Sunday, August 19, 2012

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ዜና ዕረፍት የሃይማኖት መሪዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጹ ነው

ማኅበረ ቅዱሳን በቀጣዩ ፓትርያርክ ምርጫ ላይ ጣልቃ ለመግባት ቅስቀሳ ጀምሯል
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አርፈዋል፡፡ በዘመናቸው ለቤተክርስቲያን፣ ለአገርና ለወገን ያበረከቷቸው እጅግ በርካታ ጠቃሚ ስራዎች አሉ፡፡ በተለይም ዛሬ በቤተክርስቲያኒቱ በተለይም በስብከተ ወንጌልና በመንፈሳውያን ኮሌጆች ዙሪያ የሚታየው ለውጥና የብዙዎች ሕይወት በእግዚአብሔር ቃል መለወጡ በቅዱስነታቸው ዘመን የታየ አንዱ ፍሬ ነው፡፡

ከተቋቋሙበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ዓመታት የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ደጀ ሰላምና ብጤዎቹ ብሎጎች ግን የቅዱስነታቸውን ሰብእና ሲያንኳስሱ፣ ሲያዋርዱ መኖራቸው ሳያንስ አሁን ዜና ዕረፍታቸውንም ተከትሎ የእርሳቸውን ሰብእና በማበላሸቱ ሥራ ተጠምደው ይገኛሉ፡፡ ክፉዎች የጠሉትን ሰው በሕይወቱ እያለ ብቻም ሳይሆን፣ ሞቶም ቀብሩን እስከማበላሸት እንደሚደርሱ የታወቀ ነው፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች እያደረጉ ያለውም ይህንኑ ነው፡፡ የቅዱስነታቸው የቀብር ሥነስርአት በአዲስ አበባ እንዳይፈጸምና አክሱም ላይ እንዲሆን ለማድረግ የማኅበሩ ሰዎች ውስጥ ለውስጥ እንቅስቃሴ ጀምረው የነበረ ቢሆንም፣ ሳይሳካለቸው መቅረቱንና ሐሳቡ በራሱ ብዙዎችን እንዳሳዘነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህም ቅዱስነታቸው በክብር እንዳይሸኙና በጎ ስራዎቻቸው ጎልተው እንዳይወጡና ታፍነው እንዲቀሩ ለማድረግ ማኅበሩ ካለው ከንቱና ጭፍን አቋም የመነጨ እንደሆነ ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እየገለጹ ነው፡፡

የማኅበሩ ሐሳብ ይህ ቢሆንም፣ በቅዱስነታቸው ድንገተኛ ዜና ዕረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚገኙና አብረዋቸው የሰሩ የሃይማኖት አባቶች የቅዱስነታቸውን መልካም ስራዎች በመዘከር ትልቅ አባት ማጣታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባላት፣ በውጭ የሚገኙ ልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ በአገር ውስጥ የሚገኙ መንግስታዊ ተቋማት በቅዱስነታቸው ዜና ዕረፍት የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ ይህም ቅዱስነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ስለነበሩ ብቻ ሳይሆን፣ በዓለም ሰላምና በሃይማኖቶች መካከል መቻቻል እንዲኖር ካበረከቱት ከፍተኛ አባታዊ አስተዋፅኦ የተነሳ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ የሚገኙት የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባላት ማለትም ከካቶሊክ፣ ከመካነኢየሱስ፣ ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ ከሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት እና ከእስልምና መሪዎች በጋራ ሆነው የሰጡት መግለጫ ቅዱስነታቸው በሃይማኖት መካከል ሰላምና ፍቅር እንዲኖር ለሰሩት ትልቅ ሥራ ምስክር ነው፡፡

