Tuesday, August 21, 2012

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስና ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ምን እንማራለን?

በዚያን ጊዜም ሰዎች መጥተው ጲላጦስ ደማቸውን ከመሥዋዕታቸው ጋር ስላደባለቀው ስለ ገሊላ ሰዎች አወሩለት።
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ እነዚህ የገሊላ ሰዎች ይህ ስለ ደረሰባቸው ከገሊላ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ኃጢአተኞች የሆኑ ይመስሉአችኋልን?
እላችኋለሁ፥ አይደለም፤ ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ።
ወይስ በሰሌሆም ግንቡ የወደቀባቸውና የገደላቸው እነዚያ አሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሁሉ ይልቅ በደለኞች ይመስሉአችኋልን? አይደለም፥ እላችኋለሁ፤
ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።
(ሉቃ. 13፥1-5)
2004 ዓ.ም. አገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ታላላቅ ሰዎችን በሞት የተነጠቀችበት ዓመት ነው፡፡ የቤተክርስቲያናችንና የአገራችን መሪዎች ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እና የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንዲህ በአንድነት በሞት የተጠሩበት አጋጣሚም ያለ አይመስለንም፡፡ የመሪዎቻችን በአንድ ሰሞን በሞት መጠራትና የነገሮቹ ግጥምጥሞሾች በኢትዮጵያውያን ላይ ልዩ ልዩ ስሜት ፈጥሯል፡፡ ሁለቱንም መሪዎች የሚጠሏቸው ብዙዎቹ ሳይቀሩ አዝነዋል፡፡ ሌሎቹ የሚጠሏቸው ደግሞ ጸሎታቸው እንደተሰማ ቆጥረው ደስ ብሏቸው ይሆናል፡፡ እንዲህ የምንለው አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ በአቡነ ጳውሎስ ላይ ሲያሟርቱ የነበሩና የዘንድሮው በዓለ ሲመታቸው የመጨረሻቸው ነው ብለው የጻፉ ብሎጎች ስለነበሩ ነው፡፡ መለስ ዜናዊ ታመው በሕክምና ላይ እያሉ ሞታቸውን ብቻ ሲያቀነቅኑ የነበሩ ሚዲያዎችም ስለነበሩ ነው፡፡

እልፍ ሲልም ለሁለቱም ሞት የእነርሱን ጸሎት በምክንያትነት የሚያቀርቡ ግብዞችም አልጠፉም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዋልድባ ገዳም መሬት ላይ ለስኳር ፕሮጀክት ቆርሰው ስለወሰዱ፣ አቡነ ጳውሎስም ዝም ስላሉና ስላላወገዙ የባሕታውያኑ ጸሎት ነው ለዚህ ያበቃቸው፤ በእስልምናው አካባቢ ደግሞ አክራሪ እስልምናን አስመልከተው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በፓርላማ ላይ ስለተናገሩ የእኛ ዱኣ ነው ለዚህ ያበቃቸው እየተባለ ሲወራም ሰምተናል፡፡ ይህ ሁሉ ግን የተሳሳተ ፍርድ ነው፡፡ ዛሬ ሕያው የሆነና የእለተ ሞቱን ተራ የሚጠብቅ ማቹ ሰው እንዲህ የሚል ከሆነ እጅግ ተሳስቷል፡፡ 

እንዲህ ብለው የፈረዱ ሰዎች ስለራሳቸው የተሳሳተ ግምት ያላቸው፣ ራሳቸውን ጻድቅ ሌላውን ኃጢአተኛ አድርገው የሚመለከቱ ግብዞች እንደሆኑ የእግዚአብሔር ቃል ይመሰክርባቸዋል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ስለገሊላ ሰዎች አሟሟት ለኢየሱስ ያወሩለት ሰዎች የተሰጣቸው ምላሽ እንዲህ የሚል ነበር፡፡ «እነዚህ የገሊላ ሰዎች ይህ ስለ ደረሰባቸው ከገሊላ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ኃጢአተኞች የሆኑ ይመስሉአችኋልን? እላችኋለሁ፥ አይደለም፤ ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ። ወይስ በሰሌሆም ግንቡ የወደቀባቸውና የገደላቸው እነዚያ አሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ከሚኖሩት ሁሉ ይልቅ በደለኞች ይመስሉአችኋልን? አይደለም፥ እላችኋለሁ፤ ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።»

እነዚህ የቤተ ክርስቲያናችንና የአገራችን መሪዎች ትናንት እንደእኛ በሕይወተ ስጋ የነበሩ፣ ለቤተ ክርስቲያናቸውና ለአገራቸው ብዙ ራእይና እቅድ የነበራቸው፣ እንደእኛ እንኖራለን ብለው የሚያስቡ፣ በአመራር ላይ ሳሉ ብርቱም ደካማም ጎን፣ የሚመሰገኑበትም የሚወቀሱበትም ነገር ያላቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ ዛሬ ግን ከመካከላችን በሞት ተለይተዋል፡፡ እነርሱ ሞተው እኛ በሕይወት የቀረነው ግን እነርሱ ከእኛ የተለዩ ኃጢአተኞች ሆነው፣ እኛ ደግሞ ከእነርሱ የተሻልን ሆነን አይደለም፡፡ ይህን ድንገተኛ ጥሪ አስበን ንስሃ እንድንገባ ነው፡፡ አሊያ እኛም እንደእነርሱ መጠራታችን አይቀርም፡፡ ስለዚህ በእነርሱ ላይ መፍረድ ትተን ስለራሳችን ልናለቅስ ይገባል፡፡ በሞታቸው ተደስተን የእግዚአብሔርን ሳይሆን የራሳችንን የልብ መሻት ለመፈጸም የምናልም ካለንም እጅግ ተሳስተናል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ቀድመውን ይህን ዓለም በተሰናበቱ ሰዎች ላይ እንዳንፈርድና እኛም ንስሓ እንድንገባ ይመክረናልና፡፡

