Friday, August 31, 2012

በአገር ውስጥ በውጪም ያሉ አባቶችለቤተክርስቲያን አንድነት ሊሠሩ ይገባል

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ካንቀላፉ በኋላ ሲኖዶሱ ትልልቅ ስራዎች ከፊቱ ተደቅነዋል፡፡ አቡነ ጳውሎስ የተሸከሟቸውን ትልልቅ ሸክሞች የመሸከም ዕጣ ፈንታም በሲኖዶሱ ላይ ወድቋል፡፡ ከእነዚህም ዋናዎቹ አዲስ ፓትርያርክ መሰየምና በውጪ ከሚገኘው ሲኖዶስ ጋር በመነጋገር ቤተክርስቲያኗ አንድ የምትሆንበትን ሥራ መስራት ነው፡፡

በዚህ ቤተክርስቲያኗ ፓትርያርኳን በሞት ባጣችበትና በዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ እየተመራች ባለችበት ወቅት ቤተክርስቲያን አንድ እንድትሆን የሚጠይቁ ወገኖች አሉ፡፡ በቅርቡ በብሎጋችን ላይ መግለጫዎቻቸውን ያወጡ በደቡብ አፍሪካ «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ቤሪያ ሰላም ዝክረ አበው የሰላምና አንድነት ማኅበር» እንዲሁም በሰሜን አሜሪካ በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው «የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ /ቤት» ቤተክርስቲያኒቱን አንድ ለማድረግ ጊዜው አሁን መሆኑንና የአንድነቱ ጉዳይ  እልባት ሳያገኝ ሌላ ፓትርያርክ የመሾሙ ጉዳይ እንዲታሰብበት የሚጠቁሙ መግለጫዎችን አውጥተዋል፡፡
 
የቤተክህነቱን ፖለቲካ ስንከታተል የቆየን ሁሉ እንደምናስታውሰው ለሁለት የተከፈሉትንና እርስ በእርሳቸው የተወጋገዙትን ሲኖዶሶች ለማስታረቅ የተጀመረ የእርቅ ሂደት አለ፡፡ አንዳንድ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ሲቀናቀኑ የነበሩ ጳጳሳት ለዕርቁ ሂደት እርሳቸው ዕንቅፋት እንደሆኑ ሲናገሩ ነበር፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎችም ይህንኑ እያራገቡ ቅዱስነታቸውን ሲኮንኑ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ቅዱስነታቸው አሁን የሉም፡፡ አሁንስ የቤተክርስቲያንን አንድነት ላለማምጣት ሰበቡ ማን ይሆን?

የማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ያሉት ነገር የለም፡፡ ለነገሩ ማኅበረ ቅዱሳንም በውጭ ባለውና በአገር ቤቱ ሲኖዶስ መካከል አንድነት እንዲመጣ እንደማይፈልግ በአሁኑ ወቅት የማኅበሩ ብሎጎችም ሆኑ እንደዳንኤል ክብረት ባሉ የማኅበሩ ሰዎች ብሎጎች ላይ ከሚወጡ ጽሁፎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ዳንኤል ክብረት የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ዜና ዕረፍት ተከትሎ መወሰድ አለባቸው ያላቸውን «ከፊታችን ያለው መንገድ» በሚል ርእስ በብሎጉ ላይ በሰቀለው ጽሑፍ ውስጥ፣ «በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ቀኖናና ትውፊት መሠረት አንድ ፓትርያርክ ሲያርፉ የሚከናወኑ ሥርዓቶች አሉ፡፡ እነዚህም በስድስት ይከፈላሉ፡፡»
1.   ሁኔታውን ማወጅ
2.   የኀዘን ጊዜ መወሰን
3.   ዐቃቤ መንበር መሠየም
4.   የቀብሩን ሥነ ሥርዓት ማከናወን
5.   የምርጫውን ሂደት ማከናወን
6.   መምረጥ
በሚሉ ነጥቦች ሥር ያቀረበው ሐተታ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ለሁለት እንደተከፈሉ እንዲቀጥሉ እንጂ ወደአንድነት እንዲመጡ የተወሳ ሐሳብ የለም፡፡ በተለይ በተራ ቁጥር 5 እና 6 ላይ የተጠቀሱት የቤተክርስቲያኗ አባቶች እንደተከፋፈሉ እንዲቀጥሉ የዳንኤልና የመሰሎቹ ሐሳብ መሆኑን እንረዳለን፡፡ ዳንኤል ያጎረሳቸውን የሚውጡ አድናቂዎቹ ሀሳቡን እንዳለ ተቀብለው ምስጋና ሲያዥጎደጉዱለት አንዳንድ አላምጠው የሚውጡ አስተያየት ሰጪዎች ግን ዳንኤል በዚህ ወቅት ሊታለፍ የማይገባውን ስለቤተክርስቲያን አንድነት መጠቀስ ያለበትን ነጥብ ባለመጥቀሱ ተቃውመው አስታያየት ሰጥተውታል፡፡

