Thursday, August 2, 2012

የሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በያዘው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል ወይ?

ማኅበረ ቅዱሳን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቱን ሳያምንበትና እያወገዘው ካሳተመው የሊቀ ጉባኤ አባ አበራ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለቸውን ጽሑፎች አለፍ አለፍ እያልን ስናቀርብ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ መጽሐፉ ከገበያ መጥፋቱንና በአሮጌ ተራ ዋጋው እጅግ መናሩንም ጠቁመናል፡፡ አንዳንዶች ግን መጽሐፉ በድረገጽ ላይ መሰቀሉን ጠቁመውናል፡፡ ይህ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን የተነሣውን የሕትመቱን ጉዳይ አልፈውታል፡፡ በተጻፈው መጽሐፈ ቅዱሳዊ እውነት ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል ወይ የሚለውንም ለመመለስ ድፍረት ያገኙ አልመሰለንም፡፡ እኛ እስከምናውቀው ድረስ ግን ማቅ በዚህ መጽሐፍ ተጠቀሱትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ሲቃወምና በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቱ እንመራለን ያሉትን የቤተክርስቲያን ልጆች ሲያወግዝ ነው የኖረው፡፡ ለዛሬው ይህን ጥያቄ እናቅርብ፤ ሊቀ ጉባኤ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገውን (በተወሰነ መልኩ ትውፊትንም ጨምረዋል) ስለጸጋ የጻፉትን ማቅ ያምንበታል ወይ? እስኪ ከመጽሐፉ የሚከተለውን እንመልከት (ትምህርት ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት ከገጽ 234-237 የተወሰደ)
የጸጋ ትርጉም፣ ምንነቱና ዓይነቱ
        ጸጋ ምን ማለት እንደሆነ ከማየታችን በፊት ጸጋ ከየት መጣ? በማን በኩል መጣ? የሚለውን በመመልከት እንጀምራለን፡፡ የኦሪት ሕግ በሙሴ በኩል እንደ መጣልን ጸጋን ደግሞ በክርስቶስ እንዳገኘን በዮሐንስ ወንጌል ተጽፏል፡፡ እንዲህም ተብሏል ‹‹ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ፡፡›› ይህም ማለት ጸጋ እግዚአብሔር በምስጢረ ሥጋዌ በክርስቶስ ሰው መሆን የተገኘ ነው ማለት ነው፡፡
        ስለዚህ ‹‹ቃል ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፣ … እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናል›› በማለት ወንጌላዊ ዮሐንስ የጸጋን ነገር ገልጾልናል፡፡ እንግዲህ ጸጋ በክርስቶስ ሰው መሆን የተገኘና በእርሱ ላመኑት ሁሉ በነፃ የሚሰጥ ነው፡፡ ጸጋ በአጠቃላይ አነጋገር እግዚአብሔር ዓለሙን እንዲሁ ከመውደዱ የተነሣ አንድ ልጁን ለዓለም መድኃኒት አድርጐ መስጠቱን የገለጸበት የፍቅሩና የምሕረቱ የሥራ ውጤት ነው (ዮሐ. 1 Ę12-18፤ 3 Ę16፤ 1ኛ ዮሐ. 4 Ę7-12)፡፡ በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ በሙሴ ሕግ በኩል ሳይሆን በክርስቶስ ጸጋ በመምጣቱ ያመኑትን እንዲሁ አጽድቋቸዋል (ሮሜ 3 Ę21-26፡፡ እንግዲህ የጸጋ መነሻ ምንጩ ከእግዚአብሔር ፍቅርና ከማዳን ሥራው ነው፤ በተለይም ለእኛ ሲል ሕማምና ሞትን ከተቀበለልን ከክርስቶስ ሥጋና ደም ነው፡፡
