Tuesday, September 4, 2012

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሥርአተ ቀብር ተፈጸመ

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ሥነሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የጠቅላይ ሚንስትሩ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 27/2004 ዓ.ም ተፈጸመ፡፡ ከቀብር ሥነ ሥርአቱ አስቀድሞ ዜና ህልፈታቸው ከተሰማበት ከነሐሴ 15 ቀን ጀምሮ ልዩ ልዩ የስንብት መርሀ ግብሮች ተዘጋጅተው የነበረ ሲሆን፣ ሥርአተ ቀብሩ በተፈጸመበት ዕለትም በመስቀል አደባባይ በርካታ የአፍሪካ መሪዎች፣ የሌሎችም መንግስታት ተወካዮች፣ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች የተገኙበት የመጨረሻ የስንብት መርሀ ግብር ተካሂዷል፡፡

ጠዋት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስከሬን ከቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ በሰረገላ ተጭኖና በተለያዩ የጦር ሰራዊት አባላትና የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በሃይማኖት አባቶች፣ ሃይማኖታዊ አልባሳት በለበሱ ካህናትና ዲያቆናት፣ በቤተሰቦቻቸውና በወዳጅ ዘመዶቻቸው ታጅቦ የሄደ ሲሆን በመስቀል አደባባይም በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ ሥርአቱን ታድሟል፡፡ የተለያዩ የአፍሪካ መሪዎች፣ የመንግሥታት ተወካዮች ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ አቶ አዲሱ ለገሰም የጠቅላይ ሚኒስትር መለስን የሕይወት ታሪክ በንባብ አሰምተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕይወት ዘመናቸው ስለራሳቸው መናገርም ሆነ መስማት የማይወዱ ሰው መሆናቸውን ጠቅሰው ከአንደበታቸው የተዘነጋች ቃል ብትኖር “እኔ” የምትለው ቃል መሆኗን ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ግን ስለእርሳቸው መናገር ግድ ሆኖብናል ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዘመናቸው ከትግል ወቅት አንሥቶ እስከ ዓለም አቀፍ መድረክ ድረስ ያከናወኗቸውን ታላላቅ ተግባራት ዘርዝረዋል፡፡ በመጨረሻም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለቤት ቀዳማዊት እመቤት አዜብ መስፍን ንግግር አድርገዋል፤ የመለስ ሞት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ለመሪው ላሳየው ፍቅር ለኢትዮጵያ ሕዝብም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም ከመስቀል አደባባይም ወደቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የመልስ ጉዞ ተደርጎ ከቀኑ 9፡30 ላይ የቀብራቸው ሥነሥርዓት ተፈጽሟል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዜና ኅልፈት ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ አገራችን በከፍተኛ የሐዘን ድባብ ውስጥ ሰንብታለች፡፡ ሴቱ፣ ወንዱ፣ ሕፃኑ፣ ሽማግሌው፣ ወጣቱ፣ ጎልማሳው፣ ብቻ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለማለት በሚቻል መልኩ ሐዘኑን በተለያየ መንገድ ሲገልጽ ሰንብቷል፡፡ እንደ ብዙዎች እምነት ለአንድ የአገር መሪ እንዲህ ሲታዘንና ሲለቀስ ከአጼ ምኒልክ ወዲህ የመጀመሪያው ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሕዝቡ ልብ ውስጥ ያላቸውንም ስፍራ አሳይቷል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አስደንጋጭ ሞት እርሳቸው ከዚህ ዓለም የተሰናበቱበት አጋጣሚ ብቻ ሳይሆን ብዙዎች መለስን በሚገባ ማወቅ የጀመሩበት ጊዜ በመሆኑ ሐዘኑን እጽፍ ድርብ እንዳደረገው ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ መለስ ዜናዊ የተለዩ ሰው ነበሩ። የተለዩ የሚያደርጋቸው የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው በወጣትነታቸው ትግል ስለጀመሩ አይደለም። 17 ዓመት ታግለው ከሌሎች ጓዶቻቸው ጋር የደርግን መንግሥት ስለጣሉም አይደለም። ከዚያም ለ21 ዓመታት ኢትዮጵያን ስለመሩም አይደለም። ብዙ የትግል ጓዶቻቸውም በዚህ ውስጥ አልፈዋልና፡፡ እርሳቸው ባለራእይ ስለነበሩ፣ እንደ ባለራእይ ስለተነሡ፣ እንደ ባለራእይ ስለኖሩና እንደ ባለራእይ ስለሞቱ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው። ታላላቅ ሐሳቦችን በማመንጨት፣ በመተንተንና ወደሥራ እንዲለወጡ በሳል አመራር በመስጠት፣ በተለያዩ አጋጣሚዎችም ርቱዕ በሆነና በማይሰለች አንደበታቸው አስተማሪ የሆኑ ክርክሮችን በማድረግና ማብራሪያዎችን በመስጠት መላ ዘመናቸውን ያሳለፉት አላማዬ ብለው ለያዙት ራእይ ዋጋ በመስጠትና ለተፈጻሚነቱ ተግተው በመሥራት ነው፡፡ ዜና ህልፈታቸው ከተሰማ ወዲህ በትግሉ ወቅትና በሥልጣን ዘመናቸው የሰጧቸውን ቃለ መጠይቅ፣ ትንታኔዎች ማብራሪያዎች በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ሲተላላፉ ለተከታተለ ሰው በእርግጥም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አላማዬ ብለው ለያዙት ጉዳይ ባለራእይ እንደነበሩ መገንዘብ ችሏል፡፡ 

