Wednesday, July 11, 2012

የግንቦቱ ሲኖዶስ ካወገዛቸው ግለሰቦች መካከል ሦስቱ ውግዘቱን በመቃወም ጠቅላይ ቤተክህነቱን ይግባኝ ጠየቁ

(ደብዳቤ የጻፉት ዲ/ን አሸናፊ መኮንን፣ ዲ/ን አግዛቸው ተፈራ እና መምህር ጽጌ ስጦታው መሆናቸው ታውቋል)
የግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ቤተክርስቲያንን የዓለም መሳቂያና መሳለቂያ በማድረግ ያዋረደበትን ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡ ይህን የራሱን ክብር የቀነስበትን፣ በታሪክ ተወቃሽ የሚያደርገውንና ብዙዎችን ያሳዘነውን፣ የቤተክርስቲያንን ሕግና ስርአት ባልተከተለና፣ በየትኛውም መስፈርት ሲመዘን ሕገ ወጥ ሆኖ የተገኘውን ውግዘት፣ «ተወጋዦቹ» እየተቃወሙት ነው፡፡ አንዳንዶቹም ይግባኝ እየጠየቁበት መሆኑ ተሰምቷል፡፡ እስካሁን ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ለጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤትና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት በጻፏቸው ደብዳቤዎች ተቃውሟቸውን ያሰሙትና የተላለፈባቸው ሕገወጥ ውግዘት እንዲነሳና ጉዳያቸው እንደገና እንዲታይ የጠየቁት ዲ/ን አሸናፊ መኮንን፣ ዲ/ን አግዛቸው ተፈራ እና መምህር ጽጌ ስጦታው መሆናቸው የታወቀ ሲሆን ለዛሬው የዲ/ን አሸናፊ መኮንንን ደብዳቤ እናቀርባለን (ሙሉውን ደብዳቤ ከዚህ ጽሑፍ በታች ያገኙታል)፡፡
እንደሚታወቀው ዲ/ን አሸናፊ መኮንን  እስካሁን 16 መንፈሳዊ መጻሕፍትን በመጻፍ ለበርካታ ምእመናን መጽናናትን ያመጣና እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ያስነሳው እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጅ ነው፡፡ መጻሕፍቱ በአብዛኛው መንፈሳዊ ሕይወት ላይ ያተኮሩ፣ እየጣፈጡ የሚነበቡ፣ ሕይወትን የሚፈትሹና ለብዙዎች የመንፈስ እርካታን ያመጡ በመሆናቸው በየቤተክርስቲያኑ ደጅና የኦርቶዶክስ መጻሕፍት በሚሸጡባቸው የመጻሕፍት መደብሮች ውስጥ እየተሸጡ ለምእመናን በቅርበት የሚደርሱ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥም በስፋት የሚነበቡና የማኅበረ ቅዱሳንን የተረት መጻሕፍት ከገበያ እያስወጡ ያሉ መጻሕፍት መሆናቸውን ብዙዎች የሚመሰክሩት ሐቅ ነው፡፡
ዲ/ን አሸናፊ በጻፈው ደብዳቤ በሲኖዶሱ ውሳኔ ከልብ ማዘኑን የገለጸ ሲሆን፣ የተላለፈው ውግዘት የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት ያልተከተለ፣ የቤተ ክርስቲያኗን ህግና ስርአት ያፈረሰ፣ ታሪክን ያላገናዘበ መሆኑን አትቷል፡፡ ደብዳቤው በምድራውያን ፍርድ ቤቶች እንኳ የከሳሽ ክስ ብቻ ተሰምቶ ብይን እንደማይሰጥና ለተከሳሽም ቃሉን የሚሰጥበት እድል እንደሚሰጥ ጠቅሶ፣ «ውግዘት የተካሄደው የቤተክርስቲያን እምነትና ቀኖና ተነክቷል ተብሎ ከሆነ ይህ አካሄድም የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና ያፈረሰ ነው» ሲል ይሞግታል፡፡ እርሱ አንቀጸ ብርሃን የሚባል መንፈሳዊ ማኅበር የሌለውና ዳንኤል ተሾመ የሚባልና በተሐድሶ ዙሪያ መጽሐፍ የጻፈ ሰው እንደማያውቅ የገለጸ ሲሆን፣ ማኅበረ ቅዱሳን ግን እርሱን በኑፋቄ የሚከስበት ነጥብ ሲያጣ እንዲህ አይነቶቹን የሐሰት መረጃዎች በማቀበል ሆነ ብሎ ሲኖዶሱን አሳስቷል፡፡ ማንንም ለማነጋገር የፈራ የሚመስለው ሲኖዶስም ሁሉንም ሳይጠራና ሳያነጋግር፣ ተከሳሾቹም ስለቀረበባቸው መረጃ ምላሽ እንዲሰጡ ሳያደርግ በጭፍንና በጅምላ ማውገዙ እንደዚህ ያሉ ታሪካዊ ስሕተቶችን እንዲፈጽምና ራሱ እንዲገመትበት አድርጓል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ዲ/ን አሸናፊን ለመክሰስና