        በሙሴ በኩል የመጣው ሕግ ይህን አድርግ ይህን አታድርግ በማለት ልናደርገው የሚገባንና የማይገባንን ለይቶ የሃይማኖት፣ የሞራልና የማኅበራዊ ግዴታችንን የሚያስታውቀንና እንድንፈጽምም የሚያስገድደን ትእዛዝ ነው፡፡ ትእዛዙን ባንፈጽም ግን ቃል ኪዳኑን እንዳፈረስን ተቆጥሮ እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣት ይፈረድብናል፡፡ የሙሴን ሕግ የጠበቀና ያከበረ በሕይወት እንደሚኖር ተነግሯል፡፡ ነገር ግን በታሪክ እንደምናየው ማንም ሕጉን ጠብቆ ከሞት ፍርድ የዳነ የለም፡፡ የመጀመሪያው ትእዛዝ ለአዳም ተሰጥቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ትእዛዙን በማፍረሱ የሞት ሞት ተፈረደበት፡፡
        የሙሴንም ሕግ በትክክል የፈጸመ ባለመኖሩ ሰው ሁሉ ከሞት ፍርድ አላመለጠም፡፡ ምክንያቱም ሁሉ ስለ በደለ ነው፡፡ ‹‹ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፣ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ ቸርነት የሚያደርግ የለም፣ አንድ ስንኳ የለም፡፡›› ብሎ ሐዋርያው ጳውሎስ መዝሙረ ዳዊትን ጠቅሶ ያስተማረንን እናስተውላለን (ሮሜ 3 Ę11-12)፡፡ ስለዚህ በሙሴ ሕግ ማንም ሊጸድቅ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ሕግ ሰውን ከኃጢአቱ ለማላቀቅ ችሎታና ኃይል ስለሌለው ነው፡፡ እንዲያውም የሕግ መኖር ኃጢአትን አላገደም፣ [በ]ሕግ መተላለፍ እየበዛ፣ የኃጢአትም ምንነት እየጐላና እየታወቀ ሄደ እንጂ (ሮሜ 7 Ę7-12)፡፡
        በክርስቶስ የተገኘው ጸጋ ግን ኃጢአትን የሚደመስስ፣ ሰውን ከእግዚአብሔር የሚያስታርቅ፣ መንግሥተ ሰማያትን የሚያሰጥ ሆኗል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደዚህ ዓለም ልኮ ለሰዎች ሁሉ ቤዛ አዳኝ አድርጎ በመስጠቱ የመዳን ጸጋችንን አገኘን፡፡ ስለዚህ ሕጻን ተወለደልን ወንድ ልጅም ተሰጠን በማለት ኢሳይያስ የተነበየው በክርስቶስ መወለድ ጸጋችንን ማግኘታችንን ይገልጻል፡፡ ‹‹ወንድ ልጅም ተሰጥቶልናል›› የሚለው ቃል ስጦታን ማለት የጸጋ ስጦታን ያመለክታል (ኢሳ. 9 Ę6)፡፡ ስለ እኛ ስለ መዳናችንም ሰው የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ በሰውነቱ የሕግን ቀንበር ተሸክመ ስለ እኛ ትእዛዛትን ሁሉ ፈጽሟል፡፡ በዚህም ሕግን በፈጸመው ሰውነቱ ሕግን ባለመፈጸማችን የተፈረደብንን የሞት ቅጣት በእኛ ምትክ ተቀብሎ አድኖናል፡፡ ጸጋም በእርሱ ሞት ያገኘነውን የዘላለም ሕይወት ይመለከታል፡፡
        ስለዚህ ስለ ሥጋ ድክመት ሕግን ለመፈጸም ባለመቻላችን ያጣነውን ሕይወት በክርስቶስ ሕማማትና ሞት አገኘነው፡፡ በእርሱም በማመናችን እንደፈቃዱም በእርሱ መንፈስ በመመላለሳችን ሕግንና ትእዛዛትን ሁሉ እንደፈጸምን ተቆጥረናል፡፡ ስለዚህም በክርስቶስ ላለነው ሁሉ ኩነኔ እንደሌለብን ተጽፏል፡፡ (ሮሜ 8 Ę1-4)፡፡ እንግዲህ ከክርስቶስ ሰውነት በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደሙ የተገኘው ጸጋ ዓለምን ሁሉ ከኃጢአትና ከሞት ጥላ ሥር ላሉ ሁሉ ከዚህ የበለጠ የሕይወት ጸጋ የት ይገኛል? የብርሃን ሕይወትስ የት አለ?
ጸጋ ምንድን ነው? ዓይነቱስ?
        እንግዲህ ጸጋ ምን ማለት ነው? ጸጋን ከመሠረቱ ልንረዳው የምንችለው እኛን ለማዳን ሲል ክርስቶስ ሰው በመሆኑ፣ በሕማሙና በሞቱ ምክንያት ኃጢአትን ደምስሶ ሰውን ከእግዚአብሔር በማስታረቁ ነው፡፡ ይህም ማለት የጸጋ የመጀመሪያ ዓላማና የሥራ ውጤት የአዳምንና የልጆቹን በደል መደምሰስና ከፈጣሪም ይቅርታን ማስገኘት ነው፡፡ ‹‹እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ›› በማለት ዮሐንስ መጥምቁ ስለ ክርስቶስ መስክሯል (ዮሐ. 1Ę29)፡፡ ‹‹ወደሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ያነጽሐነ እምኲሉ ኃጣውኢነ - የኢየሱስ ክርስቶስም ደም ከኃጢአታችን ሁሉ ያነጻናል››         (1ኛዮሐ.1Ę 7)፡፡ ለሰዎች ኃጢአት የተሠዋ በጉ፣ የፈሰሰው ደሙ ለኃጢአተኞች ሁሉ ፈውስ፣ መድኃኒት ሆኗል፡፡ ጸጋ ማለትም ይህ ነው፡፡ ስለዚህ ነው የክርስቶስ ሥጋና ደም በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው፡፡ ስለዚህም ምሥጢረ ቁርባን የምሥጢራተ ሁሉ መሠረትና የጸጋ ሁሉ መገኛ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም የደኅንነታችን ጸጋ በመስቀል ላይ ከተሠዋው ከክርስቶስ ሥጋና እንዲሁም ከፈሰሰው ደምና ውኃ የተገኘ ነውና፡፡
        እንግዲህ ጸጋ ማለት በመጀመሪያ ደረጃ በክርስቶስ ቤዛነት ከእግዚአብሔር የሚገኝ የኃጢአት ሥርየትና እርቅ ነው፡፡ ፍጡር ከፈጣሪ መታረቅ የመጀመሪያ የጸጋ ውጤት ነው፡፡ የጠፋው ልጅ ከአባቱ ጋር የመታረቁን ታሪክ እዚህ ላይ እናስታውስ (ሉቃ. 15 Ę11-24)፡፡ ክርስቶስ በጸጋው እንዳጸደቀን፣ እርቅና ሰላምን እንደሰጠን፣ ኃጢአት ባለበትም እንዴት ጸጋውን እንዳበዛልን እንመልከት (ሮሜ 5 Ę1-31)፡፡
        ጸጋ የኃጢአት መደምሰሻ ነው ስንል በዚህ ብቻ የሚቆም አይደለም፡፡ ጸጋ ኃጢአትን ከደመሰሰ በኋላ በኃጢአት ምክንያት የመጣውንም ሞት  ያስወግደዋል፡፡ በክርስቶስ ሕማምና ሞት የተገኘው ጸጋ የዘላለም ሕይወትን ያስገኛል፣ ገነት መንግሥተ ሰማያትን ያሰጣል፡፡ ስለዚህ ጸጋ ከሁሉ ነገር በላይ ነው፡፡ ምክንያቱም ጸጋ የእግዚአብሔር ፍቅር የሚገለጽበት የቸርነቱና የምሕረቱ ውጤት ነውና፡፡
        እንግዲህ በሁለተኛ ደረጃ በጥንተ አብሶ በአዳም ኃጢአት፣ ሕግ በማፍረሱ ምክንያት ያመጣብንን መርገም ሽሮ ሞትን ደምስሶ በክርስቶስ የተገኘው ጸጋ የዘላለም ሕይወትን አሰጥቶናል፣ ያጣነውን ገነት አስመልሶናል፡፡ ስለዚህ ጸጋ ማለት ጽድቅንና መዳንን ለማግኘት የሚረዳን ከእግዚአብሔር የሚገኝ ስጦታ ነው፡፡ በጸጋው አዲስ ሕይወትን አግኝተን አዲስ ፍጥረት ሆነናል፡፡ ጸጋ የእግዚአብሔር ልጅነትን አሰጥቶ የመንግሥቱ ወራሽ አድርጐ የመጨረሻውን ተስፋና ደስታ ለመካፈል ያበቃናል (2ኛቆሮ. 3Ę17፤        ኤፌ. 1Ę5-8፤ 2 Ę5-10፤ ገላ. 6 Ę15፤ ሮሜ 8 Ę14-17)፡፡
        በዚህና በመሳሰሉት ልዩ ልዩ የጸጋ ትርጓሜ ለመገንዘብና ለማስገንዘብ የምንፈልገው ነገር ቢኖር ጌታ አምላክ ከሰው ልጅ የሚያገኘው ጥቅም ሳይኖር እንዲያውም የፈጣሪውን ቃል ኪዳን ተላልፎ በመበደሉ የእግዚአብሔር ጠላቱ ሆኖ ሳለ (ሮሜ 5 Ę6-11) እርሱ ግን በዓይነ ምሕረት ተመልክቶ ታላቅ የቸርነትና የርኅራኄ ሥራ ማድረጉ ለሰው ልጅ ያለው ፍቅር ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ በአድናቆት እንድንመለከተው ነው፡፡ ‹‹በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ- እግዚአብሔርን ሥራህ ግሩም ነው በሉት›› (መዝ. 65Ę3) እያልን ታላቁን የፍቅር ሥራውን በአንክሮና በተዘክሮ ሆነን እንማረዋለን፡፡ እንግዲህ   ይህ እጅግ የሚያስደንቀው አምላካዊ የፍቅር ሥራው ሁሉ ጸጋ ይባላል፤ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ እንዲሁ በነፃ ያደረገለት የረድኤት ሥራ ነውና፡፡ ጸጋንም ጸጋ ያሰኘው ከቸሩ እግዚአብሔር ያለምንም ዋጋ ለሰዎች ደኅንነት በነፃ የሚሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ ከኃጢአትና ከሞት ድነን ከመንፈሳዊ ልደት እስከ ዘላለማዊ ሕይወት እስከ መንግሥተ ሰማያት ድረስ በነፍስ በሥጋ የሚደረግልን ረድኤተ እግዚአብሔር ሁሉ ጸጋ ማለት እንደሆነ እናምናለን፡፡ እንግዲህ ስለዚህ የጸጋ ስጦታዎች ሁሉ ምን እናድርግ ብለን እናስባለን፡፡  በመዝሙረ ዳዊት ‹ምንተኑ አዐስዮ ለእግዚአብሔር በእንተ ኲሉ ዘገብረ ሊተ- ለእግዚአብሔር ስላደረገልኝ ሁሉ ምንን እከፍለዋለሁ›› (መዝ. 115 Ę3) እንደተባለው ከምስጋና ሁሉ የሚበልጠውን የምስጋና  መስዋዕት ለእርሱ ብቻ ከማቅረብ በቀር ሌላ ምን እናደርጋለን፡፡ ምስጋና የባሕርዩ ለሆነ አምላክ በእውነት ምስጋና ይገባዋል፡፡