በቀብራቸው ሥነሥርኣት ላይ የተገኙ የአፍሪካ መሪዎችና ሌሎችም የመንግስታት ወኪሎች የመሰከሩትም ስለ መለስ ባለራእይነት ነው፡፡ በእርግጥ ከላይ የተጠቀሱት ታላላቅ ተግባራትም ለመለስ ታላቅ ሰብእናን ያጎናጸፏቸው ናቸው። ከእነዚህ ታላላቅ ተግባራት በላይ ግን እነዚህን ታላላቅ ተግባራት ያከናወኑበት ራእይ ይበልጣል፡፡ መለስን ትምህርት አስጥሎ ወደ ጫካ ያስገባቸው ራእይ ነው። መለስን በብዙ መከራና ችግር ውስጥ አልፈው ለ17 ዓመታት መራራ ትግል እንዲታገሉ ያደረጋቸው ራእይ ነው። ወደሥልጣን ከመጡ በኋላም ያለዕረፍት በተከተሉት የፖለቲካ መስመር መሰረት ሌት ተቀን ለእናት አገራቸው እንዲሠሩ ያደረጋቸው ራእይ ነው። መንግሥታቸው እስከ ምርጫ 97 ድረስ ከሕዝቡ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ ቆይቶ የሕዝቡን ድምፅ ከተነፈገ በኋላ ራሱን ፈትሾ የአቅጣጫ ለውጥ ማድረግ ከጀመረና ተጨባጭ ለውጦች መታየት ከጀመሩ ወዲህ ግን ከሕዝቡ ጋር ያለው ግንኙነት እየተሻሻለ መምጣቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ የለውጥ ሂደት ውስጥ ባለራእዩ መሪ መለስ ዜናዊም ዋና ተዋናይ ነበሩ፡፡ ቀደም ብለው በማራኪ ንግግራቸውና ትንታኔያቸው ይወደዱ የነበሩት መለስ፣ ወደታች በመውረድ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማነጋገርና በማወያየት ወደሕዝቡ ልብ መግባት ጀመሩ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነበር ቀድሞ ልብ ያልተባለውና በተቃዋሚዎች የፖለቲካ ቅኝት ብቻ እየተመዘነ በጥላቻ ዓይን ብቻ ሲታይ የቆየው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ማንነትና ባለራእይነት ሌላ ገጽ መያዝ የጀመረው፡፡ ይበልጥ ደግሞ ሞታቸው ከተሰማ በኋላ ጎልቶ ወጣ፡፡

ብዙዎች በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን ሲገልጹ ልዩ ልዩ ስሜቶቻቸውን ሲዘረዝሩ ሰንብተዋል፡፡ ለምሳሌ፣ ምን ነበረ እንደተመኙት ጥቂት አርፈው ቢሞቱ? ምናለበት ያስጀመሩትን የዓባይ ግድብ ፍጻሜ አይተው ቢሞቱ? … ይህ ሁሉ ግን መለስ ባለራእይ መሆናቸውን ካለመገንዘብና ከጥልቅ ፍቅር የመነጩና በስሜት የታገዙ አስተያየቶች ናቸው፡፡ ለመለስ ግን እነዚህ ምንም አይደሉም፡፡ መለስ በሕይወት ሳሉ በአንድ ወቅት እንደተናገሩት ለእርሳቸው መኖር ለግል ሕይወት መኖር ሳይሆን፣ ለሕዝቦች ደስታና እርካታ፣ ትርጉም ላለው ዓላማ፣ ለብዙዎች ለሚተርፍ ሕይወት መኖር ነው፤ ይህ ደግሞ የባለራእዮች አኗኗር ነው፡፡ ባለራእይ ለሌሎች እንጂ ለራሱ አይኖርምና፡፡

