Friday, August 17, 2012

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሞት ለደጀ ሰላም ብሎግ ሰርግና ምላሽ ሆኗል

የቅዱስነታቸው ድንገተኛ ዜና ዕረፍት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ በብዙዎች ዘንድ ድንጋጤን የፈጠረ ቢሆንም የማኅበረ ቅዱሳን ድረገጽ የሆነው ደጀሰላም ደስታውን እየገለጸና ቅዱስነታቸው አርፈውም ለቅዱስነታቸው ያለውን ቅጥ ያጣ ጥላቻ እያስተጋባ መሆኑን ድረገጹ በዕለቱ ካወጣው ዘገባ መገንዘብ ተችሏል፡፡  

ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያኒቱን በመሩባቸው ባለፉት 20 ዓመታት በርካታ ስራዎችን ሠርተዋል፤ ሰው እንደመሆናቸውም ሊሳሳቱ ይችላሉ፡፡ ቅዱስነታቸው በርካታ ለቤተክርስቲያኒቱ የሚጠቅሙና ቤተክርስቲያኒቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነት እንዲኖራት ማድረግ እንደቻሉ፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት መሆናቸው፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚደንት፣ የዓለም የሰላም አምባሳደር መሆናቸው በቂ ምስክር ነው፡፡ ይህም ቅዱስነታቸው በዲፕሎማሲው መስክ የተሳካላቸው ሰው በመሆናቸው የተገኘ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ይህን ጨምሮ በቅዱስነታቸው ዘመን የተሠሩ ለአገርና ለወገን የሚጠቅሙ በርካታ ሥራዎች መኖራቸው የሚካድ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ቅዱስነታቸው የሠሯቸው ብዙዎቹ ሥራዎች ለማቅ እንቅፋት በመሆናቸው፣ የቅዱስነታቸውን ስም በክፉ ብቻ እንጂ በመልካም አንሥተው የማያውቁት ደጀሰላምና ብጤዎቹ ብሎጎች፣ ቅዱስነታቸው አርፈውም ሳለ እርሳቸውን ማብጠልጠል መቀጠላቸው ብዙዎችን እያሳዘነ ነው፡፡ ለምሳሌ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን የመንፈሳዊ ኮሌጆች መስፋፋትና መጠናከር፣ በልማዳዊና ባህላዊ መንገድ ሃይማኖተኛ ነኝ ለሚለው ማቅ ትልቅ እንቅፋት ፈጥሮበት ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ስለሃይማኖት ምንም የማያውቀው ማቅ ቅዱስነታቸውን መናፍቅና የተሐድሶ መናፍቃን መሪ ናቸው በማለት፣ መንፈሳዊ ኮሌጆችም የመናፍቃን መፈልፈያ ሆነዋል እያለ ሲቀሰቅስ ቆይቷል፡፡ እስካሁን በሃይማኖት ሽፋን ሲንቀሳቀስ የኖረውና የመንፈሳዊነት አንዲት ጠብታ ቀርቶ ጥሩ ፖለቲከኛ እንኳን መሆን ያልቻሉት የማኅበሩ ብሎጎች በቅዱስነታቸው ሞት ደስታቸውን መግለጣቸው በብዙዎች ዘንድ ድንጋጤን ፈጥሯል፡፡
 
ሞት ለሰው ሁሉ የማይቀር ዕጣ ፈንታ በመሆኑ፣ ሰውን ወደፈጣሪው ለመመለስ ትልቅ የንስሐ ትምህርት ነው፡፡ መጽሐፉም «ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ በልቡ ያኖረዋልና።» (መክብብ 7፡2) ይላል፡፡ ስለዚህ ከሞት ትምህርት ይወሰዳል እንጂ በሞት አይቀለድም፡፡ ልብ ያለው ሕያው የሆነም በልቡ ያኖረዋል፤ ራሱንም ይመለከትበታል፡፡ ነገም እኮ እኔ በሞት እጠራለሁ፤ ስለዚህ ዛሬ ምን ማድረግ አለብኝ ሊል ይገባዋል፡፡ ልበ ደንዳናዎቹ የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች ጸሐፊዎች ግን በቅዱስነታቸው ሞት ማዘንና ከቅዱስነታቸው ሞት መማር አልቻሉም፡፡ ድንገተኛ የሆነውንና ብዙዎችን እጅግ ያስደነገጠውን የቅዱስነታቸውን ዜና ዕረፍት እንደትልቅ ድል መቁጠራቸውም ጭካኔያቸውን አሳይቷል፡፡ የቅዱስነታቸውን ዜና ዕረፍት ተከትሎ «ቤተክርስቲያኒቱን መቆጣጠር ያለብን እኛ ነን» በሚል ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት የማኅበሩ አመራሮች፣ ያለሙት ከተሳካላቸው ቤተክርስቲያኒቱ እንዴት ባሉ ጨካኞች እጅ ልትወድቅ እንደምትችል ከወዲሁ መገመት አያዳግምት፡፡

እነርሱ ነገ የማይሞቱ መስሏቸው በቅዱስነታቸው ዕረፍት የተሰማቸውን ደስታ እየገለጹ መሆናቸውና ያላቸውን ጥላቻ አለመሸሸጋቸው የማኅበሩን ጭካኔናና ኢሰብአዊነት አሳይቷል፡፡ በቅዱስነታቸው ዕረፍት ብዙዎች ጥልቅ ሐዘናቸውን እየገለጹ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ደጀሰላም ማንንም ሊያሳምን የማይችል ተራ አሉባልታ ይዞ መውጣቱ ራሱን ትዝብት ላይ ጥሏል፡፡ ለምሳሌ የቅዱስነታቸው ድንገተኛ እረፍት በብዙዎች ዘንድ ጥልቅ ሐዘን ፈጥሮ ባለበት በመጀመሪያው ቀን፣ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ልጆቻቸውንና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን «ውሉደ ጳውሎስ /እነ እጅጋየሁ በየነ/ በፓትርያርኩ ስም ‘ጳውሎስ ፋውንዴሽን’ ለማቋቋም እየተሯሯጡ ነው፤ የሀብት ቅርምቱን ለማመቻቸት ይሆን?» በሚል ያቀረበው ዘገባ እንኳን ጠላትን ወዳጅንም የሚያሳምን እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ እንዴት መሞታቸው ሲሰማ የተጠቀሱት የቅዱስነታቸው ወዳጆች ደጀሰላም ላለው ነገር ይሯሯጣሉ?

ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ «አስከሬናቸው ይመርመር» ማለታቸውን «አልሞቱም» የሚል ቃል ጨምረውበት ለምን ለማደናገር ፈለጉ? ቅዱስነታቸው ማረፋቸው ከታወቀ በኋላ ወ/ሮ እጅጋየሁ እንዴት «አልሞቱም» ይላሉ? ይህ የደጀሰላምን አሉባልታ ጸሐፊዎች ማንነት የሚያሳይ ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡ አስከሬናቸው ይመርመር ያሉት የቅዱስነታቸው ቤተሰቦች ጭምር ናቸው እንጂ ወ/ሮ እጅጋየሁ ብቻ እንዳልሆኑ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይናገራሉ፡፡ ውጤቱ እስካሁን አልተገለጸም እንጂ አስከሬናቸው መመርመሩንም ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል፡፡ ደጀሰላም ግን ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ለይቶ ወ/ሮ እጅጋየሁ ላይ ብቻ ማተኮሩ ስለጉዳዩ የሚያወቁትን ሁሉ አሳዝኗል፡፡ የቅዱስነታቸው አስከሬን ይመርመር መባሉ ተገቢነት አለው፡፡ አስከሬናቸው ይመርመር መባሉ ደጀሰላምን ለምን እንዳስከፋው ግን ግልጽ አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም በሰላም ወደ ሐኪም ቤት ሄደው ሳይመለሱ እንደወጡ በቀሩት አባታችን በብፁዕ አቡነ መርሐክርስቶስ ላይ የደረሰው ደርሶ ከሆነ ማጣራቱ አይከፋም፡፡ ከአቡነ መርሐ ሞት በስተጀርባ የእነርሱ እጅ እንዳለበት በሰፊው ሲወራ ነበርና፡፡

በቅዱስነታቸው ዕረፍት ኢሰብአዊነት በተሞላው ጭካኔ ያላገጠው ደጀሰላም፣ ቅዱስነታቸው ሕመማቸውን ታግሰው አሞኛል ልተኛ ሳይሉ በጾመ ፍልሰታ በቅዳሴ ላይ እየተገኙ መቀደሳቸውንና ማስቀደሳቸውን ከማድነቅ ይልቅ፣ ፈጽሞ ሊነገር በማይገባ መንገድ እርሳቸውን ለመኮነን መጠቀሙ ማኅበሩ የሚገኝበትን ደረጃ አሳይቷል፡፡ ቅዱስነታቸውን ያዋረዱ መስሏቸው ሕመማቸውንና በአደባባይ ሊነገር በማይገባ መንገድ ተራ ጽሁፍ መጻፋቸው ለቤተክርስቲያን ደንታ የሌላቸው ጨካኞች መሆናቸውን አመላክቷል፡፡ በዚህ ያዋረዱት ቤተክርስቲያንን እንጂ ቅዱስነታቸውን አይደለም፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስነታቸውን አብዝቶ ቢጠላቸውም፣ እርሳቸው ግን ራሳቸውን የሁሉ አባት አድርገው ይቆጥሩ ስለነበር «እነርሱም ልጆቼ ናቸው፤ እኔ እኮ የሁሉም አባት ነኝ» በሚል በማኅበሩ ላይ እንኳ እርምጃ ሳይወስዱ እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ እንደቆዩ ይታወቃል፡፡ ቅዱስነታቸው ባላቸው የይቅርታ ልብ ከበደሏቸው ከብዙዎች ጋር እርቅን ፈጥረው ያሳዘኗቸውን ሁሉ ይቅር ብለው ይሾሙአቸው እንደነበረ ብዙዎች ይመሰክራሉ፡፡ ማኅበሩ ግን የእርሳቸውን ስም በክፉ ከማንሳትና ሊያስወግዳቸው ከማሰብ የቦዘነበት ጊዜ እንዳልነበረ በየብሎጎቹ ዘወትር ያወጣቸው ከነበሩት ጽሁፎች መረዳት ይቻላል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ሥርአተ ቀብር ለማስፈጸም በተዋቀረው ኮሚቴ ውስጥ ላለፉት 20 ዓመታት ሲያሳድዳቸውና ስማቸውን በክፉ ሲያብጠለጥል የነበረው ማኅበር በቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ በሰብሳቢው ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም በኩል መካተቱ በቅዱስነታቸው ወዳጅ ዘመዶች በኩል ቅሬታን ፈጥሯል፡፡
 

41 comments:

 1. The fact of the matter is, he ( Aba Poulos) was your father who rooted you carelessly in the Ethiopian Orthodox Church. Both you and MK are the same valueless token with extended poisonous tongue and selfish evil intended desire.

