሃል እንዳይፈጠር ፤ ገደብ የለሽነቱን እንደሚገልጽ ነው ፡፡ መጠኑንም ሳይገልጽ በተራዳዒነትሽ ለሚታመኑ በማለት ሊያስቀምጠው ይችል ነበር ፤ ነገር ግን እንደተገለጸለት ጽፎታል ፡፡

   በተረፈ ሌላው ዓለም ለምን አልደረሰውም የሚለው ጥያቄ የቋንቋ ግርዶሽ በመሃከላችን ስላለ ብቻ ነው ፡፡ አንተም እንደጠቀስከው ኢትዮጵያዊው እንኳን ይኸን ምሥጢር ጠንቅቆ አያውቀውም ፤ ለምን ቢባል ? የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍት በግዕዝ ተጽፈው ስላሉ ተራው ምእመን ቢያነባቸውም ስለማይረዳቸው ነው ፡፡ እንዲህ እንደ ተስፋ ያሉ ግዕዝ ቀመስ ወጣቶች ለመጐንተልም ሆነ ለሌላ ምክንያት ሲተረጉሙት ያልሰማው ሁሉ ምሥጢሩን ይረዳል ፤ ወደፊት ምን ማድረግ እንደሚገባውም ይማራል ፡፡ ሌላው ወገንም ደግሞ የቤተ ክርስቲያን የተደበቀ ትምህርቷ ተጋለጠ በማለት ይጫፈራል ፡፡ እናም ተስፋ ሁለቱንም ወገኖች ጠቅሟል ፡፡ በተረፈ ጊዜውን እግዚአብሔር ሲፈቅድ እንደ ሄኖክ መጽሐፍ ዓለምም እያስተረጐመ ማንበቡና ይኸን የቅድስና በረከት መጋራቱ እንደማይቀር ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ እስቲ አንተው ፣ እንደ ሎጅኩ የባዕድ ቋንቋውን በደንብ ተራቀህበት ከሆነ ፣ ተርጉምና በድረገጽ እንኳን አስነብባቸው ፡፡ ዓመት ሳይሞላ አገራችን በጐብኝ ብዛት ትጥለቀለቅልህ ነበር ፡፡

   Delete
 23. Please do not miss the symbolism type of literature that we have. when it is expressed in «ጌታም ተናገራት እንዲህ አላት በአራት ወር ውስጥ በየቀኑ የሚወርደውን የዝናም ነጠብጣብ ያህል ነፍሳትን አሥራት ሰጥቸሻለሁ» it means that the promise that Our Lord Jesus gives will be for all those countless of peoples who believe in the promise that he gave to her. Let me ask you a question, what does it mean when Our Lord promise Abraham that " your children will be as the number of stars in the sky and as countless as the sand at the shore? Should we take the meaning literally? Do you know the number of stars in the sky, there number is in trillions times trillions (you can read science magazines), but do you think the number of people created till now reaches this size?? If not why Does Our Lord God said this. (It is symbolism)

  A

  ReplyDelete
  Replies
  1. you missed the point, how come you compare Abrahams promise with hers. First Abraham's promise is biblical and it is logical and is about having his genetration multiplied and spritualy who ever belives in the son of God will be coniderd to be included in Abaraham's spritual children. That happend in the past and is happening now and we can prove it. What I am saying is who wrote የክርስቶስ ሰምራና ሌሎች መሰል ገድል. just give me someone in the history of holy church. Who had that grace to see her and God talking to be a witness to write this. If this is true it should be included in the holy bible as one of revilation. If this is true we don't have to be ashemed of it and hide it in Ethiopia. Let the world knows the truth. Who is the original writer who is capable of being selected to be a witness.

   Delete
  2. wow you said agood point"Who had that grace to see her and God talking to be a witness to write this" that is interesting question but z queston is for you let me ask you as you before who had that grace to see abraham&god talking to be awitness to write about abraham????????

   Delete
 24. To be part of those who are given to Kirstos Semera, first you should belive in it. So don't worry - SIOLe will not be empty as there will be peopel like you.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you brother for judging me and put me in SIOLe, but refuse to believe your word and I rely on and I believe in the Son of God and the powerful sacrifice made for me and the power of his blood. I stongly give priority to the word of God than other writings which might not be true at all. I realy don't have to believe Kirstos Semera. Our Lord is enough for my salvation. Thank you anyway

   Delete
  2. Do you think with out the son of God , the door for heaven will open?

   Delete
 25. Please, as a literary production try to understand the symbolism and the mysticism in the Ethiopian hagiographies. Even the Bible is full of symbolism and mystical expressions. If we read those symbolic and mystical expressions literally they don't make sense at all. That is why the fore father's of the Holy Apostolic Catholic Church like Origen, St. Augustine, St. Ephraim, St. Cyril, etc. followed the allegorical way of interpreting the scriptures.