ቤተ መንግሥቱ መሪውን በክብር እየሸኘና ወደሚቀጥለው የሕይወት ምዕራፍ ለመሸጋገር እንደወሰነ እያደረገ ካለው መረዳት ይቻላል፡፡ ዛሬ መላው ሀገሪቱ ማለት ይቻላል በሐዘን ድባብ ተውጣ ነው የዋለችው፡፡ የመለስ ዜናዊ ሞት ብዙዎችን አስደንግጧል፡፡ ብዙዎችን መሪር ሐዘን ላይ ጥሏል፡፡ አስከሬናቸውን ለመቀበል በብዙ ሺህዎች የሚቆጠር ሕዝቡ የወጣው ቀን ላይ ነው፡፡ «እንወድሃለን እናከብርሃለን» «ሐዘናችን ትልቅ ነው» የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮችና የመለስን ፎቶዎች ይዞ እስከ ምሽት ድረስ ሲጠባበቅ ቆይቷል፡፡ እስከ እኩለ ሌሊትም ድረስ በላዩ ላይ እየወረደ የነበረውን ዝናብ ከምንም ሳይቆጥር  ለመሪው ያለውን ፍቅርና አክብሮት በሀዘንና በልቅሶ ሲገልጽ አምሽቷል፡፡ 4 ሰዓት ሊሆን ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አስከሬን የያዘው አውሮፕላን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰ ሲሆን፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የመለስ ቤተሰቦች በልቅሶና በዋይታ አስከሬኑን ተቀብለዋል፡፡ አስከሬኑም በከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የፖሊስ ማርሽ ታጅቦ ነው ወደ ቤተመንግስት ያመራው፡፡ ወጣቶች «ጀግና አይሞትም» እያሉ ሆታ እያሰሙ ለመለስ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር ሲገልጹ ነበር፡፡ የአቀባበል ሥርአቱ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የዘለቀ ሲሆን ከቦሌ እስከ ቤተመንግስት ድረስ በተዘጋጀው የአቀባበል ስርአት በየመንገዱ ዳር የተሰበሰበው በብዙ ሺህ የሚቆጠረው ሕዝብ ወንዱ ሴቱ ህጻን አዛውንቱ ጧፍ አብርቶ በጥልቅ ሀዘን፣ በልቅሶና በዋይታ ነበር የመሪውን አስከሬን የተቀበለው፡፡ በአጠቃላይ ሕዝቡ ለመለስ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ያሳየበት ዕለት ነው ማለት ይቻላል፡፡

አሳሳቢው የቤተክህነቱ ጉዳይ ይመስላል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ላይ አድመው የነበሩትና በእርሳቸው ላይ የነበራቸው ተቃውሞ ያፋቀራቸው ጳጳሳት አሁን አንድ ይሆኑ ወይ? የሚለው አጠያያቂ ሆኗል፡፡ ሲኖዶሱን እየመራው ያለው የሥጋና የደም ሀሳብ እንጂ በስሙ የሚነገድበት መንፈስ ቅዱስ አለመሆኑ ግልጽ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ጥቂቶች ፍላጎታቸውን ለማሳካት በየጳጳሳቱ ቤት እየዞሩና የሎቢ ስራ ሲሰሩ አምሽተው በበነጋው  ሲኖዶሱ ይሰየምና ውሳኔ ያሳልፋል፡፡ ለምሳሌ ቅዱስነታቸው እንዳረፉ ዐቃቤ መንበር ከቀብር ስነስርአቱ በኋላ ይሰየማል ሲል ነሐሴ 11 ወስኖ የነበረው ሲኖዶሱ፣ ነሐሴ 14 ቀን ቃሉን አጥፎ ዐቃቤ መንበር ሰይሜአለሁ ሲል መግለጫ ሰጠ፡፡ ቀጣዩ ምን ይሆን?

አባቶች ሆይ እባካችሁ ለቤተክርስቲያን አስቡ፤ ኃላፊነታችሁንም ተወጡ፡፡

ለማንኛውም አቡነ ጳውሎስና ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ላይመለሱ ተለይተውናል፡፡ እኛም ነገ መከተላችን አይቀርም፡፡ ስለዚህ እኛም እንደምንሞት እናስብ፡፡ ስለራሳችንም ንስሓ እንግባ፡፡
32 comments:

 1. ለግብዝነቱ ደግሞ አንተንና ወዳጆችህን ማን ይስተካከላል። ግብዝ መናፍቅ። አንተ አይደለህ እንዴ ተሳስታችኋል የኛ የጴንጤ አመለካከት ነው ትክክል እያልክ ስትገበዝ የምትውል። ዛሬማ የቤተክርስቲያናችን መሪ አልክ? ማፈሪያ። ያንተን የጴንጤ ት/ት እንኳን የኛ ቤ/ያን ቀርቶ የሌላኛው ጴንጤ ፖስተር አይቀበልህም። ለዛ አይደል እንደ አሜባ የምትፈለፈሉት?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Kale Hiwot Yasemalen.

