Monday, August 6, 2012

ማሕበረ ቅዱሳን ጉባኤ አርድዕት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከማንም በላይ ስጋት ላይ ጥሎኛል በማለት ለጳጳሳቱ 2.5 ሚሊዮን ብር በመበጀት የእግድ ደብዳቤ እንዲዘጋጅ አስደርጓል ተባለ።

ከይሄ ነው እውነቱ
(ምንጭ፦ ዐውደ ምሕረት/ www.awdemihret.blogspot.com / www.awdemihret.wordpress.com) የቅርብ ምንጮቻችን እንደገለጡት “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የተሰኘው በአገር ውስጥና በውጭ አገር ባጭር ጊዜ በርካታ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን እየማረከና እያስከተለ የመጣውን ጉባኤ ለማሳገድ ማኅበረ ቅዱሳን ለጳጳሳቱ ጉርሻ የሚሆን የ2.5 ሚሊየን ብር በጀት መደበ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የገንዘብ ምንጩ ከምን እንደሆነ እንዳይታወቅ እና ኦዲት እንዳይደረግ የሚታገለው ገንዘቡን እንዲህ ላለው ሕገ ወጥ ተግባር በስፋት ስለሚጠቀምበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአመራር አካላትና ከፍተኛ ሊቃውንትን ማዕከል ያደረገው ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ በከፍተኛ ደረጃ እያካሄደው ባለው ቅዱስ ተግባር ምክንያት የማሕበሩ ደጋፊ የሆኑት ጳጳሳት ካህናት ሰባክያንና ምእመናንን ቀልብ እየሳበ በመምጣቱ ማኅበረ ቅዱሳንን የተለመደውን ድጋፍ እንዳያገኝ  እያደረገው መምጣቱ ታውቋል።
ከዚህ በፊት ሁሉንም የቤተክርስቲያኒቱ አካላት በተለያየ መንገድ እየከፋፈለ ቤተክርስቲያኒቱን ለውድቀት እያፋጠነ የቆየውና ያለው ማሕበረ ቅዱሳን በተለይ በአሁኑ ሰዓት ከአክራሪዎችና ከፖለቲከኞች ጋር ግንባር በመፍጠር እያካሄደ ያለውን እኩይ ተግባር እየተጋለጠበት በመምጣቱና በአገር ውስጥና በውጭ አገርም ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት በመምጣቱ ከዚህ ያድኑኛል ያላቸውን አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስንና አቶ ተስፋዬ ውብሸትን(የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ) በመደበው በጅት በመደለል  በዋና ሥራ አስኪያጁ በአቡነ ፊልጶስ እና በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ ሕዝቅኤል አማካኝነት “ጉባኤ አርድእትን “ አናውቀውም ይታገድልን የሚል ደብዳቤ እንደሚያጽፉ የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸዋል። 