        ስለ እግዚብሔር የጸጋ ስጦታዎች በብዙ መንገድ መተርጐማቸውን እያሰብን ዓይነታቸውንና ብዛታቸውን በጽሑፍ ወይም በሰንጠረዥ ዘርዝሮ ለማሳየት አይደለም፡፡ እንዲያው በክርስቶስ ያመኑ ሁሉ ጸጋ በጸጋ እንደሆኑና ጸጋም በእጅጉ እንደበዛላቸው ለማስገንዘብ ያህል ነው እንጂ፡፡ በክርስቶስ የመጣልን ጸጋ በጥንተ ተፈጥሮ የወደቀውን ሰው በሐዲስ ተፈጥሮ አድኖ የመጨረሻ ዕድል ፋንታቸውን ከእግዚአብሔር ከቅዱሳኑ ጋር እንዲሆን አብቅቶታል፡፡ በመርገመ ሥጋና በመርገመ ነፍስ ፋንታ በረከተ ሥጋና በረከት ነፍስን ሰጥቶታል ብለን ለመመስከር ያህል ይህን አጭር የጸጋ ትርጓሜ ለማሳየት ሞክረናል፡፡
        ከሞላ ጐደል የጸጋ ትርጉም ይኽን ሲመስል በክርስቶስ የመጣውን የጸጋ ስጦታ ሁሉ በእምነትና በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለመቀበል እንድንችል የሚያበቃንን መንፈስ ቅዱስን መዘንጋት የለብንም፡፡ የክርስቶስን ጸጋ ለመቀበላችንም ሆነ ከተቀበልንም በኋላ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ረድኤት ያስፈልገናል፡፡ በጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ የሚያደርገንና የሞቱና የትንሣኤውም ተካፋይ የምንሆንበትን ሁኔታ በልቡናችን እንድረዳውና በተግባርም እንድንፈጽመው ያስችለናል፡፡
        ክርስቶስን ጌታ እንደሆነ ያለ መንፈስ ቅዱስ ለመመስከር እንደማንችል ሐዋርያው ጳውሎስ አስተምሮናል (1ኛቆሮ. 12 Ę3)፡፡ ይህን ካልመሰከርን ደግሞ በክርሰቶስ የመጣልንን ጸጋ ለማግኘት ይቅርና ገና በአመክሮ እንዳሉትና እንዳልተጠመቁት ንዑስ ክርስቲያን እንኳ ለመሆን አንችልም፡፡ ስለዚህ የጸጋን ትርጉም በትክክል የምንገነዘበውና የጸጋንም ስጦታ ለመቀበል የምንችለው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እንደሆነ እንረዳለን፡፡ እንግዲህ ‹‹ጸጋ እግዚአብሔር›› ማለት ከሁሉ አስቀድሞ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ እርሱም በመጀመሪያ ሥራው ሰውን በሀብት ስቦ በረድኤት አቅርቦ ወደ እግዚአብሔር በንስሐ መልሶ በክርስቶስ ማመንን ይሰጠዋል (ዮሐ. 6Ę37 እና 44-45)፡፡ የክርስቶስን የማዳን ጸጋውን፣ ጽድቁንና ቅድስናውን ሁሉ ገንዘብ ለማድረግ ማለት የራሳችን ሊሆን የሚችለው ከእግዚአብሔር በተሰጠን በልቡናችን ውስጥ ባደረው በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ረድኤት ነው፡፡ በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው ልዩ ልዩ ጸጋ ሁሉ በግብረ በመንፈስ ቅዱስ ይከናወናል፡፡ ከዚህም ሌላ በአማኞች ልቡና አድሮ መንፈስ ቅዱስ መልካም ሥራዎችን እንዲያከናውኑ ልዩ ልዩ ጸጋና ሀብት ያድላቸዋል፤ ለእያንዳንዱም እንደሚገባውና እንደሚጠቅመው አውቆ ‹‹ከመክፈልታት ሱታፌ ሀብት›› እና ‹‹ከመክፈልታተ ምግባር›› የሚያስፈልገውን ይሰጠዋል፤ ይህንንም የሚያደርገው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር እንዲጸና የእግዚብሔር ወንጌለ መንግሥት እንዲስፋፋ ነው (1ኛ ቆሮ. 12፤ ሮሜ 12 Ę6-8 ትርጓሜውን ተመልከት)፡፡