  Otherwise, we can't answer the questions like what is hell? What is paradise? what does "ዘዐይን ኢርእየ፤ ወእዝን ኢሰምዐ፤ ውስተ ልበሰብእ ዘኢተኀለየ" mean? We have to start thinking about symbolism very seriously.

  Of course, if any book doesn't go along with the Bible it should be discarded from the list of spiritual books. However, who is the one that is responsible to make such a decision? It is not bad to question whether a Book is inspired by the Holy Spirit or not for that is how Our forefathers distinguished the inspired ones from the uninspired writings. Yet, it should be in spirit of humility, humbleness and openness. Unless we speak to each other in humble spirit we can never find the way of the Lord for He is humble.

  Moreover, the final decision over a book's being useful for spirituality or not should be given by the Holy Synod of the Church.Your Synod may be weak but you can't make it stronger by taking decisions into your own hands. The History of the Western Church tells us a lot. History is written for us to learn from it.

  The Problem with the Eastern Church is that they don't stand together.They can't even help each other as Christians. Look what is happening in Jerusalem at Der Sultan. They are highly burdened with feelings of nationalism and patriotism which have less to do with Christianity. Each and every one of them are highly burdened with their national flags and identity. Particularly Ethiopians are almost sacrificing Christianity to national identity.

  People, let us get out of our boxes of nationality. What your church needs is theologically educated and spiritually awake people at the Synod, who can make decisions based on theological and spiritual backgrounds. Otherwise your house will be a dilapidated one for you are all busy in fighting each other. Learn from the western church. It was just like you some centuries back. And that costed them a lot. Now Christianity is considered as backward thinking among many Europeans. Atheism is spreading fast. The clergy and the bishops now regret for what was happening in their church for hundreds of years and now they are trying to correct those errors. Now they are getting stronger and stronger, thanks to God. Establish your clergy with knowledge of what Christianity is: Our identity. We are universals. Yet we have countries to live by. I had a lot to say guys. But...

  ReplyDelete
  Replies
  1. መልካም ምልከታ
   who is the one that is responsible to say a book is spiritual or not?

   Delete
  2. Anyone can claim a particular book to be "spiritual." However, that claim should be certified by the Church after thorough investigation by her theologians. The problem with the Ethiopian church is lack of theological knowledge among most of the clergy. That is what makes the church to be led by lay groups of young people who are filled only with zeal. Zeal is not by itself bad. Nevertheless, it can be so destructive if not controlled and guided by knowledge.

   A zealous person will cherish everything he finds in the church. Try to defend whatsoever he found in the church from any kind of change. He is determined to die as well as to kill for what he thinks is the church's treasure. He doesn't distinguish between the essential and the peripheral matters.
   As of my understanding, this is the sentiment that we see among many Ethiopians. Most of them have no theological hint, let alone the perplexity and complexity the discipline has. Yet, they are so zealous about their church. They will die for the church or kill, if they think that the church is threatened by anyone. Unfortunately, this zeal could have been used in a positive way if the leaders were dedicated to the church in knowledge and spirituality. But the synod is highly politicized. Most of the bishops are not that knowledgeable; and those who are knowledgeable are extremely afraid not to be labeled as heretic by the populist and opportunist bishops and their vanguards.

   You can see how Abba Paulos was labeled as a heretic by the late Aleqa Ayalew (may the Lord rest his soul in peace) and MK. You can also call to memory how the late Abba Merhakristos was targeted. We can also call to our memory what recently has been written on Deje Selam about Reverend Dr. Merawi Tebeje. My father told me that the late Abuna Teophlos was also labeled as a non-orthodox by some people. Some years back, I do also remember the American synod's Abba Melchizedek to be labeled by MK as heretic on Sm'aa Tsdq newspaper. We all also know what happened to Abba Woldetnsae. These people and many others like them today could have changed the church. But the change resistant culture in the church and its fruits have completely but unproductively blocked them. (I wonder what Abba Gorgorios would have said if he was alive today.)
   It is because of these two main factors- the politicization of the synod and the lack of knowledge among the bishops and most of the clergy in the church- that led the church to fall in the hands of young people who are zealous but ignorant in theological matters.

   As someone said somewhere on the internet, in Ethiopia Christianity has now come to be a mere culture not a way of life. It is easy to see the people trying to satisfy God with some kind of formula. You will see people fasting from the stomach while their tongues are inflamed with insulting each other. You will see icons almost in each and every taxi in Addis while the chauffer and the assistant driver rob people by making them to pay more than the tariff. To me, this is a joke on Christianity: the new covenant by works of mount Calvary.

   Delete
  3. በጥያቄዬ መሠረት ሃሳብህን ስላካፈልከኝ አመሰግናለሁ ፡፡

   Delete
  4. Please! you comment almost an article , where are you? It is my first time to read such kind of useful article, which is telling the problem and as well as the solution to our church. God bless you!

