Tuesday, September 25, 2012

የ«ተሐድሶዎች» አላማ ምንድን ነው?

ተሐድሶ የሚለው ስም አነጋጋሪ ከሆነ ሰንብቷል። በብዙዎች ዘንድም አሉታዊ ስም ሆኖ ይታያል።  ስሙን ለራሱ ያወጣ ወገን ባይኖርም፣ ስሙን ተቀባይ የሆነ ወገን ግን አልጠፋም። ተሐድሶ የሚል ስም የተለጠፈባቸው ወገኖች ቤተ ክርስቲያን ከእውነተኛው የክርስትና ትምህርት ወጥታ በስሕተት ትምህርት ውስጥ ትገኛለችና ስሕተቶቿን በማረምና የጣለችውን የከበረ እውነት በማንሣት ወደ ትክክለኛው መንገድ መመለስ አለባት የሚሉ ናቸው። እነርሱ እንዲህ የሚል አቋም ቢኖራቸውም፣ ተሐድሶ የሚለውን ስም ያወጡ ወገኖች ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው የሚመለከቷቸው። ለሌላውም የሚያስተዋውቋቸው አፍራሽ ሀይል አድርገው ነው። በተደጋጋሚ የኦርቶዶክስን ቤተክርስቲያንን ለማፍረስና ፕሮቴስታንት ለማድረግ እየሠሩ ነው የሚል ክስ ሲያቀርቡ ነው የሚደመጠው። እውን የ«ተሐድሶዎች» አላማ ኦርቶዶክስን ወደ ትክክለኛው መንገድ መመለስ ነው ወይስ ወደፕሮቴስታንታዊ ማንነት መለወጥ?

Wednesday, September 19, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሹመት ደስተኛ አለመሆናቸውን ቤተክህነት አካባቢ በሚያናፍሱት ወሬ እየገለጹ ነው

ዐቃቤ መንበሩ «መናፍቃኑ ኃይለ ማርያምን ጠቅላይ ሚኒስትር ሊያደርጉት እየጸለዩ ነው አሉ፤ እርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነ ማለት ለእኛ እጅግ ክፉ ነገር ነውና የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን» ብለዋል
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢህአዴግ ሊቀመንብር ሆነው መመረጣቸውንና በቀጣይም ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ቃለ መሐላ የሚፈጽሙ መሆናቸው ከተገለጸ ጊዜ ጀምሮ፣ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ በመሆናቸው ምክንያት በማኅበረ ቅዱሳን መንደርና በቤተክህነቱ አካባቢ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ግንኙነት ባላቸው አካላት ዘንድ «ጴንጤ አይገዛንም» የሚል ቅስቀሳ ውስጥ ውስጡን እየተደረገ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡

በዘመን መለወጫ በዓል ላይ በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ በተዘጋጀው መርሀግብር ላይ የተገኙትና ንግግር ያደረጉት አቃቤ መንበር አባ ናትናኤል ትዝብት ላይ የጣላቸውን ንግግር ማድረጋቸውን በስፍራው የነበሩ ምስክሮች እየገለጹ ነው። አቡነ ናትናኤል በአቃቤ መንበርነት ከተሾሙ ጀምሮ ጊዜውን እየተሻሙና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ለመምሰል ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን እያደረጉ ካለው እንቅስቃሴ መታዘብ ተችሏል፡፡ «እርሳቸው ወንበር ላይ አስቀምጡኝ» ከማለት «እርሳቸው የሚበሉትን ስጡኝ» እስከማለት መድረሳቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

Tuesday, September 18, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን የጥናት እና ምርምር ማእከል ባዘጋጀው በ፬ኛው የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን ጥናት ጉባኤ ላይ የተደረገ አጭር ደሰሳ

   የማኅበረ ቅዱሳን የጥናት እና ምርምር ማእከል ባዘጋጀው በኛው የኢትዮጵያ ቤተ-
                   ክርስቲያን ጥናት ጉባኤ ላይ የተደረገ አጭር ደሰሳ፡፡
በፍቅር ለይኩን፡፡ [fikirbefikir@gmail.com/befikir12@yahoo.com]

‹‹ሁሉን መርምሩ የተሻለውን ያዙ!›› የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ሕያው ቃል ባለ አእምሮ የሆነ ሰው ሁሉ በማስተዋልና በጥበብ መንፈስ ሆኖ መልካሙን ከክፉ ለመለየት ጥናት እና ምርምር በእጅጉ አሰፈላጊ መሆኑን የሚያሳስበን ኃይለ ቃል/ምክር ይመስለኛል፡፡ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በአይሁድ ምኩራብ ተገኝቶ በተደጋጋሚ ስለ ጌታችን፣ አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት፣ ጌትነት እና አዳኝነት የሰበከላቸው ልበ ሰፊዎቹ የቤሪያ ሰዎች፡- ‹‹ነገሩ እንዲህ ይሆንን በማለት መጻሕፍትን በመመርመር ቃሉን በሙሉ ልብ ተቀበሉ ይለናል፡፡›› (ሐዋ  ፲፯፣፲፩)