Thursday, July 12, 2012

የግንቦቱ ውግዘት መነሻ የሆነው የማኅበረ ቅዱሳን ክስ ዶሴ፣ የሊቃውንት ጉባኤው ጥናት ውጤትና የሲኖዶሱ ቃለ ጉባኤ

እነዚህን አራት ሰነዶች ስለሚከተሉት ምክንያቶች ለአንባቢያን አቅርበናል።
1ኛ) ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ፥ የእውነተኞች የቤተ ክርስቲያን ልጆችን አንገት ያስደፋና አሳፋሪ ታሪክ ቢሆንም ታሪክ ነውና ለቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች እና ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች እንዲሁም ፍላጎት ላላቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ በቀላሉ እንዲያገኙት ለማቅረብ ወደድን።
 
2ኛ) ውሸት እና ስህተት ዝም ከተባለ እንደ እውነት እና ትክክለኛ ነገር ስለሚቆጠር በክሱና በውግዘቱ ውስጥ «ኑፋቄ» በተባሉ ነጥቦች ዙሪያ ብዙ የምንለው ስላለን አስቀድመን ለአንባቢያን ጥሬ መረጃውን ማቅረቡ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። እነዚህን ሰነዶች ማንበቡ በሚቀጥሉት ቀናትና ሳምንታት የምናቀርባቸውን ጽሑፎች ለማገናዘብ ይጠቅማል።
  

 መልካም ንባብ . . .
  

10 comments:

 1. እባካችሁን የዲ.አሸናፊን ማመልከቻ እንዲሁም ሐሙስ ሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም የለጣ ችሁትን
  1ኛ- የማኅበረ ቅዱሳን የክስ ዶሴ በግለሰቦች ላይ (21 ገጽ)
  2ኛ- የማኅበረ ቅዱሳን የክስ ዶሴ በማኅበራት ላይ (31 ገጽ)
  3ኛ- የሊቃውንት ጉባኤው ጥናት ውጤት በማኅበራት እና ግለሰቦች ላይ (49 ገጽ)
  4ኛ- የሲኖዶሱ ቃለ ጉባኤ እና ውግዘት (48 ገጽ) ተጭኜ አልከፈት በማለቱ ለማንበብ አልቻልኩና በሚከተለው የኢ-ሜይል አድራሻዬ ላኩልኝ፡- dilnesabegeta@yahoo.com

  ReplyDelete
  Replies
  1. መጫን ያለብህ በቀይ ቀለም የተጻፈውን ነው እንጅ በሰማያዊ ቀለም የተጻፈው ቃል አይከፍተውም ፡፡ መጨረሻው ላይ በቀይ የተጻፉትን ቃላቶች ተጫናቸው ፤ ይከፈታል

   Delete
 2. የሊቃውንት ጉባኤው ጥናት /ሊቃውንት ክስ/ ውጤት በማኅበራት እና ግለሰቦች ላይ በሚለው በክፍል 5 ስለ አንቀጸ ብርሃን ከቀረበው መረጃ ውስጥ የገጽ 13 ተደግሞ ቀርቦ ገጽ 14 ጐድሏል ፡፡ ይኸ ገጽ በቅርብ በእጅ ካላችሁ አንድ ብቻ ስለሆነች ብታቀርቡና ብታስነብቡን ለማለት ነው ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. "የሲኖዶሱ ቃለ ጉባኤ እና ውግዘት" በሚለው ውስጥ ተጠቃሎ ስለቀረበ የጐደለውን ከዛ አንብቤዋለሁ ፡፡ ሌሎችም የጐደለ የመሰላችሁ ካላችሁ መልሶ ስለሚያቀርበው ይህንኑ መንገድ ተጠቀሙ

   Delete
 3. las vegas yalu mahibere kahinat Abune Fanueiln Anikebelim Maletachewin Deje Selam zegibolinal MAhibere Kahinat yetebalut 1 Melake SAlem Abba Gebire Kidan 2 D. MIsikir 3 zemari wondwosen Nachew YEdebu Asitedadar Melake Kidan SAmueil Min Alu ?DEbirun yaderajut Melake Kidan NAchew enj Abba G/KIdan Ayidelum Abba Gebre Kidan Mahibere KidusanN lemetsekemiya yemifelgu sew nachew KE HAger yewtsut BEsidetegaw sinodos new 4 Ametat yagelegelut Yesidetegawn sinodos new Las vegas yewsedachew Kesis Dejene New zare TEleyayitewal KEsis Dejene Abba G /Kidann mayet ayifelgim Abba G/KIdan las vegas kemetsu Jemiro Kesis Dejene Ayigabezim Menekusew moya yelewim silemilu new Menekusew Besebesebut genzeb papas lemehon felgew Ethiopia hedew nebere Alitesakam semonun sefa adirgachihu giletsut dehina hunu