   Delete
  5. Thank you for your kind words if they are candid. Knowing me in person will not contribute that much. But let's say that I used to be one among the zealous group. So I know what it feels to be filled with simple zeal. Simple zeal is always simple. Just simple.

   If you think the points I raised are useful, please translate it in to Amharic and share it with people. God willing, I will continue writing what I think will be useful to the Ethiopian church.

   Selam

   Delete
 26. Life: when it is purposeless, it is meaningless, when it is meaningless it is worthless.

  ReplyDelete
 27. ገድል አንባቢዎች ምነው በዙ?ምናልባት በገድል አንባቢነታቸው ገንዘብ አጠራቅመው ከተማ ውስጥ
  ሕንፃ ገንብተው ይሆን? ቢሆን ነው እንጂ ባይሆን ኖሮ ዳዊት ደጋሚ ይመስል ገድል አንባቢ እንዲህ
  ከመጠን ባላለፈም ነበር፤ ምን ይደረግ የዋህ ብእሲ ኩሎ ዘነገርዎ የአምን ያነንም ይህነንም ያልተረዳ የነገሩትን ሁሉ ይቀበላል እንደሚባለው በዚህ ወገን ላይ አደናጋሪዎች እየመጠቁ እየነጠቁ ሂደዋል፤
  ውሎ አድሮ እውነተኛው ፈራጅ ለተፈራጁ ወገን እውነተኛ ፍርድን ይፈርዳል እግዚአብሔር እግዚ'እ
  መስተበቅል እርሱ በስውር ሳይሆን በይፋ የሚበቀል መሆኑ ግልጽ ነው፤

  ReplyDelete
  Replies
  1. በወልድ ዋሕድ በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተገለጠው ፍቅርና የተሰጠው መዳን ለሰው ልጆች ሲገለጥና በተግባር ሲተረጎም የኖረው በቅዱሳን ሕይወት ነው፡፡ ይህም ሕያው ወንጌል የሆነው ሕይወታቸው ነው፡፡

   የቅዱሳን ሕይወት የነገረ መለኰታዊ አስተምህሮ መገለጫውና መታወቂያ ፍሬው ነው፡፡ ነገረ መለኰታዊ አስተምህሮ በራሱ ብቻ ግብ የሚሆን ሳይሆን ወይም ለማወቅ ብቻ ተብሎ የሚደረግ ሳይሆን ዋናው ዓላማውና ግቡ በቅድስና ሕይወት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ መንገዱን እንዲያሳየንና እንዲረዳን ነውና፡፡

   የቅዱሳን ሕይወት በክርስቶስ ላለው ሕይወት ሕያውና ተግባራዊ ምስክር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ከስሙ ጀምሮ ክርስቶስን የተሸከሙ፣ የክርስቶስ ማደሪያዎች ናቸው፡፡ እኛን ክርስቲያን ያስባለን እርሱ ክርስቶስ ተብሎ ነውና (ክርስቲያን ማለት ዘክርስቶስ - የክርስቶስ የሆነ ማለት ነውና)፡፡ ቅዱሳን ደግሞ ከክርስቲያኖች ወገን ሞትን ድል አድርጎ በተነሣውና ለዘለዓለም ሕያው በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው የተቀደሰ እምነት ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ፍጹማን ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የእነርሱ ሕይወታቸው በሙሉ የክርስቶስ ሕይወት ነው፣ ሃሳባቸውም እንዲሁ የክርስቶስ ሃሳብ ነው፡፡ በእነርሱ ያለው ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ እነርሱ ከክርስቶስ ውጭ ከራሳቸው ለራሳቸው የሆነ ነገር የላቸውም፡፡ ቅዱሳን በክርስቶስ ይኖራሉ፣ ክርስቶስም ደግሞ በአባታዊ ቸርነቱና በጸጋው በእነርሱ አድሮባቸው ይኖራል፡፡

   የቅዱሳን ሕይወት በክርስቶስ ላለው ሕይወት ምስክር ብቻ ሳይሆን በምድር ላይ የክርስቶስ ሕይወት ቀጣይ አካል ተደርጎ ሊወሰድም ይችላል፡፡ የቅዱሳን ሕይወት የክርስቶስ ሕይወት በእያንዳንዱ ቅዱስ ላይ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የተገለጠው መገለጥ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንደ እውነቱ ሲታይ ኦርቶዶክሳዊ የክርስትና ሕይወትን ከቅዱሳን የሕይወት ምስክርነት ነጥሎ ማየት አይቻልም፡፡ በወልድ ዋሕድ በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተገለጠው ፍቅርና የተሰጠው መዳን ለሰው ልጆች ሲገለጥና በተግባር ሲተረጎም የኖረው በቅዱሳን ሕይወት ነው፡፡ ይህም ሕያው ወንጌል የሆነው ሕይወታቸው ነው፡፡ በመሆኑም ሕያው ምስክር ሆኖ ኢአማንያንን ሲያሳፍራቸው፣ ምእመናንን ደግሞ ሲያጸናቸውና ሲያጽናናቸው ኖሯል፡፡ ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስና የማዳኑ ሥራ አማናዊነት ማረጋገጫዎችና ማሳያዎች ናቸው፡፡

