Thursday, August 23, 2012

የቅዱስነታቸው ሥርአተ ቀብር በታላቅ ሥነስርአት ተፈጸመተቃዋሚዎቻቸው እንዳሰቡት ቀብራቸው ጭር አላለም
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሥርኣተ ቀብር ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2004 . ከቀኑ 730 በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅና በደመቀ ሥነስርአት ተፈጸመ፡፡ ቪዲዮ ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑሥርዓተ ቀብሩ ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ዝብ የተገኘ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸውን በሕይወተ ሥጋ እያሉ በተለይም በግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በማኅበረ ቅዱሳን መሪነት አድመውና ቡድን ፈጥረው እጅግ ሲቃወሟቸውና ሲያበሳጯቸው የነበሩ አንዳንድ ጳጳሳትን ጨምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የእህት አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ ተገኝተዋል፡፡

ቅዱስነታቸውን በሕይወት ሳሉም ጭምር ሲቃወሟቸውና ሲያሳጧቸው የነበሩት እነአባ ሳሙኤል፣ ቀብራቸው የደመቀ እንዳይሆን ዜና ዕረፍታቸው ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በልዩ ልዩ መንገድ ሲሰሩ የነበረ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ እንደ ምንጮቹ ከሆነ ሲኖዶሱ የቀብር ሥነሥርዓቱ ነሐሴ 17 መሆኑንና የቀብራቸው ስነስርዓት ተፈጽሞ ዐቃቤ መንበር እስኪሰየም ድረስ ዋና ስራአስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቤተክህነቱን ሥራ እንዲመሩ መወሰኑን ተከትሎ፣ ለቅዱስነታቸው ቅርበት ያለቸው ወገኖች የቀብራቸው ሥነሥርዓት የደመቀ እንዲሆንና በልዩ ሥነሥርዓት እንዲከናወን በማሰብ ቀኑ ከሐሙስ ወደ እሑድ እንዲለወጥ ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ በተጨማሪም የቅዱስነታቸው አስከሬን ከመስቀል አደባባይ ተነሥቶ ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲሄድ እንዲደረግ ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡ ተቀባይ ግን ስላላገኙ ለአንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን አሳውቀው ባለሥልጣኑ ለዋና ሥራ አስኪያጁ ይነግራሉ፡፡ ዋና ሥራ አስኪያጁም ሐሳቡን ለሲኖዶስ አባላት አቀርባለሁ ብለው ያቀርባሉ፡፡

ይሁን እንጂ በዚህ ደስ ያልተሰኙትና የቀብራቸው ስነሥርዓት እንዳይደምቅ የፈለጉት እነአቡነ ሳሙኤል «አንድ ጊዜ ወስነናል፤ ጉዳዩንም ከውጪ ለሚመጡና በቀብር ሥነሥርዓቱ ላይ ለሚገኙ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎችና እንግዶች አንዴ ነግረናልና አይሆንም» ይላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ከዚሁ ጋር የወሰኑትንና በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን የሰጡትን መግለጫ ቀልብሰውና ብፁዕ አቡነ ፊልጶስን በመቃወም ከቅዱስነታቸው የቀብር ሥነርአት በኋላ እንመርጣለን ሲሉ የወሰኑትን ውሳኔ በማጠፍ፣ አቡነ ፊልጶስን ከአመራር ሰጪነት ውጪ በማድረግ ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ዐቃቤ መንበር አድርገው መሾማቸው የሚታወስ ነው፡፡

በዚህ መንገድ እንዳይደምቅ ብዙ የተደከመበት የቅዱስነታቸው ሥርዓተ ቀብር ግን ከተገመተው በላይ እጅግ በደመቀና በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ በተገኘበት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡ ሊሸሸግ ያልቻለው የቅዱስነታቸው በጎ ገጽታም በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌሺዥን ሰፊ የዜና ሽፋን አግኝቷል፡፡ በቀብራቸው ላይ የተገኙ የመንግሥት ባለሥልጣናትም ቅዱስነታቸው ለቤተክርስቲያንና ለአገር ያበረከቱትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድነቅ ለቅዱስነታቸው ያላቸውን ክብር ገልጸዋል፡፡ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ቅዱስነታቸው ወደውጭ የተዘረፉ ቅርሶችን በማስመለስና መንፈሳዊ በዓላት የቱሪስት መስህብ እንዲሆኑ በማደረግ የተጫወቱትን ሚና የጠቀሱ ሲሆን፣ ሌሎችም ባለሥልጣናት በተመሳሳይ የቅዱስነታቸውን መልካም ሥራዎች ጠቅሰው ቅዱስነታቸውን ዘክረዋል፡፡ በብጹዕ አቡነ ገሪማም ሰፋ ያለ የሕይወት ታሪካቸውን በንባብ አሰምተዋል፡፡