እውነት ነው፤ የመለስን የፖለቲካ ኣካሄድ ሌሎች ላይደግፉት ወይም ሊቃወሙት ይችላሉ፡፡ በሥልጣን ላይ በቆዩባቸው ዓመታት እርሳቸውም ሆኑ መንግስታቸው የፈጸሙት ስሕተት ይኖራል፡፡ ሌሎች እርሳቸውንም ሆነ መንግስታቸውን ቢደግፉም ሆነ ቢቃወሙ፣ አንድ ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል ሐቅ ግን አለ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ላመኑበት ዓላማ ታግለዋል፤ ዓላማቸውንም አሳክተዋል፡፡ ሰው ሊሠራ የሚችለው ከፈጣሪ በተሰጠው ዕድሜ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስም ከማንኛችንም በላይ የተሰጣቸውን ዕድሜ ለተሰጡለት አላማ ያለዕረፍት፣ በአግባቡና በውስጣቸው የተቀመጠውን ራእይ እውን ለማድረግ በመታገል ኖረው ተጠቅመውበታል፤ ሩጫቸውንም ጨርሰዋል፡፡ እርሳቸው ከሌላው ሰው የሚለዩት ባለራእይ በመሆናቸውና ለራእያቸው በመኖራቸው ነው፡፡ ሰው ይወለዳል፤ ባለራእይ ግን ይፈጠራል፡፡ 

እግዚአብሔር ሆይ ለእዚህች አገር መልካምነትን የሚያልሙ ሌሎች ባለራእዮችንም አስነሣልን!!

8 comments:

 1. ግሩም ትንታኔ ነው!ጎበዝ ቁልጭ አድርገሃታል::ስብከት የምትሰብክ ነው የምትመስለው::መንፈሳዊነት የተላበሰ ለመንፈሳዊ የእምነት መሪዎችም ትምህርት የሚሆን እጥር ምጥን ያለች አስተምህሮ መልዕክት እንዳስተላለፍክ አሰብኩኝ::ግን የሆነስ ሆነና ከዚህ ነገር መንፈሳውያነን የሚሉ የሚማሩት ነገር ይኖር ይሆንን?እግዚአብሔር በዚህ ሁኔታ እየተናገረ ያስቡ ይሆንን?እባክህ ካላሰቡ እንዲያስቡ ካሰቡ እንዲጠናከሩ መልዕክቴ ይድረሳቸው::መሪ ለራሱ ሳይሆን ለሌሎች እንደሚኖር እኮ ከጌታችን ኢየሱስ ሕይወት መማር እኮ ይቻላል አልገባ ብሎን ነው እኮ አገልጋይ መሪ የቤ/ክ እየተባለ ምድራዊ ሀብት ሰዎችን እየደፈጠጡ ማከማቸት የሆነው::ይህ ብቻ አይደለም በኦርቶዶስ ቤ/ክ ውስጥስ የሚዘረፈው ሙዳየ ምጽዋት ለምን ይመስላችኋል?ለምድራዊ ምቾት ነው እኮ ኧረ ወደ አእምሮ መልስ ይባል?
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 2. where have u been so far? it is too late to post this as a news after three days. shame on u

  ReplyDelete
 3. is the argument no MK news

  ReplyDelete
 4. tiru eyeta new. thank you

  ReplyDelete
 5. for the first time, an article without word mahber kidusan...

  ReplyDelete
 6. ምነው እንደ ሐይማኖተኛ ስለ ፍትሐቱ ምንም ሳትሉ ቀራችሁ? ለነገሩ ይች ይች ለእናንተ አትዋጥላችሁም? እንዲያው ዝም ብላችሁ እራሳችሁን ሃይማኖተኛ እና የኢ/ኦ/ተዋህዶ አባላት አድርጋችሁ ትቆጥራላችሁ እንጂ፤ እናንተ እኮ ዐይን ያዎጣችሁ ተኩላዎች ናችሁ፡፡ ምንለ እጃችሁን ከእኛ ላይ አንስታችሁ የራሳችሁን እምነት በቤጣችሁ ብታራምዱ?

  ReplyDelete
 7. emnte /hayemanot / yalew sew aymeselegnem kerstena yetenesaw yemote elet mehonu yetaweqal mekn yatum behulet yekersetena sem neber yefetut yeneberew anedie G/EGEZIABEHIER ,G/MAREYAM YELUT YENEBEREW

  ReplyDelete