ለምሳሌ (AnonymousAugust 17, 2012 8:17 AM) «i am really sorry to read this from u Dn Daniel, i used to respect u and taught u r one of the most wise man in our church ,but now u did very unforgetabel mistake.You were expected to talk about bringing the two side fathers together, but u just start talking about electing new patriaric...u should be sorry for what u write...i used to like u ...
but now...»
የሚለው ይጠቀሳል፡፡
አዎን እነዳንኤል ቀጣዩን ፓትርያርክ ስለመምረጥ እንጂ በውጪ እና በውስጥ ያሉት አባቶች አንድ ስለሚሆኑበት ነገር ሐሳብ እንኳ የላቸውም፡፡ ይህ ለምን ሆነ? ቢባል ብዙ ምክንያቶች ሊዘረዘሩ ይችላሉ፡፡ አንዱ ምክንያት ግን በውጪ ያሉ አባቶች ብዙዎቹ ወንጌልን ስለሚሰብኩና ከማኅበሩ ጋር በአመለካከት ስለሚለዩ ነው፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ ወንጌል በመስበክ የሚታወቁትን የወንጌል ገበሬ አባ ወልደ ትንሣኤን በየመጽሔቱ ተሐድሶ ናቸው ሲል ይወነጅላቸው የነበረው ማኅበር፣ በአባ መልከ ጼዴቅ ደካማ ጎን በመግባትና እርሳቸውን በማሳሳት አባ ወልደትንሣኤ እንዲታሰሩ እስከማስደረግ የደረሰ ድራማ መስራቱን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ በአባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት ተወግዶ አባቶች ወደአንድነት ቢመጡ ማኅበረ ቅዱሳን ኪሳራ እንደሚደርስበት ያውቃል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ ዝምታን መርጧል፡፡

ከቅዱስነታቸው የቀብር ሥነሥርዓት በኋላ በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በውጪ ካሉት አባቶች ጋር የተጀመረው የእርቁ ጉዳይ ተነሥቶ ውይይት መደረጉን አውደ ምሕረት ብሎግ ዘግቦ ነበር፡፡ ከዘገባው ለመረዳት እንደሚቻለው ስብሰባው በእርቁ ጉዳይ ላይ የተነጋገረው ጉዳዩ ወቅታዊ ሆኖ ስላገኘው ነው ማለት ያስቸግራል፡፡ ምናልባትም ለስብሰባው ምክንያቱ፣ ወይም በስብሰባው ላይ አጀንዳው ለመነሳቱ ምክንያቱ በውጪ ከሚገኙት አባቶች መካከል ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ተናገሩ የተባለው ነገር ሊሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ አለ፡፡ በእርግጥ የአቡነ መልከጼዴቅ ንግግር በተጀመረው የእርቅ ሂደት ላይ ጥላውን ሊያጠላ እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ ሆኖም ለእውነተኛ እርቅ የቆሙ አባቶች ነገሩን ማብረድና ጠላትን ማሳፈር አለባቸው እንጂ ለመልስ ምት በመዘጋጀት ችግሩን ማባባስ የለባቸውም፡፡ ሌላ ፓትርያርክ ለመሾም ከመጣደፋቸው በፊት ይህን ጉዳይ በጥሞናና በአርቆ አስተዋይነት መመልከት አለባቸው፡፡ በአቡነ መልከጼዴቅም በኩል ለእርቁ መሳካት ሲሉ ስለተናገሩት ቃል የተናገሩበትን ምክንያት ቢያብራሩ ጉዳዩን ለማለሳለስ ጠቃሚ ነው፡፡ አሊያ አባቶች እንደ ተለያዩ ሊቀጥሉ ነው፡፡ ስለዚህ ለቤተክርስቲያኗ አንድነትና ሰላም የሚያስቡ ወገኖች ሁሉ የተቻላቸውን ሊያደርጉ በሚገባበት ወቅት ላይ ያለን ይመስለናል፡፡