  ReplyDelete
 2. ይህ መሰሪ ማኅበር አሜሪካዊውን ጳጳስ አቡነ ማትያስን ፓትርያርክ ለማስደረግ እቅድ ሳይኖረው አይቀርም። ምክንያቱም የማቅ አፈ ቀላጤ ደጀ ሰላም ለዐቃቤ መንበርነት ስማቸውን ከጠራቸው ቀደምት ጳጳሳት መካከል አቡነ ማትያስን ሳያካትት ቀርቷል። ምክንያቱም ዐቃቤ መንበር ለፓትርያርክነት ሊወዳደር ስለማይችል እሳቸውን ከዚያ ውጭ አድርጎ ለፓትርያርክነት የማቅረብ እቅዱ አንዱ ስልት ሳይሆን አይቀርም። አቡነ ማትያስ፤
  1/ አሜሪካዊ እንጂ ኢትዮጵያዊ አይደሉም። በኢትዮጵያ ህግ ሁለት ዜግነት አይቻልም። እንዴት አሜሪካዊ ሰው ፓትርያርክ ይሆናል?
  2/ አቡነ ማትያስ እድሜአቸውን ሙሉ አሜሪካ ኖሩ እንጂ የዚህችን ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ምእመናን ኑሮ እየኖሩ፤ ረሃብና ጽሙን እየተካፈሉ፤ ኢጥሙቃንን እየመለሱ፤ ገጠርና በረሃውን እያቌረጡ ከህዝቡ ጋር ያልኖሩ የአሜሪካ ቅምጥል፤ ጢም ብቻ እያዩ ለሹመት ማሰብ ተገቢነት የለውም።
  3/ ማቅ ትግሬነታቸውን ተጠቅሞ፤ መንግስት ካጃጃለ በኋላ የራሱን ፍላጎት በሳቸው ጀርባ ለመፈጸም ያቀደው ነገር እንዳለ መጠርጠር ጥሩ ነው። አለበለዚያ በ1971 በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ተ/ሃይማኖት ከተሾሙት ቀደምት ጳጳሳት ውስጥ ለዐቃቤ መንበርነት ሳይጠቅስ የቀረው ተንኮል ቢኖረው እንጂ ረስቶ አይደለም።
  ደጀ ሰላም እንዲህ ስትል ዘግባለች።
  በ1971 ዓ.ም የተሾሙት አባቶች፤ ከሀገር ውስጥ፡- ብፁዕ አቡነ በርቶሎሜዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፤ በውጭ ሀገር በሓላፊነት ላይ ከሚገኙት ውስጥም ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ፤

  ReplyDelete
 3. አይሞከርም!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
  ሊሆን አይችልም!ዶ/ሩ እዚያ ምን ሊሰሩ?ከዚህ ቀደም ያደረጉት ይበቃል!ቅሬታችን ይቀጥላል::
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 4. ይሁን እንጂ ...
  በሚለው ፈንታ ይህን የቤተ ጳውሎስን መልዕክት ሙላበት
  በኢትዮጵያ ቤ/ን ታሪክ ቤተ ክርስቲያኒቱን ካስተዳደሩ አባቶች መካከል እጅግ አነጋጋሪና አከራካሪ የነበሩ ሰው ቢሆንም በፓትሪያሪክነት ስልጣን ከመጡ ጀምሮ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንኙነቷንና ተሰሚነቷን በማሳደግ ከፍተኛ የሆነ አስተዋእፆ የነበራቸው አባት እንደነበሩ በብዙዎች ዘንድ ይነገርላቸዋል፡፡ ፓትሪያሪክ አቡነ ጳውሎስ በዓለም አቀፍ በሆኑ ትልልቅ ስብሰባዎች ላይ ስለ ዓለም ሰላም፣ ስለ ሴቶች መብትና የትምህርት ዕድል፣ ስለ ሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ፣ በHIV/AIDS በመሳሰሉት የዓለማችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተግዳሮቶች ላይ በአፍሪካና ዓለም አቀፍ ደረጃ ድምፃቸውን በማሰማትና የላቀ አስተዋዕፆ በማበርከት ትልቅ ድርሻ የነበራቸው፣ በተባበሩት መንግሥታት፣ በወርልድ ኢኮኖሚ ፎረም፣ በዓለም ሃይማኖቶች መሪዎች ስብሰባ ላይ በመገኘት በሚያደርጓቸው ንግግሮችና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ትልቅ ስምንና ዝናን ያተረፉ አባት ናቸው፡፡
  የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽንም ፓትሪያሪክ አቡነ ጳውሎስ ለዓለም ስደተኞች ባደረጓቸው የላቀ እንቅስቃሴና አስተዋዕፆ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ የናሰን ሜዳሊያ እ.ኤ.አ 2000ዓ.ም ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
  ለተቀረው መግለጫችሁ ሰፊ ጊዜ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደፊት አለን ፡፡

  ReplyDelete
 5. Ahunes Abezachihut.... You guys always spread hate among our mother church memembers.

  ReplyDelete
 6. lemin endezeh tenchachachhu.endemnawqew qdusnetachew lenante kifu alneberum.kengdh gin ende amlak fekad lenante mecheferyanetua leyabeka ychlal.

  ReplyDelete
 7. please visite and add the following
  http://eotc-peace-and-unity.blogspot.com/
  blessings

  ReplyDelete
 8. አዎ ብዙ ሰርተዋል። አዲሱ እቅዳቸውም የቦዜኔዎች መሰብሰቢያ ያላችሁትን የገዳም መሬት በሸንኮር አገዳ ማልማት ነበር። ነገር ግን ገዳሞች ሳይዘጉ የገዳሞች ባለቤት ቀድሞ በመምጣት ተከላከለ። እናንተም ከማቅ ላይ ያረፈውን ደም መጣጭ ቅማላችሁን አራግፉና የገዳሙን ባለቤት አዳምጡ። የማቅአችሁን ጉዳይ ለባለቤቱ ተውት፤ ባለቤቱ በናንተም ላይ በትሩን እንዳይጥልባችሁ ተጠንቀቁ፤ ንስሐ ግቡ።
  በነገራችን ላይ፤ ይህ ጽሑፍ ከማቅ ሳይሆን ከናንተው ከራሳችሁ ነው፤ ማቅ በዚህ ጽሑፍ ተጠያቂ አይደለም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የአባታችን ሞት ምክንያት በተፈጥሮ በሽታ ማለትም የስኳርና የደም ብዛ ችግር ስለነበረባቸው እንጅ ከሌላ ምክንያት ጋር አይያያዝም ፡፡ አሏቸው የተባሉት ሁለቱም የበሽታ ዓይነቶች ጥብቅ የህክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ፣ መድኃኒት በሰዓቱ መውሰድ የሚፈልጉ ስለሆኑ ፣ ከጾም ጋር የማይስማሙ ናቸው ፡፡ እንዲያውም ምናልባት አክራሪ ጿሚ ከሆኑ /አልጠራጠርም/ መድኃኒታቸውን በተገቢ ሰዓት ስላልወሰዱ ሊሆን ይችላል የሚሞቱት ፡፡ እግዚብሔር ሰው ስላልሆነ ሰውን በመግደል አይታደግም ፣ የአባቶች ጸሎትም ቢሆን ሰዎች እየሞቱ ገዳም እንዲተርፍ አይደለም ፡፡ ጸሎታቸው ሁሉ ፣ ልቦናቸውን መልስላቸው ፣ እኛ ያየነውንና የተረዳነውን ምስጢር እነርሱም እንዲያውቁ አግዛቸው ሊሆን ነው የሚችለው ፡፡ ታድያ የአብዬን ወደ እምዬ ለምን እናዘዋውራለን ፡፡ እግዚአብሔር አንድ ቅዱስ አባትን ገድሎ ገዳም ከሚያስከብር ፣ ውሃውን ወደ ደም ቀይሮ ወይንም ወንዙን አድርቆ ፣ ሜዳውንም ተራራ አድርጐ ፣ ለሙን መሬትም የድንጋይ ንጣፍ አልብሶ ማስተጓጐል ይችላል ፡፡ የሱን የገዳም የመታደጊያ ብልሃት ገና ወደፊት እንጠብቃለን ፡፡ የኔ የደንባራው ጸሎት እንኳን እገሌን ግደል አይልም ፡፡

