Friday, August 31, 2012

በአገር ውስጥ በውጪም ያሉ አባቶችለቤተክርስቲያን አንድነት ሊሠሩ ይገባል

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ካንቀላፉ በኋላ ሲኖዶሱ ትልልቅ ስራዎች ከፊቱ ተደቅነዋል፡፡ አቡነ ጳውሎስ የተሸከሟቸውን ትልልቅ ሸክሞች የመሸከም ዕጣ ፈንታም በሲኖዶሱ ላይ ወድቋል፡፡ ከእነዚህም ዋናዎቹ አዲስ ፓትርያርክ መሰየምና በውጪ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጋር በመነጋገር ቤተክርስቲያኗ አንድ የምትሆንበትን ሥራ መስራት ነው፡፡

በዚህ ቤተክርስቲያኗ ፓትርያርኳን በሞት ባጣችበትና በዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ እየተመራች ባለችበት ወቅት ቤተክርስቲያን አንድ እንድትሆን የሚጠይቁ ወገኖች አሉ፡፡ በቅርቡ በብሎጋችን ላይ መግለጫዎቻቸውን ያወጡ በደቡብ አፍሪካ «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ቤሪያ ሰላም ዝክረ አበው የሰላምና አንድነት ማኅበር» እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ /ቤት» ቤተክርስቲያኒቱን አንድ ለማድረግ ጊዜው አሁን መሆኑንና የአንድነቱ ጉዳይ  እልባት ሳያገኝ ሌላ ፓትርያርክ የመሾሙ ጉዳይ እንዲታሰብበት የሚጠቁሙ መግለጫዎችን አውጥተዋል፡፡

Monday, August 27, 2012

Thursday, August 23, 2012

የቅዱስነታቸው ሥርአተ ቀብር በታላቅ ሥነስርአት ተፈጸመተቃዋሚዎቻቸው እንዳሰቡት ቀብራቸው ጭር አላለም
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሥርኣተ ቀብር ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2004 . ከቀኑ 730 በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅና በደመቀ ሥነስርአት ተፈጸመ፡፡ ቪዲዮ ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑሥርዓተ ቀብሩ ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ዝብ የተገኘ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸውን በሕይወተ ሥጋ እያሉ በተለይም በግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በማኅበረ ቅዱሳን መሪነት አድመውና ቡድን ፈጥረው እጅግ ሲቃወሟቸውና ሲያበሳጯቸው የነበሩ አንዳንድ ጳጳሳትን ጨምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የእህት አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ ተገኝተዋል፡፡

Tuesday, August 21, 2012

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስና ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ምን እንማራለን?

