Thursday, August 16, 2012

ሰበር ዜና - ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አረፉ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 5ኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በ76 ዓመታቸው ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ከቆዩ በኋላ ዛሬ ሌሊት ማረፋቸው ተሰማ፡፡ የቅዱስነታቸውን መሞት ተከትሎ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች በከፍተኛ ስብሰባ ተጠምደው አርፍደዋል፡፡ ስብሰባቸውንም ጨርሰው ወደጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ በመሄድ ግቢውን ወረውታል፡፡

በየድረገጾቻቸው የዘንድሮው በዓለ ሲመታቸው የመጨረሻ ነው ሲሉ ያሟረቱት የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች ያሰቡት የተሳካላቸው መስሏል፡፡ ቀጣዩ ፓትርያርክ ማን ይሆናል? የሚለው ግን ትልቅ ጥያቄ እየፈጠረ ነው፡፡ እርሳቸውን ለመጣል አንድ የሆኑት ጳጳሳት ያ አንድነት አሁን አብሯቸው እንደማይሆንና ለአንዱ የፓትርያርክነት ወንበር እንደሚሟሟቱ ይጠበቃል፡፡ በኢየሱስ መሞት እንደተፋቀሩት እንደጲላጦስና ሄሮድስ ማቅ የያዛቸው ማኅበረ ቅዱሳንም የራሱን ሰው እንዳዘጋጀ ውስጥ አዋቂዎች እየተናገሩ ነው፡፡ ስብሰባውም ከዚህ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ታውቋል፡፡
የቅዱስነታቸውን ማረፍ ተከትሎ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ  ፊልጶስ ዛሬ ከረፋዱ 5 ሰዓት ላይ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ «በሕይወት ዘመኔ እንደ እርሳቸው አይነት ቀን ከሌት የሚሰራ የሥራ ሰው አላየሁም፤ እየሰሩ ነው ያረፉት» ሲሉ ለቅዱስነታቸው ያላቸው አድናቆትና አክብሮት ገልጸዋል፡፡ የቀብር ሥነ ስርአታቸውም በልዩ ዝግጅት በደመቀ ሁኔታና በክብር እንደሚከናወን የገለጹ ሲሆን፣ መቼ እንደሚሆን የሚወስነው ሲኖዶስ መሆኑን ብፁዕነታቸው አስታውቀዋል፡፡ ከመግለጫው በኋላም የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞችን በሙሉ ለስብሰባ ወደቢሯቸው ጠርተዋል፡፡ ሲኖዶሱም ስብሰባ መጀመሩ ታውቋል፡፡ በመግለጫው ላይ የተገኙ የማቅ ሰዎች የጠቅላይ ቤተክህነትን ግቢ የወረሩ ሲሆን በቡድን በቡድን ሆነው ስራ በመከፋፈል በከፍተኛ ሁኔታ ስልክ ሲደዋወሉና ከወዲያ ወዲህ ሲቅለበለቡ መታየታቸው ተስተውሏል፡፡

41 comments:

 1. እናንተ ማን ገደላቸው ይ ማኅበረ ቅዱሳን ይሆን? እነ አያልቅበት እሰኪ ምን አዲስ ነገር ልትነግሩን አቅዳችኋል ‹‹ማቅ አዲስ ፓትርያርክ ሊሾም ላይ ታች ይላል፡፡ ለዚህም ማስፈጸሚያ 3 ሚሊዮን ብር ለሊቃነ ጳጳሳቱ ሰጥቷል›› የሚል ወሬ እንደምታስነብቡን እጠብቃሉ፡፡ ለማንኛውም የአባታችንን ንፍስ ይማርልን!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለማቅ ሶስት ሚሊዮን እኮ የሻይ ወጪ ነው። ነብስ ገባሪ ማኅበር ገንዘብ ይገደዋል ብለህ ከሆነ አትሳሳት። አሾፍኩ ብለህ ምስጢር አታውጣ

   Delete
  2. Think twice before you speak once.