   Delete
  2. tenese afehene kemetekefete yetefabehene tuto felege wate

   Delete
 9. We know that MK is cannot represent the church because from the begging this group is not religious even better to be called political group. This group is possessed by devil.

  ReplyDelete
 10. As Christian we are not happy by the death of abune Paul but this stupied mahber is very happy. The only creature to be happy is satan because he is a killer and I am seeing the same thought from the MK ohhhh sory mahbere irkusan

  ReplyDelete
 11. Death for MK!!! For the enemy of holly gospel

  ReplyDelete
 12. ከአቡነ መርሐ ሞት በስተጀርባ የእነርሱ እጅ እንዳለበት በሰፊው ሲወራ ነበርና!!! ye inne man???? please please please remember for a while that there is God Who knows every thing!

  ReplyDelete
 13. all the death of the prime minister ( meles zenawi ) and the patriarch( abune powlos) is the result of their racist, corrupted, and maltreatment of our church. particularly it is the GOD that did this due to THE PLAN OF DESTRUCTION WALDIBA MONASTERY. MONKS HEAVILY HURT, WEEPING DEEP.IT IS GOD'S RESPONSE, ALL OF YOU GET WHAT YOU SOW.KEEP ON YOUR TURN. BREAKING NEWS SAMORA YENUS ALSO SERIOUSLY ILL AND LEFT THE COUNTRY.

  ReplyDelete
 14. ከአባታችን ሞት በኋላ የተማርኩትን ለማካፈል ፡፡

  በአባታችን ደረጃ ያለ አንድ ብፁዕ ሰው በስጋ ሲሞት ነፍስ ይማር አይባልም ፤ "በረከታቸው ይደርብን ወይም አይለየን" ነው የሚባል ብለው አንድ ግለሰብ ጽፈው አንብቤአለሁና ያለ ዕውቀት ከመሳሳት እንቆጠብ ፡፡ ለማለቱ እኔም ምን እንደሚባል ቀድሞ ልምዱ ስለሌለኝ ስህተት ፈጽሜአለሁ ፡፡ አዲስ ጻፊዎች ግን ይኸን ቃል ተጠቀሙ ፡፡ ትክክለኛ አገላለጽ የምትሉትን ሁሉ ብታሰፍሩ ዳግም ሌላ አባት ሲሞት አንሳሳትም ፡፡

  ReplyDelete
 15. በአባ ጳውሎስ እረፍት በቤተ ክርስቲያናችን የተሰገሰጉ የጴንጤና የመናፍቃን መንጋ አላማ ይከሽፋል!! አይሳካም!! ከሽፏል ። ከሸፈ፣ ከሸፈ። ስለዚህ ቁጭ ብለህ አልቅስ፤ የቤተክርስቲያናችን የኢየሱስ አዳኝነት ትምህርት፥ የድንግል ማሪያም እና የቅዱሳን ክብር አይቀየርም። እንኳን ሄደው ኖረውም የጴንጤዎች አላማ አልተሳካም። አንተ አታምንበትም እንጂ ነፍሳቸውን ይማር እንላለን። በመሞታቸው ግን ለቤ/ያን አዲስ ነገር መጥቷል። አንተ በግልህ ወደ ቤቴል የጴንጤ አዳራሽ ትሄዳለህ። እኛ እዚሁ እንቆያለን። ማቅ ማቅ አትበል።. የማቅ ትምህርት የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ነው። ያንተና የመሰሎችህ ግን የጴንጤ ትምህርት ነው። ስለዚህ ማቅን እንመርጣለን

  ReplyDelete
 16. Ataminum Enji Mirmeraw bezih ayabekam Niseha Enegiba.Abata gorbata hulu Yikesefal!

  ReplyDelete
 17. elelel elele....

  ReplyDelete
 18. ተሐድሶ መናፍቃን ነፍስ ይማር አይቀድምም?
  ደጀሰላምም ሆነች ሌሎች እውነተኛ የተዋህዶ ብሎጎች ከዚህ በፊት በነገሯችሁ መሰረት እግር በእግር እየተከታተሉ የቤ/ን ጠላቶችን ያሳፍራሉ፤ለቤ/ክን ልጆች ጠቃሚ መረጃን ይሰጣሉ፡፡ እንግዲህ ብዙ ተመክራችኋል፤አልሰማ ስላላችሁ ሌላ ነገር ጠብቁ ፤ ቅዱሳንና ማረፊያቸውን ተዳፍራችኋል፤ ሌላ ማንም መልስ ሰጪ የለም፤ ሁሉም ምድራዊውን መንግስት ፈርቷል ፤ ልዑል እግዚአብሔር መድኃኔለም ክርስቶስ መልስ መስጠት ጀምሯል፤ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ፤

  ReplyDelete
 19. you get a big job. meles and paulos got their own wage. please do not be mindless vandalism, bigoted, stupid.

