Tuesday, August 7, 2012

አውደ ምሕረት ብሎግ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳትታይ ከተከለከለች 10 ቀን አለፋት

ኢትዮጵያ ውስጥ አውደ ምህረትን ለማንበብ www.awdemihret.wordpress.com ይጠቀሙ
ማኅበረ ቅዱሳን በስውር ብሎጎቹ በኢንተርኔት ጫካዎች ውስጥ መሽጎ ህዝበ ክርስቲያኑን ሲያሳስት፣ ቤተክርስቲያንን ሲያምስ፣ የእርሱን አላማ የተቃወሙ በመሰሉት በፓትርያርኩና በሌሎችም አባቶች ላይ መሠረተ ቢስ የስም ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት አባላቱና ሌሎችም ኦርቶዶክሳውያን ጥላቻ እንዲያድርባቸው በማድረግ ለተለያዩ አመፆች ሲቀሰቅስ መቆየቱና በዚሁ ተግባሩ የቀጠለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የእርሱን የተሳሳቱ ዘገባዎች ሚዛናዊ ለማድረግ ጥረት የሚያደርጉና የእርሱ ወደረኛ የሆኑ የተለያዩ ብሎጎች ብቅ ብቅ ብለው ኢንተርኔት ተከታታይ የሆነው ወገን ከአንድ አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን ከሌላም አቅጣጫ ዘገባዎችን እንዲያገኝና ሚዛናዊ አስተሳሰብን እንዲያዳብር የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ስለዚህ ዛሬ ማኅበረ ቅዱሳን የጻፈውን ብቻ ሳይሆን ሌሎቹስ ምን አሉ? የሚል ማኅበረሰብ መፍጠር ተችሏል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳንን ሐሰተኛ ዘገባ በመተንተንና በተጨባጭ ማስረጃዎች በማክሸፍ ህዝቡ ሚዛናዊ መረጃ እንዲያገኝ እያደረገ ያለውና በአጭር ጊዜ ብዙ ተመልካቾችን ያፈራው አውደ ምሕረት ብሎግ በአገር ውስጥ እንዳይታይ ብሎክ ተደርጓል፡፡ ትኩረቱን ማኅበረ ቅዱሳን ላይ አድርጎ የተለያዩ ዘገባዎችን ሲያቀርብ የነበረው አውደ ምሕረት ብሎግ፣ ካለፈው አርብ ሳምንት ጀምሮ በአገር ውስጥ እንዳይታይ ተደርጓል፣ ከዚህ በስተ ጀርባ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ስውር እጁን የዘረጋው ማኅበረ ቅዱሳን እንዳለም እየተነገረ ነው፡፡ እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ ብሎጉ ትኩረት ያደረገው በማኅበረ ቅዱሳን ላይ በመሆኑና የእርሱን እኩይ ተግባር እየተከታተለ በመዘገብና ለሕዝብ ይፋ በማድረግ በቤተክርስቲያንና በአገር ላይ የደቀነውን አደጋ በማጋለጥ ስለ ማኅበሩ ውስጠ ማንነት ለህዝቡ እያቀበለ ባለው መረጃ ብዙዎች ማኅበሩ ማን እንደሆነ እያወቁት መጥተዋል፡፡ በተለይም በቅርቡ ማኅበሩ ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳውን ለማስፈጸም የዋልድባን ጉዳይ በመለጠጥና ለፖለቲካ ፍጆታ አውሎ በ«ስውር» ብሎጎቹ በመጠቀም በተለይ በውጪ ያለውን ሕዝብ ሲቀሰቅስ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህንንም እግር በእግር እየተከታተለ የማኅበሩን ፕሮፓጋንዳ በማክሸፍ ሚዛናዊ ዘገባ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ እንደምንጮቻችን ከሆነ በብሎጉ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰበት ማኅበሩ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሰገሰጋቸው ስውር እጆቹን ተጠቅሞ አውደምሕረት ብሎክ ማስደረጉን ይናገራሉ፡፡
በአውደ ምሕረት ብሎግ ውስጥ  ውስጥ አዋቂ የማኅበረ ቅዱሳን አንዳንድ አባላት እንደሚገኙበት በየጊዜው ከማኅበሩ ሾልከው ከሚወጡና አውደ ምሕረት ላይ ከሚነበቡ ዘገባዎች መገንዘብ የሚቻል ሲሆን፣ ይህም ማኅበሩ ከውጪ ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ከራሱ አባላት ጭምር ጥላቻን እያፈራና ተቃውሞ እየደረሰበት መሆኑን የሚያመለክት አንድ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ በዚህ ደስ ያልተሰኘው ማኅበረ ቅዱሳን ብሎጉን ለማዘጋት በከፍተኛ ሁኔታ ሲንቀሳቀስ እንደነበረ የሚናገሩት ውስጥ አዋቂዎች፣ አንዳንድ ጥገኛ አስተሳሰብ ባላቸውና በመንግስት መዋቅር ውስጥ በሚገኙ ስውር እጆቹ ተጠቅሞ ብሎጉን እንዳዘጋው እየተነገረ ነው፡፡
አውደ ምህረት ለውጭ አንባቢዎችዋ በቀድሞ አድራሻዋ ሊያገኙዋት የሚችሉ ሲሆን የአገር ውስጥ አንባቢዎችዋ ግን በአዲሱ አድራሻዋ www.awdemihret.wordpress.com ሊያገኙዋት ይችላሉ፡፡