   Delete
 2. ewnwet new lerase malkese yisalal.

  ReplyDelete
 3. ነፍስ ሲገድል የነበረ አውሬ ስለሞተ ማዘን አይገባም።አዲስ አበባ ላይ እያለቀሰ ያለው ተቆጭቶ ነው።እንደ ጋዳፊ በጥፊ ሳንልው እንዴት ቀድሞን ሞተ ብሎ ተቆጥቶ ነው የሚያልቀሰው ወጣቱ።ለመለስ ዜናዊ የሚያለቅስ ወጣት ካለ ጅል ነው ማለት ነው።ወጣቱን አይደል እንዴ አደገኛ ቦዜኔ እያለ ሲያርድ የነበረው ? እንዷለም ወጣት አይደለም እንዴ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ? መለስ ዜናዊ እንኳንም የሞተ።አረፍን።ተገላገልን።ከውሸት፤ከዝሪፊያ፤ከነፍስ ግድያ፤ አገራችንን ከሚያዋርዱ ኃይሎች እጅ ተገላገልን።አረፍን።እንኳንም የሞተ።እንኳንም ላይመለስ የሄደ።
  ለሂትለር የሚያዝን ልብ የለንም !!!!!

  ይሄ ወደል ጳጳሳችሁ የራሱ ጉዳይ ነው።ይሄ ሸሌ የሞተው በቢያኔስ ቀን አሉ ደግሞ።በ 8 እውነት ነው እንዴ ? አባ ፈቃደ ስላሴን አስገድሎ ሲያበቃ የቀበር ቦታ እንዳይሰጠው ሲያከላክል የነበረ አይደልምን ? ታዲያ እንዲህ ያለ ሰው ሲሞት እፎይ እንላለን እንጂ ለምን እናዝናለን ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ባለጌ ነህ በዚህ ሂሊናህ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስትል አታፍርም እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ

   Delete
  2. አባ ሰላማዎች አንዳንድ ጊዜ እንዲህ ያለው ጋጠወጥ የሚሠጠውን ኮሜንት ብሎክ ብታደርጉ ጥሩ ነው፡፡ የእናንተንም ማንነት ያሳንሰዋል፡፡ ይሄ እኮ ግልጥ ብልግና ነው፡፡

   Delete
  3. what is this are you mad?

   Delete
  4. I don't think you have any relgion and i can't say any thing.

   Delete
  5. የሚጽፉና የሚናገሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው !! በነሱ ሞት ምክንያት አንተ ደግሞ ኃጢአትን አትሸከምላቸው ፡፡ ሰው ከእንስሳ የሚለየው ፣ በማይቀረው ሞት ጊዜ ለጠላቱ እንኳን በአግባቡ ስለሚያዝን ነው ፡፡ ለነገሩ እንስሳም ቢሆን የሞተ ቢጤውን ሲያይ ይደነብራል ፤ ስለዚህ መልካም የክርስቲያን ቋንቋን ተናገር ፡፡ ከሰዎች መሃል አንድም ንጹህና ስህተት ያላደረገ ፣ ወደፊትም የማያደርግ አይኖርምና ፣ ቋሚ ቤተሰብን ጨምረን በበደላችን አናሳዝን ፡፡ ስህተት የፈጸሙትን ያህል አሌ የማይባል መልካም ነገርንም ሠርተዋል ፡፡ እንኳን የአንድን አገር ህዝብ የአንድ ቀበሌ ህዝብን እንኳን ሙሉ በሙሉ ፍላጐቱን አርክቶ የሚያስደስት ሊቀ መንበር አይኖርም ፡፡ ሥራው ከባድ ነው ፡፡ እግዚብሔር ሲረዳህ ግን ፣ የሁሉንም ዓይን ይሠውርልህና በትንሽዋም ነገር ፍቅርን ታገኛለህ ፡፡ ሰዎች አልተበደሉም እያልኩ አይደለም ፡፡ ነገር ግን ቂመኛ አንሁን ፤ መጽሐፋችን የኛ በደል ይቅር ይባል ዘንድ የሌሎቹንም ይቅር በሉ ስለሚል ይህን እላለሁ ፡፡ ድርጅታቸው ከአንድ ወገን ፣ በሌላው ደግሞ ህዝብ እያነጣጠረ ያስቸግራቸዋል ፡፡ ይህን በትንሽ ቢሮ አስተዳዳሪ ሆነህ ብትሞክረው ፣ ከላይ መንግሥት ከታች ደግሞ ሠራተኞችና ተገልጋዮች ግራ እንደሚያጋቡህ ዓይነት ማለቴ ነው ፡፡ ኃላፊነት ምን ጊዜም ቀላልና ቀና አይደለም ፡፡ ከተጠቃሚዎች እንዳትቆጥረኝ ፣ ስደተኛ ነኝ ፡፡ ይህን በማለትህ የሚናደዱ ቤተ ዘመዶች ይኖራሉ ፤ ታድያ ሰውን ማሳዘንና ማስቀየም ደግ ነገር ነው ? ወይስ ከሞቱም በኋላ ድንጋይ እየወረወርክ ለመምታት ይከጅልሃል ?