ለማስወገዝ የተንቀሳቀሰው በዋናነት የእርሱ መጻሕፍቱ በቤተክርስቲያን ውስጥ በስፋት በመነበባቸውና ለብዙዎች የመንፈስ እረፍትንና እርካታን በማምጣታቸው ቀንቶና ተመቅኝቶ እንደሆነ ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡ ዲ/ን አሸናፊ እስካሁን የጻፋቸውን 16 መጻሕፍት በግንቦት 2003 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ገሪማ ፊርማ ለሊቃውንት ጉባኤ በተጻፈ ደብዳቤ የሊቃውንት ጉባኤው ለሥራ እንዲጠቀምባቸው መመሪያ ተላልፎ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም ማኅበረ ቅዱሳን ነገር እየሰራ ዲ/ን አሸናፊን ለማስወገዝ፣ ከፓትርያርኩ ጋር ግጭት ውስጥ የነበሩትን ጳጳሳት በማሳደም ውስጥ ለውስጥ ብዙ ሴራ ሲጎነጉን መቆየቱ ታውቋል፡፡ ከሰሞኑ አንዳንድ የማቅ ቀንደኛ ጳጳሳት ለምሳሌ አባ ጢሞቴዎስና አባ ዮሴፍ በሰዎች ፊት፣ አሸናፊን ያወገዙት እንደተባለው ኑፋቄ ስለተገኘበት ሳይሆን እርሱን ከፓትርያርኩ ለመነጠል በማሰብ እንደሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ በተለይ አባ ጢሞቴዎስ እንዳሉት «ዲያቆን አሸናፊን ያወገዝነው ምንም ለማይጽፈው ለገብረ መድኅን (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ነው) ጽሑፍ እየጻፈለት ስለሆነ ይህን ለማስቆም ነው፡፡ በተጨማሪም ወ/ሮ እጅጋየሁ የጻፉትንና ያሳተሙትን መጽሐፋቸውን «የጻፈው አሸናፊ ስለሆነ ነው» በማለት ማቅ የሰጣቸውን የተሳሳተ መረጃ እንደወረደ በማስተጋበት ይህም ለማውገዝ ሌላው ምክንያት እንደሆናቸው ሲናገሩ ተሰምተዋል፡፡ በዚህም ቤተክርስቲያኗን እንመራለን የሚሉ አንዳንድ ጳጳሳት በምን ደረጃ ላይ እንዳሉ መገመት ይቻላል፡፡
ከዚህ ቀደም እውነትን በመመስከራቸውና ተከሰው ቀርበውና ተከራክረው በመርታታቸው «ጥፋተኛ» ተብለውና ቀኖና ተቀብለው ያለበደላቸው ደብረ ሊባኖስ ተልከው የነበሩትን መምህር ጽጌ ስጦታውንና መምህር ግርማ በቀለን፣ እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ ከወገሯቸው መካከል አንዱ የነበሩትና ዛሬ በሰዎች ፊት ያን አሳፋሪ ስራቸውን እንደጽድቅ እያወሩ የሚገኙት፣ አሁንም ከተወገዙት መካከል አንዱን ቢያገኙትም በድንጋይ እንደሚወግሩት እየዛቱ ያሉት የያኔው መነኩሴ የአሁኑ ጳጳስ አባ ዮሴፍም «ዲ/ን አሸናፊ የተወገዘው እርሱን ከፓትርያርኩ ለመነጠል ተፈልጎ ነው» በማለት በሰዎች ፊት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ከዚህ ሁሉ ድራማ በስተጀርባ ማህበረ ቅዱሳን የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሯሯጥ፣ ከላይ የተጠቀሱትና ሌሎቹም አንዳንድ ጳጳሳት በአንድ በኩል ነውራቸውን ማቅ እንዳያወጣባቸው እርሱን ለማስደሰት፣ በሌላ በኩል አቡነ ጳውሎስን ያለ ሰው በማስቀረት በእርሳቸው ላይ ያሻቸውን ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን እንደሚያሳይ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉ ያሉ ወገኖች ይናገራሉ፡፡
በሕገ ወጥ መንገድ ውግዘት ያስተላለፈው ሲኖዶስ ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ ማውገዙና ሕግ ማፍረሱ ሳያንስ፣ በመግለጫው መጨረሻ ላይ የተወገዙት ይቅርታ ከጠየቁ ቤተክርስቲያን በሯ ክፍት ነው ማለቱ የተወገዙትን ወገኖች በእጅጉ እንዳሳዘነ እየተነገረ ነው፡፡ ለሕገ ወጥ አሰራሩ ይቅርታ መጠየቅና ውግዘቱን ማንሳት ያለበትም ራሱ ሲኖዶሱ ሊሆን ይገባል የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ የሌሎቹን ወንድሞች ደብዳቤዎች ይዘትና ደብዳቤዎቹን በቀጣይ እናቀርባለን፡፡