በቅዱስነታቸው ዜና ዕረፍት የተደሰተው ማኅበረ ቅዱሳን ግን ከእርሳቸው ሞት በላይ ያሳሰበውና ከፊቱ የተደቀነው የቤት ስራ ቀጣዩ ፓትርያርክ ማን የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ መንግሥት ጣልቃ ይገባብኛል በሚል ስጋት ውስጥ መወደቁን በደጀሰላም ብሎግ ይፋ አድርጓል፡፡ «የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ፤ ‘የገበያ ግርግር’ ይሆናል» በሚል ርእስ ያወጣው ዘገባ መንግስትን በጣልቃ ገብነት የሚከስና ሁሉን ለእርሱ በሚመች መንገድ ለማከናወንና የራሱን ፓትርያርክ ለመሾምና ቤተክርስቲያኒቱን ለመቆጣጠር ዕቅድ እንዳለው አመላክቷል፡፡ «የምዕመናን እና የሰንበት /ቤት ወጣቶችን ውክልናም በተመለከተ ምዕመናን እና ወጣቶቹ በቅጡ ሊመክሩበት ይገባል። የምንመርጠው ፓትርያርክ እንጂ የቀበሌ ሊቀ መንበር አይደለም። ከየአህጉረ ስብከቱ የሚወከሉ ሰዎች በቢሮ ለቢሮ የደብዳቤ ልውውጥ እና በድርጅታዊ አሠራር የሚላኩ መሆን የለባቸውም። ለዚህም በየ አብያተ ክርስቲያናቱ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ኃላፊነት አለባቸው።» ሲል የገለጸው በሰንበት ትምህርት ቤቶች ስም ለራሱ ስፍራ ለማመቻቸት የተናገረው እንደሆነ ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ስም የራሱን ሰዎች አደራጅቶ ቤተክርስቲያንን ሲበጠብጥ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ስለዚህ አሁን መንግሥትን በጣልቃ ገብነት እየከሰሰ ራሱ ግን በፈለገው መጠን በፓትርያርኩ ምርጫ ጣልቃ ለመግባትና የራሱን አሻንጉሊት ለማስቀመጥና የቀረነው ትልቅ የቤት ሥራ ለመሥራት የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ ከፍተኛ ቅስቀሳ መጀመሩን ግልጽ እያደረገ መጥቷል፡፡

በቀጣዩ ፓትርያርክ ምርጫ ላይ ማኅበረ ቅዱሳን ጣልቃ ለመግባትና የራሱን ሰው ለማስቀመጥ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውና ከፍተኛ ትግል እያደረገ እንደሆነ እየታየ ነው፡፡ ስለዚህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ሁሉ ቤተክርስቲያናችን በጨካኙና አባት አዋራጁ ማኅበር እጅ እንዳትወድቅ፣ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያኒቱ የሚበጀውን፣ ለወንጌል መስፋፋት፣ ለቤተክርስቲያንና ለአገር ጥቅም የሚቆም፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለቤተክርስቲያናችን ያስገኙላትን ታላቅ ስምና ዝና መጠበቅና ማስቀጠል የሚችል፣ አባት እንዲያስቀምጥ መጸለይና የድርሻችንን መወጣት ይኖርብናል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅዱስነታቸው ስርአተ ቀብር ሐሙስ ነሐሴ 17/2004 ዓ.ም. ከቀኑ በ6 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ሲኖዶሱ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡      

 

23 comments:

 1. ይገርማል
  ቀበሮ እንደ በግ ለቤተክርስቲያን ተቆርቁሪ መስሎ ሲጮህ
  ይልቅስ ቤተክርስቲያናችንን መጠበቅ ያለብን ከእናንተና እናንተን ከሚመስሉ ነዉ
  አሁንም አይናችሁን ጨፍኑና እናሙኛችሁ ትሉናላችሁ
  በእዉነት ትገርማላችሁ
  እግዚአበሔር ልቦና ይስጣችሁ ምን ይባላል