 ከዚህ በፊት እንደገለጽነው አቶ እስክንድር  ከመንግሥት ሥራ ከተባረረ በኋላ ሙሰኞች ወደ የማይባረሩባት ቤተክህነት በመግባት ከግብረ አበሩ ጋር በመሆን ከፍተኛ ምዝበራ እየፈጸመ ያለ ግለሰብ ሲሆን በተለያየ ጊዜ ከማሕበረ ቅዱሳን የአመራር አካላት ጋር ባደረገው ስብሰባ ጳጳሳቱ የግል ቤት በመገንባትና በተለያየ ሥራ የተጠመዱ በመሆናቸው ገንዘብ ስለሚያስፈልጋቸው ለሁሉም የሚከፋፈል 2.5. ሚሊዮን  ብር ከመደባችሁ የእግድ ደብዳቤ ማጻፍ ይቻላል በማለት የማኅበረ ቅዱሳንን ሰዎች  ያሳመነ ሲሆን ጉባኤ አርድእትንም የሚመለከተውን የእግድ ደብዳቤ ለማጻፍ ቅድመ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ታውቋል። ገንዘቡን ለማግኘት  እነ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስና አቶ ተስፋዪ ውብሸት  የተጠቀሙበት ዘዴ አሁን ማሕበሩ  ይህንን ካላደረገ  ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ጉባኤው የጉባኤ አርድእትን መተዳደሪያ ደንብ ያጸድቅለታል። የሚል ሲሆን ይህም ከጉባኤ አርድእት ዓላማ ውጭ እንደሆነ ታውቋል። ምክንያቱም በጉባኤ አርድእት መመስረቻ ጽሑፍ እንደተገለጸው ጉባኤ አርድእት ጉባኤና የቤተክርስቲያኒቱ አካል በመሆኑ በአሏት ሕገ ደንቦች የሚመራ እንጂ  ማሕበር ስለአይደለ የሚጸድቅም ሆነ የሚታገድ መተዳደሪያ ደንብ ስለሌለው ነው፡፡
በመሆኑም  ሐሳብንም ሆነ መንፈስን ሊያግድ የሚችል አካል ስለሌለ ጉባኤው ሊታገድ የሚችል ነገር የለውም። የጉባኤ አርድእትን ራእይ ተልእኮና ዓላማ አግዳለሁ የሚል ካለ በአጠቃላይ የቤተክርስቲያኒቱን ሊቃውንትን ካህናትን ሰባክያንንና ዲያቆናትንን ከቤተክርስቲያኒቱ አስወግዳለሁ ብሎ እንደ መነሳት ነው።
ስለዚህ እነ እስክንድር ባወጡት ዕቅድ አማካኝነት ይህ የተባለው ደብዳቤ ቢወጣ “ጉባኤ አርድእትን በበለጠ ያጠናክረዋል፤ ያስተዋውቀዋል እየተባለ ሲሆን  በአንጻሩም የማሕበሩን እኩይ ተግባርና የእነዚህን አባቶች ነን ባዮች ጥቅማዊ ተልእኮ አግዝፎ እንደሚያሳይ ብዙዎች ይስማማሉ። የእግዱን ደብዳቤ በቶሎ እንዲጽፉ አቡነ ፊሊጶስና አቡነ ሕዝቅኤል እየተወተወቱ ሲሆን ደጀ ሰላምም ዜናውን ሰርታ ጨርሳ ለመልቀቅ ደብዳቤው እየጠበቀች መሆኑን ማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ ያሉን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ ከተወሰነ ጳጰሳት በቀር ለአብዛኛዎቹ ጳጳሳት በነብስ ወከፍ 50000 ሺህ ብር ይደርሳቸዋል የተባለለት የእጅ መንሻ ብር ጳጳሳቱን አየር ዳባሽ ውሳኔ ያስወስናቸው ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  
ሌላው አቶ ተስፋዬ ውብሸና አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ  የመንግሥት ታማኞች ነን፤ ማሕበረ ቅዱሳንን በጥብብ ለመጣል ልዩ ስተራቴጂ ከሚመለከተው አካል ጋር ቀርጸናል፡፡ ጳጳሳቱንም በየክፍሉ ለያይተናቸዋል፤ ዕርቅ ብለን በማስገባት እንዘጋቸዋለን። በማለት ቅዱስ ፓትርያሪኩን እያወናበዱ የፓትርያርኩን ውድቀት እያመቻቹ እንደ ሆነ ተነግሯል። ለዚህም ምንጮች እንደመረጃ አድርገው የሚያቀርቡት፤
1 የቤተክርስቲያኒቱ የ53ኛ ነጻነት መታሰቢያ በዐልና የቅዱስ ፓትርያርኩ የ20ኛ በዐለ ሢመት አከባበር የደመቀ እንዲሆን የሁሉም አህጉረ ስብከት ሥራአስኪያጆች እንዲገኙ እንዲወሰን የቀረበውን ሐሳብ ዋና ሥራአስኪያጁ ሲቃመሙት እሳቸውን በማሳመን እንዲመጡ ከተወሰነ በኋላ የሊቀጳጳሱን ሀሳብ በመጠምዘዝ እንዳይመጡ ማስደረጋቸው፡
2 በ1991 የወጣው ሕገ ቤተክርስቲያን  እንዲሻሻል የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት  ጥረት ሲያደርጉ እነአቶ እስክንድር ግን ጉዳዩን ለማጓተት በአስተዳደር ጉባኤ ወስነናል በማለት ሲያጨበረብሩ ቆይተው በመጨረሻ ሐሰት ሆኖ መገኘቱ፤
3 በትንሣኤ ዘጉባኤ ሊሠራ የታቀደውን ሕንጻ ከዋና ሥራአስኪያጁ ጋር በመሆን ክፉኛ መቃወማቸው፡
4 ጌታችን በቅዱስ ወንጌል፡ እነዚህ ሕጻናት ዝም ቢሉም ድንጋዮች ያመሰግናሉ እንዳለው፡ በቅዱስ ፓትርያርኩ ጉያ ሥር የተደበቁት እነእስክንድርና መሰሎቻቸው ሁሉ በቅዱስ ፓትርያርኩ የ20ኛ በዓለ ሢመት አከባበር ላይ የተቃውሞ ደምጽ ሲያሰሙ ራእይ ለትውልድ በተባለው ድርጅት በቀረበው እጅግ የተዋጣለት ፕሮግራም ተቃውሞ ማሰማታቸው፤
5ኛ በተመሳሳይ መልኩ በክራውን ሆቴል በተደረገ ግሩምና ድንቅ በዐል ተመሳሳይ አቋም መያዛቸው ሁለቱ ግለሰቦች ሌላ ተልዕኮ ያላቸው መሆኑን በግለጽ ያሳያል ይላሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ተስፋዩ ውብሸት የአቶ ገዛኸኝ ወንድም ሲሆን አቶ ገዛኸን ከዚህ ቀደም ማለትም በ1986 ዓ/ም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ጸሐፊ በመሆን በቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ትርምስ የፈጠረና ማሕበረቅዱሳንን በበለጥ እንዲጠናከረ ያደረገ ሰው ሲሆን ከቤተክህነት ከተባረረ ጊዜ ጀምሮም የዚህ ክፋት የተሞላበት ማሕበር ዋና ደጋፊና አቶ ተስፋዬንም ወደ ክፋት ጎዳና እየነዳ ያለ ሰው ነው፡፡ አሁንም ወንድሙ አቶ ተስፋዩ ውብሸት አንድም የቤተክርስቲያኒቱ ዕውቀት ሳይኖረውና በዘመናዊም  ይህ ነው የሚባል እውቀት  ሳይኖረው የቤቶችና ሕንጻዎች ድርጅት ዋና ሥራአስኪያጅና የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራአስኪያጅ በመሆን ቤተክርስቲያኒቱን እያመሳት ይገኛል፡
ስለዚህ ማሕበረ ቅዱሳን የተባለው ቀንደኛ ጥቅመኛና የፓለቲካ ደርጀት እነዚህን አካላት መሠረት አድርጎ ቤተክርስቲያናችን ለመታደግ ቆርጠው የተነሱትን ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በመቃዎም ሌት ተቀን እየጣረ ይገኛል። አሁንም ድረስ ለብዙዎች እንቆቅልሽ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን የጉባኤ አርድእትን ጥላ እያየ እንዲህ የመርበድበደዱ ሚሥጢር ነው፡፡ አንዳንዶች ይህን የማኅበሩን ሁኔታ በጋዜጣ ላይ የሽጉጥ ስእል አይቶ በድንጋጤ ፖሊስ ከሚጠራ ንክ ሰው ጋር ያመሳስሉታል፡፡     