   Delete
  6. ያሳዝናል ከአንተ ጋር ተቆጥረን ነው 80 ሚሊዮን የሞላነው? ከለብ አዝኜልሀለሁ። በሬሳ ላይ ቂም መያዝ ትልቅ በሽታ ነው።

   Delete
  7. እዚህ ጋ ሂትለር ለምን ሞተ፤ቢን ላደን ሲሞት ለምን እንኳን ሞት ትላላችሁ ለምትሉ፤መለስ ዜናዊ በመሞቱ ለምን እፎይ ትላለህ ብላችሁ ልዩ ልዩ አስተያዮቶችን የሰታችሁ ሁሉ፤

   ከመለስ እጅ ከሞት ያመለጥኩ ሊገለኝ ሲፈልግ የነበረው ስይጣን ሲሞት እንደም ሁኖ አዝንለታለሁ ? የ97ቱ ምርጫ የ11 ዓመት ህጻን ልጇን ያጣች መለስ ሞተ ቢሏት "ተመስገን አምላኬ'ብትል ምንድ ነው ስህቱቷ ? መለስ ሞቷል ይሄ አያሳዝንም።የሚያሳዝነው እናንተ እንደምትሉት ሃጢያቱን ተናዞ ንስሃ ገብቶ ተስካሩን ለእናንተ አብልቶ የሰበራትን አገር ሳይጠግን አለመሞቱ ነው።እኔ እንደማምነው የእርሱ መኖር መከራችንን ከማብዛት በቀር የሚያተርፍልን በጎ ነገር የለም።እግዜርም ከሰማይ ወይም ከዚህ ሁኖ የሰውየን የልብ ድንዛዜ ዓይቶ ገደለው ወይም ወሰደው።በዚህ እኛ የተፈፋን ደስ አለን።እና ምንድ ነው እግዜር ያደረገውን አይተን ደስ ቢለን ምንድ ነው ስህተቱ ? ግብዝ ሁላ።ሃይማኖትህ ከባህል ጋር ቀላቅለህ ከምትደናበር ሂደህ ሙጋድ ብትፈለጥ ይሻልሃል።

   Delete
  8. እያሉን ያሉት "በግድ ቂም ያዙ፡፡" ከኾነ ምላሻችን "አንይዝም!" ነው፡፡ ቂም የተያዘበትን ስልቻ ሲበላና ሲመርዝ፣ መርዙንም ለሌሎች ሲያጋባ እንጂ ለቁስላችን ፈውስ ሲኾን አላየንም፡፡ የሞቱትም፣ የታሠሩትም፣ ያሉትም፣ የሚመጡትም ወገኖቻችን ናቸው፡፡ የማንንም ጉዳት አንፈልግም፡፡ የማንም ጉዳት እኛን አይጠቅመንምና፡፡ በሰው ጉዳት እጠቀማለሁ ብሎ የሚያስብ ሠይጣን ብቻ ነው፡፡

   Delete
  9. በመጀመሪያ ደረጃ፣ እርስዎን ማን የወጣቱ ተወካይ አደረገዎት?

   ሁለተኛ፣ በዝናብ ቆሞ መንገድ ላይ ተሰልፎ የነበረውን ያን ኹሉ ወጣት ልብ እንዴት ሊያውቁ ቻሉ?

   ሦስተኛ፣ እንደእርስዎ ቂም ስላልቋጠረ ወጣቱን “ጅል” ብሎ ከመሳደብ በላይ ምን አምባገነንነት አለ? ቢችሉ ኖሮ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ሊቀበል የወጣውን ወጣት በጠመንጃ በየቤቱ ክትት እንዲል ያደርጉት ነበረ ማለት ነው፡፡ ለጊዜው ግን ማድረግ የሚችሉት መሳደብ ብቻ ስለኾነ በስድብ ተገትተዋል፡፡

   ታሪኳን ካስተዋሉ ኢትዮጵያን ሲያደሟት የኖሩት እንደርስዎ ቂም ይዘው፣ ደምን በደም ማጠብ የሚፈልጉ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ቂመኛ አስተሳሰብ የበቀል ጥማቱን በደም ያረስርሰው እንጂ ከዚያ በኋላ ኢትዮጵያ ሊቢያ፣ ወይም ሶርያ ብትኾን ጉዳዩ አይደለም፡፡

   እርስዎ መለስን በአምባገነንነት ይወቅሳሉ እንጂ እንዲህ ዓይነቱን ጽንፈኛና ቂመኛ አእምሮ ይዘው እያለ እርስዎን ሥልጣን ብንሰጥዎ ሀገሪቱን በደም እንደሚያጠምቋት አምናለሁ፡፡ እኛ ግን ለጊዜው የደም አፍሳሽ እጥረት ስላልገጠመን እስኪ ለቀቅ ያድርጉን፡፡