15 comments:

 1. ...lol. You guys are funny: You start your article with "...በስውር ብሎጎቹ በኢንተርኔት ጫካዎች ውስጥ መሽጎ ህዝበ ክርስቲያኑን ሲያሳስት፣ ቤተክርስቲያንን ሲያምስ..." We know where Mahiber Kidusan office is, but you don't have any physical address or location. You are just in the cyber world. So, I just read your article as it is written about you. lol... Anyways, we know you guys... you come to destroy our church. You are just a wolfe!

  ReplyDelete
 2. Kesis Negne K Denver!!August 7, 2012 at 2:32 PM

  Awude Miheret, Enkuan LE Akime Egid Abekashi!!!!!!!! Berichi Belulin Betam Ye Mahiberun Ekuy Tegibar Asawikanalech Abatochinim Endinakebir Ereditanalechinaaaaaaaa

  ReplyDelete
 3. ማቅ ክፉ እርከስ መንፈስ ያደረበት ስለሆነ የሐይማኖት ፍቅር ወይንም የእግዚአብሄር ቃል የማይገድበውና እግዚአብሄርን የማይፈራ ማህበር ነው። ሁሉንም በገንዘብ እየደጎመ ለሌውን ማጥፋት ነው።በመጨረሻዉ ዘመን የሚነሱት ሰዎች ጨካኝ ሰሰውም የማይራሩ ናቸው ተብሎ በቅዱስ ቃሉ የተነገረው ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ግድ ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ ተዋህዶ ልጆች ነቅተውበታል በማቅ ላይ። ለዚህም ነው እውነትን የሚያጡ እንደ እነ አውደ ምህረት ያሎት website ለመዝጋት የሚታገለው። ከሰማይ ከአምላክ ዘንድ ካልሆነ የሰው ክፋት ለእራሱ ነው የሚደርሰው። ሰዉ የእጁን አያጣም ሐማም የእጁን አግኝቷዋል። አውደ ምህረቶች በርቱ ጠንክሩ ያለ ፈተና ዉጤት የለምና ። አምላካችንም እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስም ያሁሉ ፈተና ተቀብሎ እኛን ነፃ አውጥቶተናል።

  ReplyDelete
 4. It is impossible to hide the truth for ever!
  If you try to cover it from here, it bursts on the othe side!!!
  Above all, God is against MK's hidden agenda.
  If MK decides to stay in the church, it has to stop poisoning the church with politics.