8 comments:

 1. Hulum wushet, Tehadeso yet tigebi, mederesha atash aydele

  ReplyDelete
 2. Egzioo Min Nekachew mk Ahun Yihen bir Achebrebrew ke wch ager yalu meemenan asratachewn yesebesebewen le papasat yisetal egzioo zendero gubo ayena gubo tekeba abatena lij min yebalala lemanegnawem Gubae Ardit temseretual min yibelu eltric yiyazu keahun behuala mk alekoleshal yebtekeresteyan lijochen masaded ok yigebash kegbash achebrebari hula anchi dejesela negn bay mk anchin belo kresteyan kersetyan yehone sew kahena weyim papasat kerto tera yehone sew ayesadebibm anchi gi ke gebre aberohesh gar honesh abatochn metesadebi weyeu lanchii weyeee eperm eshetttt anet poletikegna wenbede usa tekemetehe ke esat gar metadergew neger hulu tawekobehal dejeselama ebakachehu bertu bezu sera ke enanete yitebekal brtu yedingil lij medehaniyalem yiredachehu amen ehetachehu negnn ke Germen

  ReplyDelete
 3. አልሰሜን ግባ በለው የማይሰማ የለም፤ ጉባኤ አርድዕት/ ጉባኤ አራጅ/ ህገ ወጥ ስለሆነ ተዘግቷል በቤጸክኅነጽ ደረጃ /፤ በህገ ወጥ ይቻላል ድሮስ ተሐድሶ መናፍቅ በየሜዳው መሰባሰብ/ አዳራሽ/ በጎችን መስረቅ የለመደው ነው ምን ፈቃድ ያስፈልጋል፡፤