   ሐዋርያው የቀደሙትን ቅዱሳን ተግባራቸውን ጠቅለል እያደረገ ከገለጸ በኋላ “እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን … ” ያለው ለዚህ ነው፡፡ እነዚያ ሁሉ ቅዱሳን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋና እውነት ሲሉ ያን ሁሉ መከራ በሕይወታቸው መቀበላቸውና በሞታቸው ሳይቀር መመስከራቸው አስቀድሞ በአበውና በነቢያት በኩል ተስፋውን የገለጠውና የሰጠው፣ ኋላም ሰው ሆኖ ያንን ታላቅ ተስፋ በተግባር የፈጸመው እርሱ እውነተኛና የታመነ ስለ መሆኑ መመስከራቸው ነው፡፡ አንድ ነገር ብዙ የታመኑ ምስክሮች ባሉት መጠን የበለጠ ተአማኒ እንደሚሆነው ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል ለፈጸመውና ላዘዘው ነገር እውነተኛነት የቅዱሳን ሕይወት አማናዊ ምስክር ነው፡፡ ራሱ ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን “ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” ብሏቸዋል፡፡ ስለሆነም ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በየዘመናቱ በመስቀሉ ካፈራቻቸው ቅዱሳን ልጆቿ ነጥለን እናስባት ብንል የሚቻል አይሆንም፡፡ ባለቤቱ ክርስቶስ “እኔ የወይን ግንድ ነኝ፣ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ” ያለው ይህን እውነታ የሚያስረዳ ነው፡፡

   የቅዱሳን ሕይወት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ወደ አባቱ በማረጉ ወይም ደግሞ በደቀ መዛሙርቱ ሞት ምክንያት በምድራችን ላይ ተቋርጦ ያልቀረ ለመሆኑ ተግባራዊ ምስክርነቱን ይሰጣል፡፡ በቅዱሳን ሐዋርያት ሲሠራው የነበረውን ሥራ በየዘመናቱ በተነሡ ቅዱሳን አማካይነት እንደየ ጸጋቸው ሲሠራው ኖሯልና፣ ወደፊትም ይሠራዋልና፡፡ እርሱ ሥራውን እስከ ዛሬም ድረስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኩል በቅዱሳኑ አማካኝነት ይቀጥላል፡፡ ስለሆነም የቅዱሳን ሕይወት የመድኃኒታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወትና ትምህርት የሚገልጥና የዚያ አካል ስለሆነ የቅዱሳንን ሕይወት ማንበብ፣ መጻፍና ማወቅ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተገቢ ተግባሯ ነው ማለት ነው፡፡

   በተለይም ደግሞ የቅዱሳን ሕይወት ላይ ላዩን የሚያነቡ ሰዎች የማያዩትና የማይደርሱበት ጥልቅና ረቂቅ የሆነ ጥበብን የያዘ ነው፡፡ የቅዱሳንን ሕይወትና ትምህርት ስንማርና ስናስብ በማስተዋል መንፈስ ሆነን ሊሆን ይገባል፡፡ አባባላቸውና ትምህርታቸው ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ካላቸው ረቂቅ ተዋሕዶና ጥልቅ ከሆነ መንፈሳዊ የሕይወት ልምዳቸውና ተሞክሯቸው የተወሰደ ስለሆነ እንደ ሰማን ወይም እንዳነበብን ወዲያዉኑ ከመተቸትና አስተያየት ከመስጠት ልንቆጠብ ይገባል፡፡ ሁሉን ነገር በእኛ የእውቀትና የመረዳት ችሎታና ደረጃ ብቻ መመዘንና መወሰን የለብንም፡፡ አንዳንድ ጊዜ አባባላቸው ግራ የሚያጋባ ወይም ተቃርኖ ያለው መስሎ ቢሰማን እንኳ ጊዜ መስጠት፣ አለበለዚያም ዝም ብሎ ማለፍ ይገባል እንጂ “እንዴት እንዲህ ይባላል?” ወደሚል አላስፈላጊ ሒስ ወይም ነቀፋ ውስጥ መግባት የለብንም፡፡

   Delete
  2. በወልድ ዋሕድ በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተገለጠው ፍቅርና የተሰጠው መዳን ለሰው ልጆች ሲገለጥና በተግባር ሲተረጎም የኖረው በቅዱሳን ሕይወት ነው፡፡ ይህም ሕያው ወንጌል የሆነው ሕይወታቸው ነው፡፡