   Delete
  10. ስህተትህ አስተያየቱን የጻፍከው ስለ ሃይማኖት ጉዳይ ውይይትና ገለጻ በሚደረግበት ብሎግ መሆኑ ነው ፡፡ በተቃዋሚ ድረ ገጾች ላይ በሃሳብህ ተሳታፊ ብትሆን ፣ ብዙ ደጋፊና ተከታዮች ታገኛለህ ፡፡ በእዚህ የምናነበው ግን እንደ ወንጌል ቃል ለመኖር ብለን የየራሳችንን እምነት ለማካፈል የምንጫጭር ነን እንጅ ፤ አብዛኞቻችን ፖለቲከኞች አይደለንም ፡፡ ምናልባት አቅራቢዎቹ ከአንዳንድ ሥራቸው ቢመስሉም ፤ ታዳሚዎች ግን አይደለንም ፡፡ አሁን በደል ፈጽመዋል የምትላቸው ሰው በእግዚአብሔር እጅ ናቸው ፤ አንተ ምንም ብትላቸው አይሰሙህም ፣ በምትናገረው አይናደዱም ፣ ለመማርና ለማረምም ዕድል የላቸውም ፡፡ ቋሚውን ቤተዘመድ ግን ቁርሾ እንዲይዝ ፣ ከሃዘኑም በቶሎ እንዳይጽናና ታደርጋለህ /የሞተበት ሰው የሚሰማውን ስለማውቀው ነው የምመክርህ/ ፡፡ ተቃውሞ የተነሳው ሙሶሊኒንና ቢንላዲንን በመስደብህ ሳይሆን ፣ የምትሰድብበት ሥፍራ ትክክል አይደለም በማለት ነው ፤ ከእምነታችን አንጻርም ሙት ወቃሽ መሆን ምንም እርባና አይኖረውም ፤ የወንጌል ቃልም አይደግፍም በማለት ነው አመለካከታችንን ለማካፈል የሞከርንልህ ፡፡ ለእኔ እንዲያውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክርስቲያን እንደነበሩ የሚያሳይ ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ መስቀል ሲሳለሙ በምስል በማየቴ እጅግ ተጽናንቼአለሁ ፡፡ አንተ ከምትገምተው በተጻራሪው እምነታቸው ትንሽም ቢሆን ሊረዳቸው ይችላል ብዬ ስለገመትኩ ፡፡

   በተረፈ ከጳጳሱ ፊት ለፊት ፣ ስለ እርሳቸው ደህንነት ተብሎ የሰው ህይወት መጥፋቱ ራሱ የሚያስመንን ነው እንጅ ሥልጣን ላይ የሚያሰነብት አልነበረም ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የአሥራ ዓመት ወጣቶችን እንኳን እንደ ተቃዋሚ በመቁጠር በጥይት እየተደበደቡ እንዲገደሉ ትእዛዝ መስጠታቸው ትክክል ሠርተዋል ብሎ ማንም አያምንም ፡፡ ነገር ግን ሁሎችም ከነበደላቸው ወደ እግዚአብሔር ፊት ቀርበዋልና ፍርዱን ለእግዚአብሔር እንተወው ፡፡ እኛ እርስ በርሳችን የሚያቃቅረንን ነገር አናንሳ ፡፡ በተለይም ወንጌልን ከሞላ ጐደል ባነበበነው ወገኖች መሃል ይሄ ሊኖር አይገባም ፡፡ ሳጠቃልለው እዚህ ጥቂት መስመር ከምትሞነጫጭር የሟች ታሪካቸውን በመጽሐፍ ጽፈህ ብታቀርበው ምናልባት ለተጎዱት ሰዎች ቋሚ መታሰቢያ ይሆናቸዋልና አስብበት ፡፡

   Delete
 4. በኢቲቪ የምሰማው እንጉርጉሮ ሀዘን ውስጥ ከተተኝ፡፡ ይሄን ስሜት እወደዋለው፡፡ለወትሮው የበሬ ወለደ ልማታ ዜናዎቹን አማተር ብሔራታ ዳንኪራውን ትቶ ሀገር እንደታዝን ማድረጉ እንዴት ጥሩ ነው፡፡አዎ ማዘን አለብን ማዘን ያገባናል፡፡እኛ ያላዘንን ማን ይዘን እኛ ያልተከፋን ማን ይከፋ

  ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ በልቡ ያኖረዋልና።

  ይቀጥል! ይቀጥል! ለምን ሳምንት ብቻ በየቀኑ ስልሳ የኢትዮጵያውያን ሬሳ ከአረብ ሀገራት ይመጣ የለም እንዴ? ይቀጥል! ይቀጥል! በረሀብ በየአመቱ ሚሊዮኖች የምግብ እጥረት ያጋጥማቸዋል ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በሺዎች የሚቆጠሩ ይሞታሉ፡፡ ታዲያ ሟች እያለ ለምን ለቅሶ ይቀራል? ይቀጥል ይቀጥል የሀገሬ ሀብት ንብረቷ ይዘረፍ የለም እንዴ? የነገ ተስፋዋን ሞቶ የለም እንዴ ? ጭቆና ባህሉ የሆነ ሕዝብ ምን ተስፋ አለው አንዱ አንዱን ሲጨቁን ሲላቀስ ይኑር እንጂ እነእስክንድር ከብዙ ሺዎች ጋር ታስረው የለም እንዴ ማንበብ እና መጻፍ ፣ መናገር ፣ መሰብሰብ ተከልክለን አይደል አይደል ታዲያ እኛ ያላለቀስን ማን ያልቅስ ይቀጥል! የምን ጨምበላላ! የምን አሸንዳ !