  ReplyDelete
 20. ለመሆኑ ብጹነታቸው የትግራይ ተወላጅ በመሆናቸው በማህበረ ቅዱሳን መሰደብ ይገባቸዋል?
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ህዘብ የሚወዳቸውን ታላቅ ምሁር አባት ለምን ዘር የተነሳ ይሰደባሉ?
  ከእግዚአብሐር ቃል ምን እናማራለን ?
  ጌታችን ምን እንድናደርግ አዞናል? ፍቅር ወንስ ስድብ?

  ReplyDelete
 21. እውነተኛና ሚዛናዊ ከሆናችሁ ይህን አስተያየት በብሎጋችሁ ታወጡታላችሁ፤ ካልሆናችሁ አታወጡትም፡፡ ለመሆኑ ደጀ ሰላም blog የእነሱ ለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አላችሁ፡ ስለ ኣባ ጳውሎስ የተባለውስ ነገር ውሸት ለመሆኑ ምን ማስረጃ አላችሁ; ከእናንተና ከመሰሎቻችሁ ጋር አብረው ይህቺን ቤተክርስቲያን ለመናፍቃን ለመሸጥ እያስማማችሁ ስንት ብጥብጥ አለፈ፡፡ ስንቱስ ከቤተክርስቲያን ራቀ፣/ለነገሩ የእናንተም አላማ ይሄው ነው፡፡/ ስንቱስ በሃፍረት አንገቱን ደፋ; ለመሆኑ እናንተ እነማን ናችሁ;
  በእውነት ፓትርያርኩ የተጣሏቸውን ይቅር ለማለትና ሥልጣን ለመስጠት ሞክረው ያውቃሉ; ኣሜሪካ ከሚኖሩት አባቶች ጋር ለምን አልታረቁም; ይቅር ተባባሉ፣ በፍቅር ኑሩ ብለው ለማስተማር ሞራሉ ነበራቸውን; ዓላማቸውን ለማስፈጸም ሲሉ እነ በጋሻውን፣ ጌታቸው ዶኒን፣ “አባ” ሰረቀን፣ የአዋሳዎቹን … አዎ “ይቅር” ብለው ስልጣን ሰጥተዋል - ለምን በኣላማ አንድ ስለነበሩ፡፡ 20 ዓመት ሙሉ በስልጣን ላይ ሲኖሩ ከአንድ የሃይማኖት አባት የማይጠበቅ ስንት ርካሽ ስራ ሰርተዋል; ባለትዳሯን ሴት እጅጋየሁን ከባሏ ጋር አፋትተው የቤት እመቤት ማድረግ፣/ ባይሆንማ ያስታርቋቸው ነበር፡፡ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን እንደተገደለው ባህታዊ ያለ ስንት ሰው በስውር ሞተ፣ ስንቱ እያለቀሰ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ወጣ፣ ስንቶቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከቤተክርስቲያን ግቢ እየተደበደቡ እንዲወጡና እንዲታሰሩ አስደረጉ፣ የስንቶች ጳጳሳት አባቶች ቤት ተደበደበ፣ ስንት ገንዘብ ተበላ/ተዘረፈ፣ አምባ ገነንነት ከአንድ የሃይማኖት አባት ይጠበቃል; ሰው በሕይወት እያለ ለምን ሃውልት ያሰራል; ያን ሁሉ የመዓርግ ስም መደራረብ ለምን አስፈለገ; ለክብር፣ ለዝና፣ ለውዳሴ ከንቱ፣ ለምን; ይህ ሁላ ከካባ ላይ ለምድ መደራረብ አስፈለገ; … ይህን ካስተናገዳችሁ በሌላ ጊዜ እመለሳለሁ፡፡ ቻው፡፡

  ReplyDelete
 22. እውነተኛና ሚዛናዊ ከሆናችሁ ይህን አስተያየት በብሎጋችሁ ታወጡታላችሁ፤ ካልሆናችሁ አታወጡትም፡፡ ለመሆኑ ደጀ ሰላም blog የእነሱ ለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አላችሁ፡ ስለ ኣባ ጳውሎስ የተባለውስ ነገር ውሸት ለመሆኑ ምን ማስረጃ አላችሁ; ከእናንተና ከመሰሎቻችሁ ጋር አብረው ይህቺን ቤተክርስቲያን ለመናፍቃን ለመሸጥ እያስማማችሁ ስንት ብጥብጥ አለፈ፡፡ ስንቱስ ከቤተክርስቲያን ራቀ፣/ለነገሩ የእናንተም አላማ ይሄው ነው፡፡/ ስንቱስ በሃፍረት አንገቱን ደፋ; ለመሆኑ እናንተ እነማን ናችሁ;
  በእውነት ፓትርያርኩ የተጣሏቸውን ይቅር ለማለትና ሥልጣን ለመስጠት ሞክረው ያውቃሉ; ኣሜሪካ ከሚኖሩት አባቶች ጋር ለምን አልታረቁም; ይቅር ተባባሉ፣ በፍቅር ኑሩ ብለው ለማስተማር ሞራሉ ነበራቸውን; ዓላማቸውን ለማስፈጸም ሲሉ እነ በጋሻውን፣ ጌታቸው ዶኒን፣ “አባ” ሰረቀን፣ የአዋሳዎቹን … አዎ “ይቅር” ብለው ስልጣን ሰጥተዋል - ለምን በኣላማ አንድ ስለነበሩ፡፡ 20 ዓመት ሙሉ በስልጣን ላይ ሲኖሩ ከአንድ የሃይማኖት አባት የማይጠበቅ ስንት ርካሽ ስራ ሰርተዋል; ባለትዳሯን ሴት እጅጋየሁን ከባሏ ጋር አፋትተው የቤት እመቤት ማድረግ፣/ ባይሆንማ ያስታርቋቸው ነበር፡፡ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን እንደተገደለው ባህታዊ ያለ ስንት ሰው በስውር ሞተ፣ ስንቱ እያለቀሰ ከቤተክርስቲያን አገልግሎት ወጣ፣ ስንቶቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከቤተክርስቲያን ግቢ እየተደበደቡ እንዲወጡና እንዲታሰሩ አስደረጉ፣ የስንቶች ጳጳሳት አባቶች ቤት ተደበደበ፣ ስንት ገንዘብ ተበላ/ተዘረፈ፣ አምባ ገነንነት ከአንድ የሃይማኖት አባት ይጠበቃል; ሰው በሕይወት እያለ ለምን ሃውልት ያሰራል; ያን ሁሉ የመዓርግ ስም መደራረብ ለምን አስፈለገ; ለክብር፣ ለዝና፣ ለውዳሴ ከንቱ፣ ለምን; ይህ ሁላ ከካባ ላይ ለምድ መደራረብ አስፈለገ; … ይህን ካስተናገዳችሁ በሌላ ጊዜ እመለሳለሁ፡፡ ቻው፡፡