   የቅዱሳን ሕይወት የነገረ መለኰታዊ አስተምህሮ መገለጫውና መታወቂያ ፍሬው ነው፡፡ ነገረ መለኰታዊ አስተምህሮ በራሱ ብቻ ግብ የሚሆን ሳይሆን ወይም ለማወቅ ብቻ ተብሎ የሚደረግ ሳይሆን ዋናው ዓላማውና ግቡ በቅድስና ሕይወት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ መንገዱን እንዲያሳየንና እንዲረዳን ነውና፡፡

   የቅዱሳን ሕይወት በክርስቶስ ላለው ሕይወት ሕያውና ተግባራዊ ምስክር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ከስሙ ጀምሮ ክርስቶስን የተሸከሙ፣ የክርስቶስ ማደሪያዎች ናቸው፡፡ እኛን ክርስቲያን ያስባለን እርሱ ክርስቶስ ተብሎ ነውና (ክርስቲያን ማለት ዘክርስቶስ - የክርስቶስ የሆነ ማለት ነውና)፡፡ ቅዱሳን ደግሞ ከክርስቲያኖች ወገን ሞትን ድል አድርጎ በተነሣውና ለዘለዓለም ሕያው በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው የተቀደሰ እምነት ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ፍጹማን ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የእነርሱ ሕይወታቸው በሙሉ የክርስቶስ ሕይወት ነው፣ ሃሳባቸውም እንዲሁ የክርስቶስ ሃሳብ ነው፡፡ በእነርሱ ያለው ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ እነርሱ ከክርስቶስ ውጭ ከራሳቸው ለራሳቸው የሆነ ነገር የላቸውም፡፡ ቅዱሳን በክርስቶስ ይኖራሉ፣ ክርስቶስም ደግሞ በአባታዊ ቸርነቱና በጸጋው በእነርሱ አድሮባቸው ይኖራል፡፡

   የቅዱሳን ሕይወት በክርስቶስ ላለው ሕይወት ምስክር ብቻ ሳይሆን በምድር ላይ የክርስቶስ ሕይወት ቀጣይ አካል ተደርጎ ሊወሰድም ይችላል፡፡ የቅዱሳን ሕይወት የክርስቶስ ሕይወት በእያንዳንዱ ቅዱስ ላይ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የተገለጠው መገለጥ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንደ እውነቱ ሲታይ ኦርቶዶክሳዊ የክርስትና ሕይወትን ከቅዱሳን የሕይወት ምስክርነት ነጥሎ ማየት አይቻልም፡፡ በወልድ ዋሕድ በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተገለጠው ፍቅርና የተሰጠው መዳን ለሰው ልጆች ሲገለጥና በተግባር ሲተረጎም የኖረው በቅዱሳን ሕይወት ነው፡፡ ይህም ሕያው ወንጌል የሆነው ሕይወታቸው ነው፡፡ በመሆኑም ሕያው ምስክር ሆኖ ኢአማንያንን ሲያሳፍራቸው፣ ምእመናንን ደግሞ ሲያጸናቸውና ሲያጽናናቸው ኖሯል፡፡ ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስና የማዳኑ ሥራ አማናዊነት ማረጋገጫዎችና ማሳያዎች ናቸው፡፡

   ሐዋርያው የቀደሙትን ቅዱሳን ተግባራቸውን ጠቅለል እያደረገ ከገለጸ በኋላ “እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን … ” ያለው ለዚህ ነው፡፡ እነዚያ ሁሉ ቅዱሳን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ተስፋና እውነት ሲሉ ያን ሁሉ መከራ በሕይወታቸው መቀበላቸውና በሞታቸው ሳይቀር መመስከራቸው አስቀድሞ በአበውና በነቢያት በኩል ተስፋውን የገለጠውና የሰጠው፣ ኋላም ሰው ሆኖ ያንን ታላቅ ተስፋ በተግባር የፈጸመው እርሱ እውነተኛና የታመነ ስለ መሆኑ መመስከራቸው ነው፡፡ አንድ ነገር ብዙ የታመኑ ምስክሮች ባሉት መጠን የበለጠ ተአማኒ እንደሚሆነው ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል ለፈጸመውና ላዘዘው ነገር እውነተኛነት የቅዱሳን ሕይወት አማናዊ ምስክር ነው፡፡ ራሱ ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን “ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” ብሏቸዋል፡፡ ስለሆነም ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በየዘመናቱ በመስቀሉ ካፈራቻቸው ቅዱሳን ልጆቿ ነጥለን እናስባት ብንል የሚቻል አይሆንም፡፡ ባለቤቱ ክርስቶስ “እኔ የወይን ግንድ ነኝ፣ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ” ያለው ይህን እውነታ የሚያስረዳ ነው፡፡