21 comments:

 1. ke kassahun alemu blog yawerdkut new ተሐድሶ እንዴት ይታያል?ተሐድሶ እንቅስቃሴ በቤተ ክርስቲያኒቱ መኖሩ እርግጥ ከሆነ ምንጩ ከየት ነው? ከውስጥ ወይስ ከውጭ? ከውስጥ ነው የሚባል ከሆነ የትኛውን የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረታዊ መርህ ነው አድሳለሁ የሚለው? ለማደስ ያነሳሳው ምክንያትስ ምንድን ነው? ምክንያቱስ አግባብንት ያለውና በቂ ነው? እሺ ይሁን ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማደስም በቂና አግባባዊ ምክንያትም ይኑረው አካሔዱስ ትክክል ነው ወይ?…› እነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች አጥጋቢና አዎንታዊ መልስ ሊያገኙ ይገባል፡፡ ያለበለዚያ የተሐድሶው እንቅስቃሴ ችግር አለበት፡፡

  ReplyDelete
 2. ene degmo bekassahun alemu blog betste asteyayet tshufen lfetsm ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ተቀናቃኝ እንዳለባት አምናለሁ። እንኳን ከራሷ ልጆች ፣ተቀናቃኞቿ የሚያነሱባትን ሃሳብ ሁሉ ከተቀናቃኝ ስለመጣ ብቻ ውድቅ ልናደርገው አይገባም። ጠላት የሚያነሳቸው ሃሳቦች እሱ የሚያሸንፍበትን መዝ’ዞ ቢሆንም ሳያውቀው አስተማሪ ሆኖ ሊገኝ ይችላል።