  ReplyDelete
 4. እናንተ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጆች ምን ሆናችሁ ነው እንዲህ አርር ድብን የምትሉት፡፡ ቤተክርስቲናችን እኮ ድሮም ቢሆን ማንንም በስርዓት የሚሄድ ክርስቲያን አታወግዝም፡፡ እነዚህ ሰዎች በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ሆነው እያለ ሥራቸው ግን የፕሮቴስታንት መሆኑን አገር ያውቀዋል፡፡ እኛው ቤት ሆነው የኛንው ቤት የሚያፈርሱ ውስጥ ተላቶች እንደሆኑ እናንተም የአላማቸው ተጋሪዎች እንዲያውም አዝማቾቻቸው የምታውቁት ሀቅ ነው እኮ፡፡
  ስለዚህ ከቤተክርስቲያናችን ላይ ዞር አንልም ቢሉ ጊዜ ተወገዙ በቃ፡፡ ሐዋርያት በተለያዩ ሥፍራዎች በሚገኙ ኢአማንያን ዘንድ መስለው በመገኘት ወንጌልን አስተምረው እንዳሳመኑ ከናንተ ይልቅ የኛ ቤተክርስቲያን ታስተምራለችና እናውቃለን፡፡ ግን በተቃራኒው ሐዋርያት የትም ቦታ ያመኑ ክርስቲያኖችን በመካከላቸው ገብተው ሲበጠብጡ አላየንም አልተማርንምም፡፡ እናንተ ግን ዛሬ በቤተክርስቲያናችንና በምእመናን መካከል ተሸሽጋችሁ ቤተክርስቲያኒቱን እንወርሳለን ትላላችሁ፡፡ ለዚህም የረጅም ጊዜ ዕቅድ ነድፋችሁ ብዙ በጀት መድባችሁ ትንቀሳቀሳላችሁ ይህንንም እናውቃለን አይተነዋል ደርሶብናልምና ምስክሮች ነን፡፡ በናዝሬት በአስበ ተፈሪ በአርባምንጭ በጅማ በአዲስ አበባም አንዳንድ አድባራት ከ 1980 ጀምሮ ያደረጋችኋቸውን ሙከራዎች እኔ ከልጅነቴ ጀምሬ ሳያቸው ስሰማቸው ያደገሁት ጉዳይ ነው፡፡ ደግሞ እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙ እውነተኛ የኦርቶዶክስ ልጆች ምስክሮች ናቸው፡፡
  ይህንን የረጅም ዘመን ዕቅዳችሁን በማጋለጥና በማክሸፍ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘውን ማህበረ ቅዱሳንን ዘወትር በመክሰስ የምታሸንፉ ይነስላችኋል፤ግን ትልቁ ቁምነገር እሱ አልነበረም፡፡ የቤ/ክ ጠባቂዋ የማያንቀላፋውና በደሙ ፈሳሽነት የመሰረታት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ልብ አለማለታችሁ ነው ችግራችሁ፡፡ ማህበሩ ባልነበረበት ዘመናት ቤተክርስቲያናችን እንደነበረች ፤ ፈተናዎችንም ሁሉ በጌታ ሃይል በአሸናፊነት ስትወጣ እንደኖረች አለማስተዋላችሁ ነው ድክመታችሁ፡፡ ይህን ብታውቁ ኖሮ አንድን ማህበር ለማፍረስ ስንት በጎ ነገር ልትሰሩበት የምትችሉትን ያላችሁን ገንዘብና እውቀት በከንቱ አታባክኑም ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የሚሳዝነኝ ጌታን ያገለገላችሁ እመሰላችሁ እሱንው እየተዋጋችሁት መሆኑ ነው (ልክ የሳውልን አይነት አገልግሎት ግን እሱ ቅንነት መንፈሳዊ ቅናት ነበረው ጥመትና ተንኮል ብቻ አልነበረበትም ስለዚህም ጌታ ምርጥ ዕቃው አደረገው)፤ የእናንት ለህይወት የመሰላችሁ የሞት አገልግሎት ነው፡፡
  ስለዚህ በከንቱ ዕድሜያቸሁን አትጨርሱ፡፡ በንስሀ ተመለሱ፡፡ አንመለስም ካላችሁም ነብርና ፍየል፤አንበሳና ጊደር፤ተኩላና በግ በምንም ተዓምር በአንድ በረት መኖር ስለማይችሉ አትስበኩ ብላ ቤ/ክ ስለማትከለክላችሁ እናንተም በዚያው በአዳራሻችሁ እኛም አባቶቻችን ባቆዩልን ቤ/መቅደስ እንገልገል አትረብሹን አትበጥብጡን፡፡ ጌታችን እንክርዳዱ ከስንዴው ጋር በዚህች ምድር እስከ አጨዳው ዘመን እንዲኖር ስለፈቀደ መኖር መብታችሁ ነው አትከለከሉም፤ ፍርዱ የጌታችን ነውና፡፡ እኛ ምንም እናምልክ ምን እናንተን አያገባችሁም ወንጌል ያልተዳረሰባቸው ስንት ቦታዎች እያሉ እኛን አማኞችን ለምን ታውኩናላችሁ፡፡ ትጋቱና ጽናቱ ካላችሁ ያላመኑትን አሳምኑ እኛን ተውን፤እኛ ጥንትም ዛሬም ነገም የጌታ ነንና አትድከሙ፡፡