   የቅዱሳን ሕይወት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ወደ አባቱ በማረጉ ወይም ደግሞ በደቀ መዛሙርቱ ሞት ምክንያት በምድራችን ላይ ተቋርጦ ያልቀረ ለመሆኑ ተግባራዊ ምስክርነቱን ይሰጣል፡፡ በቅዱሳን ሐዋርያት ሲሠራው የነበረውን ሥራ በየዘመናቱ በተነሡ ቅዱሳን አማካይነት እንደየ ጸጋቸው ሲሠራው ኖሯልና፣ ወደፊትም ይሠራዋልና፡፡ እርሱ ሥራውን እስከ ዛሬም ድረስ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኩል በቅዱሳኑ አማካኝነት ይቀጥላል፡፡ ስለሆነም የቅዱሳን ሕይወት የመድኃኒታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወትና ትምህርት የሚገልጥና የዚያ አካል ስለሆነ የቅዱሳንን ሕይወት ማንበብ፣ መጻፍና ማወቅ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተገቢ ተግባሯ ነው ማለት ነው፡፡

   በተለይም ደግሞ የቅዱሳን ሕይወት ላይ ላዩን የሚያነቡ ሰዎች የማያዩትና የማይደርሱበት ጥልቅና ረቂቅ የሆነ ጥበብን የያዘ ነው፡፡ የቅዱሳንን ሕይወትና ትምህርት ስንማርና ስናስብ በማስተዋል መንፈስ ሆነን ሊሆን ይገባል፡፡ አባባላቸውና ትምህርታቸው ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ካላቸው ረቂቅ ተዋሕዶና ጥልቅ ከሆነ መንፈሳዊ የሕይወት ልምዳቸውና ተሞክሯቸው የተወሰደ ስለሆነ እንደ ሰማን ወይም እንዳነበብን ወዲያዉኑ ከመተቸትና አስተያየት ከመስጠት ልንቆጠብ ይገባል፡፡ ሁሉን ነገር በእኛ የእውቀትና የመረዳት ችሎታና ደረጃ ብቻ መመዘንና መወሰን የለብንም፡፡ አንዳንድ ጊዜ አባባላቸው ግራ የሚያጋባ ወይም ተቃርኖ ያለው መስሎ ቢሰማን እንኳ ጊዜ መስጠት፣ አለበለዚያም ዝም ብሎ ማለፍ ይገባል እንጂ “እንዴት እንዲህ ይባላል?” ወደሚል አላስፈላጊ ሒስ ወይም ነቀፋ ውስጥ መግባት የለብንም፡፡

   Delete
  3. ወደ ገዳም ለመግባት ወይም ለመመነን ዋነኛው ምክንያት በአጭሩ ሲገለጽ ፍቅረ እግዚአብሔር ነው፡፡ አንድ ሰው እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ በሚወድበት ጊዜ ሙሉውን ጊዜውን ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ለመኖር ይወስናል፡፡ ራሱን ከምንም ሳይቆጥር ወደ ንጽሐ ልቡና እና ወደ ፍጹምነት ለመድረስ ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ሲል መከራዎችን ከእግዚአብሔር ጋር በመሆን በትዕግሥትና በአኰቴት ይቀበላል፡፡

   ስለዚህ ገዳማዊ ሕይወት የዚህን ዓለም ምኞትና ፍቅር ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ሲሉ በመተው ዘወትር እግዚአብሔርን ብቻ በማሰብ የሚኖርበት ሕይወት ነው፡፡ በዚህም አባቶቻችን በገዳም መልአካዊ ሕይወትን ኖረውበታል፡፡ በሚገባ ከኖሩበት መነኰሳት ምድራውያን መላእክት ናቸውና፡፡ እነርሱም ራሳቸውን ከሁሉም ነገር በመከልከል ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ በትሕትና፣ በትህርምትና በትጋት የሚኖሩና “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፣ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም፡፡ ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል፡፡” የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል ሰምተው የሚያልፈውን ዓለም በማያልፈው ዓለም በመተካት የፍጹምነትን ሕይወት በመምረጥ የሚፈጽሙ ናቸው፡፡

   በክርስትና ገዳማዊ ሕይወት የክርስቶስን ትምህርት በመከተል የተጀመረ ሲሆን ዓላማውም ራስን በመካድ ወደ ፍጹምነት ለመድረስ ነው፡፡ በዚህም ጌታችን በወንጌል “ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሂድና ያለህን ሽጠህ ለድሆች ስጥ፣ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፣ መጥተህም ተከተለኝ” ብሎ የተናገረውን ቃል የፈጸመውን ታላቁን አባት ቅዱስ እንጦንስን ይመስሉታል፡፡ የክርስትና ገዳማዊ ሕይወት መሠረቱ ክርስቶስ በመሆኑ “ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይ ወፎችም መሣፊሪያ አላቸው፤ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም፡፡" ብሎ ጌታችን የተናገረውን ራስን ከዚህ ዓለም ብዕልና ደስታ በፈቃድ ባዶ የማድረግ ሕይወት በተግባር የሚተረጎምበት ነው፡፡ ይህ ሕይወት በዚህ ዓለም ለዘለዓለማዊ ቃሉና ትምህርቱ ታዛዥ በመሆን ክርስቶስን ለመምሰል የሚያስችል ሕይወት ነው፡፡

   የእናታችን የቅደስት ክርስቶስ ሠምራ በረከትና አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን

   Delete
  4. ይህን ሁሉ ቅብጥርጥር ማብዛት መዳን በቅዱሳን በኩል ልትል ነው?