  ReplyDelete
 5. ንስሓ መልካም ነው ያውም ላወቀበት ዳሩ ግን በቃኝ አለማለት ሹመትና ዘረኝነት
  እስካሉ ድረስ የሰው ሕይወት የሽምብራ እሸት ነው ሁሉም በጊዜው ይነቀላል
  እናም ከመፈካከር ወደ መመካከር ለብቻ ከመደነባበር ባንድነት ወደ መተባበር መገሥገስ ያስፈልጋል፤ ነፍስ ይማር!

  ReplyDelete
 6. ንስሓ መልካም ነው ያውም ላወቀበት ዳሩ ግን በቃኝ አለማለት ሹመትና ዘረኝነት
  እስካሉ ድረስ የሰው ሕይወት የሽምብራ እሸት ነው ሁሉም በጊዜው ይነቀላል
  እናም ከመፈካከር ወደ መመካከር ለብቻ ከመደነባበር ባንድነት ወደ መተባበር መገሥገስ ያስፈልጋል፤ ነፍስ ይማር!የሰው ልጆች በራሳቸው ላይ ምን እንደተዘበበ ሳይረዱ
  በሉቃስ ወንጌል እንደተጻፈ ሁለት መርዶዎች ይዘው ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀረቡና
  በጥያቄ መልክ በባል ቀን ስለተጨፈጨፉትና አሮጌ ግንብ ተንዶ ስለፈጃቸው ሰዎች
  ምን ታስባለህ አሉት ለሁለቱም መርዶ መልሱ አንድ ነበር እርሱም ንስሓ ግቡ!

  ReplyDelete
 7. Fairly good point!

  ReplyDelete
 8. Abaselamawoch ebakachehu balege yehnu sewoch yemtsfuten asteyayetoch batawetu teru new ahun eyesedebe yetsafew sew egziabher yiker yibelew betam balege new enezhi sewoch eko betam telk sera new yeserut yemigeremew betarik yemejemereyawochu sewoch nachew bekiber be hagerachew yetkeberut man new yehager meri or ye hayemanot abat bekiber behageru yetkebrew egziabher mikeneyat alew lelaw enezhi sewoch nachew lehulum mikeneyat yehonut ahun man yihun mekeneyat ketayoun enayalen enede tekla minesteru pm meles zenawi yehone meri mechem anagegnem ende abatachen yehonem abat anagegnem

  ReplyDelete
 9. Relatively good news...but a lot remains to come to the right track. Thanks

  ReplyDelete
 10. Aba Selamawoch Mot Menorun Tawuqalachohu? Lezehi new Yemot sira Yemitserut? Zare Ahun Telewutachihu Nisha gibuna Yematichilutin Dingay Lemefnqli Atimokiru::Ketifatachihu Temelsu::

  ReplyDelete
 11. ይድረስ ዋልድባን የስኳር ፋብሪካና የአቶ መለስንና የአቡነ ጳውሎስን ዕረፍት ለማያያዝ ለምትሞክሩ ኹሉ፡-

  እባካችሁ እግዚአብሔርን በተንሸዋረረ መነጽር እያያችሁ ክርስትናን የናይጄሪያ ጥንቆላ አታስመስሉት፡፡
  “እግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ዐረፍተ ነገር ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስና ለአቡነ ጳውሎስ አይሠራም ያላችሁ ማን ይኾን? አቡነ ጳውሎስና ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ልክ እንደእኔና እንደእናንተ የእግዚአብሔር ውድ ልጆች አይደሉም ብላችሁ የምታስቡ ከኾነ ትልቅ ስሕተት ታሳስታችኋል፡፡ በብዙዎቻችሁ አስተያየት ውስጥ የሚታየኝ አስተሳሰብ እናንተ የእግዚአብሔር ወዳጆች ስትኾኑ እነዚህ ሰዎች ደግሞ የእግዚአብሔር ጠላቶች ናቸው የሚል ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡ የሒትለር ወታደሮችም ያንን ኹሉ አይሁዳዊ ሲጨፈጭፉ ለእግዚአብሔርና ለአባት ሀገራቸው ብለው እንደሚያደርጉት ያስቡ ነበር፡፡ ይህ ግን እግዚአብሔርን በራሳችን አምሳል ጠፍጥፈን ለመሥራት መሞከር እንጂ ሌላ ምንም አይደለም፡፡ እግዚአብሔር እኛ የምንወድደውን እንዲወድድ እኛ የምንጠላውን እንዲጠላ መፈለግ እግዚአብሔርን የእኛ ፍላጎት ዘበኛ ማድረግ ነው፡፡ ክርስትና ይህንን አያስተምረንም፡፡ የሚያስተምረን ፈቃዱ በሰማይ እንደኾነች እንዲሁም በምድራውያኑ በእኛ ላይ እንድትኾን ነው፡፡ የእርሱ ፈቃድ ደግሞ አንዳችን ለአንዳችን በፍቅርና በትሕትና እንድንኖር ነው፡፡ የክርስትና አዕማድ ንጽሕና፣ ድኽነትና ትሕትና ናቸው፡፡