22 comments:

 1. Mk now use criminal immigerant that provided mis information from kenya to attack and killing church fathet and servant here in USA. Some false monk that paid by mk to arranged and givimg information to killed paulos his name is aba zelebanose play key role to leading of this crime. Zelebanose was arested drug and prostute case last Monday. Death to mk.

  ReplyDelete
 2. Why do u write ur idea?why do u refer normal blog as an evidence? Always u talk about MK? Is there any Agenda.......??????????

  ReplyDelete
 3. መናፍቁ ልዮነቱ 20 ዓመት ሆነው እኮ። ድርድሩ ፖትርያርኩ ኖረው እንደተደረገው አዲስ ተሹሞም ማድረግ ይቻላል። ፕትርክና አንተ የማትፈልገው ሲኖዶስ የሚሰጠውና ካልተገባህ የሚያነሳው እንጂ ርስት አይደለም። ስለዚህ ፖትርያርኩ አሁን ሀገራቸው ገብተው በሰላም ገዳማቸው ገብተው የቀራቸውን ዘመን ያደረጉትን በደል እያሰቡ መኖር እንጂ ለ28 ዓመት ቤተክርስቲያን በሁለቱ የደረሰባትን በደል ተጨማሪ አመት እንድትበደል አያስፈልግም። አንተ በመሃል ለምንፍቅናህ እንዲመችህ ነው እንጂ ጥሩ ነገር የለህም። ከእባብ እንቁላል ርግብ አይጠበቅም። ካንተም እንደዛው ነው።

  ReplyDelete
 4. Could you please elaborate on What Abune MelkeTsedeq said recently with regard to reconcillation or the death of Abune Paulos? He seems to be the one who has a lot of influence on the North American Side.

  ReplyDelete
 5. ABA SELAMAWECH,

  EGZEABEHER KENANTE GAR YEHUN. ENDEZIHE WENET YEMENGREN SELELELE KETELUBET. MAHEBERE AGANEINET ENDHONE SERE BETEKRISTIAN YEHONE NEFSE GEDAY SELE ERKE MEN YAWEKAL. KEDUSE ABATACHEN GENA HOSPITAL SIHEDU MOTU BELO YAWERA SEYTAN YENOR MESLOTAL.

  ReplyDelete
 6. Great, E/G yibarkachihu tiru milketa new!!!

  ReplyDelete
 7. አባ ሰላማዎች በ እውነት እውነታዊ ጽሁፍ እና መልካም አስተያየት ነው!

  እርቀ ሰላሙ ተፈጽሞ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ወደ መንበራቸው መመለስ አለባቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት የሚያሳስበን ከሆነ::

  ReplyDelete
 8. ማቅ የተደበቀው የእግዚአብሔር ጥበብ ልዩ ስለሆነ ጨልሞበታል። ነገር ግን ክፉ መንፈስ ያደረበት በመሆኑ ቅዱስ እግዚአብሔር መንገድ ምስጥሩ እዳያገኝ ቀዳዳው በቅዱሳን መላዕክት ዘግቶበታል። የማቅ ጳጳሳት ከእርሱ እየሸሹ ስለሆነ ግራ ገብቶታል። ከበሮ ስያዩት ያምራል ስይዙት ግን ይከብዳል እንደተባለው የማቅ ደጋፊ ጳጳሳት ሀላፊነቱን ስይዙት እጅግ ግራ ገብቶአቸዋል። ድሮ ፉከራው በሌላ ሰው ሸክም ነብረና ። ተራው ደረሳቸው። ምን ይውጣቸው? እንዴት አድርገው ከእንደህ ሀይለኛ እሳት ቦታ ይውጡ? ጉዱ ገና ነው ኦርቶዶክሶች አትቸኩሉ እግዚአብሔር ስለ ማቅና ተከታዮቹ ጳጳሳት ተዓምር ድንቅ ስራውን ያሳየናል ።ቸር ያሰማን

  ReplyDelete
 9. read the response posted on "ahati tewahedo" blog. you will be satisfied by that.