   Delete
 2. እስቲ አሁን እነኳን ቆም ብላችሁ ለጥቂት ጊዜ አስቡ፡፡ ቤተክርስቲያንን ክርስቶስ እንደማይተዋት ተገንዘቡ፡፡ ወደልቦናችሁ ተመለሱ፡፡

  ReplyDelete
 3. የዋልድባ አባቶች ጸሎት የቤተክርስቲያን አምላክ ፈረደ እንግዲህ ጉዳችሁ ፈላ ተሃድሶዎች ኡኡ በሉ

  ReplyDelete
 4. ምን ዜና ነው ?ምን ልክፍት ቢይዛችሁ ፣ ሟች ሳይቀበሩ ፣ እናንተም ለወጉ ነፍስ ይማር ሳትሉ ሌላ ጣጣ ውስጥ ገባችሁ ? በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ናችሁ ፡፡ አንድ አባት ሲሞት የህይወት ታሪኩ ፣ የሠራው ገድል ፤ ስለቅድስናው ይተረካል እንጅ ገና ግብዓተ መሬት ሳይፈጸም የስልጣን ወሬን ምን አመጣው ? ችግራችሁ ሥልጣን ነበር ማለት ነው ፡፡
  እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ ፡፡
  የአባታችንንም ነፍስ ይማርልን ፡፡ ሌላ የሚባለውን አላውቅበትም ፤ የቅዱሳኑን የጻድቃኑን የሚባል ነገር አለ ቢያንስ ጨምሩበትና ተገላገሉ ፡፡ አሳፈራችሁኝ ፡፡

  ReplyDelete
 5. የብጹዕነታቸው ሞት እጅግ ያሳዝናል። ነገር ግን ለእርሳቸው ታላቅ እረፍት ነው። እንድህ ጭካነ የበዛበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መኖር የሚመኝ ማንም የለም። እግዚአብሔር አምላክ የእርሳቸውን ንጽህና ተመልክቶ ከስቃይ አለም ከእምነት ይልቅ ብጥብጥ በነገሰበት ዓለም እንዳይኖሩ በሰላም ወስዶአቸዋል። ሊቃነ ጳጳሳቱ በነዋይ የሰከሩ ስለሆነ ስለ ሐይማኖቱ ግድ የሌላቸው በመሆኑ ፤ ለተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መከራ ይበዛባታል እንጅ ፈዉስ አይገኝላትም። ማንም ሰው ከመሞት አይድንም ነገር ግን ብጹነታቸው ብዙ ሳይሰቃዩ መሞታቸው ለራሱ እግዚአብሔር ምን ያል እንደምወዳቸው ያሳያል። ሰው ብጠላህ ዋጋ የለውም ስለራሱም አንኳን አንድም አያውቀውምና። ማቅ ብደሱቱ የእነርሱም ሕይወት በእግዚአብሔር እጅ ናት። በእውነት እርሳቸው አርፈዋል ግን ዛሬም የማቅ ንስሐ አባት ይሾም ይሆን? ምልሱን እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚሰጠው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የጠንቋይ ያለህ?
   ማኅበረ-ቅዱሳን አቡነ ጳውሎስን የሚተካ ማን ይሆን እንደሆነ ለማወቅ ጠንቋይ እያፈላልገ ነው ። ምክንያቱም ማኅበሩ ፓትርያርክ ይሆኑልኛል በማለት ያጫቸው ጳጳሳት(አቡነ ማቴዎስ፣ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ አቡነ ኤልያስ፣ አቡነ ሰላማ) ቀደም ብለው ሙቷልና።