  ReplyDelete
 2. መጽሐፍ በሰው ጉዳት አትደሰት ነገ ባንተ የሚሆነውን አታውቅምና ይላል፤
  አስመሳይ የዘመናችን ቅዱሳን ግን በሰው ሞትና ጥፋት ሲፈነድቁ ይሰማሉ፤ (ክርስቶስ
  የመጣ የጠፋውን ሊፈልግ የተጎዳውን ሊያድን)የሚለውንም ፊቱስ ይቅርና ጀርባውን
  አላዩትም በመሆኑም የራሳቸውን ዱርሽት በመንበሩ ላይ ለማስቀመጥ ደፋ ቀና ሲሉ
  መንደር ለመንደር ሲንቀዋለሉ ይታያሉ፤ ፈጣሪ ግን የጥበበኞችን ጥበብ ብላሽ እንደሆነ
  ያውቃልና ያሰናክላችዋል፤ እናተ ታችኛውን ወልገድጋዳ መንገድ ይዛችሁ ትባክናላችሁ፤
  እግዜር ባዘጋጀው በላይኛው ጎዳና ግን ሳታስቡት ድንገት ትቀደማላችሁ ትላለች ጥበብ

  ReplyDelete
 3. መጽሐፍ በሰው ጉዳት አትደሰት ነገ ባንተ የሚሆነውን አታውቅምና ይላል፤
  አስመሳይ የዘመናችን ቅዱሳን ግን በሰው ሞትና ጥፋት ሲፈነድቁ ይሰማሉ፤ (ክርስቶስ
  የመጣ የጠፋውን ሊፈልግ የተጎዳውን ሊያድን)የሚለውንም ፊቱስ ይቅርና ጀርባውን
  አላዩትም በመሆኑም የራሳቸውን ዱርሽት በመንበሩ ላይ ለማስቀመጥ ደፋ ቀና ሲሉ
  መንደር ለመንደር ሲንቀዋለሉ ይታያሉ፤ ፈጣሪ ግን የጥበበኞችን ጥበብ ብላሽ እንደሆነ
  ያውቃልና ያሰናክላችዋል፤ እናተ ታችኛውን ወልገድጋዳ መንገድ ይዛችሁ ትባክናላችሁ፤
  እግዜር ባዘጋጀው በላይኛው ጎዳና ግን ሳታስቡት ድንገት ትቀደማላችሁ ትላለች ጥበብ

  ReplyDelete
 4. የማትራባ መናፍቅ:: አንተስ ማንን ለማስመረጥ እየጣርክ ነው:: አጋርህ እጅጋየሁስ ተፅናናች? የውርሱስ ነገር መልክ ያዘላት:: የነ ሰረቀስ ነገር? እንዴት ሆነብህ? በቃ ያሰባችሁት ሳይሳካ ቀረ??? ፈረሰ ያላችሁት ድርጅት የተኩላን መንጋ ከቤቱ የሚጠርግን እረኛ ሊመድብ ነው?? ፈረሰ ያልከው? ስለመፍረሱ ስንት ያላዘንክበት??

  ReplyDelete
 5. kedada hulu. before abune paulos is burried you accuse MK. shut your blog instead of accusing innocents.

  ReplyDelete
 6. MK still going on strength. Ay Tehadisowoch gud felabachihu.

  ReplyDelete
 7. ማህበረ ቅዱሳን ካለበትማ መልካም ሥራ ይሰራ ልማለት ነው መልካም ዜና ነው ያሰማችሁን።

  ReplyDelete
 8. Ye abatachinin nefs yimar ay abadabilosoch min tihonu engidh, beqa balebetu hulun aderege madiregim siltan alew. Manim be manim mot des aylewm hulachim wodziya enhedalenina,enante gin mk endetedesach adirgachihu enante ende azagn honachihu qerebachihu,b/c kezih behwala enante endefelegachihu bebetekirstiyan dankira merget,genzebuan meqramet aqome yihm ende egir esat fejachihu gena yaqatilachihual,enante eko ariyos nachihu,hodamoch bewongel sim yemitinegidu,egzeabher libona yistachihuna wode betu yagibachihu. Ergitegna negn kehone qen behual mk abatachinin gedelachew endemitilu ,maferiyawoch