  ReplyDelete
 23. until know I belive you because you write the fact with evidenc but now I don't know why you lay. When I heard the bad news of our church, I expect from you MK kills the pop. anway you are also human being so same times you might made a mistake.GOd bless you work.

  ReplyDelete
 24. whydid you hide my suggetion weshewoch MK matifo new endilachiue new yemitifalgut. hodam lenant yblagn engi endamatawetut eyaweku naw astyaytun ylakulachhu.

  ReplyDelete
 25. "አባ ሰላማዎች" እኔ የብሎጋችሁ ተከታታይ ነኝ:: አሁን አሁን ግን በእናንተ ላይ ቅሬታ እያደረብኝ ነው:: የምትጽፉት ሁሉ ስለ ማቅ ብቻ እየሆነ መጣ:: ብሎጋችሁም "የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ብሎግ" እስኪመስል ድረስ በማቅ ተጥለቅለቀ:: እኛ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ነው መስማት የምንፈልገው እንጂ የአንድ ማህበር የዕለት ተዕለት ውሎ ላይ ብቻ የሚያተኩር ትችት አይደለም:: ዓላማችሁ ማቅን ማጥፋት ብቻ ከሆነ እርሱ የጠፋ ዕለት የእናንተም የስራ ማብቂያ ይሆናል ማለት ነው::በተጨማሪም ዓላማችሁ የጠላትነት ይሆናል::ወይ መሰረታዊ ዓላማችሁን ረስታችሁታል ወይ ደግሞ በማቅ ምክንያት ተስፋ ወደመቁረጥ የደረሳችሁ ይመስላልና አስቡበት::

  ReplyDelete
 26. I have a suspicious on mahibere kidusan may be they are the one had a roll to kill Abune Paulos.

  ReplyDelete
 27. I hate "mahibere kidusan"

  ReplyDelete
 28. Abune pawlos killed by mk. Medical result release for public soon from Balcha hospital. But mk make offer 4.5billion birr to hide the drama for examainer to change his report format that is sad for all Eotc.

  ReplyDelete
  Replies
  1. billion haa???? kuter yemtakem aymeslem endew zim belachu atebedu MKen tilashet meleklek endehu lemadachu new!! Menafeq hula....

   Delete
 29. አስካሁን ድርስ ገለልተኛ ነኝ ሲል የነበረው ዳላስ አካባቢ የሚገኘው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቦርድ አባላት ለ አቡነ ጳውሎስ ቀብር መለክተኛ ለመላክ መእመኑ ሳይሰማ በድብቅና አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ አጸደቁ።

  ReplyDelete
 30. Yetibebe mejemeria Egziabeheren mefrat new, tibebum hegegatochun metebek new. Ebakachue Leteneshua melasacheu lugam Ashebulat. Keafacheu alfa seweneten wedeseol tawerdalechena Demiski zeatlanta

  ReplyDelete
 31. እንሆ ቅዱሰ አባታችን በግበረ ኤዎሰታቴዎሰ እና ዮሃንስ አፈወርቅ ከአጽራረ ቤተ ከርስትያን ጋር ሲዋጉ መዋእለ ስጋቸውን ፈጽመው አርፈዋል::
  1 የደርጎችን ፈቃድ በመጋፈጥ ቤዛ ቤተ ክርስትያን ታስረዋል
  2 ቤተ ክርስትያን በኢኮኖሚ ራስዋን አስችለዋል
  3 መንፈሳዊ ኮሌጆችን አሰፋፈተዋል
  ከዚህ በሃላ
  1 ህግ ይወጽእ እም ፅዮን እንደተባለው ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ ጥነተ ቦታው አኩሱም ይመለስ::
  2 ኣጽመ ቅዱሳን በረከት አለውና የቅዱስ አባታችን አጽም የተም መቀበር የለበትም ስለዚህ ወደ መንፈሳዊ ቤቱ መደራ: ገዳመ ኣቡነ ገሪማ ይምጣ ::
  3 ከሌብ ከኣባ ጴንጤሌዎን ጋር በገዳም : አጽብሃ ከአብርሃጋር በመንፈሳዊ ቤቱ :እንዲሁም ገበረመስቀለ በደብረ ዳሞ በመካነ ቅዱሳን አበው እንደተደመረው :ደቂቀ እስጢፋኖስ የመምህራቸውን አዕም ከምድረ ሸዋ ወደ ምድረ አግኣዚ አንዳፈለሱ :ቅዱስ አቡነ ጳውሎስም በመንፈሳዊ ቤታቸው መደራ ከነ አሉላ ጋር ይደመሩ:: በአቡነ ገሪማ እቅፍም ይግቡ::
  ዘቦ እዝን ሰሚኣ ለይስማእ!!!!!