   Delete
 6. ayii yetehadiso project keshefe

  ReplyDelete
 7. We missed a great man of God!we are very very very sorry.Now we will see who will carry all the burden.
  በጣም የሚያሳዝን ዜና ነው::በዘመናቸው የቤ/ክ ገበና የተሸከሙ አባት ናቸው::መቼም እግዚአብሔር ስለማይሳሳት አናማውም ሆኖም ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ የምንጸልይበት ጊዜ ነው::የዚህች ቤ/ክ ታሪክ እንዳይበላሽ::መጠነቀቅ አለብን እኒህ አባት ትልቅ የወንጌል ሰውና የመጽሐፍ ቅዱስ አፍቃሪ ነበሩ::በኮሌጅ ተማሪዎች የቤ/ክርስቲያኒቱ ታሪክ እንዲለወጥ የጣሩ ናቸው::የቀደመው ጸሎታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን!ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናት ይሁንልን::አሁን እንግዲህ ያሉት አባቶች የቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ እንዳይበላሽ ይጋደሉ::ለነገሩ መንግሥትም ቢሆን የሩቅ ተመልካች እንዲሆን አንሻም ሰለፊያዎች እንዳሉ እንዳይዘነጋ ማለት ነው!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 8. ነፍስ ይማር። ባታምኑበትም። ጊዜው ደረሰና የአስመሳይ ጴንጤዎች ከቤተ ክርስቲያናችን መጠረጊያቸው የምርም ደረሰ። እሳቸውን ይዛችሁ ያልተሳካላችሁ አሁንማ ተሸነፋችሁ። ሰይጣን ሁሌም እንደተሸነፈ ነውና የናንተም ሰይጣናዊ ስራ ተሸነፈ። ሲኖዶሱም የናንተንም የሳቸውንም ሽንፈት ባለፈው ስብሰባ በአይናቸው አሳይቷቸዋል።
  ማቆች በርቱ። ለቤተ ክርስቲያን አንድነት የሚሰራና ለጴንጤ መናፍቅ የማይተኛ አባት ይመጣልን ዘንድ እመኛለሁ።

  ግን ግን አሁን ስንት ልጆችና ሚስት ለውርስ እንደሚመጡ እንደምትፅፉ ነው መቼም¡ አይደል?

  ReplyDelete
 9. THIS SITE OR BLOG APPEARS TO BE A POLITICAL/OPPOSITION GROUP BLOG.
  WHAT DO YOU MEAN BY THIS STATEMENT?

  "እርሳቸውን ለመጣል አንድ የሆኑት ጳጳሳት ያ አንድነት አሁን አብሯቸው እንደማይሆንና ለአንዱ የፓትርያርክነት ወንበር እንደሚሟሟቱ ይጠበቃል፡፡"


  ReplyDelete
 10. I am afraid that incapable person may be elected by tephozo. Let us be cool and wise so that we give God the chance to elect the one who is capable.

  God Give Wisdom to The Soul of Abune Paulos!!!!!

  ReplyDelete
 11. Dn. Ledet Z AwassaAugust 16, 2012 at 11:49 AM

  Meneshachehume medereshachehume Mahibere Kidusan new beka! Yegermale
  Semonune degemo gedeluwachew yemile zena etebekalehu! Bertu Wulude Setan

  Temezeneh kelehe tegegneh!!!!


  ReplyDelete
 12. I am sorry about abba Paulos He was anice person God bless his soul

  ReplyDelete
 13. Hahahaha aba paulos bememotachew sle MK mn yilu yihon bye neber hahahaha lehulu zbaznke wereachu hulu MK matafecha chew new yabatachinn nefs begenet yanur

  ReplyDelete
 14. beabatachn ereft betam aznalehu
  NEBS YEMARLIN

  Ebacach ortodoxawyan yeh kegna yitebkal wey? yeand abat lejoch mehonachen atzengu"

  MK MK MK MK LESLTAN NEBER LEKA ERUCHACHW YIGERMAL KENANT AYTEBEKIM
  EGZEAR LEBONAWN YISTACHU

  ReplyDelete
  Replies
  1. "እኛ ታሪክ ያለን በታሪካችን እንኮራለን
   እነሱ ታሪክ የሌላቸው ይፈሩ"

   ብፁዕ አባ ጳውሎስ
   በሆለታገነት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አንድ መቶኛ ዓመት
   ክብረ በዓል ዋዜማ ላይ የተናገሩት

   Delete
 15. የቅዱስነታቸው ዕረፍት ስንሰማ በጣም አዝነናል።
  ቅዱስነታቸው በዕውቀት፣ ብርኅራኄ፣ በስነ ምግባር፣ ዓለምን በመምራት የሚተካ መነኩሴ ይኖር?
  አቡነ ጳውሎስ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያናችን 2ኛው ቅዱስ ጳውሎስ( ሳውል) ናቸው።
  ሁሌ እናስባቸዋለን!!!