7 comments:

 1. Kat adicted false priest of mk his name is Erget kulla yelma here in Atlanta accusing abaselama as enemy of EOTC, but the fact is, this gang wotemesha goremessa, has no formal education either in eotc or any thing else. He has no idea about formal church education excepet accustation of our favorite web abaselama. His collagues meregeta nekatebeb who abuse the regulation of church by telling of our naive members as fortune teller tenqola. They have homosexual relationship too. Those gang taking money from the church with out paying of tax to use cheating, fu... and beating of our church in undercovering of mk mafya. In very similar way one of other pretender he does not speak amaharic which is came from rural tigraye aba zelebanose a father of one child from black women in the east of Atlanta similarely doing business with mk to demolish the true preacher and web to cover his zemot behind mk. Aba selama please reaserch more to inform our followers to away from those gangster. On the conclussion we have suffered from those gangster who have involved part time priest ful time leba. auuuu --------auuuu ye feteh yaleh ---- death to mk!!!! Aba zelebanose his wife name is sebel telahun lemma.

  ReplyDelete
 2. ማቅ ሰውና ብዛቱን አምላኪ በመሆኑ ጸጋ የሚለውን ሊቀበለው ቀርቶ ሊሰማው አይፈልግም ክፋትና ተንኮልን የተሞላ አካል ነውና፤ ጸጋ የሚለውን ቃል የሚሰማና
  የሚቀበል ብዛቱንና ከብዛቱ ያሰባሰበውን ሀብት የሚመካበትን ብልሃት ሲያጣ ያን ጊዜ
  ጸጋ እድዚአብሔር ምን እንደሆነ ሳይወድ በግድ ይገነዘባል፤ እስከዚያው ድረስ በውጭም በውስጥም የሚገኙ ጳጳሳትን የቤተ ክርስቲያን ምርጥ ሊቃውንትን እንዲሁም
  ለግብሩ ተባባሪ ያልሆኑ የሰንበት ት/ቤት ዋና ዋና አባላትን ሲያሳድድ ይሰነብታል
  በመጨረሻም እንደ ጢስ ተኖ ይጠፋል፤ ክርስቶስ ተፋቀሩ ማቅ ተፃረሩ ያስደንቃል!
  (እንዲህ ያለ ዘመን የተገላቢጦሽ አህያ ወደ ሊጥ ውሻ ወደግጦሽ)