  አብዛኞቻችሁ ዋልድባን የምታውቁት አይመስለኝም፡፡ ኼዳችሁም እንደማታውቁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ምን ያህል ሰፊ ቦታ መኾኑንም ያስተዋላችሁ አይመስለኝም፡፡ ከኹሉም በላይ ማስተዋል ያለብን ዋልድባን ዋልድባ ያደረገው የመናንያኑ መንፈሳዊ ተጋድሎ እንጂ የመሬቱ ስፋት ወይም ቅርጽ አይደለም፡፡ መሬቱን ለገዳሙ መንፈሳዊነት ዕንቅፋት አታድርጉት፡፡ ገዳማውያኑ የጥሪት ችግር የለባቸውም፡፡ ተዉአቸው በሰላም ይኑሩበት፡፡ አማናውያኑ መናንያን እንኳን ለቁራሽ መሬት ለዐለሙ ኹሉም ግድ የላቸውም፡፡ ከኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር በስተቀር በምንም ነገር ፍቅር አይታሠሩም፤ ከአምላካቸው ጋር ካልኾነ በስተቀር አይጣበቁም፡፡ የዚህ የከተማን የመሬት ንትርክ ገዳማቱ ውስጥ አታስርጉ፡፡ ሰይጣን ሞኝ አይደለም:: ኹልጊዜም ክፉ ሲያሠራ መልካም እየሠራችሁ እንደኾነ ያሳምናችኋል፡፡ ይህ የእርሱ ስትራቴጂ ነው፡፡ አጅሬ እያታለላችሁ እንዳልኾነ በምን እርግጠኞች መኾን ትችላላችሁ?

  እስኪ ዝም በሉና እግዚአብሔርን ስሙት፡፡

  ReplyDelete
 12. Nisiha Malet Enante Lejemerachihut Menged Mataqsha Yemayihonu Abatochin Foto Ena Sim Yizo Mewutatu New? Yetgnaw Wonigelawe Mask Atiliko Sebke?Nisiha Gibu::::

  ReplyDelete
 13. Selamawoch Nisiha Mindinew? Bedeneden lib Yemitnoru Enante Yetifat Sewoch Nisiha mindin new?

  ReplyDelete
 14. ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የጽርፈትና የጥፋት ዘመቻ የሚያካሂዱት በዋናነት የራሳቸው ማንነት የጠፋባቸው ምዕራባውያን(ሉተራውያን) ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት ከመቶ ዓመታት በላይ በራሳቸው ጥረትና ስልት የወጡትን ያህል ወርደዋል፤ የወረዱትንም ያህል ወጥተዋል፤ ነገር ግን የተመኙትንና የፈለጉት በእጃቸው ማድረግ አልቻሉምና ሌላ ስልት ሌላ ስትራቴጂ መቀየስ ግድ ነው፡
  ፡ ይህ ስትራቴጂ ደግሞ ከዘመኑ ሥልጣኔ ጋር ሻማና ክር ሆኖ በመመሳሰል እንዲቀረጽ የተደረገ በመሆኑ ብዙዎቻችን የተሃድሶአውያን ተላላኪነት በፍጹም ሊገባን አልቻለም፡፡

  ተሃድሶ የፕሮቴስታንቱ ዓለም ተላላኪ መሆኑ ግልጥ ያለ ነገር ነው፡፡ ማስረገጫው ደግሞ በዚሁ አዚም የተማረኩ ወገኖች ይኸው ቡድን በሚያደረግው የጸሎትና የዝማሬ ዝግጅት ላይ ሲገኙ የገጠማቸው ፕሮቴስታንታዊ ሥርዓት ነው፡፡

  በመሠረቱ ማንም ሃሳቡን ማራመድ ይችላል፤ የፈለገውን ማመንም እንዲሁ፤ ዓለማመንም የራሱ መብት ነው፡፡ በእኛ ቅኝት ዝፈኑ ማለት ግን በእኔ ሳንባ ተንፍሱ፣ በእኔም አፍ ተናገሩ ማለትን ግን የትኛውም የሰው ልጅ ሊቀበለው የማይችል ጉዳይ ነው፡፡

  ልጅ የቤተሰቡ ነገር ካልተመቸው ወጥቶ በራሱ መንገድ ራሱን መምራት የሚጠበቅ ነው፤ የቤተክርስቲያን ነገር በልበ ደንዳናነቱ አልዋጥለት ያለውም እንዲሁ፡፡ ልጅ ነውና ይመከራል፣ ይዘከራል፣ የሚጠቅመው ይነገረዋል፣ እኔ ነኝ የማውቀው ካለ መንገዱ ሰፊ ነው መጓዝ ይችላል፡፡

  የተሃድሶአውያን መሠረታዊ ችግር ሁለት ነው፥ በእኔ እምነት፥

  አንደኛ
  ግብዝነት፥ እንደ ፈሪሳዊ፡፡ በእውቀት የደረጀን፣ ለወንጌል አገልግሎት ቀሚስ የታጠቅን፣ የበሰበሰ የአስተዳደር ሥርዓትን መቀየር የምንችል ምሩቃን፣ ልሂቃን ብሎ መኮፈስ፡፡ በመሠረቱ ክርስትና በእውቀት ሳይሆን በልጅነት፣ በጸጋ፣ በሰማዕትነት፣በየዋህነት የሚወረስ መንግሥት ነው፡፡ ሊቀ ሐዋርያ ቅዳስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ የቁልቁሊት ተሰቅሎ ያገኘው መንግሥት ነው፣ የሐዋርያት መሪ የነበረውም በትምህርቱም ልሂቅነት አይደለም፡፡ አስተውሉ!!!