  ReplyDelete
 16. ነፍስ ይማር፡፡
  አቡኑ ብቻ አይደለም ያረፉት የቤተክርስቲያን ጡትነካሾችም(ተሀድሶ መናፍቃን) አርፈዋል፡፡

  ReplyDelete
 17. ማህበረ ቅዱሳን የሚጎድለው መንፈሳዊነት ብቻ ሳይሆን ሰብአዊነትም ነው ከሞት የሚቀር የለምና ይህን ያህል ደስታ ማሰማት አይገባም ሁላችንንም ይቅር ይበለን።

  ReplyDelete
 18. እንደ አባታችን በእውነት ለወንጌል የቆመ አባት እናገኝ ይሆን

  ReplyDelete
 19. ቤተ ጳውሎስ ስለ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያቀረባችሁት ዘገባ እስከ አሁን በየትኛውም ብሎግም ሆነ ድረ ገጽ ከተዘገቡት ዘገባዎች በእጅጉ የሚስብና ታላቅ የሆነ ቁም ነገርን ያዘለ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ በተለይ ዘረኝነትና ጎጠኝት በእጅጉ በነገሰባት ቤተ ክርስቲያናችን የቅድስት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችንን ዓለም አቀፋዊነትና ሐዋርያዊነት የገለጻችሁበት መንገድ በእውነት በእጅጉ ደስ አሰኝቶኛል፡፡ በእርግጥም የቅዱስነታቸው የትውልድ ምድር የሆነችው አድዋ አባቶቻችን ዘር፣ ጎሳ፣ ሃይማኖት፣ ወንድ ሴት ሳይባል በነቂስ በመዝመት ለሀገሩ ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ቀንዲል የለኮሰባት ሕያው የታሪክ ምስክር ምድር ናት፡፡
  ይህን የነፃነት ዘመቻ በቀዳሚነት በማስተባበርና በመምራት ግንባር ቀደሙን ሚና የተጫወተችው ደግሞ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ናት፡፡ ዘረኝነት መንፈስ ለሚንጠው ቤተ ክህነቱ የቅዱስነታቸውን ህልፈት ታሪክን ሚዛናዊና ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ሳይለያይ ያቀረባችሁበት ዘገባ It’s one of the best of all! በቀጣይ ቤተ ጳውሎሶች እጅግ በተካናችሁበትና እጅግ በሚያስደምመኝ የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊ ታሪክና የሀገራችንን ፖለቲካ ሂደት ከቤተክርስቲያናችን ጋር ያለውን ቁርኝነት ሚዛናዊ በሆነ መንገድ በመተንተንና በማስረዳት በላቁ ጸሐፊዎቻችሁ በቀጣይ ስለ ፓትሪያሪክ አቡነ ጳውሎስ እንደተለመደው ድንቅ የሆነ ጹሑፉን እንደምታስንቡብን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
  ምናለ ሌሎች ብሎጎችና ድረ ገጾች የእናንተ ዓይነት ሚዛናዊ የሆኑ በሃይማኖት፣ በታሪክና በፖለቲካ ትንታኔ እውቀት የበሰሉና የተካኑ ጸሐፍት ቢኖራቸው ብዬ ተመኘሁ፡፡ ቀጣይ ጹሑፋችሁን በጉጉት እጠብቃለሁና አደራችሁን ስለ ቅዱስ አባታችን ታሪክ፣ ሥራዎቻቸውና ዓለም አቀፋዊ ሰብእና አስነብቡን፡፡
  ዘርዓ ያዕቆብ ነኝ ከሀገረ ኢየሩሳሌም ጽዮን ሰማያዊት!