  ReplyDelete
 10. yegna lebetekirstian andinet asabiwoch, lemin eskahun bezih guday lay zim bilachihu norachihu. Achiberbariwoch, now the time is up, shut up ur mouth

  ReplyDelete
 11. አዎን ልክ ናችሁ ለእናንተም አሜሪካ ያሉት ቢመጡላችሁ ይሻላል:: በፓትርያርኩ መሞት ቀኑ ስለጨለመባችሁ::

  ReplyDelete
 12. u abaselama r an ass fuck you!!!!! you are devils that are the personification of evil and the enemy of God and humankind.u try to expand protestant in our country. we know ur mission.ur supporter paul died. what would say now? what is the difference between you and Judas Iscariot? b/c Thirty pieces of silver was the price for which he betrayed Jesus

  ReplyDelete
 13. False criminal monk zelebanose formerly aba that who sleeping with men and women working with mk to promote as arc bishop in October to gain supportance in the holy synod for mk game. You can immagine how mk puzled and hurt our anncient church to demolish using balager criminal monk. According to Meregeta yohanse this monk zelebanose criticaly ill which is suffering from HIV Aids.

  ReplyDelete
 14. you are tehadiso menafik. you don't have any moral value to say anything about the church.

  ReplyDelete
 15. ጎበዝ እንዴት ነገሩ? ስለምን እርቅ ነው እምታወሩ? እነ አባ ሃብቴ እርቅ የሚፈልጉ ቢሆን ንሮ አባ ወልደስንበትን ወደ አስመራ ልከው እዛ ያሉትን ታጣቂዎች "ውረድ በለው ግፋ በለው!" ያስብሉ ነበር? በኢሳት የወጣውን ዜና አይታችሁታል።http://www.ethsat.com/2012/08/27/abune-mekarios-meets-opposition-movements-based-in-eritrea/ እርቅ ስለተመኙት ብቻ አይመጣም። ቅን ልቦና ያስፈልጋል።አባ መልከጼዴቅ ፖለቲካውን ለሚመለከታቸው ትተው የሚዛቅ ዶላር ባላቸው መናፍቃንና አክራሪ ሙስሊሞች ከሁለት አቅጣጫ እየተመታች ያለችውን ድሃ ቤተ ክርስቲያን ሊደርሱላት ይገባል። ፓትሪያርክ በፓትሪያርክ ላይ የሚባለው አጫቃጫቂ ነገር አሁን በቦታው የለም። አቡነ ጳውሎስ ቀድመውን ሄደዋል እኛም እንከተላቸዋለን። የማይሞቱ ሁለት ነገሮችን እናስቀድም-ሃይማኖታችንና አገራችን። ሕርያቆስ ነኝ

  ReplyDelete

 16. ፓትርያርክ ጳውሎስና ያስፈጇቸው ሊቃነ ጳጳሳት
  http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/4180

  ReplyDelete
 17. Aba selamawoch Ewunet Le Andinet Yemitsru nachihu lela le la Alama Yelachihum?Bizu Bizu Asinebibachihunal swun Minalibat Bitatalilut Hilenachihun Egzeabehern mataleli tichilu Yihon?