  ReplyDelete
 3. የተወገዙት ይቅርታ ከጠየቁ?? ከመወገዛቸው በፊት ይቅርታ እንዲጠይቁ ዕድሉ ለምን አይሰጣቸውም ነበር፤ በውግዘቱ አባ ጳውሎስ እና አንዳንድ አባቶች እንዳልተስማሙበት ሰምቼ ነበር፡፡ እንዲህ ዓይነት አሰራር ከቀጠለ የቅዱስ ሲኖዶሱን ክብር የሚቀንስ ይመስለኛል፡፡

  ፀጋዬ ብርቅነህ
  ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

  ReplyDelete
 4. እስራኤላውያን ከባቢሎን በተመለሱ ጊዜ እያሱ የተባለ ካህን የገለግላቸው ነበር፤ ሰይጣን ግን ካህኑ እያሱን በእግዚአብሄር ፊት ሲከሰው እና ሲያሳጣው እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ማህበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ለእራሱ ጥቅም ሲል ብቻ የሚከሳቸው እስከመቼ ድረስ ነው ኢያሱን ከሰይጣን ክስ ነጻ ያደረገ፤ ዲያቆን በጋሻውን ከማህበረ ቅዱሳን ክስ ነፃ ያደረገ እግዚአብሔር ሌሎች አገልጋዮችንም ነፃ እንደሚያደርግ አንጠራጠርም፡፡
  ፀጋዬ ብርቅነህ
  ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

  ReplyDelete
 5. asue dink sehafi new. beewnet.

  ReplyDelete
 6. Ashiye ayzoh yetegefahew sile ewnet new.Ewnet degmo ke megareja jerba hona atiqerim

  ReplyDelete
 7. I really feel Sad about the Holy synod decision. so let us pray together to sweep out this devilish spirit society mk from our church and country. My brother in Christ Deacon Ashenafi don't lose heart. Abba.

  ReplyDelete
 8. ደብዳቤው ፍቅርን ያዘለ በመሆኑ ክርስትና እንዲህ ነው ያሰኛል። ሰው በማያውቀው ይገደልነበረ ዛሬ በማያውቀው ይወገዛል። በርታ ብዙዎች ካጠገብህ ነን። መርዳት እንፈልጋለን መንገዱን አጥተን ነው አድራሻህን አሳውቀን። ምእመናን ዩ ቲዩብ ላይ ዺ/አሸናፊ መኮንን ብላችሁ ብትገቡ ስብከቱን ብታዳምጡ ማነው መናፍቅ ትላላችሁ። አጽዳቂው ማን ነው? የሚለውን ጋብዣለሁ። ዲ/ አሸናፊ በርታ አሁንም ጻፍ አሁንም ስበክ ተጨማሪ ስብከቶችህን አሰማን።

  ReplyDelete
 9. Asheye! Megefatihn yemimesl megefat yetegefu ijig tikit nachew.wud yeKIRISTOS wedajoch bicha!! Des yibelih keGETA gar mekera besimu bemekebelih.antenim yemnimesl bizu nen.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሹ ደብዳቤህ እንዴት ልብን ይነካል? እውነት ማን ጋ እንዳለም በቂ ምስክር ነው፡፡ ነገር ግን ደስ ይበልህ፡፡ አንተ ከክርስቶስ አትበልጥም፤ ክርስቶስን ከሰቀለና ዳግም ቢያገኘውም ከሚሰቅለው ቤተክህነት ከዚህ የተሻለ ነገር አትጠብቅ፡፡ የረታኸው አንተ ነህ፡፡ የእውነት መንገዷ ይህች ናት፡፡ አንተ በእውነት መንገድ ላይ ስላለህ ነው የተወገዝኸው፡፡ ክርሰቶስን ብቻ ባትሰብክ ኖሮማ ማንም አይነካህም ነበር፡፡ ስለዚህ ደስ ይበልህ፤ ስለጌታ ስም ተነቅፈሃልና፡፡