  ReplyDelete
 20. Goodness, you don't even care that he has died.
  It takes class to take time and pay your respect to his holiness. But you have none of that.
  Shame on you

  ReplyDelete
 21. ቤተ ጳውሎሶች ስለ ቅዱስ ፓትሪያሪኩ ያቀረባችሁት ዘገባ ከየትኛውም ስለ ቅዱስነታቸው ከቀረቡ ዘገባዎች የሚስብና በእጅጉ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ ግን እ.ኤ.አ በሚል የቀረበው የቅዱስነታቸው የትውልድ ዘመን ስህተት ነው፣ ደግሞስ ለምን በአውሮፓውያን አቆጣጠር ማቅረብ አስፈለገ፡፡ ቅዱስነታቸው የተወለዱት በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1928 ዓ.ም ነው፡፡ ምናልባት የአውሮፓውያን አቆጣጠር ነው የሚስማማን ካላችሁ ደግሞ ቅዱስነታቸው ልደት የሚሆነው እ.ኤ.አ 1935 ዓ.ም ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ቢስተካከል ጥሩ ነው፡፡ በፊደል ግድፈትና የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን አጻጻፍ ስልት በሚገባ በመከተል የማትታማው ቤተ ጳውሎስ በዚህ ጹሑፍ የፊደል ግድፈትና የፊደል አጠቃቀም ስህተት አስተውያለሁ፡፡ ጹሑፍ ውበትና ለዛ ሳይጎድለው የፊደል ግድፈት አለበትና አስተካክሉት፡፡ በተረፈ ቀጣይ በቅዱስነታቸው ታሪክ ላይ ለማውጣት ያሰባችሁትን ጹሑፍ በጉጉት እንጠብቃለን፡፡
  ታዛቢዎቹ!

  ReplyDelete
 22. ከሁሉ አስቀድሞ ነፍስ ይማር! ስለተሰጠው አስተያየት ግን (ያቦን ፍየል ያጠፋ ያበዛል ልፍለፋ)ነውና
  የማቅ ጆሮ ጠቢዎች(ሰላዮች)ላይ ታች በመሯሯጥ ቆላ ደጋ በመርገጥ ክፋታቸውን ለማስረገጥ ብዙ ይላሉ
  ነገሮችን ያዛባሉ፤ ሦስት ሚሊዮን ቀላል ነው በዋልባ ስም የሚያሰባስቡት ዶላር ስንኳን ቤተ ክህነቱን
  መንግሥትን ሳይቀር ያስገለብጣል፤ ነገር ሸራቢዎች እንዲህ እያምታቱ ሁሉንም በመዳፋቸው ውስጥ ለማስገባት ይጣጣራሉ፤ ይሁንጂ መንግሥትና ክህነት በፈጣሪ ቁጥጥር እንጂ በፍጡር ባለመሆኑ ባለቤቱ
  ለፈቀደው ያሸክመዋል፤ ከዚህ ሁሉ ጣጣ አርፈው ቢቀመጡ ይሻላችዋል አለዚያ ግን ምከረው ካልሰማ
  መከራ ይምከረው!

  ReplyDelete
 23. የቅዱስነታቸውን ማረፍ ተከትሎ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ዛሬ ከረፋዱ 5 ሰዓት ላይ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ «በሕይወት ዘመኔ እንደ እርሳቸው አይነት ቀን ከሌት የሚሰራ የሥራ ሰው አላየሁም፤ እየሰሩ ነው ያረፉት» ሲሉ ለቅዱስነታቸው ያላቸው አድናቆትና አክብሮት ገልጸዋል፡፡ የቀብር ሥነ ስርአታቸውም በልዩ ዝግጅት በደመቀ ሁኔታና በክብር እንደሚከናወን የገለጹ ሲሆን፣ መቼ እንደሚሆን የሚወስነው ሲኖዶስ መሆኑን ብፁዕነታቸው አስታውቀዋል፡፡ ከመግለጫው በኋላም የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞችን በሙሉ ለስብሰባ ወደቢሯቸው ጠርተዋል፡፡ ሲኖዶሱም ስብሰባ መጀመሩ ታውቋል፡፡ በመግለጫው ላይ የተገኙ የማቅ ሰዎች የጠቅላይ ቤተክህነትን ግቢ የወረሩ ሲሆን በቡድን በቡድን ሆነው ስራ በመከፋፈል በከፍተኛ ሁኔታ ስልክ ሲደዋወሉና ከወዲያ ወዲህ ሲቅለበለቡ መታየታቸው ተስተውሏል፡፡