በዚያን ጊዜም ሰዎች መጥተው ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስላደባለቀው ስለ ገሊላ ሰዎች አወሩለት።
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ እነዚህ የገሊላ ሰዎች ይህ ስለ ደረሰባቸው ከገሊላ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ኃጢአተኞች የሆኑ ይመስሉአችኋልን?
እላችኋለሁ፥ አይደለም፤ ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ።
ወይስ በሰሌሆም ግንቡ የወደቀባቸውና የገደላቸው እነዚያ አሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሁሉ ይልቅ በደለኞች ይመስሉአችኋልን? አይደለም፥ እላችኋለሁ፤
ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።
(ሉቃ. 13፥1-5)
2004 ዓ.ም. አገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ታላላቅ ሰዎችን በሞት የተነጠቀችበት ዓመት ነው፡፡ የቤተክርስቲያናችንና የአገራችን መሪዎች ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እና የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንዲህ በአንድነት በሞት የተጠሩበት አጋጣሚም ያለ አይመስለንም፡፡ የመሪዎቻችን በአንድ ሰሞን በሞት መጠራትና የነገሮቹ ግጥምጥሞሾች በኢትዮጵያውያን ላይ ልዩ ልዩ ስሜት ፈጥሯል፡፡ ሁለቱንም መሪዎች የሚጠሏቸው ብዙዎቹ ሳይቀሩ አዝነዋል፡፡ ሌሎቹ የሚጠሏቸው ደግሞ ጸሎታቸው እንደተሰማ ቆጥረው ደስ ብሏቸው ይሆናል፡፡ እንዲህ የምንለው አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ በአቡነ ጳውሎስ ላይ ሲያሟርቱ የነበሩና የዘንድሮው በዓለ ሲመታቸው የመጨረሻቸው ነው ብለው የጻፉ ብሎጎች ስለነበሩ ነው፡፡ መለስ ዜናዊ ታመው በሕክምና ላይ እያሉ ሞታቸውን ብቻ ሲያቀነቅኑ የነበሩ ሚዲያዎችም ስለነበሩ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ላለፉት 21 ዓመታት ኢትዮጵያን የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ትናንት ከምሽቱ 5፡40 ሰዓት ላይ መሆኑን መግለጫው አመልክቶ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይፋ የሆነው ዛሬ ማለዳ ነው፡፡ በውጭ በሕክምና ሲረዱ በነበረበት ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዙሪያ «ሞቱ - አልሞቱም» የሚሉ የተለያዩ ወሬዎች ሲናፈሱ የቆዩ ቢሆንም መንግሥት በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አስታውቆ ነበር፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን እግዚአብሔር ሀገራችንን ወደተሻለ ሰላም እና የአንድነት መንፈስ እንዲመራልን ፈቃዱ ይሁን።

Monday, August 20, 2012

መሪ አልባውና በመንፈስ ቅዱስ ስም እመራለሁ እያለ በማቅ መመራቱን በተግባር እያሳየ ያለው ሲኖዶስ በሚለዋወጠው ውሳኔው ሕዝቡን ግራ እያጋባ ነው

በመጀመሪያ የሰጠውን መግለጫ የሚቃረንና ከበስተጀርባ ሽኩቻ መኖሩን የሚያሳይ ውሳኔ ያሳለፈው መሪ አልባው ሲኖዶስ፣ ያለ በቂ ምክንያት ከቅዱስነታቸው ሥርዓተ ቀብር በኋላ አከናውነዋለሁ ያለውን የዐቃቤ መንበር ምርጫ ጉዳይ እንደገና ለውጦ ዛሬ እርጅና የተጫጫናቸውንና ብዙም ጤና የሌላቸውን ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን በመሾም ያልተጠበቀ መግለጫ ሰጠ፡፡ ውሳኔውና መግለጫው ጊዜውን ያልጠበቀና የቅዱስነታቸው ስርአተ ቀብር ያልጠበቀ በመሆኑ ብዙዎችን ያሳዘነ ቢሆንም፣ እንደ ዳንኤል ክብረት ያሉት በፓትርያርኩ ዕለተ ሞት መሾም ነበረበት ይላል ሕጉ ብለው መከላከያ እያቀረቡ ነው፡፡ እስካሁን እየተሠራ ያለውን ድራማ በተመለከተ ሰፋ ያለ ዘገባ የምናቀርብ ሲሆን፣ ዛሬ የሚካሄደውን የዐቃቤ መንበር ምርጫ አስመልክቶ አውደ ምሕረት ብሎግ በሰበር ዜና በዋዜማው ያቀረበችውንና እውነት ሆኖ የተገኘውን ዜና እናቀርብላችኋለን፡፡ 

ሰበርዜና (ዐውደ ምህረት፤ ነሐሴ 13 2004 ዓ/ም)፡-በማኅበረ ቅዱሳን እየተዘወረ ያለውና መሪውን ያጣው ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስን ከአመራር ሰጪነት ለማውረድና ዐቃቤ መንበር በአፋጣኝ ለመሰየም ለነገ ቀጠሮ ይዟል

 • ማህበረ ቅዱሳን አቡነ ናትናኤል ይሁኑልኝ ብሏል።   
 •   ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ


  ሰበር ዜና (ዐውደ ምህረት፤ ነሐሴ 14 2004 ዓ/ም)፡ አቡነ ናትናኤል በአቃቤ መንበርነት ተሾሙ 

     ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

  የብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን እረፍት አስከትሎ እየወጡ ያሉ የሰላም እና የአንድነት መግለጫዎች

  በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ቤሪያ ሰላም ዝክረ አበው የሰላምና አንድነት ማህበር  በሀገር ቤት እንዲሁም በውጭው ዓለም ለሚገኙ ብጹአን አባቶች እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሚከተለውን መልዕክት ያስተላልፋል።  መግለጫው በሀገር ቤት ያሉ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለቤተ ክርስቲያኗ ሰላምና አንድነት ከሁሉም ቅድሚያ በመስጠት የተሰደዱት አራተኛውን ህጋዊ ፓትርያሪክ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱና የፈረሰው ቀኖና ተስተካክሎ የምእመናንን የአንድነት ጥያቄ እንዲመልሱ ይማጸናል።

  ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

   እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ጽ/ቤት  ቤተ ክርስቲያን ለወደፊቱ ተለያይታ እንዳትቀር ከሀገር ውጭና በሀገር ውስጥ ባሉት አባቶች መካከል ያለው ልዩነት በአንድነት ሳይፈታ ሌላ ፓትርያርክ የመተካቱን ጉዳይ ቅዱስ ሲኖዶስ ከወዲሁ በከፍተኛ አትኩሮት እንዲያስብበት የሚማጸነውን መግለጫ ከዚህ ቀጥሎ ማንበብ ይችላሉ።

  ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

  Sunday, August 19, 2012

  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ዜና ዕረፍት የሃይማኖት መሪዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጹ ነው

  ማኅበረ ቅዱሳን በቀጣዩ ፓትርያርክ ምርጫ ላይ ጣልቃ ለመግባት ቅስቀሳ ጀምሯል
  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አርፈዋል፡፡ በዘመናቸው ለቤተክርስቲያን፣ ለአገርና ለወገን ያበረከቷቸው እጅግ በርካታ ጠቃሚ ስራዎች አሉ፡፡ በተለይም ዛሬ በቤተክርስቲያኒቱ በተለይም በስብከተ ወንጌልና በመንፈሳውያን ኮሌጆች ዙሪያ የሚታየው ለውጥና የብዙዎች ሕይወት በእግዚአብሔር ቃል መለወጡ በቅዱስነታቸው ዘመን የታየ አንዱ ፍሬ ነው፡፡

  Friday, August 17, 2012

  የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሞት ለደጀ ሰላም ብሎግ ሰርግና ምላሽ ሆኗል

  የቅዱስነታቸው ድንገተኛ ዜና ዕረፍት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በብዙዎች ዘንድ ድንጋጤን የፈጠረ ቢሆንም የማኅበረ ቅዱሳን ድረገጽ የሆነው ደጀሰላም ደስታውን እየገለጸና ቅዱስነታቸው አርፈውም ለቅዱስነታቸው ያለውን ቅጥ ያጣ ጥላቻ እያስተጋባ መሆኑን ድረገጹ በዕለቱ ካወጣው ዘገባ መገንዘብ ተችሏል፡፡  

  ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያኒቱን በመሩባቸው ባለፉት 20 ዓመታት በርካታ ስራዎችን ሠርተዋል፤ ሰው እንደመሆናቸውም ሊሳሳቱ ይችላሉ፡፡ ቅዱስነታቸው በርካታ ለቤተክርስቲያኒቱ የሚጠቅሙና ቤተክርስቲያኒቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነት እንዲኖራት ማድረግ እንደቻሉ፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት መሆናቸው፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚደንት፣ የዓለም የሰላም አምባሳደር መሆናቸው በቂ ምስክር ነው፡፡ ይህም ቅዱስነታቸው በዲፕሎማሲው መስክ የተሳካላቸው ሰው በመሆናቸው የተገኘ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ይህን ጨምሮ በቅዱስነታቸው ዘመን የተሠሩ ለአገርና ለወገን የሚጠቅሙ በርካታ ሥራዎች መኖራቸው የሚካድ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ቅዱስነታቸው የሠሯቸው ብዙዎቹ ሥራዎች ለማቅ እንቅፋት በመሆናቸው፣ የቅዱስነታቸውን ስም በክፉ ብቻ እንጂ በመልካም አንሥተው የማያውቁት ደጀሰላምና ብጤዎቹ ብሎጎች፣ ቅዱስነታቸው አርፈውም ሳለ እርሳቸውን ማብጠልጠል መቀጠላቸው ብዙዎችን እያሳዘነ ነው፡፡ ለምሳሌ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን የመንፈሳዊ ኮሌጆች መስፋፋትና መጠናከር፣ በልማዳዊና ባህላዊ መንገድ ሃይማኖተኛ ነኝ ለሚለው ማቅ ትልቅ እንቅፋት ፈጥሮበት ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ስለሃይማኖት ምንም የማያውቀው ማቅ ቅዱስነታቸውን መናፍቅና የተሐድሶ መናፍቃን መሪ ናቸው በማለት፣ መንፈሳዊ ኮሌጆችም የመናፍቃን መፈልፈያ ሆነዋል እያለ ሲቀሰቅስ ቆይቷል፡፡ እስካሁን በሃይማኖት ሽፋን ሲንቀሳቀስ የኖረውና የመንፈሳዊነት አንዲት ጠብታ ቀርቶ ጥሩ ፖለቲከኛ እንኳን መሆን ያልቻሉት የማኅበሩ ብሎጎች በቅዱስነታቸው ሞት ደስታቸውን መግለጣቸው በብዙዎች ዘንድ ድንጋጤን ፈጥሯል፡፡

  Thursday, August 16, 2012

  ሰበር ዜና - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አረፉ

  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 5ኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በ76 ዓመታቸው ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ከቆዩ በኋላ ዛሬ ሌሊት ማረፋቸው ተሰማ፡፡ የቅዱስነታቸውን መሞት ተከትሎ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች በከፍተኛ ስብሰባ ተጠምደው አርፍደዋል፡፡ ስብሰባቸውንም ጨርሰው ወደጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ በመሄድ ግቢውን ወረውታል፡፡

  በየድረገጾቻቸው የዘንድሮው በዓለ ሲመታቸው የመጨረሻ ነው ሲሉ ያሟረቱት የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች ያሰቡት የተሳካላቸው መስሏል፡፡ ቀጣዩ ፓትርያርክ ማን ይሆናል? የሚለው ግን ትልቅ ጥያቄ እየፈጠረ ነው፡፡ እርሳቸውን ለመጣል አንድ የሆኑት ጳጳሳት ያ አንድነት አሁን አብሯቸው እንደማይሆንና ለአንዱ የፓትርያርክነት ወንበር እንደሚሟሟቱ ይጠበቃል፡፡ በኢየሱስ መሞት እንደተፋቀሩት እንደጲላጦስና ሄሮድስ ማቅ የያዛቸው ማኅበረ ቅዱሳንም የራሱን ሰው እንዳዘጋጀ ውስጥ አዋቂዎች እየተናገሩ ነው፡፡ ስብሰባውም ከዚህ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ታውቋል፡፡