  ReplyDelete
 18. ሃሳባችሁ በጥቅሉ ለተመለከተው መልካም ይመስላል ፡፡ ነገር ግን ብዙ ችግሮችንና መፍትሄአቸውን ለማግኘት ቅኝት ያደረገ አይደለም ፡፡
  1. አቡነ መርቆርዮስ ከአገሪቱና ከቤተ ክርስቲያን ኮብልለው የሄዱት ገዳም አይደለም ፡፡ የፖለቲካ ስደተኛ ተብለው ነው በውጭ አገር የሚኖሩት ፡፡ በስደት ባሉበት ደግሞ በስማቸውም ይሁን በአካላቸው ከመንግሥት ተቃዋሚዎች ጐራ ጋር የተደጋገመ የአንድነት መግለጫ አላቸው ፡፡ በቅርቡ እንኳን ከአርበኞች ግንባር ጋር የሚል ነገር በስማቸው ተነቧል ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያለፈውን ሥራቸውን ሁሉ /ከደርግ ሥርዓት ጋር በተያያዘ የተፈጸመውን / ይቅር ብላ ብትቀበላቸው ፣ በስደት የሄዱበትን የፖለቲካ እርምጃ እንደምን መጠቅለል ይቻላቸውና አሁን ካለው መንግሥት ጋር ስምምነት ይፈጥራሉ ? ወይስ በመጨረሻ ዕድሜ ላይ ስለ ምድራዊ ጣጣ ሲባል የማያምኑበትን ጉዳይ መቀበል ይገባቸዋል ?
  2. ቀደም አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሥልጣን ሲመጡ የቤተ ክርስቲያንን ህገ ደንብ በጠበቀ መልኩ እንዳልነበረ በብዙዎች እየተነገረ ያለ ጉዳይ ነው ፡፡ ዋነኛ የመከራከሪያው ነጥብም የቀደሙትን ፖትርያርክ ሞት አላወጁም የሚል ነው ፤ ከዚህም ጋር በተያያዘ የግብፅ ቤተ ክርስቲያን እንኳን እውቅና አልሰጠቻቸውም ፡፡ ታድያ አሁን ይመለሱ ሲባል እንደ አዲስ ተሽዋሚ ተቆጥሮ ወይስ በምን መግለጫ የቀደመውን ስህተት ያስተካክሉታል ፡፡ ጥያቄዬ በሰውኛ /ምድራዊ/ ቋንቋ ሳይሆን በመንፈሳዊ ሚዛን ስንመለከተው ለማለት ነው ፡፡

  ReplyDelete
 19. durose ke- balege seytan mahber aball mine yetebeqalna newu? mk woro bella asemesaye krestiyan newu. Amlakachne gene ye-eyandandachineene lebe yawqalna, ms getan matalele aychalem, yalefew yibkachihu ahune Egziabharem tegistu yibqkaw, mote le-telatachin le-mahibere aganente.

  ReplyDelete
 20. አባ መርቆሬዎስ ፈቃድዎት ቢሆን ወደ ኢትዮጵያ ይግቡና ቅዱስ ሴኖዶስ ያወጀውን ሱባኤ አንዱ ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ። እዚያም በመቆየት ወደ መንበሩን እንዲመለሱ የሚጸልዩትን በጸሎት ያበረታቱ።

  ReplyDelete
 21. ኧረ ተዉ ጎበዝ አንገበዝ!ዕርቀ ሰላም አምጣ ብሎ ማምጣት ወደሚቻለው በማንጋጠጥ ፈንታ ዕገሌ
  ዘረኛ ነው በሥልጣን ወንበር ላይ ሆኖ ዘመዶቹን ብቻ ያሰባስባል እገሌ ሸረኛ ነው በስደት ሀገር ሆኖ
  ሸር ይሠራል የማለት ትርጉሙ ምን ይባላል? ኢትግበራ ለእኪት ወኢይረክበከ እኩይ(If you do not wrong no wrong will ever come to you)ክፉ አትሥራ ክፉ አያገኝህም
  ይላልና ይህ ሁሉ ጣጣ የሚመጣ በምድር ላይ ደግ ሰውና ቅን አስተሳሰብ የውሀ ሽታ በመሆኑ ነው
  ቢሆን የተሻለ ባይሆንም ወደዚያው ተጋ ያለ ጨርሶ ግን የባሰ እንዳይተካ ሊታሰብ ይገባል፤ሲባልም
  ሽማግሎቹ ከመሮጥ ማንጋጥጥ እንደሚሉት ልብን ለፈጣሪ መስጠትና ለዕርቀ ሰላም መትጋት ይገባናል፤

  ReplyDelete