  የቅዱስነታቸውን ማረፍ ተከትሎ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ዛሬ ከረፋዱ 5 ሰዓት ላይ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ «በሕይወት ዘመኔ እንደ እርሳቸው አይነት ቀን ከሌት የሚሰራ የሥራ ሰው አላየሁም፤ እየሰሩ ነው ያረፉት» ሲሉ ለቅዱስነታቸው ያላቸው አድናቆትና አክብሮት ገልጸዋል፡፡ የቀብር ሥነ ስርአታቸውም በልዩ ዝግጅት በደመቀ ሁኔታና በክብር እንደሚከናወን የገለጹ ሲሆን፣ መቼ እንደሚሆን የሚወስነው ሲኖዶስ መሆኑን ብፁዕነታቸው አስታውቀዋል፡፡ ከመግለጫው በኋላም የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞችን በሙሉ ለስብሰባ ወደቢሯቸው ጠርተዋል፡፡ ሲኖዶሱም ስብሰባ መጀመሩ ታውቋል፡፡ በመግለጫው ላይ የተገኙ የማቅ ሰዎች የጠቅላይ ቤተክህነትን ግቢ የወረሩ ሲሆን በቡድን በቡድን ሆነው ስራ በመከፋፈል በከፍተኛ ሁኔታ ስልክ ሲደዋወሉና ከወዲያ ወዲህ ሲቅለበለቡ መታየታቸው ተስተውሏል፡፡

  የቅዱስነታቸውን ማረፍ ተከትሎ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ዛሬ ከረፋዱ 5 ሰዓት ላይ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ «በሕይወት ዘመኔ እንደ እርሳቸው አይነት ቀን ከሌት የሚሰራ የሥራ ሰው አላየሁም፤ እየሰሩ ነው ያረፉት» ሲሉ ለቅዱስነታቸው ያላቸው አድናቆትና አክብሮት ገልጸዋል፡፡ የቀብር ሥነ ስርአታቸውም በልዩ ዝግጅት በደመቀ ሁኔታና በክብር እንደሚከናወን የገለጹ ሲሆን፣ መቼ እንደሚሆን የሚወስነው ሲኖዶስ መሆኑን ብፁዕነታቸው አስታውቀዋል፡፡ ከመግለጫው በኋላም የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞችን በሙሉ ለስብሰባ ወደቢሯቸው ጠርተዋል፡፡ ሲኖዶሱም ስብሰባ መጀመሩ ታውቋል፡፡ በመግለጫው ላይ የተገኙ የማቅ ሰዎች የጠቅላይ ቤተክህነትን ግቢ የወረሩ ሲሆን በቡድን በቡድን ሆነው ስራ በመከፋፈል በከፍተኛ ሁኔታ ስልክ ሲደዋወሉና ከወዲያ ወዲህ ሲቅለበለቡ መታየታቸው ተስተውሏል፡፡

  ReplyDelete
 24. SELETEFETEREW NEGER BETAME YASAZENALE E/BEHARE ETHIOPIAN YEKALEKIDANU AGER ESKEHONECH YETEBEKATALE SELAM LE ETHIOPIA YEHUNE NEFESE YEMARE.

  ReplyDelete
 25. Who killed aba paulos? Is it true they mix poisenus chemical with Kidus kurban then he got poisened? ,the source claimed mk did.

  ReplyDelete
  Replies
  1. lol... I think you guys have poisened mind. Anyways, ye-abatachin burakie yidereben!