  ReplyDelete
 32. እንሆ ቅዱሰ አባታችን በግበረ ኤዎሰታቴዎሰ እና ዮሃንስ አፈወርቅ ከአጽራረ ቤተ ከርስትያን ጋር ሲዋጉ መዋእለ ስጋቸውን ፈጽመው አርፈዋል::
  1 የደርጎችን ፈቃድ በመጋፈጥ ቤዛ ቤተ ክርስትያን ታስረዋል
  2 ቤተ ክርስትያን በኢኮኖሚ ራስዋን አስችለዋል
  3 መንፈሳዊ ኮሌጆችን አሰፋፈተዋል
  ከዚህ በሃላ
  1 ህግ ይወጽእ እም ፅዮን እንደተባለው ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ ጥነተ ቦታው አኩሱም ይመለስ::
  2 ኣጽመ ቅዱሳን በረከት አለውና የቅዱስ አባታችን አጽም የተም መቀበር የለበትም ስለዚህ ወደ መንፈሳዊ ቤቱ መደራ: ገዳመ ኣቡነ ገሪማ ይምጣ ::
  3 ከሌብ ከኣባ ጴንጤሌዎን ጋር በገዳም : አጽብሃ ከአብርሃጋር በመንፈሳዊ ቤቱ :እንዲሁም ገበረመስቀለ በደብረ ዳሞ በመካነ ቅዱሳን አበው እንደተደመረው :ደቂቀ እስጢፋኖስ የመምህራቸውን አዕም ከምድረ ሸዋ ወደ ምድረ አግኣዚ አንዳፈለሱ :ቅዱስ አቡነ ጳውሎስም በመንፈሳዊ ቤታቸው መደራ ከነ አሉላ ጋር ይደመሩ:: በአቡነ ገሪማ እቅፍም ይግቡ::
  ዘቦ እዝን ሰሚኣ ለይስማእ!!!!!
  ፈቃደ ስላሴ ይሁን:: ዓሜን
  ኣባ ኣቡነ ረድኣ ቤተ ኤወስታቴዎሰ ፍጹም
  ወኣዲ በግብር ከመ ገሪማ ግሩም
  እፎ ፈለስከ ጊዜ ፍልሰታ ለእም
  ወእፎ ገደፍከነ በጊዜ ህሰም ወተስናን
  እንዘ ንሴፎ በጻሕቅ ተፍጻሜተ ሙዜም ዘፅዮን::
  ኣባ ኣቡነ ረድኣ ቤተ መደሃኒነ እግዚእ ወእለ ሰላማ ስዩም
  መኑ ዘጸውኣከ ወሃበ አይቴሰ ኮነ አሰረ ፍኖትከ
  ለእመ ኮነ ሃበ እለ ኣረጋዊ ወሃበ እለ የምኣታ ኣበዊከ
  ህየ ከመ ልማድከ
  ኢታህጽጽ እንክ በይነ ሃጢኣትነ ከሊሓ
  በስኢለ ኣብ ወእም በይነ እከይነ ወሃጢአትነ ዘበዝሓ
  ለይትመሃው እምነስረዊሁ ከመ ጥቅመ ባቢል ዘኖሃ::
  ኦ ቀሰ መደራ ዘእለ ገሪማ ጥንተ ርስት
  በከመ ቀዳሚሰ ኮነ በሞተ ቅዱሳን ዘትካት
  ፈኑ ሃቤነ ሃበ ትግራይ አጽመ ዚኣከ ቅድስት
  አምጣነ ልማድ ጸንሓ ተደምሮ ዘምስለ አበው ቀድምት
  በከመ ተደመረ ካሌብ በዘ ሊቃኖሰ በዓት
  ወዓዲ ገብረመስቀል በውስተ ዳሞ እንተ ይእቲ ፍኖተ ገነት::
  ኦ ሊቅ ማእምረ መጻሕፍት ከመ ዮሃንስ አፈወርቅ አበ ግብርከ
  ወተወካፌ ህሰም መራድ በአፈ መሰርያን አጽራረ ደቂቀ እሰጢፋኖሰ አሃዊከ
  ከመ ቀዳሚሰ ዮም ግብረ ጉህላዌ ወዜና አህስሞ እመ ኣፈድፈዱ በላእሌከ
  ይእዜሰ ግብተ ተፈልጦትነ አቅደምከ::
  ኮነኑ ተፈጸመ ነቢረ ዘምስለ እከይነ ለኩለሄ ጸላኢከ::
  ኮነኑ ተፈጸመ ብሄርከ ወለጥከ::
  ኦ ካህነ አግአዚ አሰረ ኣበው ዘእለ አትናቴዎስ ወቄርሎስ ዘተሎከ
  ዮም በዛቲ ሰዓት እትመሃጸነከ
  በስመ አብ አሀዜ ኵሉ እንተ አግሀደ ዓለመ
  ወዓዲ በስመ ወልድ ዘከአወ ደሞ ህየንተ አዳም ዘሐመ
  ወሳልሰ በመንፈስ ቅዱስ እለኪያከ ካህናቲነ ዘሤመ
  ወራብኣ በስመ ድንግል ዘበእንቲኣሃ ተስፋ ኣበዉነ ተፈፀመ
  ከመ ንስእል ወንትመሃጸን በተማህጽኖ ኣጽምከ
  በከመ ቀዳሚሰ ኮነ በሞተ ቅዱሳን ዘኢትዮጵያ
  ፈኑ ሃበ ትግራይ (ጥንተ ኢትዮጵያ) አጽመ ዚአከ ከመ ኣፍለሱ አጽመ ያዕቆብ ደቂቀ ራሄለ ወልያ
  በጊዜ ጸኣት ወተመይጦ እም ብሄረ ባእድ በብሂለ ሃሌ ሉያ
  በስልጣነ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ግብረ ኬንያ::
  ኦ አጽቀ ሌዋውያን ጳውሎስ ወልደ ገሪማ
  ለእመ ኮነ በምእር ንግደተ ነፍስከ ሃበ ራማ
  ከመእንተ መብረቅ በግብት ከመ ቃለ ወልድኣብ ፈለማ
  ተጸገው ኣስበ ተጋድሎ ወዘስጋከ ጻማ::
  ወንሀነሂ እመ ተሎነ በኣሰርከ እንተ ይእቲ ፍና ጽድቅ
  እይትነገፍ አንከ እምብሄርነ ነገረ ሀይማኖት ወጽድቅ
  አኮኑ ተተከልነ ሃበ መሃዘ ማየ ህይወት በከመ ተነግረ በአፈ ዳዊት ሊቅ::
  ወበእንተዝ ነገር ለእመ ሰብኣ ብሄር በእያአምሮ ጠየቁ
  አውስኡ ከመ መድሃኒነ እግዚእ ገደፈ አለ ሳሙኤል ደቂቁ
  አመ እእረፈ በክብር ለዝንቱ ዓለም እምጻህቁ::
  ኤዎሰታቴዎሰሂ ገደፈ እለ ኣብሳዲ በምርፋቁ;;
  ወትምህርተ እስጢፋኖስ ፈድፈደ በእለ አበከረዙን አአጽቁ
  እነዘ ይትመሰዉ ከመ ስመዕ ሰብአ ብሄሩ ለድብፀር
  በግብረ ኑፋቄ ወጉህላዌ ከመ ለሓመድ ይግህፎ ነፋሰ እምገጸ ምድር::
  ኦ አሃው ሰብኣ ሃገር ዘምድረ ኣግአዚ ቅድስተ
  ብነ ስራሕ ከመ ንህንጽ መዓልተ ወሌሊተ
  ለፅዮን እምነ በእያእርፎ ከመ ንህነፅ ቤተ
  ኣኮኑ ጳውሎስ ሃናጼ ሙዜም ሃበ እግዚኡ ተከብተ::
  ዝንቱስ ነገር በእደ ጳውሎስ ተፈለመ ወተከስተ
  ርሂቅነ እምግብረ ጥበብ እንዘ ናፈደፍድ ሐጢአተ::
  ኦ ሰብእ ሃገር ናፈድፍድ አዘክሮ ወአጠይቆ
  በይነ ዘሓለፈ ዘመን በግብረ ጌጋይ ወተላጽቆ
  እንዘ ገዳማተ ክብር ይማስኑ በግብረ መራዳን
  እለ ያዘንሙ እሳተ እመ ሃበ ኣየር ሃበ ማህደራ ለፅዮን
  እመ ረሳኢነ ይእዜ ዘረከበነ ሃዘን
  ኣመ ይውኢ ማህደራ ለፅላተ ሙሴ በአህማረ እከይ ዘእየራት
  ወዳግመ ከመ ዘሓለፈ ይረክበነ እመ ደቀስነ ዘእንበለ ስኢል ወፆሎት
  ወካእበ ይደልወነ ከመ ናዘክር ለለእለት
  በኢያጽርዖ ኩለሄ ለለሠዓት
  ኦ ሰብኣ ሃገር ዘኣድያማቲሃ ለጥንተ ኢትዮጵያ
  አእምሩ ወተመሃሩ ከመ ፈድፌደ ወበዝሓ ክብረ ደቂቃ ለልያ
  በኣዘክሮ ትርሲተ ወጽጋዌ ጥበብ እንዘ ልሳነ ሰብእ ይትቀነያ
  ለነኒ ከመዝ ይደልወነ ልሳናቲነ ይንብባ ወይህልያ
  በኣውሰዖ ወኣወድሶ ጥበበ አበዊነ በብሂል ኬንያ
  ኣነኒ አወስእ ዘበ ንእስየ ቃለ ምእዳን
  እንዘ አብል ንሕንጽ ማህደረ ነዋያት ዘፅዮን
  ኣምጣነ አሜሃ ነበርነ ወጌስነ በመርሃ ዕውራን
  ለነዊህ መዋዕል መጠነ አሰርቱ ምአተ ዘመን
  ህየንተ በግብረ ጥበብ ዳኢሙ በአፍቅሮ ሃኬት ወተስናን
  እንዘ ንሴፎ ካለኣነ ሃበ ጽግም ወይምን
  መዋኢልነሰ ሀለፈ ወተሰለጠ በእንባዜ ወርስኣን::
  ዮምሰ ተጸጎነ ዘመነ ልምላሜ ወሠላም
  አኮ አኮ ከመ ትማልም ህሱም
  ወበእንተዝ ናሰኒ ማህደረ ድንግል : ማህደረ ኣምላክ ፍፁም
  ሃዲገነ ተጻብዖ ከመ ትትሐሠይ ማርያም::
  ንፈጽም ዘተወጥነ በመዋዕሊነ ማህፈደ ንዋያት ዘእም
  ዘአኩስም ፅዮን ሙዜም::