  ReplyDelete
 5. ይገርማል ይገርማል ይገርማል ለማመን የሚያስቸገር ነገር ነው የምታስነብቡን እኔ ደግሞ ምን ሆኑ ዐውደምህረቶች እያልኩ ማንን እንደምጠይቅ ግራ ገብቶኝ ለካ ጉዱ እዚያው ነበር ያለው ይሄነው ይሏችኋል መንፈሳዊ ጦርነት በርቱ!ደግሞ እየተጋገዛችሁ መዋጋታችሁ መልካም ነው እንዲህ እንደሚል ቃሉ >>2ኛ ነገሥት 10:9-12)ተረዳዱ ዓላማችሁ አንድ ስለሆነ<እኛም ከጀርባችሁ ነን!እኒህ ቅዱስ አባታችን እስካሉ ትግላችሁን አታቁርጡ በኋላ ደግሞ ለመ
  ንግሥቱ የሚቆረቆረው አምላካችን የበለጠ ነገር ያደርጋል::
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 6. Believe it or not MK will continue with strength.

  Thanks to The Almighty God Jesus Christ.

  May our Mother & Lady Bless MK.

  ReplyDelete
 7. Maninetachihun yegelete Egziabher yimesgen. Mahibere Kidusanin Egziabiher Yatenkirilen. Hulchinim be Amlak fekad kegonu nen EWUNETIN SILEYAZE.

  ReplyDelete
 8. On the Insert tab, the galleries include items that are designed to coordinate with the overall look of your document. You can use these galleries to insert tables, headers, footers, lists, cover pages, and other document building blocks. When you create pictures, charts, or diagrams, they also coordinate with your current document look. You can easily change the formatting of selected text in the document text by choosing a look for the selected text from the Quick Styles gallery on the Home tab. You can also format text directly by using the other controls on the Home tab. Most controls offer a choice of using the look from the current theme or using a format that you specify directly. To change the overall look of your document, choose new Theme elements on the Page Layout tab. To change the looks available in the Quick Style gallery, use the Change Current Quick Style Set command. Both the Themes gallery and the Quick Styles gallery provide reset commands so that you can always restore the look of your document to the original contained in your current template. On the Insert tab, the galleries include items that are designed to coordinate with the overall look of your document.
  You can use these galleries to insert tables, headers, footers, lists, cover pages, and other document building blocks. When you create pictures, charts, or diagrams, they also coordinate with your current document look. You can easily change the formatting of selected text in the document text by choosing a look for the selected text from the Quick Styles gallery on the Home tab. You can also format text directly by using the other controls on the Home tab. Most controls offer a choice of using the look from the current theme or using a format that you specify directly. To change the overall look of your document, choose new Theme elements on the Page Layout tab. To change the looks available in the Quick Style gallery, use the Change Current Quick Style Set command. Both the Themes gallery and the Quick Styles gallery provide reset commands so that you can always restore the look of your document to the original contained in your current template. On the Insert tab, the galleries include items that are designed to coordinate with the overall look of your document. You can use these galleries to insert tables, headers, footers, lists, cover pages, and other document building blocks.