   Delete
  2. በመጣጥፎቻችን አልፎ አልፎ ሳይታወቀን የሰይጣን አገልጋዮች እየሆንን ይመስላል ፡፡ የዛሬው ደግሞ እጅግ ከፋ ፡፡ ጸሐፊው እንዲህ እንደሚገምተው ዓይነት ጥርጣሬን ህዝብ በሚያነበውና በሚቀባበለው ሥፍራ ላይ ለጥፎ ማስነበቡ ፣ በክርስትናው ላይ ስውር ደባ እንዳለው ይመስላል ፡፡ ኀብረተሰቡ ፣ እንደ ሰለጠኑት አገሮች ምእመን የመቁረብ ልምድ የለውም ፣ ሥጋና ደሙን ይፈራል ፤ እየተባለ ሲነገር ፤ እናንተና ጣፊው በዚህ ስንኩል መልዕክት ሥጋወ ደሙን በጥርጣሬ እንዲመለከት ፣ ልጆቹንም በመንፈሳዊነት ሆኖ እንዳያቆርብ ክፉ ዘርን እየዘራችሁ ነው ፡፡ በመሞታቸው ሁላችንም ልንቆጭ እንችል ይሆናል ፡፡ ነገር ግን የቁጭትና የሃዘን አገላለጹ መልክ እንዲያጣ በሃይማኖታችንም ላይ ጉድፍን እንዲረጭ መደረግ የለበትም ፡፡ ጥርጣሬው ቢኖር እንኳን እዛው ሠፈር ውስጥ ከባልደረቦች ጋር መወያየትና መወሰድ ያለበትን እርምጃ መጀመር እንጅ ፣ ክፋትን ለህዝብ ማስተላለፍ ትልቅ በደል ነው ፡፡ አቤል የቀደዳትን መንገድ ሁላችንም ሳናልፍባት አንቀርም ፡፡ በማዕረግ ስማቸው ሳይገለገሉበት ፣ ለክብረ በዓል ያጌጡበትን ልብስ ታጥቦ ዳግም ሳይለብሱት ትተው እየሄዱ ፣ ነገን ከልጆቻቸው ጋር ሊሠሩ ያቀዱትን እንደተዘረጋ ሳያጥፉ በድንገት ሲወድቁብን እያየን ፣ ዘለዓለማዊ የሆንን ያህል የምናስብና የምናደርገውን የማናውቅ ብዙ ደካሞች ፣ በዚህም አሳበን እንኳን ሃይማኖትንና ፈጣሪን ከመጉዳት አላረፍንም ፡፡

   ይኸ ጊዜ የጸሎትና የምህላ መሆን ሲገባው ፤ ሌላ በደልና ኃጢአትን መርጨቱ እናንተም ለህዝብ ማቀበላችሁ በጣም አሳዝኖኛል ፡፡ እንደ ቤተሰብ ባንወዳቸው እንኳን ፣ ሰው እንደመሆናቸው ፣ ላይመለሱ በሥጋ ሲለዩን ፣ ማድረግ የሚገባን ኃዘንን በአግባቡ መጋራትና መግለጽ እንጅ ፣ በሰበብ ባስባቡ ፣ ምክንያት እየፈለጉ የሰዎች ኃጢአትን መቆለሉ ደግ አይደለም ፡፡ ጸሐፊው የወረደብን ቁጣ ብዙ መሆኑ ለማመልከት ፣ በቤተ መቅደስ አገልግሎት እንኳን የሰዎች ተንኰልና ደባ እንደገባና እንዳለም እያመላከቱን ነው ፡፡

   ይህን ጥርጣሬ የጻፍክ ሰው ፣ ሌላ ምንም አልልህም ፤ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ፡፡ ላታስበው ትችላለህ ፣ ነገር ግን የኢየሱስን ሥጋና ደምን ነው ያረከስከው ፣ መርዝ ይሆናል ያልከው ፡፡ በእምነት ሆነው ላሉ ክርስቲያኖች የእባብ መርዝን ቢጠጡ እንኳን ሊገድላቸው እንደማይችል ጌታ በማርቆስ ወንጌል 16፡18 ገልጾታል ፡፡ ታድያ የጌታ ሥጋና ደም በሰዎች የተንኰል ጥበብ ወይም መርዝ ተሸነፈ ወይስ አባታችን ያለ እምነት ሆነው ወሰዱት ልትለን ፈልገህ ነው ? መርዝህ ክፉ ነው ፤ የመስቀሉን መስዋዕት ነው ባለማስተዋል ያቃለልከው ፡፡
   አሁንም እግዚብሔር ይቅር ይበልህ ፤ ይቅር ይበልህ ፤ ይቅር ይበልህ፡፡

   Delete
  3. Dear
   Don't be mistaken.He was diabetic. He developed gangrhene up th his knees. His physicians advised him to undergone operation. he refused. Before his death he was suffering from severe pain due to that. In medicine for this kind of person death is inevitable.I am sure that he knows that he will die. Gebah aydel egren alkoretim bilew gangrhene new yegedelachew. What I appreciate from him id the he was a strong guy, he didn't expose that he was a chronic patient. It was not visible in his life.