  Sunday, August 12, 2012

  የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

  Read in PDF

  ክፍል 6
  በከሣቴ ብርሃን ማኅበር ላይ ኑፋቄ ተብለው ከቀረቡት መካከል ገድል ወይስ ገደል በተሰኘው መጽሐፍ ላይ የሊቃውንት ጉባኤውና ሲኖዶሱ በኑፋቄነት የፈረጁትንና አውግዘናል ያሏቸውን ሐሳቦች በክፍል 3 ጽሑፋችን ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ ከዚያ የቀጠለውን ሐሳብ ደግሞ በዚህ ክፍል እናቀርባለን፡፡ ብዙዎቹን የከሳቴ ብርሃን የተባሉትን ጽሑፎች ለማግኘት ስላልቻልን፣ ሲኖዶሱ ቀንጭቦና አዛብቶ ያቀረበውን ለመተቸት ተገደናል፡፡ የከሳቴ ብርሃንን ብዙዎቹን ጽሁፎች ማግኘት ብንችል ግን ከሲኖዶሱ ቅንጫቢ ጽሑፍ ጋር በማስተያየት ሚዛናዊ ዘገባ ማቅረብ በቻልን ነበር፡፡ እስካሁን ካቀረብናቸው ዘገባዎች ለመረዳት እንደተቻለው፣ ሲኖዶሱ ያጸደቀው የሊቃውንት ጉባኤው ጥናት በአብዛኛው የተወገዙትን ግለሰቦችና ማኅበራት ለመክሰስ እንዲመች ተቆርጦና ተቀጥሎ አንዳንዴም እነርሱ ያልጻፉትንና ያላሉትን እንዳሉ አስመስሎ ያቀረበ መሆኑን መጥቀስ እንፈልጋለን፡፡ የሊቃውንት ጉባኤውና ሲኖዶሱ ያስወግዛል ብለው ቆርጠውና ቀጥለው ያቀረቡት «ኑፋቄ» በእነርሱ እይታ እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስና በአበውም ትምህርት ትክክለኛ ትምህርት ነው፡፡ ስለዚህ ያወገዙት እውነትን ነው ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡ ለሁሉም በከሳቴ ብርሃን ላይ ኑፋቄ ተብለው የቀረቡትን ነጥቦች ወደ መተንተንና ኑፋቄ መሆን አለመሆናቸውን በእግዚአብሔር ቃል ወደመፈተሽ እንለፍ፡፡

  Wednesday, August 8, 2012

  “ያለ ወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም!” የሚለው ጥቅስ ምንጩ ማነው?

  በቅድሚያ የዚህ ጥቅስ ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ አለመሆኑን መናገር ያስፈልጋል፡፡ የዚህ እንግዳ ትምህርት ምንጭ መጽሐፍ ቅዱስ በፍጹም አይደለም፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ማን ነው የሚያድነው ተብሎ ቢጠየቅ መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (የሐዋርያት ሥራ 4፡12) በማለት ከኢየሱስ በቀር መዳን በሌላ በማንም እንደሌለ ይነግረናል፡፡ ልብ እንበል፤ በዚህ ጥቅስ ውስጥ “መዳን በሌላ በማንም የለም፤” የሚለው በአጽንኦት የተነገረ ቃል ነው፡፡ እንዲህ ማለት ያስፈለገውም እንድንበት ዘንድ ከሰማይ የተሰጠን ስም ኢየሱስ ብቻ ስለሆነ ነው በማለት ምክንያቱን ጭምር ይናገራል፡፡ ስለዚህ ይህን እውነት ተቃውሞ መጽሐፍ ቅዱስ “ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም” ሊል በፍጹም አይችልም፡፡ አላለምም፡፡

  Tuesday, August 7, 2012

  አውደ ምሕረት ብሎግ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳትታይ ከተከለከለች 10 ቀን አለፋት

  ኢትዮጵያ ውስጥ አውደ ምህረትን ለማንበብ www.awdemihret.wordpress.com ይጠቀሙ
  ማኅበረ ቅዱሳን በስውር ብሎጎቹ በኢንተርኔት ጫካዎች ውስጥ መሽጎ ህዝበ ክርስቲያኑን ሲያሳስት፣ ቤተክርስቲያንን ሲያምስ፣ የእርሱን አላማ የተቃወሙ በመሰሉት በፓትርያርኩና በሌሎችም አባቶች ላይ መሠረተ ቢስ የስም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት አባላቱና ሌሎችም ኦርቶዶክሳውያን ጥላቻ እንዲያድርባቸው በማድረግ ለተለያዩ አመፆች ሲቀሰቅስ መቆየቱና በዚሁ ተግባሩ የቀጠለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የእርሱን የተሳሳቱ ዘገባዎች ሚዛናዊ ለማድረግ ጥረት የሚያደርጉና የእርሱ ወደረኛ የሆኑ የተለያዩ ብሎጎች ብቅ ብቅ ብለው ኢንተርኔት ተከታታይ የሆነው ወገን ከአንድ አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን ከሌላም አቅጣጫ ዘገባዎችን እንዲያገኝና ሚዛናዊ አስተሳሰብን እንዲያዳብር የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ ማኅበረ ቅዱሳን የጻፈውን ብቻ ሳይሆን ሌሎቹስ ምን አሉ? የሚል ማኅበረሰብ መፍጠር ተችሏል፡፡