  ReplyDelete
  Replies
  1. < የተም malet min malet new tsehafiw ye kidist bete kirstianin kibr enkuwan balemaweko askedimo limaru betegeba neber besrachew baytsediku enkuan beftihatu be zewetr kidase tselotina be Q.SILASE katederal betekeberut kidus atsim yibarekalu.mastewalun yistot.

   Delete
  2. የተምን ካላወቁ ትምህርት ቤት ገብተው ይማሩ!!

   Delete
 33. MAHBERE KIDUSAN abalatu hulu be Abune Pawlos ereft betam aznewal.Tsifet betachew heje ayehuachew. Hulum asazenugn. Ke Sira Asfetsami jemro eske tibeka dires betam aznewal. Abune Pawlos Mahberun betam aseqaytewtal.Lijochu gin qim alyazum. Egzyabher yasadigachihu Mahbere Kidusanoch. Ewnetegna Lijoch nachihu.
  Kiros W/Amanuel
  Imigration Office

  ReplyDelete
 34. seytan yesewochin mot yimegnal amlak gn yesewochin dinet.

  ReplyDelete
 35. hulaceneneme geta yefewsene

  ReplyDelete
 36. betamyegermal hunetawechsitatayu mknytum sew kemote buhala mewkes men ytekmal slesih keahun buhala leketayu men yshalallel blene meweyayet yasfelgal bye amnalehu

  ReplyDelete