  ሁለተኛ፥
  ከፍጹማዊው ሕግ ይልቅ ለሰው ሠራሹ ሕግ ቅሩብ መሆናቸው ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ከላይ የተገለጹት በሕግ ውስጥ በስውር የተቀመጡ ኢክርስቲያናዊ አሠራሮችን በመተግበር ለመፈጸም መሞከር፡፡ ተኩላ በበግ ለምድ እንዲሉ በሕግ ማዕቀፍ ስም በሰው ልጆች ላይ የተቀመጡትን አሳሪ ሕግጋትን ከዲያብሎሳዊ መንገድ ከሚከለክሉ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ይልቅ ሙጭጭ ብሎ መያዝ፡፡ አካሄዱ ሥጋዊነትን ያጋለጥ እንደሆነ እንጂ መንፈሳዊነትን የሚያውጅ አንዳች ኃይል የለውም

  ReplyDelete
  Replies
  1. እየገለበጥህ በየቦታው ደጋግመህ ስታስነብብ ፣ ቀደም የተገኘበትን ምንጭ ጥቀስ ፡፡ ይኸ በሌላ ርዕስ ሥር ከዶግማ ጋር በመያያዝ ቀርቦ የነበረ ጽሁፍ ነው ፡፡ ነገር አትቀላቅል ፤ አሁን በሞቱ ሰዎች ያለ የተለያየ አመለካከትን እየተናበብን እንጅ ስለእምነት ጉዳይ እየተነጋገርን አይደለም ፡፡

   ተሃድሶ የሚለው ፍልስፍና ቀደም የነበረ ቢሆንም ፣ በዚህኛው ዘመን ግን መልክና ይዘቱን በመቀየር ፣ የተዋህዶ ዶግማንና የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትን ለመናድና ለመሸርሸር የተነሳ የሉተራውያን ሤራ ነው ፡፡ ርዕሱ ሲነሳ በጊዜው በደንብ እንፋጭበታለን ፡፡

   Delete
 15. Kelay zimta bemil melis yesetehew Egziabher aemrohin abzito yibarkew yeliben tenefesikilign tebarek

  ReplyDelete
 16. Lemanignawum bego hilina yinurih!

  ReplyDelete
 17. Hi what is going on can some body tell me what they token about.it is really imbaressing,I know one thing no body is perfect in this entier world,as human they made mistake it is not abig deal.why they made it,bc they were devoted to change the nation.they was facing the truth that makes there live short.but they did great and exterminds job i gave theme acredt.fabulos job.no body denie this.stop bleming dont put ur finger to somebody elese,put ur finger on u.u know we eth we dont have good heart insted of appersition we stand on negative.that is not good.ps be postive,oh GOD ps for giveus,it is abig loss for the church,country even for the world.it might be take 1 or 2 century to get this kind of gays.that means if we are lucky.or elese forget it.some how we goon pay the consecons.it is not far take my word.ps GOD change this crude people.

  ReplyDelete
 18. "በአቡነ ጳውሎስ ላይ ሲያሟርቱ የነበሩ" what does this mean? you pretend as religious but believe in some MuART. doma ras!!!!!

  ReplyDelete
 19. ቀን ይነዳ እንደ ፍሪዳ እያንዳንዱ ሰው ቀኑ ሲደርስ ይጠራል ከዚያም መንታ መንገድ ይዞ ይሄዳል፤
  የትኛው ቀጥታ ወይም ጠማማ እንደሆነ ማን ደግ ማን ክፉ መሆኑንም የሚገነዘብ አይገኝም ሁሉንም
  ሟችና ተለዋጭ ሰው የሚፈጥረው ነው፤ በሰው ዘንድ ደግ በፈጣሪ ዘንድ ኢምት ነውና አሁንም ሰዎች
  በእነገሌ ጸሎት እነገሌ ጠፉ ይላሉ መልካም ነው ይበሉ! ጸሎተኞቹሳ ሲጠፉ ምን ሊባል ነው፤ ፈጣሪም
  የማይታይ ሆኖ ነውጂ የሚታይ ቢሆን ኖሮ አንድ ይሉት ነበር፤ መተቻቸት መተማማትና እርስ በርስ መበላላት እንዲሁም መመካከር መተባባርና እርስ በርስ መፈቃቀር ድሮ የነበረ አሁንም ያለና ወደ ፊትም
  የሚቀጥል ነው፤ዳሩ ግን ማንም የሥነ ፍጥረቱ አካል የሆነ ፍጡር ሁሉ ባያውቀውም ዕንኳ ፈጣሪ መኖሩን ሊያስብ ይገባል፤ ያ ባይሆን እግዜር ብትር ፍለጋ አይወጣም ደጋ(ሽመል ምልመላ አይወርድም ቆላ እናም አትሸማቀቁ ተጠንቀቁ!

  ReplyDelete