   Delete
 26. Alutawi asteyayet yesete hulu mk new yemitilu hulu libona yistachihu. MK contribut a lot to our church for the past 20 years. Le kidus abatachin nebis yimar.

  ReplyDelete
 27. ቅዱስነታቸው በሱባኤ ወቅት ማረፋቸው በራሱ ጻድቅ ሰው ያሰኛቸዋል። ሰው ብጠላህ እግዚአብሄር ከፍ ያደረገህ ከሁሉ ይበልጣል። ማህበረ ቅዱሳን በቅዱሳን ስም የምነግድ ከፉ ሰይጣን ነው። ትላንት በጌታችን ሞት ክፉዎች ደስ እንዳላቸው ዛሬም በዘመናችን ያሉት የፈሪሳዊያን እርሾዎች በቅዱስነታቸው ሞት በደስታ መስከር ምን ይሉታል? የክርስቲያና ህይወት የሌላቸው አረመነዎቸ ናቸው፡ አምላክ ከእነዚህ ሰይጣናዊ መንፈስ ይጠብቀን ሀገራችንም ቤተ ክርስቲያናችንም ይጠብቃት።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዴት ነው የሚባለው ? ለሟች ፍትሃት ማድረግ በሚቻልበት ወቅት ሲሞት ነው ፣ ወይስ ማድረግ በማይቻልበት ፣ በጾም ወቅት ሲሞት ጻድቅ ተብሎ የሚተረጐመው ? አንድ መነኩሲት አሳዳጊ እናቴ ፣ ለቅበላ ሦስት ቀን ሲቀረው ጠዋት ደህና ታይታ ያለ ህመም ከሰዓት ሞታ ስለተገኘች ፣ አይ ጻድቅ ናቸው ፣ ጾም ሳይገባ ፣ ፍትሃታቸውም እንዳይታጐል ፣ሳይታመሙም እንዲህ መሆኑ የፈጣሪ ጥሪ ነው ብለው ስላድናኑን ፣ እውነት ነው ብዬ እስከ ዛሬ ልቤ ደንድኖልኛል ፡፡ ተሸውጄ እንዳይሆን እስቲ የምታውቁ አስረዱን ፡፡ ጥያቄዬ ይኰነናሉ ብሎ ለመሞገት አይደለም ፡፡ እንኳንስ በርሳቸው ደረጃ ያለ ሁሉን የተረዳና በሃይማኖት ሥርዓት የተመራ ሰው ፣ እኔም እንኳን መንግሥተ ሰማያት እገባለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡

   Delete
  2. ተምሮ ስለማስተማር ፡-
   በአባታችን ደረጃ ያለ ቅዱስ ሰው በስጋ ሞት ሲለየን "ነፍስ ይማር" ተብሎ የሃዘን መግለጫ አይነገርም ወይም አይጻፍም ፡፡

   የሚባለው "በረከታቸው ይደርብን" ወይም "የቅድስነታቸው በረከት አይለየን" ነው ፡፡ ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ ቢሆንም ካሁን በኋላ የምትጽፉ ሰዎች አባባሉን አስተካክሉ ፡፡

   Delete
 28. አባ ጳውሎስ በቆሻሻ ስፍራ የወደቁ ጽጌረዳ...ቆሻሻውን እያየ ማን ያንሳቸው..

  ReplyDelete
 29. I would like to say sorry!

  ReplyDelete
 30. First of all I would like to express my heart full sorry!
  What is the controversy I read now?
  nefs yimar

  ReplyDelete
 31. ያሳዝናል፤ ሁሉ ነገር ማኔ ቴቄል ፋሬስ ሲሆን፤
  ልብ ያለው ልብ ይበል፤
  አሁን ጊዜው ከበድ ያለ ስለሆነ ሁሉ ትተን ወደ ፈተና እንትገቡ ተግታችሁ ፀልዩ እንደተባለ ብትፀልዩ

  ReplyDelete
 32. Minim MENIFESAWINET Yemayitaybachihu Aba Selamawoch ""ENANTE KEWODET NACHIHU KE EGIZEABHER WOYS KE DEYABILOS?""

  ReplyDelete