  Monday, August 6, 2012

  ማሕበረ ቅዱሳን ጉባኤ አርድዕት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከማንም በላይ ስጋት ላይ ጥሎኛል በማለት ለጳጳሳቱ 2.5 ሚሊዮን ብር በመበጀት የእግድ ደብዳቤ እንዲዘጋጅ አስደርጓል ተባለ።

  ከይሄ ነው እውነቱ
  (ምንጭ፦ ዐውደ ምሕረት/ www.awdemihret.blogspot.com / www.awdemihret.wordpress.com) የቅርብ ምንጮቻችን እንደገለጡት “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የተሰኘው በአገር ውስጥና በውጭ አገር ባጭር ጊዜ በርካታ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን እየማረከና እያስከተለ የመጣውን ጉባኤ ለማሳገድ ማኅበረ ቅዱሳን ለጳጳሳቱ ጉርሻ የሚሆን የ2.5 ሚሊየን ብር በጀት መደበ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የገንዘብ ምንጩ ከምን እንደሆነ እንዳይታወቅ እና ኦዲት እንዳይደረግ የሚታገለው ገንዘቡን እንዲህ ላለው ሕገ ወጥ ተግባር በስፋት ስለሚጠቀምበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአመራር አካላትና ከፍተኛ ሊቃውንትን ማዕከል ያደረገው ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ በከፍተኛ ደረጃ እያካሄደው ባለው ቅዱስ ተግባር ምክንያት የማሕበሩ ደጋፊ የሆኑት ጳጳሳት ካህናት ሰባክያንና ምእመናንን ቀልብ እየሳበ በመምጣቱ ማኅበረ ቅዱሳንን የተለመደውን ድጋፍ እንዳያገኝ  እያደረገው መምጣቱ ታውቋል።

  Thursday, August 2, 2012

  የሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በያዘው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል ወይ?

  ማኅበረ ቅዱሳን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቱን ሳያምንበትና እያወገዘው ካሳተመው የሊቀ ጉባኤ አባ አበራ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለቸውን ጽሑፎች አለፍ አለፍ እያልን ስናቀርብ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ መጽሐፉ ከገበያ መጥፋቱንና በአሮጌ ተራ ዋጋው እጅግ መናሩንም ጠቁመናል፡፡ አንዳንዶች ግን መጽሐፉ በድረገጽ ላይ መሰቀሉን ጠቁመውናል፡፡ ይህ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን የተነሣውን የሕትመቱን ጉዳይ አልፈውታል፡፡ በተጻፈው መጽሐፈ ቅዱሳዊ እውነት ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል ወይ የሚለውንም ለመመለስ ድፍረት ያገኙ አልመሰለንም፡፡ እኛ እስከምናውቀው ድረስ ግን ማቅ በዚህ መጽሐፍ ተጠቀሱትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ሲቃወምና በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቱ እንመራለን ያሉትን የቤተክርስቲያን ልጆች ሲያወግዝ ነው የኖረው፡፡ ለዛሬው ይህን ጥያቄ እናቅርብ፤ ሊቀ ጉባኤ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገውን (በተወሰነ መልኩ ትውፊትንም ጨምረዋል) ስለጸጋ የጻፉትን ማቅ ያምንበታል ወይ? እስኪ ከመጽሐፉ የሚከተለውን እንመልከት (ትምህርት ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት ከገጽ 234-237 የተወሰደ)