ከፊሉን ሥነ ስርዓት እዚህ ላይ በመጫን ከኢትዮቱብ መመልከት ይችላሉ

10 comments:

 1. Aba selamawoch endet nachehu?

  Koye ene emelewu beyezenachehu MK yemile kelele yemayenebeb yemeselachehuwal malete new? Ye Melese Zenawi zena laye bech atahu menew ejachewu yelebetem ende?

  Lebona yesetachehu

  ReplyDelete
 2. ማቅ በውጭና በውስጥ የሚኖሩ የቤተ ክርስቲአኒቱን አማኞች የሚያስወግዝ በቤተ ክህነቱም እንደወተት
  ዝንብ ጥልቅ ብሎ የሚያዝዝ የሚናዝዝ ከሆነ ወደመለስተኛ አምላክነት ተቀየረ ማለት ነው እንዴ?
  አይሆንም እንጂ ከሆነ (አንትሙሰ ከመ ሰብእ ትመውቱ ወከመ አሀዱ እመላእክት ትወድቁ)እንደሰውም
  እንደ መልአክም ሳይሆኑ ዓውሎ ንፋስ የገባበት ገለባ ይሆናሉ'They are like chaff. psalm 1/ 4 መዝ ፩. ፬(እርሱና መደዴዎቹ)ማለት ነው.

  ReplyDelete
 3. mina ale silekebrachew bicha bitaworun kele indih aderege kele indeza lemadirge asibo neber minamin minamin........

  ReplyDelete
 4. On my understanding abaselama ranking the first stage to inform concise information to the followers. Here in Atlanta, one false his name is Tagaye Abazebanose that he sleping men and women used church money for fu...., cheating and other use. To protect him self he acting like mk supporter. Why mk do not care violation of chuch rule if you support them. Mk made puzel and fiction in the Eotc. Now is time abaselama to protect the Eotc from Tequla mk. I will be send all mis conduct of zelebanose video soon. Death for crack smoker mk elements.

  ReplyDelete
 5. Aba Selamawoch Ye Abatachi Aba Selama Amilak Sirachihun
  Bemezin Mane Teqel Fares hono endemign Aminalhu Ersu Yifaredachihu Yetifat Lijoch Nachihuna::

  ReplyDelete
 6. Ine imilew; lemenokse yedemeke yekebit sine-siriat min yadergiletal? Wiy teeeeewut! tewut! Lekas yemenoksen kibir atawkumisa!!!

  ReplyDelete
 7. photow eko ye wuchi hager new enji kidist selasie cathedral aydelem. Minew zorebachu ende? New were lemadamek?

  ReplyDelete
 8. ምነው እንደ ጣቃ ቀደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደደ አላችሁ ፎቶ መለየት አይችሉም ብላችሁ ነው? እንኳን እኛ እናንተም የዞረባችሁ አውቃችሁታል ገሪባ ሁሉ

  ReplyDelete
 9. For me I say Abune Paulos has a very respected burial ceremony. That is really great. He deserve that as a father to the church. But you abaselama's don't try to prove that he has a very nice burial ceremony. Check how it looks on the link below. Put such kinds of photos.

  http://andadirgen.blogspot.com/2012/08/blog-post_23.html


  Amilak masitewalun yistachihu.

  ReplyDelete
 10. Oh abaselam u try to foolish us by post Funeral photo of Pope Shenouda. it shows us u r a big big............ foolish .
  U can find the photo from http://theorthodoxchurch.info/main/funeral-snaps-of-pope-shenouda-from-cairo/

  ReplyDelete