  ReplyDelete
 3. ማቅ ሰውና ብዛቱን አምላኪ በመሆኑ ጸጋ የሚለውን ሊቀበለው ቀርቶ ሊሰማው አይፈልግም ክፋትና ተንኮልን የተሞላ አካል ነውና፤ ጸጋ የሚለውን ቃል የሚሰማና
  የሚቀበል ብዛቱንና ከብዛቱ ያሰባሰበውን ሀብት የሚመካበትን ብልሃት ሲያጣ ያን ጊዜ
  ጸጋ እድዚአብሔር ምን እንደሆነ ሳይወድ በግድ ይገነዘባል፤ እስከዚያው ድረስ በውጭም በውስጥም የሚገኙ ጳጳሳትን የቤተ ክርስቲያን ምርጥ ሊቃውንትን እንዲሁም
  ለግብሩ ተባባሪ ያልሆኑ የሰንበት ት/ቤት ዋና ዋና አባላትን ሲያሳድድ ይሰነብታል
  በመጨረሻም እንደ ጢስ ተኖ ይጠፋል፤ ክርስቶስ ተፋቀሩ ማቅ ተፃረሩ ያስደንቃል!
  (እንዲህ ያለ ዘመን የተገላቢጦሽ አህያ ወደ ሊጥ ውሻ ወደግጦሽ)

  ReplyDelete
 4. are mlese setu makoche

  ReplyDelete
 5. may the Almighty God bless you ministry. we always remember you all in our daily prayer.

  ReplyDelete
 6. mknoch endenante yemiyasb aemro yalachew sew nachew ye like gubaen metshafm bihon sayanebu ayatmutem se le getachin adaghnetem bezanetem yawkalu, ,gen enanten liteyikachihu eski ketntawiabatoch(ancient fathers) ,,emnet yal migbar,, endihu,, bektsbet ,,yasedkal yale abat ngerugh,mechem zelachihu ,kidus awgstinosen, endatteksulgh ersu sew betsega yitsdkal ale enji yal migbar yitsdkal alalem,adera melsachihun etebkalehu sefa yale tsihuf bihon yimeretal

  ReplyDelete
 7. አባ ጳውሎስም ታመሙ ምን ይሻል ይሆን?

  ReplyDelete