   ቅዱሳን አርአያና ምሳሌ፤ መምህራንና እውተኛውን መንገድ የሚያሳዩ ብርሃኖች እንጂ የሰው ልጅ አዳኞች አይደሉም። መዳንስ

   «መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና» የሐዋ 4፤12 ይህ የወንጌል እውነት ነው።

   Delete
 28. በመጀመሪያ የአባቶቻችንን ፎቶ መልሱልንና የእናንተኑ ሉተርን ፤ አርዮስንና መቅደንዮስን ….. ሌሎችንም Background ማድረግ ትችላላችሁ፤
  ሌላው ምንፍቅናው ዛሬ የተጀመረ መስሏችሁ ነው ፤ ከእናንተ በፊት ስለተዋህዶ፤ስለአማላጅነት፤ገድላትና ቃልኪዳናቸው ወዘተ… ምን ያልተባለ አለ፤ ለሁሉም ከአባቶች የማያዳግም መልስ ተሰጥቷቸዋል፤
  ስለዚህ ለሉተራውያን፤ ለመሐመዳውያን፤ለአርዮስ ተከታዮች መልስ ተሰጥቷል፡፡
  በሐይማኖት ሎጂክ፤ የሳይንስ ቀመር፤ በምርምር የሚደረስበት ሳይሆን በእምነት
  ሲሆን ክርስቶስ በምሳሌ ሲያስተምር የሰው አዕምሮ የሚረዳውን ያህል እንዲገባው እንጂ
  ለፍልስፍና አይደለም፤ አንተ የማታምነውን፤ጥርጣሬህን ፤ ምንፍቅናህን ለመመለስ ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ በመፅሐፍ እንደተባለ ስለተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ብዙዎች ንስሐ ገብተው እስኪመለሱ ይጠብቃል፤ ሺህ ዓመት እንደ አንድ ቀን፤አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት ይላልና፤// ተሐድሶ መናፍቃን ይህ ቁጥር/ አገላለፅ ምን ለማለት ይሆን?
  ጥያቄ ልጨምርላችሁ በመፅሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሲገባ/ ለኖህ፤ለአብርሃም፤ለዳዊት ሌሎችም ትዕዛዜንና ሕጌን ለሚጠብቁ እስከ ሺህ /ትውልድ/ዘመን ድረስ ምህረቴን አደርጋለሁ ይላል፤ሺህ ትውልድና ዘመን መቶ ዓመት/ሺህ ዓመት/ መቶ ሚሊዮን/ አንድ ቢሊዮን?

  ReplyDelete
 29. menfesn besiga memermer keto indet yichalal .Menafikan endih nachihu.Geta beine yemiyamin hulu neger yichalewal yilal keinem belay teamiratin tadergalachihu yilal.Itiyopiyawiwa nigist iyerusalemn bemegobnytwa bemechereshaw zemen tiferdalech aylim inde? gishen gobnytem degmo inya mengistum yemanwersebet mikniyatm indih new .yetekedese sifra sewn kidus yadergal.

  ReplyDelete
 30. Jesus is the only way to go heaven . This is the orthodox way. No teaching that saints are the way to go heaven.If some body says saints are the way to heaven, so the that man is out of apostles teaching ( Acts 4: 12). so hi guys e.o.t.c is practicing that saints are way to heaven ,, so the church exit heresy(menefekena) teaching.

  ReplyDelete
 31. ABA SELAMA enkulechelich ቅዱስ ፓትርያርኩ ከማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጋር ልዩ ቃለ መጠይቅ አደረጉ

  ReplyDelete
 32. tadyia kale meteywk biyadergus?????mogne nehe lebel amlakhen temelket ersu bicha new yemayelwet papas yihedal papas yemetal

  ReplyDelete
  Replies
  1. yap.zemenu yekadirewoch adel.kadire kekadire ga new hibretu.