  ReplyDelete
 9. እየተከታተለ የማኅበሩን ፕሮፓጋንዳ በማክሸፍ ሚዛናዊ ዘገባ ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ እንደምንጮቻችን ከሆነ በብሎጉ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰበት ማኅበሩ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሰገሰጋቸው ስውር እጆቹን ተጠቅሞ አውደምሕረት ብሎክ ማስደረጉን ይናገራሉ፡፡
  በአውደ ምሕረት ብሎግ ውስጥ ውስጥ አዋቂ የማኅበረ ቅዱሳን አንዳንድ አባላት እንደሚገኙበት በየጊዜው ከማኅበሩ ሾልከው ከሚወጡና አውደ ምሕረት ላይ ከሚነበቡ ዘገባዎች መገንዘብ የሚቻል ሲሆን፣ ይህም ማኅበሩ ከውጪ ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ከራሱ አባላት ጭምር ጥላቻን እያፈራና ተቃውሞ እየደረሰበት መሆኑን የሚያመለክት አንድ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ በዚህ ደስ ያልተሰኘው ማኅበረ ቅዱሳን ብሎጉን ለማዘጋት በከፍተኛ ሁኔታ ሲንቀሳቀስ እንደነበረ የሚናገሩት ውስጥ አዋቂዎች፣ አንዳንድ ጥገኛ አስተሳሰብ ባላቸውና በመንግስት መዋቅር ውስጥ በሚገኙ ስውር እጆቹ ተጠቅሞ ብሎጉን እንዳዘጋው እየተነገረ ነው፡፡

  ReplyDelete
 10. ወረኛ በሙሉ ማኅበረ ቅዱሳን ብሎጉን እንዳይታይ አደረገው ስትሉ ትንሽ አታፍሩም። ለነገሩ ከእንክርዳድ ምን ይለቀማል። በፍርድ ቀንም መንግሥተ ሰማያት እንዳንገባ ያደረገን ማኅበረ ቅዱሳን ነው ሳትሉ አትቀሩም። ቱሉቱላ . . .

  ReplyDelete
  Replies
  1. nonymousAugust 8, 2012 4:36 PM

   ወረኛ በሙሉ ማኅበረ ቅዱሳን ብሎጉን እንዳይታይ አደረገው ስትሉ ትንሽ አታፍሩም። ለነገሩ ከእንክርዳድ ምን ይለቀማል። በፍርድ ቀንም መንግሥተ ሰማያት እንዳንገባ ያደረገን ማኅበረ ቅዱሳን ነው ሳትሉ አትቀሩም። ቱሉቱላ .

   Delete
 11. ሁሉ ቃልቻ ማን ይሸከም ስልቻ፤ ሁሉም በየቤቱ ጻድቅ ቅዱስና እውነተኛ ነኝ ባይ ከሆነ የዚህ ወይም
  የዚያ ማኅበር አባል ያልሆነ ወይም ራሱን ቅዱስ ነኝ ብሎ ለሠየመው አካል አጎብዳጅ ካልሆነ እንደሚያሳድዱት በላይኛውም ሀገር ለማሳደድ ሙከራ ያደርጉ ነበር፤ ዳሩ ግን ምድራውያን አሳዳጆች የሰማይ ተሰዳጆች ይሆናሉና ሳይታለም የተተረጎመ ነው(ጅብ ሊሠር ሄዶ ተሠሮ ገባ)በብዛታቸው በጉልበታቸው በተንኮላቸው ሰዎችን የሚያሳድዱ የሚያስወግዙና የሚያወግዙ ሁሉ በፈጣሪ ዘንድ ተቀባይነት
  አያገኙም፤ በሰው ዘንድ አቦ አቦ(ቅዱሳን) የተሰኙ በፈጣሪ ዘንድ ዋጋ ቢስ ናቸው፤ እንደተጻፈ ሉቃ 16
  14-15 እስመ በኀበ ሰብእ ዐቢይ በኀበ እግዚአብሔር ትሑት ወምኑን ውእቱ(What is highly valued among men is detestable in God` s sight.

  ReplyDelete
 12. woy aba selamawoch,taskalachu hulgeze sidebergn lemesak sifeleg tazenanugnlachuna ekuy tegebar ayalkemeena EGEZIABHAIR wode eunet menged eskimelesachu ....bertu ke diablos gar.

  ReplyDelete
 13. yegna tul tula aydekemachum ende?

  ReplyDelete
 14. We are not as yours we are as ours we are vigilant people,
  we teach you until you come back to your mental home by repentance.

  ReplyDelete