  ReplyDelete
 9. You said አባት አዋራጁ ማኅበር እጅ እንዳትወድቅ, You are the funniest people I ever know

  ReplyDelete
 10. Endenante abat yemiyaward ale ende? Tewegzachihuwal mn kerachu achebchabiwoch

  ReplyDelete
 11. አይ አባ ሰላማዎች ከንቱ ከንቱ የከንቱ ከንቱ የሆናችሁ ቤተ ክርስቲያንን ለማ ፍረስ የተነሳችሁ መሆናችሁን ይብልጥ አሁን አወቅሁ። በጥላቻ መንፍስ የተሞላችሁ ናችሁ አሁን ይህዘገባ ምን ለማለት ተፈልጎ ነው ርጉማን

  ReplyDelete
 12. TEZEKER MAHIBERINE ZAKIDEMIKE FETIREAugust 20, 2012 at 3:17 AM

  what is the real difference b/n u & those who stand against biblical movements in our church as for me u both r the same with different playing cloth (MALIYA) may God have mercy on all of those who couldn't understand the real agenda of the Almighty God

  ReplyDelete
 13. Mahebre kiusan Be Hager west becha ayedelem be wechim hager ye abatachen memot betm yasdesetew yimeselal yenesu kerstena yihen yahel new yemigeremew abatachen gena afer west saygebu yemerchaw negr asasebot be ejeselam blogu lay chneketun mwejun ketelual mengest talika endayegeba min malet new asamero new migeba ende mk balege abat awaraj yebtekresteyan lijochn asadaj endichmalek mtngest zim belo yemeyye meselachew abaselamawoch enanetem bertu ensu yemyaderguten be betekihent bekul teketatelu Egziabher yerdachehu amen ke Germen frankfurt Askale mareyam

  ReplyDelete
  Replies
  1. when will you write with out complaining Mahibere Kidusa. Look your complain never related to the title. please write only what you title need to say. it seems simple blind resentment. any ways a deed says more than a word. please open and look what MK done. all r for the sake of the church. none of them appointed by some one who have ...... on our church and country. please at least try to a source of information than disseminating a harsh hate

   Delete
 14. kkkk yeayt miskrua dinbit.

  ReplyDelete
 15. Leboch Nachu "aba selama".
  Ahun min yibalal derso azagn mehon? Leboch

  ReplyDelete
 16. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚመራ አቃቤ መንበር ሰየመ፡፡ በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቃቤ መንበር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትርያርክ እስኪመርጥ ድረስ ቤተ ክርስቲያንን በበላይነት ይመራሉ

  ReplyDelete
 17. Abune Fanuel is the best candidate to succoer of Abune paulos. Mk may not agreed. Bc mk not part of Eotc who care about them. They can be elect o we n pateriarc Dr. ato mesfene, who was fired from the church.

  ReplyDelete
 18. MK please stop disturbing our church. This is not your issue, it is the issue of 40000000 ppl. You are nothing but building your own image which is invalid for us. So pls pls do not disturb us.

  ReplyDelete
 19. ማህበረ ቅዱሳን ግዜ መግዛት ፈልጎአል ማለት ነው!! ‹‹የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ ‹የገበያ ግርግር ….› ይሆናል›› በሚል ባወጣው ጽሑፍ ያሰፈረውን አንድ አንቀጽ ብንመለከት፤ ‹‹በዚህ መሠረት ባለፉት ዓመታት በተለያየ ምክንያት በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ የተሾሙ፣ በምግባራቸውም በእምነታቸውም አስነቃፊነት በተለያዩ ጊዜያት የምዕመናን ቅሬታ፣ ዕንባና ሐዘን የወረደባቸው ሰዎች ዞረው “ፓትርያርክ መራጮች” ሆነው ይመጣሉ ማለት ነው። በርግጥ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ “የምርጫው አፈጻጸም ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይሆናል” ቢልም አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ውጤቱ ሳይታለም የተፈታ ነው›› ይላል፡፡ ይህ በጣም አስገራሚ ጉዳይ ነው!! በዚህ ጽሑፍ ማቅ ተጨማሪ ግዜ የሚያስፈልገው ለምን እንደሆነ ግልጽ ጥቆማ ሰጥቶአል፡፡ የዘረዘራቸው የቤተክርስቲያን አባቶች እስካሉ ድረስ እሱ የሚፈልገው እንደማይሳካ ስለተጠራጠረ ግዜ ስጡኝና ላጽዳቸው፣ ካሉበት ፈልጌ ልጠራርጋቸው፤ የተለያየ ስም እየለጠፍኩ ከስፍራቸው ላባርራቸው ነው መልእክቱ፡፡ ከዚያ በኋላ ቤተክርስቲያን እሱ በሚለው ብቻ የምትፈስስ ጅረት ትሆናለች ነው፡፡