  ReplyDelete
 5. “Thursday, July 12, 2012
  የግንቦቱ ውግዘት መነሻ የሆነው የማኅበረ ቅዱሳን ክስ ዶሴ፣ የሊቃውንት ጉባኤው ጥናት ውጤትና የሲኖዶሱ ቃለ ጉባኤ
  እነዚህን አራት ሰነዶች ስለሚከተሉት ምክንያቶች ለአንባቢያን አቅርበናል።
  1ኛ) ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ፥ የእውነተኞች የቤተ ክርስቲያን ልጆችን አንገት ያስደፋና አሳፋሪ ታሪክ ቢሆንም ታሪክ ነውና ለቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች እና ለመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች እንዲሁም ፍላጎት ላላቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ በቀላሉ እንዲያገኙት ለማቅረብ ወደድን።

  2ኛ) ውሸት እና ስህተት ዝም ከተባለ እንደ እውነት እና ትክክለኛ ነገር ስለሚቆጠር በክሱና በውግዘቱ ውስጥ «ኑፋቄ» በተባሉ ነጥቦች ዙሪያ ብዙ የምንለው ስላለን አስቀድመን ለአንባቢያን ጥሬ መረጃውን ማቅረቡ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። እነዚህን ሰነዶች ማንበቡ በሚቀጥሉት ቀናትና ሳምንታት የምናቀርባቸውን ጽሑፎች ለማገናዘብ ይጠቅማል።

  • የማኅበረ ቅዱሳን የክስ ዶሴ በግለሰቦች ላይ (21 ገጽ) ፦ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
  • የማኅበረ ቅዱሳን የክስ ዶሴ በማኅበራት ላይ (31 ገጽ) ፦ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
  • የሊቃውንት ጉባኤው ጥናት ውጤት በማኅበራት እና ግለሰቦች ላይ (49 ገጽ) ፦ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
  • የሲኖዶሱ ቃለ ጉባኤ እና ውግዘት (48 ገጽ) ፦ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

  መልካም ንባብ . . .” የሚለውን ፅሁፍ ማንበብ ስላልቻልኩኝ ቀጥሎ ባለው የኢ-ሜይል አድራሻ ላኩልኝ፡-
  dilnesabegeta@yahoo.com

  ReplyDelete
  Replies
  1. "ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ" የሚለውን በቀይ ቀለም የተጻፈውን ጽሁፍ ተጫነው ይከፈታል

   Delete
 6. እናንተ ምነው ሳናነበው አናሳችሁት እባካችሁ?NOT FOUND ERROR 404 እያለን ነው እኮ!መልሱልን እንጂ የእነዚህ ጉደኞ ታሪክ አያልቅ መቼም!!
  ዮሴፍ ነኝ
  ከአርማትያሱ

  ReplyDelete
 7. NOT FOUND ERROR 404 እያለ ስለሆነ እንደገና ጫኑት
  ወለቱ ከመቐለ

  ReplyDelete