   Delete
  2. Ashenafin btifozo sayhon besraw awkenwal

   Delete
  3. Ewnet new nege lehulachin endih new ahun yehbret giz new

   Delete
 10. እስመ ወድቀ መስተዋድይ ዘአስተዋደዮሙ ለአበዊነ(አኀዊነ)ቅድመ እግዚአብሔር መዓልተ ወሌሊተ ሳያቋርጥ ቀን ተሌት ወንድሞችን የሚያሳጣ የሚያጣላና የሚያካስስ አሳባቂው ወደቀ ራእ ዮሓ 12. 10
  የተባለው እርሱ ወድቋል የርሱ አሻክርት መንፈሳውያን ቅዱሳን ነን ባዮች ግን ሥራው እንዳይተጓጎል ሲከሱ ሲያካስሱ ሲያወግዙ ሲያስወግዙ ያፍዝ ያደንግዝ ሥራቸውን ሲያንዛዙ እና ሰወችን ባልሆነ አቅጣጫ
  ሲያጓጉዙ ይታያሉ ለገቢያቸው ብለው ከመንገድ ውጭ ይሠራሉ፤

  ReplyDelete
 11. ene menem tehadsowochen bekawemem yeashenafi wugezeten alesmamabetem.ene ashenafin yemawekew beguadeghaye new yeashenafin metshft legud yewedachewal ke tensu letselot beker hulum yersu metshaft alut.ene enkua yashenafi metshafochun badenkachewem bezu gize ya abune shenodn metshaft manbebe yishalaleghal meknyatum ene getemegh, misale,tarik yebethabet metshaft alewdem ayemechjem nebere silezih ashenafi yekenon metas chigr binorbet enkua yemisewegez aydelem bay negh silzih kidu sinodos gudayun bekin leb endiyaylet yasfelgal escahun gudeghechen tezuazure ewn emetshaftu nufake ayatachihoal biye teyekealehu hulum gen ye sinodusu wesane dubda new yehonebachew.

  ReplyDelete
 12. ye dn aethachew ena ye tsege stotawun gene escaltestecakelu deres wugethetun edegfalehu

  ReplyDelete
 13. የዚህኛው አስተያየት ለመቅረብ ተራው መቼ ይሆናል ? ቃሉ ስለሚጎሽማችሁ ማፈናችሁ ነው ?
  የናንተን ተደማሪ ማወጣወጥ ትታችሁ የግለሰዎቹን ማመልከቻ ብቻ ብታስነብቡን መልካም ነው ፤ የነርሱው ይበቃናል ፡፡ ያልነበራችሁበትን እንዲህ ተብሎ ፣ እንዲያ ተብሎ እያላችሁ በአባቶች መካከል ቦይ መቅደዱ ደግ ሥራ አይደለም ፡፡ በራሳቸው መሃል ችግር ካላቸው የሚፈታበትን መንገድ መቃኘት እንጅ ፣ ይባል አይባል ከቶም ሳትሰሙ ፣ በስማ በለው ስምን እየጠቀሳችሁ ፣ ወሬ ማራገቡን አቁሙ ፡፡ ለማንም አይጠቅምም ፤ ምናልባትም እንደ ሰው ፣ ሰውን እልህ ያጋባ ይሆናል ፡፡ የተበደሉት አቶ አሸናፊ መኰንን በጻፉት ማመልከቻ እንኳን በጅምላ ሲኖዶሱ አሳዝኖኛል ፣ ፓትርያርኩንም ኃላፊነታቸውን አስመልከተው ቅር ብሎኛል አሉአቸው እንጅ እገሌ አባ እገሌ ብለው የአባቶችን ስም እየጠቀሱ እንዲህና እንዲያ ተባልኩ አላሉም ፡፡ ቀዝቃዛ ማለትም የተረጋጋ፣ የጥሩ ክርስቲያን ወግን የሚያንጸባርክ ማመልከቻ ነው ፡፡