  ውድ ወገኖቼ፤ የምለውን ካላመናችሁ ማህበሩ ቀጥሎ የጻፈውን ተመልከቱ፤ ‹‹የምዕመናን እና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ውክልናም በተመለከተ ምዕመናን እና ወጣቶቹ በቅጡ ሊመክሩበት ይገባል። የምንመርጠው ፓትርያርክ እንጂ የቀበሌ ሊቀ መንበር አይደለም። ከየአህጉረ ስብከቱ የሚወከሉ ሰዎች በቢሮ ለቢሮ የደብዳቤ ልውውጥ እና በድርጅታዊ አሠራር የሚላኩ መሆን የለባቸውም። ለዚህም በየአብያተ ክርስቲያናቱ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ኃላፊነት አለባቸው።›› የአንቻኮል ጥሪው አላማ ተረጋግተን የሰከነ ምርጫ እናድርግ ሳይሆን የሚጠረጉ ሰዎች ተጠራርገው እሰኪወጡ ግዜ እንግዛ ነው!! በዚህ አጋጣሚ በየቦታው ባሉ ካህናት አባቶችና አገልጋዮች ላይ ሊቀሰቀስ የሚችል አድማና የይውጡልን ዘመቻ እንደሚኖር መጠርጠር ደግ ነው፡፡ ማቅ እሱ የሚፈልገው ካልተዘፈነ፤ እሱ የሚመርጠው ካልተሾመ ለአገራችንም ሆነ ለቤተክርስቲያናችን አይተኛም ማለት ነው! ለመኾኑ አንድ ተራ ማህበር ታላቂቱንና ታሪካዊቱን ቤተክርስቲያን እንዲህ አድርጎ እንዲፈነጭባት የተፈቀደው ለምንድን ነው? ሰውስ የለም ወይ? መንግሥትም ሆነ በኃላፊነት ላይ ያሉ አባቶች ሁኔታውን በቅጡ ተረድተው በአግባቡ ካልያዙት ይህ የማዘናጊያ ጥሪ አላማው በጣም ግልጽ ነው!!

  ReplyDelete
 20. Who is MK after all to playback deciceve role in churh affairs. Who give them such esteem, for those who do not know about this business and secular group they seemed to be church scholars. That is extremely baseless. MK is a gtroup of secularly 'educated' devilish group. Their life and religious knowledge is too shallow, superficial and pretentious christiran. So don't give any credentiality. The've nothing to do with such precious and sacred issue.

  ReplyDelete
 21. Mk and his flowers are inward Heretic of this age.
  and they are outward superficial holy people.
  Be on your guard against false prophets .ማቴ 7. 15-16
  በዚህ ዘመን ሳይሆኑ ነን ባዮች በያቅጣጫው እየበረከቱ ሄደዋልና ጥንቃቄ ሳያስፈልግ አልቀረም፤
  ራዕ ዮሓ. 3. 9-10

  ReplyDelete
  Replies
  1. we emz halefu ele pawlos emne pafu meles wepawlos hibure teshemu hibure halefu.abet

   Delete