   Delete
 33. ክርስትና ከተሰበከበት ጊዜ ጀምሮ እንክርዳድን በመዝራት ንጹሕ የሆነውን የትምህርተ ክርስትናን ስንዴ ጥራት ለማበላሸት በማቀድ በጠላት የተደረገው ሙከራ ቀላል እንዳልሆነ ይታወቃል (ማቴ. 13፥24-30)፡፡ ጠላት እንክርዳድን በስንዴ መካከል የመዝራቱ ዐላማ ምን እንደ ሆነ የክርስቶስ ጉባኤ (ቤተ ክርስቲያን) ከተረዳችውና በጥንቃቄ ከተከታተለችው ዓመታት ተቈጥረዋል፡፡ የጠላት አፈ ሙዝ ምን ጊዜም ከክርስትና ትምህርት በተለይ ጌታ እግዚአብሔር ወልድንና ጌታ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በሚመለከት ዶክትሪን ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ይህም ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሰዎች የኀጢአታቸውን ስርየት በመቀበል ከኵነኔ የሚድኑት እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሆኖ በሰው ቦታ ተተክቶ የሰውን ኀጢአት በመሸከሙና በመቀጣቱ ነው፡፡ ስለ ሆነም ጌታ የተቀበለው ቅጣት ለኔ ስለ እኔ ነው በማለት የታመኑበት ብቻ እንደሚድኑ የተረጋገጠ ሆኗል (ዮሐ. 3፥14-18)፡፡ ይህን የወንጌል ማእከላዊ ምስክርነት በፍጥረታዊ ሰው ልብ ውስጥ በማስገባት መለኮታዊውንም ብርሃን በመፈንጠቅ ይታመኑበት ዘንድ የሚረዳቸው ጌታ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው (1ቆሮ. 2፥10-13)፡፡ የአባባሉን እውነትነት የምንቀበል ከሆነ ይዋጀው ዘንድ ቤዛው ሆኖ የሞተለትን ኢየሱስ ክርስቶስንና እንዲያምን የሚረዳውን መንፈስ ቅዱስን የሰደበ፥ የናቀ፥ ያቀለለ፥ ሰው በምን መንገድ ሊድን ይችላል? እንደዚህ ያለው ሰው መውጪያ ወደሌለው ዐዘቅት ውስጥ ወድቆ በጭንቅላቱ የቆመ ሰውን ይመስላል (ማቴ. 12፥31-32)፡፡ ሰይጣን የራሱን ያህል ብቻ ሰው እግዚአብሔርን በማወቅ እንዲወሰን ቸል ቢልም፥ ሰው ከሰይጣን ተለይቶ ለእግዘአብሔር የሚሆንበትን የመዳኛውን መንገድ ሊዘጋበት ይፈልጋል ማለት ነው፡፡ ስመ ክርስትና ካላቸው ወገኖችም እንደዚህ ያሉ የክርስትናን ታሪካዊ ነገር ብቻ እንዲያምኑ ሰይጣን የለቀቃቸው ሰዎች መገኘታቸው ቢያስደንቅም የመኖራቸው ጕዳይ ግን ርግጠኛ መሆኑ አያከራክርም፡፡

  ReplyDelete
 34. Aba selamawoch you are depend on logic not on the power of GOD

  ReplyDelete
 35. "Test everything. Hold on to the good. Avoid every kind of evil." 1 Thessalonians 5:21–22

  ReplyDelete
 36. ክርስቶስ ቅዱሳኑን ከእኔ የሚበልጥ ሥራ ትሠራላችሁ በአሥራ ሁለቱ ወንበር ተቀምጣርሁ ትፈርዳላችሁ …. ብሏቸዋል፡፡ ፡፡ ፡፡ አንተ ግን ዲያቢሎስ አባቴ ብለህ ክርስቶስ ያከበራቸውን፣ ስለ ስሙ ብለው መከራ የሚቀበሉትን የስድብ አፍህን ትከፍታለህ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ከሚያስጠላ ከያዘህ አጋንንት ያላቅህ
  The Son of the Beloved St. Kirstors Semra

  ReplyDelete
 37. Bemejemeriya Yeabatochachinin photo legnaw tewulinina yeabatachihun yediyabilos photo weyim degmo yeAriyosene photo teteekemu.2nga degmo sile kidusan kibir yeniket kalat kemitanebenibu metsihaf kidusin bedenb mermiru.Kewededikute gara kal kidanen adergalehu yilalina.

  Benatachihu Orthodox tewahidon lematfat atrituu.silemayihonilachihu.

  ReplyDelete
 38. ገድል እያነበባችሁ ገደል ከመግባት በክርስቶስ ዳግም መወለድ ይበላጣል

  ReplyDelete
 39. ጳጳሱ ያድርጉትም አያድርጉትም የሰው ሚስት እስካላባለጉ እና አስገድደው እስካልደፈሩ ድረስ በማንም ሰው ላይ የሚያመጣው ጉዳት እና የሚፈይደው ዓቢይ ነገር የለም፡ ትልቁ ወንጀል ግን በጥላቻ እና በብቀላ የእሳቸውን ስም ለማጥፋት እና የሚወክሉትን ድርጅት ለመጉዳት ይኽን ጽሑፍ ጽፎ በድረ ገጽ መበተን ነው፡ ምክነያቱም ሕገ ምንኩስና ሕገ ትሩፋት እንጂ ሕገ ርትዕ አይደለም ከእሳቸው ስህተት ይልቅ የስም አጥፊዎቹ ስህተት በእጅጉ የከፋ ነው።

  ReplyDelete