  የተወሰኑ መጽሐፍቶቻቸውንም አንብቤአቸዋለሁ ፡፡ ያረጋጋሉ /ያጽናናሉ/፣ ተስፋን ይሰጣሉ ፣ የአባት ቃል ይህልም ይከብዳሉ ፡፡ ይህን የትም ሥፍራ መመስከር እችላለሁ ፡፡ የተወቀሱበት የትምህርተ ሃይማኖት መፋለስ ተገልጾላቸው ቢያስነብቡን ለሁላችንም መማሪያ ይሆን ነበር ፡፡ እንደ ቃላቸው ከሆነ ግን እስከ አሁን ለእሳቸውም አልደረሰም ፡፡

  ReplyDelete
 14. ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ ይላሉ ፤ ቤ/ክን አሳድጋ ተራቀቅን/አወቅን እስኪሉ ዳቦዋን/ ቆሎዋን ቆርጥመው ካደጉ በኋላ ተሐድሶ ያስፈልጋታል በሚል ከመናፍቃን ጋር ቤ/ክን ውስጥ መሽገው ለማፈራረስ ሲሰሩ የተደረሰባቸው/ ለጊዜው ሰው የደረሰባቸው በጣም ጥቂት ናቸው፤፤ክርስቶስ በመንሹ የሚለያቸው ገና ብዙ አሉ፤፤
  ደብዳቤ መፃፍ አይደለም ንስሐው / የደረመሳችሁትን ገዳም፤በትምህርታችሁ ያቆሰላችሁት ምዕመን/ ያደማችኋትን ቤ/ክን በይፋ ንስሐ ስትገቡ / ለአፈፃፀሙም ቀኖና ከተሰጣችሁ በኋላ የቤ/ክን አባል ሆኖ መቀጠል ይቻል እንደሆን እንጂ ትምህርታችሁን ማን ይሰማል?

  ReplyDelete
 15. የኢየሱስ መንፈስ ያለው ኢየሱስን ይሰብካል። ይህ ነው እውነት! እውነትን ያወቀ እውነትን ይናገራል! እውነትን የሚናገር ደግሞ በሰዎች ዘንድ አይወደድም! በሰዎች ዘን ያልተወደደ ሰው ድግሞይወገዛል ይገደላል! ታዲያ ይችን እድል( መወገዝን መገደልን) በቀላሉ ማን ያገኛታል? እንዴት መታደል ነው እውነትን መስክሮ በሰዎች ፊት መሞት በጌታ ዘንድ ደግሞ መኖር! አሸ በርታ!!!!!!!

  ReplyDelete
 16. አያድርስ! አስመሳይ ነጋዴዎች የጽድቅ ነጋዴን በመምሰል ወደ ገዳማትና አድባራት ተጠግተው
  ቤ/ክርስቲያንን እንረዳለን እያሉ ለራሳቸው በጆንያ ለሌላው እንደ ይሁዳ በከረጢት ይሰበስባሉ ያድላሉ
  መልካም ነው መቸውንም ቢሆን የሰው ልጆች ብዙውን ለራሳቸው ትቂቱን ለሌላው ማድረግ የተለመደ ነው ዳሩ ግን ራሳቸውን የሚቀድሱ ሌላውን የሚያድሱ እነርሱ እነማናቸው ለመሆኑ ተሐደሰ ተቀደሰ የሚለውን ፍቹን ተገንዝበውታል?ይህስ ይቅርና በስሙ ያገኙትን እያግበሰበሱ በጥፋት ጎዳና ይገስግሱ፤
  ያውም መጥፎና አስመሳይ አሳቦቻቸው በፈጣሪ ኃይል እስቲፈራርሱ ከገጸ ምድር እስኪደመሰሱ ነው
  ራስን በማሞገስ ሌላውን በማኮሰስ ስንኳን መንፈሳዊ ሥጋዊ ሥራም አይንቀሳቀስ በመሆኑም ብታርፉ
  ይሻላል አለዚያ ሰይፈ በቀል ይመዘዛል፤ ያም ከሆነ መድረሻ ይታጣል፤

  ReplyDelete