  ReplyDelete
 4. እግዚአብሄር የአስነሳውን ማን ያስቆማል? ማቅ የሰበሰበውን ንዋይ ለክፉ ስራ ከማዋልና ለጥፋት ከመበተን አይመለስም። ትግስቱን እግዚአብሔር ይስጠን አንጅ አርድእት ገና ብዙ ሥራዎቸን አምላካችን ያሰራዋል።ማቅ በቁሙ የሞተ ማህበር ስለሆነ እንድሁ ነፍሱ እስክትወጣ ይፈራገጠላ።በአሁኑ ወቅት የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናዋን እየጣሰ እምነቱን በማዳከም ላይ የሚገኘው የጨለማ አባት ከፉ መንፈስ ያደረበት ማቅ ቁልቁል እየሄደ ስለሆነ ከብር ለአምላካችን ይሁን

  ReplyDelete
 5. ይወድስከ አፈ ነኪር ወአኮ አፈ ዚአከ(ሌላ ያወድስህ እንጂ የገዛ አፍህ አይለም)የሚለውን ያላየ ያልሰማ
  ወይም እያየ እየሰማ የማይረዳ የማይለማ ማቅ የጊዜው ሐሳዊ መሲሕ በመሆኑ ጳጳሳቱን በገንዘብ ድጎማ መከፋፈሉ ባህል እየሆነ መጥቷል፤ጳጳሳቱም የክፉ ሁሉ ምንጭ ገንዘብ መውደድ መሆኑን እያወቁ እንዳላወቁ እውነተኛ አማኞችን እያጨቃጨቁ ይገኛሉ፤የዘመኑ የተለያዩ ሐሳውያነ መሲሕ ማኅበራት ቤተ ክርስቲያንን ለማደናገርና ግራ ለማጋባት ተቋቁመዋል በቀዋሚ ፍቅር ሳይሆን በጊዚያዊ ብር ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ በጨለማው ዓለም ገዥ ተመድበዋል፤መንጋዎቹን ለማሰባሰብ ሳይሆን ለመበታተን እስከሆነ
  ድረስ ትርጉሙና ውጤቱ ምንድነው? ማኅበር ማለት መተባበር ተስማምቶ ባንድነት መኖር ነበር ካልሆነ
  ሳይሆኑ ነን የሚሉ ሆሉ የጨለማው ዓለም ገዥ አሻክርት ናቸው፤ራዕ ዮሓ.2 .2-3

  ReplyDelete
 6. አይ ድንቁርና!! እንደው በአሁን ጊዜ የሚጻፍ ስንት ሞልቶ በሬ ወለደ እያላችሁ ባትተበትቡ ጥሩ ነበር። እንደው ስታስቡት ማህበረ ቅዱሳን 2.5 ሚሊዮን የሚሰጠው ምን ለማግኘት ነው? ጉባኤ አርድዕት እኮ ከታረደ ከርሟል እኮ። ስታስቡት ማህበረ ቅዱሳን በሆዳቸው የሚያስቡ የደደቦች ክምችት ይመስላችኋልን? ስንት ምሁራን የታጨቁበት መሆኑን ማወቅ ግድ ይላል። ስለዚህ እባካችሁ ጸሃፊዎቹም ሆናችሁ አስተያየት ሰጪዎቹ በግብታዊነት እና በውሸት አትጻፉ። ካልገባችሁ ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ግልጽ አሰራር ስላለው ጠይቃችሁ ተረዱ።

  ReplyDelete
 7. የራሷን ታሳርራለች የሰውን ታማስላለች (ጠይቅችሁ ተረዱ)አዬ ጉድ! እናተ ለመሆኑ ለመረዳት ቀርቶ
  ለመጠየቅ ራሳችሁን አቅንታችኋል ወይ? ይህም ይቅርና በሥርዓት እጅን በማውጣት ወደተጠያቂው
  ቀርባችኋል ወይ? ይልቁንም ከመደናቆር ራስን መመርመር እናም አፍትን ርእሰከ ለካህን ማቴ 8/1-4
  አ'እምሮ ወዳለው ሄዶ ክፋትን መናዘዝና መንገር ከዚያም ለበጎ ሥራ መተባበር ነው፤

  ReplyDelete
 8. Well,what you have exposed might be true or untrue.Anyway,I know Mk.Better than you.Please,be humble and develop Jesus
  -like attitude.You can learn a lot from history that Ethiopia never fall by the conspiracy of devils agents.Many devils agents have tried their best to annihilate the peoples faith.you never succeed in the attack being judea in
  and PHARISES OUTSIDE.ADAM FAILED DOE TO GLUTTONY.YOU ALSO
  WILL FAIL SOON.YOU HAD BETTER REPENT AND BE MEN.

  ReplyDelete